የሚወዱትን ሰው አጥቶ በብቸኝነት መኖር ከተስፋ ይልቅ በትዝታ ውስጥ እንድንኖር
የሚያደርግ ነው፡፡ በማኅበረሰባችን ባህል የቤት ውስጥ ሥራዎች የሚባሉትን በአብዛኛው የሚሸፍኑት ሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች
የተማሩም ቢሆኑ ወይም ያልተማሩ፣ ሠራተኞችም ቢሆኑ ወይም የቤት እመቤቶች የቤት ሥራ ይቀርላቸው ይሆናል እንጂ የቤት አስተዳደር
አይቀርላቸውም፡፡ እነዚህ ሴቶች ሊቃውንትም ቢሆኑ ወይም ሳይንቲስቶች፣ የሀገር መሪዎችም ቢሆኑ ወይም የታወቁ ሃሳብ አመንጭዎች
የቤት ውስጥ ጭቅጭቅ ግን አይቀርላቸውም፡፡ ጓዳ የራሱ ሳይንስ አለው፡፡ የጓዳ ሳይንስ እስከዛሬ በየትኛውም ትምህርት ቤት
አይሰጥም፡፡ የጓዳ አስተዳደር በየትኛውም የአስተዳደር ትምህርቶች ውስጥ አልተካተተም፡፡
ይህ ነው እንግዲህ ለአባቴ የመጀመርያው ፈተና፡፡ ጓዳውን ማስተዳደር፡፡ በቤታችን
ውስጥ እናታችን ካረፈች በኋላ ሦስት ዓይነት የቤት ሠራተኞችን አይተናል፡፡ የመጀመርያዎቹ ቤቱን ‹‹የወንድ ቤት ነው›› ብለው
የሚያስቡና መደፋፋት፣ ማባከንና ማዝረክረክ ይቻላል ብለው የሚገምቱ ናቸው፡፡ ወንድ ጓዳ ድረስ አይዘልቅም፤ የተጠየቀውን
ይሰጣል፣ ግዛ የተባለውን ይገዛል፤ ለምን አለቀ፣ መቼ አለቀ፣ እንዴት አለቀ አይልም ብለው የሚያስቡ ዓይነት ናቸው፡፡
ሁለተኛዎቹ ሠራተኞቻችን ደግሞ ጥሩዎች ናቸው፡፡ ለእኛ ያዝኑልናል፡፡ እንደ እናት
ለመሆን ይሞክራሉ፡፡ የአባታችን ሁኔታ ያሳዝናቸዋል፡፡ ችግሩ ኀዘናቸው ከልክ ያልፍና ‹አምጵ› እያሉ ከንፈራቸውን ሲመጡለት ይናደዳል፡፡ እርሱ የሚረዳውና የሚረዳው እንጂ የሚያዝንለት አይፈልግም፡፡ ችግሩ ደግ ሠራተኞቻችን
አይበረክቱም፡፡
እንዳይበረክቱ የሚያደርጓቸው ዕድርተኞቻችን ናቸው፡፡ በሠፈራችን የወንድና የሴት ዕድር አለ፡፡ የወንድ ዕድር ገንዘብ
ከመክፈል፣ ድንኳን ከመጣልና ማታ ማታ ካርታ እየተጫወቱ ከማምሸት በቀር ሌላ ጣጣ የለበትም፡፡ የሴት ዕድር ግን እንጀራ መጋገር፣
ወጥ መሥራት፣ ማስተናገድ፣ ንፍሮ መቀቀል፣ ፍራሽ ዘርግቶ ድንኳን ውስጥ መቀመጥ፣ ቡና ማፍላት አለበት፡፡ በዚህ ሁሉ መካከል ደግሞ
ሐሜቱ አለ፣ ጠቡ አለ፣ መተቻቸቱ አለ፤ መነቋቆሩ አለ፡፡ አሁን እናቴ ካረፈች በኋላ የሴት ዕድሩ ጉዳይ የአባቴ ጣጣ ሆነ፡፡ የግድ
ዕድሩን ለመሳተፍ በእናቴ ምትክ የቤት ሠራተኞቻችን እየሄዱ ሽንኩርት እንዲከትፉ፣ ሥጋ እንዲዘለዝሉ፣ ወጥ እንዲሠሩ፣ አንዳንዴም
እንዲያስተናግዱ ይደረጋል፡፡ አንዳንዶቹ ሠራተኞቻችን እንደ መዝናኛ ስላዩት አያማርሩም፡፡ ደጋጎቹ ግን አይፈልጉትም፡፡ ሁለት ልቅሶ
ከሠሩ በኋላ ይሄዳሉ፡፡
ሦስተኛዎቹ ሠራተኞቻችን ለፈተና የሚመጡ ናቸው፡፡ እንዲያውም አንድ ቀን የቤት ሠራተኛ የሚያመጡልን የሠፈራችን ሴትዮ
እኛ ቤት ውስጥ መሆናችንን ሳያውቁ ‹‹እንግዲህ ዕወቂበት፤ ካወቅሽበት የቤት እመቤት ትሆኛለሽ፤ ካላወቅሽበት ደግሞ አንቺም እንደሌሎቹ
ትወጫለሽ›› ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡፡ መመርያው አልገባኝም ነበር፡፡ በኋላ ነው የተረዳሁት፡፡ ማታ ማታ ቤቱን የፋሽን ትርዒት ማሳያ
ታደርገዋለች፡፡ ሽቱ ተቀብታ፣ ገላዋን ታጥባ፣ ስስ ልብስ ትለብስና ሳሎን ትቀመጣለች፡፡ ነገር ዓለሟ ሁሉ አልገባኝም፡፡
አባቴ ደግሞ እኛን የቤት ሥራ ማሠራት፣ ራት አብልቶ ማስተኛት ስላለበት ከሥራው ሮጦ ቤት ነው የሚመጣው፡፡ ቤት ሲገባ
ሽቱዋ ያውደዋል፡፡ አባቴ ወንድ ነው፡፡ ይህንን አትርሱ፡፡ ያውም ገና በወጣትነቱ የሚወዳትን ሚስቱን ያጣ ወንድ፡፡ አንዳንድ ጊዜ
እኔን ይዞኝ ወጥቶ በረንዳ ላይ እናመሻለን፡፡ ከራሱ ጋር እየታገለ መሆኑን ዐውቃለሁ፡፡ አባቴ ሌሊት ሌሊት ውኃ የመጠጣት ልማድ
አለው፡፡ ማታ ከመተኛቱ በፊት በራስጌው ውኃ ይደረግለታል፡፡ ይህችኛይቱ ልጅ ግን ሆን ብላ ሲተኛ ጠብቃ መኝታ ቤቱ ትሄድና ውኃውን
ታስቀምጣለች፡፡ ሁለት ጊዜ ከተኛ በኋላ በር እንዳትከፍት ሲነግራት ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን አላቆመችም፡፡
አንድ ቀን እኔ ከትምህርት ቤት ግማሽ ቀን ተምሬ ተመለስኩ፡፡ እኒያ ሠራተኛ የሚያመጡልን ሴትዮና ሠራተኛችን በረንዳ
ላይ ቡና ይጠጣሉ፡፤ መኛታ ቤቴ ገብቼ ዘጋሁት፡፡ ሲያወሩ ግን በመስኮት ይሰማኛል፡፡ ሴትዮዋ ሠራተኛችንን ይመክሯታል፡፡ የቤት ሠራተኛ
ሆነው ገብተው በዚያው ሚስት ስለሆኑ ሴቶች ታሪክ ያጫውቷታል፡፡ ዓላማዋ ገባኝ፡፡ አባቴ ሲመጣ ነገርኩት፡፡ እንደ ልጅ ሳይሆን እንደ
እኩያ እኅቱ ነበርና የሚያወራኝ እርሱም እንደገባው ነገረኝ፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ እንድትሄድ ተደረገ፡፡
እኒያ የሠፈራችን ሴትዮ ተናደዱ ‹‹አያያዙን አልቻልክበትም፤ በየሳምንቱ እያስወጣችሁ እኔ ከየት አመጣለሁ፡፡ አያያዝ
ማወቅ ያስፈልጋል፤ ሲቀጥሩ እንደ ሠራተኛ ሲያኖሩ እንደሚስት ሲሉ አልሰማህም›› አሉና ተቆጡ፡፡
አባቴን የቤት ሠራተኞቹ ብቻ አልነበሩም የተፈታተኑት፡፡ የገዛ ጓደኞቹም ደጋግመው ፈትነውታል፡፡ እርሱ የእኛ ነገር
ነው የሚያሳስበው፡፡ በእናታችን አለመኖር በጣም እንደተጎዳን አድርጎ ያስባል፡፡ ጭንቀቱ ጉዳታችን እንዳይሰማን ለማድረግ ነው፡፡
ቤት በጊዜ ከገባ ታናሽ ወንድሜን ሽኮኮ አድርጎ እኔን ያዝልና ያጫውተናል፡፡ የቤት ሥራዬን አብሬው እሠራለሁ፡፡ ቅዳሜና እሑድ አውጥቶ
ያዝናናናል፡፡ ልብሳችንን በማሽን ራሱ ያጥባል፤ ይተኩሳል፡፡ በቦርሳዬ የያዝኩትን ምግብ ራሱ ይከታተላል፡፡ ገላችንን የሚያጥበን
እርሱ ነው፡፡ አልጋችንን የሚያነጥፈው እርሱ ነው፡፡ ተነጥፎ ካገኘው እንኳን እንደገና ገልጦ ያየዋል፡፡ ሰውነታችን የተኮሰ ወይም
የከሳ ከመሰለው ሮጦ ወደ ሐኪም ቤት ነው፡፡ እንዲያውም ጭንቀቱን ያየው የሕጻናት ሐኪሙ ‹‹መጀመርያ ይደውሉልኝና ተነጋግረን ይመጣሉ››
ባይለው ኖሮ በየሦስት ቀኑ እዚያው ይገኝ ነበር፡፡
ይህንን ቤት ቤት የሚል ጠባዩን ግን ጓደኞቹ አልወደዱለትም፡፡ ‹‹ሴቶቹ ወንድ በሆኑበት ዘመን እንዴት ወንዱ ተመልሰህ
ሴት ትሆናለህ›› ብለውታል፡፡
ከእነርሱ ጋር ወጥቶ ማምሸት እንዳለበት ደጋግመው መክረውታል፡፡ ሆን ብለው በመሥሪያ ቤቱ መስክ እንዲወጣ አድርገውታል፡፡
እንዳይቀየሙት ብሎ እንድ ቀን አብሯቸው ቢያመሽ በሚጠጣው ቢራ ውስጥ አንዳች ነገር አድርገው ዕንቅልፍ ዕንቅልፍ ሲለው አልጋ ይዞ
እንዲያድር አድርገውታል፡፡ የሚስቱ ሐሳብ ይለቀው መስሏቸውም በዚያ ቀን አንዲት ሴት አብራው እንድታድር አድርገዋል፡፡ አባቴ ግን
የሚቀየር ሰው አልሆነም፡፡ አዘውትሮ ሐዲስ ዓለማየሁን ይጠቅሳቸዋል፡፡ ደራሲ ሐዲስ ሚስታቸው ካረፈች በኋላ ለምን ሌላ እንዳላገቡ
ሲጠየቁ ‹‹እርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ›› ብለው ነበር፡፡ ይህ
ለአባቴ ትልቅ መመርያው ሆኗል፡፡ ‹‹እኔኮ ባለትዳር ነኝ፤ ከሚስቴ ጋር በተለያየ ቦታ እንኖራለን እንጂ አልተፋታንም፡፡ ባል አሜሪካ
ሚስት ኢትዮጵያ ይኖሩ የለም እንዴ! እርሷ በሰማይ እኔ በምድር እየኖርን ነው፡፤ እንድ ቀን እንገናኛለን፡፡ ስንገናኝ ምን እንድላት
ነው የምትፈልጉት?›› ይላቸዋል፡፡
ታናሽ ወንድሜንኮ እያዘለ ነበር የሚያስተኛው፡፡ ያውም በልጅ አንደበቱ ‹‹እማዬስ›› እያለ እያስጨነቀው፡፡ የሚመልሰው
መልስ እያጣ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ‹‹እማዬ ካላበላችኝ አልበላም›› ይለዋል፡፡ ፊቱን በዕንባ እየታጠበ መልሱ ይጨንቀዋል፡፡ በተለይማ
ትምህርት ቤት መሄድ ሲጀምር ‹‹እንደ ልጆቹ የእኔ እናት ለምን አታደርሰኝም›› ይለዋል፡፡ አንድ ፈጣን የሆነ የሠፈራችን ልጅ አለ፡፡
ከወንድሜ ጋር አብረው ነው የሚማሩት፡፡ እንድ ቀን ‹‹እናትህኮ ሞታለች›› አለው፡፡ ‹‹ውሸትክን ነው፤ ለሥራ ውጭ ሀገር ሄዳ ነው፤
ትምጣለች›› ሲል ወንድሜ መለሰለት፡፡ ‹‹ኧ-ራ፣ እናቴ ነግራኛለች ሞታለች፤ የተቀበረችው ደግሞ ገብርኤል ነው›› አለው፡፡ ወንድሜ
እየተንቀጠቀጠ ነበር ከትምህርት ቤት የተመለሰው፡፡ እንደመጣ የመኝታ ክፍላችንን ገብቶ ዘጋው፡፡ እኔና ሠራተኛችን ብናንኳኳ ሊከፍት
አልቻለም፡፡
ሲጨንቀን አባታችንን ጠራነው፡፤ እርሱ ደግሞ ሲደነግጥ ጊዜ ጓደኛውን ለምኖ በመኪናው ይዞት መጣ፡፡ ቢያንኳኳ ሊከፍትለት
አልቻለም፡፡ በመጨረሻ በሩን ሰብሮት ገባ፡፡ አንድ ጥግ ላይ ተቀምጦ ያለቅሳል፡፡ አባቴ እንኳን ይህንን አግኝቶ እንዲያውም ዕንባው
ቅርብ ነው፡፡ አብሮት አለቀሰ፡፡ እንኳንም ከጓደኛ ጋር መጣ እንጂ የትኛውን እናባብል ነበር፡፡ ጓደኛው እንደምንም ብሎ አረጋጋው፡፡
‹‹እናቴ ሞታለች አይደል?›› ሲል አባቴ የሚፈራውን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ አባቴ መልሱን አጥቶት ዝም አለ፡፡ ‹‹ንገረኝ›› አለው፡፡
‹‹ለምን ጠየቅከኝ›› አለው አባቴ፡፡ ‹‹ኤርምያስ እናትህ ሞታለች አለኝ›› አለና አለቀሰ፡፡
አባቴ የሚያደርገው ጨነቀው፡፡ ምን ይበለው፡፤ አሁን ከእውነት ጋር ተፋጠጠ፡፡ ጓደኛው እውነቱን እንዲነግረው አበረታታው፡፡
አባቴ ተረጋጋና እውነቱን መናገር ጀመረ፡፡ እናታችን ምን ዓይነት እናት እንደነበረች፣ እንዴት ልትሞት እንደቻለች፣ አሁን በገነት
እንዳለች፣ ወደፊት እንደሚገናኙ ለመናገር ሞከረ፡፡ ወንድሜ በትንሽ ልቡ ያዳምጠው ነበር፡፡ ከዚያም ይዞን በጓደኛው መኪና ወጣ፡፡
ከዚያ ቀን ጀምሮ ለወንድሜ በጣም ይሳሳለት ነበር፡፡ ከሠፈር ልጆች ጋር እንዳይገኛኝ ብሎ ሌላ ትምህርት ቤት አስገባው፡፡
እንዲያውም እኛ ራሳችን ለአባታችን ፈተና ነበርን፡፡ ይህን ለምን በላህ፣ ይህን ለምን ጠጣህ፣ ይህን ለምን ለበስክ፡፡
ትታመማለህ፣ ትሞትብናለህ፣ እንዲህ ትሆናለህ ፣ እንዲያ ትሆናለህ እያልን ነጻነቱን የሚገፍ ቁጥጥር እናበዛበት ነበር፡፡ እርሱም
እኛን ለማስደሰት ነጻነቱን ሳይቀር ይሠዋልን ነበር፡፡ አሁን ሳስበው ይቆጨኛል፡፡
እኔን ሴት አድርጎ ያሳደገኝ አባቴ ነው፡፡ ስለ ሴትነት፣ ስለ ወጣትነት፣ ስለ ፍቅረኛ፣ ስለ የወር አበባ፣ ስለ ሞዴስና
ስለ ሌላውም ቁጭ አድርጎ ያስተማረኝ አባቴ ነው፡፡ አባቴ ለእኔ አባቴም፣ እናቴም፣ ጓደኛዬም፣ መምህሬም ነው፡፡ እጅግ ሩኅሩኅ፣
ለልጆቹ የሚያስብ፣ ለልጆቹ ራሱን የሠዋ፣ መልካሙን የወጣትነት እድሜውን ለእኛ ለልጆቹ ሲል እንደ ሽማግሌ ያሳለፈ፤ ሰፍሳፋና ጭንቀታም
ነው አባቴ፡፡ እኔ ውስጥ እርሱ አለ፡፡ በራሴ እንድተማመን፣ የማስበውን እንድሆን፣ በትክክለኛውም መንገድ እንድጓዝ፣ ዛሬም በፊታችሁ
እንድቆም ያደረገኝ ነው አባቴ፡፡ ልጅ ለማሳደግ ሲል ልጅ ሆኗል፡፡ ሴት ልጅን ለመቅረጽ ሲል ሴት ሆኗል፡፡ ቤቱን ለማስተዳደር ሲል
እማወራ ሆኗል፡፡ ለኛ ሲል ጨዋታውን፣ ዕድገቱን፣ ጓደኞቹን፣ የውጭ ዕድሎቹን፣ የትምህርት ዕድሎቹን፣ የዝውውር ዕድሎቹን ሁሉ አምክኗል፡፡
ለዚህ ነው፡፡ ይህች ሀገር ‹‹እናት ሀገር›› እንደምትባለው ሁሉ ‹‹አባት ሀገር››ም
መባል አለባት ብዬ የምከራከረው፡፡ በአዳራሹ የነበረው ሰው ሁሉ ማራቶናዊ በሆነ ጭብጨባ አጀባት፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው፤ በተመሳሳይ ሚዲያ መጠቀም አይፈቀድም
I was crying when I read this article. It is so touching. let's all take the lesson. Thanks Dn. Daniel.
ReplyDeleteእርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ››
ReplyDeleteስሜቴን ለ2ኛ ጊዚ መግለጽ ከበደጝ
D/N betam kelib enameseginalen ehe betkikil yenebere ena lewedefitom yeminor new lesetehin mekir enameseginalen.Egziabhier Amlak kante gar yehun Amen.
ReplyDeletesuper article....
ReplyDeletewell said
DeleteDitto
Deletevery touching ,i can't control myself
ReplyDeleteWaw! Ye-abat Enat. betam yidenkal!
ReplyDeleteአስለቀስሽኝ በሕይወት የሌለሽው እናቴ ይህም ፅሁፍ የአንቺም መገለጫ ነውና ነፍስሽን በገነት ያኑረው አሜን
ReplyDeletewtbhm
እስማማለሁ ዲ/ን ዳንኤል
ReplyDeletewow !!! I can't say anything.Just am crying 'cause i lost my father
ReplyDeleteየእኔ አባት ታሪክ የተጻፈ ነው የመሰለኝ፡፡ ረዥም ዕድሜ ለምወደው አባቴ፡፡
ReplyDeletereally it is a very touching story
ReplyDeleteBetam Desse Yemile Tarik nw
ReplyDelete‹‹እርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ›› Great!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteTiru astemari tarik newu 10Q Dani
ReplyDeleteየእኔም አባት ልክ እንደዚህ ነበር እንደዚህ አይነቱ አባት አይደለም እናት ከዚያም በላይ ሊባል ይገባዋል፡፡
ReplyDeleteዓለም ምን ያህል ፈታኝ ናት፡፡ ‹‹እርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ››
ReplyDeleteዲ/ን እግዚአብሔር ያበርታህ፡፡
"............እርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ............."
ReplyDeletewyii, menew men arekuh!!!
ReplyDeleteበጣም ልብ የሚነካ ነው። እግረመንገዱን ብዙ እደዚሕ አይነት አባቶች እንዳሉ ያስተምራል።
ReplyDeletewaw!! nefse yenare
ReplyDeletedani realy i thank u for this impressive history specialy ‹እርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ
ReplyDelete‹‹እርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ›› batame telke kale nawu baewenate Hadese Alamayehu telke sawu nachewu.
ReplyDeleteBetame Yamyasasene tarke nawau.
I was visualizing their house and life like I was there and sometimes crying oh Dani life by itself is miserable why you push us to sad incidence! The very think what I want to tell you is I Love my father too. You know there are fathers whose love outshine and even you forget your mother's existence because of their unconditional love.
ReplyDeleteሰላም ዳንኤል፦በኦሮሞ ብሄረሰብ ባህል እናት ሃገር አይባልም "biyya abbaako"ወይም "አባት ሃገር" ነው የሚባለው።
ReplyDeleteLe Teru abatoch metasebiya yehun
ReplyDeleteዳኒ ስላም ላንተ ይሁን ታሪኩ በጣም ያሳዝናል ለሁሉም መልካም አባቶች ማስታወሻ ይሁን
ReplyDeleteYou want my tear, take it. I am crying!!!
ReplyDeleteThanks D. Dani. It is very helpful for me to remember the past life of my Family and to be a good father for the future.
ReplyDeletetizitan yichiral.It's kind of you[daniel] to share as always.
ReplyDeleteDani i love my father greterthan anything in my life.t is because of the things you mentioned.he is a martyr for me,a living martyr.
ReplyDelete!thanks a lot.
+++
ReplyDeleteThank you brother, I can't stop crying oh God what a wonderful father? who listen kids heart beat amazing!my beloved parents RSP‹‹እርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ›› Thank you again
DES BLONGAL BE MIGERM AGELALETS YEMIYASAMEN ASAB ... GEN MEDRAWI ABAT ENDIH BE MAROTONAWI MORAL KETAGEB... YE SEMAYE ABATCHIN BE MEN YETAGEBAL ,,, ESU LENGA YALHONELN NEGER MN ALE .. SELZIH... NGERUNG MEN ENBELEW....
ReplyDelete‹‹እርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ›› Great!!!!!!!!!!! Ende yalewn astesaseb ena metsinatn bezemenachn lalu wendoch ena abatoch endyadlachew be tselot metgat alebn D.Dani ! Abat huy ende yalewn mastewalna lezelalem ke gnagar abron yzelq zend ante ke gnagarhun amen ! D.Dani slakafelken tarik betam enamesegnalen . Yagelglot zemenhn ybarkew amen .
ReplyDeleteGreat Story with Great Message!! 10Q Dani!!
ReplyDeleteThank you Din. Dani
ReplyDeleteAnjet yemibela,negerochin komm bilen indinastewul yemiyaderg tsihuf newu.
ReplyDeletedani this is great!!!!!!!!!!!!!!!!!.
ReplyDeleteይህ ጽሑፍ ለመልካም አባቶች መታሰቢያ እንደሚሆን ሁሉ የጓዳን ቀንበር ሙሉ ለሙሉ እናት ላይ ለሚጥሉ፣ ሃላፊነታቸውን ለማይገነዘቡ፣ ይህ ይመጣል ብለው ለማይገምቱ፣ አባትነት ማለት መምከር፣ መቆጣትና እጅን ታጥቦ ጋቢ ተከናንቦ እግር ዘርግቶ የላመ የጣመ መብላትና ትዕዛዝ መስጠት ለመሚመስላቸው የዘመናችን ባሎች ምክርና ትምህርት እንዲሆናቸው እመኛለሁ፣
ReplyDeleteዳኒ የኛ አባት እናታችን ጎረቤት ሆና እናትም አባትም ሆኖ ነው ያሳደገን እግዚሀብሄር ነብሱን በገነት ታኑርልኝ ከልቤ አመሰግንሀለው ጌታ ይባርክህ እናትነትን በእማዊ ወአባዊ ነው የማውቀው አባቴ እናቴም ነበረ ነበረ.................. ጌታ ይባርክህ ዳኒ
ReplyDeleteአባቴ ከእናትም በላይ ነበር
የሱን ያክል ባልሆንም የሱን ፈር ለመከተል ጥረት እያደረኩ ነው ጌታ ላይችል አይሰጥም.......................
እርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ›
ReplyDeleteGreat Saying
You REMINDED me that I should think of the roles my father and mother playing to me!!! Be-ej yeyazut yibal yele!!! GOD BLESS YOU!!!
ReplyDeleteአንድ ጊዜ በሬዲዮ ምነው ባል በሆንኩኝ የሚል ፅሁፍ የዲ/ዳንኤል ክብረት ተብሎ ቀርቦ ሰምቻለሁ ካልተሳሳትኩ በራሱ አቅራቢነት በዚህ ጡማር ላይ አልተጦመረም ወይ ካለ የቱ ጋር ነው ያለው እባካችሁ አርስቱን ወይም ቀኑን ንገሩኝ
ReplyDeleteyes u r right, i heard it. even i read it on ze magazine too. but i cant remember the name of ze magazine.
Deleteany way 10 Q
Delete"Ye Hulet Hawultoch Wogg" Yemilewun metsihaf lay alelish/h
DeleteDear Dani,
ReplyDeleteyou broke my heart in a good way. You have touched by deep feelings and my past experience. Thank you for preparing this exceptional piece of work.
Amanuel from Tigray
wow! love it
ReplyDeleteዳኒ ዕድሜ ጤና ይስጥህ፡ በቀረበው ታሪክ በምኖረበት አካባቢ ተመሳሳይ ታሪክ ያላቸውን ሰውች እንዳስታው አድረጎኛል፡፡ እኝህ ታላቅ አባት ታዲያ ልጆቻቸው በመልከም ሁኔታ ካሳደጉ በኃላ ግን ልጆቻቸውም ህይወት ሄደት ነችና ማንም ከቤተሰቡ ጋር የሚኖር የለም እና ልጆቻቸውም አግብተው ወጡ እሳቸውም ብቻቸውን ቀሩ ትካዜ እና ቁጭት ይታይባቸውም ነበር መጨረሻቸውም መልካም አልነበረም፡፡ ስለሆነም ልጆችም ሳይሳቀቁ ወላጆችም ሳይጎሳቆሉ ተመጣጣን በሆነ መልኩ ቢሆን መልካም ነው፡፡ ሴት ልጅ ለወንድ ልጅ የምትሸፍነው ነገር ብዙ ነው ደስታም ትሰጠዋለች፡፡ ታለቁ መፅሐፋችን "የሰው ልጅ ብቻውን ሊኖር መልካም አይደለም"፡፡
ReplyDeleteየእውነት ልብን የሚነካ ታሪክ ነው ለማንኛውም እኔ በጻፍኩት ማን መዳቢ አደረገሽ ካላልከኝ እኔን ያሳደገው አልበቃው ብሎ የልጄ አሳዳጊ ለሆነው አባቴ እና መልካም ለሆኑ አባቶች ሁሉ ማስታወሻ ይሁን.
ReplyDeleteDear Dani, why are you so silent on the election/selection of the new Patriarch? We are eagerly waiting to read your timely and insightful notes on the process. Your advices when former Patriarch died, were so wise and insightful. Please say something!
ReplyDeleteThat is Hadis Alemayehu's choice but if another person does not want to be single after his wife died, I do not think it is wrong.
ReplyDeleteየሰው ልጅ ታሪክ እንዲህ ቢፃፍና ቢነገር አሳዛኝ፣ አስተማሪ ነው ።ዳኒየ እጅግ አድርጌ ነው የማመሰግነው ጥሩ ጥሩ ላንተና ለቤተሰብህ እመኛለው ፤ መልካም ነገር ያሰማን ዘንድ እ/ርን እንለምነው እንፀልይ ኢትዮ... ለዘላአለም ትኑር
ReplyDeleteዳኒ አባት አገር ላይ ቆመህ ቀረህ እኮ! ወደ እናት አገር ስማዳ ወገዳ ተመለስ እንጅ ?????? ገትረኸን ቀረህ አንተን ስንጠብቅ፡፡
ReplyDeletedani arif tsehuf new yesewen leg feer yashenefewal
ReplyDeleteIt is not a matter of loving mother or father more. It is a matter of carrying the baby. Everybody loves his mother and father equally or depending on the treatment. With out any doubt a father is not suffering the same as the mother does in child bearing. Let me ask you Dn. have you ever been laboring when you get your children????????. It is your wife who did so! have you carried the infant in your womb ever????. To those who comment, it is not the matter of loving father or mother. but which one is more expressive term, mother land or father land?
ReplyDeleteለዚህ ነው፡፡ ይህች ሀገር ‹‹እናት ሀገር›› እንደምትባለው ሁሉ ‹‹አባት ሀገር››ም መባል አለባት ብዬ የምከራከረው፡፡
ReplyDeleteዲን. እግዚአብሄር ፀጋዉን ያብዛል!
It is a good message for irresponsible mothers!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteD/N Egiziabher Yabertah
ReplyDeleteዳኒ ጠፋህ በሰላም ነው አባፊሊፖስን ባተገኛቸውም እባክህ አለሁ በለን በወቅቱ ሁኔታ ያንተን ምክርና አስተያየት በጉጉት እንተብቃለን
ReplyDeletei am crying too because i lost my loving father !!!
ReplyDeleteእኔ አባቴን አልወድም! ነገር ግን እንደዚህ አይነት አባት ሳይና ስሰማ በጣም እቀናልው የእግዚሐብሄር መልካም ፍቃድ ሆኖ እንደዚህ አይነት አባት መሆን ፈልጋለው
ReplyDeleteየእውነት ልብን የሚነካ ታሪክ ነው ለማንኛውም ለአባቴ እና መልካም ለሆኑ አባቶች ሁሉ ማስታወሻ ይሁን.
ReplyDeleteDAB
ከልብ የሚመስጥ ጽሑፍ ነው፤እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡
ReplyDeleteWonderful!!!
ReplyDeleteI wish If I can express my Mom in such a way. Very touchy......
ReplyDeleteThanks for sharing.
'እናት ቤተ ክርስቲያን' የሚበለው ለምንድን ነው? "አባት ቤተክርስቲያን"ስ ማለት እንችላለን?
ReplyDeletemenew seladdisu pope yaletsafehew
ReplyDeleteDaniel, I didn't know the love of my father that deep. Because i grew up with my brother far apart from my parents.And when the time came to join him he passed away. we had not even met. I was 12 by then.
ReplyDeleteThis story applies for me in the other way. because it was my mom who did all those for me. But as I heard,my father was as good as my mom is. And I regret I didn't enjoy his fatherhood.
So, Its healthy and appropriate if any one calls his country by the pronoun 'he' because parents give equal love to their fruits as long as they have a normal mental status!
I loved the whole story!
Enate yihin saneb salawukish nafkeshign.Abate antem bitnor indih taderegilign nebere! lene ICHIN hager yemin hager libelat????? Dani godahegn.'SALAWUKACHIW NAFKOTACHIW!!!!'
ReplyDeletevery interesting article. thank you dani.
ReplyDeleteD/N lesetehin mikir kelib enameseginalen Egziabhier Amlak yanurilin amen.
ReplyDeleteእንዴት የሚያሳዝን ታሪክ ነው በሌላ መልኩ አንዲህ አይነት አባት ማግኘት ምን አይነት መታደል ነው ምነው እግዚአብሔር አምላክ ለልጆቼ እንዲህ እሩህ ሩህ አባት ቢሰጣቸው
ReplyDeleteOh my god all of it touch my past life!! ?Betam hazingalhung yelijinet tariken astawishe......
ReplyDeletereal love
ReplyDeleteየእኔ አባት ታሪክ የተጻፈ ነው የመሰለኝ፡፡ ረዥም ዕድሜ ለምወደው አባቴ፡፡ Ameseginihalehu D/n Dani
ReplyDeleteሰላምና ጤና ዘውትር ላንተና ለቤተሰቦችህ ሁሌም እግዚአብሄር አምላክ እንዲያድልህ እመኝልሃለው ደንየ፡፡ ሁሌም አስተማሪ ነህ ፀጋውን ያብዛልህ፡፡
ReplyDeletei really thank you i see it my mom she deserve this thank you dani you are my best favorite by the way "yene Jegnoch" nice book
ReplyDeleteዳኒኤል አመሰግናለሁ የኔም አባት እንደዚህ ነው፡፡ አምላኬን እምለምነው እንደዚህ አይንት ባል እንዲኖረን ነው፡፡
ReplyDeleteዳኒኤል አመሰግናለሁ የኔም አባት እንደዚህ ነው፡፡ አምላኬን እምለምነው እንደዚህ አይንት ባል እንዲኖረን ነው፡፡
ReplyDeleteI was just crying when I read this articles! Danny ,may God bless your Father
ReplyDeleteI was just crying, I love my dad indeed. My Mam too.
ReplyDeleteDn, Daniel,God bless you and yours family