click here for pdf
አንድ አባት ነበሩ፡፡ ይህ ሕዝብ እግዚአብሔርን ቢያየው ኖሮ ያምንበት ነበር፤
በእምነቱም ይጸና ነበር ብለው ያስባሉ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ለሰው መገለጥ አለበት ብለው ያምናሉ፡፡ ይህንንም ሃሳባቸውን
ደጋግመው ለእግዚአብሔር ይነግሩት ነበር፡፡ ‹ለምን በአብርሃም ዘመን እንደተገለጥከው አትገለጥም› እያሉ ይከራከራሉ፡፡ ሃሳባቸው
ደገኛ ምኞታቸውም ቅን ነበርና ፈጣሪያቸው መለሰላቸው፡፡ ‹‹እኔ ብገለጥም መጀመርያ ነገር ሰዎች አያዩኝም፤ ሁለተኛም ቢያዩኝም
አይጠቀሙብኝም›› አላቸው፡፡
እርሳቸው ደግሞ ‹ብዙዎቹ ያውቁሃልና ይጠቀሙብሃል፤ ነገር ግን ዘመኑ ካላየን
አናምንም ስለሚል እየተጠራጠሩ ነው፤ እባክህ ተገለጥና የሚሆነውን እንየው›› ይሉ ነበር፡፡ አምላክም መልሶ ‹ስለ እኔ ማወቅና
እኔን ማወቅ ይለያያሉ፡፡ ብዙዎች ሃይማኖተኞች ስለ እኔ ያውቃሉ እንጂ እኔን ራሴን አያውቁኝም፡፡ ሃይማኖትኮ ስለ ፈጣሪ ማወቅ
ሳይሆን ፈጣሪን ማወቅ ነው፡፡ ስለ ፈጣሪ ማወቅ ዕውቀት ነው፣ ፈጣሪን ማወቅ ግን እምነት ነው፤ ስለ ፈጣሪ ማወቅ የሚቻለው
በትምህርት፣ ፈጣሪን ማወቅ የሚቻለው ግን በእምነት ነው፡፡ ስለ ፈጣሪ ማወቅ ያራቅቃል፣ ፈጣሪን ማወቅ ግን ይለውጣል› ብሎ
መለሰላቸው፡፡
እርሳቸው ግን ለብዙ ዘመናት ጥያቄያቸውን አላቋረጡም ነበር፡፡ አንድ ቀንም በሕልማቸው
በከተማዋ አደባባይ ብዙ ሺ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ እግዚአብሔር ተገልጦ አዩ፡፡
በመጀመርያ ጋዜጠኞች ተሰብስበው መጡና ‹‹ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ይፈቀድልን›› ሲሉ
ጠየቁ፡፡ ከመካከላቸውም አንዳንዶቹ የምናደርገው ቃለ መጠይቅ ‹‹ሐርድ ቶክ›› መሆን አለበት የሚል ሃሳብ ሠነዘሩ፡፡ ሌሎቹ
ደግሞ ቃለ መጠይቃችን በቀጥታ ሥርጭት መተላለፍ አለበት ሲሉ ሞገቱ፡፡ አባ በዚህ በጣም አዘኑ፡፡ ‹‹እግዚአብሔርኮ የመጣው
አግኝታችሁት በነፍሳችሁ እንድትጠቀሙበት እንጂ ለቃለ መጠይቅ አይደለም›› ብለው ተቆጡ፡፡ ጋዜጠኞቹም በዚህ ቅር ስላላቸው
እየዛቱ ሄዱና ‹‹እግዚአብሔር ለቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ አልሆንም አለ›› ‹‹እግዚአብሔርን እንዳናናግር መነኩሴው ተቆጡ›› የሚሉ
የዜና ርእሶችን ይዘው ወጡ፡፡
ከእነርሱ በኋላ የመጡትም ሰዎች በዓለም ላይ በጥንት ጊዜ ስለተፈጸሙና አከራካሪ
ስለሆኑ ነገሮች እግዚአብሔርን ለመጠየቅ የሚፈልጉ ምሁራን ነበሩ፡፡ እነዚህ ምሁራን በዓለም ላይ እንዴት እንደተፈጠሩ ግልጽ
ስላልሆኑ፣ በመላ ምት ስለሚታመኑ፣ በቂ ማስረጃ ስላልተገኘላቸው፣ ከሃይማኖት ትምህርት ጋር ስለማይጣጣሙ የሳይንስ ሃሳቦች፣
በድሮ ዘመን ነበሩ ስለሚባሉ፣ ግን ስለጠፉ ነገሮች መጠየቅ እንደሚፈልጉ ለአባ ተናገሩ፡፡ ይህ ነገርም አባን እንደገና
አሳዘናቸው፡፡ ‹እግዚአብሔር የመጣበት ዓላማ የእናንተን ምሁራዊ ጥያቄ ለመመለስ አይደለም፤ የነፍሳችሁን ጥያቄ ለመመለስ እንጂ፤
ይህንንማ በተሰጣችሁ አእምሮ መርምራችሁ ድረሱበት፤ ይልቅ ተመርምሮ የማይደረስበትን የነፍሳችሁን ነገር ለምን አትጠይቁም› ብለው
አዘኑ፡፡
ምሁራኑም ‹እግዚአብሔር ሳይንሳዊ ለሆኑ ጥያቄዎች መልስ የለውም ማለት ነው››እያሉ
እየቀለዱ ተመልሰው ሄዱ፡፡
እነርሱ እንደሄዱም የነገ ሕይወታቸው ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ለማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች
መጡ፡፡ የማገባው ማንን ነው? ምን ዓይነት ልጅ እወልዳለሁ? ውጭ ሀገር የምሄደው መቼ ነው? በቀጣይ የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ ምን
ይሆናል? ስንት ዓመት እኖራለሁ? ከሞትኩ በኋላ የት ነው የምገባው? የሚሉ ሚሊዮን ጥያቄዎችን ይዘዋል፡፡ እግዚአብሔር የነገውን
ጭምር ስለሚያውቅ ይህንን እንዲነግራቸው ተማጸኑ፡፡ አባም እንደገና አዘኑ፡፡ ‹‹የነገውን ዕጣ ፈንታ ለመንገር እግዚአብሔር
አልመጣም፤ የነገውን ዕጣ ፈንታ የምታስተካክሉበትን መንገድ ለማሳየት እንጂ፡፡ የነገውን ዕጣ ፈንታችሁን ለመንገር ቢመጣ ኖሮ
ከእንስሳት ነጥሎ ለምን አእምሮ ይሰጣችሁ ነበር፡፡ ጠንቋይ ቤት ስትሄዱ የምታቀርቡትን ጥያቄ እንዴት እግዚአብሔር ፊት
ታቀርባላችሁ፡፡ የነገ ዕጣ ፈንታችሁ በእናንተ እጅ ነው፡፡ ማሣመርም ማበላሸትም ትችላላችሁ›› አሉና መለሱላቸው፡፡
ሰዎቹም እየተናደዱ ተመለሱ፡፡ ‹‹ታድያ ነገ የምሆነውን ካልነገረኝ እግዚአብሔር ምን
ያደርግልኛል›› ይሉ ነበር፡፡
ከእነርሱ ቀጥለውም ከእግዚአብሔር ብዙ ነገሮች የሚፈልጉ ሰዎች መጡ፡፡ ገንዘብ፣
ሚስት፣ ልጅ፣ ሥልጣን፣ የውጭ ዕድል፣ ሥራ፣ ዝና፣ ውበት፣ ቤት፣ መኪና፣ እድሜ፣ ጤና፣ የማይፈልጉት ነገር አልነበረም፡፡
አንዳንዶቹም የሚሰጣቸው ነገር ከሌሎች የሚበልጥ እንዲሆን ይፈልጉ ነበር፡፡ ሌሎችም የያዙት የፍላጎት ዝርዝር በብዙ ወረቀቶች
የተሞላ ነበር፡፡ አንዱም ሌላው እንዳያይበት ይሸፍነው ነበር፡፡ እርስ በርሳቸውም አይነጋገሩም ነበር፡፡ አንዳንዶቹም ከሚሊዮን
በላይ ቁጥር መኖር አለመኖሩን ለማጣራት ይጥሩ ነበር፡፡ የሚጠይቁት በዚያ ልክ ይሆን ዘንድ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የረሱት ነገር
ካለ እንዳይቀርባቸው ‹ወዘተ› የሚል ልመና ይዘው መጥተው ነበር፡፡
ይህም አባን በጣም አስገረማቸው፡፡ ‹‹እግዚአብሔርኮ አምላክ እንጂ የርዳታ ድርጅት
አይደለም፡፡ እርሱ ይህንን ሁሉ እንደመና የሚሰጣችሁ እናንተ ምን ሠርታችሁ ልትበሉ ነው? አንዳችሁም እንኳን የሚያስብ ልቡና፣
የሚፈጥር አእምሮ፣ የሚጠበብ ጥበብ ስጠኝ እንዴት አትሉም? እንዴትስ ደግሞ ለራሳችሁ ብቻ የሚያስፈልጋችሁን ይዛችሁ ትመጣላችሁ?
ለሌላውስ? ደግሞስ የጎደላችሁን ብቻ ይዛችሁ ስትመጡ ስላላችሁ ነገር ምነው አንዳች ምስጋና አልተነፈሳችሁም?›› ሰዎቹም በአባ
መልስ ከመበሳጨታቸው የተነሣ ‹‹ታድያ እግዚአብሔር ለችግሬ ካልደረሰለኝ ለመቼ ሊሆነኝ ነው›› እያሉ ተማርረው ተበተኑ፡፡
እነዚህ ሲወጡ ሌሎች ደግሞ መጡ፡፡ ግማሹ ሞባይል ስልክ፣ ሌላው አይፎን፣ ሌላው
አይፓድ፣ ሌላው ደግሞ ካሜራ ይዟል፡፡ አንዳንዶቹ እግዚአብሔርን ሊጠይቁ ሲጠጉ አንዳች የሆነ ውሳጣዊ ነገር ይኖራቸዋል ብለው
አባ ደስ አላቸው፡፡ እርሳቸውም ጠጋ አሉ፡፡ ወጣቶቹ ግን ‹‹የኢሜይል አድራሻ አለህ፣ ፌስ ቡክ አለህ? ትዊተርስ›› እያሉ
ነበር የሚጠይቁት፡፡ አባ ተገርመዋል፡፡ ሌሎቹም ሞባይላቸውን አውጥተው ስልክ ለመቀበልና ለመመዝገብ ጓጉተዋል፡፡ የቀሩትም ጠጋ
እያሉ በሞባይላቸው፣ በአይፓዳቸውና በካሜራቸው ፎቶ ግራፍ ይነሣሉ፡፡ እነዚህ ምንም ዓይነት ጥያቄ የላቸውም፡፡ እነርሱ
የሚፈልጉት የፌስቡክ፣ የኢሜይልና የትዊተር አድራሻ ነው፡፡ እነርሱ የተጠመዱት ስልክ ለመቀበል ነው፡፡ የእነርሱ ዓላማ ጠጋ
ብለው ፎቶ መነሣት ነው፡፡ አባ እንደመሳቅ እያሉ ያይዋቸው ነበር፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርም፣ መጠየቅም፣ አንዳች መቀበልም፣ አይፈልጉም፡፡
የሚሰጡትም የሚቀበሉትም ነገር የለም፡፡ የእነርሱ ዓላማ አድራሻና ፎቶ ብቻ ነው፡፡ መጠጋት ብቻ ነው የሚፈልጉት፡፡ መቅረብ
አይፈልጉም፡፡መግባትም አይመኙም፡፡ እነርሱ ለአይፎናቸውና ለአይፖዳቸው፣ ለፌስቡካቸውና ለትዊተራቸው እንጂ ለነፍሳቸው
አልተጨነቁም፡፡ ነገ በፌስቡካቸው ላይ እንዴት አድርገው እንደሚለጥፉት ነው የሚያስቡት፡፡ ስንት ሰው ‹ላይክ› እና ‹ሼር›
እንደሚያደርጋቸው ነው የሚታሰባቸው፡፡ ዓላማቸው እንደ ፈያታዊ ዘየማን ቀድመው ገነት መግባት ሳይሆን ቀድመው ፌቡክ ላይ
መለጠፍ ነው፡፡እነርሱ የእግዚአብሔርን ፎቶውን እንጂ መንግሥቱን አልፈለጉም፡፡
ቀስ በቀስ ሁሉም ከአካባቢው ጠፉ፡፡ አንድ የገረመው ሰውም የተከፈተ ላፕቶፕ ይዞ ወደ
አባ ዘንድ መጣ፡፡ ‹‹ምንድን ነው?›› አሉ አባ፡፡ ፌስቡኩ ሁሉ በፎቶ ግራፍ ተጥለቅልቋል፡፡ ብዙዎች ዋናውን የፌስ ቡክ
ፎቷቸውን ቀይረውታል፡፡ ፎቶዎችንም ብዙ ሰው ‹ላይክ› እና ‹ሼር› አድርጓቸዋል፡፡
‹አዩ አይደለም አባ› አላቸው ፈጣሪ፡፡ ‹‹የዛሬ ሁለት ሺ ዓመት እንደተገለጥኩት ሆኜ
ዛሬ ብገለጥ ኖሮ አራቱ ወንጌሎች በብሎግ፣ የየዕለቱ ትምህርት በትዊተር ነበር የሚወጣው፡፡ አምስት ገበያ ሰው እኔን መከተል
ትቶ አምስት ሺ ሰው በፌስ ቡክ ላይክ ያደርግ ነበር፤ እነ ጴጥሮስም ሲሳሳቱ አልቅሰው ንስሐ አይገቡም ነበር፤ ዲሊት ያደርጉት
ነበር እንጂ፤ ፈሪሳያንንና ሰዱቃውያንን የሚከራከራቸው ሳይሆነ ‹አን-ላይክ› የሚያደርጋቸው ይበዛ ነበር፡፡ አዳምን ለማዳን ብዬ
ቅድስት ነፍሴን ከቅዱስ ሥጋዬ ስለይ እንደ ቅድስት ድንግል ማርያምና እንደ ቅዱስ ዮሐንስ የሚያለቅስ ሳይሆን ፌስ ቡኩ ላይ ‹R
I P› የሚል ይበዛ ነበር፡፡
ሐዋርያትም ወንጌልን ሲያስተምሩ እንደ አይሁድ የሚወግራቸው እንደ ኔሮን የሚሰይፋቸው
አይኖርም፡፡ በፌስ ቡክ የሚሰድባቸው፣ ‹አን-ፍሬንድ› የሚያደርጋቸው፤ ሥዕላቸውን አጣምሞ በፎቶ ሾፕ እየሠራ የሚዘብትባቸው፤ ‹የእገሌ
ደጋፊ ስለሆናችሁ ነው፣ የእገሌ ተቃዋሚ ስለሆናችሁ ነው› የሚላቸው ይበዛ ነበር፡፡ ዛሬ ሰማዕትነት በሰይፍና በድንጋይ ሳይሆና
በብሎግ፣ በትዊተርና በፌስቡክ ነው፡፡
ጲላጦስ አሳልፎ ሰጥቶኝ አይሁድ ሲገርፉኝ የሚያሳየው ሥዕል በፌስ ቡክ ሲወጣ ደግሞ
ትውልዱ በሙሉ ‹ላይክ› ያደርግ ነበር፡፡ በሦስተኛው ቀን ስነሣ ደግሞ ‹ሼር› ያደርጋል፡፡ አዩ አባ ዛሬኮ የሰውን ሃሳብና
ችግር ሼር የሚያደርግ የለም፤ የሰው ፎቶ ግን ብዙዎቹ ሼር ያደርጋሉ፡፡ ዛሬኮ ሰው ሞተ ሲባል ከማዘን ይልቅ ‹ላይክ› እና
‹ሼር› ነው የሚደረገው፡፡ ታድያ በዚህ ዘመን ለምን ተገለጥ ይሉኛል? በዚህ ዘመንኮ የሁሉም ነገር ዋጋ ከ‹ላይክ›ና ከ‹ሼር›
አይበልጥም፡፡ ዛሬ እኔን ‹የሚወደኝ› ሰው ነፍሱን ለወገኑ አሳልፎ በመስጠት አይደለም ፍቅሩን የሚገልጠው፡፡ ‹እኔ ጌታን
እወደዋለሁ፤ እናንተስ?› እያለ ‹ላይክ›ና ‹ሼር› አድራጊ በማብዛት ነው፡፡ ወደፊት ደግሞ ጾምና ጸሎት በፌስቡክ ይሆናል፡፡
ቅዳሴ ማስቀደስም ‹ላይክ›ና ‹ሼር› በማድረግ ይገለጣል፡፡ እና በዚህ ዘመን ለምን ተገለጥ ይሉኛል? ዋጋው ከ‹ላይክ› ና
ከ‹ሼር› ላያልፍ፡፡›› አላቸው፡፡
አባ ከእንቅልፋቸው ነቁ፡፡
ጥብርያዶስ፣
እሥራኤል
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ
ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፤ በተመሳሳይ ሚዲያ መልሶ ማቅረብ ክልክል ነው
ዲያቆን ስራህን አምልክ ይባርከው መልካም እይታ ነው፡፡
ReplyDeleteያላስተዋልነው፣ ግን የምንኖርበት እውነታ!
ReplyDeleteyewerede honebign
ReplyDeleteI am sorry to say that gin ymelekethal meselegn.
Deleteአምላክም መልሶ ‹ስለ እኔ ማወቅና እኔን ማወቅ ይለያያሉ፡፡ ብዙዎች ሃይማኖተኞች ስለ እኔ ያውቃሉ እንጂ እኔን ራሴን አያውቁኝም፡፡ ሃይማኖትኮ ስለ ፈጣሪ ማወቅ ሳይሆን ፈጣሪን ማወቅ ነው፡፡ ስለ ፈጣሪ ማወቅ ዕውቀት ነው፣ ፈጣሪን ማወቅ ግን እምነት ነው፤ ስለ ፈጣሪ ማወቅ የሚቻለው በትምህርት፣ ፈጣሪን ማወቅ የሚቻለው ግን በእምነት ነው፡፡ ስለ ፈጣሪ ማወቅ ያራቅቃል፣ ፈጣሪን ማወቅ ግን ይለውጣል› ብሎ መለሰላቸው፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥልኝ ዳኒ!
ቃለ ሕይወት ያሰማልን!!
Like! lol
ReplyDeleteDani.... Tiru eyita new gin tinish weredebign...
ReplyDeletetinish bicha? bedenb new yeweredew
Deleteምን አልባት የአእምሮ ብቃታቹ ከፍ ብሎ ይሆናልና የተሻለ ብሎግ ፈልጉ!!!
Deleteአለበለዛም ሰሙን ሳይሆን የውስጡን ሀሳብ ተመልከቱ፡፡ መምሰል እንጂ መሆን የማይችልና የማይፈልግ ማቴርያልስቲክ ትውልድ እንደበዛ ይነግራቹዋል፡፡ ቢያንስ ስትተቹ እንኳን በዚህ በዚህ ምክንያት ፅሁፉን አልወደድኩትም ለማለት ያልቻላቹ ሰዎች ሾላ በድፍን የሆነ ትችት ማቅረብ ማንንም አያንፅም፡፡
Yigermal! Dn. Danel betam yemigerm neger new yametahiw! gin wedemecheresha yalalahiw meslegn. Bedenb bitakerew endet yale finishing yiwetaw neber. Fetarin betikikle yemiyawukut Abam menorachew and neger new! Bequm neger gin, wedefin min lihon yichilal belachihu tigemitalachehu?
ReplyDeletethis is fact! our daily life...may God bless you dn dani
ReplyDeleteአቤት አቤት ! እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ like ወይም share ላደርግ ነበር ?????
ReplyDeleteበውነት በሳል ና አስተዋይ ነወት ።ቅድስት ድንግል ማርያም ትባርክወት
So amazing I'm 100% agree. hope this will help to read our selve, our heart, our mind .
ReplyDeleteThank you.
ReplyDeleteDes Ayelem ke eskezarew yewerede sera new
ReplyDeleteዳኒ የሥራህን ይስጥህ ምን እንዳደረግሁ ታውቃለህ? share ና like ገጽህ ላይ መጣ ብዬ ደስ ነበር ያለኝ እና ገና ሳላነብ like ሞከርኩ እሱ ድርቅ ሲልብኝ share ወይ ፍንክች ሲል ነው ማንበብ የጀመርኩት:፡ ተማርኩ እንጂ ወዳጄ ያንተን ነገር ግን በBBC
ReplyDeletelong life to u dn.Dani,stay blessed!
ReplyDeleteዳኒ ልክ እንዳነበብኩት ሼር ኣደረግኩት ደስ ኣይልም ኣልተማርኩመብትም ግን ኣልልም ምክኒያቱም አምላክም መልሶ ‹ስለ እኔ ማወቅና እኔን ማወቅ ይለያያሉ፡፡ ብዙዎች ሃይማኖተኞች ስለ እኔ ያውቃሉ እንጂ እኔን ራሴን አያውቁኝም፡፡ ሃይማኖትኮ ስለ ፈጣሪ ማወቅ ሳይሆን ፈጣሪን ማወቅ ነው፡፡ ስለ ፈጣሪ ማወቅ ዕውቀት ነው፣ ፈጣሪን ማወቅ ግን እምነት ነው፤ ስለ ፈጣሪ ማወቅ የሚቻለው በትምህርት፣ ፈጣሪን ማወቅ የሚቻለው ግን በእምነት ነው፡፡ ስለ ፈጣሪ ማወቅ ያራቅቃል፣ ፈጣሪን ማወቅ ግን ይለውጣል› ብሎ መለሰላቸው፡
ReplyDelete' የሚለው ጽሑፍ ልብ ይነካል
ዋጋው ከ‹ላይክ› ና ከ‹ሼር› ላያልፍ፡፡ God bless u
ReplyDeleteI shared it in facebook
ReplyDeleteስለ ፈጣሪ ማወቅና ፈጣሪን ማወቅ ይለያያሉ!!!!! kalehiywot Yasemalin.
ReplyDeletethanks
ReplyDelete<...አዩ አባ ዛሬኮ የሰውን ሃሳብና ችግር ሼር የሚያደርግ የለም፤ የሰው ፎቶ ግን ብዙዎቹ ሼር ያደርጋሉ፡፡
ReplyDeleteእውነት ነው! ቃለ ህይወት ያሰማልን!
Thank you! Egiziaber Yibarikih!
ReplyDeletethis is our daily live.. you see what level of commitment we have for our religion(eminet)!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteThank you Dani
---አዳምን ለማዳን ብዬ ቅድስት ነፍሴን ከቅዱስ ሥጋዬ ስለይ እንደ ቅድስት ድንግል ማርያምና እንደ ቅዱስ ዮሐንስ የሚያለቅስ ሳይሆን ፌስ ቡኩ ላይ ‹R I P› የሚል ይበዛ ነበር፡፡ dani egziabher tsegawin yabizalih
ReplyDelete"ስለ ፈጣሪ ማወቅ ዕውቀት ነው፣ ፈጣሪን ማወቅ ግን እምነት ነው፤ ስለ ፈጣሪ ማወቅ የሚቻለው በትምህርት፣ ፈጣሪን ማወቅ የሚቻለው ግን በእምነት ነው፡፡ ስለ ፈጣሪ ማወቅ ያራቅቃል፣ ፈጣሪን ማወቅ ግን ይለውጣል› ብሎ መለሰላቸው፡"
ReplyDeleteSelamun yabzalih !!
keep going!
ReplyDeleteትላንት ክርስትናን በሰልፍ ምክንያት እተወው ነበር ስትልቅር አለኝ ዛሬ ደግሞ ስለ እግዚያብሄር እንዲ መጣፍ ለኔ እንኮ ከብደኝ ፡ በቀጥታ መናገር እየተቻለ እግዜርን
ReplyDeleteበጣም ጥሩ ነዉ፡፡ በርታ!!
ReplyDeleteእግዚአብሔር በስራዉ ሁሌ እንደተገለፀልን ነዉ:: በአካል ደግሞ ለሁለተኛ ግዜ በግርማ ሞገስ ይህቺን ዓለም ሊያሳልፍ ይገለፃል:: አባ እርስዎ በፀሎትዎ እኛ ደካሞቹን አስቡን እንጂ አቸኩሉ:: ዳኒ እንዲህ ያሉ መሳጭ ትምህርትህ ይብዙ::TNX
ReplyDeleteEnd samarwt cate ayenehe yetqualanow mayete techelbtalhe
ReplyDeleteስለሰው ሲነግሩን ሆይ ጉድ ! እንዴት አየኸው ባክህ ማለት ስለራሳችን አውነት እውነቱን ሲያወሩን ደግሞ የወረደ ነው ማለት፡፡ ለመሆኑ በዚህ ጽሁፍ የቀረበው ምልከታ ከምን አንጻር ወረደባችሁ ? ለኔስ መልካም እይታ ነው፡፡ ፈጣሪየን ለማወቅ ይረዳኛልእና፡፡ በርታልን ዳ/ን ዳንዔል፡፡
ReplyDeletemelkam eyta
ReplyDeletewow dani betam wedijwelwa wegihena awenit nawu ena aresu senit like ina share yiderkuta e/r libona yistena kela hewit yisemilena dn.dani..
ReplyDeleteTEBAREK YEDENGL LEJI TSEGWEN YABEZALEH
ReplyDeleteፈጣሪን ማወቅ የሚቻለው ግን በእምነት ነው፡፡
ReplyDeleteEXCELENT ARTICAL
ReplyDelete...ስንት ሰው ‹ላይክ› እና ‹ሼር› እንደሚያደርጋቸው ነው የሚታሰባቸው፡፡ ዓላማቸው እንደ ፈያታዊ ዘየማን ቀድመው ገነት መግባት ሳይሆን ቀድመው ፌቡክ ላይ መለጠፍ ነው፡፡እነርሱ የእግዚአብሔርን ፎቶውን እንጂ መንግሥቱን አልፈለጉም፡፡...አዩ አባ ዛሬኮ የሰውን ሃሳብና ችግር ሼር የሚያደርግ የለም፤ የሰው ፎቶ ግን ብዙዎቹ ሼር ያደርጋሉ፡፡ ዛሬኮ ሰው ሞተ ሲባል ከማዘን ይልቅ ‹ላይክ› እና ‹ሼር› ነው የሚደረገው፡፡ ...
ReplyDeleteየጽሑፉ ሔሳብ ‹ላይክ› እና ‹ሼር› ማድረግ ቦታ ሊኖረው ይገባል ለምሳሌ ይህን ጽሁፍ ፌስቡክ ላይ ‹ላይክ› እና ‹ሼር› ማድረግ ለሌሎች ማሰተማርያ እንዲሆን ያደርጋል እንጂ ‹ላይክ› እና ‹ሼር› አታድርጉ አይደለም። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይሀን ጽሑፍ ‹ላይክ› እና ‹ሼር› አደረግን ብለው ሲጸጸቱ ስላነበብኩ ነው።
ReplyDeleteዲን. ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
ብዞዎቸ እንዲያዩት ሼር አደረኩት እግዜር ይባርክህ!
ReplyDeletebetam new miwodik, bertalinn
ReplyDeleteቀስ በቀስ ሁሉም ከአካባቢው ጠፉ
ReplyDeletethanks dani
KaleHiwot Yasemah Wendme. Ahunim ene kecomment alalefkum.
ReplyDelete10q Dani I like it too
ReplyDeleteሃይማኖትኮ ስለ ፈጣሪ ማወቅ ሳይሆን ፈጣሪን ማወቅ ነው!
ReplyDeleteBest View
ReplyDeleteThanks God bless you
ReplyDeleteWow It's interesting. But you have to tell us how to escape from this prison which is controlled by Devil. You have a responsibility too. I appreciate your endeavor. God bless your work
ReplyDeleteEigiziabiair fitsamiehin yasamirelieh
ReplyDeleteThnx dani Egziabhehar Qale hiwot yasemalen.
ReplyDeleteEgeg betam awaki neh bizu temehert aggnechebetalhu tegbarawe kadergkut adnakehe negne
ReplyDeleteit is really true pomp i am agree with this idea at this time
ReplyDeleteይህም አባን በጣም አስገረማቸው፡፡ ‹‹እግዚአብሔርኮ አምላክ እንጂ የርዳታ ድርጅት አይደለም፡፡ እርሱ ይህንን ሁሉ እንደመና የሚሰጣችሁ እናንተ ምን ሠርታችሁ ልትበሉ ነው? አንዳችሁም እንኳን የሚያስብ ልቡና፣ የሚፈጥር አእምሮ፣ የሚጠበብ ጥበብ ስጠኝ እንዴት አትሉም? እንዴትስ ደግሞ ለራሳችሁ ብቻ የሚያስፈልጋችሁን ይዛችሁ ትመጣላችሁ? ለሌላውስ? ደግሞስ የጎደላችሁን ብቻ ይዛችሁ ስትመጡ ስላላችሁ ነገር ምነው አንዳች ምስጋና አልተነፈሳችሁም?››
ReplyDeleteDn. Daniel, I really appreciate your perspective of this issue as usual. God bless you !!!
ReplyDeletelong live to Dn. Daniel
I appreciate ur view as usual thanks
ReplyDeleteMay God bless your fingers bro!
ReplyDeletebetam migeremegn neger 'weredebin' mitelut felit new..eski ye-enanten yeteshale neger asnebebun..letichit sayihon lemelewet enabib!
ዳንየ ፣ ከገባን ይኸው ነው የዘመኑ ጾሎት የንጉሶች ንጉሥ እንዳባቶቻችን ሁሉን ትተን በጾሎት የምንጠመድበት ልቦና ይስጠን ።አሜን
ReplyDelete