Wednesday, May 29, 2013

‹በባል እንዲህ አርገሽ ትጫወቻለሺ›ሴትዮዋ ባሏ ሞቶ ዐርባውን ታወጣለች፡፡ እንዳጋጣሚ የባሏ ዐርባና የቅዱስ ገብርኤል በዓል ይገጥማል፡፡ እርሷም ሁለቱንም እደግሳለሁ ብላ ትነሣለች፡፡ ቅልጥ ያለ ድግስም ትደግሳለች፡፡ ‹ፈረስ የሚያስጋልብ› የሚባል ዓይነት ዳስ ይጣላል፡፡ አገሩ በሙሉ አልቀረም ይጠራል፡፡ በሀገራችን ድግስ ሲደገስ የተጋባዥ አጠራር ወግ አለው፡፡ ከካህናቱ ጀምሮ እስከ ጨዋው የሚጠራበት ሰዓት፣ የሚቀመጥበት ቦታና የሚቀርብለትም ነገር ይለያያል፡፡ ሴትዮዋ ይህንን አላወቀችም ሀገሩን ሁሉ በአንድ ላይ ጠርታ ድብልቅልቁን አወጣችው፡፡ ሁሉም ለመቀመጫና ለምግቡ ሲሻማ ድግሱ ተበለሻሸ፡፡ በተለይ የተዝካሩ ምንነትና ሥርዓት ያልገባቸው ሕጻናት ልጆች የሚያደርጉት ሩጫ አስገራሚ ሆነ፡፡ አብዛኞቹ ተጋባዦች በተዝካር ላይ የሚባለውን፣ የሚመረቀውንም ሆነ ሲወጣ የሚነገረውን የማያውቁ ነበሩ ፡፡ አስተናጋጆቹም ልምድ የሌላቸውና ነገሩ ያልገባቸው ነበሩና ችግሩን ከመፍታት ይልቅ እነርሱ ራሳቸው ችግሮች ሆኑ፡፡
በሁኔታው የተገረሙ የኔታ እንግዳው የተባሉ ካህን
ወይዘሮ አሰለፈች ታስገርሚያለሺ
ብስል ከጥሬውን ሁሉንም ጠርተሺ
በባል እንዲህ አርገሽ ትጫወቻለሺ
(‹በባል› ሲሉ በሰምና ወርቅ በአንድ በኩል ‹በባልሽ ላይ›[የባሏ ተዝካር ነበርና] በሌላም በኩል ‹በበዓሉ ላይ› ማለታቸው ነበር)
ብለው በመጨረሻ አሸበሸቡ ይባላል፡፡
 ይህ ታሪክ ትዝ ያለኝ ቅዳሜ ዕለት ነበረ፡፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት ለማክበር ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ተጉዤ፡፡ ጥሪው ከቀኑ ሰባት ሰዓት ይል ነበርና በሰዓቱ ነበር የደረስነው፡፡ በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መኪና አቁመን ወደ ታች ስንወርድ ሕዝቡ እንደጎርፍ ይወርድ ነበር፡፡ ‹ሃይገር› መኪኖች ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ እያመጡ ይዘረግፋሉ፡፡ እናቶች፣ አባቶች የተወሰኑ ወጣቶች፣ አንዳንዶቹም ከግንባታ ላይ ተነሥተው የመጡ የሚመስሉ ሠራተኞች ወደ ታች ይወርዳሉ፡፡ እኔም መርሐ ግብሩ ምን ዓይነት ቢሆን ነው ይህንን ሁሉና ይህንን ዓይነቱን ሕዝብ የሚያሳትፈው እያልኩ ጉጉቴን ጨመርኩ፡፡ በ‹ሃይገር› መኪኖቹ የፊት መስተዋት ላይ ‹የወረዳ እንትን ተሳታፊዎች› የሚል ተለጥፎባቸዋል፡፡ ከየወረዳው የተወጣጡ ነዋሪዎች መሆናቸውን ተረዳሁ፡፡ በምን መሥፈርት ይሆን ከአንድ ወረዳ ሕዝብ መካከል እነዚህ ተመርጠው የመጡት? እያልኩ እገረም ነበር፡፡
ወደ ሚሊኒየም አዳራሹ መግቢያ ስንደርስ ሰልፉ ከበሩ ግራና ቀኝ እንደ ዘንዶ ተጥመልምሏል፡፡ እኔ ደግሞ ሲፈጥረኝ ሁለት ነገር አልወድም ‹ሰልፍና ግፊያ›፡፡ መንግሥተ ሰማያት በሰልፍና ግፊያ የሚገባ ቢሆን ኖሮ ክርስትናዬን ዛሬውኑ እተወው ነበር፡፡ ተሰልፌና ተጋፍቼ እንደማልገባ አውቃለሁና፡፡ በኋላ ግን ‹ባጅ› የተሰጣችሁ ግቡ ሲባል ቅድሚያ አግኝቼ ገባሁ፡፡ የደኅንነት ሳጥኑን ፍተሻ አልፈን ስንገባ ሕዝብ ግጥም ብሏል፡፡
አስደናቂው ነገር የሚጀምረው እዚህ ነው፡፡
የተለያዩ ዓይነት እንግዶች ወደ አዳራሹ ተጋብዘዋል፡፡ ለእነርሱ የሚሆን ቦታ ግን አልተዘጋጀም፡፡ የተዘጋጀው ለመሪዎቹና ለተከታዮቻቸው ብቻ ነው፡፡ ከተለያዩ ሀገሮች የመጡ፣ ልዩ መግቢያ የተሰጣቸው ሰዎች በአዳራሹ ውስጥ እዚህም እዚያም ቆመዋል፡፡ ወንበሮቹ ከየወረዳው በመጡ ነዋሪዎች አስቀድመው ተይዘዋል፡፡ የቀሩት ወንበሮች ከዐሥር አይበልጡም ነበር፡፡ አንዳንዶቹ በፈረንሳይኛ፣ ሌሎቹም በእንግሊዝኛ ያማርራሉ፤ በዐረብኛና በፖርቹጊዝ የሚራገሙም ነበሩ፡፡ በሌሎች በሮች በኩል ወደሚገባባቸው ሌሎች መቀመጫዎች ለመግባት ይጠይቃሉ፤ የሚከለክል እንጂ ለምን እንደተከለከለ መልስ የሚሰጥ ግን አልነበረም፡፡ ‹የአስተባባሪዎቹ ቢሮ› የሚል ወደተለጠፈበት ክፍል ብዙዎች ይገቡና የሚያስተናግዳቸው አጥተው ንዴታቸውንና ቁጣቸውን ጨምረው ይመለሳሉ፡፡  
ወንበሮቹ የተደረደሩት በመካከለኛው መደዳ ብቻ ነው፡፡ ሌሎች ወንበሮች እንደተከመሩ ናቸው፡፡ መቆሙ የሰለቻቸው የአዲስ አበባ ወረዳዎች ተሳታፊዎች ከተከመሩት ወንበሮች መናድ ጀመሩ፡፡ ያኔ አዲስና በፕሮግራሙ ያልተካተተ የሃምሳኛ ዓመት ትንግርት ተፈጠረ፡፡ ወንበር ለማግኘት የሚደረግ ትርምስ፡፡ እርግጥ ነው በአፍሪካ ወንበር እንዲሁ በቀላሉ አትገኝም፤ በብዙ ትርምስ እንጂ፡፡ አንዳንዱ አትርፎ ለመሸጥ በሚመስል መልኩ ስድስትና ሰባት ወንበር ተሸክሞ ይሄዳል፣ ሌላው ወንበሬን ወሰድክብኝ ብሎ ይጣላል፡፡ ወንበር ያገኘው ደግሞ በመሰለው መልኩ እየደረደረ ጓደኛውን ይጣራል፡፡ እናቶችና አዛውንት፣ ዐቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞችን ያስታወሳቸውና ያዘነላቸው አልነበረም፡፡
እየቆየ የተከመረውም ወንበር አለቀና ሕዝቡ መሬት ላይ መቀመጥ ጀመረ፡፡ ይኼኔ ነበር አስገራሚ ማስታወቂያ ከመድረኩ መሰማት የጀመረው፡፡ ‹‹የፊተኞቹ ወንበሮች ለዐለም ዐቀፍ እንግዶች የተያዙ ስለሆነ፣ እንግዶቹም ቦታ አጥተው ስለቆሙ እባካችሁ ተነሡ ይላሉ አዘጋጅ ግሩፖቹ›› የሚል ማስታወቂያ ተደጋግሞ ተነገረ፡፡ ይህ በሠፈራችን ሠርግ እንኳን የማይደረግ ስሕተት እንዴት በአፍሪካ ኅብረት 50ኛ ዓመት ሊከሰት እንደቻለ አስገራሚ ነው፡፡ በብዙ ሠርጎች ለሙሽሮች አጃቢዎች የሚዘጋጁ ወንበሮች ፊታቸውን በዞሩ ወንበሮች ታጥረው በተመደቡ ሰዎች ይጠበቃሉ፡፡ እዚህ ግን ለእንግዶች የተዘጋጁ መሆናቸውን የሚናገሩ ጠባቂዎች እንኳን አልነበሩም፡፡ ሌላው ቀርቶ በገመድ አጥሮ ጠብቆ ማቆየት ይቻል ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ካለፈ በኋላ ራሳቸው እንግዶቹ ቆመው ‹ተነሡላቸው› የሚል ቀልድ መቀለድ ግን ራስን ከማስገመት ያለፈ ዋጋ አልነበረውም፡፡ ማስታወቂያውን ሰምቶ ቦታ የለቀቀም አልነበረም፡፡ እንዲያውም ብዙዎች ወንበሮቻቸውን ወደፊት እያስጠጉ መተላለፊያውንም ዘጉት፡፡
በዚህ ክርክር መካከል አውቶቡሳቸውን ሞልተው የአፍሪካ ኅብረት ሠራተኞች መጡ፡፡ ከመላዋ አፍሪካ የተወጣጡትና አህጉሪቷን ወክለው የሚሠሩት እነዚህ ሠራተኞች አዳራሽ ሲገቡ ተዘጋጅቶላችኋል የተባሉት ቦታ ሞልቶ ነበር፡፡ ‹ሸክላ ሠሪ በገል ይበላል› የሚባለው እነርሱ ላይ አልሠራም፡፡ ከመድረኩም ‹እባካችሁ እንግዳ እናክብር፣ ተነሡ› የሚለው ማሳሰቢያም ሰሚ አላገኘም፡፡ ‹ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ ባለ ዕዳ አይቀበለውም› በሚል ሕዝብ መካከል ይህንን ማሳሰቢያ መናገር ድሮም ፍሬ ሊኖረው የሚችል አልነበረም፡፡
ፕሮግራሙ ተጀመረ፡፡ የአልጀሪያ ሙዚቀኛ በቤኒን ከበሮ መቺዎች ታጅቦ አምስት ሙዚቃዎችን አከታትሎ አቀረበ፡፡ ለአንድ ሙዚቀኛ፣ ያውም ከወንበሩ ሳይነሣ አምስት ሙዚቃ የማቅረብ ዕድል ከተሰጠው መላው ቀልጧል ማለት ነው አልን፡፡ እርሱም ቢሆን ‹ራሴን በራሴ ካላንቆለጳጳስኩት ማን ያንቆለጳጵስልኛል› የሚለውን የአማርኛ አባባል ሰምቶ ነው መሰል እርሱ የአልጀርያ ሰው መሆኑን፣ ከበሮ መቺዎቹም ከቤኒን መምጣታቸውን ራሱ ነገረን እንጂ የተናገረለት መርሐ ግብር መሪ አልነበረም፡፡ ምናልባት የአዲስ አበባ ወረዳዎች ተሳታፊዎች ያውቁታል ተብሎ ተገምቶ ይሆናል፡፡
እየቆዩም የልዩ ልዩ የአፍሪካ ሀገሮች ሙዚቀኞች እየመጡ እየሄዱ ባህላዊ ሙዚቃቸውን አቀረቡ፡፡ አልፎ አልፎ በስክሪኑ ላይ ከሚጻፈው በቀር አዳራሹን ለሞሉት የአዲስ አበባ ወረዳዎች ተሳታፊዎች ማን የት ሀገር እንደሆነና የሚያቀርበውም ነገር ትርጉም ምን እንደሆነ የሚነግረን አልነበረም፡፡ በአካባቢያችን የነበሩት እናቶችና አባቶች እንደ ሰርከስ ትርዒት እግራቸውን ወዲያና ወዲህ የሚያደርጉትን ሴት ዳንሰኞች እያዩ ‹ኤዲያ ምኒቷ ናት ባካችሁ› እያሉ ይገረሙ ነበር፡፡ ሙዚቃው እየጨመረ ሲሄድ በአዳራሹ ውስጥ ከአፍ እስከ ገደቡ ሞልቶ የነበረው ሕዝብ እንደ ስንቅ እየቀለለ መጣ፡፡ እንዲያ ለወንበር ሲሻማ የነበረው ሰው፣ ታግሎ ያመጣውን ወንበር እየተወው ሄደ፡፡ ለነገሩ ልማድ ነው ታግለው ያገኙትን ወንበር እየተው መሄድ፡፡
ብዙዎቹ በፈረንሳይኛና በእንግሊዝኛ የሚተላለፈውን መልእክት ሊረዱት አልቻሉም፡፡ ከአሥር ሺ በላይ የወረዳ ነዋሪዎችን ጠርቶ ፈረንሳይኛና እንግሊዝኛ ማውራት ባሎን በሚሊኒየም ነው የሆነው፡፡ ምናለ እነዚህን ቋንቋዎች ወደ አማርኛ የሚተረጉም ሰው ከመድረክ ቢኖር፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ ቋንቋዎችን ሊረዳ የሚችል ተጋባዥ ቢጠራ፡፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የዛሬ 50 ዓመት በአዲስ አበባ ሲመሠረት የመክፈቻውን ንግግር ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ያደረጉት በአማርኛ ነበር፡፡ የዛሬ ሃምሳ ዓመት መክፈቻ የነበረ ቋንቋ ሃምሳኛ ዓመቱ ሲከበር መተርጎሚያ እንኳን መሆን አቃተው፡፡
መሪዎቹ መምጣታቸው ተነግሮ ዋናው መርሐ ግብር በአፍሪካ ኅብረት መዝሙር ተከፈተ፡፡ ተነሡና አብራችሁ መዝሙሩን በሉ ተባልን፡፡ አሁን ምን አለ በግራና በቀኝ በነበሩት ስክሪኖች የመዝሙሩን ስንኞች ቢያቀርቡልን? ከየት አምጥተን ነው የአፍሪካ ኅብረትን መዝሙር አብረን የምንለው? ስክሪኑ ቅዳሜ ማታ የሚተላለፈውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ እየደጋገመ ሲያስተዋውቅ እንዴት ይህንን ማድረግ አቃተው?
ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ከአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር ዴላሚና ዙማ የእንግሊዝኛ ንግግር በኋላም የልዩ ልዩ ሀገሮች ሙዚቀኞች ቀጠሉ፡፡ የየት ሀገር ባህል ነው? ምን እያሉ ነው? በዐሥር ሺዎች ለሚቆጠሩት የወረዳ ተሳታፊዎች የሚነግራቸው አልነበረም፡፡ እነርሱም ነገር ዓለሙ አልጥም ሲላቸው ‹ዋናው ፊት ማስመታታችን ነው› ብለው ነው መሰል አዳራሹን እየለቀቁ ወጡ፡፡ ከዐሥር ሰዓት በኋላም አዳራሹ ድግስ እንዳለቀበት ተዝካር ባዶውን መቅረት ጀመረ፡፡
መሪዎቹም ሆኑ መርሐ ግብር መሪዎቹ፣ በስክሪን ብቅ እያሉ ንባብ የሚያሰሙንም ተናጋሪዎቹ ስለ አፍሪካ የነገው ትውልድ እየደጋገሙ ያነሡ ነበር፡፡ በአዳራሹ የታደሙት አብዛኞቹ ‹የየወረዳው ተሳታፊዎች› ግን የነገው ትውልዶች› ሳይሆኑ ‹የትናንትናው› ነበሩ፡፡ የነገው ትውልድ እንዲሳተፍ ከተፈለገ ከየወረዳዎቹ ከማምጣት ከየኮሌጆቹ፣ ከየትምህርት ቤቶቹና ማሠልጠኛዎቹ ወጣቶችን መጥራት ይቻል ነበር፡፡ በአንድ በኩል ሙዚቃውም የሚመስጣቸው፣ በሌላም በኩል ቋንቋውም የሚገባቸው እነርሱ ነበሩ፡፡ ከዚህም ባለፈ ደግሞ ስለ ነገው ትውልድ የሚነገረውን ሰምተው ለመተግበር እድሉ የነበራቸውም እነርሱ ናቸው፡፡
ከሁሉም በላይ ይህንን መሰል ዝግጅቶችን ለመሳተፍ ፍላጎት ይጠይቃል፡፡ በወረዳ ውክልና የሚሆን አይደለም፡፡ ከየወረዳዎቹ ይምጡ ከተባለም መርሐ ግብሩን የሚመጥኑ፣ ነገሩም የሚስባቸውና የሚገባቸው ቢሆኑ መልካም ነበር፡፡
በመርሐ ግብሩ መገባደጃ ላይ የነፍስ ኄር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊን አጭር የሕይወት ጉዞ የሚያሳይ ፊልም ቀርቦ ነበር፡፡ በዓሉ የመላ አፍሪካውያን በዓል እንደመሆኑ መጠን ከሁሉም መሪዎች ተነጥሎ የአቶ መለስ ታሪክ ብቻ ባይቀርብ መልካም ነበር፡፡ እንደ እርሳቸው ሁሉ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ያጣናቸው ሌሎች የአፍሪካ መሪዎችም አሉ፡፡ የእነዚህን መሪዎች አጭር ታሪክ አካትቶ ቢቀርብ ኖሮ ከበዓሉ ጋር ይሄድ ነበር፡፡ ፓን አፍሪኒዝም የሚለውን ሃሳብ በሰፊው እየሰበኩ የአንድን ሀገር ጉዳይ ብቻ በአፍሪካ በዓል ላይ ማቅረብ ከሃሳቡ ጋር አይሄድም፡፡ የግድ መቅረብ ነበረበት ከተባለ ደግሞ ሕዝብ ከመሄዱ በፊት እንዲቀርብ ማድረግ ይቻል ነበር፡፡ 

አሁን ግራና ቀኝ ዘወር ስል በአዳራሹ የማያቸው የሌሎች ሀገሮች ዜጎችንና በጉባኤው ውስጥ ሥራ ተሰጥቷቸው የግድ መቀመጥ ያለባቸውን ሠራተኞች ብቻ ነው፡፡ የሚከልሉት ሰው አለመኖሩን ሲያዩ ጋዜጠኞችም በኋላ በኩል ከተሰጣቸው ቦታ እየለቀቁ ፊት ለፊት መጥተው ካሜራዎቻቸውን ተከሉ፡፡ ሰው ከሄደ፣ አዳራሹም ወና መሆን ከጀመረ በኋላ ነበር የብዙዎቹ መሪዎች ንግግር መደረግ የጀመረው፡፡ እኔ የምለው ይሄ ረጅምና ለጆሮ የማይስብ ንግግር ማድረግ የአፍሪካ መሪዎች ጠባይ ነው እንዴ፡፡ እንዲያ ባለ አዳራሽ፣ በዚያ በረፈደ ሰዓት እጥር ምጥን ያለ ጆሮ ገብ የሆነ ንግግር ቢያደርጉ ምናለ፡፡ አፍሪካ ተረቶች፣ ምሳሌዎችና አፈ ታሪኮች የሞሉባት አህጉር ናት፡፡ ምናለ እነዚህን ተጠቅመው ንግግራቸውን ቢያንስ ደስ ብሎን እንድናዳምጠው ቢያደርጉ፡፡ እኔ ከዑጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በቀር አፍሪካዊ ተረትና ምሳሌ የጠቀሰ መሪ አልሰማሁም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም አንድ ደስጣ ወረቀት የሚያህል ንግግር  ይዘው ብቅ ሲሉ ልባችን ድክም ይል ነበር፡፡ እንዲያም ቢሆን ሲሰሙት የሚጥም፣ ጆሮ ገብ የሆነ ስሜት ያለው ንግግር ቢያደርጉ ምን አለ? ንግግርኮ የተጻፈ ማንበብ ብቻ ሳይሆን ሰው ሊሰማው በሚችል መልኩ ማቅረብም ነው፡፡ ያ መሆን ካልቻለ ደግሞ ‹የንግግር ጥበብ መጀመሪያ ነገር ማሳጠር ነው› የሚለውን መተግበር ነው፡፡
ከዩዌሪ ሙሴቪኒ ንግግር በቀር  ቅርጽና መልክ ያለው፣ ነገሮችን ነጥብ በነጥብ ያስቀመጠ፣ ፍልስፍናዊና ተጠየቃዊ የሆነ ንግግር አልሰማሁም፡፡ ሙሴቪኒ አፍሪካውያን ሊያነሷቸውና ሊመልሷቸው ይገባል ብለው ያቀረቧቸው አምስት ጥያቄዎችና የሰጧቸው መልሶች አስገራሚ ነበሩ፡፡ ለቅኝ መገዛታችን፣ በባርነት ለመሸጣችንና ላለማደጋችን አውሮፓውያንን ብቻ ሳይሆን ቀደምቶቻችንንም ሆነ ራሳችንን ጭምር መውቀስ አለብን ሲሉ ያቀረቡት ንግግር በአዳራሹ የነበሩትን በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ቁጭ ብድግ ያስደረገ ነበር፡፡ 

የመሪዎቹ ንግግር እየቀጠለ ሲሄድ አንድ ወር ሙሉ ሲያጠኑ የከረሙት ሕጻናት የማቅረቢያ ጊዜያቸው እያለፈ ነበር፡፡ እነዚህ ልጆች አንድ ወር ሙሉ ለአፍሪካ ኅብረት ሃምሳኛ በዓል ታቀርባላችሁ ተብለው ሲያጠኑ መቆየታቸውን፣ ዛሬም ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምረው ወደ አዳራሹ መምጣታቸውን እናቶቻቸው በኀዘንና በምሬት ነበር የሚተቹት፡፡ የልጆቹ መርሐ ግብር ግን ይቀርባል ከተባለበት ሰዓት እያለፈ፣ እነርሱም ወደ ድካምና ረሃብ እያመሩ መሆኑን ነበር የሚናገሩት፡፡ ለአልጀሪያው ሙዚቀኛ አምስት ሙዚቃ ከመስጠት ለእነዚህ ልጆች አንድ ዕድል መስጠት እንዴት ሳይቻል ቀረ፡፡ ሲሆን ልጆች ናቸውና አስቀድመው አቅርበው ወደየቤታቸው መጓዝ ነበረባቸው ካልሆነ ደግሞ ሳይመሽ እነርሱን መሸኘት ይገባ ነበር፡፡ ምን ያደርጋል፣ የአፍሪካ ሕዳሴ በሚነገርበት አዳራሽ የሕዳሴው ተስፋዎች ጊዜ የሚሰጣቸው አጥተው ከአዳራሹ ጀርባ እያዛጉ ነበር፡፡
ሕጻናቱ ያዛጋሉ፤ መሪዎቹ ንግግራቸውን ተራ በተራ ይቀጥላሉ፡፡ የየወረዳዎቹ ተሳታፊዎችም ጠቅልለው ከአዳራሹ ወጥተዋል፡፡ የሚያጨበጭብ እንኳን አልነበረም፡፡ ወደ ሁለት ሰዓት አካባቢ የሕጻናቱ መርሐ ግብር መታጠፉ ለልጆቹ ተነገራቸው፡፡ በየደቂቃው ስለ ነገዎቹ የአፍሪካ ትውልዶች እየተነገረ የእነዚህን ትውልዶች ፕሮግራም በማጠፍ ስለ አፍሪካ ኅብረት 50ኛ ዓመት መልካም ትዝታ እንዳይኖራቸው ተደረገ፡፡ መሪዎቹ ሁሉ በየንግግሮቻቸው በአፍሪካ ሕጻናትና ወጣቶች ላይ ያላቸውን ተስፋ ነበር የሚናገሩት፡፡ ሕጻናቱ ግን ፕሮግራማቸው ተሠርዞ በኀዘን እየወጡ ነበር፡፡
እኛም ተዳክመን ሁለት ሰዓት ላይ ለመውጣት ስንዘጋጅ ‹የለመደብኝ አይቅርብኝ› ብሎ መብራት ኃይል መብራቱን ድርግም አደረገው፡፡ መሪዎቹ በጨለማ ተዋጡ፡፡ እኛም እንዲህ ችግራችንን እዩልን እንጂ፡፡ መብራት ኃይልኮ እራት እየበላን፣ ሠርግ እየደገስን፣ በዓል እያከበርን፣ ትምህርት እየተማርን፣ ቅዳሴ እየቀደስን እንዲህ ድንገት ነው ድርግም የሚያደርግብን አልን በልባችን፡፡ የአዳራሹ ጀነሬተር ‹አውቶማቲክ› አልመሰለኝም፡፡ ሞተሩ እስከሚነሳ ረዥም ሰዓት ፈጅቷል፡፡ በዚህ መካከልም መሪዎቻችን በሞባይል መብራቶች በያሉበት ተቀምጠዋል፡፡ አዳራሹ በጨለማ ከመዋጡ ጥቂት ቀደም ብሎ ግን መሪዎቹ ‹አፍሪካ የጨለማ አህጉር እየተባለች ስሟ በመጥፋቱ›  እየተቆጩ ነበር፡፡ ይህንን ቁጭት ከሰማን ከደቂቃዎች በኋላ ግን አዳራሹ በጨለማ ተዋጠ፡፡
ስንወጣ ‹ፓን አፍሪካኒዝምና የአፍሪካ ሕዳሴ› የሚለውን ፖስተር በመውጫው በኩል በትልቁ ተሰቅሎ እያየነው ነበር፡፡

72 comments:

 1. A perfect comment

  ReplyDelete
 2. አዳራሹ የታደሙት አብዛኞቹ ‹የየወረዳው ተሳታፊዎች› ግን የነገው ትውልዶች› ሳይሆኑ ‹የትናንትናው› ነበሩ፡፡ የነገው ትውልድ እንዲሳተፍ ከተፈለገ ከየወረዳዎቹ ከማምጣት ከየኮሌጆቹ፣ ከየትምህርት ቤቶቹና ማሠልጠኛዎቹ ወጣቶችን መጥራት ይቻል ነበር፡፡ በአንድ በኩል ሙዚቃውም የሚመስጣቸው፣ በሌላም በኩል ቋንቋውም የሚገባቸው እነርሱ ነበሩ፡፡ ከዚህም ባለፈ ደግሞ ስለ ነገው ትውልድ የሚነገረውን ሰምተው ለመተግበር እድሉ የነበራቸውም እነርሱ ናቸው፡፡....ምን ሚሊኒየም ብቻ የትም ብትሄድ ያው ነው! ትውልድ ድሮ ቀረ ነው ዲስኩሩ ሁሉ! ቤትክርስቲያን ብትሄድ አሁንም ወጣቱ ይወቀሳል ግን እሚገርማችሁ... እንደውም ሊመሰገን ይገባው ነበር ባሁኑ ጊዜ እኮ አሁን በአለም ላይ በፊልም መልክ በኢንተርነት በቲቪ by dstv በማስታወቂያ እጅግ አምሮ ተሽሞንሙኖ የዘመኑን ቴክኖሎጂ ህኡሉ አሙጦ ተጠቅሞ ሃጥያት በሃይልና በጥበብ ይሰበካል!ቤተክርስቲያን ለዚህ ኧላፍ ወጊያ መልስ መስጠት ቀርቶ ቋሚ የትምርተ ሃይማኖት ማስተማሪያ አልአዘጋጀችም!!! እርሱዋ ራሷ አራያ እንዳትሆን ራሱዋ ፍሬ አልባ በለስ ሆናለች ግን አሁንም ለወጣቱ ጥፋት ወጣቱ ራሱ ይወቀሳል!....

  ReplyDelete
 3. ስለ አፍሪካ የነገው ትውልድ እየደጋገሙ ያነሡ ነበር፡፡ በአዳራሹ የታደሙት አብዛኞቹ ‹የየወረዳው ተሳታፊዎች› ግን የነገው ትውልዶች› ሳይሆኑ ‹የትናንትናው› ነበሩ
  10Q if you can notice this happen always on ETV. All of them dictators nothing special they can talk but when you come to the truth (feyale wediya kezemezeme wedihe) sorry for Africa

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዳኔ ፤ መቸስ በሕር ማዶ የምንኖረው ወገኖቾሕ ከድርጌቱ አስደነቄነት ባቫገር ፤አስቄኝ በመሆኑ እናመሰግናለን። ለመሆኑ የመብረት መጥፋትጉዳይ መጨረሻው ምን ይሆን?

   Delete
 4. ስለዚህ ምንም ብንሰራም ባንሰራም ያ ትውልዶች ስለኛ ትውልድ የመናገር ሞራላዊ መብት የላችሁምና ዲስኩራችሁን አቁሙት ለእኔ art የሚመችኝ ከሆነ ለናንተ ደግሞ art ለሃገሪቱ ፋይዳ የለሽ ከመሰላችሁ መሰላችሁ ይምሰላችሁ cultural imperialism አቆርቁዞን ያያችሁ ከመሰላችሁ መሰላችሁ ይምሰላችሁ.............. አገር ወዳድ ሳይሆን ጎሳ ወዳድ ከመሰላችሁ ይምሰላችሁ.... ግን የሂስ መአት አታውርዱብን!!! መብቴ መብቴ ያለው ማን ነበር???

  ReplyDelete
 5. Min Tadergewaleh?

  ReplyDelete
 6. እንዴት ያሳፍራል በእማማ ሞት!!! ያለዛሬም ጥምብ በልቼ አላቅ አለ ጅብ፡፡ ምነው! ምነው! ምነው!! ዳኒ ይህን ጽሑፍ አንብቤ ስጨርስ የውጭ አገር ወይም የአገር ውስጥ እንግዳ ወይም የወረዳ ተወካይ ሆኜ በቦታው ባለመገኘቴ እግዚአብሔርን አመሰገንኩት፡፡ ግን እንደ አንድ እንግዳ ተቀባይ ኢትዮጵያዊ የተሰማኝ ሀፍረት ልቤ ውስጥ እንደ አለት ከብዶ ይሰማኘኛል፡፡ ኢቲቪ ምነው ይህን ሳይነግረን ቀረ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Endet ke ETV tiru(ewnet) Titebikaleh/sh? Betam tighermaleh/sh wendime/ehite. Thanks dani.

   Delete
  2. ኢቲቪ ምነው ይህን ሳይነግረን ቀረ?
   ምነው ወዳጄ አልሰማህም እንዴ; ኢቲቪ ውሸት ሲቀምም ሳለ እውነት ወደ ወዳጆቿ ጥላው እብስ አለች፡፡

   Delete
 7. EGZIABEHER LE AFRICA MERIWOCH EWUNETUN YEGLETSELACHEWU;; EGZIABEHEREN MAMLEK KEJEMERU AFRIKA YEALEM ENAT TEHONALECH. AMEN

  ReplyDelete
 8. እኛም ተዳክመን ሁለት ሰዓት ላይ ለመውጣት ስንዘጋጅ ‹የለመደብኝ አይቅርብኝ› ብሎ መብራት ኃይል መብራቱን ድርግም አደረገው፡፡ መሪዎቹ በጨለማ ተዋጡ፡፡ እኛም እንዲህ ችግራችንን እዩልን እንጂ፡፡ መብራት ኃይልኮ እራት እየበላን፣ ሠርግ እየደገስን፣ በዓል እያከበርን፣ ትምህርት እየተማርን፣ ቅዳሴ እየቀደስን እንዲህ ድንገት ነው ድርግም የሚያደርግብን አልን በልባችን፡፡

  ReplyDelete
 9. ‹የለመደብኝ አይቅርብኝ›
  እኛም እንዲህ ችግራችንን እዩልን እንጂ፡፡ መብራት ኃይልኮ እራት እየበላን፣ ሠርግ እየደገስን፣ በዓል እያከበርን፣ ትምህርት እየተማርን፣ ቅዳሴ እየቀደስን እንዲህ ድንገት ነው ድርግም የሚያደርግብን አልን በልባችን፡፡ የአዳራሹ ጀነሬተር ‹አውቶማቲክ› አልመሰለኝም፡፡ ሞተሩ እስከሚነሳ ረዥም ሰዓት ፈጅቷል

  ReplyDelete
 10. በባል እንዲህ አርገሽ ትጫወጫለሺ....ማፈሪያ...በከሸፈ ትዉልድ..አኩሪ የነበረ ታሪካችን እየተበላሸ ይገኛል..

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ አገራችንን ያከሸፋት እኮ የናንተው ፋኖ ተሰማራ ትውልድ ነው ሌላው ቀርቶ ያሁኑ መሪዎቻችን እኮ የናንተው ትውልድ ናቼው = መቀነቴ አደናቀፈኝ ከተጠያቂነት አያድንም=እውነቱን ልንገርህ ወዳጄ እናንተ ከሃይለ ስላሴ ትውልድ የተቀበላችሁዋትን ሞገስ ያላትን ኢትዮጲያን አዋርዳችሁ ለኛ አስረከባችሁን አሁን ያለው ትውልድ ኢትዮጵያን የሚያውቃት ድሃ ሀገር መሆኑዋን ብቻ እንጂ ያችን ባለ ግርማ ሞገስ አገር አይደለም !!! ይህ ትውልድ በቀደሙት ትውልዶች እስኪበቃው ድረስ ተዘልፏል፡፡ የአገር ፍቅር እንደሌለው ተወርቶበታል፡፡ ሳይመሰከርበት በአገር ክህደትና ደንታ ቢስነት ተወንጅሏል፡፡ የዚያ ዘመን ጀብደኝነት ታሪክ ተጋሪ ባለመሆኑና የዚያ ዘመን መፈክሮች አቀንቃኝ ባለመሆኑ ተወርፏል፡፡ አገሪቱን በግራና በቀኝ ቀስፈው የያዙ ጽንፈኞች ትውልዱ በፈለጉት መንገድ አልሄድ ሲላቸው “ወኔ ቢስ” ብለው ተሳልቀውበታል፡፡ ይህ ዘመን የ”ዲጂታል” ዘመን በመሆኑና በ”አናሎግ” መሥራት ባለመፈለጉ ብቻ ትውልዱ በርካታ ውርጅብኞች ደርሰውበታል፡፡ አሁን ግን ፍትሐዊ የሆነ ብያኔ ሊሰጠው ይገባል፡፡ የአስተሳሰብና የአመለካከት ልቀት ለተሻለች አገር መፈጠር የሚያስፈልግ በመሆኑ የጋሻ ጃግሬነት ፖለቲካ አራማጅነት የትም አያደርስም፡፡ በመሆኑም ትውልዱ ከእንዲህ ዓይነቱ ኩነና ተላቆ የአገሩ አለኝታ ይሆን ዘንድ ፍትሐዊ ግምገማ ይደረግለት፡፡ በግራና በቀኝ ጠርዞች ያሉ ጽንፈኞች ይህንን ያስቡበት፡፡.... ባንተው አባባል ወዳጄ የናንተው የክሽፈት አብዮታዊ ትውልድ ቢበቃውስ? ይህ ትውልድ ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገው ዕውቀት ነው፡፡ የዘመኑ ቴክሎጂና አስተሳሰብ በደረሰበት የዕድገት ደረጃ ትውልዱ ጥራት ያለው ትምህርት ያስፈልገዋል፡፡ ዓለም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ለማመን በሚያዳግት ፍጥነት እየገሰገሰ በመሆኑ፣ አገራችን ኢትዮጵያ ከምግብ ተረጂነት ወጥታ ራሷን በአስተማማኝ ሁኔታ የምትችልበት ዕውቀት ያስፈልጋታል፡፡ የኋላ ቀርነትና የረሃብ ተምሳሌት የሆነች አገር ችግር ፈቺው መድኃኒቷ ዕውቀት ብቻ በመሆኑ፣ ትውልዱ በሥርዓት ታንጾ መማር አለበት፡፡ የሚማረው ትምህርት ችግር ፈቺና ሁሉን አቀፍ ሆኖ አገሪቷን ከተዘፈቀችበት ማጥ ውስጥ ያወጣት ዘንድ የግድ ይላል፡፡ ይህ ትውልድ መማር አለበት ስንል ሁለንተናዊውን ችግራችንን አብጠርጥሮ በማወቅ ከዘመኑ ጋር እኩል የምትራመድ አገር መፍጠር አለበት፡፡ ምክንያታዊ በሆነ አስተሳሰብና ለዕድገት በሚበጅ ዕውቀት ራሱን አጎልምሶ አገሪቷን ከበለፀጉ አገሮች ተርታ ማሰለፍ አለበት፡፡ ይህንን ለማሳካት ደግሞ በተግባር የተደገፈ ጥራት ያለው ዕውቀት መቅሰም የግድ ይለዋል፡፡

   አዲሱ ትውልድ ነፃነት ይፈልጋል፡፡ ይህ ትውልድ የተረጋጋና አካባቢውን በሚገባ ይረዳ ዘንድ መብቱ ሊከበርለት ይገባል፡፡ የፈለገውን የመምረጥ፣ የሚመስለውን ሐሳብ የመያዝ፣ ሐሳቡን በነፃነት የመግለጽና የማስረዳት መብቱ ያለምንም ዕቀባ እንዲከበርለት ያስፈልጋል፡፡ በፖለቲካዊም ሆነ በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የማንም ጥገኛ ሳይሆን ለዕውቀትና ለምርምር የሚያደርገው ጥረቱ ሊደገፍ ይገባል፡፡ በፈለገው የፖለቲካ ድርጅት፣ የሙያ ማኅበር፣ የሲቪል ማኅበረሰብና በመሰል ተቋማት የመደራጀት ሰብዓዊ መብቱ መከበር ይኖርበታል፡፡ ለአገር ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችለው የትውልዱ ነፃነት ያለምንም ጣልቃ ገብነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ በነፃነት አንገቱን ቀና አድርጎ የሚራመድ ትውልድ ሲኖር የተረጋጋና የበለፀገ ማኅበረሰብ ይፈጠራል፡፡ ችግር ፈቺነት የሚገኘው በነፃነት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ “ያ ትውልድ” በመባል የሚታወቀው የአብዮታውያን ጎራ ከ35 ዓመታት በፊት በፈጸመው ስህተት ሳይፀፀትና ለደረሰው ውድመት የጋራ ኃላፊነትን ሳይወስድ ዛሬም እንደያኔው ማዶ ለማዶ ሆኖ ይተነኳኮሳል፡፡ በተለይ ባለፉት ዓመታት ውስጥ የምንሰማቸው እንካ ሰላንቲያዎቹ ማንነትን የሚፈታተኑና በጭፍን ጥላቻ የተሞሉ ናቸው፡፡ በእንዲህ ዓይነቱ አሳፋሪና አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ አዲሱ ትውልድ ለጋሻ ጃግሬነት ይፈለጋል፡፡ ዘር፣ ሃይማኖትና አመለካከት በጠላትነት የሚያስፈርጁበት ዘመን ላይ እንድንደርስ ያደረገን ትናንት ከአንድ ርዕዮተ ዓለም ሲቋደስ የነበረው ሴረኛ የፖለቲካ ትውልድ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ በጭፍን ጥላቻ ውስጥ ሆኖ ዛሬም እንደ ትናንቱ ለመገደደል የሚያደባው የያኔው ትውልድ ለእዚህኛው ትውልድ እንዴት አርዓያ ሊሆን ይችላል? እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል! ...

   Delete
  2. ....ዘመኑ ትውልድ በርካታ ጥያቄዎች አሉት፡፡ ትውልዱ ሰላም ይፈልጋል፡፡ ከድህነት መላቀቅ ይፈልጋል፡፡ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቹ እንዲከበሩለት ይፈልጋል፡፡ ሐሳቡን በነፃነት የመግለጽና የመደራጀት መብቱ እንዲከበርለት ይሻል፡፡ እነዚህ መብቶቹ እንዲከበሩለት የሠለጠነና ዲሞክራሲያዊ ሒደት እንዲኖር ይፈልጋል፡፡ ይህንን ሒደት ማንም ሳይሆን የሚያመቻችለት ራሱ ይሆን ዘንድ የግድ ይላል፡፡ በሕገ መንግሥቱ ዋስትናና ዕውቅና ያገኙ መብቶቹ እንቅፋት ሊገጥማቸው አይገባም፡፡ የገዢው ፓርቲ ወይም የተቃዋሚዎች መፈክር አንጋቢ እንዲሆን እየተፈለገ የሚጋረጡበት መሰናክሎች ይወገዱ ዘንድ የግድ ይሆናል፡፡ የዘመኑ ወጣቶች እንደተባለው “ፋኖ ተሰማራ” ብለው ካልተነሱ ተብሎ ቅስቀሳ የትም አያደርስም፡፡ መሬትን በካሬ ሜትር የመለካት ዓይነት አስተሳሰቡ ከካሬ ሜትር አልላቀቅ ካለው “ያ ትውልድ” የተለየ የ“ዲጂታል” መለኪያ “ጂጋ ባይት” ላይ መድረሱን ማወቅ የግድ ይላል፡፡ አስተሳሰብ ከመሬት ተነስቶ ህልቆ መሳፍርት ወደ ሌላው ጠፈር መዝመት በቻለበት በዚህ ዘመን፣ የመሬት ላይ እንፉቅቅ የትም እንደማያደርስ በግራና በቀኝ ያሉ ጽንፈኞች ቢረዱት ይመረጣል፡፡ይህ የእኛ ትውልድ ከእነዚህ የሚማረው በጎ ነገር የለም፡፡ የትግላቸው መነሻ ግብ ሥልጣን ብቻ በመሆኑ ሽኩቻው የደራው ሥልጣን ላይ ብቻ ነው፡፡ እነሱ ያነገቡለትን ዓላማ ከዳር ለማድረስ የወደቁት ETHIOPIAYANOCH አፅም እንደሚፋረዳቸው እንኳን ረስተውታል፡፡ እነዚህ ለዚህ ትውልድ ምን ይረባሉ? አዲሱ ትውልድ ይህንን የአዙሪት ቀለበት በመበጠስ የአገሪቱን የፖለቲካ ባህል መለወጥ አለበት፡፡ በአገራችን ስለ ፖለቲካ ካለው ግንዛቤ ጀምሮ እስከ አጠቃላይ ድባቡ ድረስ ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ የማኅበረሰቡን ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚያዳብሩ ተቋማት ያስፈልጋሉ፡፡ አዲሱ ዲሞክራሲያዊና አሳታፊ አስተሳሰብ በውይይቶች እያዳበረ የመደማመጥና የመከባበር ባህል ሊዳብር የግድ ይላል፡፡ ፖለቲካችን የገባበት አረንቋ እጅግ በጣም አሳሳቢና አስከፊ ከመሆኑ የተነሳ በእዚህች አገር የጋራ ራዕይ እንዳይኖር ፈተና ሆኗል፡፡ በሃይማኖት፣ በዘር፣ በጾታ፣ በቋንቋና በባህል ልዩነቶች ውስጥ ተከባብሮ የሚኖረውን ሕዝብ ባሕርይ እየተፈታተነ ነው፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ታይተውና ተሰምተው የማይታወቁ ግጭቶች እየተሰሙ ነው፡፡ የዚያ ትውልድ ትሩፋት የሆኑ በጽንፈኝነት የታጀቡ ጥላቻዎችና የክፋት አስተሳሰቦች በቃችሁ ሊባሉ ይገባል፡፡ አዲሱ ትውልድ በጋራ ችግሮች ላይ በሠለጠነ መንገድ ሊመክር ይገባዋል፡፡ ሥልጡኑን የፖለቲካ መንገድ ለአገራችን በማስተዋዋቅ ከጠነዛው ፖለቲካ መላቀቅ አለብን፡፡

   በሴራና በአሻጥር የተተበተበው ያ አብዮታዊ ትውልድ ሥርዓት ባለው መንገድ ገለል ተደርጎ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ማዕቀፍ ሊፈጠር የግድ ይላል፡፡

   Delete
  3. ር ግን አሁንም በግራና በቀኝ ክንፎች የቆሙት የያኔዎቹ ትውልዶቻችን የዘመኑን ትውልድ ለመጠቀም ፈልገው ምላሽ ሲያጡ ‹‹ሀሞቱ የፈሰሰ›› እያሉ ያንቋሽሹታል፡፡

   ለአገር አንድነትና ለሕዝብ ፍቅር የሌለው በማስመሰል የስድብ ናዳ ያወርዱበታል፡፡ ይኼ ትውልድ የራሱ ዓላማና ፍላጎት እንዳለው መረዳት ያልፈለጉ የያኔዎቹ ልሂቃኖቻችን ሳይቀሩ የእነሱ ፍላጎት ‹‹ተሸካሚ›› እንዲሆን ይማስናሉ፡፡ እነሱ ያለፉበት ‹‹ፋኖ ተሰማራ›› በተግባር ተተርጉሞ ለማየት ስለሚፈልጉ ይኼ ትውልድ መፈክራቸውን ዛሬም ያስተጋባ ዘንድ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህ ፍላጎት ጀርባውን ሲሰጣቸው ‹‹ጫት ቃሚ፣ ሰካራም፣ ሐሺሻም…›› እያሉ ቅጽል ይጨምሩለታል፡፡ ሥልጣን ላይ ያለው ወገን ወጣቱ በሙሉ በየቀበሌውና በየክፍለ ከተማው ተገኝቶ ስለሱ ሲዘምርለት ቢውል ደስታውን አይችለውም፡፡ ወጣቱ የእሱ መፈክር አንጋቢና ዓላማ አስፈጻሚ እንዲሆን መሬቱን ሲቧጥጥ ያድራል፡፡ ለሥልጣን ያልበቃው ተቃዋሚ ደግሞ አደባባዮቹን በሙሉ በዓርማውና በመፈክሩ እንዲያጌጥለት ቆሞም ተኝቶም የሚያስበው ወጣቱን ነው፡፡ ቢቻል ድንጋይ ወርውሮ ካልቻለ ደግሞ ቢጮህለት ደስታውን አይችለውም፡፡ ይኼን ትውልድ በራስ መነጽር ብቻ እየተመለከቱ መወንጀል ትርፉ ስህተት ነው፡፡ ከስህተት የማይማር ደግሞ የዘራውን ሲያጭድ ይኖራል፡፡ አገር ከኋላ ቀርነት የምትላቀቀው አዲሱ ትውልድ መልካም አርዓያ ሲኖረው ነው፡፡ ይኼን አርዓያነት ባይታደለውም፣ ያለፈው ትውልድ ካለፈው ስህተቱ ባይማርም፣ የጽንፈኝነት ፖለቲካው አየሩን ቢሞላውም፣ መቻቻል የሚባለው የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ዳዋ ቢለብስም፣ የዘመኑ ትውልድ ለአዲሱ ዘመን አስተሳሰብና የአኗኗር ዘይቤ ልቡን መስጠቱን ማወቅ አለብን፡፡ አለበለዚያ ‹‹ የጠፋው ትውልድ, ግራ የገባው ትውልድ›› እያሉ ሆድ ማስባስ ለማንም አይጠቅም፡፡...

   Delete
  4. የከሸፈ ትውልድ ነው ያልከን....ፉከራው ሲያልቅበት ቀረርቶ ሞላበት! ያሉት አበው ወደው አይደለም....ወንድሜ እኛ ያሁኑ ትውልዶች ከናንተ ሙሉ በሙሉ የከሸፈ ነገር ብቻ ነው የተቀበልነው ያልከሸፈ ነገር ከናንተ ተቀብለን ቢሆን ኖሮ ያስኬድ ነበር ግን እንዳለመታደል ሆኖ ያልከሸፈ ነገር የቀረችው የጦርነት ገድላችን ነበረች ያንንም ደርግ በሻቢያ በዝረራ ሲሸነፍ እርሷም እልም አለች- የባድመ ጦርነት ተቀስቅሶ ያ ሰውየ አፉን ባይዝ ኖሮ የአፍሪካን ሃያል እና ግዙፍ የደርግ ሰራዊት የማሸነፉን ገድል እና ጉራውን ሲነዛብን ይኖር ነበር ነበር ባይሰበር ምኑ አትለኝም የ1000meter ጥልቅ ምሽጉ ! በሌላ አነጋገር አንድ ሊከሽፍ የነበረን ነገር ታደግን ማለት አይደለም!ገብቶሃል አይደል ወዳጄ! !!!እና ቀድሞ የከሸፈውን እንዴት ነው የምናከሽፈው???

   Delete
  5. አይ የኔ ነገር ስነ ቃሉን አከሸፍኩትኮ.. ላስተካክል ይፈቀድልኝ “ቅኔ ሲያልቅበት ቀረርቶ አለበት”

   Delete
  6. ይሄ እንግዲህ በእንግሊዝኛ "rant" የሚሉት አይነት ነገር መሆኑ ነው። ተናግረህ የወጣልህ ይመስለኛል።

   ለማስታወስ ያህል አንዳንድ ነጥቦችን ልጥቀስልህ፤

   - ይህ የዘርና የሃይማኖት ክፍፍል ሊመጣ እንደሚችል ቀድመው የተረዱ ሰዎችም ነበሩበት፣ ያ ትውልድ።

   - ወጣቱ አንተ ባልከው መንገድ ነፃ ሆኖ፣ በሚፈልገው መንገድ ተደራጅቶ፣ ትክክል ነው በሚለው ዘርፍ በሐገሩ ጉዳዮች ላይ እንዳይሳተፍ ያገደው ማን ይመስልሃል? አንተ "ለስልጣን የጓጉ" ያልካቸው የዚያ ትውልድ አባላት የሆኑ ተቃዋሚዎች በአዲስ ትውልድ እንዳይተኩ በሩን አጥብቆ የዘጋው ማን ይመስልሃል?

   መወቀስ ያለበትን ለይተህ ውቀስ።

   Delete
  7. ወዳጄ እነዚህ እምትላቼው ሰዎች እኮ የሚናገሩትንም አያውቁ! "አማራ የሚባል ጎሳ(ብሄር) ስለመኖሩ የሚያሳይ ማስረጃ የለም፡፡ ልክ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ ከዚህ ወጣ እዚህ ገባ እንደሚባለው አይነት ማስረጃ የለም፡፡" ብሎ መደምደም ምን ማለት ነዉ? ይሄ ሁሉ ብሄር (ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ) ባለበት አገር ዉስጥ አማራ የሚባለዉ ወገን ለብቻው ምንም የራሱ ማንነት ሳይኖረዉ እንዴት ሊኖር ቻለ?እንጂነር ይልቃል! ከሰደበኝ የደገመኝ ያለው ማን ነበር! ይህ ሰው ሳያውቀው እኮ ምን እይአለ እንደሆነ ገባህ አያድርገውና ethiopia ብትበታተን አማራ ራሱን ችሎ ህልውናው ሳይጠፋ መቀጠል አይችልም እያለን እኮ ነው ምክንያቱም ብሄር አይደለም ብሄር ካልሆነ መሸንሸኑ ነው gojam,wollo ,gonder...enjinerer the second weyane go to hell! አማራ በብሄር ተደራጀም አለተደራጀም ኢትዮጵያ አልቆላታል::

   Delete
 11. ‹የንግግር ጥበብ መጀመሪያ ነገር ማሳጠር ነው›

  ReplyDelete
 12. የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የዛሬ 50 ዓመት በአዲስ አበባ ሲመሠረት የመክፈቻውን ንግግር ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ያደረጉት በአማርኛ ነበር፡፡ የዛሬ ሃምሳ ዓመት መክፈቻ የነበረ ቋንቋ ሃምሳኛ ዓመቱ ሲከበር መተርጎሚያ እንኳን መሆን አቃተው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አማርኛን ለአስራ ሰባት ዓመት በጫካ ሃያ አንድ ዓመት በቤተ መንግስት እንደተዋጋነው አትርሱ።

   Delete
  2. Dawit ለምን ትፅፍበታለህ ታነብበታለህስ ሕሊና ካለው ሰው እንዲህ አይነት ንግግር አይጠበቅም ለነገሩ ያለህ አትመስልም ዘረኛ

   Delete
  3. ዳዊት የራስህን ለማንሳት የሌላውን ማስታል ድድብና ነው

   Delete
 13. asafarintu leqedemut meriwochna yeafrika hibiret ezih endihon letageluti chimer new

  ReplyDelete
 14. እንዴት ያሳፍራል በእማማ ሞት!!! ያለዛሬም ጥምብ በልቼ አላቅ አለ ጅብ፡፡ የውጭ አገር ወይም የአገር ውስጥ እንግዳ ወይም የወረዳ ተወካይ ሆኜ በቦታው ባለመገኘቴ እግዚአብሔርን አመሰገንኩት፡፡ ግን እንደ አንድ እንግዳ ተቀባይ ኢትዮጵያዊ የተሰማኝ ሀፍረት ልቤ ውስጥ እንደ አለት ከብዶ ይሰማኘኛል፡፡tnxs

  ReplyDelete
 15. 1ኛ. ሕጻናትን ማጉላላትና ስለነገዋ አፍሪካ ማሰብ የተጋጩበት በዓል
  2ኛ. የዚህ ድርጅት ፋና ወጊዎችን እነ ክዋሜ ንክሩማን ጨምሮ በአምሳ ዓመታት ውስጥ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን አካትቶ ዶኩዩመንታሪ ፊልም ማቅረብን ትቶ አቶ መለስን መዘከር
  3ኛ. ለዚህ ቀን እንኳን የማይበቃ ኢኤኃኮ የአገሪቱ የኃይል አቅርቦት ችግር ሥር የሰደደ መሆኑን ያሳየበት ነው፡፡

  በታይታና በሪፖርት ብቻ ቀጣዩን አምሳ ዓመት እንገፋው ይሆን? መለስን በማወደስ ብቻ የአፍሪካ ችግር ይቀረፋል? የአፍሪካ መሪነትን ሚና መጫወት ይቻላል? አይ የኢትዮጵያ ነገር፡፡

  ልቅም ያለ ትዝብት፣ ፍሰት ያለው ትችት ነው ያቀረብከው ዳንኤል፡፡

  ReplyDelete
 16. Shame shame shame shame on us.

  ReplyDelete
 17. አንጀት በሚያርስ አገላለፅ ሁኔታውን ተችተኸዋል፣ እንዲህ አይነት የመስተንግዶና የመርኃ ግብር መሪዎች ለዛ ቢስነት በጣም እየተለመደ ሄዷል፡፡ ነገሩ ጥበብን የሚፈልግ ነገር ሲሆን ጠቢባኑን የሚያቀርባቸው ስርአት የለም፡፡ መርኃ ግብር አመራርን ማህበረ ቅዱሳን እንዲያስተምር ምናለ ቢፈቀድለት፤ ያንድ ሀይማኖት ጉዳይ ለሚመስላቸው እጅግ ከባድ ነው እንጅ፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ባንድ አዳራሽ ቢገባ በስርአት እንደሚያስተናግዱት ታዝቢያቸዋለሁ፡፡ ዳኒም አካላቸው ነውና የአፍሪካን ህብረት ታድሞ በንስር አይኑ ገምግሞ በመስተንግዷቸው ዘጭ አድርጓቸዋል፤ ስህተታቸውን ከማረም ውጭ ምንም ማስተባበያ አያስፈልጋቸውም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ድንቅ ሃሳብ ወንድምዬ ለማኀበረ ቅዱሳን ይሰጠው በ7 ሺህ ሕዝብ አይተናቸዋል

   Delete
 18. Ygrmal yeafrica hebret mkmeca yelahcene lje kemal belat Addis Ababa Ethiopia

  ReplyDelete
 19. It is very shame. I think dani the Ethiopian culture ignored by this generation. The coming generation asks his/her grandfather history, at that time what is the answer for the rise questions. God bless Ethiopian.

  ReplyDelete
 20. Tena Yistelign Dn. Daniel Kibret

  I would like thank you for your perspective and critique in many subjects. Most of them are constructive and educational. They also mirror your own view as it is. As you know it, you are best known as spiritual preacher or " MEnfesawi Memhir" than neutral blogger.
  Most of the time I read your articles from point view of spiritual writer/blogger. So I expect a high level of word choice and careful sentences that fit your level of knowledge and high morality.

  What I want to say is that your expression of comparing the heaven with little suffer of being in line is not comparable. I hope you don't forfeit Heaven for "being in line" for real because if you are not in heaven automatically you are in Seol.

  Therefore, I just want to say the sentence" መንግሥተ ሰማያት በሰልፍና ግፊያ የሚገባ ቢሆን ኖሮ ክርስትናዬን ዛሬውኑ እተወው ነበር " makes me uncomfortable. It can be interpreted in different ways even if you don't mean it.

  Other than that the article is very touchy. I thank you for your effort to show us the 50th African Anniversary event.


  From Chicago

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear samuel, andande beqalat lay betam
   'serious' mehon tiru aydelem. negerin eyawazu nw.

   Delete
  2. Hi Sami, I share ur idea but I faced difficulty to understand what Daniel want to mean. Really I am shocked when I read that. But I think Self is as such simple, but Daniel gave his all life to God.
   lelaw lelaw aybeltim ke meselef yilk. Sons & daughters of God leave so many things for God. Ene demo Dani be self yemigeba bihon noro 10 amet bihon enkuan eselef neber Genet lemegbat. yihema kelal new. ene ende christian salwash, salserk, salsadeb,salzemut, sew saltela, yalegnin akafiye, etc menor new yakategn. Dani u r lucky that these things are simple for u rather than self meselef.

   Delete
 21. Let God bless your hands!! You have eagle eyes!![ eagle is sign of your site,too:)! kassahun z bata le mariam

  ReplyDelete
 22. All of you are too Boring!

  ReplyDelete
 23. ከዩዌሪ ሙሴቪኒ ንግግር በቀር ቅርጽና መልክ ያለው፣ ነገሮችን ነጥብ በነጥብ ያስቀመጠ፣ ፍልስፍናዊና ተጠየቃዊ የሆነ ንግግር አልሰማሁም፡፡ ሙሴቪኒ አፍሪካውያን ሊያነሷቸውና ሊመልሷቸው ይገባል ብለው ያቀረቧቸው አምስት ጥያቄዎችና የሰጧቸው መልሶች አስገራሚ ነበሩ፡፡ ለቅኝ መገዛታችን፣ በባርነት ለመሸጣችንና ላለማደጋችን አውሮፓውያንን ብቻ ሳይሆን ቀደምቶቻችንንም ሆነ ራሳችንን ጭምር መውቀስ አለብን ሲሉ ያቀረቡት ንግግር በአዳራሹ የነበሩትን በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ቁጭ ብድግ ያስደረገ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 24. Dani your idea is impresive but some coments are too long does it mean our african leaders trnsfers there long speach trani "ነገራችሁ እንደሽማግሌ ወሬ የተንዛዛ አይሁን"

  ReplyDelete
 25. ነገራችሁ እንዳፍሪካ ማሪዎች ንግግር የተንዛዛ አይሁን

  ReplyDelete
  Replies
  1. እረ ይንዛዛ እንጂ ወዳጄ መፈክር እንደሆነ የትም አላደረሰንም

   Delete
 26. መብራት ኃይልኮ እራት እየበላን፣ ሠርግ እየደገስን፣ በዓል እያከበርን፣ ትምህርት እየተማርን፣ ቅዳሴ እየቀደስን እንዲህ ድንገት ነው ድርግም የሚያደርግብን አልን በልባችን
  ብዙዎቹ በፈረንሳይኛና በእንግሊዝኛ የሚተላለፈውን መልእክት ሊረዱት አልቻሉም፡፡ ከአሥር ሺ በላይ የወረዳ ነዋሪዎችን ጠርቶ ፈረንሳይኛና እንግሊዝኛ ማውራት ባሎን በሚሊኒየም ነው የሆነው፡፡ ምናለ እነዚህን ቋንቋዎች ወደ አማርኛ የሚተረጉም ሰው ከመድረክ ቢኖር፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ ቋንቋዎችን ሊረዳ የሚችል ተጋባዥ ቢጠራ፡፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የዛሬ 50 ዓመት በአዲስ አበባ ሲመሠረት የመክፈቻውን ንግግር ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ያደረጉት በአማርኛ ነበር፡፡ የዛሬ ሃምሳ ዓመት መክፈቻ የነበረ ቋንቋ ሃምሳኛ ዓመቱ ሲከበር መተርጎሚያ እንኳን መሆን አቃተው፡፡ መሪዎቹም ሆኑ መርሐ ግብር መሪዎቹ፣ በስክሪን ብቅ እያሉ ንባብ የሚያሰሙንም ተናጋሪዎቹ ስለ አፍሪካ የነገው ትውልድ እየደጋገሙ ያነሡ ነበር፡፡ በአዳራሹ የታደሙት አብዛኞቹ ‹የየወረዳው ተሳታፊዎች› ግን የነገው ትውልዶች› ሳይሆኑ ‹የትናንትናው› ነበሩ፡፡ የነገው ትውልድ እንዲሳተፍ ከተፈለገ ከየወረዳዎቹ ከማምጣት ከየኮሌጆቹ፣ ከየትምህርት ቤቶቹና ማሠልጠኛዎቹ ወጣቶችን መጥራት ይቻል ነበር፡፡ በአንድ በኩል ሙዚቃውም የሚመስጣቸው፣ በሌላም በኩል ቋንቋውም የሚገባቸው እነርሱ ነበሩ፡፡ ከዚህም ባለፈ ደግሞ ስለ ነገው ትውልድ የሚነገረውን ሰምተው ለመተግበር እድሉ የነበራቸውም እነርሱ ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 27. @ Samuel Alemie... don't take words so seriously. Dani is being humorous.

  ReplyDelete
 28. ... አንዳንዱ አትርፎ ለመሸጥ በሚመስል መልኩ ስድስትና ሰባት ወንበር ተሸክሞ ይሄዳል....ለነገሩ ልማድ ነው ታግለው ያገኙትን ወንበር እየተው መሄድ፡፡...
  i love this dani keep it up!!!!!!

  ReplyDelete
 29. Really it is funny view. የክቡር ዘበኛ ዱላዉ ቀረ እንጂ የንጉስ ግብር ለመብላት የሚደረግ ግርግር ይመስል ነበር::ዳኒ ሚሊኒየም አዳራሽ እንዳንተ አይጥሩን እንጂ በኤቲቪ እንድናይ ጋብዘዉናል እኮ::እኛ መቼ ይህንን ትርምስ አይተን:: ኤቲቪ ምን አለ አንዳንድ ቀን እንኳን እንደዚህ እዉነቱን ሹክ ብሎን ከስህተታችን ብንማር ቢማሩ::

  ReplyDelete
 30. ''mengiste semay be self ena begifiya yemigeba bihon kiristinayen zarewenu etewew neber''yemitilewa ababal altemechegnim.especially kante ayitebekim .beterefe leleaw hasab arif new.

  ReplyDelete
 31. መንግሥተ ሰማያት በሰልፍና ግፊያ የሚገባ ቢሆን ኖሮ ክርስትናዬን ዛሬውኑ እተወው ነበር፡፡ ተሰልፌና ተጋፍቼ እንደማልገባ አውቃለሁና፡፡
  alitemechegnim
  ayimechegnimim

  ReplyDelete
 32. መንግሥተ ሰማያት በሰልፍና ግፊያ የሚገባ ቢሆን ኖሮ ክርስትናዬን ዛሬውኑ እተወው ነበር፡፡ ተሰልፌና ተጋፍቼ እንደማልገባ አውቃለሁና፡፡.........አቤት ይሄንን ቃል በጋሻው ተናግረኦት ቢሆን ምድር ትጨስ ነበር!

  ReplyDelete
  Replies
  1. yes of course.B/c MK will ventilate it. But they don't handle Daniel. He is smarter than them but not Begashaw. Even though Begashaw is real orthodox follower (personally I don't agree with those who say he is Tehadiso or protestant), he is some what taken by worldly life, i.e why. They don't get a great mistake in Daniel. If Begashaw devote him self totally for the GOD & church,indeed he will win all of his oppositions. Sorry for him, some what looser. By the way where is he now? I expect he is in some monastry, this is what he need "Subae" at this time to return back his grace that God gave him t

   Delete
 33. Thank u D.Dinel for real discribtion of the program,when i read it, felt as i was there.Excellent views.what i could do is only one thing,pray to Ethiopia,bc we are missing so much from world.
  tio,Sc

  ReplyDelete
 34. Dear All,
  Though,one has a right to express his/her own view on any issue,I found this one very complicated.Danel,has been playing here and there.in his expression...እናቶች፣ አባቶች የተወሰኑ ወጣቶች፣ አንዳንዶቹም ከግንባታ ላይ ተነሥተው የመጡ የሚመስሉ ሠራተኞች ወደ ታች ይወርዳሉ፡፡ He undermine those people coz they didn't look wealthier as they look old and dirty...and በዚህ ክርክር መካከል አውቶቡሳቸውን ሞልተው የአፍሪካ ኅብረት ሠራተኞች መጡ፡፡ ከመላዋ አፍሪካ የተወጣጡትና አህጉሪቷን ወክለው የሚሠሩት እነዚህ ሠራተኞች አዳራሽ ሲገቡ ተዘጋጅቶላችኋል የተባሉት ቦታ ሞልቶ ነበር፡፡ ‹ሸክላ ሠሪ በገል ይበላል› የሚባለው እነርሱ ላይ አልሠራም፡፡ ከመድረኩም ‹እባካችሁ እንግዳ እናክብር፣ ተነሡ› የሚለው ማሳሰቢያም ሰሚ አላገኘም፡፡ It is clear that he wanted those people from Keble to give their sit for the respected AU staff and other wealthy guests.
  Correct me if I am wrong,but that has put you down.As a blogger,always be neutral and try to see things in perspective.Or simply read what you will post over and again before you do so;so that you won't confuse readers.
  God Bless!

  ReplyDelete
  Replies
  1. u are totally wrong, if u really want to hear that. He didn't undermine anyone, he just express the situation. And nothing confuse me. እንዲያውም ዳኒ ብዙ ጊዜ ደፈር ብሎ አይተችም እንጂ ከወረዳ እና ቀበሌ እየጠሩ በየስብሰባው የሚይሳትፏቸው ሰዎች ስለሚሰበሰቡበት ጉዳይ ግንዛቤ መያዝ እንኳን የማይችሉ መንግስት በተለያየ ጥቅም እና ደረቅ ፕሮፓጋንዳው ሰብስቦ ያስቀመጣቸው የመንግስት ሎሌዎች ናቸው:: ድሮስ በትምህርት/ግንዛቤ ብቁ የሆነ ሰው ለዚህ መንግስት ካድሬ ሊሆን ይችላልን?? ማፈሪያ መንግስት!!

   Delete
 35. hulla wadhola mahed lemadhan now mazen aysflgm

  ReplyDelete
 36. enquwan yalhedkugn

  ReplyDelete
 37. በጋሻው ተናግረኦት ቢሆን ምድር ትጨስ ነበር! why?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yezih chilota alew bileh new......

   Delete
 38. .አቤት ይሄንን ቃል በጋሻው ተናግረኦት ቢሆን ምድር ትጨስ ነበር! what does it means?

  ReplyDelete
 39. "ለነገሩ ልማድ ነው ታግለው ያገኙትን ወንበር እየተው መሄድ፡፡"

  ታግለው ያመጡትን ወንበር እየተው መሄድ ልማድ ሳይሆን የተፈጥሮ ግዴታ ነው፤ በተለይም በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ

  ReplyDelete
 40. Wendme Daniel

  Bachru yihen tsega yabezalh amlak yimesgen. Betam asteway neh. Egziabher degagmo degagmo yibarkh

  Amha( Germany )

  ReplyDelete
 41. መሪዎቹ ሁሉ በየንግግሮቻቸው በአፍሪካ ሕጻናትና ወጣቶች ላይ ያላቸውን ተስፋ ነበር የሚናገሩት፡፡ ሕጻናቱ ግን ፕሮግራማቸው ተሠርዞ በኀዘን እየወጡ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 42. እርግጥ ነው በአፍሪካ ወንበር እንዲሁ በቀላሉ አትገኝም፤ በብዙ ትርምስ እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 43. እኛም ተዳክመን ሁለት ሰዓት ላይ ለመውጣት ስንዘጋጅ ‹የለመደብኝ አይቅርብኝ› ብሎ መብራት ኃይል መብራቱን ድርግም አደረገው፡፡ መሪዎቹ በጨለማ ተዋጡ፡፡ እኛም እንዲህ ችግራችንን እዩልን እንጂ፡፡ መብራት ኃይልኮ እራት እየበላን፣ ሠርግ እየደገስን፣ በዓል እያከበርን፣ ትምህርት እየተማርን፣ ቅዳሴ እየቀደስን እንዲህ ድንገት ነው ድርግም የሚያደርግብን አልን በልባችን፡፡ የአዳራሹ ጀነሬተር ‹አውቶማቲክ› አልመሰለኝም፡፡ ሞተሩ እስከሚነሳ ረዥም ሰዓት ፈጅቷል፡፡ በዚህ መካከልም መሪዎቻችን በሞባይል መብራቶች በያሉበት ተቀምጠዋል፡፡ አዳራሹ በጨለማ ከመዋጡ ጥቂት ቀደም ብሎ ግን መሪዎቹ ‹አፍሪካ የጨለማ አህጉር እየተባለች ስሟ በመጥፋቱ› እየተቆጩ ነበር፡፡ ይህንን ቁጭት ከሰማን ከደቂቃዎች በኋላ ግን አዳራሹ በጨለማ ተዋጠ፡፡
  ስንወጣ ‹ፓን አፍሪካኒዝምና የአፍሪካ ሕዳሴ› የሚለውን ፖስተር በመውጫው በኩል በትልቁ ተሰቅሎ እያየነው ነበር፡፡
  God bless u Dani!!!!!!!!!! nice point of view

  ReplyDelete
 44. ይኼ ትውልድ የራሱ ዓላማና ፍላጎት እንዳለው መረዳት ያልፈለጉ የያኔዎቹ ልሂቃኖቻችን ሳይቀሩ የእነሱ ፍላጎት ‹‹ተሸካሚ›› እንዲሆን ይማስናሉ፡፡

  ReplyDelete
 45. first of all i appreciate the way u observe things.if the programmers do this, what can we say about the hospitality of we, Ethiopians!!!??
  may God hill u!

  ReplyDelete
 46. Adnakih nen daniel.egziabheir yetbekh.

  ReplyDelete
 47. እራትና መብራት አይንሳህ እየተባለ በሚመረቅባት ሐገር መብራት ኃይል የሚባል ሰሙን ወስዶ መብራት ነሳችሁ…ልማድ ነዉ፡፤ስምን ይዞ መቅረት፡፤ልማድ ሲዉል ሲያድር ደግሞ ገላ ይሆናልና ይኸዉ ገላ ሆነ!!!

  ReplyDelete