Wednesday, March 27, 2013

የተሳሳቱ ስልኮች


click here for pdf
‹‹አንድ ቀን ነው፤ ባለቤቴ ከበረራ የምትመለሰው ሌሊት ስለሆነ በግማሽ ልቤ ተኝቼ ስልኳን እጠብቅ ነበር፡፡ እኩለ ሌሊት ላይ ስልኬ ጮኸ፡፡ እኔም ቁጥሩን ሳላይ እንዴው በዳበሳ ስልኩን አነሣሁት፡፡ ‹ሃሎ አያ ግርማ› አለኝ የደወለው ሰው፡፡ ‹ተሳስተዋል ጌታዬ፤ ይህ የአያ ግርማ ስልክ አይደለም› ስል መለስኩለት፡፡ ‹ኧረ እባክዎን ፈልጌያቸው ነው› አለኝ፡፡ እኔም መሳሳቱን ደግሜ አስረዳሁትና ስልኩን ዘጋሁት፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በምሽት እየደወለ ‹አያ ግርማ የሉም› የሚለኝ ሰውዬ ሊያቆም አልቻለም፡፡ እየቆየሁ የስልክ ቁጥሩን ሳውቀው ማንሣት አቆምኩ፡፡ ነገር ግን ልጆቼ ወይም ባለቤቴ ስልኩን ሲያነሡት አሁንም ‹አያ ግርማ የሉም› ይለኛል ያ ሰው፡፡ ደጋግሜ መሳሳቱን ነግሬዋለሁ፡፡ ግን የሚሰማ አልሆነም፡፡ እንዲያውም ጓደኞቼ መቀለጃ አድርገውት ሲያገኙኝ ‹አያ ግርማ› ይሉኝ ነበር፡፡
አንዳንዴ ቀን፣ ብዙ ጊዜ ግን ሌሊት ይደውላል፡፡ አላነሣ ስለው በሌላ ስልክ ቀይሮ መደወልም ጀምሮ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ ባለቤቴ ከበረራ የምትመለሰው ሌሊት ስለሆነ ስልኬን አልዘጋውም፡፡ ሰውዬው አሰለቸኝ፡፡ አንድ ሌሊት በሰባት ሰዓት አካባቢ በሌላ ስልክ ደወለና እንደለመደው ‹አያ ግርማ የሉም› ሲለኝ ድምፄን አስተዛዝኜ ‹አያ ግርማኮ ዐረፉ› አልኩት፡፡ ጩኸቱን ለቀቀው፡፡ ቤቱን ሲያደባልቀው ይታወቀኛል፡፡ ከዚያ አንዲት ሴትዮ ስልኩን ተቀበሉና ‹መቼ ዐረፉ› አሉኝ ‹ትናንት ዐረፉ› አልኩ በተሰበረ ድምጽ፡፡ እርሳቸውም ‹በሉ አይዟችሁ እግዚአብሔር ያጽናችሁ› ብለው ዘጉት፡፡ ከዚያ በኋላ ዐረፍኩ፡›› ብሎ ያጫወተኝ አንድ ወዳጄ ነው፡፡
 የሞባይል ስልክ ከተስፋፋ ወዲህ የተሳሳቱ የስልክ ጥሪዎች የዕለት ተዕለት ገጠመኞቻችን ሆነዋል፡፡ አንዳንዱ ሰው የደወለበት ቦታ ትክክል መሆኑን እንኳን ለማረጋገጥ አይፈልግም፡፡ ልክ ስልኩ እንደተነሣለት ወደ ጉዳዩ ይገባና ይዘከዝከዋል፡፡ የተደወለለት ወገን ግራ ገብቶት ‹የት ነው የደወሉት› ሲለው ነው ‹እገሌ አይደለህም እንዴ› ማለት የሚጀምረው፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ይበልጥ የሚወሳሰበው ደግሞ የሚደወልለት ወገን ተመሳሳይ ጉዳይ ካለው ነው፡፡
አንዳንዱም የደወለበትን ቦታ ሳያውቅ ምሥጢሩን የሚዘከዝክ አለ፡፡ አንዱ ይደውልልኛና ‹እኔ የምልህ የቤቱን ዋጋ በምን ያህል ልቀንሰው? ከፍ ካደረግነው ቀረጥ እንበላለን፡፡ እንትናን ስጠይቀው እነርሱም በግማሽ ቀንሰው እንደ ተዋዋሉ ነግሮኛል፡፡ እና በሰባት መቶ ሺ ብናደርገውስ?› አለና ዘከዘከልኝ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ ‹ማን ጋ ነው የደወሉት?› ብዬ ጠየቅኩት፡፡ ‹እንትና አይደለህም እንዴ› ሲል በድንጋጤ ድምጽ መለሰልኝ፡፡ ‹አይደለሁም ተሳስተዋል› ስለው ይቅርታ እንኳን ለመጠየቅ ልብ ሳያገኝ በድንጋጤ ዘጋው፡፡ እርግጠኛ ነኝ ለጥቂት ሰዓታት ‹ምናልባት ሀገር ውስጥ ገቢ ይሆን የደወልኩት? አሁን በስልክ ተከታትለው ቢይዙኝስ› እያለ ሳይጨናነቅ አይቀርም፡፡
የተሳሳቱ ስልኮች ያጣሏቸው ፍቅረኛሞችና ባለትዳሮችም አሉ፡፡ አንዳንድ ደዋይ የደወለበትን ቦታ ሳያጣራ ለፍቅረኛ ወይም ለትዳር አጋር የሚባለውን ሁሉ ያወርደዋል፡፡ አንድ ጓደኛዬ አንድ ማለዳ ልብሱን እየለበሰ ሞባይሉ ይጮኻል፡፡ እርሱም ሸሚዙን ለመልበስ እንዲያመቸው ስልኩን ‹ስፒከሩ› ላይ ያደርግና ‹ሃሎ› ይላል፡፡ ከወዲያ የደወለችው ሴት ‹አንተ ምን ብትንቀኝ ነው ቀጥረኽኝ የምትቀረው? ሚስትህ እንዳትሰማብህ ብለህ ነው አይደል? እርሷ የምትሄድ መስሎህ ቀጠርከኝ፣ ስትቀር ዘግተህኝ አደርክ፡፡ ባለጌ ነህ ባለጌ› ብላ ጮኸችበት፡፡ እርሱም ሚስቱም አመዳቸው ቡን አለ፡፡ ‹የት ነው የደወልሽው› አለና ጠየቃት፡፡ ‹አንተ ጋ ነዋ፤ አንተ ጋ፡፡ ልትሸውደኝ ፈለግክ፡፡ ሚስትህ አጠገብህ አለች መሰል› አለችውና ጠረቀመችበት፡፡
እውነትም ሚስቱ ትናንት ፊልድ ልትወጣ ነበረ፡፡ በአጋጣሚ የአውሮፕላን ትኬት ጠፍቶ ነው የቀረችው፡፡ ሚስቱ ግራ ገባት፡፡ ባሏን ታምነዋለች፡፡ ግን ይህች ሴት እንዴት የርሷን መሄድ ዐወቀች፡፡ እንዴትስ አሁን ከአጠገቡ መሆንዋን ዐወቀች፡፡ ልቧ እየተምታታባት ፈዝዛ ቀረች፡፡ ባል ደዋይዋ በስሕተት መደወሏን ለማስረዳት ማለ ተገዘተ፤ ሚስትም ለማመንም ለመካድም ተቸገረች፡፡ ወደ ደዋይዋ ዘንድ መልሶ ሲደውል ስልኳን አታነሣውም፡፡ ይህ ችግር የተፈታው የእርሷ እኅት ለሴትዮዋ ደውላ ካገኘቻትና ደዋይዋ የደወለችው በስሕተት መሆኑን፤ እርሱንም ፈጽማ እንደማታውቀው ካረጋገጠች በኋላ ነበር፡፡ የደወለችበትን ሰው ስሙን እንኳን አታውቀውም፡፡
ሰው የደወለበትን ቦታ ሳያረጋግጥ እንዴት መርዶ በስልክ ያረዳል? አንዳንዴኮ አጋጣሚዎች የሚፈጥሩት መገጣጠም አለ፡፡ አንድ የታክሲ ደንበኛዬ እንዲህ አጫውቶኛል፡፡ አንድ ቀን ለታክሲ ተራ ይዞ እያለ በሞባይሉ ይደወልና፡፡ ‹የሳሙኤል ጓደኛ ነህ አይደል› ይለዋል፡፡ ‹አዎ፣ ደኅና አይደለም እንዴ› ይላል ደንግጦ፡፡ ‹‹አይ እርሱስ ደኅና ነው፤ አባቱ ስላረፉ ጓደኞቹ ቀስ ብላችሁ እንደታረዱት ነው›› ይለዋል፡፡ እርሱም ስለደነገጠ የደዋዩን ስም እንኳን አልጠየቀም፡፡ ሌሎቹን ባለ ታክሲዎች ሰብስቦ ይነግራቸዋል፡፡ እነርሱም ተመካክረው በጠዋቱ ቤቱ ይሄዳሉ፡፡
በማለዳ ባለ ታክሲዎች በቤቱ የተሰበሰቡበት ሰው ግራ ይገባዋል፡፡ ደግሞም ሁሉም ጋቢ ለብሰዋል፡፡ ‹ምን ችግር ተፈጠረ?› ይላል ሳሙኤል፡፡ መጀመርያ መርዶውን የሰማው ባለ ታክሲም ‹አይ አባትህ ስላረፉ ልናጽናናህ መጥተን ነው› ይለዋል፡፡ ሳሙኤል ግራ ገባው፡፡ ‹የኔ አባት› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹አዎ ትናንት ተደውሎ ተነግሮን ነው› ይላል ባለ ታክሲው ጓደኛው፡፡ ሳሙኤል በግርምት ሁሉንም ያያቸዋል፡፡ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ውስጠኛው ክፍል ሲገባ ተከትለውት ይገባሉ፡፡ በድንጋጤ በራሱ ላይ አደጋ የሚፈጥር መሰላቸው፡፡ ሳሙኤል አንድ በር ሲከፍት አንድ አረጋዊ ሰው ጋቢያቸውን ለብሰው ዳዊት ይደግማሉ፡፡ ‹አባቴኮ ይኼውና› ይላቸዋል፡፡ መርዶ አርጂዎችም ይደነግጣሉ፤ ግራም ይጋባሉ፡፡
ያ መጀመርያ ወሬውን ያመጣውን ባለ ታክሲ ይጠይቁታል፡፡ እርሱም በርግጠኛነት መስማቱን ይምላል፣ይገዘታል፡፡ የሰውዬውን ስምና ስልክ ግን አልያዘውም፡፡ ክፋቱም ከሰውዬው ስልክ በኋላ ብዙ ስልክ ስላስተናገደ ለመለየት አልቻለም፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ድንጋጤው ወደ ጨዋታ፣ ከዚያም ወደ ቀልድ ተቀይሮ ቁርስ በልተው መውጣታቸውን ነግሮኛል፡፡ እዚህ ያለ መርዶው የደገጠ ሰው እንዳለ ሁሉ፤ ሌላ ቦታ ደግሞ ተደውሎለታል ተብሎ በመቅረቱ የሚታማ ይኖራል፡፡
ደውሎ ‹ማነህ› የሚልም አለኮ፡፡ ‹አንተ ማን ብለህ ደወልክ› ሲሉት ‹አንተ ራስህ ማነህ› ብሎ የሚያፋጥጥ፡፡ ኧረ ከዚህ የከፋውም የደወለበትን ቦታ ሳያረጋግጥ ቀልድ ይቃጣዋል፡፡ የተደወለለት ሰው ግራ ሲገባውና ሲናደድ ‹እኔን አታውቀኝም› ብሎ የልጅ ቀልድ የሚቀልድ ሞልቷል፡፡
የደወልነው ስልክ በቴክኒክ ምክንያት ወይም በራሳችን ስሕተት ምክንያት ያልታሰበ ቦታ ሊገባ ይችላል፡፡ ስሕተቱን በጊዜ ለማረምም ሆነ በተሳሳተ ስልክ ላይ ብዙ ወጭ ላለማውጣት፤ ከዚያም አልፎ በሌላው ሰው ሕይወት ውስጥ ችግር ላለመፍጠር የስልክ አጠቃቀም ሥነ ምግባር ወሳኝ ነው፡፡
እስኪ ስንቶቻችን ከደወልን በኋላ ሰላምታ እናቀርባለን? ስንቶቻችንስ የደወልንበት ቁጥር ትክክል መሆኑን እናረጋግጣለን? በስልክ ግንኙነት ውስጥ ‹ሃሎ› ማለት ብቻ አይበቃም፡፡ ቢቻል ‹ጤና ይስጥልኝ› ብሎ ‹የእገሌ ስልክ ነው?› ብሎ ማረጋገጥም ያስፈልጋል፡፡ ስልኩ እንደተነሣ ‹እገሌ ወይም እገሊት የለችም› ብሎ ማፋጠጥ ‹እገሌ ነህ አይደል› ብሎ ማንጓጠጥም ሥነ ምግባራዊ አይደለም፡፡ አንዳንዱ ሰውም ያለጠበቀው ሰው ሲያነሣው ይቅርታ እንኳን አይጠይቅም፡፡ ጆሮ ላይ ድርግም ያደርገዋል፡፡ ይህም አንዳንድ ሰዎችን የማያውቁትን ስልክ እንዳያነሡ እያደረጋቸው ነው፡፡
ሰው በተናደደ ጊዜ ስልክ ባይደውል ይመረጣል፡፡ በአካል ግንኙነት ወቅት በእጅ ስንዛሬ፣ በፊት ገጽታና በዓይንና ጥርስ ሁኔታ ብዙ መልእክቶችን አብሮ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡ በስልክ ግን ድምጽ ብቻ ነው ያለው፡፡ እንዲህ ሲሆን ደግሞ ደዋዩ በቁጣ ስሜት ምክንያት ሊሳደብ፣ ክፉ ቃል ሊወጣው ወይም አላስፈላጊ ነገር ሊናገር ይችላል፡፡ ይህንን ያደረገው የተሳሳተ ስልክ ላይ ከሆነ ደግሞ በተቀባዩ ላይ የባሰ ንዴት ይፈጥራል፡፡ ማን ያውቃል አንዳንድ ጊዜ የምንፈልገውን ቁጥር ከስልክ መዝገባችን ነክተን ስንደውል በስሕተት የላይኛውን ወይም የታችኛውን ነክተን እንደውል ይሆናል፡፡ ታድያ ያ ወዳጃችንን እንዲያ በስድብና በቁጣ አጥረግርገነው መልሰን እንዴት ፊቱን እናያለን?
ፈረንሳዮች በባህላቸው ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋቱ 3 ሰዓት ሰው ጋር ስልክ አይደውሉም ይባላል፡፡ የኛ ባህል ምን ይላል? ዕረፍት ማለት የቢሮን ሥራ ወደ ቤት ማምጣት አይደለም፡፡ ዕረፍት ማለት የኩነት ለውጥ ነው፡፡ ገዳም ወርደንም፣ መዝናኛ ቦታ ገብተንም፣ ቅዳ ውስጥ ሆነንም፣ አልጋ ላይ ተጋድመንም፣ ከቤተሰብ ጋር ከብበንም አሁንም ሞባይሎቻችን ሥራቸውን ካላቆሙ ዕረፍት ምኑ ላይ ነው? በተለይ ደግሞ በምሽት ለሚደወሉ ስልኮች አንዳች የእግድ የመግባቢያ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የሌሊት ስልኮች የትዳር አጋርን፣ ልጆችንና አልፎ አልፎም መላ ቤተሰብን የሚበጠብጡ ናቸው፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ፣ አደጋ ተከስቶ ካልሆነ በቀር ከምሽቱ አራት ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ሰው ጋር ስልክ መደወል በባህላችን ነውር መሆን አለበት፡፡
ግድግዳቸው ከሰንበሌጥ የማይሻል አንዳንድ ቤቶች ደግሞ አሉላችሁ፣ ጎረቤት የሚያወራውን ሁሉ እንደ መዳብ ሽቦ የሚያስተላልፉ፡፡ ቀን እንኳን ብዙ ጩኸት ስላለ ብዙም አይሰማም፡፡ ሌሊቱ ግን ጸጥ ስለሚል በስልክ የሚወራው ሁሉ ጎረቤት ተሻግሮ በማግስቱ የቡና አጀንዳ ይሆናል፡፡ አንዱም ለዚህ ነው በስልኮች ላይ የሰዓት እላፊ መጣል ያለበት፡፡
ምንም እንኳን ስልክ ሀገራችን ከገባ ከመቶ ዓመት በላይ ቢሆነው፣ የስልክ ሥነ ምግባራችን ግን ገና ያልለየለትና የተደባለቀ ነው፡፡ ለፊት ለፊት ግንኙነት ብዙ ወጎችን በዘመናት ቀምረናል፡፡ ስልክ ግን ገና አልተቀመረለትም፡፡ ምን ተብሎ ንግግር ይጀመር? ምን ተብሎ ያብቃ? ስሕተት ሲፈጠር ምን እንበል? የትኛውን ጊዜ ከስልክ ነጻ እናድርገው? ልጆቻችን ስልክ መያዝ ያለባቸው ከስንት ዓመት ጀምረው ነው? ስልክ እና ዕረፍት እንዴት ይስማሙ? ስልክና የእምነት ቦታዎችስ? እና መሰል ጉዳዮች ማኅበረሰባዊ ውይይቶችን ይፈልጋሉ፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ በመሆኑ በሌላ ሚዲያ ማውጣት ክልክል ነው

41 comments:

 1. በጣም አስተማሪ ፅሁፍ ነው እኔ አንድ የታዘብኩተ ነገር ሰዎች በሕዝብ ስልክም ሆነ በሱቅ ስልክ ደውለው ሲጠቀሙ አጠገባቸው ቋሞ አለማዳመጥ፣ ስልክ ሲደውሉ ሠላምታ ሰጥቶና ስምን ጠይቆ የራስ ማንነት አስተዋውቆ መጀመር ፣ ስሜታዊ ሆኖ ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ፣ መነገር የማይገባቸውን ቃላት መናገር ፣ነገ የሚፀፅትና የሚጎዳን ነገር በስልክ ማስተላለፍ ሊታረሙ የሚገባቸው ነው እያንዳንዳችን እስኪ ስልክ ስናነጋግር በአካል ተገናኝተን ማውራት የሚገባንን ሁሉ ነገር በታከሲ ውስጥ የምናወራ ወዘተ ስልክ እኔ እንደሚገባኝ አጠር ያለ መልዕክት ማስተላለፊያ እንጂ በአካል መገናኘት ለምንችል ሰዎች ስርዓት አልባ የሆኑ ቃላትና ድርጊት መፈፀሚያ አይደለም ከዚሀ ፅሁፍ በኋላ ግን ብዙዎቻችን የምንታረም ይመስለኛል ፡፡ እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ አሜን

  wtbhm

  ReplyDelete
 2. betely ye eminet botawoch

  ReplyDelete
 3. yeeminet botawoch lay eyetaye yalew yesilikgideleshinet sirate betekirstiyan yemifekidew yakil eyehone new. Ebakachihu bezih guday lay techubet

  ReplyDelete
 4. አዬ ወንድሜ ዛሬ ዛሬ ተሰለጠነ አና ነገር ዓለሙ ተረሳ አንጂ ዱሮስ በባለገመዱ ስልክ ስንጠቀም የነበረ ጊዜ ስነሥርዓት ነበረ። ደዋይ ጤና ይስጥልኝ ብሎ ይጀምራል (አንደዛሬው አማርኛ አንደማያውቁቱ 'አብሮ ይስጥልኝ ' አይደለም መልሱ ግን)፣ 'አገሌን ማግኘት ይቻል ይሆን?' ብሎ አንዲህ የሚባል የለም ከተባለም የደወለውን ቁጥር ነግሮ ያረጋግጣል። አንዳልከውም ከመሸ አና በሌሊት አይደወልም፣ አስቸኩአይ ሆኖ ከተደወለ አንኩአን ከሰላምታው ለጥቆ 'ከመሸ ስለደወልኩኝ ይቅርታ' ተብሎ ነበር ወደጉዳዩ የሚገባው። ይሄ ተንቀሳቃሽ ስልክ ከመጣ ወዲህ የማናየው የማንሰማው ጉድ የለም፣ ሽንት ቤት ቁጭ ብሎም የሚያወራ አጋጥሞኛል። አንደኔ አመለካከት የስልኩ ጉዳይ የአጠቃላዩ የባህል መሸርሸር አንዱ መገለጫ አድርጌ ነው የምቆጥረው። ስርነቀል የባህል ምልሰት (restoration) ወይም መነሳሳት (renaissance) ያስፈልገናል ባይ ነኝ።

  ReplyDelete
 5. ስልክና የእምነት ቦታዎችስ? እና መሰል ጉዳዮች ማኅበረሰባዊ ውይይቶችን ይፈልጋሉ፡፡

  ReplyDelete
 6. Teru Milketa Endewim kemishitu 4 seat Bezu New Gudayachinen Begize Atenaken Ke Mishitu 1 Seat Behuala yalewin gize Le Betsebachin ena Le Lijochachin Binadergew Yemertal Ene Balehunbet Ager Yebase Neger Kalimeta Bestker Ke Mishitu 2 Seat Behuala Aydewelim Yehim Ater yale Melikit Lemasetelalf Kehone New enji Ke Mishitu 1 Behuala Baydewel Yemertal Mekniyatum ye lijoch ena ye betsebin seat lalemeshamat Hulem kemishitu 1 seat kehone ye lijoch seat new yebalal enam yehinen bahilachewin ewdilachewalhu be egnam ager yehinen aynetu bahil Bidaber Ena bisefafa mignote Ena Tselote New Tsegawin yabizalih Dn.Danii

  ReplyDelete
 7. በጣም አስተማሪ ፅሁፍ ነው እኔ አንድ የታዘብኩተ ነገር ሰዎች እንደ እኔ እንደ እኔ፣ አደጋ ተከስቶ ካልሆነ በቀር ከምሽቱ አራት ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ሰው ጋር ስልክ መደወል በባህላችን ነውር መሆን አለበት ባይ ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 8. በጣም አስተማሪ ፅሁፍ ነው እኔ አንድ የታዘብኩተ ነገር ሰዎች እንደ እኔ እንደ እኔ፣ አደጋ ተከስቶ ካልሆነ በቀር ከምሽቱ አራት ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ሰው ጋር ስልክ መደወል በባህላችን ነውር መሆን አለበት ባይ ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 9. ምንም እንኳን ስልክ ሀገራችን ከገባ ከመቶ ዓመት በላይ ቢሆነው፣ የስልክ ሥነ ምግባራችን ግን ገና ያልለየለትና የተደባለቀ ነው፡፡ ለፊት ለፊት ግንኙነት ብዙ ወጎችን በዘመናት ቀምረናል፡፡ ስልክ ግን ገና አልተቀመረለትም፡፡ ምን ተብሎ ንግግር ይጀመር? ምን ተብሎ ያብቃ? ስሕተት ሲፈጠር ምን እንበል? የትኛውን ጊዜ ከስልክ ነጻ እናድርገው? ልጆቻችን ስልክ መያዝ ያለባቸው ከስንት ዓመት ጀምረው ነው? ስልክ እና ዕረፍት እንዴት ይስማሙ? ስልክና የእምነት ቦታዎችስ? እና መሰል ጉዳዮች ማኅበረሰባዊ ውይይቶችን ይፈልጋሉ

  ReplyDelete
  Replies
  1. WHY DON'T U CONRIBUTE UR IDEA? JUST REPEAT WHAT HE'S SAID DOESN'T HELP.

   Delete
 10. teru eyeta nwe bzohahenen yastemerale bya amenalhu Egzabhare yabertah!

  ReplyDelete
 11. አንተ ምን አለብህ አግብተህ ጨርሰሃል። እኔ ግን ከእጮኛዬ ጋር ያለኝን ናፍቆት የምወጣው አንት ማዕቀብ በጣልክበት የሌሊቱ ክፍል ነው። ጎረቤት ቀርቶ ዓለም ቢበጠበጥ፣ እንኳን የቡና ላይ መወያያ ቀርቶ የ ዓለም መገናኛ ብዙሃን የፊት ገጽ ቢሆን እኔና ፍቅሬን በዚያ ሰዓት ከማውራት የሚከለክለን የለም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የምፈራልህ ፍቅርህን በሙባይል ጨርሰህ ስትጋቡ ባዶ እንዳትቀሩ ነው።

   Delete
  2. "ላላገቡና፡ ለመበለቶች: ግን፡ እላለሁ፡-እንደ፡ እኔ፡ ቢኖሩ፡ ለእነርሱ፡ መልካም፡ ነው፤ ነገር፡ ግን፡ በምኞት፡ ከመቃጠል፡ መጋባት፡ ይሻላልና፡ ራሳቸውን፡ መግዛት፡ ባይችሉ፤ ያግቡ፡፡"1ኛ ቆሮ 7፡8-9

   Delete
  3. ለመጀመሪያው መልሴ ፍቅር አያልቅም ነው፣ የቆረንጦስ ሰዎች እንኮ ሞባይል አልነበራቸውም /ሳይተጫጩ መገባት ደግሞ ድሮ በነሱ ጊዜ ቀረ አሁን በስልኬ እስኪበቃኝ ጀንጅኜ አግባለሁ እንጂ /

   Delete
  4. I LIKE!!! Same here...

   Delete
 12. ጥሩ እይታ ነዉ ዳኒ በእዉነት ለስልክ አጠቃቀማችን መልክ ቢበጅለት መልካም ነዉ።

  ReplyDelete
 13. This is very interesting article.I think ''telephone handling'' type of explanations or trainings are needed to be provided to students in schools,hospitals,Universities etc.On the other hand the mass media should do a lot.
  Because it has a great impact on our tourism,business,etc relation ship with the rest of the world. Thank you Dani.
  Getachew

  ReplyDelete
 14. Thanks Dani, this is a Good lesson.

  ReplyDelete
 15. ፍፁም ዘ.


  ከአራት አመት በፊት ገና ከዩኒቨርስቲ እንደወጣሁ ተቀጥሬ በምሰራባት መስርያ ቤት እያለሁ የገጠመኝን ላውጋችሁ፡፡

  አንድ የማላውቀው ስልክ አላስቆም አላስቀምጥ የሚል አጭር ‘ሚስድ ኮል’ ያደርጋል፡፡ በአዲስ አበባ አነጋገር ጩቤ የሆነ ከመብረቅ የፈጠነ እንደሚሉት፡፡


  ድንገት እኮ የሚያውቀኝ ሰው ይሆናል ብዬ በማሰብ መልሼ ብደውል ማን ልበል? ይለኛል ያንጓጥጠኝም ጀመር፡፡ ሰውዬው በጥቂት ገንዘብ የሞባይል ባለቤት መሆን መቻሉ እንጂ ስልኩን እየተጠቀመበት አልመሰለኝም፡፡ ይባስ ብሎ ሙልጭ አድርጎ ሰደበኝ፡፡ ተናደድኩ፣ ውስጤ ቅጥል አለ ( ትዝ አይለኝም እንጂ ምናልባትም በወቅቱ ስልኬ በቂ መደወያ ካርድ ሳይኖረኝ ከዚያችም ላይ ቆጥቤ ይሆን ይሆናል የደወልኩለት )


  በነጋታው ጓደኛዬ አዲሱን ቢሮዬን ላሳየው ቀጠሮ ስለነበረን ብቅ ብሎ ነበር፡፡ እናም ያ አብሻቂ ልጅ የሰራኝን እያወራን እያለ በመሀል አንድ መላ መጣልኝ፡፡ ትላንት ከተደወሉልኝ ስልኮች መሀል የልጁን ስልክ ፈልጌ በቢሮ ስልክ ደወልኩ፡፡


  “ጤና ይስጥልኝ ጌታዬ የምደውለው ከፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡ ጥቆማ ደርሶን ነው፡፡ በትላንትናው እለት በዚህ በደወልኩሎት ስልክ ማለትም በእርስዎ ስልክ ወደ ተለያዩ ስልኮች በመደወል ስድብ እና አግባብ ያልሆኑ ቃላትን ተናግረዋል በዚህም የሰዎችን ጊዜ እና ገንዘብ አባክነዋል።


  ‘ማ…ን እ..ኔ…?’


  ‘አዎን እርስዎ፡፡’


  ‘አላደረጉም?’


  ‘ማ..ማ..ለት ሳ..ላውቅ.. ስነካካ ነው፡፡ ሆን…ብዬም አይደለም ጌ…ታ…ዬ..፡፡’


  ‘ለማንኛውም ጉዳዮትን ባልደረባችን ሳጅን ጉግሳ ይዘውታል። አድራሻዎንም ከቴሌ ማግኘት ስለምንችል ጉዳይዎትን እንከታተላለን፡፡’


  ‘እባክዎን ጌታዬ ሳ..ላውቅ ስነካካ ነው፡፡ እባካችሁን ይቅርታ አድርጉልኝ፡፡ ሁለተኛ አይለመደኝም፡፡’


  ‘የሆነ ሆኖ አሁን ጉዳዩ በህግ የተያዘ ስለሆነ የህግ ውሳኔ ይፈልጋል፡፡ እናም ከቻሉ እኛንም ባያደክሙን፤ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ሄደው እጅዎን ቢሰጡ’


  ‘ኧረ ጌ….ታ..ዬ!...”


  ስልኩን ዘጋሁት፡፡ ከጓደኛዬ ጋር ሳቃችንን ለማቆም አልቻልንም፡፡


  በርግጥ ቂም በቀል ጥሩም ባይሆን ሰውዬው ግን በአግባቡ የተማረ ይመስለኛል፡፡ ይህንን ሰው ለማስተማር እኔም ወታደር ቤት ሳልገባ የሳጅንነት ማእረግ ተላብሼ ‘ጉግሳ’ የሚል ገፀ ባሕሪ ተላብሼ ተውኛለሁ፡፡ ይህን ሰው አሁን ላይ ሳስታውሰው የባሰ መዘዝ ሳላመጣ ብሎ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እጁን ለመስጠት ሔዶ ይሆን?፡፡ በማያውቀው ስልክ ቁጥር ሲደወልለት ሳጅን ጉግሳ ይሆኑ እያለም ሲሳቀቅ ሰንብቶ ይሆን? እላለሁ ፍርሀት እንደ ቀትር ጥላ እየተከታተለው የቤታቸው በር ሲንኳኳ ፖሊሶቹ መጡ በማለት ሲደነብር ይታየኛል፡፡

  ReplyDelete
 16. አንድ ገጠመኝ ልንገራችሁ ሰውየው በተደጋጋሚ ለወንድሜ ይደውልልታል ሰውየው እንደተሳሳተና የሚፋልጋቸው ሰው ስልክ እንዳልሆነ ነገሮ ሰልኩ ይዘጋል ይህ የሆነው ቀን ነው ሌሊት ላይ ስልክ ጮኽ ወንድሜም በድንጋጤ ያን ስልክ አነሳ ቀን የደወሉት ሰው ናቸው አሎ የሸህ እከሌ ቤት ነው አሉ ሰውየው በሁኔታው የተናደደው ወንድሜም አወ አለ አንተማን ነህ አሉ ደዋዩ ኪታብ ነኝ ብሎ መዝጋቱን አስታውሳለሁ ከዚያን ጊዜ ወዲህ ስልኩን ዘግቶ ነው የሚተኛው

  ReplyDelete
 17. ዳኒ ጥሩ እይታ ነው። እግዚያብሔር ይባርክህ! እኔም በጣም ብዙ ነገር እታዘባለሁ በተለይ በተለይ ታክሲ እና የህዝብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ መወራት ያለባቸውን ሳያውቁ ሳይሆን አራድነት የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ገጥሞኛል፡- አንዳነዱ የሚደውልለትን ሰው ቅርበት የሚያሳይ ይመስል " አንተ እነከፍ ወይም ማቹ" ብሎ የሚጅምር ሞልቶአል፣ አንዳንዱ አብሮት ካለው ጋር ሆኖ ስልኩን ላውድ ስፒከር ላይ አድርጎ ተሳፋሪውን ሳይወድ በግዱ ቴሌ ኮምፈረንስ ያስማዋል ፣አንዳንዱ የስድብ መዝገበ ቃላት ሲያወርድ ወይም የስድብ ሌክቸር ሲሰጥ ትሰማለህ ብቻ ምን አለፋህ የድምፅ ብክለት ያልገባው ስንት አለህ መሰለህ ፣ ለሁላችንም እግዚያብሔር ማስተዋሉን ይስጠን ስለሌሎች የምናስብ ያድርገን።

  ReplyDelete
 18. Hello Daniel
  How are you doing? Glory to God, he gave us excellent father like you. I am not comment on your article but I have question to you or suggestion. I am not living in Ethiopia but I heard everyday news about Amharan problems. The current government killed and removes many Amharan from their village however I didn't heard from Ethiopian Orthodox church leader about this situation. I believe Ethiopia is the country of all Ethiopian's so why our church leaders haven't step up to protest the government policy. It is obvious that they have much evidence to condemn because most of immigrant stayed in Addis Ababa and Gojam. My suggestion if our fathers take step they can reach some agreement with the current government. Have a bless day!!!

  ReplyDelete
 19. ዳኔ ከወንዝ ማዶ የምንኖር ደንበኞችህ አገር ቤት ለሆነ ነገር ብዙ ማለት ባንችልም ፤ ገቤያ ወጥተን ልንሸምተው የማንችል ሳቅ በመሳቃችን ልናመሰግንህ እንወዳለን። በርታ!

  ReplyDelete
 20. Why ur blog is very quite about those people who are displaced from Benshangul (amharic speakers. this is really evil and dangerous for the country and the church too.

  ReplyDelete
 21. very interesting and correct but you know after 3:00 o'clock at night, their is discount for phone calls. I think that is one of the reason that most people calls after 3 o'clock

  ReplyDelete
  Replies
  1. U'RE RIGHT MY FRIEND. YENURO WIDINET ENDENE GEBTOHAL

   Delete
 22. ከዚህ በኋላ ይመጣል ብለን ነቅተን የምንጠብቀው እየሱስ ክርስቶስ የእግዚሀብሔርን ልጅ ብቻ ነው፡፡
  . በልጁ በእየሱስ የሚያምን ሁሉ ይድናል ስለሚል ዮሐ. ምዕ 1
  . እኔ እውነትም ህይወትም መንገድም ነኝ ከእኔ በቀር ወደ አብ የሚወስድ ሌላ መንገድ የለም፡፡
  . አትፍሩ ብዙ ወሬዎችን ብትሰሙም እትታወኩ፡
  ወደ እውነት ሁሉ የሚመራችሁ የእውነት መንፈስ እሱ የመራችኋላ፡
  ለደቀመዛሙርቱ ሀይልን ሳትቀበሉ ወደ እየሩሳሌም አትውጡ ብሏቸዋል፤
  . በእምነትና በጽድቅ እግዚሀብሔርን እያመለካችሁ እየሱስ ሲመጣ ሀሌሉያ እየሱስ ቶሎ ና እያላችሁ
  መጠበቅ እንጂ መወዛገብ ለምን
  እሲ እኮ እሁንም አጠገባችሁ ሆኖ እምነታችንን እና በዶነታችንን ይመለከታል ለምን ለእያንዳንዱ ሰው ሙሴና ነብያት አለላችሁ ፤የሚለው ክፍል መጽሀፍ ቅዱስ በግልጽ ተጽፎአል ማንም መንፈሳዊ አስተማሪ ቢያስተምረን እንኳን ከመጽሀፍ ቅዱስ ጋር እናመሳክር እግዚሀብሔርን እንመነው ለምን አብራልን ግለጽልን ብለን እንለምን በሰው ከመነዳት ይልቅ እኔ የቅርንብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም ያለውን እንመነው /ተኝተንም፤ቁጭ ብለን ፤ስንሄድ እርዳን መንገድህን አሳየኝ/ በሉት እድሉ ያለው ዛሬ ብቻ ስለሆነ
  በእግዚሃብሔር መንፈስ የሚመሩ እነርሱ የእግዚሀብሔር ልጆች ናቸው ፡፡ የሐ.ወንጌል

  ReplyDelete
  Replies
  1. yehegnawem yetesasate misscall sayehon ayeqerem ke topicu gare alehed alegn yeqereta dani hasabehen egaralehu

   Delete
  2. ከዚህ በኋላ ይመጣል ብለን ነቅተን የምንጠብቀው እየሱስ ክርስቶስ የእግዚሀብሔርን ልጅ ብቻ ነው፡፡............Algebagnem kegodau gar yeteyayaze neger selalehone

   Delete
 23. Thank you for raising the issue, from what i know, we have a telephone etiquette in Ethiopia(I was once scolded by my friend's mother for calling a little after 9pm/2100). But only few had telephone then, and the etiquette was limited among the few users. After 1983 E.C, there was a flock of people from different corners of the country in to Addis Ababa and many have no etiquette to almost anything, not that they intentionally ignored it but they don't even know manners/etiquette of communication, sanitation, transport, etc. In fact there are others on the otherhand who know, but ignore these manners intentionally, associating it with different groups/ societies they despise.
  Regardless of anything, lessons for etiquettes of communication and manners of interaction should be provided to customer service desk persons in Kebeles, Hospitals, and other government offices. these are places where every member of the society is reached. This in the long run is important in societal development which is directly or indirectly tied to economic and political weavings of the country.

  ReplyDelete
 24. One day, when I was new comer for U.S.A, I have being given a phone call to one of my friends. . It was a night time in Ethiopia. I said " Hello Asne." and I heard also a continous " Hello voice" from the other side. First, it seemed me that my friend is kidding, because he always speak laughingly. Unfortunately, the line was wrong and I heard a hard voice from that side, it said " you idiot! so what does it mean you from U.S.A ? Do you hear me ? You ---- Diaspora!!" Oh my God, I didn't know even to spell the word 'diaspora;.After that time, I check any voice at least twice before I say something.

  ReplyDelete
 25. እዚህ እኔ በምኖርበት አገር ደግሞ ይገርማችኋል ያገሬው ሰዎች ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን እንኳን ሲያነሱ በቋንቋቸው "ሄሎ ይህ የንትና ስልክ ነው" ብለው ነው የሚጀምሩት:: እንደመጣሁ ሰሞን ግራ ገብቶኝ ነበር እነሱ ግን እንደዛ ሳይል ስልክ ያነሳ ሰው ነው የሚገርማቸው:: እናም እኛ አገር እንደዚህ ማድረግ ብንጀምር ብዬ አሰብኩና ስንቱ አጋጣሚውን ያለአግባብ ሊጠቀምበት እንደሚችል ሳስበው ወዲያው ተውኩት::

  ReplyDelete
 26. +++
  ቃለ ሕይወት ያሰማልን!
  በጣም አስተማሪ ነው እግዚአብሔር ይስጥልን ።

  ReplyDelete
 27. ሰውዬው ፊልድ ሆኖ ወደ ቤቱ ስልክ ይደውላል››
  ጭር…ጭርርር…ጭርርር
  እሱ፡ ሄሎ
  የማያውቀው የሴት ድምፅ፡ ሄሎ
  እሱ፡ ማን ልበል?
  እሱዋ ፡ እርሶ አይደል እንዴ የደወሉት? ማንን ብለው ደወሉ?
  እሱ፡ ኧኸኸ… ባለቤቴን ፈልጌ ነዋ: ለመሆኑ አንች ማነሽ?
  እሱዋ ፡ ውይ ይቅርታ ጋሼ፡ አዲስ የተቀጠርኩ
  ሰራተኛ ነኝ
  እሱ፡ ነው እንዴ ? ታድያ እንደሱ አትይም? በይ ባለቤቴን አገናኚኝ
  እሱዋ ፡ እሳቸው እማ ከባላቸው ጋር ምኝታ ቤት ተኝተዋል
  እሱ፡ ምን? እኔ አይደለሁ እንዴ ባለቤ ምን
  ማለትሽ ነው?
  እሱዋ ፡ እንጃኔ ጋሼ: ታድያ ምኝታቤት አብረዋቸው ያሉት ሰውዬ ማን ናቸው?
  እሱ፡ እኔ የት አውቅልሻለሁ? ማወቅም
  አልፈልግም ለመሆኑ ስንት ነው ደሞዝሽ?
  እሱዋ ፡ 150 ብር ነው ጋሼ
  እሱ፡ በይ ባለቤቴንም አብሩዋት ያለውንም ውርጋጥ ፀጥ ካረግሺልኝ 10000 ብር እሰጥሻለሁ

  After 30 minutes

  ሰራተኛ የተባለችውን አረገች እና ለባልየው ደወለች...

  ጭር…ጭርርር…ጭርርር
  እሱዋ ፡ ሄሎ ጋሼ
  እሱ፡ እንዳልኩሽ አደረክሽ?
  እሱዋ ፡ አዎ ጋሼ
  እሱ፡ ጎበዝ ስመጣ የማረግልሽን አታውቂም
  እሱዋ ፡ እሺ ጋሼ፡ ግን ሬሳዎቹን የት ላርጋቸው?
  እሱ፡ እም… በቃ ቤታችን ጀርባ ያለው ወንዝ ውስጥ ጨምሪያቸው
  እሱዋ ፡ የምን ወንዝ ጋሼ? እንዴ ቤቱ ጀርባ እኮ ወንዝ የለም
  እሱ፡ ቆይ ይሄ 0111234454 አይደለም እንዴ? ውይ በጣም ይቅርታ የተሳሳተ ቁጥር ሳልደውል አልቀረኹም

  ReplyDelete
 28. ere tele erasu qinash yalebet seat yemilew yetegnawn new? mata aydelew ende swochu bicha sayhonu mengist enkuan mastekakel alebet

  ReplyDelete
 29. wow! interesting issue

  ReplyDelete
 30. i appricate ur teaching but i dont get u when u talk about the pope merkoriyos that these ppl in america are orthopente that is not fair we dont need to lie inorder to get respect by the so called aba paulos and co. u can read here all about american churches ...there are some who follow aba paulos who was now gone...anyway read this and know the truth .http://medhanialemeotcks.org/pdf/FIKARE.pdf

  ReplyDelete