ይላል፡፡ ወደ ውስጥ ስትዘልቁ አንድ ከትከሻቸው ደልደል፣ ከመልካቸው ጠየም፣ ከቁመታቸው መካከለኛ የሆኑ ሰው ታገኛላችሁ፡፡ ሰውዬው የተማሩት የአካውንቲንግ ሞያ ነው፡፡ ጭላሎ አግሪካልቸራል ደቨሎፕመንት ዩኒት ከተባለ ተቋም ነበር በዲፕሎማ የተመረቁት፡፡ መጀመሪያ የሐረርጌ ክፍለ ሀገር ኦዲተር፣ ከዚያም የሐረሪ ክልል ሲመሠረት የክልሉ ዋና ኦዲተር ሆነው ሠርተዋል - ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ፡፡
የሐረር ሰውም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን እኒህን ሰው የሚያውቃቸው በአካውንታንትነታቸውም
ሆነ በኦዲተርነታቸው አይደለም፡፡ እርሳቸው ከዚያም በላይ ከብረዋል፤ ከዚያም በላይ አገልግለዋል፣ ከዚያም በላይ ታምነዋል፣
ከዚያም በላይ በሕዝቡ ልብ ውስጥ ነግሠዋል፡፡
አብዱላሂ ሸሪፍ በታሪካችን መጥፋት፣ በቅርሶቻችን መበላሸትና ሳይሰበሰቡ ባክነው
መቅረት፣ ትውልዱም ታሪኩንና ባህሉን የሚያውቅበት ዕድል ሳይፈጠርለት በመቅረቱ ያዝናሉ፡፡ እንደብዙዎቻችን ግን አዝነው ብቻ
አልቀሩም፡፡ የሺ ኪሎ ሜትር ጉዞ በአንድ ርምጃ ይጀመራል፤ የብዙ ዓመታት ገድል በአንዲት ሰዓት ይወጠናል ብለው አሰቡ፡፡
የአካባቢውን ሕዝብ ቅርሶች፣ ባህላዊና የወግ ዕቃዎች፣ መጻሕፍትና መዛግብት፣ ሥዕሎችና ፎቶዎች፣ ሙዚቃዎችና አልባሳት መሰብሰብ
ጀመሩ፡፡ አንዳንዱን በልግሥና ያገኛሉ፤ ሌሎቹን ምግብ እየተውም ቢሆን ይገዛሉ፡፡ ቤታቸው ከ1980ዎቹ መጀመሪያ አንሥቶ
በቅርሶች፣ ባህላዊና የወግ ዕቃዎች መሞላት ጀመረ፡፡
‹‹የዛሬ 23 ዓመት ራስን ማጣት የፈጠረብኝ ቁጭት ነው መነሻዬ›› ይላሉ አብዱላሂ
ሸሪፍ፡፡ ይህንን ቁጭት አብዱላሂ ሸሪፍ ‹የማንነት ነውጥ› ሲሉ ይጠሩታል፡፡ ‹ታሪክ እያለህ፣ ባህል እያለህ፣ ቅርስ እያለህ፤
ለዚህ ደግሞ በቂ ማስረጃ እያለህ ግን እንደሌለህ ስትቆጠር አትናደድም፣ አታብድም›› ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ‹‹ማንነትህ ሲፈተን
ምን ይሰማሃል?›› ይሉና ተጠያቂውን አፍጥጠው ያያሉ፡፡ አስተያየታቸው ልቡናን ሠርሥሮ ይገባና የደም ዝውውርን ሊያቆም
ይዳዳዋል፡፡ ‹‹የምትፈተነው ስለሌለህ አይደለም፣ የምትፈተነው ያለህን ማቅረብ ባለመቻልህ ብቻ ነው፡፡ ለፈተና ያቀረበን
የታሪክና የቅርስ ድህነታችን አይደለም፤ ለፈተና ያቀረበን ስንፍናችን ነው፡፡ ይህን ስንፍናችንን ማስወገድ ከቻልን የምናቀርበው
ሞልቶናል›› ይላሉ ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ፡፡
አብዱላሂ ሸሪፍን ሙስሊም ክርስቲያኑ ያምናቸዋል፡፡ ቅርሱንና የወግ ዕቃውን አደራ ብሎ
የሚሰጠው ለእርሳቸው ነው፡፡ እንደ ወርቅ ተፈትነው ያለፉ ሰው ናቸው፡፡ አደራ የምይነኩ፡፡ ቃልን የማይበሉ፤ ለምድር ለሰማይ
የከበዱ፡፡ ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ ለ17 ዓመታት በቤታቸው ነበር ቅርሶችን፣ የወግና የባህል ዕቃዎችን ይሰበስቡ የነበሩት፡፡
መጀመሪያ ከመደበኛ ሥራቸው ጋር ጎን ለጎን ነበር የሚሠሩት፣ከ12 ዓመታት ወዲህ ግን ይኼው ሆኗል ሥራቸው፡፡ ‹‹የምሠራው
ለገንዘብ ብዬ አይደለም፤ ከማገኘው ይልቅ ለቅርሶቹ የማወጣው ይበልጣልና፡፡ የምሠራው ለእርካታ ነው፡፡ የኔ ዋናው ጥያቄ ምን
አገኛለሁ? አይደለም፤ ዛሬ ማታ ምን እሠራለሁ? ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሥራዬን የምሠራው ማታ ማታ ነው፡፡ በሚያልፍ ምድር
የማያልፍ ሥራ እየሠራሁ መሆኔን ለራሴ እነግረዋለሁ፣ በየጊዜው ራሴን አሳምነዋለሁ፡፡ ልጄ አንተም የኅሊና ርካታ የማታገኝበትን
ሥራ አትሥራ፡፡ የማይረካበትን ሥራ የሚሠራ እንስሳ ብቻ ነው፡፡ እንስሳ የታዘዘውንና ሌሎችን የሚያስደስተውን ብቻ ነው የሚሠራው፤
አንተ ግን የሚያረካህንና ስታስበው ነፍስህን የሚያስደስታትን ነው መሥራት ያለብህ›› ይላሉ ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ ሲመክሩ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ከ1200 በላይ ጥንታውያን መጻሕፍትን፣ ከ400 ሰዓት በላይ የድምጽ
ቅርሶችን፣ ጥንታውያን ሳንቲሞችን፣ ከመካከለኛው ዘመን ጀምረው የነበሩ የጦር መሣርያዎችን፣ ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ እድሜ
ያስቆጠሩ ፎቶዎችን፣ የሐረርን የንግድ ግንኙነት የሚያሳዩ ሳንቲሞችን፣ መዛግብትን፣ የወግ ዕቃዎችን ሰብስበዋል፡፡ እነዚህ
ቅርሶች በዋናነት የሐረሪ፣ የአርጎባ፣ የአማራ፣ የኦሮሞና የጉራጌ ቅርሶች ናቸው፡፡ በሐረርና አካባቢው በተደረጉ ቁፋሮዎች
የተገኙ መስቀሎች፣ የአንገት ማተቦች፣ የነገሥታት ማኅተሞች በአብዱላሂ ሸሪፍ ሙዝየም ውስጥ አሉ፡፡ እንዲያውም ከ100 ዓመት
በላይ እድሜ ያለው መጽሐፍ ቅዱስም አሳይተውኛል፤
ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ
መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ለጎብኚዎች፣ ለአጥኚዎችና ለሚዲያ ሰዎች መረጃ የሚሰጥበትን መንገድም አመቻችተዋል፡፡ ለዚህም ነበር
በመኖሪያ ቤታቸው የመጀመሪያውን ሙዝየም በራሳቸው ወጭ የከፈቱት፡፡ በቤታቸው ውስጥ ለ17 ዓመታት ሲሠሩ ቆዩ፡፡ በ1990/91
ዓም የሼክ ሸሪፍ መኖሪያ ቤት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግለሰብ የቅርስ ስብስብ ሥፍራ ተብሎ በመመዝገብ ወደ ‹‹ሸሪፍ የግል
ሙዝየም›› ተለወጠ፡፡ የክልሉ መንግሥትም የአብዱላሂ ሸሪፍን ጥረት ሲያይ በቅርስነት የተመዘገበውን የራስ ተፈሪ (ዐፄ ኃይለ
ሥላሴ) ቤት ሰጣቸው፡፡ ዛሬ በቦታው ‹ሸሪፍ የሐረር ከተማ ሙዝየም›› የሚባል ታላቅ ሙዝየም ከፍተዋል፡፡
ቅርሱን በማሰባሰብ፣ በመመዝገብና በመጠበቁ ሥራ የሼክ አብዱላሂ ቤተሰብ በነቂስ ነው
የሚሳተፈው፡፡ ለዚያውም ከመሥዋዕትነት ጋር፡፡ ‹‹ሦስቱ ልጆቼና ባለቤቴ እነዚህን ዘመን የተጫናቸውን መዛግብት ሲያገላብጡ
የአስም ሕመምተኞች ሆነዋል፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን ሥራውን አላቋረጥንም›› ይላሉ በኩራት፡፡
አብዱላሂ ሸሪፍ በተለይም ጥንታውያን የብራና መጻሕፍትን፣ መዛግብትን፣ ፎቶዎችንና
ሥዕሎችን ወደ ዲጂታል ቅጅ የመገልበጡን ሥራም እያከናወኑት ነው፡፡ ‹‹ጎብኚዎችና ተመራማሪዎች ቅርሶቹንና መዛግብቱን ሳይጎዱ
የሚፈልጉትን መረጃ በቀላሉ ያገኛሉ፡፡ ከዚህም በላይ ዋናው ቅጅ ቢጠፋ በውስጡ ያለውን ነገር ለታሪክ ማቆየት ይቻላል፡፡
ቢዘረፍም ቅጅውን በማስረጃነት በመያዝ ለመከራከርም ይመቻል›› ይላሉ- ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ፡፡
ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ ‹‹አባቶችችን ለመሥራት ያልደከሙትን እንዴት እኛ ለመጠበቅ
ይደክመናል› የሚለው ሃሳብ ቀንና ሌሊት እንዲተጉ አድርጓቸዋል፡፡ እርሳቸው ለመሰብሰብ፣ ለመመዝገብ፣ ዲጂታል ለማድረግና
ለማሳየት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ታሪክን ለመተንተን፣ ለማስረዳትና በቀላል ቋንቋ ለመግለጥም የታደሉ ናቸው፡፡ እርሳቸውን
ማነጋገር የጀመረ ሰው ቀጠሮውን ይሠርዛል፤ የቆመ ይቀመጣል፤ የሄደ ተመልሶ ይመጣል፤ ማዳመጥ የጀመረ ማስተዋሻና መቅጃ ማውጣት
ይቀጥላል፡፡ መተረክ ይችሉበታል፤ ቁጭት መፍጠር ያውቁበታል - የሐረር የታሪክ አባት- አብዱላሂ ሸሪፍ፡፡
ከሠርጸ ፍሬ ስብሐት ጋር ጉብኚታችንን ፈጽመን ልንወጣ ስንል አብዱላሂ ሸሪፍን እንዲህ
ብዬ ጠየቅኳቸው ‹‹አሁን ይህንን ቅርስ ይሽጡልኝ የሚል አካል ቢመጣ ምን ይሉታል››
ቆጣ አሉ፡፡
‹‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት
አልችልም››
‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም››
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመጀመሪያ ለአንተ በሀገርም ይህን በሀይማኞት በመታበረክተው ጠቃሚ ጽሁፎች ያለኝ አክብሮት የላቀ ነው፡፡እግዝኣብሄር ረጅም ዕድሜና ጤና እንዲሰጥህም እመኛለሁ፡፡
Deleteይህ ጽሁፍ ልጽፍ የተገፋፋሁት አንድም ከሀይማኖት አስተማሪነትህና በጡማሪህ በሚትጽፋቸው ጽሁፎች ውስጥ አስተያየቶች በተጨማሪም በሚድያ በምትሰጠው ማብራሪያና አንዲሁም እኔ የተወለድኩበት አካባቢ ያለው ባህላዊና ሀይማኖታዊ ቅርሶች ማንም በጥልቀት ያልዳሰሳቸውና ያልታፈላቸው እንዲሁም ካለኝ ግንዛቤ በአንተ በኩል በጥልቀት ምስትራቸው ታወጣዋለህ የሚል ግላዊ አስተሳሰብና እምነትም ስላለለኝ ነው ለአንተ ጥያቄ ያቀረብኩት፡፡
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አንድ ነገር ግን ላሰታውስህ ምፈልገው ነገር አለኝ ፡-በራያ ኦፊላ ደጋማው እና ቆላማው ለምሳሌ ያህል በኣላማጣና መኾኒ አካባቢ ዙርያቸው የሚገኙ ትላልቅ ሀይማኖታዊ ቅርሶች አሉ በተጨማሪም የህዝቡ ያልተነካ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ባህል አለ፡፡ይህን ለክልሉ፤ለሀጋረችንና ለዓለም ማህበራዊ፤ኢኮኖሚያ፤ባህላዊ፤አካባቢያዊና ሀይማኖታዊ ጠቄሜታ እንዲያበረክት የአንተ ትልቅ ድርሻ እንዲኖር ከፍተኛ ፍላጎት አለኝ፡፡የሀሸንጌ ባህር አፈጣጠር ከሀይማኖታዊ ጋር የተያያዘ ነው የሚል አለ ይህም ብጠና ጠሩ ነው፡፡ሌላው የማይጨው ጦርነት በተካሄደበት ወቅት በውግያው ምክንያት የሞቱ ጣሊያኖች በዚሁ ሐይቅ አካባቢ አለ፡፡ታላቅ የህጉምብርዳ ደንም በዚሁ ይገኛል፡፡በቆላውም አካባቢ ታርካዊና ባህላዊ ቅርሶች አሉ ፡፡ አንድ የሚያስደንቀኝ ነገር አለ በአላማጣ ደብረ ኢየሱስ ቤተክሪስትያን የሚኖሩ ትልቅ ባህታዊ አባት አሉ አባታችም ትልቅ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ እንህ ትልቅ አባት ሽምግለዋል ስለሆነም ከአባታችን ለሀገርም ይሁን ለዓለም መተላላፍ የሚገቡ ምስጥራዊ ሀይማኖታዊና ትፉታዊ አሉ ብየ እገሚታለሁ እሳቸውን አግኝቶ ማነጋገርም ትልቅ ለጥናትህ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡አንድ ሁሉም እምያስገርመኝ ነገር ኣላማጣ ከተማ አካባቢ ሓሸያ ማርያም የሚትባል ቤተክርስያን አለች ሓሸያ ማርያም ተብሎ ይጠራል ትልቅ አስተርዮ ማሪያም በዓል ይከበራል፡፡እቺ ቤቴክርስትያን አካባቢውም ስለሆነም ይህ ሀሳቤ ተቀብለህ እስከ አሁን ያልተዳደሰሱ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች ሁሉም እንዲያውቃቸውና የበለጠ ጥቅም እንዲውሉ እንዲታደርግ በእግዛብሄር ስም እጠይቅሀለሁ፡፡
በአጻጸፌና በቃላት አጠቃቀሜ ስህተት ልኖረኝ ይገባል ይህም የተሳሰተውን በማረም ይለቁን ጠቀሚውን ፊሬ ሃሳብ ተረዳናለህ የሚል ሀሳብ በመጨመር ይህ የተየቅሁህ ጥያቄ እንደ አንድ ተራ ሰው አይተህ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን ዕድገትም ይሁን ባህላዊና ሀይማኖታዊ ጠቄሜታ እንዲሁም ለአንተ ለሚታደርገው ሁለተናዊ ምርምርና ጥናት ጥሩ ለየት ያለ ግብዓት ታገኝበታለህ የሚል ሀሳብም አለኝ፡፡
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመጀመሪያ ለአንተ በሀገርም ይህን በሀይማኞት በመታበረክተው ጠቃሚ ጽሁፎች ያለኝ አክብሮት የላቀ ነው፡፡እግዝኣብሄር ረጅም ዕድሜና ጤና እንዲሰጥህም እመኛለሁ፡፡
ይህ ጽሁፍ ልጽፍ የተገፋፋሁት አንድም ከሀይማኖት አስተማሪነትህና በጡማሪህ በሚትጽፋቸው ጽሁፎች ውስጥ አስተያየቶች በተጨማሪም በሚድያ በምትሰጠው ማብራሪያና አንዲሁም እኔ የተወለድኩበት አካባቢ ያለው ባህላዊና ሀይማኖታዊ ቅርሶች ማንም በጥልቀት ያልዳሰሳቸውና ያልታፈላቸው እንዲሁም ካለኝ ግንዛቤ በአንተ በኩል በጥልቀት ምስትራቸው ታወጣዋለህ የሚል ግላዊ አስተሳሰብና እምነትም ስላለለኝ ነው ለአንተ ጥያቄ ያቀረብኩት፡፡
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አንድ ነገር ግን ላሰታውስህ ምፈልገው ነገር አለኝ ፡-በራያ ኦፊላ ደጋማው እና ቆላማው ለምሳሌ ያህል በኣላማጣና መኾኒ አካባቢ ዙርያቸው የሚገኙ ትላልቅ ሀይማኖታዊ ቅርሶች አሉ በተጨማሪም የህዝቡ ያልተነካ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ባህል አለ፡፡ይህን ለክልሉ፤ለሀጋረችንና ለዓለም ማህበራዊ፤ኢኮኖሚያ፤ባህላዊ፤አካባቢያዊና ሀይማኖታዊ ጠቄሜታ እንዲያበረክት የአንተ ትልቅ ድርሻ እንዲኖር ከፍተኛ ፍላጎት አለኝ፡፡የሀሸንጌ ባህር አፈጣጠር ከሀይማኖታዊ ጋር የተያያዘ ነው የሚል አለ ይህም ብጠና ጠሩ ነው፡፡ሌላው የማይጨው ጦርነት በተካሄደበት ወቅት በውግያው ምክንያት የሞቱ ጣሊያኖች በዚሁ ሐይቅ አካባቢ አለ፡፡ታላቅ የህጉምብርዳ ደንም በዚሁ ይገኛል፡፡በቆላውም አካባቢ ታርካዊና ባህላዊ ቅርሶች አሉ ፡፡ አንድ የሚያስደንቀኝ ነገር አለ በአላማጣ ደብረ ኢየሱስ ቤተክሪስትያን የሚኖሩ ትልቅ ባህታዊ አባት አሉ አባታችም ትልቅ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ እንህ ትልቅ አባት ሽምግለዋል ስለሆነም ከአባታችን ለሀገርም ይሁን ለዓለም መተላላፍ የሚገቡ ምስጥራዊ ሀይማኖታዊና ትፉታዊ አሉ ብየ እገሚታለሁ እሳቸውን አግኝቶ ማነጋገርም ትልቅ ለጥናትህ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡አንድ ሁሉም እምያስገርመኝ ነገር ኣላማጣ ከተማ አካባቢ ሓሸያ ማርያም የሚትባል ቤተክርስያን አለች ሓሸያ ማርያም ተብሎ ይጠራል ትልቅ አስተርዮ ማሪያም በዓል ይከበራል፡፡እቺ ቤቴክርስትያን አካባቢውም ስለሆነም ይህ ሀሳቤ ተቀብለህ እስከ አሁን ያልተዳደሰሱ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች ሁሉም እንዲያውቃቸውና የበለጠ ጥቅም እንዲውሉ እንዲታደርግ በእግዛብሄር ስም እጠይቅሀለሁ፡፡
በአጻጸፌና በቃላት አጠቃቀሜ ስህተት ልኖረኝ ይገባል ይህም የተሳሰተውን በማረም ይለቁን ጠቀሚውን ፊሬ ሃሳብ ተረዳናለህ የሚል ሀሳብ በመጨመር ይህ የተየቅሁህ ጥያቄ እንደ አንድ ተራ ሰው አይተህ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን ዕድገትም ይሁን ባህላዊና ሀይማኖታዊ ጠቄሜታ እንዲሁም ለአንተ ለሚታደርገው ሁለተናዊ ምርምርና ጥናት ጥሩ ለየት ያለ ግብዓት ታገኝበታለህ የሚል ሀሳብም አለኝ፡፡
Yetewedik Deacon Daneal melkam sira yeseru sewochin tarik minim leyunet sataderg endnawekachew silmtaderg geta yibarkih.
ReplyDeleteGod bless you Deacon Daneal I now so many things from your blog.
ReplyDeleteBravo Shehu!!‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም›› Thanks Danny for your great effort!!
ReplyDeleteእኔ የማየት እድሉ አጋጥሞኛል:: ያዩትን ነገር ሌላ ሰው አሳምሮ ሲነግሮት እንዴት ያስደስታል::
ReplyDeleteድጋሚ ሂድ ሂድ አለኝ::
አመሰግናለሁ ዳኒ
ልጄ አንተም የኅሊና ርካታ የማታገኝበትን ሥራ አትሥራ፡፡ የማይረካበትን ሥራ የሚሠራ እንስሳ ብቻ ነው፡፡ እንስሳ የታዘዘውንና ሌሎችን የሚያስደስተውን ብቻ ነው የሚሠራው፤ አንተ ግን የሚያረካህንና ስታስበው ነፍስህን የሚያስደስታትን ነው መሥራት ያለብህ›› ይላሉ ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ ሲመክሩ፡፡
ReplyDeleteThank you Daniel you are doing good.
ReplyDeleteWoooow Dinik new
ReplyDeleteቆጣ አሉ፡፡
‹‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም››
ዳንኤል ጥሩ ትምህርት ነው አሁን ትውለዱ የጐደለው ማንነት አይደል ቆጣ ብለው
Delete" ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም " ማለታቸውስ በውስጣችን የማንነት ጥያቄ ዘር ሊዘሩብን ነው እኮ !
I really admire and thank him for his willingness and interest for keeping our wealth which has real meaning and value for all of us. But I am worried for the future and want to ask if somebody or the government carry the responsibility of taking care of the treasures. Otherwise all things done will be wasted.
ReplyDelete‹‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም››
ReplyDeleteአሪፍ አባባል ነዉ፡፡
እናመሰግናለን ዲያቆን ዳንኤል
‹‹አባቶችችን ለመሥራት ያልደከሙትን እንዴት እኛ ለመጠበቅ ይደክመናል›
ReplyDeleteበጣም ጥሩ እይታ ነው እንደዚህ አስማሪ ጽሁፎች ይቀጥሉ ትውልድ የሚቀርጹ
ReplyDelete‹‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም››
ReplyDeleteበጣም ጥሩ ታሪክ
ReplyDeletebetam tru. Yamral. Hulunm ande lematfat eyesebesebu bihons. Dani: muslimoch min endemiseru yematawk lememsel atmokr. Strategiw kebad new. 17 amet kasebut 50 amet yewodefit guzo tnshu new.
ReplyDeleteI will visit it and tell to others what esteemed man has done.
ReplyDeleteአባቶችችን ለመሥራት ያልደከሙትን እንዴት እኛ ለመጠበቅ ይደክመናል› thanks my dear ,it is really interesting ...
ReplyDeleteእንደ ወርቅ ተፈትነው ያለፉ ሰው ናቸው፡፡ አደራ የምይነኩ፡፡ ቃልን የማይበሉ፤ ለምድር ለሰማይ የከበዱ wow real man
ReplyDeleteበሚያልፍ ምድር የማያልፍ ሥራ እየሠራሁ መሆኔን ለራሴ እነግረዋለሁ፣ በየጊዜው ራሴን አሳምነዋለሁ፡፡ ልጄ አንተም የኅሊና ርካታ የማታገኝበትን ሥራ አትሥራ::
ReplyDeleteበሚያልፍ ምድር የማያልፍ ሥራ እየሠራሁ መሆኔን ለራሴ እነግረዋለሁ፣ በየጊዜው ራሴን አሳምነዋለሁ፡፡ ልጄ አንተም የኅሊና ርካታ የማታገኝበትን ሥራ አትሥራ፡
ReplyDelete‹‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም››
ReplyDelete‹‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም››
ReplyDeleteይህ ቅርስ ለሚሸጡ ራስ ወዳድ ሰወች ጥሩ ትምህርት ነው
ReplyDeleteThis is one of our peculiarities. Wonderful job! God bless You Dani. Amen Leykun Leykun.
ReplyDeleteMelkam tikoma new shehunim geta yabertachew egnanim libona seton maninetachinin yemniwod yadrgen.
ReplyDeleteene gin hije ayewalehu
ቆጣ አሉ፡፡
ReplyDelete‹‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም››
"እንስሳ የታዘዘውንና ሌሎችን የሚያስደስተውን ብቻ ነው የሚሠራው፤ አንተ ግን የሚያረካህንና ስታስበው ነፍስህን የሚያስደስታትን ነው መሥራት ያለብህ "
ReplyDelete"አባቶችችን ለመሥራት ያልደከሙትን እንዴት እኛ ለመጠበቅ ይደክመናል"
‹‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም››
ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ
Thank You Dn. Dani!!! I always proud of you.
Every of his words are exhilarate and inspire everyone those tries to help our country.
bravo
DeleteDani this capacity is not of yours,but of God and keep it up with him
ReplyDeleteThank you Dn Daniel for revealing such wonderful man.God bless you and your effort!!!
ReplyDeleteA hero is born among a hundred, a wise man is found among a thousand, but an accomplished one might not be found even among a hundred thousand men.Bravo Dani
ReplyDelete‹‹አባቶችችን ለመሥራት ያልደከሙትን እንዴት እኛ ለመጠበቅ ይደክመናል›
ReplyDelete‹‹አባቶችችን ለመሥራት ያልደከሙትን እንዴት እኛ ለመጠበቅ ይደክመናል›
ReplyDeleteዋው ዳንኤል ዘጣና ዳር፡-
ReplyDeleteበእርሳቸው ውስጥ የተቀመጠውን እንከንየለሽ ኢትዮጵያዊነት፣ ድንበርየለሽ አርቆ አሳቢነት አሳይተሃል፡፡ አንተም እንደዚሁ!
ማናችንም ብንሆን ደግሞ ይህንኑ ዓይነት መንገድ ለመከተል ትምህርት፣ ሃብት፣ ምናምን ወዘተ እንደማይጠይቀን፤ ያንን ዓይነት ልብ ብቻ እንደሚያስፈልገን አሳየተሃል፡፡
በርታ!
ታላቅ አባት ናቸው። እግዚኣብሔር ይባርካቸው
ReplyDeleteሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ እና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ምርጥ ኢትዮጲዊያን
‹‹ይህ ማንነቴ ነው፤ ማንነቴን አልሸጥም፤ እንደ ሰው ተወልጄ እንደ እንስሳ ልሞት አልችልም››
ReplyDeleteኢትዮፕያ እንደዚህ አይነት ሰዎቸች ነው የሚያስፈልጋት ከአክራሪ ሀይማኖተኛ ና ከትምከት የፀደዱ ሼህ ረጅም እድሜ ከጤንነት ጋር እመኝሎዎታለሁ ከዳኒ ጋር ፡፡