አዲሱ የዓባይ ድልድይ
|
ኅዳር 24 ቀን ከሌሊቱ ዐሥር ሰዓት ከአዲስ አበባ ተነሥተን ጉዟችንን ወደ ሰሜን
ምዕራብ አደረግን፡፡ ድንበሩ ሰጠ መኪናውን እያገላበጠ፣ እኔ ከጎኑ ተቀምጬ፣ ኤልያስና ቀለመወርቅ ከኋላ ሆነው በጫንጮ በኩል
ወጣን፡፡ በዘመነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶባቸው ከነበሩት ቦታዎች አንዷ የሆነችውን፣ ታቦቷም በዘመነ
ሱስንዮስ ወደ ጎንደር ሔዶ በዘመነ ምኒሊክ የተመለሰውን፣ ታሪኳም ‹ዜና ፍልሰታ ወምጽአታ ለታቦተ ማርያም› በሚለው ጎንደር
ደብረ ብርሃን ሥላሴና አዞዞ ተክለ ሃይማኖት በሚገኘው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈላትን ደብረ ጽጌን ተሳልመን፤ የብዙ ቅዱሳን
መፍለቂያ የሆነውን አስቀድሞ ደብረ አስቦ፣ በኋላም በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በ1437 ዓም በድላይ ከሚባለው የአዳል
ገዥ ጋር ተዋግተው ድል ካደረጉ በኋላ በጸሎት የተራዷቸውን የደብረ አስቦ መነኮሳት አመስግነው፣ ለገዳሙም ርስት ሰጥተው በዚሁ
ዓመት ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› ሲሉ የሰየሙትን ገዳም እንዲሁ በሩቁ እየተሳለምን ወረድን፡፡
የፍቅር እስከ መቃብሮቹ በዛብህና ሰብለ ወንጌል የተቀበሩባትን ጎሐ ጽዮን ማርያምን
አልፈን የዓባይን በረሃ ቁልቁል ተያያዝነው፡፡ ምንም እንኳን ጃፓኖች መንገዱን እንደገና ቢሠሩትም የዓባይ በረሃ ግን ለጃፓንም
የሚመለስ አይመስልም፡፡ ጋራው አሁንም ድንጋይ ያወርዳል፡፡ መንገዱ ይገመሳል፡፡ አንዳንዴም ተጠባብቆ መተላለፍ ግዴታ ይሆናል፡፡
አስደናቂውን የዓባይን ድልድይ አልፈን ሽቅብ ወደ ደጀን አመራን፡፡ ደጀን እምብዛም
አልተለወጠችም፡፡ በርግጥ አንዳንድ ፋብሪካዎች ወደ አካባቢው በመምጣታቸው ሽር ጉድ የምትል ከተማ ትመስላለች፡፡ ዕድገቷና ታሪኳ
ግን አይመጣጠንም፡፡ አሁንም ከወዲህም ከወዲያም ለሚመጡ መንገደኞች የምሳና ቁርስ መመገቢያነቷን ግን አልተወችም፡፡
የታደለች ፓሪስ፣ በሞጣ መንገድ ላይ በስሟ የሚጠራ
የገጠር ሻሂ ቤት አላት
|
ትዝ የሚለኝ አንድ ጊዜ ወደ ሰሜን ስናመራ እዚህ ምግብ ልንበላ እንወርዳለን፡፡ አራት
ሆንና አንድ ምግብ ቤት ገባን፡፡ ምግብ ቤቱ አንዲት እናት ራሳቸው ሠርተው የሚሸጡበት ዓይነት ነው፡፡ አስተናጋጇ ደግሞ ልጃቸው
ናት፡፡ አራታችን አራት ዓይነት ምግብ አዘዝን፡፡ ልጃቸው ልትነግራቸው ገባች፡፡ እኒያ እናት ወገባቸውን በመቀነት ታጥቀው
መጡ፡፡ ‹‹እናንተ ናችሁ አሁን ምግብ ያዘዛችሁት?›› አሉን፡፡ እኛም መለስን፡፡ ‹‹በሉ ልጆቼ ለአራታችሁ አራት ዓይነት ምግብ
መሥራት አልችልም፤ ተስማምታችሁ አንድ ምግብ እዘዙ›› አሉን፡፡ ስቀን አንዱን አዘዝን፡፡
ወደ ኣባያ በረሃ መውረጃ
|
መጣ ምግቡ፡፡ መቼም ጣዕሙ እስካሁን በዓይኔም በአፌም ይሄዳል፡፡ ለቤታቸው የሠሩትን
መሆን አለበት የሰጡን፡፡ ለነገሩ የአሁኑን አላውቅም እንጂ የደጀን ምግብ መልካም ነበር፡፡ በተለይ እንጀራቸው ከትሪው ይበልጥ
ነበር፡፡ በመካከሉ እንጀራው እያለ ወጡ አለቀ፡፡ አንድ ጊዜ ጨመሩልን፡፡ ግን አሁንም እንጀራው ንክች አላለም፡፡ ልጃቸውን
የወጥ ጭማሪ ጠየቅናት፡፡ እርሷም ልትነግራቸው ገባች፡፡ ወገባቸውን በመቀነት እንደታጠቁ መጡ፡፡ ጎንበስ አሉና በአምስቱ ጣታቸው
እንጀራውን እያነኮቱ፡፡ ‹‹እንዴ ይሄማ የነካካ እኮ ነው፤ ብሉ፡፡›› እያሉ ፈተፈቱት፡፡ በሳቅ ፈርሰን ምግቡን ሳንበላው
አትርፈነው ወጣን፡፡
የበላይ ዘለቀ ሐውልት (ብቸና) |
የደብረ ማርቆስን መንገድ ትተን ወደ ሞጣ መንገድ ታጠፍን፡፡ የበላይ ዘለቀን ሀገር
ብቸናን አገኘናት፡፡ በመሐል ከተማው ላይ በበላይ ስም አደባባይ ተሠርቷል፡፡ በላይም በልጅጉን እንደያዘ ምስሉ ይታያል፡፡ እነ
መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬን ያፈራውንና በፍቅር እስከ መቃብር ላይ የፊታውራሪ አሰጌንና የፊታውራሪ መሸሻን ጦርነት
ለማስቀረት ካህናቱ ከዲማ ጊዮርጊስ ጋር ይዘውት የወጡትን ብቸና ጊዮርጊስን ለማየት ከከተማው ወጣን፡፡ አንድ አምስት ኪሎ ሜትር
እንደ ተጓዝን ግን መንገዱ ለሁለት ተቆርሶ ታርሶ አገኘነው፡፡ እንዲያውም ከመካከላችን አንዱ ፊታውራሪ መሸሻ ወደ ዲማ ሄደው
የዲማ ጊዮርጊስ ቅጽር ጸጥ ብሎ ባገኙት ጊዜ ያሉትን እያስታወሰን ወደ መንገዳችን ተመለስን፡፡
የዲማ ጊዮርጊስ መገንጠያ |
የአቡነ ተከስተ ብርሃንን፣ የአቡነ ተክለ አልፋንና የአቡነ ቶማስን በኣት ዲማ
ጊዮርጊስን እያለፍን ነው፡፡ በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት (1374-1406ዓም) የተተከለው ዲማ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ
መዛሙርት አንዱ የነበሩት አቡነ ተከስተ ብርሃንና በንጉሥ ልብነ
ድንግል(1501-1533 ዓም) ዘመን የነበሩት፣ በፊትም በኋላም የማየት ሥልጣን የተሰጣቸው አቡነ ተክለ አልፋ የጸለዩበትና
ያስተማሩበት ታላቅ ገዳም ነው፡፡ አንዱ ባለ ቅኔ እንዲያውም
‹ተክለ አልፋ በሰዶምና በገሞራ ጊዜ ቢኖሩ ኖሮ አይተርፉም ነበር›› ብሎ ተቀኝቷል፡፡ ለምን ይመስላችኋል፡፡ ‹‹እስኪ
ተወያዩበት›› አለ የሦስተኛ ክፍል የአማርኛ መጽሐፍ፡፡
የደብረ ወርቅ ማርያም መግቢያ በር
|
ዲማን አልፈን ከዘመነ ኦሪት እስከ ዘመነ ወንጌል ታላላቅ ሥራዎች የተሠሩባትን ደብረ
ወርቅ ማርያምን አየናት፡፡ በደብረ ወርቅ ውስጥ ‹ወይኒቱ› የምትባለውና ቅዱስ ሉቃስ እንደሳላት የሚነገረው የእመቤታችን ሥዕል፣
ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ በድላይን ድል ካደረጉ በኋላ የማረኩት የበድላይ የብረት ልብስ፣ የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ የወርቅ ዘውድ፣ ደጉ
ዮሐንስ የሰጧቸው ስንክሳሮች፣ ዐፄ እስክንድ(1471-87) የሰጡት ባለ ሥዕል ብራና፣ በገዳሙ ታላቅ ተጋድሎ ያደረጉት የቅዱስ
አቡነ ሠርጸ ጴጥሮስ መስቀል፣ የዐፄ እስክንድር ልጅ እቴጌ ማርታ የሰጡት አርባዕቱ ወንጌል፣ ንግሥት ዘውዲቱ የሰጡት ባለ ወርቅ
ጉብጉባት ካባ፣ ራስ መኮንን የሰጡት የመጾር መስቀል እና ሌሎችም በሙዝየሙ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ዐፄ እስክንድርም የተቀበሩት እዚህ
በመሆኑ መቃብራቸው አሁንም ይታያል፡፡
ደብረ ወርቅ ማርያም
|
ደብረ ወርቅን ለቅቀን ተገነጠልንና ወሎንና ጎጃምን እንዲያገናኝ አዲስ በተሠራው
መንገድ ወደ መርጡለ ማርያም አመራን፡፡
የዐፄ እስክንድር መቃብር |
ታሪኳን ከኦሪት ጀምራ፣ ከታቦተ ጽዮን ጋር ተሣሥራ፣ በእቴጌ ሰብለ ወንጌል ታላቅ
የሕንፃ ጥበብን አስመስክራ፣ ከግራኝ የተረፈ ቅርሷን እስከ ዛሬ የምታስጎበኝ ናት መርጡለ ማርያም፡፡ የግራኝም ካባ ያለው እዚያ
ነው፡፡
መርጡለ ማርያም
|
እጅግ የገረመኝ ነገር ግን የመርጡለ ማርያምን ቅርሶች በሚገባ የያዘው ሙዝየም ሲሠራ ታላቁን አስተዋጽዖ በኅዳር 1983
ያደረጉት ባለፈው ሥርዓት የግብርና ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር ገረመው ደበሌ መሆናቸው ነው፡፡ ይህ ነገር በዚያ ዘመን
ስለነበሩት ባለ ሥልጣናትና እምነታቸው የነበረኝን ሃሳብ የሞገተ ነው፡፡ የመርጡለ ማርያምም ካህናት እስከዛሬ ስማቸውን በጠዋትና
በማታ ያነሡታል፡፡
አዳራችን ሞጣ ላይ
ሆነ፡፡
ሞጣ ቀራንዮ ምነው አይታረስ
በሬሳላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረስ
ተብሎ የተገጠመውን እያስታወስን ሞጣ ላይ አደርን፡፡ በማለዳ ከሞጣ ተነሥተን የአባያን
በረሃ ተያያዝነው፡፡
ባሕርዳር ተነሥተው ሞጣ እስከሚደርሱ
ዐሥር ወንዞች አሉ ሕዝብን የጨረሱ
ብለው ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት ነበር የሞጣ ባሕርዳር መንገድ ባለፈው መንግሥት ጊዜ
የተሠራው፡፡ መንገዱ ወይ ጥገና አይጎበኘውም ወይም ጥገና አይበቃውም፡፡ እኛ ያጠፋነው በዚህ መንገድ ላይ ስንሄድ ንስሐችንን
ጨርሰን አለመምጣታችን ነው፡፡ ባሕርዳር የደረስነው በስግደትና አስተብርኮ ነው፡፡ የብዙ ሊቃውንት ማፍሪያ የሆነውን አዴት
መድኃኔዓለምን ተሳልመን በደብረ መዊዕ በኩል ገሠገሥን፡፡
ደብረ መዊዕ ማርያም የተተከለችው በ16ኛው መክዘ ነው፡፡ ንጉሥ ሱስንዮስ ወደ ካቶሊክ
እምነት በገቡ ጊዜ በደብረ መዊዕ ታላቅ የሊቃውንት ጉባኤ ተደርጎ ነበር፡፡ እነ አባ ተስፋ ኢየሱስ፣ እነ አባ ዘጊዮርጊስ
ዘዋሸራ፣ እነ አባ እንጦንስ፣ እነ አባ ግርማ ሥሉስ ዘውይት በጉባኤው ላይ ተገኝተው ነበር፡፡ ጉባኤው በመምህር አካለ ክርስቶስ
እየተመራ ስለ ተዋሕዶ እምነት ጥልቅ ውይይት አደረገ፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ መሆናቸውን የሰማው የሱስንዮስ ጦር በድንገት መጣና
ከበባቸው፡፡ ጥቅምት 19 ቀን 1621 ዓም 7000 ካህናትንና ምእመናንን ፈጃቸው፡፡
ደብረ መዊዕ ማለት የማሸነፊያ ቦታ፣ ተራራ ማለት ነው፡፡
አለፍን ወደ ባሕርዳር ከተማ፡፡ እኛ ከተማ ስንደረስ የብሔር ብሔረሰቦች በዓልን
ለማስተናገድ ሸብ ረብ እያለች ነበርና ሞቅታ ላይ ነበረች፡፡ እኛም ከቅዳሜ ገበያ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚወስደው መንገድ በኩል
አድርገን ወደ ምክር ቤቱ አቅጣጫ ተጓዝን፡፡ ባሕርዳር ጊዮርጊስ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በጎንደር ዘመን የመጡ
ሚሲዮናውያን ያርፉባቸው ከነበሩ ቦታዎች አንዱ ዛሬ የባሕርዳር ጊዮርጊስ የተተከለበት ቦታ ነው፡፡ ፖርቹጋሎቹ የሠሩት ሕንጻ
ዛሬም ለደብሩ የዕቃ ቤት ሆኖ እያገለገለ ነው፡፡
ባሕርዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ
|
ከተማዋን በዓባይ ድልድይ በኩል አልፈናት ወጣን፡፡ ዓባይን ለሁለተኛ ጊዜ ማቋረጣችን
ነው፡፡ በፎገራ ሜዳ በኩል ስናልፍ ታላቁ ሊቅና ቀልደኛ አለቃ ገብረ ሐናን አስታወስን፡፡ ሀገራቸው ናባጋ ጊዮርጊስ በስተግራችን
በኩል ነው፡፡ የተሾሙበትን የአቡነ ሐራን ገዳም ደግሞ በስተ ቀኝ በኩል አልፈነዋል፡፡ አለቃ ተከስሰው ወደ ዐፄ ምኒሊክ ችሎት
የመጡት የአቡነ ሐራን ገዳም እህልና ገንዘብ ለገበሬ በመስጠታቸው ነበር፡፡ በዘመናቸው ድርቅ መጣና ገበሬዎቹ ቢቸገሩ አለቃ
የገዳሙን ገንዘብ አውጥተው አደሏቸው፡፡ በዚህም ካህናቱ ከስሰዋቸው አዲስ አበባ መጡ፡፡ በዚያውም እንጦጦ ራጉኤልን ለመሾም
በቁ፡፡
አዲስ ዘመን ላይ ስንደርስ ወደ ደብረ ታቦር ተገነጠልን፡፡ አስፓልቱ እንደ ኑግ
የተለጠለጠ ነው፡፡ ሽር ብትን ማለት ብቻ ነው፡፡ የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ አፈ መምህር ገብረ ሥላሴና
የሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎች ክርስቲያናዊና ወንድማዊ የሆነ አቀባበል ነበር ያደረጉልን፡፡ የጎንደሩ ሙሉቀን አስቀድሞ ደብረ ታቦር
ደርሶ ነበር፡፡ አፈ መምህር ገብረ ሥላሴ አስፈላጊውን የትብብር ደብዳቤ አዘጋጅተው፣ በሚያስፈልግ ሁሉ ለመተባበር ስልካቸውን
ሰጥተው ነበር የሸኙን፡፡
አሁን ጉዟችን
እኔ እየተከተልኩ እሷ እየመራችኝ
ስማዳ ስማዳ ስማዳ አገባችኝ
ወደ ተባለላት ስማዳ ነው፡፡ መልካም መንገድ፡፡
ማን ያውቃል ይህ ሁሉ ድካማቸሁ በሚቀጥለው ጉዞ ቦታው በአጭሩ እንዲገኝ ስንቅ ይሆናችሁ ይሆናል በርቱ እኛም በሀሳብ ስማዳ ደርሰናል ድንግል ትከተላችሁ በጣም እድለኞች ናችሁ እግዚአብሔር እኛንም ይህን የበረከተ ቦታ ለማየት ያብቃን አሜን
ReplyDeleteye-vegasu
ReplyDeleteDanie it feels like i am traveling with you,can't wait to travel again,what a great man u are.
ቃለ ህይወት ያሰማልን ወንድማችን ዳ.ዳንኤል....እግዚብሄር ከናተ ጋር ይሁን።እከመጨረሻዉ በናት ቤተክርስቲን ጉያ ያኑርህ...መጽናኛችን ነህ....
ReplyDelete‹‹በሉ ልጆቼ ለአራታችሁ አራት ዓይነት ምግብ መሥራት አልችልም፤ ተስማምታችሁ አንድ ምግብ እዘዙ›› አሉን፡፡ ስቀን አንዱን አዘዝን፡፡
ReplyDelete‹‹እንዴ ይሄማ የነካካ እኮ ነው፤ ብሉ፡፡›› እያሉ ፈተፈቱት፡፡
amaze yea men..... nigus from south gonder.
Deleteዳኒ ጥበቡ የማያልቅበት ልዑል እግዚአብሔር ደግሞ ደጋግሞ ጥበብንና ማስተዋልን ኃይልንና ዕውቀትን ያድልህ!
ReplyDelete"ተክለ አልፋ በሰዶምና በገሞራ ጊዜ ቢኖሩ ኖሮ አይተርፉም ነበር" ብሎ ተቀኝቷል፡፡ ለምን ይመስላችኋል?
መልስ፡-ወደ ኋላ ማየት ክልክል ስለሆነ!
Dani...Thank you for sharing this insight... interesting and informative.
ReplyDeleteMay the good Lord bless you and keep you always in His care, on this journey and continue annointing you.
Amen
ዳኒ ጥበቡ የማያልቅበት ልዑል እግዚአብሔር ደግሞ ደጋግሞ ጥበብንና ማስተዋልን ኃይልንና ዕውቀትን ያድልህ!
ReplyDelete"ተክለ አልፋ በሰዶምና በገሞራ ጊዜ ቢኖሩ ኖሮ አይተርፉም ነበር" ብሎ ተቀኝቷል፡፡ ለምን ይመስላችኋል?
መልስ፡-ወደ ኋላ ማየት ክልክል ስለሆነ!
You should have mentioned that Bahir Dar Giorgis had a historicl contribution for your spritual progress. As you were the one who passesd through the well known sunday school in the country- St. Giorgis sunday school.
ReplyDeleteIn any case your script is good and please keep working on this. Thanks
beselam temelesu
ReplyDeleteዲ. ዳንኤል ቃለህይወት ያሰማልን
ReplyDeleteከዋናው የጉዞህ ዓላማ በተጨማሪ በእግረ መንገድህ የምታስተዋውቀን መንፈሳዊና ታሪካዊ ቦታዎች እጅግ ደስ የሚል ነው፤
"... ከቅዳሜ ገበያ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ.. " ቅዳሜ ገባያ የጎንደር ሲሆን የባህርዳሩ ጣና ገባያ ነው፡፡
No..አሁን ይሆናል ጣና ገበያ የተባለ፣ ዱሮ ግን ቅዳሜ ገበያ ነበር የሚባል፡፡
DeleteGreat!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteDanie it feels like i am traveling with you,can't wait to travel again,what a great man u are.
ReplyDeleteአይይ..... በቃ አኔም አዳሬን ስማዳ ላድርገዋ። እኔስ ብንቀጥል ደስ ባለኝ ነበር ያለ እናንተ አይሆንልኝምና ካደራችሁ ልደር። ታድያ ነገ በጠዋት እሺ!
ReplyDeleteegziabhare tsegawen abzito abzito abzito yisteh!!!!! abune filposen sitsalem egnanem betselotih asiben.
ReplyDeleteDn dani eg/r yebarkhe edemena tsgawen yabezalhe.
ReplyDeleteአይይ..... በቃ አኔም አዳሬን ስማዳ ላድርገዋ። እኔስ ብንቀጥል ደስ ባለኝ ነበር ያለ እናንተ አይሆንልኝምና ካደራችሁ ልደር። ታድያ ነገ በጠዋት እሺ!
ReplyDeleteዲ. ዳንኤል !!!!!
ReplyDeleteቃለህይወት ያሰማልን::
ጥበቡ የማያልቅበት ልዑል እግዚአብሔር ደግሞ ደጋግሞ ጥበብንና ማስተዋልን ኃይልንና ዕውቀትን ያድልህ,
እግረ መንገድህን የምታስተዋውቀን መንፈሳዊና ታሪካዊ ቦታዎች እጅግ ደስ የሚሉ ናችው::
May God with you guys!
ReplyDeleteu are a real Ethiopian historical researcher than those immoral professors that says 'keshefe..' for their purpose.
ReplyDeletepls present in book version ur tour for details
good ....berta
kale hiwot yasemalen
ReplyDeleteዳኒ አብረናችሁ እየተጓዝን ነው ግን ምነዋ በዛ እንደ ኑግ በተለጠለጠው አስፋለት ላይ ስንከንፍ አውራምባዎችን ረሳናቸው…. ለሁሉም ፈጣሪ ይርዳቹ፡፡
ReplyDeleteBereketachw yidresen
ReplyDeleteEgziabher Yibarkih gin you need to finish the story. Lib manteltel tiru aydelem
ReplyDeleteYe`Ethiopia Tarik alkeshefem!
ReplyDeleteWhy didn`t you visit Motta Giorgis,Yene`Arat Ayina Goshu Hager?
ReplyDeleteSiteguazu Teguzen Setarfu Arfen Yehew Semada Dersenal Betam Lib Anteltai New MEDEHANIALEM Yemayalikewin Tsgawin Ahunim Yabizalih Kale Hiwoten Yasemalim Danii
ReplyDeletewondimachin Diaqon Danel.. libihin emimeremir egziabher lezih hulu lifatih ena dikamih belikih yisTih. lezerih memekiya yarigih. Amen.
ReplyDeleteዲን ዳንኤል በቅድሚያ የከበረ ሰላምየ ይድረስህ አቡነ ፊልጶስን ፍለጋ በሚል በጀመርከው
ReplyDeleteአቢይ ጉዳይ እኛም በዚያው እግረ መንገድ ብዙ የማናውቃቸውን ቅዱሳት መካናትን እያስጎበኘኸን በመሆኑ
የጻድቁ አቡነ ፊልጶስ በረከት እስከመላ ቤተሰብህ ይጠብቅህ ድካምህን ይቁጠርልህ ሌላው በጉዞህ የጎበኘሀቸውን ገዳማትና አድባራት
እራሳቸውን አስችለህ በታሪካቸው ብትመለስባቸው እና እኛም የማናውቃቸውን ትላላቅ ቦታዎች ብናውቃቸው በጣም ጥሩ ነው በተረፈ ድካምህን ይባርክ
Dani ye Debretabor megenteya addis Zemen hone endie?
ReplyDeletewaye Dani yemawkewn ena yersahutn negwr slastawskegne betam amesegnihalehu!!! please you just write again the detail about M/mariam!!
ReplyDeleteegzihabere yistelen
ReplyDeleteእንኳንም ቶሎ አላገኛችሁት እግረ መንገዱን ብዙ ቦታዎችን እና ታሪኮችን እንድናውቅ አደረጋችሁን፡፡ እግዚያብሄር የነፍስ ዋጋ ያድርግላችሁ፡፡
ReplyDeletemeche endalekebegn salakewu zeme beye bemenabeme behasabem botawochun eyesalku yemawuqawun eyastawasku seketelachehu neber egzihabeher yiketelachewu "enes ehedalew gara garawune 2x enes ehedalawu chaka chakawune 2x agegnew endehon aba fileposene."
ReplyDelete...አዲስ ዘመን ላይ ስንደርስ ወደ ደብረ ታቦር ተገነጠልን...the way to Debre Tabor is from Woreta not from Addis Zemen.
DeleteMay God bless you for all things you are feeding us.
በፊትም በኋላም የማየት ሥልጣን የተሰጣቸው አቡነ ተክለ አልፋ lezih new kehwalam mayet seltan seltsTacwe be sodomna gomora gizem ayterfum neber yetbalew
ReplyDeleteWELADIT AMLAK ASKEDMN SELAM EGZIABHER YESEFENBET GUZO TGUZENAL ... ENGANM KANT EYETGOZN NEW... GEN YEMGERMEW BE YE MENGEDU YEMTANESACHEW TARIKOCH DES BONGAL
ReplyDeleteይሕንኑ ዳኔ ነው የማውቀው፤ እግዝአብሔር ሞልቶ ይስጥልኝ፣በብእርህ እያዋዛህ ስታስተምረን እኛም ከማንበብ ባሻገር ደብሩን ገዳሙን ለመሳለም ያበቃን ዘንድ የድንግል ልጅ እንለምናለን።ባሕር ማዶ ላለን እንደኔ እምነት እንዲህ አይነቱ ጵሑፍሕ አስተማሪ ብቻ ሳይሆን ፈዋሽም ነው።
ReplyDeleteበርታ የድንግል ልጅ አይለይህ።
ደብረ መዊዕ ማለት የማሸነፊያ ቦታ፣ ተራራ ማለት ነው፡፡
ReplyDeleteለኔ አዲስ መረጃዎች፦
ReplyDelete1,በደብረ ወርቅ ውስጥ ‹ወይኒቱ› የምትባለውና ቅዱስ ሉቃስ እንደሳላት የሚነገረው የእመቤታችን ሥዕል
2,እጅግ የገረመኝ ነገር ግን የመርጡለ ማርያምን ቅርሶች በሚገባ
ጉባኤው በመምህር አካለ ክርስቶስ እየተመራ ስለ ተዋሕዶ እምነት ጥልቅ ውይይት አደረገ፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ መሆናቸውን የሰማው የሱስንዮስ ጦር በድንገት መጣና ከበባቸው፡፡ ጥቅምት 19 ቀን 1621 ዓም 7000 ካህናትንና ምእመናንን ፈጃቸው፡
3,ታላቁ ሊቅና ቀልደኛ አለቃ ገብረ ሐናን አስታወስን፡፡ ሀገራቸው ናባጋ ጊዮርጊስ በስተግራችን በኩል ነው፡፡ የተሾሙበትን የአቡነ ሐራን ገዳም ደግሞ በስተ ቀኝ በኩል አልፈነዋል፡፡ አለቃ ተከስሰው ወደ ዐፄ ምኒሊክ ችሎት የመጡት የአቡነ ሐራን ገዳም እህልና ገንዘብ ለገበሬ በመስጠታቸው ነበር፡፡ በዘመናቸው ድርቅ መጣና ገበሬዎቹ ቢቸገሩ አለቃ የገዳሙን ገንዘብ አውጥተው አደሏቸው፡፡ በዚህም ካህናቱ ከስሰዋቸው አዲስ አበባ መጡ፡፡ በዚያውም እንጦጦ ራጉኤልን ለመሾም በቁ፡፡
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
Abree teguazikugn!!!
ReplyDeletedanie, when i readit i feel travelled with you. do not wait until the great man we gate or we meat with him.
ReplyDeleteD/N dikamachihun Egziabhier amlak beselam yasfetsmilachihu amen
ReplyDeleteam travelling with u. nigus from south gonder
ReplyDeletedani btam teru temeret new bezu abatoch lebetekeresetiyane tegadelo yaderegu alu betenatel tarikachewen agineteh metsehaf betazegagelen lehagerem leteweledem teru new
ReplyDeleteWhy you sielent about the current issues, election of patriarch and peace issues
ReplyDelete