Friday, February 1, 2013

ይድረስ ለቅድስት ድንግል ማርያም (የመጨረሻ ክፍል)ድንግል ማርያም ሆይ
ይህ የመጨረሻዬ ደብዳቤ ነው፡፤
አንዳንድ ወዳጆቼ አሁን እንዲህ ያለው ነገር ለድንግል ማርያም ይጻፋል? አሉኝ፡፡ እኔ ደግሞ እንዲህ ያለው ነገር ለርሷ ያልተጻፈ ለማን ይጻፋል አልኳቸው፡፡ እናቶቻችን የጭንቅ አማላጇ የሚሏትኮ ጭንቅን እርሷም ስላየችው ነው፡፡ ማደርያ አጥቶ መንከራተትን አይታዋለች፡፡ ልጇም ቢሆን ‹‹ለቀበሮዎች ዋሻ ለወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም›› ብሎ ተናግሯል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ አሁን የቤት ጉዳይ ይህንን ያህል ደርሶ ነው ለእርሷ አቤት የምትለው? አሉኝ፡፡ ‹‹በግ የሌለው ሰው ቀበሮ አውሬ አትመስለውም›› አለ የሀገሬ ሰው፡፡
‹ምነው ቤት አትገዛም?› ትይኝ ይሆናል፡፡ ላደለውማ ቤት መግዛትን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ቢያንስ ልጆቼን የሚቆጣቸው ብቻ ሳይሆን በየቀኑ የሚቆጥራቸው አይኖርም፡፡ በዚህ ሰዓት ግባ፣ በዚህ ሰዓት ውጣ የሚለኝ አይኖርም፡፡ ግንኮ የኛ ሀገር ቤት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጨዋች ሆነብን፡፡ እኛ በልጆቻችን ስም ብቻ የምናውቀውን ‹ሚሊዮን› ዋጋ አድርጎ የሚጠራ ቢኖር ቤት ሻጭ ብቻ ነው፡፡ 
የሌላው ሀገር ሰው በሚሊዮን ቀርቶ በቢሊዮን ቤት ቢገዛ ከባንክ ተበድሮ ነው፡፡ ዕድሜ እስካለው ያቅሙን እየከፈለ ይኖርበታል፡፡ በኋላ ደግሞ ወይ ዕዳው ያልቃል ወይ ዕድሜው ያልቃል፡፡ እኛጋኮ ‹‹ሚሊዮኗን ቆጥራችሁ አምጧት›› ነው፡፡ እንዴት ሚሊዮን ይቆጠራል? ለመሆኑ ስንት ዓመት ተጠራቅሞ ነው ሚሊዮን የሚቆጠረው፡፡ ትናንትና ከተማዋን ይገዛ የነበረ ብር ዛሬኮ ከተማ ገብቶ ለማደርያም አልሆን እያለ ነው፡፡ ‹ቀን የጎደለበትን ጠገራ አይጥ ይበላዋል›› አለ አበሻ፡፡ ትናንትና የአራተኛ ክፍል ማለፊያና መውደቂያ ቁጥር የነበረው ‹አርባ ስልሳ› ይኼው ዛሬ የቤት ማግኛ ቁጥር ሆነ፡፡ የታደለ ቁጥር፡፡  
እነዚህ የድሮ ዘመን ልጆች
ባልንጀሮቼ ቁሙ በተራ
እንጨት ሰብሬ ቤት እስክሠራ
እንኳን ቤትና የለኝም አጥር
እደጅ አድራለሁ ኮከብ ስቆጥር
ያሉት ነገር ዘፈን ነው? ትንቢት?
የሀገሬ ሰው ሲያንጎራጉር ‹አልበር እንዳሞራ ሰው አርጎ ፈጥሮኛል› ይላል፡፡ አሁንማኮ ሰውና አሞራ አንድ ሆኗል፡፡ ሰውም በቤት መወደድ ምክንያት ማደርያ አጥቶ ይዞራል፡፡ አሞራም ይኼው ዛፉ ሁሉ ተቆርጦ አልቆበት ጎጆ የሚሠራበት አጥቶ ይዞራል፡፡
አሁን እስኪ ከመሐል አራት ኪሎ ተነሥተን የአዲስ አበባ ጥግ ስንገባ ምን እንደምንመስል አስቢው፡፡ መቼም ሀገር አይደግ፣ ሀገር አይልማ አይባልም፡፡ ነገር ግን አሮጌ ከተማን ማፍረስና አሮጊትን ወጣት ማድረግ ከባድ ነው፡፡ ለዚህኮ ነው ብዙ ሀገሮች የጥንቱን ከተማ ከማፈራረስ ብለው ሌላ አዲስ ከተማ የሚገነቡት፡፡ እኛስ ሀገር ምናለ አዲስ ከተማ ብንገነባ፡፡ ስንቱን አፍርሰን እንዘልቀዋለን፡፡  
አራት ኪሎኮ ለኛ መኖርያ ብቻ አልነበረም፡፡ የ50 ሳንቲም ድንች፣ የስሙኒ ሽንኩርት፤ የ10 ሳንቲም ዘይት፣ የአርባ ሳንቲም እንጀራ ገዝተን የምንጠግብበት ጎተራችንም ነበር፡፡ አራት ኪሎ ላይ ተሸክሞም፣ ጫማ ጠርጎም፣ ተበድሮም ገንዘብ ማግኘት ይቻላል፡፡ አሁን እዚህ የከተማው ጥግ በድኽነት ዐቅም የሀብታም ሠፈር ገብተን፣ እንኳን በስሙኒ በሃያ አምስት ብር ምግብ ማግኘት አልቻልንም፡፡ ያ የመቶ ዓመት ዕድራችንም ፈረሰ፡፡ እዚህ ደግሞ ሁሉ ባለ ፉካ ነው፡፡ እንኳን ዕድር ሳይኖረን የሞትን ዋጋ በዕድርም አልቻልነው፡፡
ይኼው በቀደም ዕለት እዚህ ሠፈር አንድ ሀብታም ሞቶ ልቅሶ ብንሄድ ለካስ የሠፈሩ ዕድር እንደ አራት ኪሎ ዕድር አይደለም፡፡ ቢራ በየዓይነቱ፣ ክትፎ በየመልኩ፣ አትክልት በየ ስሙ፣ ዳቦ በየጋጋሪው፣ እንጀራ በየጠባዩ ተደርድሮ ቡፌ ስናነሳ ነበር፡፡ ድግሱ ድንኳን ውስጥ ባይሆን፣ የሟቹ ፎቶ ተሰቅሎ ባናየው፣ ቤተሰቡም ጥቁር ባይለብስ ኖሮ ባልተጠራንበት ሠርግ በከተፋ የገባን ይመስለን ነበር፡፡
አበሻ ሲተርክ ‹ዓባይ ማደርያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል› ይላል፡፡ ‹ይህንንስ ስለማን ተናግሮታል ቢሉ› አሉ ሊቃውንቱ ‹አንድም ስለ ራሱ ተናግሮታል› ይላሉ፡፡ ‹እንደምን ነው ቢሉ ብዙ የከተማ ሰው ቤት የለውምና፡፡ ግንድስ ያለው ማንን ነው ቢሉ የቤት ዕቃውን፡፡ ይህስ እንደምን ነው ቢሉ፡፡ ዓባይ ግንዱን ከዛፉ ገንድሶ ከየትም እንዲያመጣው፣ ቤት የሌለው የከተማ ሰውም የቤት ዕቃውን ከየትም ይሰበስባልና፡፡ አንድም ዓባይ ማደርያውን ሳያውቅ ግንዱን ይዞ እንደሚዞረው፡፡ ተከራይም የቤቱን መጠንና ልክ ሳያውቅ ዕቃ እየገዛ ይዞ ሲዞር ይኖራልና›› ብለው ይተነትኑታል፡፡
እንዴው ችግሩን ሲዘረዝሩት ቢኖሩ አያልቅም፡፡ ‹‹ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም›› ይባላልና፡፡ ይልቅ መተሳሰብ፣ መረዳዳትና መገናዘብን እንዲሰጠን ለምኝልን፡፡ አከራይና ተከራይ፣ ሻጭና ገዥ ሁሉም የአንድ ሀገር ዜጎች ናቸውና ምናለ ቢተሳሰቡ፡፡ ተስፋ የቆረጠ ጎረቤት ያለው ሰው በጤና ውሎ መግባት አይችልም፡፡ ሰው ጨዋ የሚሆነው ተስፋ ሲኖረው ነው፡፡ የርሱ ጣራ ወደ ታች እየሄደ የጎረቤቱ ፎቅ እንደ ሸንበቆ ሲያድግ ሰው ተስፋ ይቆርጣል፡፡ ያን ጊዜ ደግሞ በጎረቤቶቻችን ሀገሮች እንደምናየው አርዶና ዘርፎ የሚበላ መንጋ እናፈራለን፡፡
እንደው መቼም የአሥራት ሀገርሽ ስለሆነችም እንደሁ እንጃ የኛ ሀገር ሌባኮ አልፎ አልፎ ሰይጣን ሲጣጋው ካልሆነ በቀር በጎረቤቶቻችን እንደምንሰማቸው ያሉ አሰቃቂ ወንጀሎችን አይፈጽምም፡፡ አንዳንድ ሀገርኮ ከነዋሪው ይልቅ ሌባው የተሻለ ነጻነት አለው፡፡ ባለ ድርጅቱና ባለ ቤቱ ሁሉ አምስት ስድስት በር ሠርቶ፣ በሩን በብረት ጠርቅሞ፣ በአራት ቁልፍ ዘግቶ፣ ያም አልበቃው ብሎ ካሜራና ሽቦ አጥሮ እንኳን፣ ግድያና ዝርፊያ አይቀርለትም፡፡ እዚያ ሀገርኮ ዜና የሚሆነው ‹‹ሌባው ሳይገድል ሰረቀ›› ተብሎ ነው፡፡ እኛ ሀገር ግን መግደሉ ነው ዜናው፡፡
ሰው እንደ ዐቅሙ ከመደብ እስከ ቪላ ቤት፣ ከጆንያ እስከ ብርድ ልብስ ካለው ቢያዝንም ሆድ አይብሰውም፤ ቢቸገርም ዐቅሉን አያስተውም፡፡ ይኼ የተሰነጠቀ ዱላ የያዘ ጥበቃ በሚንጎራደድበት ወርቅ ቤት በር ላይ ተቀምጦ የሚለምነውኮ ጨዋነት ይዞት እንጂ መስረቅ አቅቶት አይደለም፡፡ ታድያ ይኼ ሰው ተስፋ እንዳይቆርጥ ነው መስጋት፡፡
ቤታችንን ስናከራየው፣ በሚችለው ዋጋ ስንሸጥለት ንግድ ብቻ አይደለም፡፡ ለራስ የሚከፈል ዋጋም ጭምር ነው፡፡ ሌባና ቀማኛ፣ ማጅራት መችና ኪስ አውላቂ፣ እኅቶቻችንን ደፋሪና ልጆቻችን አማራሪ እንዳይበረክት እያደረግንም ጭምር ነው፡፡ እነዚህ እኛ ግቢ የሚያድጉ ልጆች ናቸው የነገዎቹ የሀገሪቱ መሪዎች፡፡ እየተማረሩና ጥላቻን እየሰነቁ ካደጉ፣ ነገ የሚያወጡት ፖሊሲ ለሁላችንም አይበጅም፡፡ ገንዘብ ያለውን ሰው እንደ ጨካኝና ቀማኛ፣ ስግብግብና አጥፊ እያዩት ካደጉ በቀል ያረግዛሉ፡፡ ቤታቸውን ያስፈረሰባቸው፣ ከቀያቸው የነቀላቸው፣ ከከተማ ጥግ የወሰዳቸው ያ ባለጠጋ ለእነርሱ የአባታቸው ገዳይ መስሎ ይታያቸዋል፡፡
በዓለም ላይ አምባገነንና ጨፍጫፊ ሆነው ብቅ ያሉ መሪዎች የኋላ ታሪክ ሲታይ በልጅነታቸው ወቅት የደረሰባቸው ነገር በጎ አልነበረም፡፡ ሂትለር ምንም እንኳን ለፈጸመው ጭካኔ የሚበቃ ምክንያት ባይኖረው በልጅነቱ በመንደሩ ከነበሩ አራጣ አበዳሪዎችና ባዕለ ጠጎች በቤተሰቡ ላይ ይደርስ የነበረው ግፍና ጭቆና በለጋነት ስሜቱ ላይ ያሳደረው በቀል ግን ቀላል አልነበረም፡፡
እንዲህ ያለው መተሳሰብ እንዲኖር ደግሞ መንግሥት ቤት ሠርቶና በዕጣ አከፋፍሎ አይዘልቀውም፡፡ ባለ ሀብቱም የሚከራይ ቤት እንዲሠራ መደረግ አለበት፡፡ የኪራይ ቤት ዓይነቶች ደረጃ ወጥቶላቸው መንግሥትም በርካሽ ዋጋ መሬት ሰጥቷቸው እንዲሠሩ መደረግ አለበት፡፡ የኪራዩ ተመን ግን በመንግሥትና በአከራዩ በጋራ ሊተመን ይገባል፡፡ ይኼው አሥር ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት ካይሮ የቤትን ተመን አከራይ ብቻውን አያወጣውም፡፡ የተከራየውንም እንደፈለገ ውጣ ማለትም አይችልም፡፡ የኪራዩ ተመን በመንግሥትና በአከራዩ በጋራ ነው የሚወጣው፡፡ መንግሥት የሕዝቡ ወኪል በመሆኑ ተከራዩን ወክሎ ለሕዝቡ የሚበጀውን፣ አከራዩንም የማይጎዳውን ዋጋ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ እንዲህ ሲሆን ሕዝብ ተስማምቶ ይኖራል፡፡
ደግሞም ለሚከራይ ቤት ደረጃም ይውጣለት፡፡ አሁን ሃያ ቤት ለሚያከራይ ግቢ አንዲት የመጸዳጃ ቤት ቀዳዳ በቂ ናት? በተለይ ጠዋትና ማታኮ በአንዳንድ ግቢ የሚታይ የመጸዳጃ ቤት ወረፋ የስኳር ወረፋ ነው የሚመስለው፡፡
አሁን አሁን ሰው ሰፊ ግቢውን ጥግ አስይዞ የሚከራዩ ክፍሎች መሥራት ለምዷል፡፡ ኮንዶሚኒየሙም ቢሆን ጉርብትናን ከአጥር ወደ ግድግዳ አምጥቶታል፡፡ ለመሆኑ ግን የጉርብትና ሕግ አለ እንዴ በሀገራችን፡፡ ለመሆኑ አንድ ሰው ሊጠቀም የሚችለው የድምጽ መጠን ምን ያህል ነው? ከፍተኛ ድምጾችን እስከ ስንት ሰዓት ነው ሊጠቀም የሚችለው? በዚህኛው በኩል ሚስማር ሲመታ በዚያኛው በኩል የተሰቀለ ሰዓት አመድ እንዳይሆን ምን ሕግ ይጠብቀዋል?
አኛ በአብዛኛው የለመድነው በአጥር ተለያይቶ መኖር ነውና ለግድግዳ ጉርብትና ባሕልም ሕግም ያለን አይመስለኝም፡፡ አሁን ግን የአፓርትማና የኮንዶሚኒየም ሰዎች ከሆንን ላይቀር ባሕሉም ሕጉም ሊኖረን የግድ ነው፡፡ አሁን አንዳንድ ኮንዶሚኒየም በረንዳ ላይ ያልተቀመጠ ነገር የለምኮ፡፡ ከሰሉ፣ ማንደጃው፣ ዱካው፣ ባልዲው፣ መጥረጊያና መወልወያው፤ የልጆቹ መጨዋቻ፤ በዚሁ ከቀጠለኮ መጀመርያ በላስቲክ፣ ቀጥሎም በላሜራ ማጠር ይመጣል፡፡
ኧረ ምን እርሱ ብቻ፤ እንዴው ለመሆኑ እያንዳንዱ የኮንዶሚኒየም ወይም የአፓርትማ ነዋሪ የሱሉልታ የሳተላይት መቀበያ ጣቢያን የሚያህል ዲሽ መትከል አለበት? ለሁሉም የሚሆን አንድ ዲሽ መትከል፣ ያም ካልሆነ ደግሞ ውበትንም ቦታንም ሳያበላሽ የሚተከል የዲሽ መጠን ሊኖር አይገባም? ይኼንን በማዳበርያ ያደገ እንጉዳይ መስሎ የበቀለውን ዲሽ ማስቀረት የሚቻልበት መንገድ የለም እንዴ?
ለመሆኑ በጋራ መኖርያ ቦታዎች ላይ የሚቋቋሙ የንግድ ድርጅቶች ምን ዓይነት መሆን አለባቸው? አንድ ሰው ቤቱን ለፈለገው ሁሉ ማከራየት ይችላል እንዴ? ቤት ማለት ግድግዳና ጣርያው ብቻ አይደለምኮ፤ ሠፈሩም ነው፤ አንድ ሰው ቤቱን የሚከራየው ሠፈሩንም ፈልጎ ነው፡፡ የዚያን ሠፈር መልክዕ የተወሰኑ ግለሰቦች በፈለጉት መንገድ መለወጥ ከቻሉ ለመኖርያ ቤት የተከራየው ወይም የገዛው ሰው የቀለጠው መንደር ውስጥ ሊገባ ነውኮ፡፡
ይኼ የቤት ጉዳይ መቼም ማለቂያ የለውም፡፡ እስኪ ለአከራዩና ለተከራዩ አንጀት፣ ለመንግሥትም ልቡና፣ ለመሐንዲሱም ጥበብ፣ ለሕግ አስከባሪውም ጥብዐት፣ ለደላላውም አእምሮ፣ ለባለ ገንዘቡም ኅሊና ስጭውና ተሳስበን እንድንኖር አድርጊን፡፡
ሰላም ለኪ፡፡


©ይህ ጽሑፍ በሳምንታዊው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ በመሆኑ በሌላ ፕሬስ ላይ ማውጣት ክልክል ነው54 comments:

 1. የኔ ስጋ እደ ሰጋ
  ስንት መአልት አልፎ ስንት ሌሊት ነጋ

  ReplyDelete
 2. ኧረ ምን እርሱ ብቻ፤ እንዴው ለመሆኑ እያንዳንዱ የኮንዶሚኒየም ወይም የአፓርትማ ነዋሪ የሱሉልታ የሳተላይት መቀበያ ጣቢያን የሚያህል ዲሽ መትከል አለበት? ለሁሉም የሚሆን አንድ ዲሽ መትከል፣ ያም ካልሆነ ደግሞ ውበትንም ቦታንም ሳያበላሽ የሚተከል የዲሽ መጠን ሊኖር አይገባም? ይኼንን በማዳበርያ ያደገ እንጉዳይ መስሎ የበቀለውን ዲሽ ማስቀረት የሚቻልበት መንገድ የለም እንዴ?

  ReplyDelete
 3. የኔ ስጋ እንደሰጋ
  ስንት መአልት አልፎ ስንት ሌሊት ነጋ

  ReplyDelete
 4. እንዲህ ያለው መተሳሰብ እንዲኖር ደግሞ መንግሥት ቤት ሠርቶና በዕጣ አከፋፍሎ አይዘልቀውም፡፡ ባለ ሀብቱም የሚከራይ ቤት እንዲሠራ መደረግ አለበት፡፡ የኪራይ ቤት ዓይነቶች ደረጃ ወጥቶላቸው መንግሥትም በርካሽ ዋጋ መሬት ሰጥቷቸው እንዲሠሩ መደረግ አለበት፡፡ የኪራዩ ተመን ግን በመንግሥትና በአከራዩ በጋራ ሊተመን ይገባል፡፡

  Always nice observation. Thanks Dani

  ReplyDelete
 5. dani...for me your letters, for the holy mariam,are not touchable. why? I don't know or I can't express my feeling.
  tsuhufi gilb hunobignal..joroyen yaz adirgognal..any ways God bless you!

  ReplyDelete
  Replies
  1. @ Anonymous It is not a fiction it’s going to touchable; it’s reality. If you are a victim one of renting house’s you will not addressed the above message. Well like I said “Betegab west yale rehaben ayawekem”

   Delete
 6. "............እያንዳንዱ የኮንዶሚኒየም ወይም የአፓርትማ ነዋሪ የሱሉልታ የሳተላይት መቀበያ ጣቢያን የሚያህል ዲሽ መትከል........" Safi tintena yifeligal/ Andi tilik gudy new dani

  ReplyDelete
 7. ዲያቆን ዳንኤል፣ እንዴት የተባረከ ጽሑፍ ነው ያቀረብክልን። ተባረክ።

  እኔም እስቲ ለድንግል ማርያም ጸሎቴን ላቅርብ፡

  ድንግል ሆይ፣ ሳያምኑሽ ለሚለምኑሽ ይቅርታን ከልጅሽ አስገኝላቸው። ፓለቲካ አምላካቸው፣ ዘራቸው ጣኦታቸው፣ ክደታቸው ክብራቸው ለሆኑት ሁሉ ይቅርታና ምህርተን ስጫቸው። አንድ ሰውን አንድ ጊዜ ማታለል ይቻል ይሆናል፣ ሚሊዮን ህዝባን ሚሊዮን ጊዜ ለማታለል ከሚማስኑ ጅሎች አውጭን።

  እስከወዲያኛው፣ አሜን!

  ReplyDelete
 8. ዲያቆን ዳንኤል ይሄ የሁላችንም ፀሎት መሆን አለበት እመብርን ለቤት አከራዮች የሚያስተውሉበት ልቦና ትስጣቸዉ።

  ReplyDelete
 9. In what kind of evaluation , Daniel is "yemayawuk"? enih yesim professor. Let he read this blog, he will believe that he,himself is less knowledgable than Daniel. Man alebign bay professor, Thanks God, he didn't get the opportunity to lead Ethiopia. I think he is more cruel than Mengistu & Meles.

  Woyyyyyyyyyyy sew alemawok, endelbachew tenageru. I think Daniel will keep silent, since he already said what to say & he is a better person than he is.

  ReplyDelete
 10. I really agree with your points. When are we going to stop removing houses to construct a new building or road while we can build even a city? We have to consider how much we hurt the society by relocating or even ignoring (my family is a victim and I finally left the country because I do not feel I'm home and the rest of the family is still suffering and bouncing from rent to rent). This is not how you develop a city or build apartment villages. May be Chain used this method but it does not mean it is correct. Every body seems too careless on how to build, where to build, and inspect the standards and so on. A lot should be done in this area. In addition, I do not think it is the government's responsibility to control the price offers requested by the lease owners as it is a business. I am not underestimating the government, but it is poorly incompetent and lacks knowledge on how to control. To tell you the truth THEY DO NOT CARE whether you live by the road as a homeless or not!!! This is the truth and every body not touched by this situation kept silence as long as they are not hurt. The construction area is too corrupted from bottom to top. You mentioned about the size of the dish people mount on every possible corners of the condominium. For example this problem could be able to be solved just by leasing office around that area. But this simple problem still exists. You see how big problems get complicated while we still not solving the problem as easy as 1+1. I just do not give up anyways. God bless !!!

  ReplyDelete
 11. እነዚህ የድሮ ዘመን ልጆች
  ባልንጀሮቼ ቁሙ በተራ
  እንጨት ሰብሬ ቤት እስክሠራ
  እንኳን ቤትና የለኝም አጥር
  እደጅ አድራለሁ ኮከብ ስቆጥር
  ያሉት ነገር ዘፈን ነው? ትንቢት?

  Amazing view

  ReplyDelete
 12. It is a very nice article.Since shelter is a basic necessity, the gov't which is trading with stake holders ,the brokers who are making the price to rise, and the real estate investors shouldn't think to get a huge profit from the sector..

  Right now the lease price of land is making the price of houses to increase 1000% in 3 years time.Is this because the income of the people increased meaningfully? No, all the stake holders which are the gov't,brokers,real estate investors,and others are making it to happen. That is why a huge amount of money is circulating in this area hindering the manufacturing sector from growing meaningfully. These stake holders are rent collectors, even including the gov't. To shift this capital to the proper direction ,the price of land should be made as low as possible. The real estates and brokers participate in a bid indirectly and give a very big price for a plot per m2 so that their asset value increases.

  These stake holders are crashing the bone of the people. Did the gov't do good things in the past? Yes, but does the problem aggravated ,yes. If the price of land is made as low as possible , the people who are trading in this area will start to think to invest in other areas which can add value. Otherwise the trade around house will exploding effect on the current inflated price of houses which is beyond the capacity of the ordinary citizen,and the middle income earner.

  In the current price of houses a middle income earner who save 20,000birr a year will own a house after 50 years.On what bases do the real estate investors increase every year more than 100,000birr on their houses? Even while the price of cement which is the main ingredient to build a house has meaningfully decreased.

  Why in the 21 century, a time the technology to build a very big building is very cheap and taking very small time. Had the price of land been very low, the people could have built their own house and they could save some money which can be invested in a sector which can add value. Why is the gov't playing a game in this sector? Why do the gov't send this 40/60 scheme to the kebele to a place which is the play ground of most corrupted people.Why doesn't the gov't stop the political game and give a genuine answer for the problem?

  Why do the gov't make the price of land to increase unlimited which in turn making the price of houses to increase and so is the rent. What the hell is the gov't doing?

  Do these officials have big ears? ,yes they have big ears , Do they have big mouth? yes, they have. Do they have big belly? yes, do they have big heart ? I am in doubt.

  The addisababa city administration had meeting last month ,I am really surprised that they never mentioned their failures, they rather gave a big applause to their work. What is really going on? This isn't the EPRDF I know where meeting are a battle field to accept once own mistake and to show the failure of others for the better. The boat have holes ...  Habtamu (Oslo)

  ReplyDelete
 13. nice observation.

  ReplyDelete
 14. አንዳንድ ወዳጆቼ አሁን እንዲህ ያለው ነገር ለድንግል ማርያም ይጻፋል? አሉኝ፡፡ እኔ ደግሞ እንዲህ ያለው ነገር ለርሷ ያልተጻፈ ለማን ይጻፋል አልኳቸው፡፡

  ReplyDelete
 15. complains!!!!! on the news,papers,music what's worth it.critics is the simplest thing a person can do.At least you are dn so teach us how to be thankful,if you can't, the least you can do is not to write it.

  ReplyDelete
  Replies
  1. why not? yikrta malet sihitetin alemenagerna alemastekakel malet new? or who said dn can not express his feeling on the right way?

   Delete
  2. "Complains!!!!! on the news papers,music..." Unless what to complain means is to go to forest handling weapon? I think you are one of problem maker! or beneficiary from problem encountered the poor.

   Delete
  3. anonymous 12:15 yeah dn can do but i hope they hadn't say dear st.mary part 1(complain) part 2(complain) part 3(complain) if u know wt i mean. and anonymous 4:04 First be polite then i said "news papers music" b/c i hope this blog will be more of (not all) religion and history. we heard complains everywhere even when i'm asleep and i don't understand what you said lastly if u complement anything alike does it mean you are........

   Delete
 16. የሌላው ሀገር ሰው በሚሊዮን ቀርቶ በቢሊዮን ቤት ቢገዛ ከባንክ ተበድሮ ነው፡፡ ዕድሜ እስካለው ያቅሙን እየከፈለ ይኖርበታል
  why this government live for people even one day
  thank you

  ReplyDelete
 17. የሀገሬ ሰው ሲያንጎራጉር ‹አልበር እንዳሞራ ሰው አርጎ ፈጥሮኛል› ይላል፡፡ አሁንማኮ ሰውና አሞራ አንድ ሆኗል፡፡ ሰውም በቤት መወደድ ምክንያት ማደርያ አጥቶ ይዞራል፡፡ አሞራም ይኼው ዛፉ ሁሉ ተቆርጦ አልቆበት ጎጆ የሚሠራበት አጥቶ ይዞራል፡፡

  ReplyDelete
 18. ሰው ጨዋ የሚሆነው ተስፋ ሲኖረው ነው.......

  ReplyDelete
 19. ቤታችንን ስናከራየው፣ በሚችለው ዋጋ ስንሸጥለት ንግድ ብቻ አይደለም፡፡ ለራስ የሚከፈል ዋጋም ጭምር ነው፡፡ ሌባና ቀማኛ፣ ማጅራት መችና ኪስ አውላቂ፣ እኅቶቻችንን ደፋሪና ልጆቻችን አማራሪ እንዳይበረክት እያደረግንም ጭምር ነው፡፡ እነዚህ እኛ ግቢ የሚያድጉ ልጆች ናቸው የነገዎቹ የሀገሪቱ መሪዎች፡፡ እየተማረሩና ጥላቻን እየሰነቁ ካደጉ፣ ነገ የሚያወጡት ፖሊሲ ለሁላችንም አይበጅም፡፡ ገንዘብ ያለውን ሰው እንደ ጨካኝና ቀማኛ፣ ስግብግብና አጥፊ እያዩት ካደጉ በቀል ያረግዛሉ፡፡ ቤታቸውን ያስፈረሰባቸው፣ ከቀያቸው የነቀላቸው፣ ከከተማ ጥግ የወሰዳቸው ያ ባለጠጋ ለእነርሱ የአባታቸው ገዳይ መስሎ ይታያቸዋል፡፡

  ReplyDelete
 20. አበሻ ሲተርክ ‹ዓባይ ማደርያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል› ይላል፡፡ ‹ይህንንስ ስለማን ተናግሮታል ቢሉ› አሉ ሊቃውንቱ ‹አንድም ስለ ራሱ ተናግሮታል› ይላሉ፡፡ ‹እንደምን ነው ቢሉ ብዙ የከተማ ሰው ቤት የለውምና፡፡ ግንድስ ያለው ማንን ነው ቢሉ የቤት ዕቃውን፡፡ ይህስ እንደምን ነው ቢሉ፡፡ ዓባይ ግንዱን ከዛፉ ገንድሶ ከየትም እንዲያመጣው፣ ቤት የሌለው የከተማ ሰውም የቤት ዕቃውን ከየትም ይሰበስባልና፡፡ አንድም ዓባይ ማደርያውን ሳያውቅ ግንዱን ይዞ እንደሚዞረው፡፡ ተከራይም የቤቱን መጠንና ልክ ሳያውቅ ዕቃ እየገዛ ይዞ ሲዞር ይኖራልና›› ብለው ይተነትኑታል፡፡

  ReplyDelete
 21. ዲያቆን ዳንኤል ይሄ የሁላችንም ፀሎት መሆን አለበት እመብርን ለቤት አከራዮች የሚያስተውሉበት ልቦና ትስጣቸዉ።

  ReplyDelete
 22. በጣም አመሰግናለሁ ዳኒ! በለፉት አምስት አመት ውስጥ የደረሰብኝን ለመናገር ቃላት የለኝም! የተለያዩ ሦስት ቤቶች ተከራይቻለሁ ሁሉም ጉዱያስብላሉ፡፡ ሳስበው በጣም ያነገሸግሸኝል፡፡ የሚያሳዝነው መበት የሚባል ነገር እና ካለም የመንጠይቅበትም ህግ አለመኖሩ ነው፡፡ እሺ የአከራዮችስ የሁን መንግስት ግን ለህዘብ አሳቢ የህዝቡን መብት አስከባሪ ነው? ምነው እንደ ቫት አና ታክስ የለች ህግ የአከራይና የተከራይ ህግ በተጠና መንግድ ማዘጋጀት ተሳነው፡፡ ለነገሩ አኮ ብዙ በለስልጣን ቤት አከራይች ናቸው፡፡ ታዲያ ህግ ደግሞ ለነሱም አይበጅ፡፡ወይ አለመታደል ሙሉ ደሞዛችንንም ለቤት ክራይ ከፍለን ደግሞ ነፃነት የሚባል ነገር ማጣታችን ነው የሚገርመኝ፡፡የቤት አከራይን ነገር ሳስብ ስደት እመኛለሁ፡፡ከፍለን ነፃት የሚባል ነግር አይታሰብም፡፡ ብዙዎች በቱን ተከራይተን ምግብ ሳናበስል፣ ሽንት ቤት ሳንጠቀም፣ መብራት ሳናበራ፣ ልብስ ሳናጥብ እንዲያው ለመኝታ ብቻ እንድንጠቀም የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ልጅ እያላቸው ለሰው የማይራሩ ቤት ሲፈርስ እያዩ የኛም እጣፈነታ እኮ አይታወቅም ብለው ደግ የማያስቡ አረ ስነቱ ጉድ፡፡ አይመንግስት እነዲያው መቼ ይሆን እነደአከራይ ሆነህ ሳይሆን እነደተከራይ እነደ ሻጭ ሳይሆን እነደ ሸማች ሆነህ ለኛ የምታስበው፡፡ የሚበጀውን ያምጣልን፡፡

  ReplyDelete
 23. You were a good preacher. You now are a good blogger. The two are different: the former is spiritual and the latter is of this world. Your problem: you started to mix them up. You are trying to mix what can't be mixed, oil and water. The solution, however, is one bold decision: either going back to the beggining to your former deed or to continue blogging without mixing it with the sacred. You can't climb two trees just because you have two legs.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hi Kinfe Michael

   Please respond to me. In what way are we living? Is it not both spritual & worldly.
   In the morning we go to church & then when we come back home, we are worried about our life,having home etc. please think on it, it is interrelated. He is writing for us, to show the problems of the society to the concerned & responsible persons,but not necessarily express his position. I think Daniel can have a house, if he apply for his household consumption what he earns like any other preacher, but I do not think so. He always strives for the church. But I do not have house, while I pay taxes & others what is expected of me to the Gov't.I am always get angry with that. As a citizen, it is the right to get land/home, but every thing is getting complicated

   What is the role of the preacher if he doesn't help those with the problems? Do not you know that previous prophets talk face to face the mistakes of Kings & Queens. This is one look of a religious person. There are alot of priests & monks, who always preach about God, but we need a lot of spritual persons like Daniel who involved in social issues.

   Delete
  2. Kinfe you are really wrong! He is expressing his feelings, the true feelings he experiancing. The true feelings shows spritual. That is why he wrote for emebirihn and us.
   God bless

   Delete
  3. I would like to ask Kinfe-Michael and those who share his thoughts this: Why do you always pledge Daniel and his blog to be "full-time spiritual?" Can't a blog be a medium to share ideas and views on everything? Why are you trying hard to block free-thinking in the name of "Spiritualism?" God is the absolute democrat, and I believe Christianity is a faith of free will. And a specific question to you,Kinfe-Michael, how do you justify your argument that being a blogger is worldly? And how in the world can writing about social problems be "mixing the two worlds?" I say the one who tries to blindfold himself/herself from the truth is the one who chose to wander in the dark. Please my friend,read this blog's emblem. It introduced the blog as "Reflections on Ethiopia's History, Culture, Religion, Politics, and Tradition." Don't single out religion,because we cannot escape our life-related issues by only talking religion.

   Delete
 24. hi Dani i have read your almost all Ur works and i have been inspired by them i am a grade 12 student and if u can pls write about Ur bibliography that will inspired more youths like me to be a good reader my also be a great author, please dani write something about ur self in the next work .god bless Ethiopia

  ReplyDelete
 25. 10q dani this is my first comment to you in the housing problem the government play a poor role in the contraction you see sir starting from 1997EC Still now the government construct and and transfer only 70,000 homes but the registration data indicate more 500,000 home less are there; when we take this in two consideration the government build only 7,000 home per year what we cans say the government is only talker rather than problem solver b/c this is not there burning issue. they only focus on how to stay in the power but this was the best way they are not using it

  ReplyDelete
 26. tirwene aseteyayet becha eyemereteke lemene post taderegalehe?

  ReplyDelete
 27. ምነው ዳኒ መሐል አራት ኪሎን፣ ያቺ የሲኦል ምሳሌ የሆነችዋን ሰፈር ባታነሳት መልካም ነበር፡፡ እኔም ያራት ኪሎ ልጅ ነበርኩ፣ ያውም የባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ፣ ጅሩ ሰፈር፡፡ መቼም ስኖርበት ጥሩ ኑሮ የምኖር ያህል ይሰማኝ ነበር፡፡ ለምን ብትል ሁሉም ነገር በቀላሉ ይገኛል፣ እንዳልከው ሽንኩርቱም፣ ቃሪያውም፣ ዘይቱና እንጀራውን አሥር ብር ባልሞላ ይገኝ ይሆናል፣ ግን ግን ሌላውስ? አረቄውም በ5ዐ ሣንቲም፣ሴቱም በ1 ብር ጫቱም በትንሽ ብር ይገኛል፡፡ ሳንሞት የሞትን ሆነን ለዘመናት አዘቅጥ ውስጥ ኖረን አሁን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ብርሃንን አይተናል፡፡ ኑሮ ቢወደድም ተስፋ አለን ቢያንስ ፀዳ ያለ ሰፈር እየኖርን በፊት ያሳለፍነውን ሕይወት እየተፀየፍን፣ ንፁህ አየር እየተመገብን፣ እየታጠብን፣ ለብቻችን እየተፀዳዳን እዚህ ላይ ደርሰን ነገም ሌላ ቀን ነው እያልን ኑሮው እንዲስተካከልልን እንፀልያል፡፡ “ተስፋ ያለው ሰው ጨዋ ነው እንዳልከው”፡፡ ሌላው ደግሞ እስኪ እነዛን አሮጌ ቆርቆሮች በአይነ ሕሊናህ ተመልከታቸው፡፡ አሮጌነታቸው አልበቃ ብሎ በነፋስ እንዳያፈነግጡ የተደረደረባቸው የድንጋይ መዓት፣ የጋራ መጸዳጃ ቤት፣ የጋራ ልብስ ማስጫ፣ የጋራ ማድ ቤት ወዘተ፡፡ እግዚኦ ላንተ አራት ኪሎም ሠፈር ሆኖ “አሮጌ ከተማን ማፍረስና አሮጊትን ወጣት ማድረግ ከባድ ነው፡፡ ለዚህኮ ነው ብዙ ሀገሮች የጥንቱን ከተማ ከማፈራረስ ብለው ሌላ አዲስ ከተማ የሚገነቡት፡፡ እኛስ ሀገር ምናለ አዲስ ከተማ ብንገነባ፡፡ ስንቱን አፍርሰን እንዘልቀዋለን፡፡“ አልክ፡፡ ሁለቴ ብቻ አይደለም በጣም በጣም ብዙ ግዚ አስበህ ይህን ሃሣብ መሰንዘር የነበረብህ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Are you saying that the above problems, i.e Areke, Prostitution, drug...solved just because we build a condominium ? Just because you stayed away from the problem, it does not necessary mean it is solved. The truth is, we are seeing the worst. Another thing, if constructing is easy and cheap while investing in new areas than removing the old ones, why he does not mention his ideas and state his best options ? Have you considered the poors those who could not afford to buy a condominium what would happen ? Even the middle class could not afford it. Even if you give it for free it will be challenging for those to even afford the the food the consume let alone the transportation fee.
   God bless!

   Delete
  2. Thanks for your reply. Is there any poor peoples those who couldn't afford to buy condo? You seems very foolish. Go and ask delalas to get more information about this. It is time to begin small business from this God's gift. You may sell by doubling up the price to the 2nd person. At the end they will have another home and some money.

   Delete
  3. Let me be clear here. Condominium at first place planned to help the poors by building economical houses so that they may benefit from it.In my openion, this will be achieved only if they lived in it with their families . Besides it is not for bussiness at all. IT IS FOR SURVIVAL. Have you thought about the abject poverty people living now? How come a poor mother who is struggling and agonizing herself daily for her kids day to day food, can have the money and think to make a business that you are saying. Who is going to stand for them, help them in different techiniqes? Thanks
   God bless!!!

   Delete
 28. እንደው አሮጌው ሰፈር መፍረሱ ለበጎ ከሆነ ምነው ባለይዞታው በኖረበትና ባደገበት አካባቢ ዕድሩ ሳይፈርስ ማህበራዊ ቁርኝቱን ሳያጣ ቅድሚያ ተሰጥቶት የሚጠቀምበት ሁኔታ ቢቸቻችለት
  የአካባቢውን ውበት እኮ ያበላሹት አሮጌ ቤቶች እንጂ አሮጌ ነዋሪዎች አይደሉም
  እጅግ ከባድ የሚሆነውና ውጤቱም የሚከፋው አሮጌ ቤቶችን ማፍረሱ ሳይሆን የሰዎችን ማህበራዊ መስተጋብር ማፈራረሱ ነውና ቆም ብሎ ማሰቡ ይበጃል
  የአከራይ ተከራዩን ጉዳይ ከማስገበር ባለፈ ቢሰራበት እላለሁ
  እግዚዓብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
  አሜን

  ReplyDelete
 29. እንዲህ ያለው መተሳሰብ እንዲኖር ደግሞ መንግሥት ቤት ሠርቶና በዕጣ አከፋፍሎ አይዘልቀውም፡፡ ባለ ሀብቱም የሚከራይ ቤት እንዲሠራ መደረግ አለበት፡፡ የኪራይ ቤት ዓይነቶች ደረጃ ወጥቶላቸው መንግሥትም በርካሽ ዋጋ መሬት ሰጥቷቸው እንዲሠሩ መደረግ አለበት፡፡ የኪራዩ ተመን ግን በመንግሥትና በአከራዩ በጋራ ሊተመን ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 30. dani,its' nice article. keep it up your writing!!!

  ReplyDelete
 31. ደቂቀ ጸሃፍት ዘሳንሆዜFebruary 12, 2013 at 7:16 AM

  ወይ ጉድ ዲ/ን ዳንኤል ለኔ ይህ ጽሁፍህ የጸሎት ድርሰት አይመስለኝም የአጻጻፍ ስልትህን ለማሳመር ስትል የአባቶቻችንን የጸሎት ድርሰት የማይመስል የተዘማነነ ጸሎት አይሉት አቤቱታ ሊገባኝ አልቻለም። ስለ ድንግል ማርያም፤ የገና በዓል አልያም የቤት ውድነት በጸሎት መልክ የፖተልከውን የኑሮ አቤቱታ ሱባኤ የሚያውጅ ወይም መፍትሄ የሚጠቁም ጽሁፍ ለያይትህ ብትጽፋቸው በተዋጣልህ ነበር። አንዳንዴ ስራዎችህን መንፈሳዊነት ለማላበስ ስትል መንፈሳዊነቱን እንዳታራቁተው ጥንቃቄ ብታደርግ ደስ ይለኛል። ወይ የለየለት የነገረ ድህነት ትምህርት አላስተማርከን ወይ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን አላስተማርከን ወይ የማረፊያ/የመጠለያ/ ሀሳብ አልነገርከን። ቀየጥከውና አደናበርከኝ። እየጸለይክ ይሁን እያማረርክ መንፈሳዊ ይሁን አለማዊ ይዞታው የማይታወቅ የተቀየጠ ጽሁፍ አታስነብበን እባክህ። በርግጠኝነት ተረድተህዋል ከዚህ የተሻለ መጻፍ ትችል ስለነበር ነው። እውነታው ግን እውነት ነው። ይህ የጦማሪነት ጦስ ነው እንጅ የጋዜጠኝነት/የደራሲነት/ አልያም ጸሃፊነት ሙያህ ውጤት አይደለም

  ReplyDelete
 32. እነዚህ የድሮ ዘመን ልጆች
  ባልንጀሮቼ ቁሙ በተራ
  እንጨት ሰብሬ ቤት እስክሠራ
  እንኳን ቤትና የለኝም አጥር
  እደጅ አድራለሁ ኮከብ ስቆጥር
  ያሉት ነገር ዘፈን ነው? ትንቢት?
  የሚገርም እይታ
  ተባረክ ዳንኤል

  ReplyDelete
 33. It is awesome article indeed,
  These days it is not House the only problem but one of the out come of other core problems such as Racist and Corruption
  May God Bless Ethiopia !

  ReplyDelete
 34. Dani betam tiru asteway sew neh.betatam adenkiha. Haile ke DDU

  ReplyDelete
 35. Dani yehulum sew asyeyayet bileyayim.bene bekul gin temchitehegnal ketelibet.

  ReplyDelete
 36. ዲ/ን ዳንኤል መንፈሳዊ ሕይወትህንና ትጋትህን እሰከ ፍጻሜው ያሳምርልህና በዚህ ትውልድ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ ውለታ ካደረጉ የቁረጥ ልጆች አንዱ ነህ ብዬ አምናለሁ ፡፡ አንድ ቅሬታ ግን አለኝ በልብ ወለድ ጽሁፍህ አንድ አባት ፣ አንዲት ልጅ፣ ወይም በቁማችው ወይም በህልማቸው በአንድ ወቅት ከእግዚአብሄር ወይም ከእመቤታችን ጋር ተነጋገሩ ብሎ መጻፍህ ወይም መድረስህ 0ድፍረት ይመሰለኛል ፡፡ ሙሉውን የእ/ር ስም ወይም የእመቤታችንን ስም እየጠሩ አስተማሪም ይሁን አስቂኝ ድረሰት መጻፍ ትክክል አይመስለኝም፡፡
  በእርግጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ፣ በድርሳናት፣ ገድላትና በተአምራት ቅዱሳን አምላካቸውን ወይም እመቤታችንን ያናገሩበትን በምሳሌ ወስዶ ማስተማር መልካም ነው ትውፊትም ነው ፤ ለምሳሌ ሶሎሞን ከእ/ር ጋር ያደረገው ንግግር ተጠቅመህ እንደምታስተምረው ፡፡ ነገር ግን ከቤ/ክ አስተምህሮ ውጪ ምናባዊ ታሪክ ፈጥሮ ለንባብ ማቅረብ ወይም ለስብከት መጠቀም ትክክል አይመስለኝም ፡፡ እነደው ይህ አስተያየት ጎዶሎ ነው ብትል እንኳ እንዲህ አይነት የድርሰት አጻጻፍን ለክፉ መንገድ ለሚያውሉት በር አይከፈትም ? በእምነታቸው ላልጠነከሩትስ አሳሳች /የድፍረት መነሻ አይሆንም ? ዛሬ በየጫት ቤቱ ገሀነምና መንግስተ ሰማይ የቀልድ አፍ መክፈቻ ሆነዋል ፤ ቅዱሳን መላእክትም እንዲሁ፡፡ በአንድ ወቀት እገሌ ጳጳስ/ቄስ/ዲያቆን ገሀነም ገቡና እንዲህ ተባሉ እንዲ ሆኑ ብሎ ልብ ወለድ መጻፍ ለዚህች ቤ/ክ በታሪክ ና በትውፊት ከሚቆሙላት ሳይሆን ከሚያላግጡባት ቢጻፍ አይገረምም ፡፡ ስለዚህ እንደ እኔ ከሆነ በፈጠራ ታሪክ በአንድ ወቀት እገሌ የሚባሉ ሰው እ/ር አናገሩትና የህንን አላቸው ማለት ትክክል አይመስለኝም ፡፡ ይህ ሐሳቤ ትክክል ካልሆነም እንደው ወረድ ብለህ (እ/ር እና እመቤታችንን ሳትጨምር) አንድ ሰው በህልሙ ወይም በቁሙ ከአንድ መልአክ/ከጻድቅ ጋር ተነጋገረ እንዲህም ተባባሉ ብለህ ብትደርስ ይሻላል፤ እነሱን ማሳነሴ ሳይሆን እነሱ ፍጡራን ስለሆኑ ለሚያነብም ለሚሰማም ይቀላል ብዬ ነው፡ ለምሳሌ በኮንዶሚኒየም ጉዳይ የእምቤታችን ስም መጠቀሱን ከተቃወሙት አንዱ እኔ ነኝ ፡፡ መስጋና ይግባትና እመቤቴ የዛ ጽሁፍ ማሳመሪያ የሆነች ነው የመሰለኝ፤፤
  ዲ/ን ዳንኤል የስነ ጽሁፍ ድሀ አይደለህም ምነው በዚህ መንገድ ትምህርት ማስተላለፍን ትትህ ሌላ የምንወድለህን ስለ ሀይማኖታዊና ማህበራዊውን ጉዳዮች አፍ በሚያስከፍት አጻጻፍህ ብትጽፍልን ?

  መልካሙን ሁሉ ከምመኝልህ


  ReplyDelete
 37. ዲያቆን ዳንኤል ስላሳሰብከለን ተባረክ ሰው እኮ የምድርን ኑሮ ዝንተ አለም የሚኖረ ይመስለዋል ግን ዳኒ አከራም ተከራዮም …..ሁለም ተከራይተው እንዳሉ አያስቡትም /አናስበውም/ ለመሆኑ አከራይ ተከራይን ሲያከራየው ተከራይቶ እግዚአብሔር ፈቅዶለት እንደሆነ ቢገባው ምን አለ
  እኔስ ልበላቸሁ የአባቶቻችንን ቃል አዎ አገራችን በሰማይ ነው የምንግሰት
  በንኖርም ብንሞተ የእግዚአብሔር ነንና
  ዳኒ በህይወት በጤና ያቆይህ

  ReplyDelete
 38. እነዚህ የድሮ ዘመን ልጆች
  ባልንጀሮቼ ቁሙ በተራ
  እንጨት ሰብሬ ቤት እስክሠራ
  እንኳን ቤትና የለኝም አጥር
  እደጅ አድራለሁ ኮከብ ስቆጥር
  ያሉት ነገር ዘፈን ነው? ትንቢት? በነሱ ግዜ ዘፈን ነበር ለካስ ትንቢቱ ሲገለጥ ጊዜ ገለጠውና ምስጢሩ ሲፈታ ትንቢት ኖሮአል ፡፡ በውነቱ ካናገራቸው እግዚአብሔር በቀር የፈታው ያለ አይመስለኝም በዚያን ግዜ ይህ ግዜአዊ ምስጢር ስለሆነ ግዜ ፈታው እላለሁ

  ReplyDelete