እንዴው በዚያ የደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ ሰሞን እጅግ የታወቁት የእንግሊዝ
እግር ኳስ አሠልጣኝ አንዱን እንኳን የብሔራዊ ቡድናችንን ተጫዋች ስም መጥራት አቃታቸው አሉ፡፡ ትዝብት ነው፡፡ እኛ ከነጫማና
ከነከናቴራ ቁጥራችሁ ልቅም አድርገን ስናውቃችሁ፤ ምነው ጃል እንዲያ ሠላሳ ዓመት ለፍተን ያፈራናቸውን ተጨዋቾች እንዴት
ስማቸውን አያውቋቸውም፡፡
ለመሆኑ ኢትዮጵያን የማያውቅ ሰው የእንግሊዝን እግር ኳስ ማሠልጠኑ ራሱ ተገቢ ነበር?
ይህችን በአፍሪካ ውስጥ ቅኝ ያልተገዛች፣ በአድዋ ጦርነት ነጭን ያንበረከከች፣ የራስዋ ፊደልና ዜማ ያላት፣ የራስዋ ቋንቋና ሥነ
ጽሑፍ ያላትን፣ በዓለም አንደኛ የሆነችውን ኢትዮጵያን ሳያውቁ እንዴት የእንግሊዝን ትልቅ ክለብ ሊያሠለጥኑ በቁ፡፡ እነዚህ
ፈረንጆች ለእግር እንጂ ለጭንቅላት ግድ የላቸውም ማለት ነው? እነዚህን ልጆች ለማፍራት ሠላሳ ዓመት እንደፈጀብን እንዴት
አድርገን በነገርንዎ፤ ታድያ እነዚህን ዓለም ያወቃቸውን ልጆቻችንን ካላወቋቸውማ ሌሎቻችንንማ ከነመፈጠራችንም አያውቁንም ማለት
ነው፡፡
እኛ እዚህ በእናንተ ምክንያት ስንት መከራ እንዳየን አያውቁልንም ማለት ነዋ፡፡ ስንት
ስብሰባ ዛሬ የማንቸስተር ጨዋታ ስላለ፣ አርሴናል ስለሚጋጠም እየተባለ እንደተሠረዘ አታውቁልንም ማለት ነዋ፤ መጋቢት 3 ቀን
የተወለደ ልጅ በእናንተ ጨዋታ ምክንያት ‹የአርሴናል ጨዋታ ከሚያልፍ አንተ መጋቢት ስድስት ብትወለድ ይሻላል› ተብሎ ልደቱ
መጋቢት ስድስት መከበሩን አታውቁልንማ፡፡ ይህንን ሁሉ ተውት፤ በስንት ጭቅጭቅ የቆረጡትን የሠርግ ቀናቸውን አርሴና ማንቼ
ይጋጠማሉ ብለው፣ እነርሱ የተሸነፉ እንደሆነ እኔና አንቺ ከምንገጥም የእነርሱ ጨዋታ ከእኛ ሠርግ ጋር እንዳይገጥም እናድርገው
ብለው መሠረዛቸውን አታውቁልንማ፡፡
የእናንተማ ድፍረት መች ተዘርዝሮ ያልቃል፡፡ እንኳንና ዓለማዊው መንፈሳዊው ፕሮግራም
ሲወጣ እንኳን መጀመርያ የእናንተ ፕሮግራም ታይቶ ነው፡፡ እናንተ በቴሌቭዥን ብቅ ካላችሁ ድመት ብቅ እንዳለበት የአይጥ ሠፈር
አንድ ሰው በሠፈሩ ዝር አይልም፡፡ ደግነቱ አውቃችሁትም ይሁን ሳታውቁት በቅዳሴና በሶላት ሰዓት አለመጫወታችሁ በጀ እንጂ
አስቀዳሽና ሰጋጅ ከየት ይመጣ ነበር፡፡
እና ይህንን ሁሉ ለእናንተ ፍቅር ስንል ማድረጋችንን አታውቁልንማ፡፡
እናንተኮ እዚህ ሀገር የጫት ቤት ስም ሆናችኋል፤ የሐበሻ ቀሚስ ሆናችኋል፤ የቦሎ
መለጠፊያ ሆናችኋል፤ ሻርፕ ሆናችኋል፤ ነጠላ ሆናችኋል፤ የምግብ ትሪ ሆናችኋል፤ ሻሂ ቤት ሆናችኋል፣ የምግብ ዓይነት ሆናችኋል፤
እኛ እናንተ ምን እንደበላችሁ፣ ምን እንደ ጠጣችሁ፣ ምን እንደምትወዱ፣ ምን እንደምትጠሉ፤ የትኛው ጭማቂ፣ የትኛው ሾርባ፣
የትኛው ጥብስ፣ የትኛው ቴላቲሊ እንደሚማርካችሁ፤ ከነ ሜኖ ዝርዝሩ ስናጠና እየዋልን፡፡
ቆይ ታድያ የማታውቁልን ከሆነ ልብሳችሁን ለብሰን፣ ማልያችሁን አጥልቀን፣ ሻርፓችሁን
ተከናንበን፤ ዐርማችሁን አንግበን፣ ስማችሁን ቡዳ እንደያዘው ሰው ስንጠራ የምንውለው ለምንድን ነው? ቆይ ታድያ ካላወቃችሁን
ቤታችንን ትተን፣ አዳራሽ ከትመን፣ አንዳንድ ጨብጠን፣ ዕንቅልፋችን አጥተን፣ በሆታ እየዘመርን እስከ ዕኩለ ሌሊት ለምን
እንደግፋችኋለን፡፡
ደግሞ ስንሰማ እናንተ የምታውቁት የ ‹ኤ› ቡድን፣ የ‹ቢ› ቡድን የ‹ሲ› ቡድን ብቻ
ነው አሉ፡፡ እዚህ እኛ ሀገር በእናንተ ስም የተቋቋምነውን ቡድኖች ምንም አታውቁንም ማለት ነው፡፡ ታድያ ማነው ያደራጀን፤
ያደለው ቅድመ ዕውቅናና ዕውቅና ይሰጣል፤ እናንተ ከነመፈጠራችንም አታውቁትም፡፡ ትዝብት ነው ትርፉ፡፡
እናንተ ምን ታደርጉ፤ እናንተ በሚሊዮን እየተከፈላችሁ የምትጫወቱትን ጨዋታ እኛ
የአንድ ብር ዳቦ ገምጠን እናይላችኋለን፡፡ እናንተ ለእግራችሁ፣ ለጥፍራችሁ፣ ለጣታችሁ ሳይቀር ኢንሹራንስ ተከፍሏችሁ ስትጫወቱ፣
እኛ ለነገ ምሳ ማግኘታችንን እንኳን ዋስትና ሳይኖረን የተተመነውን ሁሉ ከፍለን እናያችኋለን፤
ለነገሩ በኛም አይፈረድም፡፡ ድሮ ድሮ ‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ› ነበር
የሚባለው፡፡ አሁንማ ተቀይሮ ‹በእንግሊዝ ጨዋታ አይቆጡም ጌታ› ሆኗልኮ፡፡ አሸነፋችሁም፣ ተሸነፋችሁም፣ ደከማችሁም፣
በረታችሁም፣ ባለጋችሁም፣ ተቀጣችሁም፣ ወጣችሁም፣ ገባችሁም ስለ እናንተ እንደልብ ማውራት ይቻላል፡፡ መጻፍ ይቻላል፡፡ ፈቃድ
የሚቀማ የለ፤ ፍርድ ቤት የሚያቆም የለ፡፡ በእናንተ ላይ ለመተቸትና፣ ለመራቀቅ፣ ለመተንተንና ለመከራከር የምናገኘውን ነጻነት
በማን ላይ እናገኘዋለን፡፡ ይህ ነጻነትኮ እንኳን በፖለቲከኞቹ ላይ በጊዮርጊስና በቡና፣ በደደቢትና በንግድ ባንክ፣ በመብራት
ኃይልና በአዋሳ ከነማ ቡድኖች ላይ እንኳን አይገኝም፡፡ ይህን ይህን ሳስበው እንኳን ኖራችሁ ያሰኘኛል፡፡ እናንተ ባትኖሩ
ስለምን እንከራከር ነበር?
ረስቼው ነበር፤ ይልቅ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ እንዲህ የማታውቁን ከሆነ የት
ልትሰሟቸው ነው ታድያ የሀገራችን ጋዜጠኞችና የሀገራችን ስፖርት ተንታኞች ቬንገር ይህን ማድረግ አለባቸው፣ ፈርጉሰን ይህንን
ማድረግ የለባቸውም፡፡ ሩኒ እንዲህ ቢያደርግ ጥሩ ነው፣ ቫምፐርሲ ይህ ምግብ ይሻለዋል፣ ላምፓርድ ከእንትና ጋር መጣላት
አልነበረበትም እያሉ ልባቸው እስኪወልቅ ምክር የሚሰጧችሁ፤ እና ይህንን በኤፍ ኤም የሚሰጣችሁን ምክርና ተግሣጽ፣ ይህንን ሁሉ
የባለሞያዎቻችንን ትንታኔ፣ አትሰሙትም ማለት ነው? እኛኮ አንዳንድ ሬዲዮ ጣቢያዎች ‹በኦን ላይን እንገኛለን› ሲሉን የምትሰሟቸው
ይመስለን ነበር፡፡ እንዴው ማ ይሙት አንዳንድ አሰላለፋችሁን የምትቀይሩት እኛ የሰጠናችሁን ሃሳብ ሰምታችሁ አይደለም፤ ወይስ
በኮፒ ራይት እንዳትከሰሱ ፈርታችሁ ነው፡፡
እንዴው ግዴለም ለእኔ ንገሩኝ፤ ከአንዳንድ ጋዜጠኞቻችን ጋር በስልክ አትገናኙም?
ኢሜይል አትደራረጉም? ምሥጢር አታሾልኩላቸውም? ታድያ እንዴት ነው ነገሩ፤ ዛሬ ማታ እዚህ አመሹ፣ እንዲህ ዓይነት ሕልም አዩ፣
አሟቸው ነበር፣ ሲያቃዣቸው ነበር፣ የበሉት ምግብ ሌሊቱኑ አልተስማማቸውም ሲሉንኮ ደውለውላችሁ ወይም ደውላችሁላቸው የተገናኛችሁ
ይመስለን ነበር፡፡ ለካስ ጥንቆላ ነው፡፡
ይኼው ልጆቻችን ወደፊት እንደ ቴዎድሮስ ጀግና፣ እንደ ምኒልክ ጥበበኛ፣ እንደ ዓምደ ጽዮን ደፋር፣ እንደ ላሊበላ አርቆ
አሳቢ፣ እንደ ዮሐንስ ታጋሽ፣ እንደ ሐዲስ ዓለማየሁ ደራሲ፣ እንደ በዓሉ ግርማ ጋዜጠኛ፣ እንደ ቅጣው እጅጉ ሳይንቲስት፣ እንደ
አፈወርቅ ተክሌ ሰዓሊ፣ እንደ ጸጋዬ ገብረ መድኅን ባለ ቅኔ፣ እንደ በላይ ዘለቀ ቆፍጣና ወታደር እንሆናለን አይሉምኮ፡፡ አቆራረጣቸው፣
አካሄዳቸው፣ አጨዋወታቸው እንደ እናንተ ሆኗል፡፡ መሆን የሚፈልጉት ሁሉ ሩኒን፣ ቫምፐርሲን፣ ሜሲን፣ ድሮግባን፣ ሮናልዶን ሆኗል፡፡
ከመቼ አድገን፣ ታዋቂ ተጨዋች ሆነን ለእንግሊዝ በተሸጥን ይላሉ፡፡
አይ የአድዋ ጀግኖች ተሸወዳችሁ፡፡ እናንተ ሰው ተሸጦ ወደ ፈረንጅ ሀገር እንዳይሄድ ብላችሁ አልነበረም እንዴ የተዋጋችሁት?
እኛ እንደ ሌሎቹ አፍሪካውያን ወገኖቻችን በሠንሠለት ታሥረን፣ ከሀገራችን ወጥተን፣ ባዕድ ምድር ተሽጠን እንዳንሄድ አልነበረም እንዴ
የተዋደቃችሁት? አሁንማ መሸጥ ልማድ ሆኖ፣ ልጆቻችሁ ይኼው የሚሸጡበትን ቀን በተስፋ እየጠበቁ ናቸው፡፡ አይ አርሴና ማንቼ የማትሠሩን
ነገር የለ፡፡
‹እጅህን ስጥ አለኝ ፈረንጅ› አሉ የዋሑ ቴዎድሮስ፤ እስኪ ቀና ብለው ይመልከቱ፤ ስንቱ እጁን ብቻ ሳይሆን ልቡንም እንደሰጠልዎ፡፡
እርስዎ ክንዴን ለጠላት አልሰጥም ብለው ነው ጥይት የጎረሱት፤ ልጆችዎኮ አርሴናል ተሸነፈ ብለው ነው ጥይት የሚጎርሱት፡፡ እርስዎ
እንግሊዞችን ሰብስበው መድፍ ማሠራትዎን ትውልዱ ረስቶልዎ ዛሬ የመድፈኞቹ ነገር ሲያስጨንቀው ቢያዩ፣ ቴዎድሮስ ሆይ የጠጡትን ጥይት
በኦፕሬሽን ያስወጡት ነበር፡፡ ዛሬ የርስዎ ሀገር ልጅ
‹ገደልንም እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው
ማረክንም እንዳይሉ ሰው የለ በጃቸው›
የሚለውን ቴዎድሮስ ይሙቱ ረስቶታል፡፡ እርስዎ እንግሊዞች ሲመጡ እንዴት እንደተቀበሏቸው አያውቅም፣ አያጠናምም፣ አይጨነቅምም፡፡
አሁን እርሱን እየጨነቀው ያለው፡፡ የዘንድሮን ዋንጫ የወሰደው ማንቼስተር ዩናይትድ የተባለው ቡድን እርስዎ መድፍ ያሠሯቸውን የዛሬዎቹን
መድፈኞች ለመግጠም ኤምሬት ስታድዮም ሲገባ መድፈኞቹ ተሰልፈው እያጨበጨቡ ይቀበሏቸው ወይስ አይቀበሏቸው? የሚለው ነው፡፡ የለም
ቴዲዬ እርስዎና ዐፄ ዮሐንስ ሳይሸወዱ አልቀሩም፡፡
እና ይህንን ሁሉ ሆነንላችሁ ደግሞ ስማችንን አታውቁትም አሉ፡፡ እኛን ካላወቃችሁ ታድያ ምንድን ነው የምታውቁት፡፡ ይኼው
ሂሳብ በእናንተ ከመማር በላይ ምን እናድርግ እንግዲህ፡፡ ሜሲ ትናንት ሦስት ጎል አገባ፣ ዛሬ ደግሞ ሁለት ጎል አገባ፤ በጠቅላላው
ስንት ጎል አገባ? ካልተባሉኮ ልጆቻችን ሊደምሩ አልቻሉም፡፡ ከአሥራ አንዱ የፉልሃም ተጨዋቾች ሁለቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ ከወጡ ስንት
ተጨዋቾች ሜዳ ላይ ይቀራሉ፤ ካላልን ማን ይቀንስልናል፡፡ ሩኒ በሳምንት የሚያገኘው ገቢ 120 ሺ ፓውንድ ነው፡፡ በዓመት 52 ሳምንቶች
አሉ፡፡ ሩኒ በዓመት ስንት ያገኛል? ካላልን ማን ያባዛልናል? እና ይህንን ሁሉ ሆነን አታውቁንም? እኛ ብቻ ነን የምናውቃችሁ?
እንዲህ ጥናታችንን ትተን እናንተን እያጠናን፣ እንዲህ ከአድዋ ጦርነት ታሪክ ይልቅ የእናንተን የዌምብልደን ፍልሚያ ታሪክ እያጠናን፣
እንዲህ ከሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት ይልቅ የእናንተን የገቢ ዕድገት እየተከታተልን፣ ከብር የመግዛት ዐቅም መዳከም ይልቅ የሜሲ
የማግባት ዐቅም መዳከም እያሳሰበን፣ ከምግብ ዋጋ መጨመር ይልቅ የዳኝነት መዛባቱ መጨመር እያስጨነቀን፤
ተው እንጂ አርሴና ማንቼ አስተያየት አድርጉ፤
እናንተ የመጀመርያውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ስትወስዱ ሥጋ እኛ ሀገር 20 ብር ነበር፤ ዛሬ ሃያኛ ዋንጫችሁን ስትወስዱ
ግን ሥጋ 100 ብር ገብቷል፡፡ እና የናንተ ሃያኛ ድል በኑሯችን ላይ 500% ዋጋ ተጨምሮበት የምናከብረው መሆኑን እንኳን አታውቁልንም
አይደል፡፡ እናንተ የማታውቁን እኛ የምናውቃችሁ፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፤ በሌላ ተመሳሳይ ሚዲያ
መጠቀም አይፈቀድም
Danel zarese yelebacheahen lekelekachenen s
ReplyDeleteelengerken sew yelbun sengrute ykorkokruten yahel yeskael endetebalew new yaskegen.
Please read the message very well so that you will not extremist like this.Foot ball these by itself not only an entertainment but also a business.Let us take European management style of their football as a lesson and work on ours so that it can seek the world attention because we have seen it during African cup of nation.Attending European football by itself is not bad but the problem is the ever growing emotional thinking/support towards EU football.
DeleteEgziabher yistilin Dn Daniel
ReplyDeleteደስ በሎኝ አነባለሁ፣ እስቃለሁ፣ አውቃለሁ ደግሞም አዝናለሁ፡፡ ጽሁፎችህን በናፍቆት እጠብቃለሁ፡፡ እግዚአብሔር ረዥም ዕድሜ ይስጥህ፤ የምታወጋን አትጣ፡፡
ReplyDeleteአስተያየቴ አገም ጠቀም ነው፡፡ ባልሸሹም ዞር አሉ መንገድ እኔም የባህር ማዶ ፊልም አድናቂ ነኝ እነሱን በየትኛውም ቁና መስፈር አልችልም፡፡
ReplyDeleteኳስን ግን በተመለከተ እኔም በሬድዮ ጭቅጭቅና በመደጋገም ብዛት ከማውቃቸው በቀር ማንንም አላውቅም፣ ማወቅም አልፈልግም፣ የግል ህይወታቸውም ሆነ የበለጠ ደግሞ በሙያቸው….‹‹ ትጋት/ጥረት/ልፋት›› ከሚሉት ተደጋጋሚና የማይለወጡ የእግር ኳስ ስኬት መልእክት በሻገር ምንም የተለየ ለማህበረሰባዊም ሆነ ለየግል ህይወት inspire አድርገውኝ ወይም መፍትሄ ጠቁመውኝ አያውቁም፣ አንተ ስለማትወድ ነው እንዳትሉኝ ፉትቦል በሊታ ጓደኞች አሉኝ እነሱም ኳስ ለገሃዱ እውነተኛ አለም ያለው ፋይዳ ዘረጥ እሞቦጥ ነው ይላሉ
…ፊለምስ እንዳትለኝ... አንድ ቀን በ ፊልም ቨርሰስ ፉትቦል በሚል አምድ አስተያየት ጋብዘኝና አንነጋገራለን፡፡ ለአሁኑ ግን የእግር ኳስ አድናቂ ጓደኞቼ ሙድ መያዣ ሆኜ ብቀር ይሻለኛል፡፡
አስተያየትህ ለእግርኳስ አድናኪዎች የሚያንገፈግፍ፣ የሚያናድድ ለበጣዊ እውነት ቢሆንም ቅሉ ከጓደኞቼ ህይወት እንዳየሁት ለወንድሞቼ ከመጠጥ ስካርና ከክፉ ሱስ በጣም የሻላል ባይ ነኝ፡፡
ነጋቲ
ከ Dani ዋና ሀሳብጋ ቅሬታ የለኝም ግን @ሆሳዕና ከ አንድ አባባልጋ ተመሳሰልሽብኝ፡፡ነገሩ እንዲ ነው...ሠዉዬዉ ነወ አሉ፡ድኩላ ሊያድን ወቶ አባሮ መያዝ/መግደል/ስያቅተዉ፡"አቦ ሂጂ ስጋሽ እራሱ አይጥምመ "አለ ይባላል፡፡Hosana,21ኛዉ ዘመን ለይ ሆነን Football ቢዝነስ፡ሳይንስ በሆነበት ግዜ ለይ "ስለ ስፖርት ማወቅ አልፈልግም"የሚል ዜጋ...
Deleteፍየል ወዲያ ሆነብኝ ነገሩ…you are funny! i like you but whats up with the 21th century, fried?football isnt like the ever changing technology or lifestyle, it has the same number of players same rule and finally same output. have you ever ask yourself what could possibly a kid learn if he grew up watching only football?...ALMOST NOTHING!
Deletehow old are you?
በመሰረታዊ ሃሳቡ ላይ ጸብ የለኝም ነገር ግን አንተ ራስህ በታሪክ መኖር በሚል አንዴ ካስነበብከን ጽሑፍ ጋር ይጋጫል። ከሽፏል ተብለህ ዛሬም ጭራሽ የስፖርት ጋዜጤኛ ታሪካችንን አይውቅም ብለህ ቡራ ከረዩ ትላለህ እንዴ? ከሃይሌ ገብረሥላሴ የሚቀል ስም ያለው ተጫዋችን እንኳ መጥራት ያልቻሉት ተጨዋቾቹ መጠራት የማይችሉ ስለሆኑ እንጅ ቸክሎ መጥቶም ቢሆን አቆላምጦ ነበር የሚጠራቸው። ያለነው 21ኛው ክ/ዘመን ላይ ነው ወዳጄ
ReplyDeleteante degmo atakabdew enji. Do you think he seriously is mad that our players are not known? I don't think so. He is just saying, we know every detail about them, which is true, and they don't know us, which is true(for whatever reason. I get so mad sometimes,one day, here in America, my brother called his work and asked a day off, I asked him why. He told me "Arsenal teshenefo tenadeje new". I swear to God, this is true and I wanted to scream... so sometimes we take it too far about Manche thing. And it is not only Ethiopia, but I don't think the guy will be able to say one player's name of many African countries team.
Deleteወዳጄ ምንም አይገባም ያልከው ነገር ሁሉ ከቻልክ ደግመህ አንብበው ግን ችግር እንዳለብህ ያስታውቃል
DeleteyeEthiopia tarik alkeshefem bilo sikeraker neber:: ahun degmo keshfual eyalen new:: Yeprofesserun hasab lemekebel yihen yakil megderderu gize mabaken yasmesilibetal ....eyalen new yalew ayiii
Deleteante yalgebah endehone tadia min yidereg? yihene yeandu club achebchabi tihonaleh
Deleteበመጀመሪያ የኛ ሚዲያ ለነሱ በሚሰጠው የተጋነነ ትንታኔም ይሁን እኛ ለእንግሊዝ ኳስ ያለን የተጋነነ ፍቅር ጋብ እንዲል በሚለው እስማማለሁ። ነገር ግን ልጆችን በኳስ ተጨዋች፣ አርቲስት ምሳሌ እያደረጉ ማስተማሩ የ21ኛው ክ/ዘመን ስጦታ እንጅ ክፉ ነገር አይደለም።ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ዓለም በሙሉ የምዕራቡ ባሕል ተጸዕኖ ወራሽ ሆኗል። እንደ ሰሜን ኮሪያ በርህን ዘግተህ መቀመጥ ደግሞ አንችልም ትክክለኛ መንገድም አይደለም። ያጣ የነጣን ደሃዎችና መሃይሞች ነን።ችግር ኖሮብኝ ሳይሆን እውነታው ይህ ስለሆነ ነው። ከምዕራባውያን የወረስነው ስንት አስጸያፊ ባሕል እያለ ለምን ኳስ ደጋፊና ተንታኝ ሆናችሁ ብሎ እምቡር እምቡር ማለት አይገባኝም
Deleteደስ በሎኝ አነባለሁ፣ እስቃለሁ፣ አውቃለሁ ደግሞም አዝናለሁ፡፡ ጽሁፎችህን በናፍቆት እጠብቃለሁ፡፡ እግዚአብሔር ረዥም ዕድሜ ይስጥህ፤ የምታወጋን አትጣ፡፡
ReplyDeleteይህ ጽሁፍ በጣም ትምህርት ስለሰጠኝ እና ከኔ ካለፈ ሕይወት ጋራ ስለሚመሳሰል አስተያየት ለመጻፍ ተነሳሳው።
ReplyDeleteይገርማል እኮ ድሮ ድሮ እኔም ከሀገሬ ሳልወጣ የታወቁ ሆቴሎች በመሔድ የሚጠጣና የሚበላ በማዘዝ ከሌሎች መሰል ጓደኞቼ ጋራ የኳስ ደጋፊ ነበርኩ።
ያውም ብዙ ያልተለመደ "የሴት እግርኳስ ደጋፊ" አሁን አሁን የሰውን ሀገር ምንነት እና ማንነታቸውን ሳይ እርግፍ አድርጌ ተውኩት እውነት ነው እነሱ የማያውቁን እኛ የምናውቃቸው የምናደንቃቸው !
አሁን አሁን ደግሞ ከሀገሬ ከወጣሁ እየገረመኝ የመጣው የሀገር ናፍቆት ሲያይልብኝ እስኪ ሀገሬን ባለው ቴክኖሎጂ በመጠቀም እንዴት አደርሽ ልበላት ብዬ ETV ስከፍት ይገርማልም ያስቀኛልም
እኔ ስላለሁበት ሀገር የ እግርኳስ የተጨዋቾች ማንነት ደሞዛቸው ስለሚበሉት ስለሚጠጡት ምኑ ቀረ ወ.ዘ.ተ ... ብዬ ብተወው ይሻላል የምሰማው ከሀገሬው የቴሌቪዥን ስርጭት ሆነ።
አንዳንዴ አማርኛ ሆነ እንጂ የሚነጋገሩበት ቋንቋ የማንን ጣቢያ ነው የከፈትኩት እላለሁ ።
ምነው ቢቻል የሀገሬን ወጣት እያመጣሁ ለ አንድ ሳምንት ሳምንት እንኳን የሰው ሀገር ምን እንደሚመስል አሳይቼ በመለስኩት .
ውድ ዳንኤል
እረጅም የአገልግሎት እድሜና ጤና ይስጥልን።
ጽሑፎችህ ብዙ አስተምረውናል። የምንግዜም አክባሪህ ነኝ!
ከጀርመን ፍራንክፈርት
ውይ ውይ ውይ ዳኒዬ አምላክ በነገር ሁሉ ይባርክህ!ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ...የኔ ዘመን ወጣት በፈቃዱ ለዚያውም ሃገሩ ላይ ተቀምጦ ቅኝ የሚገዛ ሰነፍ ነው! ለራሱ ታሪክ የማይደንቀው ለጠገበ ማጨብጨብ ብቻ
ReplyDeletetikikil
DeleteMay God bless u Dani
ReplyDeleteIt is really funny I enjoyed it.
ReplyDeleteDani, be ahunu gize yale minim tekenakagn benetsanet kemangnawm sew ga lemawrat yemiaschil sport bicha new. Bergit belk binadergew melkam neber. Wedenm tegedenm kesew ga lemawrat (kebichegninet lemlakek) sinl egir kuas meketatel and yeken teken sirachin adirgenwal. Gazetegnochim andu ye enjera gemedachew argewtal. Sile poletika endanawera gedeb alew, sile haymanotm (menfesawi guday) mawrat yeminchilew be menfes kemimeslun ga new. Kdza wichi anaweram. Ere endewm eresu sinesa gena yemiyazagam aytefa. Hatiatachin tezerzirobin nisha gibu yetebaln ymesil eresun enferawalen. Engdih wedo ejun leba'edan yesete baria malet enen chemiro yezih zemen tiwlid new. Ante gin berta. Endezih aynet koskuash tsufochin eyetsafk asnebiben. Biyans tegedo (were lemawrat bilo) erasun lebarnet yesetewn tadinaleh wed maninetu endimeles tadergaleh. Ketilbet!!!!!
ReplyDelete@ayyyi ሰምተሃል ይላል የሰፈራችን ልጅ:: ማለት የተፈለገው ገብቶን አለመታረማችን ሲያስገርም እንደገና ነገር ማጠማዘዝን ምን አመጣው? ለማንኛውም ሰምተሀል!
ReplyDeleteአድሜና ጤና ይስጥልን ግሩም ምክርም ነው።
ReplyDeleteስለ እንግሊዝ ጨዋታ ሲነገር የእንግሊዝ ጨው ነው ትዝ እሚለኝ። አይ የእንግሊዝ ጨው! አሃሃ! በትንሽ ማንኪያ እንደ ማንቼ ጠላዥ ሽው! ሲደረግ ጠላትህ ሽው! ይበልና ሆድ ድርቀትህም ሽው! እልም ይላል። ታዲያ ምን ያደርጋል ጦቢያም በአገሯ የተሰራ የእንግሊዝ ጨው ጭልጥ! ስታረግ ጫት ቃሚ በሙሉ ተቴሌቪኑ ተሰድሮ የእንግሊዝ ጨዋታ ሲመለከት ነበር። የጦቢያን ሆድ ድርቀት አበበን ተመስሎ «የእንግሊዝ ጨው» እንደ ቅዘን አርጎ አሰወገደላት። ሆይ ጉድ ሆይ ጉድ ነው ጃል! ሆይ ጉድ!
ReplyDeletetikikil new
ReplyDeleteSelam Dn. Daniel,
ReplyDeleteYou observed it well what is happening. But you did not indicate why this is happening. It is ok to have information and admire well performing one but should not be as an addiction. I am not economist but I feel that there are some service (non- produce) based business like entertainments might their consumption influence over weighs the actual benefit they provide. But they are the ones that can easily be sold and able to flood the public. Most games in general and foot ball in particular seems to have such character. Articulated media services are the ones that maneuver our mind to be attracted to these. These media usually have access those who are less occupied. I mean those who have relaxed time than those who are overwhelmed by their daily assignments. It is less true that people who are more tightened with serious job have interest to games. On the other hand if there is apple time (I did not want to say idle but that is exactly what I mean), people may seek where to spend it. Game might be appropriate compared to other addictions. Yet, all addictions (including being workaholic-person who works much) are dangerous in any of their form though the degree varies. Hulum bemeten behon tiru new. yanesahiw neger gin eyazinana lik likachinin new yenegerken. Enameseginalen. But Seriously, such things need critical analysis regarding their socio-econimic impact on others. It some times is on purpose that we less developed countries are exposed to these kind of dumps. Go in many other developed country most follow little even the foot ball going on in their own country. Some times internal strength (eg. if our foot ball is strong) repeals the influence of others. If we are inferior it is a must to dream others'. Articles of you kind really influence many to let them think what is going on. Please go it! Siletarik meglebabet gin yemitiketelewan sinign lagarachihu asebku.
የተገላቢጦሽ
ላሟ ኮርማ ሆና በሬ ጥጃ ወልዶ
የተዘራው ጠፍቶ ያልተዘራው ታጭዶ፣
ቁልቁለት ተወጥቶ አቀበት ተወርዶ፣
ፈረስ ቀፎ ገብቶ ንብ በጋጣ ታስሮ፣
ዓሣ በገደል ላይ በባሕር ዝንጀሮ፣
ጠል ያደረቀውን ሐሩር አለምልሞት፣
ውሃ ያቆሸሸው አቧራ አፅድቶት፣
እንደው በጠቅላላው የዚህ ዓለም ነገር፣
የተገላቢጦሽ ሆነብኝ እያደር፡፡
ዮ. ሠርፀ (J. Sertse)-1994 ዓ.ም.
ዛሬ ከአርሰናል ተሰናበት ኩኝ ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ሁለት ግዜ በንዴት ላፕ ቶፔን ሰብሬለሁ
ReplyDeleteበዜህ ጽሁፍ እራሴን ተመልክቻለሁ እስቲ 90 ደቂቃ ይቅርና 45 ደቂቃ ለጻፍ ልሞክር
በዚህ ፋንታ የሃገሬን ልጆች ጨዋታ ልመልከት። ለልጆቻችን የመጫወቻ ቦታ በተመለከተ
ውጤት ያለው ሥራ ለመሥራት እንነሳ
Yes, it is better to stop supporting arsenal as it is distracting for you.And,please recall that the critical message of the writer is giving attention for our developing football.And all of us have also a national obligation to contribute for our football and whatever.There fore ,please entertain football weather Arsenal or what so ever but never and ever make personal distraction .But the question is the team/Arsenal/have constructed their Stadium means the owners are accumulating wealth .but what about us.
Deletegood decision guy.i like u.
DeleteBetam des yemil akerareb new. Lemiastewul Ejig betam tekami kumnegerochin yazele, ke'ande besal menfesawi temeramari Yemitebek Tsihuf new. Deginetu ene yequas neger besirinjim biwogugni ayigebagnim. endet des yilal enquanm aligebagni; ahunm lezelalemu ayigibagni.
ReplyDeleteDn, Daiel Egziabiher Tsegahin yabizalih berta
Metalem A. Ze-Kombolcha, Debub Wollo
ayesemame enge des yelale
ReplyDeleteTEKURET LEMANENTACHEN YESETE ENA GENE CUBA YETMASESME SEMECHALUJE MERESME YETENA ENDAL SEMECHALUYE GEN LEMEN MESHAFE NEGREN HULU BELEKE ADERGE YELE YELE EDME ENA TENA YESHE Teweldu kuche belo meweyaet yegbwal!!!
ReplyDeleteይህ ነጻነትኮ እንኳን በፖለቲከኞቹ ላይ በጊዮርጊስና በቡና፣ በደደቢትና በንግድ ባንክ፣ በመብራት ኃይልና በአዋሳ ከነማ ቡድኖች ላይ እንኳን አይገኝም፡፡ ይህን ይህን ሳስበው እንኳን ኖራችሁ ያሰኘኛል፡፡ እናንተ ባትኖሩ ስለምን እንከራከር ነበር?
ReplyDeleteአይ ዲ/ን ጭራሽ የእንገሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አላወቀንም ትላለህ የእኛ ልጆች የእንገሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ተጫዎች እስከ ጫማ ቁጥሩ ሲያዉቁ የእኛን ተጫዋች ሰ ግን አያቁም
ReplyDeletehi
ReplyDeleteBaygermachu Enem dirom alawqachewum bawqachewum gudaye aydelum gn hule yemiqochegn betkkil slegna hager wondmoche newu slemayawquachewu sewoch ers bers sitalu sinaqoru sidebadebu yasazenugal.
ReplyDeleteNice article, keep doing the great work!!!
ReplyDeleteይኼው ሂሳብ በእናንተ ከመማር በላይ ምን እናድርግ እንግዲህ፡፡ ሜሲ ትናንት ሦስት ጎል አገባ፣ ዛሬ ደግሞ ሁለት ጎል አገባ፤ በጠቅላላው ስንት ጎል አገባ? ካልተባሉኮ ልጆቻችን ሊደምሩ አልቻሉም፡፡ ከአሥራ አንዱ የፉልሃም ተጨዋቾች ሁለቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ ከወጡ ስንት ተጨዋቾች ሜዳ ላይ ይቀራሉ፤ ካላልን ማን ይቀንስልናል፡፡ ሩኒ በሳምንት የሚያገኘው ገቢ 120 ሺ ፓውንድ ነው፡፡ በዓመት 52 ሳምንቶች አሉ፡፡ ሩኒ በዓመት ስንት ያገኛል? ካላልን ማን ያባዛልናል? እና ይህንን ሁሉ ሆነን አታውቁንም? እኛ ብቻ ነን የምናውቃችሁ?
ይሄን ለባሌና ለልጄ ማስታወሻ እሰጣቸዋለሁ፡፡
ReplyDeleteእድሜና ጤና ይስጥህ
wtbhm
<...‹እጅህን ስጥ አለኝ ፈረንጅ› አሉ የዋሑ ቴዎድሮስ፤ እስኪ ቀና ብለው ይመልከቱ፤ ስንቱ እጁን ብቻ ሳይሆን ልቡንም እንደሰጠልዎ፡፡...አይ አርሴና ማንቼ የማትሠሩን ነገር የለ፡፡>
ReplyDeleteexcellent artical?????????
ReplyDeleteደስ በሎኝ አነባለሁ፣ እስቃለሁ፣ አውቃለሁ ደግሞም አዝናለሁ፡፡ ጽሁፎችህን በናፍቆት እጠብቃለሁ፡፡ እግዚአብሔር ረዥም ዕድሜ ይስጥህ፤ የምታወጋን አትጣ፡፡
ReplyDeleteጽሁፍህን ሳነብ እራሲን እየታዘብኩ እጅግ በጣም ተመስጨ በራሲ እያዘንኩና እየሳኩ ተምሪበታለሁ አመሰግናለሁ ያላየሁትን እንዳይ ስላደረከኝ::
ReplyDeleteእግዚአብሄር ይባርክህ! ለሁሉም ማስተዋልን ይስጥልን፡፡
ReplyDeleteጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ReplyDeleteጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ
እእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእእ
ፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ
--------
ReplyDelete!!!እናንተ Internet ሲቋረጥ ግራ የሚገባችሁ ጋዜጠኞች (internet ተርጓሚዎች) ግን ወዮላችሁ !
ReplyDeleteምን በእግር ኳስ ብቻ ብዙ ብዙ ብዙ ነገራችን ረስተን እኛም ተረስተናል።
ReplyDeletewow Dani God bless you.Even though i like foot ball very much i have to accept the reality on the ground.we Ethiopian should have to look in ourselves.Please wake up country fellow men!
ReplyDeleteአንተ በጥቂት መሥመር በቃለ ኃይል እንዳስቀመጥከው ሕዝቡ በእግር ኳስ አቅጣጫውን ካልሳተ የሥራ አጥነት ጥያቄ፣ የኑሮ ውድነት ጥያቄ፣ የደመወዝ ጥያቄ፣ ... መንግሥትን አንድ ቀን የሚያሳድረው ይመስልሃል?
ReplyDeleteአሁን ኳሱ ረገብ ሲል ደግሞ ሌላ አጀንዳ እንጠብቃለን፡፡ በመላኩ ፈንታ የጀመረው አዲስ የቡና ቁርስ እስከ ነሐሴ መጀመሪያ ቀለባችን እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ዲያቆን ዳንኤል ጽሑፍህን ካነበብኩ በኋላ ሁለት አስተያየት ልሰጥህ ተነሳሁ - ምናልባት ቢጠቅምህ። አንደኛው እነዚህ ወጣቶች አንተ እንደጠቀስከው ስለታሪካቸው፣ ስለባህላቸው ወዘተ ለማወቅ ሌላውን ማስወገድ (በአንተ ምሳሌ በእንግሊዝ ጨዋታዎች መዝናናት) የግድ የማያስፈልጋቸው መሆኑ ነው። ሁለቱ ተጻራሪ ወይም በፈረንጁ mutually exclusive አይደሉምና ነው። ወጣቶች የራሳቸውን ታሪክ፣ ባሕል፣ ማንነት ወዘተ ጠንቅቀው አውቀው በሌላውም ቢዝናኑ ጉዳት የለውም። አንተም የምትጠላ አይመስለኝም። የግድ ሁሉ ሰው የታሪክና የባሕሉን መጻሕፍት እያሳደደ ማንበብ አለበት ካላልክ (እያንዳንዳችን እውቀትን የምንገበይበት መንገድ በተፈጥሮ ስለሚለያይ አይቻልም) እስቲ እነዚህን ልጆች እንደኳሱ የውጭውን ፊልም ጥበብ ተጠቅመህ እንደ "ገመና" ወይም "ሰው ለሰው" ድራማ የአገራቸውን ታሪክና ባሕል በጥሩ ቅንብር በምስልና በድምጽ በተከታታይ በቴሌቪዥን አቅርብላቸውና ከዚያ በኋላ ይህን ወቀሳ ብትጽፍ ያምራል። ይህ ሳይሆን ይልቁንም በተጠና መንገድ እየቀረበላቸው ያለው ይኸው ኳሱ ብቻ ከሆነ ጣትህን ማዞር ያን እያደረገ ወዳለው ነው። ምናልባት ይህ የፊልምና የትያትር ባለሙያዎች ኃላፊነትም ሊሆን ይችላል። አይታወቅም። ውጤት የሚያመጣ ጥናታዊ ጽሑፍ እንዲሆንልህ እነዚህን የአገራችንን የፊልምና የትያትር ሰዎች "ለምን በታሪክና ባሕል ላይ ጥሩ ሥራዎች አታቀርቡም?" ብለህ መጠየቅ ሊኖርብህ ይችላል። በርግጠኝነት እነርሱም በምን ምክንያት ይህን የመሰለ ሥራ እንደማያቀርቡ በምን ዓይነት የሥራ ድባብ ውስጥ እንዳሉ ይነግሩሀል። ያንንም በግልጽ ጻፍልን። ከዚያ ችግሩ እነርሱ ዘንድ ወይም ሌላ ቦታ ከሆነ የት እንዳለ አንተም እኛም እንደርስበትና በዚያ ላይ ደግሞ ግፊት ማድረጋችን ይቀጥላል። ውጤትም እናገኛለን - እውነተኛ ምንጩን ስለምናውቀው። ከዚያ በመለስ ጽሑፉ ውጤት የሌለው ድካም እንዳይሆንብህና አንተንም እንዳያስተችህ መጠንቀቅ ጥሩ ስለመሰለኝ ነው። ሁለተኛውን ሌላ ጊዜ እጽፍልሐለሁ። በርታ ወንድሜ!
ReplyDeletessew bemeselew neger mezinanat yichilal enya linigedibew ayichalenim anid ante bichahin bitichoh semi endemayinorih laregagitilih ewodalew ante bicha rasihin endetekorkari mekuterim adega alew andande yhe sew yemisifibet eries silata bado kemihon bileh post yemitaderig yimesilenhal
ReplyDeletemeftihewochin metekomim limed
At first place, why do we bother whether an English coach knew us or not ? There are many people who do not know where Ethiopia is at. So what ? It is someones ignorance not our business at all. Besides the coach does not has to know us. Does he ? It is not his main concern to him. Besides Danny, we had a great country and great history but at the moment we are NOTHING! We reached the point where our history does not make sense rather it looks like tale. All the youngsters are giving up, tiered of thinking, and want to relax somewhere, somewhere he can forget the stress he has. Are not they the one who got nowhere to go somewhere? Why do not you write something better which is white true and beneficial to the people if you have this chance ? Why do not you write how these poor Ethiopian young generation can not go to public library, gym, universities...Why do not you write who is rich and how ? Who is poor and how ? There are huge scenarios at hand rather than wasting time in minor problems .........
ReplyDeleteThank you the "anonymous" who posted this comment. You nailed it. Lets call a spade a spade. Actually only delusional ppl think that an English coach may know the names of Ethiopian players. For what reason he would know them? Are they giving him any profit or anything at all? 99% Americans do not even know where Ethiopia is on the map. Get over it and work hard to improve your importance period.
Deleteዳኒ እንኳን ለትንሳዬው ብርሃን አደረሰህ አደረሰን እንዲሁም በሰላም አድረሶ ለመለሰ ጌታ መድሐኒት ዓለም ምስጋና ይግባው፡፡ ይህ ጉዳይ ሁላችንም ቤት የሚዳስስ ነው፡፡ የእግር ኳስ ጨዋታ አዝናናኝነቶ መልካም ሆኖ ሳለ እንዲሁም አንዳንድ የሚከሰቱት ነገሮች ላይ ለመማሪያነት መተርጎሙ በአንድ ወቅት በዚህ ጦማር ላይ በ Wednesday, April 25, 2012 “የነፍሴ ጨዋታ” በሚል ርዕስ ጹሁፍ ላይ እንደቀረበው አይነት አስተማሪነቱ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ውስጡ ገበቶ ሰምጦ ማንነትን መርሳት ግን ክፉ በሸታ ነው ይህ ብቻ አይደለም የአፍሪካን አንድነት መስርተን አፍሪካዊነን ማለት የሚከብደን ሆነናል ማንነታችን ከማጣታችን በፊት ልንባንን ይገባል ልጅ ዳኒ የመለኮት ማደሪያ ድንግል ማሪያም ትጠብቅህ፡፡
ReplyDeleteበአሁኑ ሰዓት በ4 ብር 90 ደቂቃ ሙሉ ከኳስ ዉጪ ምንም የሚያዝናን ነገር የለም:: ሻይ እንኳን እንጠጣ ብንል ከዚያ በላይ ያስፈልግናል :: ስለዚህ በኳሱ ተዝናንተን ጋዜጠኞቹ በነፃ በሚያሰሙን ትንተና አወራርደን መተኛት ነዉ:: የእንግሊዝ ክለቦች የሚሉትን ሰምተዉ የሚያስተካክል ለሚመስላቸዉ ጋዜጠኞችና ተሳታፊዎች ግን ፅሁፉ በራሳቸዉ ንግግር እና ተግሳፅ አፍረዉ ባይደበቁም ስቀዉ የሚታረሙ ይመስለኛል
ReplyDeleteAndand Anonymusoch ewnetu sinegerachhu ATBESACHU Ish?
ReplyDeletei want to say something for football supporter in side of dani, he said and what i understand our people see football like a work rater than refreshment center.you can support European football, but it must have limit.
ReplyDeletemost of the people give reason why they impressed this much in football.
1.. football is cost effective .
2..it is best place rather than a passing time in chat,drinking .but i say it is not the real solution to alleviate the above problem to make cost effective refreshment center make change with in our economy,and finally if you pass your time in talking about football to compensate your time pass in chat,there is no any difference b/n the because all your method is doing cause fear to face the problem that is way you you go to football make another method to kill your time rather than doing work.
Yemanreba Atela tewld nen!Abatun ayawk ayatun yetykal yluhal endhe new
ReplyDeleteውይ ውይ ውይ ዳኒዬ አምላክ በነገር ሁሉ ይባርክህ!ጩኸቴን ነው የጮህክልኝ...የኔ ዘመን ወጣት በፈቃዱ ለዚያውም ሃገሩ ላይ ተቀምጦ ቅኝ የሚገዛ ሰነፍ ነው! ለራሱ ታሪክ የማይደንቀው ለጠገበ ማጨብጨብ ብቻ
ReplyDeleteI think this is one of the tool that the western use to play their political game when we all are focusing on such things they do their business it does not mean that we should not entertain but let us question our self that all these things like football films and so on are used as an entertainment?
ReplyDeleteDani Keep it up I hope that one day we all wake up
ጽሁፍህን ሳነብ እራሲን እየታዘብኩ እጅግ በጣም ተመስጨ በራሲ እያዘንኩና እየሳኩ ተምሪበታለሁ አመሰግናለሁ ያላየሁትን እንዳይ ስላደረከኝ::
ReplyDeleteጽሁፍህን ሳነብ እራሲን እየታዘብኩ እጅግ በጣም ተመስጨ በራሲ እያዘንኩና እየሳኩ ተምሪበታለሁ አመሰግናለሁ ያላየሁትን እንዳይ ስላደረከኝ::
ReplyDeleteYegaemal Aheya kaJebe Yekaremal
ReplyDeleteI LIKE UR ARTICLE AND ANYTHING U WRITE !
ReplyDelete" Atse Tewodrose yehan beyayu nuro, yetetutin tiyet beserjery yasotut neber"
Atse Tedrose ena Yohannis teshewedu,lezi bersu fekade kign limegeza hizeb hiyewetachewin selesewu.
GOOD OBSERVATION ???????????
ReplyDeleteGOOD OBSERVATION
ReplyDeletebetam yemigrem eyeta berta
ReplyDeleteስማችሁን ቡዳ እንደያዘው ሰው ስንጠራ የምንውለው? p/s write on it, buda (What is buda? who is buda ? how?....) . 10q
ReplyDeleteegziabhir yibarkeh
ReplyDelete