Saturday, March 9, 2013

አባድሮች፣ እናመሰግናለንከሀገር ወጣ ብዬ የተለያዩ ሀገሮች ስዘዋወር ከምቀናባቸው ነገሮች አንዱ የደንበኞች አያያዛቸው ነው፡፡ ‹ደንበኛ ንጉሥ ነው› የሚለው እዚያ በገሐድ ይታያል፡፡ ምናልባት ደንበኞች አገልጋዮቻቸውን ሲያመናጭቁ እንጂ አገልጋዮቹ ደንበኞቹን ሲያመናጭቁ ብዙ ጊዜ አታዩም፡፡ እኛ ሀገር ብዙ ቦታ ከፍላችሁም ለምናችሁም ነው፡፡ ከምግብ ቤት ዐቅም እንኳን ጥሩ ምግብ ቶሎ ለማግኘት የወይ ባለቤቱን ወይ አስተናጋጁን ማወቅ አለባችሁ፡፡ መክፈላችሁ ብቻ በቂ አይደለም፡፡
የደንበኞች መኖር ነው የነጋዴዎች የህልውና ምንጭ፡፡ ደንበኞችን መከባከብ ራስን መከባከብ ነው፡፡ አንድን ደንበኛ በሚገባ መያዝ ብዙ ደንበኞችን ያለ ማስታወቂያ ለመሳብ ያስችላል፡፡ አንድን ደንበኛ ማስቀየም ደግሞ ለብዙ ደንበኞች ክፉ ስም እንዲያወጣ ዕድል ይሰጣል፡፡ 
ይህንን በብዙ ሀገሮች ታዩታላችሁ፡፡ የደንበኛነት ካርድ ይሰጧችኋል፤ ልዩ ቅናሽ ያደርጉላችኋል፡፡ አዲስ ነገር ሲመጣ ይነግሯችኋል፡፡ ቅድሚያ ይሰጧችኋል፡፡ እንዲያውም የእንግሊዝ ነጋዴዎች ታማኝ ደንበኞቻቸውን ውድ የሆኑ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን  በነጻ እስከ መጋበዝ ይደርሳሉ፡፡ በዚህም የተነሣ ታላላቅ ኮርፖሬሽኖች የእግር ኳስ ትኬቶችን አስቀድመው በመግዛት ለደንበኞቻቸው በስጦታ ያበረክታሉ፡፡
አውሮፓ ሳንሻገር እዚህ ጎረቤታችን ኬንያና አለፍም ብሎ ኡጋንዳ የደንበኞች ክብካቤ ልዩ ነው፡፡ ስማችሁን መዝግበው ከማስቀመጥ ጀምሮ በደንበኝነታችሁ ርዝማኔ ልክ የቅናሽ አገልግሎትና የነጻ ስጦታ እስከ መስጠት ይደርሳሉ፡፡ እጅግ ታማኝና ከእነርሱ ጋር ለዘመናት ለዘለቁት ደንበኞቻቸው ደግሞ የአውሮፕላን ትኬት ችለው የቱሪስት ቦታዎችን ያስጎበኛሉ፡፡
ይህንን ማየት ነበር እኛ ሀገር የሚናፍቀኝ፡፡ ያልፈለጋችሁትን ምግብ አምጥቶ ‹አንድ ጊዜ ትኬት ተቆርጦበታል ምንም ማድረግ አልችልም› የሚለውን መልስ የማይሰጥ፤ አስተያየት ስትሰጡት ‹ይቅርታ› ብሎ ለማረም የሚጥር፣ ያላችሁትን ሳያመጣ የማይረሳችሁ፣ አስጠብቆ የለም የማይል፣ ‹ተበላሽቷል ለውጠው› ስትሉት ‹ከደመወዜ ነው የሚቆርጡት› የማይል፤ ደንበኞቹን የማያውቅ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ የማያስተዳድረው፣ ከዚያም አልፎ ደንበኞቹን ‹እግዜር ይስጥልኝ› የሚል ነጋዴ የማየት ምኞት፡፡
ትናንት አዘውትረን ወደምንጎበኘው አባድር ሱፐር ማርኬት የጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ ሄድን፡፡ አባድርን የማውቀው አራት ኪሎ በሚገኘው ቅርንጫፋቸው ከዛሬ ሃያ ዓመት አካባቢ ጀምሮ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ በኋላ ግን የጉርድ ሾላው ቅርንጫፍ ደንበኛ ነኝ፡፡ አንድ ጊዜ ‹ለምን ደንበኞቻችሁን አትመዘግቡም› የሚል ሃሳብ ሰጠን፡፡ በደስታ ተቀበሉት፡፡ በሳምንቱ ምዝገባውን ጀመሩ፡፡ አስተናጋጆቹ ደንበኞቻቸውን በቅርበት ያውቃሉ፡፡ በስም ይጠራሉ፤ ይከባከባሉ፡፡ ባለቤቶቹ በየጊዜው ይከታተሉትል፤ የምትሰጧቸውን አስተያየቶች በደስታ ይቀበላሉ፡፡ ደግሞም ያርማሉ፡፡
እጅግ የሚገርመኝ ነገር የሱፐር ማርኬቶቹ ባለቤቶች ሙስሊሞች ሆነው የክርስቲያኖች በዓል ሲሆን ‹እንኳን አደረሳችሁ› ብለው ለክርስቲያን ደንበኞቻቸው ስጦታ ያዘጋጃሉ፡፡ እኔ እንዲህ የሚያደርጉ ክርስቲያን ነጋዴዎች አልገጠሙኝም፡፡ ለምሳሌ የገና በዓል ዕለት ቤቱ የክርስቲያን ቤት እስኪመስል ድረስ በገና ዛፍና ስጦታ ያሸበርቃል፡፡ ኢትዮጵያዊው የእምነት መከባበርና መገናዘብ የሚታይበት ቤት ነው - አባድር፡፡
ታድያ ትናንት ማታ ከሱፐር ማርኬቱ ስንወጣ አንድ ፖስታ ሰጡን፡፡ ፖስታውን ስንከፍተው የስጦታ ካርድ ነው፡፡ ደንበኞቻችን ስለሆናችሁ ይህንን ካርድ ሰጥተናችኋል ብለው ከሱፐር ማርኬቱ በነጻ ዕቃ የምንወስድበት ካርድ ሰጡን፡፡
 የገረመኝ ሁለት ነገር ነው፡፡ በአንድ በኩል ደንበኞቻቸውን ለይተው ማወቃቸው፡፡ ማክበራቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ደስታቸውንና ትርፋቸውን ማካፈላቸው፡፡ የስጦታው ማነስና መብዛት ለእኔ ቁም ነገር የለውም፡፡ ትልቁ ቁም ነገር ማሰቡ ነው፡፡ መክበሩ ነው፡፡ ዋጋ መስጠቱ ነው፡፡
አባድሮች ለሁላችንም አርአያ የሚሆን ሥራ አሳይተዋልና ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ ‹ካልፈለግከው ተወው› በሚባልበት ሀገር ደንበኛን ‹እንፈልግሃለን› የሚል ሲገኝ ምስጋና ይገባዋል፡፡ አባድሮች እናመሰግናለን፡፡

35 comments:

 1. It is very good work. Abader supermarket has been like initiator to ethiopian culture on customer. D/n dani tiru neger new yasayehen. Lelelam gize adadis negerochen asayen....... 10q

  ReplyDelete
 2. ውድ ዳንኤል የዚህ መደብር ሂደት የሚበረታታና የሚመሰገን ነው። እንደዚህ ያለው ደንበኞችን የመንከባከብ ይዘት የተለመደ እንዲሆን አንተም የበኩልህን በድረ-ገጽህ ያሰፈርከው መጣጥፍ የሚመገን ነው። ሌሎች ነጋዴዎችም የነአባድር አራት መቶ ብር በዚህ ጽሑፍ አማካይነት ብቻ ከመቶ እጥፍ በላይ በገበያ እድገት ያለምንም ጥርጣሬ እንደሚመለስላቸው ሊገነዘቡት ይገባል። አንተን ወንድሜን የምልህ ግን፤ ከጽሑፉ እንደምንገነዘበው፣ በነአባድር መልካም ዦሮ ተሰሚነት ያለህ ስለመሰለኝ እባክህን በሚያትሟቸው መገናኛ መልእክቶች ላይ ሁሉ፤ (ሀ) እንደ 'ምስክር ወረቀት' የመሰሉ የአማርኛ ቃላት እያሉ ምን ቢቸግራቸው ነው አንዴ "ሠርቲፊኬት" አንዴ "ሥርተፊኬት" ብለው መዘባረቃቸው? (ለ)'አባድር የገበያ ማዕከል' የሚለው ሥያሜ ለዘመናዊቱ ኢትዮጵያ አልመጥን ብሎ ይሆን በአማርኛው ጽሑፍ "አባድር ሾፒንግ ሴንተር" ብለው ራሳቸውን የሠየሙት? (ሐ)በባዕድ ቋንቋ የሚጽፉትን ሁሉ በታላቅ ጥንቃቄ አርመው፣ አሳርመው ካላቀረቡት ለማስተላለፍ የፈለጉት ቁም ነገር ተራ መሳቂያና መሳለቂያ ብቻ ነው የሚሆነው። እነዚህንና የመሳሰሉትን ግድፈቶች ደግሞ እንደተቆርቋሪ ወገን ሳናሳይ፣ ሳናስገነዝብ ብናልፍ አማርኛችንንም ኾነ ሌሎች ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን እያወቁም ሳያውቁም በማውደም የተሠለፉትን አጥፊ ወገኖች መቀላቀላችን ነውና ዝም ብለህ እንደማታልፈው ወደፊት "አባድሮች የለገሥኳቸውን ምክር ተቀብለው አረሙ" ብለህ አጭር መልዕክት እንደምታሠፍርልን ተስፋ አለኝ። ይመኩ ታምራት

  ReplyDelete
  Replies
  1. Gud eko new aydel Yimeku... Diaqon Danelin lemasdeset yihonal...

   Delete
  2. ይመኩ፤ ልብ አላልከውም እንጂ 'ምስክር ወረቀት' በማለት ፋንታ 'certificate' ለማለት መጀመሪያ 'ሠርቲፊኬት'፤ ቀጥለው 'ሥርተፊኬት' ሦስተኛው ላይ ደግሞ 'ሰርተፍኬት' ነው ብለው ያተሙት! ዳንኤል በጽሑፉ ካስቀመጠው እንደተረዳሁት ይሄንን ስጦታ ያስረከቡት ያለፈው ዓርብ የካቲት 29 ቀን 2005 ዓ/ም መሆኑ ነው። ታዲያ 'አጉል ፍርንጅና' ይሏችኋል፣ ባላጣነው፤ ባልቸገረንና የኛው በሆነው ባሕረ ሐሣብ ከመጠቀም ይልቅ ባዕዳዊውን ጎርጎርዮሳዊ ቀመር እንጠቀም ብለው March 8, 2012 ተሰጠ ብለው ነው የመሰከሩት። ታዲያ የስጦታው የጊዜ ገደብ አንድ ዓመት ብቻ በመሆኑ የተጻፈ ዕለት ነው ዋጋ ቢስ የሆነው ማለት ነው። ዳንኤል ሆይ! ጽሑፉን ያለ አወዛጋቢው ምስክር ወረቀት ብታወጣው አይሻልም ኖሯል? ወይስ ተለምዶው በሌለበት አገር የ400 ብር ስጦታ ስላገኘህ ከመደሰትህ ብዛት እነኚህን ግድፈቶች ልብ ሳትላቸው ነው ያወጣኸው?

   Delete
  3. Thanks Yimeku, you put important things.

   Delete
  4. There are also mistakes in the English version like "This certificate will we accepted...."

   We can observe such mistakes everywhere in the city and in our daily media broadcasts. Dia. Daneal said a lot on such language barriers on his article on a researcher presentation for farmers.

   Delete
 3. ለጸጉር ቤቴ ጥሩ መላ ነው ያስተማሩኝ::ሀሳብ የሚሸጥበት ሀገር ቢኖረን አንተ በቀን ምን ያህል ታገኝ ነበር? አምላክ ይክፈልልን ወንድማችን:: እንዲህ ያለውንማ ባህል እስኪሆን መሥራት አለብን:: አሁን አሁን እኮ መመሰጋገን ኃጢአት ነው የሚመስለው:: ያወቀበት ግን አየህ አያያዝ አርአያነታችሁን እንከተላለን:: ምሳሌነታችሁንም እንይዛለን:: አባድሮች በርቱልን::

  ReplyDelete
 4. Tiru new,beleloch sewochim zend bilemed melkam new.

  ReplyDelete
 5. እኔም ዛሬ ለአግዮስ ኅትመትና ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃ.የተ.የግ.ማ በዛሬው እለት የካቲት 30፣2005 ዓ.ም የክብር ደምበኛ በመሆኔ ታላቅ ኩራት ተሰምቶኛል.

  ReplyDelete
 6. YA EXACTLY IT IS APPRECIATED .
  BUT CAN U WRITE ABOUT CUSTOMER AND SERVICE PROVIDER RELATION SHIP BETWEEN SCHOOLS/TEACHERS/ AND STUDENTS/PARENTS/.
  THIS IS BECAUSE OUR SCHOOLS/TEACHERS KNOW NOTHING ABOUT IT,ESPECIALLY GOVERNMENT SCHOOLS.

  ReplyDelete
 7. I think this is a good experience to all of business men.I want to say keep it up "Abadires".Dani you have a great personal view.God bless you.

  ReplyDelete
 8. Impressive indeed!

  ReplyDelete
 9. አያልቅበት ዳንኤል መቸስ ዐይን ሰጥቶህ የሚያነብ ካገኘህ አንተ አያልቅብህ ነገር ነህ መሰል። አዲስ አበባ ስገባ የአባድሮችን መስተንግዶ አይቼ አባድሮች እናመሰግናለን እል ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
 10. ‹ካልፈለግከው ተወው› በሚባልበት ሀገር ደንበኛን ‹እንፈልግሃለን› የሚል ሲገኝ ምስጋና ይገባዋል፡፡ አባድሮች እናመሰግናለን፡፡  ReplyDelete
 11. thank u dany u are trying to teach good part of living together or good culcher of other countries we will try is not easy to cupcher ones

  ReplyDelete
 12. ዳኒ በጣም እናመሰግናለን እጅግ በጣም ጥሩ እይታ ነው፡፡ እኔ እና ባልጀሮቼ የአራት ኪሎ ከሚገኝው አባድር ተጠቃሚ ነን፡ እና በጣም የሚመሰገኑ ናቸው ዋጋቸውም ቢሆን ከሌላው አንፃር ተመጣጣኝ ነው፡፡ እንዲያውም ባንድ ወቅት አምስተኛ ፓትሪያሪክ የነበሩትኝ አቡነ ጰዉሎስን በጋዜጠኛ ቃለ መጠይቅ ተደጎላቸው የሚመገቡት ምግብ ስጠይቃቸው አባድርም ዳቦ ቆሎ የተገኘውን ገዝተን እንጠቀማለን ሲሉ ሰምቻለሁኝ፡፡ አባድር ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

  ReplyDelete
 13. Melkam new hasabhn tekeblew degmom berasachew tenesashinet endih madregachew yihunina " ene endih yemiyadergu krstian negadewoch algetemugnm " maletihn alwededkutim yewondm mikir bleh bekininet kayehew belibih armew........

  ReplyDelete
  Replies
  1. You are right Deacon Z. But if Daniel didn't face, it doesn't describe all the situations. Muslimoch ye sitota card minamin silemayabezu inj egnam enisetachew neber. Sile Gena zaf , it is certain culture that enter to Ethiopia with the name of christianity, it is not ours. Any ways Daniel will consider your idea, since he gave hasty generalization.

   Delete
 14. በእውነት በልቤ ሁል ጊዜ የሚመላለስ ነገር ነው የፃፍከው ለምን ስለተደረገን ነገር አናመሰግንም ለምን ልምድ አናደርገው እንኳን በንግድ ዓለም ቀርቶ ጓደኛህን እንኳን ይህን ታደርግልኝ ብለሀው እሺ ብሎ ሞክሮት ሳያደርግልህ ቢቀር አመሰግናለሁ ብለህ ሌላ ጊዜ ብቱና ሰዎችን የሚተባበር ታደርገዋለህ ሌላ ከዚህ ጋር አብሮ መታሰብ ያለበት ነገር ቆሻሻዎችን በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ለሚጥሉ አካባቢያቸውን ላፀዱ ሰዎች ጎበዞች ናችሁ እግዚአብሔር ይሄን በጎ አመለካከታችሁ አይቀይርባችሁ ማለት ቢያን ከአውቶብስ ስንወርድ የያዝነውን (የተጠቀምንበትን) ትኬት በአካባቢው ካለ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ መክተት የሚከቱ ሰዎችን ማበረታታት ለበጎ ነገር ፣ለሰው ክብር መስጠት ውጤቱ ለራሳችን ነው ማን ያውቃል አንድ ቀን ሁሉም ይሳካ ይሆናል እናመሰግናለን የምናውቅ ቆሻሻ በየመንገዱ የማንጥል ለሰዎች ቀና መልስ የምንሰጥ እንሆን ይሆናል ለአንተም ይህን ለስነበብከን አምላክ ዋጋህ ከፍ ያድርገው
  wtbhm

  ReplyDelete
 15. በተለያዩ የሕይወት ዘርፎች ባለው የአገልግሎት አሰጣጥ ደንበኛ ክቡር መሆኑ ቀርቶ ክብረ ነክ በሆኑ ቃላት ምላሽ በሚሰጥባት አዲስ አበባ እንዲህ ዓይነት በጎ ነገር መስማቱ በራሱ ደስ ይላል- ምናለ እንደ 'ወረርሽኝ' ቢስፋፋ ብያለሁ ---ዲያቆን ዳንኤል ደስ የሚል ዜና በማሰማትህ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ ብያለሁ

  ReplyDelete
 16. ዲያቆን ዳንኤል ለጤናህ እንደምን አለህ
  አንድ አድርገን ብሎግ Thursday, march 7, 2013 ………..” ‘ተሀድሶን’ ጠርገን ሳናስወጣ ‘ተዋህዶ’ የሚሉ ደግሞ ብቅ ብለዋል” በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ አስነብበውን ነበር፡፡
  እኔን ጨምሮ አንዳንድ ወንድሞቼንና እህቶቼን ይሄ ቅባት ፣ፀጋ ፣ዘጠኝ መለኮት…..ወዘተ የሚሉት ነገር ፈጽሞ አልገባንም፤ ስለዚህ አንተ ጊዜ ወስደህ ስለ ቅባት ፣ፀጋ ፣ዘጠኝ መለኮት…..ወዘተ በአንተ ብሎግ ላይ ብትጽፍልን( እንድታስተምረን) በትህትና እጠይቅሃለው፡፡

  http://andadirgen.blogspot.com/2013/03/blog-post_7.html
  አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
 17. Most of the time Ethiopian business men does not consider customer when they open business.You found good business men like Abadir but they treat customer well because they have good respect for all human being.it will change through time and education.

  ReplyDelete
 18. ለሌሎቹ አርአያ የሚሆን ተግባር ነው አባድር ያከናወናው:: ታዲያ ዳንኤል መልካም የሰሩትን ማመስገን ማበረታታት ተገቢ እንደሆነው ሁሉ ሊታረሙ የሚገባቸው ደንበኛ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስልጠና የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎት ሰጪዎች ስማቸውን ጠቅሰን ታረሙ ማለት አለብን ምክንያቱም እስከዛሬ ድረስ በጅምላ እየተናገርን ያመጣነው ለውጥ የለም ለማንኛውም እይታህን ወድጄዋለሁ

  ReplyDelete
 19. Good advertizement, lol

  ReplyDelete
 20. they are really typical Ethiopian. thanks abadir super market

  ReplyDelete
 21. ዲ/ን ይህንን አይነት አስተያየት ካሁን ቀደምም አስነብበኸናል።
  እኔን የሚገርመኝ አንድን እቃ በደንብ አይተህ፣ ይሆነኛል አይሆነኝም ብለህ፣ ለመግዛት እንኳ አለመቻሉ ነው። ወይ መግዛት ወይ አለመጠየቅ ነው አማራጩ። እኔ በይሉኝታ የምገዛበት አጋጣሚ አለ። ሰውየውን ካስለፋሁት በሚል ወይም ላለመጣላት። በእውነት አንዳንዶች በግድ ነግዱ የተባሉ ይምስል ጠይቀህ ካልገዛህ ይበሳጫሉ።
  ለማንኛውም ለኛ ሀገር ነጋዴወች ጥሩ መልዕክት ነው እናመሰግናለን።

  ReplyDelete
 22. ወንድም ዳንኤል እንደምን ሰነበትክሳ፡፡
  በተለያየ ሁኔታ ላይ የሚነሱ ርእሰ ጉዳዮች መመዘን የሚገባቸው እንዲያው በጥሬው ትክክል ናቸው ወይንም አይደሉም በሚለው ብቻ ሳይሆን ከጊዜና ከቦታ አንፃር ምን ያህል አግባብነትና ወቅታዊነት አላቸው ከሚለው እይታ ጭምር ነው፡፡በዚህ እይታ ስንሄድ አንድ ወቅታ ላይ ስለ ጋዳፊ ሞትና የአገዛዙ ፍፃሜ በተለመደው የእኛ ሀገርና የውጪውም ሀገር የተለመደው mainstream የሚዲያ ዳሰሳ እይታ ፅፈህ እንደተለመደው ድጋፍም ተቃውሞም ገጥሞህ ነበር፡፡ታዲያና ስለጋዳፊ ሞት የፃፍከውን ያህል ስለ ታዋቂው የ21 ክፍለ-ዘመን የሰከነው ሶሻሊዝም አራማጅ ሁጎ ሻቬዝ አሳዛኝ ሞት ዝም ጭጭ ማለትህ የጤና ነውን?በእርግጥም ስለ የ21ኛው ክፍለ-ዘመን የሰከነው ሶሻሊዝም አራማጅ ብቻም ሳይሆን ስለ እውነተኛው አብዮታዊ ዲሞክራሲ ማንሳት ካለብን ሁጎ ሻቬዝ በዚህ ብሎግ ላይ መነሳት ያለባቸው የዘመናችን ታላቅ የፖለቲካ አብዮተኛ ናቸው፡፡በዚህች የህይወት ዘመኔ የተረዳሁት አንድ ትልቅ ነገር ቢኖር የዘመናችን ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ፖለቲከኞች ከእውነት ጋር በጣሙን የተጣላን የዘመናችን የለየልን አድርባዮች እንደሆንን ነው፡፡አዎ የዘመናችን ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ፖለቲከኞች የምእራቡን አለም በተለይም ዲቪ ሎተሪ የሰጠችንን አሜሪካንን እንደ ትክክለኛና ቅዱስ ነገር የማምለክ አባዜ እንደተጠናወተን ነው፡፡ስለዚህም የምእራቡን አለም በተለይም ዲቪ ሎተሪ የሰጠችንን አሜሪካንን የሚቃረን ነገር ሁሉ እንደ ሰይጣን አድርጎ የመሳል አባዜ እንደተጠናወተን ነው የተረዳሁት፡፡አንተም በዚህ ትብታብ ውስጥ የተጠመድህ ስለሆንህ ከዚህ በፊት ስለ ጋዳፊ የተዛባ መረጃም ቢሆን የተወሰነ ዘገባ ያላወራኸውን ያህል ስለ ታዋቂው ሁጎ ሻቬዝ ግን ጭራሽ ዝም ጭጭ ማለትህ ብዙም የሚገርም አይደለም፡፡ኢትዮጵያውያን በእውነት ላይ ስላመፅንና እውነትንም ወግጅ ብለን ስለከዳናት እነሆ ዛሬ እራሳ እውነት ፊት አዙራብን እየተሰቃየን ነው፡፡እውነት አርነት ያወጣል እንደተባለው ስለሆነ ደግሞ ከሀሰት ጋር የተዛመደ ባርነትን እንጂ አርነትን አያውቃትም፡፡ ሁጎ ሻቬዝ የ21ኛው ክፍለ-ዘመን የሰከነው ሶሻሊዝም አራማጅ ብቻም ሳይሆን የእውነተኛው አብዮታዊ ዲሞክራሲ አራማጅ ነበር፡፡አዎ ሁጎ ሻቬዝ አብዮተኛ ነበር ምክንያቱም የጥቂት አለም አቀፍ ሀብታም ልሂቃንን ህልውናና ጥቅም የሚያራምድ ስርዓት የሆነውን የግሎባል ካፒታሊዝምን ኒዎ-ሊበራልና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት በቆራጥነት የተዋጋ ታላቅ ፖለቲከኛ ነበር፡፡በምትኩም የዘመናችንን የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ሶሻሊዝምን ከእውነተኛ አብዮታዊ ድሞክራሲ ጋር በቬንዝዋላና በላቲን አሜሪካ ያስፋፋና በተለይም ለታችኛው ድሃ የህብረተሰብ ክፍል ብልፅግና ክብርና ነፃነት መገኘት የታገለና በከፍተኛ ሁኔታም የተሳካለት ታላቅ ሰው ነበር፡፡አብዮታዊ ዲሞክራሲ የመጥፎ ስርዓት መገለጫ ይመስል የእኛን ሀገር አገዛዞች አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚከተሉ እያሉ እራሳቸው ደንቁረው ሌላውንም ህዝብና ዜጋ ለሚያደነቁሩ የዘመናችን ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ፖለቲከኞች አብዮታዊ ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ ካልገባቸው ሁጎ ሻቬዝንና ቬንዝዋላን እንደ አርአያ ማየት ይችላሉ፡፡አዎ ሁጎ ሻቬዝ ለቬንዝዋላ ህዝብና ዜጋ እውነተኛ የፖለቲካ ነፃነትን(ዲሞክራሲንና የዜግነት ክብርን) ከእውነተኛ የኢኮኖሚ ነፃነት (ክፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ጋር) ጋር አቀናጅቶ ለመስጠት የቻለ ታላቅ የዘመናችን ፖለቲከኛ ነበር፡፡የዘመናችን ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ፖለቲከኞች የምእራቡን አለም የውሸት ዲሞክራሲ እንደ በቀቀን ሲያቀነቅኑና እንደወረደ ሳያኝኩ ሲውጡ ስለኖሩ ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ስልጣን አላካፍል ስላላቸው ብቻ ይህንን ስርዓት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነው የሚከተለው ማለታቸው የታሪክ ምፀት ነው፡፡አዎ እውነተኛ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚከተለው የቬንዝዋላው ሁጎ ሻቬዝ ነበር/ነው፡፡ስለዚህም ወንድም ዳንኤል ስለዚህ ታላቅ ሰው ምንም ትንፍሽ አለማለትህ ምክንያቱ ምድን ነው?ይህ ሰው እኮ ለሀገሩ ድሃ የህብረተሰብ ክፍል ብቻ ሳይሆን ለመላው የአለም ድሃ ህዝብ የቆመ እውነተኛ ቀናኢና የ21ኛው ክፍለ-ዘመን የሰከነው ሶሻሊዝም አራማጅ ሰው ነበር፡፡ዲያቆን ዳንኤል ክርስትና እኮ መሰረቱ ሶሻሊዝም ነበር፡፡ከርስቶስ እኮ የተወለደው በበረት ውስጥ እንጂ ባማረ ቪላ ወይንም ቤተ-መንግስት ውስጥ አልነበርም፡፡የማርያም እናትና አባትም እኮ በመንፈሳዊ ነገር ሀብታሞች ነገር ግን በቁሳዊ ነገር ድሃዎች ነበሩ፡፡ታዲያ ይህ አይነት ታላቅ የሶሻሊዝም አራማጅና የድሃዎች ጠበቃ ሲሞት ዝም ማለት እውን የክርስትና መንፈስ ያለው ነገር ነውን?ውድ ዳንኤል ሶሻሊዝም ፈጣሪን ይክዳል ብለው የሚያስወሩት ጥቂት የካፒታሊስቱ አለም አቀፍ ልሂቃን ናቸው፡፡ምክንያቱም ድሃው ህዝብ በተለይም እንደ ኢትዮጵያውያን አይነቱ በፈጣሪ ስለሚያምን ከፈጣሪ የሚያጣላ ነገር እንደሆነ አድርገው በመሳል በዚህ ሽፋን ህዝቡ የሚበጀውን ሶሻሊዝምን እንዳያራምድባቸውና የእነሱ የጥቂት ልሂቃን ስርዓት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ብለው የሸረቡት ሴራ ነው፡፡ስለዚህ ወንድም ዳንኤል ስለ ሁጎ ቫቬዝ ዝም ጭጭ ማለት የወጣንበትን ማህበረሰብና ፈጣሪንም ጭምር የመካድ ያክል ነው፡፡እውነተኛ ሚዲያዎችን በትክክል ካዳመጥህ የቬንዝዋላ ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላው የላቲን አሜሪካና የአለም ህዝብ ነው ያዘነው፡፡በዚህ ሰው መሞት የሚደሰቱት ጥቂት የካፒታሊስቱ አለም አቀፍ ልሂቃን ናቸው፡፡ምክንያቱም ይህ ሰው ለድሃው ህዝብ ኑሮ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገውን የሀገሩን የነዳጅ ሀብት ናሽናላይዝ በማድረግ ልክ እንደ ጋዳፊ ሁሉ የውጭ ባእዳን ሃይሎች እንደፈለጉት እንዲመዘብሩት አልፈቅድም ያለ ሰው ነበር፡፡እናም ስለተገፉና ስለተረገጡ ድሃዎች ግድ የሚልህ ከሆነ ስለዚህ የድሃዎች እውነተኛ ጠበቃ የሆነ ታላቅ ሰው አንድ በል፡፡አዎ ቅድሚያ የጥቂቶችን ህልውናና ፍላጎት የሚያራምደውን ግሎባል ካፒታሊዝምን ሰርተፍኬት ገለመሌ እያልክ በከንቱ ከምታሽሞነሙን እንደዚህ አይነቱን የድሃ ህዝብ ጠበቃ የሆነና የ21ኛው ክፍለ-ዘመን እውነተኛ የሶሻሊዝም አራማጅ የሆነን ሰው አስታውሰው፡፡
  ከምስጋና ጋር፡፡


  ReplyDelete
 23. Ye Hagerachin Negadewoch yehinin Tshuf Biyanebut Endet Teru Neber Minalibat Ye Abadirochin Felg Biketelu Teru Eyita New Danii EGZIABHER Tsegawin Yabizalih

  ReplyDelete
 24. ዳኒ ይህን ጽሁፍ በመጻፍህ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት አራት ኪሎ አባድር አጠገብ ያለው ሱፐር ማርኬት ገብቼ የልጅ ዳይፐር ለመግዛት ዋጋውን ጠይቄ ካሸሪዋን እንድታሳየሀኝ ብጠይቃት “ምኑን ነው የማሳይሽ” የሚል መልስ ሰጠችኝ፡፡ እኔም በጣም ተበሳጭቼ ከዛ ወጥቼ አባድር ብሄድ ያውም በጣም በቅናሽ ዋጋ የፈለኩትን ጥያቄ ጠይቄና ዳይፐሩን አገላብጨ አይቼ ገዛሁ፡፡ ሰው እንዴት የፈለገውን ነገር ሳያይ ይገዛል?

  ReplyDelete
 25. hey am really proud of u

  ReplyDelete
 26. kezihe belaye sele የቬኔዝዌላ ፕሬዚዳንት ሁጎ ቻቬዝ yesafekew engedihe ye przidantu afeqari kehoneke ante bednebe aderegehe safelene danine behone balehonew meneqefune tewewe wondeme esu eko yagatemewen tiru neger new yenegerene antem yagatemehe tiru neger kale meletefe techelalehe eneme addis admase laye yanebebkuten sele የቬኔዝዌላ ፕሬዚዳንት ሁጎ ቻቬዝ ameteche letefewalehu

  ኧረ መልሱን ስጪኝ ዝምታው ምንድነው ቅድምም አሁንም የመረጥኩ አንቺን ነው” ባለፈው ማክሰኞ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቬኔዝዌላ ፕሬዚዳንት ሁጎ ቻቬዝ፤ በጣም ዝነኛ ነበሩ - ሰውን በመዘርጠጥና በመዝለፍ፡፡ በቀዳሚነት መዝለፍና መዘርጠጥ የሚቀናቸው የሥልጣን ተፎካካሪዎቻቸውን ተቃዋሚዎችን ነበር፡፡ በመቀጠል ደግሞ የአሜሪካን ፕሬዚዳንትና ካፒታሊዝምን እንደጉድ ሲዘረጥጡና ሲያብጠለጥሉ ኖረዋል (የነዳጅ ሃብታቸው በሰጣቸው የልብ ልብ!) ሁጐ ቻቬዝ እ.ኤ.አ በ1999 ዓ.ም እጩ ፕሬዚዳንት ሳሉ አንዳንድ የተጠራጠሯቸው ወገኖች አጓጉል ጥያቄዎች አቅርበውላቸው ነበር፡፡ (ያውም እኮ በሥልጣን ዙሪያ!) “በአምስት ዓመት ውስጥ ሥልጣን ያስረክባሉ?” ተባሉ (አያችሁ ሠይጣን ሲፈትናቸው!) እሳቸውስ ምናቸው ሞኝ ነው! “እንዴታ! እንደውም ቀደም ብዬ ለማስረከብ ፈቃደኛ ነኝ” አሉና ቂብ አሉ - የሥልጣን መንበሩ ላይ፡፡

  ከዚያማ ማን ወንድ ይምጣ - ከሥልጣን የሚያወርዳቸው፡፡ አምስት ዓመት ሳይሞላኝ እወርዳለሁ ያሉት ቻቬስ፤እንደሌሎቹ አምባገነን ባልንጀሮቻቸው ህገመንግስት እየሰረዙና እየደለዙ ቬኔዝዌላን ለ14 ዓመታት እንዳሻቸው ፈነጩባት (ፈነዱባት ይሻላል!) ፕሬዚዳንቱ ምርጫ በመጣ ቁጥር ተቀናቃኞቻቸውን ሙልጭ አድርገው በመስደብና በማንጓጠጥ ይታወቃሉ፡ (እንደኢህአዴግ “መጡም ቀሩም አይጠቅሙም አይጎዱም” ዓይነት እንዳይመስላችሁ!) አምባገነንነት ላይ የነዳጅ ዶላር ሲጨመርበት ምን እንደሚከሰት አስቡት! የማታ ማታ ግን ለሁለት ዓመት ያህል ከካንሰራቸው ጋር ሲታገሉ ቆይተው ህይወታቸው አለፈ - ከሥልጣን ሱሳቸውም ተገላገሉ፡፡ ሶሻሊዝም አቀንቃኝ የነበሩት የዓለማችን አወዛጋቢው ፕሬዚዳንት ቻቬዝ ስለካፒታሊዝም ሲናገሩ፤ “አዲስና የተሻለ ዓለም ለመገንባት ትክክለኛው መንገድ ካፒታሊዝም አይደለም ፤ ካፒታሊዝም በቀጥታ የሚወስደን ወደ ገሃነም ነው” ብለው ነበር፡፡

  ለመሆኑ አሁን እሳቸው ያሉት የት ነው? ገነት ነው ገሃነም? (ገነትም ሆነ ገሃነም ያቺ የሚወዷት ሥልጣን ምድር ቀርታለች!)

  ReplyDelete
 27. መልካም᎓እይታ᎓ነዉ᎓᎓

  ReplyDelete