<ዕሩቅ ብእሲ> በግእዙ ሰው ብቻ፣ ሥጋ ብቻ፣ የተራቆተ፣ ምንም ነገር የሌለው
እንደ ማለት ነው፡፡ ቃሉ ከነገረ መለኮት ትምህርት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ አይደለም፣ ሥግው ቃል
አይደለም፣ ሰው ብቻ ነው የሚለውን ትምህርት ለመቃወም በተሰጡ ትምህርቶች ላይ ነው ቃሉን የምናገኘው፡፡ እዚህ ግን ሌላ ትርጉም
ነው የምንሰጠው፡፡ ‹ዕሩቅ ብእሲ› ምንም ነገር የሌለው፣ ሥጋ ብቻ ያለው ሰው፣ ሌላ አንዳች ነገር ያልተዋሐደው፣ እንዴው ሥጋና
ደም የሆነ ሰው ማለታችን ነው፡፡
ዕሩቅ ብእሲ የራሱ የሆነ ሞያ፣ ሞራል፣ ሀብት፣ ጸጋ፣ ክብር፣ ዝና የለውም፤ ዕሩቅ
ብእሲ ራሱን ችሎ አይቆምም፣ እንደ ሐረግ መደገፊያ፣ እንደ እንሽላሊት መታከኪያ ይፈልጋል፡፡ እንደ ሙጫ መጣበቂያ እንደ አልጌ
መሸሸጊያ ይሻል፡፡ እንደ ገደል ማሚቱ የሚያስተጋባው፣ እንደ በቀቀን የሚቀዳው ነገር ይፈልጋል- ዕሩቅ ብእሲ፡፡
ዕሩቅ ብእሲ ማነህ? ሲሉት ‹ፈረስ አባቴ ነው› ይላል፣ ስሙን ሲጠይቁት እገሌ ዘመዴ
ነው፣ ይላል፣ ሲተዋወቁት እገሌንኮ ዐውቀዋለሁ ብሎ ይተርካል፣ የሚኖርበትን ቤት ከጠየቁት እገሌ የተባለው ሰው ቤት ውስጥ ቤተኛ
መሆኑን ይናገራል፣ ቀበሌውን ከጠየቁት ቀበሌ የሚያውቀው ባለ ሥልጣን መኖሩን ያወራል፤ የተማረበትን ከጠየቁት ስለሚያውቀው ምሁር
ይዘረዝራል፣ የሚሠራበትን ከጠየቁት የሚያውቃቸውን መሥሪያ ቤቶች ይናገራል፡፡ ያነበበውን ከጠየቁት የተዋወቃቸውን ደራሲዎች ስም
ያቀርባል፡፡ የሄደበትን ሀገር ከጠየቁት የሚያውቃቸውን የውጭ ዜጎች ይደረድራል፡፡ ስለ ሀብቱ ከጠየቁት እገሌና እገሌ የተባሉ
ሀብታሞችን እንደሚቀራረብ ይደሰኩራል፡፡ ካነበበው ጋዜጣ ይልቅ በተዋወቃቸው ጋዜጠኞች ይኩራራል፤ ከተመለከተው ፊልም ይልቅ
እጃቸውን በጨበጣቸው ተዋንያን ይጎርራል፤ ከተሳለመው ቤተ ክርስቲያን ይልቅ ስልካቸውን በመዘገባቸው ሰባክያንና ዘማርያን
ይደሰታል፡፡ ስለገዛው መኪና የሚያወራው የለውም፤ መኪና ስለገዙ ሰዎች ግን ብዙ ነገር ይላል፡፡ ሳይጠራ ይመጣል፣ ሳይመደብ
ያስተናግዳል፣ ሳይመረጥ ኮሚቴ ይሆናል፡፡ ሳይታሰብ ቤተኛ ይሆናል - ዕሩቅ ብእሲ፡፡
ለዕሩቅ ብእሲ የተለያዩ ስብስቦች በጣም ይመቹታል፡፡ ራሱን ከማጋለጥ
ይታደጉታልና፡፡ለራሱም የሚለጥፈው ስም ያገኛል፡፡ ዕሩቅ ብእሲ በገዥው ፓርቲ ውስጥ አለ፤ በተቃዋሚውም ውስጥ አለ፡፡ ገዥው
ፓርቲ ውስጥ ያለው ዕሩቅ ብእሲ ርዕዮትም፣ ዓለምም የሌለው ነው፤ ብቃትና ችሎታ በጎኑ ያላለፈ ነው፤ መፍጠር አይችልም፣
ማነብነብ ግን ተክኗል፤ መምራት አይችልም፣ ለማጀብ ግን ማንም አይችለውም፤ መሥራት አይችልም፣ ለመሞዳሞድ ግን ነፍስ ነው፤
ለፓርቲው ምንም አይሠራም፣ በፓርቲው ግን ይሠራል፤ የፓርቲው ፕሮግራም አይገባውም፣ ስለ ፓርቲው ፕሮግራም ግን ከእርሱ በላይ
የሚያወራ የለም፤ ስለ ፖሊሲው አያውቅም፣ ሁሉንም አመራሮች ግን ያውቃል፤ ወደ ፓርቲው አልቀረበም፣ ወደ ጥቅሞቹ ግን በጣም
ተጠግቷል፡፡ በራሱ ስም መቆም ስለማይችል በፓርቲው ስምና በባለ ሥልጣናቱ ስም ይነግዳል፡፡ የሚያውቀውን ሳይሆን የሰማውን
ያወራል፡፡ ድሎትን የሚመገብበት ሆድ እንጂ መከራን የሚችልበት ትዕግሥት ስለሌለው ለድግሱ ከፊት ለሰማዕትነቱ ግን ከኋላ ነው
የሚሰለፈው፡፡
ዕሩቅ ብእሲ ወደ ገዥው ፓርቲ የሚመጣው ዓለማው ፖሊሲው፣ ስትራቴጂው ገብቶት፣
በርዕዮተ ዓለሙ ተስማምቶ፣ በዚህ መሥመር ታግዬ ለውጥ አመጣለሁ ብሎ አይደለም፡፡ ጥገት ላም ላገኝ እችላለሁ ብሎ እንጂ፡፡
በራሱ መንገድ፣ በራሱ ችሎታ፣ ከሌሎቹ ጋር ተወዳድሮ፣ በራሱ ተራምዶ፣ በራሱ ታግሎ ለመጓዝና ያሰበበት ለመድረስ ዐቅም የለውም፣
ልብም የለውም፣ ትዕግሥትም የለውም፡፡ ስለዚህ የተሻለው አማራጭ መጠጋት ነው፡፡ ሲጠጋ የፓርቲው ‹የስሙ ቀዳሽ የክብሩ ወራሽ›
ይሆናል፡፡ የፓርቲውን ስም ለስንፍናው መደበቂያ፣ ለድክመቱ መሠወሪያ፣ ለዐቅመ ቢስነቱ ማገሚያ ያደርገዋል፡፡ ቀጥ ብሎ መቆም
የማይችለው ሐረግ፣ በብዙ ቋሚዎች መካከል ይገባና የቆመ መስሎ ይታያል፡፡
የፓርቲ ሽፋን ባያገኝ ኖሮ በዕውቀቱ ማን ይሾመው ነበር? በየት ተወዳድሮ የውጭ ዕድል
ያገኝ ነበር? በምን ዐቅሙ ቤትና መኪና፣ ክብርና ዝና ያገኝ ነበር? ‹ቅዳሴው ቢያልቅበት ቀረርቶ ሞላበት› እንደሚባለው
‹ዕውቀትና ችሎታ ቢያልቅበት አባልነት ሞልቶበት ነው እንጂ፡፡ ‹ዓሊ ለተዳረ ሲራጅ በግ አረደ› እንዲሉ ሌሎች በታገሉ፣ ሌሎቹ
በደሙ፣ ሌሎች ሌት ተቀን በለፉ፣ ዕሩቅ ብአሲ ተቀለጣጥፎ እፍታ እፍታውን ይወስደዋል፡፡ እርሱ እቴ ከመታወቂያው እንጂ ከትግሉ
የለበትም፡፡
ዕሩቅ ብእሲ በተቃዋሚው ውስጥም አለ፡፡ መቃወም እንጀራው የሆነ፡፡ ከአንዱ ፓርቲ
ወጥቶ ወደ ሌላው ፓርቲ ሰይጣን እንዳሳተው መነኩሴ በኣት ሲለውጥ የሚኖር፤ ከኮሚኒስትነት ወደ ሶሺያሊስትነት፣ ከሶሺያሊስትነት
ወደ ሊበራልነት፣ ከሊበራልነት ወደ አብዮታዊነት ሲቀያየር፣ ከኅብረ ብሔር እስከ ብሔር፣ ከብሔር እስከ ብሔረ ሰብ፣ ከብሔረ ሰብ
እስከ ጎሳ ፓርቲ ሲገባና ሲወጣ ስቅ የማይለው፡፡ በሄደበት ሁሉ ወይ ሊቀመንበር፣ ወይ ጸሐፊ፣ ወይ የፖሊት ቢሮ፣ ወይ ማዕከላዊ
ኮሚቴ፣ ወይ ሥራ አስፈጻሚ፣ ወይ ኦዲት ኮሚሽን፣ ወይ ቃል አቀባይ እንደሆነ የሚኖር፡፡
የተቃዋሚው ጎራ ውስጥ ባይኖር ኖሮ፣ ራሱንም ‹ተቃዋሚ› በሚባል የንግድ ምልክት ውስጥ ባይከትት ኖሮ ማንም ሊሰማው፣ ሊያየው፣ ሊመርጠው
የማይችል ነው- ዕሩቅ ብእሲ፡፡ ጋዜጣ ላይ ለመውጣቱ፣ ሬዲዮ ላይ ለመቅረቡ፣ የውጭ ዕድል ለማግኘቱ፣ መግለጫ ለመስጠቱ ዋነኛው
ምክንያት ተቃዋሚ መሆኑ ብቻ የሆነ፡፡ ስለ ዕውቀቱ፣ ስለ ብስለቱ፣ ስለ አመራር ክሂሎቱ፣ ስለ ትግል ስልቱ፣ ስለ አእምሮ
ምጥቀቱ ተብሎ ሊነገርለት የማይችል፣ የህልውናው ምንጭ ተቃዋሚነት የሆነ ነው- ዕሩቅ ብእሲ፡፡ እነዚህ አነስተኛና ጥቃቅን
ፓርቲዎች ባይኖሩ ኖሮ እርሱን ማን ሊቀ መንበር ያደርገው ነበር?
ለዕሩቅ ብእሲ ማኅበራት ምቹ ናቸው፡፡ በራሱ ሠርቶ፣ በራሱ መታወቅ ለማይችለው ዕሩቅ
ብእሲ አንድ ቀን ስብሰባ ላይ መጥቶ በአፈ ጮሌነት ለመመረጥና ወንበር ለመያዝ ይመቹታል፡፡ እኔ እንዲህ ነኝ ማለት ስለማይችል
እኔ የዚህ አባል ነኝ፣ የዚህ ሰብሳቢ፣ የዚህ ዋና ጸሐፊ፣ የዚህ አመራር የሚለውን ካባ ይደርበዋል፡፡ ከዚያ ውጭ ህልው
ስለማይሆንም ካባውን ላለመገፈፍ ይሟሟታል፡፡ ለእርሱ ማኅበር የመሥሪያ ቦታ አይደለም፤ በኅብረት የማገልገያ መንገድም
አይደለም፡፡ ለእርሱ ማኅበር ካባው ነው፡፡ ‹ዕሩቅ ብእሲ› ዎች የሞሉበት ማኅበር መጀመርያ በዓላማ ይቋቋምና በኋላ ዓላማውን
ረስቶ ማኅበሩ ብቻ ይቀራል፡፡
ዕሩቅ ብእሲ ‹ዕሩቅ› ነውና ምንጊዜም ሽፋን ይፈልጋል፡፡ ዕራቁቱን መሆኑን ያውቀዋልና
እንደ አዳም በለስ ውስጥ ገብቶ መሸሸግ አለበት፡፡ ሀብታም እንደማይሆን ለራሱ ያሳምንና የሀብታም አጫዋች ይሆናል፡፡ ሲስቁ
ይስቃል፣ ሲሸታቸው ያስነጥሳል፣ ሲበሳጩ የርሱ ጨጓራ ይነዳል፤ ሲያማቸው እርሱ መርፌውን ይወጋል፤ ያልሆኑትን ነዎት ብሎ፣
ያልሠሩትን ሠሩት ብሎ፣ የሌላቸውን ሰጥቶ፣ ከሰው ተራ አውጥቶ ከመላእክት ተራ ይከታቸዋል፡፡ የእገሌ ጋሻ ጃግሬ፣ የእገሌ ቀራቢ
እንዲባል ያደርጋል፡፡ የሚቀጥርበት ድርጅት የለውም አስቀጥራችኋላሁ ብሎ ግን ይጎርራል፣ የሚሰጠው ገንዘብ የለውም አሰጣችኋላሁ
ብሎ ግን ይሰበስባል፤ የሚያወራው ነገር የለውም እገሌ እንዲህ ሲል ከጎኑ ነበርኩ ብሎ ግን ይዘባነናል፡፡ ሴቶችን ወደራሱ መሳብ
እንደማይችል ያውቃል፣ ወደ ሚሳቡበት ግን ያስጠጋል፡፡
ዕሩቅ ብእሲ ብዙ ታዋቂ ሰዎችን ይቀርባል፡፡ እርሱን የሚያውቀው አያገኝም፤ በታዋቂዎች
ደረት ላይ ልጥፍ ብሎ ግን ትንሽ መታወቅን ቆረስ ያደርጋል፡፡ ከታዋቂዎች ጋር የተነሣው ብዙ ፎቶ አለው፡፡ ስለ ታዋቂዎቹ ሲነሣ
ያንን እየመዠለጠ ‹እርሱማ ወዳጄ ነው፣ እርሱማ አብሮ አደጌ ነው፣ እርሱማ ጓደኛዬ ነው፣ እርሱማ በእጄ ነው፣ ከእርሱ ጋርማ
ሁሌ ነው የምንገናኘው› ይላል፡፡ ካስፈለገም ሞባይሉን መዥረጥ አድርጎ ‹ልደውልለት› ይላችኋል፡፡ ዕሩቅ ብአሲ የግብዣ ወረቀት
ከየትም ብሎ አያጣም፡፡ ወረቀቱን ከታተመበት ዓላማ በላይ የሚጠቀምበት ጋባዡ ሳይሆን ዕሩቅ ብእሲ ነው፡፡ ለርሱ የታላቅነቱ
ምንጭ ነው፡፡፡ ‹ቀላል አይደለሁም› ለማለት ወጣ አድርጎ ያሳያችኋል፡፡ ወይም ልክ በአጋጣሚ እንዳደረገው አድርጎ ጠረጲዛችሁ
ላይ ጣል ያደርገዋል፡፡ ሌላ የሚያወራው ቁም ነገር የለውማ፡፡
ዕሩቅ ብእሲ በእምነት ተቋማትም ውስጥ ሞልቷል፡፡ ውስጣቸውን የማያጠሩ፣
ለአገልጋዮቻቸውና ለተከታዮቻቸው ጥብቅ መመዘኛ የሌላቸው፣ ለንጽሕናና ቅድስና ትኩረት የማይሰጡ፣ ጠባቡን በር ያሰፉ የእምነት
ተቋማት የዕሩቅ ብእሲ መሸሸጊያ ናቸው፡፡ ዕሩቅ ብእሲ እዚያ የሚሄደው አምኖ ለመጽደቅ፣ ተጋድሎ ድል ለማድረግ፣ አገልግሎ
በረከት ለማግኘት፣ በጎ ሠርቶ ዋጋ ለመቀበል አይደለም፡፡ የሃይማኖትን ሽፋን ለማግኘት እንጂ፡፡ ድክመቱን፣ ዐቅመ ቢስነቱን፣
አላዋቂነቱን፣ ስንፍናውንና ጎደሎነቱን ታግሎ ከማሸነፍ ይልቅ የሃይማኖት ስም ይሰጠዋል፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲታረም፣
እንዲስተካከልና እንዲሞረድ ሲነግሩትም ‹የዚህ እምነት ተከታይ በመሆኔ ነው› የሚል ታርጋ ይለጥፍለታል፡፡
አንዳንዱ ሰው ሰባኪ ባይሆን ኖሮ ምን ይሆን ነበር? ዘማሪ ባይሆን ኖሮ ምን ይሆን
ነበር? አገልጋይ ባይሆን ኖሮ ምን ይሆን ነበር? ለመሆኑ ዓለምን ንቆ ነው ወይስ ዓለም ንቃው? ዕሩቅ ብእሲ ዓለምን አይንቅም፤
ዓለም ግን ትንቀዋለች፡፡ ዕሩቅ ብእሲ ዓለምን በቤተ እምነት ውስጥ ይፈልጋታል፡፡ ዕሩቅ ብእሲ ቤተ እምነቱ መዳኛው ሳትሆን
እንጀራው ናት፡፡ ‹አብላ› የሚለውን ሕግ ‹ብላ›፣ ‹አጠጣ› የሚለውን ሕግ ‹ጠጣ›፣ ‹እርዳ› የሚለውን ሕግ ‹ተረዳ›፣ ‹አክብር›
የሚለውን ሕግ ‹ተከበር›፣ ስጥ የሚለውን ሕግ ‹ተቀበል› ብሎ የሚተረጉመውም ለዚህ ነው፡፡ እርሱ ወደ ቤተ እምነቱ መጥቷል
እንጂ ወደ እግዚአብሔር አልመጣም፡፡ ቀርቧል እንጂ አልገባም፡፡
ዕሩቅ ብእሲ በየመሥሪያ ቤቱም አለ፡፡ እንደምንም ብሎ እዚያች ቦታ ተቀጥሯል፡፡
ከዚያች ከወጣ ግን መውደቂያ የለውም፡፡ የሚተማመንበት ዕውቀትም፣ ችሎታም፣ ብቃትም፣ ክሂሎትም፣ ሞራልም፣ ትጋትም የለውም፡፡
ስለዚህ ያችን ወንበር መልቀቅ የለበትም፡፡እርሷን ላለመልቀቅ ሁን ያሉትን ሁሉ ይሆናል፡፡ እሺም ይላል፣ እምቢም ይላል፡፡
ሳያምን አንገቱን ይነቀንቃል፣ ሳይገባው ያጨበጭባል፣ ሳይመለከተው ሃሳብ ይሰጣል፣ ሳይረዳው ቃል ይገባል፣ የእርሱ ዓላማ ኮከብ
ሠራተኛ መባል አይደለም፤ የእርሱ ዓላማ በባለ ሥልጣናቱ ፊት ሞገስ ማግኘት ነው፡፡ ይህን ካረጋገጠ በቃው፡፡
ዕሩቅ ብእሲ ዕውቀት ከመጨመር መዓርግ መጨመር ይወዳል፤ ዕሩቅ ብእሲ ከስሙ ይልቅ
ዝነኛው፣ ታዋቂው፣ ታላቁ፣ ቅዱሱ፣ ምርጡ፣ የሚለው ቅጽል ያስደስተዋል፡፡ ዕሩቅ ብእሲ የሥራ ስሞችን ሁሉ የመዓርግ ስሞች
አድርጓቸዋል፡፡ ተማሪ፣ አርሶ አደር፣ አርቲስት፣ ድምጻዊ፣ ጋዜጠኛ፣ ገጣሚ፣ ኢንቨስተር፣ ወዘተ መዓርግ የሆኑት ዕሩቅ ብእሲ
አስገድዷቸው ነው፡፡ ዕሩቅ ብእሲ በሚዲያ እንዴት እንደሚቀርብ ምን እንደሚናገር አይጨነቅም፡፡ ውስጡ አንዳች የለምና ‹እ እ እ›
እያለ ማዜም ነው፡፡
ዕሩቅ ብእሲ ብቻውን ሊቆም የማይቻለው፣ መደበቂያ የሚያስፈልገው፣ መንጠላጠያ የሚሻ፣ መመሠጊያ የሚፈልግ፣ መደገፊያ የሚቧችር፣ በሌላው ጌጥ የሚያጌጥ፣ በሌላው ትጋት የሚያተርፍ፣ በሌላው ስም
የሚመካ፣ ውስጡን በውጩ የሚደብቅ አስገራሚ ፍጡር ነው፡፡ የሌለበት ቦታ የለም፤ የሌለበት ፓርቲና ድርጅት፣ እምነትና ተቋም፣ ማኅበርና
ስብስብ የለም፡፡ ዕሩቅ ብእሲ - ያው ተንጠላጥሎና፣ ተከልሎ፣ ያው በሰው ትከሻ ላይ ሲራመድ፣ ያው በጀግኖች መካከል ተደብቆ፣ ያው
ተለጥፎና ተጣጥፎ ይታያል- ያው!
ሰላመ እግዚአብሄር ይብዛልህ ዳኒ እንደምን ከረምክ እንደውምን ልበልህ የልብ አውቃ ከማለት በቀር ያልከው ሁሉ እውነትነው ባንተላይ ምን መጨመር ይቻላል እንደው ልብይስጣቸው ራሳቸውን ዞርብለው ለማየት ማንነታቸውን ለመፈተሽ አናቸውን ያብራላቸው ከማለት በቀር ዳኒ እድሜና ጤናውን ከነቤተሰብህ የማያልቅበት አምላክ ያስጣችሁ ስራህን ይባርከልህ አሜን
ReplyDeleteመልካም እይታ ነው እግዚአብሄር ባለህበት ይጠብቅህ
ReplyDeleteDn. Dniel,
ReplyDeleteThank you for sharing your views. It is well done. As you sad,there are so many people with "double face", where always awaking the society. I think we should be careful about them since they spoil our environment.
I have ssome fewcomments on the article:
1. I think the title is not perfeclty matching with the content since most of us know the thing from the religious point of view. For the future better to take care of similar things.
2. In one or two parapgraphs, you should say something how we prevent ourseleves or the community from these people.
God bless you and your beloved family!
Kebede
Megbiyaw lay yalewun mabrarya bedenb kanebebkew tesmami title mehonun tigenezebaleh
Delete@ Kebede, good comment especially the first one, i like it, and thank you Dani, for sharing such wonderful views.
DeleteWondime beselam new indih yemititsifew?
ReplyDeletewaw amazing article Good views "erukebesi" like a satanic he is live in everywhere God can be save from this satanic (erukebesi).God please save Ethiopia from erukbesi
ReplyDeleteዕሩቅ ብእሲ በተቃዋሚው ውስጥም አለ፡፡ መቃወም እንጀራው የሆነ፡፡ ከአንዱ ፓርቲ ወጥቶ ወደ ሌላው ፓርቲ ሰይጣን እንዳሳተው መነኩሴ በኣት ሲለውጥ የሚኖር፤ ከኮሚኒስትነት ወደ ሶሺያሊስትነት፣ ከሶሺያሊስትነት ወደ ሊበራልነት፣ ከሊበራልነት ወደ አብዮታዊነት ሲቀያየር፣ ከኅብረ ብሔር እስከ ብሔር፣ ከብሔር እስከ ብሔረ ሰብ፣ ከብሔረ ሰብ እስከ ጎሳ ፓርቲ ሲገባና ሲወጣ ስቅ የማይለው፡፡ በሄደበት ሁሉ ወይ ሊቀመንበር፣ ወይ ጸሐፊ፣ ወይ የፖሊት ቢሮ፣ ወይ ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ ወይ ሥራ አስፈጻሚ፣ ወይ ኦዲት ኮሚሽን፣ ወይ ቃል አቀባይ እንደሆነ የሚኖር፡፡
ReplyDeletekkkkk...ay dani! mechem nebsih ayimarim....sile zer botelika woqash honeh meTah degmo? ....kkkkkk gud eko new... tinfash kalwoTa tinish yigermal yilalu abew siterku
Ayyy kibrom wolday
Deletetsihufu anten silemineka new aydel?
Dear Danial
ReplyDeleteI really enjoy reading this article. In fact my reading of the article was right after I watched a you-tube clip about Azeb Mesfine speech at EPRDF meeting regarding her late husband. I really saw such nature on that Azeb Mesfine video clip but also I can see such nature on the collective nature of the rolling party. All the propaganda, visionary leader, hedasa gedebe... it is really "eruqe system",,
All the propaganda, visionary leader, hedasa gedebe... it is really "eruqe system",,ha ha ha ho ho ho
Deleteአንዳንድ ጊዜ ሳስብህ ግርም ትለኛለህ:: እግዚአብሔር በኪነጥበቡ
ReplyDeleteሁል ጊዜ ሹክ የሚል ነው የሚመስለኝ:: አርሱ አንዲ በረከቱን ችፍፍ
አድርጎልህ እየዛክ አየዛክ ለታዳሚያኑ በአፍ በአፉ ስትመግበው
የማያልቅብህ በሁሉም ዘርፍ ጠልቀ የምትገባና በአጉሊ መነጥር
የምትመለከትና ለታዳሚዎች አንደ ጅረት እንዲፈስ የምታደርግ ትልቅ
መምህር ነህ ::እግዚአብሔር ጤናና ዕድሜ አንዲሰጥልን አንለምነዋለን
የእግዚአብሔር ችሮታው ረድኤቱ ብዙ ነውና የምታያቸው አይታዎች
ለፍሬ በቅተው ብዙሃኑ አፎይ ተመስገን አንዲል እግዚአብሔር ይርዳን
ቃለ ሕይወት ያሰማልን መምህር ዳንኤል
Amen
DeleteAmen
Deleteamen
Deleteamen
Deleteወንድም ዳኒ ገዢው ፓርቲ አድርባይነትን አጸዳለሁ ብሎ ከተነሳ በህዋላ የተጻፈ በመሆኑ እጅግም አልመሰጠኝ:: እየተከተልን ከመጻፍ ቀደም ብንል አስተማሪነቱ የጎላ ነው የሚል እምነት አለኝ:. አይመስልህም ? በተረፈ እግዚአብሄር ካነንተ ይሁን ፤ እግዚአብሄር ይባርክህ ፡፡
ReplyDeleteDn. Daniel,
ReplyDeleteyou did a good job here. you gave us a good detail and clear meaning of the current regime's term,"aderbynet." i am sure most people will understand what does it mean "aderbyenet." yes, indeed our country is filled with this kind of people on the leadership place and they are dragging the people and the country to the ditch. our country needs enlighted writers like you to show us the right and the wrong. May God bless you and your family
ehhhhhh,
ReplyDeleteIt is all about us, not for an ideal person. One way or in the other, it is all about us: the writer and the reader, the speaker and the listener, the actor and those who support this actor, the members of the political party who nominate this actor as their chair person, the religious group who nominate this actor as their preacher, .... all of these groups are addressed within this article as a "ERUK B'ESI". This is because, as my thought, this actor can't exist without the support of the others, one can't exist without the other. They are complementary.
Thanks for Daniel,
Sisay
ዕሩቅ ብእሲ ዓለምን በቤተ እምነት ውስጥ ይፈልጋታል፡፡ ዕሩቅ ብእሲ ቤተ እምነቱ መዳኛው ሳትሆን እንጀራው ናት፡፡ ...................እግዚአብሄር ባለህበት ይጠብቅህ!!!!
ReplyDeletehulunim yedabesikewu and aquam lalemeused yimeslal. ye gileseboch tigat yeqomuletin alama ayasimeseginewum. letifat yekome lett teken yemitega, abejeh eseyi ayasbilewum.
ReplyDeleteI like your article but you need to stand clear. You can not justify faulty objectives based on individuals dedication and knowledge. You need to denounce the whole rather than picking on parts.
Ameseginalehu
A nice article
ReplyDeleteዲ/ን ዳኒኤል መልካም እይታ ነው እግዚአብሔር ያበርታህ
ReplyDeleteስለ እሩቅ ብእሲ አነበብኩ፡፡ ሁሌም እንደማደርገው ፅሁፎችን ሳነብ መጀመሪያ መፈተሽ የምጀምረው እኔን ነው፡፡ እያንዳንዱ ቤቱን ካፀዳ አካባቢው ሁሉ ይፀዳል ተብሎ የለ፡፡ ፅኁፍ ሳነብ ይሄ ለእነ እከሌ ጥሩ ነው ብዬ ሳይሆን ለኔ ጥሩ ነው ብዬ ነው፡፡ ሣየው ሳላውቀው ይሁን አውቄ አንዳንዱ ነገር አለብኝ፡፡ ትላንት አምርሬ ስጠላው የነበረውን ዛሬ ወድጄዋለሁ፡፡ ትላንት መሬት መሸጥ መለወጥ አለበት ብዬአለሁ፣ ዛሬ ደግሞ መሬት የህዝብና የመንግስት መሆን ነው ያለበት ብዬአለሁ፡፡ ትላንት ከድህነት የሚያወጣን ሊበራል ኢኮኖሚ ነው ብያለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ በኢኮኖሚ ውስጥ የመንግስትን ጣልቃ መግባት እደግፋለሁ፡፡ ትላንት መለስ ዜናዊን ጠልቼአለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ ወድጄዋለሁ ምነው ባላጣሁት ብዬአለሁ፡፡ የአባይ መገደብ የኢህአዴግን እድሜ ማራዘም ነው ብዬ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ አባይ በምንም አይነት በአጭር ጊዜ ካልተገደበ በድህነት እንደጠወለግን እና ዘላለም እንደለመንን እንቀራለን ብዬአለሁ፡፡ ዛሬ ላይ ደግሞ የአባይ ካድሬ ከዚያም በላይ ሆኜአለሁ፡፡ ትላንት እነ ማህሌትን ካለገኘሁ አለም የምትደፋብኝ መስሎኝ ጮኬአለሁ፡፡ አብጄ ትምህርቴን አቋርጬአለሁ፡፡ ዛሬ እነ ማህሌት በጨው ጣፍጠው ቢቀርቡልኝም አልቀምሳቸውም፡፡ ትላንት አሜሪካ ሄጄ ሙትት ባልኩ ብዩአለሁ፡፡ ዛሬ አሜሪካንን አይደለም የትም ሀገር ብዞር ሞቴን አልመኝም፡፡ እርግጥ ነው መደገፊያ ዛፍ እንደሚፈልግ ሀረግ ራሴን ችዬ መቆም አያቅተኝም፡፡ ተቃዋሚ ጥሩ ሃሳብ ካመጣ እና ለሀገሬ ከበጀ እቀበላለሁ እንጂ ለምን ከተቃዋሚ አፍ ወጣ ብዬ መራራ አላደርገውም፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን ጥሩ ከሰራ ጥሩ መጥፎ ከሰራ መጥፎ ከማለት ውጪ ስር የሰደደ ጥላቻ የለኝም፡፡ በመሰረቱም የሚያሳምን ሃሳብ ሲመጣ ሃሳብን ከሃሳብ ጋር ያለጥላቻ ተከራክሮ በሚያሳምን ሃሳብ ጋር መሄድ ቀድሞ የነበረ ሃሳብን መተው ትክክለኛ መንገድ እንጂ ሩቅ ብእሲ አያሰኝም ፡፡ ለመሆኑ እንዴት ታዩኛላችሁ? ስለ እሩቅ ብእሲ አነበብኩ፡፡ ሁሌም እንደማደርገው ፅሁፎችን ሳነብ መጀመሪያ መፈተሽ የምጀምረው እኔን ነው፡፡ እያንዳንዱ ቤቱን ካፀዳ አካባቢው ሁሉ ይፀዳል ተብሎ የለ፡፡ ፅኁፍ ሳነብ ይሄ ለእነ እከሌ ጥሩ ነው ብዬ ሳይሆን ለኔ ጥሩ ነው ብዬ ነው፡፡ ሣየው ሳላውቀው ይሁን አውቄ አንዳንዱ ነገር አለብኝ፡፡ ትላንት አምርሬ ስጠላው የነበረውን ዛሬ ወድጄዋለሁ፡፡ ትላንት መሬት መሸጥ መለወጥ አለበት ብዬአለሁ፣ ዛሬ ደግሞ መሬት የህዝብና የመንግስት መሆን ነው ያለበት ብዬአለሁ፡፡ ትላንት ከድህነት የሚያወጣን ሊበራል ኢኮኖሚ ነው ብያለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ በኢኮኖሚ ውስጥ የመንግስትን ጣልቃ መግባት እደግፋለሁ፡፡ ትላንት መለስ ዜናዊን ጠልቼአለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ ወድጄዋለሁ ምነው ባላጣሁት ብዬአለሁ፡፡ የአባይ መገደብ የኢህአዴግን እድሜ ማራዘም ነው ብዬ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ አባይ በምንም አይነት በአጭር ጊዜ ካልተገደበ በድህነት እንደጠወለግን እና ዘላለም እንደለመንን እንቀራለን ብዬአለሁ፡፡ ዛሬ ላይ ደግሞ የአባይ ካድሬ ከዚያም በላይ ሆኜአለሁ፡፡ ትላንት እነ ማህሌትን ካለገኘሁ አለም የምትደፋብኝ መስሎኝ ጮኬአለሁ፡፡ አብጄ ትምህርቴን አቋርጬአለሁ፡፡ ዛሬ እነ ማህሌት በጨው ጣፍጠው ቢቀርቡልኝም አልቀምሳቸውም፡፡ ትላንት አሜሪካ ሄጄ ሙትት ባልኩ ብዩአለሁ፡፡ ዛሬ አሜሪካንን አይደለም የትም ሀገር ብዞር ሞቴን አልመኝም፡፡ እርግጥ ነው መደገፊያ ዛፍ እንደሚፈልግ ሀረግ ራሴን ችዬ መቆም አያቅተኝም፡፡ ተቃዋሚ ጥሩ ሃሳብ ካመጣ እና ለሀገሬ ከበጀ እቀበላለሁ እንጂ ለምን ከተቃዋሚ አፍ ወጣ ብዬ መራራ አላደርገውም፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን ጥሩ ከሰራ ጥሩ መጥፎ ከሰራ መጥፎ ከማለት ውጪ ስር የሰደደ ጥላቻ የለኝም፡፡ በመሰረቱም የሚያሳምን ሃሳብ ሲመጣ ሃሳብን ከሃሳብ ጋር ያለጥላቻ ተከራክሮ በሚያሳምን ሃሳብ ጋር መሄድ ቀድሞ የነበረ ሃሳብን መተው ትክክለኛ መንገድ እንጂ ሩቅ ብእሲ አያሰኝም ፡፡ ለመሆኑ እንዴት ታዩኛላችሁ?
ReplyDeleteGood
DeleteDani , minalebet alfo alfo enkuan sile dogmawochachin sile haymanotachen bezih blog ematitsifew? Though I like your social issue notes, I always feel hunger to know about my religion from you.ewunet asbibet
ReplyDeleteዲ/ን ዳኒኤል መልካም እይታ ነው እግዚአብሔር ያበርታህ
ReplyDeleteI would like to hear your views about the current ethnic cleansing happening in the country. It is not politics. It is about humanity
ReplyDeleteManinetnen Mefetesha Tsihuf Nat Ena MEDEHANIALEM Tsegawin Yabizalih
ReplyDeleteየዕሩቅ ብእሲነት ምንጩ የእግዚአብሔር ብርሃን በሕይወት ውስጥ አለመኖር ነው። ሰው የተፈጠረውና በሕይወት የሚኖረው በእግዚአብሔር መጋቢነትና ጠባቂነት መሆኑን ሲዘነጋ ወይም እምነቱ ሲጠፋ በነገሮችና በሁኔታዎች ላይ ጥገኛ ይሆናል። ለንደዚህ አይነት ሰዎችም ልናዝንላቸውና እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ (ወደ ህይወት ጎዳና) ልንመራቸው ይገባናል፣ በጨለማ ውስጥ ያለ በጨለማ መሆኑን አያውቅምና !!! አምላክ ሰው የሆነበት ምክንያትም የጠፉ ነፍሶችን ለመማርክ ነውና እኛም እንደሱ እነኚህን የጠፉ ነፍሶችን ድክመታቸውን ከመናገር አልፎ እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ ተመለሱ ብለን መምከር ይገባናል። እግዚአብሔርን ማምለክ ጸጋንና ጥበብን ያላብሳልና !!!
ReplyDeleteየድንግል ልጅ አይለይህ ፣ ግሩም ነው። ዳኔ : ባልሳሳት መሸወድ የሜለው ቃል በተለይ በአንተ አስተምህሮና ጽሑፍ ቦታ ባያገኝ ደስ ይለኛል።
ReplyDeleteD/N Daniel betkikil yeneberw ena ayewn new yetsafkew betam tiru ena linebeb yemigebaw new Egziabhier Amelak edme tena yestih amen
ReplyDeletetiru melket new be ewent !hgru gen man smeto yekyerbtale nwe...ka ena gmero lemelwet fekadgnohe ayedelenem beha ant gen gedathen tewethale Egzabhare yabertahi!
ReplyDeleteit is good and educable thought but the title and the contents are d/t/ ruqebiese /for me just human being
ReplyDeletewhydont u right about the displesd peoples on the name of amhara ?
we are waiting for u /siletefenaqelu sile misqayu wogenochachin stafilin than u
yihun yidereglin
ReplyDeleteKe arestu wichi.hulu mulu new gashe......tinish degmo anzazahew malet 1 aynet hasabochin kemabzat mewchawin metekom betechale.eko ......bcha tebarek
ReplyDeleteዲ.ዳንኤል” እሩቅ ብእሲ” አልከው ግሩም፤ በፓርላማ ቋንቋ የድል አጥቢያ አርበኛ በጠበብቱ ጥራዝ ነጠቅ ፤በዘመኛው ባዶ ቢባል ያንሰው ይሆን እንጂ አይበዛበትም!
ReplyDeleteያም ሆኖ እባክህን በነካ እጅህ የህይወት “ የሆድ “ታሪካቸውን ፃፍና አስነብበን?
ምኞቴ ከፍሎሪዳ
there are so many people acquiring this type of behavior,so you put
ReplyDeletenice image to be know every body,god bless you.
there are so many people acquiring this type of behavior,so you put nice image to be know every body,god bless you.
ReplyDeletetiru new
ReplyDeletethis a perfect truth of human beings
ReplyDeleteAndualem H.M Tucson AZ,April 22,2013,7pm
ReplyDeleteDn.Daniel,you did agreat job in every angle for our society,you gave us agood detail and clear meaning of the "Eruqe Besi" this guys are dangerous for their loyalities too.
ዕሩቅ ብእሲ ብቻውን ሊቆም የማይቻለው፣ መደበቂያ የሚያስፈልገው፣ መንጠላጠያ የሚሻ፣ መመሠጊያ የሚፈልግ፣ መደገፊያ የሚቧችር፣ በሌላው ጌጥ የሚያጌጥ፣ በሌላው ትጋት የሚያተርፍ፣ በሌላው ስም የሚመካ፣ ውስጡን በውጩ የሚደብቅ አስገራሚ ፍጡር ነው፡፡
ReplyDeletethank you Dn.Dani
Great Looking Dn Daniel Thank you for sharing your views.
ReplyDeleteGreat views Dn Daniel
ReplyDeleteThanks for sharing your views
Just to ask im not sure በአለም መናቅ kemenfesawinet akuya endet tayutalachu??
ReplyDeleteጽድቅ ወይስ ኩነኔ?
ቃለ ሕይወት ያሰማልን መምህር ዳንኤል
ReplyDeleteምኞቴ ከፍሎሪዳ; SETANB/I BEMEGEMERIA ENE MEN MEHON ALEBEGN; MANEGEN; !!!!!!!!AMLAKE KENE MEN YEFELGAL!!!!!!!!!!! yemilewen aseb/asbi yalebelezia aygebahem/chem
Great as ever
ReplyDeleteስለ ሩቅ ብእሲ ለመጻፍ ያነሳሳህ መንፈስ ስለ ቅርብ ብእሲ እንዲያጽፍህ ምኞታችን ነው፡፡ ክብረት ይስጥልኝ፡፡
ReplyDeletebetam yasetemeral lawekebet
ReplyDeleteIt is very good insight and nice article as of usual. But I want to recommend those who write other stories here. I think the intention of Dani is to express individuals who have such kinds of bad behaviors and he want to teach them what the way they are going is not good and not likely by normal peoples. Read the article carefully and use it properly. Please don't talk about other issues here, which is not valuable for the readers and Dani too.
ReplyDeleteneed some design improvement.
ReplyDeleteWe need such type of updated and matured article!
ReplyDeletenice one !!!
ReplyDeletePlease say something about Jemanesh Solomon and her new religion!
ReplyDeleteArtist Jemanesh Solomon and her partners are polluting our religion: I expect you need to say something about it.
ReplyDeleteYou have told us what we are experiencing. Some of us are living an artificial life, which is full of hypocrisy.
ReplyDeleteThank you Daniel
Tewut bakachu dani anbesaw new.
ReplyDeleteከዚህ በፊት በሚሉት ሀረጋት አውቅ ነበር ነገር ግን በነት አላውቀውም።
ReplyDelete