Friday, May 24, 2013

ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት (1935-2013) ዐረፉ

click here for pdf


ኢትዮጵያ የመካከለኛው ዘመን ታሪክ ሊቅ የሆኑትና አያሌ መጻሕፍትንና የጥናት ጽሑፎችን በልዩ ልዩ ብሔራዊና ሀገር ዐቀፍ መድረኮች ያቀረቡት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም እንዲመሠረት ተጋድሎ ካደረጉ ምሁራን አንዱ የሆኑት፣ የኢትዮጵያ ጥንታዊ መዛግብት በማይክሮ ፊልም እንዲሰባሰቡ፣ እንዲጠኑና እንዲታወቁ ከደከሙት የመጀመርያዎቹ ሊቃውንት መካከል የሚቆጠሩት፣ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ግንቦት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በአሜሪካን አገር ቺካጎ ከተማ ዐረፉ፡፡


የኢትዮጵያ መካከለኛው ዘመን ታሪክ ሊቅ የነበሩት ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በተለያዩ የአመራር ኃላፊነቶች እጅግ ስኬታማ ሕይወት የመሩ ምሁር ነበሩ፡፡ የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክን በተመለከተ አያሌ የምርምር ሥራዎችን ለአገርና ለዓለም ያበረከቱ ሲሆን፤ በተለይም ቤተ መንግሥትና ቤተ ክህነት በኢትዮጵያ (Church and State in Ethiopia, 1270-1527) የተሰኘው መጽሐፋቸው በመስኩ እስካሁንም ወደር ያልተገኘለት የምርምር ውጤት በመሆኑ ዓለም አቀፍ እውቅናን አስገኝቶላቸዋል፡፡


የረቀቀ የምርምር ችሎታቸው ለተማሪዎቻቸው ትልቅ ተምሳሌት የነበረ ሲሆን፤ ይህንኑ የምርምር ቴክኒክም ለተማሪዎቻቸው በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ውስጥ ያካሂዱ በነበረው ልዩ የመስክ ምርምር ዘይቤና በከፍተኛ ጥንቃቄ ያርሟቸው በነበሩት ድርሳኖች አማካይነት ለተማሪዎቻቸው ለማስተላለፍ የበቁ ምሁር ነበሩ፡፡ የምርምር ሥራዎቻቸው ዓለም አቀፍ እውቅናን አትርፈውላቸው፣ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (ሎስ አንጀለስ)፣ በኖርዝዌስተርን ዩኒቨርሲቲ፣ በበክኔል ዩኒቨርሲቲ እና ኧርባና ሻምፔን በሚገኘው ኢሊኖይ ዩኒቨርሲቲ በጎብኚ ፕሮፌሰርነት ለማገልገል በቅተዋል፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የኮሌጅ ደ ፍራንስ የክብር ሜዳይና የድኅረ ምረቃ ትምህርት ያካሄዱበት ከነበረው የዩኒቨርሲቲ ኦፍ ለንደን የአፍሪቃና እስያ ጥናት ማዕከል የክብር ፌሎውነት ሽልማት አስገኝቶላቸዋል፡፡

ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ከምርምር መስኩ ባሻገር ለአያሌ ዓመታት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በተለያዩ የአመራር ኃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ዋነኞቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡- እ.ኤ.አ. ከ1977-84 በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ዳይሬክተርነት፤ ከ1986-92 በሳሻል ሳይንስ ኮሌጅ ዲንነት፤ ከ1995-99 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ዳይሬክተርነትና ዋና ኤዲተርነት፡፡ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተርነታቸው፣ ተቋሙን ፈታኝ በሆኑ ዓመታት ብቁ አመራር ከመስጠታቸውም በላይ 8ኛውን ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ጥናት ጉባኤ በማዘጋጀት የኢትዮጵያ ጥናት ባለቤቱ ወደ ሆነችው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ምንጊዜም የማይዘነጋ ውለታ ጥለው አልፈዋል፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስም አሁን እንደምናየው ትልቅ አሳታሚ ድርጅት ለመሆን የበቃው ፕሮፌሰር ታደሰ በጣሉት መሠረት ላይ ነው፡፡ 

በአያሌው የደከሙለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የማይክሮ ፊልም ቤተ መጻሕፍት ክፍል እስካሁንም በስማቸው እየተጠራ ይገኛል፡፡

ፕሮፌሰር ታደሰ ያረፉት ባደረባቸው ሕመም ለረጅም ጊዜ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሲሆን፤ ባለቤታቸውን ወ/ሮ አልማዝ ሥዩምን ከ10 ወር በኋላ ተከትለው ነው፡፡ ሦስት ሴት ልጆቻቸው በአሜሪካን አገር በከፍተኛ ኃላፊነት ሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡39 comments:

 1. እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአባቶቻችን በአብርሃምና ይስሃቅ እቅፍ ያኑርልን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Nefshwn yeamar

   Delete
  2. እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአባቶቻችን በአብርሃምና ይስሃቅ እቅፍ ያኑርልን።

   Delete
 2. Sorry.any ways he did what is expected of him.Great

  ReplyDelete
 3. nefsachewun ymarlen

  ReplyDelete
 4. ETHIOPIA LOST ANOTHER GREAT PERSONALITY!!HE WAS ONE OF THOSE WE CAN NOT REPLACE WITH SOMEBODY ELSE NOWADAYS!! HE WAS ONE OF THE GREAT ELITES OF ETHIOPIAN MEDIEVAL HISTORY.MAY GOD KEEP HIS SOUL IN HEAVEN!!!

  ReplyDelete
 5. Let God receive his soul in peace.I hope a condolence to his family.
  We miss him!

  ReplyDelete
 6. ሦስት ዓይነት ሙታን አሉ:: ሳይሞቱ የሞቱ ፣ሞተው የሞቱ ፣ሞተው ያልሞቱ:: ሊቁ በሥጋ የተለዩን ሥራቸው ሕያው ያደረጋቸው ኢትዮጵያዊ ናቸው:: ነፍስ ይማር!

  ReplyDelete
 7. ክቡር ሞቱ ለጻድቅ
  ሞቱ ለኃጥዕ ጸዋግ

  የጻድቅ ሞት ክብር ሲሆን
  የኃጢያተኛ ግን መራራ ነው

  ReplyDelete
 8. melekam neger new yeasrut nefashown yemarahow

  ReplyDelete
 9. yadereguet melakem neger batam tru new nefashwon yemar

  ReplyDelete
 10. እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአባቶቻችን በአብርሃምና ይስሃቅ እቅፍ ያኑርልን ammen ።

  ReplyDelete
 11. እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአባቶቻችን በአብርሃምና ይስሃቅ እቅፍ ያኑርልን።

  ReplyDelete
 12. እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአባቶቻችን በአብርሃምና ይስሃቅ እቅፍ ያኑርልን።

  ReplyDelete
 13. እጅግ እናዝናለን!ነፍስ ይማር!

  ReplyDelete
 14. I really socked when i read this articles!!!

  ReplyDelete
 15. It is a big sad day for our country. He was one of the great intellectual who can defend the history of our country. May God be rest his soul in the hand of our fathers Abrham, Yissak and Jacob.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዕድሜ ባይጠገብም አማሟትን የሚያሳምረው እራሱ እግዚአብሄር ነውና ቀናቸው ደርሶ ሞተዋል ብንልም መልካም እና ሰብዓዊ ፍቅራቸው ከእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ህሊና ውስጥ በመኖሩ ለተውልድ እያበበ ይኖራል::ነብስ ይማር::
   በአንጻሩ ደግሞ እነዚያ ኢትዮጵያን እያደሙ ሊገድሏት ዕድሜአቸውን የተንኮል ተግባር ሲፈፅሙ የሞቱ እንደተረገሙ ይታወሳሉና ክፋታቸውን ባስታወስን ቁጥር በገሃነም ሲለበለቡ እና ሲበሰብሱ ይኖራሉ::

   Delete
 16. CHERU AMILAKACHIN Nefisachewin Ke Ene Aberiham Yisihak Ena Yaikob Ekif Wist Yanurilin Le Betsebochachew Metsinanatin Yesetlin

  ReplyDelete
 17. nefsachewun ymarlen

  ReplyDelete
 18. nebs yemar betam asazagn new

  ReplyDelete
 19. ከአመታት በፊት የ6 ኪሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ፡፡በእነ ዶክተር ዮናስ አድማሱ..... ስራዎች እና እዉቀት እደመም ነበር፡፡ እኚንታላቅ ምሁርና ተመራማሪ ግን በወቅቱ በቅጡ ባለማወቄ ራሴን ታዘብኩት፡፡
  ነፍስ ይማር! የእሳቸዉንም ፈለገግ ተከታዮች ያብዛልን፤ አሜን!

  ReplyDelete
 20. nefsachewun ymar!!!

  ReplyDelete
 21. wedaje Daniel
  Your article and what I read some where is identical attributing it to Prof. Bahiru. If the narrative is yours it is surprising how other copied with out acknowledging the source.

  ReplyDelete
 22. Prof Tadesse lives forever through his work and contribution to the society. I'd like to express my deep and sincere condolences to all Ethiopians, who lost this great intellectual, especially to his family.
  RIP Sir!
  Dr. Tsegaye Tadesse, University of Nebraska-Lincoln, USA.

  ReplyDelete
 23. የተማረ ለዚያውም ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያለን ምሁር ማጣቱ አሰረ ፍኖታቸውን ለሚከተሉ በትምህርታቸው ለወለዷቸውና ለእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ታላቅ ሀዘን ነው ፣ ይሁን እንጂ ሰው ናቸውና ወትገብዕ ውስተ መሬት ሊያንቀላፉ ግድ ነው ....... መልካሙ ስራቸው ግን ከመቃብር በላይ ሁሌም ይናገራል ፠ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአባቶቻችን በአብርሃምና ይስሃቅ እቅፍ ያኑርልን ፠ አሜን ።

  ReplyDelete
 24. Rome 3;23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤
  24 በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
  Yohanes 3;16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
  Yohanes 3;18 በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል
  silezih wegenoch mot aykerim Eyesusn amino memot bicha new yemiatsedkew.

  ReplyDelete
 25. Ebakihe D.Daniel, betekirstian yelimat report madamecha eyehonech memtatua ayasasibim tilaleh?? ene eko betekirstian yemehedew ye egziabherin kal bemesmat sheketen lemaragef, shekimen lemakilel new. Ahun Ahun Gin le kibre bealat sayiker limena ena yelimat report yemisemabet honual. eshi yet heden kalun enadamit????? ere bakihe Daniel silezihe neger asibibetna hizbu endiweyaybet yehone neger adirg.

  ReplyDelete
 26. Aba TekleHaimanotJune 3, 2013 at 5:16 AM

  I express my condolences to his family and friends. Prof Taddesse Tamrat was indeed one of the best sons of Ethiopia. I belive he is still alive in the great works that he contributed to his motherland. This guy could have been Emeritus Professor at any prestigious US University, but he chose to serve his country under such difficult circumstances.

  ReplyDelete
 27. Ymotewus mote beseraw sera mote anelm ngergine ketach eybekel yalew ybukaya moote mene yideregal yasasebal!

  ReplyDelete
 28. እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአባቶቻችን በአብርሃምና ይስሃቅ እቅፍ ያኑርልን።

  ReplyDelete