Tuesday, June 25, 2013

‹‹ሥልጣን ልቀቁ?››click here for pdf
ኢትዮጵያ ከቦትስዋና ጋር ስትጫወት ተገቢ ያልሆነ ተጨዋች አሰልፋችኋልና ሦስት ነጥብ ታጣላችሁ ብሎ ፊፋ የሚባል ቡዳ አገሩን ቀወጠው፡፡ እንደ አውነቱ ከሆነ እንዲህ ዓይነት ነገር ማድረግ የሌለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ፊፋ ከአድኅሮት ኃይሎች ጋር ካልተሰለፈ በቀር ሌላ ምክንያት ሰጥቶ ኢትዮጵያን መጣል ይችል ነበር፡፡ ለኛ የኢትዮጵያ ነጥብ መቀነስ አይደለም ችግራችን፤ ነጥቡ መቀነሱን ሕዝቡ መስማቱ ነው፡፡ እኛኮ ቀስ አድርገን ‹ኪራይ ሰብሳቢዎች የሀገራችንን የስፖርት ራእይ ለማደናቀፍ ከፀረ ሕዝብ ኃይሎች ጋር በመሆን የደቀኑብን ሤራ ነው› ብለን ሕዝቡን ማሳመን እንችል ነበር፡፡
መጀመሪያ ከበላዮቻችን ጋር እንነጋገራለን፤ ሂስ ከተሰጠንም ሂሳችንን እንውጣለን፣ ግምገማችንንም እንቀበላለን፣ ዋናው ይሄ አይደለም፤ አንዴት አድርገን ለሕዝቡ እንንገረው? የሚለው ነው፡፡ ሕዝብ እንደነገርከው ነው፡፡ እንደ አሰማሙ ነው፡፡ አቀናብረን ከነገርነው አቀናብሮ ይሰማል፡፡ ግን ምን ያደርጋል፣ ፊፋ የሚባል ቡዳ ለሕዝብ መነገር የሌለበትን ለሕዝብ ተናገረና መከራ አሳየን፡፡
አሁን አዳሜ ዕድል ስታገኝ ጊዜ ‹ለምን ሥልጣን አትለቁም› ትላለች፡፡ 
 እስኪ ተዪው አሉኝ ያልደረሰባቸው
እንዲህ በቀላሉ የሚተው መስሏቸው
አለች የሀገሬ ዘፋኝ፡፡ ሥልጣን እንዲህ በቀላሉ የሚተው መስሏቸዋል፡፡ እኛ በቀጣዩ ምርጫ እንዴት አድርገን ተመልሰን እንደምንመጣ እያሰብን እነርሱ ሥልጣን ልቀቁ ይሉናል፡፡ ‹ከአንድ ሙዚቃ በኋላ ተመልሰን እንገናኛለን› አሉ የኤፍ ኤም ጋዜጠኞች፡፡
ስለ ሥልጣን መልቀቅ እዚህ ሀገር የሚያስብ ሰው ካለ የመጨረሻው ጅል እርሱ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ስለ ሥልጣን አያውቅምና፡፡ ‹‹አቤቱ የሚናገሩትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው››፡፡ እነዚህ ሰዎች ሥልጣንን ያልቀመሷት ሰዎች ናቸው፡፡ ቢቀምሷት ኖሮ ‹አጥብቃችሁ ያዟት› ይላሉ እንጂ ‹ልቀቋት› አይሉም ነበር፡፡ መንፈሳውያን ነን፣ ዓለምን ንቀናል የሚሉት አባቶች እንኳን ለሥልጣን በሚታገሉባት ሀገር እኛን ዓለማውያኑን ‹ሥልጣን ልቀቁ› እንደማለት ያለ የዓመቱ ምርጥ ቀልድ የለም፡፡
ጎበዝ እዚህ ሀገር ባለ ሥልጣን ማለትኮ ትንሽ ፈጣሪ መሆን ማለት ነው፡፡ ሰው የሚሰግድልህ ሥልጣን ሲኖርህ ነው እንጂ ዕውቀት ሲኖርህ አይደለም፣ ሰው የሚኮራብህ ሥልጣን ሲኖርህ እንጂ ችሎታ ሲኖርህ አይደለም፡፡ እስቲ የትኛው የአክስትህ ልጅ ነው እገሌ የተባለው ሳይንቲስትኮ ዘመዴ ነው ብሎ የሚኮራው? የባለሥልጣን ግን እንኳን ዘመዱ ድመቱም አረማመዱ የተለየ ነው፡፡ ጅል- ሥልጣን ልቀቁ ይላል እንዴ፡፡ ሥልጣን የሻሂ ቤት ወንበር መሰላችሁ እንዴ፡፡
ችሎታ ካለህ አንተ ወደ ሀብት ትሄዳለህ፤ ሥልጣን ካለህ ግን ሀብት ወደ አንተ ትመጣለች፤ ዕውቀት ካለህ ዕድልን ፍለጋ ትንከራተታለህ፣ ሥልጣን ካለህ ግን ዕድል አንተን ፍለጋ ትንከራተታለች፤ ዕድለኛ ከሆንክ በዕድሜህ አንድ ጊዜ ሎተሪ ይደርስሃል፣ ሥልጣን ካለህ ግን በየቀኑ ሎተሪ ይወጣልሃል፡፡ ዘመድ ካለህ ውጭ ቤትህ ውጭ ሀገር ይሆናል፤ ገንዘብ ካለህ መሬት ትገዛለህ፤ ሥልጣን ካለህ ግን መሬት ትሸጣለህ፤ ንግድ ፈቃድ ካለህ ስለ ቀረጥ ታወራለህ፤ ሥልጣን ካለህ ግን ስለ ቀረጥ ነጻ ታወራለህ፤ 
ዓይኔን ግንባር ያርገው ብሎ ይምላል ሰው
የቀኑን ጨለማ እንደኔ ባይቀምሰው
አለ ማየት የተሳነው ለማኝ፡፡
ሥልጣን ልቀቅ የሚሉ ሥልጣን የለቀቁ ምን እንዳጋጠማቸው ያላወቁ ብቻ ናቸው፡፡ ወዳጄ እዚህ ሀገር ሥልጣን ለቅቆ በሰላም የኖረ ሰው ታውቃለህ? እኔ የማውቀው ዐፄ ካሌብን ብቻ ነው፡፡ እርሳቸው ሥልጣናቸውን ለልጃቸው ለገብረ መስቀል ለቅቀው አባ ጰንጠሌዎን ገዳም ገቡ፡፡ እንደ እርሳቸው አደርጋለሁ ብለው አድያም ሰገድ ኢያሱ ሥልጣናቸውን ቢለቅቁ አይደል እንዴ የገቡበት ገዳም ድረስ ሄደው የግፍ ሞት የገደሏቸው?
ፈረንጅ በትንሽ በትልቁ ሥልጣን ለቅቄያለሁ የሚለው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? በቀላሉ ነዋ የሚያገኘው፡፡ በየቴሌቭዥኑ ለፍልፈህ፣ ልብ የሚያጓጓ ንግግር ተናግረህ፣ የሰው ካርድ ጠብቀህ የምታገኘው ሥልጣንና ጉቦ ሰጥተህ፣ ደም ተፍተህ፣ ለስንቱ ጉልበተኛ አጎንብሰህ፣ ተለማምጠህና ከሰው በታች ሆነህ የምታገኘው ሥልጣን አንድ ነው እንዴ? ደግሞ ፈረንጅ ምን ችግር አለበት፤ ‹በፈቃዴ ሥልጣኔን ለቅቄያለሁ› ቢል ‹ይህስ ኅሊና ያለው ነው፣ ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ነው› ተብሎ ያም ያም ይሻማበታል፤ ሥልጣኑ ይቀርብህ እንደሆነ እንጂ ገንዘቡና ክብሩ አይቀርብህም፤ ረ እንዲያውም ከባለሥልጣኑ በላይ ልትከበርም ትችላለህ፡፡
እስኪ እዚህ ሀገር ከሥልጣን ውረድና እንኳን ሥራ ቀጠሮ የሚቀጥርህ ታገኝ እንደሆነ ሞክራት፡፡ እንኳን ሌላ የገዛ ዘመድህ ሊያስጠጋህ አይፈልግም፡፡ እንኳን ዘመድህ የገዛ ሰውነትህ ይሸሽሃል፡፡ ሥልጣን እያለህ አንተ እንኳን ለዘመድህ ለጎረቤትህ ሁሉ የባንክ አካውንት ስታስከፍት ትኖራለህ፤ ሥልጣንህን ስታጣ ግን እንኳን የዘመድህ የአብሮ አደግህ አካውንት አይቀራቸውም፤ ይጠረቅሙልሃል፡፡
እና ምን ልሁን ብዬ ነው ሥልጣን የምለቅቀው? እኔ ሥልጣኔን ከማጣ ኢትዮጵያ እንኳን ሦስት ነጥብ ለምን ኳስ ሜዳዋን አታጣም፡፡ ደግሞስ ውርደት በኛ ነው እንዴ የተጀመረው፡፡ ‹አህያውን ፈርቶ ዳላውን› አለ፡፡ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ማግስት ባድሜን በፍርድ ቤት ክርክር አግኝተናል ተብሎ ሕዝብ ወጥቶ በአደባባይ ጨፈረ፤ ሚዲያውም አራገበው፡፡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ግን ባድሜኮ ለኛ አልተፈረደም፤ በፎርፌ ተበልተናል፤ ያልተገባ ተጨዋች አሰልፈን፣ ባድሜን አጥተናል ተባለ፡፡ ሕዝብ ኩምሽሽ አለ፡፡
እና ያን ጊዜ ማን ‹ሥልጣን ልቀቁ› አለ፡፡ ማንስ ሥልጣን ለቀቀ? አሁን በኛ ላይ ነው እንዴ ሁሉም ጥርስ የሚያወጣው፡፡ አስጨፍሮ ድልን መቀማት በኛ ነው እንዴ የተጀመረው፡፡ ባድሜን ያህል ቦታ ያሳጣ ምንም ሳይደረግ፣ ሦስት ነጥብ ያሳጣን ሥልጣን ልቀቅ ማለት ፍርሃትን እንጂ ጀግንነትን አያሳይም፡፡
ከመስቀል አደባባይ እስከ ሳሪስ ያለው የመሐል መንገድ መቶ ሚሊየኖች ወጥተውበት ተሠራ፡፡ አቤት አገራችን አለፈላት፤ ሦስት መንገድ በአንድ አቅጣጫ ተገነባ ብለን እልል አልን፣ አደነቅን፤ አዳነቅን፡፡ ቴሌቭዥኑም የዕድገት ማሳያ አድርጎ ደጋግሞ ከሙዚቃ ጋር አሳየን፡፡ ገና ደስታችንን ሳንጨርስ ግን መንገዱ ሲታረስ አገኘነው፡፡ በስሕተት ነው፤ ያልተገባ ተጨዋች ተሰልፎ የገነባው ነውና ለባቡር ይፈርሳል ተባለ፡፡ ሀገሪቱ መቶ ሚሊየኖች ያወጣችበትን መንገድ አምስት ዓመት እንኳን ሳያገለግል ማረስ ከሦስት ነጥብ በላይ ሀገርን ማሳጣት አይደለም እንዴ፡፡ ግን ያን ጊዜ ማን ተናገረ፡፡ ማን ሥልጣን ልቀቁ አለ፡፡ የትኛው ሥራ አስፈጻሚ ተቀጣ፤ የትኛውስ የጽ/ቤት ኃላፊ ተባረረ፤ የትኛው ምክትል ፕሬዚዳንት ሕዝብ ፊት ቀርቦ አለቀሰ፡፡ ዝም አይደል እንዴ የተባለው! እኛ ላይ ሲሆን ነው እንዴ ዘራፍ የምትሉት? ‹ጓደኛው ቢያቅተው ወደ ሚስቱ ዞረ› አሉ፡፡
አንድ ሰውዬ ያሉትን ልንገራችሁማ፡፡
ሰውዬው ሀብት ያካበቱት እየዘረፉ ነው፡፡ ሲነቃባቸው ደግሞ አላደረግኩም ብለው ድርቅ ይላሉ፡፡ ቢታሠሩም፤ ቢደበደቡም አያምኑም፡፡ ልጃቸውንም እንደ እርሳቸው አድርገው አሳደጉት፡፡ እርሱም ሀብታም ሆነ፡፡ አንድ ቀን ሲዘርፍ ተያዘና ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ‹ሰርቀሃል ወይ›› ሲባል ‹አዎ› ብሎ አመነ፡፡ ተፈረደበት፡፡ አባትዬው ይህንን ታሪክ ሰሙ፡፡ ‹‹ልጅዎኮ ሰርቆ ተፈረደበት›› አሏቸው፡፡ ‹‹በምቀኝነት ነው እንጂ የኔ ልጅ እንዲህ አያደርግም›› ብለው ተሟገቱ፡፡ ‹‹እንዴ እርሱ ሰርቄያለሁ ብሎ ያመነውን እርስዎ እንዴት ይክዳሉ›› አሏቸው፡፡ አባትዬውም ‹‹ልጄ ቢሰርቅም ሰርቄያለሁ አይልም›› ብለው ሞገቱ፡፡ ሰዎቹም ‹‹ብሏል በጆሯችን ሰምተነዋል›› አሏቸው፡፡ እርሳቸውም ‹‹ፈጽሞ አይልም›› ብለው ተከራከሩ፡፡
ሰዎቹ ግራ ገባቸው፡፡ ‹‹እንዴት በጆሯችን የሰማነውን እርስዎ ይክዳሉ›› ብለው ጠየቋቸው፡፡ ‹የኔ ልጅ ሰርቄያለሁ አይልም› አሉ አባት፡፡ ‹‹ለምን›› ሲባሉ ‹‹ያለ አባቱ ከየት ያመጣዋል›› አሉ አሉ፡፡ መስረቅ እንጂ ማመንን አላስተማሩትማ፡፡ አሁንም እኛ ያለ አባታችን ከየት እናመጣዋለን፡፡
እናንተ በሥልጣን ላይ ያሉትን የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ብቻ ነው የምታዩት፡፡ እስኪ በተቃዋሚው መንደር አስሱ፡፡ እነዚያው ሰዎች አይደሉም እንዴ በዙር ሥልጣኑን የያዙት? መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ተመልከቱ፤ መሥራችና ፕሬዚዳንት ራሳቸው አይደሉም እንዴ? ሲቪል ማኅበራቱን እዩ፤ የመሠረቱት ናቸው አሁንም ወንበሯን የተቆጣጠሯት፡፡ ውጡ ደግሞ ወደ ዲያስጶራው፡፡ በአንዲት መንደር ሃያ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የሚመሠረተው ለምንድን ነው? ሁሉም ሊቀመንበር መሆን ስለሚፈልግ አይደለም እንዴ? ፓርቲዎቹ ሲሰነጣጠቁ የሚውሉት በርዕዮተ ዓለም ተለያይተው ነው? ፈጽሞ፡፡ የተለያዩት በወንበር ነው፡፡ አብያተ ክርስቲያናቱ ሲከፋፈሉ የሚውሉበት ዋናው ምክንያት ምንድን ነው? ሁሉም የደብሩ አስተዳዳሪ፣ ሁሉም ቦርድ፣ ሁሉም ገንዘብ ያዥ መሆን ስለሚፈልግ ነዋ፡፡  
ደግሞኮ አንዳንዶቹ የሚገርሙ ናቸው፡፡ ‹ፌዴሬሽኑ ራሱን ተጠያቂ ማድረግ ሲገባው ግለሰቦች ላይ አነጣጠረ› ይላሉ፡፡ ፍየል መፈለግ በኛ ነው እንዴ የተጀመረው፡፡ ‹ምን ሹም ቢያጠፋ ባላገር ይክሳል› የሚለውን አልሰሙም መሰል፡፡ ምን ፌዴሬሽኑ ቢያጠፋ የሆኑ ፍየሎችማ ለእርድ መቅረብና ኃጢአት ማስተሥረያ መሆን አለባቸው፡፡ እንዲሁ ነውኮ የኖርነው፤ አንተ ታጠፋለህ፣ ፍየልህን ታርዳለህ፡፡ የጦስ ዶሮ ሲባል አልሰማችሁም፡፡ እንተ ትታመማለህ፣ ምንም ባላጠፋው ዶሮውን አርደህ፣ ሦስት ጊዜ አዙረህ ትወረውራለህ፡፡ ከዚያስ? ‹ጦስህን ይዞ ይሂድ› ትላለሃ፡፡
እና፣ ውረዱ፣ ልቀቁ ምናምን አትበሉ፡፡ እዚህ ሀገር ‹ውረድ› የሚባለው ዛፍ ላይ የወጣ ሰው፣ ‹ልቀቅ› የሚባለው ሰይጣን የያዘው ሰው ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰሞን ተንጫጭቶ ለሚረሳ ሕዝብ መውረድና መልቀቅን ምን አመጣው፡፡ ገና የባሰ ነገር ታያላችሁ፡፡
እንኳን ሦስት ነጥብ ተቀነሰ ተብሎ ይቅርና ሀገሪቱ ማጣሪያ በተደጋጋሚ ስትወድቅ፣ ከአፍሪካ ዋንጫ 31 ዓመት ስትርቅ፣ የምሥራቅ አፍሪካ ዋንጫ ሲርባት፣ ክለቦቿ ከአፍሪካ ክለቦች ዋንጫ አርባ ክንድ ሲርቁ፣ ማን ሥልጣን ለቀቀና ነው እኛ ሥልጣን የምንለቀው? አቦ አትቀልዱ፡፡
ጁባ፣ ደቡብ ሱዳን
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፡፡

72 comments:

 1. ባድሜን ያህል ቦታ ያሳጣ ምንም ሳይደረግ፣ ሦስት ነጥብ ያሳጣን ሥልጣን ልቀቅ ማለት ፍርሃትን እንጂ ጀግንነትን አያሳይም፡፡wow!from kb

  ReplyDelete
 2. hahahahha Egzer yistih Abo

  ReplyDelete
 3. የሚገርም እይታ ነው ዲን. ዳኒኤል ያላሰብኩትን እንዳስብ አድርገሀኛል በተለይ የምትለዋን ሃረግ ወድጃታሎህ!በቸር ሰንብት

  ReplyDelete
 4. ለመሆኑ መለስ 97 ላይ ስልጣን ለቆ ቢሆን ሰዉ እንዳሁኑ ያለቅስለት ነበር በፍጹም! እንዲያውም ባንዳ አገር ሻጭ ከፋፋይ ዘረኛ ይባል ነበር አሁንሳ .. ጀግና አይሞትም!አባይን የደፈረ መሪ....ለዚህም የኢትዮጲያ ህዝብ በዲሞክራሲ ያልታደለው.... ከታች ጀምሮ ዲሞክራቺያዊ እሳቤ ቢዳብር ኖሮ አገራችን እዚህ ላይ አደርስም ነበር!!!ለቀላሉ ነገር ፍትሃዊ ካልሆን ለከባዱ ፍትሃዊ አንሆንም... በቀላሉ ነዋ የሚያገኘው፡፡ በየቴሌቭዥኑ ለፍልፈህ፣ ልብ የሚያጓጓ ንግግር ተናግረህ፣ የሰው ካርድ ጠብቀህ የምታገኘው ሥልጣንና ጉቦ ሰጥተህ፣ ደም ተፍተህ፣ ለስንቱ ጉልበተኛ አጎንብሰህ፣ ተለማምጠህና ከሰው በታች ሆነህ የምታገኘው ሥልጣን አንድ ነው እንዴ? ደግሞ ፈረንጅ ምን ችግር አለበት፤ ‹በፈቃዴ ሥልጣኔን ለቅቄያለሁ› ቢል ‹ይህስ ኅሊና ያለው ነው፣ ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ነው› ተብሎ ያም ያም ይሻማበታል፤ ሥልጣኑ ይቀርብህ እንደሆነ እንጂ ገንዘቡና ክብሩ አይቀርብህም፤ ኧረ እንዲያውም ከባለሥልጣኑ በላይ ልትከበርም ትችላለህ፡፡
  እስኪ እዚህ ሀገር ከሥልጣን ውረድና እንኳን ሥራ ቀጠሮ የሚቀጥርህ ታገኝ እንደሆነ ሞክራት፡፡ እንኳን ሌላ የገዛ ዘመድህ ሊያስጠጋህ አይፈልግም፡፡ እንኳን ዘመድህ የገዛ ሰውነትህ ይሸሽሃል፡፡ ሥልጣን እያለህ አንተ እንኳን ለዘመድህ ለጎረቤትህ ሁሉ የባንክ አካውንት ስታስከፍት ትኖራለህ፤ ሥልጣንህን ስታጣ ግን እንኳን የዘመድህ የአብሮ አደግህ አካውንት አይቀራቸውም፤ ይጠረቅሙልሃል፡፡
  እና ምን ልሁን ብዬ ነው ሥልጣን የምለቅቀው?

  ReplyDelete
 5. nice view. all the crisis that we see in our country are not caused by individual's mistakes it is rather a system failure. kezih chigir lemewtat ende 'MUSSIE' mesih yaselgenal.

  ReplyDelete
 6. ዳንኤል እንደምን ነህ )

  በጣም አስተማሪ የሆነ ጽሑፍ ነው፤፤

  መድሐኒዓለም ይጠብቅህ

  ወለተ ሚካኤል

  ReplyDelete
 7. ውረዱ፣ ልቀቁ ምናምን አትበሉ፡፡ እዚህ ሀገር ‹ውረድ› የሚባለው ዛፍ ላይ የወጣ ሰው፣ ‹ልቀቅ› የሚባለው ሰይጣን የያዘው ሰው ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰሞን ተንጫጭቶ ለሚረሳ ሕዝብ መውረድና መልቀቅን ምን አመጣው፡፡ ገና የባሰ ነገር ታያላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 8. We are facing series individual and institutional incapablity that could drag the country to total destruction. There are thuosand of cases of complete failures by various individuals and institutions in Ethiopia. What shall we do? Nowadays, only when a person is politically wrong his all wrong doings collected and presented to court, otherwise one can enjoy his power and life without any accountability.

  ReplyDelete
 9. አሻግሩን


  ምልክቱን ካየን በእናንተ እጆች
  ካላችሁን ልጆች ልጆች
  ልክ እንደ ኖህ ሰብስባችሁ
  በመርከቡ አሳርፋችሁ
  ምድረበዳ ሳታቆዩን
  ንፍር ውሃው ሳይተኩሰን
  ዶፍና ጎርፍ ሳያርሰን
  እስኪ እንለፍ አሳልፉን
  ከንውፅውጽታው አሳርፉን
  እንደ ሙሴም ከፊት ምሩን
  ቀድሞ ማዳን አስተምሩን
  የአበው ልጆች ወዴት ናችሁ
  እንዲረዳን ጸሎታችሁ
  ውሰዱና በደረቁ
  ዛሬም ግብፆች ይደነቁ
  የቱ ጋ ናችሁ ሙሴዎቹ
  ሲያስጨንቁን ፈርኦኖቹ
  አሻግሩና ተሻግራችሁ
  እንዲፈጸም ተልዕኮአችሁ

  ከደጀ-ሰላም የግጥም መድብል የተወሰደ
  (ዘፍቅርተ 2002)

  ReplyDelete
  Replies
  1. We all need to be Moses we all need to be Noah of our time

   Delete
 10. ፡ ለሰው ልጆች ትልቅ ፈተናው ምቾቱን መሠዋት ነው፡፡ ያለፉትን መቶ ዓመታት እንኳ እንደገና መለስ ብለን ስንመለከት ኢትዮጵያ በማያባራ የችግር ማዕበል እየተመታች ነው፡፡ በዚህ ሁሉ መንፈሳዊ ነገር ፍለጋ ውስጥ ይህ ሁሉ መከራ ለምን መጣብን የሚሉም ብዙ ናቸው፡፡ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ከጀመረ እንኳ ብዙ የእርስ በርስ እልቂቶች ተከስተዋል፡፡ የሰገሌ ጦርነት፣ የማይጨው ጦርነት የብዙ ኢትዮጵያውያንን ህልውና ቀጭተውታል፡፡ ለ17 ዓመታት የፈጀው የእርስ በርስ ጦርነት በቅርቡ እንኳ የተፈጸመው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ለብዙ ሕጻናት ለብዙ ወጣቶች ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡ አንድ ትውልድም በሦስት ቀን ጦርነት ተሠውቷል፡፡ በረሀብም እጅግ አሰቃቂ የሆኑ ቀኖች አልፈዋል፡፡ የ1966 ዓ.ም የ1977 ዓ.ም የረሀብ አደጋዎች ሕፃናት የእናቶቻቸውን ሬሣ እስኪጠቡ ያደረሰ ብርቱ ቀን አልፏል፡፡ እኛም ተወልደን እዚህ እስከደረስን የኢትዮጵያን መልካምነት በቅጡ አላየንም፡፡ አገራችን ስንት የተማሩ ወጣቶች በአደባባይ የተረሸኑባት፣ ለተገደሉበት ወላጆች የጥይት የከፈሉባት፣ በዘረኝነት በጎሣ ግጭቶች ሕፃናት ሳይቀር በአሰቃቂ ሁኔታ የተሰለቡባት የተገደሉባት የደም ምድር ናት፡፡ በየዕለቱ ስመ እግዚአብሔር የሚጠራባት አገር ይህ ሁሉ ለምን ደረሰባት? ፍለጋችን የእግር ይሆን ወይስ የልብ? መንገዱን አጥተነው ነው? ወይስ አግኝተነው?

  በቀይ ሽብር ዘመን በጎዳና ላይ የወደቀው ወጣት ብቻ ሳይሆን ትልልቅ አእምሮም ነበር፡፡ ለ17 ዓመታት ይጋዝ የነበረው ያ ሁሉ ወታደር ሳይመለስ የቀረው ከገዛ ወገኑ ጋር ለመጫረስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያለው ላይቀር ስንት ወላጆች የወላድ መሓን ሆኑ፡፡ ያ የአደባባይ ጦርነት ባለቀ ጊዜ የጓዳ ጦርነት የሆነው በሽታ ላለፉት 2ዐ ዓመታት ስንቱን ጐበዝ በቁመቱ ልክ ጣለው፣ ስንቱን ቆንጆ አረገፈው፡፡ በጦርነቱ የሞተውን ያህል በበሽታ ቀብረን የተቀመጥን ሕዝቦች ነን፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ችግሩ ምንድነው? ያለ ማንም አልነበረም፡፡ ዛሬም በሌሎች ልቅሶ ለመርካት እንጂ የራሳችንን ደስታ ለማግኘት የማንጸልይ ሆነናልና እግዚአብሔር ያስበን!

  መፍትሔውን ከሰው የሚጠብቅ ሕዝብና ወገን መከራው ማለቂያ የለውም፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሥልጣን ቢለቁ ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ ደረጃ ትደርሳለች ተብሎ ታመነ፡፡ ደርጉ መጣ፣ ብዙ መፈክር ተሰማ። "ያለ ምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም" ሲባል ያለ ደም ያለፈ ዓመት ሳይሆን አንድ ቀን አልነበረም። አራዊት ወደ ከተማ በቀን የወጡ እስኪመስል ሰው አውሬ ሆኖ ጎረቤት ያሳደገውን ልጁን በላ፡፡ አገሪቱ በማይለካ የደም ባሕር ተጠመቀች፡፡ ከዚያ በኋላ ጸሎትና ምኞት ጠፍቶብን፡- "ደርጉ ሥልጣን ይልቀቅ እንጂ ምነው ሰይጣን በዙፋን ተቀምጦ በገዛን" አልን፡፡ ደርጉም ሥልጣን ለቀቀ፣ የመጣውም መንግሥት አልጣመንም፡፡ አሁንም ሌላ መሪ እንጂ ሌላ ምሕረት እንደሚያስፈልገን አላወቅንም፡፡ አፋችን እግዚአብሔርን ይጠራል ልባችን ግን ክዷል፡፡ የሚያስፈልገን መሪ vምሕረት ነው፡፡ምድራችን ፍቅርን ጥለው ጥላቻን፤ ይቅርታን ትተው በቀልን ያረገዙ ምስኪኖች ወድቀውባታል፡፡ አንዱ አንዱን ለሞት የሚፈልግበት ሰዋዊ ሥርዓት ነግሶባታል፡፡ ዘመኑን ባለማወቅ የሚባዝኑ ሰነፎች ሞልተዋታል፡፡ ሐሰትን እንደ እውነት፤ ኃጢአትን እንደ ጽድቅ ቁጠሩልን ባዮች ተቀምጠውባታል፡፡

  ይህ ዘመን ከክፉ መሻታቸው ጋር የሚስማሙ አገልጋዮችን የሚፈልጉና እውነት ሲነገር የሚያኮርፉ “አማኞችን”፤ የመዳንን ወንጌል በተረት የሚሸፍኑ ሰባኪዎችን፤ ስለሰው ሞራል ኃጢአትን የሚፈቅዱ መሪዎችን፤ የእውነትን ልዕልና ከማስከበር ይልቅ በኑሮ ፍርሀት ዝምታን የመረጡ አለቆችን አፍርቷል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. May God visit this land by his own

   Delete
  2. Ewinetin tenagiro yemeshebet mader sew betefabet zemen hono megegnet lehod sayihon lehlina maderin enilimed D/ Daniel Egiziabiher yistilin

   Delete
  3. እግዚአብሔር ይስጥልኝ!!!!!

   Delete
 11. Daniel, Thank you. You tell them if they have a heart to hear you and your observations. you are really indeed an excellent socio-political writer.

  ReplyDelete
 12. ስልጣን ልቀቁ ብንላቼው ይቀየሙናልና ፌደሬሽኑን በሙሉ unfriend ብናደርገው?ምን ይመስላችኋል? እኔ ይህን ብቻ ሳይሆን የወገን ፍቅራችን Face book ከማድመቅ ባለፈ እና በተዋደድ እና በተፋቀርን እና ያለን Share በተዳረረግን እና ተቃቅፊን በተላቀስን ዘር መቁጠር እና በፓርቲ መዘርዘር ትተን እና አብረን በተመገብን እላለሁ!!! ኢትዮጲያዊነታችን እና እኛነታች ከfacebook አልፎ Post በተደረገ እና እላለሁ።ፖለቲካችን ልክ በwebsite እንደ ምናየው ቀላል በሆነና ችጋረችንን ተመካክረን በፈታን እና አንተ ትብስ አንቺ ትብስ እኔ እብስ በተባባልን እና በተማማልን እና ቃል በተጋባባን እና ሀገራችን ባለማን እላለሁ።ወዳጅነታችን ልክ እንደ face book በሆነ እና “በተዋደድን” እና “በተፋቀርን” እና በተመሰጋግንን እና በተዋደድ እና በተሞከሻሸን እና Add በተዳራረግን እና ባልፈለግን ጊዜ ደግሞ unfriend በተዳራረግንን እና ፍቅራችንም በፍቃዳችን ላይ በተመሠረተ እና የማንፈልገቸውን ሰዎች profile እንዳያዩብን ባደረግን እና “ፈታችንን ባስመታን” እየማንፈልጋችውን ሰዎች በቀላሉ በሸወድንን እና privacy በተበቅን እና ሕይወታችን Facebook ተኮር በሆነች ትምህርታችን ልክ እ profile ባማረ እና በተዋበ እና ባስታካከልነው እና ባበጃጀነው እና ውጤታማ ባደረግነው እና ጥበብን ባፈለቅን እና ድህነትን አሳሩን በሳየነው እና ዓለም ሁሉ አጀብ ባለ እና ደስ በተሰኘን እና በብልጥግና ስማችን በተፋቀ እና መዝገበ ቃለቱን የጻፉት ሰዎች ይቅርታ በጠየቁንን እና እያልኩ በfacebookኛ እመኛለሁ።http://abinetababu.wordpress.com/

  ReplyDelete
 13. Dani Ahune gene tinish Wet yergetk aymeslihim ? Kechalk poletikawin legna tewina haimontihin atbiq...embi kalkim beglstese be poletika tederajthe naa....yane enasayihalen.yemin huletunim eyatakesu mehed newe...

  ReplyDelete
  Replies
  1. Poletikegnaw hulu haimanot yelesh new endie? Weys haimanot yalew sew slepoletika mawrat menager ayfekedletim? Aye yegna poletikegna, dinkem poletikegna alu! Yhin neber tew yetebalew, semi tefa enji. Enante poletikegna tebyewech sew benetsanet yemawrat mebitun atinfegu new yetebalew. Tifatachihun wede lela atalakiku, amen bilachihu tekebelu, akim siatrachihu neger eyetemezezachihu sewn atashemakiku new eyalin yalenew. Libona ystachihu.

   Delete
  2. ይህ እኮ ፖለቲካ አይደለም የሀገር ጉዳይ ነው፡፡ ደግሞስ ሁሉም ሰው ፖለቲከኛም ሀይማኖተኛም ከመሆኑ በፊት እኮ ሰው ነበር ብሎ ጋሽ ዳንኤል ከተናገረ እኮ ቆዬ፡፡ ተው እንጂ እናስተውል! ነው ወይስ ይቺን ሀገር ፖለቲካ ብቻውን እንዳላቆማት አያውቁም እንዴ ስንት ነገር አለ!?

   Delete
 14. Wow "እዚህ ሀገር ‹ውረድ› የሚባለው ዛፍ ላይ የወጣ ሰው፣ ‹ልቀቅ› የሚባለው ሰይጣን የያዘው ሰው ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰሞን ተንጫጭቶ ለሚረሳ ሕዝብ መውረድና መልቀቅን ምን አመጣው፡፡ ገና የባሰ ነገር ታያላችሁ፡፡" May God with You!

  ReplyDelete
 15. ልደቱ የት ገባ?

  ReplyDelete
 16. They call it local democracy. Bad stuff they bearing from overseas, to replace the good things we have in local, and they keep encourage the bad things we have in local. That is their best experience.

  ReplyDelete
 17. ውረዱ፣ ልቀቁ ምናምን አትበሉ፡፡ እዚህ ሀገር ‹ውረድ› የሚባለው ዛፍ ላይ የወጣ ሰው፣ ‹ልቀቅ› የሚባለው ሰይጣን የያዘው ሰው ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰሞን ተንጫጭቶ ለሚረሳ ሕዝብ መውረድና መልቀቅን ምን አመጣው፡፡ ገና የባሰ ነገር ታያላችሁ፡፡ a very nice expression, bless you Dani!!

  ReplyDelete
 18. Edmena Tena Emejelhalu Lelochachen kezhe teufe mmare yegebanal hulume neger yalfal!!!

  ReplyDelete
 19. እና፣ ውረዱ፣ ልቀቁ ምናምን አትበሉ፡፡ እዚህ ሀገር ‹ውረድ› የሚባለው ዛፍ ላይ የወጣ ሰው፣ ‹ልቀቅ› የሚባለው ሰይጣን የያዘው ሰው ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰሞን ተንጫጭቶ ለሚረሳ ሕዝብ መውረድና መልቀቅን ምን አመጣው፡፡ ገና የባሰ ነገር ታያላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 20. እውነትን ፍለጋ! መች ይሆን ... ?

  than you Dani!

  ReplyDelete
 21. Ere endih beqal tenegroachewu Ejachewu yezewu bigotutuwachewu enja mutegn newu yemilut,zare yihn agegntewu
  hager sisetu gn mnm alalum 3netib gn ateftenal atan balu sewoch lay gn hulum tirs aweta. Yiqer libalu yalebelezia yeqedmowun hager yasatunm hisab yaweraredu. Egziabher yesteh Daniel.

  ReplyDelete
 22. ምንድን ነው የምትለው ዲ/ን
  መልቀቅማ አለባቸው በሚገባ በባህር ዳር የሆነውን አልሰማህም እንዴ የሰው ህይወት እኮ አልፏል እና እነዚህ እኮ .................. ይቅር

  ReplyDelete
  Replies
  1. ባህር ዳርና ሐዋሳ የሞተው እኮ በፌዴሬሽኑ ስህተት አይደለም፡፡

   የኢትዮጵያ ህዝብ ሃዘንም ደስታም ስለማይችልበት ነው፡፡

   Delete
  2. ምነው ወንድሜ እነዚህ እኮ ሙያቸው እግር ኳስ ነው፡ ሃኪሞች በቸልተኝነት ሲሞትባቸው እንኳን ወርደው አያውቁም፡፡ ደሞ ሞት ለኛ ብርቅ ነው እንዴ

   Delete
 23. Thanks Man, I love it

  ከመስቀል አደባባይ እስከ ሳሪስ ያለው የመሐል መንገድ መቶ ሚሊየኖች ወጥተውበት ተሠራ፡፡ አቤት አገራችን አለፈላት፤ ሦስት መንገድ በአንድ አቅጣጫ ተገነባ ብለን እልል አልን፣ አደነቅን፤ አዳነቅን፡፡ ቴሌቭዥኑም የዕድገት ማሳያ አድርጎ ደጋግሞ ከሙዚቃ ጋር አሳየን፡፡ ገና ደስታችንን ሳንጨርስ ግን መንገዱ ሲታረስ አገኘነው፡፡ በስሕተት ነው፤ ያልተገባ ተጨዋች ተሰልፎ የገነባው ነውና ለባቡር ይፈርሳል ተባለ፡፡ ሀገሪቱ መቶ ሚሊየኖች ያወጣችበትን መንገድ አምስት ዓመት እንኳን ሳያገለግል ማረስ ከሦስት ነጥብ በላይ ሀገርን ማሳጣት አይደለም እንዴ፡፡ ግን ያን ጊዜ ማን ተናገረ፡፡

  ReplyDelete
 24. Bitter truth that you can't avoid!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 25. "ምንድን ነው የምትለው ዲ/ን
  መልቀቅማ አለባቸው በሚገባ በባህር ዳር የሆነውን አልሰማህም እንዴ የሰው ህይወት እኮ አልፏል እና እነዚህ እኮ .................. ይቅር"

  ለመሆኑ በባድመ የሞተውን 70 እና 80 ሺህ በምርጫ 97 የሞተውን በትንሹ 193 ዜጋ ዘነጋነው መሠለኝ 2 ሰው ባሕር ዳር ላይ ስለሞተ መውረድ አለባቸው የምንለው፡፡

  ዳኒ አንዳንዴ ኮሶ መሆንህን የሚወዱልህ አይመስለኝም ምክንያቱም ኮሶን የሚወደው ከሕመሙ መዳን የሚፈልገው ነው፡፡ በአምባገነንነተ ልክፍት የተያዘን በኮሶ ለማዳን መሞከር ኮሶ ሻጩን ምንች የሚያስመታው ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
 26. egziabher yetebekeh lela menem alelem, yenzia yetenanesh lejoch amlak yetebekeh

  ReplyDelete
 27. sihtetachew silamenu yikirta tedergolachew hizbun yikisutal d/n daniel kibret 10q 4 ur expression

  ReplyDelete
 28. ሰሎሞን በርሄJune 27, 2013 at 8:31 AM

  ጥሩ እይታ ነው ሰላም ሁን

  ReplyDelete
 29. Dani! it is good looking! you made me to think too about our Football and All sport Organizations.

  ReplyDelete
 30. d. Daniel it was such a greate lesson.for those who wants to take some advise.thanks

  ReplyDelete
 31. Thanks to D.DK and a one who post this paragraph "ይህ ዘመን ከክፉ መሻታቸው ጋር የሚስማሙ አገልጋዮችን የሚፈልጉና እውነት ሲነገር የሚያኮርፉ “አማኞችን”፤ የመዳንን ወንጌል በተረት የሚሸፍኑ ሰባኪዎችን፤ ስለሰው ሞራል ኃጢአትን የሚፈቅዱ መሪዎችን፤ የእውነትን ልዕልና ከማስከበር ይልቅ በኑሮ ፍርሀት ዝምታን የመረጡ አለቆችን አፍርቷል፡፡"

  ReplyDelete
 32. Daniel ! i a just like your FB page with in a week long ! and am so thankful that i have learned so much thing ! may GOD Bless you!!!

  ReplyDelete
 33. ይህ የእግር ኳስ ጋዜጠኞች በጣም ጠንካራ ስራ ነው፡፡ ጥሩ የኮንስትራክሽን ጋዜጠኞች ቢኖሩን ኖሮ ለ 100 አመት የተሰራው ኮንዶሚኒየም ያለምንም የተፈጥሮ አደጋ በ5ኛ አመቱ መስመጥ ጀምሮ አንድም ሰው ሳይጠየቅ፣ አንድም ሰው ሳይባረር ሌላ 1 ሚሊየን ሰው መመዝገብ አይጀመርም ነበር፡፡ በጤናውም በሃኪሞች ቸልተኝነት ለሚሞቱ ሰዎች አንድም ተጠያቂነትን የሚከተተልና የሚዘግብ ጋዜጠኝነት አላየንም፡፡ ፀረ-ሙስና ኮሚሽንም ያለ ደህና አቀጣጣይ ጋዜጠኝነት የትም የሚደርስ አይመስልም፡፡

  ReplyDelete
 34. እዚህ ሀገር ‹ውረድ› የሚባለው ዛፍ ላይ የወጣ ሰው፣ ‹ልቀቅ› የሚባለው ሰይጣን የያዘው ሰው ብቻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 35. እዚህ ሀገር ‹ውረድ› የሚባለው ዛፍ ላይ የወጣ ሰው፣ ‹ልቀቅ› የሚባለው ሰይጣን የያዘው ሰው ብቻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 36. thank u Daniel. please, if you have time wrote more about our weak sides.I think it is good for future generation to correct our views.

  ReplyDelete
 37. በእውነት ተባረክ! ጋሼ ዳንኤል ትልቅ ምክር ነው ብዙ ከመናገር ማሰብን ተምሬበታለሁ

  ReplyDelete
 38. ስህተትን ማረም ነው የሚቀለው ወይስ መወነጃጀል 

  ReplyDelete
 39. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ባለፈው የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የፓትሪያሊክ ምርጫ ጉዳይ የሰጠኸው ሀሳብ ባልስማማበትም በዚህ የሃገራችን ወቅታዊ የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳይ ደሞ አንጀቴን አራስከው......

  ReplyDelete
 40. betam emamesegenaleh daniel yehe ager selatan keteyaze ayelekekebetem yeneberen chera keyazu................... new negeru

  ReplyDelete
 41. /ደበበ ሰይፉ/

  ትግራይ ላከ ወሎ ጋ አበድሮኝ ብሎ አንድ ቁና ጤፍ
  ወሎም አፈረና የለኝም ማለቱን ባህሉን መዝለፍ
  ቆሌውን መንቀፍ
  ላከ ወደሸዋ ምናልባት ቢሰጠው ለሰው እሚተርፍ።
  ሸዋም አፈረና የለኝም ማለቱን ወደ ሐረር ዞረ
  ሐረርም መልሶ ባሌን አተኮረ
  ባሌም ወደአርሲ አርሲ ሲዳሞን
  ሲዳሞም ተክዞ፣ ግን የለኝም ብልስ ማን ያምነኛል ብሎ
  ወደ ጋሞ ላከ አቁማዳ ጠቅሎ።

  ጋሞን ብርድ መታው ሐዘን ገባውና
  የራሱን ምንዳቤ የግል ስቅየቱን ችሎት በጥሞና
  በጋቢ ጀቡኖ የልቡን ጠባሳ ሲኖር እንደ ደህና
  ዛሬ የወንድሙን የእርዳኝ አቤቱታ መስማት አልቻለና።
  አውጥቶና አውርዶ ላከ ወደ ከፋ እጅግ አስተዛዝኖ
  ከሀፍረት ያድነኛል ከረሃብ ያወጣኛል ሲል በአያሌው አምኖ።
  ከፋ እንደደረሰው በድንገት አቁማዳው በነብሱ ዋይታ
  ሐራራው ተሰማው የሥጋው ድንፋታ
  ብልሀት አዛጋ ቆይቶ ቆይቶ የተስፋ ጠል ቀዳ
  ሊልክ ከኢሉባቦር አበድረኝ ብሎ እህል በአቁማዳ።

  ጭምት ኢሉባቦር ይኖር የነበረ የቤቱን ጉድ ጓዳ በሞኛሞኝ
  ገላው ቆዳው ውስጥ ወሽቆ
  ጠየቀ ወለጋን ሐፍረቱን ደብቆ ኩራቱን ዘቅዝቆ
  ኬት አመጣ ብሎ ወደኔ ላከብኝ እያለ ወለጋ እጅጉን ተደሞ
  ሄደ ወደ ጎጃም ዛሬን ሁነኝ ብሎ ሊማፀነው ቆሞ።

  ጎጃምም ተሰምቶት ሰቀቀን ሐዘኑ ደረት እየመታ፣ ቅኔ እያወረደ፣
  እንባ እያፈሰሰ
  ወግና ኩራቱን በየቦዳው መሀል እየነሰነሰ
  ዐባይን ተሻግሮ ከጎንደር ደረሰ።
  ፋሲል ላይ ተነጥፎ ጎንደርም ሐዘን ላይ ነበረ ተቀምጦ
  ተድላ ልጁ ሞቶ ገናን ክንዱ ታጥፎ በዘመን ተድጦ
  ጎጃም መጣ ሲሉት የእዝን የተመኘን ልቡን በታዘበ
  የኩራት ካባውን ሊጥል ባንጓበበ
  የወንድሙ መምጣት እቅጩ መንስዔ መሆኑን
  ሲረዳ ረሀብ አበሳ
  ጥንትም አልሆነኝም ከእንግዲህ ይበቃኛል ለይሉኝታ አልሳሳ
  ብሎ ከአፋር እህል ለመበደር በርትቶ ተነሳ።

  የዘመዱ እጦት ነበርና እጦቱ በዝቶ ሰቀቀኑ
  ታመመ ደም ጎረፈ ከዓይኑ፡፡
  ወደ ትግራይ ላከ መላ ባገኝ ብሎ ከአደራ ደብዳቤ
  (እባክህ ላክልኝ አንድ አቁማዳ እህል ልሞት ነው ተርቤ።)

  ትግራይ አስተውሎ አቁማዳው የራሱ መሆኑን ለይቶ
  ረሀብ ዕጣቸው የሁል ወንድሞቹ መሆኑን አካቶ
  ሐዘኑ አነቀው፤ ትንፋሹ መረረው፣ ትካዝ ሆዱ
  ገብቶ።
  “እኔና ወንድሞቼ” አለ በለዘብታ
  ለራሱ እንዲያወራ የራሱን ስሞታ፤
  “እኔና ወንድሞቼ ሁላችን . . . ሁላችን
  ከባዶ አቁማዳ ነው እሚዛቅ ፍቅራችን
  ይህ ነው አንድነታችን
  ይህ ነው ባህላችን
  ዘመን ማዛጋቱ በያንደበታችን።
  ለኋላ ትውልዶች ተረት እንዳይመስል ይህ ብካይ
  እሮሮ
  ይህ ጠፍ ስብእና ይህ ስቁይ አእምሮ
  እንዳኖረው ያሻኛል ይህንን አቁማዳ ከፍ ካለ ስፍራ
  መጥቆ እንደባንዲራ
  ምንም ባዶ ቢሆን በውስጡ አይጠፋና የታሪክ
  አዝመራ።”
  ይህንን ተናግሮ ከአክሱም ሐውልት ዘንድ
  ትግራይ ተጠግቶ
  አንዴ እየፀለየ አንዴ እየዘመረ ያለመጠን ተግቶ
  ጫፉ ላይ ሰቀለው ያን አቁማዳ አውጥቶ።

  ReplyDelete
 42. ትችት የእውቀት አድማስ ማጎልመሻ ነው ብየ ባምንም ፣ የዳኔን መጣጥፎችን በተመለከተ ግን በየትኛውም መስክ ቤሆን አንድ ግዜ ተነበው የሜይረሱ ሳይሆን ቆም ተብለው የሜስተዋሉ ናቸው ብየ አምናለሁ።
  በርታ።

  ReplyDelete
 43. መቼም በዚህ በኛ ዘመን ኳስ የዘመኑ ጻኦት የሆነት ጊዜ ነው፡፡ ማለት ያገር ፍቅር ቢሆን መልካም በሆነ ነበር ግን አይደለም እንዲሁ ጠላታችን ሰሠይጣን ደግ ስራን አይወድምና ትውልዱን በኳስ ፍቅር ጣለን …… ዛሪ ለናቷ ሽንኩርት ለመክተፍ ጊዜ የሌላት ልጅ ለኳስ ዘጠና ደቂቃ ከዚያም በላይ ትመድባለች ለቤተሰቡ የተደፋ ውሃ ለማቅናት ጊዜ የሌለው ጎረምሳ ውሎና አዳሩ ለኳስ ስለኳስ ሲሆን ስናይ ሰነባብተናል ፡፡ አዛውንት እናቷ የተቦካውን መጋገር አቅቷቸው ሲወድቁ ሲነሱ እያየች የበሰለውን በልታ ኳስ ትሄዳለች ይህ ደግሞ በጎረምሳ ከሆነ የበሰል ከሌለ እናቱን ይገላምጣል የናቱ ድካም አቅም ማነስ ለሱ መኑም አይደል ፡፡ አረ ስነቱ ቤት ይቁጠረው እነጂ ለቤተሰቡ ሱቅ የማይላክ ጎረመሳ ለኳስ ቤቱን ጥሎ ፣ ብርዱን ፣ራቡን ግፊያወን ታግሳ ውጭ የውላል ያድራል ፡፡ ግን አናቱ አባቱ ታመው ሆስፒታል ካደረ የቤቱን ልብስ ሁሉ መጥቶለት ለብሳ ወይ ዛሬ ብርድ ሳይመታኝ አይቀርም ወገቤ ተንጫጫ እራሴ ሊፈነዳ ነው ብቻ እንዳገላለጣቸው ይገልጡታል
  ከናት ፍቅር የኳስ ፍቅር ይልጣልን…….?ባይሆን እንኳ አጉሩን ከቤተቡ እኩል ማይት ይቻላል ካስ ከሆነ ግን ሁሉኑ ይረል ዝናብ ዶፉን ቢወርደው አይሰማውም ታዲያ ይህ የሆነው ከንቱ ወዳሴን ከመሻት ነው ምክንያቱከም ኳስ የዘመኑ ፆኦት ነውና ወሪው ሁሉ ስለኳስ ስለሆነ እሱም በዚያመሀል እንዲወራለት ስለሚፈልግ ጭፈራውን የሰውን መብዛት ለማይት ብቻ ፡፡
  የገአር ፍቅርና የኳስ ፍቅር ለይተን አላየንም ያገር ፍቅር ካለን ችግር መፍተሄ ሊያስፈልጋን እንጂ ስንጣን ልቀቅ ሊያስብለን አይችልም ሰው ማለት አገር አገር ማለትም ስወ ነው እኛግን ፍቅር ስለየለን ክፉ ፈረገድን እንደመሩን ባንሄድ ደግነው የህሌና ዳኝነት ከሁሉ ይበልጣልና ፡፡ የነገር ፍፃሜ ከመጀመርያው ይሻልልና አንድም የባሰ አለና የያዝከውን አትልቀቅ ይባልልና መጨረሻቻን ማየት ይሻላል እስካሁን በቻሉት ኳሳችንን እዚህ ያደረሱ ተብለው መመስግን ሲገባቸው በይሆን ተሳስተዋልና ይቅርታ መጠየቅ ይገባቸዋል ማለት ነበረብን
  እንዲያው ወገኖቼ ኳስ ስንቱን መሰላችሁያስረሳን የሚስት፣የባል ፣የልጅ ፣የእናት ፣አባት ፣ የወንድም ፣የእህት የአምላክ ፍቅር ሳይቀር አስረስቶናል ለዚህሁሉ ያልሆን ትውልድ ግን በጭራሽ ላገሩ ሊሆን አይችልም ቢልም እንኳ ወሸታም ነው ፡፡ የገር ፍቅር ካለን ደግሞ በዚቺ የፈረድነው በአገራችን ስለሚደረገው 90% ን ስለማናውቅ ብናውቅም መፍረድ ስለማንችል ወይም እንድነፈረድም ስለማንጠየቅ ብንፈረደም ስለሚፈረደበን ወሸት በቻዋን አተቆምምና ስናጂባት አለን እውነት ስላገራችን ሳይሆን ስለኳስ የሞትን ሆነናል አህያወን ብንፈራ ዳወላወን ደበደብነው
  ተሳስተው 3 ነጥብ ላሳጡት እንዳህ ዳልን
  አውቀው አገር ለሚሸቱት ምን እንላለን
  እሬቱን በማር ለሚያጎርሱን ምን እንላለን
  ወሸትን ቀሰውባት የወሸት ዲያቆኖች ላረጉን ምንእንላለን
  ስላገራቸው ሳይሆን ስለስልጣናቸው ለሚሞቱን ምን እንላለን
  ወገን ተማሪ ሲማር ከከባድ ወደቀላል ይሄዳል አያጠራ እያወቀ በአእምሮና በአካል እደገ በዙይጓዛል ከከባዱ ቢጅምር ግን ኣለዋቂ ይሆናል እኛም የሚጥቅምንን ከፈለግን ከዚሕ 90 ጊዜ የከፋወን እናጥራው ቀስ ብለን 80ውን… 10 ስንል እናድጋልን በይናችን ያለውን ጉደፍ ካወጣነው ቀሪውን ሰውነታችንን እናየዋለን የሚሆነውን እናደርጋለን እንደኔ ችግር ሲወገድ ከትለቅ ወደትንሽ ነው እንጂ
  ልባችንን አምላክ ወደኛ ይመልስልን

  ReplyDelete
 44. wowwwwwwww
  nice view

  ReplyDelete
 45. wowow...i thought this site was focusing on our church but now it seems changing to politics...people will come and go but at the same time they are 2 kind of people...i saw you preaching in the church but now you are preaching sport...i leave it to god..it all matter is how we can worshiping god. in my opinion who cares about sport....

  ReplyDelete
 46. No no...see carfully wat Dan wrote about before you grossly forward any crisis...he just wrote about fair & fact, nothing else! Yap!, it is a crystal truth zat our country has been in a such suitation...Dani u r exactly right, go on...

  ReplyDelete
 47. millions thanks for telling us the real situation of the foot ball federation. and how much position is difficult to come down.
  ዓይኔን ግንባር ያርገው ብሎ ይምላል ሰው
  የቀኑን ጨለማ እንደኔ ባይቀምሰው
  አለ ማየት የተሳነው ለማኝ፡

  ReplyDelete
 48. I always appreciate ur view thanks D/Daniel God bless u

  ReplyDelete
 49. I always appreciate ur view thanks D/Daniel God bless u

  ReplyDelete
 50. በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በላሊበላ ገዳም የተፈጸመ ታሪክ ነው፡፡ አንድ መነኩሴ በጣም ኃይማኖታቸውን አጥባቂና በጾም በጸሎት የተጉ በመሆናቸው በካህናቱ እና በምዕመናን ዘንድ በእጅጉ ይወደዳሉ፡፡ እናም ካህናቱም ምዕመኑም ተሰብስበው በአንድ ድምጽ ‹እባክዎ አባታችን የገዳሙ አስተዳዳሪ ይሁኑልን› ብለው ይለምኗቸዋል፡፡ እሳቸውም ‹በፍጹም! እኔ ጾምና ጸሎት እንጂ አስተዳደር አልችልም› ብለው እምቢ ይላሉ፡፡ ካህናቱ እና ምዕመኑም ተስፋ ሳይቆርጡ በጳጳሳት ያስለምኗቸዋል፣ እሳቸውም በአቋማቸው ጸንተው እምቢ ይላሉ፡፡ ከዚያም በፓትሪያርኩ ቢለመኑ አሁንም እምቢ አሉ፡፡ በመጨረሻ በንጉሱ ተጠይቀው እና ተለምነው አስተዳዳሪነቱን ለመያዝ ቻሉ፡፡
  ነገር ግን ከአንድ ዓመት በኋላ እርሳቸው እንዳሉት ማስተዳደር ሳይችሉ ቀሩ እና ከፍተኛ የአስተዳደር ጉድለትና ብጥብጥ ነገሰ፡፡ ያ እርሰዎ ካላስተዳደሩን ሞተን እንገኛለን ያላቸው ካህናት እና ምዕመን አሁን ደግሞ ‹አባታችን ማስተዳደር አልቻሉም እና ስልጣንዎን ይልቀቁ› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም ‹ እናንተ ምን አግብቷችሁ ነው አልሾማችሁኝ!› ብለው እምቢኝ አሉ፡፡ በጳጳሳት ቢለመኑ፣ በፓትርያርኩ ቢጠየቁ አሁንም እምቢ አሉ፡፡ . . .
  በመጨረሻ ንጉሱ በቃ ስልጣን ልቀቁ እና እርሰዎ እንደቀድሞው በጾምና በጸሎት ተግተው ለእኛም አምላካችንን ለምኑልን ቢሏቸው አሁንም የመልዕክተኞችን ቃል አላምንም አልቀበልም አሉ፡፡ በመጨረሻም፣ ወታደር ተልኮ በግድ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ተደርጓል፡፡ ( አንዴ ስልጣንን አለመቅመስ ነው እንጂ ከቀመሱ በኋላማ ያሳውራል፡፡)

  ReplyDelete
 51. betam des yilal. dink eyita. Egziabher yibarkh.

  ReplyDelete
 52. dani you know yeleben yenefsen selmtenager ewenet yemesemaw kante selehone egziabher selam ene tena yesetehe wondem
  አፋችን እግዚአብሔርን ይጠራል ልባችን ግን ክዷል፡፡ የሚያስፈልገን መሪ vምሕረት ነው፡፡ምድራችን ፍቅርን ጥለው ጥላቻን፤ ይቅርታን ትተው በቀልን ያረገዙ ምስኪኖች ወድቀውባታል፡፡ አንዱ አንዱን ለሞት የሚፈልግበት ሰዋዊ ሥርዓት ነግሶባታል፡፡

  ReplyDelete
 53. d/dani you are the one who have a wonderful view that the so called intellectuals don't have i like you observation
  god bless you dear brother !
  አፋችን እግዚአብሔርን ይጠራል ልባችን ግን ክዷል፡፡ የሚያስፈልገን መሪ vምሕረት ነው፡፡ምድራችን ፍቅርን ጥለው ጥላቻን፤ ይቅርታን ትተው በቀልን ያረገዙ ምስኪኖች ወድቀውባታል፡፡ አንዱ አንዱን ለሞት የሚፈልግበት ሰዋዊ ሥርዓት ነግሶባታል፡፡

  ReplyDelete
 54. ውረዱ፣ ልቀቁ ምናምን አትበሉ፡፡ እዚህ ሀገር ‹ውረድ› የሚባለው ዛፍ ላይ የወጣ ሰው፣ ‹ልቀቅ› የሚባለው ሰይጣን የያዘው ሰው ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰሞን ተንጫጭቶ ለሚረሳ ሕዝብ መውረድና መልቀቅን ምን አመጣው፡፡ ገና የባሰ ነገር ታያላችሁ፡፡ thnx daneil.

  ReplyDelete
 55. All True Ethiopians are dead!!!

  ReplyDelete
 56. በአንዲት መንደር ሃያ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የሚመሠረተው ለምንድን ነው? ሁሉም ሊቀመንበር መሆን ስለሚፈልግ አይደለም እንዴ?

  ReplyDelete
 57. እነሱ አንድን ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ሌላውን የሚያርዱ እርኩሳን መናፍስት ናቸው፡፡
  -ደርግን ለማስጠላት የሃውዜንን ጭፍጨፋ ያቀነባበሩ
  -ኦነግን ለመደምሰስ የአማራን ህዝብ ማረድ…
  እነሱ መውረድ ሳይሆን መጥፋት አለባቸው፤ከሰለጠነው አለም ጋር የተጋጩ ናቸውና

  ReplyDelete