click here for pdf
እናቱ ለአሥራ አምስት ዓመት ልጇ የአክስቱን ሞት እንዴት እንደምትነግረው
ተጨንቃለች፡፡ ይህቺ የአባቱ እኅት የሆነችው የልጁ አክስት ልጅ አልነበራትምና እንደ ልጇ ታየው ነበር፡፡ አብራው ኳስ ታያለች፤
አብራው ትዝናናለች፣ አብራው ታጠናለች፣ አብራው ትዋኛለች፣ አብራው ፊልም ታያለች፣ አብራው ኳስ ትጫወታለች፡፡
እንዲህ የምትሆንለትን አክስቱን ሞቷን ሲሰማ ያብዳል ብላ እናቱ ተጨንቃለች፡፡ እናም
ትንቆራጠጣለች፡፡ ከትምህርት ቤት ሲመጣ መጀመርያ መክሰስ አበላችውና ወደ መኝታ ቤት ወሰደችው፡፡ ከዚያም በሰው ልጅ ሕይወት
ውስጥ መኖርና መሞት ያለ መሆኑን፤ አንዳንድ ጊዜ የምንወዳቸው ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ ትነግረው ጀመር፡፡ ልጁ ግራ ገባው፡፡
‹እይውልህ ልጄ› አለች እናቱ ድምጽዋ ሆድዋ ውስጥ ገብቶ ሊጠፋ እየደረሰ፡፡ ‹‹ያች
የምትወድህና የምትወዳት አክስትህ በድንገት ትናንት ማታ ዐረፈች›› አለችው፡፡
‹‹ምን?››
አለና ሶፋው ላይ ተደፍቶ ድምጽ ሳያወጣ አለቀሰ፡፡ ከዚያም ከተደፋበት ተቃንቶ አንገቱን ሰበረና ይነቀንቅ ጀመር፡፡
እናቱ የሚያደርገውን ሁሉ እንዲሁ ትከታተላለች፡፡ እንደሰማ አገር ይያዝልኝ ይላል፤
በድንጋጤ አቅሉን ይስታል፤ መሬት ላይ ይፈጠፈጣል፤ ዓባይ ዓባዩን ያነባዋል ብላ ነበር የጠበቀችው፡፡ እንዲህ ቢሆንባት ምን
ማድረግ እንደምትችል ነበር ስትጨነቅ የቆየችው፡፡ አንዳንድ ጎረቤቶቿንም ስትጠራቸው መጥተው እንዲረዷት ተማጽናቸው ነበር፡፡
‹‹አንተ፣ ያች እንደዚያ የምታሞላቅቅህ አክስትህ ሞታ እንዲህ ነው የምትሆነው››
አለችው ተናድዳ፡፡
‹‹ምን ሆንኩ?››
‹‹አታለቅስም እንዴ?››
‹‹እያለቀስኩ አይደል እንዴ፤ ዕንባዬን አታይውም››
‹‹ለእርሷ እንደዚህ ነው የምታለቅስላት፤ ማፈሪያ ነህ፡፡ እርሷኮ ላንተ ያልሆነችው
የለም፡፡ እንደ ሕጻን አብራህ ትጫወታለች፤ እንደ ጓደኛ ፊልም ቤት ይዛህ ትገባለች፤ እንደ እናት ትሳሳልሃለች፤ ለእርሷ
እንደዚህ ነው የምታለቅሰው›› እናቱ አዝና ሶፋው ላይ ዘርፈጥ ብላ ተቀመጠች፡፡
‹‹ታድያ እንዴት ነው ለርሷ የሚለቀሰው?›› አላት ዕንባውን እየጠረገ፡፡
‹‹እትዬ እትዬ፤ ጉድ አደረግሽኝ፤ ሳትነግሪኝ፤ ምነው ጥለሽኝ ሄድሽ፤ እየተባለ ነዋ››
‹‹እንዴ እማዬ እንዴት ልትነግረኝ ትችላለች? በድንገት ነው የሞተችው አላልሽኝም? ደግሞስ ጥለሽኝ ሄድሽ ማለት ምን
ማለት ነው? እና ይዛኝ እንድትሄድ ፈለግሽ?››
እናቱ አፏን እጇ ላይ ጭናለች፡፡
‹‹አይ የዛሬ ዘመን ልጆች፤ የልቅሶው ወግ እንደዚህ ነው፤ የቅርብ ዘመድ እንዲህ ነው የሚያለቅሰው፤ የሸንኮሬ ልጅ ‹ጥሪኝ
አክስቴ ጥሪኝ› እያለ ጠዋት ሲያለቅስ ባየኸው››
‹‹እንዴ እርሱ ደግሞ ምን ነክቶታል፡፡ ባለፈው ‹ና ግቢውን እናጽዳ› ብላ ስትጠራው ያልመጣውን አሁን የት ነው ጥሪኝ
የሚላት? ውሸታም ነው፡፡ አሁን አንቺ ብትጠራሽ ትሄጃለሽ?››
እናቱ አማተበች፡፡ ‹‹ደረቅ ነህ ልጄ፤ ደረቅ ነህ፤ ነውር ነው፣ በእውነት ነውር ነው እንደዚህ አይባልም፡፡ በዚህ ዓይነት
ለእኔም ጊዜ እንደዚሁ ነው›› ከልቧ አዘነች፡፡ ደግሞም ታያት፡፡ እርሷ ሞታ፤ ልጇ ዝም ሲል፤ ሰው ሁሉ ዓይንህን ላፈር ሲለው፡፡
‹አሁን የርሷ ልጅ ይኼ ይሁን› እያለ በዓይኑ አፈር ድሜ ሲያበላው፡፡ ታያት፡፡
‹‹እማዬ ግን አንቺ የምትፈልጊው ካሰብሽው ቦታ የሚደርስልሽ ልጅ ነው ወይስ ስትሞቺ የሚያለቅስልሽ? እኔን ሠራ ነው
ወይስ እንዳለቅስ? ደግሞም ያኔ የምሆነውን ያኔ ነው ማወቅ የሚቻለው፡፡ እኔ ማዘን ያለብኝ ለራሴ ነው ወይስ ለሰው? ኀዘን እንደ
ፊልምና ድራማ ለሕዝብ መታየት አለበት?››
‹‹እርሱማ ልክ ነበርክ ልጄ፤ ግን ሰው ይቀየምሃል፤ ዘመዶቻችን ይቀየሙሃል፡፡ በልቶ ካጅ፣ ወጭት ሰባሪ፣ እጅ ነካሽ
ይሉሃል ልጄ፡፡››
‹‹ይበሉኛ፤ እኔ የት እሰማቸዋለሁ››
‹‹እኔ እሰማለኋ››
‹‹አትስሚያቸዋ፤ ተያቸው››
‹‹እንዴት አድርጌ ልጄ፡፡ የሰው ምላስ መርዝ ነው ይገድላል፡፡ ዱላ ነው ይሰብራል፡፡ እኔ ልጄን በክፉ እንዲያነሡብኝ
አልፈልግም፡፡ የሰው ጥርስ ውስጥ ትገባለህ ልጄ፡፡ ደግሞ እርሷ ናት እንዲህ ያደረገችው ይሉኛል፡፡ የአባትህ ዘመዶች ይጠምዱኛል፡፡
አንተስ ብትሆን አክስትህ ናት፤ እንዲያ የምትወድህ አክስትህ ናት፤ ምናለ ብታለቅስላት?››
‹‹ቆይ ግን አሁን ማልቀስ ያለብኝ ለእርሷ ነው ለእኔ››
‹‹እንዴት እንዴት?››
‹‹አጉራሼ፤ አልባሼ፤ ጠያቂዬ፤ ሆዴ፤ ደጋፊዬ እያሉ የሚያለቅሱት ለሟቹ አዝነው ነው ወይስ እነርሱ ስለቀረባቸው? ማረፊያችን
ነበርሽ፤ ማን ላመትባል ይጠራናል ብሎ ማልቀስ አሁን ለሟች ነው ለራስ? ቆይ ግን ሰው ስለ ሰው የሚመሰክረው ሲሞት በልቅሶ ዜማ
ብቻ ነው እንዴ?››
‹‹የዛሬ ልጆች መፈላሰም ትወዳላችሁ እንዴው፤ አለቀሰ አላለቀሰም? የሚል እንጂ ለምን አለቀሰ? የሚል ዕድር እስካሁን
የለም፡፡ አቤት እገሌ እንዴት ቢወዳት ነው፤ አቤት እገሌ አለቃቀሱን ስትችልበት ይባላል እንጂ ለራሱ ነው ወይስ ለሟች? ተብሎ ድንኳን
ውስጥ አይጠየቅም፡፡ ይኼው በቀደም አንዱ የነ እትዬ የሰው ሐረግ ድንኳን ገብቶ ለያዥ ለገራዥ እስኪያስቸግር መሬት እየወደቀ ሲያለቅስ
ቆየ፡፡ ሰው ሁሉ ምን ቢዋደዱ ነው እስኪል ድረስ፡፡ ማን ይገላግለው፡፡ ሰውን ሁሉ ዕንባ በዕንባ አራጨው፡፡ በመጨረሻ በቄስ ተገዝቶ
አቆመና ቀና ሲል ሰዎቹንም አያውቃቸውም፤ ፎቶዋን አያውቀውም፡፡ ለካስ ድንኳን ተሳስቶ ኖሯል፡፡ ይቅርታ ጠይቆ ወጣ አሉ፡፡ እዚያኛውም
ሄዶ እንዲሁ ሲያለቅስ ነበረ አሉ፡፡››
‹‹እና አሁን ይኼ በማያገባውና በማያውቀው ልቅሶ ገብቶ የሚያለቅሰው የፍቅር መግለጫ ነው?››
‹‹ባህሉ ነዋ ልጄ፡፡ መቼም ቢሳሳትም ልቅሶውን ሁላችንም አደነቅንለት፡፡ ወንድ ልጅ እንደዚህ ሲያለቅስ እኔ አይቼ አላውቅም፡፡
‹ዘመዶቹ ታድለው› ነው ያልነው፡፡ አስለቃሽም አያስፈልጋቸው፡፡ እኛን እንኳን የረሳነውን ሁሉ እያስታወሰ አስለቀሰንኮ፡፡››
‹‹እሺ አሁን ምን አድርግ ነው የምትይኝ››
‹‹እንሂድና አንድ ጊዜ ብቻ ሰው እንዲያይህ ‹አጉራሼ አልባሼ› ብለህ ጯጩኸኽ እንገላገል››
‹‹እኔንኮ አላጎረሰችኝም፣ አላለበሰችኝም››
‹‹ይኼ ልጅ ምን ሆኗል ዛሬ፡፡ አብራህ አልነበረም ኳስ የምታየው? ከርሷ ጋር አልነበረም ፊልም የምትገባው? ደውለህ
ለርሷ አልነበረም እገሌ አገባ፤ እገሌ ተሸነፈ ትላት የነበረው? ሶደሬ አልወሰደችህም? ጌም አልጋበዘችህም? ዋና አላስዋኘችህም?
በጣም ታሳዝናለህ፡፡ እንዴት እንደዚህ ትላለህ?›› ተቀየመችው፡፡
‹‹እና ይኼ ማጉረስ ማልበስ ነው? የምጎርሰው ራሴ ነኝ፣ የምለብሰውም ራሴ ነኝ›› አላት፡፡
‹‹ኤዲያ፤ የስምንተኛው ሺ ልጆች፤ አባባሉንም አታውቁትም፡፡ ይህኮ አባባል ነው፡፡በል አሁን ከሄድክ እንሂድ ሰው ጥርስ
ውስጥ እንዳታስገባኝ፡፡ ››
‹‹እኔኮ አልችልበትም፡፡ እንደናንተ ማድረግ አልችልበትም፡፡ እናንተኮ የብዙ ዓመት ልምድ አላችሁ››
‹‹ሆሆይ›› ሳቋ መጣ ‹‹የመሥሪያ ቤት ቅጥር አደረግከው እንዴ ልምድ ምናምን የምትለው፡፡ ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም
ሲባል አልሰማህም፡፡››
‹‹እሺ ሄጄ ምን ላድርግ?››
‹‹ድንኳን እስክንደርስ ዝም ትላለህ፡፡ ልክ ድንኳኑ አካባቢ ስንደርስ እኔ እጮኻለሁ፣ አንተም እኔን ተከትለህ ትጮህና
‹አልሰማሁም ነበር፤ አልሰማሁም ነበር› እያልክ ኡኡ ትላለህ››
‹‹እንዴ እማዬ ይኼው ሰማሁ አይደል እንዴ፤ ይኼማ ውሸት ነው፡፡››
‹‹ልጄ እኔ እናትህን ስማኝ፤ እንደዚያ ነው የሚባለው፡፡ አባባል ነው፡፡ ደግሞ በገላጋይ ካልሆነ በቀር ልቅሶህን እንዳታቆም››
‹‹እንዴ ዝም በል እያሉኝ ልቀጥል? እንዲያውም ምክንያት ካገኘሁ ተገላገልኩ››
‹‹እንዲያውም ከቻልክ መሬት ውደቅ››
‹‹እንዴ እማዬ እኔ በረኛ አይደለሁ ለምን መሬት እወድቃለሁ››
‹‹በርህ ይጥፋና ባህል ነው አልኩህ፡፡ ሰው ያደንቅሃል፤ እንዲያውም ትንሽ ተንከባለል››
‹‹እማዬ አሁንስ አበዛሽው፣ ሳቄ ቢመጣስ፡፡ አንቺኮ የድራማ አክት የምታስጠኚኝ ነው የመሰልሽኝ››
‹‹በል ተወው ደግሞ ታዋርደኛለህ›› አለችና ወደ ምኝታ ቤት ገብታ ጋቢና ፎጣ ይዛ መጣች፡፡
‹‹በል እንካ ጋቢውን ትከሻህ ላይ፣ ፎጣውን አንገትህ ላይ አድርግ፡፡ ስታለቅስ በፎጣው ተሸፈን፡፡ ዕንባ እንኳን ባይመጣብህ
የሚያይህ የለም፡፡››
‹‹የልቅሶ ቤት ዩኒፎርም መሆኑ ነው›› አላት፡፡ ‹‹ሆሆ›› አለች አንገቷን እየነቀነቀች፡፡
ሄዱ፡፡ ልቅሶው ቤት በር ላይ ከመድረሳቸው በፊት አንድ ጓደኛው ደወለና የሆነ የእግር ኳስ ውጤት ነገረው፡፡ ውጤቱ አስደሳች
ነበር፡፡ እርሱን እያሰበ ድንኳኑ በር ላይ ሲደርሱ እናቱ ያስጠናችው ነገር ተረሳው፡፡ ጉዱ ፈላ፡፡ መኪናዋን ሲያዩ ለቀስተኞቹ ተንጋግተው
ከድንኳኑ ወጡና ከበቧቸው፡፡ እናት ከመኪናዋ እየጮኸች ወረደች፡፡ ልጁ ግን የሚባለው ነገር ጠፍቶታል፡፡ ከእናቱ ጎን ሆነና በፎጣው
ተሸፍኖ ‹‹እማዬ ምን ነበር ያልሽኝ፤ ስቴፑ ጠፋኝኮ›› አላት፡፡ እናቱ በዓይነ መዓት አየችውና ጩኸቷን ቀጠለች፡፡
እርሱ ግን በአፉ እየጮኸ በልቡ ስቴፑን አሰበው፡፡ አልመጣለት አለ፡፡ ቀና ሲል የአክስቱን ፎቶ በአንድ አልቃሽ እጅ
ላይ አየው፡፡ ያን ጊዜ የሆነ የኀዘን ስሜት መጣበት፡፡ ልቡ ተንቦጨቦጨ፡፡ ትዝ አለው ነገር ዓለሙ፡፡ እናም ወደራሱ ልቅሶ ተመለሰ፡፡
‹‹እትዬ እትዬ አይስክሬም ማን ይገዛልኛል፤ ሶደሬ ማን ይወስደኛል፤ ጌም ማን ያጫውተኛል፤ እትዬ እትዬ ኳስ ከማን ጋር
አያለሁ፡፡ ሩኒ ሲያገባ ለማን እነግራለሁ፤ ሮናልዶ ሲስት ከማን ጋር አወራለሁ፤ ሜሲ ሲያገባ ለማን እደውላለሁ፡፡ እትዬ ደውይልኝ፤
ማን አገባ በይኝ፤ ማን ተጫወተ በይኝ፤ እትዬ፡፡ እትዬ ዛሬኮ ማንቼ ይጫወታል፤ ከማን ጋር አያለሁ፡፡ እትዬ የዛሬው ጨዋታኮ ወሳኝ
ነው›› አስነካው፡፡
ወዲያው አንድ በእርሱ እድሜ ያለ ልጅ ነጠር ነጠር እያለ መጣና በጆሮው ‹‹ማንቼ ተጫውቶ ቅድም ተሸነፈኮ›› አለው፡፡
ይህን ጊዜ መሬት ላይ ወድቆ እየተንከባለለ ‹‹እርምሽን ባትኖሪ ማንቼ ተሸነፈልሽ፤ እርምሽን ባትኖሪ ቫምፐርሲ ሳያገባ
ቀረ፡፡ እርምሽን ባትኖሪ ማንቼ ነጥብ ጣለ፡፡ የፈራሁት ይኼን ነበር፡፡›› ለቀስተኛው ሁሉ ልቅሶውን ቀስ በቀስ እየተወ እርሱን
ያየው ጀመር፡፡ እናቱ ግን ሾልካ የት እንደገባች አልታወቀም፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፡፡
በሌላ ፕሬስ ላይ መጠቀም አይፈቀድም
እየሳቅኩኝ ቁምነገርህን አገኘሁት…በርታ ዲ/ን ዳንኤል…ከጎንደር ልደታ
ReplyDeletevery nice
Deleteit is nice, this is the problem we are facing in this days . i say "Emebirhan titebikihe"
DeleteIt is so funny. I can't stop laughing. Wey! Manchea
ReplyDeletedani God bless u!
I cannt stop loughing Ahahaaa .
balfew na gibiwn enatsda bila sitteraw yalmetawn yet new tirgn yemilat...
ermishin batnori manche teshenefe!ahahah
hahahahha...i cant stop laughing
ReplyDeleteIntersting view. It kinda give me mixted feeling how things have changed in this generation.
ReplyDeleteየጠቅላይ ሚኒስትሩን ለቅሶ አስታወስከኝ። በተለይ ያንን "አባታችን እሳቸውን ተማምነን ነው ጎዳና የወጣነው" ያለውን።
ReplyDelete"አባታችን እሳቸውን ተማምነን ነው ጎዳና የወጣነው"
DeleteThis is an amazing way of showing how the Ethiopian youth is dying of the western disease soccer. the youth does not know his contry but knows the life history of each player. the youth is morally dying.
ReplyDeleteWhat is the moral of the story?
ReplyDelete"Be Yourself"
ዳኔ ምን ልበልህ በእውን ይህ ጽሁፍ ያንተ ነው? ወይስ ለዛሬ አምዶን ለሌላ ሰው አዋስከው?
ReplyDeleteI just have one question, what is the main idea behind, to be ourselves ( what the kid do ) or to keep our culture (what the mother force him to do)?????? anyone who understand it.
ReplyDeleteወዳጄ ዳንኤልኮ እዚህ ጽሑፍ ላይ የትውልድን የባህልና የእሴት ልዩነት ነው እያሳቀ የነገረን፡፡ ለእናቱ ዋና ጉዳይ የሆነው ነገር ልጁን ሊገባው አልቻለም፡፡ በሰው ጥርስ ውስጥ መግባት፣ መታማትና ልቅሶ አያውቅም መባል ለርሱ ምኑም አይደለም፡፡ የእርሱ እሴትኮ ኀዘን የግል ጉዳይ ነው ለምን ለሕዝብ አለቅሳለሁ? ከሚለው መሠረታዊ ጥያቄ የሚመነጭ ነው፡፡ የሚያለቅሱበት ምክንያትም ተለያይቷል፡፡
Deleteቀጣዩን ትውልድ አንድን ነገር አድርግ ስንለው የማስረዳትና የማሳመን ግዴታ አለብን፡፡ እንዲሁ ባህል ስለሆነ፤ ሰው ስለሚያማ፣ ጥርስ ላለመግባት ቢባል ማንም አይቀበልም፡፡ አመክንዮን ይፈልጋል፡፡ ይህንን ነው ዳንኤል ያሳየን፡፡ የትውልዱን የባህልና የእሴት ልዩነት፡፡
ጽሁፉ ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪም ያስተላልፋል ብዬ የማስበው መልክት፤ ምንም እንኳን ባህላችን ከጊዜው ጋር አብሮ መራመድ ቢኖርበትም ከዚሁ ጎን ለጎን መታሰበብ ያለበት ጉዳይ ያለውን ባህልም ሁሉን ነገር መጥፎ ነው ውይም በጎ ብቻ ብለን መደምደም እንደሌለብን ያሳያል። ለምሳሌ 'ቀና ሲል የአክስቱን ፎቶ በአንድ አልቃሽ እጅ ላይ አየው፡፡ ያን ጊዜ የሆነ የኀዘን ስሜት መጣበት፡፡ ልቡ ተንቦጨቦጨ፡፡ ትዝ አለው ነገር ዓለሙ፡፡ እናም ወደራሱ ልቅሶ ተመለሰ' የሚለው ዓ/ነገር የዚህ የለቅሶ ባህላችን ምን አልባት ሊቀየር የሚገባው ነገሩ ጎልቶ ቢታይም በጎ ጎንም እንዳለው ማስታወስ አለብን ባይ ነኝ።
DeleteWhat Dn. Daniel wants to convey with humor is how we supposed to express feelings of sorrow or grief naturally without any artificial makeup due to social pressure. Besides, he highlighted and revealed how wrong we are in showing our sympathy with a self centered attitude while we are losing our beloved relative.
DeletePersonally, what I really admire and like about the western culture is especially when they perform their funeral.It is quite silent. But underneath it, as I tried to feel it, I feel deep grief, born from love.
God bless!!!
It is a good view dani.God bless you.
ReplyDeleteበየቤታች የምናየው ነው ያሳየህን እናመሰግናለን ሙሉ ለሙሉ እየሳቅሁ አነበብኩት
ReplyDeletebetam asakegn, gen tekekel new ene ethiopia sehed
ReplyDeletekelejochu gar megbabat alchalkum meknyatum ene yekomkut yezare 16 amet keagere seweta neberena semeles alfewegnal
May GOD bless u Dani
ReplyDeleteወዳጄ ዳንኤልኮ እዚህ ጽሑፍ ላይ የትውልድን የባህልና የእሴት ልዩነት ነው እያሳቀ የነገረን፡፡ ለእናቱ ዋና ጉዳይ የሆነው ነገር ልጁን ሊገባው አልቻለም፡፡ በሰው ጥርስ ውስጥ መግባት፣ መታማትና ልቅሶ አያውቅም መባል ለርሱ ምኑም አይደለም፡፡ የእርሱ እሴትኮ ኀዘን የግል ጉዳይ ነው ለምን ለሕዝብ አለቅሳለሁ? ከሚለው መሠረታዊ ጥያቄ የሚመነጭ ነው፡፡ የሚያለቅሱበት ምክንያትም ተለያይቷል፡፡
ቀጣዩን ትውልድ አንድን ነገር አድርግ ስንለው የማስረዳትና የማሳመን ግዴታ አለብን፡፡ እንዲሁ ባህል ስለሆነ፤ ሰው ስለሚያማ፣ ጥርስ ላለመግባት ቢባል ማንም አይቀበልም፡፡ አመክንዮን ይፈልጋል፡፡ ይህንን ነው ዳንኤል ያሳየን፡፡ የትውልዱን የባህልና የእሴት ልዩነት፡፡
Dani wosetu Teru temhert alew Dess yelale biyasazenem yasekal Bertalen
ReplyDeletethank you D/N Daniel God bless you.
ReplyDeleteVery Intersting and Exciting !!! Keep on Going
ReplyDeleteHahahaha!!!!!!!!!
ReplyDeleteyigermal bahilachin wedet eyehede endehone!!!!
Diakon Daniel! stay blessed
ReplyDeleteexactly! ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም። ዕድሜና ጤና ይስጥልን ዳኒ።
ReplyDeleteYigermal. Ahune "Manchen" lekistibet resto akistun maseb yiketew. Lib wosaj "manche". Bizu gud ale bezih tiwuld lay.
ReplyDeleteትውልዱ የቱጋ እንደቆመ የሚያሳየ ፅሁፍ ነው...በርታ
ReplyDeleteIt is a very interesting,kale-siga yasemalin.
ReplyDeletekale-siga yasemalin
Deleteሰላምና ጤና በእግኢአብሔር ስም እየተመኘሁ የዌብ ፔጅህን ግርጌ (footer) ታስተካክል ዘንድ እመክርሃለው፡፡ Awesome Inc. template. Template images by wingmar. Powered by Blogger. የሆነውን በራስህ ብትቀይረው ቀላል ነው፡፡ ርዳታ ካስፈለገህ በ addis_mahe2020@yahoo.com text አድርግልኝ፡፡
ReplyDeleteNothing to say
ReplyDeleteWOW denke new eyasake yastmral,
ReplyDeleteተመቸኸኝ ዳኒ!! the 4G generation አለቃቀስ ::ሴትዬዋ 2G ያለች ይመስለኛል:: Ethiopia አሑን ያለው ነካ 3G ነው!
ReplyDeleteDanii..EGZIABHER AMILAK Tsegawin Selabezalih Tshufochih Hulu Asetemariwoch Nachew Enes Yesakugn Temarku Ahunim AMILAKE Kidusan tsegawin yabizalih
ReplyDeletebetam des emil new
ReplyDeleteወገኖቸ የዳኔን መልእክት እንደተለመደው ግሩም ነው በማለታችሁ ደስተኛ ነኝ ለጥያቄም የሜቀርብ አይደለም። አዎ ግሩም ነው ። ዳኔ አንድ ሐሳብ አለኝ ባሕልን ፤ እርማትን ፤ ምክርን ፤ የመሳሰሉት መጣጥፎችን የመስኮት ዓምድ ክፈትልን እና አንተው እየተከታተልከን እኛው እንጻፍ። አንተ ግን ወንድሜ እግዝአብሔርም ረድቶህ አንተም ረጋ ያልክ አስተዋይ በመሆንሕ ብዙ የውጭና የሐገር ውስጥ አስገራሜና ትምህርት ሰጭ መጽሐፍቶችና ጥንታዌ ታሪኮች ከሆኑት ክምችቶቾህ ብታቃምሰን ውድዋን ግዜሕንም በዜያ ብታሳልፍ እወዳለሁ።
ReplyDeleteሰላመ እግዚአብሔር ይብዛልህ ዲ/ን ዳኒ እስካሁን እያሳቀኝ ነው ግን ደግሞ ትምህርት ወስጀብታለው "እርምሽን ባትኖሪ ማንቼ ተሸነፈ ..." መምሰል ቢያቅተው መሆኑን ግን አልከበደውም የስው ልጅ ከህይውታችን ልናስወግድ የሚገባን ትልቁ ነገር ሰው ሰራሽነትን ነው። መንፍሳዊ ስራ መስራት መንፈሳዊ አያስብልም መንፍሳዊ መሆን እንጂ። ሰይጣናት ትገዝተው ቤ/መቅደስ ቢስሩ/እንደ ጠ.ስልሞን ዘመን/ ታዲያ ሰይጣናት መንፈሳዊ ናቸው ማለት እንችላልን፤ በፍጹም.. ስልዚህ በኛ ባልሆነ ነገር ከምንመስል በኛ በሆነ ነገር እንሁን ኦሪጂናሊቲ ይታይብን።"የሰው የሰው ነዉ" እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይርዳን አሜን!!
ReplyDeleteፈጣሪ እግዚአብሄር ቃለ ህይወት ያሰማልን ። አምላካችንም እኛን እራሳችንን እንድንሆን እንጂ ሌላውን ብይሉኝታ ከመምስል ይጠብቅን "ብኖር ለእግዚአብሄር ብሞትም ለእግዚአብሔር" ለማለት እንድንችል ፍጣሪ ያብቃን እሱ ለኛ ብዙ ነገር ሆኗልና። ህይውታችን እውንተኛ መንገድ ላይ የምትቆመው እራሳችንን መሆን ስንችል ብቻ ነው መንፍሳዊ ስራ ምስራት መንፈሳዊ አያደርግም መንፈሳዊ መሆን ነዉ መንፈሳዊ የሚያስብለው "በዘመነ ጠ.ሰለሞን ሰይጣናት ተገዝተው ቤ/መቅደሱን ሰርትዋል ታዲያ ምንፍሳዊ ሰራ ሰራ ቢስሩም ስይጣናት መንፈሳዊያን ናቸው ማለት እንችላልን? በፍጹም! በራስ ባልሆነ ነገር ከመምስል በራስ ባመኑበትና ብራስ በሆነ ነገር መሆን ይበልጣል። ፈጣሪ ይርዳን! የድንግል አማላጅነት አይለይን። አርቴፊሻል ህይወት ከኛ ይራቅ።
ReplyDeleteyameral!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteI found it really how the young generation is far from the ancestors!
ReplyDeleteፈጣሪ እግዚአብሄር ቃለ ህይወት ያሰማልን ። አምላካችንም እኛን እራሳችንን እንድንሆን እንጂ ሌላውን ብይሉኝታ ከመምስል ይጠብቅን "ብኖር ለእግዚአብሄር ብሞትም ለእግዚአብሔር" ለማለት እንድንችል ፍጣሪ ያብቃን እሱ ለኛ ብዙ ነገር ሆኗልና። ህይውታችን እውንተኛ መንገድ ላይ የምትቆመው እራሳችንን መሆን ስንችል ብቻ ነው መንፍሳዊ ስራ ምስራት መንፈሳዊ አያደርግም መንፈሳዊ መሆን ነዉ መንፈሳዊ የሚያስብለው "በዘመነ ጠ.ሰለሞን ሰይጣናት ተገዝተው ቤ/መቅደሱን ሰርትዋል ታዲያ ምንፍሳዊ ሰራ ሰራ ቢስሩም ስይጣናት መንፈሳዊያን ናቸው ማለት እንችላልን? በፍጹም! በራስ ባልሆነ ነገር ከመምስል በራስ ባመኑበትና ብራስ በሆነ ነገር መሆን ይበልጣል። ፈጣሪ ይርዳን! የድንግል አማላጅነት አይለይን። አርቴፊሻል ህይወት ከኛ ይራቅ።
ReplyDeleteፈጣሪ እግዚአብሄር ቃለ ህይወት ያሰማልን ። አምላካችንም እኛን እራሳችንን እንድንሆን እንጂ ሌላውን ብይሉኝታ ከመምስል ይጠብቅን "ብኖር ለእግዚአብሄር ብሞትም ለእግዚአብሔር" ለማለት እንድንችል ፍጣሪ ያብቃን እሱ ለኛ ብዙ ነገር ሆኗልና። ህይውታችን እውንተኛ መንገድ ላይ የምትቆመው እራሳችንን መሆን ስንችል ብቻ ነው መንፍሳዊ ስራ ምስራት መንፈሳዊ አያደርግም መንፈሳዊ መሆን ነዉ መንፈሳዊ የሚያስብለው "በዘመነ ጠ.ሰለሞን ሰይጣናት ተገዝተው ቤ/መቅደሱን ሰርትዋል ታዲያ ምንፍሳዊ ሰራ ሰራ ቢስሩም ስይጣናት መንፈሳዊያን ናቸው ማለት እንችላልን? በፍጹም! በራስ ባልሆነ ነገር ከመምስል በራስ ባመኑበትና ብራስ በሆነ ነገር መሆን ይበልጣል። ፈጣሪ ይርዳን! የድንግል አማላጅነት አይለይን። አርቴፊሻል ህይወት ከኛ ይራቅ።
ReplyDelete....ቆይ ግን ሰው ስለ ሰው የሚመሰክረው ሲሞት በልቅሶ ዜማ ብቻ ነው እንዴ?››
ReplyDeleteቆይ ግን ሰው ስለ ሰው የሚመሰክረው ሲሞት በልቅሶ ዜማ ብቻ ነው እንዴ?››
ReplyDeleteበአንድ የሕጻናት ማደጊያ ማእከል ውስጥ ያደገ የስፖርት ጋዜጠኛ ገጠመኙን ሲያካፍለን እንዲህ ብሎ ነበር:: ከማእከሉ ሠራተኞች አንድ ሰው ያርፍና ሕጻናቱ በሕብረት ልቅሶ እንዲደርሱ ይደረጋል:: ንፍሮአቸውን ሲቅሙ ቆይተው ድንገት ውጡ ተባለ:: ልጆቹ ሲወጣ ምን እንደሚባል የነገራቸው አልነበረምና የበሉትን ንፍሮ አስበው ለሟች ቤተሰቦች ዓመት ዓመት ያድርስልን! እያሉ ተሰናበቱ::በነርሱ ማን ይፈርዳል? የኛስ ልጆች እንዴት እያደጉ ነው?
ReplyDeleteልጆች ቢያንስ የሁለት ቢበዛ የአራት ነገሮች ውጤት ናቸው:: የወላጆችና የውሎ ሲደመር የማኅበራዊ ተቋማትና/ቤተ እምነቶችን ጨምሮ/ የመንግሥት:: መተንተኑን እናቆየውና ኃላፊነታችንን እንወጣ::
nice example.
Deletekeep it up! i like woge....... nigus chanie from debretabor.
ReplyDeleteKeep up the good work
ReplyDeleteDANI yemr mitchel sew neh....
ReplyDeleteዲ።ን ዳኒ ማስተላለፍ የፈለገው ባለፈው በ መለስ ሞት ምክንያት ህዝቡን በግደታ ኢንድያለቅስ የተገደደበትን ሁነታ ነው። በጣም ኣሪፍ ነው።
ReplyDeleteየመንግስት ካቢኒወች ሂዝቡን ኣስገደደው በጠብመንጃ ኢንባ ኢንድያወጣ ስይደበደብ ነበርና።።።።።።።።ኢግዚኣብሀር ይብርኪ።
አህያ ነህ/ነሽ
DeleteHOW u r stupid!meles was a wise person !!
DeleteRIP to our great leader !
DeleteThis is a VERY BIG LIE. No one was forced to cry without his/her will.If you wanna comment, just do it properly. Don't make this lovely blog a reflection for your stupid, dirty politics.
Delete
DeleteIt's really funny:)and educational. May God bless u
ReplyDelete‹‹እማዬ ምን ነበር ያልሽኝ፤ ስቴፑ ጠፋኝኮ›› አላት፡፡ እናቱ በዓይነ መዓት አየችውና ጩኸቷን ቀጠለች፡፡
ReplyDeleteNice one! I really enjoyed the message and the way it is conveyed. I think the moral of the story is crystal clear. Thank you Dn. Daniel!!!
ReplyDeleteit was so nice fiction
ReplyDeletebetam astemari new 10q dani
ReplyDeleteIt is really interesting keep it up
ReplyDeleteዳኒ በጣም ያምራል፡፡ ግን ማልቀስ ያለብን ለሞተ ነውስ በቁሙ ለሞተ ??
ReplyDeleteit is interesting God bless you dnai
ReplyDeleteit is very interesting and based on facts . God bless you Dan!!!
ReplyDeleteyasikal 10Q demom real new. yhin hulu gin yeminonew lesew new lehlina?
ReplyDeleteእንባ እስኪወጣኝ ድረስ እየሳቅሁ ነው ያነበብኩት ተምሬበትአለሁ፡፡ከፅሁፉ እንደተማርኩት ማስመሰል እንደሌለብን ራሳችን መሆን እንዳለብን ተረድቻሃለሁ፡፡ለቅሶ ላይ ብዙ መጥፎ ባህሎችም ስላሉ መቀረርፍ ያለባቸው ቢቀረፉ መልካም ነው፡፡ከሞትን በኋላ ከመላቀስ በህይዎት ዘመናችን መረዳዳት ብንችል የተሸሻለ ነው፡፡ጥሩ እየሰራን መሆናችን ካወቅን ለሰው ወሬ ጆሮ አንስጠው፡፡
ReplyDeleteInteresting, moving and touching! The moral lesson is incredible. One more thing: if we don't have such a 'lakso' tradition we need psychologists for every move; and most have know depression and we need Prozac and the likes. If not, some of us go to serial anti-social acts in what we see in American schools... the "me generation" is coming through westernization in a form of Americanization. We are in a crisis, system failure, and dysfunctional process of taking 'civilization' wrongly.
ReplyDeletezemenih yibarek ! ahunim tsegaw yibzalik !
ReplyDeletebetam salaleks ykerhut alkshu alkshe alaw
ReplyDeleteጥሩ ትምህርት ነው የሰጠሀህነን ሰው በህይወት ባለ ጊዜ ሳይረዳዳ ሲሞቱ ማልቀስ ትርጎም የለውም
ReplyDeleteInteresting!
ReplyDeleteሰው በህይወት ባለ ጊዜ ሳይረዳዳ ሲሞቱ ማልቀስ ትርጎም የለውም
ReplyDeleteሰው በህይወት ባለ ጊዜ ሳይረዳዳ ሲሞቱ ማልቀስ ትርጎም የለውም
ReplyDeleteit is really funny and transmit a strong message
ReplyDeleteewnetegna neger new. sew and neger kelibu kalhone mechereshiaw ayamrim!!! E/R yistelen letsafew sew.
ReplyDeleteDn. Daniel thank you so much! But who do you think right and have sympathy. I was reading alone! I was laughing all through the conversation of the mom and here kid. But all the time the kid reacted I was being hit by a pain. You reminded me so many events in my life. Yes, for me the kid was right. He also did the same truth at end. In reality people who deeply mourn usually may not have any voice, they may shed tears! Or may not at all! The pain goes deep internal and accordingly their tears may also flow in! He is right those who shout and fall are most the time are actors! Who cares about what people might say. I say the title would have been more sound if it had rather been 'Ye asteway lij leqiso' instead of 'Yezenach lij leqiso'. Sadness is from heart of hearts which for some remain to be life time but these kind of people might not have any voice at the day they departed the one the love most! Here below is one of my piece just to reflect one of my experience in my life.
ReplyDeleteለመውደድም ገደብ ይኑረው!
መለየት ግድ ሆኖ እውነት የሆነ ዕለጠ፣
ሐዘን እንዳይሰብርህ እንዳትወድቅ ድንገት፣
ከሰዎች ተጋርተህ የምትኖረው ሕይወት፣
በመጠኑ ይሁን ገደብ አብጅለት፡፡
ይህን ሳታስተውል ክፉንም ሳታስብ፣
ከሰዎች ተዋደህ ኖረህ ያለገደብ፣
የግድ ያጣህው ዕለት የምትወደውን ሰው፣
ልብህ ይሰበራል ዳግም ላትጠግነው፡፡
ዮ. ሠርፀ ፼፩ ዓ.ም (J. Sertse 2009)
Sorry I see some flaw in piece I posted earlier here is the corrected one
ReplyDeleteለመውደድም ገደብ ይኑረው!
መለየት ግድ ሆኖ እውነት የሆነ ዕለት፣
ሐዘን እንዳይሰብርህ እንዳትወድቅ ድንገት፣
ከሰዎች ተጋርተህ የምትኖረው ሕይወት፣
በመጠኑ ይሁን ገደብ አብጅለት፡፡
ይህን ሳታስተውል ክፉንም ሳታስብ፣
ከሰዎች ተዋደህ ኖረህ ያለገደብ፣
የግድ ያጣህው ዕለት የምትወደውን ሰው፣
ልብህ ይሰበራል ዳግም ላትጠግነው፡፡
ዮ. ሠርፀ ፼፩ ዓ.ም (J. Sertse 2009)
nice
ReplyDelete