ይህንን ደብዳቤ ላንቺ የምጽፈው የገናን በዓል ከልቤ የምወደው በዓል ስለሆነ ነው፡፡ የምወደው
ደግሞ የገና ዛፍ ተተክሎ፣ በጥጥ ተውጦ፣ በከረሜላ ተከብቦ፣ በመብራትም አሸብርቆ ስለሚያስደስተኝ አይደለም፡፡ እንዲያውም
እንዲህ ያለው ነገር ብዙም አይመስጠኝም፡፡ ቤተ ልሔም ዋሻ ውስጥ ለተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ዛፍ ማሸብረቅ፣ በረዶ አይታ
በማታውቅ ሀገር ውስጥ የበረዶ ምሳሌ የሆነውን ጥጥ ማግተልተል፤ ልጇን የምታለብሰው አጥታ የበለሶን ቅጠል ላለበሰች እናት
ከረሜላና ኳስ ማንጠልጠል ለእኔ ትርጉሙ አይገባኝም፡፡ መቼም ፈረንጅ መሆን ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች አንዱ እርሱ ሲያብድ የሠራውንም
ቢሆን ፋሽን ነው ብሎ የሚከተለው አለማጣቱ ነውና ምን ይደረግ፡፡
እኔ የገናን በዓል የምወደው ቤታችን የሚጋገረውን ድፎ ዳቦ፣ በሠፈር የሚታረደውን
ቅርጫ፣ በሰሞኑ የሚደረ ገውንም የገና ጨዋታ ብዬ እንዳይመስልሽ፡፡ ምንም እንኳን ባህሉ ደስ ቢለኝ፣ የኔ በመሆኑም ቢያኮራኝ፣
ብዙዎቹ ነገሮች ግን ከታሪክነት ወደ ተረትነት ሊቀየሩ በመዳረሳቸው የኔ ቢጤውን የዚህ ትውልድ ልጅ አንጀቱ ውስጥ
አይገቡለትም፡፡ እኔ የተከራየሁባቸው ሰዎች ሁሉ እንኳን ድፎ ዳቦ መድፋትና ሻሂም በኤሌክትሪክ ማፍላት ስለሚከለክሉ እኔ ድፎ
ዳቦን በቃል እንጂ በተግባር ረስቼዋለሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሬ ገዝቶ ቅርጫ መግባት የባንክ አክስዮን እንደመግዛት ሆኖ
ስላገኘሁት፣ ጫጩቶቹን ጭልፊት እንደወሰደበት አውራ ዶሮ ‹ከዐቅሜ በላይ ነው› ብዬ ትቼዋለሁ፡፡ እዚህ ሀገር ቅርጫና ምርጫ
እንግዲህ ላይሆንልን ነው መሰል፡፡
የገና ጨዋታ እንጫወትባቸው የነበሩት ሜዳዎች ሁሉ ወይ ኮንዶሚኒየም ተሠርቶባቸዋል፣
ወይ ታጥረዋል፣ ያለበለዚያም ለአንድ ሀብታም ተሰጥተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንኳንስ ባዶ የሆነ ሜዳ ፀጉር ያልበቀለበት መላጣና
ትንሽ ዘርጠጥ ያለ ቦርጭም ከተገኘ ቦታው ለግንባታ መዋሉ የማይቀር ነው፡፡ ታድያ የገና ጨዋታ ምናልባት ወደፊት የኮምፒውተር ‹ጌም›
ሆኖ ሲመጣ ካልተጫወትነው በቀር በምን ዕድላችን፡፡ ደግሞምኮ ‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ› የሚለው ግጥም ፋሽኑ ስላለፈበትና
‹ጌታም› ስለሚቆጡ፣ ተቆጥተውም የገና መጨዋቻውን ሜዳ ስለወሰዱት ወደፊት አዲስ ግጥም እስኪመጣ ድረስ ሐሳባችንን በይደር
አቆይተነዋል፡፡
ለእኔ የገና ጨዋታ ከጨዋታዎች ሁሉ የሚበልጥብኝ ከዚህ ሁሉ በተለየ ምክንያት ነው፡፡
መጻሕፍት እንደነገሩን፣ ሊቃውንትም እንዳስተማሩን፣ ሰዓልያንም እንዳቆዩን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሰሽ ለቆጠራ ከናዝሬት
ወደ ቤተ ልሔም በመጣሽ ጊዜ፣ ከተማው በሙሉ ገንዘብና ዘመድ ባላቸው ሰዎች ተይዞ ነበር አሉ፡፡ ይገርማል፤ ከተማ ገንዘብና ዘመድ
ባላቸው ሰዎች መያዙ ከጥንት የወረስነው ነው ማለት ነው፡፡ ልክ እንደዚያው ጊዜ ዛሬምኮ ከተማው ገንዘብና ዘመድ ባላቸው ሰዎች ተይዞ
እንኳን አዲስ ማደርያ ማግኘት ቀርቶ ዛሬ ባደሩበት ነገ መልሶ ማደርም አልተቻለም፡፡ የሀገራችን ባለ መሬትን ጸሎት መቼም ታውቂዋለሽ፡፡
‹ከሀብታም ዓይንና ከክፉ መሐንዲስ ሠውረኝ ነው› አሉ የሚለው፡፡ ሀብታምም በዚያ ሲዞር ካየው ይህንን ላልማ ብሎ እንዳይነቅለው፤
ክፉ መሐንዲስም ካላጣው ቦታ በሳሎኑ ላይ የሚሄድ መንገድ ያወጣበት እንደሆነ ቤቱን አፍንጫዋን የተገጨች ቮልስ እንዳያስመስለው እየፈራ
ነው፡፡
የሀገራችን ደራሲ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ‹ወለተ ነዳያን- የድኾች ልጅ› ብሎሻልና አንቺ ከስንቅ በቀር ምንም ያልነበረሽ
በመሆንሽ ማንም ሊያስጠጋሽ አለመፈለጉን መጻሕፍቱ ሁሉ ተባብረው ጽፈዋል፡፡
እኔ መቼም በዚያች በገና ዋዜማ የሚያስጠጋሽ አጥተሽ እንዴት ልትንከራተቺ እንደምትችይ በዓይነ ኅሊናዬ አስበዋለሁ፡፡
ድሮስ ድኻን ማን ያስጠጋዋል፡፡ ድኻ ይሸጣል እንጂ አይገዛም፤ ድኻ ያበላል እንጂ አይበላም፤ ድኻ ያዋጣል እንጂ አይዋጣለትም፡፡
እኔም ታድያ እንዳንቺው ቤት ያጣሁ ከርታታ በመሆኔ እንደ ገና በዓል የምወደው በዓል የለም፡፡ ይኼው በቀደም እንኳን
የተከራየሁባቸው ሴትዮ መጡና ‹ልጄ ከውጭ ሀገር ስለምትመጣ ቤቱን በሚቀጥለው ወር እንድትለቅ› አሉኝና ሄዱ፡፡ ሰው ችግሩ ሲጨምር
ጸሎቱም በዚያው ልክ ይጨምራል ለካ፡፡ ድሮ ድሮ የዕለት ልብስ የዓመት ጉርስ ብዬ ነበር የምጸልየው፡፡ ዛሬ ዛሬማ የአከራዮቹ ልጅ
ከአሜሪካ እንዳትመጣም መጸለይ ሊኖርብኝ ነው፡፡ አንዱን ደላላ እንዲያውም በቀደም አንድ ቤት ሊያሳየኝ ሲል ‹ልጃቸው አሜሪካ ናት
ወይስ እዚህ› ብዬ ስጠይቀው ‹ምነው አንተ ውክልና ልትወስድ ነው እንዴ የምትገባው› ብሎ ሳቀብኝ፡፡
ዐለመኛው ቀበሌ ‹‹መታወቂያ ስጠኝ›› ሲሉት ‹‹አድራሻህ የት ነው?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ደግሞ ድኻ ምን አድራሻ አለው፡፡
እንዳከራዩት ነው፡፡ ዛሬ ቀበሌ አንድ፣ ከሳምንት በኋላ ቀበሌ አሥራ አምስት፣ ከወር በኋላ ደግሞ ጭራሽ ከተማውን ለቅቆ ሊሄድ ይችላል፡፡
እኛኮ በፈጣሪ ፈቃድ ብቻ አይደለም የምንኖረው፣ በአከራዮቻችንም ፈቃድ ጭምር ነው፡፡ ለኛ ለከርታታ ዜጎች ከርታታ ቀበሌ ካልተመሠረተልን
በቀር ዜግነታችን ጥያቄ ውስጥ ወድቋል፡፡አንደኛው ቀበሌ ተወልዶ፣ ሌላ ቀበሌ አድጎ፣ ሌላ ቀበሌ ሥራ ይዞ፣ ሌላ ቀበሌ አግብቶ፣
ሌላ ቀበሌ አርግዞ፣ ሌላ ቀበሌ ወልዶ፣ ሌላ ቀበሌ አድጎ፣ ሌላ ቀበሌ ለሚሞት ደኻ ‹‹ቋሚ አድራሻ› እንደሚሊ ቅጽ ያለ ምጸት የለም፡፡
ይኼው ምነው የከብት ጭራ ተከትለው ለሚዘዋወሩ አርብቶ አደሮች የሚዘዋወር ትምህርት ቤት ተከፍቶ የለም እንዴ? እንዴው
ድንግል ማርያም በአማላጅነትሽ ምናለ ለኛስ ተዘዋዋሪ ቀበሌ እንዲቋቋምልን ብታደርጊ፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ በፌድራል ሥር መተዳደር
ነው ያለብን፡፡ ቢያንስ ከሀገር እስክንወጣ፡፡ የቀበሌ መታወቂያ ለማውጣት አድራሻ ስለሌለን በፓስፖርት ብቻ መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡
የኛ ሠፈር ደላሎች እንኳን በመኪና ስትመጭና በእግርሽ ስትመጭ፣ ዝንጥ ብለሽ ስትመጭና እንደነገሩ ሆነሽ ስትመጭ ፈገግታቸው
ይለያል፡፡ የሚከራይ ቤት የኔ ቢጤው ሲጠይቃቸው ‹ዋጋው ውድ ይሆንብሃል እንጂ› ይሉታል፡፡ ይወደድብኝ አይወደድብኝ የኔ ሐሳብ አስፈላጊ
አይደለም፡፡ የሰውን ቤት ዋጋ በሚተምኑበት ዓይናቸው አለባበሴንና የሰውነት ይዞታዬን አይተው ዐቅሜን ይተምኑልኛል፡፡ አንዳንዴም
ቀለል ካልሽባቸው ‹‹ለማን ነው?›› ይሉሻል፡፡ ተልከሽ የመጣሽ ነው የሚመስላቸው፡፡ እንኳን ደላላው የምትከራይው ግቢ ስትገቢ እንኳን
ውሻው በጤና አያይሽም፡፡ አለባበስሽን አይቶ ከሚከራዩት ክፍሎች አንዱን ሳይሆን የርሱን ማደርያ የምትከራዪው ይመስለዋል መሰል ያጉረመርምብሻል፡፡
አንዱን ደላላ እንደምን ተሟግቼ ቤት ሊያሳየኝ ሄደ፡፡ አከራይዋ ሴትዮ መጀመርያ እጄን አዩት፡፡ በኋላ ደላላው እንደነገረኛ
ከሆነ መኪና መያዝ አለመያዜን ከያዝኩት ቁልፍ ለማረጋገጥ ነው አሉ፡፡ እንዲያውም በኋላ ለብቻው ጠርተው ‹መዝገብ ቤት ነው አይደል››
ብለው ጠይቀውታል፡፡ ‹‹እንዴት ዐወቁ›› ሲላቸው ‹‹ያዘው ቁልፍ የአሮጌ ቁም ሳጥን ቁልፍ ነው›› አሉት፡፡
ከዚያ ደግሞ ፊቴን አዩት፤ ፊቴን አይተው ሲጨርሱ ከንፈራቸውን መጠጡልኝ፡፡ ‹ወላጅ አልባ› ሕጻን መስዬ ታየኋቸው መሰል፡፡
እኔ ደግሞ ማዘናቸውን አይቼ አይጨክኑብኝም መስሎኝ ፈገግ ስል፣ ኮስተር ብለው ጫማዬን በጎሪጥ ቦረሹት፡፡ ጫማዬን አለማስጠረጌ የቆጨኝ
ያኔ ነው፡፡
‹ካንተ ቀደም ብሎ አንድ ሰው መጥቶ ተከራዬው› አሉኝ፡፡ ሰውነቴን ሁሉ ‹ሲቲ ስካን› ካነሡኝ በኋላ የምርመራው ውጤት
ይኼው ሆነ፡፡ ተሰናብተን ስንወጣ ደላላውን በዓይናቸው ጠቅሰው ወደ ኋላ አስቀሩት፡፡ እኔም ከግቢው ወጣሁ፡፡ አንድ አሥር ደቂቃ
ቆይቶ እየተነጫነጨ መጣ፡፡
‹ምን ዓይነት ሴትዮ ናቸው› ይላል ደጋግሞ፡፡ የሆነውን
ይነግረኝ ዘንድ ወጥሬ ያዝኩት፡፡
በመጨረሻ ‹ወቀሱኝ› አለኝ፡፡
‹ምን አድርገህ› ስል ጠየቅኩት፡፡
‹ይህኮ የተከበረ ግቢ ነው፤ ካመጣህ ሁነኛ ሰው አምጣ፤ እኔ ተከራይ እንጂ አትክልተኛ አልፈልግም› አሉኝ አለ፡፡
እንግዲህ ቅጥነቴን አይተው የለበስኩ ሳይሆን ልብሱን እንደመስቀያ ያንጠለጠልኩት መስሏቸዋል ማለት ነው፡፡
ለነገሩ የርሳቸው ይሻላል፡፡ አስቀድመው ቁርጡን የተናገሩት፡፡ አንዳንዶቹኮ ለግቢያቸው የሚያወጡት ሕግ ከወኅኒ ቤት
ሕግ የባሰ ነው፡፡ ማታ ከ12 ሰዓት በኋላ መግባት፣ ጠዋት ከ12 ሰዓት በፊት መውጣት አይቻልም፡፡ በሳምንት ከሁለት ቀን በላይ
ልብስ ማጠብ አይፈቀድም፡፡ ማንኛውንም ነገር በኤሌክትርክ መጠቀም አይቻልም፡፡ ሲወጡና ሲገቡ ለባለቤቶቹ ሰላምታ መስጠት ያስፈልጋል፡፡
ቴፕና ሬዲዮ ድምጹን ከፍ አድርጎ መክፈት አይፈቀድም፡፡ ጓደኛ ማብዛት
አይቻልም፡፡ እና እዚህ ከመከራየት አንድያውኑ ሂሳቡን ለመንግሥት ከፍሎ ቃሊቲ መታሠር አይሻልም፡፡
(ይቀጥላል)
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፡፡
በመጀመሪያ እንኩዋን አደረሰህ. ዳኒ እንደቀልድ አድርገህ የጻፍከው ቁምነገር ውስጤን በመኮርኮሩ እያነባሁ ነው ያነበብኩት ዳኒ ያሳየህንእኮ የሰውልጅ ምንያህል መድረሻ ማጣቱን ነው ድሀእኮ የዜግነት መብቱን ማጣቱንነው የነገርከን እኮ ሰወ ለሰው እንዴት እንደተጨካከነ ነው አቤት እግዚኦ መቸነው የሚነጋው የድንግል ማርያምን ልጅ የሰማይና የምድሩን ጌታ አለም የተቀበለችው በንዲህ ያለጭካኔ ስለነበር ከኛ በፊት ሁሉን ስለሚያውቀው መዘርዘርና ማስረዳት የሚያስፈልገን አይመስለንም እንዲሁ በደፈናው መገፋታችንን መናቃችንን ተመልክተህ በቃበለን በምህረትህ ጎብኘን ማለቱ ሳይሻለን አይቀርም ዳኒ ይብቃኝ ብዙ ማለት ቢቻልም መቀጠልግን አልቻልኩም ጽሁፍህን ሳነብ በህሊናየ የሚመላለሱት የጨረቃቤት ነው ተብለው ቤታቸው የፈረሰባቸውን ሰዎች አስታውሸ ገናን እንዴት ሆነው አሳልፈውት ይሆን በማለት ነው ዳኒ ስራህን እግዚአብሄር ይባርክልህ አሜን!
ReplyDelete"ye hoden awtiche lingerish" yalew manew le FEDERAL yihon
ReplyDeleteየእኔን ገጠመኝ ላካፍላቹህ፡፡ከመታወቂያ ጋር በተገናኘ፡
ReplyDeleteእኔ አሁኑ ጊዜ በአ/አ ከተማ አንድ ድርጅት ዉሰጥ ሰራተኛ ና በአአዩ የቴክኖሎጂ ት/ት 2ኛ ድግሪ ተማሪ ስሆን የመመረቂያ ወረቀት በመስራት ላይ እገኛለሁ፡፡ የምኖረዉም 3በ4 በማትበለጥ ቤት ከብሪቲሽ ኢምባሲ ( እረ ….ከብሪቲሽ ክፍለ ከተማ) ተጎራብቼ፣ የደሞዜን 35 ፐርሰንት ለአንዲት ተጨቃጫቂ አዛዉንት እየከፈልኩ ነዉ፡፡ለነገሩ በቅርብ ወደ 4 ድጂት/1000/ አደርሰዋለሁ ሲሉም ያሰፈሩኛል፡፡
እነደተለመደዉ ከእለታት አንድ ቀን እግሬን ለማፈታት ምሽት ላይ ኤፍ ኤም በጆሮየ ሰክቼ የብሪቲሽ ክፍለ ከተማ ተከትዬ ጉዜን ቀጠልኩ፡፡ለነገሩ ነዉ እንጂ ኤፍ ኤምን ከማዳመጥ ይልቅ ከራሴ ጋር ነበር የምከራከረው፡፡ለአንድ አገር አምበሳደር መኑሪያ ይህን ያህል፣ለኔ ለዜጋዉ 3በ4 ቤት ፣ያዉም 1/3 ደሞዜን እየከፈልኩ፣ያዉም መብራት ከ5፡00 በሁላ እንዳታበራ፣ዉሃ ቆትበህ ቅዳ፣ዘመድ/ጉደኛ እነዳታመጣ፣ማታ 2፡00 ሰኣት ግባ በሚሉ ህጎች ተተብትቤ እየኖርኩ እያለኩ ፣ ከራሴ ጋር አወራለሁ፡፡ በተለይ ቶሎ አላልቅልኝ ያለዉ ወክ እና ከራሴ ጋር ከያዝኩት ሙግት ስመለስ ኤፍ ኤሙ ስለ አዲስ ኮንዶምኒየም ምዝገባ ሊጀመር መሆኑን ሰማሁ፡፡በዚህ ጊዜ ነበር መታዋቂያ እንዴት ማዉጣት እንደምችል አሰበኩ፡፡ በበነጋታዉ በቅርብ ወደሚገኘዉ ቀበሌ በመሄድ ስጠይቅ መሸኛና ያከራይ ተያዠ ያስፈልጋል ተባልኩ፡፡ከኖርኩበት ከወጣዉ ወደ 6/7 አመት በስራ ምከንያት ሆኖኛል፣አከራዬ በቀላሉ እሺ እንደማይሉ ተረዳሁ፡፡ ሆኖም ግን ተስፋ ባለመቁረጥ መሸኛዉን እንደምንም አስመጣዉና አከራየ ከዚህ ቤት እንደምኖር ይንገሩላኝ ስላቸዉ…እህ…እህ…..እህ… ቤቱን ለቀህ መዉጣት ትችላለህ አሉኝ፡፡ እኔ እነደሆነ አማሪካ እና አረብ ያሉት ልጆቼ /ዲያስፖራ/ደህና ይሁኑ፣ የዘዉኛል ብለዉ ገላመጡኝ፡፡እረ ባክወ ስላቸዉ…አዬ…አንተ መበራት እስከ 7፡00 እያበረህ ረብሸሃል አሉ፡፡አዛዉነቲቱን ትቼ ወደ ቀበሌ ስሄድ ሊያዳምቱኝ አልቻሉም፡፡ ቢጨነቀኝ እኔ ኢትዮጰያዊ አልመሰልም ስል ቀለድኩቸዉ፡፡ኮስተር ብዬ ደግሞ እኔ ጎዳኒስት ነኝ አልኩቸዉ ፡፡ ወይ ፍንክች!!! ለዚ ነዉ ሰዉ ፎርጂድ ስራ የሚፈለገዉ ….አልኩ፡፡/በግልጽ መፍትሄ ከመፈለግ ትክከል ወደ አልሆነ መንገድ የሚያመራዉ/፡፡ በዚህ ጊዜ የተለያዩ ሀሳቦች በአእምሮየ ተመላለሱ፡፡በቤት ሰራተኛነትና በጽዳት ተሰማርተዉ እነዲህ ያጠገቡቸዉ አዛዉነት ሳሰብ እንዴት ሀገራቸንን በምርመርና በስራ እንዴት ነዉ የምናሳደጋት ብዬ አሰበኩ፡፡ አንድ መፈተሄ የማይሉ ቀበሌዎች ሳስብ እንዴት ነዉ መልካም መንግሰት፣ዜግነትን፣ህዝበን ማገልገል …..ምናመን
ከዚያ በሁላማ በቴክኖሎጂ ስር የምሰራዉን ምርምር ትቼ በማህበራዊ ና ቢዝነስ፣መልካም መንግሰት፣ዜግነት፣እኩልነት፣ቅንነት፣በአገር ወዳድነት የሚሉ ጉዳዮች/ርእሶች/አምሮዬን ሞልተዉ ዋናዉ ስራዬን ትቼ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ ሁኛለሁ፡፡ ከአአዩ ዘነደሮ መመረቄን እነጃ!!!
የነገርከን ገጠመኝ የብዙዎች የተለመደ ህይወት በመሆኑ እንደገጠመኝ አያዩትም፡፡ ምናልባት አንተ 6/7 አመት ስትኖር ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የገጠመህ ትመስላለህ፡፡ ስለዚህ እንደሌሎቹ ብዙ ስላልደረሰብህ ልትፅናና ያስፈልጋል፡፡ ቢሆንም አቀራረብህን ወድጄዋለሁ ነገር ግን ስትፅፍ አንዳንድ የቃላት ግድፈቶችን ለማረም ብትሞክር ጥሩ ይመስለኛል፡፡
Deleteግን ዳኒ ስትታይ እኮ ቀጫጫ እና አትክልተኛ አትመስልም፡፡ ምናልባት ሴትዮዋ ገና ሲያዩህ ቀልባቸው አልወደደህ ይሆናል፡፡ እኔም ተመሳሳይ ነገር ገጥሞኛል አሁን ይህንን ገጠመኝ መፃፌ ያንተን ታሪክ መድገም ይሆንብኛል ግን ለማንኛውም ዳኒ አመሰግንሃለሁ፡፡
DeleteI got your point and it makes me cry but get ferrous by my self becauses it does not feel me as if I was in ethiopia
ReplyDeleteአዝናኝ ነው
ReplyDeletedegu,it is good mesage keptup.
ReplyDeleteD Daneil Wedet New Yalehew ? America Or Ethiopia ? Lemenfesw Gubae Felgenihi Nebere Yalehibetin Post Adirgilin
ReplyDeleteAhun bemote rndih aynetu tera tiyake comment mehal yiteyekal? Lelelam gize adrashawun sitfelg beWebpagu bestekegn kelay bekul tagegnwaleh. dkibret@gmail.com mobile 251911474503
DeleteDani!Egziabher hail ena birtatun yistih. Mastewalun Yabizalih yichemirlih.
ReplyDeleteDn. Daniel,
ReplyDeleteI will love if you write an article on the exact date of Jesus's birth. I am sure you have enough resources to compile one! It can't definitely be January 7th (according to Julian calender) nor Dec. 25th (Gregorian calender). Our calender is different from both of these but when it comes to Chirstmas it is the same as the former, which doesn't make sense. We celebrate new year on Meskerem 1 but Christmas on Tahesas 29!? Just doesn't make sense!
Looking forward to hearing from you!
Igziabiher yistilign.Indew yeketema nuro yemigerm new. Ines yegeter lij negn ahun ye universty temari sihon wedefit lenuroye yachew geter sayishalegn aykerim. lenantem dingil Mariyam tselotachihun tismachihu.
ReplyDeletegood job
ReplyDeletegood view
but why you keep quite to provide your criyical view and analysis on our church Ethiopia Orthodox Tewahido Church
i mean not your sponsored
view as of last week
but the real and your critical analysis view
i appreciate you, you are my role model and icone
Good bless you
i like this one ለኛ ለከርታታ ዜጎች ከርታታ ቀበሌ ካልተመሠረተልን በቀር ዜግነታችን ጥያቄ ውስጥ ወድቋል፡፡
ReplyDeleteVery interesting Article, But the topic is too heavy for the article.
ReplyDeletebetikikil!
Deleteyih adis guday metsihaf online yelem? endet new linagegnew yeminichilew?
ReplyDeletebe fegegta new yanebebkut. ahun ahun mesakina fegeg malet kebad neber.
ደግሞ ድኻ ምን አድራሻ አለው፡፡ እንዳከራዩት ነው፡፡ ዛሬ ቀበሌ አንድ፣ ከሳምንት በኋላ ቀበሌ አሥራ አምስት፣ ከወር በኋላ ደግሞ ጭራሽ ከተማውን ለቅቆ ሊሄድ ይችላል፡፡ እኛኮ በፈጣሪ ፈቃድ ብቻ አይደለም የምንኖረው፣ በአከራዮቻችንም ፈቃድ ጭምር ነው፡
ReplyDeleteYES YOU ARE RIGHT
DeleteI did not like the topic!!!
ReplyDeleteSOME JOKES LIKE " CITY SCAN"... " Le St. Mary yalegn kiber yemeslegnal.
Dani, 2 or 3 weeks before Christmas day i faced the same plm. they told me that guests are coming from London so that i have to leave. After looking for another house I got a house and in the exact date of CHRISTMAS i entered into. thanks GOD!!! KERTATAW TEKERI ENE NEGN...
BETAM YASASEBEGN GUDAY GIN YEKEBLE METAWEKYA NEW. I AM FROM gojjam. fisrt by kebele id and my home do not match. if i change the id it will be for the 3rd time. ahhhh i am so tired.
ANYWAYS KE TOPIC BESTEKER TEMECHTOHGNAL
ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteድንቅ ፅሑፍ፡፡
‹‹እኛኮ በፈጣሪ ፈቃድ ብቻ አይደለም የምንኖረው፣ በአከራዮቻችንም ፈቃድ ጭምር ነው፡፡ ›› የምትለው ብትስተካካል፡፡
ዳኒ እንኳን አደረሰህ ስለምታነሳቸው ነገሮች በጣም እናመሰግናለን፡፡ ፀጋ ይብዛልህ ድንግል ትጠብቅህ፤ የቤት ነገር ግን በጣም የሚያሳስብ ነው እራስ ወዳድነታችን ጎልቶ የሚታይበት ነው ኮንዶሚኒየም እንኳን የሚደረሳቸው አብዛኛው የፓሪቲ አባል የሆኑ ናቸው ከደረሳቸው በኃላ እንኳን የቀበሌ ቤቱ ሳይለቁ እያከራዩ ይኖራሉ፡፡ እኛም ዛሬ ተከራታች ብንሆንም ነገ ቤት ስናገኝ እንዴት ይሆን የምንሆነው? ማስተዋሉን ይስጠን፡፡
ReplyDeletemin yidereg ,endezih honen BeMinilik hager , not colonized but -----
DeleteMelktu tiru hono sale, keEmebetachin gar yeteyayazebet huneta tinish yebeza yimeslal. እንዴው ድንግል ማርያም በአማላጅነትሽ ምናለ ለኛስ ተዘዋዋሪ ቀበሌ እንዲቋቋምልን ብታደርጊ. yeEmebetachin amalaginetn ezih gar min ametaw?
ReplyDeleteስሟን በከንቱ ባንጠራ!
DeleteYegermal,,, kemetawekiaw gar yetegenagew tsihuf rasu betam mesach new yehuletachunm tsihuf anebebkut yegermal egna gin meche yehon yeminkeyerew melkam astedader metesaseb megbabat metemamen lay yemindersew????
ReplyDeleteFrehiwot ke kotebe
ላጤዎችን እንጂ ልጆች ያላቸውን ኣናከራይም ስለሚሉት ኣካራይዎችስ ምን እንበል? ጉድ ሳይሰማ መስከረም ኣይጠባም?
ReplyDeleteዳኒ እንኮን አደረሰህ
ReplyDeleteምን ይሁን ብለህ ነው, ሰው ማለት መሞቱን የማያስብ ስለሰው የማይጨነቅ አረመኔ ነው.እንደቀልድ አድርገህ ስለሰው ማንነት ሰለአስተማርከን ቃለ ህይወት ያሰማልን.
this one also nice አንዳንዶቹኮ ለግቢያቸው የሚያወጡት ሕግ ከወኅኒ ቤት ሕግ የባሰ ነው፡፡ ማታ ከ12 ሰዓት በኋላ መግባት፣ ጠዋት ከ12 ሰዓት በፊት መውጣት አይቻልም፡፡ በሳምንት ከሁለት ቀን በላይ ልብስ ማጠብ አይፈቀድም፡፡ ማንኛውንም ነገር በኤሌክትርክ መጠቀም አይቻልም፡፡ ሲወጡና ሲገቡ ለባለቤቶቹ ሰላምታ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ቴፕና ሬዲዮ ድምጹን ከፍ አድርጎ መክፈት አይፈቀድም፡፡ ጓደኛ ማብዛት አይቻልም፡፡ እና እዚህ ከመከራየት አንድያውኑ ሂሳቡን ለመንግሥት ከፍሎ ቃሊቲ መታሠር አይሻልም፡፡ eski asebut yete enenure ahune ahunema chuhe chuhe yelagale euuuuuuuuu
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል አንድ ሺህ አንድ የሆኑ ብዙ ዝርዝር ችግሮችን ማውራቱ አስፈላጊ ቢሆንም ቅሉ ግን በራሱ በቂ መፍትሄ አይሆንም፡፡የችግሩ ዋና መንስኤ ደግሞ የምንከተለው ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ስርዓት ውጤት ነው፡፡አዎ የካፒታሊዝም የመጨረሻ ደረጃው ይህ አይነት ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ገፅታ ያለው ስር የሰደደና የተስፋፋ ዘርፈ ብዙ ጦርነት በሽታ ስደት ድህነት እርዛት ኢ-ሰብዓዊነት ኢ-ሞራላዊነት ኢ-ፍትሃዊነት የበዛበት ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ሃይማኖታዊ ተፈጥሯዊ ወዘተ ቀውስ ሁሉ የችግሩ ዋና መገለጫው ምልክት ነው፡፡ካፒታሊዚም የተቀመጠለትን የእድገት ደረጃ (Natural Life Cycle) ሲጨርስ የራሱን መቃብር ይቆፍራል ሲባል መጀመሪያ ግን የብዙሃኑን ድሃ ህዝብ መቃብር ቆፍሮና በዚህ አይነት ስቃይና ቀውስ ግብአተ መሬት ፈፅሞ ነው እንደ ስርዓት እርሱም በተራው ግብአተ መሬቱ የሚፈፀመው፡፡ሌላው ካፒታሊዝም የሚመራበት የህይወታና የፖለቲካ ፍልስፍና ምንድን ነው?መቼም ብዙዎቻችን ነፃ-ገበያና ዲሞክራሲ ነው እንደምንል የሚጠበቅ ነው፡፡ነገር ግን ይህ ብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ የዋህ ምሁርና ፖለቲከኛ የማሞኛ ስልት ነው፡፡እውነታው ከዚህ የተለየ ነው፡፡
ReplyDeleteካፒታሊዝም የሚመራው “The fittest individual or group under any cost (misery, death, impoverishment) of others and under any means (war, deception, oppression, manipulation) wins and survives in life.” በሚለው የዳርዊን Natural Selection አስተሳሰብና ማንኛውም ነገር(ሰውንም ጨምሮ) ለገንዘብ ስለገነዘብ በገነዘብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ገንዘብን የበለጠ ለማከማቸት ሲባል በዚህ ስሌትና ሂደት ውስጥ እንደ ግብአት የሚያገለግል ሸቀጥ ነው በሚል መርህ ነው፡፡ካፒታሊዝም በዚህ አይነት ኢ-ሰብዓዊነት የጎደለው ኢ-ፍትሃዊ ፍልስፍና የሚመራ አለም አቀፍ ስርዓት ነው፡፡የደርግ ስርዓትን መውደቅ ተከትሎ ኢትዮጵያም በሯን በርግዳ ተመክሮበትና በውዴታ ሳይሆን በግዳጅ ተጭኖባት የተቀበለችውና ላለፉት 21 ዓመታትና አሁንም እያራመደችው ያለቸው ይህንን አይነት ስርዓት ነው፡፡ኪራይ ሰብሳቢነት ሙስና እንደዚሁም መሪዎቻችን ሲሰርቁ መያዝ እንጂ መስረቅ ነውር አይደለም እያሉ በአደባባይ የተናገሩለት ቅኔው በተዘዋዋሪ የዚህን ስርዓት ውስጣዊ አይቀሬ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡በምእራቡ አለም ያለውና በካፒታሊዝም ፍልስፍና ስር የሚቀነቀነው ግለሰባዊ ነፃነት ለእኛ አይነቱ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብና ለተቀረውም አፍሪካዊና የታዳጊው አለም የማህበረሰብ አወቃቀር ጋር ፈፅሞ የሚጣጣም አይደለም፡፡በዚህ በቅጡ ሳንመክርበት በራችንን በርግደን በተቀበልነው ኢ-ሰብዓዊና ኢ-ፍትሃዊ የሆነ አለም አቀፍ የካፒታሊስት ስርዓት የተነሳ ኢትዮጵያዊ የሆነው የማህበረሰብ አወቃቀራችን (Social Structure and Social Fabric) ቀስ በቀስ እየተቃወሰና እየተዳከመ በስተመጨረሻም እንደ ሀገር ለመቀጠል በሚቸግር የመበታተን አደጋ ውስጥ የሚከተን ነው የሚሆነው፡፡ስለዚህም መፍትሄው ዳግም የሶሻሊዝምን መልካም እሴቶች በሰከነ መንገድ እንዲያንሰራሩ ማድረግ ነው፡፡ክርስትና እኮ በራሱ ሶሻሊዝም ነበር ሲመሰረት፡፡የክርስቶስንና የተከታዮቹን የሃዋርያትን ህይወት በራሱ በጥሞና ስንመረምር እኮ በአብዛኛው ሶሻሊስታዊ(Social=ማህበራዊ) ነበር፡፡ሶሻሊዝም እምነት የለሽ ነው እየተባለ የሚወራው ወሬ የሸፍጠኞቹ የካፒታሊስቱ ልሂቃን መሰሪ ፕሮፖጋንዳ ነው፡፡መረን የለቀቀውና ኢ-ሰብአዊነት የተሞላበት የምእራቡ አለም የካፒታሊስት ስርዓት ግለሰባዊ ነፃነት(Unbridled and insane instinctive and barbaric Individualism) እና ሊበራል-ዲሞክራሲ ቅኔው በቅጡ የገባን አይመስለኝም፡፡ይህ አካሄድ ሰው ማህበራዊ እንስሳ ነው የሚለውን የተፈጠሮ ህግ የሚቃረን ጭምር ነው፡፡ዛሬ በሀገራችን ባእድ የሆነና ሰይጣናዊ የሆነ ጭካኔና ዘመናዊ አውሬነት የገነነው አንድ የሆነ ግራ የሚያጋባና በቅጡ ያልተረዳነውን ከውጪ የመጣና የተጫነብንን ስርዓት እያራመድን ስለሆነ ነው፡፡እንደ ማህበረሰብና አንደ ሀገር አንድ አድርጎ ለዘመናት ያቆመንን ማህበረሰባዊ ማንነታችን ትስስራችንንና እና መስተጋብራችንን በቅጡ ባልገባን የባእድ መጤ የህይወት ዘይቤ የተነሳ ቀስ በቀስ እያጣነው ነው፡፡በእውነት ለመናገር ምን እየተፈጠረና ምን እያደረግን እንደሆነ በራሱ የገባን አይመስለኝም፡፡በአርአያ ስላሴ ሰው ሆነን የተፈጠርንበትን የሰውነት መለኮታዊ ባህሪ እየለቀቅን የነበረን Life-Force ቀስ በቀስ እያጣን በምትኩ በቁሳቁስ ግፊት የምንመራ ፈረንጆች እንደሚሉት Unconscious Zombie እየሆንን ነው የመጣነው፡፡የሰው ክቡርነት ዛሬ በሀገራችን የአንድ ብልጭልጭ ቁሳቁስን ያህል አይቆጠርም፡፡በእምነታችንና በሃይኖማታችን ድርና ማግነት ጭምር የተሰራው ኢትዮጵያዊነታችን ወደ መጥፋት ደረጃ ነው የደረሰው፡፡ሃይማኖታችን ጭምር በራሱ ዛሬ በገንዘብ ማእቀፍ ውስጥ እንዲወድቅ እየሆነ ነው፡፡አሁን በሀገራችን ያለው ሁኔታ ሰዎች በደመ-ነፍስ(Instinctive and Impulsive Subconscious Drive) የመኖርና ያለመኖር የህይወት ትግል ውስጥ ያሉበት ፈታኝ ወቅት ነው፡፡እራስን ለማዳን ባለው የህይወት ግብግብ ውስጥ ውንብድናው ሙስናው ጭካኔውና ይሉኝታ ቢስነቱ ከዚህ የተነሳ ነው፡፡አሁን ያለው ሁኔታም ልክ እንደ ጫማው ማስታወቂያ ቅድሚያ ከኮርማው አደጋ ማምለጥ ነው ለጫማው በኋላ ይታሰብለታል አይነት ነው፡፡
አዎ ግሎባል ካፒታሊዝም ደግሞ የሰውን ልጅ ወደ ዚህ አይነት ዘመናዊ የቀን አውሬነት እየቀየረው ነው፡፡አዎ ሰው ሰውን የሚበላበት ዘመን፡፡አበላሉ ግን በቀርፅ እንጂ በይዘት ከአውሬነት ባህሪ ብዙም የተለየ አይደለም፡፡መጨረሻው ደግሞ በዚህ መረን የለቀቀ ውስጣዊ ያልተገራ እንስሳዊ ባህሪ ግፊትን ለማስተናገድ በሚደረግ ከንቱ መፍገምገምና ምድራዊ ቁሳቁስን የማግበስበስ እንስሳዊ ባህሪ የተነሳ ሰው በአርአያ ስላሴ የተፈጠረ ክቡር ፍጡር መሆኑን እንዲስት ማድረግ ነው፡፡የ666 መጨረሻውም ደግሞ ሰው ለስጋው ምቾትና ለሆዱ ሲል አምላኩን እንዲስት የሚገደድበት ፈታኝ ሁኔታ እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፡አዎ በሀገራችንም የፓርቲ አባል ካልሆንክ ቤት ስንዴ ዘይት ስራ ወዘተ አታገኝም እየተባለ አይደለምን፡፡ይህስ የኛው ጉድ የ666 ፈር ቀዳጅ 222 ወይንም 333 መሆኑ ነውን?
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡
You writer, OMG,please write more , i think you have capable of writing and you have more idea, i like your message, thank you
Deleteኪራይ ሰብሳቢነት ሙስና እንደዚሁም መሪዎቻችን ሲሰርቁ መያዝ እንጂ መስረቅ ነውር አይደለም እያሉ በአደባባይ የተናገሩለት ቅኔው በተዘዋዋሪ የዚህን ስርዓት ውስጣዊ አይቀሬ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡በምእራቡ አለም ያለውና በካፒታሊዝም ፍልስፍና ስር የሚቀነቀነው ግለሰባዊ ነፃነት ለእኛ አይነቱ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብና ለተቀረውም አፍሪካዊና የታዳጊው አለም የማህበረሰብ አወቃቀር ጋር ፈፅሞ የሚጣጣም አይደለም፡፡በዚህ በቅጡ ሳንመክርበት በራችንን በርግደን በተቀበልነው ኢ-ሰብዓዊና ኢ-ፍትሃዊ የሆነ አለም አቀፍ የካፒታሊስት ስርዓት የተነሳ ኢትዮጵያዊ የሆነው የማህበረሰብ አወቃቀራችን (Social Structure and Social Fabric) ቀስ በቀስ እየተቃወሰና እየተዳከመ በስተመጨረሻም እንደ ሀገር ለመቀጠል በሚቸግር የመበታተን አደጋ ውስጥ የሚከተን ነው የሚሆነው፡፡ስለዚህም መፍትሄው ዳግም የሶሻሊዝምን መልካም እሴቶች በሰከነ መንገድ እንዲያንሰራሩ ማድረግ ነው፡፡ክርስትና እኮ በራሱ ሶሻሊዝም ነበር ሲመሰረት፡፡የክርስቶስንና የተከታዮቹን የሃዋርያትን ህይወት በራሱ በጥሞና ስንመረምር እኮ በአብዛኛው ሶሻሊስታዊ(Social=ማህበራዊ) ነበር፡፡ሶሻሊዝም እምነት የለሽ ነው እየተባለ የሚወራው ወሬ የሸፍጠኞቹ የካፒታሊስቱ ልሂቃን መሰሪ ፕሮፖጋንዳ ነው፡፡መረን የለቀቀውና ኢ-ሰብአዊነት የተሞላበት የምእራቡ አለም የካፒታሊስት ስርዓት ግለሰባዊ ነፃነት(Unbridled and insane instinctive and barbaric Individualism) እና ሊበራል-ዲሞክራሲ ቅኔው በቅጡ የገባን አይመስለኝም፡
Thank you dear writer. This was more intelectual and precise to explain our social and economical problems. Please write more or let us know if you have a blog to share with. I am looking for people who writes such ideas in Amharic so that I can read and understand it well.
DeleteTilikua deha tinishuan deha atiwedatim Alu. Betam Eyazenku yemilew binor ken siyagegn yegna sew kifu new. Lerasu wegen yemayihon. Kezih yebelete kifat yelem.
ReplyDeleteEne gin ahun ahun degu ethiopiawin Nafeku yemayew hulu fetariwun yemayifera gifegna bicha new. Bigebachew eko libis aytew sewun kemegemet sinesiriatih tihitinah begezachew. HODAMOCH Ante eko lelijochawu astemari, yetefa tarikachinin astawash temeramari, Talak sew neh ,legna le Ethiopia
Egizer lib yistachew
ዲያቆን ዳንኤል ጽሑፍህን በጣም ነው የማደንቀው እግዚአብሔር አብልጦ እንድታገለግል ያድርግህ ይህ ጽሑፍ ለበዓሉ በጣም የሚስማማ ይሆናል ብዬ በማሰብ በተለይ በአንተ ተተርጉሞ ቢፃፍ ብዞዎችን ይዳስሳል በማለት ኮሜንት ላደርግ ተነሳሳሁ
ReplyDeleteAs you well know, we are getting closer to my birthday. Every year
there is a celebration in my honor and I think that this year the
celebration will be repeated. During this time there are many people shopping
for gifts, there are many radio announcements, TV commercials, and in
every part of the world everyone is talking that my birthday is getting
closer and closer.
It is really very nice to know, that at least once a year, some
people think of me. As you know, the celebration of my birthday began many
years ago. At first people seemed to understand and be thankful of
all that I did for them, but in these times, no one seems to know the
reason for the celebration. Family and friends get together and have a lot
of fun, but they don't know the meaning of the celebration.
I remember that last year there was a great feast in my honor. The
dinner table was full of delicious foods, pastries, fruits,
assorted nuts and chocolates. The decorations were exquisite and there were
many, many beautifully wrapped gifts. But, do you want to know
something? I wasn't invited. I was the guest of honor and they
didn't remember to send me an invitation.
The party was for me, but when that great day came, I was left
outside, they closed the door in my face......... and I wanted to be with
them and share their table. In truth, that didn't surprise me because in
the last few years all close their doors to me.
Since I was not invited, I decided to enter the party without
making any noise. I went in and stood in a corner. They were all drinking;
there were some who were drunk and telling jokes and laughing at
everything. They were having a great time. To top it all, this big fat man all
dressed in red wearing a long white beard entered the room yelling
Ho-Ho-Ho! He seemed drunk. He sat on the sofa and all the children
ran to him, saying : "Santa Claus, Santa Claus"... as if the party
were in his honor !
At 12 midnight all the people began to hug each other ; I extended
my arms waiting for someone to hug me and .... do you know .... no
one hugged me. Suddenly they all began to share gifts. They opened them
one by one with great expectation. When all had been opened, I looked
to see if, maybe, there was one for me.
What would you feel if on your birthday everybody shared gifts and
you did not get one ? I then understood that I was unwanted at that
party and quietly left. Every year it gets worse. People only remember to
eat and drink, the gifts, the parties and nobody remembers me. I would
like this Christmas that you allow me to enter into your life. I would
like that you recognize the fact that almost two thousand years ago I
came to this world to give my life for you, on the cross, to save you.
Today, I only want that you believe this with all you heart.
I want to share something with you. As many didn't invite me to
their party, I will have my own celebration, a grandiose party that no
one has ever imagined, a spectacular party. I'm still making the final
arrangements. Today I am sending out many invitations and there is
an invitation for you. I want to know if you wish to attend and I will
make a reservation for you and write your name with golden letters in my
great guest book. Only those on the guest list will be invited to
the party. Those who don't answer the invitation, will be left outside.
Do you know how you can answer this invitation? it is by extending
it to others whom you care for...
I'll be waiting for all of you to attend my party this year...
See you soon .... I love you !
-Jesus
Thank you Lord for giving us your Son, Jesus Christ and his mother, Mary. Please, Lord help us to know/remember the reason why we celebrate your Birthday everyday. Thank you, Lord for giving me fathers, mothers, brothers and sisters who can share/pass your good messages and make me think good thoughts in return. Please, Lord Bless us and Guide our lives. Amen.
DeleteYegaremal Daniel
ReplyDeleteThanks Dani ... interesting point and view as always!
ReplyDeleteየኛ ሠፈር ደላሎች እንኳን በመኪና ስትመጭና በእግርሽ ስትመጭ፣ ዝንጥ ብለሽ ስትመጭና እንደነገሩ ሆነሽ ስትመጭ ፈገግታቸው ይለያል::
ReplyDeleteለስጋው ምቾትና ለሆዱ ሲል አምላኩን እንዲስት የሚገደድበት ፈታኝ ሁኔታ እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፡አዎ በሀገራችንም የፓርቲ አባል ካልሆንክ ቤት ስንዴ ዘይት ስራ ወዘተ አታገኝም እየተባለ አይደለምን፡፡ይህስ የኛው ጉድ የ666 ፈር ቀዳጅ 222 ወይንም 333 መሆኑ ነውን?
ReplyDeletethank you Diakon!!!!
ReplyDeleteዳኔ የጌታ እናት አትለይህ።
ReplyDeletetnsh sakugn, thnx.
ReplyDeleteDani i like it !! you know i am very frustrating now a days!!i am a new groom and when i think of that i feel as if marriage is wrong.
ReplyDeleteGod bless Ethiopia and Ethiopian !!
ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteድንቅ ፅሑፍ፡፡
‹‹እኛኮ በፈጣሪ ፈቃድ ብቻ አይደለም የምንኖረው፣ በአከራዮቻችንም ፈቃድ ጭምር ነው፡፡ ›› የምትለው ብትስተካካል፡፡
American endemetan bet lemekerayet senteyek
ReplyDeleteandua lejachu meblat jemraleh alchen betam yasazenal................
ሰላም!
ReplyDeleteወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል "....እንዴው ድንግል ማርያም በአማላጅነትሽ ምናለ ለኛስ ተዘዋዋሪ ቀበሌ እንዲቋቋምልን ብታደርጊ፡፡ ...". ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው? አምናለሁ በምልጃዋ አትጠራጠርም። እኛኮ በፈጣሪ ፈቃድ ብቻ አይደለም የምንኖረው፣ በአከራዮቻችንም ፈቃድ ጭምር ነው፡፡ ስትልስ? እንዴት ያለ ስብከት ነው? እኔ እንደውም "ይድረስ ለቅድስት ድንግል ማርያም" ብለህ ስትጀምር በአንቀአዶ ኅሊና ወስደህ ነገረ ልደቱን ልትነግረን፤ የነበረውን ሁኔታ በመልእክት መልክ ልታስረዳን መስሎኝ. የነገሩ ዓላማ እና ርዕሱ ጋር ስላልሆነልኝ አዘንኩ። ቢታረም እላለሁ።
አንዳንድ አከራዮች የቤታችንን ወጪ ሁሉ ሊቆጣጠሩ ይፈልጋሉ...አመጋገብ ጨምረሻል ይህ ደሞ የውሀ ፍጆታ ይነካል የሚሉም አሉ...እመቤቴ ማደሪያ ታዘጋጅልን እንጂ......
ReplyDeleteአምላካችን ድንቅ አምላክ ነው ሁሉን ያያል ባላሰብክበት ጊዜ ሁሉን ነገር ያሟላልሀል ባዶ እጅ ብትሆንም ሁሉን ነገር ይሞላልና አንድ ቀን ባልጠበቁት ጊዜ ምንም ሳይኖርህ በማይመረመር ጥበቡ በባዶ እጅህ ባለቤት ያደርግሀልና ፀልይ የአምላካችን ስራ ከአይምሮ በላይ ነው ሁሉን ነገር መቻል ነው ያለማዘን ነው አንድ ቀን ባለቤት ትሆናለህ ተስፋ አትቁረጥ!!!
ReplyDeleteDear Dn Daniel I really happy with your idea and interesting message. You write what we are facing. Our state is not from this land that why virgin Mary and her son Jesus has no constant place to leave or get rest, they select Bethalehem cave. thank you!
ReplyDelete