አንዳንዴ ትልቅ ነገር እንመኛለን፣ እንሻለን፣ እናስሳለንም፡፡ ትልቅ ሀብት፣ ትልቅ
ሥልጣን፣ ትልቅ ትዳር፣ ትልቅ ቤት፣ ትልቅ ዘመድ፣ ትልቅ ትምህርት፣ ትልቅ ሥራ፣ ትልቅ ቢሮ፣ ትልቅ ድርጅት፣ ከፍ ያለ
እንጀራ፣ ከፍ ያለ ደመወዝ፣ ከፍ ያለ ጓደኛ፣ ከፍ ያለ ጸጋ እንመኛለን፡፡ መመኘቱ በራሱ አንድ ነገር ነው፡፡ የሀገሬ ሰው ‹ቸር
ተመኝ ቸር እንድታገኝ› ይላልና፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ አፍርንጅ ሲጨምርበት ‹ጨረቃን ለመምታት ወርውር፣ እርሷን እንኳን ብትስት
ከከዋክብቱ አንዷን ታገኛለህና› ይላል፡፡ አፍሪካዊ ወገኖቻችንም ‹ለንጉሥነት ብትጸልይ ቢያንስ ጭቃ ሹምነት አታጣም› ይላሉ፡፡
ቀጣዩና ዋናው ጥያቄ ግን የተመኘነውን ብናገኘው፣ ያሰብነውን ብንደርስበት፣
የፈለግነውን ብንጨብጠው፣ አያያዙን እንችልበታለን ወይ? ነው፡፡ ያገኘነውን ነገር ለማስተዳደር፣ ለመያዝና ለመከባከብ የሚያስችል
ዐቅም አስቀድመን አከብተናል ወይ? ‹ሳያርሱ ዝናብ መመኘት ጎርፍ አምጣ ማለት ነው› የሚል አጎት ነበረኝ፡፡ ለምንመኘው ነገር
የሚበቃ ዝግጁነት ከሌለ የሚመጣው ነገር በረከት ሳይሆን መርገም ይሆናል፡፡ ምሕረት ሳይሆን መዓት ያወርዳል፡፡
ያለ ዕድሜ ጋብቻና ያለ ዕድሜ መውለድን ዓለም እየተቃወመው ያለው ማግባት ወይም
መውለድ ክፉ ስለሆነ አይደለም፡፡ ነገር ግን ማግባትም መውለድም ኅሊናዊ፣ አካላዊ፣አእምሯዊና ማኅበራዊ ዝግጁነት ስለሚጠይቅ
ነው፡፡ ያለበለዚያ ‹ልጂቱ ልጅ ወልዳ› የሚባለው ወይም ደግሞ
‹አንዲት ልጅ አግብቼ ነፍስ ያላወቀች
ስወጣ ስገባ አባባ እያለች›
የተባለው ነገር ይደርሳል፡፡ ሚስትነትና ባልነትን ያልተረዱ፣ ይህንንም ለመፈጸም
የሚያስችል አካላዊ ብቃት የሌላቸው፣ ቤት ማስተዳደርን ከልምድ እንኳን ያላዩ፣ ወይም ለማየትና ለመማር በሚያስችል ዐቅም ላይ
የሌሉ ሰዎችን ወደ ትዳር ማስገባት እንዲጠፉም እንዲያጠፉም መፍረድ ይሆናልና፡፡
ሕንዶች እንዲህ ይተርታሉ፡-
ሁለት ዓሣ አጥማጆች ዓሣ ሊያጠምዱ ወደ አንድ ወንዝ ወረዱ፡፡ አንደኛው ልምድ ያለው
ሲሆን ሌላኛው ጀማሪ ነው፡፡ ልምድ ያለው ዓሣ አጥማጅ ዓሣውን ያጠምድና በትልቅ መያዣው ውስጥ ይከትተዋል፡፡ ብዙ ጊዜም ታላላቅ
ዓሣዎችን ነው የሚያጠምደው፡፡ ጀማሪው አጥማጅም ያኛውን እያየ ማጥመጃውን ወደ ወንዙ ይወረውር ነበር፡፡ ትንንሽ ዓሣዎችን ሲይዝ
ወደ ማጠራቀሚያው ያስገባቸው ነበር፡፡ ታላላቅ ዓሦችን ሲይዝ ግን መልሶ ወደ ወንዙ ይጨምራቸዋል፡፡ ይህንን እያየም ያ ልምድ
ያለው ዓሣ አጥማጅ ይገርመው ነበር፡፡ ትልልቁን እየጣለ ትንንሹን ሲሰበስብ፡፡ ምናልባትም ባለማወቅ ይሆናል አለና፡-
‹ከትንንሹ ይልቅ ትልልቁ ዓሣ እንደሚጠቅምህ አታውቅም?› አለው፡፡
‹አውቃለሁ› ሲል መለሰለት፡፡
አሁን ይበልጥ ግራ ገባው፡፡
‹ታድያ ይህንን እያወቅክ ለምን ትልልቁን ዓሣ ስትይዝ መልሰህ ወደ ወንዙ
ትከተዋለህ?› አለና ጠየቀው፡፡
‹የያዝኩት ዕቃ ትንንሽ ዓሣዎችን ብቻ የሚይዝ ነው፡፡ ለትልልቅ ዓሣ የሚሆን ዕቃ
የለኝም፡፡ ለዚህ ነው የምመልሳቸው› አለው፡፡
አንዳንድ ሰው ምኞት ብቻ ነው ያለው፡፡ ምኞት ያለ ዝግጁነት፣ ያለ ሐኪም ምክር
እንደሚወሰድ መድኃኒት ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል፡፡ ውጭ ሀገር ለመሄድ የሚመኝ እንጂ ውጭ ሀገር ቢሄድ ሊያደርገው የሚችለውን
ለማወቅ፣ ልምድ ለመቅሰምና ለመጠየቅ የሚፈልግ ማን ነው፡፡ ገንዘብን የሚመኝ እንጂ ቢያገኘው እንዴት ሊያስተዳድረው እንደሚችል ዕውቀት
ሸምቶ የሚጠብቅ ማን ነው፡፡ ከታች ሆኖ ላይኛውን ሥልጣን የሚመኝ እንጂ እዚያ ሲደርስ ሊመራበት የሚችለውን ዕውቀት፣ ዝግጁነትና
ዐቅም የሚያካብት ማን ነው?
የሀገራችን ሰው ‹ዕብድ የያዘው መልክ አይበረክትም› ይላል፡፡ መልኩ ሳይሆን መልኩን
ማን ነው ያዘው? ነው ወሳኙ ማለቱ ነው፡፡ ማግኘቱ ሳይሆን አያያዙ፡፡ መውለዱ ሳይሆን አስተዳደጉ፣ ሀብቱ ሳይሆን አስተዳደሩ፣
ሥልጣኑ ሳይሆን አመራሩ፡፡ ዝናው ሳይሆን አጠባበቁ፣ ዕድሉ ሳይሆን አጠቃቀሙ፡፡
በሀገራችን ታሪክ የሚያስቆጩ የሚባሉ እንደ ታላላቅ ዓሦች የሚቆጠሩ ዕድሎች አምልጠውናል፡፡
አንድነታችንን ይበልጥ ለማስተሣሠር፣ ከድህነት ለመውጣት፣ ልዩነቶቻችንን ለመፍታት፣ የኋላ ቁርሾዎቻችንን ለመፋቅ፣ የፖለቲካ
ሂደታችንን ለማዘመን፣ አስተዳደራችንን ለማሠልጠን፣ ድንበራችንንና ክብራችንን ለመጠበቅ፣የሚያስችሉ ዕድሎች፡፡
እነዚህን ዕድሎች ሳንጠቀምባቸው የቀረነው ዕድለ ቢስ ስለሆንን አልነበረም፡፡ ዕድሎቹን
ለመጠቀም የሚያስችል ብስለት፣ ጥበብ፣ ታጋሽነት፣ ዐቅም፣ ፖለቲካዊ ዝግጁነት፣ ሆደ ሰፊነት፣ ቆራጥነትና ለሀገር አሳቢነት
ቀድመን ባለመያዛችን እንጂ፡፡ የያዝነው ዕቃ ትንሽ ያጋጠመን ዓሣ ግን ትልቅ ሆነና ማስቀመጫ አጣን፡፡ የነበረን አማራጭም
ዕድሎቻችንን ሁሉ ወደመጡበት መወርወርና እንዳልመጡ ማድረግ ነበር፡፡
ያ ልምድ የሌለው ዐሣ አጥማጅ ሁለት አማራጮች ነበሩት፡፡ አንደኛው ለዕቃው የሚመጥን
ዓሣ ማጥመድ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለዓሣው የሚመጥን ዕቃ ማዘጋጀት፡፡ እርሱ ግን ለዕቃው የሚመጥን ዓሣ ማጥመድን መረጠ፡፡
ስለዚህም ከዕቃው በላይ የሆነ ዓሣ ሲያጋጥመው ወደ ወንዙ መመለስን መረጠ፡፡ ትልቁን ዓሣ ማጥመድ፣ ዕድልም ችሎታም ይጠይቃል፡፡
ትልቁን ዓሣ ማግኘት ለብዙ ጊዜ የሚያደክመውን ተግባር በአንድ ጊዜ ለማድረግ መቻል ነው፡፡ ከብዙ ዓሦች የሚገኘውን ገቢ ከአንድ
ዓሣ ማግኘት ነው፡፡ ለሌላ ዕድል በር የሚከፍት ገንዘብ በአንድ ጊዜ መዛቅ ነው፡፡ ግን ማስቀመጫው ከሌለ ምን ዋጋ አለው?
ሳንጠቀምባቸው ያመለጡንን ዕድሎች ብንገመግማቸው አንዱ ምክንያት ይህ ሆኖ
እናገኘዋለን፡፡ ስለ ዕድሉ እንጂ ስለ ዕድሉ አያያዝ ያቀረብነው ወይም የያዝነው ነገር ባለመኖሩ፡፡ ዕድሎች መቼም ቢሆን
ይኖራሉ፡፡ ትናንትም፣፣አሁንም፣ ነገም አሉ፡፡ ዕድለኛ ያልሆነ ሰውም የለም፡፡ የዕድሎቻችን ዓይነቶች ይለያያሉ እንጂ፡፡ ዕድል
በደጁ የማታልፍለት ሰው የለም፤ ነገር ግን ዕድሎችን ለመጠቀም ዝግጁነታችን ይለያያል እንጂ፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ መጥፎ
ዕድል የለም የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ መጥፎ ዕድል ማለት ያለ ዝግጁነት የተገኘ ዕድል ማለት ነው ይላሉ፡፡
ለፖሊሲዎች የሚሆኑ ሰዎችን ማምጣትና ለሰዎች ዐቅም የሚሆኑ ፖሊሲዎችን መንደፍ
ይለያያሉ፤ ለመዋቅር የሚሆኑ ሰዎችን ማምጣትና ለሰዎች የሚሆን መዋቅር መቅረጽ ይለያያሉ፡፡ ታላላቅ ሃሳቦችን አምጥቶ ታላላቅ
ሃሳቦችን ሊይዙና ሊተገብሩ የሚችሉ ዐቅም ያለቸው ሰዎችን ከማምጣት ይልቅ ለታናናሽ ሰዎች የሚመጥኑ ሃሳቦችን የምናጠምድበት ጊዜ
አለ፡፡ ምክንያታችን ደግሞ የያዝነው ዕቃ ትንሽ መሆኑ ነው፡፡ እኛም ለዓሣው የሚመጥን ዕቃ ከማምጣት ይልቅ ለዕቃው የሚመጥን
ዓሣ መጥመድ ስለምንፈልግ፡፡
ሰውን እናትና አባቱ አንድ ጊዜ ይወልዱታል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ራሱን ለአዳዲስ ዕድሎች መውለድ የራሱ ድርሻ ነው፡፡
አንዲት ሴት ለመውለድ ዘጠኝ ወር ሙሉ ትዘጋጃለች፡፡ በሂደት ልጁ ልጅ ይሆናል፡፡ እርሷም እናት፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ በውስጧ ብዙ
ኩነቶች ይከናወናሉ፡፡ እርሷንም ልጇንም የሚለውጡ፡፡ የተፈጥሮ ሂደት ሲያበቃም ልጁም ልጅ ሆኖ ይወለዳል፣ እርሷም ወልዳ እናት ትሆናለች፡፡
ራስን ለተሻለ ዕድል መውለድም እንዲሁ ነው፡፡ መፈለግ ብቻውን ዋጋ የለውም፤ የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት መጣጣር፣
ብናገኘው ለሚያስፈልጉን ነገሮች መዘጋጀት፣ ለማስተዳደር የሚሆን ዐቅምንም መገንባት ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ቀድመው ሳይደረጉ
የሚመጡ ታላላቅ ዕድሎች እያዘንን የምንጥላቸው ታላላቅ ዓሣዎች ነው የሚሆኑት፡፡
ሴትዮዋ ለጸሎት በቆመች ቁጥር ትልቅ ሀብት ስጠኝ እያለች ትለምን ነበር፡፡ ከብዙ ልመናዋ በኋላም አንድ ሀብታም ሰው
አገባችና ሀብት ላይ ወደቀች፡፡ ያገባችውም ሰው ብዙም ሳይቆይ ዐረፈና ያንን ሁሉ ሀብት እርሷ ወረሰችው፡፡ በቤቱ ውስጥ ብዙ አገልጋዮች፣
ብዙ ከብቶች፣ ብዙ አጋስሶች ነበሩ፡፡ በየቦታው አያሌ ገባሮች፣ አራጣ ተበዳሪዎች፣ ጉልተኞችና ከብት አርቢዎችም ነበሩ፡፡ በየጊዜው
ሙግትና ጭቅጭቅ አያጣውም፡፡ ከአስገባሪዎችና ከገባሪዎች ጋር ክርክር አለው፡፡
ይህንን ሁሉ ውጣ ውረድ በየጊዜው እያለፈች መሄድ ሰለቻትና ወደረሳችው ፈጣሪዋ ተመለሰች፡፡ ‹‹ምነው አምላኬ እንዲህ
ያለው ጣጣ ውስጥ ከተትከኝ፤ እንዴት እንዲህ ያለ የመከራ እንጀራ ውስጥ ትጥለኛለህ› እያለች ታማርር ነበር፡፡ አንድ ቀን ፈጣሪዋ
ተገለጠና፡፡
‹ለምን ታማርሪኛለሽ› አለና ጠየቃት፡፡
እርሷም ‹ ለምን አላማርርህም፤ እንዲህ ያለ ወጥመድ ውስጥ ስትከተኝ፣ አንዱን ስፈታው ሌላ ይመጣል፤ አንዱን ስጨርስ
ሌላ ይተካል› አለችው፡፡
‹ያኔ የለመንሽኝን ልመና ታስታውሽዋለሽ‹ አላት
‹አዎ፣ ሀብት ስጠኝ ብዬ ለምኜሃለሁ› አለችው፡፡
‹ታድያ ሀብት እንጂ ጥበብ መቼ ለምነሽኛል፡፡ እንቺኮ የለመንሽውን አላጣሽም፤ የለመንሽውን የምታስተዳድሪበት እንጂ›
አላት፡፡
‹አየሽ ገንዘብ ማግኘትና ባዕለ ጸጋ መሆን ይለያያል፡፡ ገንዘብ ለማግኘት ሥራ እና ዕድል ብቻ ይበቃሉ፡፡ ገንዘብን ለማስተዳደር
ግን ዕውቀትና ችሎታ ያስፈልጋል፡፡ ገንዘብ ያገኙ ሁሉ ባዕለ ጸጋዎች አይሆኑም፡፡ ባዕለጸጋዎች ገንዘባቸውን ማግኘት ብቻ ሳይሆን
ማስተዳደርም የሚያውቁ ናቸው፡፡ መልክ ያላቸው ብዙዎች ናቸው፣ መልካቸውን ማስተዳደር የሚችሉ ግን ጥቂቶች፤ ሥልጣን ያላቸው ብዙዎች
ናቸው፣ ሥልጣናቸውን ማስተዳደር የሚችሉ ግን ጥቂቶች፤ ዝና ያላቸው ብዙዎች ናቸው፣ ዝናቸውን ማስተዳደር የሚችሉ ግን ጥቂቶች፤ ቤት
ያላቸው ብዙዎች ናቸው፣ ቤታቸውን ማስተዳደር የሚችሉ ግን ትቂቶች፤ ትዳር ያላቸው ብዙዎች ናቸው፣ ትዳራቸውን ማስተዳደር የሚችሉ
ግን ጥቂቶች፤ ዕውቀት ያላቸው ብዙዎች ናቸው፣ ዕውቀታቸውን ማስተዳደር የሚችሉ ግን ጥቂቶች፡፡ ያገኙትን ነገር ለመጠቀምና ለማስተዳደር
የሚያስችል ዐቅም ከሌለ፣ አንድን ነገር ማግኘት ብቻ ታላቅ ነገር አይደለም፡፡› አላት፡፡
እኛም ይህንን ሰምተን ‹ይህች ጥፊ ለአርሳኒ ናት› አልን፡፡
©
ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ በመሆኑ በተመሳሳይ ሚዲያ መጠቀም አይፈቀድም
ሳያርሱ ዝናብ መመኘት ጎርፍ አምጣ ማለት ነው›
ReplyDeleteያገኙትን ነገር ለመጠቀምና ለማስተዳደር የሚያስችል ዐቅም ከሌለ፣ አንድን ነገር ማግኘት ብቻ ታላቅ ነገር አይደለም፡፡›
Dn. Daniel Tsegawene yabezalehe melkam eyeta new.
ReplyDeleteDn. Daniel, Egziabehaire Yibarkeh.
ReplyDeleteAstermari tsehufe new.
Hiwot
‹ታድያ ሀብት እንጂ ጥበብ መቼ ለምነሽኛል፡፡ እንቺኮ የለመንሽውን አላጣሽም፤ የለመንሽውን የምታስተዳድሪበት እንጂ›
ReplyDeletenice view.keep it up Dani...from Kibrom k
ReplyDeleteDani iwinet bilehal yewistien iko new yenegerikegn. Tifiwam leinie lerasie mehonuwan bedenib new yawekut, indih betifi yemimeta sigegnima tifiw yidegemilign kemalet wichi lila min ilalehugn.
ReplyDeleteIyanidndwa yanesahat neger yeiyanidandachinin guda yemitineka nat tikmiwam ijig betam tiliq.
Yebeletewin tsega Irsu Andie yadilih.
kebede
በጣም የሚያስደስትና ብዙ ጊዜ የማናስተውለውን ነገር ነው የፃፍከው እራሳችን ኗሮን ያልተጠቀምንበትን ሳይሆን ሌሎች ይዘውት ሳይጠቀሙበት የቀሩት ነገር ላይ አስተያየት እንሰጣለን እንዲህ ቢሆን ኖሮ እንዲህ አድርጎ ቢጠቀምበት ኖሮ እንዲህ አድርጎ ቢለውጠው ኖሮ ግን ከዚህ ፅሁፍ የምንረዳው የትኛ ነገር ለኛ ተሰጥቶናል በአግባቡስ እየተጠቀምንበት ነው ወይ የሚለውን እኔ በበኩሌ ይሄን ስጠኝ ፣ይሄን ጨምርልኝ ወዘተ ብዬ አምላኬን መለመን እንጂ የማስተዳድርበት ፀጋ ስጠኝ ብዬው አላውቅም ነበር ግን እስከ ዛሬ አዋቂው ጌታ ሁሉ እሱ አስተካክሎ ነው የሰጠኝ ለሁላችንም ስጦታውን ከማስታወል ጋር ይስጠን አሜን
ReplyDeleteለአንተም አስተዋይ አእምሮህን ይበልጥ ያስፋልህ አሜን
wtbhm
ግሩም ነው፡፡ የኔ ሀሳብ ግን ዝግጁነትን እንዴት ማምጣት ይቻላል?
ReplyDeleteጥያቄ ነው፡፡
Dani betam yamerale erasen enday argehegenale
ReplyDeleteበእውነት ደስ የሚል ፅሁፍ ነው፡፡ ሠዎች ሁልጊዜ የምንመኘውና ያለንበት ሁኔታ ግን ፍፁም አልተገናኝቶም ነው፡፡ በዚህ ረገድ መልክቱ ተገቢና አነቃቂ ነው፡፡ይበል ያሠኛል!!!!!!
ReplyDeleteEgziabher yistlen Dn. Daniel.እኛም ይህንን ሰምተን ‹ይህች ጥፊ ለአርሳኒ ናት› አልን፡፡
ReplyDeletethank you
ReplyDeleteE/R yitebikih
እኛም ይህንን ሰምተን ‹ይህች ጥፊ ለአርሳኒ ናት› አልን
ReplyDeleteDn. Dani ejeg betam enamesegnalen. Arekeh tayalehena hulem astemareh neh! Long live!!
ReplyDeleteIt is very..very interesting!!!!
ReplyDeleteDn. Daniel, it is very interesting view and everybody problems. Keep it up.
ReplyDeleteዳኒ በጣም አስተማሪ ጽሑፍ ነው እራሴን ያየሁበት እግዚአብሔር ይስጥልን ፡፡
ReplyDeleteዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን ፡፡
ReplyDeleteደስ የሚል ጽሁፍ ነው፡፡ አዎ መለመን ያለብንን ማወቅ አለብን፡፡ ብዙ አስተምሮኛል፡፡ ከእግዚያብሄር ለእኔ የተላከልኝ መልእክት ነው የመሰለኝ፡፡ ተባረክ፡፡
ReplyDeleteDANI Betam Tru Eyta New Enem Tegarchewalehu,Egziabhear Yibarkih.
ReplyDeleteዲ/ዳንኤል በጣም ግሩም እይታ ነው አብዛኞቻችን ከስንት አንድ ጊዜ የሚያጋጥመንን ዕድል በአግባቡ ሳንጠቀምበት በዋዛ ፈዛዛ ያልፋል ትልቁ ነገር የምናገኘውን ዕድል ለመጠቀም ዕውቀትን እና ክዕሎትን ማዳበር እንደሚገባን ማነቀቃቂያ ደውል ስለደወልክልን በጣም ምስጋና ይገባሃል፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይባርክልን።ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና መጻፍን ማግኘት አልቻልኩም።እንዳታሳትመው ተከልክለሃል የሚባል አልቧልታ አለ።እረ ይታተምልን እንቢ ካልህ ያለው ፎቶ ኮፒ አርገን እንጠቀም?
ReplyDeleteegzyaber amelake kalote yasemalen dani
ReplyDeleteShot for the moon .Even if you miss .you will land among the stars.
ReplyDeleteThis essay transmit one important thing . to Get what you need you have to try and re-try to reach to your goal .No achievement is gained with out painful effort.
Anyways , one can get wealth but one may lack good financial management knowledge..S/he gets the money and spends as if there is no tomorrow. .....Ye negen Egziabher yawekal ......we have also an other proverb << Eat to day , you do not know what tomorrow holds>> all these proverbs do not help to manage your wealth but urges you to spend more . .Wealth did not come overnight.(unless theft is made) . It is advisable to keep some for rainy days .(EKM)
አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲቆን ዳኔኤል። እሚገርምክ ልክ የልቤን ነው የጻፍክልን። ተቃዋሚ ተብየዎች መንግስታችንን ገርስሰው ለመጣል ሌት ተቀን ያሴራሉ። መንግስታችን ቢወድቅ ለኢትዮጵያ ምን አይነት ራዕይ እንዳላቸው አያውቁትም። እንዴው ዝም ብለው ብቻ ትልቁን አሳ ለመያዝ ልሃጫቸውን ያዝረከርካሉ። ልሃጫም እሚለው ቃል በትክክል የሚሰራው ለነዚህ የቀን ጅቦች ነው እንጅ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንማ ራዕያቸውን በተግባር ያሳዩ፣ ሳይማሩ የተማሩ፣ ስልጣን ሳይይዙ ስልጣንን ያወቁ፣ ትልቁን አሳ መያዝ እሚችሉ ነበሩ። ጓጉንቸር በሬ አክላለው ብላ ፈነዳች ያላል። ታዲያ እነዚህ የቀን ጅቦች እንደ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንሆናለን እያሉ በየቦታው እየፈነዱ ይገኛሉ። ሌላ ምን ይባላል? ተባረክ ብሩክ ሁን ዳንኢል ክበረት። ትክክለኛ ወቅታዊ መልክት ነው ያስተላለፍክ። እግዚያብሔር ይባርክህ እንጅ ሌላ ምን ይባላል።
ReplyDeleteአዜብ (ከአሜሪካ)
ጓጉንቸርስ ባለበት አለ
Deleteazeb, azeb???????????
DeleteEnes Be Temsito Anbebkut Betam Astemari Tshuf Tibebun Mastewalun AMILAKACHIN Yadilen MEDEHANIALEM Tsegawin Yabizalih Dn.Danii
ReplyDeletebetikikel yerasene hiwot endaye adergrhrgnal egzabehern lemenkut setegn gin yesetegne mastedader aketogn hehew Getand eyamarerku enoralhu.
ReplyDeleted.daniel it is very interesting view!!
ReplyDeletegood view thank you.
ReplyDeleteግሩም እይታ ነው።
ReplyDeleteበዚህ አጋጣሚ እንኳን ለ፫ኛ ዓመት የጡመራ መድረክ ምስረታ በዓል አደረሰህ/ሰን።
wow i realy get a good message
Deleteዳኔ ሁሌም እደሜና ጤናህን ከሜለምኑት ውስጥ ነኝ። በርታ።
ReplyDeleteEwnet bilehal Dani Betam des yemil mikir
ReplyDeleteDani Betam des yemil Mikir new Amlak yibarikih
ReplyDeleteEwnet new betam des yemil mikir new
ReplyDeletebetam des yemil eyita new Amlak yibarikih
ReplyDeleteEnameseginalen Amlak yibarikih
ReplyDeleteበጣም አስተማሪ ጽሁፍ ነው እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡!!
ReplyDeleteዳኒ ተባረክ፣, ሎተሪም እንደዛው ነው!!
ReplyDeleteበጣም አስተማሪ ጽሁፍ ነው እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡!!
Deleteበእዉነት በሁለት በኩል የተሳልክ ሰዉ ነህ እግዚአብሔር ይባርክህ!!!!
ReplyDeleteTo Get what you need you have to try and re-try to reach to your goal .No achievement is gained with out painful effort.
DeleteI have seen my self.
ReplyDeletenice Dani keep it up I like ur View
ReplyDeletetibeb new mistru. Abatachin hoy tibebin sitegn woym siten. Temsgen, astwulo endnastwul yemiaderg memhir silsetehn.
ReplyDeletethankyou!!!
ReplyDeletewhat a nice idea. you are good man
ReplyDeletewow deni betam tiru iyeta nawu e/r yaberka!!!
ReplyDelete