Monday, February 18, 2013

አባ ፊልጶስን ፍለጋ(ክፍል አራት)ደብረ ታቦር ኢየሱስ ከሩቅ ሲታይ
click here for pdf 
ወጋችንን ደብረ ታቦር ላይ ነበር ያቆምነው፡፡ ሪቻርድ ፓንክረስት እንደሚነግሩን በአካባቢው ትውፊት መሠረት ደብረ ታቦርን መሠረቷት የሚባሉት የኦሮሞው ተወላጅና በትውልድ ሙስሊም ሆነው በኋላ ክርስትናን የተቀበሉት ራስ ጉግሳ መርሳ ናቸው፡፡ ራስ ጉግሳ 1791-1818 ዓም ድረስ አካባቢውን አስተዳድረዋል፡፡ ራስ ጉግሳ ዋና ከተማ አድርገው መጀመርያ የከተሙት ከጎንደር በስተ ደቡብ ምሥራቅ 60 ኪሎ ሜትር ላይ በሊቦ ነበር፡፡ በኋላ ግን ለተፈጥሯዊ ምሽግ ወደምትስማማው ተራራማ ቦታ ሄደው ከተማቸውን በመቆርቆር ቦታውን ‹ደብረ ታቦር› ብለው ጠሩት፡፡
ራስ ጉግሳ አብዛኛውን ዘመናቸውን ያሳለፉት፣ ብዙዎቹን ሥራ የሠሩትና በኋላም ዐርፈው በ1818 ዓም የተቀበሩት እዚሁ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ነው፡፡ የራስ ጉግሣ ልጅ ኢማም ከአባቱ ቀጥሎ የገዛውና በመጨረሻም በ1821 ዐርፎ የተቀበረው እዚሁ ነው፡፡ ከእርሱ በኋላ ራስ ማርዬ፣ ራስ ዶሪ (እስከ 1824 ገዝተው እዚያው ዐርፈው ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ተቀብረዋል)፣ ራስ ዓሊ ዐሉላ(ታላቁ ራስ ዓሊ) በደብረ ታቦር መንበራቸውን ዘርግተው ገዝተዋል፡፡

እኤአ በ1843 ደብረ ታቦርን የጎበኛት ፈረንሳዊው ዲ አባዲ በከተማዋ ውስጥ በዚያ ጊዜ ከ1600- 1700 የሚጠጉ ቤቶች እንደነበሩ ጽፏል፡፡ የሕዝቡም ብዛት ወደ 10 ሺ ይጠጋ ነበር፡፡ ለሁለት ዐሥርት ዓመታ ያህል ደብረ ታቦር ላይ የከተሙት ራስ ዓሊ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን በመሥራት ይታወቃሉ፡፡ በደቡብ ምሥራቅ እናቲቱ ማርያም፣ በምሥራቅ ልጅቱ ማርያም፣ በሰሜን ጠጉር ሚካኤል የሚጠቀሱላቸው ናቸው፡፡ በጎንደር ታሪክ ውስጥ በትውልድ ሙስሊም የሆኑት የኦሮሞ ሥርወ መንግሥት ታሪክ የሚጠናቀቀው ደብረ ታቦር ላይ ነው፡፡
ዐፄ ቴዎድሮስ በየካቲት 1848 ዓም መንበረ ሥልጣኑን ሲይዙ ደብረ ታቦር አንዷ የመቀመጫ ከተማቸው ነበረች፡፡ በጥር 1849 ዓም የግብጹን ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስን የተቀበሉት እዚሁ ደብረ ታቦር ነበር፡፡ በ1853 ዓም ከወይዘሮ ጥሩ ወርቅ ጋር የተጋቡትም እዚሁ ደብረ ታቦር ነበር፡፡ ቴዎድሮስ የውጭ ሀገር ባለሞያዎችን በመጠቀም ከደብረ ታቦር እስከ አሞራ ገደል፣ በመጨረሻው ዘመናቸውም ከደብረ ታቦር እስከ መቅደላ መንገድ አሠርተው ነበር፡፡ በከተማዋ የሚገኘውን ደብረ ታቦር መድኀኔዓለምን አሠርተዋል፡፡ ይህ ጊዜ የቴዎድሮስ ጠባይ የተቀየረበት በመሆኑ ምዕራብ ጎጃም አዴት የሚገኘውን መድኃኔዓለምን አቃጥለው ሀብቱንና ቅርሱን ለደብረ ታቦር መድኀኔዓለም በመስጠታቸው
እንግዲህ ለታቦት አልሰጥም ስለት
አዴት መድኃኔዓለም ነዶ አገኘሁት
ብላ አንዲት ሴት ገጥማለች ይባላል፤፤
ዐፄ ቴዎድሮስ ሴፓስቶፖል መድፋቸውንም ያሠሩት በደብረታቦር ከከተማው አጠገብ በሚገኘው ሰላምጌ በተባለው ቦታ ነው፡፡
እጅግ የሚያሳዝነውም ዐፄ ቴዎድሮስ ከተማዋና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅቀው ወደ መቅደላ ሲጓዙ ወታደሮቻቸው መስከረም 30 ቀን ከተማዋን አቃጠሏት፡፡

በስማዳ መንገድ የሚገኙ ቋጥኞች
ደብረ ታቦር የዐፄ ዮሐንስ አራተኛም ከተማ ነበረች፡፡ ነገር ግን የቀድሞ ነገሥታት የነበሩበትን አካባቢ ትተው ‹ሠመራ- መረጣት› በተባለው አካባቢ አዲስ ከተማ ቆረቆሩ፡፡
ዐፄ ዮሐንስ ራስ አዳልን ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ብለው በጥር 1873 ዓም በጎጃም ላይ ያነገሡዋቸው ደብረ ታቦር ላይ ነበር፡፡ አቡነ ጴጥሮስ፣ አቡነ ሉቃስና አቡነ ማርቆስ የተባሉት ግብጻውያን አባቶች በደብረ ታቦር ተቀምጠው ነበር፡፡ እንዲያውም አቡነ ማርቆስ ዐርፈው በ1874 ዓም የተቀበሩት እዚያው ነው፡፡ ስለ ከተማዋ አስደናቂ ታሪክ ልቡ ይበልጥ ለማወቅ የፈለገ ቢኖር የሪቻርድ ፓንክረስትን The History of Däbrä Tabor (Ethiopia): Bulletin of the School of Oriental and African Studies, University of London, Vol. 40,No. 2 (1977), pp. 235-266) ቢያነብ ይበጀዋል፡፡
አሁን ከተማዋን እንልቀቅና ወደ ስማዳ እናምራ፡፡ መንገዱ ወደ ስማዳ እስኪገነጠል ድረስ አስፓልት ነው፡፡ ወደ ስማዳ ከተገነጠለ በኋላ ግን ‹ማሩኝ› የሚያሰኝ ኮረኮንጅ ነው፡፡ ደግነቱ በመንገድ ላይ ብዙ የሚታይ ነገር አለው፡፡ የዝማሬ መዋሥዕቱን ማስመስከሪያ ዙር አምባን በሩቁ ትሳለማላችሁ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከዐፄ ገብረ መስቀልና ከአቡነ አረጋዊ ጋር ወደ ቦታው መጣ፡፤ ቦታውን ወደዱት ነገር ግን የመውጫው ነገር ቸገራቸው፡፡ ያን ጊዜ መልአከ እግዚአብሔር ‹አባ ሆይ ዙርና ወደ ተራራ ውጣ› ስላላቸው ቦታው ‹ዙር አባ› መባሉን የአካባቢው ትውፊት ይናገራል፡፡ እልፍ ስትሉ ደግሞ ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ እድሜ ያለው የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንደ ዙር አምባው ሁሉ ተራራ ላይ ከነ ሙሉ ግርማ ሞገሡ ይታያችኋል፡፡

የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን
በመንገድ ላይ ተፈጥሮን እንድታደንቁ የሚያደርጓችሁ የቋጥኝ ተራሮች አትለፉኝ አትለፉኝ ይላሉ፡፡ ስማዳ የጤፍ ሀገር ነው፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባና በአካባቢው የተወደደው የአድአ በርጋ ነጭ ማኛ ጤፍ መነሻው ስማዳ ነው፡፡ ዐፄ ምኒሊክ ለቤተ መንግሥታቸው የሚሆን ነጭ ጤፍ ቢያጡ ከስማዳ አስመጥተው በአድአ በርጋ ስለዘሩት ይኼው ጤፉም ለምዶ ቀረ፡፡ የስማዳ ጥንታዊው ታዋቂ ማኛ ጤፍ ‹ስይት› ጤፍ ይባላል፡፡ ችግሩ በአንድ ቦታ የሚበቅለው መጠን አነስተኛ በመሆኑ ለቅንጦት እንጂ ለአዘቦት አይሆንም አሉ፡፡

መሪጌታ ሐረገ ወይን
በመንገዳችን ላይ በላይ ጋይንት ወረዳ ውስጥ የምትገኘውን ወለላ ባሕር ከተማን እናገኛታለን፡፡ እዚያ ደግሞ የታወቁት ሊቅ መሪጌታ ሐረገ ወይን ይገኛሉ፡፡ መሪጌታ ሐረገ ወይን እግዚአብሔር ጸጋ የሰጣቸው የታሪክ ሊቅ ናቸው፡፡ ከመቄት በታች ያለውን ሀገር በተመለከተ የማያውቁት ነገር የለም፡፡ የእያንዳንዱን ጎጥ ታሪክ ያውቁታል፡፡ እጅግ የሚገርመው ደግሞ ታሪኩን እንዳይረሱት በደብተር ላይ ጊዜ ሲያገኙ ይጽፉታል፡፡ 

ዕድሜ ጠገቧ የመሪጌታ ሐረገ ወይን ደብተር
እርሳቸው እንደነገሩን ከሆነ አካባቢውን ከግራኝ ጥፋት በኋላ ያቀኑት በፄ ሠርጸ ድንግል ዘመን ወደ አካባቢው የመጡ አራት ቅዱሳን ናቸው፡፡ ዐፄ ሠርጸ ድንግል ወደ ጎንደር ሲሻገሩ አራት ሊቃውንትን አመጡን አአራት ቦታ መደቧቸው፡፡ አባ መሰንቆ ድንግል(ለቤተልሔም)፣ አባ ለባዌ ክርስቶስ(ለዙር አምባ)፣ አባ ብእሴ እግዚአብሔር (ለገርባ ማርያም)ና አባ ተክለ ወልድ(ለደብረ ማርያም)፡፡ በሌላ ታሪክ ላይ እነዚህ አባቶች የመጡት ከጉራጌ ምሁር ኢየሱስ መሆኑን ይገልጣል፡፡ 
መሪጌታ ሐረገ ወይንን ስለ አቡነ ፊልጶስ ስለ ጌርጌስና ደብረ ሐቃሊትም ጠየቅናቸው፡፡ እርሳቸው የማያውቁት ነገር የለምና፡፡ ‹ወገዳን አልፋችሁ ሂዱ ሁሉንም እዚያ ታገኙታላችሁ› አሉን፡፡ እኛም መስቀላቸውን ተሳልመን ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ የስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ ስንደርስ እኩለ ቀን ነበር፡፡ እኔና ሙሉ ቀን ወደ ወረዳው ቤተ ክህነት አመራን፡፡ የወረዳው ሊቀ ካህናት በደስታ ነው የተቀበሉን፡፡ ደብዳቤያችንን ተመልከተው እርሳቸው የወረዳውን መስተዳድር ለማነጋገር ሄዱ፡፡
ከወረዳው መስተዳድር አብረውን የሚጓዙ ሁለት ፖሊሶችን ማስፈቀዳቸውንና ነገ በጠዋት ብንነሣ የተሻለ መሆኑን አስታወቁን፡፡ እኛም ለረዥም መንገድ ስለተጓዝን ማረፉን ወደድነው፡፡ በከተማው የተሻለ ነው የተባለው ሆቴል ውስጥ ሃያ ብር ከፍለን አደርን፡፡ ከተማዋ በጸጥታ የተሞላች ናት፡፡ ከእኛ ሆቴል ጀርባ ግን አንድ ጅብ የሚያህል ማይክራፎን ተከፍቶ አገሩን ያተራምሰዋል፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት በሁለት የእንግሊዝ የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚካሄደውን እግር ኳስ እያስተዋወቀ ነው፡፡ ቦታ ሳይሞላባችሁ ግቡ ይላል፡፡ ቤቱ የኳስ ማሳያ ቤት መሆኑ ነው፡፡ ወደ አምስት ሰዓት ላይ እርሱም ጸጥ አለ፡፡ እኛም ተኛን፡፡

የሌሊት ጉዞ
ከሌሊቱ ዐሥር ሰዓት ተነሣን፡፡ የወረዳው ሊቀ ካህነት ከአንድ ሌላ አባት ጋር ቀድመው ደርሰዋል፡፡ አንደኛው የፖሊስ አባልም መጥቷል፡፡ አንደኛው ግን አልመጣም፡፡ በሞባይል ስልኩ ሲደወል ዝግ ነው ይላል፡፡ ለሠላሳ ደቂቃ ያህል ጠበቅነው፡፡ ምንም ነገር ስለ እርሱ ማወቅ አልቻልንም፡፡ በመጨረሻ አንደኛውን ፖሊስ ብቻ ይዘን በፒክ አፕ መኪናችን ጉዞ ጀመርን፡፡ የወገዳን ከተማ ለቅቀን አሥር ኪሎ ሜትር ያህል እንደሄድን መኪናዋ ማቃሰት ጀመረች፡፡ 


ፀሐይ በስማዳ ተራሮች ብቅ ስትል
መንገዱ ድንጋዮች ወጣ ወጣ ብለው የተቀመጡበት እንጂ መንገድ ሆኖ የተሠራ አይመስልም፡፡ ከጎማዋ ቁመት የማይተናነስ ድንጋይ መሐል ላይ ቁጭ ብሎ ‹እስኪ የምታደርጉትን አያለሁ› ይላል፡፡ ከዚያ በላይ ደግሞ መንገዱ ተራራማ ነው፡፡ 

ውጭ- አልወጣም
ድንበሩ ሂጅ ይላል መኪናዋ ‹እንዴት አድርጌ› ትላለች፡፡ እኛ እንጨነቃለን፡፡ በዚህ መሐል የቀረው ፖሊስ ደወለ፡፡ ‹በእግሬ እየመጣሁ ነው ጠብቁኝ› አለ፡፡ ‹ባትልስ የት ይደረሳል› እያልን፣ መኪናችንንም እየገፋን ጠበቅነው፡፡ እውነትም ቆፍጣና ፖሊስ ነው ሮጦ ደረሰብን፡፡ እንደደረሰ ‹እንዴት ይቺን መኪና ይዛችሁ ትመጣላችሁ› ብሎ ሊውጠን ደረሰ፡፡ ‹ዕራቁቱን ለተወለደ ልጅ ደበሎ መቼ አነሰው› አለ የሀገሬ ሰው፡፡

ሂጂ- አልሄድም
መኪናዋ ስንገፋት፣ ስትገፋን ጥቂት ከሄደች በኋላ ‹ከዚህ በላይ በምንም ዓይነት አልንቀሳቀስም› አለች፡፡ ብንገፋት፣ ብንጎረጉራት ወይ ፍንክች፡፡ ሁላችንም በየድንጋያችን ተቀመጥን፡፡ ምን እናድርግ? እንሂድ ወይስ እንቅር? ያንን ሁሉ ለፍተን ጫፍ ላይ ስንደርስ ልንሸነፍ ? ምንስ አማራጭ አለን ?
 (ይቀጥላል)

52 comments:

 1. አማራጭ አላችሁ፤ ቀጥሉ፤ እግዚአብሔር ከእናነተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 2. Diakon Daniel Good Job! God bless You. I am really very interesting to read more history like this. thank you.

  ReplyDelete
 3. በጉዟችሁ መጨረሳ ምን ያጋጥማችሁ ይሆን? እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን::

  ReplyDelete
 4. አይዟችሁ፤አላማችሁ ጉዟችሁ ለታሪክ ለአገር ለወገን የሚጠቅም ነውና በርቱ።ቀጥሉ ወደ ፊት።የአባ ፊልጾስ አምላክ ይርዳችሁ።

  ReplyDelete
 5. Let me correct you D.Daniel. I am fro Debretabor. Debretabor was founded not by Rasgugsa but by Atse Seife Yared. This mistake should not have come from a person like you. who is expected to know history. better to write about Yaredic Lyrics and the history of st.Yared. Gondar is the only place in ethiopian orthodox church history that kept the legacy of st.yared and tewaney. do not forget this. you can write about st.yared history.

  ReplyDelete
 6. ............‹ወገዳን አልፋችሁ ሂዱ ሁሉንም እዚያ ታገኙታላችሁ›.........Oh Geta hoyi....Antes wedet nehe!!!..........Enezihin wendimochachinen yerdachew!!!Amen!!!

  ReplyDelete
 7. go Dani go never give up! not for you, let not Satan do hear you.

  ReplyDelete
 8. ዲ/ን ዳኔኤል የኢትዮጲያ ከተሞች የታሪክ አባት !!!
  በርታ በርታ በርታ

  ReplyDelete
 9. Hay Dani! the problem is from the driver, please change it, The car will move with out any problem...................where is Elias?

  ReplyDelete
 10. አማራጭ አላችሁ እንጅ፤ ቀጥሉ፤ ደርሳችኋል፤ ቦታው እሷን እልፍ እንዳላችሁ ያለው ነው፤እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 11. Debre Tabor city is flourished 3 centuries before Gondar, i.e, in the 14th century. The time you specified is wrong! It is better to review another source. You could have full information had you asked the concerned public offices there. You better revise this article.

  ReplyDelete
 12. ተረባርበንም ገፍተናትም ቢሆን ዛሬ ካሰብነው በደረሰን ነበር ግን የእሱ ፈቃድ ሆነና መኪና በመግፋት ቀጥ ልንል ግድ ሆነ በእናትህ ሹፌሩ የምትችለውን ሁሉ አድርግና በአምስተኛው ክፍል መንገዱን ጨርሰው የሆነው ሁሉ ይሁናና ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለን ብቻ እንዳይነጋ ማን ያውቃል እደጅ አድራለሁ ኮከብ ስቆጥር ብለን ጥሩ በረከትና ትዝታ ልናተርፍ ይሆናል ያስጀመረን የሚያስጨርስ ይርዳን አሜን

  ReplyDelete
 13. ኧረ ዳኒ ልብ ማንጠልጠሉን አበዛኸው እኮ፣ ስማዳ ደርሶ መመለስ የለም፡፡ በእግር በእግር ቀጥሉ ..... በሉ ቶሎ ቶሎ ሂዱና ደርሳችሁ ንገሩን፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 14. Daaannnnnnnnnnnnnnnniiiiiiiiiii. Ahuns Yhe Yqetlal Selechegn. May be I'm gonna Hate u 4 the first time. I love u Anyway.

  ReplyDelete
 15. ዲ. ዳንኤል ክብረት
  ጉዞህ እጅግ ደስ ይላል፡፡ አስተማሪነቱም አያጠያይቅም፡፡ በእርግጠኛነት የአባታችንን የመቃብር ቦታም እንደምታገኙት አምናለሁ፡፡
  ነገር ግን በዛሬው ጽሁፍ ላይ አንዳንድ አስተያየት አለኝ፡፡……………………..
  ስለ ደብረታቦር ከተማ ታሪክ በጻፍከው ላይ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ከ670 አመት በላይ ታሪክ ያላት ከተማ ናት እንጅ አንተ እንዳቀረብከው የ200 እና የ300 አመት ብቻ አይደለም፡፡ ራስ ጉግሳ አደሷት እንጅ አለመሰረቷትም፡፡ ለዚህም ማስረጃዎች አሉ፤
  በ1300 ወቹ
  አጼ ሰይፈ አርድ (1344-1372) በደብረታቦር ተራራ (እየሱስ ተራራ) ላይ የእየሱስ ቤክርስቲያንን መሰረቱ ። ይህ ቤ/ክርስቲያን አሁን ድረስ ከዚያ ዘመን የመነጩ ቅርጻቅርጾች ሲኖሩት ነገር ግን በ18ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ራስ ጉግሳ ሙርሳ በቤተክርስቲያኑ አጠቃላይ ለውጥ አድርገዋል። ስለሆነም በቤ/ክርስቲያኑ የሚገኙ ስዕሎች ባብዛኛው ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ዋዜማ የሚመነጩ ናቸው።
  በ1500 ወቹ
  የደብረታቦር ስም በአጼ ልብነ ድንግል ዜና መዋዕል ላይ ሰፈረ።
  በ1700 ወቹ
  በ1700ወቹ መጨረሻ አካባቢ አሊ ጓንጉል (ትልቁ አሊ) የተባለ የየጁ ስርወ መንግስት መሪ በደብረ ታቦር አካባቢ ሃይለኛ መሪ በመሆን ከሱ በኋላ ለ80 ዓመታት ያክል የጸና ስርዓት በአካባቢው እንዳንሰራፋ ባህሩ ዘውዴ መዝግቧል እንደ ታሪክ አጥኝው ሞርድካይ አብር አስተያየት የደብረታቦርን ከተማ የመሰረታት ይሄው ትልቁ አሊ ነበር። እንደ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክኸርስት ግን ራስ ጉግሳ ሙርሳ ነበር።
  ስለዚህ የሪቻርድ ፓንክረስትን ብቻ ዋቢ ማድረግ በቂ ነው ብየ አላስብም፡፡ ደግሞ በእርግጠኛነት መድሀኒያለም አቡነ እንድሪያስን ጠይቀሀቸው ቢሆን ኖሮ በደንብ ይገልጹልህ ነበር፡፡
  2. አጼ ቴዎድሮስ መድፍ ያሰሩበት ቦታ ሰላምጌ ሳይሆን ጋፋት ነው፡፡ ጋፋትም ወደ ሰላምኮ ጊዎርጊስ አጠገብ ቢሆንም ምንአልባት የፊደል ግድፈት ካልሆነ ሰላምጌ የሚባል ቦታ በአካባቢው ያለ አይመስለኝ፡፡
  በተረፈ ግን እግዚአብሄር አገልግሎትህ ይባርክ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዴ እናንተ ሰዎች ምን ነካችሁ፡፡ ከተማን መመሥረትና በዚያ አካባቢ ቤተ ክርስቲያን መትከል ወይም አንዳች ነገር ማድረግ ይለያያሉ፡፡ ለምሳሌ የአዲስ አበባን ከተማ የቆረቆሯት ዐፄ ምኒሊክና እቴጌ ጣይቱ ናቸው፡፡ በአካባቢው ግን ከዐፄ ዳዊት ጀምሮ በተለይ እንጦጦ ላይ ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ ንጉሥ ሣሕለ ሥላሴም ቀራንዮ መድኃኜዓለምን የተከሉት ከተማዋ ከመቆርቆሯ ቢያንስ 200 ዓመት በፊት ነው፡፡ እነዚህ ግን አዲስ አበባን ቆረቆሩ አይባልም፡፡ ዳንኤል ሪቻርድ ፓንክረስትን ጠቅሶ የነገረን የከተማዋን ታሪክ ነው፡፡ ያውም ከነምንጩ አስቀምጧል፡፤ የተለየ ታክና የተሻለ ምንጭ አለኝ ያለ ጽፎ ያምጣና ያስነብበን፡፡
   ዓይናለም ከስድስት ኪሎ

   Delete
  2. dear Aynalem, I appreciate your argument, but Debre Tabor has been long history. before the discovery of America there were three known cities in Africa, they were Tumbuktu in MALI, Harar and Debre Tbor in Ethiopia. i will attach you the full history of Debre Tabor if i got your email. Daniel him self will make correction for sure. Daniel has to refer other historical books, or ask elderly people. I know Pope Endrias of the south Gondar is very professional man. the pope may tell him to make corrections. it is not simple opposition but it is basic man!! stay blessed!!
   Muluken Tesfaw
   Bahir Dar

   Delete
  3. endezia kehone ras gugsa mursa debretabor keteman alkorekorum:: esachew yaregut yeeyesus betekristianin mades bicha new:: ketemawun beahunu melk korekoru libal emigeba atse tewodros nachew:: gin yihem ayawatam mknyatum kesachew behuwala ketemawu tekatluwal:: atse minilik nachew malet new ketemawan yekorekoru mknyatum kesachew behuwala yalew ketema new eskahun yezelekew:: kezih hulu tsegur sinteka, yeatse seyfe aridin mesrachinet lemeserez lemn asfelege?

   Delete
  4. @ዓይናለም ...ባህሩ ዘውዴ እና የአጼ ልብነ ድንግል ዜና መዋዕል ብሎ ጠቅሷል እኮ አላነበብከውም እንዴ፡፡

   Delete
  5. To anonymous Feb. 19
   The above guy has already posted the source. But what is needed is why that difference comes. I believe Pankhurst had saw the above mentioned source, why he says differently on his article needs extra elaboration.

   Delete
 16. Please let us to read your articles by posting in Pdf format.

  Thanks
  Getaneh and freinds

  ReplyDelete
 17. ዳኒ በጣም መሳጭ ታሪክ ነው

  አይ አበሳችሁ መኪናዋ አልሄድም ካለች አንዱ አማራጭ በእንሰሳ ጀርባ ካልሆነም በእግር መጀመር ነዋ

  ይህንን ለማወቅ ጓጉቻለሁኝ

  ከበደ

  ReplyDelete
 18. dani amlake yerdahe ketayou ayzegaye

  ReplyDelete
 19. God will be with you, don't give up!!!!

  ReplyDelete
 20. Thank dani....Yekenahe

  ReplyDelete
 21. ድንበሩ ምን ነካው? መኪናን እንደ አሻንጉሊት የሚጫወትበት ሰው የስማዳ መንገድ ያሸንፈዋል፡፡ የደንገጎን ዙርያ ጥምጥም እንዲያ መኪናውን ሁሉ ሲጫወትበት ይህችን ተራራ ብሎ አቃተኝ ይላል፡፡ ኤልያስ አለ አይደል እንዴ ለምን አያግዘውም፡፡ ድንበሩ ይህችን ተራራ መውጣት ካቃተህማ ድሬዳዋ አትገባትም፡፡
  ሰላሙ፣ ከነምበር ዋን

  ReplyDelete
 22. For a person like me who has fresh memory of D/T and Simada, the story is more exciting. Longing to read the next part...
  Many thanx,

  ReplyDelete
 23. Yach yedrowa yemerigeta debter min mistir endeyazech betnegren noro!

  ReplyDelete
 24. ሰላሙ፣የነምበር ዋን
  KKKKKK
  menew DENGEGON FERTEH NEW

  ReplyDelete
 25. Thank You! Deacon Daniel.
  Sorry to read that you guys are not be to use a car but it is okay, don't give up! you will get it. I am not trying to tell you what to do. I have so much respect for you but I just want to give guys a little boost remember how our father went to that place. ... "አቡነ ሰላማ አባ ፊልጶስን በአልጋ ላይ አድርጎ በሸክም ወደ ደብረ ሐቃሊት ወሰደው፡፡"....you guys can do it.
  may God bless you!

  ReplyDelete
 26. በእግርስ ይነኩት ነበር፡፡

  ግን መኪናዋን ማን ሲጠብቅ ይከርማል? ወይስ ሹፌሩን ልታስቀሩት? ወይስ በአካባቢው ሌባ አይኖርም?

  መጨረሻቸው ናፈቀኝ!

  ReplyDelete
 27. Zafina terrara amaregn

  ReplyDelete
 28. a very interesting article ... I hope Dn Dani will respond to the controversy raised in relation to the history of Debre tabor. Dani, you can get more and more historical and religious things to share for us if you spend few days in Debre tabor.

  ReplyDelete
 29. እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን::

  ReplyDelete
 30. ዳኔ ከወንዝ ማዶ ብሆንም ፣ ድካማቾሁን በተመለከተ በዓይነ ህልናየ ጰሑፍሕን አንብቤ እስከም ጨርስ እናንተው ጋ ነበርኩ። ከድካማችሁ ባሻገር ድርጌቱ ለአገረ ለቤተክርስቴያን እንዲሁም ለዜጋ በጣም ያኮራል። የድንግል ልጅ ይከተላችሁ ፣ ቀጣዩን በጉጉት አንጠብቃለን።

  ReplyDelete
 31. Bertu D/n Egzihaber Kenate Gar new

  ReplyDelete
 32. ዳንኤል እንደምን አደርክ

  ቶሎ ጨርስልን ታሪኩን በጣም ነው ልብ የሚሰቅለው

  አብሬህ እንደሄድኩ ቁጠረው መኪናዋ ስትቆም ስጨነቅ


  ወለተ ሚካኤል

  ReplyDelete
 33. Danii Mecchershawin Lemawek Libe Betam Chikul Biloal Ye Abatachin Ye Aba Filipos AMILAK Yerdachihu Berketachew Be Hulachin Yederbin Qale Hiwoten Yasemalin Amennnn

  ReplyDelete
 34. Oh Daniel it is very exciting really crucial history. Thank you very much.
  I am sure you will get halakit!!!
  Muluken ,It was my expectation as you can perform such kinds of interesting job!!! Go a head !!!
  Desalegn AAu

  ReplyDelete
 35. Belaynew A.
  እያደረግኸው ያለኸው ነገር በጣም አስደሳችና ትልቅ ሥራ ነው፡፡ ደግሞ እንደ ልበ-ወለድ ልብ አንጠልጣይ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍህ አንዳንድ ስህተቶችን አስተውያለሁ፡፡
  የመጀመሪያው የደብረ ታቦር ከተማ የተመሠረተችበት ጊዜ ነው፡፡ ደብረታቦር የተመሠረተችው በ 14ኛው ክ/ዘመን ነው፡፡ በመቀጠልም ታላቁ ራስ ዓሊ ብለህ የገለጽከው በዘመነ መሣፍንት መጀመሪያ ላይ የኖረና ለዘመነ መሣፍንት መጀመር ትልቁን አስተዋጽኦ የፈጠረው ነው፡፡ አንተ ግን ለማለት የፈለግኸው (እኔ እንደሚመስለኝ) ትንሹ ራስ ዓሊ፣ የራስ ጉግሳ የልጅ ልጅ፣ የራስ አሉላ ልጅ ነው፡፡ ራስ ዓሊ ከ1823 እስከ 1845 ዓ.ም፣ አይሻል ላይ በደጃች ካሳ (በኋላ ዐጼ ቴዎድሮስ) እስከተሸነፈበት ጊዜ ድረስ ገዝቷል፡፡ መቀመጫውም የደብረ ታቦር ከተማ ነበረች፡፡
  ራስ ኢማም ብለህ የጠቀስካቸውም ትክክለኛ መጠሪያቸው ራስ ይማም ነው (ምናልባት የትየባ ግድፈት ይሆን?)፡፡

  ReplyDelete
 36. Egziabhier amlak mechereshawn yasamrlachihu amen!

  ReplyDelete
 37. ዲ.ዳንኤል ስለ ደ/ታቦር የጻፍከውን አንብቤ አዘንኩ፡፡ ታሪክን አታዛባ፡፡ ደ/ታቦር በዐጼ ሠይፈ አርዕድ በ14 ክ/ዘመን ነው የተቆረቆረችው፡፡ ንጉሡ የታቦር ተራራን ተመልክተው ይህስ የኢየሩሳሌሙን ታቦር ይመስላል በማለት የደ/ታቦርን በተ ክርስቲያን ተክለው ከተማዋንም ከመጀመርያ ስሟ ከጁራ ወደ ደ/ታቦር ለወጠውታል፡፡ ያን ያክል ተጉዘህ እንዴት እና ለምን የደ/ታቦር ኢየሱስን ቤተ ክርስቲያን ሳትሳለም እንደሄድክ እንጃ….. በተረፈ እንደዚህ አይነት ጉዞዎችን ስታስብ በብሎግህ ላይ እንዲህ አይነት ታሪክን የምታውቁ፣ቦታው ያለበትን ልትጠቁሙን የምትችሉ ብለህ ፣…… ብትገልጽ በወሎ በትግራይ ያደረከው ልፋት ይቀንስልህ ነበር፡፡ ምክያቱም አንተ ቦታው የት ነው እያልኩ የኳተትክበትን በዛ አካባቢ የመጣን ሰዎች ስለምናውቀው ጠቁመንህ ያለ እንግልት ከቦታው ትደርስና ጥነታትህን ታከናውን ነበር፡፡ ከደ/ታቦር

  ReplyDelete
 38. daniel mennew mekinawa koma kerech weyes enante dekemachehu ?????
  EYETEBEKEN NEW

  ReplyDelete
 39. እናቴን ነው ያስታወሰኝ እና ውስጤ ነክቶታል that is impressive history...

  ReplyDelete
 40. ከላይ ያለው "ደብረታቦር ኢየሱስ በሩቅ ሲታይ "የሚለው ፎቶው የሚያሳየው ደብረታቦር መድኃኔዓለምን ነው::ይስተካከል::

  ReplyDelete
 41. This an interesting work. Know God is with you. you are the end of your finding. Go ahead till the final thing you desire. God bless your work!!!

  ReplyDelete
 42. Diakon Daniel Egziabher edmena tena yesteh

  ReplyDelete
 43. Diakon daniel Egziabehe Edme yesteh

  ReplyDelete
 44. Egziabeher Yebarkeh

  ReplyDelete