click here for pdf
አንዳንዱ የሞተበት ቀን የድል ቀን ተብሎ ይከበርበታል፤ ሕዝብ የመሞቻውን ቀን
የሚናፍቁለት ሰውም አለ፡፡ አንዳንዱ እንኳን ተወለደ ሳይባልለት እንኳን ሞተ ይባልለታል፡፡ አንዳንዱ እንዲሞት ይጸለይለታል፤
ሌላው እድሜው እንዲያጥር ይረገማል፡፡ ከዚህ የተለየ ነው ማንዴላ፡፡
ሚሊየኖች እንዳይሞት የሚጸልዩለት፤ ሚሊየኖች እንዲኖር የሚመኙለት፤ ሚሊየኖች
ከእድሜያቸው ተቀንሶ ቢሰጠው የሚፈቅዱለት፤ ሚሊየኖች እነርሱ ሞተው ሊያኖሩት የሚሹት፤ ሚሊየኖች በየቀኑ የጤናውን ሁኔታ
ከራሳቸው ጤና በላይ የሚከታተሉለት ሰው ነው ማንዴላ፡፡
አፍሪካ አያሌ መሪዎችን በቅርብ ዘመናችን አስተናግዳለች፡፡ አያሌ የነጻነት ታጋዮችን
አይታለች፡፡ እንደማንዴላ ታሥረው የታገሉ ነበሩ፡፡ እንደ ማንዴላ ድርጅት አቋቁመው የተዋጉ ነበሩ፤ እንደ ማንዴላ ሕዝባቸውን
ለነጻነት ያበቁ ነበሩ፤ እንደ ማንዴላም ከነጻነት በኋላ የመጀመሪያው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የሆኑም ነበሩ፤ እንደ ማንዴላ ከሀገር
ተሰደው የኖሩ ነበሩ፤ ታድያ ማንዴላን ምን ልዩ አደረገው?
ማንዴላ የታገለው ለፍትሐዊነት ነው፡፡ ደጋግሞ ይናገር እንደ ነበረው ‹‹እኛ
የታገልነው የነጭ የበላይነትን በጥቁር የበላይነት ለመተካት አይደለም፤ የታገልነው ነጮች፣ ጥቁሮችና ሌሎች በእኩልነት
የሚኖሩባትን ደቡብ አፍሪካ ለመመሥረት ነው›› ይል ነበር፡፡ በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ከነጻነት ትግል በኋላ ጭቆና አልቀረም፡፡
ነገር ግን ነጭ ጨቋኞች በጥቁር ጨቋኞች ተተክተዋል፡፡ በነጮች ተይዞ የነበረው የገዥነት ቦታ ለሥልጣን በበቁት ታጋዮች
ፓርቲዎችና ጎሳዎች ተተካ፡፡ የነጻነት ተዋጊዎች የፍትሕና እኩልነት አስፋኞች ሳይሆኑ አዳዲሶቹ ገዥ መደቦች ሆነው ብቅ አሉ፡፡
በነጮች ተይዞ የነበረውን ሀብት ነጻ አውጭ ግንባሮችና ፓርቲዎች ወረሱት፡፡ ስለዚህም ሕዝቡ በትግሉ ጨቋኞችን በሌሎች ጨቋኞች
ተካቸው እንጂ ፍትሕና እኩልነትን ለማግኘት አልታደለም፡፡
ማንዴላ ይህንን ነበር የተዋጋው፡፡ እንደተመረጠ ብዙዎች የነጮች መሬት ተቀምቶ
ለጥቁሮች እንዲሰጥ፣ ነጮች ከሀገሪቱ እንዲባረሩ ይፈልጉ ነበር፡፡ እርሱ ግን አላደረገም፡፡ ‹መሬቱ ፍትሐዊ በሆነ መልኩ
እንዲዳረስ እንጂ መሬት አልባ ነጮች የመፍጠር ዕቅድ የለንም› አለ፡፡ ጥቁሮች ይበልጥ ነጻ የሚወጡት የበለጸገች ደቡብ አፍሪካ
ስትኖር እንጂ በደኸየች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አይደለም ብሎ አመነ፡፡ ለዚህ ደግሞ የብዙ ዘመን ሀብትና ልምድ ያላቸው ነጮች
ወሳኞች መሆናቸውን ተገነዘበ፡፡ ለዚህም ነበር በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ያየነው ምስቅልቅል በደቡብ አፍሪካ ያልተከሰተው፡፡
ማንዴላ የዕርቅና የፍቅር ሰው ነበር፡፡ በነጮችና በጥቁሮች መካከል ለዘመናት
በአፓርታይድ የተፈጠረውን መከፋፈል፣ መጠላላትና መገፋፋት በዕርቅና በይቅር ባይነት እንጂ በመሣሪያና በበቀል ሊጠፋ እንደማይችል
የተረዳ መሪ ነው፡፡ አፓርታይድ ሲገረሰስ የይቅርታ ኮሚሽን ተቋቁሞ፣ ነባር የሕዝብ ለሕዝብ ችግሮች በተቻለ መጠን በይቅርታና
በዕርቅ እንዲወገዱ ሠርቷል፡፡ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ከነጻነት በፊት የነበሩ ገዥዎችና አበሮቻቸው ወደ እሥር ቤት
ሲወረወሩና ወደ ውጭ ሲሰደዱ፤ በደቡብ አፍሪካ ግን የከፋ ወንጀል ካልፈጸሙና ይቅርታ ለመጠየቅም ከፈቀዱ ችግሩን በዕርቅና
በይቅርታ ለመፍታት ተችሏል፡፡ በዚህም ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ ብቻ ሳይሆን ሀገርን አፍርሶ ከመሥራት አባዜ ነጻ እንድትወጣ
አድርጓታል፡፡
ማንዴላ ለሰዎች ልጆች ሁሉ የቆመ መሪ ነበረ፡፡ ከዊኒ ማንዴላ ጋር ያፋታቸው ዋነኛው
ምክንያት ዊኒ ማንዴላ በነጻነት ትግሉ ወቅት ‹ለነጻነት ትግሉ› ሲባል ፈጽመውታል የተባለው ኢ ሰብኣዊ ድርጊት በእርቅና ይቅርታ
ኮሚሽኑ መጋለጡ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ለነጻነት ትግሉ ሲባል ቢደረግም፣ ምን እንኳን ዊኒ ማንዴላ ቢሆኑም ማንዴላ ግን
ሊታገሡት አልቻሉም፡፡ የነጻነት ታጋይ ድርጅቱ ኤ ኤን ሲ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ የፈጸማቸው ኢሰብአዊ ድርጊቶች ካሉ ይቅርታ
የመጠየቅ ግዴታ አለበት ብለው የሚያምኑት ማንዴላ በዚህ ምክንያት ከዊኒ ጋር ተለያይተዋል፡፡ ከነጻነት በኋላ አያሌ የነጻነት
ታጋይ ድርጅቶች በትጥቅ ትግላቸው ወቅት የፈጸሙት ኢሰብአዊ ድርጊት፣ ወንጀልና ግፍ ተሠውሮ እንዲቀር ሲደረግ ማንዴላ ግን ኤ ኤን
ሲ ይቅርታ እንዲጠይቅ አድርገዋል፡፡
ማንዴላ ሰላማዊ መንገድን ብቻ ይመርጥ የነበረ መሪ ነበር፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ምንም
እንኳን የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረውን ኤ ኤን ሲ የመራ ቢሆንም ሰላማዊ የትግል መንገድ ከማንኛውም የትግል መንገድ ሁሉ ቅድሚያ
እንዲያገኝ ሲታገል የኖረ ሰው ነው፡፡ ይህ ትግሉ ከአፓርታይድ መሪዎች ጋር ብቻ ሳይሆን በኤ ኤን ሲ ውስጥ ከነበሩ ሌሎች
አመራሮች ጋርም ጭምር ነበር፡፡ የጠመንጃ ትግል ለሰላማዊ ትግል፣ ለድርድርና ለውይይት የተዘጋውን በር ማስከፈቻ እንጂ ሰላማዊ
መንግሥት የመመሥረቻ መንገድ አይደለም ብሎ ያምን ነበር፡፡ በአፓርታይድ የመጨረሻዎቹ ዘመናት እነ ፒተር ቦታ ከኤ ኤን ሲ
መሪዎች ጋር ለመደራደር ያቀረቡትን ጥያቄ አንዳንድ የድርጅቱ አመራሮች አልቀበል ሲሉ ‹እኔ ብቻዬንም ቢሆን እደራደራለሁ› እስከ
ማለት አቋም ወስዶ ነበር፡፡ ከአፓርታይድ ጋር የሚደረገው ትግል
በጠመንጃ አሸናፊነት ሳይሆን በሃሳብ አሸናፊነት መጠናቀቅ አለበት የሚል አቋም ነበረው፡፡
በደቡብ አፍሪካ ሁሉንም ያሳተፈ የመጀመሪያ ምርጫ በተደረገ ጊዜ የአፍሪካ ብሔራዊ
ኮንግረስ ሕገ መንግሥቱን ብቻውን ለማጽደቅ የሚያስችለውን ድምጽ አላገኘም ነበር፡፡ ይሄንን አጋጣሚ ማንዴላ በደስታ ነበር
የገለጠው ‹‹ሁሉንም ሕዝብ የሚመራ ሕገ መንግሥት ብቻችንን ማጽደቅ የለብንም፤ ይህ አጋጣሚ መልካም ነው፤ ከሌሎቹ ጋር
ተማክረን፣ ተደራድረንና ተስማምተን እንድናጸድቅ ያደርገናል› ብሎ ነበር፡፡
ማንዴላ ሥልጣን መያዝን ብቻ ሳይሆን መልቀቅንም ያስተማረ ሰው ነው፡፡ ማንዴላ ደቡብ
አፍሪካን ለአንድ ዙር ብቻ ነው የመራው፡፡ በቀጣዩ ምርጫ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ዘመናት በሚደረጉ ምርጫዎችም የማሸነፍ ዕድል
ነበረው፡፡ ነገር ግን በቃኝ አለ፡፡ እየተወደደ፤ እየተመሰገነና እየተከበረ በቃኝ አለ፡፡ በደቡብ አፍሪካውያን ብቻ ሳይሆን
በመላው አፍሪካ ብሎም በመላው ዓለም ‹አይከን› የመሆንን ጸጋ ተጎናጸፈ፡፡ የነጻነት፣ የጽናትና የትዕግሥት፣ የሰላምና የዕርቅ፣
የይቅር ባይነትና ከጥላቻ ውጭ የሆነ ፖለቲካ ‹አየከን› ሆነ ማንዴላ፡፡ በመላው ዓለም ሕዝብ ልብ ውስጥ ማንም ሊነቅለው የማይችል
ዛፍ፣ ማንም ሊያፈርሰው የማይችል ሐውልት ሆነ ማንዴላ፡፡
ለዚህ ይመስለኛል ማንዴላን ዓለም በሙሉ የሳሳለት፤ ለጤናውም ሆነ ለእድሜው
የጸለየለት፤ የተጨነቀለትና ልቡን ከልቡ ጋር ያስተባበረለት፡፡ እንደ እርሱ ዓይነት ሰዎች እንደ ሄሊኮሜት በዘመናት አንድ ጊዜ
ብቅ የሚሉ ናቸው፡፡ ተወደው ሥልጣን ላይ የሚቀመጡ፣ ተወደውም ከሥልጣን የሚወርዱ፤ ተወደውም ያለ ሥልጣን የሚኖሩ፡፡ እንደ
ማንዴላ ዓይነት ሰው እንኳን ሌላው የአፍሪካ ሀገር ራሱ ኤ ኤን ሲም ዳግም ሊያገኝ አልቻለም፡፡ መከፋፈል ዕጣ ፈንታ የሆነውም
በዚህ ምክንያት ነው፡፡
መሪነትና ባለ ሥልጣንነት ምን ያህል እንደሚለያዩ ማንዴላ አንድ ማሳያ ናቸው፡፡
ማንዴላ ባለ ሥልጣን አልነበሩም፤ መሪ እንጂ፡፡ ባለ ሥልጣን በሰው ገንዘብ ውስጥ እንጂ በሰው ልብ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ባለ
ሥልጣን ይፈራል እንጂ አይከበርም፤ ባለ ሥልጣን ቢሮ አለው እንጂ ሀገር የለውም፤ ባለ ሥልጣን የሚላላኩት ሠራተኞች እንጂ
የሚጸልዩለት ወገኖች የሉትም፡፡ ባለ ሥልጣን የሚያዘው ሰው እንጂ የሚያፈቅረው ሰው አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ፊርማውን የሚፈልግ
እንጂ እድሜውን የሚፈልግ የለም፤ ባለ ሥልጣን ብዙ ገንዘብ እንጂ ብዙ ልቦች አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ከሥልጣን ወዲህ እንጂ
ከሞት ወዲያ ተዝካር የለውም፡፡
ማንዴላ ከሞት በኋላም ይኖራል፡፡ በብዙ ልቦች ውስጥ ይኖራል፡፡ መቃብር እርሱን
ሊያስረሳ አይቻለውም፡፡ እርሱ ከመቃብር በላይ የሆነ ተግባር አለውና፡፡ ማንዴላ የአንድ ሀገር መሆኑ ቀርቶ የዓለም ሆኗል፡፡
መሬት ላይ የሚቆም ሐውልት አያስፈልገውም፤ እርሱ በሕዝቦች ልብ ውስጥ የማይፈርስ ሐውልት በሕይወት እያለ ሠርቷልና፡፡ ብዙ ባለ
ሥልጣናት በሕይወት እያሉ በሰው ልብ ውስጥ ሐውልት መሥራት ስለማይችሉ፣ ከሞቱ በኋላ የድንጋይ ሐውልት ይሠራላቸዋል፡፡ ነገር
ግን ሐውልታቸው መልእክት አልባ ሐውልት ይሆናል፡፡ እንደ ማንዴላ ያሉ መሪዎች በመሬት ላይ ሐውልት ሲተከልላቸው ደረቅ ሐውልት
አይሆንም፤ መልእክት ያለው ሐውልት እንጂ፡፡
ማንዴላ አይሞትም፤ ጀግና አይሞትምና፤ የማንዴላ አይረሳም፤ ሕዝብ ልብ ውስጥ የገባ
ሰው አይረሳምና፤ ማንዴላ አያልፍም፣ በጎ ሥራ አያልፍምና፡፡
በብዙ እንባ መሀል ሀገሬን እያሰብኩ አንብቤ ጨረስኩት ዳንኤል እውነት ኢትዮጵያስ መቼ ይሆን ማንዴላ የሚኖራት? እንጃ
ReplyDeleteመሪነትና ባለ ሥልጣንነት ምን ያህል እንደሚለያዩ ማንዴላ አንድ ማሳያ ናቸው፡፡ ማንዴላ ባለ ሥልጣን አልነበሩም፤ መሪ እንጂ፡፡ ባለ ሥልጣን በሰው ገንዘብ ውስጥ እንጂ በሰው ልብ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ባለ ሥልጣን ይፈራል እንጂ አይከበርም፤ ባለ ሥልጣን ቢሮ አለው እንጂ ሀገር የለውም፤ ባለ ሥልጣን የሚላላኩት ሠራተኞች እንጂ የሚጸልዩለት ወገኖች የሉትም፡፡ ባለ ሥልጣን የሚያዘው ሰው እንጂ የሚያፈቅረው ሰው አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ፊርማውን የሚፈልግ እንጂ እድሜውን የሚፈልግ የለም፤ ባለ ሥልጣን ብዙ ገንዘብ እንጂ ብዙ ልቦች አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ከሥልጣን ወዲህ እንጂ ከሞት ወዲያ ተዝካር የለውም፡፡ Good Views Dn Daniel we want now a man like Mandela 4 Ethiopia
ReplyDelete‹‹እኛ የታገልነው የነጭ የበላይነትን በጥቁር የበላይነት ለመተካት አይደለም፤ የታገልነው ነጮች፣ ጥቁሮችና ሌሎች በእኩልነት የሚኖሩባትን ደቡብ አፍሪካ ለመመሥረት ነው››
ReplyDelete<> We all prays to him, he is not only the son of Africa but the son of the world.
ReplyDeleteHe teaches what love and power means for the African dictator leaders.
Thanks Dany for your literature!!
ኢትዮጵያ የማንዴላ ወዳጅ ነበረች- ማንዴላም የኢትየዮጵያ፡፡ እንደሱ አይነት ልጅ እንዲሰጠን እመቤቴ ትርዳን፡፡
ReplyDeleteአለ የኛዎቹስ kb z Adigrat
ReplyDeleteI like it so much. It is really difficult to write about Mandela even in thousands page of book. He is just a gift of God for Africa
ReplyDeleteFekadeselassie
Oh yup he's really a GIFT OF GOD
Delete‹‹እኛ የታገልነው የነጭ የበላይነትን በጥቁር የበላይነት ለመተካት አይደለም፤ የታገልነው ነጮች፣ ጥቁሮችና ሌሎች በእኩልነት የሚኖሩባትን ደቡብ አፍሪካ ለመመሥረት ነው››
ReplyDeleteThe current leadership problem esp. in Africa would otherwise have not been inexistence had leaders followed his footsteps and we wouldn't hve been misfourtune now!
ReplyDeleteማንዴላ ከሞት በኋላም ይኖራል፡፡ በብዙ ልቦች ውስጥ ይኖራል፡፡ መቃብር እርሱን ሊያስረሳ አይቻለውም፡፡
ReplyDeleteማንዴላ አይሞትም፤ ጀግና አይሞትምና፤ የማንዴላ አይረሳም፤ ሕዝብ ልብ ውስጥ የገባ ሰው አይረሳምና፤ ማንዴላ አያልፍም፣ በጎ ሥራ አያልፍምና፡፡
ጀግና የሚሞተው በፈቃዱ ነው፡፡ ጀግና ይሞታል ሞቱ ግን ሌሎችን ያኖራል፡፡
ጀግና ያለምክንያት አይሞትም፡፡ የጀግና ሞቱ ያልተስተካከለውን ለማስተካከልና አዲስ ርዕዮተ ዓለም ለማሳየት ነው፡፡ በጀግና ሞት የሚገፈፍ ጨለማ፡ የሚተካ ብርሃን፡ የሚሻር ባርነት የሚገለጥ የነጻነት ጎህ አለ፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ ቢሞትም ከዘመናት በኋላ የታገለለት የነጻነት ጎህ አሜሪካን ከአድማስ እስከአድማስ ሸፍኗል፡፡ ጥቁሮችንም ቀና አድርጓል፡፡ የኦባማን ዙፋን ያቆመው የኪንግ መስዋዕትነት ነው፡፡
የጀግና ሞት ጀግኖችን የወልዳል፤ መልካሞችንም ያበዛል፡፡ በእስጢፋኖስ ሞት የተበተኑ አማኞች ክርስትናን ከሮም ድንበር አሻግረዋል፡፡ የሰማዕታቱ ሞት ሰማዕታትን ወልዷል፡፡ በሰማዕትነት ሲሞቱ የአማኞች ቁጥር ጨመረ እንጂ አልቀነሰም፡፡
ጀግና በሥራው ህያው ነው፤ ሥጋው ወደ አፈርነት ቢመለስም ስራው ከመቃብር በላይ ሲያበራ እና ሲያስተምር ይኖራል፡፡ “አቤል ሞቶ ሳለ በመስዋዕቱ እስከአሁን ይናገራል፡፡” ዕብ.11፡5 በእርግጥ አቤል ሞቷል የአቤል ንጹህ መስዋእት ግን ትውልድን ይናገራል፡፡ የተወደደ ሥራ ያላቸው ጀግኖች ክፉዎችን የምንገስጽባቸው አንደበቶች ናቸው፡፡ የእኛ ጀግኖች በጀግና ፊት ሚዛን ይደፋሉን? ለእኛ ኖሩ ወይስ ለምኞታቸው?
ጀግና በትእዛዝ አይለቀስለትም፡፡ መልካምነቱ የብዙዎችን ልብ ስለሚወርስ እውነተኛ እንባ ውለታ ካለባቸው ልቦች ይፈልቅለታልና፡፡ ጀግና ለተጠቁት ደራሽ ስለሆነ ህሊና ያለቸው ይወዱታል፡፡ ለሚወደድ ጀግና ደግሞ የአዞ እንባ ተገቢ መብአ አይደለም፡፡
የእኛ ጀግኖች በጀግና ፊት ሚዛን ይደፋሉን? ለእኛ ኖሩ ወይስ ለምኞታቸው?ግና ማለት የወገኑን ጥቅም የሚያስቀድም፤ በእርሱ ሞት የሌሎችን ሕይወት የሚያደላድል ወገኖቹ ነገ እንዲኖሩ ዛሬውን የሚሰዋ ለሌላው ጥቅም ሲል የሚጎዳ ጉዳቱንም እንደጥቅም የሚቆጥር፤ ስለከፈለው መስዋዕትነት የማይጸጸት ነው፡፡ የእኛ ጀግኖች በጀግና ፊት ሚዛን ይደፋሉን? ለእኛ ወይስ ለምኞታቸው ኖሩ?
ጀግና አርቆ ተመልካች ባለራእይ ነው፡፡ ነገ የሚሆነውን ቀድሞ ተመልክቶ ሊመጣ ስላለው ክብር ክብሩን ይሰዋል፡፡ ሙሴ ጀግና መስፍን ነበር፤ ሕዝቡን ከመከራ ለማውጣት የራሱን የተደላደለ ኑሮ ሰውቷልና፡፡ ፈርዖን የገነባለትን የምቾት ዓለም ለወገኑ ፍቅር ሲል ንቋልና፡፡ ለሕዝቡ ነፃነት ሲል ባርነትን መርጧልና፡፡ የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶ የሚታይ መከራን ተጋፍጧል፡፡ ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቶ ጊዜያዊ ክብርን ንቆ በመከራ ከተጠቃው ወገኑ ጋር መሆንን መርጧል፡፡ የእኛ ጀግኖች በጀግና ፊት ሚዛን ይደፋሉን? ለእኛ ኖሩ ወይስ ለምኞታቸው?
አዕምሮህ ይለምልም!
ReplyDeleteባለ ሥልጣን ይፈራል እንጂ አይከበርም፤
ReplyDelete‹‹እኛ የታገልነው የነጭ የበላይነትን በጥቁር የበላይነት ለመተካት አይደለም፤ የታገልነው ነጮች፣ ጥቁሮችና ሌሎች በእኩልነት የሚኖሩባትን ደቡብ አፍሪካ ለመመሥረት ነው›› ይል ነበር፡፡
ReplyDeleteማንዴላ አይሞትም፤ ጀግና አይሞትምና፤ የማንዴላ አይረሳም፤ ሕዝብ ልብ ውስጥ የገባ ሰው አይረሳምና፤ ማንዴላ አያልፍም፣ በጎ ሥራ አያልፍምና፡፡
ReplyDeletewawu dane God bless u forever
Deleteእኛ የታገልነው የነጭ የበላይነትን በጥቁር የበላይነት ለመተካት አይደለም፤ የታገልነው ነጮች፣ ጥቁሮችና ሌሎች በእኩልነት የሚኖሩባትን ደቡብ አፍሪካ ለመመሥረት ነው›› ይል ነበር፡፡
ReplyDeleteእስኪ ደሞ ወደኛ ሐገር መለስ ብለን ስናይስ ትግሉ ምን ይመስል ነበር ምንስ ሆነ ምን ? ምንስ ተደረገ ?
please God don't take away from us such unforgettable leader.
ReplyDeleteI hope We will have amazing leader one day.
ReplyDeleteManish, MN
"Nelson Mandella may be a hero to South Africa.
ReplyDeleteBut that is all.
Don't get hypnotized by western propaganda.
They adore him b/c he didn't make the whites pay for their crimes.
And, b/c he left the economic apartheid untouched.
Even in terms of political independence, South Africa's policy-making is still under the influence of white Bankers, corporations, etc.
Mandella's party, ANC, couldn't yet summon the courage to repeal the 1913 Land law. After 23 years of freedom, South Africa made only little land reform.
Perhaps, I should quote Mengistu Hailemariam's comment to a journalist a few years ago: "Africans and others struggled in favor of South Africa's independence, but nobody knows what ANC is doing since then".
Well, I suspect the answer lies at those secret negotiations between Mandella and the white men in the last two years before his release from prison.
Too bad, he might die without telling us about those secret negotiations."
This is an article I found on Facebook page an Ethiopian guy. I believe in it, though!
ደቡብ አፍሪካነ ብዙ ጊዜ ጎበኝቻታለሁ ማንዴላ ያደረጉላተ ነገረ ቢኖር መሬተ አልባና አፐርታይድን በተሻለ መንገድ በሰለጠነ ዘዴ በበለጠ እንደጠናከር ነዉ ያደረጉት ይህንን ያላየ ሰዉ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ሰዉዬዉን ለማምለክ ይቀጣዋል እለማታዉቁተ ጉዳይ መጻፍ የተለመደ ነዉ ዳንኤል ከምትጽፈዉ ደቡብ አፍሪካነ እነደምታዉቀዉ ገምቼ ነበር አሁን ግን አንተም የከሃዲዉ ማንዴላ ዛር ላይህ ላይ እንደሰፈረ ነዉ የገባኝ ጠበል ብትወርድ ይሻለሃል
Deletevalentine day ሳይሆን የለቅሶ ቀን አማረኝ !አዎ በውነት እንደህዝብ በአንድ ላይ የበደልነውን የተብደልነውን እያነሳን እርስ በርስ የምንላቀስበት አንዲት የለቅሶ ቀን..ቂማችንን በሌላ ሳይሆን እርስ በርስ በመላቀስ የምንወቃቀስበት የምንሽርበት ቀን! በውነት የኢትዮ>»ህዝብ ሁሉ በአንድ ላይ ካዘኑት ጋር ሲያዝን አንድ ላይ ሲያለቀስ ምን ይፈጠር ይመ ስላችሁዋል ትቪው ሁሉ ነገሩ ሱባኤ ሲገባ...እኔ ተአምር ይታየኛል የሚያፋቅር ተአምር የሚስተቀቃቅፍ ተምር የሚያስተዛዝን ተአምር!
ReplyDeleteከሰው መሆን በፊት ፖለቲካ አልመን
Deleteቃል ከማወቅ በፊት በቃ ተፋልመን
ለተከፋፈልነው ሰው አገር ተሰደን
እናልቅስ አንድ ላይ ሳር ሰርዶ ጎዝጉዘን
ፍራሹን አውርደን
ላልተጠቀምንበት ሙያና ችሎታ
ላልደከመው ጉልበት ለአገር ግንባታ
ለወገኑ ድጋፍ ላልፈሰሰው ንብረት
ሙታን ተሰብስበን እናልቅስ በኅብረት
ኅልፈት ሆኖ ይታይ ይመዝገብ ከሙታን
ሐሜት ትጥቃችንን ከፋፍሎ ካስፈታን
አውርዱለት ሙሾ አልቃሽ አቁሙና
ድኅነት ላልረታ ዕውቀት ፍልስፍና
ተጋርዶ ህሊናችን ዓይናችን ተዘግቶ
ላልፈለግነው ታሪክ ለማናውቀው ከቶ
ላፈርንበት ባህል ሰልጥነን ለተውነው
ልብ እንዳንል ደፍነን ልብ ለነሳነው
ደረት ይደቃል ፀጉር ይነጭ በቃ
ጊዜአችን ላለቀ በተረት ምሳሌ በወሬ ጥረቃ
ማልቀስ ይህን ጊዜ እንደሰማ መርዶ
የሰው አገር ዜጋ ለሚያሳድግ ወልዶ
አሁኑኑ እናልቅስ! . . .
አዋርዶ የሚገለን ከዚህ ሞት የከፋ
አይዟችሁ አይመጣም ሙታን አለን ተስፋ!
(ዓለም ፀሐይ ወዳጆ፤ የማታ እንጀራ፣ 2002)
ቋንቋና ዜማችን
Deleteቀረርቶ ፉከራችን
እስክስታ ዳንኪራችን
ማየታችሁ በስብሰባ
ማጀባችሁ በጭብጨባ
ሸጋ ነው ማክበራችሁ
መልካም ነው መውደዳችሁ::
ለዘንድሮም ለአምና
ላደረጋችሁት ሁሉ
አቅርበናል ምስጋና
ግን ባህላችን ስትወዱ
ተሰብስበን እናለቅስ
በአደባባይ እንጮህም ዘንድ ፍቀዱ
ይሄም ባህላችን ነውና !
በመኮንን ዘለቀ
29/03/2004 ዓም – ኖርዌይ
Black South Africans are only nominally better than the previous regime. Economically, they live in abject poverty. Militarily, they are not in the top echelons. Politically, they are twisted by the whites. Guess what the image of Mandela would have been, had he objected to these miseries. The Western media can make or break any one. They media could have tainted him bad images and we may not have lionized him that much. Any way, may Almighty God help him recover from his illness. Amen.
ReplyDeleteባለ ሥልጣን ፊርማውን የሚፈልግ እንጂ እድሜውን የሚፈልግ የለም
ReplyDeletewhat about our history? thank u Dani.
ReplyDeleteThank you Dan Dani
ReplyDeleteI always remember Mandela when i read the quote of Albert Einstein "Try not to become a man of success, but rather try to become a man of value." Mandela is a value of Africa he suffered a lot for his people not for his success. We Ethiopian want a leader, he has a value, rather than his success.
ReplyDeleteSelme Dani selme ena Tena kerjme edme gar emjelheluje lejem hager endhe yemenamogsw lalem yemeterfe meri endesetene emejaluje Anentne TEGUNE YABSALEH!!!!!!!!
ReplyDeleteLong live to Mandela,,,oh God have mercy!
ReplyDeleteለአገሩ ጥሩ ሥራ ሰርቷል የራሳችን ስንት ጀግኖች ነበሩ አሉን አንድም ቀን አንስተን አናውቅም ለምንፈልገው ዕምቅ የክፋት አጀንዳ ለማውጣት ስንፈል እንባዝናለን!! የእነ አጼ ቴዎድሮስ፤ የእነ አሉላ አባ ነጋ ግን ምንም አናነሳም እንደዕድል ሆኖ የአገራችን ሰው በበጎ ሥራ ሲነሳ አንወድም ምቀኝነት!!
ReplyDelete‹‹እኛ የታገልነው የነጭ የበላይነትን በጥቁር የበላይነት ለመተካት አይደለም፤ የታገልነው ነጮች፣ ጥቁሮችና ሌሎች በእኩልነት የሚኖሩባትን ደቡብ አፍሪካ ለመመሥረት ነው››
ReplyDeletewhat we Ethiopians Can learn from this cote!!!?
መሪነትና ባለ ሥልጣንነት ምን ያህል እንደሚለያዩ ማንዴላ አንድ ማሳያ ናቸው፡፡ ማንዴላ ባለ ሥልጣን አልነበሩም፤ መሪ እንጂ፡፡ ባለ ሥልጣን በሰው ገንዘብ ውስጥ እንጂ በሰው ልብ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ባለ ሥልጣን ይፈራል እንጂ አይከበርም፤ ባለ ሥልጣን ቢሮ አለው እንጂ ሀገር የለውም፤ ባለ ሥልጣን የሚላላኩት ሠራተኞች እንጂ የሚጸልዩለት ወገኖች የሉትም፡፡ ባለ ሥልጣን የሚያዘው ሰው እንጂ የሚያፈቅረው ሰው አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ፊርማውን የሚፈልግ እንጂ እድሜውን የሚፈልግ የለም፤ ባለ ሥልጣን ብዙ ገንዘብ እንጂ ብዙ ልቦች አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ከሥልጣን ወዲህ እንጂ ከሞት ወዲያ ተዝካር የለውም፡፡
ReplyDeleteoh mad ethiopians
ReplyDelete“ያበደ” አላበደም
“ያላበድን” አብደናል፣
“ጤነኞች” የሆንን እውነቱ ጠፍቶናል፣
ፍቅር እንደ መጥፎ ያቅለሸልሸናል፣
መቻቻል እንደ ሬት ያንገፈግፈናል።
እኛ በራሳችን ብዙ ግፍ ሰርተናል፣ “ያበደ” አላበደም “ያላበድን” አብደናል።
እየተገላለጥን እራቁት ሆነናል፣ አለም በቃኝ ብሎ ብልህ ይመንናል፣
እብደት በቃኝ ብሎ “እብድ” ልብስ ያወልቃል፣
መርሳትን ያጠልቃል፣
እሱ ትክክል ነው “ያበደ” መች አብዷል
እኛ ግን ቀውሰን ፍቅርን አውልቀናል፣
ጤነኛ ነን ባዮች “ያላበድን” አብደናል።
እየተገፋፋን ተንጋለን አልቀናል፣
“ያበደ” አላበደም “ያላበድን” አብደናል።
የፖለቲካ ቁማርተኞች ሆይ፣ የፖለቲካ ነጋዴዎች ሆይ፣ እውነቴን እነግራችኋለሁ፣ የያዛችሁትን ስልጣን ላለመልቀቅ (ከመንግስት ወገን ያላችሁት) የሌላችሁን ስልጣን በኛ አስክሬን ላይ ተረማምዳችሁ ለማግኘት (ተቃዋሚ ነን የምትሉት) የዛሬዋን ኢትዮጵያ በዛሬዋ ሶርያ ለመለወጥ ዝግጁ ናችሁ ብዬ እፈራችኋለሁ። ቁጥር ነን ለናንተ እኛ፤ ስንራብ በቁጥራችን ትከራከራላችሁ፤ ስንገደል በቁጥራችን ትከራከራላችሁ፤ ስንፈናቀል በቁጥራችን ትከራከራላችሁ፤ በቃ ቁጥር ነን ለናንተ እኛ።
ሃይማኖቶቻችን ተረቶች ናቸው ለናንተ፤ እንደ ጭቃ ጠፍጥፋችሁ እንደገና ብትሰሩን ሁሉ ያምራችኋል፤ ታሪካችን ተረት ናት ለናነተ፤ እንደሚመቻችሁ መልሳችሁ ብትጽፏት ደስ ይላች ኋል፤ ለእውነት ደንታ የላችሁም እናንተ፤ በስልጣን እና በጉልበት እውነትን ተፈጥራላችሁ። መጀመሪያ የሌለ አላማ ትፈጥራላችሁ፤ ለዚያ አላማ እንድንሞትለት ታደርጋላችሁ፤ ከዚያ ይሄ እኮ ሰው የሞተለት አላማ ነው ትሉናላችሁ። ቆይ እኛ የናንተ ህልም ስእል ማሳመራይ ቀለሞች ነን? በምንድነው የገዛችሁን? በእውቀት ነው የገዛችሁን? በገንዘብ ነው የገዛች ሁን? በፍቅር ነው የገዛችሁን? ምንድነው የልብ ልብ የሚሰጣችሁ?
እኛ ጥሎብን ብዙ የህይወት እይታችን የተቀዳው ከሃይማኖትና ከባህል። ቅንነት፣ ፍቅር፣ የዋህነት፣ ጓደኝነት፣ መተሳሰብ ወዘተ ያማልሉናል። ሰላም እንፈልጋለን። ሃብት ብናገኝ ከድ ህነት ብንወጣም እንወዳለን። ዘፋኝ እንኳን የምንወደው "ፍቅር ያሸንፋል" የሚል ከሆነ ነው። ለናነተ ይሄ ሁሉ የቁማር ገንዘብ ነው። እኛ ግብ የምንለው ለናንተ መሳሪያ ነው። ስልጣንን እና ባለስልጣንን ለመነቅነቅ በምንወዳቸው እና በምናከብራቸው እሴቶቻችን ላይ ትረማመዳላችሁ። ስልጣንን ለመጠበቅ በእንባችን፣ በሃዘናችን፣ በሃይማኖታችን፣ በታሪካችን፣ በቋንቋችን፣ በብሶታችን፣ በተስፋችን፣ ባለን ነገር ሁሉ ትቆምራላችሁ። ለናንተ ሲባል እንዳንፋቀር ታረጉናላችሁ=የሚያፋቅረን ነገር ስታገኙ ማንሳት አትፈልጉም የሚያባላን ካገኛችሁ ግን አቧራውን ታጨሱታላችሁ!! የምትፈልጉት እኛን አደራጅታችሁ መንዳት ነው። እናንተ እንድታስቡ እኛ እንድንከተል። ተረታችሁን እየሰማን እንድናንቀላፋ።
ልዩነታችን፣ ራሳችንና ሌሎችን የምናይበት መንገድም ዋነኛ የቁማር ገንዘባችሁ ነው። የፖለቲካ ትርፍ ካያችሁ፣ ፍርሃት፣መከፋፈል ሌላው ቀርቶ ጥላቻ እንኳን ስር ቢሰድ ደንታ የላችሁም። እንደየሁኔታችሁ ስልጣንን ለመጠበቅ ወይም ስልጣንን ለመነቅነቅ የማትጫኑት ቁልፍ የለም። ለሃይማኖታችን ያለን ቀናኢነት፣ ለቋንቋችን እና ለራሳችን ያለን ክብር፣ ስለሌሎች ህዝቦች ያለን የተሳሳተ አመለካከት፣ የተጠቃሚነት መንፈስ፣ የተጎጅነት መንፈስ፣ ሁሉም ከመጫን የማትመለሷቸው ቁልፎች ናቸው። ለዚሁ ቁማርና ትርፍ ስትሉ ጀግና ትገድላላችሁ፣ ጀግና ትፈጥራላችሁ፣ እውነት ትሰውራላችሁ፣ እውነት ትፈበርካላች ሁ፣ ጠላት ትፈጥራላችሁ፣ ወዳጅ ትመስላላችሁ፣ ትገድላላችሁ፣ ታሳድዳላችሁ፣ ታዋርዳላችሁ፣ ትዋረዳላችሁ። ግን አንድ ነገር አስታውሱ በሁልቱም ወገን ያላችሁ አንድ ቀን አምላክ ስራ መስራት ይጀምራል ያኔ ያፋቅረናል ያኔ ያላቅሰናል ያኔ እናንተ በሰራችሁት ታፍራላችሁ!Tessema Simachew
A rare mind manifestation. I just wish i could talk to you. I read so much into these words. I agree that one day GOD will hear our prayers!!!
Deleteወንድም ዳኒ የምትሰጣቸው ሃሳቦች ሁሉ ይመቹኜል፤ በርታልነን
ReplyDeleteቋንቋና ዜማችን
ReplyDeleteቀረርቶ ፉከራችን
እስክስታ ዳንኪራችን
ማየታችሁ በስብሰባ
ማጀባችሁ በጭብጨባ
ሸጋ ነው ማክበራችሁ
መልካም ነው መውደዳችሁ::
ለዘንድሮም ለአምና
ላደረጋችሁት ሁሉ
አቅርበናል ምስጋና
ግን ባህላችን ስትወዱ
ተሰብስበን እናለቅስ
በአደባባይ እንጮህም ዘንድ ፍቀዱ
ይሄም ባህላችን ነውና !
ውበት ልምላሜ
ReplyDeleteፍቅር ብልጽግናን
ሰላምና እፎይታን
ባፋችን አሳደን
አሳደን አሳደን
መያዙ ቢያቅተን፤
ያው እንታያለን!!!
አኩፋዳ ይዘን፤
በነውር ተንቆጥቁጠን…
በርዛት አጊጠን…
በጦር ተኩነስንሰን…
በሬሳ አሸብርቀን…
enem የለቅሶ ቀን አማረኝ ! ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ- ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
ReplyDeleteከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተገልሎ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ-ሰው ተደብቆ
መሽቶ፥ የማታ ማታ ነው፥ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው፡፡ . . .
ብቻውን ነው የሚረታው፡፡ . . .
ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ተማምጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ . . .
መሽቶ፥ ረፍዶ፥ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ፥ በዝምታ ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር . . .
የኋላ የኋላ፥ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
ዓይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ ዓይኑ የሚረጥብ
የብቻ፥ እንባ ወዙ እሚነጥብ፡፡
ብቻውን ነው፥ ብቻውን ነው . . .
የእንባ ጭለማ ለብሶ ነው
ወንድ ልጅ ወዙ እሚነጥበውዕጣውን ለብቻው ቆርሶ
ብቻውን ሰቀቀን ጐርሶ
ብቻውን ጭለማ ለብሶ
ገበናውን ሣግ ሸፍኖ
ክብሩን በሰቆቃ አፍኖ
ሌሊት፥ የማታ ማታ ነው
ሕቅ እንቁን እሚነጥበው
ኤሎሄውን እሚረግፈው . . .
ከዓይኑ ብሌን ጣር ተመጦ
ከአንጀቱ ሲቃ ተቆርጦ
ደም አልሞ ፍም አምጦ
ከአፅመ-ወዙ እቶን ተፈልጦ
ከአንጀቱ ሲቃ ቆርጦ
ደም አልሞ ፍም አምጦ
ከአፅሙ ወዙ እቶን ተፈልጦ
እንደጠፍር-ብራቅ እምብርት
እንደእሳተ ገሞራ ግት
‘ርቅ ነው ወንድ ልጅ እንባው
ደም ነው፥ ፍም ነው እሚያነባው፤
ንጥረ ሕዋስ ነው ሰቆቃው
ረቂቅ ነው ምሥጢር ነው ጣሩ፥__ብቻውን ነው የሚፈታው፥
ብቻውን ነው የሚረታው፡፡
ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ሰቀቀኑን በሆዱ አጥሮ
በአንጀቱ ገበና ቀብሮ
ውሎ ጭጭ እፍን ብሎ፥ እንደደመና ተቋጥሮ
ጣሩን ውጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተሰትሮ፥ . . .
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
ከቤተ-ሰው ተደብቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ፥
ተሸሽጎ ተከናንቦ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ . . .
የብቻ ብቸኝነቱ፥ የጭለማ ልብሱ እስኪደርስ
በዓይን አዋጅ ሃሞቱ እንዳይረክስ
ቅስሙ በገበያ እንዳይፈስ
ተገልሎ በእኩለ-ሌት፥ ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ፡፡
ይሆናል፡፡ እንደ ማንዴላ ያሉ መሪዎች በመሬት ላይ ሐውልት ሲተከልላቸው ደረቅ ሐውልት አይሆንም፤ መልእክት ያለው ሐውልት እንጂ፡፡ማንዴላ አይሞትም፤ ጀግና አይሞትምና፤ የማንዴላ አይረሳም፤ ሕዝብ ልብ ውስጥ የገባ ሰው አይረሳምና፤ ማንዴላ አያልፍም፣ በጎ ሥራ አያልፍምና፡፡
ReplyDeleteገሩም ምከር ነው ሳይመሽ ከሰራንበት።
ReplyDeleteI heard many powerful words about him but this comparisons is so touch because it pass through my heart.
ReplyDeletethanks
LONG LIVE MANDELA!
ReplyDeleteI think most of you guys, including Daniel don't know the truth in SA. More than 90% of TRUE SAs live under poverty and the mistake was made in the early 1990s.
ReplyDeletePlease do a bit of research before publishing such kind of stories.
thank you Dani.Girum iyita new.
ReplyDeleteመሪነትና ባለ ሥልጣንነት ምን ያህል እንደሚለያዩ ማንዴላ አንድ ማሳያ ናቸው፡፡ ማንዴላ ባለ ሥልጣን አልነበሩም፤ መሪ እንጂ፡......................
ለዲ/ን ዳንኤል በዚህ ጉዳይ መልእክትህን እንድታስተላልፍ እወዳለሁ::በአንድ ጽሑፍህ ይሟላል እንጂ አይሞላም ዓይነት ሀሳብያዘለ መልእክት መመልከቴን አስባለሁ:: ማንዴላ እንደኛ ሰው ናቸው ስለዚህ የሰውነት ሥራቸውን ሠርተው ሲያልፉ በጎም ክፉም ማሳላፋቸው ሊዘነጋ አይገባውም:: በሚመሰገኑበት አመስግኖ መጻፍ ስህተት የለውም:: መልአክ ናቸው ካልተባለ በቀር:: ወንድማችን ፍጽምናቸውን ሳይሆን ሥራቸውን ነው የጻፈው:: ምሳሌ ልናደርጋቸው የምችልበት ነጥብ አለን ያ ነው የተወሳው:: ጃማይካውያን ስለ ኃይለ ሥላሴ ይጽፋሉ ማየት የሚፈልጉበት መስበክ የሚሹትን ሊያደንቁ የሚያስፈልጋቸውን ሥራዎቻቸውን ነው አብዝተው የሚያወሱት:: ይሄንን ማድረግ በምንም መመዘኛ ስህተት ተብሎ አያስወቅስም:: ጠቃሚ ከሆነ ተቃራኒውን ሌላ ገጻቸውን ማስነበብ ይቻላል እንጂ እየደረሱ መቀዋወም ምን ይሉታል? ማወቅ ያለብን ነጥብ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ መልአክም ፈጽሞም ሰይጣን አለመሆናቸውን ነው:: ሰዎች ነን ነፍስም ሥጋም አለን፣ ደካማም ብርቱም ነን፣ . . . አርአያነት ሲወሳ ግን ምንግዚም በጎነገር ጎልቶ ይነሳል:: ለሀገር ለወገን እንሠራለን የሚሉ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ሰው ለማፍራት ከሆነ የሚደክሙት የማይሆን ነውና ይታረሙ:: በሰውነት እንመንና ከሰው የምንጠብቀውን እናገኛለን::
ReplyDeleteMandelan yezih zemen akal hogne behiwot eyalu Gedlachewun bemesmate rasen Ejig yetadelhu tiwulid adirge asbalehu. yemietilew tiwulid ke Mandelan kemetshaf yagegnachewal. ene gin be akal. Hulachihum Simugn "Mandella ke KIRSTOS ketlew lesew lij yenoru sew nachew". GOD BLESS MANDELLA
ReplyDeleteD/n Dany, I don't have any word to say about you. I simply say GOD bless youuuuuuuu!
ReplyDeleteGOD bless youuuuuuuuuuuuu!.
ReplyDelete‹‹እኛ የታገልነው የነጭ የበላይነትን በጥቁር የበላይነት ለመተካት አይደለም፤ የታገልነው ነጮች፣ ጥቁሮችና ሌሎች በእኩልነት የሚኖሩባትን ደቡብ አፍሪካ ለመመሥረት ነው››
ReplyDeleteበእውነት ግን አሁን በደቡብ አፍሪካ ነጮች እና ጥቁሮች በእኩልነት እየኖሩ ነው ?መልሱን ለዚህ ጽሁፍ አንባቢዎች እና ለዳንኤል ክብረት ትቼዋለሁ፡፡የኤፍሬም ስዩም ሙዚ-ቃል የግጥም አልበም ላይ ማንዴላ የተሰኘውንም ግጥም እንድታነቡት ጋብዣችኋለሁ፡፡
Icon min malet new?
ReplyDeleteHello leaders of Africa,it is the right time to learn from MANDELA you can have the chance to be honor by your people. All of u didn't leave your power for your people. you are still holding all the power of your own country w/c means you are colonizing your own brother & sister. you are violating the rights of innocent ppl. you are changing our natural resources by gun with westerns. please don't leave AFRICA for western robbers. we are the children of today & you were last generation to lead Africa after colonization. we the new generation of today ask you to leave your power for your people we all need a better place to leave but we haven't still create it
ReplyDeleteWe love madeba
ReplyDeleteWe love Madeba
ReplyDeleteWe love madeba
ReplyDeleteI LOVE YOU WE LOVE YOU MANDELLA. YOU REMAIN IN OUR HEARTS FOREVER.
ReplyDeleteThere is one proverb from Mandela.. Readers are leaderes. ...really he was leader...
ReplyDeleteWhat does Nelson Mandela Death Teach for the world leaders? This is a time for the world leaders to realize remarkable things Nelson Mandela had done for his country and world. They have to honor him by doing the right thing. He was iconic figure and leader who thought lessons to the world by example. He didn’t fight enemy those who put him in jail for 27 years, but instead he reconciled the country with love and dignity during hardship that he faced from White people. He also transformed better future for all race. It is very sad especially for African leaders those who are slaughtering their own citizens for difference ideology. It is not about a color of your skin, what tribes you come from, what race you born with or where you come from, it is how you feel for all human being as whole. We have lost one of most influential and profoundly best human being in our generation.
ReplyDeleteመሪነትና ባለ ሥልጣንነት ምን ያህል እንደሚለያዩ ማንዴላ አንድ ማሳያ ናቸው፡፡ ማንዴላ ባለ ሥልጣን አልነበሩም፤ መሪ እንጂ፡፡ ባለ ሥልጣን በሰው ገንዘብ ውስጥ እንጂ በሰው ልብ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ባለ ሥልጣን ይፈራል እንጂ
ReplyDeleteአይከበርም፤ ባለ ሥልጣን ቢሮ አለው እንጂ ሀገር የለውም፤ ባለ ሥልጣን የሚላላኩት ሠራተኞች እንጂ የሚጸልዩለት ወገኖች የሉትም፡፡ ባለ ሥልጣን የሚያዘው ሰው እንጂ የሚያፈቅረው ሰው አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ፊርማውን የሚፈልግ እንጂ እድሜውን የሚፈልግ የለም፤ ባለ ሥልጣን ብዙ ገንዘብ እንጂ ብዙ ልቦች አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ከሥልጣን ወዲህ እንጂ ከሞት ወዲያ ተዝካር የለውም፡፡
ማንዴላ ከሞት በኋላም ይኖራል፡፡ በብዙ ልቦች ውስጥ ይኖራል፡፡
ReplyDelete'ብዙ ባለሥልጣናት በሕይወት እያሉ በሰው ልብ ውስጥ ሐውልት መሥራት ስለማይችሉ፣ ከሞቱ በኋላ የድንጋይ ሐውልት ይሠራላቸዋል፡፡ ነገር ግን ሐውልታቸው መልእክት አልባ ሐውልት ይሆናል፡፡ እንደ ማንዴላ ያሉ መሪዎች (ሰዎች) በመሬት ላይ ሐውልት ሲተከልላቸው ደረቅ ሐውልት አይሆንም፤ መልእክት ያለው ሐውልት እንጂ'- እኛም ለወገን ለአገር ለአኅጉር ብሎም ለዓለም የሚተርፍ ታሪካዊ ሥራ በመሥራት ወይም የሚሠሩትን በማበረታታት እና በመደገፍ እንደ ማንዴላ ያለ በሕዝብ ልብ ውስጥ የሚቀር ሐውልት ለማቆም አምላካችን ልብ ይስጠን!
ReplyDeleteI see comments made about Mandela blaming him that he conspired with the whites to let them stay in SA and the poverty level is high within the black community. Everyone has a choice to excel, Mandela can not do magic in their lives so its up to the individuals to get real, make an effort and change their lives. I believe Mandela is an Icon and he is exceptional. African leaders have a hell of a lot to learn from him. May your soul rest in peace Mandela
ReplyDeleteላንተም ዕድሜና ጤና ይስጥሕ እሳቸውንም ነፍሳቸውን ይማር
ReplyDeleteላንተም ዕድሜና ጤና ይስጥህ እሳቸውንም ነፍስ ይማር
ReplyDeleteላንተም ዕድሜና ጤና እሳቸውንም ነፍስ ይማር
ReplyDeleteSometime I hate you Dannie, because while when I was waiting your post. it just pass quick and you add another, where do you get these idea. When did these post, I haven't read it, I just find it when I was searching for a new one. So how can I get your everyday post to my email, because I already have my email in your website which means it should come to my email. But I don't get it. Over all I will see you on summer If God will I want visit Ethiopian even tho when I am Eritrean. I will see you there I love you
ReplyDelete