Wednesday, July 17, 2013

‹‹ታች በሌ››

የዛሬ ሃያ ዓመት ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ እንደተመረቅኩ የመምህርነት ሥራዬን የጀመርኩት እነዋሪ በምትባል በሰሜን ሸዋ ውስጥ ከምትገኛና ከአዲስ አበባ 165 ኪሎ ሜትር በምትርቅ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ነበር፡፡ እነዋሪ ከመርሐቤቴ እስከ ዜና ማርቆስ የሚኖረው ቆለኛና ደገኛው ጅሩዬ የሚገናኙባት የቀለጠች የገበያ ከተማ ናት፡፡ በተለይም በፍራፍሬ ምርቷ ትታወቃለች፡፡ ኤፍሬም እሸቴ የእነዋሪን ሙዝ ‹ከማጠሯ መጎጠሯ› እያለ ይቀልድባት ነበር፡፡
ከእነዋሪ እየተነሣሁ እስከ ዠማ ወንዝ ድረስ ለሠርግም፣ ለንግሥም ቆላውን እወርድ ነበር፡፡ ገበሬዎቹ ከቆላው ይመጡና እኔን በቅሎ ላይ አውጥተው በትከሻቸው ላይ ውጅግራ ጠበንዣቸውን ደልደል አድርገው ተሸክመው የጋቢያቸውን ግማሽ ጠቅልለው አናታቸው ላይ በማስቀመጥ፣ ከግራና ከቀኝ በቅሎዋን እየነዱ፣ ያንን እንደ ያሬድ መዝሙር በጆሮ የሚንቆረቆረውን ወጋቸውን እያወጉ፣ እንደ ዝንጀሮ ገደሉን በኩራት ይወርዱታል፡፡ ተረታቸው፣ ቀረርቷቸው፣ ፉከራቸው፣ ዘፈናቸው፣ የታሪክ ትረካቸው፣ ስለ ጀግኖቻቸው የሚገጥሙት ግጥም አሁንም በጆሮዬ እንደ መስክ ነፋስ ሲያልፍ ይሰማኛል፡፡ 

አንድ ቀን ታድያ አይዋ ሰጥ አርጌ የሚባሉ ቆፍጣና ገበሬ አብረውን ወደ ዠማ ሲጓዙ ታች በሌ ስለሚባል ሽፍታ አወጉኝ፡፡ ታች በሌ በተለይ በሞረቶች ዘንድ በጣም የታወቀ አስቂኝ ሽፍታ ነው፡፡ አንድ ሰው ያላሰበበትን፣ ያልተዘጋጀበትንና ያለ ዐቅሙ የሆነውን ነገር ጀመረ ሲባል ዠማዎች ‹‹ምን የእርሱ ነገርኮ የታች በሌ ሽፍትነት ነው›› ይሉታል፡፡ አንድ ሰው በስሜት ብቻ ተነሣስቶ እንዴው የጀብደኛነትን ሥራ ሲሠራ፣ አንድን ነገር አስቦ ከመሥራት ይልቅ ከሠራ በኋላ ሲያስብ ዠማዎች እንዲሁ ‹ታች በሌ› ይሉታል፡፡ ለምን?
ታች በሌ የዠማ ሰው ነው፡፡ የኖረው ከዛሬ ሁለት መቶ ዓመት በፊት በሸዋው አስፋ ወሰን ዘመን ነው  አሉ፡፡ በዚያ ዘመን ሞረትን ይገዙት የነበሩት ጥዱ የተባሉ ኃይለኛ በላባት ነበሩ፡፡ እንዲያውም ጥዱና አስፋ ወሰን እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩም የሚፈታተኑም ኃይለኞች ስለነበሩ ግጥሞቻቸው ዘመን ተሻግረው ደርሰውናል፡፡ አስፋ ወሰን ሞረትን ማስገበር ስለፈለጉ
ለሞፈር ለቀንበር የሚሆነኝን
ሳልቆርጠው አልቀርም ዘንድሮ ጥዱን፤
ብለው ለአዝማሪ ነገሩ አሉ፡፡ ይህን የሰሙት ጥዱም
አስፋ ወሰን ይፋት ጠንክረው ይረሱ
ሞረት ጥዷል ብለው ከሚመላለሱ፤
ብለው መለሱላቸው ይባላል፡፡
ጥዱ ኃይለኛ አስገባሪ፣ አስጨንቆ ገዥ ነበሩና ብዙ ገበሬዎችን እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደ ብረት ቀጥቅጠው፣ እንደ ጫማ ረግጠው ይገዙ ነበር፡፡ ከተገዥዎቹ ገበሬዎች አንዱ የነበረው ታች በሌ መረረው፡፡ በልጅነቱ በሰሜን ሸዋ በረሃዎችና ጫካዎች ሸፍተው ገዥዎችን ስላስጨነቁ ሽፍቶች እየሰማ ነበርና ያደገው መሸፈት አማረው፡፡ አንድ ቀን ከብት ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች መሸፈቱን ነግሮ የአጎቱን ቁመህ ጠብቀኝ መንትፎ ሸፈተ፡፡ ሸፍቶም ጫካ ገባ፡፡ አገሩም ‹ታች በሌ ሸፈተ› እያለ ከሚዳ እስከ እነዋሪ አወጋ፡፡ አንዳንዱ አደነቀ፤ ዘፈነለት፤ አንዳንዱ ተጠራጠረ፣ አንገቱን ነቀነቀበት፡፡ ‹በምን ልቡ ነው የሸፈተው›› ያሉም ነበሩ፡፡ ጥዱም እገለዋለሁ ብለዋል ተባለ፡፡
ታች በሌ ዠማ ወንዝ በረሃ ውስጥ ወርዶ አንድ ጫካ ውስጥ ተቀመጠ፡፡ መጀመሪያ ስሙ በድፍን ሸዋ ሲገንን፣ ስሙ በየሠርግ ቤቱና በየድግስ ቤቱ የዘፈን መቋጠሪያ ሲሆን እየታየው ልቡ በደስታ ሞቆ ነበር፡፡ ዋል አደር ሲል ግን ታች በሌን ጥያቄዎች ጭንቅላቱን እየሞሉ ያስጨንቁት ነበር፡፡ ለመሆኑ በቂ ስንቅ ይዘሃል? የሸፈትከውኮ በጀግናው ጥዱ ላይ ነው፤ ለመሆኑ በቂ ጥይት ታጥቀሃል? ለመሆኑ ቢመጡብህ የምትሸሽበት የማምለጫ ስርጥ መርጠሃል? አንተ መንደርህ እያለህ አንድ ቆቅ እንኳን አድነህ የማታውቅ እንዴት ጥዱን ለመዋጋት ጫካ ገባህ? ለመሆኑ ዛሬ የታጠቅከውን ቁመህ ጠብቀኝ ተኩሰህበት ታውቃለህ? ቢበላሽ ማን ይጠግንልሃል? ከዛሬ በፊት ለመሆኑ ጫካ ውለህ አድረህ ታውቃለህ? ከአውሬ ጋር ታግለህ ታውቃለህ?
እነዚህ ጥያቄዎች ጭንቅላቱን ሲወጥሩት ታች በሌ መልስ አልነበረውም፡፡ የዠማን በረሃ ወደ መርሐ ቤቴ ሲያልፍበትና ወደ ጅሩ ሲወጣበት እንጂ ውስጡ ገብቶ ሥር ማንሥሩን አይቶት አያውቅም፡፡ እንዲያውም አሁን ሲያስበው ትንሽ ፍርሃት ሳይኖርበት አይቀርም፡፤ እንደ ሌሎቹ እንኳን ቅራት (ከብትን በረሃ ውስጥ ሌሊት መጠበቅ) ለብቻው አድሮ አያውቅም፡፡ ደግሞ አሁን ሸፍቷልና የሚያወያየው እንኳን የለም፡፡ እየዋለ እያደረ ሃሳብ ሲበዛበት ታች በሌ ይጨንቀው ነበር፡፡ ሽፍትነት ሲያስቡትና ሲሸፍቱት አንድ አልሆነለትም፡፡ እርሱ እዚህ በረሃ ውስጥ ምን እንደሚያደርግ ጨንቆታል፣ እዚያ መንደር ውስጥ ግን በስሙ ይዘፈን ይሆናል፡፡ የልቡን ማን አየለት፡፡ ለእርሱ ከሚዘፍኑለት ስንቅና ትጥቅ ቢያቀብሉት ነበር የሚሻለው፡፡
ታች በሌ ለአንድ ሳምንት በረሃው ውስጥ ተቀመጠ፡፡ ስንቅና እድሜ እያደር ይቀላል እንዲሉ የያዘው ነገር ሁሉ እያደር ያልቅበት፣ እርሱም ብቸኛነትን አልለመደውም ነበርና እያደር ሆድ ይብሰው ጀመር፡፡ አንዳንዴም ሲያስበው መሸፈት እንዳልነበረበት ራሱን ይሞግታል፡፡ አሁን እንዴት አድርጎ ወደፊት መጓዝ እንደሚችል ያስባል፤ ግን ምንም ሃሳብ ሊመጣለት አልቻለም፡፡ ወደ ኋላ እንዳይመለስ ሰው ምን ይለዋል? አንዳንዴ የተወለደበትን ቀን ትቶ የሸፈተበትን ቀን ይረግማል፤ አንዳንዴ ደግሞ እንኳን ሸፈትኩ ይላል፡፡ ቢጠብቅ ቢጠብቅ ጥዱም ሆኑ የጥዱ አንጋቾች ወደ አካባቢው ዝር ሊሉ አልቻሉም፤ ታድያ ሳይዋጋ ሽፍታ ተብሎ እስከ መቼ ሊቀመጥ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነኮ ጥቂት ቆይቶ ይረሳል፡፡
ታች በሌ እየቆየ ነገር ዓለሙ መረረው፤ መሸፈቱንን እንጂ ለምንና ምን ሊያደርግ እንደሸፈተ ለኅሊናው ማስረዳት አልቻለም፤ ቀጥሎ ምን እንደሚያደርግና ከዚያስ መጨረሻው ምን እንደሆነ ሊያውቀው አልቻለም፡፡ እገሌ ሸፈተ ሲባል እንጂ ሽፍትነት ምን እንደሆነ፣ ሸፍቶ ምን እንደሚደረግ በልቡ ምንም ነገር አልያዘም፡፡
አንድ ቀን ታች በሌ ድንገት የሚኖርበት መንደር ያለች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅዳሴ ሰዓት ከች አለ፡፡ አገርም ጉድ አለ፡፡ ካህናቱም ጨዋውም እያየው አፉን ይዞ ቀረ፡፡ ታምር ተሰምቶ የሰንበት ቂጣ ሊታደል ሲል ታች በሌ ድንጋይ ይዞ ሕዝቡ እግር ሥር ወደቀና ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው ብሎ በዚያ መከረኛ ላይ አላክኮ ካህናቱ ድንጋዩን አነሡለት፡፡
አንድ ሰሞን የታች በሌ ነገር የሞረቴ ሁሉ አፍ ማሟሻ ሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ ለሞረቴ መሸፈት ቀላል አልሆነም፤ ‹‹ደግሞ እንደ ታች በሌ ሲርብህ እንዳትመጣ›› የሚባለው ብዙ ነው፡፡ እንዲያውም አንድ ሰው ሸፈተ ሲባል አቅራሪዎቹ
ምከሩት፣
ምከሩት፣
ምከሩት፣
ይህንን ታች በሌ ለምን አትመክሩትም፤
ይህንን ታች በሌ ለምን አትነግሩትም፤
ልብ ካልሸፈተ እግር አይሸፍትም ….. ሃ!
እያሉ ይመክሩት ነበር፡፡ ታች በሌ ሳያስቡ ለሚወስኑና ሳያስቡ ለሚያደርጉ ሁሉ የሚሰጥ ቅጽል ሆነ፡፡
ታች በሌያዊ አስተሳሰብ የሀገራችን ተቋማት አንዱ ችግር ነው፡፡ አንዳንድ ፓርቲዎች፣ ማኅበራት፣ ድርጅቶች፣ ኩባንያዎችና ስብስቦች ሳይታሰቡ ተመሥርተው ሃሳብ የጠፋባቸው ናቸው፡፡ ለሃሳብ ተቋም ከመመሥረት ይልቅ ለተቋማቱ ነው ሃሳብ እየተፈለገ ያለው፡፡ ቁጭት ሁሉ፣ ብስጭት ሁሉ፣ ስብስብ ሁሉ፣ ገንዘብ ሁሉ፣ አጋጣሚ ሁሉ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ተቋም፣ ማኅበር ለመመሥረት መዋል የለበትም፡፡ እነ ዕገሌ ስለ መሠረቱ፣ እነ እገሌ ስለተሰባሰቡ፣ የዕገሌ አካባቢ ሰዎች በስማቸው ፓርቲ ስለመሠረቱ፣ የዚህ ዓይነት ሞያ ሰዎች ማኅበር ስላቋቀቋሙ፣ የዚያ ሀገር ሰዎች ኮሙኒቲ ስለ ፈጠሩ፣ እንቶኔና እንቶኔ ኩባንያ ስላቋቋሙ እኛም ማቋቋም የለብን፡፡  
መጀመሪያ ሃሳብ ይቅደም፡፡ ማሰብ ማለት ደግሞ ሃሳብን ብልጭ ማድረግ ማለት አይደለም፡፡ ይህማ ታች በሌን መሆን ነው፡፡ ብልጭ ያለውን፣ ቁጭት የፈጠረውን ሁሉ ሳያስቡበት ተጣድፎ ማድረግ፡፡ ማሰብ እንዲህ አይደለም፤ ግራ ቀኝ የታሰበበት፣ የተጠናና የተነበበበት፣ ከቀደምቶች ልምድ የተቀሰመበት፣ ከተሳካላቸውም ካልተሳካላቸውም ትምህርት የተወሰደበት፣ እንዴት እንደሚኬድ፣ ግቡ ምን እንደሆነ፣ የተሻለው መንገድ የትኛው እንደሆነ፣ የሚያስፈልጉ ነገሮች ምን እንደሆኑ፣ ከነ ማን ጋር መተባበር እንደሚገባ፣ ምን ሊያጋጥም እንደሚችል፤የፍልስፍና መስፈንጠሪያው ምን እንደሆነ አጥልቆና አልቆ መመርመር ነው- ማሰብ፡፡
አንዳንድ ሰው አስቤያለሁ ሲል ‹‹ይህ ነገር በአእምሮዬ መጥቶልኛል›› ማለቱ ነው፡፡ ይህኮ ሰው በመሆኑ ብቻ የሚያጋጥመው ነው፡፡ በአምስቱ የስሜት ሕዋሳቱ መረጃዎች ወደ አእምሮው ሲገቡ ልክ በቁልፍ እንደሚነሣ መኪና ቅንጭሌውን ሊያስነሡት ይችሉ ይሆናል፡፡ ይህ ግን መኪናው በቁልፉ ስለተነሣ ብቻ ሄደ እንደማይባለው ሁሉ ሰውዬውም አሰበ አያስብለውም፡፡ መጀመሪያ የመኪናው ባትሪ ቀጥሎ ሞተሩ መነሣት አለበት፡፡ ሞተሩ ደግሞ ሌሎችን ሁሉ አንቀሳቅሶ ሙሉ መኪናው መሥራት አለበት፡፡ ያን ጊዜ መኪናው ሄደ ይባላል፡፡
ሰውም ሃሳብ ብልጭ ስላለለት፣ የሆነ ቁጭት ስለተፈጠረበት፣ ከሆነ ሰው አንዳች ነገር ስላገኝ፣ በአጋጣሚ አንድ መረጃ ስለደረሰው፣ ቅናት ስላደረበት፣ ዕድል ስለተፈጠረለት፣ ዘመዶቹ ክፈት እንረዳሃለን ስላሉት ብቻ ተቋም፣ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ማኅበር መመሥረት የለበትም፡፡ አንዳንዶች የሆነ ነገር ለማድረግ አስበው ከመሰባሰብ ይልቅ ተሰባስበው ምን እንናድርግ? ብለው ያስባሉ፡፡ አንዳንድ ፓርቲዎች እንደ ታች በሌ ሳያስቡ የሸፈቱ ናቸው፡፡ የተለየ ሃሳብ፣ የተለየ ፍልስፍና፣ የተለየ አቋም፣ የተለየ መንገድ ሳይኖራቸው እንዴው በፓርቲዎቻችን ቁጥር ላይ አንድ ለመጨመር ያህል ብቻ የተመሠረቱ፡፡ ፓርቲው ከተመሠረተ በኋላ ነው ፕሮግራም፣ መመሪያ፣ ፍልስፍና፣ መንገድ፣ የሚያዘጋጁት፡፡ በሃሳብ ስለማይመሠረቱ ከተመሠረቱ በኋላ በሃሳብ ይለያያሉ፡፡ ሳስበው እንዲያውም ለሁሉም ችግሮቻችን መፍትሔ ስጡ ስንባል ኮሚቴ ማቋቋም የሚቀናን ለማሰብ ጊዜ ስለማንሰጥ ይመስለኛል፡፡ የስብሰባ፣ሞቅታ የፈጠራቸው ኮሚቴዎች ሃሳብ አጥተው ሲላጉ አባሎቻቸውን አንጠባጥበው መቼ እንደፈረሱ እንኳን ሳይታወቅላቸው ይፈርሳሉ፡፡ ታች በሌዎች በቁጭት ብቻ ተነሥተው የመሠረቷቸው የሞያ ማኅበራትም ከዓመታዊ ጉባኤ ያለፈ ሃሳብ ሊመጣላቸው ስላልቻለ፡፡ በአንድ ሊቀ መንበር ሃያ ዓመት እያዘገሙ እንዴት ናችሁ? ሲባሉ ‹አለን›› እያሉ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው ይኖራሉ፡፡
አንዳንዶችም አሉ፤ ምን እንደሚጽፉ ሳያስቡ መጽሐፍ ለመጻፍ የሚነሡ፡፡ ምን እንደሚገጥሙ ሳያስቡ ግጥም ለማሳተም የሚውተረተሩ፡፡ ምን እንደሚያቀርቡ ሳያስቡ ፊልም ለማዘጋጀት ገንዘብ የሚያሰባስቡ፡፡ የተለየ ሃሳብ ሳይኖራቸው የሬዲዮ የዐየር ሰዓት የሚገዙ፡፡ ምን እንደሚጠይቁ ሳያስቡ የቃለ መጠይቅ ማይካቸውን ተጠያቂው ላይ የሚተክሉ ቀልደኞች፡፡ ለነገሩ በሠፈር አንድ ሱቅ ሲከፈት የሠፈሩ  ሰው ሁሉ አጥሩን እየቀደደ ሱቅ መሥራት የተለመደበት ሀገር ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ያዋጣል ወይ? ከጎረቤቴ በምን እለያለሁ? እኔ ምን አዲስ ነገር አመጣለሁ? ብሎ ሳያስብ ነው ሱቁን ቦግ የሚያደርገው፡፡ ሱቁን ከሠራና ዕቃ ካስገባ በኋላ ነው ማሰብ የሚጀምረው፡፡ ይህ ነገር ወደ ተቋሞቻችንም ተጋብቷል፡፡ ምን ተቋሞቻችን ብቻ ትዳሮቻችንም እንዲህ እየሆኑኮ ነው፡፡ ማግባት የሚፈልግ እንጂ እንዴትና ለምን እንደሚያገባ፣ የጋብቻው ጠባይና አካሄድ ምን እንደሚመስል አስቀድሞ የሚያስብ ጥቂቱ ነው፡፡  የሆነ ቦታ ለመሄድ እያሰብኩ ነው፤ የሆነ ነገር ሳልከፍት አልቀርም፤ አንድ የሆነ መጽሐፍ ልጽፍ እያሰብኩ ነው፤ የሚላችሁ ሰው ሳያስብ አንዳች ነገር ሊያደርግ የተዘጋጀ መሆን አለበት፡፡
አስቦ መሥራት እንጂ ሠርቶ ማሰብ ኪሣራው ብዙ ነው፡፡ ገበያ መውጣታቸውን እንጂ ምን ሊገዙ እንደወጡ፣ ቤት መሥራትና መግዛት እንጂ ምን ዓይነት ቤት እንደሚገዙ ወይም እንደሚሠሩ፣ ውጭ ሀገር መሄድ እንጂ ለምንና እንዴት እንደሚሄዱ፣ የማያስቡ አሉ፡፡ በአንዳንድ ሀገሮች የነበረውን መንግሥት ስለመቀየር እንጂ በቅያሪው ስለሚመጣው መንግሥት ስላልታሰበበት የመጣው ከሄደው የባሰበት ጊዜ አለ፡፡ ለዚህ ነው ታች በሌያዊ የሆነውን መንገድ ትትን ሃሳብ ከተቋም ይቅደም የምለው፡፡ ሃሳብ ከድርጊት ይቅደም፡፡ ሃሳብ ከመመሪያም፣ ከዐዋጅም፣ ከማፍረስም፣ ከመሥራትም፣ ከመሸለምም፣ ከመቅጣትም፣ ከመሄድም ከመምጣትም ይቅደም ፡፡
አንድ ሰው እንዲያውም ይህንን ነግሮኛል፡፡ የአንድ ገበሬ ውሻ ሁልጊዜ መንገድ ዳር እየቆመ አላፊ አግዳሚውን መኪና ለመያዝ እየተከተለ ይጮኻል፡፡ የገበሬው ጓደኛ ይኼ የውሻው ጠባይ ይገርመዋል፡፡ አንድ ቀን ገበሬውን ‹‹ለመሆኑ ይኼ ውሻህ መኪናውን ተከትዬ እይዘዋለሁ ብሎ ነው እንዲህ መከራን የሚያየው?›› ይለዋል፡፡ ገበሬውም ሳቅ ብሎ ‹‹እኔ ለመያዝ መታገሉ አይደለም የሚያስገርመኝ፤ የሆነ ቀን ሊይዘው ይችላል፡፡ እኔን የሚገርመኝ መኪናውን ቢይዘው ምን እንደሚያደርገው ውሻው አለማሰቡ ነው›› አለው ይባላል፡፡ ታች በሌያዊ  አስተሳሰብ ማለት ይህ አይደለም ታዲያ፡፡

52 comments:

 1. በአንዳንድ ሀገሮች የነበረውን መንግሥት ስለመቀየር እንጂ በቅያሪው ስለሚመጣው መንግሥት ስላልታሰበበት የመጣው ከሄደው የባሰበት ጊዜ አለ፡፡

  ReplyDelete
 2. እሩቅ ሳትሔድ ግብፅን አታይም ! አታድርስ ነው።

  ReplyDelete
 3. tena yistilign memhir. sile kidst silasei college ande neger bel enji. sint memhranin yafera college temariwochun betno yizega sibal aykochim???

  ReplyDelete
  Replies
  1. esu esuma merageb yelebetem

   Delete
  2. የግድ ኮሌጁ በስም ካልተጠቀሰ በቀር፤ አጠቃላይ የጹሑፉ ጭብጥ እሱንም የሚዳስስ ይመስለኛል።

   Delete
 4. aya jebo awone sele semonu selfe menagerhe new
  alefobehale arfehe tekemete

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሕልምና ትርጉም እንደ ፈቺው ይሎል እንዲህ ነው።

   Delete
 5. አንድ ለራሴ! አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
 6. Dani,
  I give credit to Tachebele, at least he admitted his mistake, and asked apology. there to many "Keaferku Aymelesgne" people.

  ReplyDelete
 7. ‹‹እኔ ለመያዝ መታገሉ አይደለም የሚያስገርመኝ፤ የሆነ ቀን ሊይዘው ይችላል፡፡ እኔን የሚገርመኝ መኪናውን ቢይዘው ምን እንደሚያደርገው ውሻው አለማሰቡ ነው››

  ReplyDelete
 8. ሰሎሞን በርሔ /ሱዳን/July 17, 2013 at 10:31 AM

  ይህ ጉዳይ እኛ ዘንድም የሚከስትበት ጊዜ አለ:: ሁሉም ነገር በስሜት ያይደለ እየተስተዋለ ቢሆን መልካም ነው:: ዲያቆን ዳንኤል እናመስግናለን::

  ReplyDelete
 9. quale hywot yasemalegn

  ReplyDelete
 10. አንድ ቀን ገበሬውን ‹‹ለመሆኑ ይኼ ውሻህ መኪናውን ተከትዬ እይዘዋለሁ ብሎ ነው እንዲህ መከራን የሚያየው?›› ይለዋል፡፡ ገበሬውም ሳቅ ብሎ ‹‹እኔ ለመያዝ መታገሉ አይደለም የሚያስገርመኝ፤ የሆነ ቀን ሊይዘው ይችላል፡፡ እኔን የሚገርመኝ መኪናውን ቢይዘው ምን እንደሚያደርገው ውሻው አለማሰቡ ነው›› አለው ይባላል፡፡ ታች በሌያዊ አስተሳሰብ ማለት ይህ አይደለም ታዲያ፡፡

  ReplyDelete
 11. ታች በሌዎች በቁጭት ብቻ ተነሥተው የመሠረቷቸው የሞያ ማኅበራትም ከዓመታዊ ጉባኤ ያለፈ ሃሳብ ሊመጣላቸው ስላልቻለ፡፡ በአንድ ሊቀ መንበር ሃያ ዓመት እያዘገሙ እንዴት ናችሁ? ሲባሉ ‹አለን›› እያሉ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው ይኖራሉ፡፡

  ReplyDelete
 12. ኦ ዲ/ን ዳንኤል! ቃላቲከ ያጠልሉ አዕጽምተ ከመ ዜማ ያሬድ አቡከ፤ ወያስተፈሥሁ ልበ ከመ ወይን ዘቤተ እምከ፡፡እስተቲ
  እስቲ ለዲ/ን ዳንኤል አንዲት …የግእዝ ቅኔ
  “ዘርአ ቤተ ዳንኤል ምክር ፍኖተ ኢንተርኔት ዘወድቀ፣
  ለሕጹጹነ ልብ አእዋፍ ይኵኖሙ ስንቀ፡፡”
  Kassa ze raya

  ReplyDelete
  Replies
  1. can you tell us the meaning of this kine? I wish I know geez.

   Delete
  2. ሲመስለኝ ቅኔዉ ሚለዉ፡

   የዳንኤል ቤት(ብሎጉን)የምክር ፍኖት በኢንተርኔት ዘራ
   ለተሳሳቱ ልቦች ይሁናቸዉ ስንቅ፡፡

   ይህ እኔ የተረዳሁበት መንገድ ንዉ የቅኔ እዉቀት የለኝም ግን ለመርዳት እመክራለሁኝ፡፡ ከተሳሳትኩኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ፡፡

   Delete
 13. Let us see our selves on your mirror & try to learn from it.Any way thanks a lot.I am always eager to read your posts.God bless you.

  ReplyDelete
 14. ስለታች በሌ ሳነብ አንድ ነገር አስታወስከኝ የአያቶቼን አገር ከዛሬ ሐያ አመት በፊት እንደዚህ አይነት ጨዋታዎችን ይነግሩኝ እና አውቅ ነበር የሚገርመው ነገር ከት/ቤት ጓደኞቼ ጋር በእድሜ እኩያ ከሆነው ማለት ነው የእኔ ነገር አይገጥም ነበር ሁል ጌዜ ነገርን በምሳሌ ስለሜናገሩ እኔም የእነሱ አባባል እንደልብስ ወርሼው ማለትን ነው አሁን እንደዚህ አይነት ነገር በምሳሌ የለምእኮ እንደው ደክመህ እንደነታች በሌ አባባል ለአሁን ትውልድ መሳቂያ ነው የሚሆኑት እኒስ የናፈቀኝ ከከተማው ሰው ይልቅ የገጠሩ ሕብረተሰብ ነው ሲያናግርሕ በፍቅር ሲጠላሕም በግልፅ ወደኋላ የሚባል ነገር የሌለበት ሕብረተሰብ የአሁን ትውልድ በሬ ካራጁ ይውላል ብቻ ነው እባክህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አስቦ መሥራት እንጂ ሠርቶ ማሰብ ኪሣራው ብዙ ነው፡፡ tikikil bilehal Dn. Daniel. enamesegnalen.

   Delete
 15. ውጭ ሀገር መሄድ እንጂ ለምንና እንዴት እንደሚሄዱ፣ የማያስቡ አሉ ይህ መልዕክት በአብላጫው በውጭ ሃገር በስደት ላይ የምንገኘው ሁሉ ያካተተ ነው ማንም አስቦ አልሞ የተሰደደ አለ ለማለት ያቅታል ሁሉም ቢጠየቅ እኔ እኮ እንደዚህ አልመሰለኝም ነበር ስደት
  ለመማር ለመሥራት ወገንን ለ መርዳት ቤተሰብን ከድህነት ለማውጣት ነበር ነበር ፍላጎቴ
  ነገርግ ሁሉ ነገር ተለውጦ ረጅው ተረጂ ሆኖ ለረጅም ዘመናት እንኳን ሊሰራና ሊማር በመኖሪያ
  ፈቃድ ውጣ አትውጣ ጭቅጭቅ ስንቶች የአዕምሮ በሽተኞች እራሳቸውን ያጠፉ ባህር ውስጥ የሰጠሙ ቤቱ ይቁጠረው

  ReplyDelete
 16. amazing one! great, u r working on our mind! poverty is the result of ignorance, lets kick out ignorance......then poverty will be forced out.

  ReplyDelete
 17. ሳስበው እንዲያውም ለሁሉም ችግሮቻችን መፍትሔ ስጡ ስንባል ኮሚቴ ማቋቋም የሚቀናን ለማሰብ ጊዜ ስለማንሰጥ ይመስለኛል፡፡

  Thanks Dani. You made my day.

  ReplyDelete
 18. melikam eyitanew belelochim zuriya yalehin eyita akafilen, egzer yisitilin

  ReplyDelete
 19. I believe Dn. is getting closer to show us his true colour. He seems worried to me with Ethiopian people opposition movement and trying to influence and discourage. To me people can be tired of reparation and "divide and rule" ethnocentric rule. It seems to me that he has no clue about social dynamics. It can be like a wave that can be transmitted. Dn you can visualize a drop of water in a big pool with a very tinny small circle that progressively increases its circumference and grow as big as the size of the big pool. I mean do not see the problem of starting something with crude emotion and purifying it at a later stage. You seem to me misusing your religious based popularity to invisibly support the ruling class. I mean I know you know how to please your readers. I can see you brainwashing. Look at your victims jumping in to hasty generalization and talking about Egypt. Even so Egyptians and Tunisians are at least played a good role model in saying no to Tyrants. Formation of clear party
  mission and vision can not be all ways the first step to at least to say no to the barbaric rule.
  Please let people think their way including like Mr Tachbele and go to the bush and start something and then we will see if they fail to get supporters and come back for apology. Mr Tachbele's case is very very different than the idea that you are targeting to discourage.
  Let the almighty God be with you Memhir.

  ReplyDelete
  Replies
  1. As per understanding it is to say only "ከተቋም ሐሳብ ይቅደም" So ባይለጠጥ

   Delete
  2. I think you have completely missed the central point of this article, my friend. Let me spell it out for you in a single sentence: "Think First, act next!" I don't understand why you're so against this universal truth. You've said that you didn't see the problem of starting something with crude emotion and purifying it at a later stage. Well, the problem that I see is, when we start re-thinking the motive, and understand the scale of the damage that this motive, driven by "crude emotion" may have brought, the aftermath may not be irreversible. Especially, if the end-result is the loss of lives, a pile of apologies will never make up for the damage. So why is it difficult for us, the people of the 21st century, to give priority to the thinking part before we jump straight into action? Daniel's viewpoint has got absolutely nothing to do with brainwashing; it's rather an eye-opener for all of us to choose the right course of action on our every decisions. I suggest you too should open your eyes now and see the truth in this country. You'll find the truth for yourself, for that's what we've been witnessing over the years.

   Delete
  3. You do not care when your people kill and imprison non-stop. You care only when the arrow direction points towards your group. That is when you start seeing us in the 21st Century. Aren't we witnessed more than 200 people killing in our capital in day light? or was that before the 21st century? How about not giving permission to sit and think and plan?
   My last but not least is to you personally, I am not sure about your reading ability and habit, but I can give you so many references on the core issue. That is tangible evidences that led people to success starting from "crude emotion" and resistance or saying no to....It really amazes me to read you saying Woyane was correct to go to the bush with the crude emotion and not purified yet and is still in hate full of emotion of the people's religion, ethnicity,etc.

   Delete
 20. ወታደር ግርማ ወንድሙ ቄስ ሆነው ክርስቶስ የሰራቸውን ታኣምራት እሰራለሁ እያለ በህዝብ ሲጫወት: ይህ ሁሉ ግፍ ሲሰራ የቤተክርስቲያን አባቶች የት ሂደው ነበር::
  ይህንን ቪዲዮ በድንብ አድርጋቹ ተመልከቱ፥፥ አስገራሚ ድራማ፥አንዱ ተዋናኝ በተለያዮ ጊዜ ትውናውን ሲሰራ ይመልከቱ::
  http://www.youtube.com/watch?v=7KtapCuogrc

  ReplyDelete
  Replies

  1. "ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤" ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ 1 : 27

   “የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።” 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፥ምዕራፍ 1 ቁር 18

   Delete
 21. Yerasen tarik negerkegne...but I still liked it. Great job, qale hiwot yasemalin.

  ReplyDelete
 22. melkam eyeta new enamesegenalen Dani.

  ReplyDelete
 23. it is a good view thank u d.daniel

  ReplyDelete
 24. አስቦ መሥራት እንጂ ሠርቶ ማሰብ ኪሣራው ብዙ ነው

  ReplyDelete
 25. I have starting to think.

  ReplyDelete
 26. ወንድም ዳንኤል በጣም ጥሩ ምክር ነው የመከርከን ግን ለሚገነዘብ እንጂ ለሌላው ወሬ ነው፡፡ ይሁንና እግዚአብሔር ወደፊትም ከአንተ ጋር ሆኖ ይህንን መንገድህን እስከፍፃሜው ያቅናልህ፡፡ ሌላው ግን የዲ/ን ዳንኤል ድረ ገጽ ብዙ አንባቢ አለው በማለት የማይገናኝ ሀሳብ ለማንሳት የሞከራችሁ ወገኖች ቆም ብላችሁ አስቡ፡፡ ታች በሌ መጀመሪያ መሸፈቱ ሳይሆን ብዙ ሳይደክም አቅሙን አውቆ መመለሱና ይቅርታ መጠየቁ ትልቅ ትምህርት ቤት ከመግባት በላይ መሆኑን ያስረዳናል፡፡ ስለ መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ለማውራት የፈለግከው ወይ ጠንቋይ፣ ወይ አስጠንቋይ፣ ወይ ባለዛር ውላጅ በመሆንህ በአንተ ላይ ያደረ አጋንንት አይነጥላ አዙረህ እንዳታይ እንደ ጋሪ ፈረስ ሸብቦ እየነዳህ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ኃይል በመርሳት ወታደር ነበር፣ነጋዴ፣ገበሬ እያልክ ብታወራ የምታመጣው የለም የዓለም ሕዝብ አንተ ከምትለው ሀሳብ ባለፈ በሲዲ ብቻ ሳይሆን በአካል ተገኝቶ በመረዳት ሕይወቱን ከሞተ ስጋ ብቻ ሳይሆን ከሞተ ነፍስም እያዳነ ነውና ንስሐ ገብተህ ሰይጣንን ክደህ በእግዚአብሔር መንገድ ብትሔድ ይሻላል እላለሁ፡፡
  ዲ/ን ዘላለም

  ReplyDelete
 27. Thank you Deacon Denial Kibret ....for someone to change or to start to do something does not only need once thinking or one time brain storm idea.the particular person or thing who or which want to change himself or herself needs to answer 3/4 question: do I have the equivalent means to tackle the problem? Do I have the strategy to combat the problem? The final question is after I removed the problem can I make sure the problem will never come back again or do I have everything to make sure I will not face the same problem after I removed the problem........But please someone would you answer me since every human being has not have the same capacity to do something or to accommodate the same thing! My question is what if someone reach at the boiling point of the problem and does not have the time for critical thinking or does not have a capacity for a critical thinking?

  ReplyDelete
 28. ግንኮ አንዳንዴ ማሰብ ማብዛትም የማያስፈልግበት ቦታ አለ፡፡ intuition, instinct ወይም gut reaction ይሉታል፡፡ብዙ ስታስብ ወይም ስታወራ ያደረከዉ ይመስልሃል፡፡ ከዚ ከዚ እንደ ታችበሌ ከስህተት መማር ሳይሻል አይቀርም፡፡

  ReplyDelete
 29. ወንድም ዳንኤል በጣም ጥሩ ምክር ነው

  ReplyDelete
 30. ወንድም ዳንኤል በጣም ጥሩ ምክር ነው የመከርከን

  ReplyDelete
 31. I HAVE LEARNT ALOT THANK YOU DANI FOR YOUR INVESIGATION . I HOPE THAT SUCCESS FOR YOU.

  ReplyDelete
 32. dani and tiyake liteykh ebakih melislign ende metshaf kidus fikir menden new simet new weys men

  ReplyDelete
 33. Thankyou!Decon Daniel Your view always give me a peace of mind

  ReplyDelete
 34. Our thought need to drive us a..l..w..a..y..s, not z reverse. Bro, thanks 4 sharing Ur precious opinion on life.

  ReplyDelete
 35. ዉዳሴ ከንቱ እንዳይሆነብህ .......................።

  ReplyDelete
 36. ዉዳሴ ከንቱ እንዳይሆነብህ ።

  ReplyDelete
 37. ዉዳሴ ከንቱ እንዳይሆነብህ ።

  ReplyDelete
 38. ዉዳሴ ከንቱ እንዳይሆነብህ ።

  ReplyDelete
 39. የተለየ ሃሳብ፣ የተለየ ፍልስፍና፣ የተለየ አቋም፣ የተለየ መንገድ ሳይኖራቸው እንዴው በፓርቲዎቻችን ቁጥር ላይ አንድ ለመጨመር ያህል ብቻ የተመሠረቱ፡፡ ፓርቲው ከተመሠረተ በኋላ ነው ፕሮግራም፣ መመሪያ፣ ፍልስፍና፣ መንገድ፣ የሚያዘጋጁት፡፡ በሃሳብ ስለማይመሠረቱ ከተመሠረቱ በኋላ በሃሳብ ይለያያሉ፡

  ReplyDelete