Tuesday, April 23, 2013

አማርኛ ከሠላሳ ዓመት በኋላ 
የዛሬ ሠላሳ ዓመት በ2035 ዓም በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች መካከል የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ውድድር ይደረጋል፡፡ በውድድሩም ከዚህ በታች የማቀርብላችሁ ወግ ‹እኔና ትምህርት ቤቴ› በሚል ርእስ ተወዳድሮ አንደኛ ይወጣል፡፡
ይህ ኦፖርቹኒቲ ስለ ተሰጠኝ ታንክዩ፡፡ አቦ ይመቻችሁ፡፡ ሀገራችን ኢቶጲያ ሚራክልየስ ሀገር ናት፡፡ አይ ሚን ነፍስ ነገር ናት፡፡ ይህንን ስል ግን ሙድ እንዳትይዙብኝ፡፡ እዚህ ሀገር ብዙ ነገር ነፍ ነው ማለቴ ነው፡፡ ዋተር ነፍ ነው፣ ኦፕን ኤይር ነፍ ነው፣ ሰን ሴትና ሰን ራይዝ ነፍ ነው፡፡ ማዩንቴይን ነፍ ነው፤ የሚደብረው ነገር ሮዶቹና ቪሌጆቹ ምልክት የላቸውም፡፡ ፎር ኤግዛምፕል የኛን ቤት ለሰው ስንነግር ‹ኒር እንትና ጫት ቤት› ነው የምንለው፡፡ ቢኮዝ እዚህ ሀገር ጫት ቤት ነፍ ነዋ፡፡ አት ዚስ ፖይንት ኤክስፕሌይን ማድረግ አለብኝ፡፡ የአያቴን ካፕ ቦርድ ስሾፍ አዲስ ዘመን የሚባል አንድ የድሮ ኒውስ ፔፐር አገኘሁና፡፡ ኮለመኑ ላይ ‹በምግብ ራስን መቻል› የሚል ነገር ሾፍኩ፡፡ ነገሩ ክሊር አልሆነልኝም ነበር፡፡ ዋት ኢዝ ‹ራስን መቻል›? ራስ ማለት ‹ሄድ› አይለደም እንዴ? መቻልስ ምንድን ነው? አንዱን ፍሬንዴን አስክ ሳደርገው ‹መቻል የሚባል ኦልድ ውሻ ጎረቤታችን አለ› አለኝ፡፡ ስለዚህ ራስን መቻል ሚን ‹የመቻል ራስ› ማለት ነው፡፡ 

ሶ፣ ዋት ኢዝ ዘሚኒንግ ኦፍ በምግብ ራስን መቻል? የመቻል ምግብ ማለት ነው? ማዘርን ስነግራት ለፒፕሉ ሁሉ ነፍ ምግብ ማቅረብ ነው አለችኝ፡፡ ዛት ኢዝ ጉድ፡፡ እዚህ ግን ጫት ሾፕ ብቻ ነው ነፍ ያለው፡፡ ግራንድ ማዘሬ ወደ ሰኩል ስትወስደኝ ‹እዚህ አፈር ፈጭተን አደግን› ትላለች፡፡ አም ሰርፕራይዝድ፤ ለምን አፈር ይፈጫሉ፡፡ ወይኔ ወፍጮ የለም እንዴ በእነርሱ ጊዜ? ደግሞስ አፈር ከየት አገኙ? አይ ወንደር፡፡ ግራንድ ማዘሬ ግን ይኼ አሁን ፎቅ ቢዩልት የተደረገበት ፕሌስ ሁሉ ሜዳ ነበር አለች፡፡ እኔ ግን በቴሌቭዥን ከማየው የስታዲዮም ሜዳ በቀር ሌላ ሜዳ አላውቅምና አይ ዶንት ቢሊቭ ኸር፡፡ እርሷ ግን ‹አሁን እናንተ በተገዛ አሸዋ የምትጫወቱት አፈር ስለሌለ ነው› ትላለች፡፡ ዌል ዌር ኢዝ ዘአፈር? አይ አስክድ ኸር፡፡ ‹አፈሩን ሁለት ነገር ሸፈነው፤ ሕንጻና ኮብል ስቶን› አለችኝ፡፡ ኢት ኢዝ አሜይዚንግ፡፡ ኦልዱ ቲቸር ደግሞ ‹ፈረንጆች ተራራ ሊያዩ እዚህ ሀገር ሲመጡ፣ እኛ ሜዳ ልናይ ውጭ ሀገር እንሄዳለን› ይላሉ፡፡
የምጽፈው ኤሎት ኦፍ ነገር ነበረኝ፤ ግን ፕሮብሌሙ ያኛው የአምሐሪክ ቲቸር ይቆጣሉ፡፡ ለምን ግን ይቆጣሉ፡፡ ቲቸርየን ጠይቀነው ነበር፡፡ ‹የአማርኛን ትምህርት በኮሌጅ የተማሩ የመጨረሻው ሰው ናቸው፤ ከእርሳቸው በኋላ ቆመ፡፡ እኛ በትርፍ ጊዜያችን ነው የተማርነው›› አለን፡፡ ለካስ ኦልድ ሆነው ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሐግ ልንሰጣቸው ሄደን ‹ቲቸርየ ፒስ ነዎት› ስንላቸው ‹ፕስ ለድመት ነው›፣ የሚሉን ለካስ ኦልድነት ይዟቸው ነው፡፡ወይኔ ሲያሳዝኑ፡፡ የኛ አምሐሪክ ቲቸርማ የጨሱ ናቸውኮ፡፡ሞርኒንግ ላይ ሲገቡ ‹ጪሶቹ ፒስ ናችሁ› ይሉናል፡፡ ደግሞ ሐርድ አይበጥሱም፡፡ ሆሞርክ ብንሠራ ባንሠራ እርሳቸው ‹ቴክ ኢት ኢዚ› ነው የሚሉን፡፡ ኦል ፒፕሉ ይወዳቸዋል፡፡ የኢቫሉዌሽን ፖይንት ሲሞላ ሀንድረድ ነው የምናሽራቸው፡፡ ኦልዱ ቲቸር ግን ከዳይሬክተሩ ሃርድ ዋርኒንግ ተሰጥቷቸዋል አሉ፡፡ ‹አምሐሪክን ሲምፕሊፋይድ ማድረግ ካልቻሉ ይጫራሉ› ተብለዋል፤፤
ኦልዱ ቲቸር ስትሪክት ናቸው፡፡ ሆምወርክ ካልሰራህ ሂ ዊል ኪል ዩ፡፡ ግሥ፣ ዐረፍተ ነገር፣ መልመጃ፣ ምንባብ የሚባሉ ዎርዶች ያሉት እርሳቸው ጋ ብቻ ነው፡፡ አቤት እነዚህ ወርዶች ሲደብሩኝ፡፡ የኛ ቲቸር ግሥ ምንድን ነው? ስንለው ሳቀ፡፡ የክላሳችን ልጆች ግን በሌላ ተረጎሙት፡፡ አያቴ ስትሰማ ብልግና ነው አለችኝ፡፡ ዐረፍተ ነገር የሚለውን ግን ቲቸርየም አልገባቸውም፡፡ የድሮ ቃል ነው አሉኝ፡፡ አንድ ጂኒየስ ልጅ እንዲያውም ኦልድ ቲቸራችን ጋ ያሉት ወርዶች ሙዝየም ተሠርቶ ይቀመጡ አለ፡፡ ቢኮዝ የርሳቸውን ወርዶች ለፓረንቶቻችን ስንነግራቸው ‹ከማን ጋር ነው የዋላችሁት ዛሬ?› ብለው ሐርድ ይሰጡናል፡፡ እነርሱም አያውቋቸውም፡፡ አንዲት ቺክ እንዲያውም ‹ኦልድ ቲቸራችንን እርሳቸው የሉሲ ግራንድ ሰን ናቸው› ብላ አስቃናለች፡፡
ላስት ዊክ ፎር ኤግዛምፕል ለክላሳቸው ልጆች ‹በአዲስ አበባ በእንግሊዝኛ የማይጠሩ የት/ቤት ስሞችን አምጡ› ብለው ሆም ወርክ ሰጡ፡፡ ልጆቹ ዘይ ኦል ክራይድ፡፡ ዘይ ኩድንት ጌት ኤኒ ኔም በአማርኛ፡፡ ፊውቸር፣ ቱሞሮ፣ ፋንታሲ፣ዴንቨር፣ ካሊፎርኒያ፣ ሆላንድ፣ ኦክስፎርድ፣ ካምብሪጅ፣ ቢል ጌት፣ አንስታይን፣ ሼክስፒር ነው ኔማቸው፡፡ የአማርኛ ኔም ከየት ያምጡ፡፡ በኋላ አንዲት የስኩላችን ታይፒስት ገቨርመንት ስኩል ሂዱ አለቻቸው፡፡ ዛት ኢዝ ናይስ አይዲያ፡፡ ኦልሞስት ኦል ጎቨርመንት ስኩልስ ስማቸው አማርኛ ነው፡፡ ሶ ዊ ካን ዲቫይድ ዘ ስኩልስ ኢን ቱ ቱ ፡፡ በአማርኛና በእንግሊዝኛ የሚጠሩ፡፡
ኖት ኦንሊ ዚስ፣ ኦልዱ ቲቸር ብዙ የማያርፉባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ክላሱን ለሁለት ዲቫይድ አድርገው ሃፎቹ አምስት የኢትዮጵያ ሊደሮች ስም፣ ሃፎቹ ደግሞ አምስት የአሜሪካ ሊደሮች ስም ጻፉ አሉ፡፡ የአሜሪካ ሊደርስ የተሰጣቸው ዘይ አር ቬሪ ግላድ፡፡ የኢትዮጵያ የተሰጣቸው ግን ዘይ አር ቢካም ክሬዚ፡፡ ‹ፕሊስ ቲቸርዬ ወደ አናዘር ግሩፕ ቀይሩን› እያሉ አለቀሱ፡፡ ፎር ዮር ሰርፕራይዝ ሁለቱ ፋዘራቸውን አመጡ፡፡ የአንዷ ፋዘርማ ለቲቸር ሐርድ ነው የሰጧቸው፡፡ ‹ልጆቹ ኢትዮጵያን ሂስትሪ ሳይማሩ እንዴት የኢትዮጵያን ሊደር ትጠይቋቸዋላችሁ› ብለው ነቀሉ፡፡ ኦልድ ቲቸር ደግሞ አስገቡላቸው ‹ልጆች ታሪካቸውንና ማንነታቸውን እንዲያውቁ ማድረግ የወላጆችም ግዴታ ነው› አሉ፡፡
መፋጠጡ የመጣው አት ላስት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሊደር የተሰጣቸው ልጆች ‹እኛ የኢትዮጵያ ሊደር ሊሞላልን ስላልቻለ በእንግሊዝ አሟልተነዋል› ብለው ሁለት የኢትዮጵያ ሦስት የእንግሊዝ ሊደርስ አመጡ፡፡ ኦልዱን ቲቸር ማድሊ ያሳቃቸው ግን የኢትዮጵያ ሊደር ብለው ያመጡት የሁለት የፊልም አክተሮችና የአንድ ቤስት ሲንገር ስም መሆኑ ነው፡፡ ኦልዱ ቲቸር ከኛ ቲቸሮች ጋር አይስማሙም፡፡ እርሳቸው ያከራሉ፡፡ የኛ ቲቸር ግን ‹ሲከርር ይበጠሳል› ይላሉ፡፡ ላስት ሳተርደይ በአምስቱ ክላሶች መካከል ሰልፍ ላይ የአማርኛ ኮምፒቲሽን ይደረግ ብለው ፐርፎርም አድርገን ነበር፡፡ ኳስሽኑን ያወጡት የኛ ቲቸር ናቸው፡፡
‹ያለው› በሚለው ዐርፍተ ነገር ሥራ? ይላል የፈርስቱ ኳሽን፡፡ ልጁ ይብራራልኝ አለ፡፡ ማለቴ ኤክስፕሌይን ይደረግልኝ፡፡ ‹ያለው በሚለው ቃል ሴንቴንስ ሥራ› አሉት ቲቸራችን፡፡ ገባው፡፡
‹ሁኔታ ነው ያለው› የሚል ነገር ሲናገር ተጨበጨበለት፡፡ ኦልዱ ቲቸር ግን አዘኑ፡፡ ‹ይህ ብክነት ነው፡፡ እንዲህ ሆኗል፣ ተደርጓል ብሎ ማጠቃለል ሲቻል፡፡ የተደረገበት ሁኔታ ነው ያለው እያሉ ሦስት ግሥና አንድ ገለጫ ማባከን ምንድን ነው? ብለው ተቆጡ፤ ግን አሞንግ አስ ግስና ገላጭ የገባው አልነበረም፡፡ አንት የኛ ክላስ ልጅ ግን ግሥና ገላጭ ‹የድሮ ቲቸሮች ኔሞች ናቸው› አለችን፡፡
አንዱ ደግሞ ‹ትናንት› በሚለው ዐረፍተ ነገር ሥራ ሲባል፡፡ በስንት ኤክስፕላኔሽን ‹የፋዘሬ ፋዘር ትናንት ደየመ› ብሎ ሴንቴንስ ሠራ፡፡ የኛ ቲቸር ሲያጨበጭቡ ኦልዱ ግን ነኩት፡፡ እንዲያውም ሊበጭጩ ነበር፡፡ ነቅለው ተነሡና ‹ደየመ ምንድን ነው?› አሉና አፋጠጡት፡፡ ልጁም ‹ጫረ ነዋ› አላቸው፡፡ እንደገና ጨሱ፤ ‹ጫረስ ምንድን ነው?› አሉት ‹ተነጠፈ ነዋ› ልጁ ሳቀ፡፡ ወላጆቹ ግን ‹ሀግ› ሰጡት፡፡
የአማርኛ ቲቸር ቀጠሉ፡፡ አንድ የአምሐሪክ ዲክሽነሪ አወጡና ‹ለሚከተሉት ወርዶች ሚኒንጋቸውን ተናገር› አሉ፡፡ ኦልዱ ቲቸር ሲቲ ስካን አደረጓቸው፡፡
መስጠት፡- መንፋት ነዋ፤ አለ ልጁ ‹ራይት› አሉት መምሩ፡፡
መፈንከት፡- ብር መዘርዘር
ምስኪን፡- ነፍስዋ ጀለስ
ቡርቴ፡- ቀሽት
ፍሬው ኃይሉ፡- ባለ ተሳቢው አውቶቡስ
አልመጣም ቀረሁኝ፡- የቧንቧ ውኃ
አየሁሽ፡- መብራት ኃይል
በልጆቹ ጂኒየስነት ተጨበጨበ፡፡
‹የመጨረሻው ኮምፕቲሽን ዕንቆቅልሽ ነው› ሁሉም ኮምፕልኬትድ ሆነበት፡፡ የአንዱ ልጅ እናት ‹የምን ቋንቋ ነው ይኼ› ብላ አስክ አደረገች፡፡ ኦልዱ ቲቸር ‹አማርኛ ነዋ› አሏት፡፡ ‹ኦልድ አምሐሪክ መሆን አለበት፤ እናንተ እንደ ዋልያ ኢንደሚክ የሆኑትን ዎርዶች ብቻ ነው እንዴ የምታመጡት፤ ኢዝ ኖት ፌይር ›› አት ላስት ኢንግሊሽ ቲቸር ኢክስፕሌይን አደረጉልን፡፡ ለካስ ኢት ሚንስ ‹ ሪድል›
‹ስሄድ አገኘኋት ስመለስ አጣኋት›
‹የኛ መንደር› አለች አንዲት ጂነስ፤ እንደ ጉድ ተሳቀ፤ እንደ ጉድ፡፡
‹ቤቷን ዘግታ የምትዘፍን›
ናይት ክለብ
‹ዓባይ ማደርያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል›
ቤት የሌለው ባለ መኪና
እኔ በኮምፕትሽኑ አንደኛ ስለወጣሁ አንድ ሚሊዮን ብር ተሸለምኩ፡፡ የተሰበረውን የሩሜን በር አሠራበታለሁ፡፡ ካርፔንተሩ በናይን ሀንድረድ ታውዘንድ እሠራልሻለሁ ብሎኛል፡፡ ግራንድ ማዘሬ ሰርቲ ይርስ ኤጎ ቤቷን በአንድ ሚሊዮን ብር መግዛቷን ነግራኛለች፡፡ ናው ኢት ኢዝ ዘ ፕራይስ ኦፍ ኤ ዶር፡፡
በዚህኛው የአምሐሪክ ኮምፒቲሽን ኮምፒት ያደረግኩትም ለዊንዶው የሚሆን ነገር ዊን ባደርግ ብዬ ነው፡፡
(ሁሉም ቆሞ በተማሪዋ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ችሎታ አጨበጨበ፡፡ ዳይሬክተሩም የልጂቱ ሥነ ጽሑፍ አማርኛ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ያስመዘገበውን ፈጣን ዕድገት ያሳያል ሲሉ ደሰኮሩ፡፡) 

 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፤ በሌላ ሚዲያ ማውጣት ክልክል ነው

94 comments:

 1. Dani Yemayekerew wudeketachinin askedemehe eyaredahen new? Bereget wodemanenetachin anemelese yehon???. Any ways thanks for your nice observation!!!

  ReplyDelete
 2. that looks great but is it not the same in the other native languages? please comment those who speak other Ethiopian languages

  ReplyDelete
  Replies
  1. He need to write about Ethiopian national language. Not about other Ethiopian languages. People who live in any country may speak a number of languages but these people should have only one national language.

   Delete
  2. For your information; Ethiopia doesn't have a National language !! Amharic is the Working language.

   Delete
  3. I am afraid that people like you still exists. I think it was not mentioned about other countries, but about another Ethiopian languages.

   Delete
  4. people calm down! There is no National or official language in Ethiopia. Amharic is a federal government's working language.But, what Daniel has wrote applies for every other language spoken in Ethiopia. We are forgetting our identity,our religion,our language and our culture. what makes us different from the peoples of other African countries, if we don't at least keep the things that make us different?

   Delete
  5. The way I see it amharic is the national language weather it is stated offically or not. The last few generation some how managed to establish a country establish a common language and they where building a country from a ground. And what are we doing? Trying to put our signature on history as the generation who collapsed it. This said, do you think other ethiopian languages are immuned from the danger? I dont think so. The way Daniel put it is some what with a funny way. But is a clear and present danger. At last for it is our collective and individual responsibility to keep a language of every ethiopian etnic group. Torenet lay hagerachen heberet ena mesmamat yegelachen that is really uncivilized. Sorry that I put my comment in english. My phone have only english phonts.

   Delete
 3. Semi yelem enastekaklew bibal adamach yelem!!!

  ReplyDelete
 4. በጣም እማዝነው የእነዚህ ልጆች አማርኛ አለመቻላቸው ሳይሆን እንግሊዝኛም በደንብ አለመቻላቸው ነው፡፡ እራሳቸውን አገር ውስጥ ካሉ እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች ጋር በማወዳደር ጥሩ ደረጃ ላይ ያሉ ይመስላቸዋል፡፡ የአገራቸውንም ሆነ የውጪውን ባህል አያውቁትም ባህል ካላወቅክ ደግሞ መናገር አትችልም ማለት ነው፡፡
  ከውጭ የመጣ አለቃ አለኝ እናም አንዳንዴ እንግሊዝኛ ድበዳቤ ሳረቅ ቲፒካል አማርኛ ይለኛል፡፡ እያንዳንዱን ቃላት ቢያውቃችውም ለመረዳት ግን ይቸግረዋል ፡፡ ለምን ቃላቱን ቢያውቃቸውም ባህሌን የቃላት አጠቃቀሜን አያውቀውም፡፡ ስለዚህ እንደነሱ አባባል ሪስክ ላይ ናቸው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. I don't not blame the kids (new generation) at all. I blame their parents and the society who are ashamed speaking their own native language.

   Delete
 5. ተስፋ አለኝ የሁላችንም ጥረት ታክሎበት የያዝነውን መንገድ እንደምናስተካክል፣በቴሌቭዥን ቃለ መጠይቅ የሚደረግላቸው ባለስልጣናት ግን ምክር ሊለገሳቸው ይገባል።
  በዚህ አጋጣሚ VOA እና EBS አቅራቢዎችን ማመስገን ያስፈልጋል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. voa and dochevelle yes! ebs? they need to work more on this.

   Delete
 6. Selam Dn. Daniel, I appreciate most of ur comentaries. However, on this one I have totally a different expectation in the fate of future Amharic. Yes, as u tried to show us the pain and suffering of our national language, language as any other developing phenomina, can grow at a given time and become weaker on the other time. Fortunately, when we see the history of Amharic, it would not be easily gets fragile or fragmented. Historicaly, it came in to the national service as a defense to the then national language Geez against the foreign language Arebic. At that particular time the Arebs and their languages were expanding aaround middle east and to the Meditranean costs. Egypt fall down and lost her ancient Coptic language, etc., here, thanks to Amharic the defendant language, which saved not only the language Geez but the nation as a whole. In the struggle between Arabic language introduced by the popes from the Coptic church who already surrenderd and lost their own tried to abolish ours. They used to have a desecive power in convincing the kings and clergy people who had also power on the church. Because of these and other circumstances, in the struggle between Arabic and Geez, Geez heavily wounded and pushed out in its service as national and governmental language. At this crucial historical time the defendant Amharic language took over the role of defense both the nation and Geez. Here, Amharic defended not only Geez and itself as a language, but all other Ethiopian languages too. Hence, recognizing the past and present role of Amharic language, we who can understand the history, nature and role of Amharic, our expectation is way different than your worry. Our young generation themselves will play the same as what Amharic did in our earlier history. Hope, some of u will be their and as a the witness.

  ReplyDelete
  Replies
  1. And I think Daniel's worry is reasonable. By the way is Amharic our national language or federal official language?

   Delete
  2. No national language in Ethiopia friend Wake up!!!!!!!!!!!!

   Delete
  3. I don't think it is time to speak about the history of Amharic, We are in trouble.Thus we must solve the problems ASAP.

   In addition I, in my own idea, had Geez been our national
   language , would feel fascinated ,though I don't really know the language.

   Delete
 7. who is ''ዳንኤል ክብረት''? is he artist? or writer? or is he........?????

  ReplyDelete
  Replies
  1. don't you know daniel? he is a writer and spiritual preacher.

   Delete
  2. what do u mean

   Delete
  3. I met him in Dallas nearly 9 years ago. He is a good preacher, but since I hate MK. I distanced from him. I still have respect for him.

   Delete
  4. Bravo ,hating MK or any other institution mustn't forbid us to respect some brilliants in it.
   But why do you hate MK? It is ,having many problems , the powerful existing organization in the land to save EOTC and preach the truth to the world collaborating with other institutions and persons like u.

   Delete
  5. i don't understand why MK is hated this much,our church would deteriorate if Mk stooped all the current activities and duties.Mk has proved that its indeed the backbone of the church.whether u like it or not Mk will continue protecting our church from all the outside and inside interference. MK is the gamechanger.

   Delete
  6. አይ እንደዚህ አይነቷን አስተያየት እንኳ "ማሲነቆ እራሱ ግጥም ከራሱ" ብያታለሁ፡፡ እሽ አንተ ማሲንቆውን ከያዝከው ሌላው ግጥሙን ይስጥህ ምናልባት አንተ ዜማ ልትጨምርበት ትችላለህ ያውም ላድማጭ የማይዋጥ ካልሆነ፡፡ ወይም ማሲንቆውን ሌላው ከያዘው አንተ ደግሞ ግጥሙን ስጥ ከባለማሲንቆው ከዜማ ጋር ታዳምጠዋለህ፡፡

   Delete
 8. ዳይሬክተሩም የልጂቱ ሥነ ጽሑፍ አማርኛ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ያስመዘገበውን ፈጣን ዕድገት ያሳያል ሲሉ ደሰኮሩ

  ReplyDelete
 9. really good refresher and learn so much from it. "we lost a lot which reflect our identity"

  ReplyDelete
 10. ጂማ ዩኒ.'Graduate Assistant'ለመቅጠር ብለው ባወጡት ማስታወቂያ ላይ ዋና የመወዳደሪያ መሥፈርቱ የተማርከውን ምን ያህል አውቀሃል ሳይሆን የእንግልዚኛ ቋንቋን ትናገራለህ ትጽፋለህ ተብለው እንደተገመገሙ ከተለጠፈው ማስታውቂያ ላይ አይቼ ብዙ ነገር ተሰማኝ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የዩኒቨርሲቲዎች ኦፊሻል ቋንቋ እንግሊዝኛ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲዎች እንግሊዝኛ መናገር በማይችሉ መምህራን እየተሞሉ ነው። ይህ በጣም ያሳዝናል። ስለዚህ እንግሊዝኛ በቅጡ የማይችል ሰው ዩኒቨርስቲ ያስተምር እያልክ ከሆነ ተሳስተሃል። የዳንኤል ጽሑፍም አንተ ካነሳኸው ጉዳይ ጋር የሚገናኝ አይመስለኝም።

   Delete
  2. Why did the official language of Universities became English. Is it to hide the secrets and knowledge found from the university from the students.
   "We university students think in amharic (or our mother tongue) write in English. The teacher reads in English understands in mother tongue and gives you comments in mother tongue."
   Is English a highway that we lose our time moving through it ?

   Delete
 11. ፕራዮሪት ምናምን የሚባል ነገር አታርፍም ልበል? ዋት ኢዝ ዘ ቢግ ዲል ኢን ሴቪንግ አማርኛ? ኢትዮፕያ ውስጥ ስንት የሚጻፍበት ነገር እያለ አማርኛ ምናምን ትላለህ እንዴ? ዋናው ኮሚኒኬት ማድረጉ ነው, isn't it stupid to write ደብሊው ደብሊው ደብሊው instead of www.አንዴ ተቀድመናል በቃ ማመን መቀበልና ላይፍን መቅጨት ነው.& thank you 4 telling us dat we'll not have 5 leaders till 2030 which mean #HMD will stay in throne like the the deceased #MZ. Don't be against change ok, do u understand?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Why we wait until 30 years here ayyyi is one example of early Bird!

   Delete
  2. Hahhahahaha u'r right

   Delete
  3. I think this should be one of the priorities we have inorder to survive as a country. in long term this is very dangerous and we need to work hard. thank you daniel for your concern.

   Delete
  4. አይ ትንሽ ብቻ ማወቅ? ይሄኔ በወር 50 ብር ከፍለህ በእንግሊዝኛ ስለተማርክ «አሜሪካዊ» የሆንክ መስሎህ ይሆናልኮ change change ምትለው። እነሱ ቢሰሙህ ምን እንደሚሉህ ባወክ!አንተ ሞኝ። አንተ ለነሱ ስታጨበጭብ እነሱ ግን ሰው ለመሆንህ እንኳን ማስረጃ ሊጠይቁህ ይችላሉ። ከየት አባህ እንደምታመጣ አንጃልህ እንጂ። ቋንቋቸውን ስለተናገርክ ሳይሆን ምታድገው እንደነሱ ስለሰራህ ነው። ምን ዋጋ አለው "a little knowledge is dangerous than atomic bomb!" ሆነ ነገሩ።

   Delete

  5. አንተ ለነሱ ስታጨበጭብ እነሱ ግን ሰው ለመሆንህ እንኳን ማስረጃ ሊጠይቁህ ይችላሉ። ከየት አባህ እንደምታመጣ አንጃልህ እንጂ anjeten kibe atetahegn gosh

   Delete
  6. ይህች የዘር አመላችሁ ከቤት ወጣች እንዴ? ይህች ከልከሎሳ የሚባል የሚጋልባት የበረሃ ዛር ናት፡፡ ተው ተው እነርሱ እንደሆኑ ምንም አይሉም፡፡ ንስሃ ገብተው ጨድር ተጠምቀዋአል፡፡ እንዲህ ዓይነት የዘር መነካካት ለ“ኬ.ኬ.ኬ”ዎችም አልበጃቸውም፡፡ ተው ተው አታነካካ፡፡ ደግሞ ምን ልትል ነው “ምን እንደሚሉህ ባወቅህ” ያልከው በእውነቱ ነጻ አሰተሳሰቡን ለማሸማቀቅ እየሞከርክ ካልሆነ እኛ ሁሉ ምስክር ነን ምንም አይሉም፡፡ ከፈለግህ ግጠመኝ ቀጥል እንከራከር፡፡

   Delete
  7. betam yemiyasazin neger new quanquachin metebek yehulachin halafinet new dn. daniel kibret betam lameseginh ewedwlehu. and asteyayet ayche eko new."sint yemisaf neger eyale amargna minamin tilaleh..." yilal yihen betsafew sew betem aznalehu maninetun yeresa sew new ewnet lemenager yefereng quanqua menager yesiltane milikt yemihonew bemejemeriya yerasin siyawku new lemanignawm dn. daniel kibret betam adenkihalehu asteyayeten be englizigna fidel bemetsafe yikrta eteyikalehu amesegnalehu

   Delete
 12. enem leerft gebche azenkugn enam seteyek anchi yezare 16 amet lay komeschal tebalku. egnem betam azegne temelesku abso yechi teraz netek englisch

  ReplyDelete
 13. ዳንኤል፡መጀመሪያ፡እንኩዋን፡ለ፫ኛ፡አመት፡አደረሰሕ።ለመንግሥቱ፡እኔ፡ልመልሥለት። ዳ፨ን፡ዳንኤል፡ማለት፡እጅግ፡በጣም፡የሚደነቅ
  መምሕር፡ፀሐፊ፡ለሐይማኖቱ፣ለሐገሩ፣ለባሕሉ፡እና፡ለሕዝቡ፡ተቆርቛሪ፡ነው።እኔ፡አንተን፡ብሆን፡መጠየቅ፡አያስፈልገኝም፡ዝም፡ብዬ፡ፅሑፉን፡ሳነብ፡ማንነቱን፡እረዳለሁ፡ስለዚህ፡ወንድሜ፡አንተም፡ማስተዋሉን፡ይስጥሕ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Sintayehu
   may God bless you that was good response for people like
   him please let us be positive.

   Delete
 14. ሰላም ዲያቆን ዳንኤል
  በአማርኛ ለቋንቋ በኩል ያለህን ስጋት እኔም እጋራዋለው። በእኔ እምነት፤ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለእድገቱ ከፍተኛ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል ፤ ለዚህም በአሰጣጡ ላይ ወይም በመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅት ላይ ትኩረት ማድረግ ትምህርቱ እንዳይሰለች ይልቁን በሚያዝናና መልኩ ግንዛቤ እንዲያስጨብጥ ማድረግ ይቻላል፤ ለምሳሌ የክርክር መድረክ(Debate) ከ፫ኛ እና ፬ኛ ክፍል ጀምሮ ቢዘጋጅ፤ ልጆጁ ለቋንቋው ከንቱ ንቀት ሳይኖራቸው በምክንያታዊነት ማስረዳትን፤ የቃላት ኣጠቃቀምን ይማራሉ፤ ይኼው የክርክር መድረክ በደራስያን ማኅበር ድጋፍ ሰጪነት በትምህርት ቤቶች መካከል በመደበኛነት ቢከናወን ብሔራዊ ትኩረት ከመሳቡም ባሻገር የግል ትምህርት ቤቶችንም ለተሳትፎ ማነሳሳት ይችላል የሚል ግምት አለኝ።
  ለዚህ ሁሉ ግን አሁን ያለው የግጥም፣ድርሰቶችና አጠቃላይ የሥነጽሁፍ ዘርፎች እድገት መቀጠል አለበት። የሥነጽሁፍ ባለሙያዎችም ሙያው ከፍላጎት ባለፈ ሊያስገኝ የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማሳደግ የሚቻልበትን መንገድ ማሰብ የሙያቸው አካል አድርገው ቢንቀሳቀሱበት ለተተኪው ትውልድ ዘላቂ የሆነ የስራ ዘርፍ መፍጠር ያስችላል። በተጨማሪ የሥነጽሁፍ ባለሙያዎች ወይም በዘርፉ ያሉ ማኅበራት የሙያ እና የባለሙያ ሥነምግባር በመቅረጽ የሥነጽሁፍ ሙያ ከፍ ያለ ግምት እንዲሰጠው መጣር አለባቸው ብዬ አምናለው።ከዚህ በመነሳት፤ ወላጆችም ልጆቻቸው ግምት በሚሰጠው የሙያ ዘርፍ አንዲሳተፉ ያበረታታሉ
  ምናልባት ይኼ አካሄድ ቋንቋውን ወላጅ አልባ ወይም አሳዳጊ አልባ አድርጎ አያስቀረው ይሆናል። በዚህ አጋጣሚ አንተ ለምታደርገው አስተዋጸኦ ከልብ አመሰግናለው።

  ReplyDelete
 15. be wenetu kehone yenga amaringa melkiten beytegabew melku ayastelalfem wayes beras koakawa alemekurat new chigru?

  ReplyDelete
 16. ግን ምን ያልጠፋን ነገር አለ?
  ቋንቋ፣ሥነ ምግባር፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ሃገር ወዳድነት፣ ብርታት ወዘተ ('ወዘተ'ም ካልጠፋ!)
  ደግሞ የኑሮ ውድነቱ!
  ከ፴ ዓመት በኋላ ምንአልባትም የአንድ ሚልዮን ብር ኖት ይኖረናል።

  ሁላችንም ኃላፊነት አለብን!

  ዲ/ን እግዚአብሄር ያበርታህ።

  ReplyDelete
 17. Ye Addis Ababa University yekuankua "mihuran" yihin anbibewut yihon?

  ReplyDelete
 18. yihe be ewinetu litasebibet yigebal.

  ReplyDelete
 19. ዳኒ እንኳን ለሶስተኛ አመትህ በሰላም አደረሰህ።ቤተ ክርስትያን ባትኖር ኑሮ እስካሁን ቋንቋው ጠፍቶ ነበር።ይህ ችግር የብዙ ሀገሮች ችግር ለምሳሌ ጎረቤት ኬንያ ብንሄድ ኪስዋሂሊ ከብዙ ቋንቋዎች ጋር በመቀላቀል ሻንግ የሚባል ቋንቋ ፈጠሩ አሁን የገጠሩ ህዝብ ከተማ ሲገባ በዚህ ቋንቋ ለመግባባት የግድ አሰተርጓሚ ሊያስፈልገው ነው።

  ReplyDelete
 20. hello Daniel, You really can predict what exactly will happen after some year, which is very sad is in most of private schools also 'English Language' is Medium and in some schools even in kindergarten, speaking in Amharic is forbidden... they have to talk in English in the compound and at home also they insisted to speak English also. in my Opinion i do not mean Speaking or Knowing any language is very good , but first they, we, parents, teachers, the society should give credit for out Native language Amharic. Even i think Geez also can be included in the curriculum. Daniel thanks for your outstanding views.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተስ ራስህ በአማርኛ ለተጻፈ መጣጥፍ በእንግሊዝኛ ስትተች ምን እያደረግህ ይመስልሃል? እነዚያ ት/ቤቶች ግን ተማሪዎቹ እንግሊዝኛ ቋንቋን አቀላጥፈው መናገር እንዲችሉ የራሳቸውን ዘዴ መከተላቸው አያስወቅሳቸውም። አማርኛው የቤት ቋንቋቸው ስለሆነ የትም አያመልጣቸውም። የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ለዕውቀትም ሆነ ለዕድገት አስፈላጊ የሆነ አለምአቀፍ ቋንቋ ነው። ሲንጋፖር በአጭር አመት ውስጥ የኤኮኖሚ ጣራ የሆነችውና ከአንደኛው ዓለም ጋር የተቀላቀለችው የሃገሯን ኦፊሻል ቋንቋ እንግሊዝኛ እንዲሆን በመወሰኗ ነው። እዚህ እኛም ሀገር በቋንቋ ጉዳይ ሲፖተልኩ ከመኖር እንዲህ ዓይነት እርምጃ ሳያስፈልግ አይቀርም ባይ ነኝ።

   Delete
  2. I don't agree with what you said about singapore. I believe economy has nothing to do with language. how about japan, china, most of europian countries etc. be reasonable. do you mean we need a single language or english language to do better than we are doing now.

   Delete
  3. Japan, China, Korea, etc... took them a century or so to reach their current economic status. But it took Singapore less than 30 years. If Singapore had decided otherwise, it would have remained poor and her people fighting each other on ethnic languages.

   Delete
 21. "እኔ በኮምፕትሽኑ አንደኛ ስለወጣሁ አንድ ሚሊዮን ብር ተሸለምኩ፡፡ የተሰበረውን የሩሜን በር አሠራበታለሁ፡፡ ካርፔንተሩ በናይን ሀንድረድ ታውዘንድ እሠራልሻለሁ ብሎኛል፡፡ ግራንድ ማዘሬ ሰርቲ ይርስ ኤጎ ቤቷን በአንድ ሚሊዮን ብር መግዛቷን ነግራኛለች፡፡ ናው ኢት ኢዝ ዘ ፕራይስ ኦፍ ኤ ዶር፡፡" (ኑሮና አማርኛ በ2035)

  ReplyDelete
 22. ይቅርታ ወንድም ዳንኤል
  እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የአማርኛን ቃላት በእንግሊዝኛ እየቀላቀሉ ማውራት ጸያፍ የሆነ እንደሆነ በዛሬውም ሂደት ላይ ተቀምጧል፡፡ በውነቱ ከሆነ እንዲህ አይነት ሁኔታ የሚፈጠረው ተፈጥሮአዊ እውነታ እንጂ የዘመን ብዛት ወይንም ዘመናዊነት ብቻ ተደርጎ መወሰዱ ከዚህ በፊት በ‹ኮድ ሚክሲንግ› ላይ የተሰሩ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ‹ኮድ ሚክስ› ለምን ይደረጋል ቢባል ዋነኛው ምክንያቱ የልሳነ ክልዔነት ውጤት መሆኑን ሁሉም ይስማሙበታል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በርካታ ቋንቋ ያሉባቸው ማህበረሰብ እንዲህ ዓይነት ክስተት ማየት የተለመደ ነው፡፡ ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ ብቻ ሳይሆን ከሃገርኛ ቋንቋዎች በመዋዋስ ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ለምሳሌ ሰንጋ፣ ቀበቶ ከአማርኛ ሱቅ፣ ሸሚዝ ከአረብኛው ወዘተ በርካታ የተውሶ ቃላቶችን ያዩዋል፡፡ ቃላትን ብቻ ሳይሆን የቃላት ሽራፊዎችን ‹ሞርፊሞችን› ለምሳሌ ብዛትን አስመልክቶ- ቾኮች፣ መኪኖች ወዘተ በተጨማሪም ሐረጋትንና ዓረፍተ ነገሮችንም በመቀላቀል እንደሚናገሩ ይስተዋላል፡፡ ርግጥ አንዳንዶች ለጉራ፣ በስካር መንፈስ፣ በህልም ዓለም ወዘተ ሲጠቀሙም ይታያል፡፡ እናም ወዳጄ ይህንን ነገር እናስቁመው ቢባል ሁሉንም ሰው አንድ ቋንቋ ብቻ ተናገር/ዕወቅ ብሎ ማቀብ ይሆናል፡፡ ተፈጥሮአዊነቱን ከመቀመል አማራጭ የለም፡፡ ኩነኔው ግን የረፈደበት ይመስለኛል፡፡
  ከምስጋና ጋር

  ReplyDelete
 23. Ye Sew Werk Ayademik Yelalu Abew Siteretu Wede Rasachin Yeminemelsebetin Gize MEDEHANIALEM Ayarikeben Teru Eyeta new Dn.Dnii AMILAKE KIDUSAN Ye Ageligilot Gizehin Yarzimelh

  ReplyDelete
 24. ዲያቆን ዳኒ ኧረ እንደውም ይህንን ያህል አማርኛ እየቀላቀለ የሚያወራ ወጣት ይኖራል ብዬ አልገምትም:: የዛሬ 35 ዓመት አማርኛ የአሁኑን ግዕዝ እንዳይሆን እሰጋለሁ::

  ReplyDelete
 25. ጎበዝ በጊዜ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ነው ብዙ ያጣናቸው ባህሎቻችን እንደቀልድ ሸሸት ሸሸት ብለው እንደቀሩ እንይ በመጀመሪያ ደረጃ መሰልጠን ማለት የራስ ትቶ የሰው የሆነው ሁሉ መቀበል አይደለም የሚለው ነገር ሊሰመርበት ይገባል የሚኮረጁና የማይኮረጁ ፣ በከፊል የሚኮረጁ በጭራሽ ሊኮረጁ የማይገባቸው ብለን ብናስብ ተገቢ ነው የሁላችን ኃላፊነት ነው ዳንኤል ኃላፊነቱን በዚህ አዝናኝ መሳይ ፅሁፍ ልቅም አድርጎ አሳይቶናል እኛም ከቤታችን ፣ከልጆቻችን ከታናናሾቻችን ጀምረን አለባስ ፣ ቋንቋ፣ ወዘተ ብለን ልንመክር ልናስተምር ይገባና ኃላፊነቱ የሁላችን ነው፡፡ ሁላችንም በሚገባ ኃላፊነታችንን ከተወጣን ልጆቻች አውቀው ማደግ የሚገባቸውን ነገር አውቀው እንዲያደጉ ካደረግን ማን ያውቃል የቅድመ አሃቶቻችን አይነት ጥርት ባለ ቋንቋችን የተፃፈ ውድድር ይሆን ይሆናል ጊዜ አለን በርትተን እንነሳ ዳንኤል ለአንተም እድሜና ጤና ይስጥህ አሜን

  wtbhm

  ReplyDelete
 26. Replies
  1. You miss the main points. It is not about exaggerated but how to protect this crisis would not happen.

   Delete
 27. first of all i want to say thank you to you and next to that when i read about our Amharic language when i think about what will be happen in the future it will be desccating and boaring for the coming generation it will bleam us because we lost our idnetity totally. Thank you for you because you show us the coming genenration in the mirror what will be happen.

  ReplyDelete
 28. daniel is an artist , writer ,deacon ,preacher and so on.....atleast he is not stupid like ............

  ReplyDelete
 29. በስመ አብ
  ዲ/ን ዳንኤል ምንድን ነው ትንቢቱ ይህስ አይሁን ማንነትን ማጣት ነውና፡፡

  ReplyDelete
 30. I agree Dani that is why the current government has been destroyed Amharic speaker people. I don't mind if the Wayana government changes the national language from Amharic to Tigrina but they don't have any substitution plan, their view is to kill Amharic speaker people. I know why you expect this but I believe God will change everything with in one day. God bless you and God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Stupid people politicize everything. Do you know the Amharic of Meles. It was a very good one -- I can say perfect but you know he is a woyane. It is your uncles and aunts who are encouraging their kids to speak in English. Fuck off with your stupid opinion.

   Delete
 31. Dani ante bekeld akerebkewu injy hagerun yecheresewu tiraz netekinet newu. Bemejemeriya Englizegna quanqua asregitewu ye mayichilu memihiran Englizegna yastemiralu. ignam balemawekachin inisakek ina kegna belay yalutin adinaky honen inkeralen. Bezalay libachin yalewu wuchy hager mehed lay silehone beka ingilizegna kulf newu. Betam yemidenkegn gin tiru ingilizegna menager yemichilu sewoch amarigna indet asamirewu indemiyaweru. Bcha Huletegna derejam sinimar ye gubizina mistir neger magenazeb sayhon Englizegna meredat neber . alebeleziya physics ayigebahim. igna ahun tarik semten magenazeb balakaten neber History timihrt bamarigna bihon. indiyawum min astaweskehn yehone sewuye neber ihen hasab migaragn ye Darwin metshaf "survival of the fites" wede amarigna lemekeyer yetagele, yet derso yihon? bcha ine milewu lijochun yetebelashe migib iyabelan lemin tenegna indihonu intebikachewalen newu!?!?

  ReplyDelete
 32. አሁን ከባነንን የተሻለ ነገን መፍጠር እንችላለን ፤በኣማርኛ ብቻ ሳይሆን በሎሎችም የአገራችን ቋንቋዎች፤ ከልሆነ ግን ከ2035 ሊቀርብ ሁሉ ይችላል፡፡ለሁሉም ጥሩ እይታ ነው ዳኒ፡፡

  ReplyDelete
 33. ዲያ.ዳንኤል ይህ አይሁንብን ያስፈራል፡፡ መጠንቀቁ አይከፋም አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር ክልክል ነው ተብሎ በሚነገርበት ት/ቤት የሚማሩ ልጆች ከዚህ የተሻለ ነገር አንጠብቅም ሁላችንም ይህ እንዳይሆን እንጣር ለአንት እግዚአብሔር ይስጥልን ከዚህ በፊት በዚህ አርዕስት ከተሰሩት የተሻለ የማንቂያ ደውል ነው በርታልን የአገልግሎት ዘመንህን ያብዛው አሜን፡፡

  ReplyDelete
 34. Sorry I would have written it in Amharic. Unfortunately, my computer lacks Amharic font. Any ways, Dn. Daniel forecasted it well. It seems some thing funny but very serious issue. Degradation of a language might not be as such big concern but most threatening issue in it is degradation of mind- generation. Look how Dn. Daniel presented the way of thinking at that time. So dreadful. They almost are the way kids are thinking.

  Do you know how much Ethiopian have a slaved mind. Better now in other African. English has degraded the world no one understand this. Look almost all the developed nations except North Americas (US and Canada) and Australia are non English speaker. Look from Europe, Germany, Russia others all their scientific records are in their own languge. Go to Asia, Japan, recently, the Koreans (Both south and North- technology wise north also has become on top), China, Singapore others far eastern, they little speak English. Latins are also now recovering. Other other hand, so called non English English speakers such as Africa. Simply slave mind. Unfortunately, English has become language of communication for most of the world. Normally Science and technology does not exist in English. For slaved mind, English is like a symbol of civilization. One can critically observe that except for the aforementioned English origin nations, English and/or other colony language speakers have remained to be backward and poor. Look Indians who were for 150 years colony of English. It resisted the English language and here now pacing towards science and technology. Perhaps, English has spoiled the world and Indians have spoiled English language. For Ethiopians in particular, shame that more slaved mind than even the other African. As Dn. Daniel mentioned look names of private schools, nearly all business trade names, cafes, restaurants etc including menu's of these survive providers. They might not serve at all any foreign customers but all their deliveries are in English.
  What about government institutions themselves including ministries. eg 'transportina megenagna; informationina communication; ketema limatina construction; xxxx agency, so shameful namings as if the Amharic or any alternative language were deprived of words to name such confusing namings.

  The issue might seem silly but really critical.

  Dn Danial thank you!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Do you think Nigeria made English her official language because of "slave mind" as you call it? Do you think Uganda, Ghana, SA did the same because of "slave mind"? Me, I don't think so!!

   Delete
 35. In case, the appropriate word is missed from Amharic, the country can form namings by agregating from other languages or full term from either of its languages. Eg. school name Dandi Boru- (Very meaningful, pleasant name). But for poor Addis students, they might have come out for mob against this name if they had been told it is from Afan oromo. Most Addis Abebe thinks this as if it were foreign term. Ofcourse Dandi Boru is one of the best school of the city. meaning 'Yenegew Menged'.

  I appreciate the owners.

  ReplyDelete
 36. ኢትዮጵያዊያን ወላጆችና መምህራን ሆይ አሁኑን ብንነቃ አይሻልም?
  SG DALLAS

  ReplyDelete
 37. I feel that your article is full of pessimistic.

  ReplyDelete
 38. በብዙ ተባረክ ዳኒ! ይህ ማንነትን የመጣል እንጂ የመሰልጠን ጉዳይ አይደለም። በአለማችን የራሳቸውን ሳይለቁ የሰለጠኑ፣ በማንነታቸው የሚኮሩ ብዙ ሃገራት አሉ እኛ ግን ምን ነክቶን ነው የአባቶቻችን ልጆች መሆን ያቃተን? እኔ በተለይ በት/ቤቶች እጅግ አፍራለው! ታሪኩን የማያውቅ፣ማንነቱን የናቀ ከንቱ ትውልድ ለመፍጠር ሲባዝኑ...ኧረ ጋይስ ዊ አር ኪሊንግ ኦወር ላንጉኤጅ ፕሊስ ሌትስ ዎርክ ሃርድ...እንዴት እናስጠላለን!

  ReplyDelete
 39. ዳይሬክተሩም የልጂቱ ሥነ ጽሑፍ አማርኛ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ያስመዘገበውን ፈጣን ዕድገት ያሳያል ሲሉ ደሰኮሩ

  ReplyDelete
 40. The funny think on the other hand is that we simply have English speakers but who can little read and write. One might be surprised a student 8th and above grade who can't write and read English but talks fluently. For native English speakers that might be true since they learn it from their parent, for people like Ethiopian who consider English as symbol of their academic level but not write and read. Yet, there are other version of scholars who are recently emerging. These are non of the above. They can't speak, write, read but are lecturers in universities where English is medium of instruction. Ere yegna neger temtatual! Gudayun Dn Daniel endeweg biyakerbewum betam asasabi new. I am not concerned barely on the language but way of thinking. It is good if some body speaks any language perfectly. But minds should think critically. I suggest Dn Daniel and/or others to bring the issue (mind sets and move of Ethiopian thoughts) to a more public forum for debate.
  Some of you might understand Dn. Daniel article in different way for me however has little to do with Amharic language rather it implied where we are moving. Look he raised, inflation, 1 million birr today and after 35 years; how chat has become a concern, generation can't understand leave alone 100 and more years history but 35 years back, etc. Form it is beyond language degradation! Please let's have a serious forum on this issue. preferably, on public media, radio or TV. giving citizens change to comment in any forms; letter, telephone, in person, interview and so on. Where are we really moving?! Development?!! For a nation to develop it needs strong minds.

  Thank you Dn Daniel!

  ReplyDelete
 41. ዳይሬክተሩም የልጂቱ ሥነ ጽሑፍ አማርኛ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ያስመዘገበውን ፈጣን ዕድገት ያሳያል ሲሉ ደሰኮሩ

  lik ye EPRDF ayinetu astemari

  ReplyDelete
 42. betam konjo eyta newu amesegnalehu

  ReplyDelete
 43. It is good to speak one language without mixing with another and your concern is appropriate but you are worried about Amharic language while the people who speak Amharic are systematically mariginalized and paying too much just because they have happen to speak only Amharic in the "wrong" place.

  ReplyDelete
 44. thinks for your view....BY THE WAY WHO IS KILLING AMHARIC ,,,? I THINK THE RULING GUNTA IS THE FIRST ACCOUNTABLE GROUP FOR THIS ISSUE

  ReplyDelete
 45. Ariqo mayet endezih new. Yegil timihirt bet west yemederegut dergitoch ena betesebochachin englizgna yetenagere yaweqe adregew maseb kalaqomu yamaregna neger yasferal.

  ReplyDelete
 46. Dear all,

  You can't avoid a problem already created in the same way the problem has been crated! This is a quote from the famous scientist Einstein, Albert. I don't think that it has any worth to blame one or the other for any problem created in our country. Some body might do some thing wrong but can hardly be solved in same way that the wrong doer did. Best way is analyze the problem and try to solve if possible in opposite way that problem has happened. I also feel that better to use public forums for more universal solutions than singling out each issue of our mind. Human mind is dynamic. Can be changed with time and situation. one time so evil person might become most kind person. Please let's influence people to wards positive. Let's think first weather the message we are conveying here is from our own ego or not.  ReplyDelete
 47. በጣም የሚገርመው በወላይታ ዩኒቨርሲቲ 'የመምህራን እንግሊዘኛ ቋንቋ እንዴት እናሳድግ' በሚል ስልጠና ወቅት ከአንዳንድ መምህራን እንግሊዘኛ ብሔራዊ ቋንቋ እናድርግ የሚል ሀሳብ ተነስቶ ነበር።

  ReplyDelete
 48. ወይ ጉድ….ግርም እኮ ነው የሚለው የ ተለያዩ መስሪያቤቶች ስም በእንግሊዝኛ ቃላት በአማርኛ ፊደላትስ ተጽፈው አልገጠማችሁም?
  እኔ ለምሰራበት መስሪያቤት ከአንድ የመንግስት መስሪያቤት ደበዳቤ ተጻፈ ደብዳቤው ይመለከተኝ ነበርና ያመጡት ሴት ወደኔ ተመርተው ይዘው መጡ፡፡የደብዳቤው አድራሻ ማለትም የኛ መስሪያቤት አድራሻ የተጻፈው ግን በ አማርኛ እንግሊዝኛ ነበርና ቀና ብዬ ሰትዬዋን ምነው አማርኛ መጻፍ አቅቶ ነው? በዬ ብጠይቅ እኔ ምናውቄ ምሁራኑ ናቸው ብለውኝ እርፍ…የፈራሚውን መዓረግ ሳየው እንዴት እንዳፈርኩ?!….እንደው ምን ይሻለን ይሆን?

  ReplyDelete
 49. ዲ/ን ላመሰግንህ እፈልጋለሁ!! አሁን ብዙ ሳንርቅ ዩኒቨርሲቲ ላይ ለሙድ መሰለኝ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡
  ንጉስ ጫኔ ነኝ ከ ደ/ታቦር

  ReplyDelete

 50. ፈጣን ደብል ዲጂት ዕድገት

  ReplyDelete
 51. I would have preferred a sound represented in only 26 letters to some 7* 33 or 231 letters. I didn't have the privilege, but my child has. What then is the big deal...go find some work for yourself.

  ReplyDelete
 52. I couldn't agree more.I noticed it 10 years ago (when I was in high school) when news readers use some English words like "program"&"project" when it come to some words we get used to them so we think they are amharic.Since Deacon Daneil give us a wake up call we better start working on it.I don't think he wrote this b/c he needs admiration but to brainstorm together to find a solution.Let me share u mine and you can add idea#1Lets have weekly Amharic quiz that we share on FB #2Lets have amharic quiz compitition in youth clubs and sunday schools of all churches(orthodox,Protestant,Catholic&Muslims)b/c this is not some thing religious but national...this is my personal Idea if you agree am more than happy to join
  P.S when I say You it means the whole audience not only Deacon Daneil


  Fiker

  ReplyDelete
 53. Ehe document chelemtegninet yetayebet yimesilegnal. yefelege bihon Amarignachin be mechiwoch 30 ametat edndi ayhonim. Bihonim ye diber yelesh yenigd sirat tesemo gin endemaykad ergetegna negn.

  ReplyDelete
 54. i'm afraid in z future, no one see & understand zis uncustomed habit.including me. but we should aware what things comes nxt if we're stand against our cultural,spritiual,countrial we're on z way 2 dead...

  ReplyDelete
 55. አንዳንድ ጊዜ ከአንባብያን የሚሰጠው አስተያየት ዓይንና ጀሮ ያለው አይመስለኝም፡፡ እሽ ዳንኤል እንደዚህ አድርጎ የመወያያ መነሻ አሳብ አፈለቀ አንባቢው ደግሞ የበሰለ አስተያየት መስጠት ሲገባው፤ አንዱ ብድግ ብሎ ከምን ስሜት እንዳመነጨው ባይታወቅም ልክ “ምናገባህ ” ሲል ሌላው ደግሞ “ዝምበል አንተ ” ዓይነት ነገር ሲያስተጋባ በጣም ያስቀኛል፡፡ ይህችን ዓይነቷ አመል አንድ ቀን ዕድል አግኝታ ወደ ስልጣን ሰትመጣ ልክ እንደእነንትና ዝምበል አትናገር እያለች እስር ቤት ትዶለናለች የሚል ስጋት ስላለኝ፤ የጠባይ ለውጥ እናምጣ እላለሁ፡፡
  እኔ ግን አልሰሜን ግባ በሉት ካላላችሁኝ በቀር ዳንኤል የአማርኛ ምቀኛ ሁኖ ተነስቷል ባይ ነኝ፡፡ ለመሆኑ ጥንታዊ ቋንቋችን ግዕዝ የጥንታውያን ቋንቋዎች ድምር እናዳለበት የምታውቁ ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ የኢብራይስጥ፣ የግሪክ፣ የዓረበኛ እና የሌሎችም፡፡ ምናልባት ከባቢሎን ግንብ በፊት የነበረው ቋንቋ ግዕዝ ነበረ ስለሆነም ግዕዝ ሳይሆን ወራሹ ግዕዝ ነው ተወራሹ የሚል ዓይነት ጥናት ካልቀረበልን በቀር፡፡
  ግዕዝ ምንም እንኳ በምልአትም በጥንካሬም ከአፍሪቃውያ ወለድ ቋንቋዎች የደረጀ ሁኖ በዛሬው ዕድሉ የግቢ ውስጥ የተግባር ማኪያሄጃ ቢሆንም፤ የምልዓቱና የጥንካሬው ጀርባ ግን “ኮሌክቲቭ” መሆኑ ጭምር ነው እላለሁ፡፡ እንግሊዝኛን የወሰድን እንደሆን “ኮሌክቲቭ” እና ይህንንም ሁኔታ እንደመልካም ዕድል በመቁጠር በየቀኑ መዝገበ ቃላቱን ክፍት አድርጎ ሲደረጅ ሲመላ እናየዋለን፡፡ በእኔ ግምት አማርኛ በ2035 ዓ.ም በጣም ጠንካራ ቋንቋ ሁኖ ይወጣል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ምክንያቱም ከሁለትም ከሶስትመ ከአራትም ከዚህ በላይም ሰላሳ ዓመታት ጀምሮ በእንደዚህ ዓይነት መንገድ ስለተጓዘ፡፡ አብዛኞቻችን ከመወለዳችን በፊት በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ከአገር ውጭ ጋብቻዎቹ ጣሊያንኛውን፣ እንግሊዝኛውን፣ አረብኛውን፣ አብራይስጡን ወዘተውን፤ ከወላጁ ግዕዙን፤ ከአገር ቤት አገቡኞቹ ትግርኛውን፣ አገውኛውን ኦሮምኛውን ወዘተውን አቀላቅለን እንናገርበታለን፡፡ እያደገ ነው ይሉሃል ይህ ነው፡፡
  ምንአልባት ለእኛ (አሁን እየኖርን ላለነው) የማያስደስት ለዛ ሊመሰለን ቢችልም በዕድገት ጎዳና ላይ ነው እላለሁ፡፡ ለምሳሌ ዘብጥያ ከርቸሌ የሚሉትን ቃላት እንደየአገባባቸው ሲደመጡ ይቅርና ስንጠቀምባቸውም አይስተዋልም፡፡ ይሁን እንጅ በቋንቋ ውስጥ ህልውናቸው የምልዓቱን ሚዛን አስጠብቀው ይቀጥላሉ፡፡ ነገር ግን በእነርሱ ፋንታ መታሰር የሚለው ግስ እየተለዋወጠ በአውዱ ውስጥ በሚሰጠው ትርጉም እንረዳዋለን፡፡ ሆኖም በቅርቡ ምናልባት አስር ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ሌላ እነዚህን ተኪ ቃል በአንዳንድ አካባቢ ብቅ ብቅ እያለ ይሰማል፡፡ ሸቤ! አንዳንዶቻችንን ዛሬ ያስቀናል፡፡ ይህ ቃል ግን እያሸነፈ የማይሄድበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ እንደ”ኬር-ዳሽ”…፡፡ እና ምንችግር አለው? በዛልን ነው የሚባለው!
  ከዚህ ባለፈ ግን ለዚህ ሁሉ ነገር የኃይል ትብብር የምንጠይቅ ከሆነ፤ አሁን አንዳንድ ልናስወግዳቸው የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለማሳካት የማያስችል የኃይል ብክነት ውስጥ እንዳንገባ እሰጋለሁ፡፡ ፍልስፍናው፣ እይታው፣ ትችቱ፣ ትንበያው፤ ያዝናናል፣ ያስቃል፣ ትንቢቱ ከተፈጸመም ነቢዩ ዳንኤልን ያንጊዜ መሾም፣ ካልተፈጸመም ጠላቱ እልም ይበልና እርሱም እስከዚያ ጊዜ ስለሚደርስ ሐሰተኛውን ነቢይ በድንጋይ ወግረህ ግደል ይላል፤ ከሞላው ሐሰተኛ ነቢይ ሁሉ እርሱን ብቻ መቀጣጫ እናደርጋለን፡፡ ምናልባት አንዳንዶቻቻን ከሰላሳ ዓመት በኃላ የሚመጣው የቋንቋችን ግስቁልና ከምር ማሳሰብና ማበሳጨት ከጀመረን - የፈለገው ቢሆን ወደእንስሳነት ተመልሰን በሰውልጅ ቋንቋ ወደማንግባባበት እንደማንገባ ከወዲሁ ተንብያለሁ!
  ዳንኤል ዘጣና ዳርን እረጅም ዕድሜ ይስጥልኝ!
  ከጣና ዳር፡፡

  ReplyDelete
 56. በርግጥ እዉነት ነዉ፡፡ ይህ አይሆንም አይባልም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን አሁን ብዙ ነገር ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ሲተላለፍ እንደመጣ ሁሉ እኛም ሃለፊነት አለብን የተቀበለነዉን ለአሁኑ ተዉልድም ቢሆን ለሚመጣዉ ማሰወቅ ይኖርብናል፡፡ ስለዚህ ከሁን ጀምሮ ጀኔረሽኑን ማሰተማር፣ማሳወቅ ይኖርብናል ብዬ አስባለሁ፡፡

  ReplyDelete
 57. ዋተር ነፍ ነው፣ ኦፕን ኤይር ነፍ ነው፣ ሰን ሴትና ሰን ራይዝ ነፍ ነው፡፡ ማዩንቴይን ነፍ ነው፤ የሚደብረው ነገር ሮዶቹና ቪሌጆቹ ምልክት የላቸውም፡፡

  ReplyDelete
 58. I think it is better if the alphabet of amharic is changed to latin. I beleive oromic and other southern languages are developing within few years because they used latin alphabet which is suitable for computers(internet etc). And it is undeniable that the growth of other ethiopian languages weakens amharic. so restricting other language in informal way may hasten the development of our language Amharic, since it is national language.

  ReplyDelete
 59. betam yemiyasazin neger new sew endet maninetun yiresal? englizigna menager yakoral ende?yerasin kalaweku yesew min yiseral?"yesew werk ayademk" new negeru

  ReplyDelete