Friday, July 12, 2013

እየበሉ መራብ


ሁለተኛው ጉዳይ
(ባለፈው ሳምንት ከወላጆች ጋር በሁለት ጉዳዮች ለመነጋገር ተነሥቼ ነበር፤ የመጀመሪያውን ሳምንት አቅርቤአለሁ፤ በየቦታው መወያያ መሆኑን ፍንጭ አግኝቻለሁ፤ እስኪ ሁለተኛውን ዛሬ ላቅርብ)
አንዲት እኅት እንዲህ አወጋችኝ
ለዶክትሬት ጥናቷ ከአሜሪካ ትመጣና አጎቷ ቤት ታርፋለች፡፡ አጎቷ ‹አላቸው› ከሚባሉት የከተማችን ባለ ሀብቶች አንዱ ነበር፡፡ ሁለት ወንዶች ልጆች አሉት፡፡ ልጆቹ የሰባትና የዐሥር ዓመት ልጆች ናቸው፡፡ ልጆቹ በተደጋጋሚ ይታመማሉ፡፡ በሳምንት ቢያንስ አንድ ጊዜ ከሐኪም ቤት አይጠፉም፡፡ ‹‹አንድ ጊዜ እኔ ምሳ ስበላ ልጆቹን ጠራኋቸውና አብረን እንድንበላ ጋበዝኳቸው፡፡ እንጀራ እንደማይበሉ ነገሩኝ፡፡ ምንድን ነው ታዲያ የምትበሉት? አልኳቸው፡፡ ከሱፐር ማርኬት የሚገዛ አንድ የምግብ ዓይነት ነገሩኝ፡፡ ሞግዚታቸውም ያንን ይዛላቸው መጣች፡፡ በዚያ ጊዜ አንዳች ነገር ከነከነኝና ምሳዬን ከጨረስኩ በኋላ ወደ ማዕድ ቤቱ ገብቼ ሞግዚቷን ጠየቅኳት፡፡ ምንድን ነው እነዚህ ልጆች አዘውትረው የሚበሉት? እስኪ አሳይኝ? አልኳት፡፡ መደርደሪያውን ስትከፍተው ሁሉም ከሱፐር ማርኬት የሚገዙ የተፈበረኩ ምግቦች ናቸው፡፡ እጅግ በጣም ገረመኝ፡፡ 

በቀጣዩ ቀን ከልጆቹ ጋር ብስክሌትና ኳስ አብሬ ተጫወትኩ፡፡ ብዙ ጊዜ ወላጆቻቸውን ስለማያገኙ ከእኔ ጋር በመጨዋታቸው ደስ አላቸው፡፡ ከሰዓትም አብሬያቸው እንድጫወት ለመኑኝ፡፡ እኔም ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሜ ከእኔ ጋር አብረው ምሳ ከበሉ ብቻ እንደምጫወት ነገርኳቸው፡፡ ቅር እያላቸው ለጨዋታው ሲሉ ተስማሙ፡፡ ቋቅ እያላቸውም በምሳ ሰዓት እንጀራውን በወጥ አብረውኝ በሉ፡፡ ቃል እንደገባሁትም አብሬያቸው ተጫወትኩ፡፡ በቀጣዩ ቀን ከባልትና ቤት የገንፎ እህል ገዝቼ መጣሁ፡፡ ከዚያም ገንፎ ሠራሁና አብረን እንድንበላ ጋበዝኳቸው፡፡ እንደምንም በሉልኝ፡፡ ቆሎ የሚባለውን ነገርማ ነክተውት ቀርቶ አይተውት አያውቁም፡፡ እኔ ግን ቆሎ ለጥርሳቸው ጥንካሬ እንደሚጠቅም፤ ኳስ ተጫዋች መሆን ከፈለጉ ደግሞ መጠንከር እንዳለባቸው፤ ለዚህም ከልዩ ልዩ ጥራጥሬ የተሠራው ቆሎ እንደሚጠቅም ነገርኳቸው፡፡ አብሬያቸው እየተጫወትኩ ስለምነግራቸው ተቀበሉኝ፡፡
በመጀመሪያው ቀን ለጥርሳቸው እንዳይከብዳቸው ለዘዝ ያለ ቆሎ እንዲበሉ አደረግኩ፡፡ ኳስ እንጫወትና በዕረፍት ሰዓት ቆሎ በልተን ውኃ እንጠጣለን፡፡ የተሰጠውን ያህል ያልበላ ይቀጣል እያልን ጨዋታ አደረግነው፡፡ ቂጣውንም በዚህ መልክ ነበር ያስለመድኳቸው፡፡ ማር የተቀባ ቂጣ መብላት አልለመዱም፡፡ ብስክሌት ለመንዳት ግን ቂጣ አስፈላጊ መሆኑን ነገርኳቸውና በብስክሌታቸው ጭኜ ስንነዳ እንበላ ነበር፡፡
እንዲህ እያደረግኩ ሰምተዋቸውም ተመግበዋቸውም የማያውቋቸውን ምግቦች አስለመድኳቸው፡፡ የሚገርምህ ነገር በየሳምንቱ ሐኪም ቤት መሄዱ ቀረ፡፡ ለካስ የእነዚህ ልጆች ችግር የምግብ ችግር ነበር፡፡ ከሱፐር ማርኬት የሚመጡ ምግቦችን እንጂ በባህላችን የሚዘጋጁና ለልጆች የሚያስፈልጉ ነገሮችን የያዙ ተፈጥሯዊ ምግቦችን አይመገቡም ነበር፡፡ ለካስ ልጆቹ እየበሉ የሚራቡ ነበሩ፡፡
ወላጆቻቸው ገንዘብ አላጡም፤ መግዛት የማይችሉም አይደሉም፡፡ ነገር ግን ልጆቻቸውን የወደዱ የሚመላስቸው፣ ልጆቻቸውንም የተከባከቡ የሚመስላቸው ከየሱፐር ማርኬቱ የሚገዙ የተፈበረኩ ምግቦችን በመግዛት፣ በጣፋጮች በማንበሽበሽ፣ ለልጆቹ ስሜት እንጂ ለልጆቹ ጤንነት የማይጠቅሙ የተፈበረኩ ምግቦችን በመስጠት ነው፡፡ ለእነርሱ ዘመናዊነት ማለት የታሸገ ምግብ ነው፣ ጣፋጭ ምግብ ነው፤ የሚገዛ ምግብ ነው፡፡ ርግጥ ነው ልጆቹ ደስ ይላቸዋል፡፡ ‹‹ማሚ እወድሻለሁ፤ ዳድ እወድሃለሁ›› እያሉ ደስታቸው እንዲጨምር ያደርጉታል፡፡ ደጋግመውም እንዲገዙላቸው የሚፈልጉት ይህንኑ ይሆናል፡፡ እነርሱም ብላ አትብላ ከሚለው ጭቅጭቅ ይድኑ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ልጆቹን እየገደልናቸው ነው፡፡ በሁለት መንገድ፡፡
በአንድ መልኩ ማኅበራዊነትን እናሳጣቸዋለን፡፡ አንድ ልጅ ሀገሩን እንዲወድድ፣ ለሀገሩ እንዲያስብና ማኅበረሰቡን ዐውቆ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ‹ማኀበር› socialization ያስፈልገዋል፡፡ ከማኅበረሰቡ ጋር መግባባት፣ መላመድና ማኅበረሰቡን መሆን፡፡ ከማኀበሪያ መንገዶች አንዱ ደግሞ አብሮ መብላትና መጠጣት ናቸው፡፡ እነዚህ ልጆች ሠርግ፣ ማኅበር፣ ተዝካር፣ ግብዣ እንዴት ነው የሚቀበሉት?  ነገስ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዴት ነው የሚሠሩት? በሌላም በኩል እዚህ ሀገር የሱፐር ማርኬት ምግቦች በዘላቂነት አይገኙም፡፡ ይቀያየራሉ፡፡ ዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ልጆችህ የለመዱት ምግብ ነገ የለም ትባላለህ፤ ያን ጊዜ ልጆቹን ሌላ ነገር ማስለመድ ችግር ይሆንብሃል፡፡
ምን ይሄ ብቻ፡፡ ብዙ ጊዜ የታሸጉ ምግቦች የሚሠሩባቸው ነገሮች ልጆችን ያቃዥቧቸዋል፡፡ ስሜታውያን አድርገው ዕረፍት አልባ ያደርጓቸዋል፡፡ ያን ጊዜ ልጆቹ ረባሾች፣ ቀዥቃዣዎች፣ የማይሰሙ፣ ቀልበ ቢሶች ተደርገው በወላጆቻቸው፣ በቅርብ ዘመዶቻቸውና በሌላው ማኅበረሰብ እንዲነወሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ይሄም ለልጆቹ ከማኅበረሰቡ ጋር አለመቀላቀል አንዱ ምክንያት ይሆናል፡፡
ሁለተኛው ጉዳት ደግሞ ልጆቹን የቅንጦት ረሃብ ውስጥ መጣሉ ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ በምዕራቡ ዓለም ተፈጥሯዊ ምግቦችን መመገብ የሥልጣኔና የጤንነት ምልክቶች ናቸው፡፡ ውድ ምግቦችም ተፈጥሯዊ ምግቦች ናቸው፡፡ እኛ ሀገር እነዚህን ተፈጥሯዊ ምግቦች ብዙ ጊዜ የሚያገኙት ‹ድኾች› ናቸው፡፡ እስኪ ዝም ብለህ እይ በከተሞቻችንኮ የተጠበሰ በቆሎ መብላት፣ ቆሎ መብላት፣ ንፍሮ መብላት እየቀረ ነው፡፡ እነዚህ ምግቦችኮ ያልያዙት የንጥረ ነገር ዓይነት አልነበረም፡፡ ገንፎ እንኳንስ ከምግብ ዝርዝራችን ከአራስ ቤትም እየጠፋ ነው፡፡ እኔ የጃፓኖች ምግብ ቤት ገብቼ ከዶሮ ሥጋ ጋር የተቀቀለ በቆሎ ነበር ያቀረቡልኝ፡፡ አሁን እኛ ሀገር እንግዳ ጠርተህ የተቀቀለ በቆሎ ብታቀርብ ስምህ ነው የሚጠፋው፡፡ አንተ ራስህ ግሪክ ሀገር የተጠበሰ በቆሎ በሰባት ዶላር መግዛትህን ስትናገር ሰምቼሃለሁ፡፡ እኛ ሀገር ግን የተጠበሰ በቆሎ ምብላት የድህነት ምልክት ነው፡፡
ልጆቻችንኮ የተመጣጠነ ምግብ እየተመገቡ አይደለም፡፡ ይህ የሆነው በማጣታችን ምክንያት ብቻ አይደለም፡፡ ርግጥ ነው በምግብ እጥረት የሚጎዱ ሚሊዮን ልጆች አሉን፡፡ እኔ ግን የማወራህ በቅንጦት ረሃብ ውስጥ ስላሉት ልጆች ነው፡፡ ድንች እንደ ልብ በሚገኝበት ሀገር፣ በርካሽ ገዝቶ ቀቅሎ ማብላት ሲቻል እንዴት የታሸገ ድንች ጥብስ እናበላቸዋለን፡፡ እኛ በውድ ዋጋ ገዝተን ከምናበላቸው የታሸገ የድንች ጥብስ ይልቅ እነዚህ መንገድ ዳር የተቀቀለ ድንች ገዝተው (እምቦቲቶ) የሚበሉት ይበልጣሉ፡፡ እነርሱ ጋር ችግሩ ንጽሕናው ነው፡፡ በይዘቱ ግን ትክክለኛውና ጤነኛው የእነርሱ እምቦቲቶ ነው፡፡ ቡላና የገብስ ቂጣ እንደልብ በሚገኝባት ሀገር እየኖርን እንዴት ልጆቻችንን በታሸገ ዱቄት እናሳድጋቸዋለን?
ይኼ ፈጽሞ ልጅን መውደድ ሊሆን አይችልም፡፡ የማይሆኑ ምግቦችን እየመገብን ልጆቻችን በትምህርታቸው ሰነፍ ሆኑ ብለን ደግሞ እናማርራለን፡፡ እኔ ድሮ ድሮ የገጠር ልጅ ለምን ጎበዝ እንደሚሆን አሁን ነው የገባኝ፡፡ ገጠርኮ ልጆች ሁሉንም ዓይነት ምግብ ይበላሉ፡፡ የሚዘሩትንና የሚያበቅሉትን ተወው፡፡ ከጫካ የሚገኙ፣ ጤናማ የሆኑና በንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ስንት ምግቦች ነበሩ፡፡ እነዚህ ምግቦች እኔ ሕጻን እያለሁ ከገበያ በቀላሉ እናገኛቸው ነበር፡፡ አሁን እንኳን ከተማ ገጠር መገኘታቸውንም እንጃ፡፡ እነ እንኮይ፣ እነ ሾላ፣ አነ ባምባ፣ እነ ኮሽም፣ እነ ግብጦ፣ የት ሄዱ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምታገኛቸው ከ500 ዓመት በላይ የኖሩት አበውኮ እነዚህን ተፈጥሯዊ ፍራ ፍሬዎች ነበር የሚመገቡት፡፡
የገጠሩም ሰው ዛሬ ዛሬ ሥልጣኔ የሚመስለው ልክ እንደ ከተማው ያለ አመጋገብ ነው፡፡ እነርሱ የሚያወጡት ቅብዐ ኑግ እኛ ከዱባይ ከምናስመጣው ዘይት እንደሚበልጥ ልንነግራቸው ይገባል፡፡ ልጅን መውደድ ማለት የሱፐር ማርኬት ምግብ መመገብ ሳይሆን በአካባቢው የምናገኛቸውን ምግቦች እያፈራረቁ እያመጣጠኑ መመገብ ማለት መሆኑን መንገር አለብን፡፡ ይህ አስተሳሰብ በመዛባቱ የተነሣ ቤተሰቦቻቸው በትክክለኛ መንገድ የሚያሳድጓቸው ልጆች እንኳን እንደ ሌሎቹ የተፈበረኩ ምግቦችን ስላልበሉ እያማረሩ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሬዲዮውና ቴሌቭዥኑ በእነዚህ ምግቦች ማስታወቂያዎች የተሞሉ ናቸዋ፡፡
ሲሆን ሲሆን በየብሔረሰቡ ያሉትን ምግቦች አጥንተን ወደ ሀገራዊው ባህል እንክተታቸው፡፡ አንደኛ በቀላሉ ይገኛሉ፡፡ እኛው ጋ ነዋ የሚበቅሉት፤ ሁለተኛ የተፈጥሮ ናቸው፡፡ ከጎጂ ነገሮች ነጻ ይሆናሉ፡፡ ሦስተኛ አሠራራቸው ቀላል ይሆናል፤ በባህል ተሞክረውና ተፈትነው የወጡ ናቸውና፡፡ እነ ጣልያንኮ ፒዛን ከኤርትራ ነው የወሰዱት፡፡ የትግራይ ሰዎች ቂጣውን በቅቤና በአዋዜ የመብላት የቆየ ባህል ነበራቸው፡፡ ጣልያኖች አዋዜውን በቲማቲም ተኩትና ፒዛን አመጡት፡፡ ዛሬ ልጆቻችን ፒዛ ነው እንጂ ቂጣ አንወድም ሲሉ ዝም እንላቸዋለን፡፡
ባይሆን ባህላዊ ምግቦችን ለልጆች በሚጣፍጣቸውና በሚስባቸው መንገድ እንዴት እናቅርባቸው? ብለን ወላጆች መምከር አለብን፡፡ እንደ ምዕራባውያኑ ልጆቹ ከተጎዱና ለአደጋ ከተጋለጡ በኋላ ጉዳዩ ሀገራዊ ጉዳይ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም፡፡ እንዲያውም ከከተማው ይልቅ የገጠሩ ሕዝብ በባለሞያዎች የሚሰጠውን ሃሳብ እየተቀበለ የልጆቹን አመጋገብ እያስተካከለ መሆኑን አንዳንድ ቦታዎች አይቻለሁ፡፡ ጭብጦውን እንዲቀይሩ አይደለም፡፡ ጭብጦውን ከልዩ ልዩ እህሎች በተፈጨ ዱቄት እንዲሠሩት ነው ያስተማሯቸው፡፡ ካገኙ ትንሽ ወተት እንዲያደርጉበት፣ ከተቻለ ደግሞ ቅቤ እንዲጨምሩበት ነው የሚያስተምሯቸው፡፡ ክክ ወጡን እንዲተውት አይደለም የነገሯቸው፤ ክኩን የአተር ብቻ ከማድረግ የሌሎችንም ጥራጥሬዎች እንዲያደርጉት ነው፡፡ ››
ለእኔ እያብራራችልኝ በሄደች ቁጥር ንዴቷ እየጨመረ መጣ፡፡ ሞያዋም፣ ትምህርቷም ስቧት ብዙ ነገር ታዝባለች፡፡ ነገር ግን ከዘመዶቿ ጋር እንኳን በዚህ ጉዳይ መስማማት አልቻለችልም፡፡
‹‹ምናልባትኮ ወላጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ሲልኩ አልበላም ስለሚሏቸው ይሆናል›› አልኳት፡፡
‹‹ልጆችኮ አልበላም የሚሉት ከብዙ ነገር አንጻር ነው፡፡ የምግቡ አዘገጃጀት፣ የጓደኞቻቸው ተጽዕኖ፣ የመመገቢያው ዕቃ፣ ሌሎችም አብረው መታየት አለባቸው፡፡ እንዲያውም እነዚህ ከሱፐር ማርኬት የሚገዙ ምግቦች ልጆቹን ለሌሎች ምግቦች ማለማመጃ ሊሆኑን ይችላሉ፡፡ ሌሎች ምግቦችን ለሚመገቡ ልጆች እንደ ሽልማት በመስጠት፡፡ በሌላም በኩል ልጆቻችን በራሳቸው እንዲተማመኑ ማስተማርም አለብን፡፡ ማሳመን አለብን፡፡ ራሳቸውን እንዲሆኑ፡፡ ይሄ ባህሌ ነው፤ ይህንን እወዳለሁ እንዲሉ፡፡››
ሃሳቧ እጅግ አብዝቼ እንዳስብ አድርጎኛል፡፡ በተለይም ‹የቅንጦት ረሃብ›› ያለችው ነገር ልክ ነው እያልኩ ከራሴ ጋርም ከቤተሰቤ ጋርም ብዙ ሰዓታት ተነጋግሬበታለሁ፡፡ እስኪ ወላጆች ተነጋገሩበት፡፡ ወቅቱ ትምህርት ቤቶች የተዘጉበት በመሆኑ የልጆቻችንን አመጋገብ ለማስተካከል ምቹ ጊዜ ላይ ነን፡፡  ለመሆኑ በየቤታችን የቅንጦት ረሃብ የለም? በየቤታችን የልጆቻችን አመጋገብ የታሰበበት ነው? ስለምንገዛላቸው እንጂ ስለሚመገቡት ነገር እናስባለን፡፡ እኛ ገዛን፣ ሞግዚቶቻቸውስ ይመግቧቸዋል? እስኪ የሰሞኑ የቤተሰብ አጀንዳ ይኼ ይሁን፡፡45 comments:

 1. betam yemigerm eyetea new daniel beand weket telek ena tawaki behone temehert bet asetemari hogne esera neber ena bizu ligoch yemiyezut megeb betam yemiyasazen new .lemesalee nuddles yemibal neger .eyetah betam arif new ligoch amegagebachew betam tenekke yefelegal .

  ReplyDelete
 2. እንዲህ ንገሩን እንጂ:: እኔ አሁን ዶክተር ነኝ?
  ከምር እኮ ማስተካከል ያለብን ነገር ነው:: ውጭ እያለሁ እንደውም የማስታውሰው ነገር ሀብታሞች እኛ አገር እንደምናስበው የፋብሪካ ምግብ አይደለም የሚጠቀሙት:: የታሸገ ምግብ መብላት ለምን የሀብት መገለጫ እንደመሰለን አላውቅም:: በአንድ ስብከትህ ያልከውን አስታወሰኝ "የኛ ሀገር ሀብታም የሚታወቀው መሚያገባው ገቢ ሳይሆን በሚያወጣው ወጪ ነው::" ለውጡን የግድ ማምጣት አለብኝ:: እኔ ግን ውይይቱን ዛሬ እንደምጀምረው ልነግርህ እፈልጋለሁ::
  ፀጋውን ያብዛልህ!

  ReplyDelete
 3. Well said.... it is very important and timely. thank you Dani

  ReplyDelete
 4. አብዛኛው የሀገራችን ወላጅ የሚያስጨንቀው ያለውን ገንዘብ አብቃቅቶ ዋጋው ዝቅተኛና ለወር የሚበቃ ምግብ ማቅረቡን እንጂ አብዝቶ የሱፐር ማርኬት ምርቶች መመገብ እንደችግር የሚያስጨንቅ ደረጃ መደረሱን አልደረስኩበትም፤ ወቸጉድ!?

  ReplyDelete
 5. wow great dani egizabiher yesitih


  ReplyDelete
  Replies
  1. በጣም ይገርማል፣እዚህም አካባቢ ያአሉት ደግሞ በብራንድ የተለከ ፉሆነው
   አግቼአችዋለሁ

   Delete
 6. የልቤን ሃሳብ አወጣህልኝ ጌታ ይባርክህ ጸጋውንም ያብዛልህ እስኪ እኛም አንባቢዎች የሰማነውን በቤታችን እንጀምረው

  ReplyDelete
 7. it so current issue and every body should have to take in to consideration

  ReplyDelete
 8. አንድ ልጅ ሀገሩን እንዲወድድ፣ ለሀገሩ እንዲያስብና ማኅበረሰቡን ዐውቆ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ‹ማኀበር› socialization ያስፈልገዋል

  ReplyDelete
 9. አሁን የውስጤን ሀሳብ መግለጫ የተሰካካ ቃላት አገኘሁለት እግዚአብሔር ይባርክር አሜን
  wtbhm

  ReplyDelete
 10. እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥህ !!! ጊዜውን የጠበቀ ምክሮች ነበሩ. ታሪክ የሚመዘግበው አስተማሪ እይታዎችህን ለማንበብ በመቻሌ በጣም ደስተኛ ነኝ ፡፡ በርታ ገና ብዙ እንጠብቃለን እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 11. yihema iyanebu iskista malet eko new

  ReplyDelete
 12. yihema iyanebu iskista new

  ReplyDelete
 13. አብዛኛው የሀገራችን ወላጅ የሚያስጨንቀው ያለውን ገንዘብ አብቃቅቶ ዋጋው ዝቅተኛና ለወር የሚበቃ ምግብ ማቅረቡን እንጂ አብዝቶ የሱፐር ማርኬት ምርቶች መመገብ እንደችግር የሚያስጨንቅ ደረጃ መደረሱን አልደረስኩበትም፤ ወቸጉድ!?
  yihe yeabzagnaw Ethiopiawi cheger ayedlem ,.
  Ahun Be Qen Ande Enquan Belto Mader New.

  ReplyDelete
 14. sami ketegen makeru weketawi nebere.

  ReplyDelete
 15. Kale hiwot yasemalin! Chigiru ke hager wuchi bemininorim Ethiopiawuyan yayele new. Lijoch ena welajoch be anid maed keribew mebilat fetsimo eyetefa new, be migibu liyunet! Welajoch wede Ethiopia sihedu enkuan andun shanta belijoch yetashege migib moltew new, ye bahilawi migibun silemaybelulachew. Silezih wuyiyitu ke hager wuchi leminorutm welajoch critical new.

  ReplyDelete
 16. It is a great idea with great looking.Thanks Dn.Dani.God bless you with your beloved family.

  ReplyDelete
 17. Thank you D.Daniel interesting and wonderfull view for me and for Ethiopians.God Bless you.......

  ReplyDelete
 18. I don't know how to fix the issue but my child eats only very few foods and none of them r injera. We've tried and still trying to offer but we fail a lot. The guilt is killing us inside.

  ReplyDelete
 19. Wey dani ke europe wede ethiopiya yetashege migib gezitew chinew mihedu 'mihuran' ena betesebochachachew alu.yetashege migib gezito memegeb yehabtaminet megelecham chimir honoal eko.
  lemisale yetashege boqolo,serdin,zeyit,qibe...

  ReplyDelete
 20. ዳንኤል እንደተለመደው በጣም መልካም ፅሁፍ ነው:: ሆኖም "እነ ጣልያንኮ ፒዛን ከኤርትራ ነው የወሰዱት፡፡ የትግራይ ሰዎች ቂጣውን በቅቤና በአዋዜ የመብላት የቆየ ባህል ነበራቸው፡፡ ጣልያኖች አዋዜውን በቲማቲም ተኩትና ፒዛን አመጡት፡፡ ዛሬ ልጆቻችን ፒዛ ነው እንጂ ቂጣ አንወድም ሲሉ ዝም እንላቸዋለን፡፡ " የሚለው ሃሳብ ትክክል አልመሰልኝም፡ ምክንያቱም ፒትሳ ጣልያኖች ኤርትራንና ትግራይን ከማወቃቸው ረጅም ዓመታት በፊት ነበረና:: አንዳንድ ፅሁፎች እንዲያውም ከአንድ ሺህ ዓመታት በላይ ታሪክ አንዳለው ይጠቁማሉ:: ብዕርህ አይንጠፍ::

  ReplyDelete
 21. It happens often so, because majority of our rich ppl lack sufficient education to analyze what we have and have not. Case in point is athlet Haile Gebresallasie who did not teach his children Amharic!

  ReplyDelete
 22. abzagnaw hibreteseb yemibelawun baTabest seat yihenin maqreb min yemlut new. Wey tadamin alemaweq

  ReplyDelete
  Replies
  1. በትክክል የታዳሚው ችግር ነው ልጆቻችን የታሸገ ምግብ ባያዝዙም ቆሎና ንፍሮን እኮ የባላገር ምግብ ብለው እየናቁ አይደለም?ስንቶቻችን ከተሜዎችስ አስበን በቤታችን እናዘጋጀዋለን? ይልቁን አርቀው የሚያዩና ስለትውልዱ የሚጠነቀቁ ደግሞ አቅጣጫ የሚያሳዩ ባለአእምሮዎች ይብዙልን ነው የሚባለው በጎ ህሊና ይስጠን!!!!!

   Delete
  2. ኧረ የብዙ ቤት ችግር ነው ልጆቻችን አቅርቦቱን ቢያጡም በምኞት እየተቃጠሉ ነውኮ ሆሆሆ! ባይሆንም እንኳ ሳይቃጠል በቅጠል ብሎ ነውና በበጎ ህሊና ማየትና ማበረታታት አይሻልም?

   Delete
 23. ዲ/ን ዳንኤል እይታህን ወድጄዋለሁ እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ፡፡ሃብታሞች ባቻ አይደሉም በዚህ ችግር እየገቡ ያሉት የድሃ ልጆችም ከሚያዩት ነገር በመነሳት ችግሩ እየበከላቸው እየበከለንም ነው የተዘጋጀ ምግብ በአንድ በኩል ስንፍናችንንም ያሳያል ምግብ የማብሰልም ልጅ በሥርዓት የማሳደግም ስንፍና፡፡ ብቻ በሁሉም አቅጣጫ ልናስብ እንደሚገባ ጠቋሚ ጽሁፍ ነው፡፡

  ReplyDelete
 24. ዲን ዳንኤል እውነት ለመናገር ያነሳኸው ጉዳይ የሁላችንም ቤት ያንኳኳ ነው:: ልጆቻችን እያሳደግን ያለበት መንገድ እጅግ አሳዛኝ እንዲሁም አስፈሪ ነው:: ከቤት ውስጥ ብንጀምር ህጻናቱን የማሳደግ ሙሉ ሃላፊነት በሞግዚቷ ተጥሏል (ይብሉ አይብሉ; ይጠጡ አይጠጡ; ይልበሱ አይልበሱ ወላጅ አያውቅም) ወደ ትምህርት ቤትም ስንሄድ (ምን ይማሩ; በማን ይማሩ ስለምን ይማሩ ወላጅ የሚያውቀው ነገር የለም) ልጆች እንኳን የወላጆቻቸው የእናታቸውም ፍቅር ማግኘት እልቻሉም:: ድሮ ድሮ አባት አምሽቶ ሲገባ ልጆቹ ተኝተው ይተብቁ ነበር: አሁን ግን አባትም እናትም ሲገቡ ልጆች ተኝተዋል ዳኒ እንደዚህ አይነት ትውልድ ነው እየመጣ ያለው እርግጥ ነው ወላጅ ካልሰራ መኖር አልቻለም! መፍትሄውን መጠቆም ባልችልም የሆነ እርምጃ ግን ያስፈልገናል:: ወቅታዊና አንገብጋቢ የሆነውን ጉዳይ አንስተህ ስላወያየሀን በጣም እናመሰግናለን::እኔም በግሌ ማስተካከል የምችለውን ያህል እርምጃ እወስዳለሁ::

  ReplyDelete
 25. ኧረ የብዙ ቤት ችግር ነው ልጆቻችን አቅርቦቱን ቢያጡም በምኞት እየተቃጠሉ ነውኮ ሆሆሆ! ባይሆንም እንኳ ሳይቃጠል በቅጠል ብሎ ነውና በበጎ ህሊና ማየትና ማበረታታት አይሻልም?

  ReplyDelete
 26. ewunet lemenager daniel yanewahwu guday tikekelegna newu egna ethiopian betam teqami bahiLLL
  Emnet amegageb . alebqbes alen gin yewuchun yemanawukewu bahil yizen eyehdn newu lemehonu bahilachinn yizen meselten ayichalem ende? yichalal selezih begudayu ly enewoyayibet

  ReplyDelete
 27. weygud!!!!!!!!! minyishalenal!!!!!!!!!!!!! ere gobeth zimblen tegnitenal ke enkilfachin enenka!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  Dani tsegawn yabzalih!

  ReplyDelete
 28. መልካም እይታ ነው፡፡ በጣምም ወድጀዋሎሁ፡፡
  በጣም የሚገርመው እኔም የሱፐር ማረኬት ምግቦች ጥሩ ይመስሉኝ ነበር፡፡
  አሁን ግን በተፈጥሮ ጥሩ ይዘት ያለውን የሀገራችን ምግብን ለልጆች ወደር የለለው መሆኑን ተረድቻሎህ ደግሞም ለተግባራዊነቱ እተጋሎህ፡፡


  ReplyDelete
 29. EGZBHER YSTLENE DN.DANILE ena nuroy Amrica hager newe lelja injera besero sabela balbta bezume aydgfwem ebkhe kecalke sele injera ena shero tkmee saflene asnbebwalu bngracne laye leja betame desblote ymtblaw mgebe injera beshero newe desaylem.

  ReplyDelete
 30. ዳ/ን ዳንኤል
  እንደዚህ ያለው ጠቃሚ ሀሳቦች ነው አገሪቷን ወደ ፊት የሚወስዳት በነገራችን ላይ በአሁኑ ጊዜ ለካንሰር አጋልጦ የሚሰጥ አንዱ እና ዋናው የታሸጉ የሱፐር ማርኬት ምግቦች ናቸው። እግዚአብሔር አምላክ የአገልግሎት እድሜህን ያርዝምልን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. በአሁኑ ጊዜ ለካንሰር አጋልጦ የሚሰጥ አንዱ እና ዋናው የታሸጉ የሱፐር ማርኬት ምግቦች ናቸው።

   http://banoosh.com/blog/2013/06/28/top-10-most-unhealthy-cancer-causing-foods-never-eat-these-again/

   D/n Daniel God bless you more!

   Delete
 31. WOW !!!


  Egziabher mastewalun yabzalih Dani !!!

  ReplyDelete
 32. dany arefe eyeta new egzabehare yebarkehe abo

  ReplyDelete
 33. እንዲዚህ በደንብ አርጋችሁ ንገሩልን ምነው አሁን አሁን ጐመን የድሃ የሚባለው ቀርቶ የሐብታም ሆኖ ተወደደብን ለእኛ ለአዋቂዎች እንደየቤታችን አመል ልጆቻችንን አብልተን እንዳናሳድግ ይኸው ውጥረት ሆነ ሐብታሙንማ ተወው ያሳደገ መስሎት ገድሎታል በብዙ ነገር በአበላል ብቻ እንዳይመስልህ በስነምግባርም ጭምር ድፍረትና በራስ መተማመን የራሱ ነገር እንደለ ሆኖ ፈርያ እግዜአብሔር እንዲኖራቸው እንኳን አላደረጓቸውም ይሄንን ስልህ በሁሉም ቤተሰብ ሳይሆን ሠለጠንን በሜሉት አካባቢ ነው ስለዚህ እራሳቸውን እንዲያውቁ ማስረዳት ቢኖር ጥሩ ነው የምለው ፡፡

  ReplyDelete
 34. Daniel endesemeh melkam menfes yaleh selehonk tebarek. Bezu tsehufochehen anebalehu: selemlkam hassabeh egziabher kef yadergeh. Yehe guday hulachenenm yemimeleket new, egziabher redtogn ene lijochen babzagnaw gize yageren megebnew yemablaw enem yemewedew esun new. Hule behassabe gen menale yehagere nutritionistoch sele egnaw ager megeb bedenb bitsefu, bemedia biyakerbu, enquan lerasachin lelochim eneterfalen eko. ferenj azuro debalkona keleso legnaw bewed kemeshetu befit beneneak melkam new.

  ReplyDelete
 35. ዳኒ በጣም አመሰግናለሁ የሆዴን ሁሉ ስለዘረዘርክልኝ እግዚእብሔር ይባርክህ
  ሁለቱም ጉዳዮች ግን ክዚህ ትውልድ ፊት የተደቀኑ ጽኑ ፈተናዎች ናቸው ብል ማጋነን እይሆንብኝም መውጫ ቀዳዳውን የድንግል ማርያም ልጅ እርሱ ምድሃኔዓለም ያመላክተን
  አሜን

  ReplyDelete
 36. የምታነሳቸው ሃሳቦች በሙሉ በጣም የሚያስፈልጉንና የሚጠቅሙን ናቸው እግዚአብሔር ይባርክ

  ReplyDelete
 37. ዳኒ ያቀረብከው ፅሁፍ ትክክለኛና የእያንዳንዱን ቤት የሚያንኳኳ ነው፡፡ እግዚያብሄር ይባርክ ፀጋውን ያብዛልህ፡፡ በደንብ ላስተዋለው ብዙን ጊዜ ምንም የሌላቸው የሃብታም ልጆችን ስታነጻፀረው የደሃ ልጅ የሁነው በጣም ጤናማና በጣም የተለየ እንክብካቤ ካለው የሃብታም ልጅ የተሻለ ሆኖ ታገኘዋለህ የዚህ ሚስጥር አንተ በሰፊው የገለፅከው ነው፡፡ ስለዚ ወላጆች ያንተን ፅሁፍ መነሻ አድረገው በሰፊው ለነጋገሩበት ይገባል፡፡ ዳኒ ይንን ፅሁፍ ሁሉም ሰው የማንብብ ዕድሉን ሊያገኘው ስለማይችል በተለያየ ሚዲያ በተለይ ለሬዲዮ ውይይት ብታቀርበው የበለጠ ሃሳብህ ውጤታማ ይሆናል ብዬ አስባለውኝ፡፡ በርታ እግዚያብሄር እድሜና ጤናውን ያድልህ፡፡

  ReplyDelete
 38. ዳኒ ያቀረብከው ፅሁፍ ትክክለኛና የእያንዳንዱን ቤት የሚያንኳኳ ነው፡፡ እግዚያብሄር ይባርክ ፀጋውን ያብዛልህ፡፡ በደንብ ላስተዋለው ብዙን ጊዜ ምንም የሌላቸው የሃብታም ልጆችን ስታነጻፀረው የደሃ ልጅ የሁነው በጣም ጤናማና በጣም የተለየ እንክብካቤ ካለው የሃብታም ልጅ የተሻለ ሆኖ ታገኘዋለህ የዚህ ሚስጥር አንተ በሰፊው የገለፅከው ነው፡፡ ስለዚ ወላጆች ያንተን ፅሁፍ መነሻ አድረገው በሰፊው ለነጋገሩበት ይገባል፡፡ ዳኒ ይንን ፅሁፍ ሁሉም ሰው የማንብብ ዕድሉን ሊያገኘው ስለማይችል በተለያየ ሚዲያ በተለይ ለሬዲዮ ውይይት ብታቀርበው የበለጠ ሃሳብህ ውጤታማ ይሆናል ብዬ አስባለውኝ፡፡ በርታ እግዚያብሄር እድሜና ጤናውን ያድልህ፡፡

  ReplyDelete
 39. አብዛኛው የሀገራችን ወላጅ የሚያስጨንቀው ያለውን ገንዘብ አብቃቅቶ ዋጋው ዝቅተኛና ለወር የሚበቃ ምግብ ማቅረቡን እንጂ አብዝቶ የሱፐር ማርኬት ምርቶች መመገብ እንደችግር የሚያስጨንቅ ደረጃ መደረሱን;;
  I am also not sure.
  I doubt if this is really an issue for our majority public at this point in time.
  In medicine there is a saying:
  "it better to know the rare features of a common disease than a common feature of a rare disease". So I don't take as a big deal at this very point of time for most Ethiopians! but thanks for the note

  ReplyDelete