መኪናዋ
ተገፍታ ለመጨረሻ ጊዜ ስትወጣ
|
የአካባቢው ገበሬዎችና አሣፍረናቸው የነበሩ ሌሎች ገበሬዎች ተባብረው መኪናዋን በዳገቱ
መግፋት ጀመሩ፡፡ ድንበሩ አንዴ ገብቶ መሪ ይዞ ይነዳል፣ አንዴ ወርዶ ጎማውን በካልቾ ይማታል፡፡ ሙሉቀን በትጋትና ተስፋ
ባለመቁረጥ መኪናዋን ከፖሊሶቹና ከገበሬዎቹ ጋር ይገፋል፡፡ ቀለመወርቅ መኪናዋን የሚመለከት የሕግ ዐንቀጽ የሚፈልግ ይመስል
አንገቱን ደፍቶ አንዳች ነገር ያስሳል፡፡ ኤልያስ መነጽሩን ከፍ እያደረገ ለድንበሩ የመፍትሔ ሃሳብ ያቀርባል፡፡ ይህ ሁሉ ግን
መኪናዋን ዳገት እንድትወጣ አላስቻላትም፡፡
እኛም
የወጣችውን መኪና በእግር ስንከተል
|
ቀለመወርቅ ‹ድንጋዩን አንሡ› የሚለው ጥቅስ ትዝ ብሎት ነው መሰል መኪና መንገዱ
ውስጥ ገብቶ ጭንቅላት ጭንቅላት የሚያህሉ ድንጋዮችን ማንሣት ጀመረ፡፡ መኪናዋም ጥረቱን አደነቀችለት መሰል ወደላይ የመውጣት
ተስፋ ሰጠች፡፡ ገበሬዎቹም ያለ የሌለ ኃይላቸውን ተጠቅመው ወደ ላይ ገፏት፡፡ ‹ተመስገን› ዋናውን ዳገት እያቃሰተች ወጣችና
አፋፍ ላይ ቆመች፡፡ የሁሉም ፊት ከኀዘን ወደ ደስታ፣ ከቀቢጸ ተስፋ ወደ ተስፋ ተቀየረ፡፡
‹‹አይዟችሁ ከዚህ በኋላ ሌላ ዳገት የለም›› አለን አብሮ የነበረው ቆፍጣናና
ጉልበታም ገበሬ፡፡ መኪና የገፋበትን ክንዱን እየወዘወዘ፡፡ እውነትም እንዳለው ቀሪው መንገዳችን ሜዳ ነበረ፡፡ ከውስጥ እኛ፤
ከውጭ ገበሬዎቹ ተሣፈርንና ያለፈ ነገራችንን እያነሣን ወደ መዳረሻችን ጉዞ ቀጠልን፡፡
መኪናዋ
በዳገቱ መጨረሻ ላይ
|
እነሆ የኳሳ ደረስን፡፡ በመኪና ልንሄድበት የምንችለው የመጨረሻው ቦታ የኳሳ ከተማ
ናት፡፡ ሊቀ ካህናቱ የምንሄድበትን በረሃ በሩቁ አመለከቱን፡፡ ‹ልብ የሌላትን መኪና ገፍቶ እዚህ ያደረሰ አምላክ ልብ የሰጠንን
እኛን እዚያ ማድረስ አያቅተውም› ብለን አመንን፡፡ የከተማው ፖሊስ ጣቢያ መኪናችንን አቆምን፡፡ ሁለቱ ፖሊሶች፣ የወረዳው ሊቀ
ካህናት፣ ከወረዳው ቤተ ክህነት የመጡ አንድ ሌላ ዳዊት ደጋሚ ካህን እና እኛ አራታችን በእግር ለመገስገስ ተዘጋጀን፡፡ እኒህ
ዳዊት ደጋሚ ካህን የሚገርም ተሰጥዖ አላቸው፡፡ እኛ እንሂድ አንሂድ ስንጨነቅ፣ ሰው ሁሉ የመሰለውን እየሰነዘረ ሲከራከር፣
መኪና ስትሄድ፣ መኪና ስትቆም እርሳቸው ዳዊት መድገማቸውን አያቆሙም፡፡ ባይሆን እንደ መሐል ከተማ ሰው ዲፕሎማሲ ባለመቻላቸው
ድንበሩ ተቀይሟቸው ነበር፡፡ ‹ምን ያህል መንገድ ይቀረናል?> ሲላቸው መልሳቸው ‹ገና ምኑ ተነካ› ነው፡፡ ‹ሞራል አይሰጡም፤ ተስፋ ያስቆርጣሉ›
አለ ድንበሩ፡፡ እርሳቸው እንደሆነ ቁርጥ ያለ የዘመድ ዋጋ ነው የሚያውቁት፡፡
ዳገቱ
አለቀ
|
ከየኳሳ ከተማ ሁለተኛው ምእራፍ ተጀመረ፡፡ በሩቁ የምናቋርጠው በረሃ ተዘርግቷል፡፡ መንገድ
ላይ የደብረ ዕንቁ አገልጋይ የሆኑ መሪጌታ ይጠብቁናል፡፡ ለአንድ ሰዓት ያህል ከተጓዝን በኋላ ኤልያስ ማንከስ ጀመረ፡፡ ከዚህ
ጉዞ ላለመቅረት ብሎ እንጂ እግሩን ኦፕራስዮን አድርጎ ነበር፡፡ ያደረገው ጫማ ሸበጥ ነገር ነው፡፡
የወንዝ
ዳር ረፍት
|
ድንበሩና አንደኛው ፖሊስ
ከፊት፣ ካህናቱና ሙሉ ቀን ከመካከል፣ ከእነርሱ ቀጥሎ ቀለመወርቅ፣ እኔና ኤልያስ በስተመጨረሻ ‹አዴም ነዲያቸው› እያልን እንጓዝ ነበር፡፡ የኤልያስ እግር መቁሰል ጀምሯል፡፡
በበረሃው
መግቢያ በር
|
መንደሮችንና እርሻዎችን እያቋረጥን ነበር የምንጓዘው፡፡ አሥር ዓመት የማይሞላቸው
ሴትና ወንድ እረኞች እጃቸውን አፋቸው ላይ አድርገው በግርምት ያዩናል፡፡
አዲስ ጠረን የሸተታቸው ከብቶች በአጠገባቸው ስናልፍ
ቀንዳቸውን ሊፈትሹብን ይፈልጋሉ፡፡ ሰላምታ የማይጓደልባቸው የስማዳ ገበሬዎች ከዐጨዳቸው ላይ ብዲግ እያሉ፣ በሽክና ጠላቸውን
ይዘው በመጋበዝ በሰላምታ ያሳልፉናል፡፡
የቸሩ
የስማዳ ገበሬ ግብዣ
|
አሁን የመሪጌታ ጥዑመ ልሳን እርሻና መንደር ጋ ደረስን፡፡ እኒህ መሪጌታ ‹በከንቱ
የተቀበላችሁትን በከንቱ ስጡ› የሚለውን ቃል አክብረው፣ ከተማውን ትተው እዚህ ገጠር ተቀምጠው ደቀ መዛሙርት የሚያፈሩ መሪጌታ
ናቸው፡፡ ምርግትናውን ከክህነት፣ ክህነቱንም ከግብርና አስተባብረው እያረሱ ያስተምራሉ፣ እያስተማሩም ያርሳሉ፡፡ ደቀ
መዝሙሮቻቸው በአንድ በኩል ለመምህራቸው የጉልበት አገልግሎት ይሰጣሉ፤ በሌላ በኩል ከመምህሩ ዕውቀት ይሸምታሉ፡፡ ተማሪዎቻቸውን
በመደዳ ያስቀምጡና በሬያቸውን ይጠምዳሉ፡፡ ወዲያ ሲሄዱ ለአንዱ ቀለም ይነግራሉ፣ ወዲህ ሲመጡም ለሌላው ቀለም ይነግራሉ፡፡
እርሻውም የታደለ ነው፤ ቃለ እግዚአብሔር እየፈሰሰበት ይታረሳል፣ ይዘራል፣ ይታጨዳል፣ ይወቃል፡፡ ይህንን የመሰሉ ሰዎች
ያመረቱት እህል እየተቀላቀለበት ሳይሆን አይቀርም ሞሰባችን ረድኤት የነበረው፡፡
እረፍት
በመሪጌታ እርሻ አጠገብ
|
በመሪጌታው እርሻ ጎን ዕረፍት አደረግን፡፡ እግረ መንገዳችንንም እርሳቸውን እንጠብቅ
ዘንድ፡፡ የመምህሩ ቤት ከመንገዳችን በስተ ቀኝ ከዛፎቹ ሥር ነው፡፡ ዙርያውን በተማሪዎቻቸው ጎጆዎች ተከብቧል፡፡ አሁን የአጨዳ
ጊዜ በመሆኑ ተማሪዎቻቸውን አስተባብረው ወደ አጨዳ ሄደዋል፡፡ አውድማቸው የተቀመጥንበት አካባቢ ነውና እህሉን ወደዚህ
ያመጣሉ፡፡ ከባለቤታቸው ጋር እያወጋን ጠበቅናቸው፡፡ እግረ መንገዳቸውን አብረውን ያሉት ካህን ስለ ጌርጌስ ያወጉን ጀመር፡፡
አባ ፊልጶስ
ከጌርጌስ ወደ ሐቃሊት የመጣበት በረሃ
|
‹ጌርጌስ ማለት ያ ከማዶ የምታዩት ሜዳማ ተራራ ነው፡፡ በደብረ ዕንቁ እና በጌርጌስ መካከል ታላቅ በረሃ አለ፡፡ ጌርጌስ
አጠገብ የጃምባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ያለበት ጋሼና የሚባል ቦታ አለ፡፡› ‹በዜና መዋዕሉ ከጋሼና እስከ ዐንቆ የሚለው
ይህንን ነው ማለት ነው› አልኩ፡፡ አቡነ ፊልጶስ ወደ ሐቃሊት ሲመጣ ከአቡነ ሰላማ መተርጉም ጋር የተገናኘው በጌርጌስ መሆኑን
ገድሉ ይነግረናል፡፡ ይህቺ ቦታ ከጥንት ጀምሮ የጳጳሳት መቀመጫ ነበረች፡፡ አሁን በትክክልም የአቡነ ፊልጶስን የመጨረሻ ቦታ
እያገኘነው ነው ማለት ነው፡፡
የመሪጌታ
ተማሪዎች ጎጆ
|
አንቆስ ማናት? ደብረ ዕንቁ ትሆን? ይህንን እያሰብኩ እያለ፡፡ ያን ጊዜ አንደኛውን ፖሊስ ዝም ብለን ክንቀመጥ ብዬ
‹እንዴው ስለ ሀገሩ ምን ይዘፈናል?› አልኩት፡፡ እርሱም እንዲህ አለኝ
ላሊበላን መሳም በከንቱ ድካም ነው
ከየኳሳ በታች ዐንቆ መጨምጨም ነው
እጅግ የሚገርም ሰምና ወርቅ ቅኔ፡፡ የኳሳ መኪናችንን ያቆምንባት ከተማ ናት፡፡ ‹ከየኳሳ
በታች ዐንቆ መጨምጨም ነው› አለ፡፡ ‹ዐንቆ ማናት?› አልኩት፡፡ ‹ዐንቆ ማለት ደብረ ዕንቁ ናት› አለኝ፡፡ እፎይ አልኩ፡፡ ‹ከዐንቆ
እስከ ጋሼና› የሚለው ተፈታ ማለት ነው፡፡ ‹ሐቃሊት የተባለችውኮ ደብረ ዕንቁ ናት፤ ሐቃሊት ማለት በበረሃ ያለች ቦታ ማለት
ነው› አሉና ካህኑ ይዘረዝሩት ጀመር፡፡ ገርሞኝ ነበር በደስታ የማያቸው፡፡ ‹ሐቃሊት የታለች?› አልኳቸው፡፡
ሐቃሊትን ትንሽ ከሄድን በኋላ ታያታለህ፤ ጌርጌስ ያውልህ፡፡ አቡነ ፊልጶስ የታመመው እዚያ ነው፡፡ ወደ ሐቃሊት የመጣው ታቹን
በበረሃው አድርጎ ነው፡፡ በበረሃው ከመጣ በኋላ እዚህ ዳገቱ ላይ ሲደርስ ዐረፈ፡፡ ያረፈበት ቦታ ይኼውልህ፤ አሁን የታቦት
ማርገጃ አድርገነዋል›› አሉና አሳዩኝ፡፡ ቦታውን ወድቄ ተሳለምኩት፡፡ ዙርያውን ታጥሮ አንዲት ዛፍ በቅላበታለች፡፡ አካባቢው
ለጥ ያለ ሜዳ ነው፡፡
የመሪጌታ ተማሪ ነዶ ተሸክሞ |
እኒህ ዳዊት ደጋሚ ካህን ብርቱ ናቸው፡፡ መምህሩ እስኪመጡ ተማሪዎቻቸው ያመጡትን
የጤፍ ነዶ በአውድማው ላይ ይከምሩላቸው ጀመር፡፡ የቄስና የሴት እንግዳ የለውም ማለት ይኼ ነው፡፡ መምህሩ ነዷቸውን ተሸክመው
መጡ፡፡ የተሸከሙትን አወረዱና ሰላም አሉን፡፡ ከእርሳቸው ጋር ወደ ደብረ ዕንቁ ለመሄድ መምጣታችንን ስንነግራቸው በደስታ
አብረውን ለመሄድ ተነሡ፡፡ ወደ ቤታቸው ደርሰው ልብሳቸውን ቀየሩና ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ፡፡
መሪጌታ
ነዶ ተሸክመው
|
እነሆ አሁን የበረሃውን መንገድ ለማግኘት አባ ፊልጶስ ከጌርጌስ ሲመጣ ባረፈበት ሜዳ
በኩል አቋርጠን መንገድ ጀመርን፡፡ መሪጌታ በሁለት ነገር ጠቅመውኛል፡፡ በአንድ በኩል ታሪክና ጨዋታ ዐዋቂ ስለሆኑ መንገዱን
ያለ ድካም እንድንጓዝ አድርገዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በእድሜ ጠገቡ ጃንጥላቸው የስማዳን ፀሐይ መክተውልኛል፡፡
ወደ በረሃው
ጉዞ
|
አሁን ኤልያስ እያነከሰ፣ ድንበሩ መሐል መጥቶ ፣ ቀለመወርቅና ሙሉቀን ከካህናቱ ጋር አብሪ
ሆነው ወደ ቆላው ልንገባ ነው፡፡ ቆላው ሁለት ተራሮችን ወጥቶ መውረድና ሦስተኛውን ተራራ መውጣት ይጠይቃል፡፡ መሪጌታ አቡነ
ፊልጶስ ከጌርጌስ ወደ ሐቃሊት የመጣበትን በረሃ አሳዩን፡፡ ከጎንና ጎን ተራራ ያለበት ገደል ነው፡፡
ከመጀመርያው ተራራ ወርደን |
አሁን ደብረ ሐቃሊት ከሩቁ
ትታያለች፡፡ ሲቀርቧት የምትርቅ ሞሰበ ወርቅ የመሰለች ተራራ ናት፡፡ ወደ እርሷ ለመድረስ ግን ሁለት ተራሮች እንደ መቅድም
ሆነውላታል፡፡ ታምሯ እርሷ ናት፡፡
ኤልያስ፡-
ከሁለት እግር ወደ ሦስት እግር
|
ወደ ሁለት ሰዓት የፈጀ የመውጣትና የመወረድ ጉዞ በማካሄድ ላይ ነን፡፡ ቆላው
ውስጥ፡፡ አሁን የምንሄድበት መንገድ አንድ ሰው ብቻ የሚያሳልፍ የተፈጥሮ ድልድይ ነው፡፡ በግራና በቀኝ ገደል ነው፡፡ ‹ከዚህ
የተንከባለለ ወይ በሽሎ ወይ ዓባይ ነው የሚገኘው› ብለውኛል መሪጌታ፡፡ እኛም ከሁለቱ በአንዱ ላለመገኘት በጥንቃቄ መሥመር
ሠርተን በመጓዝ ላይ ነን፡፡ አንዱን ተራራ ይህንን በመሰለ እንደ ባሕረ እሳት መንገድ በቀጠነ መሷለኪያ አለፍነውና ሌላ ተራራ
ከፊታችን ተገተረ፡፡
ከደብረ
ዕንቁ ማዶ የሚገኘው ጌርጌስ ነው
|
እርሱ ደግሞ ዐለቶች ተሰባስበው በማኅበር የመሠረቱት ነው፡፡ ከዐለቱ በስተጀርባ ተዙሮ
ወደ ፊቱ ለመምጣት ከቁጥቋጦና ስለታም ድንጋዮች ጋር ትግል ይጠይቃል፡፡ በዐለቱ ጫፍ ላይ ሆናችሁ የመጣችሁበትን መንገድ ወደታች
ስታዩት እናንተ ከጠፈር ጥግ ያላችሁ ነው የሚመስላችሁ፡፡ ሁሉም ነገር የጣት ቁራጭ አክሎ ነው የሚታየው፡፡ ዐለታማውን ተራራ
ተጠማዝዘን ወረድነውና ተራራውን ከደብረ ዕንቁ ጋር ወደሚያያይዘው ቀጭን መንገድ ገባን፡፡ ይህም በግራና ቀኝ ገደል ያጀበው፣
ከቅድሙ ሰርጥ ግን ሰፋ የሚል መንገድ ነው፡፡
ሁለተኛው
ዐለታማ ተራራ
|
ከባዱ ዳገት ወደ ደብረ ዕንቁ የሚያስወጣው ነው፡፡ ተራራውን እንደ ዘንዶ መጠማዘዝን
ይጠይቃል፡፡ ደግነቱ መንገዱ ደልደል ያለ ነው፡፡ ለሃያ ደቂቃ ያህል ከዞርነው በኋላ አንድ ቦታ አገኘን፡፡ ‹ይህ ቦታ ምዕራፈ
ወለተ ጴጥሮስ ይባላል› አሉን መሪጌታ ጥዑመ ልሳን፡፡ ‹‹ወለተ ጴጥሮስ ይህንን ገዳም ውኃ በመቅዳት አገልግላለች፤ ውኃ ቀድታ
ስትመጣ የምታርፍበት ቦታ ስለሆነ ምዕራፈ ወለተ ጴጥሮስ ተባለ›› አሉን፡፡ ይህ ታሪክ በወለተ ጴጥሮስ ገድል ላይ ተጽፏል፡፡
ምእራፈ
ወለተ ጴጥሮስ
|
ምዕራፈ ወለተ ጴጥሮስን ካለፍን ከሃያ ደቂቃ በኋላ የገዳሙን በር አገኘነው፡፡ እነሆ
ጉዟችን ወደ መጠናቀቂያው እየደረሰ ነው፡፡ የገዳሙን በር ከዘለቃችሁ በኋላ ሌላ መንገድም ይጠብቃችኋል፡፡ ያውም ተራራማ
መንገድ፡፡ ደግነቱ ብዙም ሩቅ አይደለም፡፡
ከተራራው
ሥር
|
ፊት ለፊታችን ደብረ ዕንቁ ማርያም ታየችን፡፡ አንቺን ፍለጋ ስንት ጊዜ ለፋን፣
ስንቱንስ ሀገር አቋረጥን፡፡ ስንቱን ተራራና ገደልስ ተሻገርን፡፡ መሪጌታ ቤተ ክርስቲያኑን አስከፈቱልን፤ እኛም ወደ ወስጥ
ዘለቅን፡፡ ጸሎት ካደረስን በኋላ ‹ክህነት ያላችሁ ወደ ውስጥ ዝለቁ› አሉ መሪጌታ፡፡ እኛም ወደ ቅድስቱ ዘለቅን፡፡ አቡነ
ፊልጶስ ተቀብሮበት የነበረውንም ቦታ ከመንበሩ ሥር አሳዩን፡፡ የአቡነ ፊልጶስ ዐፅም ለ140 ዓመታት የቆየው እዚህ ነበር፡፡
በዐፄ እስክንድር ዘመን (1471-1487 ዓም) በእጨጌ መርሐ ክርስቶስ ጊዜ በእጨጌ መርሐ ክርስቶስ ጥያቄና በንጉሡ ፈቃድ
ከደብረ ሐቃሊት ፈልሶ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገባ፡፡
አባ ፊልጶስ
ያረፈበት ቦታ
|
ገዳማውያኑ መልካም አቀባበል ነበር ያደረጉልን፤ ገድሉን እያነበቡ ታሪኩን በመንገር፤
ገዳማዊ የሆነውን ምግብ በማቅረብ፤ የበረከቱም ተካፋይ በማድረግ፡፡ ደብረ ዕንቁ በኢትዮጵያ ታሪክ ያልተጠና ብዙ ነገር አላት፡፡
የአቡነ ሰላማ መተርጉም መቀመጫ ነበረችና ምናልባት ጳጳሱ ከአሥራ አንድ በላይ የሚሆኑ መጻሕፍትን ከዐረብኛ ወደ ግእዝ የተረጎሙት
እዚህ ቦታ ይሆን ይሆናል፡፡
ደብረ
ሐቃሊት በር ደረስን
|
እርሳቸው ለዐረብኛው እንጂ ለግእዙ አዲስ ናቸውና ታላቁን ሥራ የሠሩት በደብረ ዕንቁ የተሰባሰቡ
ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ሊሆኑም ይችላሉ፡፡ ደብረ ዕንቁ በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን የተዋሕዶዎች መሸሸጊያና መወያያ በመሆንም ታላቅ
ታሪክ አላት፡፡ እነ ዐራት ዓይና ጎሹን የመሳሰሉ የቅርብ ዘመን ሊቃውንትም መፍለቂያ ናት፡፡ በደብረ ዕንቁና በዲማ ጊዮርጊስ
ሊቃውንት መካከል የነበረው የዘመናት ግንኙነትም ሊጠና የሚገባው ነገር ነው፡፡
ብቻ እኛ እዚህ ደርሰናል፡፡ በጉዟችን የረዱንን የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከትን፣
የስማዳ ወረዳ ቤተ ክህነትን፣ የስማዳ ወረዳ መስተዳድርን፣ የደብረ ዕንቁ ገዳም አባቶችንና ሌሎችንም እግዚአብሔር ዋጋቸውን
ይክፈል እንላለን፡፡
ደብረ
ዕንቁ ማርያም
|
እንደነ አቡነ ፊልጶስ ያሉ በቤተ ክርስቲያን ዘላለም የሚያበራ፣ ለትውልዱም የሥነ ምግባርና የሞራል ስንቅ
የሚሆን ታሪክ ያላቸው ሰማዕታት አባቶች እንደ አዲስ አበባ ባሉ ታላላቅ ከተሞች ቤተ ክርስቲያን ሊታነጽላቸውና ትውልዱ
እንዲያውቃቸው ሊደረግ ይገባል፡፡
አባ ፊልጶስ
ያረፈበት ቦታ፣ ከመንበሩ ሥር
|
በአንዳንድ ቅዱሳን ስም አምስትና ስድስት ቤተ ክርስቲያን በአንድ ከተማ ከመትከል ለእነ አቡነ
ፊልጶስ አንድ ዕድል መስጠት በታሪክም በሰማይም የሚያስመሰግንና ዋጋ ያለው ተግባር ይሆናል፡፡ በማኅበር ተሰባስበው ክርስቲያናዊ
ሥራ የሚሠሩ ወጣቶችም እንደ አቡነ ፊልጶስ ባሉ አባቶች ስም
በመጠራትና ታሪካቸውን ከፍ በማድረግ የበረከታቸው ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ታሪክ ይጋብዛቸዋል፡፡
እረፍት
በገዳሙ ግቢ
|
እነሆ እንደመጣነው ልንመለስ ነው፡፡ ያው ተራራና ገደል፣ ያችው መኪና ይጠብቁናል፡፡
የገዳሙ
ግብዣ
|
Dn Daniel,
ReplyDeleteGod Bless You.
You did a very great job. I think you suggestion is timely so as the EOTC followers should do something in the name of Abbune Filphose. Everyone should contribute to this timely idea so as to get from our Holy Fathers.
I hope Elias is now fine and changed from three legs to two legs.
Yegedamu gibiza gin betam betam asikenagn yihew fit lefitie iyayehut mirakie teb iko ale. Andegna bereketu huletegna siyategib!!!!!!!!
Yihin tarik bichal betinatawi metshiet lay lemasatem bimoker tiru yihonal yemil iminet alegn keante balawikim.
God bless you and your beloved family.
kebede
I like your silence about the election of the new patriarch (Abune Mathias....be etta eskaltemerete deres hazenachin yeketilal
ReplyDeleteIm happy & satisfied
ReplyDeleteThank You Dk. Daniel for your committment
ReplyDeleteእንኳን ደህና ገባችሁ መመለሱስ አያቅታችሁም ለእናንተ የተሰጠ ጸጋ ለእኛም ይትረፈን!ሰላም ግቡ መግባቱንስ ገብታችኋል
ReplyDelete..............ቦታውን ወድቄ ተሳለምኩት፡፡ D. Daini I am crinying............crying.........!!! Anten baderegegn alku!!! Temegnehu!!! Yantem bereket yidresegn.......Temegnehu!!!....Kiristinan menor endante new!!! Wish you long life!!! May God blessing increaase for you!!!
ReplyDeleteYabatachen bereket kehulachen gare yihune !!!yagelegelote zemenehen fetarie amelak arezemeleh!!! Danie
ReplyDeleteit is very interesting.
ReplyDeletei dont have any word to explain abt u really u know how to write and deep i wanna say only wow
ReplyDeleteዳኔ ከውጣ ውረዱ ባሻገር ያገጘኛችሁት በረከት ፍጹም መታደል ነው። አኛም በመንፈስ ከበረከታችሁ ይድረሰን። አንተም በዜሁ በርታ። የድንግል ልጅ በሰላም ይመልሳችሁ።
ReplyDeleteThank You Deacon Daniel!
ReplyDeleteI hope Brother Elias Will be fine by now. I is timely for us who ......."‹ልብ የሌላትን መኪና ገፍቶ እዚህ ያደረሰ አምላክ ልብ የሰጠንን እኛን እዚያ ማድረስ አያቅተውም› ብለን አመንን፡፡"....please!! our heavenly father give for EOTC like......."እንደነ አቡነ ፊልጶስ ያሉ በቤተ ክርስቲያን ዘላለም የሚያበራ፣ ለትውልዱም የሥነ ምግባርና የሞራል ስንቅ የሚሆን ታሪክ ያላቸው ሰማዕታት አባቶች" We need them NOW.>>
Thank You Deacon Daniel!
ReplyDeleteI hope Brother Elias Will be fine by now. I is timely for us who ......."‹ልብ የሌላትን መኪና ገፍቶ እዚህ ያደረሰ አምላክ ልብ የሰጠንን እኛን እዚያ ማድረስ አያቅተውም› ብለን አመንን፡፡"....please!! our heavenly father give for EOTC like......."እንደነ አቡነ ፊልጶስ ያሉ በቤተ ክርስቲያን ዘላለም የሚያበራ፣ ለትውልዱም የሥነ ምግባርና የሞራል ስንቅ የሚሆን ታሪክ ያላቸው ሰማዕታት አባቶች" We need them NOW.>>
ENATACHN KIDESTE KEDUSAN DENGL MARYAM YEZEN YE MANDERSEBT YEMIYAKTEN NEGER YELEM ... YE ABBATACHIN BERKETACHEW ENA REDITAHEW AYERAKEBN ... LANTEM KUDUS EGZIABHER WAGAHN BE SEMAYAWIT EYERUSALIM YEKFELH ... LE TEBABERUH ,,BETSEBHM BEREKET EGZIABHER AYRAKBACHEW ..AMEN
ReplyDeleteI was very very eager to see the destination.You just proved where our Father Philipos was. I was crying when you told me ቦታውን ወድቄ ተሳለምኩት. I did with you in my heart. I believe God will give us His Blessings when we know this kind of miracle history.
ReplyDeleteDn Daniel,May God Bless you and your family.....ዛሬ የበረከት ምንጭ የሆኑ አባቶችን እያጣንበት ባለ ዘመን እንደ አንተ ያሉ ወንድሞችን ያላሳጣን እግዚአብሄር ይመስገን!!!!!
ቃለሂዎት ያሰማልን ዳኒ ሀገራችንና ቤተክርስቲያናችንን እንዲህባለ ልብን በሚመስጥመልኩ በነጻ አብረንህ እንድንጉዋዝ ስላደረከን ካባ ፊሊፓስና እንዲሁም የጻድቁን ድርሻ በቸርነቱ ቃል ከገባልን ከአምላካችን እድሜና ጤና ከነወንድሞችህ ያሰጥህ በርታ ስራህን እግዚአብሄር ይባርክ አንተንም የሚተካ ለማፍራት ያብቃህ አሜን
ReplyDeleteBY THE WAY HOW MANY PPL DO U KNOW ...LIKE/SAME U GUYS? AND HOW MANY NEEDS OUR BETEKRSTIAN...TO BE CONTINUE AS A CENTER OF RELIGIOUS,HISTORY AND CULTURE.
ReplyDelete+++ ENANTEN GEN EGZABHER YIBARK+++
yetekeberk D.N. DANEAL
ReplyDeleteEGZIABHER YEBARKEH EYALEKESKU ABRYACHEHU TESALEMKUT!!!!!!! MEN ENDEMELEH KALAT YATREGNAL EGZIABHERAMLAK BEFETENA YATSNAH LELA MENEM ALELEHEM; MELKAMUN HASABEHEN HULU YEFETSEMELEH, betesebehen yetebekeleh, Edmen ena tenan yesteh yetsadkan, yesemaetat amalagenet ayeleyeh
AMEN
Dear dacon Daniel
ReplyDeleteGod bless you for shearing the St blessing with us.what an effort welldone!!
May God bless you more and more!!!!!
የቅዱሱ አባታችን አባ ፊሊጶስ በረከታቸው ይደርብን!!!
ReplyDeleteDn. Daniel Egziabher amlak qale hiwot yasemalin. Ye Abatachin ye Abune Philipos bereket behulachinim lay yederebin. Rejim ye agelgelot zemen yestih. Betam des yemil tarik new. kezih hulu dekam behuwala bemagnetih egnam endenawkew bemadregih betam enamesegenalen. Ahunim lewedefitu bezu yaltenegeru yabatochachinin tegadel be Egziabher cherenet tasmeleketen zenid ye Dingil Maryam lij Getachin Medhanitachin Eyesus Kirstos tsegana bereketun yestih.
ReplyDeleteDn Danieal . It is really very interesting and a kind of digging for the truth research style. We read good research style paper in your website since you started Ethiopia. May be I am wrong, I did not read church history related to southern part of Ethiopia. Brotherly, I am bagging you to do something in the next plan of research and I believe on you one day you may do it. The history of Ethiopian Orthodox Church in southern Ethiopia currently under suppresses and some hidden organ tries to make the church as history less in southern Ethiopia. Only you and similar people can only show the role the church in south for coming generation
ReplyDeletePlease Daniel just thinks those things in your mind is
Abune Anoriowes monastery at Dera during exile
Abune Aron Z weqait exile
The history of Ambericho at hadya
History of Genze Mariam
Temporary place ofAste Zeriaqobe and church history at Dewaro , Guragie zone and wenje
Temporary place of Asete serste Dingle
History of Birbir Mariam-I read what is written until now, but it not enough for me. Aste Gebre meskel and Saint yeard changed from old testament into new testament. Who made Old Testament in there?
Problem and solution
Research is not easy as we talk but if we are take responsibility as a church son, things it might going easy. Put your plan on website area of interest to study with cost and interested groups may make fundraising and cover the cost.
Yes.Thank you.I hope Dn.Dani may plan for the future.
DeleteDear Dn Daniel,
ReplyDeleteThank you !! More to follow .hope we will get the book after some time.
keep up the good work!!!
Dani, I was worried , since you keep silent for long time. I thought ,is he sick? Thanks God you are fine.
ReplyDeleteI am surprised u said nothing on the new patriarich. Lenegeru min yibalal, gira tegaban eko.
Thank you D/daniel kalhiwot yasmalen eg/r abezeto yebarkhe amen.
ReplyDeleteእግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልን::በፀጋ ይጠብቅልን:: ሌሎችንም ቅዱሳን አባቶቻችን እንደዚህ ብታሳውቁን መልካም ነው...
ReplyDeleteWell done !!!!
ReplyDeleteበዕድሜና በፀጋ ይጠብቃችሁ ዲ/ን ዳንኤል፣ዲ/ን ድንበሩ...
ReplyDelete(ሌሎችንም ቅዱሳን አባቶች እንደዚህ አሳውቁን::)
Two police? what are you...a government cadre?
ReplyDeleteኧረረረ ሚሚየ እንዲህ አይነት ጥያቄ አይጠየቅም፡፡ መጀመሪያ እስኪ ታሪኩን አንብቢ………..
DeleteWho said police serves cadres only? For your information they are in Ethiopia. And in Ethiopia Police and Police stations are everywhere. Those who get services are CITIZENS.
Delete+++
ReplyDeleteI like your silence about the election of the new patriarch! Bless You
+++
Temsegen Ye Abatachin Ye aba Filipos AMILAK Wagachihun Etif Derb Adergo Yekifelachu Enanite Be Akal Egna Bemnfes Berket Endenagnegn Seladergachihun Tiwlid Yemayersaw Sira New Eyeserah Yalhew MEDEHANIALEM Edemena Tenawin Yadilh Qale Hiwoten Yasemalin Daniiii
ReplyDeleteGreat JOb!!!! we have no word than this.
ReplyDeleteMay God Bless You
Getaneh
እግዚአብሔር ይስጥልን
ReplyDeleteበጣም መልካም የሆነ ታሪክ ነው፡፡ መልካሙን ሁሉ ይስጥልን እላለሁ ለ ዳ. ዳኒኤል ክብረትና ለጓደኛቹ፡፡
በእውንት የእኛ ክርስቲያኖች አባቶች የሰረቱት ታሪክ ለእኛ ለአሁኖቹ ትልቅ ስንቅና ወኔ የሚሆነን ነው፡፡
እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቀን አሜን፡፡
እግዚአብሔር ይስጥልን
ReplyDeleteበጣም መልካም የሆነ ታሪክ ነው፡፡ መልካሙን ሁሉ ይስጥልን እላለሁ ለ ዳ. ዳኒኤል ክብረትና ለጓደኛቹ፡፡
በእውንት የእኛ ክርስቲያኖች አባቶች የሰረቱት ታሪክ ለእኛ ለአሁኖቹ ትልቅ ስንቅና ወኔ የሚሆነን ነው፡፡
እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቀን አሜን፡፡
በጣም ደስ የሚል ስራ ነው የፃድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ዳኒ እና ባልንጀሮቹ እንዲሁም በጉዞው ላይ የተሳተፉ በሙሉ ምስጋና ይገባቸዋል።
ReplyDeleteእጅግ በጣም የሚደነቅ ተግባር ማለት ተቀብሮ የተዳፈነን እውነት ከምንም መረጃ ተነስቶ እንዲህ ወደሚጨበጥ ህያው ቅርስነት መለወጥ ነው፡፡ በጉዞው ሂደት የተሳተፉና የተባበሩ ወገኖች ሁሉ ሃያሉ እግዚአብሔር ዋጋቸውን ይክፈላቸው እላለሁ በመጨረሻም ለተነሳው ሃሳብ ሙሉ ድጋፌን እሰጣለሁ ለተግባራዊነቱም ከኔ የሚጠበቀውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፡፡
ReplyDeleteፊት ለፊታችን ደብረ ዕንቁ ማርያም ታየችን፡፡ አንቺን ፍለጋ ስንት ጊዜ ለፋን፣ ስንቱንስ ሀገር አቋረጥን፡፡ ስንቱን ተራራና ገደልስ ተሻገርን፡፡
ReplyDeletethank you God bless you, you did your best to this generation.
thank you
በጣም ዕድለኞች ነን እናተ በተግባር በድጋም እኛ ደግሞ በጭንቀተ በሃሳብ የአባታችንን በረከት አገኘን አንድ ቀን ደግሞ በአካል እንደናንተ ለማየት እንበቃ ይሆናል ማን ያውቃል የአባታችን በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን ዕድሜና ጤና ለደከማችሁ ለእናንተና ለተባበሯችሁ ሁሉ ይስጥልን አሜን
ReplyDeletewtbhm
ዲያቆን ዳንኤል ታድለሃል ምነው አንተን ባረገኝ ብዬ በጣም ቀናሁ እግዚአብሔር የጻዲቁን በረከት ይከፈልህ
ReplyDeleteእንዴት ነህ እኔስ እንደ አባ ፊልጶስን የፖትሪያርኩን ምርጫ ተከታትለህ
ReplyDeleteታስነብበናለህ ብየ ነበር ግን አልሆነም ለምን? ቄሱም ዝም መጽሐፊም ዝም
ሆነብህ ወይምስ እብድ እህል ገዝቼ ሚስቴን አሳበድኳት እነዳለው ሰው ሆኖብህ
‘ቢናገሩ አፈኛ ዝም ቢሉ ሞኝ’ የሚሉት ነገር ሆነ እኮ:: እረ በራሳችን ዛቢያ እንሽከርከር ወገን:: ኃጢያት ኃጢአት የሚሆነው ሰው ሲያውቀው/ሲገለጥ/ ብቻ አይደለም:: ስናስበው ጀምሮ የተገለጠና የሚያስጠይቅም ነው:: ስማችን የተደበቀው እኮ ከሰዎች ነው:: ቅኔና አሽሙር እንደተቀላቀለበት ሰው የምን ማላገጽ ነው:: ተከባብረን መወያየቱ አይሻልም?
Deleteየቅዱሱ አባታችን አባ ፊሊጶስ በረከታቸው ይደርብን!!!
ReplyDeleteEgizabhare yesteline kal hiwot yasemalene.
Bereketachew Yedereben! Dn. Dani Amlak Wagaehen yekefeleh! Legam Endih yalu Kudesanen bereket endenkafel Ye Kidusan Amlak Lebuna yesten! Fikadum Yehunelen!
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል፡- እግዚአብሔር ይስጥልን፤ ማየት የማንችለውን እንድናይ አድርገኸናልና ምስጋና ይጋባሃል፡፡ በእውነት ለመናገር ሁሉንም ክፍሎች ሳነባቸው በጉዟችሁ ሁሉ አብሬያችሁ በአካል ያለሁ ያክል ነው ይሰማኝ የነበረው፡፡ አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ይጠብቅህ፡፡ ጸጋህን ያብዛልህ፡፡
ReplyDeleteመጣዓለም አማረ፣ ደ/ወሎ ኮምቦልቻ
God Bless you Brothers. It was a blessed journey.
ReplyDeleteI have One Question(Suggestion)to Dn. Daniel
Would tell the Exact History of Dekike Estifanos who were Murdered in the cover of Protestantism by Atse Zera Yaekob and his Descendants in a very painful and immoral manner.
I hope You can do it better than Professor Getachew if you are not Biased to one King rather than truth.
At that time I will accept your Title of "Yebetekrestian tarik Temeramari"
May The Almighty God bless you.
God bless you!! Thank you!
ReplyDeletethank you brother.
ReplyDeleteHi, nice article as always Dn Daniel, God bless you
ReplyDelete"እንደነ አቡነ ፊልጶስ ያሉ በቤተ ክርስቲያን ዘላለም የሚያበራ፣ ለትውልዱም የሥነ ምግባርና የሞራል ስንቅ የሚሆን ታሪክ ያላቸው ሰማዕታት አባቶች"
Can any one share a link or a resource to read about Abune Philipos?
GOD Bless U!!!
ReplyDeleteበማኅበር ተሰባስበው ክርስቲያናዊ ሥራ የሚሠሩ ወጣቶችም እንደ አቡነ ፊልጶስ ባሉ አባቶች ስም በመጠራትና ታሪካቸውን ከፍ በማድረግ የበረከታቸው ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ታሪክ ይጋብዛቸዋል፡፡
ReplyDeleteመልካም ምክር እግዚብሔር ፀጋውን ያብዛልን ለወንድማች ዳኒኤል እና ለባልደቦቹ
Thank you so much.God bless you.
ReplyDeletetilk kibr yalachewn abatoch asawekn yentes tigat endet talak new amlak keri zemenhn yibark amen .simads endet yaltawekech bereket yetakefech hager nat .
ReplyDeleteI was wondering were you at for the last few month. You chosed to be away . On this holly trip. As always. Amazed on ur adventure trip along sprituality keep us on ur prayer . Hope we see you on baele weld. Or when you come to Nashville . Tn. It seems both church is open for you now here in mashville. Missed u brother. See u in canada baleweld. Loveed ur trip
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል!
ReplyDeleteበአጭሩ ወደር የሌለው ስራ ነው፦ እግዚአብሔር በዚህ መስክ ትጋትን ያብዛልህ። በነገራችን ላይ እንዲህ መሰሉን ምርምርና ስራ በተለያየ ነገር መደገፍ የሚቻልበትን መድረክ ብታዘጋጅ መልካም ይመስለኛል።
ከትም
God bless You ዲ/ን ዳንኤል!.How fantastic to visit and search the place where Saints lay for rest .Though I am late to comment እግዚአብሔር ይስጥልን፤ ማየት የማንችለውን እንድናይ አድርገኸናልና ምስጋና ይጋባሃል
ReplyDeletemay God bless you! it is great job that you made know more about kristianity in the old days!
ReplyDeleteI did not know there was another Abune Philpos in that part of our country. I know Abune Philpos of Debre Bizen which is now in Eritrea. Abune Philpos was one of Abune Ewostatewos'(1265-1344AD) disciple who went to Armenia because he wanted Saturday be observed equally as Sunday, and other Ethiopian fathers, like Sereqe Birhan, and the king refused this at that time. Abune Ewostatewos died in Armenia in 1344.After his death, his disciple Abune Philpos came back to Ethiopia with his other brethren and established Debre Bizen in about 1380s. The Saturday's issue was resolved at Debre Mitmaq (Bulga Shewa) by Emperor Zerayaeqob in 1442. So now I learn that there was another St. Philpos in Ethiopia. I thank you Deacon Daniel for that. I also saw your journey to my birth place area of Simien, Northern Gonder . You are doing great job although I disagree some times with your stand on some issues. However, I encourage you to continue your tour and research about our ancient country and church and share with us, your readers, your discoveries. May God be with you during your travel and always, amen.
ReplyDeleteCongratulations!
ReplyDeleteFirst of all, God, who is the power, thought and sound for all of us, his children, be praised. You, the mic and instrunment throughout all this time, here the respect and praise that you deserve. Wesbihat le Egziabher.
ReplyDeleteEgziabeher Yebarkeh
ReplyDeleteGod bless
ReplyDeleteye abatachin abune philipos bereket kante gar yiun.
ReplyDeleteyedawit degamiw kahin lig negn.
ዲያቆን ከምን መጀመር እንዳለብኝ ባላውቅም የጉዞ ማስታወሻ በሚለው ጦማርህ አቡነ ፊልጶስን ፍለጋ የሚለዉን ካነበብኩ ወዲህ ዉስጤ ተነክቶአል። ምክንያቱ ምን መሰለህ ዲያቆን ይህቺ ደብረእንቁ የምትባል ቦታ እኔ ተወልጄ ያደኩበት ሀገር ስማዳ ስላለች እና እኔ ግን ታሪኩን እና ቦታውን አለማውቄ በጣም ስለገረመኝ ነው እናም ዲያቆን ያንተ ሥራና ልፋት ለኔ እና ለመሰሎቼ በጣም አስተማሪና መካሪ ነው ።ስለዚህ ዲያቆን በርታ የአቡነ ፊልጶስ በረከት ካንተ ጋር ይሁን ።
ReplyDelete