የዳንኤል ዕይታዎች ‹የዓመቱ በጎ ሰው› የምርጫ ኮሚቴ ሰባት አባላት ነበሩት፡፡
እነዚህ አባላት ከተለያዩ ሞያዎችና አካባቢዎች የመጡ ሲሆን በ‹የዳንኤል ዕይታዎች› አማካኝነት ለአንድ ወር ያህል አንባብያን
‹በጎ ሰው› የሚሉትን እንዲጠቁሙ ዕድል ተሰጥቶ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት በ159 ጠቋሚዎች 70 ግለሰቦችና ሰባት ተቋማት ተጠቁመዋል፡፡
እነዚህን 70 ኢትዮጵያውያንና ሰባት ተቋማትን አመዛዝነው አሥር ምርጦችን እንዲሰይሙ
በተለያዩ ክልሎችና ሞያዎች ለሚገኙ እርስ በርሳቸውም ለማይተዋወቁ 9 ሰዎች ተሰጠ፡፡ በዚህም መሠረት ከጠቋሚዎችና ከመራጮች የተሻሉ
ድምፆችን ያገኙ አሥራ ሰባት ሰዎች ተመረጡ፡፡
እነርሱም
- እንዳለ ጌታ ከበደ
- መዓዛ ብሩ
- ብንያም በለጠ
- ቴዎድሮስ ጸጋዬ
- ዶ/ር ቴዎድሮስ መሰለ
- ንቡረ ዕድ ገብረ ሕይወት መልሴ
- ዶ/ር በላይ አበጋዝ
- ሸገር ሬዲዮ
- ደ/ር አበበ ከበደ
- ዶ/ር በላቸው ጨከነ
- ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ
- ወ/ሮ አበበች ጎበና
- ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ
- ማኅበረ ቅዱሳን
- ፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት
- ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን
- ወ/ሮ ሙሉ ሰሎሞን
ተመርጠዋል፡፡ የመጨረሻውን ድምጽ የሰጠው የምርጫ ኮሚቴው ሲሆን ከመራጮቹ መካከል 3/4ኛና
ከዚያ በላይ ድምጽ ያገኙትን በመውሰድ አምስት ሰዎችን ‹የዓመቱ በጎ ሰው› የሚል ሽልማት እንዲቀበሉ ወስኗል፡፡ እነዚህም
ንቡረ ዕድ ገብረ ሕይወት መልሴ
የርእሰ አድባራት አዲስ ዓለም ማርያም አስተዳዳሪ ናቸው፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ
በትምህርት ያላደረሱት መስክ የለም፤ በሲመትም የታላቋ ደብር አለቃ ሆነዋል፡፡ ይህ እልቅናቸው እንደሌሎቹ ቤት ልሥራ፤ ዘር
ልዝራ አላሰኛቸውም፡፡ ነገር ግን ሀገራዊ ጉዳይ ያሳስባቸው ነበር፡፡ እርሳቸው አረጋዊ ናቸው፤ በእርጅና ጎንበስ ብለው ድካምን
የሚጋፉት፤ እርሳቸው በዕድሜ ጣርያ ላይ ያሉ ናቸው፤ ዐርፈው መቀመጥ የሚያስፈልጋቸው፤ ግን እንዲህ አላደረጉም፡፡ በዚህ
የእርጅና ዕድሜያቸው በመላው ዓለም እየዞሩ፣ እየለመኑና እያባበሉ ኢትዮጵያዊ ዕውቀት የሚገኝባቸው፣ ነገር ግን እንደ ዋልያና
ቀይ ቀበሮ በመጥፋት ላይ ያሉት የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዲጠበቁ፣ ተሻሽለውም እንዲቀጥሉ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ
ለማሰባሰብ ተግተዋል፤ ድካም ሳያግዳቸው የሰው ፊት እያዩ ለአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሆን ገንዘብና ቁሳቁስ ሰብስበዋል፡፡
ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመሆን በወጠኑት በዚህ አገልግሎት ዛሬ ከመጥፋት ድነው፣
ከመድከም በርትተው ታሪካዊውን፣ ሃይማኖታዊውንና ሀገራዊውን ዕውቀት የሚያካሂዱ አያሌ የአብነት ትምህርት ቤቶችን አፍርተዋል፡፡
ያሉትን ከመጠበቅም በላይ አዳዲሶች በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ እንዲከፈቱ አድርገዋል፡፡ አረጋዊው ንቡረ ዕድ ገብረ ሕይወት መልሴ!
መዓዛ ብሩ
በመረዋ ድምጽ፣ ልብን ሰርሥሮ በሚገባ፣ ቤተኛ በሚያደርግ የቃለ መጠይቅ ጥበብ እንደ
መልካም ወገኛ በማጫወት የተካነች ናት፡፡ ለጋዜጠኝነት ሞያ ባላት ፍቅር ኢትዮጵያዊ መልክ ያላቸውን፣ ታሪክና ባህልን
የሚያስታውሱንን ታላላቅ ሰዎቻችንን እንድናውቅ የሚያደርጉንን ፕሮግራሞች የሚያቅፍ የሬዲዮ ጣቢያ በመመሥረትና በመምራት፣
ታላላቅ ሰዎቻችንን ሞት ሳይቀድመን በፊት ቅርስ ሆነው እንዲቀሩ፣ የማይታወቁ ጀግኖቻችን ለአደባባይ በቅተው እንዲታወቁ
በማድረግ፤ አንድ የተለየ ጣዕምና ሚና፣ አንድ የሚደመጥና የሚናፈቅ፣ አንድ ልዩ ቀለምና ጠባይ ያለው የሬዲዮ መሥመር ሸገር
ሬዲዮን በመዘርጋት የተዋጣለት ተግባር እያከናወነች ትገኛለች፡፡
ዕወቁኝ ዕወቁኝ አትልም፣ ስለ ራሷም ማውራት አትወድም፣
ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ እንዲል ግን ሥራዋ ማንነቷን ገልጦላታል፡፡ ዛሬ የሰላምታ ያህል ከብዙዎች የሚደመጠውን ‹ኢትዮጵያ
ለዘላለም ትኑር› የሚለውን ጣፋጭ ሐረግ ገና የሬዲዮ ጣቢያ ሳይኖራትና የቅዳሜ ጨዋታን በኤፍ ኤም 97.1 ላይ ከሌሎች አጋሮቿ
ጋር ስታዘጋጅ ጀምራ መርሕ አድርጋ ይዛዋለች፡፡መዓዛ ብሩ!
አቶ ብንያም በለጠ
የ35 ዓመት ወጣት ነው፡፡ አያቱ በጎንደር ከተማ የታወቁ ነበሩ፡፡ ችግረኞችን
በመርዳትና ሰው ለሌላቸው ሰዎች መጠጊያ በመሆን ነበር
የሚታወቁት፡፡ እንዲያውም የተቸገረ ሰው ላመጣላቸው ሰው ወሮታውን በእህል ይከፍሉ እንደነበረ የከተማው ሰዎች ዛሬም
ያስታውሷቸዋል፡፡ አባቱም በዚያው መንገድ ተጓዙና ሰው መርዳት ሆነ ነገር ዓለማቸው፡፡ በወቅቱ የሼል ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ
የሆኑት አባቱ አቶ በለጠ ደመወዛቸው 4000 ብር ነበር፡፡ በቤት ውስጥ ግን ልጆቻቸው ሽሮ እንኳን አጥተው ጦም የሚያድሩበት
ጊዜ ነበር፡፡ ጠጥተውበት አይደለም፣ ቁማር ተጫዉተዉ ተበልተውም አልነበረም፡፡ ለችግረኞች የሚራሩ በመሆናቸው ለድኾች አከፋፍለው
ስለሚጨርሱት እንጂ፡፡
መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ ያፈራል ነውና፤ ይህንኑ በጎ ነገር ልጃቸውም ወረሰው፡፡
ለታክሲ የተሰጠውን ገንዘብ በእግሩና በአውቶቡስ እየተጓዘ በመቆጠብ ችግረኛ ተማሪዎችን ይረዳበት ነበር፡፡ እንዲህ እየኖረና
እየተማረ አድጎ አሥራ ሁለተኛ ክፍል አራት ነጥብ አመጣ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ገብቶ ሕግ ተማረ፡፡ ከዚያም ተመርቆ ጥቂት
ጊዜ ሠራና አሜሪካ ገባ፡፡ እዚያም ከቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ የማስትሬት ዲግሪውን ሠራ፡፡
እዚያ አረጋውያንን በሚንከባከብ ድርጅት ውስጥ ሲሠራ የሀገሩን አረጋውያን ነበር በልቡ
የሚያስበው፡፡ እንዲያም ብሎ እዚያ እየሠራ ገንዘብ በመላክ እዚህ የሠፈሩን ድኾች ይረዳ ነበር፡፡ እንዲህ እንዳደገው ዓለም
የሚንከባከባቸውና ርግማናቸውን ሳይሆን ምርቃታቸውን የሚያተርፍ ተቋም በሀገሬ መቼ ነው የሚኖረው? እያለም ያስብ ነበር፡፡ እዚያ
ማዶ ሆኖ የሚልከው ገንዘብ እዚህ በሚገባው ቦታ እየዋለና የሚፈለገውን ውጤት እያመጣ አለመሆኑን አየና ነገር ዓለሙን ሁሉ ጥሎ
ሀገሩ ገባ፡፡
በቤተሰቦቹ ቤት ይህንን ክብር ያለው ግን ቆራጥነትና ትዕግሥት፣ ትጋትና ቻይነት
የሚጠይቅ አገልግሎት ሲጀምረው፤ ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹና ወዳጆቹ ሁሉ ‹አበድክ › ብለውታል፡፡ እርሱ ግን አለማበዱን በተግባር
ለማሳየት ተጋ፡፡ ቀስ በቀስም ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ተባባሪ አደረጋቸውና ‹መቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ድርጅትን› መሠረተ፡፡ ዛሬ
በዚህ ድርጅት 170 አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን ይረዳሉ፡፡ እርሱም መኖርያው ከአረጋውያኑ ጋር ነው፡፡ የበሉትን ይበላል፤
የጠጡትን ይጠጣል፡፡ አቶ ብንያም በለጠ!
ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን
የአፍሪካ የምግብ ችግር ከምርት
ብቻ ሳይሆን ከምርቱ ገበያ ጋር የተያያዘ ነው የሚል እምነት አላቸው፡፡ በዚህም የተነሣ ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገሮች
ላይ ሠርተዋል፤ ተመራምረዋል፡፡ በዓለም ባንክ፣ ዋሽንግተን በሚገኘው ዓለም ዐቀፍ የምግብ ፖሊሲ ጥናት ማዕከል፣ እና በተባበሩት
መንግሥታትም በከፍተኛ ኃላፊነት ሠርተዋል፡፡ በኢኮኖሚክስ ዲግሪያቸውን ከኮርኔል ዩኒቨርሲቲ፣ ማስትሬታቸውን ከሚችጋን ዩኒቨርሲቲ
አግኝተዋል፤ በአፕላይድ ኢኮኖሚክስ ደግሞ ፒ ኤች ዲያቸውን ከስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ወስደዋል፡፡
አቶ ሰሎሞን የዶ/ር እሌኒን ሽልማት ሲቀበሉ
|
ለምግብ እህል እጥረት አንዱ
ችግር የገበያው ሁኔታ ነው የሚከለውን የጥናት ውጤታቸውን እውን ይዘው ከነ መፍትሔው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2004 ወደ
ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ሃሳባቸውን ወደ ተቋም በመለወጥም በኢትዮጵያ የምርት ገበያ እንዲመሠረት ዋነኛዋ ሐሳብ አፍላቂና አንቀሳቃሽ
ኃይል ሆነው ሠሩ፡፡ በዚህም ምርምርንና ጥናትን በጥራዞች ላይ ከማዋል ባሻገር ለሀገር ችግር መፍትሔ አድርጎ መጠቀም እንደሚገባ
አሳዩ፡፡ ዛሬም ናይሮቢ ላይ ከመሠረቱት ቢሮ እየተነሡ በአፍሪካ ይህንኑ ሐሳባቸውን ለማካፈልና አፍሪካን ከምግብ እጥረት
ለማላቀቅ በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን!
እንዳለ ጌታ ከበደ
ደራሲ ነው፡፡ ሰባት ያህል መጻሕፍትን አቅርቦልናል፡፡ የተወለደው ወልቂጤ ሲሆን
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሚከታተልበት ጊዜ ‹ተስፋ› ብሎ በሰየማት አነስተኛ የመጻሕፍት መደብሩ ለከተማዋ ነዋሪዎች እጅግ
አነስተኛ በሆነ ዋጋ እያከራየ የንባብ ባሕል እንዲዳብር ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ እንደ ተከራዮቹ ሞያና የትምህርት ደረጃ ስለ
መጻሕፍቱ አጭር ማብራርያ እየሰጠ፤አንብበው ሲመልሱም ስለ
መጻሕፍቱ አስተያየት እየተቀበለ ያበረታታ ነበር፡፡
በወልቂጤ ከተማ ውጤታማነትን ለማበረታታት በራሱ ተነሣሽነት በትምህርታቸው ከፍተኛ
ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማቶችን ይሸልማል፡፡
የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ዋና ጸሐፊ ሲሆን በዚህ የሥራ ድርሻው አዳዲስ ሐሳቦችን
በማመንጨትና በመተግበር ደራስያን እንዲጠቀሙ ድርሰትም እንድታብብ እያደረገ ነው፡፡ በገንዘብ እጥረት ምክንያት የአእምሮ
ሥራቸውን ማሳተም ላልቻሉ ደራስያን በተዘዋዋሪ ገንዘብ ድርሰቶቻቸውን የማሳተሙን ሐሳብ አቅርቦ ከሌሎች ጋር ሆኖ እንዲተገበር
አድርጓል፡፡
ከኢትዮጵያ ጡረተኞች/አዛውንቶች ጋር በመተባበር መድረኮችን አዘጋጅቶ ወጣቶችና
አረጋውያን ተገናኝተው ልምድ እንዲለዋወጡ አድርጓል፤
በወር አንድ ጊዜ በብሔራዊ ቴአትር የሕጻናት ዝግጅት በሕጻናት እንቀዲርብ በማድረግ ፣
የንባብ ባህል በሕጻናት ላይ እንዲዳብር የሚችለውን ሁሉ አድርጓል፡፡ እንዳለ
ጌታ ከበደ!
ተስፋ ያዘለ ሃሳብ
ይህ ‹የበጎ ሰው ሽልማት› ራሱን በቻለ ሁኔታ ተቋቁሞ ወደፊትም በየዓመቱ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ሌሎች ጀግኖችን ለመፍጠር
ያሉትን ማድነቅና ማክበር ያስፈልጋል፡፡
congratulations daniel!!! among i mentioned, MEAZA BIRRU, selected. great and im so happy to know abot Biniam Belete for the first time, he was a hidden hero..........dani u r doing well, hope3 next year we will have more than 5 awardee.
ReplyDeleteGOD BLESS UR EFFORTS
ሌሎች ጀግኖችን ለመፍጠር ያሉትን ማድነቅና ማክበር ያስፈልጋል፡፡
ReplyDeleteevery thing what u did is nice. keep it up.
Deleteዕወቁኝ ዕወቁኝ አትልም፣ ስለ ራሷም ማውራት አትወድም፣ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ እንዲል ግን ሥራዋ ማንነቷን ገልጦላታል፡፡...........መዓዛ ብሩ!!! ቤተኛ በሚያደርግ የቃለ መጠይቅ ጥበብ እንደ መልካም ወገኛ በማጫወት የተካነች ናት! CONGRATULATIONS!
ReplyDeleteThank you. I like how Me'aza interviewing. She always does her homework, and ask interesting questions which makes interviewees speak more. Congratulations መዓዛ ብሩ!!!
DeleteAlmaz from NY
yes she is so great, wish we have dozens of her. i've also a fantasy to be interviewed by her sometime............i know im crazy.....but she really deserves much more
DeleteIt is a good start, however I wonder how come Prof. Mesfin is not included in the list.
ReplyDeleteውይ ምነው ዳኒ በጎ ሰው ማለት ስኬታማ ሰው ማለት ነበር እንዴ አዪዪዪ...በል ተወው በቃ
ReplyDeletesorry most of the people you read about are low level life and has a long way to go to be as you say successfull....
Deleteስኬታማነት በኑሮ ደረጃ ከሃብታሞች ተርታ መመደብ አይደለም፡፡ ስኬታማነት በኔ አመለካከት ልክ እንደነዚህ ሰዎች አይነት ማለት ነው፡፡ ስለዚህም "የአመቱ ስኬታማ ሰው" ቢባሉ የተሻለ ነበር፡፡ በጎነት የስኬታማነት ቁልፍ ነው፡፡ ያለ በጎነት ስኬታማነት ሊኖር አይችልም፤ ያለ ስኬታማነት ግን በጎነት ሊኖር ይችላል ባይ ነኝ፡፡ ጀግንነትና በጎነት የስኬታማነት ግብአቶች ናቸው፡፡ የኔ መረዳት ከዚህ ያለፈ አይደለም፡፡ ዲ.ዳንኤል በርታ፡፡
DeleteENDEWEM AZWAZWARKEW!! yale begonetema seket molutal!! sew lerasu becha eyasebe yefelegew yenuro tariya mederese yechelal!! yehe seketam yasebelewal!! bego gen ayasebelewem!! sew eko bego emiyasebelew lelelaw teru neger siayeseb ena sisera new!! selezih yetemeretut sewoch bego sewoch nachew!!
DeleteDakon Danel: tebarek enji lela mn yibalal? ejig emiyamir zigjit neber:: lemehonu lelochin sitishelim eraskin endet eresahew? bel eraskin sitishelim emiyasay foto letifilinina saqina destachinin chemirilin::
ReplyDeletebetam des yilal. lehagerina lehizb balewuleta lehonu sewoch kibirna ewqina mestet yasmeseginal. tebarek dn daniel. temerachochim enkuan des alachihu. bertu.
ReplyDeletetehselamiwochu Albezum???
ReplyDeleteበጣም ያንሳሉ
DeleteAn excellent piece of work.
ReplyDeletekeep going
may God be with you
This is a very nice initiative. Those who are doing best to their people and country should be recognized so that we can develop such culture and we can make small contributions which will become large altogether.The situation we have today in the country seems that no one is there to do something good.We are killing each other, destroying our culture,relationship,affection....which contribute towards having no vision. As a result people have forgotten doing good for others. Finally, i have a reservation on Dr. Eleni's award. I know that she has done a great job for the country, but why she left Ethiopia and establish an organization in Kenya? I believe that if the organization was established here it would have created job opportunity for her citizens. Is she an Ethiopian?????
ReplyDelete'ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር'.
Of course she is! Establishing a company abroad doesn't mean she's ignorant of her country. The only reason that her company is founded in Nairobi is that more favorable conditions for its line of work are found there than in Addis.
Deleteበጎ ሰው የበጎ ሰዎችን ሥራ ለማየት አይኑ እንደ ከዋክብት የበራ ነው፡፡ መልካም ጅምር ነው፡፡ ዳኒ ብርትት በልልን፡፡ ለሌሎቹም፣ ዓይኖቻቸው ከብዙ ጥሩ ሥራዎች መካከል ጥቂቱን፣ እጅግ በጣም ጥቂቱን ክፉ ሥራ እያዩ፣ እያጎሉ፣ እያጋነኑ ለሚያስነብቡን የጡመራ መድረኮች ትልቅ ትምህርት መስጠት የሚችል የበጎ ሥራ ጅምር ነውና በርታልን፡፡ እንወድሃለን፡፡
ReplyDeleteእባክህ ዳኒ ይህ ነገር ይቀጥል
ReplyDelete"ሌሎች ጀግኖችን ለመፍጠር ያሉትን ማድነቅና ማክበር ያስፈልጋል፡፡"
ReplyDeleteYemakebrih Wondime Dn. Daniel, Ejig Betam des yemil sira new Yeserahew. Kezih Yebelete enditisera Egziabiher Yirdah.
gerum sera
ReplyDeleteGosh! Tebarek:: Ethiopia wst sew sishelem lemayet beqan:: Mnm enkuwan bemtadergachew negeroch hulu mulu bemulu balsmamam yhnn dnq hasab sletegeberkew Eniem anten beametu tlq sra yesera sew byie shelmiehalehu- behasabie::
ReplyDeleteየተመሰገነ ሥራ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርክ፡፡
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል በአንድ ወቅት ቀርቦ የነበረውን አይከኖቻችንን አንርሳ የሚለውን አስታወሰኝ፡፡ ወ/ሮ አበበች ጎበና ዝርዝር ውስጥ ቢኖሩም አለመመረጣቸው፡፡ ይህ ነገር ወደፊት በይበልጥ ተጠናቅሮ እንደሚቀጥል ተስፋ አለኝ ሌሎችም ቢከተሉት፡፡ በመንግስት ደረጃም እውቅና የሚያገኙበት ሁኔታ ቢመቻች መልካም ይሆናል፡፡
ReplyDeleteበመሠረቱ እኔ በጎ ሰዎችን አልጠቆምኩም ነገር ግን የተመረጡን ሰዎች ሳይ ግን ኮሚቴው የህሌና ስራ በመስራቱ ሳላመሰግን ባልፍ በጎን ፣ጥሩ የሚሰሩን አለማበረታታት ወዲህም ቅናት ወዲህም ክፋት ነውና ለህሌናችሁ ሠርታችሁ ጥሩ መርጣችኋልና ተባረኩ እግዚአብሔር አስተዋይ ህሌና ደግሞ ደጋግሞ ያክልላችሁ አሜን
ReplyDeletewthbm
i know am too late for this but i just want to say
ReplyDeletei personally dont like the guy and his point of view, but what ever i feel doesnt matter and count when it comes to the practical aid he have been doing for the country, the ethiopian community and his friends...
i believe he may not have done anything like many of wealthy people in Addis if he doesnt want to
so even-though i wouldnt say "man of the year", i would at list nominate him.
Shaeh Mohamed Al Amudi
የማይገባው ሰው ነው ሀገራችን ላይ ምን እየሰራ እንደሆነ ብታውቁ ይህን አትናገሩም ነበር የኢትዮጵያ መሬት ለሳውዲ በርካሽ ዋጋ እየገዛ እኛን ረሀብተኛ እያደረገ ነው። የጋምቤላን ግማሽ መሬት በ158 ብር ኪራይ ለ99 ዓመት ለሳውዲ ገዛ የአፋርን እንዲሁ፤ የመንግስትን እርሻዎች በአጠቃላይ እየገዛ ነው ይህን የሚያደርገው ለሀገራችን ዜጎርች መሰላችሁ ለማንኛውም እሱ አይደለም መልካም ሊሰራ ለኢትዮጵያ ይቅርና ከኢትዮጵያ ውጪ በኢትዮጵያዊነት መጠራት አይፈልግም ይሄን ሊንክ ተመልከቱ ፎርብስ ላይ የሳውዲ ዜግነት ተብሎ ነው የተጠራው
Deletehttp://www.forbes.com/billionaires/list/#page:1_sort:0_direction:asc_search:saudi%20arabi_filter:All%20industries_filter:All%20countries_filter:All%20states
ከተዘረዘሩት ሊስቶች ውስጥ 65ኛው ሳውዲ ኢትዮጵያዊ ተብሎ ሊሸለም አይገባውም መቼም
i don know why WE R EASILY DECEIVED by shows and interviews! the man is ready to eat our flesh any time soon just he is waiting for the right time! .....i believe u know what happened to JUNEDIN SADO......so the guy is the pivot........he wants to be seen as hero and non secular, but deep down he is arming ppl to fight and win ETHIOPIA. HOW CAN WE HONOR THE CANNIBAL? rather everyone watch out!!!!!!!!
Deleteበእውነት ኮሚቴው ብታም ትሩ ነገር ነው የሰራው. የህዝብን ድመጽ ተቀብሎ ለሽልማት ትክክለኛ ሰዎችን ስለመረጣችሁ ኮሚቴዎችን እጅግ አድርጌ ላመሰግነ እወዳልው፡፡ ተሸለመጭም በዚህ ተግባራቸው ሊቀጥሉ ይገባል፡፡
ReplyDeleteኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
እግዚአብሔር ይባርክህ መልካም የሰራን ማመስገን መልመድ ጥሩ ነው ይህ ሽልማት መታሰቢያነቱ ለሌሎችም በየቦታው መልካም ለሚሰሩ ይሁንልን እኛም የቻልነውን በጎ ስራ እንድንሰራ እግዜር ይርዳን
ReplyDeletedani thank you very much i am happy about this all....i loved them all. fro
ReplyDeleteSelam Daniel
ReplyDeleteCould you please brief the other accomplishment too? I think it worth to do that.
Do. Daniel you are such an amazing person! I think you are one among the very few assets of Ethiopia! May GOD blesses yo
ReplyDeleteu for the wonder full job you did!! It is worth appreciating and motivating the good work of others.
Congratulations Dr. Belachew!!! I am really happy for you and I believe you deserve the precious award you got. May the Almighty GOD blossom your kind heart more and more and you will be continuing your good work and will be an exemplar to your spiritual brothers and sisters.
መልካም ጅማሬ ነው::መቼም አበሻ ሲባል ማመስገን ይቸገራል::ለነገሩ ተመስግኖ ያላደገ ከየት አምጥቶ ያመሰግናል::የሚቀጥለው ትውልዳችን ተስፋ አለው እግዚአብሔር ይረዳናል::መልካም ጅማሬ ነው::መቼም አንተ ጉደኛ ነህ::ግን ሽልማቱን በአንተ ስም ባታደርገው ምን ይመስልሃል?ለወደፊቱ ማለቴ ነው!!
ReplyDeleteኒቆዲሞስ
Dani, Betam Telek Sera New Bego Yemiseruten Sewoch Betlyaye zerfe Mabertatate yeketel.
ReplyDeleteAntem Yehen Bemasebeh Egziabher yerdah.
እግዚአብሔር ይጠብቅህ ያበርታህ!!! እመአምላክ በምልጃዋ አትለይክ ፡፡እግዚአብሔር ይጠብቅህ ያበርታህ!!! እመአምላክ በምልጃዋ አትለይክ ፡፡
ReplyDeleteየዳንኤል ዕይታዎች!
ReplyDelete(ዳ)ግም ሳስበው ዕይታህን
(ን)ብ እንደሰራው
(ኤ)ክሰለንት ነው
(ል)ንገርህማ
(ክ)ብር ይገባል
(ብ)ትበረታ
(ረ)ዥም ዕድሜ
(ት)ዕግስትህ ትብዛ!
እናት አባትህ ይኩሩ
ሚስት ልጆችህ ይደሰቱ
ዕውቀትህ ትብዛ
ሕሊናህ ይመስገን
ጣትህ ትባረክ
አምላክ ይርዳህ
የኢትዮጵያ ማሕፀን የወለደችህ የልብ አድርስ ሰው ነህ!
I don't have any piece of information about other awardees except Dr. Eleni G. Medhin. I am happy to see all the awardees are duly selected and recognized Hero of the Community.
ReplyDeleteBut I am very much elated when I saw that current single Legacy had no more place here.
what a great job Dani, I can't thank you enough.
ReplyDeleteKeep it up and God be with you
What an outrageous start up! Keep up the good job Dn. Daniel. I would love to know more about Beniam Belete...can any one drop his email to me pls...?
ReplyDeleteHi Diakon Daniel, I am glad to hear such nomination and selection of people ("not artists" as we are more accustomed to that). But there seems to be some confusion about success in life or profession and to be kind person. If you entitle it "Person of The Year" that would make more sense. Otherwise, you better focus on people who are doing humanitarian tasks and pledged their life for the good of others.
ReplyDeleteDear anonymous yezih tumera(tsihuf) mirt asteyayet byewalehu!
DeleteMeles zenawi was good man of z century not the year.zat is all I can say history will tell.but I like to say we should all be concerned about our place in history if we r made to be history makers.
ReplyDeleteDear anonymous lehulum bota ena gize alew.
Deleteበሌላ በኩል ደግሞ በዚያው ልክ፣ እንዲያውም ባመዛኙ ማህበረሰባችን በጎ ለሰራ፣ ለልማትና የሀገር ድንበር ለጠበቀ ለጦር ጀግና፣ለወግና ትውፊት አክባሪ ብሎም ጠባቂ የሚያሞግስበትና የሚሸልምበት የራሱ ሥርዓት ያለው ነው። ሙያ በልብ ነው በሎ ቢናገርም ሕብረተሰባችን ደብቀን የሰራነውን መልክም ነገር ሁሉ በይፋ አውጠቶ የሚያወድስበት ዘዴው ድንቅ መሆኑ ታሪክ ይመሰክራል። ዛሬ ግን ወያኔን ያልደገፈ ወይም ለፕሮፓጋንዳ ይጠቅማል ያልተባለ ሰው ሸላሚም፣ አሸላሚ ወይም ተሸላሚ ሆኖ ሲቀርብ አላየነም። ለወያኔ ፕሮፓጋንዳ ግብዓት ከጠቀመ ጤፍ ነግዶ የከበረ ነጋዴ አርሶ ጤፍ ያመረተ ልማታዊ ገበሬ ተብሎ ሲሸለም አይተናል።
ReplyDeleteis Rv. solomon mulugeta pro Tehadeso is Good man? what about alula?
ReplyDeleteከዚህ በላይ ያለውን አስተያየት ለጻፉት ግለሰብ:: ይህ ገጽ የመልካም ተግባራት መማሪያ እና መማማሪያ እንጂ የሰዎችን ግላዊ ነገር እያወጣን የምንሰዳደብበት አይደለም:: ፍላጎትዎን የሚያስተናግዱ ብዙ ገጾች ስላሉ ወደነዚያ ጎራ ቢሉ:: የሚሻል አይመስልዎም?
DeleteWell done!! keep it up the good work.
ReplyDeleteD..Daneil Egizaebher yebarkeh...sewoch bizu ylalu...mesrat sayehone metecht becha...sew yechalwen besera agerachen yet bedrsche....ante BERTA ...yeanten tsehufoch bezu anbebealhu temhert settwegnal Egezabher kante gar yehun....
Deletethank you
Deleteminaw nikodimis minekah!!, do you want the prize in the name of you????????
ReplyDeleteyaltenebebutn endnanebachew siladeregh enamesegnalen.
ReplyDeleteWell done Diakon Daneal.
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይባርክህ ዲ/ን ዳንኤል! መልካም የሰራን ማመስገን መልመድ ጥሩ ነው !'ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር'.
ReplyDeleteWas it only from Christian domain ? Good work but u need to reach across the isle, there are good shek as well as priests.
ReplyDeleteEchuwochin yetekomut anbabian neberu bewoktu ante bego yeseru sheki(muslim) marmeret tichil neber lewodefitm tichilaleh. Keante yemitebekewn satwota lehis atrut .
DeleteDn. Daniel, manbeb endjemir sileredahegn betam ameseginalehu...GBU!
ReplyDeleteThere is no 'bego sew' like me mekishefe ende ethiopia tarik'. The word is not clear please change it next year. Bego what??????????
ReplyDeleteሁላችሁም ተመራጦች እንኳን ደስ ያላችሁ ፡፡ በበጎ ስራችሁ ጸንታችሁ ከስኬታማነታችሁ አልፋችሁ ተነሳሽነት በልባችን እንድታብብ ስላደረጋችሁ እግዚአብሄር የበለጠ ይባርክልን፡፡ ዲያቆን እነዚህን ሰዎች ስላስተዋወከን እናመሰግናለን፡ የሩቅ ዘመዶቻችን እንደሚሉት what an amezing job
ReplyDeleteእርሱም መኖርያው ከአረጋውያኑ ጋር ነው፡፡ የበሉትን ይበላል፤ የጠጡትን ይጠጣል፡፡congera bini
ReplyDeleteAre you sure this lady is working to improve the lives of the people of Ethiopia?
ReplyDeleteዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን??????????????????????
Gebre
Ke Etissa T/Haymanot
dink new ....specially meaza beru
ReplyDeleteit is really an amazing idea that everybody should practice, therefore this kind of habit should adopt in our Ethiopia .... it is a good start but how much the voting process was fair? are they only these people? so try to widen up the scope of election ..... by the way when shall we award you Dani???
ReplyDeleteመልካም ጅማሬ ነው እናመሰግናለን ... ጥቆማ ላይ ግን ጥንቃቄ ያስፈልጋል ... እንደኔ እንደኔ በጎ ሰውነት እና ስኬታማ ሰውነት መለኪያቸው ለየቅል ነው። ከተሸላሚዎቹ መካከል አንዳንዶቹ በጎ ሰው ከመባል ይልቅ ስኬታማ ሰው የመባል እድላቸው ሰፊ ነው። ተባረክ ወንድም ዳንኤል!!
ReplyDeletedani yedenegel lege yebareke
ReplyDeletekeep it up but you should have been one of them.
ReplyDeleteI appreciate your effort but Sibhat Nega should have been at the top of the list. He is the best Ethiopian ever.
ReplyDeleteR u kidding me? what a joke!
Deleteberta..sirahin sira!
ReplyDeleteHow about Engineer Simegn?
ReplyDeleteዳኔል በጣም በጣም ደስ የሚል ተግባር ነው የማይታወቁ ጀግኖችን እንድናውቅ ስላደረግከን::በተለይ የመአዛ መመረጥ በጣም አስተዋይ ድምፅ ሰጭ ኮሚቴ መሁኑን ያመላክታል
ReplyDeleteለአንተስ ምን አይነት ሽልማት ነው የሚበረከትልህ ማንስ ነው የሚሸልምህ በጥበብ ላይ ጥበብ በዕውቀት ላይ ዕውቀት ይስጥህ
ReplyDeleteits good , daniel kibret u are doing now amazing and wonderful things God bless u . don't stop ... u are build a big bridge for the new generation how to respect for the people they do uncountable and to remember ,to give a true reward for what the do....
ReplyDeletealexrastaw
ዳኒ ስለእውነት አንተን የጠቆመ ጠፍቶ ነው;;;; አንተ ባለመኖርህ ውስጥ ያንተ ጣልቃ ገብነት ካለ ግን ምርጫው በኮሚቴ ሳይሆን ባንተ ተከናውኖዋል የሚል እሳቤ ውስጥ ይዘፍቀኛል፡፡!! ለኢትዮጵያና ብሄራዊ ሃይማኖቱዋ ባለህ አቅም ትውልድን ማዘጋጀት ይህ በጎነት አይደለም እንዴ ???ጌታ ያለቻትን አምስት ሳንቲም ለሰጠችው ሴት ትዳሩዋን ሠጠች ብሎ ማመስገኑ እኮ ለእንዳንተ አይነቱ ምሳሌ ነው! ያለህን አካፍለሃል; በቻልከው ጩኸት ልክ እስክትሰማበት ድረስ መክረኸናል! በምትዘረጋቸው ጉባዔ የተከመረውና የተመከረው ህዝብ እስኪ ይቆጠር! መልካሙዋ መአዛ ብሩ በሬዲዮ አንተም በመድረክህ ታላላቆችን ማሰብ ብቻ ሳይሆን ሸለምካቸው፤ዋጋቸውን አሳወቅህላቸው እኮ….እንዴት ነው ነገሩ???
ReplyDeleteዳኒ ካሁን ቡሃላ በሚመረጡት ላይ ሳይሆን በሚመርጡት ሰዎች ምልመላ ላይ ትኩረት ይደረግ!!! ለመሆኑ ስማቸው ብቻ ተላልፎላቸው በነሱ ልብ ባለው እውቅና ነው የመረጡት ወይስ ግለ ታሪካቸውና የሰሩት ስራ ዝርዝር ቀርቦላቸው ነው 5ቱን በጎ ሰዎች የለዩት???…ይህንንስ አድርገው ከሆነ በእውነት በእውነት የተከበሩት የሕጻናት አለኝታ ዶ/ር በላይ አበጋዝ ሳይመረጡ አይቀሩም ነበር!!! ዳኒ እዚህ ላይ እየተመረጠ ያለው በጎ ሰው እንጅ ቀለማት አይደሉም፡፡ ቀለማት ቢሆን ኑሮ የሰው ስሜቱ ይለያያል እና ምርጫው ከሂስ ዶፍ አያመልጥም ነበር፡፡ ለበጎ ሰው ግን ክብደት አለው፤መለኪያ አለው ከ አንዱ ኮከብ ክብር ያንዱ ኮከብ ክብር ይበልጣል እንዲል ወንጌል!! ስለዚህ እዚህ ላይ መራጩ ስሜት ሳይሆን የስራቸው ክብደት ነው፡፡በተመረጡት ሰዎች ዙሪያ ሁሉም ስው ሊስማማ ግድ የሚልበት ሚዛን ሊኖር ይገባል!!
ግዴለም የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም ብየ አልተርትም ፡፡እኒህ አሁን ከተከበረው ሽልማት የፈሰሱት ትውልድን ታሪክን ሀገርን ያለመለሙት ንጹህ ምንጮችን ነገ አፍሰህ ታጠጣናለህ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ዳኒየ እንዲህ ያብሰከሰከኝ ያደረከው ትኩረትን የሚስብ የድንቅ ሰው ስራህ ነውና ልክ እንደቅኔያችን ይህ አስተያየቴም "ሰሙ" ወቀሳ.. "ወርቁ" የከበረ አድናቆትና ክብር ሁኖ ባንተ እና ባንባቢዎችህ ዘንድ ይፈታ(ይተርጎም)!!!
እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ደጋሽ እንጅ ታሪክ ብቻ አያድርግህ!!!!!!! በተመኘህላትና በተጋህለት እድገቱዋ ውስጥ መሪ ያድርግህ!!!!!! እግዚአብሄር በመንግስቱ ይሰብህ ይብቃኝ!!!!!!!!
the program made good thinking in every body. keep it up
ReplyDeletelong life to u dani
ReplyDeleteHow about Professor Mesfin?
ReplyDeleteThough the domain is more narrow and more affiliated with orthodoxwiyan,i really like the idea.Everyone has done great but Binyams is amazing. He chose the most difficult and adventurous job .He really is living what the scripture teaches us to do. May God bless you brother.
ReplyDeletedani it was nice thing u do keep it up
ReplyDeleteDiakon Daniel Egziabher Edmie Eetena gar yisteh
ReplyDelete''' Biniyam berta anten endnagez Egziabeher lebona yisten'''
Diakon daniel Egziabeher Edme yadleh
ReplyDeleteDiakon Daniel lante degmo Egziabeher edme yishelemeh......yesteh.....yadleh......
ReplyDeleteDiakon Daniel edme yesteh
ReplyDeleteiam relly sorry ,this is what we have from 80million people
ReplyDeleteወዴት እየሄን እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ክስተት ነዉ፡፡ አገር፤ ባህል፡ ማንነት፤ ሀይማኖት፤ አንድነት ወዘተ የሚባሉ ነገሮች እንዲጠፉና ተስፋ የሌለዉ ህዝብ መፍጠር አላማቸዉ የሆኑ ሰዎች ስልት መሆኑ መረዳት አያዳግትም፡፡
ReplyDeleteፈጣሪ ማስተዋሉን የስጣቸዉ፡፡
Again thank you Dn. Daniel. By the way, I started to visit you blog recently. Ofcourse I have been reading your writings elsewhere. Here is my piece some how related to 'Begonet'
ReplyDeleteለሁሉ ምቹ ግን ጥቂቶች የሚኖሯት እውነት!
ለራስ ያልቀደመ ስለሌላው መኖር፣
ላጡት ተስፋ መሆን ለሌላው መቸገር፣
የዚች ፍልስፍና የዚች ጥበብ አገር፣
ምንጯ ከየት ይሆን ሥረ መሠረቷ፣
የፍቅር መኖሪያዋ የቅንነት ቤቷ፡፡
ለማገዝ የመሻት የሌላውን ሸክም፣
ስለሌላው መኖር ስለሌላው መድከም፣
ለሌላው መጨነቅ ለሌላው መታመም፣
የዚች ፍልስፍና የዚች ልዩ ጥበብ የዚች ልዩ ሚስጢር፣
የት ይሆን ቀዬዋ ያለችበት መንደር፡፡
ስስትን የማታውቅ ሞልቶ የተረፋት፣
በረከቷ የማይነጥፍ ሰጥታ የማያልቅባት፣
የክፋት መቃብር በቀሏ ምኅረት፣
እውን የምትታይ ያለፈጠራት ምናብ፣
የሕሊና ምቾት የአእምሮ ምግብ ፣
የሐሴት አፍላጋት የሚመነጩባት ይቺ ልዩ ጥበብ፣
አገሯ ወዴት ነው ሥረ መሠረቷ፣
የከተመችበት የመኖሪያ ቤቷ፡፡
ዮ. ሠርፀ J. Sertse
ke edme manes yehun ke nebab etret ene yegebalu beye yemasebachew sewoch altetekalelum gen ende zega melkam hassab yezeh menesateh ena le hagere yaleh yezeweter teqorquarenet yemeberetata new,,,amlak hassabehn ke geb endeders feqadu yehun,,,,,,,,,,,,,,
ReplyDeleteዳኒ ስለሁሉም ምን እንደምል ይከብደኛል ዝም እንዳልል ተናገር ይለኛል ምን ብዬ ልግለፀው ብቻ እግዚአብሔር እድሜና ጤናን ይስጥህ ከዚህ በላይ የምታገለግልበትን ፀጋ ይስጥህ! ላለሁበት ቦታ ጠቅላይ ሚንስትር ነኝና መልካሙን ነገር ለማድረግ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ዝግጁ ነኝ፡፡ አመሰግንሃለሁ፡፡
ReplyDeleteThe best revolutionary idea ever! good job dani!
ReplyDeleteዳኒ የከርሞ ሰው ይበለን። በርታ
ReplyDeleteAmazing No Muslim Guy!Why ?
ReplyDeleteዳኒል እግዚአብሔር እረዠም እድሜ ይስጥህ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል እየሰራህ ያለው የበጎ ሰው ሽልማት በጣም የሚበረታታ ወደፊትም በጣም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ጥሩ ጀምር ነው፡፡ አንተ ብዙ ነገር ታውቃለህ እየሰራህ ያለውን መልካም ነገር በአሉታዊ ጐኑ የሚነቅፉህን እግዚአብሔር በጐ አመለካከትና መልካም አስተሳሰብ ይሰጣቸው እያልኩ አንተ ግን በርታ ሁሌም መልካም ነገር ስታደርግ ከጐኑ ብዙ መሰናክሎች ስለሚኖሩ እጅ እንዳትሰጥ በርትተክ ቀጥል፡፡ “ማድነቅ፣ መሸለም መሰልጠን ነው” ለሌሎች በጎ ማሰብ ታላቅነት ነውና በዚሁ ቀጥልበት፡፡ እግዚአብሔር መንገድህን ሁሉ ያሳምርልህ፡፡ ኢትዮጵያ እንዳንተ ያሉ ሰዎች በርከት ቢሉላት እንዴት ደስ ይል ነበር……. ለማንኛውም ረዥም እድሜና ጤና ከነመላው ቤተሰብህ ይስጥህ፡፡
ReplyDeleteእምዬ ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርካት አሜን
ዲያቆን ዳንኤል እየሰራህ ያለው የበጎ ሰው ሽልማት በጣም የሚበረታታ ወደፊትም በጣም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ጥሩ ጀምር ነው፡፡ አንተ ብዙ ነገር ታውቃለህ እየሰራህ ያለውን መልካም ነገር በአሉታዊ ጐኑ የሚነቅፉህን እግዚአብሔር በጐ አመለካከትና መልካም አስተሳሰብ ይሰጣቸው እያልኩ አንተ ግን በርታ ሁሌም መልካም ነገር ስታደርግ ከጐኑ ብዙ መሰናክሎች ስለሚኖሩ እጅ እንዳትሰጥ በርትተክ ቀጥል፡፡ “ማድነቅ፣ መሸለም መሰልጠን ነው” ለሌሎች በጎ ማሰብ ታላቅነት ነውና በዚሁ ቀጥልበት፡፡ እግዚአብሔር መንገድህን ሁሉ ያሳምርልህ፡፡ ኢትዮጵያ እንዳንተ ያሉ ሰዎች በርከት ቢሉላት እንዴት ደስ ይል ነበር……. ለማንኛውም ረዥም እድሜና ጤና ከነመላው ቤተሰብህ ይስጥህ፡፡
እምዬ ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርካት አሜን