Thursday, April 11, 2013

የደረጃ ዕድገት


click here for pdf 
የዚህ መ/ቤት ሠራተኞች ዘንድሮስ አምርረዋል፡፡ ባለ ስንት አሐዝ እንደፈለጉ አይታወቅም እንጂ ዕድገት ዕድገት ይላሉ፡፡ ‹ላለፉት ጥቂት ዓመታት የደረጃ ዕድገት አላገኘንምና እንደገና ሊታይልን ይገባል› እያሉ አንዴ በስብሰባ አንዴ በደብዳቤ ይጯጯሃሉ፡፡ ለነገሩ ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም የሚለውን የሚያውቁ አዲስ ሠራተኞች ናቸው አሉ ጉዳዩን የሚገፋፉት፡፡ አንዳንዶች ነባር ሠራተኞች ግን ‹ነባሕነ ነባሕነ ከመ ዘኢነባሕነ ኮነ- ጩኸን ጩኸን እንዳልጮህን ሆንን› የሚለውን በመተረክ ነው ያለፈ ልምዳቸውን የሚያካፍሉት፡፡
ኃላፊዎቹ ደግሞ ጥያቄው በተደራጀ መልኩ እንዲቀርብ ነው ያሳሰቡት፡፡ በአነስተኛም ይደራጁ በከፍተኛ የቢሮው ሠራተኞች ግን አንዳች አደረጃጀት ይዘው ጥያቄዎችቸውን ቢያቀርቡ የተሻለ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ‹አንድነት ኃይል ነው› የሚለው መፈክር ከሠርቶ አደር ጋዜጣ መቆም በኋላ በብዛት ባይታይም የአደረጃጀቶች የውስጥ ፋይል ውስጥ ግን ሊኖር እንደሚችል አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ገልጠዋል፡፡ ሠራተኞችም ‹ምክር ሠናይት ለእለ ዘይገብራ - ምክር ለሚፈጽማት መልካም ናት› የሚለውን አስታውሰው ተደራጁና የደረጃ ዕድገት ጥያቄያቸውን እነሆ አቀረቡ፡፡ ባቀረቡበት ቀን በተደረገው ስብሰባም ተደራጅተው መብት መጠየቅ መብታቸው መሆኑን፣ ይህንን አሁን ለደረጃ ዕድገት ጥያቄ የሰበሰቡትን የተደራጀ ኃይል ወደ ሌሎች የልማት ተግባራትም በማዞር የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው፡፡ ይህ አሁን የቀሰሙት ተሞክሮም ተጠናክሮ እንዲቀጥል፡፡ ለዚህም እያንዳንዱ ሠራተኛ እንዲረባረብ ከኃላፊው ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡ በርግጥ አንዳንድ ሸርዳጅ የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች መደራጀት፣ መረባረብ፣ ኃይል፣ ተሞክሮ፣ ፈጣን፣ ቀጣይነት፣ የሚሉት ቃላት በዚህ አዳራሽ ውስጥ ከመብዛታቸው የተነሣ ግድግዳው ሲፈረፈርም እነርሱ ናቸው አሉ የሚወድቁት፡፡
‹የዛሬው ስብሰባ የተዘጋጀው› አሉ የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ‹ባለፈው ለጠየቃችሁት የደረጃ ዕድገት ጥያቄ በጥናት የተደገፈ በቂ ምላሽ ለመስጠት ነው፡፡ ሁሉም ነገር ጥናት ይጠይቃል፡፡እንዲሁ በግብታዊነት የሚደረግ ነገር የለም፡፡ ረጋ ብሎ፣ ጊዜ ወስዶ፣ ተቀምጦ፣ ተሰብስቦ፣ ከሌሎች ተሞክሮ ቀስሞ፣ ነው፡፡ በዚህ መሠረት መ/ቤቱ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡ አሁን የኮሚቴው ሪፖርት ይቀርባል› አሉና ለኮሚቴው ሊቀ መንበር መድረኩን ሰጡት፡፡
‹ይህ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የሠራተኛውን ጥያቄ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለመመለስ ተንቀሳቅሷል፡፡ ለዚህም እንዲረዳው እስኪ የሌሎች ሀገሮች ልምድ ምን ይመስላል? ብሎ የሦስት ሀገሮችን ልምድ ለመቅሰም ወደ ሀገሮቹ ተጉዟል› [ይህንን ሲል አሽሟጣጮቹ ‹ከሄዳችሁት ውስጥ እርስዎ ብቻ ነው የተመለሱት› አሉና አሽሟጠጡ፡፡] በዚህም መሠረት የቻይና፣ የሞንጎልያና የዚምባቡዌ ልምድ ተወስዷል፡፡ ተሞክሮው ከተቀሰመ በኋላም ዓለም ዐቀፍ ነባራዊ ሁኔታው ምን ይመስላል? የሚለውን ለማየት እንዲቻል አራት ኮምፒውተሮች ተገዝተው፣ ብሮድ ባንድ ኢንተርኔት ገብቶ ከመረጃ መረቦች እየተፈለጉ ተወስደዋል፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ድርጅቱ የ‹አይ ቲ› ማዕከል ያቋቋመ ሲሆን የኮሚቴው አባላትም የሦስት ወር ሥልጠና ከታዋቂ ተቋም ወስደዋል፡፡ መረጃውን እየፈለገ ለማምጣትም አንድ ከፍተኛ ኤክስፐርት ተቀጥሯል፡፡[አሁንም አሽሟጣጮቹ አላቆሙም ‹ኮምፒወተሩ የተገዛው ከኃላፊው እኅት ሱቅ ነው፤ ሥልጠናውንም የሰጠው የኮሚቴው ሊቀ መንበር ወንድም ነው፤ ተቀጠረ የተባለውም ኤክስፐርት የምክትል ኃላፊው ዘመድ ነው› የማናውቅ መሰልናቸው፡፡
መናገርስ እናውቃለን
ግን ብንናገር እናልቃለን ብለን እንጂ‹ አሉና ከታተፉት]
‹ከዚህ በኋላ ኮሚቴው ወደ ጥናትና ምርምር ገባ፡፡ ብዙ ነገሮችን አገናዘበ፣ በአማካሪ ድርጅቶችም ሁኔታውን አስገመገመ፡፡ በመጨረሻም የደረሰበትን ዛሬ ይኼው ሊያቀርብ ነው፡፡› ብሎ ቀና ሲል የሚያፈጥ ዓይን እንጂ የሚያጨበጭብ እጅ አጣ፡፡
‹ኮሚቴው ጉዳዩን ከሥር ከመሠረቱ ነው ያየው፡፡ በዚህም መሠረት ከፋፍሎ ያቀርበዋል፡፡ [‹ቆይ ሁሉም ነገር በዚህ ዘመን መከፋፈል አለበት እንዴ› አለ አንድ አሽሟጣጭ]
1.1       የደረጃ ዕድገት ምንድን ነው?
የደረጃ ዕድገት ከሁለት ቃላት የተመሠረት ሐረግ ነው፡፡ ደረጃ እና ዕድገት፡፡ ደረጃ የሚለው ቃል ‹ደረጃ፣ ተደረጀ፣ አደራጀ፣ ተደረጃጀ፣ ድርጅጅት፣ ድርጅት› ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን ብዙ ትርጉም እንዳለው መዛግብተ ቃላት ያስረዳሉ፡፡ የቤት መወጣጫ መሰላል ደረጃ ይባላል፡፡በሌላ በኩልም ደረጃዎች መዳቢ የሚያወጣው ደረጃም አለ፡፡ ሌሎች ደረጃዎች መኖራቸውንም ምሁራን ይገልጣሉ፡፡ የኛ ደረጃ ግ ከሁሉም የተለየ ነው፡፡ ዕድገት የሚለውም ‹አደገ፣ ተመነደገ› ከሚለው የመጣ ሲሆን ማደግ መመንደግ ማለት መሆኑን ከልዩ ልዩ ሀገሮች ልምድ ለማወቅ ተችሏል፡፡
1.2     የደረጃ ዕድገት አመጣጥ ታሪካዊ ዳራ
የደረጃ ዕድገት በዓለም ላይ ከመጣ ብዙ ዘመናት አልፈውታል፡፡ መዛግብት እንደሚገልጡት በአውሮፓ የኢንዱስትሪ አብዮት ጊዜ ሳይጀመር አይቀርም ይባላል፡፡ የደረጃ ዕድገት እንደየሀገሩ ርዕዮተ ዓለም ይለያያል፡፡ ልዩነቱን እንደሚከተለው ከፋፍለን ማየት እንችላለን፡፡
የደረጃ ዕድገት በካፒታሊስት ሥርዓት
የደረጃ ዕድገት በኮሚኒዝም ሥርዓት
የደረጃ ዕድገት በታዳጊ አገሮች፣
የደረጃ ዕድገት በገለልተኛ ንቅናቄ ሀገሮች
የደረጃ ዕድገት በአፍሪካ
1.3     የደረጃ ዕድገት በልዩ ልዩ ሀገሮች
የደረጃ ዕድገት በዓለም ላይ አንድ ወጥ የሆነ አሠራር እንደሌለው በሦስት ሀገሮች ባደረግነው ጥናት ታውቋል፡፡ በቻይና የደረጃ ዕድገት ‹ቹ ቻግ ቺግ› የሚባል ሲሆን በኮሙኒስት ፓርቲው ውስጥ በሚኖር ተሳትፎ መጠን ይወሰናል፡፡ በሞንጎልያ እጅግ ብርድ ስለነበረ ተዘዋውረን መዛግብቶቻቸውን ለማየት አልቻልንም እንጂ የደረጃ ዕድገት መኖሩን ዐውቀናል፡፡ በዚምባብዌ ከሀገሪቱ ኢኮኖሚ የተነሣ የደረጃ ዕድገት ቆሟል [አንድ አሽሟጣጭ ‹ሞንጎልያ ብርድ ከሆነ፣ ዚምባቡዌ የደረጃ ዕድገት ከሌለ ለምን ሄዳችሁ?› አሉ]
1.4     የደረጃ ዕድገት በኢትዮጵያ
 • የደረጃ ዕድገት በዐፄው ዘመን
ባለፈው በነፍጠኛው ሥርዓት ጊዜ ዕድገትና ደረጃ የሚታሰቡ አልነበሩም፡፡ ቢታሰቡም ለሥርዓቱ ቁንጮዎች እንጂ ለብሔር ብሔረሰቦች የሚሆን አልነበረም፡፡ሥርዓቱ ዘውዳዊ በመሆኑ ዕድገትና ደረጃም ዘውዳዊ ነበሩ፡፡ ያም ቢሆን እንኳን የደረጃ ዕድገትን የሚመለከቱ መዛግብትን ማግኘት አልቻልንም፡፡[ይኼኔ አንዱ አሽሟጣጭ ‹ ግእዝ አላውቅም አትልም፤ አላገኘንም ከምትል› አሉት]
 • የደረጃ ዕድገት በደርግ ጊዜ
የደርግ ሥርዓት ሰው በላ ሥርዓት ነው፡፡ ጦርነት ናፋቂ የሆነ ሥርዓት ነው፡፡ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ተብሎ ስለነበር ደረጃና ዕድገትም ራሳቸው ጦር ግንባር ዘምተው ነበር፡፡
 • የደረጃ ዕድገት በሽግግሩ ጊዜ
በሽግግሩ ዘመን ገና ኢኮኖሚያችን ስላልጠነከረ የደረጃ ዕድገትም የተጠናከረ አልነበረም፡፡ የደረጃ ዕድገት ፈጣን ዕድገት ከማስመዝገባችን በፊት ያን ያህል የተጠናከረ ዕድገት አልነበረውም፡፡ ቢሆንም ግን ተስፋ ሰጭ ጅምሮች ታይተው ነበር፡፡
 • የደረጃ ዕድገት ፈጣን ዕድገት ካስመዘገብን በኋላ
በአሁኑ ጊዜ የደረጃና ዕድገት ጉዳይ ትኩረት አግኝቶ በመሠራት ላይ ይገኛል፡፡ የሠራተኛውን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መሠረት ባደረገ መልኩ በተቀየሰው አቅጣጫ መሠረት ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ በርግጥ ወደ ተግባር ሲገባ አፈጻጸም ላይ ችግሮች መከሰታቸው አልቀረም፡፡
የተከሰቱ ችግሮች
·         የሠራተኛው የግንዛቤ ማነስ
·         ስለ ደረጃ ዕድገት የሚገልጡ በቂ ሥልጠናዎች አለመሰጠታቸው
·         የጠባቂነት መንፈስ
·         የኪራይ ሰብሳቢነት መንፈስ
·         የደረጃ ዕድገትን ከሀገር ዕድገት ነጥሎ ማየት
·         የደረጃ ዕድገትን አመካኝቶ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ማድረግ
·         በመ/ ቤቱ ውስጥ የደረጃ ዕድገትን ትክክለኛ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ መፈክሮች አለመኖር
·         የደረጃ ዕድገትን አስመልክቶ ችግር ያለባቸውን ጥቂት ሠራተኞች ለመለየት አለመቻል፡፡
የመፍትሔ ሃሳብ
ኮሚቴው ላለፉት ሦስት ወራት ባደረገው ርብርብ ይህንን ጥናት ከፍጻሜ ለማድረስ ችሏል፡፡ የዚህ ጥናት ዓላማም የመፍትሔ አቅጣጫ ማመላከት ነው፡፡
1.         ስለ ደረጃ ዕድገት ሠራተኛው ተገቢ ግንዛቤ እንዲጨብጥ የሚያስችሉ ሲምፖዝየሞች፣ ወርክሾፖችና ስብሰባዎች ማድረግ
2.       የተሻለ ተሞክሮ ካላቸው ሌሎች ድርጅቶች ልምድ መቅሰም
3.       በመ/ቤቱ ውስጥ የደረጅ ዕድገትን የሚያስገነዝቡ መፈክሮችን መስቀል
4.       የደረጃ ዕድገትን የሚያስገነዝቡ በራሪ ወረቀቶች፣ ፖስተሮችና ባነሮችን ማዘጋጀት
5.       የደረጃ ዕድገትና የሀገር ዕድገትን ለይቶ የሚያውቅ ሠራተኛ ለማፍራት እንዲቻል በዚህ ረገድ ሥልጠና ማዘጋጀት፡፡
6.       የደረጃ ዕድገትን የሚያራግቡትን ኃይሎች ለይቶ ሠራተኛው ራሱ እንዲዋጋቸው ማድረግ
በሠራተኛው ያላሰለሰ ጥረት የደረጃና ዕድገት ናፋቂዎችን ጠንክረን እንዋጋለን፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ ›
አቅራቢው ጥናቱን ሲጨርስና በመስኮቱ በኩል ከድርጅቱ ክበብ የተከፈተ ሙዚቃ ‹ልመደው ልመደው ሆዴ፣ ከእንግዲህ እደር በዘዴ› ሲል አንድ ሆነ፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ስለሆነ በሌላ ተመሳሳይ ሚዲያ ማውጣት የተከለከለ ነው

47 comments:

 1. ha ha ha ha ha ha ha ha ha ki ki ki ki ki ki ki ki ki ki ki ki ki ki ki ki, betikikil new yegeletsikew. But we get tired of hearing such kind of speech in all offices.

  ReplyDelete
 2. gud eko new! tebarek diyakon danel

  ReplyDelete
 3. "‹ልመደው ልመደው ሆዴ፣ ከእንግዲህ እደር በዘዴ›"

  ReplyDelete
 4. I like you man!! Nice "mitset"

  ReplyDelete
 5. Dear,
  Etsube denk new Kekefu yesewereh!!!!!

  ReplyDelete
 6. ዲያቆን:ዳንኤል:ደረጃ:እድገት:ምናምን:እያልክ:ከምትቀባጥር:ምን:አለበት:እስኪ: ሜዳ:ላይ:ስለወደቁት:ወገኖችህ:ቲኒሽ:ነገር:እንኩዋ:ብትፅፍ:ጌታ:ይባርክህ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. tiru miker new .dn danil seltchgeru sewech tsafe .Ayto endalu malfe yasteykal ena.yembelut yemitetut yatu misken ethiopiyawyan nachew . Eski begta yewnet Aynochehen ensu lay adrge

   Delete
  2. Why don't you write yourself? By the way, have U tried to help those who live on ሜዳ:ላይ? writing is not the only solutions!

   Delete
 7. ዲ. ዳንኤል ግሩም አገላለጽ ነው፡ በእድገት መነሻ ስብሰባውን አብረን ተከታተልን፤ሲጀመር ወንበር ስቤ መቀመጥ አልነበረብኝም ብዬ እራሴም ወቀስኩኝ፤ያም ሆኖ “ከንብ እንጂ ከዝንብ ምን ይጠበቃል” ይሉ ነበር ጋሽ ታደገ ፤አረ ለመሆኑ እኛን ቤተ ሙከራ ያደረገን ማን ነው ትላንትም ዛሬም ወደፊትም በሰው ጭንቅላትና በሰው ቤት ውራጅ ለመድመቅ እየሞከርን አለ መታደል ነው መሰል ።በሩን ከፍቼ ስወጣ ምን ታደርገዋለህ የሚል ሙዚቃ ተቀበለኝ ወዳጄ፤ምኞቴ ከፍሎሪዳ

  ReplyDelete
 8. ዲ/ን ዳኒ በጣም እያሳቀ አስተምሮኛናል ምርጥ በሆኑ ቃላት እውነታውን ስለ ተናገርክ እግዚአብሔር ይባርክህ በርታ! ወዳጅህ ክብሮም

  ReplyDelete
 9. hahaha ... dink tsihuf new Dn Daniel, this is the fact in the ground!!!!

  ReplyDelete
 10. ዳኒ በፅሁፎችህ እጅግ መጣም እናመሰግናለን፡፡ እንኳን ለሦስተኛ አመት በዓል አደረሰ፡፡ በዓሉ ያንተ ብቻ ሳይሆን የኛም ነወ፡፡ እንግዲ ከዚህ በኃላ አንተ የህዝብ እየሆንክ የምትሄድበት ሂደቶች እየተጠናከረ ያለበት ሆናቴ ነው፡፡ የህዝብ ሆኖ መፈጠር በጣም ከባድ ነው፡፡ ደስታ ብቻ አይደለም ፈተኛዎቹ በጣም ከባድ ናቸው፡፡ ሰላምታ ከመስጠት ጀምሮ ስለዚህም ድንግል ከልጃ ጋር ብርታቱን& ልቦናውን& ጥበቡን እና ማስተዋሉል ትስጥህ፡፡ የክፍለ ዘመናችን ጅራታም ኮኮብ ልጅ ዳኒ፡፡

  ReplyDelete
 11. ግሩም እይታ ነው።
  Thank you very much.

  ReplyDelete
 12. ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ፣ ይጠብቅህ በእውነት ይህ የደረጃ እድገት የሚለው በተለይም የምሁራን ጥርቅም በሚባሉ ቦታዎች ላይ ዘወትር ይስተዋላል፡፡ ሠራተኛ እየተቸገረ፣ እየተራበ፣ እየታረዘ፣ ልጆቹ የሚለብሱት የሚበሉት የትምህርት ቤት ክፍያ ወዘተ በማጣት፣ አንዳንድ ጊዜም ሠራተኞች እየቱ እየታየ የደረጃ እድገት እየተሠራ ነው ጠብቁ ይባልና፤ ጎበዥ ሠራተኛች ሥራ ከለቀቁ በኋላ፣ ጠንካራ አለቆች መሥራ ቤት ከቀየሩ በኋላ፣ አማራጭ ያጡ ከሞቱ በኋላ እድገት ተብሎ በፐርሰንት ይመጣል፡፡ ‹‹እኔ እምሞት ዛሬ ማታ እህል እሚደርስ በፍልሰታ›› እንዳሉ አባሎታችን፡፡
  ስለዚህ የዚህ ዓይነቱ የደረጃ እድገት ከሀገራችን ብሎም ከዓለማችን መጥፋ አለበት፡፡ የደረጃ እድገት ፕሮፖዛል አዘጋጁም ልክ ለራሱ እንደሚሠራ በፍጥነት ቢያዘጋጀው የተሻለ ይሆናል፡፡
  ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይጠብቅህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. mindin new yemetaworaw wodaje, mejemeriya try to understand the central theme of the article!!

   Delete
 13. This is the sadest blog post I read on this blog. The subject matter is true, I'm just sad because this is really where we are with labor management, even worse, this is the model of governance for the current ruling party/Don't ask or be axed/. Thank you Dn. Daniel, another core subject needing a focus on. GOD be with you.

  ReplyDelete
 14. aygebachewma, men waga alew

  ReplyDelete
 15. "" Qoi Hulum Neger Bezih Zemen Mekefafel alebet Ende "" Ale And Ashmuatach Endeih Be Kelid Eyawazah Astemiren Enji MEDEHANIALEM Tsegawin Yabizalih Dn. Danii

  ReplyDelete
 16. Be Negew Elet Yemiakeberew 3gna Amet Yetumera Beal Ejig yamare Ena Yedemeke Endihon Eyatemegnhu Be Dokimas Guada Kene Lijewa Yetegegnechiew EMEBETACHIN Be Antem Yetumera Beal lai Tegegnita Hulun yetesaka Tadergew Zend Tslote Ejig New

  ReplyDelete
 17. woooooooow Daniel Kibret may GOD bless u and ur family

  ዳኒ በፅሁፎችህ እጅግ መጣም እናመሰግናለን፡፡ እንኳን ለሦስተኛ አመት በዓል አደረሰ፡፡ በዓሉ ያንተ ብቻ ሳይሆን የኛም ነወ፡፡ እንግዲ ከዚህ በኃላ አንተ የህዝብ እየሆንክ የምትሄድበት ሂደቶች እየተጠናከረ ያለበት ሆናቴ ነው፡፡ የህዝብ ሆኖ መፈጠር በጣም ከባድ ነው፡፡ ደስታ ብቻ አይደለም ፈተኛዎቹ በጣም ከባድ ናቸው፡፡ ሰላምታ ከመስጠት ጀምሮ ስለዚህም ድንግል ከልጃ ጋር ብርታቱን& ልቦናውን& ጥበቡን እና ማስተዋሉል ትስጥህ፡፡ የክፍለ ዘመናችን ጅራታም ኮኮብ ልጅ ዳኒ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዲ/ዳንዔል
   አንድዋ፣ ድንግል ከነልጅዋብርታቱን . . . ወዘተ ትስጥህ ብላሃለች። ይህ ምን ማለት ነዉ? ሰጪዋ ብቻዋን መስጠት ስለማትችል ነዉ ወይስ ልጅዋ የድጋፍ ሰልፍ ስለሚያስፈልገዉ ነዉ? እነዚህን ዓይነቶች "ክርስቲያኖች" እየሰማህ ዝም ማለት በላይኛዉ ቤት እንደሚያስጠይቅህ መቸም አጥተ£ዉ አይደለም።

   Delete
 18. ሳር እስቃለሁ አለ ጓያ !!

  ReplyDelete
 19. tsuhufu aymesitim.

  ReplyDelete
 20. እየሳቁ አለቁ!

  ReplyDelete
 21. Saken sicheris asteyayet isetalehu.

  ReplyDelete
 22. የሚገርም ዕይታ ነው ልመደው ልመደው ሆዴ ተወዳል ጤፍና ስንዴ ብለን ነው ያደግነው ዛሬ ደግሞ እደር በዘዴ

  ReplyDelete
 23. ዳኔ: እንኮን በሰላም በጤና ከሞላው ቤተሰብህ ለሶስተኛ ዓመት በዓል አደረሰህ አደረሰን። መጭዉንም ቦገውን እመኝልህ አለሁ።

  ReplyDelete
 24. የደረጃ ዕድገትን የሚያራግቡትን ኃይሎች ለይቶ ሠራተኛው ራሱ እንዲዋጋቸው ማድረግ

  በሠራተኛው ያላሰለሰ ጥረት የደረጃና ዕድገት ናፋቂዎችን ጠንክረን እንዋጋለን፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ ›

  ReplyDelete
 25. hagerachin endnte eynetu ewunet ena mikniat meseret argew yemitsufu new yatachiw yihe tshihufih behulunim mesribetoch yale neger new ena yetsafkew misgana yigebahal yehulum yemengist serategna yelibun new yetenagerkilet berta. gin aderh ende leloch tsehafiwoch nen yemilu tilacha ena simet bicha yizeh endatitsif eskahun lastemarken ena lewedefitu silemitastemiren misganachin lak yale new geta yibarkih.

  ReplyDelete
 26. ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ፣ ይጠብቅህ በእውነት ይህ የደረጃ እድገት የሚለው በተለይም የምሁራን ጥርቅም በሚባሉ ቦታዎች ላይ ዘወትር ይስተዋላል፡፡ ሠራተኛ እየተቸገረ፣ እየተራበ፣ እየታረዘ፣ ልጆቹ የሚለብሱት የሚበሉት የትምህርት ቤት ክፍያ ወዘተ በማጣት፣ አንዳንድ ጊዜም ሠራተኞች እየቱ እየታየ የደረጃ እድገት እየተሠራ ነው ጠብቁ ይባልና፤ ጎበዥ ሠራተኛች ሥራ ከለቀቁ በኋላ፣ ጠንካራ አለቆች መሥራ ቤት ከቀየሩ በኋላ፣ አማራጭ ያጡ ከሞቱ በኋላ እድገት ተብሎ በፐርሰንት ይመጣል፡፡ ‹‹እኔ እምሞት ዛሬ ማታ እህል እሚደርስ በፍልሰታ›› እንዳሉ አባሎታችን፡፡
  ስለዚህ የዚህ ዓይነቱ የደረጃ እድገት ከሀገራችን ብሎም ከዓለማችን መጥፋ አለበት፡፡ የደረጃ እድገት ፕሮፖዛል አዘጋጁም ልክ ለራሱ እንደሚሠራ በፍጥነት ቢያዘጋጀው የተሻለ ይሆናል፡፡
  ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይጠብቅህ
  10q daniy

  ReplyDelete
 27. እግዚአብሔር ይስጥልን
  እውነት የደረጃ ዕድገትም ሆነ የደወዝ ጭማሪ በመስሪያ ቤታችን ውስጥ ከተሰማ ድፍን አምስት አመት ሊያስቆጥር ወራቶች ብቻ ነው የቀሩት፡፡
  አሁን አሁን ሳስበው የአምስት አመቱ የየደረጃ ዕድገትንና የደመወዝ ጭማሪ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ(ለመስሪያ ቤቱ) መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ጽሁፍንን ሳነበው በጣም አሳቀኝ “እያረርኩኝ እስቃለሁ አለች…”

  ReplyDelete
 28. ፅሑፍህ በትግርኛ ተተርጉሞ ቢቀርብ !

  ReplyDelete
 29. it is not as such interesting topic

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያልተነካ ግልግል ያውቃል ኣሉ!!

   Delete
 30. melkam tizibit new danee.

  ReplyDelete
 31. i don't knowenem bizu alsabegnim

  ReplyDelete
 32. you have nice writing skill but there are a lot of issues you have to write other than this topic. Please we always anticipate something relevant to the people of Ethiopia.
  God bless you!

  ReplyDelete
 33. betam new dani yegelestkew gin lewet yelewem endiyawem hagerachin betewesenu hodamoch egee weset yemtewedek yimeselegnal [god bless our land]

  ReplyDelete
 34. thank you Diyakon God bless you. it how our country traks look like. every thing is shaped in this way. there is a problem , there will be study, the study escape the problem, the solution adress the intention of the researcher, the it is obvious in contradtion with the majority. who think about us? god helps us

  ReplyDelete
 35. የሰውን ቁስል እየነካካህ ሆድ ታስብሰናለህ ዳኒ እኛ መስራቤት ቢ.ፐ.አር ከተባለ ይሄው ስድስት አመት ሞላው ለስልጠና ተብለው እንግሊዝ ሀገር ሄዱ ሰለጥን መጣን ብለው ሰበሰብን ምን አንዳሉ መስማት እሰከሚሰለቸን ድረስ አዳመጥን ቢ.ፒ.አር ተሰራ ተባለና ተለጠፈ ፤፤ትክክል አይደለም ተባለና እንደገና ይሰራ ተባለ ሶስት አመት ፈጀባቸውና ተሰራ ውጤት ወጣ ቀሬታ ያላቸውም ቅሬታ አሰሙ ተባለ ቅሬታ ተቀበሉ ምን እንደው አይታወቅም ዝም ነው ሁለት ወር ሆነው
  እናም አትነካካን እድገት በአፍሪካ እንበለው ወይስ በኢትዮጵያ

  ReplyDelete
 36. hahahahaha bettam asikognal lemin meseleh yehen hiwot norewalehu ena tesifo sayewu wede huwala wesedegn......

  ReplyDelete