Friday, May 31, 2013

ፓትርያርኩ ያነሷቸው አራት መሠረታዊ ነገሮች

የዘንድሮው የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሲከፈት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ጉባኤው ሊያተኩርባቸው ብሎም ውሳኔ አሳልፎ ሊፈጽማቸው ይገባል ያሏቸውን አራት መሠረታዊ ነገሮች አንሥተዋል፡፡
1.         ብልሹ አሠራርን ማረምና ማስወገድ
2.       አስተዳደሩን በአዲስ መልክ ማዋቀር
3.       የፋይናንስ አያያዝን ማስተካከል
4.       የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን እንደገና ማዋቀር
በመጀመርያ ፓትርያርኩ ከተለመደው መወድሳዊና ቢሮክራሲያዊ ንግግር ወጣ ብለው በቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊና አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ማተኮራቸው የሚያስመሰግን ነው፡፡ ከተሰየሙ በኋላ የመጀመርያቸው በሆነው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ላይ ያቀረቡት መክፈቻ ከሁለት ነገሮች አንጻር ተገቢም ተመስጋኝም ነው፡፡
1.       ከወቅታዊነት 
ብልሹ አሠራር፣ የመዋቅር ማሻሻያ፣ የፋይናንስ ሥርዓቱን ማሻሻልና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሁኔታ በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት ላይ ቅርብ የሆነ አደጋ የደገኑ ናቸው፡፡ በተለይም ሙስና ዛሬ ዛሬ የቤተ ክህነቱ ዋና መለያ ጠባይ እየሆነ ነው፡፡ ሲሞናዊነት ቤተ ክህነቱን ጥፍንግ አድርጎ በመያዙ ከጵጵስና እስከ ዲቁና ያለው መዓርግ በገንዘብ እስከ መሰጠት ደርሷል፡፡ የደብር አስተዳዳሪነት፣ የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት፣ የመመሪያ ኃላፊነት፣ የውጭ የትምህርና የሥራ ዕድል ያለ ጉቦና መማለጃ የማይሆኑ ሆነዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ በቤተ ክህነቱ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንና አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ትርጉማቸው ተለውጦ ሰባት ሺና አምስት ሺ ብር ሆነዋል፡፡ ‹ከሐዋርያት ጋር ና› ማለት አሥራ ሁለት ሺ ብር ይዘህ ና፤ ‹ሰባው አርድዕት የሉም ወይ› ማለት ሰባ ሺ ብር ያስፈልግሃል፤ ሠላሳ ፣ ስድሳና መቶ ማፍራት ሰለሳ፣ ስድሳና መቶ ሺ ብር መስጠት ሆነዋል፡፡ ስለዚህም ፓትርያርኩ በዚህ ጉዳይ ላይ ሥር ነቀል የሆነ ለውጥ በማምጣት የሙስናንም ምንጭ ማድረቅ አለብን ማለታቸው ተገቢ ነው፡፡ 
የቤተ ክህነቱ መዋቅር ከተዘረጋ ግማሽ ማዕተ ዓመት ያለፈው፣ የመዋቅር ማሻሻያ ሲያልፍም ያልነካው፣ መምሪያዎችና ክፍሎች፣ ድርጅቶችና ተቋማት  ያለ ጥናት በአንድ ቀን ውሳኔ ሲከፈቱና ሲዘጉ የሚኖሩበት፣ ሀገሪቱ ቢፒ አር ና ካይዘንን ስትተገብር ከቦታው ያልተነቃነቀ መዋቅር ነው፡፡ ምን ያህል የሰው ኃይል አላችሁ? በምን ደረጃ የሠለጠነ የሰው ኃይል ያስፈልጋችኋል? በአንድ ደብር ስንት ሰው መኖር አለበት? ቢባል ቤተ ክህነት መልስ የለውም፡፡ ኮምፒውተር በሌለበት አጥቢያ የኮምፒውተር ጸሐፊ፣ ለአንድ አጥቢያ አራት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ፣ የአብነት ትምህርት ቤት ለሌለበት ደብር የአብነት ትምህርት ተቆጣጣሪ የሚመደበው መዋቅሩ ያልተጠና የዘመድ አሠራር የተበተበው ስለሆነ ነው፡፡

የቤተ ክህነቱ የፋይናንስ አሠራር አሁን ዓለም ከደረሰበት ሳይሆን ሀገሪቱ ከደረሰችበት እንኳን ቢመዘን ለቅርስ መቀመጥ ያለበት ነው፡፡ ያልጠፉ ሞዴላ ሞዴሎች መገኛ፣ አንዳች የአካውንቲንግ ኮርስ ያልወሰደ ሰው ሚሊዮኖችን የሚያንቀሳቅስበት፤ በዘመነ ኮምፒውተር በአሮጌ መዝገብ በሠንጠረዥ የሚሠራበት፣ ያለ በጀት ወጭ የሚፈቀድበት፤ ዕቅድና መርሕ የማይመራው፣ ለሙስና እጅግ የተጋለጠ፣ የፋይናንስ ሕግ የሌለው ቤት ነው ቤተ ክህነቱ፡፡ ቤታቸውን ከፍተው እየሄዱ ሰው ሌባ ይላሉ እንዳለቺው ሴት በሩን ለሙስና ከፍቶ ሙስናን መታገል አይቻልምና የፋይናንስ ሥርዓቱ ማሻሻያ ያስፈልገዋል መባሉ ዘገየ ይባል እንደሁ እንጂ ለምን የሚያሰኝ አይደለም፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተከፋፈለበት መንገድ ፈጽሞ ጥናት የሚጎድለው ነበር፡፡ በወቅቱ ብጹዐን አባቶች የአቡነ ጳውሎስን ሥልጣን ለመቀነስ ሲሉ ብቻ ያደረጉት ነው፡፡ አማራጭ ጥናቶች ቀርበው አልተገመገሙም እንጂ በአንድ ጉሮሮ ይገባ የነበረውን ጉቦ በአራት ጉሮሮ እንዲገባ ማድረግ ባላስፈለገ ነበር፡፡ ቢያንስ ዐሥሩን ክፍለ ከተሞች በአውራጃ ደረጃ አዋቅሮ፣ በሥራ አስኪያጅ በመምራት፣ የሥልጣን ክልላቸውን ወስኖ በመስጠት ለሕዝብ ቅርብ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባ ነበር፤ ከዚህም በላይ የሰው ኃይል ምደባና ዝውውርን በማዕከል ደረጃ በሰው ኃይል ቅጥርና ዝውውር ኮሚቴ በኩል በማየት፣ የቅሬታ ሰሚ ቦርድ በማቋቋም፣ የዘመድ አሠራሩን መቀነስ ይቻል ነበር፡፡ ከዚህም በላይ በጋራ ሊሠሩ የሚገባቸውን ጉዳዮች ለማቀናጀት እንዲቻል ሀገረ ስብከቱን በአንድ ሊቀ ጳጳስ መምራት፣ ከሊቀ ጳጳሱ ጋር የሚሠራና በጉባኤ የሚወስን ዐቢይ ኮሚቴ በማቋቋምም ውሳኔዎችን ከግል ወደ ቡድን መውሰድና ሀገረ ስብከቱን በተሻለ መምራት በተቻለ ነበር፡፡ ይህንን ሁሉ ከማድረግ ግን ሀገረ ስብከቱን ከአራት ከፍሎ አራት ሥራ አስኪያጅና ሁለት ጳጳስ በመሾም እንደ ከነዓን በዕጣ ነው ያከፋፈሏቸው፡፡ ያውም ከተመደቡት ጳጳሳት አንዱ አራት ሀገረ ስብከት የሚያስተዳድሩ ነበሩ፡፡

እነዚህ ሁሉ ችግሮች ቤተ ክርስቲያኒቱን አላላውስ ስላሏት ነው በዚህ ጊዜ ለመፍትሔው እንነሣ ብለው ፓትርያርኩ ማቅረባቸው ወቅታዊ ነው የምንለው፡፡
  1. የግድ ነው
ለሌላው አርአያ ትሆናለች ተብላ የምትጠበቅ ቤተ ክህነት እርሷ ራሷ በችግር መጠቀስ የለባትም፡፡ ከዚህ በፊት የፍትሕ አካላቱ ቤተ ክህነትን የሚመለከቱ ክሶች እየበዙ መምጣታቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ማሳሰቢያ ሰጥተው ነበር፡፡ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንም ከሚደርሱት አቤቱታዎች አብዛኞቹ ቤተ ክህነቱን የሚመለከቱ መሆናቸው ይሰማል፡፡ የቤተ ክህነቱ ግቢም ሥራ በሚሠሩ ሰዎች ሳይሆን አቤቱታ ይዘው ከመላዋ ሀገሪቱ በሚመጡ ባለጉዳዮች የተሞላ ነው፡፡ በየአጥቢያውም ተአምርና ገድል ሳይሆን የገንዘብ መበላት፣ የቦታ መሸጥ፣ የዘመድ ቅጥር፣ የሙዳየ ምጽዋት መሰረቅ ሆኗል የሚሰማው፡፡ በአዲስ አበባና በታላላቅ ከተሞች የሚገነቡትን ሕንጻዎች የሚያጠና ቢኖር ከቤተ ክህነቱ ጋር በተያያዙ ሰዎች የሚገነቡት የአንበሳው ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡
ይህን ሁሉ ይዞ ወንጌለ መንግሥትን መስበክ፣ የነፍስ ድኅነትን ለማምጣት መሮጥና ሐዋርያዊ አገልግሎት መፈጸም የማይታሰብ ነው፡፡ በቤተ ክህነቱ የሚከበሩትና የሚፈሩት፣ ሰው የሚፈልጋቸውና የሚሟሟትላቸው መምሪያዎች ከገንዘብ ጋር የተነካኩትን እንጂ ከስብከት፣ ከክህነት፣ ከሊቃውንት ጉባኤ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤት፣ ከገዳማት ጋር የተያያዙትን አይደለም፡፡ ዋናው የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልዕኮ የሚያስፈጽሙት መምሪያዎች፣ የቅጣት ቦታዎች ሆነዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ እገሌ በሊቃውንት ጉባኤ ተመደበ ማለት የዕውቀት ማሳያ ሳይሆን ‹ተወረወረ› ማለት ሆኗል፡፡
የሬዲዮና የጋዜጣ፣ የመጽሔትና የፊልም ጀማሪ የነበረች ቤተ ክህነት ሚዲያዋን ሁሉ ዘግታ ዘግታ ዛሬ ሕዝብ የማያውቃቸው፣ ሕዝቡንም የማያውቁ ሚዲያዎችን ይዛ ቀርታለች፡፡ ስንት አጥቢያ አለሽ? ስንት ምእመን አለሽ? ስንት ካህን አለሽ? ስንት ገዳም አለሽ? ስትባል ቤተ ክህነት በግምት ነው የምትናገረው፡፡ ዛሬ ምእመኑ ጥያቄውን የሚመልስለት አባት ይፈልጋል፡፡ በቤተ ሰብ ምጣኔ፣ በልጆች አስተዳደግ፣ በትዳር ጉዳዮች፣ ከአዳዲስ አስተሳሰቦች አንጻር በመጡ ማኅበራዊና ሳይንሳዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ አለው፡፡ በዚህ ዘመን ቢሮ የሚቀመጡ፣ መንበረ ጵጵስናቸው ውስጥ መኖራቸው ሳይታወቅ ዓመት የሚያሳልፉ አባቶችን ሳይሆን እንደ እረኛው ከበጎች ጋር የሚሆኑ አባቶችን ሕዝቡ ይፈልጋል፡፡
ታድያ ይህንን ሁሉ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ይዞ ከመጓዝ በላይ ምን አሳዛኝ ነገር አለ፡፡ የግድ ነው፤ ቤተ ክህነት የግድ ነው፤ ራሷን መፈተሽ፣ ራሷን ማረምና ራሷን ማንቃት አለባት፤ በጊዜ ካልታከመች በሽታው ገዳይ ነው፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ የራሱን መዋቅርና አሠራር ከማስተካከል፣ በሊቃውንትና በባለሞያዎች የሚታገዝበትን መንገድ ከመፍጠር፣ ውሳኔዎቹን የሚያስፈጽምበትን ዐቅምና አሠራር ከመዘርጋት መጀመር አለበት፡፡ ዛሬ ሁሉን ዐውቃለሁ የሚባልበት ጊዜ አይደለም፡፡ አዲሱ የሮማው ፓፓ ስምንት አማካሪዎችን በቅርቡ የሾሙት የዓለምን ሂደት ተገንዝበውት ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቃውንት መደገፍ አለበት፡፡ ሃሳቦች በአንድ ቀን ጉባኤ ተጀምረው ማለቅ የለባቸውም፡፡ አስቀድሞ በሊቃውንትና በባለሞያዎች የተመከረባቸው መሆን አለባቸው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የለውጡን ሥራ ከራሱ በመጀመር ለሌሎች አርአያ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡‹ ባለ መድኃኒት ሆይ…› እንዲል፡፡
አሁን በፓትርያርኩ የቀረቡትን ሃሳቦች ቅዱስ ሲኖዶሱ መሠረት ያለው፣ ለምእመኑ ተስፋ የሚፈነጥቅና የነገውን መንገድ የሚያቀና ውሳኔ ያሳልፍባቸዋል፤ አፈጻጸማቸውም ከወረቀት ይዘላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ችግሮችን አፍረጥርጦ መፍታት እንጂ እንደ ቆጵሮስ በጎን አልፎ መሄድ መድኃኒት አይሆንም፡፡ ያለበለዚያ ግን ፓትርያርኩ እንዳሉት ‹በሁላችንም ላይ ታሪክና እግዚአብሔር ይፈርዱብናል፡፡›

62 comments:

  1. Thank you Danial for your critical comments. My suggestion with this regard is that the church has to be very careful when assigning people on the administration sections. What we are observing at this day is that most administrators of the churches are becoming supporters of the political party and can do what they want to do including corruption. When the community around the church request for investigation, no one (including the synods)can respond. So the synods has to be curios and we all need to be carefully and do what is expected from all of us. This days the church heads are becoming politicians and supporters of political party. and I am not sure how this was happened

    ReplyDelete
  2. we will thank you the Synods when it will implement his decision..........b/c there are allot of decision made before but not practical.........Any how thank you Dani!

    ReplyDelete
  3. It is really good comment Dani. We will expect the SYNODOS give directions for this Corrupted decision making process.

    ReplyDelete
  4. አምላክ ሆይ መጨረሻውን አሳምርልን!!!

    ReplyDelete
  5. ዲያቆን ያነሳኸው ሀሳብ ወቅታዊ ታላቅም ነው፡፡ግን ቤተክርስቲያን አሁን ያለችበትን ሁኔታ እንዲህ በቀላሉ ይፈታሉ ብሎ ማሰብ በጣም ከባድ ነው እርሱ ባለቤቱ ይርዳቸው እንጂ፡፡በሁሉም ነገር እኮ ውል እንደሌለው ማግ ትብትብ ብላለች እርስዋ ሆናብን ተስፋ አንቆርጥ ብለን እንጂ ብዙ ለማመን የሚከብዱ ድረጊቶች ይፈፀማሉ፡፡ከተማ ላይ ያሉትን አባቶች አለም አታላቸው ለስጋቸው ሳስተው ነው ብለን ብናስብ እንካን እሺ ገዳማት ላይ የሚፈፀም ሙስናን ምን እንለዋለን ?እርሱ ይሁነን እንጂ ነገሮች ከባድ ይመስላሉ ቢሆንም ህልም ተፈርቶ -----እንደሚባለው ገና ለገና የጥቅም ተካፋዮች የሚያደርሱት ጫና ከባድ ነው ተብሎ ተፈርቶ መተው የለበትም ፡የተጠቆሙት ጉዳዮችን ለምስተካከል ማሰቡ በራሱ አንድ እርምጃ ነው እናም አባታችን ያነሱትን ለመተግበር በፀሎትም በተግባርም እኛ ልጆቻቸው ልንረዳቸው ይገባል እላለው፡፡ አምላክ ይርዳን ድንግል ማርያም ታማልደን፡፡አሜን፡፡

    ReplyDelete
  6. ዲ/ን ዳንኤል ጥሩ ብለሐል ፡፡ እንደተባለው መጀመሪያ ስንዴና እንክርዳዱ መለየት አለበት፡፡ በድረ-ገፅና በመገናኛ ብዙሃን ነጻ የምእመናን አስተያየት መስጫ መኖር አለበት፡፡ ይህንን እንደ ግብአት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ገዥ እቅድ ማውጣት፡ገንዘብ በመመደብና ባለሙያ የሆኑ አንቱ የተባሉ ምእመናንን ያካተተ ቡድኖችን በማቋቋ ስራዎች በሰፊው ተዘርግተው መሰረታዊ ለውጥ በማምጣት ችግሮችን ደረጃ በደረጃ መቅረፍ ይቻላል፡፡ አጋጣሚውን መጠቀም ብልህነት ነው፡፡ ጉዳዩን ለአባቶች ብቻ መተው አያዋጣምና ምእመናንም ሊሳተፉበት ይገባል ፡፡ ለማንኛውም እንበርታ፡፡

    ReplyDelete
  7. Dani, You are very right. There is no other choice other than solving the corruption, structural and financial management problem of EOTC.

    ReplyDelete
  8. I think, the new father is starting strategic issues very well. Let God will be with him and with all of us for the achievement of the plan

    ReplyDelete
  9. it is really z agendas are critical, the managers changes the priests from one church to another with out considering their family,rent house, school... zey always think abt z money. even the department heads are worked zer for a long time, zey are not ready for change zer are thinking to prolong zer authority, i don't know what to say abt that diocese really it very painful.
    i thank u Dani

    ReplyDelete
  10. Musena BEGzABHR Bate west Ejge Asfari newe Abatu EGZBHERE hoye bathene ateda

    ReplyDelete
  11. Abatachinin EGZIABHER yibarklin.

    ReplyDelete
  12. Tehadso and ajenda mehon neberebet. Yalew chigr hulu endibabas yemiyadergew awkewm hone sayawku tehadso aramaji behou leboch new. Hon blew betekrstiyanun masedebna mawared blom mastelat almachew silehone. Abune matias tru abat yimeslalu_yargln. Amen.

    ReplyDelete
  13. አምላክ ቤቱን ያፀዳል

    ReplyDelete
  14. God be with you. God bless our church!

    ReplyDelete
  15. wektawi ena tegebi yehone tsihuf new dn Daneal berta

    ReplyDelete
  16. ፓትርያርኩ እንዳሉት ‹በሁላችንም ላይ ታሪክና እግዚአብሔር ይፈርዱብናል፡፡›

    ReplyDelete
  17. ፓትርያርኩ እንዳሉት ‹በሁላችንም ላይ ታሪክና እግዚአብሔር ይፈርዱብናል፡፡›

    ReplyDelete
  18. በቤተ ክህነቱ የሚከበሩትና የሚፈሩት፣ ሰው የሚፈልጋቸውና የሚሟሟትላቸው መምሪያዎች ከገንዘብ ጋር የተነካኩትን እንጂ ከስብከት፣ ከክህነት፣ ከሊቃውንት ጉባኤ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤት፣ ከገዳማት ጋር የተያያዙትን አይደለም፡፡ ዋናው የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልዕኮ የሚያስፈጽሙት መምሪያዎች፣ የቅጣት ቦታዎች ሆነዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ እገሌ በሊቃውንት ጉባኤ ተመደበ ማለት የዕውቀት ማሳያ ሳይሆን ‹ተወረወረ› ማለት ሆኗል፡፡

    ReplyDelete
  19. በቤተ ክህነቱ የሚከበሩትና የሚፈሩት፣ ሰው የሚፈልጋቸውና የሚሟሟትላቸው መምሪያዎች ከገንዘብ ጋር የተነካኩትን እንጂ ከስብከት፣ ከክህነት፣ ከሊቃውንት ጉባኤ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤት፣ ከገዳማት ጋር የተያያዙትን አይደለም፡፡ ዋናው የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልዕኮ የሚያስፈጽሙት መምሪያዎች፣ የቅጣት ቦታዎች ሆነዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ እገሌ በሊቃውንት ጉባኤ ተመደበ ማለት የዕውቀት ማሳያ ሳይሆን ‹ተወረወረ› ማለት ሆኗል፡፡

    ReplyDelete
  20. ዛሬ ምእመኑ ጥያቄውን የሚመልስለት አባት ይፈልጋል፡፡ በቤተ ሰብ ምጣኔ፣ በልጆች አስተዳደግ፣ በትዳር ጉዳዮች፣ ከአዳዲስ አስተሳሰቦች አንጻር በመጡ ማኅበራዊና ሳይንሳዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ አለው፡፡ በዚህ ዘመን ቢሮ የሚቀመጡ፣ መንበረ ጵጵስናቸው ውስጥ መኖራቸው ሳይታወቅ ዓመት የሚያሳልፉ አባቶችን ሳይሆን እንደ እረኛው ከበጎች ጋር የሚሆኑ አባቶችን ሕዝቡ ይፈልጋል፡፡

    ReplyDelete
  21. Patriarku rasachewm honu bituan papasat yehenin tsehuf yanebutal yemil gimit alegn chigirochin becha yemiyawesa sayehon mefetehewochinim chimir yemitekum bemehonu malefia tsehuf new gin Ethiopia kalew ye internet ageligelot amechi kalemehon antsar belogehin mayet layechilu selemichil endeh ayenet wektawina teqami melieketochihin le sinodosu adress aderigeh maderes betichil min yimesileha???lemanegnawem egziabeher yagizen!!!!

    ReplyDelete
  22. adisu patriarch sile waldiba gedam mn mefithe ametu yihon? new woynis kemengist gar honew.... hu hu hu! endaw eko yigermal hulu neger....

    ReplyDelete
  23. Aba TekleHaimanotJune 3, 2013 at 5:06 AM

    Sir,

    How about the suffering of the Waldeba monks and nuns who were evicted by the racist TPLF Weyane from the monastery? How about the undue interference of the regime in religious affairs? How about the recently proposed government regulation of religious organizations? Is this not timely or deserving to be an agenda item? My conscience tells me that they should be among the top agendas, and any reasonable person would agree with me.

    All the accomplices of the weyane junta will face the deserving justice from the Almighty God and the Ethiopian people when the time comes both on earth and in heaven. Make no mistake about it. We will not forget all these atorocities and nor will God.

    ReplyDelete
    Replies
    1. የሰማይ አምላክን መቼ ነው የምትመጣው እያልን ስንወተውት ንቁና ጠብቁ እንዳለው አሁን መጣ ጉድ ማየት ነው መንሹን በቤቱ መጀመሩ ነው በሁላችንም ላይ ታሪክና እግዚአብሔር ይፈርዱብናል የተባለው እውነት ነው ፡፡

      Delete
  24. Dear Dn. Daniel,

    On a different note I hope you will treat us with some read on the Lebanon's findings of Ethiopia's 16th century monks. I was so surprised when I heard about it from the reporter tv this morning.

    ReplyDelete
  25. i think the problem will be easy if they fear God before everything

    ReplyDelete
  26. betme dese Yemele ekede new addisu patriarchenen egzabher yabertwo lenel yegbal Daniel yenteme asteyat endwetro ejege btme teru new bertatena Tena yestelen elaluje betref leabtoche kedus pulos yalewn lebel"atsreke yemetel ante teserklehen atmenzer yemtel ante tamenzralhe bet twote yemtsyefe ante betmekdes........." elchuluje

    ReplyDelete
  27. be betekirisitiyan sir nekel lewit bimeta be eregitenginet Ethiopia hagerachin ke addegit hagerat tewedaderalech. fetari mecereshawin yasamirew.

    ReplyDelete
  28. መቶ አለቃ ሰሎሞን በርሔ - ከ UNISFA (Sudan)June 3, 2013 at 12:45 PM

    የማር ነጋዴዋ አህያ ትዝ ትለኛለች: አህያዋ ማር ታመላልሳለች ነገር ግን አንድም ቀን ማሩን ቀምሳው ስለማታውቅ የማርን ጣፋጭነት አታውቀውም:: እኛም እኮ እንደ አህያዋ ሆነናል: ቅዱስ ወንጌሉን ከንባብ ባሻገር በምግባር ከምትገልጸው እናት ቤተ ክርስቲያን ተወልደን ይህን በመሰለው ሊጠሩት እንኳ በሚከብደው ዓለማዊ ተግባር መገኘታችን የሚያዛዝን ነው:: ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል እንዳልከው ከዐውደ ምኅረቱ አገልግሎት በፊት መቅደም ያለበት የተበለሻሹት ነገሮችን ማስተካከል ነው:: አሁን አዲሱ ፓትሪያርክ እያንጸባረቁት ያለው ሐሳብ በሙሉ ተስፋ ሰጪ ነው: ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ ይራዳቸው:: ላንተም ቢጽፉ የማይደክሙ ጣቶችንና የማይነጥፍ ብዕርን ይስጥህ:: አሜን::

    ReplyDelete
  29. All raised issues are critical. So far All church leader should sit together and discuss on it.But , Dani , as u said in Ur writing , Before we do this , intensive research and looking for better experience from other orthodox church , for instant how Egypt Coptic church is handled finical management is needed. Thank Dani

    ReplyDelete
  30. .... ዳኒ ለወደፊቱ የ81ም መጽሃፍት ማብራሪያ እንደምትጽፍ ተስፋ አለኝ ሁለቱን አቅርበህልንአል- ለውደፊቱ ለምጥስፋቸው መጽሓፍት እንደ ረፈረንስ ሊገለግሉ የሚችሉ websites ከዚህ በፊት ካላየሃቼው ጥሩ ናችኤውና ተመልከታቼው -http://good-amharic-books.com/books.php http://www.tesfayerobele.com/resources/default.aspx the websites are desighned by protestants but they have useful books,articles..dont post the comment on your wall simply read it!god bless u...

    ReplyDelete
  31. dani lilew degmo protestantoch rasaciew benewt west nachiew see this...http://www.tesfayerobele.com/docs/books_and_articles/reformation_and_change.pdf but dont post in ur wall

    ReplyDelete
  32. ‹በሁላችንም ላይ ታሪክና እግዚአብሔር ይፈርዱብናል፡፡›

    This is the word from a good mind! From typical religious father! It won't really be easy reshape (re engineer)the existing gigantic corruption and completely messed up unethical administration. Forget about money, we completely are missing our soul since we lacked the Shepperd. I am very layman so called christian. But when I see into the Church there some times are so dreadful things. Do those who are at the higher position of the church at all have religion? Big question. I started to doubt cause Egziabiher ale enkuan bilo yemiamin sim bilo tera sew enezih Yebetekristian nen yemilutin ayadergim. Bebizuwochachin duriye yemibalut enkuan keemnetachew gar beteyayaze bebizu tamagn nachew. Dn. Danial, this is a serious issue. Discussing the issue here has little value. The Patriarch needs designers? Do you have a room that key role players come together for critical analysis of the current church fact and design for break through changes as His Holiness desires? Otherwise, the Patriarch and few good people alone can't degenerate this so rampant and interwoven ill system. Can we have contribution to help the Patriarch's idea? If so how? let's take this assignment home and contribute!

    Thank you

    ReplyDelete
  33. Thanks Father for your proposal. We expect alot from you. Let God help you. We don't want a patriarich whom we hate rather beloved & respected father like pop Shinoda.

    ReplyDelete
  34. Dear Dn. Daniel

    Now you have raised the burning issue of the day. The problem is like a communicable disease which causes country wide disaster. Hence, we need to stand by the Patriarch.    ReplyDelete
  35. ዲ/ን ዳንኤል ይህንን አሳሳቢ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች አንገት ያስደፋ ጉዳይ ትኩረት ማግኘቱን ስላሳወከን አመሰግናለሁ፡፡ አባታችን ብፁዕ አቡነ ማትያስም ለዚህ አንገብጋቢ እና አፋጣኝ መፍትሔ ለሚፈልግ ጉዳይ ትኩረት መስጠቶ በልዑል እግዚአብሔር ስም አመሰግናለሁ፡፡ ይህንን ለማድረግ የልዑል እግዚአብሔር ፍቃድና ሰዓት አሁን የደረሰ ይመስላል፤እርሶን በመምረጥም ጅራፉን ሊያነሳ ቤቱንም ከወንበዴዎች ሊያፀዳ እንደሆነ አምናለሁ፡፡በርቱ በጸሎት ይህ ሊሆን ቀላል ነው፡፡ሩጫቸውን እንደጨረሱት አበው እርሶም ለቤቱ ቀናዒ መሆን ይጠበቅቦታል ስል ሃሳቤ ውሃ ወደላይ እንደሚፈስ ያህል ይሰማኛል፡፡ ብዙ ነገሮች አሉ ምዕመናንን እና ምዕመናትን አንገት ያስደፉ በቤቱ ውስጥም ውጭም የሚደረጉ፡፡ ስለዚህ ቤቱን ለማፅዳት ሁሉም እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ከጎኖ ነን፡፡
    “የቤትህ ቅናት በላችኝ”

    ReplyDelete
  36. That is great comment, if they are going to use it!!! I know you are doing your part, but still such kind of eye opner ideas should come from all who ever understand those problems with no "sarcasm".

    ReplyDelete
  37. bemegemeriya lezihi laderesen leluai EGEZEABIHAI mesigana yediresew kenatu kedinegi mariyam gar
    gemerun kefitsami endires yehulum ortodo mimen tesatfo yasefeligal silezih abatachine yaberitalin

    ReplyDelete
  38. በእውነት እጅግ ወቅታዊ እና ቤተክርስትያነናችን ላይ የተጋረጠ ትልቅ አደጋ ስለሆነ ለመፍትሔው ልዑል እገግዝአብሔር ይርዳን

    ReplyDelete
  39. እውነት ነው አይቀርም ፓትርያርኩ እንዳሉት ‹በሁላችንም ላይ ታሪክና እግዚአብሔር ይፈርዱብናል፡፡›
    በቤተ ክህነቱ የሚከበሩትና የሚፈሩት፣ ሰው የሚፈልጋቸውና የሚሟሟትላቸው መምሪያዎች ከገንዘብ ጋር የተነካኩትን እንጂ ከስብከት፣ ከክህነት፣ ከሊቃውንት ጉባኤ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤት፣ ከገዳማት ጋር የተያያዙትን አይደለም፡፡ ዋናው የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልዕኮ የሚያስፈጽሙት መምሪያዎች፣ የቅጣት ቦታዎች ሆነዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ እገሌ በሊቃውንት ጉባኤ ተመደበ ማለት የዕውቀት ማሳያ ሳይሆን ‹ተወረወረ› ማለት ሆኗል፡፡ God please Help Us. We are belongs to you.

    ReplyDelete
  40. I am very happy and strongly agree with Abune Matias. I know many of us, we expect more than this from him. However it is difficult to bring all problem into the table because most of our fathers have been corupted and some of them don't care about Ethiopian Orthodox church. They assined from goverment to get information. Inaddition that our church is lead by the current Ethiopian goverment not by Abune Matias so it is take time for him to get it back. For example if abune Matias oppose about Waldba Gedam suger production the current goverment will send him into jail with out any doubt. We have to learned from Ethiopian Muslim. We have to pray everyday to get power from God and to destroy the current racist goverment. God bless Ethiopian!!!

    ReplyDelete
  41. Thanks D.n Dani this is very important issue so we need to see carefully

    ReplyDelete
  42. wey siyamru...tiru kadre yiwotachewal....

    ReplyDelete
    Replies
    1. Ere enasitewul minachewu kadire yimesilale? zime belo menager tiru ayidelem. Endawum getsitachewu betam des miyel gedamawi newu. Yaneswachewu hasabe tiru nachewu begile yeteshale neger yiseralu biye asibalewu

      Delete
    2. As to me he has no face of cadre.Even he seems a person whom holly spirit dwells. Really I like this patriarich. I am not expected to be Tigre to like him. Be neutral. This is about our church.

      Delete
  43. dani, pls, pls read ur comments carefully.

    ReplyDelete
  44. እግዝአብሔር ይርዳቸው።ግርማ ሞገሱን ሐይለ ጥበቡን ያድላቸው።

    ReplyDelete
  45. ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ ይህንን ጥሩ ዜና ስላካፈልከን። አባታችን ያሰቡት እንዲከናወን አምላክ ይርዳቸው።

    ReplyDelete
  46. D/N yetitsfachewn hulu ke lib salamesegin alalifm Egziabhier hayel ena bereket kante gar yehun. gin D/N sle betekirstyanachin bizu titsfaleh enem ante ketsafkachew bemetenu anebalehu betam tiru yehone mikir ena menfesawi nachew neger gin D/N sile hulet (2) maletim betam agebgabi ena jize yemayesetachew negeroch a endalu bedeb tawkaleh enzihm 1 be wechi yalew ye Ethiopia Orthodox weyem sinodos hager bet kalew Sinodos gar le erke selam atitsfim 2 sile Waldbba gedam maletim zeregninet ye golabet ena be gedamu zurya le Sukar teblow lemitaresew balemetsafih eskahun yegermegnal bergit new bichaihn yemtadergew neger yekebdal hamisa (50) lomin land sew shekimu new le hamisa sew gin getu new endetebalew hulu hulum lenezih gudayewech binesasa erke selam yewerd neber ye Egziabhier bereket ena cherinet kante gar yehun amen!

    ReplyDelete
  47. Egiziabher ketenesa manm ayaskomewm. Abatachinen bietun lemastdat kaskemetachew manem liyashenfachew aychilem. Yebetekrstyanachen tarik yirewet zend hulachenm wede amlakachen inchuh . Bekam yibelen. Wendemachin D. Danielnm Egzeabiher yastnalen. Amen.

    ReplyDelete
  48. e/r stega ena bereket yadililin dan dani

    ReplyDelete
  49. የቤተ ክህነቱ የፋይናንስ አሠራር አሁን ዓለም ከደረሰበት ሳይሆን ሀገሪቱ ከደረሰችበት እንኳን ቢመዘን ለቅርስ መቀመጥ ያለበት ነው፡፡

    ReplyDelete
  50. የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን:: ነህ 2:20

    ReplyDelete
  51. Lelaw betekhnet mahibere kidusanis letmesasay lewit sisnesa meche ensema yihon??? yadrsen!

    ReplyDelete
  52. Good insight! God bless our fathers for their due effort Amen.

    ReplyDelete
  53. danye,egziabher Yitebkh.lela yemlew yelegnm.

    ReplyDelete
  54. እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!!!

    ReplyDelete
  55. egziabeher yetasebew yakenawen zende yerdachew.

    ReplyDelete
  56. melkam eyeta new.

    ReplyDelete
  57. Wow it is wonderful idea and thank you God to have this kind of father at this movement. Sorry to say it at this time most of our church leaders are connected with the current goverment and they are away from God. Some of them are not paster (kase) they just get the position to pass information for goverment, so it is difficult to sort the right orthodox christian and the fake orthodox christian. Our goverment is working hard to destroy our strenght and unity because they don't have any confidence what they are doing right now so they think all people they will kill them. I am agree with them as some point because they have been distroing our church and historical place to get money from indian investor but we are christian , we will pray for them and we don't take revange. However even if I put different obstacle I belive God will help us to bring change in our church. Change! change ! change for our church and Ethiopia . God bless Ethiopia.

    ReplyDelete
  58. ዲያቆን ያልከዉ ትክክል ነዉ። ቤተ ክርስትያናችን ከወቅቱ አሰራር ጋር መሄድ አለባት። ቤተ ክህነት ለመግባት ከበር ጀምሮ በእጅ መሄድ መቅረት አለበት። እያንዳንዳቸዉ የስራ ሃላፊዎች እና ብፁእ አባታችን ፓትርያሪክ ለምእመናን በራቸዉ ክፍት መሆን አለበት። ሁሉም የስራ ሃላፊዎችና ኮሚቴዎች ቀጠሮአቸዉ አጭር ዉሳኔአቸዉ ግልፅ መሆን አለመበት። እጅግ እጅግ በጣም ከአድልዎ ፣ ከጎጠኝነት ፣ ጉቦ ፣ ወዘተ ከመሳሰሉት ነቀርሳዎች መፅዳት አለበት። የድንግል ልጅ ኢየሱስ ክርስትስ ከብፁእ አባታችንና ይህንን ስራ ከልብ ለመስራት ከተነሱት ጋር ይሁን። ሕዝበ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመን ሁላችንም ለዚህ ሥራ መሳካት ልባዊ ድጋፋችንንና ፀሎታችን አይለያቸዉ።
    ወስብሃት ለእግዚአብሔር
    ወወላዲቱ ድንግል ወመስቀሉ ክቡር

    ReplyDelete