እውነት እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ዘለዓለማዊ ነው፡፡ እውነትም
ዘለዓለማዊት ናት፡፡ <የሰዎችን ልጆች ጥላዎች> ሲያስበረግጉ ከኖሩት ነገሮች አንዷ እውነት ናት፡፡ ‹የሰዎች ልጆች
ጥላዎች› ያልኩት ሰው ከሚለው ስያሜ ለመለየት ነው፡፡ እነዚህ እውነትን የሚፈሯትና የሚጠሏት አካላት ሰዎች አይደሉም፡፡ ሰው
እውነትን ይወዳል፣ በእውነትም ይኖራል፣ ለእውነትም ይሞታል፡፡ እርሱ በእውነት እጆች የተፈጠረ ነውና፡፡ ነገር ግን <የሰው
ጥላዎች> አሉ፡፡ ሰዎች ያልሆኑ፤ ነገር ግን የሰው መልክ ያላቸው፣ ራስ ያላቸው ነገር ግን አእምሮ የሌላቸው፣ ሆድ
ያላቸው፣ ነገር ግን ልቡና የሌላቸው፣ አፍ ያላቸው ነገር ግን አንደበት የሌላቸው፣ ጉሮሮ ያላቸው ነገር ግን አንገት
የሌላቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች አይደሉም፡፡ እነዚህ ‹የሰው ጥላዎች› ናቸው፡፡ ጥላ እንደሚጠፋው እነርሱም ይጠፋሉ፤ ጥላን ብርሃን
እንደሚያጠፋው እነርሱንም የእውነት ብርሃን ያጠፋቸዋል፡፡
በሰሞነ ሕማማት የተፈጸመው ድርጊት ይኼው ነበር፡፡ የሰው ጥላዎች እውነትን ለመግደል ያደረጉት ሙከራ፡፡ እነዚህ የሰው
ጥላዎች ራሳቸውን እውነተኛ ከማድረግ ይልቅ አውነትን በመግደል ሐሰተኛነታቸውን መሸፈንና እንደማንነታቸው ሁሉ በእውነት ጥላ መኖር
ነበር የፈለጉት፡፡ ክርስቶስ እውነት ነው፤ ያስተማረውም እውነት ነው፤ ለሐሰት አንድም ቦታ ሳይሰጥ የገለጠው እውነትን ነው፡፡ ይህ
እውነት ግን መኖሪያቸውንና ማንነታቸውን ሐሰት ላደረጉት ‹የሰው ጥላዎች› አልተመቻቸውም፤ አመማቸው፤ በየጊዜው ራሳቸውን እንዲያዩና
ራሳቸውን እንዲወቅሱ ስላደረጋቸው አመማቸው፤ የእውነት መኖር ሐሰትን ማንጸርያ ስለሚያመጣባት አመማቸው፤ ብቻቸውን ሆነው ያለምንም
ማንጸሪያ ነን ያሉትን ሁሉ እየታመኑ እንዲኖሩ ነበር ሃሳባቸው፤ ነገር ግን እውነት መጣችና ከጎናቸው ስትቆም በቀላሉ ጥላው ከብርሃኑ
ተለየ፡፡ ብርሃን ከሌለ ጨለማን፣ ቀን ከሌለ ሌሊትን፣ ሕይወት ከሌለ ሞትን፣ ክብር ከሌለ ውርደትን፣ ነጻነት ከሌለ ባርነትን በምን
መለየት ይቻላል፡፡
እነዚህ በሰሞነ ሕማማት እውነትን ለመግደል የተነሡት የሰው ጥላዎች ሦስት ነገሮችን ነበር የተጠቀሙት፡- ሥልጣን፣
ገንዘብና ያልተማሩ ሰዎችን፡፡ ይህ ደግሞ በእነርሱ የተጀመረ ወይም በእነርሱ ያቆመ አይደለም፡፡ በዓለም ላይ እውነትን እንገድላለን
ብለው የተነሡ አካላት ሁሉ የሚጠቀሙት እነዚህን ሦስቱን ነው፡፡ ከሐዋርያት መካከል ይሁዳን በገንዘብ ገዙ፡፡ ምስክሮችንም ገንዘብ
እየከፈሉ አዘጋጁ፡፡ በሥልጣናቸው ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ዳኛ ራሳቸውም አስፈጻሚ ሆኑ፡፡ ጲላጦስ እንኳን እውነቱን ተረድቶ ‹የለም፣
ክርስቶስ ምንም ነገር አላደረገም› እያለ ሲሞግታቸው እነርሱ ግን ያልተማሩትንና ከችግራቸው በቀር ሌላ ነገር የማይረዱትን ሰዎች
ሰብስበው በጲላጦስ ላይ ተነሡበት፣ በሥልጣኑም አስፈራሩት፡፡
በዓለም ላይ ሥልጣን፣ ገንዘብና ያልተረዱ ሰዎች ሲገጥሙ እውነት ፈተና ውስጥ ትወድቃለች፡፡ ሥልጣንን እውነት ካልገራቺው
የማጥፊያ መሣርያ ይሆናል፣ ገንዘብንም እውነት ካልገራቺው የመግደያ መርዝ ይሆናል፣ ማኅበረሰብም እውነትን ለመረዳት የሚያስችል ዐቅም
ከሌለው የጥፋት ተባባሪ ማድረግ ቀላል ነው፡፡ ለእነዚህ ለሦስቱም እውነት ወሳኝ ናት፡፡ ብዙ ጊዜ ግን እነዚህ ሦስቱ እውነትን አይፈልጓትም፡፡
እውነት ካለች ገደብ አለና፡፡ ባለ ሥልጣናት በሥልጣናቸው ላይ ገደብን አይፈልጉም፣ ባለ ገንዘቦችም በገንዘባቸው ላይ ልክና መጠን
እንዲደረግበት አይሹም፣ አንዳንድ ማኅበረሰብም ለዕውቀት የሚከፈለውን መሥዋዕትነት አይሻውም፡፡ ስለዚህም እውነትን እንደ ጠላት ያዩዋታል፡፡
ዓርብ ዕለት እውነት ለፍርድ ቀረበች፡፡ በታሪክ ብዙ ጊዜ እንደታየው እውነት ስለ ራሷ ትመሰክራለች እንጂ ከእውነት
ጋር የሚቆም አካል የሚገኘው በጭንቅ ነው፡፡ ከእውነት ጋር መገኘት ዋጋ ያስከፍላልና፡፡ ክርስቶስ በዕለተ ሆሳዕና በአህያዋና በውርንጫዋ
ላይ ተቀምጦ ሲመጣ ‹ሆሳዕና› እያሉ የኢየሩሳሌምና የአካባቢዋ ሕዝብ በሆታ ተቀብለውት ነበር፡፡ ሆሳዕና ማለትም ‹አሁኑኑ አድን›
ማለት ነው፡፡ አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ አበርክቶ ሲያበላቸው ‹አሁኑኑ ንገሥ› ብለው አስጨንቀውት ነበር፡፡ አሁን ጊዜ ፊቷን
ስታዞርና እውነት ስትከሰስ ግን እነዚያው ሰዎች ካልተሰቀለ ሞተን እንገኛለን አሉ፡፡
እውነት በተከታዮቿ ብዛት አትመዘንም፣ በደጋፊዎቿ ብዛትም አትለካም፤ እውነት ደጋፊም ብታገኝ ባታገኝ፣ ተከታይም ብታፈራ
ባታፈራ፣ ምንጊዜም ብቻዋን ናት፡፡ እውነት የምትቆመው እውነት ስለሆነች እንጂ ሌላ የሚያቆማት ኃይል ስላለ አይደለም፡፡ እውነት
ራሷ ኃይል ናትና በራሷ ትቆማለች፡፡ ለዚህ ነው ሐሰተኞች ራሳቸውን የሚያስመኩት በደጋፊዎቻቸው፣ በአባሎቻቸው፣ በቲፎዞዎቻቸውና በተከታዮች
ብዛት የሚሆነው፡፡ ሐሰት ያለ ቲፊዞና ድጋፍ ብቻዋን አትቆምምና፡፡ ሐሰት እንደ ሐረግ መደገፊያ ትፈልጋለች፡፡ ሐሰት ዐቅም ስለሌላት
የገንዘብንና የሥልጣንን ዐቅም መጠቀም ትፈልጋለች፡፡
አንዳንድ ሰዎች እውነትን የሚከተሏት ሐሰት መስላቸው ነው፡፡ አንዳንዶች በእውነትና በሐሰት መካከል ያለውን ልዩነት
አይለዩትምና፡፡ ያንን የመለየት ዕድል የሚያገኙት እውነት መሥዋዕትነት ማስከፈል ስትጀምር ነው፡፡ ያን ጊዜ ከእውነት መሸሽ ይጀምራሉ፡፡
አንዳንዶች ደግሞ እውነት እንደ ሐሰት ጥቅም ብቻ የምትሰጥ መስላቸው ይከተሏታል፡፡ መሥዋዕትነቱ ሲመጣ ግን ይሸሻሉ፡፡ አንዳንዶች
ደግሞ እውነትን ለመሸከም የሚያስችል ዐቅም ሳይኖራቸው ከእውነት ጋር ይቆማሉ፡፡ ዐቅም የሚያስፈልግበት ጊዜ ሲመጣ ግን ጥለው ይሸሻሉ፡፡
የክርስቶስ ተከታዮች በአራት የተከፈሉት በዚህ ምክንያት ነበር፡፡ አምስት ገበያ ሞልተው ሲከተሉት የነበሩት ብዙዎች
እውነትና ሐሰትን መለየት አልቻሉም ነበርና ሲከተሉ ኖሩ፡፡ በዕለተ ዓርብ እውነት ከሐሰት መለየት ስትጀምር ግን ጓዛቸውን ጠቅልለው
ከሐሰት ጎራ ተቀላቀሉ፡፡ እንደ ይሁዳ ያሉት ደግሞ እውነትን ለጥቅም እንጂ ለእውነትነቷ አልተከተሏትም ነበር፡፡ በሂደት ግን ይሁዳ
ከእውነት ያሰበውን ምድራዊ ጥቅም አላገኘም፤ ስለዚህም በጊዜ ወደምትሻለውና ወደምትስማማው ሐሰት ኮበለለ፡፡ የፈለገውንም ጥቅም አገኘ፡፡
ሌሎቹ ሐዋርያት ደግሞ እውነትን ለመሸከም የሚያስችል ዐቅም አልነበራቸውም፡፡ ስለዚህም ፈታኟ ሰዓት ሰትመጣና የመሥዋዕትነቱ ጊዜ
ሲቀርብ መምህራቸውን ጥለው ተበተኑ፡፡ ዮሐንስ ግን የእውነትን መሥዋዕትነት ተረድቶ ነበረ፡፡ መከራውንም ችሎ እስከ እግረ መስቀል
ደረሰ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስን ከዮሐንስ የለየው እውነትን ለመሸከም የሚያስችል ዐቅም ማጣት ነው፡፡
እውነትን የሚያስችል ዐቅም ማለት የዮሐንስ ዐቅም ማለት ነው፡፡ ያንን ራቁቱን የተሰቀለውን፣ ሞት የተፈረደበትን፣
አላፊ አግዳሚው የሚተፋበትን፣ በጎኑ የተሰቀሉ ሽፍቶች እንኳን የሚቀልዱበትን፣ ደቀ መዛሙርቱ ጥለውት የሄዱትን ጌታ ‹እከተለዋለሁ፣
ከእርሱ ጋር ነኝ› ብሎ መቆም ውሳጣዊ ዐቅምን ይጠይቃል፡፡ አሁን በመስቀል ላይ የሚታየው ጌታ በዚያ ሰዓት እንጀራ እያበረከተ፣
ዓይነ ሥውር እያበራ፣ ሽባ እየተረተረ፣ ተአምራትና ድንቆች እያደረገ አይደለም፡፡ ተላልፎ ተሰጥቶ ምስኪን በመሰለበት ጊዜ ነው ዮሐንስ
አብሮ የቆመው፡፡ በዚህ ጊዜ አንዳች ክብርም ሆነ ጥቅም የለም፣ ስድብና ግልምጫ እንጂ፤ በዚህ ጊዜ አንዳች ሥልጣንና ዝና የለም
ተዋርዶና ንቀት እንጂ፡፡ ይህንን ሁሉ ለመቻል ነው ከእውነት ጋር የመቆም ዐቅም የሚያስፈልገው፡፡
የሰው ልጅ እውነትን ለመግደል እንዲጥር የሚያበረታቱት ሁለት የማሳሳቻ ወቅቶች ናቸው፡፡
በእውነት ሂደት ውስጥ ካሉት ሦስት ወቅቶች መካከል ሁለቱ ወቅቶች አሳሳች ወቅቶች ናቸው፡፡ ሦስቱ ወቅቶች የሁካታ
ወቅት፣ የዝምታ ወቅትና የትንሣኤ ወቅት ናቸው፡፡ ‹የሁካታ ወቅት› ሥልጣን፣ ገንዘብና ያልተረዳ ማኅበረሰብ አንድ የሚሆኑበት፣ ፍትሕ
ተደፍጥጣ ፍርደ ገምድልነት የሚነግሥበት፣ ለምን? እንዴት? የሚል ጥያቄ ቀርቶ፣ ይውደምና ይቅደም፣ ይጥፋና ይሙት፣ ‹ውረድ በለው
ግፋ በለው› ቦታውን የሚይዙበት፤ ወቅት ነው፡፡ ያኔ ማንም ሊቅ፣ ማንም ሽማግሌ፣ ማንም የእምነት ሰው ‹ተዉ› ቢል የሚሰማው የለም፡፡
ሁሉም እንደ አህያ ጆሮ እንደ ጦር ጉሮሮ አንድ ሆኖ ‹ስቅሎ ስቅሎ› እያለ የሚጮኽበት ጊዜ ነው፡፡
ይህ ወቅት ሥልጣን ያላቸው፣ ገንዘብን የያዙና ያልተረዳን ማኅበረሰብ መቀስቀስ የቻሉ ሰዎች እውነትን መግደል የቻሉ
የሚመስላቸው ጊዜ ነው፡፡ እውነት አብሯት የሚቆም የምታጣበትና ራቁቷን በገዥዎች ፊት የምትቀርብበት ጊዜ ነው፡፡ እንደሚሸለት በግ
በሸላቾቿ ፊት ዝም የምትልበት ጊዜ ነው፡፡ ጌታም የተገረፈው፣ የተሰቀለውና የሞትን ጽዋ የቀመሰው በዚህ የሁካታ ወቅት ነው፡፡ ለቀያፋና
ለሐና፣ ለአይሁድና ለሮማውያን እውነትን ገደልን ብለው ደስ አላቸው፡፡ የጨረሱም መሰላቸው፡፡ ይህ ጊዜ ኀሙስ ሌሊት ተጀምሮ ዓርብ
አሥራ አንድ ሰዓት የተፈጸመ ነው፡፡ ይህ ወቅት ሲያልቅ ሁለተኛው ወቅት ይጀምራል፡፡ ይህም የዝምታው ወቅት ነው፡፡ የዝምታው ወቅት
እውነት ድምጽዋን የምታጠፋበት፣ በመቃብር ውስጥ የምትውልበት፣ የእርሷ ታሪክ የሞት ታሪክ ነው ተብሎ የሚወራበት ረዥሙ ጊዜ ነው፡፡
ዓርብ አሥራ አንድ ሰዓት ተጀምሮ ቅዳሜ ለእሑድ እኩለ ሌሊት ድረስ የሚደርስ ነው፡፡ ሐዋርያት በዚህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠው ነበር፡፡
በኤማሁስ መንገደኞች ላይ እንደታየውም አንዳንዶቹ ነገሩን ወደ ትዝታ ቀይረውት ነበር፡፡ ሌሎቹም ክስተት አድርገው ቆጥረውትም ነበር፡፡
ሥልጣን፣ ገንዘብና ያልተረዳ ማኅበረሰብን የያዙት አካላትም በመቃብሩ ላይ ድንጋይ ገጥመው በወታደር ማስጠበቅ ጀምረው ነበር፡፡
ይህ ወቅት ነው አንዱ የማሳሳቻ ወቅት፡፡ ይህ ወቅት ባለጊዜዎቹን፣ ለእውነት ለማድላት የሞከሩትንና ከሐሰት ጋር የቆሙትን
አካላት ያሳስታል፡፡ ባለጊዜዎቹ ሁሉንም ነገር በገንዘብና በሥልጣን እንጨርሰዋለን እንዲሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ለእውነት የሚያደሉትም
ከእውነት ጋር መቆም ጥቅም የለውም፤ እውነት አታዋጣም እንዲሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ከሐሰት ጋር የቆሙትንም መንገዳቸው ትክክል ለመሆኑ
ማረጋገጫ አድርገው ይወስዱታል፡፡ ይህ ሁሉ ግን እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነው፡፡ በርግጥ ከወቅቶቹ ሁሉ ረዥሙ ጊዜ ይህ ነው፡፡ እውነት
ተዳፍና ለረዥም ጊዜ የምትቆይበት አሳሳች ወቅት ነው፡፡ ይህ ወቅት ፍርሃት የሚወድቅበት የድንጋጤ ወቅት ነው፤ ይህ ወቅት አንዳንዶችም
ተስፋ የሚቆርጡበት ወቅት ነው፡፡
በዚህ መጨረሻ ነው ሦስተኛዋ ወቅት የምትመጣው፡፡ የትንሣኤ ጊዜ፡፡ ቅዳሜ ለእሑድ እኩለ ሌሊት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር
ክፈቱልኝ ሳይል፣ ጠባቂዎቹ እንኳን ሳያዩት ክርስቶስ ተነሣ፡፡ ገንዘብና ሥልጣን፣ ያልተረዳም ማኅበረሰብ አንድ ላይ ሆነው እውነትን
ሊገድሉ፣ እውነትንም ሊቀብሩ አለመቻላቸውን የሚረዱበት፤ አሸናፊዎቹ የሚሸነፉበት ጊዜ ደረሰ፡፡ እውነት ከመቃብር በላይ፣ ሐሰትም
ከውርደት በታች ሆነች፡፡ የሥልጣን ጡጫ፣የወታደር ኃይል፣ የገንዘብ ዐቅም፣ የብዙዎች ጩኸት፣ እውነትን ገድሎ ሊቀብራት፣ ቀብሮም
ሊያስቀራት እንደማይችል ታወቀ፡፡
ከእውነት ጋር ሲጣሉ ለሚኖሩ ሁሉም ትምህርት ይሆን ዘንድ፤ በዐርባኛው ቀን ሁሉም እያያት እውነት ዐረገች፡፡ በልዕልናም
ተቀመጠች፡፡ ከእውነት የተጣሉ የሰው ጥላዎች ግን ከመቃብር በታች
እነሆ አሉ፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፤ በሌላ ተመሳሳይ ሚዲያ መጠቀም ክልክል ነው
ለተወደዳችሁ
አንባብያን
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ምእመናንን በማስጎብኘትና በማስተማር
ላይ ስለነበርኩ የየዕለቱም መርሐ ግብር የሚያልቀው አምሽቶ ስለነበር ጽሑፎቹን ማዘጋጀትና ማተም አልቻልኩም ነበር፡፡ አሁን ተመልሻለሁ፡፡
እንደ ቀድሟችንም እንቀጥላለን፡፡ ብዙዎች አስባችሁ ጽፋችሁልኛል፡፡ ፈጣሪ ያስባችሁ፡፡
Truth truth truth ..... always truth...but who stands for truth in this false world????????????? since we are created by truth we have to stand and live for truth!!!!! Thank you Dani, well come back!!!
ReplyDeleteWellcome Dn. Dani. Kale hiwot yasemalin!!!
ReplyDeleteGirum nwe dn.daniel kalhywit yasmalen!
ReplyDeletekale hiwot yasemalin!!!
ReplyDeleteenkuan beselam temelesk. kalehiwot yasmaln
ReplyDeleteWelcome back dani, it's a nice article. Bezuwochachenen eyetefetatenen yalew ewnetin yemichefelekuat sewoch guday new. E/r lehulachin mastewal yisten
ReplyDeleteWell come Dn. Dani,really it is a good view...''ewnent hoy wodet nesh? maderiashse wodet new? ''..... yeminelebet gize lay nen be'betemengistu be'betekihnetum. bakachuhe entseleye.
ReplyDeleteWell come back senagn weetu!
ReplyDeletekalehiwot yasemalin tesfa mengiste semayatin yawursilin
ReplyDeleteጥሁፉ ሰምና ወርቅ ያለው ይመስላል…ያስፈራል!
ReplyDeletethank u dani,telke timirte new yeseteken
ReplyDeleteMelkam timhert. memhirachin yaqoyiln.tegbar lai yemiaul lib yistegn.
ReplyDeleteHappy Easter Dear brother DN Daniel
ReplyDeletewell come back, I'm relief I've got some thing which is I missed for two weeks for my soul. And our brother is safe.
Welcome back d/n Daniel
ReplyDeleteሰላም ወንድማችን!
ReplyDeleteእናንት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በዚህ በወንድማችን ጽሁፍ ውስጥ ምን እንዳስተዋልኩ ታውቃላችሁ?
እንደኔ ማስትዋል ሁሉም የሰው ፍጥረት በተለይም እኛ ኢትዮጵያውያን ’’ ጽሁፉ በአማርኛ ስለተጻፈ ጸሀፊውም ኢትዮጵያዊ ስለሆነ በተለይ እኛን ይመለከታል ብዬ ነው እንደዛ ማለቴ’’••• እውነት ለቅድስት ምድር ለኢትዮጵያና በውስጧ ለሚኖሩ ህዝቦቿ ለአንድነታቸው ለሰላማቸው ለእድገታቸው መሰረት ስልሆነ እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች እውነትና እውነተኞች••••••••ኢትዮጵያን ያስፈልጓታል። አይመስላችሁም?
የትንሳኤው ጌታ ኢትዮጵያን ይባርክ ህዝቦቿንም ከእውነት ጋር ተባባሪ ያድርግ አሜን!!
ልዑል ይባርክህ ወንድሜ ዳንኤል
SG Dallas TX
hi dani this arthicle is so great you thouch my feeling to night i realy learnes what i have to do the rest of my life . i think sam people do truth , thank u.
ReplyDeleteFor Truth lots of people scarified their life. Among those Socrates, Mahatma Gandhi, Martin Luther King and the like are stood on the side of Truth. But Jesus is Truth by itself. Thank you Daniel.
ReplyDeleteenquan dena metah danie
ReplyDeleteEdmena Tena yistilin Wendim Dn. Danieil. Geta yibarikih.
ReplyDeleteበእውነት ለእውነት ስእውነት እንድንኖር አምላክ ይርዳን :: በተረፈ የኢየሩሳሌም ቆይታህ አስደስቶኛል ፍጸሜውን ያሳምርልን!!
ReplyDeleteDane enqawn adersha wel come back !!!#
ReplyDeleteWELL COME BACK D/N DANI !!!!
ReplyDeleteSILE EWUNET MESBEK ENDET DES YELAL MESELACHILACHIHU. LONG LIVE DANI...
Thank you Dani
ReplyDeleteThank you!dani ahunem tsegawen yabezalehe.
ReplyDeleteWonderful analysis of Easter. LENE BELEH SEMA.
ReplyDeleteበዓለም ላይ ሥልጣን፣ ገንዘብና ያልተረዱ ሰዎች ሲገጥሙ እውነት ፈተና ውስጥ ትወድቃለች፡፡እውነት በተከታዮቿ ብዛት አትመዘንም፣ በደጋፊዎቿ ብዛትም አትለካም፤ እውነት ደጋፊም ብታገኝ ባታገኝ፣ ተከታይም ብታፈራ ባታፈራ፣ ምንጊዜም ብቻዋን ናት፡፡
ReplyDeleteso we should not be surprised that the truth in our time is also so much so pushed aside and fake things dominated us...........from fake laughter to fake democracy, from fake love to fake investment, it all the drama we see every single day and some of us crave for the TRUTH...but ourselves put it aside and expect from others...............when is the resurrection of TRUTH dani,for our country, church, society and individuals?????????????
ReplyDeleteGood article. God bless you Dn. Daniel!!
ReplyDeleteTHAnk YOU!dani qhy.
ReplyDeleteWelcome back Dani
ReplyDeletePlease if it is possible can u post the Jerusalem Journey and in what situation our DER SULTAN pls pls pls tanx.
wow Denik " ሰዎች ያልሆኑ፤ ነገር ግን የሰው መልክ ያላቸው፣ ራስ ያላቸው ነገር ግን አእምሮ የሌላቸው፣ ሆድ ያላቸው፣ ነገር ግን ልቡና የሌላቸው፣ አፍ ያላቸው ነገር ግን አንደበት የሌላቸው፣ ጉሮሮ ያላቸው ነገር ግን አንገት የሌላቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች አይደሉም፡፡ እነዚህ ‹የሰው ጥላዎች› ናቸው፡፡ ጥላ እንደሚጠፋው እነርሱም ይጠፋሉ፤ ጥላን ብርሃን እንደሚያጠፋው እነርሱንም የእውነት ብርሃን ያጠፋቸዋል፡፡""
MAY GOD bless u and ur family
bechinket senebetin enkuan dehna metah........egziabhar kante gar yhun
ReplyDelete"እውነት ትሰለስላለች እንጂ አትበጥስም" ይላሉ አባቶች:: እውነትና ንጋትም እያደር ይጠራል:: በዚህ አለም ስንኖር እስኪ ስለእውነት እንኑር; እውነትን እናፍቅር; እውነት እንናገር; አሁን አሁንማ መዋሸት በራሱ እንደ ብልጠት እየተቆጠረ ነው:: በተለይ በስልክ ከምናወራቸው ቁም ነገሮች መሐል ውሸት ጣል ካላደረግን እኮ ያወራን አይመስለንም::" ሀሎ የት ነው ያለኸው"- "አሁን ፒያሳ አካባቢ ነኝ" ግን እኮ ጭራሽ አዲስ አበባ ውስጥ አይደለም እንዲህም ይዋሻል ግን እስከ መቼ እንዲህ እንኖራለን ጎበዝ? ዳኒ እንኯን ደህና መጣህ:: እግዜር ያበርታህ::
ReplyDeleteThanks Dani!!!!!
ReplyDeletediro diro, sewoch siwashu keAf ena keJoro ayzelim neber:: ahun gizew yeinternet new:: yecomputer new::
ReplyDeletejilina computer degmo yeyazewun muchich adirgo aylekim::
Woyolachew lewashoch:: woyowlachew leQeTafiwoch::
Woyew woyew! woyewulachew::
Wondim Daniel esti ande adebabay yewetachihu sewoch semayawi tesfa alen bemil sayehon kezegenetena kehager fiqer antsar becha selezih ewenet silu yerasachewen ena yebetesebachewen nuro mesewat aderigew le ewenet mesewa'etinet eyekefelu yalutin sewoche lemisale yahil eskinder nega ena temesegen desalegn tinish lemetsaf enimokir ergit new ewenet bewestachew endalech enam andande dereq ewenetinim engafet enji gobez!!!
ReplyDeleteenkwan beselam beke aleke memeher
ReplyDeleteድንግል ማርያም ትባርክህ:: እኛም እየራቅናት ነውና ተገተን እንጸልይ!
ReplyDeleteእውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ReplyDeleteዋለ በአደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ
የሐሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው
ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድን ነው
ከቃሉ እብለትን ባያኙበትም
ዝምታውን አይተው አላዘኑለትም
ባላወቁት መጠን ጠሉት ካለበደል
ጥፋቱ ምን ይሆን የሚያደርስ ከመስቀል(፪)
የልቡን ትህትና ፍቅሩን ሳያስተውሉት
ቸሩ ጌታችንን አቻኩለው ሰቀሉት
እሩህሩሁን ጌታ ቸንክረው ሰቀሉት
ሞትን አስወግዶ ቢሰጣቸው ህይወት(፪)
ስለቸርነቱ ስድብን ከፈሉት
ስለ ርህራሄው የእሾክ አክሊል ሰጡት
ሀሞት እና ከርቤ ሆምጣጤ ደባልቀው
መራራ አስጎነጩት ጨክኖ ልባቸው(፪)
ፈውስን ለሰጣቸው ልባቸውን ሞልተው
አሉት ወንበዴ ነው ስቀለው ስቀለው
ከእጁ በረከትን የተሻሙ ሁሉ
ይጮሁ ነበረ ይገደል እያሉ(፪)
Thanks tewedaju Yilma
Deleteከፍርሐት፣ ከሥጋትና ከጭንቀት ነጻ ሆነው የሰላም እንቅልፍ ተኝተው ማደር የሚችሉት እውነትን የያዙና የሰው ደም የሌለባቸው ንጹሐን ብቻ ናቸው። ቃኤል ወንድሙን አቤልን ያለምንም ምክንያት ከገደለ ጀምሮ ፈሪና ተቅበዝባዥ ሆኖ ትንሽ ኮሽታ ሲያስደነግጠው የኖረ ሰው ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት የአቤል ደም ወደ እግዚአብሔር በመጮኹ ነበር። ዘፍ 3፡10። የጻድቅ ደም እንቅልፍ አያስተኛም።
ReplyDeleteዳንኤልን ያለምንም በደል በተራቡ የአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ያስጣለው የጥንቷ የባቢሎን የዛሬዋ ኢራቅ ገዢ የነበረው ሜዶናዊው ዳርዮስ እንቅልፍ አጥቶ ምግብም አልበላ ብሎት ሰላሙን አጥቶ አልጋው አልመቸው ብሎ ሲሰቃይ እንዳደረ ት/ዳን 6 ቁ 18 ላይ ይናገራል። ነቢዩ ኢሳይያስ “ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል ኢሳ 57 ቁ 21። የሰው ደም እንደ ውሃ ሲያፈሱ፣ ጻድቁን ሲኮንኑ፣ ኃጥኡን ሲያጸድቁ በፕሮፓጋንዳቸው ተሰውረው ትንሽ እድሜ ያገኙ ሁሉ ሰላም የላቸውም። for example 1.ኢሕአዴግ
ይህ ፓርቲ ከተመሠረተ ጀምሮ ያፈሰሰው ደም ወደ ላይ እየፈሰሰ አንገቱ ደርሶ እያነቀው በሞት ፍርሐት ውስጥ የሚኖር ተስፋ የሌለው ፓርቲ ነው። ነገር ግን ጽዋው ገና ስላልሞላ በሕይወት ያለ ግዙፍ ፓርቲ ይመስላል። ኢሐዴግ የሕጻናት፣ የወጣቶች፣ የሽማግሌዎች፣ የምሑራን፣ የመሐይምናን፣ የባልቴቶች፣ የወታደሮች ወዘተ ደም ወደ እግዚብሔር እየጮኸበት እንቅልፍ ያጣ ድርጅት ነው። እውነተኛ ሰዎች ያስደነግጡታል በራሱ አይተማመንም፣ የቃየልን መንፈስ ተዋርሶ ስለሚጠንቁል ያገኘኝ ሁሉ የሚገለኝ ይመስለዋል።ቃኤል አቤልን ከገደለ በኋላ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል አመለከተ “በምድር ኮብላይ እና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል” አለው እግዚአብሔር ግን ይህ ፍርሐቱ የፈራውን ሁሉ ሰው በተደጋጋሚ እንዲገል ስለሚያደርገው “ቃየልን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት ይላል” ዘፍ 3 ቁ 14-15። እግዚአብሔር ቃየልን ማንም እንዳይገድለው የሚጠብቀው ምልክት ባያደርግለትና ትንሽ እረፍት ባይሰጠው ኖሮ ቃየል የፈራውን ሁሉ በመግደል ሰዎችን በጨረሰ ነበር።
ኢሕዴግን ከአራት ኪሎ እንዳይወጣ በሩን ዘግቶ ባለፈ ባገደመው ላይ እየተኮሰ እንዲቆይ ያደረገው ያፈሰሰው የደም ብዛት ስለሚጮኽበትና “ያገኘኝ ሁሉ ይገለኛል” ከሚለው ፍርሐቱ የተነሣ ነው። ይህ የቃየል መንፈስ እንዴት ይወገድለታል? 2.ማህበረ ቅዱሳን አባላቱ ወንድሞቻችን ናቸው ነገር ግን አሳባቸው እጅግ በጣም የተባለሸ ነው። መንፈሳዊ ነገር የተማሩ ቢመስሉም ምንም የሚያውቁት አንዳች ነገር የለም። አባላቱ የማህበረ ቅዱሳን አባላት የሆኑት መንፈሳዊ ነገር ተረድተው ሳይሆን የፕሮፓጋንዳ ሰላባ በመሆናቸው ነው። የሚማሩት ሃይማኖታዊ ፖለቲካ እንጂ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አይደለም። የሳይኮሎጂ ችግር ውስጥ ገብተዋል። ይህን ለማረጋገጥ አንድ ነገር እንድታስተውሉ ልጠቁማችሁ።
እነርሱ ባሉበት ሁሉ ሰላም የለም። ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ለራሳቸው ማምለክ ሳይሆን የሚፈልጉት የሌሎችን አለባበስ፣ አዘማመር፣ ካህናቱ ቅዳሴ ገብተው እስኪወጡ ድረስ እንቅስቃሴያቸውን መከታተል፣ ቃጭሉ ምን ያህል ጊዜ እንደተመታ፤ መጋረጃው መቸ እንደተዘጋ እና እንዳልተዘጋ ማየት፤ የሁሉንም ምእመናን የአምልኮ ሁኔታ መቆጣጠር፤ ትክክል አይደለም ያሉትን ለማስተካከል በመከራከር የሃይማኖት ፖሊስ መሆን ይፈልጋሉ። በዚህ አሰልቺ ክርክራቸው ስንቱ ክርስቲያን እቤቱ ቀርቷል?። ሰርግ ላይ ሲገኙ ማን ምን እንደለበሰ የሚቆጣጠሩት ማህበረ ቅዱሳኖች ናቸው። በሰርጋቸው ላይ ከውሃ በቀር ሌላ እንዲጠጣ አይፈልጉም። በቬሎ የተጋቡ ሙሽሮችን አጥብቀው ያወግዟቸዋል።
በሰዎች ላይ መከፋፈልንና የሳይኮሎጂ ችግር ሊያመጣባቸው የሚችለውና ዋናው የማህበረ ቅዱሳን የፍርኃት ትምህርት “ተሃድሶዎች እትዮጵያን ሊያጠፉ የመጡ ናቸው” የሚለው ነው። ይህ ፕሮፓጋንዳ በኦርቶዶክሳውያን መካከል መተማመን እንዳይኖር ከሳሽ እና ተካሽ ሆነን እንድንከፋፈል አድርጎናል። ፍርሐትን እንጂ እምነትን አይማሩም ኢሕዴግን ዲሞክራሲ የሚያስፈራውን ያህል ማህብረ ቅዱሳንንም ወንጌል ያስፈራዋል። ኢየሱስ የሚል ስም ያስደነግጠዋል፤ ወንጌል የኃጢአትን ቆሻሻ የሚያቃጥል እሳት መሆኑ የታወቀ ነው። 3.ሃይማኖት መሪዎች
የሃይማኖት መሪዎች የእግዚብሔርን ድምጽ ለሕዝብ ለማሰማት በእግዚአብሔር ወንበር ላይ የተቀመጡ የከበሩ ሰዎች ናቸው። ነገር ግን አቀማመጣቸው ለአደጋ አጋልጧቸዋል። መንግሥት መገሠጽ እግዚአብሔር ልብ ለሰጣቸው መሆኑን አውቃለሁ ስለዚህ ለምን አይገሥጹትም የሚል ፍርድ ለመናገር አልደፍርም። እኔም ከዚያ ቦታ ላይ ብቀመጥ ምን ላደርግ እንደምችል አላውቅምና በሰው ግፊት ሰማትነት እንዲቀበሉ አልመክርም። ነገር ግን መገጸሥ ባይችሉም ከኢሐዴግ ጋር መተባበራቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም። በልማት በመልካም አስተዳደር ቢተባበሩ ተገቢ ነው።
''በሰርጋቸው ላይ ከውሃ በቀር ሌላ እንዲጠጣ አይፈልጉም። በቬሎ የተጋቡ ሙሽሮችን አጥብቀው ያወግዟቸዋል።'' yih ababal min lemalet yihon? bezi ababalih bicha wulude arios mehonih taweke
Deleteእግዚአብሔርን ማወቅ የክርስትናው ዐቢይ ነገር ነው፡፡ የማናውቀውን አምላክ እንዴት ልናመልክ እንችላለን? ብዙዎች ግን ሳያውቁት ያመልኩታል፡፡ ጳውሎስ በአቴና ሳለ የአቴና ሰዎች ሳያውቁት መሠዊያ ሠርተው የሚያመልኩት አምላክ እንደነበራቸው አየና የማያውቁትን አምላክ ማምለክ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ብቸኛውን አምላክ አስተዋወቃቸው፡፡ ዛሬም ብዙዎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አያውቁትም ግን በስሙ ይጠራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን አያውቋትም ግን ስለእርሷ ይሟገታሉ፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ለመሆናቸውም የሕይወት ምስክርነት የሌላቸው ናቸው፡፡ ወገኖቼ! ይህ ቃል እኛን ኦርቶዶክሳውያንን ይመለከታል፡፡ የአብዛኛው ሕዝባችን መንፈሳዊ ሕይወት በእነዚህ መሠረቶች ላይ የቆመ አይደለም፡፡ ሆሳዕና! ብሎ ለማመስገን የሚቸኩል ዳግመኛም ስቀለው! ለማለት የማይዘገይ እንደ ውሃ በቀደዱለት ቦይ የሚፈስ ነው፡፡ ነገር ግን ወገኖቼ! ለማመስገንም ለመርገምም አንቸኩል፡፡ የምንሰማውንና የምናየውን በማስተዋል እንመርምር፡፡ ቃሉ ‹‹የማያስተውል ሕዝብ ይገለበጣል›› ይላልና፡፡
ReplyDeleteየእስራኤል ሕዝብ የተነቀፈው መሠረታዊ የእምነት መገለጫውን በማጣቱ ነው፡፡ ያለ እውነት ልናመልክ አንችልም፡፡ ያለ ምሕረት (በጎነት) ምስክርነት የለንም፡፡ እግዚአብሔርን ሳናውቀውም የእርሱ ነን ማለት አንችልም፡፡ ይህ ከሌለን ክርክራችን ከሰው ሳይሆን ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር ነው፡፡ ቃሉም ይህንን ያረጋግጥልናል፡፡ ‹‹እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሚኖሩ ጋር ክርክር አለው፡፡›› (ሆሴ. 1÷ 1)
ብዙዎች ለሃይማኖት የሚከራከሩ እንጂ ለሃይማኖት የሚመሰክሩ አይደሉም፡፡ ምስክሮች ልንሆን መጠራታችንን ቃሉ ይናገራል፡፡ ምስክር ያየና የሰማ ነው፡፡ ስለማናውቀው እግዚአብሔር እንከራከራለን፤ ስለማናውቃት ቤተ ክርስቲያን እንሟገታለን፡፡ የእኛን ማመን የምንገልጠው ሌሎችን በመስደብና በመንቀፍ ነው፡፡ ለክርስትናችን አብነት የምናደርገው ማንን ይሆን? መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሆነ እስኪ የእርሱን ፈለግ እናስተውል እንኳን ሊሳደብ ሲሰድቡት ምላሽ አልሰጠም፡፡ እኛ ግን በአካል መሳደብ ባንችል በዘመናዊ የመገናኛ መንገድ ለመሳደብ በአደባባይ የተገለጥን ነን፡፡
Endante ayinet tehadisowochim; Mahibere kidusanim legna betbach tewusakoch nachihu. MK & Tehadiso yelelachihubet zemen yenoru sewoch minigna yetadelu nachew.
Delete“ዓለም ዋሾ ዓለም ወላዋይ
ReplyDeleteከጃንሆይ ግቢ አልነበርሽም ወይ”
እውነት በድምፅ ብልጫ መዳኘት የማህበረሰቦችን ልማድ ነው፡፡ ለመለየት የሞከረ ይተኮስበታል፡፡ እውነት ለእኔ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡
ReplyDeleteእውነት አትሞትም፣ ብዙዎች ስለ እርሷ ሞተዋል፡፡ ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ ግን እውነት ራሱ ሞቶ ታየ፡፡ ዛሬ በአደባባይ እውነት ሲጎሳቆል እንቆጫለን፣ ታሪክ ስንመረምር ግን የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት እውነት በአደባባይ ተፈርዶበት ተሰቅሎ ነበር፡፡ ነገር ግን ሞት ሳያሸንፈው ከመቃብር በላይ ውሏል፡፡ ሌሎች እውነቶች ሁሉ ከዚህ ዘላለማዊ እውነት ውስጥ ይወጣሉ፡፡ እርሱ ግን መሠረት ነው፡፡ ይህ እውነት ማን ነው?
ReplyDeleteእውነት በድምፅ ብልጫ መዳኘት የማህበረሰቦችን ልማድ ነው፡፡ ለመለየት የሞከረ ይተኮስበታል፡፡ እውነት ለእኔ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡
ReplyDeleteyamiral dani !!!!ewunet timeneminalech enji atitefam!
ReplyDeleteEnkuan dehna temelesk kalehiwot yasemalin E/r yagelgilot zemenihin yibarkilih.
ReplyDeleteKelehiwet yasemalin.
ReplyDeleteክርስቶስ ተንሥዓ እሙታን!
ReplyDeleteእንኳን አደረሰህ ከቤተሰብህ ጋር። እንግዲህ ደስታችን በፍስክ ምግብና መጠጥ ብቻ እንዳይሆን ከእይታዎችህም አካፍለን እና ልጓም ይሁነን።
Ewnet netsa tawetachuhalech ( the truth shall set you free!). Thank you!
ReplyDeleteenkuan beselam metahe
ReplyDeleteSelam Dn. Daniel,
ReplyDeleteEnkuan dehina metah! When I started to read you script here I was thinking you are going to raise some thing happened these days. I feel that Christos walks all His ways just to show us how we should live. All what so ever happed were up on his knowledge and will! Truth is God. At the extent we go away from God, our mind surrenders to lie and/or evils. Egziabiherin lemawek balefelegut metene yemayigebawun yadergu zend lemayireba aemiro asalifo setachew yilalina. That is all! This extreme does not at all lead us where we want to reach but distancing us from truth. Egziabiherin/Ewunetin/ lemaweke bebeleginew meten gin egeza alen ewunetin lemawok. Judah did not get what he had wanted to get. Even you could not survive against the truth! Emmaus travelers were with a bit confusing story. We don’t exactly know why that happened. What I know is only God wanted that event to happen. Imagine, the travelers were talking much about Christos. They also had already heard His resurrection. But they still did not have patience to stay in Jerusalem at least until they clear out what they had heard about Him. This news had really been very important for them. But the most important program is the program of God/Christos. They had to be in that event. It might be such a simple thing for us who simply read from a bible of limited paragraph. The actual event is likely beyond that! In fact Johannes who followed the truth to the end mentioned this fact! Most of the things are beyond what we read in the bible! Christos had to also die in so that we should survive that is true! We only thank Him for that!
Anyway, my expectation of your article was not such a hard religious one but about facts of these days that might be quoted against (compared) the stories in the bible. Otherwise, it remains to be too general that has mild influence to readers. It would have been more influential if it reflects the current scenarios and exemplified by the story in Bible. That is my comment and preference but you might have your reason. Thank you!
በሰሞነ ሕማማት በእስጥፋኖስ ቤተክርስቲያን የተፈጸመው ድርጊት መምህር ግርማ ያስተምሩበትን የነበረውን መድረክ አፈረሱ፣ በመደረኩ ላይ ተደርድረው የነበሩ የቅዱሳን ስቀላትን ቀዳደዱ፣ አላማቸው ነበርና የእግዚአበሔር ቃል የሚነገርበትን አጋንንት የሚነዱበትን ጉባዔ አስታጎሉ፡፡ እና እነዚህ “ሰዎች” ማን ናቸው? በመጨረሻም ደብዳቤ ፅፈው ቤተክርስቲያኒቷ ግድግዳ ላይ ለጠፉ፡፡ መምህሩ የነበሩት በቅድስት አገር እየሩሳሌም ነበር፡፡
ReplyDeleteMemehir Grima has been exposing many hidden realities and showing the power of God for the last 15 years. I happened to learn recently. Yet many even position of the church fail to accept the truth! Who really are in the Church?!
እውነት የሆነ እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ይመስገን። እግዚአብሔር ይጠብቅሕ
ReplyDeleteHello Dani,
ReplyDeleteWe miss you sooo much. May God continue to bless you, help you in your work, and keep you in good health, peace and happiness. Amen!
ቃለ ህይወት ያስማልን
በእውነት ስለ እውነት እንኑር፡፡
ReplyDeleteወንድሜ ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
Again Selam Dn. Daniel,
ReplyDeleteLet me share with you and your readers my piece below. I am not sure if I did it already in other comments any way, it may fit here.
ሕሊና ተርቦ እውነትን ሲናፍቅ፣
ሆድ በእህል ተሞልቶ በደስታ ሲቦርቅ፣
ወደ እንዱ ስትቀርብ ሌላው ከእሷ ሲርቅ፣
ሕይወት ተቸገረች ሆኖባት ዝበርቅርቅ፡፡
የዕለት እውነት ስጠኝ እያለም ቢጸልይ፣
ጩኸቱ በርክቶ የእለት እንጀራ ባይ፣
ሕሊና ፀሎቱ ሳይደርስ ከሰማይ፣
የጉም ሽታ ሆኖ ቀረበት መንገድ ላይ፡፡
ከስቶና ጠውልጎ ሕሊና እውነት አጥቶ፣
ሆድ እየወፈረ መብልን አብዝቶ፣
ለሕይወት ቸገራት ውጥንቅጡ ወጥቶ፣
መኖርም ተሳናት አንዱን ከአንዱ አስማምቶ
ዮ. ሠርፀ (J. Sertse) -1994 ዓ.ም
ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡ ራሴን ከየትኞቹ ውስጥ/ወገን/ እንደሆንኩ አሳይቶኛል፡፡ ግን እንደ ዮሐንስ መሆን ይቻላል? እግዚአብሔር ይርዳን!
ReplyDeleteEnkuan Beselam Metah Danii Setetefa Gize Bezu neger aseben Neber EGZIABHER YEMSEGEN Ye KIDEST HAGER EYERUSALEM Berket Le Egnam Yedrsen Amen
ReplyDeleteSele EWINET Bizu Tebiloal MEDEHANIALEM Masetewal Seton Ye Ewint Sewoch Yadrigen Betleliem Behahun Seat Ewinet Betfabet Zemn Ke Andebtachin Ewint Endaywta yetebal Bemimsilbet Zemn
Danii MEDHANIALEM Ye Ageligelot Zemnihen Yarizemiln
.. be ahunu gize ye orthodox lijoch eyasiyut yalut...ke DN.Daniel besteqer
ReplyDeleteDN.Dani,yemideniq guluh eyita new EGIZIABHER yibarkih
Daniel I want to cry, when I read this post. But I couldn't yehonku dingay lib. Woyyyyoo lene.
ReplyDeleteBut Daniel please please please, why You don't write on such kind of spritual issues repeatedly. please guide us. Why you don't remember us? Lots of person in the worldly life. How can we live through christ? U only see ur side. Lots of people want to learn from u about God & Bible.I like your focus on social issues but make it 50, 50%. you are different than other bloggers, since your origin is church.
እንኳን ደህና መጣህ ዲያቆን ዳንኤል በጣም ትልቅ ትምህርት ነወ ያገኘነው እግዝያብሔር ይባርክህ$ ስእውነት እንድንኖር አምላክ ይርዳን ::
ReplyDeleteእንኳን ደህና መጣህ ዲያቆን ዳንኤል በጣም ትልቅ ትምህርት ነወ ያገኘነው እግዝያብሔር ይባርክህ$ ስለእውነት እንድንኖር አምላክ ይርዳን ::
ReplyDeleteክርስቶስ ተንሥዓ እሙታን!
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
አንዳንድ ሰዎች እውነትን የሚከተሏት ሐሰት መስላቸው ነው፡፡ አንዳንዶች በእውነትና በሐሰት መካከል ያለውን ልዩነት አይለዩትምና፡፡ ያንን የመለየት ዕድል የሚያገኙት እውነት መሥዋዕትነት ማስከፈል ስትጀምር ነው፡፡ ያን ጊዜ ከእውነት መሸሽ ይጀምራሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ እውነት እንደ ሐሰት ጥቅም ብቻ የምትሰጥ መስላቸው ይከተሏታል፡፡ መሥዋዕትነቱ ሲመጣ ግን ይሸሻሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ እውነትን ለመሸከም የሚያስችል ዐቅም ሳይኖራቸው ከእውነት ጋር ይቆማሉ፡፡ ዐቅም የሚያስፈልግበት ጊዜ ሲመጣ ግን ጥለው ይሸሻሉ፡፡ ዋናው መሳሳታችን ይሄ አይደል!
ReplyDeleteእውነተኛ አባታችን ዳንኤል ሆይ በእውነት እውነትንና እምነትን ተላብሰሃልና እግዚአብሔር ረጂም ዕድሜ ከጤና ጋር ያድልህ አሜን:: አንድ ነገር ላሳስብህ አንተን የመሰሉ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ሀገራችንና ቤተክርስቲያናችን አለኝታዎችን ለማፍራት ሞክር ካሉም ልምድ አካፍላቸውና እንዲሁ ተመሳሳይ አገልግሎትን ያገልግሉ::እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ አሜን::(ሰለ ጾመ ሐዋርያትና ጾመ ፍልሰታ የመጾም ምክንያት አጠር ያለ ማብራሪያ በትሰተን(ኝ))::
DIAKON DANEAL
ReplyDeleteENQWAN LEBREHANE TENSAEW BESELAM ADERESEH (kenebetesebocheh) SETETEFA BETAM ASEBE NEBER GEN EZIEH EGNAGAR KEKEDEST HAGER SIMELESU AGENTENEW NEBER SILUGN DES ALEGN EGZIABHER SELAM ENA TENA YABZALEH
AMEN
ዳኔ እኔ ምንም እንኻን የየዓመቱ የየሩሳሌም መንገደኛ ብሆንም የዘንድሮ ልዮ ያደረገው ግን የወጣቱ ከአዲስ አበባ መምጣትና በአንተ ውድ ወንድማችን : የተለመደው ልቅም ጥርት ያለ የትምህርት መርሀ ግብር መሰጠቱ ነው። ትምሕርትሕን ሉዩ ካደረገው አንዱ በስደት ላይ የሜገኙትን ግዚ የለየን ኤርትራውያንን ወገኖቻችንን በወቅቱ በአነሳሐቸው ታሪኮች አንገታቸውን ቀና ትክሻቸው ቀለል ሴላቸው ተመልክቸ አለሁ።ተግባርሕ ሁሉ ግሩም ስለሆነ እንደመጀመሪያሕ መጨረሻውን ያሳምርልሕ። በተጨማሪም አንድነትን አበርትተው ለሜሰብኩት ከለንደን ለመጡት አባት ምስጋናየ በአንተ በኩል ይድረሳቸው። እንዴሁም የሩሳሌም በአሰተዳደር ውስጥ ያሉ አባቶች እና ምእመን ያለውን ውጣ ውረድ ተሻግረው ምርጥ የትምህርት መርሐ ግብር : በደምብ የሜሰማ የድምጽ ማስተላለፌያ:ግሩም መስተንግዶ በማድረጋቸው እያመሰገንኩ፤ ለከርሞ ደግሞ ምእመን እግሩን አጠፍ አድርጎ ቁጭ የሜልበት አግዳሜ ወንበር ታክሎበት ለመገናኘት ያብቃን።በዚህ አጋጣሜ ከኢትዩጵያ ውጭ ለምትኖሩት ወጣት ወንድ/ሴት ወገኖቸ ቤተሰብ ከመላክ ባሻገር እራሳችሁ በመሔድ የበረከቱ ተሳታፌ ትሆኑ ዘንድ በዜህ አጋጣሜ ጥሪየን ሳስተላልፍ በደስታ ነው።
ReplyDeleteበጣም ደስ የሚል ጽሁፍ፤ ስለ ክርስቶስ እንዲህ በእውቀት ሲነገር ደስስስ ይላል፤ እርሱ ምስጋና ይግባውና እውነት ስለሆነ ብዙ እውነተኞችን አፍርቷል፡፡ እኛም ቢያንስ የእውነት አድናቂዎች ነን፤ እውነትን መያዝ ጣት የሚያስቀስር ብሎም የሚያስቆርጥ መሆኑን ስለምናውቅ፣ እውነትን ለመሸከም የታገሱትን እናደንቃቸዋለን፤ እንወዳቸዋለንለን፣ ከቻልን እንከተላቸዋለን፡፡
ReplyDeleteI just don't know what can I say. It's realy amazing article. In fact you allways write amazings. But for me it's more than ever. I even do not know when wee'll begun living for REALITY (TRUTH). Just to the point 'GOD give as a truhful heart for all us!' LORD JESUES CHRIST the son of VERGIN MERRY give you long and helthy life foor you and your family. THANK YOU!
ReplyDeleteena dani enante mkidusanoch lemndn new ewnetn behaylna begulbet ltaTefu yemtmokrut....mels sayhone and mulu article bihonlGn des yleghal lemeweyayet endiyamechien
ReplyDeleteእውነት ቤት ስትሰራ ውሸት ላግዝ ካለች ሚስማር ካቀበልች ጭቃ ካራገጠች ቤቱም አልተሰራ እውነትም አልኖረች lante new dani ewnet mkidusan ewnet new
ReplyDeleteMy appreciation for your articles couldn't make me keep silent. Please keep on giving your great lesson for the majority who read your articles.
ReplyDeleteRegards, Dani
Amazing Approach!!!!!!
ReplyDeleteAmazing Approach !!!
ReplyDeleteዓርብ ዕለት እውነት ለፍርድ ቀረበች፡፡
ReplyDeletethanks
ReplyDeleteእውነት ጋር ሲጣሉ ለሚኖሩ ሁሉም ትምህርት ይሆን ዘንድ፤ በዐርባኛው ቀን ሁሉም እያያት እውነት ዐረገች፡፡ በልዕልናም ተቀመጠች፡፡ ከእውነት የተጣሉ የሰው ጥላዎች ግን ከመቃብር በታች እነሆ አሉ፡፡
ReplyDeleteThere is no fact but interpretation.
ReplyDeleteስድብ ይመስላል
ReplyDeleteamazing view
Deletehello dear D/n
ReplyDeletereally do you follow the truth? and till i couldn't realize the truth in which area, by whom, any ways sorry writing this adea