click here for pdf
(ክፍል አንድ)
ይህንን ጽሑፍ እጽፍ ዘንድ ያነሣሣኝ መምህሬ ነው፡፡ የዛሬ ሳምንት አካባቢ በክፍላችን
ውስጥ አንድ ውይይት ነበር፡፡ የውይይቱ ጉዳይ ‹‹ሀገርን መውደድ በምን ይገለጣል?›› የሚል ነበር፡፡ በዚህ ውይይት ጊዜ እኔ
ደጋግሜ ሀገሬን ‹‹አባት ሀገር›› እያልኩ ስጠራ መምህራችንና ተማሪዎቹ ግራ ገባቸውና ‹‹ሀገር በእናት እንጂ በአባት
አትመሰልም›› አሉኝ፡፡ እኔም ‹ለምን?› የሚል ጥያቄ አነሣሁ፡፡ ተማሪዎቹም ‹‹ሀገር እንደ እናት ናት፡፡ ትመግባለች፣
ታሳድጋለች፤ ቸር ናት፤ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንደሆነው ሁሉ የሀገርም ሆድ ዥንጉርጉር ነው፤ እናት አዛኝ እንደሆነችው ሁሉ
ሀገርም ታዝናለች፤ ሀገርን መውደድ ያለብን ልክ እናትን በምንወድበት መጠን መሆን ስላለበት ሀገር በእናት ነው የምትመሰለው››
ሲሉ አብራሩልኝ፡፡
እኔ ደግሞ ‹‹ሀገር በእናት መጠራቷ ትክክል ነው፡፡ ግን ይህ ማለት ሀገርን በአባት
እንዳትጠራ አያደርጋትም፡፡ ‹እናት ሀገር› ማለት እንደሚቻለው ሁሉ ‹አባት ሀገር› ማለትም ይቻላል፤ እንደ እናትም ሁሉ አባትም
ይመግባል፤ ያሳድጋል፤ እንደ እናትም ሁሉ አባትም ቸር ነው፤ የእናት ሆድ ብቻ አይደለምኮ ዥንጉርጉር፣ የአባትም አብራክ
ዥንጉርጉር ነው፡፡ ወንድ ሁሉ ጨካኝ፣ ሴት ሁሉ ርኅሩኅ ነው ያለ ማነው›› ብዬ ተከራከርኩ፡፡ በመጨረሻም ‹ከእናት ፍቅርና
ከአባት ፍቅር የቱ ይበልጣል?› የሚል ክርክር ተነሣ፡፡ እኔ ‹የአባቴ ፍቅር ይበልጥብኛል› ብዬ ተከራከርኩ፡፡ አብዛኞቹ
ተማሪዎች፣ ኧረ እንዲያውም ሁሉም ማለት ይቻላል ‹የእናት ፍቅር ይበልጣል› ብለው ተከራከሩኝ፡፡
ያን ጊዜ ነው መምህራችን ‹ለምን የአባቴ ፍቅር ይበልጥብኛል እንዳልኩ ጽፌ እንድመጣ
ያዘዘኝ፡፡ እነሆ በታዘዝኩት መሠረት፡፡
ለቤታችን ያለነው ልጆች እኔና ታናሹ ወንድሜ ነን፡፡ እኔ የአምስት ወንድሜ ደግሞ
የሁለት ዓመት ልጅ እያለን እናቴ ሦስተኛውን ልጅ ለመውለድ ወደ ሆስፒታል ገባች፡፡ እናቴ ግን ሕይወት ልትሰጥ ገብታ ሕይወት
አጥታ ነበር የተመለሰችው፡፡ የነበረውን ነገር በትንሷ ጭንቅላቴ አስታውሳለሁ፡፡ እኔና ወንድሜ አክስታችን ቤት ነበርን፡፡ ብዙ
ጊዜ አክስታችን ቤት እንውላለን እንጂ አናመሽም፡፡ ያን ቀን ግን መሸ፡፡ ሞግዚታችን ዓይኗ እስኪቀላ ታለቅሳለች፡፡ ለምን
እንደሆነ ግን አልገባኝም ነበር፡፡ እኔን ያስጨነቀኝ ለምን በጊዜ ወደ ቤታችን እንደማንገባ ነው፡፡ በተለይም የእናቴ የመውለጃዋ
ጊዜ ሲደርስ ቤት መዋል ስለጀመረች እርሷ ጋር መጨዋትና እርሷ የሠራችውን ምግብ መብላት ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ለዚህ ነበር ወደ
ቤት እንሂድ ብዬ የጓጓሁት፡፡
ያን ቀን ግን ማምሸት ብቻ ሳይሆን አደርን፡፡ አክስታችን አልመጣችም፡፡ የአክስቴ
ልጆች ዕንቅልፋቸው እየመጣ ሲተኙ እኔ ግን ዕንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም ነበር፡፡ ትንሷ ልቤ ድው ድው ትላለች፡፡ የሆነ ነገር
ቅር ቅር ይለኛል፡፡ እንዲሁ ደርሶ አልቅሽ አልቅሽ ይለኛል፡፡ ቢጨንቀኝ ከሞግዚታችን ጋር አብሬ አለቀስኩ፡፡
የእናቴን መሞት የሰማሁት በማግሥቱ ነበር፡፡ አክስታችን ጥቁር ልብስ ለብሳ ወደ ቤት
መጣችና አኔን ወደ ሳሎን አስጠራችኝ፡፡ ከዚያም በጣም እንደምትወደኝ፤ ከልጆቿ ነጥላ እንደማታየኝ፤ አንዳንድ ጊዜም ልጆች
ወላጆቻቸውን በሞት ሊያጡ እንደሚችሉ ነገረችኝ፡፡ በግማሽ ልቤ ነበር የምሰማት፡፡ በመጨረሻም እናቴ ስልወልድ መሞቷን
ነገረችኝ፡፡ አዞረኝና ወደቅኩ፡፡ የማስታውሰው እዚህ ድረስ ብቻ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ትዝ የሚለኝ ነገር ሆስፒታል አልጋ ላይ
መሆኔን ብቻ ነው፡፡ ስነቃ መጀመርያ ዓይኔ ያየው አባቴን ነበር፡፡
አባቴ ተቀይሯል፡፡ ጠቁሯል፤ ከስቷል፤ ዓይኖቹ ዋሻ ውስጥ እንደሚበራ ብርሃን ከጉድጓድ
ውስጥ ነበር የሚታዩኝ፤ ይንቀጠቀጣል፡፡ የሸሚዙ አንገት ጥቀርሻ መስሏል፡፡ ይህንን ሳይ እናቴ እውነትም ሞታለች አልኩ፡፡
ሸሚዙን የምትመርጥለት እርሷ ነበረች፡፡ እጆቼን በእጆቹ ጥርቅም አድርጎ ይዟቸዋል፡፡ እጁ ይሞቃል፡፡ ከእነዚያ ጎድጓዳ ዓይኖቹ
እንደ ቀጭን ጅረት ዕንባው ይወርዳል፡፡ ድምጽ አያሰማም፡፡ እንቅስቃሴም የለውም፡፡ ግን ዕንባው ከቧንቧ የተለቀቀ ውኃ እንጂ
ከሰውነት የሚወጣ አይመስልም ነበር፡፡ የእኛ ቤት የቧንቧ ውኃ እንኳን አንዴ ሲሄድ አንዴ ሲመጣ ነው፡፡ የእርሱ ዕንባ ግን ተግ
አይልም ነበር፡፡
መንቃቴን ሲያይ ደረቴ ላይ ልጥፍ ብሎ አለቀሰ፡፡ ማልቀሱን ያወቅኩት በድምፁ
አይደለም፡፡ ሰውነቴ ላይ ትኩስ የሆነ ዕንባው ሲሞቀኝ እንጂ፡፡ ብቻ አንድ ቃል መናገሩን አስታውሳለሁ፡፡ ‹‹ቢያንስ እንኳን
አንቺ ተረፍሽልኝ››፡፡ ወደ ቤታችን ስንሄድ ከግቢያችን በር ላይ ትልቅ ድንኳን ተጥሏል፡፡ አግዳሚ ወንበሮቹ ላይ ጋቢ የለበሱ
ወንዶች ተቀምጠዋል፡፡ ከድንኳኑ ውስጥ ደግሞ ጥቁር የለበሱ ሴቶች ፍራሽ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ይህ በትንሷ ልቤ የቀረጽኩት ሥዕል
ዛሬም እንደ ፊልም ይመጣብኛል፡፡ የእናቴን ፎቶ ሳየው ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡
እንደገና እናቴን አላገኛትም ማለት ነው? ከትምህርት ቤት ማን ያመጣኛል? የቤት
ሥራዬን ከማን ጋር እሠራለሁ? የሚጣፍጥ ምግብ ማን ይሠራልኛል? ፀጉሬን ማን ነው የሚያጥበኝ? ማንስ ነው የሚሠራኝ? ‹ለሴት
የሚሆነውን ልብስ የምታውቅ ሴት ናት› እያለች እናቴ ነበረች የሚያማምሩ ልብሶች የምትገዛልኝ፡፡ አሁን ማን ይገዛልኛል? ታናሽ
ወንድሜንስ ማን ጡት ያጠባዋል? ገላውንስ ማን ያጥበዋል? ብዙ ነገሮች ይታሰቡኝ ነበር፡፡ ይህንን ሳስብ ሆዴን ባር ባር አለውና
እየጮህኩ አለቀስኩ፡፡
ያን ጊዜ ዘመዶቼ ሁሉ መጡና አቃቅፈው ወደ ውስጥ አስገቡኝ፡፡ አባቴና እኔ ብቻ ሳሎን
ቀረንና ሁሉም ወጡ፡፡ እርሱ መሬት መሬት ነበር የሚያየው፡፡ ሮጥኩና አቀፍኩት፡፡ ቀና ሲል ዕንባው ረጨኝ፡፡ በኋላ ከፍ ብዬ
ያነበብኩት የጸጋዬ ገብረ መድኅን ‹‹ወንድ ልጅ ብቻውን ነው የሚያለቅሰው›› የሚለው ግጥም ለእኔ በደንብ ይገባኛል፡፡ አባቴ
ብቻውን ነበር የሚያለቅሰው፡፡ ድንኳን ውስጥ ወይም አልቃሽ ሲመጣ እንደ ሌሎቹ ኡኡ እያለ አያለቅስም፡፡ አይችልበትም፡፡
ከለቀስተኞቹ አንዳንዶቹ ‹‹ቆፍጠን በል እንጂ፤ ወንድ ልጅ አይደለህም እንዴ፤ ወንድ ልጅ እንደ ሴት ሲሆን ጥሩ አይደለም፤
ኮስተር ብለ እንጂ›› ይሉት ነበር፡፡ እኔን ይኼ ይገርመኝ ነበር፡፡ አባቴ ወንድ ብቻ ነው እንዴ? አባቴኮ ወንድ ብቻ ሳይሆን
አባቴም ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ‹‹ይብላኝ ለእርሷ እንጂ እርሱማ ሌላዋን ያመጣል›› ሲሉት ይሰማቸው ነበር፡፡ ከዚህም አልፈው
‹‹ያችን ትመስል ሚስቱን አጥቶ እንደዚህ እያለ ነው የሚያለቅሰው›› እያሉ ያሙት ነበር፡፡
ከእናቴ ሞት ባልተናነሰ አባቴን የሚያስለቅሰው ይኼ ነበር፡፡ እርሱ የሚጨነቀው ስለ
እኔና ስለወንድሜ እንጂ ስለ ልቅሶው ሥነ ሥርዓት አልነበረም፡፡ እናታችን እንዴት ትከታተለን እንደነበር፤ ምግባችንን፣ መጠጣችንኘ፣
ልብሳ ችንን፣ አልጋችን፣ ገላችንን፣ ቅባታችንን፣ የቤት ሥራችንን፣ ጤንነታችንን እንዴት እንደምትከታተል ያውቃል፡፡ እርሱ
የሚጨነቀው እነዚህ ሁሉ በአንድ ጊዜ ሲቀሩብን ሕይወታችን እንዳይቃወስ ነው፡፡ ዘመዶቻችን ደግሞ ጭንቀታቸው ልቅሶውና ሥነ
ሥርዓቱ ነው፡፡ ለኛ ለስላሳ መግዛትና ማስቲካ መስጠት እኛን መከባከብ ይመስ ላቸዋል፡፡ እኛ ፊት ከንፈራቸውን እየመጠጡ ማዘን
የፍቅር መግለጫ ይመስላቸዋል፡፡ እዚያ ፍራሽ ላይ ተቀምጠው አሥር ቀን ሲቆዩ የእኔ ትምህርት ጉዳይ ብዙም አላስጨነቃቸውም፡፡
አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ሞግዚታችንን ሌላ ሥራ እያዘዟት የወንድሜ የሽንት ጨርቅ ሳይቀየር ይቀርና ምርር ብሎ ያለቅስ ነበር፡፡
መጀመርያ አካባቢ ወንድሜን አንዳች መንፈስ ነግሮት ልቡ እየተረበሸ የሚያለቅስ
ይመስለውና አባቴ አብሮ ያለቅስ ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን ሞግዚቷ ነገረችው፡፡ የሽንት ጨርቁን ገልጦ ሲያየው እውነትም መቀመጫው
ቆስሏል፡፡ ከወንድሜ በላይ አባቴ አለቀሰ፡፡ ‹‹እርሷ ብትኖር ኖሮ እንዲህ አይሆንም ነበር›› እያለ አለቀሰ፡፡ ሞግዚታችን
በጣም ጥሩ ልጅ ነበረች፡፡ ከእናቴ ጓደኛ ጋር ሆና ወንድሜን ሐኪም ቤት ወሰደችው፡፡ የሰጡት የሚቀባ ነገር ቶሎ አሻለው፡፡
መድኃኒቱ ግን ከወንድሜ በላይ ለአባቴ ነበር የሠራው፡፡ የሚድን አልመሰለውም ነበር፡፡ ከእናቴ ሞት በኋላ አባቴ ደስ ሲለው
ያየሁት መድኃኒቱ ለውጥ ማምጣቱን ሲያረጋግጥ ነበር፡፡
ሞግዚታችን የሽንት ጨርቅ እንዴት እንደሚቀየር አሳየችው፡፡ እርሱ ነገር ዓለሙን ሁሉ
ለእናታችን ትቶላት እንደነበር በኋላ ሲናገር ሰምቼዋለሁ፡፡ ከፍ ስንል ወንድሜን ሲመክረው እሰማ ነበር፡፡ ሁሉንም ነገር
እንዲለማመድ ይመክረው ነበር፡፡
የልቅሶው ቀን ሲያበቃ የአባቴን ቆሽት የሚያሣርር አንዳች ነገር መጣ፡፡
አንድ ቀን ማታ የእኔና የወንድሜ ልብስ በየሻንጣው ይከተት ነበር፡፡ ሞግዚታችን ልክ
እናቴ የሞተች ጊዜ እንዳለቀሰችው ነው የምታለቅሰው፡፡ ‹ምን ሆነሽ ነው?› ብዬ ስጠይቃት ልትነግረኝ አልቻለችም፡፡ አባቴ
ከወጣበት ሲመለስ ጠየቅኩት፡፡ እርሱም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ሞግዚታችንን ጠየቃት፡፡ ‹‹ጋሼ ምን ያደርግ ልዎታል፡፡
አክስቴ ይነግሩዎታል›› አለችው፡፡ ግራ ስለገባው ዝም አለ፡፡ ትንሽ ቆይቶ አባቴ፣ ከአክስቴና
ከሁለት አጎቶቼ ጋር ሌላ አንድ ሰውዬ ተጨምረው ወደ ሳሎን ገቡና በሩን ዘጉት፡፡ ሞግዚታችን ግን በሩ ላይ ጆሮዋን ለጥፋ ትሰማቸው
ነበር፡፡
ከብዙ ጊዜ በኋላ ሞግዚታችን ፈገግ ብላ ከበሩ ዘወር ስትል አየኋት፡፡ ተከትየ ብጠይቃት አትነግረኝም፡፡ በሩ ተከፈተና
ሰዎቹ ፈጠን ፈጠን ብለው ወጡ፡፡ ሳያቸው የተቆጡ ይመስላሉ፡፡ እኒያ ትልቁ ሰውዬ ብቻ ወደ ኋላ ቀርተዋል፡፡ ዘው ብዬ ስገባ
‹‹ቻለው ልጄ፤ ቻለው፤ ኑሮ እየቻሉ ነው›› ብለውት ሲወጡ አገኘኋቸው፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ አባቴ ድምጽ አውጥቶ ሲያለቅስ ሰማሁት፡፡
ምክንያቱን ሳላውቅ አብሬው አለቀስኩ፡፡ ለብዙ ሰዓት ስቅስቅ ብሎ ካለቀሰ በኋላ ቀና ሲል አየኝ፡፡ አቀፈኝ ጀርባዬ ላይ አለቀሰ፡፡
ተላቀስን፡፡
በኋላ ስሰማ ዘመዶቻችን እኛን ለመውሰድ አስበው ኖሯል፡፡ እኔ አክስታችን ጋር፤ ታናሽ ወንድሜ ደግሞ አጎታችን ጋር
እንዲያድግ የቤተ ዘመድ ሸንጎ ወስኖ ኖሯል፡፡ ለአባቴ ብዙም ቦታ ሳይሰጡት ልብሳችንን እስከ ማዘጋጀት ደረሰውም ነበር፡፡ አባቴን
ያስለቀሰው ይኼ ነው፡፡ ‹‹የፈለገው ይምጣ እኔ ለልጆቼ አላንስም›› ብሎ ተከራከረ፡፡ ይበልጥ ያበገነው ደግሞ ‹‹ልጆቹ በእንጀራ
እናት ባያድጉ ጥሩ ነው›› ብለው አክስቴ በሾርኔ መናገራቸው ነበር፡፡ ‹ይብለኝ ለእርሷ እንጂ አንተስ ታገባለህ› ዓይነት ነው ነገሩ፡፡
ነገሩን ስሰማ እንኳንም እምቢ አለ አልኩ፡፡ እኔ የሰው ልጅ መሆን አልፈልግም ፡፡ እናቴን አጣሁ፤ ደግሞ እንዴት አባቴን
አጣለሁ፡፡
ያመጡትን ሃሳብ እምቢ ስላላቸው ነው መሰለኝ ይቅመሰው ብለው አክስቶቼ መመላለሳቸውን ተውት፡፡ አልፎ አልፎ ብቻ ወይ
ይደውላሉ ወይ ይመጣሉ፡፡ እንደ ድሮው እኛን መውሰዳቸውንም ተውት፡፡ ድንኳኑም ተነሣ፤ ተዝካሩም አለፈ፡፡ ዕቃውም ተመለሰ፡፡ በቤቱ
ውስጥ ከተተራመሰው ዕቃ ጋር እኔ ወንድሜ፣ አባቴና ሞግዚታችን ብቻ ቀረን፡፡ የቤት ሠራተኛችንም ከልቅሶው በኋላ ወዲያው ሄደች፡፡
ሁሉም ነገር አባቴ ትከሻ ላይ ወደቀ፡፡
(ይቀጥላል)
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ
የወጣ ስለሆነ በሌላ ሚዲያ ማውጣት አይቻልም
thanks
ReplyDeletei don't know, I feel something which is difficult to express
ReplyDeleteበጣም ጥሩና አስተማሪ ይመስላል መጨረሻውን እንጠብቃለን
ReplyDeleteእናትም አባት የሆኑ አባታቶች አሉ
አባትም እናትም የሆኑ አባታቶች አሉ
መጨረሻውን ለማንበብ ያብቃን
wtbhm
You remind me to remember my dad who passed away a decade a ago without even knowing him properly. Thanks it is a great story.
ReplyDeletei don't understand that i fall but it was intersting iwan to know the last story soon.thanks d.daniel
ReplyDeleteme too
ReplyDeletei love my dad
YE MIGERM TARIK NEW MECHERESHAW YASAMIREW
ReplyDeleteyalgebagn simet wuste eyasazenew anebebkut ketayun bekirb endemitawetaw betesfa etebabekalew enamesegnalen!
ReplyDeleteYou putted it well Diacon Danil Kibret. However, as my opinion mother's love is better than father's love. I am not saying my father doesn't love me, however my mother love me more than my father does. I think this is a general truth.
ReplyDeleteDo you have a kid/kids ???
DeleteBe sewu fit kenferachewun iyemetetu ye fikir megelecha yemimeslachewu bizuwoch alu!
ReplyDeleteameseginalewu,berta!
Lemanbeb embaye aschegirogn new yechereskut...ebakih ketayun asnebiben....ehhhh....
ReplyDeleteI remember my dad who has died even with out a single photo to remember when I were a little kid. Both my mom and my father are special to me. Now my mom is becoming older and I always fear to miss her.
ReplyDeletegra gebtognal tariku yante new yesew, weys lbe-weled new? ymeleslign?
ReplyDeleteለመላኩ
Deleteየታሪኩ ባለቤት ሴት ናት እኮ።
እዉነቴን ነዉ የምለዉ ልክ ታሪኩን በአካል በቦታዉ ተገኝቼ እንዳየሁት አይነት እንባ እየተናነቀኝ ነዉ ያነበብኩ፤ ከአገራችን አንፃር የተተለመደዉ/አሁን መሻሻል ቢኖረዉም ማለት ነዉ/ ለልጆች ከአባት ይልቅ እናት የበለጠ ትኩረት ትሰጣለች፤ ይህ ሲባል ግን ግድ የለሽ እናት የለችም ማለት አይቻልም፤ ለማንኛዉም የተጀመረዉ ታሪክ የሚመስጥ ነዉ፤ ፍፃሜዉ አስተማሪ እንደሚሆን እገምታለሁ፤ በል ዲን. ዳንኤል ልዑል እግዚአብሄር አንተን የጀመርከዉን ጽፈህ ለመጨረስ እኛንም የጀመርነዉን አንብበን ለመጨረስ ያብቀን እላለሁኝ
ReplyDeleteI don't know, I feel something which is difficult to express.
ReplyDelete"I LOVE MY DAD!!!"
Asazagn tarik new mechereshawu endemiamer asbalehu, emegnlachewalehu.
ReplyDeletewho mentioned those loving and caring fathers thanks to you daniel i can see one in this touching story
ReplyDeletewho mentioned those loving and caring fathers thanks to you dani i can see one in this touching story. am dying to read z next
ReplyDeleteየአምድህ ተከታታይ ነኝ በተለይ ስለ አባት የስነበብከን በጣም ልቤን ነው
ReplyDeleteየነካኝ አባቴን እንዳስታውስ ነው ያደረከኝ፡፡ አባታችን ማለት ለልጆቹ በጣም ጥሩ
አባት ነበረ፣ ግን ሁላቸንም የተሰጠችን እድሜ አለች በእሷ ወደ ፈጣሪያችን እንሄዳለን
ነገር ግን ሁልጊዜም አባታችን ከእኛ ከልጆቹ ልብ ወጥቶ አያውቅም ፡፡
በአንድ ወቅት እህታችን ታማ ሆስፒታል ትሄዳለች ሐኪሙ በሚያክምበት ወቅት አባየ
ድረስልኝ በምትልበት ወቅት ሐኪሙ እንዴ እናቴ ድረሽልኝ እንጂ አባቴ ድረስልኝ ይባላል
እንዴ ሲላት ምን ብላ መለሰችለት መሰለህ አባቴ ከእናት ስለሚበልጥ በተጨማሪ የአባቴን
ጣአም እንጂ የእናቴን ጣአም ስለማላውቅ አባቴ ለእኔ እናትም አባትም ስለሆነ እሱ ቢደርስልኝ
ነው የሚሻለኝ አለችው እና አባት ማለት ምን ብየ እንደምገልጻ ግራ ሰለገባኝ ባቆምስ
this story make me to remember my father i always miss him he was a great father
ReplyDeleteyou make me to remember my father he was a great father i always miss him
ReplyDeleteI think most people live in communist country say mother land just like mama Ethiopia and mama Russia and those people live in capitalist country say most of time father land good example is USA.
ReplyDeleteIt reminds me my father that passed away before 15 years.
ReplyDeleteI love my mother, my father too.
Embaye tenanekegn gin malkes alchalkum kesew gar negn.
'wend bichawun new yemiyaleks'
MY PARENTS LOVES ME AND EXPRESS THEIR LOVE ONLY WHEN I GIVE THEM MONEY.
ReplyDeletehulume endeastedadegu new lemesle ene abatene sayhone enatene emeretalehu ke enate yebelete yeminesefesefe abateme ale gine lijochene lemenekebakebe mane ende enate enate enate enate......
ReplyDeleteወንድሜ ሆይ እንዲህ ቀን ሲያልፍ እንደቀላል ይወራል። ክፎ ቀን ከመጣ አባትም እናት ይሆናል። ይህን የሜያውቅ ዓምላክ አንተንና ቤተሰብህ ይባርክ።
ReplyDeleteአቦ ዳኒ ክፍል 2 አዘገየሁ
ReplyDeleteየሚያሳዝንና እባ እንደ ጅረት የሚያወርድ፤የሚያፈስ ታሪክ ቢሆነም በናፍቆትና በጉጉት እየጠበኩ ነው ክፍል ሁለትን ፡፡ ዳኒ
ReplyDeleteya some times I heard ppl who say ma father is better others say ma mother is best. For me both are best and best of best as well. I LOVE MAMA and DAD more than I CAN SAY
ReplyDeleteme to i love my dad!!!!
ReplyDeleteme to i love dad
ReplyDeleteDaniel,
ReplyDeletePlease tell everyone that you are not talking about your story.
What if , if it is his story???
DeleteO! it is lovely & haveing big message please post part two. I can't wait. Tnxs for sharing.
ReplyDeleteረረረ
ReplyDeleteመጀመሪያ ለ መምሕራችን ዲቆን ዳንኤል እድሜ ና ጤና ይሽጥልን።ጽሑፉ ትምህርት ሰጪ ነው እግዚያብሔር ማስተዋሉን ከሰጠን
ReplyDeletelelijochachin melikam abat lemehon yabikan!!!!
ReplyDeleteIt is a real reality in the community we lived. I loved my father he scarify his life for all family members as we all learnt from our Mother life. Thus, it is difficult to conclude and/or generalize Our Mama or Dad. GOD Bless your family.
ReplyDeleteNice look
ReplyDeletebetam enameseginalen awo lik neh gena lij eyaleh enat kemotech hulu neger malet chigirum, destawm ke bat gar hunew new yemasalfut. ya malt Abbat techegiro yasadigal malet silezih Abat Hager maltih lik neh.betam timhrt sech new.
ReplyDeleteዳኒ ከእናት ፍቅር የአባት ፍቅርማ እጅጉን ይበልጣል ደረቅ ጡቱን አጥብቶ ያሳድጋል እኮ እኔ በግሌ የአባቲ ፍቅር በቃላት ከምገልፀው በላይ ይበልጥብኛል፡፡
ReplyDeleteፍቅር ለእናት ብቻ ነው?
ReplyDeleteሁሉም ባሳደገበው እናት ፣አባት፣ ወንድም፣ እህትም፣
አክስትም፣ ……………… ከእናት ከአባትም በላይ
በባአእድ እጅም ማደግ አለ ስለዚህ ሀገር ……….
መጨረሻውን እኛ ለማንበብ አንተም ጽፈ ለማስነበብ ያብቃን::
oh ilove my dad so much
ReplyDeleteዻኒ ሳነበው ከስድስት አመት በፊት የሞተችው እህቴን እና ባለቤቷን አስታወስከኝ እናም አለቀስኩ፡፡ ባለቤቷ (ወንድሜ ብለው ይቀለኛል) ልጆቼ ክፉ ለምደዋል (በጣም ተንከባክባ ታሳድጋቸው ስለነበር) የእንጀራ እናት አምጥቼ እንዲሳቀቁ አልፈልግም ብሎ ዘምድ (እናቴም ጭምር) አግባ ብለው ቢለምኑት አሻፈረኝ በማለት ልጆቹን እያሳደገ ይገኛል፡፡ አባት ሀገርም ነው እንጂ ለምን እናት ሀገር ብቻ
ReplyDeletefabulous story
ReplyDelete