አበሻን በአንድ እግሩ ያስቆመ፤ ለሃያ አራት ሰዓታት የመግቢያ ትኬት ፍለጋ ያሰለፈ፤
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የብሔራዊ ቡድኑን ዐርማ የያዙ ቲሸርቶች እንዲቸበቸቡ ያደረገ፤ ሕዝብ እንደ መንጋ ንብ አንድ ዓይነት ዜማ
እንዲያዜም ያስቻለ፤ ሽማግሌን እንደ ሕጻን ያስጨፈረ፤ ሕጻንን እንደ ሽማግሌ ያስተከዘ፤ የፓርቲና፣ የዘር፣ የእምነትና የባህልን
አጥር አስጥሶ ወገንን በአንድነት ገመድ ያስተሣሠረ፤ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
ተረስተን ነበረ፤ ረስተንም ነበረ፤ ርቀን ነበረ፤ ተርቀንም ነበረ፤ ተርተን ነበረ፤
ተረት ሆነንም ነበረ፤ እግርን ከኳስ አውጥተን ለሩጫ ብቻ አውለነው ነበረ፤ እንዲያ በሩጫ ዓለምን አስደምመን፣ ኳስ ሜዳ ግን
ዘጠና ደቂቃ መሮጥ አቅቶን ደክሞን ነበረ፡፡ ሕዝባችን ከካምቦሎጆ ኳስ ወደ ዲ ኤስ ቲቪ ኳስ ፊቱን አዙሮ ነበረ፡፡ ይህንን
ቀይሮ በአፍሪካ ምድር ከ31 ዓመታ በኋላ ብቅ እንድንል ያደረገ፤ በዓለም መድረክ ‹እኛም አለንበት› እንድንል ያስቻለ - ይኼ
ሰው ጀግና ነው፡፡
ድሮም የዓለምን ታሪክ የሚቀይሩት ጀግና ግለሰቦች ናቸው፡፡ አገር በኮሚቴ አድጋ፣
ታሪክ በቡድን ተቀይሮ አያውቅም፡፡ የዓለም ክፉም ሆነ በጎ ታሪክ የተለወጠው የመለወጥ ዐቅም ባላቸው ግለሰቦች ማርሽ ቀያሪነት
ነው፡፡ ሌላው አጃቢ፣ ተባባሪ፣ ተከታይና ፈጻሚ ነው፡፡ ቢስማርክ የሚባል ሰው ባይነሣ ኑሮ ጀርመን የምትባል ሀገር ተረት ትሆን
ነበር፡፡ ካሣ (ቴዎድሮስ) የሚባል ጀግና ባይነሣ ኖሮ የዘመናዊቷን ኢትዮጵያ ቅርጽ ማን ይቀይር ነበር፡፡ አብርሃም ሊንከን
የሚባል ፕሬዚዳንት ባይነሣ ኖሮ የአሜሪካን የርስ በርስ ጦርነት ማን ይፈታው ነበር፡፡ ሌኒን የሚባል ሰው ባይወለድ ኖሮ
ኮሚኒዝም የሚባለውን ነገር ከሃሳብ አውጥቶ ማን ሥጋ ያለብሰው ነበር፡፡ ጎርባቾቭ የሚባል ሰው ባይፈጠር ኖሮ ኮሚኒዝምን ማን
ታሪክ ያደርገው ነበር፡፡ ማንዴላ የሚባል ጀግና ብቅ ባይል ኖሮ የዛሬዋን ደቡብ አፍሪካ ማን ይፈጥራት ነበር፡፡ ቴዎዶር ኸርዝል
የሚባል ይሁዲ ባይነሣ ኖሮ እሥራኤል የምትባለውን ሀገር ማን እውን ያደርጋት ነበር፡፡ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የሚባሉ ንጉሥ ባይነግሡ
ኖሮ ለሁለት የተከፈለችውን አፍሪካ ወደ አንድ አምጥቶ ማን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሠረት ያደርግ ነበረ፡፡
በቅርቡ የታሪካችን ክፍል እየተደጋገመ አንድ ነገር ሲነገረን ነበር፤ እየተነገረንም
ነው፡፡ ‹ታሪክ የሚሠራው ሰፊው ሕዝብ ነው› ይባላል፡፡ እንዴው ለመሆኑ ሕዝብ እንዴት ተሰባስቦ፣ እንዴትስ ተመካክሮ፣ እንዴትስ
ወደ አንድ አቋም ደርሶ ነው ታሪክ የሚሠራው? ሕዝብ ማለትኮ ከመቀሌ እስከ ሞያሌ፣ ከአሶሳ እስከ ቶጎ ጫሌ ያለው ነው፡፤ የት
ተዋውቆ፣ መቼ ተገናኝቶ፣ እንዴትስ አድርጎ ተደራጅቶ ታሪክ ይሠራል፡፡ ሕዝብ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃልም ተናጋሪ
እንዲሆን የሚያደርጉትኮ ግለሰቦች ናቸው፡፡
ሕዝብ ታሪክ እንዲያራምድ የታሪክ ሞተር የሚያስነሡ አውራ ግለሰቦች ያስፈልጉታል፤
ሃሳብ የሚያመነጩ፣ ሃሳቡን የሚያሰርጹና ለሃሳቡ ግንባር ቀደም የሚሆኑ ግለሰቦች ያስፈልጉታል፡፡ የአፕል ካምፓኒ መሥራች ስቲቭ
ጆብስ ብቅ ባይል ኖሮ የሞባይል ስልክን ታሪክ ማን ይቀይረው ነበር? ‹ዓለምን የቀየሩት ሦስት አፕሎች ናቸው፡፡ አዳም የበላው
አፕል፣ በኒውተን ራስ ላይ የወደቀው አፕልና ስቲቭ ጆብስ የሠራው አፕል እስኪባል ድረስ የስልክን ተፈጥሮ የቀየረው እርሱ
አይደለም ወይ፡፡ እነ ማርክ ዙከርበርግ ተነሥተው ፌስ ቡክ የሚባል ማኅበራዊ ሚዲያ ባይፈጥሩ ኖሮ የዘመኑን የግንኙነት ባህል
ማን ይቀይረው ነበር?
አዎን ሕዝብ አለ፡፡ ሕዝብም ግን ታሪክ ያራምዳል እንጂ ታሪክን አይሠራም፡፡ ግለሰቦች
የፈጠሩትን፣ ያሰቡትን፣ የፈለሰፉትን፣ ያመነጩትን የሚያራመደው፣ የሚያቀነቅነው፣ የሚያስፈጽመው፣ ገንዘብ የሚያደርገውና ያንን
ሃሳብ፣ ፈጠራ፣ ፍልስፍና፣ ግኝትና ጥበብ የኑሮ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል የሚያስችለው ሕዝብ ነው፡፡
ቡድን ታሪክ የማይሠራበት ምክንያት ታሪክ ለመሥራት ማሰብ ወሳኝ ስለሆነ ነው፡፡ ማሰብ
ደግሞ ግላዊ እንጂ በቡድን ሊታሰብ አይችልም፡፡ በቡድን መመካከር፣ መወያየት፣ ማጥናት፣ መመራመር ይቻል ይሆናል፡፡ በቡድን
ማሰብ ግን አይቻልም፡፡ ሰው የተፈጠረው በየግሉ ነው፡፡ እንደ መላእክት በማኅበር አልተፈጠረምና በማኅበር ሊያስብ አይችልም፡፡
በየግል የታሰበውን ግን በማኅበር መፈጸም ይቻላል፡፡ ቡድኖች፣ ማኅበራትና ተቋማት በግለሰቦች የሚመነጩትን ሃሳቦች የሚፈጽሙ፣
የሚያዳብሩና ሕልው እንዲሆን የሚያደርጉ እንጂ ግለሰቦችን የሚተኩ ግን አይደሉም፡፡
አንዳንድ ማኅበረሰብ ለግለሰቦች ቦታ የለውም፡፡ ‹ሰፊው ሕዝብ› የሚባል የማይጨበጥ
አካል አስቀምጧል፡፡ ሁሉንም ነገር ለሰፊው ሕዝብ ይሰጠዋል፡፡ ሕያው የሆኑትን ግለሰቦችን ገድሎ፣ ሕያው ያልሆነ ‹ሰፊ ሕዝብ›
የሚባል አካልን ያነግሠዋል፡፡ ሰፊ ሕዝብ ድርሰት ይደርስ ይመስል፤ ሰፊ ሕዝብ ዜማ ያመነጭ ይመስል፤ ሰፊ ሕዝብ ይፈጥር ይመስል፤
ሰፊ ሕዝብ ይፈላሰፍ ይመስል፡፡ የሕዝብ ሆነው የቀሩ ግጥሞች፣ ታሪኮች፣ አባባሎች፣ ዜማዎችና ባህሎች እንኳን ‹ሰፊ ሕዝብ› ውጦ
ያስቀራቸው ግለሰቦች ባልታወቀ ዘመንና ባልታወቀ ቦታ ያመነጩት ነው፡፡ ግን ምን ያደርጋል ስንት ባለ ዜማዎች፣ ስንት ባለ
ቅኔዎች፣ ስንት ጀግኖች፣ ስንት ታሪክ ነጋሪዎች፣ ስንት ተረት ደራሲዎች ተውጠው ቀርተዋል፡፡
ይኼው የሐበሻ ጀብዱ የሚባል መጽሐፍ ቢተረጎም አይደል እንዴ ከሰላሌ የሄደ አብቹ
የተባለ ጀግና ማይጨው ላይ ታሪክ መሥራቱ የታወቀው፡፡ ሰላሌ ወርዳችሁ ብታስሱ ግን አብቹን የሚያውቀው የለም፡፡ ታሪኩን ሕዝብ
ወርሶታል፡፡ ‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግና ነው› በሚለው ብሂል ተውጦ አብቹ ቀርቷል፡፡
ባህላችን ለቡድኖች፣ ለማኅበራትና ለተቋማት የሚያደላ በመሆኑ አያሌ ግለሰቦች
እንዳይሠሩ አድርጓል፡፤ የሠሩትም ቢሆኑ እንዳይታወቁ ውጧል፡፡ ሥራቸውን እንጂ ሰዎቹን ዕውቅና አንሰጣቸውም፡፡ ለመሆኑ ይህንን
ደረታችንን ነፍተን የምንኮራበትን የአኩስም ሐውልት ሐሳብ ያፈለቀው ማነው? ማን ነበር ጥበበኛው? ማን ነበር ቀማሪው? ማንስ
ነበር ያቆመው? ሐውልቱን እንጂ ማንነቱን አላገኘነውም፡፡ የታደሉት ሀገሮች ሳያውቁት ለቀሩት ጀግና ወታደር ‹ላልታወቀው
ወታደር› የሚል ሐውልት ይሠሩለታል፡፡ እኛስ ምን ነበረበት ‹‹ላልታወቀው የአኩስም ሐውልት ጠቢብ›› የሚል ሐውልት ብናቆምለት፡፡
ለመሆኑ ምን ምን ዕውቀት ያሉት ሰው ነው ያንን ለማሰብ የሚችለው? ታሪኩን በመላ ምት እንደገና ማነጽ ይቻላልኮ፡፡ ሰዓልያንና
ቀራጽያን በምናባቸው ማሰብ ይችላሉ፤ የታሪክ ምሁራን ከግኝቶቻቸው ተነሥተው መተለም ይችላሉ፡፡
ልጆቻችን ሐውልቱን እንዲያደንቁ እንጂ ጠቢቡን እንዲያደንቁ አላደረግናቸውም፡፡
የጎንደርን ሕንፃ እናደንቃለን እንጂ ስለ አርክቴክቶቹ፣ ስለ መሐንዲሶቹ፣ ስለ ግንበኞቹ አውርተን አናውቅም፡፡ ግንቡ በተአምር
የተሠራ ይመስል፡፡ በፋሲል ግንብ ውስጥም እነዚያ ጠቢባን እነማን እንደሆኑ ሊያሳይ የሚችል ምንም ነገር የለም፡፡ አንዴ
ፖርቹጋሎች አንዴ ግሪኮች አንዴ ፈረንሳዮች እያልን የመሰለንን ሁሉ በቡድን ስም ስንጠራ እንኖራለን፡፡ የጥበብ አሻራዎቻችን
በሚገኙባቸው በታላላቅ አድባራትም ያሠሩት ሰዎች ስም እንጂ የእነዚያ ጠቢባን ስም ተረስቷል፡፡ ልክ በመጻሕፍቱ ላይ ያስጻፉት
ሰዎች እንጂ የደራስያኑ ስም ተረስቶ እንደቀረው፡፡
ብዙ ጥያቄዎች አሉ፡፡ መመለስ የነበረብን ግን ያልመለስናቸው፡፡ እንዴው ለአፍ ታሪክ
ያህል እንኳን የሐበሻ ቀሚስን ማን ጀመረው? እንጀራ መጋገርን ማን አመጣው? አምባሻ ዳቦ በማን ተፈለሰፈ? ሞሰብና ሰፌድ መስፋትን
ማን አመጣው? ዋሽንትን ማን ጀመረው? ክራርንስ ማን ፈጠረው? ቆጮን ማን ጀመረው? ክትፎስ የማን ፈጠራ ነው? ገንፎንስ ማን
ፈለሰፋት፣ ጭቆና ቆጭቆጫ፣ ቃተኛና ፍርፍር፣ ቆሎና ዳቦ ቆሎ ማን ይሆን ያመጣቸው? ሽሮና በርበሬ፣ ድቁስና ሚጥሚጣ፣ አዋዜና
ስናፍጭ ማን ነበር አስቦ የፈለሰፋቸው? እነዚህን ጥያቄዎች ብንጠይቅ የብሔረሰቦችና የጎሳዎች ስም፣ የአካባቢና የጎጥ ስም እንጂ
የግለሰቦችን ስም አናገኝም፡፡ እነርሱ ተውጠው ቀርተዋል፡፡
ልጆቻችን አርአያ ሊያደርጉት፣ ሊከተሉትና
ሊፎካከሩት የሚችሉት ግለሰብን ነው፡፡ ማኅበርን ወይም ሕዝብን መከተል አይቻልም፡፡ ግለሰቦችን በዋጥናቸውና ባጠፋናቸው ቁጥር፣
ለጀግኖቻችን ክብርና አድናቆት በነፈግናቸው ቁጥር ሌላ ጀግና ማግኘት አንችልም፡፡ ሰነፎች ‹ሕዝብ› በሚባል የማይዳሰስ መዋቅር
ውስጥ ገብተው ይደበቃሉ፡፡ ሕዝብ ተጠያቂነት የለበትምና፡፡ ሰነፎችም ተጠያቂነትን ሲፈሩ ሕዝብ ውስጥ ይደበቃሉ፡፡ እንደ ጀግኖች
መሥራት ሲያቅታቸው የጀግኖችን ዋጋ ለሕዝብ ይሰጡና እነርሱም የዋጋው ተቋዳሽ ይሆናሉ፡፡
እኔም እሑድ ዕለት በተደረገው የኢትዮጵያና
የደቡብ አፍሪካ ጨዋታ ያየሁት ይኼንን ነበር፡፡ ቡድኑን አሠልጥኖና መርቶ ለድል ያበቃው አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ሳይሆን ሌሎች
ነበሩ ሲመሰገኑ የነበሩት፡፡ ከሌሊት ጀምረው ወረፋ ያዙት፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ለብሰው የደገፉት፣ ጨዋታውን ያስተላለፉት፡፡
ለስፖርት ልዩ ፍቅር ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነበሩ ስማቸው ከፍ ከፍ ያለው፡፡ እነዚህ ሁሉ ከፍ እንዲሉ ያደረገው ግን ሰውነት
የሚባል አንድ ጀግና ተነሥቶ ነው፡፡ በስታየሙ ውስጥ ግን ‹ሰውነት ሆይ እናመሰግናለን› የሚል ነገር አላየሁም፡፡
የአፍሪካ ዋንጫ ድሮም ነበረ፤ የዓለም
ዋንጫ ድሮም ነበረ፤ ከሱዳን ጋር ብዙ ጊዜ ገጥመናል፤ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ደጋግመን ተጫውተናል፡፡ አሁን ማርሹን የቀየረው
ማነው? ሰውነት የሚባል አንድ ታሪክ ሠሪ ነዋ፡፡ ማንቸስተር
ዩናይትድ ባለፈው ጊዜ ሃያኛውን ዋንጫ ሲወስድ ስታዲዮሙ ‹ፈርጉሰን ሆይ እናመሰግናለን፤ ፈርጉሰን ጀግና ነው፤ ፈርጉሰን
ለዘላለም በልባችን ይኖራል› በሚሉ መፈክሮች ተሞልቶ ነበር፡፡ ልክ ነው ፈርጉሰን የማንቸስተርን ታሪክ ለውጠውታል፡፡ ሰውነትም
የኢትዮጵያ እግር ኳስን ታሪክ ለውጦታል፡፡
ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ ዕንቁላል ነበር ይኼን ጊዜ አበሻ
የተባለውኮ ያለምክንያት አይደለም፡፡ በታሪክ ውስጥ የወሳኝነት ድርሻ ላላቸው ሰዎች
ክብር ለመስጠት እንጂ፡፡ ሰውነት የሚባል አሠልጣኝ ተወልዶ ይኼው ታሪክ አየን፡፡ ትረካችን ተለውጦ ለአፍሪካ ዋንጫ መብቃትና
አለመብቃት፤ ለዓለም ዋንጫ መብቃትና አለመብቃት ሆነ፡፡ ‹ስንት ለዜሮ ይሆን የምንሸነፈው?› የሚለው ሥጋት ቀረ፡፡ ከዚህ በላይ
ምን ጀግንነት አለ? ከዚህ በላይ ምን የገጽታ ግንባታ አለ፡፡
ተዉ ጎበዝ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
እኛ በጠባያችን አንበሳውን ካዳነው ሰው ይልቅ የገደለውን ጀግና ስለምናደርግ ነው
እንጂ፡፡ እኛ በጠባያችን ችግር ሲመጣ ለግለሰቦች፣ ድል ሲመጣ ለጋራ ስለምንወስድ ነው እንጂ፤ እኛ በጠባያችን ማኅበርና ቡድን
ግለሰብን ስለሚውጥ ነው እንጂ፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ውስጥ በአረንጓዴ ቀለም አሻራውን ያስቀመጠ
ጀግና፡፡
በቅርቡ ስለ እግር ኳስ ሜዳዎች የሥነ ምግባር ችግር በተጠራ ስብሰባ ላይ ‹አሠልጣኝ
ሰውነት መሰደብ የለበትም› ተብሎ ሲነሣ አንድ የእግር ኳሱ ባለሥልጣን ‹አሠልጣኝ ቢሰደብ ምን አለበት? አሠልጣኝን መስደብ ዛሬ
ነው እንዴ የተጀመረው፡፡ ድሮም እነ እገሌና እገሌ ሲሰደቡ ነበሩ›› እያሉ ሲቀልዱ ሰማሁ፡፡ ‹እንኳንም እርስዎ የጤና ጥበቃ
ሚኒስትር አልሆኑ› ብዬ ደስ አለኝ፡፡ የሴት ልጅ ግርዛት ይቅር ሲባሉ ‹ሴት መገረዝ የጀመረችው ዛሬ ነው እንዴ› ይሉ ነበር፡፡
ግግን ማስቧጠጥ ይቅር ሲባሉ ‹‹ግግ መቧጠጥ በኛ ዘመን ነው እንዴ የተጀመረው፤ ስንቱ ሲያስቧጥጥ አልነበረም እንዴ›› ይሉ
ነበር፡፡ እንጥል ማስቆረጥ ይቅር ሲባሉ፡፡ እንጥል ማስቆረጥ ድሮም ነበረ፡፡ ምን አዲስ ነገር መጣ›› ይሉን ነበረ፡፡ ‹‹ ያለ
እድሜ ጋብቻ ይቅር ሲባሉ ‹‹ምነው እገሊትና እገሌ ያለ እድሜያቸው አልነበረም እንዴ የተጋቡት? ዛሬ ምን አዲስ ነገር መጣ››
ይሉን ነበር፡፡ እግዜርም ዐውቆ ሰማዩን ዐርቆ ማለት ይኼ ነው፡፡
ለነ ወልደ መስቀል ኮስትሬ ክብር እየነሣን
የኢትዮጵያ ሩጫ እንዲያድግ የምንመኝ የዋሐን ጀግናን መግደልና ታሪክ ሠሪን ማጥፋት ለምዶብናል መሰል፡፡ በላይ ዘለቀን ገደልን፤
አክሊሉ ሀብተ ወልድን ገደልን፣ አቤ ጎበኛን ገደልን፣ በዓሉ ግርማን ገደልን፣ አበበ አረጋይን ገደልን፣ ዮፍታሔ ንጉሤን
ገደልን፣ አለቃ ታየን ገደልን፣ ንግሥት ዘውዲቱን ገደልን፣ ከበደ ሚካኤልን ሀብታቸውን ነጥቀን በቁማቸው ገደልን፣ ሐዲስ
ዓለማየሁን መጽሐፋቸውን እያሳተምን የእርሳቸውን ንብረት ቀምተን በቁማቸው ገደልን፣ ስንቶቹ ዘፈናቸውን እየሰማን እነርሱን ግን
ገደልን፤ ስንቶቹን ቲያትራቸውን እያየን እነርሱን ግን ገደልን፤ ስንቱን ስንቱን ገደልን፡፡
አገዳደላችን በሦስት መንገድ ነው፡፡
አሳቢውን በማጥፋት፣ ሃሳቡን በማጥፋትና ሃሳቡን በመንጠቅ፡፡ ስንት አሳቢዎች ‹ዓሣውን ለማጥፋት ባሕሩን ማድረቅ› በሚለው
ብሂላችን ምክንያት ከነ ሃሳባቸው ተገደሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ሃሳባቸው እንዳይሰማ፣ እንዳይነበብ፣ እንዳይሳካና እንዳይታይ በማድረግ
ተገደሉ፡፡ በሌላ በኩልም አሳቢውን ዝም አሰኝቶ ሃሳቡን በመንጠቅና አሳቢው ተንገብግቦ እንዲሞት በማድረግ ስንት ጀግና
አጥተናል፡፡ የነ አያ እገሌ ፈጠራዎች፣ ሃሳቦች፣ ድርሰቶች፣ ግኝቶች፣ ፍልስፍናዎች ተነጥቀው የነ አቶ እገሌ ሆነው ቀርተዋል፡፡
የነ አያ እንትና ታሪክ ለነ ክቡር እንቶኔ ተሰጥቷል፡፡ የአሳቢዎችን ጥቅም ክብርና ዝና፣ አቀንቃኞች ወስደውት ‹‹የበሬን
ምስጋና ወሰደው ፈረሱ›› ተብሎ ተዘፍኗል፡፡
አሁንም ሺ ‹ሰውነቶች› ወደፊት ተነሥተው
የሀገራችንን የስፖርት መልክ እንዲቀይሩት ከፈለግን የዛሬውን ሰውነት እናወድሰው፡፡ ሰውነት ጀግና ነው፡፡ ታሪክ የለወጠ፣
ሕዝብን ያስዘመረ፣ አገርን አንድ ቋንቋ ያናገረ፤ ቡድኑን መርቶ ውጤት የዘወረ፣ ኃላፊነትን ተሸክሞ ሀገር ያስከበረ፡፡ ከዚህ
በኋላ ያለው ውጤት እንኳን ቢቀየር ሰውነት ግን የኢትዮጵያን እግር ኳስ ወደ አንድ አይተነው ወደማናውቀው የታሪክ ምዕራፍ
አድርሶታል፡፡ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡ ሃያ አራት ሰዓት ስታዲዮም በር ላይ የተሰለፍነው ሰውነት የሚባል ሰው ተስፋ ያለው ቡድን
ስለሠራኮ ነው፡፡ እንዲያ ስታዲዮም ገብተን የደገፍነው ሰውነት የሚባል ሰው የሚደገፍ ቡድን ስላዘጋጀኮ ነው፡፡
ከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣
ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
እግዚአብሔር ያክብርህ ዲያቆን ይሄ መልካም ዕይታ ነው፤ እንደቤተክርስቲያናችን አባባል ይበል ብለናል።
ReplyDeleteA very interesting piece as usual Dani. Please share this to the ethiopian radio and tv journalists. Egzer tsegawun yabizalih berta
ReplyDeleteewnetim yihe sew JEGINA NEW...dani tiru bilehal
ReplyDeleteTo tell the truth this man is hero!
ReplyDeleteit is a good view thank you dani but i have an idea on the spirit of the people after the tournament it was stressing i hate there action we must do a limit on our emotions please say some thing on hoe to support in spiritual friendly way
ReplyDeleteYour article is provocative and good food for thought!!!Yes we need to give the right credit and respect for individuals!!!
ReplyDeletethank you dani nice view yes he is JEGENNA
ReplyDelete
ReplyDeleteከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
Amen, he is a hero indeed..
ReplyDeleteርግጥ ነው፣ ሰውነት ቢሻው በሙያው ጀግና ነው። ጽሁፉም ማስተዋል የተሞላበት የኅብረተሰብ ቅኝት ነው። ላንተ ያደለውን ማስተዋል ለኛም ያድለን። እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን።
ReplyDeleteD/N betam adnakih negn yemtsfachew hulu le Ethiopia Hizb betam tiru yehone astemiro yalew sihon ahunm yemasasihb neger binor nedemiketelew new esum sile Wadibba gedam new menekusat kebota bota sibarereu ena sigelatu tiru adelem ena endate yalu menfesawi ena mehaberawi nuro betemelekete yetsif sew neh esik andi jize be Egziabhier hayel tsaflein tiru kena menifes yaleh sew neh biye new defire ehen yalkuh batekalay sile bete krstaynachin andinet betemeleket e malete new mekinyatum zeregnet beza ehe demo le andinetachin betam adega new esu Egziabhier ayamtaw ena .lelaw ante endalkeu lik ende Sewenet Bishaw lelawm demo malet eyadadu beye chilotaw atewatsio badereg betam tiru yehone tarikawi sira yehonal malet new Egziabhier bereket kehulachin gar yehun amen .
ReplyDeleteI have no words to thank you-my eagle!!!
ReplyDeleteYou are expressing it with your blessed hand what is in my 'heart'!! God bless you Dan!!!!!
Antem jegena neh dani.
ReplyDeletethis is absolutely true i was argue with my friends a because of him. god bless you dani
ReplyDeleteለተስፋይቱ ምድር፣ ቆመናል በጋራ፡፡
ReplyDeleteየኢትዮጵያ፣ ህዝቦች
አብረን-በቀመርነው፣ ህብረብሄር ዜማ
ክተት ተጠራርተን፣ ሀገር ስናለማ
ተረት ሆኖ እንዲቀር፣ ድህነት ጨለማ
ኑ እንውጣ ራስ ዳሽን፣ ከተራራው ማማ
ለዓለመ ዓለም፣
የዳግም ልደትን ብስራት ልናሰማ
ሰውነት ጀግና ነው፡፡ ታሪክ የለወጠ፣ ሕዝብን ያስዘመረ፣ አገርን አንድ ቋንቋ ያናገረ፤ ቡድኑን መርቶ ውጤት የዘወረ፣ ኃላፊነትን ተሸክሞ ሀገር ያስከበረ፡፡ ከዚህ በኋላ ያለው ውጤት እንኳን ቢቀየር ሰውነት ግን የኢትዮጵያን እግር ኳስ ወደ አንድ አይተነው ወደማናውቀው የታሪክ ምዕራፍ አድርሶታል፡፡ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡ ሃያ አራት ሰዓት ስታዲዮም በር ላይ የተሰለፍነው ሰውነት የሚባል ሰው ተስፋ ያለው ቡድን ስለሠራኮ ነው፡፡ እንዲያ ስታዲዮም ገብተን የደገፍነው ሰውነት የሚባል ሰው የሚደገፍ ቡድን ስላዘጋጀኮ ነው፡፡
ReplyDeleteከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
I dont know how to breath, offffffffffff,,,,..... Thank You Dn Dani. I dont have ay word than this for you too.
ReplyDeleteI dont know how to breath, offffffffffff,,,,..... Thank You Dn Dani. I dont have ay word than this for you too.
ReplyDeleteTesfahun , ke AZ
"ልጆቻችን አርአያ ሊያደርጉት፣ ሊከተሉትና ሊፎካከሩት የሚችሉት ግለሰብን ነው፡፡ ማኅበርን ወይም ሕዝብን መከተል አይቻልም፡፡ ግለሰቦችን በዋጥናቸውና ባጠፋናቸው ቁጥር፣ ለጀግኖቻችን ክብርና አድናቆት በነፈግናቸው ቁጥር ሌላ ጀግና ማግኘት አንችልም፡፡ " WEDIJEWALEHU.
ReplyDeleteDniel: Negerochin beteleye ateyay enditay. Endeleloch jeginochachin, yejeginet tsega yetechereh jegnochin neh.
ከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
ReplyDeleteye u r right
DeleteBewnet SEWNET Jegna. Lezih letekeber Tsuf Antem Jegna neh. Egziabher Edime Ketenenetu ga Yistln.
ReplyDeleteWell Written!
ReplyDeleteDn. Daniel Tsega Bereketun yadelehe Ewnet new yehe sew JEGNA NEW
ReplyDeleteጋሽ ይድነቃቸው ተሰማ የአፍሪካው አባት መንግስቱ መ ንግስቱ ወርቁ ... ህልማችሁ እ ውን ሆኗል ጀግና ተተክቷል
ReplyDeleteI don't like some of your articles. But this one is the most interesting article you have ever wrote.
ReplyDeleteከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሄር ይስጥልን ዲ/ን ዳንኤል እጅግ በጣም ጥሩ እይታ ነው፡፡ ሰውነትም በእውነት ጀግና ነው፡፡ አያንዳንዳችን ስለዚህ ፅሑፍ ላልሰማው አሰምተን በየቤታችን ብንነጋገርበት መልካም ነው፡፡
ReplyDeleteይኸውልህ ዳኒ
ReplyDeleteአንድ ታሪክ ከሸፈ ማለት ይሄ ነው፡፡ ሌላ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ታሪክም በዘመኑ እውነት ነበር፡፡ ሲረሳ ተረት ይሆናል፡፡ ላሊበላ በዘመኑ ተሞግሶ ሊሆን ይችላል ወይም አይችልም፡፡ አኩሱምንም ያነጸው እንዲሁ፡፡ ሰውነትም እንዲሁ በዘመኑ ለማንም ያልተደረገለትን ሽልማት ተሸልሞ፣ ክብር አግኝቶ ለዚህ በቅቷል፡፡ እንደውም ሰውነት በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ዝናንም አግኝቷል፡፡ ከዚህ በላይ እንዴት መሆን እንዳለበት … ለዚህም ያበቃው ህዝቡ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ስለዚህ ታሪክን ከክሽፈት ለማዳን ህዝብን ከመውቀስ መቆጠብ ተገቢ ነው፡፡ ህዝብ እኮ…!
አይይይይ!! አንድ ነገር ብቻ ‹‹የሚያውቅ ሰው›› በጣም ያስቸግራል፡፡ ስለ ታሪክ የምታውቀው ‹‹ፕሮ›› መክሸፍ ያሉትን ብቻ ነው፡፡ ‹‹ላሊበላ በዘመኑ ታውቆ ነበር›› ላሊበላ ንጉስ ብቻ ሳይሆን ቅዱስም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ደግሞ ልደትና ረፍታቸው በጠቅላላው ክብራቸው የሚዘከረው ካረፉ በኋላ ነው፡፡ ‹‹ሰውነትም እንዲሁ በዘመኑ ለማንም ያልተደረገለትን ሽልማት ተሸልሞ፣ ክብር አግኝቶ ለዚህ በቅቷል፡፡ እንደውም ሰውነት በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ዝናንም አግኝቷል›› አይይይ!! ልበል በድጋሚ!! ለሰውነት የተደረገው ለማንም ከተደረገው የተለየ አይደለም፡፡ እንደውም እሱ ያመጣው እና የተሰጠው ፍጹም የተለያየ ነው፡፡ በሩጫው ወርቅና ብር ለእኛ ብርቅ አይደለም፡፡ ግን ወርቅና ብር ሲመጣ ‹‹አስሯጩ›› የሚሰጠውን እንተወውና አትሌቶቻችንና ‹‹አስልጣኞቻቸው›› ስንት ስንት ይወስዳሉ? ብዬ አልጠይቅህም፡፡ እስቲ የትኛው አትሌትና አሰልጣኝ ነው ለሚሰራው ሕንጻ መሬት ገዝቶ የሚያውቀው? ልልህ አስቤ ተውኩት፡፡ ሰውነት ግን እኔና አንተ ከመወለዳችን ጀምሮ ያላየነውን (32 ዓመት ቢሞላህ እንዲህ አታስብም ብዬ ነው) አሳይቶን የተሰጠው ምንድ ነው ብዬ አልጠይቅህም፡፡ ‹‹ከዚህ በላይ እንዴት መሆን እንዳለበት …›› ላልከው ጥያቄ ባለፈው (2010) ለዓለም ዋንጫ ስታልፍ ቀኑን ብሔራዊ በዓል አድርጋ የሰየመችውን አገር ጠይዋት ብዬ አልመክርህም፡፡ ‹‹ለዚህም ያበቃው ህዝቡ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡›› ሰውነት ተጫዋቾችን ሲመርጥ ሕዝቡ የት ነበር? ማነው ነበር ያ ወንድምህ ‹‹ጋዜጠኛው›› እንኳን? በሬድዮ ሰውነትን ሲሰድበው ‹‹ሕዝቡ›› የትኛዋን ስድብ ተጋራው? ጠዋት በቁር ተነስቶ ከልጆቹ ጋር ሲደክም ከአንሶላው የወጣ ስንት ‹‹ሕዝብ›› ነበር አብሮት የነበረው? መልሱ ስለሚጠቅምህ ያዘው፡፡ ‹‹ስለዚህ ታሪክን ከክሽፈት ለማዳን ህዝብን ከመውቀስ መቆጠብ ተገቢ ነው›› አይይ ለ4ኛ ጊዜ!! ሽማግሌው እንኳ ችግሩ ገብቶአቸው አርምሞ የመረጡበትን ነገር ……..
Deleteእውነት እውነት እልሻለሁ ዛሬ ተነስቼ ለሰውነት ሃውልት ልስራና ላሞግሰው ብል ቁጥር አንድ ነቋሪዬ የምትሆኚው አንቺ ነሽ፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት ለሰውነት የሚገባውን እንጂ የማይገባውን ክብር መስጠት አይገባም ነው፡፡ ለውጤት ማማር ወይም እሱ ብቻውን መውሰዱም አግባብ አይደለም- የቡድን ውጤት ስለሆነ! ለቡናው መጣፈጥ ስኒው ወይም ጀበናው ሳይሆን የቡናው ጥሩ መሆን እንዳለበት፣ ለእንጀራው ማማር የጤፉ መልካምነት ወሳኝ ሆኖ ሳለ ምጣዱ ወይም ማገዶው መሆን የለበትም!!
Deleteህዝቡማ ምን ያድርግሽ- ሰውነትም ቢሸለም የማንም ብር አይደለም- የህዝቡ ነው፡፡
እንደውም እንደውም ቅጥ ያጣ ሙገሳ እንዲህ ላለ ሃላፊነትን መርሳት፣ ማናለብኝነትን፣ ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ኋላም ለውድቀት ይዳርጋል፡፡ እስቲ ቀጣዩን ግጥሚያ ውጤት ይታጣ!
ድሮስ ሙገሳን የለመደ ራስ ሂስን ከመቀበል… ጥሩ አይደለም-እኔ ይቅር ብያለሁ!!
አበሻን በአንድ እግሩ ያስቆመ፤ ለሃያ አራት ሰዓታት የመግቢያ ትኬት ፍለጋ ያሰለፈ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የብሔራዊ ቡድኑን ዐርማ የያዙ ቲሸርቶች እንዲቸበቸቡ ያደረገ፤ ሕዝብ እንደ መንጋ ንብ አንድ ዓይነት ዜማ እንዲያዜም ያስቻለ፤ ሽማግሌን እንደ ሕጻን ያስጨፈረ፤ ሕጻንን እንደ ሽማግሌ ያስተከዘ፤ የፓርቲና፣ የዘር፣ የእምነትና የባህልን አጥር አስጥሶ ወገንን በአንድነት ገመድ ያስተሣሠረ፤ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
ReplyDeleteጆቻችን ሐውልቱን እንዲያደንቁ እንጂ ጠቢቡን እንዲያደንቁ አላደረግናቸውም፡፡ የጎንደርን ሕንፃ እናደንቃለን እንጂ ስለ አርክቴክቶቹ፣ ስለ መሐንዲሶቹ፣ ስለ ግንበኞቹ አውርተን አናውቅም፡፡ ግንቡ በተአምር የተሠራ ይመስል፡፡ በፋሲል ግንብ ውስጥም እነዚያ ጠቢባን እነማን እንደሆኑ ሊያሳይ የሚችል ምንም ነገር የለም፡፡ አንዴ ፖርቹጋሎች አንዴ ግሪኮች አንዴ ፈረንሳዮች እያልን የመሰለንን ሁሉ በቡድን ስም ስንጠራ እንኖራለን፡፡ የጥበብ አሻራዎቻችን በሚገኙባቸው በታላላቅ አድባራትም ያሠሩት ሰዎች ስም እንጂ የእነዚያ ጠቢባን ስም ተረስቷል፡፡ ልክ በመጻሕፍቱ ላይ ያስጻፉት ሰዎች እንጂ የደራስያኑ ስም ተረስቶ እንደቀረው፡፡
የአፍሪካ ዋንጫ ድሮም ነበረ፤ የዓለም ዋንጫ ድሮም ነበረ፤ ከሱዳን ጋር ብዙ ጊዜ ገጥመናል፤ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ደጋግመን ተጫውተናል፡፡ አሁን ማርሹን የቀየረው ማነው? ሰውነት የሚባል አንድ ታሪክ ሠሪ ነዋ፡፡
A fantastic view!
Deleteደሰ የሚል ፍልስፍና ነዉ:: በአቶ ሰዉነት ቢሻዉ ቲንሽ መስኮት ገብተህ እጅግ የመጠቀ ሰፊዉን እኛነታችንን አሳይተህናል:: ይህ ሃሳብ አድናቆት ሳይሆን ተከታይ እና አራማጅ ነዉ የሚያስፈልገዉ :: SKY ስፖርት አማርኛ ባለመስማቱ ቀረበት እንጂ አቶ ሰዉነት በቀልዶቹ እንደ ሞሪንሆ : በስብእናዉ እንደ ፈርጉሰን : በኳስ ያጨዋወት ባህሉ እንደ ቬንገር ነዉ:: እሱ ከማንም ጋር አንድ ለአምስት ሳይደራጅ በየትኛዉም ጎሳ እና ብሄር ሳይካተት ብቻዉን ጀግና ነዉ:: በፈዴሬሽን ዉስጥ ለአቶ ሰዉነት ነፃነት የሰጣችሁ ሁላችሁም ለኛ “ላልታወቀዉ ወታደር” የጀግና ሃዉልት ይገባችኋል:: ያላሰብነዉን እንድናስብ: ያላየነዉን እንድናይ ያደረግከን ዲያቆን ዳንኤል ከሁሉም በላይ ለኛ አንተ ጀግናችን ነህ::
ReplyDeleteWELL DONE DIYAKON DANIEL!
ReplyDeleteMay god bless you, you r one of Ethiopian hero too......for bring this kind of logic. By the way I always wonder about the founders of Enjera and culture dress .....keep up!
ReplyDeleteSo confused, contradicting and misleading article. To admire Sewunet, you don't have to discredit others. I agree Sewnet is hero, but players (the team) are also pivot points of the result and should be admired ... that is the team. In your analogy, no team, no people make history. To acknowledge a single person, you don't have to insult the people.
ReplyDeleteDear Weyra,
Deleteit seems u are the confused one;Daniel just reflected his view, very logical and convincing article that is well argued. i see that u just dissagree with the argument that the he infer,GOOD!!, so bring your premiss, than just criticizing the article/The Writer blindly.
@anonymous, what are your premises, you bring first?
DeleteI will wonder him more if we are one of the five African countries that will play in Brazil.I also wish FIFA`s decition to be Fair.
ReplyDeleteየአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሠረት ያደርግ ነበረ፡፡
ReplyDeleteThank you Dani
ReplyDeleteSewnit is a hero. But there are other hero in eThiopia Football Fed ration, who stopped their nagging behavior, who left the bed culture let us lead it. They are also hero, they broke the bad habit.
ከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
ReplyDeleteዳኒ ይሄ የይገባኛል ጥያቄ ነው! ለኔ ጀግና በሉኝ የሚል መልእክትም ያስተላልፋል!
ReplyDeleteበመሰረቱ የግለ ሰብና የህዝብ ድርሻ በታሪክ ሰሪነት ዙርያ ኣንድ ዓይነት ኣቅዋም ኣልተያዘበትም ኣንተ ግለ ሰብ ነውታሪክ ሰሪ ትላለህ ሌሎች ደግሞ ታሪክ ሰሪው ህዝብ ነው የሚሉ ኣሉ ሁሉቱም ኣስተሳሰቦች ጫፍ የረገጡ ናቸው
ግለ ሰብ ህዝብ ከሌለ ህልውና የለዉም ህዝብም የግለሰዎች ስብስብ ነው ስለዚህ የሁለቱም ድርሻ በተገቢው መልክ ማስቀመጥ ይኖርብሃል! የኒዮሊበራሊዝም ኣስተሳሰብህ በስፋት የተንጸባረቀበት ጽሹፍ ነው ያነበብኩት
"ከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡ "
ReplyDeleteከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
ReplyDeleteከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም ይኼ ሰው ጀግና ነው ፡፡ ጥሩ አባባል ነው አበሻ በተፈጥሮው ሲታደል ማድነቅ የሚባለውን አማርኛ ( Passé ይሁን Delete ) ያደረገው ምንም እንደሆነ አይታወቅም ስለዚህ በማድነቅ ያልታደልን ከሞተ በኋላ ግን ማንም የማይደርስብን በመሆናችን ያሳዝናል ስለዚህ ማድነቅ ባህላችን ይሁን አሁንም ይሄሰው ጀግና ነው ይሄሰው ጀግና ነው ይሄሰው ጀግና ነው ፡፡
ReplyDeleteno doubt. it is well expressed.
ReplyDeleteno doubt. it is well expressed.
ReplyDeleteThere is no doubt. It is well expressed.
ReplyDeleteበትክክል ይኼ ሰው ጀግና ነው፡
ReplyDeletewish everlasting bright life to u and Ethiopians with GOD!!!
ReplyDeleteአሁንም ሺ ‹ሰውነቶች› ወደፊት ተነሥተው የሀገራችንን የስፖርት መልክ እንዲቀይሩት ከፈለግን የዛሬውን ሰውነት እናወድሰው፡፡ ሰውነት ጀግና ነው፡፡ ታሪክ የለወጠ፣ ሕዝብን ያስዘመረ፣ አገርን አንድ ቋንቋ ያናገረ፤ ቡድኑን መርቶ ውጤት የዘወረ፣ ኃላፊነትን ተሸክሞ ሀገር ያስከበረ፡፡ ከዚህ በኋላ ያለው ውጤት እንኳን ቢቀየር ሰውነት ግን የኢትዮጵያን እግር ኳስ ወደ አንድ አይተነው ወደማናውቀው የታሪክ ምዕራፍ አድርሶታል፡፡ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
ReplyDeletedanye WE OURSELVES HAVE TO RESPECT OUR HERO. LONG LIVE DANI.
ReplyDeleteI think this is a very nice argument, and i think sewnet need more recognition than we give him now.
ReplyDeleteNicely written and the coach deserves respect. However let's not forget football results are the achievements of team work, and let's try to give credit to all that contributed to it, including the football loving Ethiopian fans. Let' not discredit contributions of lots of people around him, including technical staff and the players, for the sake of creating a hero!!! Mr Writer, Let's try to be balanced!!
ReplyDeleteየሆነ አዙሪት ውስጥ ገብተን የማያልቅ ግጥሚያ/ጌም የያዝን ይመስለኛል:: በመካከላችን ግን ታሪክ ሰሪዎች ተወልደው አድገው እየሞቱ መሆኑን ዘንግተን ክቡሩን የሰውን ሕይወት እንደ ተራ ደብዳቤ በተለመደው እንዲፈጸም እየመራን ነው የተቸገርነው::
ReplyDeleteይህን ዓይነቱን ኑሮ የሪች ዳድ ፑር ዳድ ጸሓፊ 'RAT RACE' በማለት ይጠራዋል:: ይህ አገላለጽ በፈረንጆቹ ዘንድ የተለመደ ሳይሆን አይቀርም:: ትርጉም From Wikipedia, the free encyclopedia
A rat race is an endless, self-defeating, or pointless pursuit. It conjures up the image of the futile efforts of a lab rat trying to escape while running around a maze or in a wheel. ያንተ መዝገበ ቃላት ምን ብሎ ይፈታው ይሆን?
ሰው ብቻ ያልሆኑ ሰዎች አሉኮ:: አሉ ለታሪክ ሥራ የሚወለዱ ለራስ ብቻ የማይወለዱ:: ለማኅበረሰብ ለሀገር ለወገን ለዓለም የሚወለዱ:: የሚወለዱትና የሚራቡት ግን በምንሰጣቸው እውቅናና በምንለግሳቸው ክብር ነው:: ከገባንበት አጉል ግጥሚያ ካልወጣን በቀር እንዲህ ያሉ ሙሴዎቻችንን ማግኘት አንችልም::
የቴክኖሎጂውን የኢኮነሚውን የፖለቲካውን የድህነቱን የፉክክሩን ሁሉ ባሕር እየከፈሉ ከሌላው ዓለም ጋር የሚያገናኙንን ማርሽ ቀያሪዎች ያስፈልጉናል:: ይህን የሚያምን ማኅበረሰብ ለነዚህ ሰዎች ከነስህተታቸው ክብር መስጠት የውዴታ ግዴታው ነው:: ለፈሊጣዊ አነጋገር ፈተና ብቻ "ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት" እንላለን እንጂ ይህን አምነን ለሚያጠፉ ይቅርታን መስጠት ሞታችን ሆኗል:: ተረቱም ትዝ የሚለን ምናልባት እኛ ያጠፋን ቀን ነው:: ይህን አደረክ ከማይባልና ከሳሽ ወቃሽ ከሌለበት ፈጣሪ በቀር ግን ያለ ስህተት የሚሠራ የለም::
እኔን የሚገርመኝ ለምሥጋና የተፈጠረ ፍጥረት ለወገኑ የምሥጋና ቃል እንዴት ያጥረዋል? ለዚያውም አንዳች ላደረገለት እረ መለማመድም ሳያስፈልገን አይቀርም:: የተራቀቁ ታላላቅ የምስጋና መጻሕፍትን ቅዳሴ ውዳሴ መልክ ድርሳን ገድል የደረሱ ሊቃውንትን የወለደች አገር እንዴት በዚህ ትታማ? ክብር ለሚገባው ክብር መስጠትን የሚያስተምረውን መጽሐፍ ካነበብን ከተረጎምን እኮ 2000 ዓመት ሊያልፈን ነው:: በየ ቢሮአችን ግን ምስጋና የምሥክር ወረቀት ሊጻፍላቸው ማበረታቻ ሊሰጣቸው ሲገባ የተዘነጉ ብዙ ጀግኖች ነበሩን:: እነሱን ባለማመስገን ባለመሸለም ብዙ ጀግኖችን ማምከናችንን አናውቀውም:: ለሥራቸው እውቅናና ከመስጠት በላይ ማክበር የት ነበር?
በሃይማኖት ሥርዓትም ቢሆን ለሰው ለመስጠት ካልሞተ የሚባለው ቅድስና እንጂ ለአክብሮና ለእውቅና አይመስለኝም:: ያ ባይሆን መንፈሳዊ ተቋማት ሰርተፊኬት የሚባል ወረቀት ባልኖራቸውም ነበር:: አንዳንድ አገሮች ላይ የሰዓታት ሥልጠናዎችን ወስዳችሁ አይደለም ስብሰባ እንኳን ተካፍላችሁ ብትረሱት እንኳ ባድራሻችሁ የምሥጋናና የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ይላክላችኋል::
የበጎነት የአስተዳደር የታማኝነት የትጋት የስኬት የጥበብ . . . ጀግኖቻችን ተደብቀው እንደቀሩት ቆነጃጅት የሔዋን ልጆች ተሰውረውን ሊቀሩ አይገባም:: እንግለጣቸውና ዘራቸውን እናበራክተው ወደ ብርቅዬነት የለወጥናቸው በየሙያው ስለማናተጋቸው ነው:: አሁን የአርቲስትና የስፖርተኛ ዘመን ነው:: ጀግንነት ግን በየዘርፉ በየ ሜዳው ነው:: የጀግኖች ምሥጋና ጀግኖችን ይወልዳል!
betam tiru eyita. kibir lejegnochachin!
ReplyDeleteእዉነት ነዉ እሡ ሰዉ ከሚያመሠግነዉ በላይ በስራዉ እረክታል፤ አዎ ግለሰቦች ባመጡብን፡ጣጣ እሄዉ በዘር፤በሐይማኖት፤ በሀገር፤በክልል፤በቛንቛ አረ በስንቱ ነገር ሁሉ በሁለት፡ሰዎች፡ምክኒያት፡ ተበታትነናል ብቻ ሙት፡መዉቀስ፡ትርፉ ቅዠት፡ነዉጂ ብዙ ነገር፡ ሑነናል፤ መምህር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መልካም፡እይታ፡ነዉ፡እግዚዓብሄር፡ይባርክህ።
ReplyDeleteወዳጄ ሁለት ሰው ምናምን የሚለው ድፍን ፍልስፍና አያዋጣም!እውነታው በዘር መዘርዘር መቼ ተጀመር ብሎ በእውነት መመርመር ነው! ለመሆኑ ይህ ክፍፍል ግልጽ የወጣበትን ያሁኑን ዘመን እንጂ ከዚያ በፊት የነበረውን ለዚህ እርሾ የሆነውን ታሪክ ለምን ትገድፈዋለህ! በቀድሞ መንግስታት ጊዜ ሁላችንም ተበድለናል የሚለውን አተታ አትድገምልኝ ከአንዱ ከኮከብ ክብር ያንዱ ይበልጣል እንዲሉ አበው:...
Delete...እኔ አመጻን በዐመጻ ማስተካከልን እይደገፍኩ አይደለም! ነገር ግን..ግን ግን...ቢያንስ በጅምላ የሚሳደቡ ሰዎችን ታሪክ እንዲያነቡ ነው!... ለመሆኑ በጥንጥ ጊዜ ያኔ @በመልካሙ ዘመን እናቶች ልጆችቸውን በ አቅማዳ አዝለው ከቦታ ቦታ ለንጀራ ልመና ይዞሩ ነበር ከአንዱ ቤት ወደ አንዱ የ እህል ወሃ ጉዳይ ነዋ .. ከልመና በላይ ውርደት የለም ይህን ታውቃለህ!...ከነዚያ ለማኞች ውስጥ የአንደኛው አውራጅ ተውላጆች ይበዛሉ የተግባባን መስለኝ! ለዚህ አይደል ባደባባይ እንዲህ የተባልነው ...http://www.youtube.com/watch?v=AGBae3XP5vU ያኔ ነው የተለያይነው ወዳጄ !ያኔ ለ አንድ ጨቅላ ህጻን ምን እንደሚሳልበት ታውቃለህ?እኔ ልሙት አታውቅም አልደርስብህማ ንጉስ ሰለሞን ረሃብ የሚባል አላውቅም እንዳለው ማለት ነው
Deleteblood is thicker than water.
Deleteከጀመርኩ አይቀር የልብ የልቤን ተናግሬ ይውጣልኝ ዳኒ እንድናገር ፍቀድልኝ....እኔ የሚገርመኝ ደግሞ የትግራይ ክልል ትወላጆችን ባንዳ ለማረግ ከ ፕሮ-mesfin ጀምሮ የምታረጉት ጥረት ነው! እስኪ ይሄንን ቪድዮ ተመልከት..http://www.youtube.com/watch?v=XNYvk4YmqII አሁናሁንማ ብሶበታል ቀልዱ ኩምድአው ሁሉ በትግረኛ ቋንቋ ላይ ሆኗል! ይህን ስናገር ከልቤ ነው የትግራይ ህዝ ከማንም ህዝብ በላይ ለአማራ የሚቀርብ እና አንድ ሴንስ ያለው ህዝብ ነው አዎ በድል ደርሶ ሊሆን ይችላል ይህ ማለት ግን በጅምላ የትግራይ ህዝብ አማራን ይጠላል ማ ለት ነው?
Deleteለተራው የትግራይ ህዝብ....የአማራ ህዝብ እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ እኩል የምንሟገትለትና የምንዋደቅለት ሕዝባችን ነው!የአማራ ህዝብ መፈናቀል ህመም ህመማችን ነው!የአማራ ህዝብ ሕዝብ ሐዘን ሐዘናችን ነው! የአማራ ህዝብ ደስታ ደስታችን ነው!የአማራ ህዝብ ውድቀት የኢትዮጵያውያን ሁሉ ውድቀት ነው!የአማራሕዝብ መለወጥና ማደግ በኢትዮጵያዊነታች የምንኮራ ዜጎች ሁሉ ዕድገት ነው!የአማራ ሕዝብ ጠላት ለእኛ ተራው የትግራይ ህዝብ. ሁሉ ጠላት ነው!
Delete...በተረፈ ግን ከላይ የጻፍኩት blood is thicker than water. ደስ የማይል በቅን ልብ አስተካክሉት!
Delete...finally i want to read this article! i taken from some website...Tigray: Enemy of the State?...Emperor Menelik brilliant as he was when it comes to power politics, he understood the potential challenge to his sovereign power would emanate from none other than Tigrians. He “knew” and believed “legitimate heirs” of the throne were either Amharas or Tigrians. He believed that unless the actors in the rivalry to the throne, the Tigrians, are weakened there would not be any certainty to the sustainability of his domination over whatever you call Abyssinia or Ethiopia.
DeleteAnd the only viable solution for the emperor was to cut the potential of threat to his power significantly. Then it was fine for Menilik to let go north of the Mereb river to Italians. By doing so, he has succeeded in undermining the momentum of Tigrian resistance against his hegemony. In the rule of the game it is natural that the competitors to the emperor’s power had to face all the ordeals of an enemy of the state.... During the reign of Haileselasie too, the emperor understood the dangers that Tigrians present to his power. Why? I think the first Woyane movement is an answer. The first Woyane movement had succeeded to prevail over the emperor’s forces though for a short time. With the help of British air planes, unarmed civilians mostly women and children were massacred and the movement was aborted. Then Haile Selassie deliberately starved these rebellious people and blocked all venue of enlightenment from reaching these same people. These are punishments over= “an enemy of the state.”..
....With the advent of the DERG to power in 1974 unspeakable brutalities were committed against all Ethiopians. Yet, the magnitude of suffering sustained by the Tigrians at the hands of the DERG was insurmountable. There is no need to go on detailing all the heinous crimes for the facts shout themselves. In short the people of Tigray were subjected to a deliberate and systematic aggression that would even threaten in eliminating them as a factor from the equation in the Ethiopian body politic. Again these were measures against “enemy of the state.”
DeleteNow, let us see the fate of Tigrians in the era of TPLF/EPRDF. Are they being treated as enemy of the state? Don’t take me wrong, I am not an anti EPRDF. In fact I support them like many fellow Tigrians for lack of better option. ቀና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ እንዲሉ አበው!Yes. That is exactly the contradiction and reality of every Tigrian, I believe.
Let us see the point of convergence between TPLF and the elite opposition groups and their die hard Diaspora supporters in keeping the people of Tigray at bay from any economic, social and all other developments. Of course, the premise and motives of these two groups are different.
As far as I know, TPLF during the armed struggle had always maintained its principled stance even if that principle had the potential of undermining the organization politically. Let us see two examples. 1. TPLF against all odds had endured and sustained its long held belief that the Eritrean question could only be solved through popular referendum. 2. During the Transitional period, this organization had pushed in to convincing other member organizations of the Transitional Government to accept a provision in the Transitional Charter that says primary attention would be given to those regional states that had lagged behind others in terms of development and those regions that had contributed and paid a lot in terms of sacrifices for the down fall of the DERG regime. In other wards, people of Tigray who paid the ultimate price in the armed struggle would be given primary development by the then government. I am not unmindful about the tremendous contribution of other members of our society nor am I crying for special attention to be given to Tigray at this point in time. I am just trying to show how things have been reversed the other way round. And what happened since then? Was the provision translated in to reality? The big question is, let alone primary attention, was the people of Tigray given equal opportunity in the economic and infrastructural development like other regional states? And why?እስኪ እውነት ፍረዱና ትግራይም ሂዱና እኮ እንደተባለው ትግራይ እስክትለማ ሌላው አገር ደማ?if you think so... let it be..
....Just from the beginning since EPRDF assumed power until now, there is a conspiratorial rumors funneled by the DERG remnants that the state of Tigray was sinking because of the huge flow of investments and now the region being crowded by super high ways. These rumors were spread purposefully to hinder any drop of development in the region. And the people had no means of verifying the veracity of the rumors and took them as is. The result? What the DERG remnants had failed to do through blood and iron have succeeded in preventing developments in the regional state by arm twisting the EPRDF government through malicious rumors. And you can see the sorry state of Tigray being relegated to back waters. And the tragedy is no intellectual from the region had written about this reality in spite of the glaring facts in the ground.The TPLF whose hallmark was intransigence when it comes to its principles, why did it compromise the very important issue of development in the region, the issue for which hundreds of thousands of lives have been paid for? As an Ethiopian in general and Tigrian in particular, I believe in an equitable distribution of resources and parallel development of all regions. I am happy to see and observe the developments in the Amhara region and the Southern Peoples, nations and nationalities region. After all I am Ethiopian and should be happy to witness any development in any part of our country. When you look at Tigray at this point in time, you will be saddened and heart broken to observe the injustices at the judicial and administrative institutions. Poor public governance, equally and shockingly poor infrastructures and corruption are pervasive.The poor development in Tigray is not with out the knowledge of the prime movers and shakers of the Federal Government. It seems like the TPLF leaders believe that the only way to find legitimacy among Ethiopians is by undermining development in Tigray. I understand the leaders intend to leave a historical legacy and be remembered as agents of change in the down of the 21st century. And I also perfectly understand that the leaders are trying to transcend and reach out to almost all Ethiopians. Minus Tigray, an objective assessment of the over all development in the country would give the leaders a plus (+). But it becomes ugly when the means and procedures of leaving a historical legacy and any attempt of transcending to reach out every body is at the cost of the economic and social prospects of certain group of people, as is the case of Tigray.if so "ከዛሬ ዕለት ጀምሮ እኛ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆን የትግራይ ክልል ተወላጆች የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል አይደለንም።
Deleteኢትዮጵያ ከምትባል ሀገርም ምንም ዓይነት ዕድል ፈንታ ክፍልም የለንም!" በማለት እስካልተነሳን ድረስ ያለ አንዳች ጭብጥ ከባዶ መሬት እየተነሳችሁ የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት
የመግፈፍም ሆነ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ሕዝብ ጋራ ቅራኔ ውስጥ የሚያስገባ ማንኛውም ዓይነት የአመጽ ቃል የመናገር
መብት የላችሁም።
my final message ለቅን ኢትዮጵያውያን! “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ነው ብንለያይ አንዱ የሚጠቀም አይደለም!most people i have met thought tigray has no significance since it has no natural resources!!!! Mengistu Hailemariam bray and bluff on the observance of May Day, 1989 G.C after the Derg retreat, from all of Tigray. “Tigary is worthless fighting for; it cannot even cover the cost for chalk”. This is also the existing misconceptions which still drive the toxic Diaspora to this day to the insane attitude towards Tigray.this will remind me a story i have read in website! ............. A story is told about three oxen. They are Black, White and Brown. These three friends were very close. They would play and graze the grass together the whole day and stay and watch over each other at night. These oxen were very smart. For example, when they slept at night they would form a circle. Each one of them would face different directions, and would cover any possible enemy attacks from all directions. The enemy “Hyena” was watching at these oxen, and was very surprised how they protected and covered themselves. It was impossible for him to attack and get his dinner.
DeleteThe Hyena thought of a master plan. The plan is called Divide and Conquer. On one cloudy morning while the oxen were grazing the grass peacefully, the hyena approached the Black ox discretely. The hyena said, “good morning Mr. Black”. The ox was surprised the hyena could speak his language and replied “Good Morning” with excitement. The hyena began to talk to him and admired the friendship he had with the White and Brown oxen. He continued and said, “do you know that if it were not for the White ox, you and the Brown Ox are naturally protected by the darkness of night?” As I make my routine rounds at nights, I could always spot you without any effort. Do you know why? Asked the hyena. The Black Ox replied and said, “I know white is very easy to spot at night”. “Right”, said the hyena. The Hyena suggested to the Black ox and said, “why don’t you ask the White Ox to find his own sleeping quarters, alone?”. This way when the two of you are sleeping, no one can spot you.
The Black Ox thought about the advice from the hyena and decided to have a meeting with his two friends. The Black and the Brown oxen complained to the White ox, and said “because you are easy to spot at nights, you are going to make us supper for the hyenas, and get us killed”. The White Ox did not like the conspiracy and betrayal by his two “trusted” friends and replied in anger and said, “okay! I can protect myself”, and separated from them with disgust and contempt. The Black and Brown were very happy and felt safe when the White Ox left them. The next night, while the hyenas were making their routine rounds of their areas they spotted the White Ox resting all by himself at night. They started calling each other and told all the hyenas in the area that the foolish White Ox is sleeping under the tree all by himself. Many of them started laughing for joy. And they attacked and made the ox their dinner and left the scene.
The next week the deceptive hyena decided to continue his master plan. Again in his usual desecrate way, he met with the Black Ox again. He said, you know Mr. Black, when there is a full moon at night, no one can see you, but your friend Mr. Brown glows in the moon light, especially when it is full moon. The next day the Black Ox decided to complain to the Brown Ox and the Brown was offended and left him. You guessed it! The next night the hyenas were laughing for joy again
the above commenter...መሰረታዊዉ ጥያቄ መሆን ያለበት ሁሉ ኢትዮጵያዊ ብሄረሰብ ከጎሳ የፖለቲካ አደረጃጀት አጠር ዉስጠጥ ወጥቶ አገሪቱን ከመፍረስ እንዴት ሊታደጋት ይችላል? ኢትዮጵያዊያን ብሄሮች ማለትም ኦሮሞዎች: ጉራጌዎች : አማሮች: ትግሬዎች : ደቡቦች: አፋሮች: እንዲሁም ሌሎችም የልዩነት ታሪካዊ መሰረታቸዉ ሳይሆን የጋራ የታሪክ ጭብጣቸዉን እንዲያስተዉሉና በጋራነት ወደ በለጠ አብሮነት በምን መልክ ወደፊት የጠለቀና የጸና ዉህደትን ለማምጣት እንችላለን ወደማለት እንዲሄዱ ምን አይነት አገራዊ የፖለቲካ ፍልስፍና እናራምድ ብሎ መነሳቱ ነዉ ወሳኙ ጥያቄ መሆን ያለበትና መመለስ ያለበት:: ኢትዮጵያዉያን በቅርቡም ዘመን ሆነ በቀደመዉ ዘመን የተዋሃዱ ህዝቦች ናቸዉ:: በኢትዮጵያ ዉስጥ ማንም ሰዉ ብሄሩን ቆጥሮ ከአንድ ወገን መሆኑን አስረግጦ መናገር አይችልም:: የዶ/ር ኢሌኒ ታሪክ ልክ አንድ ልብወለድ ዉስጥ እንዳለ ኢትዮጵያዊ ገጸባህሪ የሚያስደምመዉን የኢትዮጵያዉያን ዉህድ ህዝብነት የሚተርክ ነዉ:: በቅርቡ ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ስለ ኦሮሞና አማራ ህዝብ የጋራ የመነሻ ታሪክና የጋራ ማንነት አስገራሚ ጽሁፍ አቅርበዋል:: በተደጋጋሚ እንደተነገረዉ የትግሬ : ጉራጌ : አማራ እና የሌሎች ህዝቦች የጋር ማነትና ታሪክ ምን ያህል በጥልቅ መሰረት ላይ እንደቆመ ብዙ ጸህፍት ብዙ ብለዋል:: እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን እና ፖለቲከኞች ብሎም ሀይማኖታዊ ሰዎች ኢትዮጵያዉያንን በጎሳ ፖለቲካ ቅርቃር ዉስጥ መክተቱ የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ የማይወክል ከመሆኑም በላይ ለመጻኢዉ ትዉልድ የመጠላላት እና የመፈራቀቅ ሂደትን ስለሚፈጥር ከጎሳ ፖለቲካ በመዉጣት እዉቀትና ሀሳብ መር የፖለቲካ መስመር እንከተል ሲሉ ሰብከዋል ተከራክረዋል:: አሁንም ብዙዎች እየተከራከሩ ነዉ::የብሄር ፖለቲካ ፓርቲዎች ሲመሰርቱ የብሄራቸዉን ብዙሃን ድጋፍ ለማግኘት ይታገላሉ:: የብሄራቸዉን ብዙሃን ድጋፍ ለማግኘት በብሄራቸዉ ፊት ታምር ፈጣሪ ሆነዉ ይታያሉ:: የራሳቸዉን ብሄር ከፍ ከፍ ከማድረግ ጀምሮ የማይጨበጡ ተስፋዎችን እስከመጋት: የዚያን ብሄር ልዩነት ከማጉላት ጀምሮ የዚያን ብሄር የበላይነት እስከመስበክ ያሉትን የስነ ልቦና የጨዋታ ካርዶች ሁሉ ይመዛሉ:: ይባስ ብሎም እነሱ ከሌሉ የእነሱ ብሄር እንደሚጠፋ ይሰብካሉ ብሎም የብሄራቸዉ አባላት ከእነሱ ዉጭ አይኑ እንዳይመለከት ያስፈራራሉ::
Deleteሆኖም በተመሳሳይ ጊዜ ዉስጥ እነሱ ለሀገር አሳቢም መሆናቸዉንም ለማሳዬት መከራቸዉን ያያሉ:: እነዚሁ የብሄር ፖለቲካ ፓርቲዎች የቀሪዉን ህዝብ የብዙሃንነት ድጋፍ ለማግኘት ሲፍጨረጨሩም ይስተዋላል:: ሆኖም ሌሎች ብሄሮች ሲጎዱና ሲገፉ ይህ ነገር አግባብ አይደለም ለማለት ወኔ ሲያጥራቸዉ ይስተዋላላ:: this is the realty every ethiopian face including u!
senefoch mesrat siyakitachew hizb wust yidebekalu.tenkaroch yeserutin lehzb yisetuna rasachew yewagawu tekudash yihonal.(dink ababal)
ReplyDelete"ልጆቻችን አርአያ ሊያደርጉት፣ ሊከተሉትና ሊፎካከሩት የሚችሉት ግለሰብን ነው፡፡ ማኅበርን ወይም ሕዝብን መከተል አይቻልም፡፡ ግለሰቦችን በዋጥናቸውና ባጠፋናቸው ቁጥር፣ ለጀግኖቻችን ክብርና አድናቆት በነፈግናቸው ቁጥር ሌላ ጀግና ማግኘት አንችልም፡፡ "I like it!!!
ReplyDeleteThanks Dn Dan!
አዎ ሰውነት ጀግና ነው.... ብራዚል ላይ ከዋልያዎቹ ጋር በርቶ እንደምናየው አንጠራጠርም... እግዚአብሔር ይርዳቸው
ReplyDeleteይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
ReplyDeleteአገዳደላችን በሦስት መንገድ ነው፡፡ አሳቢውን በማጥፋት፣ ሃሳቡን በማጥፋትና ሃሳቡን በመንጠቅ፡፡ ስንት አሳቢዎች ‹ዓሣውን ለማጥፋት ባሕሩን ማድረቅ› በሚለው ብሂላችን ምክንያት ከነ ሃሳባቸው ተገደሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ሃሳባቸው እንዳይሰማ፣ እንዳይነበብ፣ እንዳይሳካና እንዳይታይ በማድረግ ተገደሉ፡፡ በሌላ በኩልም አሳቢውን ዝም አሰኝቶ ሃሳቡን በመንጠቅና አሳቢው ተንገብግቦ እንዲሞት በማድረግ ስንት ጀግና አጥተናል፡፡ የነ አያ እገሌ ፈጠራዎች፣ ሃሳቦች፣ ድርሰቶች፣ ግኝቶች፣ ፍልስፍናዎች ተነጥቀው የነ አቶ እገሌ ሆነው ቀርተዋል፡፡ የነ አያ እንትና ታሪክ ለነ ክቡር እንቶኔ ተሰጥቷል፡፡ የአሳቢዎችን ጥቅም ክብርና ዝና፣ አቀንቃኞች ወስደውት ‹‹የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ›› ተብሎ ተዘፍኗል፡፡
ReplyDeleteDani dejeselamoch yet tefu?
ReplyDeleteI DONT KNOW HOW I EXPLANE ABOUT YOUR EXPLANATION.YOU ARE EXPRSSING IT WITH YOUR BLESSED HAND WHAT IS IN MY HEART . GOD BLESS YOU DAN !!
ReplyDeleteሰነፎችም ተጠያቂነትን ሲፈሩ ሕዝብ ውስጥ ይደበቃሉ፡፡ እንደ ጀግኖች መሥራት ሲያቅታቸው የጀግኖችን ዋጋ ለሕዝብ ይሰጡና እነርሱም የዋጋው ተቋዳሽ ይሆናሉ፡፡
ReplyDeleteጥሩ ጽሑፍ ነው። ስለአቶ ሰውነትና በአጠቃላይ ስለግለሰብ ታሪክ ሠሪነት የጻፍከውም እንከን የለውም። ሆኖም "ሕዝብ" ባልክበት ቦታ ሁሉ "ሥርዓት"/"መንግሥት" ወይም "አስተዳደር" የሚለውን መተካት ያስፈልጋል። በላይ ዘለቀን፣ አክሊሉ ሀብተወልድን፣ ንግሥት ዘውዲቱን፣ አቤ ጉበኛን፣ በዓሉ ግርማን ወዘተ የገደለ፣ የአዲስ ዓለማየሁን፣ የከበደ ሚካኤልን ወዘተ ሥራዎች የሚቸበችብ፣ የሌሎችን ሃሳብ የሚገድል፣ የራሱ የሚያደርግና እያደረገ ያለ አስተዳደሩ እንጂ ሕዝብማ እንዲያውም እርሱ ያቆየውን ነው እኛም የደረስንበት። ምሳሌ ልጥቀስልህ። በላይ ዘለቀ በፍርድ ቤት ቀርቦ ተፈርዶበት እንደወንጀለኛ ነው የተሰቀለው። መንግሥት የሚፈልገው ሕዝቡ እንደወንጀለኛ እንዲያየው ብቻ ነበር። ሕዝቡ ግን በግጥሙ፣ በቅኔው፣ በሽለላው፣ በዘፈኑ እስካሁንም ስላቆየልን አወቅነው። ሕዝብ ለሥርዓቱ ሳያውቀው ወይም በፕሮፖጋንዳና በኃይል ተጽእኖ ሥር በመሆኑ ተባባሪ ይሆን ይሆናል እንጂ ያልካቸው ነገሮች አድራጊ ሆኖ አያውቅም። ሕዝብና ሥርዓትን ምን ለያቸው የሥር ዓቱ ቁንጮዎች ከሕዝቡ አይደለም ወይ የሚገኙት? እንደማትለኝ አምናለሁ። በሌሎች አገሮች ይህን የሚመስል ነገር መኖሩ አይካድም። ሥርዓቱ በተወሰነ ደረጃ የሕዝቡ ነጸብራቅ ነው። በኢትዮጵያ ግን ይህ ቢያንስ በቅርብ ታሪካችን ተከስቶ አያውቅም። ይልቁን ታሪክ ሠሪ ግለሰቦች የሚወጡት ባብዛኛው ከተራው ሕዝብ መካከል ነው ቢባል ትክክል ይሆናል። ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ጽሑፍ ስታወጣ ብዙ ሰው እንዳታሳስት ወቀሳህን ወደትክክለኛ አቅጣጫ መውሰድ አትርሳ። የአቶ ሰውነት ቢሻው ሥራ እንዳይጎላ እያደረገ ያለና ይህን የሚያደርገው በምን ምክንያትም እንደሆነ አንተ አሳምረህ ታውቀዋለህ። ከፈራህ እንዲህ ዓይነቱን ርዕስ ባትጽፈው ይሻላል። ሰላም ወንድሜ!
ReplyDeletebetam ewinet
ReplyDeletekalehewot yasemalen kebur wondimachen!!!
ReplyDeleteyes u R right ! he is Hero /brave man/
ReplyDeleteyou are our hero too dani. God bless you. We love you
ReplyDeleteምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ReplyDeleteግብሩ ዕንቁላል ነበር ይኼን ጊዜ አበሻ
he is hero.
Dn. Daniel,
ReplyDeleteYes, individuals with gifted mind show the way forward and the broad mass follow. That is what history shows.
I thank you for your instructive article.
May God bless you!
From Dessie
ዳኔ ለአንተ ያደለውን ማስተዋል ለኛም ይስጠን። ድሮስ ጀግናን የሜያከብረው ጀግናው ነው። ግሩም ብለሐል ። የድንግል ልጅ አይለይህ።
ReplyDeleteAwe jegina new b/c besu tarikachin agegimaelina
ReplyDeleteyes yes yes ......thank u dany
ReplyDeleteበቅድሚያ የጌታ ጸጋ ይብዛልህ!!!የጽሁፎችህ ተጠቃሚና አድናቂህ ነኝ
ReplyDeleteለመሆኑ ጽሁፎችህን ብዙ ሰው ሊጠቀም የሚችልበት ሌላ ሚዲያ አለ?
አይመስለኝም!!ምንአልባት ከዚህ የተሻለ ማምጣት የሚችሉትን ልጆች በሱ አሰለጣጠን ምክንያት ያጣነው ነገር ቢኖርስ እንዴ.... ጀግንነት እኮ እንዲሁ ሚሰጥ አይደለም ዋጋውም ውድ ነው፡፡ ምን ያህል ምርመራ ተደርጎበት ይሄ ማእረግ እንደተሰጠው አናውቅም፡፡
ReplyDeleteየጀግና መለኪያውን አስቀምጣ ወዳጃችን ከዚያ በዚያ ሰውነትን እንለካው::
Deleteጀግና ባይሆን ኖሮማ ከ30 ዓመት በሆላ ለአፍሪካ ዋንጫ ባልበቃን ነበር።ይኸው አሁን ደግሞ ለአለም ዋንጫ ተሳትፎ ሊያበቃን ትንሽ ነው የቀረው፤ ታዲያ ከዚህ በላይ ጀግና አለ።
Deletelante jegna yegdele weyse abayen yedefer new ? jegnenet ande sew yemsetew setota ayedelem
DeleteThank you Dani, you showed me the other side of the coin.
ReplyDeleterealy , telling the truth help us to not only to know the mistake but also to see for future , so it is great advice for all.
ReplyDeleteሰነፎችም ተጠያቂነትን ሲፈሩ ሕዝብ ውስጥ ይደበቃሉ፡፡ እንደ ጀግኖች መሥራት ሲያቅታቸው የጀግኖችን ዋጋ ለሕዝብ ይሰጡና እነርሱም የዋጋው ተቋዳሽ ይሆናሉ፡፡
ReplyDeleteከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም ይኼ ሰው ጀግና ነው ፡፡
ReplyDeleteegzeabhare yebarke d/daniel
Such a view is of researchers and of people of celebrated knowledge.
ReplyDeleteAm really happy to see my defects due to your strong argument , specially to the benefit of our beloved country , Ethiopia.
JEGNA NEW!
ከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም ይኼ ሰው ጀግና ነው ፡፡
ReplyDeleteኢትዮጵያችንን ወደ ቀድሞ ክብሯና ዝናዋ ሊመልሷት ያሉና ከመክሸፍ፣ ከጭንገፋና ከውርደት ታሪኳ ሊያወጧት የቆረጡና በነፍሳቸው የተወራረዱ ልጆች አሏት
ReplyDeletekengudletu hulum sew edih bisera nge gudlet alba sra enkan byegeng yetshale derga endersalen .... sewnet gen sew new .... tarik yekeyer jegna new .... kemnm belay gen ...edlenga new .... yeliloch sewoch sra new yasketelew .... enin yemamesegnew yemadenkew gazito new ...gazito new ....gazito new ...
ReplyDeletesewenet gegena nae beedemeachen ayetenew yemanawekewen yeafrica wanchnena ahun degmo yealem wanchan leyasayen naw keze belay gegennet ale danny lke nehi
ReplyDeletehaw about the synod meeting and 4 critical points of patriarich abune matias?no any info for dispora eotc members.
ReplyDeleteam proud of by this couhce
ReplyDeleteEwnetim eytah yensir nwe. ከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም ይኼ ሰው ጀግና ነው ፡፡ Yes! He is!!!!
ReplyDeleteበእውነት ይኼ ሰው ለኔ ጀግና ከጀግናም ጀግና ነው፡፡ እንዴ በትክክል የጀግና መለኪያ መስፈርቱን እኮ አሟልቷል፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን።
ReplyDeleteAntem asteway neh.
Sewent GEGNA new
ReplyDeletevery nice thought,it is deserved and it is true.I always want to write something about him,D/n Dany you read my mind perfect.1963(1970-71)at Memhir Akalewold elementary school he was my homeroom teacher.I remember him that he was serious,fun,friendly teacher and very good player.On lunch or any other breaks he always plays soccer or volleyball w/us.People please always don't be negative or just looking for something wrong or rush to criticized or judgmental.Gashe Sewnet is one of Ethiopian hero and an excellent roe module.Thank you Daniel for writing this deserved real story. story
ReplyDeleteከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
ReplyDeleteProud of him!!!
ReplyDelete‹እንኳንም እርስዎ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አልሆኑ!!!!› ብዬ ደስ አለኝ፡፡
ReplyDeleteከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡
አረ መሳሳት ወይስ መዘባረቅ? ታሪክ ሰሪው ማነው ግለስብ ወይም ህዝብ?
ReplyDeleteበቅርቡ ስለ እግር ኳስ ሜዳዎች የሥነ ምግባር ችግር በተጠራ ስብሰባ ላይ ‹አሠልጣኝ ሰውነት መሰደብ የለበትም› ተብሎ ሲነሣ አንድ የእግር ኳሱ ባለሥልጣን ‹አሠልጣኝ ቢሰደብ ምን አለበት? አሠልጣኝን መስደብ ዛሬ ነው እንዴ የተጀመረው፡፡ ድሮም እነ እገሌና እገሌ ሲሰደቡ ነበሩ›› እያሉ ሲቀልዱ ሰማሁ፡፡ ‹እንኳንም እርስዎ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አልሆኑ› ብዬ ደስ አለኝ፡፡ የሴት ልጅ ግርዛት ይቅር ሲባሉ ‹ሴት መገረዝ የጀመረችው ዛሬ ነው እንዴ› ይሉ ነበር፡፡ ግግን ማስቧጠጥ ይቅር ሲባሉ ‹‹ግግ መቧጠጥ በኛ ዘመን ነው እንዴ የተጀመረው፤ ስንቱ ሲያስቧጥጥ አልነበረም እንዴ›› ይሉ ነበር፡፡ እንጥል ማስቆረጥ ይቅር ሲባሉ፡፡ እንጥል ማስቆረጥ ድሮም ነበረ፡፡ ምን አዲስ ነገር መጣ›› ይሉን ነበረ፡፡ ‹‹ ያለ እድሜ ጋብቻ ይቅር ሲባሉ ‹‹ምነው እገሊትና እገሌ ያለ እድሜያቸው አልነበረም እንዴ የተጋቡት? ዛሬ ምን አዲስ ነገር መጣ›› ይሉን ነበር፡፡ እግዜርም ዐውቆ ሰማዩን ዐርቆ ማለት ይኼ ነው፡አሁንም ሺ ‹ሰውነቶች› ወደፊት ተነሥተው
ReplyDeleteየሀገራችንን የስፖርት መልክ እንዲቀይሩት ከፈለግን የዛሬውን ሰውነት እናወድሰው፡፡
Beiwnet Dani antem JEGNANEH !
ReplyDelete