ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ (1426-1460ዓ ም) በዘመናቸው አምልኮ ጣዖትን አስቆማለሁ
ብለው ቆርጠው ተነሥተው ነበር፡፡ ይህንን ነገር ለማስቆምም ሦስት ዓይነት መንገድ ለመጠቀም አሰቡ፡፡ መምህራንን እየላኩ ሕዝቡን
ለማስተማር፣ ለማስተማርያ የሚሆኑ ድርሰቶችን እንዲዘጋጁ ለማድረግና ራሳቸውም ለማዘጋጀት፣ በመጨረሻ ደግሞ ከዚህ ሁሉ
የተሻገረውን ለመቅጣት፡፡
በተለይም በአምልኮ ጣዖት የተያዙትን፣ ይህንንም አምልኮ ከሕዝቡ ገንዘብ ለመሰብሰብና
ሕዝቡን ለማታለል ሲሉ የሚያካሂዱትን ሰዎች የሚከታተሉ፤ ባለሥልጣናቱ በድብቅ ይህንን ተግባር ሲያከናውኑ፣ አንዳንድ ካህናትም
ከሁለቱም ወገን ሆነው ሲያጭበረብሩ፣ ታዋቂ የሆኑ ሰዎችም በዚህ ባዕድ አምልኮ ውስጥ ሲነከሩ እየተከታተሉ ለንጉሡ መረጃ የሚሰጡ
ሦስት ሰዎችን መድበው ነበር፡፡
ዘርዐ ክርስቶስ፣ ተዐውቀ ብርሃንና ገብረ ክርስቶስ የሚባሉት እነዚህ ሦስት ሰዎች ወደ
ባዕድ አምልኮ የሚሄዱትን፣ በድብቅ ይህንን ተግባር የሚያከናውኑትን፣ በተለይም የቤተ መንግሥት ሰዎች ሆነው ለሕዝቡ የባዕድ
አምልኮ ክፉ አርአያ የሚሆኑትን እንዲጠቁሙ፣ ተከታትለውም እንዲያሲዙ፣ አስይዘውም እንዲያስቀጡ ንጉሡ ሥልጣን ሰጥተዋቸው
ነበር፡፡
እየቆዩ ግን ግእዛቸው ተለወጠ፡፡ ይህንን ሥልጣናቸውን የጉቦ መቀበያ፣ የመደለያ
መብያ፣ የሙክት መዋዋያ፣ የዝምድና መመሥረቻ፣ የሀብት ማከማቻ፣ የቂም መወጫ፣ የጠላት መቅጫ እያደረጉት መጡ፡፡ ጉቦ አልሰጥ
ያሏቸውን ያላጠፉትን አጠፉ ብለው ይከሷቸዋል፤ እስከ ሞትም ያስፈርዱባቸዋል፡፡ ከዚህ በፊት በሌላ ነገር የተጣሏቸውን አምልኮ
ባዕድ ሲፈጽሙ አገኘናቸው ብለው ለንጉሡ አሳልፈው ይሰጧቸዋል፡፡ የገዛ ወዳጆቻቸውና ዘመዶቻቸው የሚፈጽሙትን ክፉ ሥራ ሁሉ
እየሸፈኑ አይተው እንዳላዩ ያልፏቸዋል፡፡ እነርሱ አንድ መንደር ሲደርሱ ሙክት ያላረደ፣ የከረመ የጠጅ ጋኑን ያልከፈተ፣ ምንጣፍ
ያላነጠፈ፣ እግር ያላጠበ ሁሉ ዓይን ይጉረጠረጥበታል፣ ጣት ይቀሰርበታል፡፡
ሕዝቡ በእነዚህ ሦስት ሰዎች ግፍና ጭካኔ ሲማረር ስማቸውን ‹‹ደቂቀ ሰይጣን-
የሰይጣን ልጆች›› ብሎ አወጣላቸው፡፡ ሕዝቡ እነዚህን ሦስት ሰዎች ‹ደቂቀ ሰይጣን› ያላቸው ስለ አራት ነገር ነበር፡፡ በአንድ
በኩል ጥቂት እውነት ይዘው ብዙ ሐሰት ስለሚጨምሩበት ነው፡፡ ሰይጣን ጥቂት እውነት ይኖረዋል፡፡ ሔዋንን ‹‹የሰማይና የምድር
ንግሥት›› ሲላት የተናገረው በከፊል እውነት ነበር፡፡ ‹‹የምድር ንግሥት›› መሆኗ እውነት ነው፡፡ ‹የሰማይ ንግሥት› ግን
አልነበረችም፡፡ እነዚህም ሰዎች ጥቂት የሚመስል እውነት ይይዙና የቀረውን ነገር እነርሱ እጅን እግር፣ አንገትና ደረት፣ ጀርባና ፊት ሞልተውበት ያቀርቡታል፡፡ ነገር ዐዋቂዎች፣
ወግ አሣማሪዎች ስለነበሩ የሰማ ሁሉ ያምናቸዋል፡፡
ሁለተኛ ደግሞ እውነትን መደራደርያ ስለሚያደርጓት ነው፡፡ አንድ ሰው የተባለውን ጥፋት ሲፈጽም ካዩት ወንጀሉ ወይም ጥፋቱ አይታያቸውም፡፡
ይህንን የሰውዬውን ጥፋትና ወንጀል እንደ መደራደርያ በመጠቀም ሊያገኙት የሚችሉት ጥቅም እንጂ፡፡ ሰውዬው የተባለውን ካደረገ፣
የታዘዘውን ከፈጸመ፣ የሚገባውን ከሰጠ የከፋውን ወንጀል ቢፈጽም እንኳን የታየው እንዳልታየ፣ የተሰማው እንዳልተሰማ፣
የተፈጸመውም እንዳልተፈጸመ ይታለፍለታል፡፡ ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆነ ግን ከሆነው በላይ እንዳደረገ ተቆጥሮ፣ ስሙ
ጠፍቶ፣ ግብሩ ከፍቶ፣ ቀንድና ጅራት ተጨምሮለት ለጥብስ ይቀርባል፡፡ የሚጠይቁት ጉቦና ለሰጭ አስቸጋሪ በመሆኑም የተነሣ ሕዝቡ
እነዚያው መጡልህ ደቂቀ ሰይጣን
ጠጅ በገበታ ሥጋውን በጋን
እያለ ይዘፍን ነበር፡፡
ሦስተኛው ደግሞ ሥልጣናቸውን የቂማቸው መወጫ ማድረጋቸው ነው፡፡ ከዚህ በፊት በርስትም
በሚስትም፣ በከብትም በዶሮም የተጣላቸውን፤ ይቀናቀነናል ይገዳደረናል የሚሉትን፤ ይንቀናል ያቃልለናል ብለው የሚገምቱትን ሁሉ
የፈጠራ ክስ እያዘጋጁ፣ ያንንም እያሣመሩና እየቀባቡ ያቀርቡ፣ አቅርበውም ያስቀጡ ነበር፡፡ ‹ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል›
እንዲሉ ባለ ጊዜዎች ነበሩና ጣል ያሉት ይጣላል፣ እሠር ያሉት ይታሠራል፣ ግደል ያሉት ይገደላል፡፡
አራተኛውና ‹‹ጉንዳንን ዝም ካሉት አናት ላይ ይወጣል›› እንደተባለው ሕዝቡን ሁሉ
ያስገረሙት የንጉሡን ልጆች፣ ሚስቶችና ወንድምና እኅቶችን ጭምር እየከሰሱና እያሳጡ ግምሾችን ማስገደላቸው፣ ከፊሎችንም
ማሣሠራቸው ነበር፡፡ ያን ጊዜ በእነዚህ ‹‹ደቂቀ ሰይጣን›› ውንጀላ ከታሠሩት መካከል ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ በኋላ የነገሡት
የንጉሡ ልጅ በዕደ ማርያምም ይገኙበት ነበር፡፡
የእነዚህ የደቂቀ ሰይጣን ግፋቸው በየቀኑ እየጨመረ፤ በትራቸው እየጠነከረ ሲሄድ ሕዝቡ
አቤቱታውን ለንጉሡም ለእግዚአብሔርም ማቅረብ ጀመረ፡፡ በመጀመርያው አካባቢ ንጉሡ ሊሰሙት ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ ‹‹አንድ
ሰይጣን የያዘው ሰው ሲጠመቅ ጎረቤቱ ሁሉ ይለፈልፋል›› እንደሚባለው ሕዝቡ ከጥፋቱ ይልቅ ቅጣቱን ተጠይፎ ስለመሰላቸው ቸል
ብለውት ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን ከበደ ሚካኤል
አይጥ ስትጠግብ ስታበዛ ሩጫ
ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ
እንዳሉት፤ ወይም ደግሞ የታክሲ ጥቅስ ጸሐፊው ብሩክ ‹‹ሟች ከመሞቱ በፊት ይንቀዠቀዥ
ነበር›› እንዳለው ነገሩ ከቤተ መንግሥቱ ባለሟሎችም አልፎ ወደ ራሳቸው ወደ ንጉሡም መጣ፡፡ እነዚህ ሰዎች የልብ ልብ
ተሰማቸውና ራሳቸው ንጉሡን በየሄዱበት መክሰስና ማማት፣ አምተውም ማሳማት ጀመሩ፡፡ ከየት መጣ የማይባል ሀብትና ከብት፣ ማርና
ወተት እያትረፈረፋቸው ይታይ ጀመር፡፡ ‹የማያድግ ልጅ አራስ ቤት እያለ ዳንኪራ ይመታል› እንዲሉ ቀድሞም ያለ ዐቅማቸው
የያዙትን ሀብት አላውቅበት ብለው ሥራቸው ሁሉ አሥረሽ ምችው ሆነ፡፡
ሁኔታው ያሠጋቸው ንጉሥ ነገሩን ማስተዋል ጀመሩ፡፡ በዚህ ወንጀል ከታሠሩት፣ ተይዘውም
ከተገደሉት ብዙዎቹ ያለወንጀላቸውና ያለ ጥፋታቸው መሆኑን፤ አንዳንዶቹም ለዚያ የሚያበቃ ጥፋት አለመሥራታቸውን እየተረዱት
መጡ፡፡ ዘርዐ ጽዮን ያንን በግፍ የሰበሰበውን ሀብትና ንብረት ጥሎ፣ ልጅና ሚስቱን በትኖ ግዞት ተላከ፡፡ በተላከበት ግዞትም
በዚያው ሞቶ
አዙረህ አዙረህ ሀገሬ መልሰኝ
በሹም የታዘዘ አፈር አታልብሰኝ
የተባለው ምኞት ሳይደርስልት በማያውቀው ሀገር ተቀበረ፡፡ ተዐውቀ ብርሃንም ‹‹የሞኝን
ጓደኛ ዘንዶ በጅራቱ ሲይዘው እርሱ በአናቱ በኩል ይመጣል›› እንደተባለው ከዘርዐ ጽዮን መማር አቅቶት በግፍ ላይ ግፍ ሲጨምር
ተይዞ ግዞት ተላከና በዚያው እንደ ባልንጀራው ሞቶ ቀረ፡፡ ከሁሉም የተረፈውና የመማርም የመታረምም ዕድል የነበረው ገብረ
ክርስቶስ ነበር፡፡ ‹የሚያድግ ልጅ አይቀየምህ፣ የሚሞት ሽማግሌ አይርገምህ› ይባላልና እርሱ ባለ ጊዜ በነበረ ሰዓት ያለ ስሙ
ስም ሰጥቶ ያለ ግበሩ ግብር አውጥቶ ያሳሠረው በእደ ማርያም በአባቱ በዘርዐ ያዕቆብ ምትክ በ1468 ዓም ሲነግሥ ቀጥቅጦ
ገደለውና መጨረሻው ሳያምር ቀረ፡፡
ሦስቱ ደቂቀ ሰይጣን ተግዘውና ተቀጥቅጠው ቢሞቱም በግብር አኽለው፣ በግእዝ አስመስለው
የወለዷቸው ልጆቻቸው ግን ብዙዎች ናቸው፡፡ ሥልጣናቸውን ለራሳቸው መጠቀሚያ፣ የጠሏቸውን ለመበቀያ፣ ለጉቦና መደለያ መቀበያ፣
ለወዳጆቻቸው መጠቃቀሚያ የሚያደርጉ፤ ተሰሚነታቸውንና ቀራቢነታቸውን ተጠቅመው ወንጀለኛውን ንጹሕ፣ ንጹሑን ወንጀለኛ የሚያደርጉ፤
እንዲህ እናደርግሃለን፣ እንዲህ እናስደርግሃለን፣ ከንጉሥ እናጣላሃለን፣ ከክብር እናሳንስሃለን እያሉ ሲያስፈራሩ የሚውሉ አያሌ
ልጆች ዛሬም አሏቸው፡፡
እንደ ወላጆቻቸው እንደ ሦስቱ ደቂቀ ሰይጣን ጊዜያቸው አልቆ በቆፈሩት ጉድጓድ
እስኪገቡ፣ ‹በመረጥሽው ዳኛ ትረች፣ በቆረጥሽው ዱላ ትመች› ነውና ባሠሩት ማሠርያ እስኪታሠሩ፣ ባወጡት መመርያ እስኪቀጡ፣
ባስፈረዱበት ፍርድ እስኪፈረድባቸው ድረስ፣ ‹ደረቴ ይቅላ፣ ሆዴ ይሙላ› ብለው የሚዘባነኑ፤ የማይነካውን ነክተው ኤሌክትሪክ
እስኪይዛቸው ድረስ አርድ አንቀጥቅጥ እንደለበሰ የኦሪት ካህን በየሄዱበት ሲያርዱ ሲያንቀጠቅጡ የሚውሉ፤ ዛሬ ትናንት፣ ነገም
ዛሬ የሚሆን የማይመስላቸው ደቂቀ ሰይጣን ዛሬም አሉ፡፡ ‹የሰው ልጅ ታሪክ የሚመሰክረው ሰው ከታሪክ አለመማሩን ነው›
እንደሚባለው ከትናንቱ ደቂቀ ሰይጣን ያልተማሩ ተረፈ ደቂቀ ሰይጣን ዛሬም አሉ፡፡
ደቂቀ ሰይጣን ስማቸው ማራኪ ነበር፡፡ ዘርዐ ጽዮን ማለት ‹የጽዮን ዘር፣ ልጅ› ማለት
ነው፤ ተዐውቀ ብርሃን ማለት ‹ብርሃን ተገለጠ፣ ታወቀ› ማለት ነው፤ ገብረ ክርስቶስ ማለትም ‹የክርስቶስ አገልጋይ› ማለት
ነው፡፡ ግብራቸውና ስማቸው ግን ፈጽሞ የሚገናኝ አልነበረም፡፡ ዛሬም እንደ ደቂቀ ሰይጣን ማራኪና አጓጊ የሆኑትን የማዕረግና
የሥልጣን ስሞች ይዘው ግብራቸው ግን የሰይጣን የሆኑትን አንዳንድ ኃላፊዎች፣ ባለ ሥልጣናት፣ ባለሞያዎች፣ ተቆጣጣሪዎች፣
ጸሐፊዎች፣ አሳላፊዎች፣ መኮንኖችና ባለሟሎች እኛም
አትዋል ይዋሉብህ አትምከር
ይምከሩ
በቆፈሩት ጉድጓድ ሳይገቡም
አይቀሩ
ብለን ልናሳፍራቸው ልናሸማቅቃቸው፤ ብሎም ለሰው የሚያቀምሷትን ጽዋ ጎንጨት እንዲሏት ልናደርጋቸው ይገባል፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ
መጽሔት የወጣ ስለሆነ በተመሳሳይ ሚዲያ ማቅረብ ክልክል ነው
ዳንኤል እነደምን ዋልክ ደህና ነህ ወይ
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥህ
እኛም በመስሪያ ቤታችን ከሀላፊዎች ጋ እየተመሣጠሩ
አንዱ ያረፍዳል ወይም ይቀራል ሲመጣ ግን ሰዓት ፊርማ
ላይ ይፈርማል፤፤
ሁሉም አርፈሽ ተቀመጭ
እኛም ብዙ እናውቃለን
ብንናገር እናልቃለን ብለን ነዉ ሲሉኝ
እኔ ደፍሬ ብናገር ምን ታመጫለሽ ኄደሽ ተናገሪ
ተባልኩ ለአለቃዉ ብናገር አልማጩን ወስዶ ምንም ስራ
የሌለበት ለአንድ ሰዉ ስራ የሌለበት ቦታ ደርቦ
አስቀመጠው፡፡
እና በዚህ አይነት የሚሠራው እየተጎዳ የማይሠራዉ
ምሽግ ውሥጥ ተደብቆ ሥራ እንዳይለቀቅ የሚረዳው ቤተሰብ ይኖረዋል፤
እየደረሰ ያለውን ግፍ ፈጣሪ ይመልከተው፤፤
ወለተ ሚካኤል
ውነትህን ነው በተለይ መቻሬ ሜዳ የሚፈፀመው ይህ ነው እኔም ከስራ የለቀቅሁት በዚሁ ነው እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው
ReplyDeleteThanks for mentioning the current issue!
ReplyDeleteዛሬም እንደ ደቂቀ ሰይጣን ማራኪና አጓጊ የሆኑትን የማዕረግና የሥልጣን ስሞች ይዘው ግብራቸው ግን የሰይጣን የሆኑትን አንዳንድ ኃላፊዎች፣ ባለ ሥልጣናት፣ ባለሞያዎች፣ ተቆጣጣሪዎች፣ ጸሐፊዎች፣ አሳላፊዎች፣ መኮንኖችና ባለሟሎች እኛም
ReplyDeleteአትዋል ይዋሉብህ አትምከር ይምከሩ
በቆፈሩት ጉድጓድ ሳይገቡም አይቀሩ
ብለን ልናሳፍራቸው ልናሸማቅቃቸው፤ ብሎም ለሰው የሚያቀምሷትን ጽዋ ጎንጨት እንዲሏት ልናደርጋቸው ይገባል፡፡
realy
ReplyDeleteENASTEWIL ! ! ! KALEHIWOT YASEMALIN
ReplyDeletemetasebianetu----for Ethiopian Government Higher officials & pops & Clergies.
ReplyDeleteDn Daniel, it is an amazing article.
ReplyDeleteአትዋል ይዋሉብህ አትምከር ይምከሩ
በቆፈሩት ጉድጓድ ሳይገቡም አይቀሩ
It is well reflecting the current developments in our CHURCH.Continue such reflecting posts to make them learn from their 'evil acts'.It is also a lesson for those who do not perceive the existence of such acts in EOTC.
ReplyDeletethis article is a lesson for all of us but not only for somebody,where ever we are we have to be innocent.beteneshu yetamene bebezu lay yeshomal.
ReplyDeleteGOD BLESS YOU D.Daniel
It is very interesting current issue.
ReplyDeleteI WAS WONDERING WHY YOU DID NOT COMMENT ON THE CURRENT CHURCH ISSUE. IT IS GOOD TO TAKE DEEP BREATH AND SEE ALL SIDES BEFORE COMMENTING. " JORO YALEW YISMA"
ReplyDeletewow best article
ReplyDeleteHello Dn Daniel
ReplyDeleteFirst I appreciate your silence regarding the professor response. Even if you keep silent, he was barked twice. Thus, at this time I think it is better to give him a response that made him learn from his mistakes.
I hope you can do this.
Dear Dn. Daniel,
ReplyDeleteGod bless you for the timey article. I think you should also reflect how we can approach this situation. My fear is that in practice it is so difficult in that way when we are approaching this issues. That means we should be wise enough to reflect to the people, boss and the like their good and bad sides so as for the fuure improvement. So better to say somethig on the handling of these kinds of issues.
kebede
‹የሰው ልጅ ታሪክ የሚመሰክረው ሰው ከታሪክ አለመማሩን ነው› እንደሚባለው ከትናንቱ ደቂቀ ሰይጣን ያልተማሩ ተረፈ ደቂቀ ሰይጣን ዛሬም አሉ፡፡
ReplyDeleteበርግጥም ዛሬ ላይ በደንብ በዝተው እና ተባዝተው አሉ እንጂ በግልጽ የሚታየውም ተስፋ መቁረጥ እና ስር የሰደደ ድህነት በነሱ የተፈለፈሉ ጠንቆቻችን ማሳያዎች ናቸው!
‹የሰው ልጅ ታሪክ የሚመሰክረው ሰው ከታሪክ አለመማሩን ነው›
ReplyDeleteDear Dn Daniel,
ReplyDeleteYesew lej bandem belelame yimarale.
keep up the good work!!
ዛሬም እንደ ደቂቀ ሰይጣን ማራኪና አጓጊ የሆኑትን የማዕረግና የሥልጣን ስሞች ይዘው ግብራቸው ግን የሰይጣን የሆኑትን አንዳንድ ኃላፊዎች፣ ባለ ሥልጣናት፣ ባለሞያዎች፣ ተቆጣጣሪዎች፣ ጸሐፊዎች፣ አሳላፊዎች፣ መኮንኖችና ባለሟሎች እኛም
"አትዋል ይዋሉብህ አትምከር ይምከሩ
በቆፈሩት ጉድጓድ ሳይገቡም አይቀሩ"
ብለን ልናሳፍራቸው ልናሸማቅቃቸው፤ ብሎም ለሰው የሚያቀምሷትን ጽዋ ጎንጨት እንዲሏት ልናደርጋቸው ይገባል፡፡
interesting. kalehywot yasemalen. ""fetsamehen yasamerelehe"""
ReplyDelete.
ደቂቀ ሰይጣን ስማቸው ማራኪ ነበር፡፡ ዘርዐ ጽዮን ማለት ‹የጽዮን ዘር፣ ልጅ› ማለት ነው፤ ተዐውቀ ብርሃን ማለት ‹ብርሃን ተገለጠ፣ ታወቀ› ማለት ነው፤ ገብረ ክርስቶስ ማለትም ‹የክርስቶስ አገልጋይ› ማለት ነው፡፡ ግብራቸውና ስማቸው ግን ፈጽሞ የሚገናኝ አልነበረም፡፡ ዛሬም እንደ ደቂቀ ሰይጣን ማራኪና አጓጊ የሆኑትን የማዕረግና የሥልጣን ስሞች ይዘው ግብራቸው ግን የሰይጣን የሆኑትን አንዳንድ ኃላፊዎች፣ ባለ ሥልጣናት፣ ባለሞያዎች፣ ተቆጣጣሪዎች፣ ጸሐፊዎች፣ አሳላፊዎች፣ መኮንኖችና ባለሟሎች እኛም
ReplyDeleteአትዋል ይዋሉብህ አትምከር ይምከሩ
በቆፈሩት ጉድጓድ ሳይገቡም አይቀሩ
ብለን ልናሳፍራቸው ልናሸማቅቃቸው፤ ብሎም ለሰው የሚያቀምሷትን ጽዋ ጎንጨት እንዲሏት ልናደርጋቸው ይገባል፡፡
bsitan yizew bizu bete kiristianin yemibedlu bizu alu sirachew enkwan papas,moneksie le bete kirstian tera diakon enkwan mehon yemaychlu dekike seitan be ewnet eyangebegebun new Amlake kidusan yesrachewn aynsachew minkusna kerto yagebu betekirstianin bimeru sayshal aykerm ketikit abatoch besteker monekisie le mimenna lebete kirstian tenk nachew chekagnoch le genzeb ena sigawi filagot yashenefachew bete mekdesun yemiyasdefru kifuwoch bizu dekike seitan alu Amlak tigstu beza
ReplyDeleteዳኒ፡ ያለው ግፍ ተነግሮ ያልቃል ብለህ ነው
ReplyDeleteከብዙ ኣመታት በዋላ ቤተሰቦቼን ለማየት ከሰሜን ኣሜሪካ ወደ ኣገሬ ከወራት ወፊት ሄጄ ነበር፥፥
ኣንዲት ኣምላክን የምትፈራ ትጉ ሰራተኛ፤ ብቃቱና ትምህርቱ ኖሮዋት በመስሪያ ቤትዋ ማናጀር የወነች ልጅ ፡ደቂቀ ሰይጣን ምን አንደሚያደርሱባት ስትነግረኝ መጣም ነው ያዘንኩት፥፥ ከሌላው ሰው በተለየ ውኔታ በኣጭር ጊዜ ወስጥ ካልተስተናገደ ከቤተመንግስት ኣስደውሎ ስራዋን በ24 ሰዓት ወስጥ አንደምታጣ ዘሩን ተመክቶ የተናገራት ሰው ኣለ፥ ሌላው ደግሞ ካለችበት ፬ኛ ፎቅም አንደሚወረውራት ያስፈራራም ኣለ፥፥
ፓርቲያቸውን ፤ ስራቸውን ወይም ደግሞ ዘራቸውን ተመክተው ደቂቀ ሰይጣን ምን አንደሚያደርሱ ተነግሮ የሚያልቅ ኣይመስልም፥፥ በኔ ኣጭር ቆይታ አንካን የደረሰው ሌላ ቀን ምን ኣልባት አዚው ኣቀርበው ይሆናል፥፥
Good thought !!
ReplyDeleteSometimes silent is good answer. We need you for the rainy day. Don't get wasted
So early in the long battle.
Stay bossed !!
zeria yakob! I DID NOT KNOW ANYTHING ABOUT HIM. THANK U SO MUCH. BUT I HAVE ANOTHER Q. ABOUT HIM
ReplyDelete1.LEMESQEL LESIHIL LE DINGIL MARIAM SIGDETIN YEJEMERENA YASJEMERE IRSU NEW YIBALAL. IS THAT TRUE? THANKS DANI
yes he is.
DeleteAbesku geberku fetariye hoy bemalawqew neger gebiche yesegedkutin sigdet hulu atiqteribign
DeleteThanks
ReplyDeleteየሰው ልጅ ታሪክ የሚመሰክረው ሰው ከታሪክ አለመማሩን ነው›
ReplyDeleteለሚገባው ትልቅ ትምህርት ነው፡፡
እናመሰግናለን!!!!
የሰው ልጅ ታሪክ የሚመሰክረው ሰው ከታሪክ አለመማሩን ነው›
ReplyDeleteለሚገባው ትልቅ ትምህርት ነው፡፡
እናመሰግናለን!!!!
"The Untouchables"
ReplyDeleteዲን ዳንኤል፣ ያነሳኸው ነጥብ እጅግ በጣም ወቅታዊ ነው። ነገር ግን በዚህ መልኩ እስከ መቼ ነው የምንቀጥለው? በምሳሌ፣ በሾርኔ፣ በጎሜ መሄዱን ትተን ፊት ለፊት መግጠም የለብንምን? ጌታችን ‘‘ቤቴ የጸሎት ቤት...‘‘ ብሎ ነበር እኮ በጅራፍ እየገረፈ ያስወጣቸው። እንዲሁ በዚሁ ከገፋን፤ እነሱም ተንኮሉን፣ ሸሩን፣ መከፋፈሉን፣ ማባላቱን በረቀቀና በመጠቀ መልኩ ይቀጥሉበታል። መስቀሉን ጨብጠው፤ካባውን ለብሰው፤ ቆቡን አጥልቀው ለጀሮ የሚሰቀጥጠውን ውሸት ሲያዥጎደጉዱት ምንም አይነት ስሜት አይታይባቸውም። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል እንደሚባለው፤ አሁን አሁን አነሱም እውነት መሳይ እውነት ላይ የሙጥኝ ብለዋል። እኒህ ሰዎች እንኳንስ ለሌላው ብርታተ መንፈስ ልዕልና ሊሰጡ ይቅርና ልእነሱ ያስፈልጋቸዋል። መንፈሳዊ ሕክምና ውስጥ ገብተው ወደ ልቦናቸው ሊመለሱ ይገባቸዋል። ጠብቁ ተብለው ለተሾሙለት ምዕመናን ደንታ ቢስ ሆነው ማዬት እንዴት ከባድ ነገር ነው! በአይነ ስጋቸው ላይ የተለጠፈውን መርገምት፤ የድንግል ማርያም ልጅ ይግፈፍላቸው፤ ለእኛም ወኔውንና አንድነቱን አድሎ ቤቱን ለመጠበቅ ያብቃን!
ReplyDeleteDn Daniel Egziabher yebarkeh.
ReplyDeleteመቼም የሰው ልጅ በሁለት ተቃራኒ ሃይሎች ፍጭት ተወጥሮ የሚኖርና የእነዚህም ሁለት ተቃራኒ ሃይሎች መሳሪያ የሆነ ፍጡር ነው፡፡እነዚህም ሁለት ተቃራኒ ሃይሎች የእርኩስ መንፈስ ሃይልና በተቃራኒው ያለው የቅዱስ መንፈስ ሃይል ናቸው፡፡መጠናቸው (degree) ይለያይ እንጂ ሁሉም የሰው ልጅ የእነዚህ ሁለት ተቃራኒ ሃይሎች ማደሪያ ነው፡፡ዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም አሁን ባለው በጥሩም ሆነ በመጥፎ እይታው ከደረሰብት ከፍተኛ ደረጃ ያለው የገንዘብ የሥልጣን የእውቀትና የሚሊታሪ አጠቃላይ የሃይል ምንጭም ከእነዚህ ሁለት ተቃራኒ ሃይሎች አንፃር ሊቃኝ የሚገባው ነው፡፡
ReplyDeleteበሀገራችንም ያለው አገዛዝና አጠቃላይ ሁኔታም ከዚህ አለም አቀፋዊ እውነታ አንፃር የሚቃኝ ጭምር ነው፡፡የሃይማኖቱም ውስብስብ ሁኔታ በራሱ በዚሁ አጠቃላይ ሰፊና ጥልቅ ተፅእኖ ፈጣሪ በሆነው የግሎባል ካፒታሊዝም ማእቀፍ ውስጥ ያለ ነገር ነው፡፡በእርግጥ ብዙውን ጊዜ በተለምዶ ሃይማኖትና ፖለቲካ አይገናኝም ቢባልም ቅሉ ግን በነባራዊው እውነታና አለም ውስጥ ግን ሃይማኖትና ፖለቲካ የሚገናኙበትም የማይገናኙበትም ሁኔታ አለ፡፡ምድራዊው መንግስት የሰማያዊው መንግስት ነፃብራቅ ነው ብሎ ለሚያምንና ለሚያስብ ሰው ሃይማኖትና ፖለቲካ በጣሙን ይገናኛሉ፡፡ምክንያቱም በሃይማኖት ውስጥ የሚታመነው ፅድቅ ኩነኔ ፍርድ ይቅርታ ወዘተ በራሱ ፖለቲካዊ ነውና፡፡እንደዚሁም በፖለቲካውም ውስጥ ስንገባ ፖለቲካው በራሱ የራሱን የሚያምንበትን የጠነከረ አይዲኦሎጂ ስለሚያራምድ ሃይማኖታዊ(Religious and Dogmatic) እንዲመስል ያደርገዋል፡፡ለምሳሌ እውነትም ይሁን ሀሰት የመለስ ራእይ ወይንም የመለስ ሌጋሲ የሚባል ነገር ፈጥሮ በህብረተሰቡ አስተሳሰብና ሰሜት ውስጥ በስፋትና በጥልቀት ማስረፅ ፖለቲካውን ልክ እንደ ሃይማኖት የማይናወፅ ተአማኒነት እንዲኖረው በሰዎች ልቦና ውስጥ መሰረት የማስያዝ አካሄድ ነው፡፡ይህንን ስናይ ደግሞ ፖለቲካ ሃይማኖት ሆኖ ያርፈዋል፡፡ዞሮ ዞሮ ግን ፖለቲካንም ሆነ ሃይማኖትን ስናራምድ እኛ አንድ የሆነ ነገር ላይ ትክክል ነው ብለን በያዝነው አንድ የተወሰነ እምነትና እውነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
በሌላ በኩል ስንሄድ ደግሞ አይሁድ ክርስቶስን ለመፈተን ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባልን ብለው ያነሱት ሁለት ስለት ያለው ፈታኝ ጥያቄም ፖለቲካዊም ሃይማኖታዊም ነበር፡፡ነገር ግን ክርስቶስ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሄርን ለእግዚአብሄር ብሎ የሚደንቅ ትክክለኛ መልስ ሲሰጥ ሸማ በየፈርጁ ይለበሳል አይነት ነው፡፡ነገር ግን አሁን በዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም በሀገራችንም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው ነባራዊ እውነታ ሃይማኖትን ለመቆጣጠር ፖለቲካውን መቆጣጠር ፖለቲካውንም ለመቆጣጠር ሃይማኖቱን መቆጣጠር የሚል እይታ ያነገበ ይመስላል፡፡በእርግጥ ፖለቲካ ሃይማኖት ኢኮኖሚም ሶስቱም እርስ በርስ የተሳሰሩ ናቸው፡፡አብርሃም እምነቱን በምግባር ገለፀው እንደተባለው ሁሉ ከውስጥ በልብ ያለው እምነት ከውጪ በሚታየው በምግባር እንዲገለፅ ነውና እንደዚሁም ከውስጥ እናራምደዋለን የምንለው ሃይማኖትና ፖለቲካውም ከውጪ በሚታየው በኢኮኖሚው እንዲገለፅ እየሆነ ነው፡፡የጋራ የሆነው ሰብዓዊነታችን ደግሞ ፖለቲካና ሃይማኖቱ የሚገናኙም ሆነ የማይገናኙ ቢሆን የዚህ የመገናኘታቸው ጉዳይ በስተመጨረሻ በዚህ የጋራ በሆነ ሰብዓዊነታችንና ህገ-ልቦና በሚባለው ነገር ሊፈተኑና ሊመዘኑ ግድ ይላል፡፡ስለዚህም ማንም በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ ሽፋን የጋራ በሆነው ሰብዓዊነታችን ላይ ወንጀል ሊፈፅም አይቻለውም፡፡ምክንያቱም መልካም ስራና ክፉ ስራ በተፈጥሮ ባለን ህገ-ልቦናችን ውስጥ ባለው የማይጠፋ ፅላት ላይ እንዲፈተንና እንዲመዘን ሆኖ የተቀረፀ ዘላለማዊ ነገር ነውና፡፡ስለዚህም ለምንሰራው ጥሩም ሆነ መጥፎ ስራ የገዛ ህሊናችን ተቀዳሚው ዋና መዛኝና ፈራጅ ዳኛ ነው፡፡በሃያልነት የሰለጠኑብን ገዥዎቻችንም ሃያልነታቸው ከየትኛው ወገን እንደሆነ ይመርምሩት፡፡ማለትም ከእርኩስ መንፈስ ሃይል ነው ወይንስ በተቃራኒው ካለው የቅዱስ መንፈስ ሃይል ነው?ነገሮችም በስተመጨረሻ የሚመዘኑት በዚህ እይታ ነውና፡፡እንደ እኔ እይታ በቅዱስ መንፈስ ሃይል ውስጥ ያለው ጊዚያዊ ደካማነትና ውድቀት በተቃራኒው ካለው በእርኩስ መንፈስ ሃይል ውስጥ ካለው ጊዚያዊ ሃያልነትና ስኬት በእጅጉ የተሻለ ነው፡፡ምክንያቱም ፀጋዬ ይበቃሃልና ሃይሌ በድካምህ ይገለጣል የሚለው መፅሃፍ ቅዱሳዊ አባባል በተቃራኒው ካለው ሃጥአን ስለመጨረሻ የማይቀር ጥፋታቸው ሲባል እጅግ የማይደፈሩ ሃያላን ይሆናሉ ከሚለው መፅሃፍ ቅዱሳዊ አባባል በእጅጉ የተሻለ ነውና፡፡ስለዚህም እያንዳንዳችን ከየትኛው ወገን ነን? ከየትኛው ወገንስ መሆን እንፈልጋለን?እንዲያው ገበያው ተመቸ ተብሎ ሁሉን መግዛት መሸጥ ማግበስበስስ ተገቢ ነውን?
ምናለ የምንበላውን ያህል ብንቆርስስ?ደግሞስ እኛ በከንቱ ደክመን ስንዋትት ኖረን የምናከማቸውን ሀብት ሌሎች ዘና ብለው እንደኛ ያልደከሙበት እንዲበሉት ይሆን ዘንዳ ይህ ሊሆን እንደሚችል ገምተን አናውቅምን?አንዱ ሊደክምና ሊያከማች አንዱ ሊበላ ሁለቱንም ህይወትና ፈጣሪ ሁለቱንም በየፊናቸው ያሰማራቸዋል፡፡አዎ የተራቡትን በቸርነቱ አጠገባቸው ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው የተባለው ለዚህ ሳይሆን ይቀራልን፡፡ከሁሉ የቸገረው ግን በዚህች ሀገር ውስጥ በቆየው የኢትዮጵያዊነት ስሜት ሃብታሙም ፈጣሪን የሚፈራ ጥሩ ሃብታም ድሃውም ፈጣሪን የሚፈራ ጥሩ ድሃ ሆኖ እንደ ድሮው እንዳይኖር መሆኑ ነው፡፡ይህ ደግሞ የጥፋት ጥፋት ነው፡፡ለእኔ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትና ሃይማኖታችን ብዙም የማይለያዩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡እናም ኢትዮጵያዊነታችን ጥልቁና ሰፊው ድርና ማግ እርስ በርስ ማስተሳሰሪያችን የሆነ ዋናው ሀብታችን ነው፡፡በዚህ ዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም የደቂቀ ሰይጣንና የባእዳን ሃይሎች የረቀቀና የተቀነባበረ ዋና የጥፋት ሰላባ የሆነው ይህ የሚያስተሳስረንና አንድ የሚያደርገን ታሪካዊ የኢትዮጵያዊነት ፀጋችን ነው፡፡ብኩርናውን ለምስር ወጥ እንደሸጠው ኤሳው እኛም በደቂቀ ሰይጣን ተገፋፍተን የቆየ የኢትዮጵያዊነት ብኩርናችንን እና ፀጋችንን ለሆዳችን እንዳንሸጥ ፈጣሪ ይርዳን፡፡ስለዚህም አሁን ለጊዜው የደፈረሰው እስኪጠራ ሃይማኖታችን ፖለቲካችን ኢኮኖሚያችን ወዘተ ኢትዮጵያዊነት ይሁን፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
Thank you! Dn. Daniel.
ReplyDeleteI respect you &your Idea but is it all we can say about current issue? I do no think, We have better wake up and stand for our church other wise it will be a history soon. I felt it as a human but WE DO NOT KNOW ABOUT GOD'S PLAN!
አሜን! እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
ReplyDeleteThat is true
ReplyDeleteእውነት ብለሃል አምላካችን እንደ ቸርነቱ አስተዋይ ልቦና ይስጠን አሜን
ReplyDeleteድንቅ ፅሁፍ ነው፡፡ እውነታውን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ፡፡
ReplyDeleteDani TEBAREK! Ketach keqebele tataqi esike Hager memrat,Kesenbet timihirtbet esike QIDUS SINODOS Tesegisigew selam lehagerna lewegen yenesu Zarem Aluuuuu!
ReplyDeletehay simply 10q
ReplyDeleteyemengistn habtina nibret enaskebralen eyalu bemesria betachew yemihonewn mayet kehlina belay new
ReplyDeleteበእውነት ፍንትው ብሎ በሚታይ ግዘፍ ነስቶ በሚጨበጥ ሁኔታ በወንድማችን በዲ/ን ዳንኤል ተጻፈ የሚገርምህ አሁን ያሉት ደቂቀ ሰይጣን የረቀቁ ከእኛ በላይ አዋቂ ለአሳር የሚሉ ይሉኝታ የሌላቸው በግድ የእነሱ ፖለቲካ አጫፋሪ ካልሆንክ እንዴት እንደገዘገዙህ ሳታውቅ ወድቀህ ትገኛለህ ብትጮህ ሰሚ የለ ግን እንደ ቅዱስ አባት ነቢዩ ኤልሳዕ ከእኛ ጋር ያለ ከእነርሱ ይበልጣል የእግዚአብሔር ፍርዱ አይዘገይም የልቦናቸውን ዓይን ያብራላቸው ምን እንላለን
ReplyDeletedani it is awesome.balesiltanochu yemewesen siltanachewin/decision maker
ReplyDelete-lekadre
-ledelala
-lebalehabit
asalifew setewal.our decision makers are the above silistu dekik nachew.ayayazachewin ayitew chibtuachewin/decision maker netekuachew.Hizibu merotal meriwun yibelal.fasil.
ጥሩ ዕይታ ነው፡፡ ወድጄዋለሁ፡፡ ግን ሰይጣን ሄዋንን የምድር እና የሰማይ ንግስት ያለበትን ስፍራ ከቅዱሱ መፅሐፍ ላይ ሰፍሮ አላገኘሁትም፡፡ አንዴት ነው መፅሐፉ ሲጻፍ የተዘለሉት ነገሮች በእረሶ ዘንድ አሉ ማለት ነው?
ReplyDelete