Friday, January 4, 2013

የባለ አእምሮ ሥራ እንሥራ
ቀሲስ ስንታየሁ አባተ

በግብፅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወኪል

 ይኽን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሳሣኝ ነገር በቅርቡ ቤተ ክርስቲያናችንና አባቶቻችን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን አስመልክቶ በተለያዩ የጡመራ ዐውዶች የሚለቀቁ ጽሑፎች ናቸው። እነዚህን ጽሁፎች ትክክል ናቸው ወይም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን አባቶች አስመልክቶ እየተባለ ያለው ነገር ትክክል ነው ወይም ሐሰት ነው ለማለት አይደለም፡፡
 በመሠረቱ ሰው የመሰለውንና ያመነበትን ሐሳብ የማቅረብ መብት አለው። ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቸረው የነጻ ምርጫ ፈቃድ አለውና ነው። ይኽን መብቱን ተጠቅም ይኽን ወይም ያንን ደግፎ ወይም ነቅፎ መናገር ይችላል። በሚናገርበት ወይም በሚጽፍበት ወቅት ግን ያ ሐሳቡ በእውነተኛ መረጃ ላይ ስለ መመስረቱ እርግጠኛ መሆን አለበት። እርግጠኛ ካልሆነ ግን ራሱን አሳስቶ ሰሚውንም ሆነ አንባቢውን ሊያሳስት በዚህም ለባልንጀራው መሰናክል ስለ ፈጠረ በእግዚአብሔር ዘንድ ይጠየቃል።


ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ሰዎች ስለሚናገሩት ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን የሚጠየቁ መሆናቸውን አስተምሯል። ከንቱ ነገርም ለሰሚውም ሆነ ለተናጋሪው አንዳች ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕይወት ጠቀሜታ አልባና እውነተኛነት የሌለው ነገር ነው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ “አትግደል” በሚለው ትእዛዘ እግዚአብሔር ላይ በሰጡት ማብራርያ አንዳንድ ሰዎች ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ሐሳብን በነጻነት ሆነው በጽሑፍ የመግለጥ መብት ተጠቅመው የብዙዎችን ስም በማጉደፍና ገመና በመግለጥ ቅስምም በመስበር መግደላቸውን ገልጠዋል።
 ባለፈው ሳምንት በአንዱ የጡመራ መድረክ የወቅቱን የቤተ ክርስቲያናችንን ሁኔታ ማለት የሽምግልናውንና ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ እየተደረገ ያለውን አንዳንድ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ተቃውሞአቸውን የሚገልጡትን ወይም የገለጡትን ተቃውሞ መልሰው የሚቃወሙትን በቃለ እግዚአብሔር አስታኮ በማሸማቀቅ ሕዝቡ አንዳች እንቅስቃሴ ከማድረግ ይልቅ በጸሎት ብቻ ችግሩ ይፈታል ብሎ እጁንና እግሩን አጥፎ እንዲቀመጥ የሚያደርጉ ለዚህም የተደራጁ አካላት መኖራቸውን ሳነብ እጅጉን ገርሞኝ ነበር።
 ይኽን ጽሑፍ የጻፈው አካል የመጻፍ መብቱ የተጠበቀ ነው። ግን ፀሐፊው እንደገለጠው ይኽን ለማድረግ የተደራጀ አካል ለመኖሩ ምን ያኽል ርግጠኛ ነው? በትክክል እንደ ተባለውም ያ ተደራጀ የተባለው አካል ካለ ቃለ እግዚአብሔርን የራስን አመለካከት ማሳኪያ አድርጎ በመውሰዱ ከፍርድ ሊድን ይችላልን? ይኽን የተሳሳተ መንገድ እንደ በጎ አካሄድ አድርገው የሚጠቀሙ አንዳንድ ግለሰቦች ቢኖሩ እንኳን ያን ያክል ቦታ ሰጥቶ እንደ አንድ የተደራጀ ቡድን ወይም አካል አግዝፎ በጡመራ መድረክ ላይ መግለጡ ራሱ ለእኔ እንዲህ ዓይነቱን አካሄድ ላላሰቡት ሳይቀር ማሳሰብ መስሎ ይታየኛል።
 አሁን አንድ ነገር ብናስብ ጥሩ ይመስለኛል። ቤተ ክርስቲያናችንን አባቶቻችንን የሚያምሰው ችግር አንዳንዶች እንደሚያስቡት አባቶች መንፈሳዊነትን አጥተው ወይም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት አይሎ አይመስለኝም። እግዚአብሔርን ያላስደሰትንበት አንዳች ጉድለት ይኖራል ብየ አምናለሁ። እግዚአብሔር ለሕጉና ለፈቃዱ ቀናተኛ አምላክ ነው። በገዛ ደሙ የዋጃቸው ምእመናን ከአሕዛባዊ የኖሮ ሥርዓት ርቀው በቀናነትና በንጽሕና እንዲያመልኩት ይፈልጋል። ይኽ አልሆን ሲል ግን ወደ በጎ ፈቃዱ እስኪመለሱ ድረስ ለማይመች አካሄድ ኣሳልፎ ይሰጣል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለክብሯ የማይገባ ነገር ሲፈጸም እኛ ካህናት በንጽሕና ማገልገል ሲሳነን፣ ሥርዓቱ ሲጓደል፣ እምነት ጠፍቶ ማስመሰል፣ መሞዳሞድና መመሰጋገን ሲበዛ እግዚአብሔር ቋንቋችንን ይደበላልቀዋል። ስለ አንድ ነገር በአንድ ቋንቋ እየተነጋገርን እንዳንግባባ ማስተዋሉን ይነሣናል። እስቲ ራሳችንን እንጠይቅ፤ ከመቅደስ እስከ ዓውደ ምሕረቱ ያለው አገልግሎት በእምነትና በፍቅር ይፈጸማል? በትዳራችን፣ በማኅበራዊ ኑሮአችን፣ በሥራ ገበታችን፣ በጓደኝነታችን ታማኝነትና እውነት አሉ? መታመንን ሰብከን እምነት አጉዳይነትን ገንዘብ ካደረግን፣ ፍቅርን አስተምረን ጥላቻን በልቡናችን ካነገሥን፣ ከእግዚአብሔር፣ ከሕዝብና ከመንግሥት አደራ ተቀብለን አደራ ካጎደልን፣ ዘረኝነትን በአደባባይ ኰንነን በመካከለችን ዘረኝነትን መሸሸጊያ ካደረግን……እግዚአብሔር እንመለስ ዘንድ በትንሹ ይቆነጥጠናል።
ለእኔ አሁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሆነ ያለው እገሌ ብለን ጣታችንን የምንቀስርባቸው ሰዎች ያመጡት ሳይሆን የሁላችን የኀጢአት ውጤት ነው ብየ አምናለሁ። ስለዚህ አሁን ጊዜው የመነቃቀፊያ አይደለም፤ የንስሐ እንጂ።
 የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ካልዓይን መርጣ መሾሟን አብዛኛው ሕዝባችን ያውቀዋል። ብዙዎቻችንም አሁን በቤተ ክርስቲያናችን እየተከሰተ ላለው ጊዜያዊ አለመግባባት ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ እንድንወስድ ባገኘነው አጋጣሚ ሐሳብ ስንሰጥ ይስተዋላል። መልካም ነው። ጥሩ ጥሩውን ከጎረቤት መውሰዱ ተገቢ ነው። ታድያ ምሳሌነታቸውን ስንወስድ በመገናኛ ብዙኀን የተገለጠውን ብቻ መሆን የለበትም። ያ ፍጻሜው ያስደስት የነበረው የፓትርያርክ የምርጫ ሥነ ሥርዓት ለዚያ የበቃው በየት በየት አልፎ ነው? ብለንም መጠየቅ ይገባናል።
ባለፈው ኮፕቶች ባደረጉት የፓትርያርክ ምርጫ ለውድድር የቀረቡት አሥራ ሰባት ሰዎች ነበሩ። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱን የምርጫ ሕግ አንጠርጥረው ቢያውቁም ምክንያቱን ለማወቅ በማይቻል ሁኔታ ሕጉ ባይፈቅድላቸውም፡ (ለምሳሌ ሀገረ ስብከት ያላቸው፣ ከዚህን ቀደም ፓትርያርክ ለመገልበጥ የሞከሩ) ሳይቀሩ በራሳቸው አነሣሽነት ተመዝግበው እስከ መጨረሻው ድረስ ሲወዳደሩ ነበር። ከእነዚህ ተወዳዳሪዎች መካከልም አንዳንድ የመንግሥት ባለ ሥልጣናትን በመያዝ ዓቃቤ መንበረ ፓትርያርኩን ማለት ብፁዕ አቡነ ጳኵሚዎስን ጫና ሊያደርጉባቸው ያስፈራሯቸው እንደ ነበሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ያስረዳሉ። ሌላ በኩል ደግሞ የወጣቶች ጉዳይ ጳጳስ የሆኑት ተወዳጁ ብፁዕ አቡነ ሙሳን የመሳሰሉት ደግሞ ከአንዴም ሁለቴ እንዲወዳደሩ ቢጠየቁ “እኔ አሁን ዕድሜየ ሰባዎቹ ውስጥ ገብቷል፤ አሁን እኔን ሾማችሁ ገና ደስታችሁን ሳትወጡ ብሞት ለሌላ ድካምና ወጪ ትዳረጋላችሁ። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ እኔ አባቴ ብፁዕ ወቅዱስ ሺኖዳ ሣልሳዊ በተቀመጠበት መንበር እቀመጥ ዘንድ ብቁ አይደለሁም” ብለው ራሳቸውን ከተወዳዳሪነት ያገለሉ ጀግኖችም ነበሩ።
  በአንድ ወቅት ጫናው የበዛባቸው ብፁዕነታቸውም ነገሩ እንዲካረር ለሚያራግቡ የመገናኛ ብዙኀንና ጫናውን በተለያዩ መንገዶች ለሚፈጥሩ የውስጥና የውጪ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው ካልታቀቡ እየተደረገ ያለውን ነገር ለሕዝባቸው አስታውቀው ወደ ገዳማቸው እንደሚመለሱ በይፋ ተናገሩ።
አቡነ ጳኩሜዎስ ከዚሁ መግለጫቸው ጎንም በሦስት የተለያዩ ጊዜያት ለሦስት ሦስት ቀናት የሚቆይ የጾምና የጸሎት ጊዜ አውጀው ነበር። እዚህ ላይ ትልቁ ነገር የምሕላ ጊዜ ማወጃቸው ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የሚገኙ የኮፕቲክ ኦርቶዶከስ አባለት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ እስከ ተራው ምእመን ድረስ እንዲሳተፍበት ያደረጉበት ጥበብ ነው። በእነዚያ የጾምና የጸሎት ዕለታት የጳጳሳቱ፣ የካህናቱና የምእመናኑ ውሎ በቤተ ክርስቲያን ነበር። ይኽ ማለት መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት የሱባኤው ተሳታፊዎች ነበሩ ማለት ነው። ይኽ ማለት ዕለቱን በሰዓታት ከፈለው ሰዓታት ይቆሙበት፣ ጸሎተ ምሕላ ያደርሱበት፣ ቅዳሴ ይቀድሱበት፣ ትምህርት ያስተምሩበት፣ ሕዝቡን ያወያዩበት ነበር ማለት ነው። በተለይ በካይሮ በሚገኙ ታላላቅ አድባራትና በሀገሪቱ በሚገኙ ገዳማት ጾሙ ጸሎቱ ይመራ የነበረው በሊቃነ ጳጳሳቱ ነበር። ከሥራቸው ጠባይ የተነሣ በመደበኛው የጸሎት ጊዜ መገኘት ያልቻሉ ሰዎች ወይ የዓመት ፈቃድ ወስደዋል፤ ወይ ደግሞ መላ ሌሊቱን ይደረጉ በነበሩት ጸሎቶች ላይ ተሳትፈዋል።
 የሱባኤው በሦስት ጊዜያት መካፋፈል ሁሉም በጉጉት እንዲጠባበቀው ታላቅ አስተዋጽዖ አድርጓል።
 እንግዲህ ያ እንደዚያ አምሮና አስለቅሶን የተፈጸመው የግብፅ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክ ምርጫ እነዚህን ሁሉ ጫናዎች ይኽን በመሰለ ጾምና ጸሎት እንባና ዋይታ መፈጸሙን ልብ በሉልኝ። የእኛስ? እግዚአብሔር ይመስገን ከ20 ዓመታት ቆይታ በኋላ ቅዱስ ሲኖዶሱ የምሕላ ዐወጅ ዐውጆ ነበር። እስቲ ከላይ በገለጥኩት አፈጻጸም መዝኑት። አበውን እንድንነቅፍ አይደለም፤ ለወደፊቱ ግን አንድ ምሕላ ሲታወጅ አስፈጻሚው፣ አፈጻጸሙ፣ ሁሉን አሳታፊነቱ (ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ሳይቀር) የጊዜው ርዝማኔ…. ከግምት ሊገባ ይገባዋል። ሠራተኛውም ከአባቶቹ ጋር በቤተ ክርስቲያን አድሮ በጸሎቱ እንዲሳተፍ ሁኔታዎች ቢመቻቹለት የእኔነቱን ያጎለብተዋል ብየ አምናለሁ።
 ወደ ግብፅ ቤተ ክርስቲያን እንመለስ። ጥቂት ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት ሕጉ በማይፈቅድ አካሄድ ለምርጫ መመዝገባቸውን ሕዝቡ ያውቅ ነበር። ዓቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ላይ ያደረሱትን ጫና ያውቅ ነበር። ግን ላግልላችሁ አላለም። ሁሉን ወደሚያውቅ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው ፈጣሪው ግን አነባ፤ ዛሬ ከፉ ብሎ የትናንት መልካም ሥራቸውን አሽቀንጥሮ ገደል ውስጥ አልወረወረም። ዛሬም እንደ ቀድሞው ይወዳቸዋል።
 እኛስ? ሰሞኑን የተወሰኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የምርጫውን መዘውር ራሳቸው በፈለጉት መንገድ እየዘወሩት ነው ተብሎ ከመስጋት ያለፈ የትችት ቃላት በአንዳንድ የጡመራ መድረኮች ላይ ስማቸውን ጭምር በመጥቀስ ተሰንዝሮ አየሁ። አሁንም የሌላውን መብት እንዳልጋፋ ፀሐፍያኑ ለምን እንደዚህ አሉ? ብየ አልወቅስም። በርግጥ ፀሐፍያኑ ያንን ነገር ሲጽፉ ለሚቆረቆሩላት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከማሰብ አንጻር ሊሆን ይችላል። ግን አንድ ነገርም እናስተውል። እነዚህ አበው ትናንት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አንዳች መልካም ሥራ አልሠሩምን? እኒያ ትናንት መልካም ሥራ የሠሩ አበው እንደ ሰውነታቸው ደክመው ቢስቱ (መሳሳታቸውን እግዚአብሔር ብቻ ቢያውቀውም) የእኛ መልስ መኰነን ነው ወይ? እነዚህ አበው ከባድ በሆነ ፍቅረ ሢመት ተያዙ እንበልና ልንጸልይላቸው ወይስ ልንጸልይባቸው ነው የሚገባው?
 ለቤተ ክርስቲያን፣ ለሃይማኖት፣ ለወገኖች የሚኖረንን ቅናት ገንቢና መንፈሳዊ በሆነ መንገድ ብቻ መግለጥ ያለብን ይመስለኛል። ስሕተት ተፈጽሟል ብለን ስሕተትን በስሕተት ለማረም መነሳሣት አግባብነት የለውም። ያ ከሆነ መጽሐፍ “ኵሉ ዐረየ ወኅቡረ ዐለወ” እንዳለው ይሆንብናል።

ስለዚህ ምን እናድርግ?
1.        አባቶቻችን አጠር አጠር ባሉ ጊዜያት የተከፋፈሉ የምሕላ ጊዜያት እንዲያውጁልን እንጠይቅ፤ ምሕላው ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ሁሉን አሳታፊ እንዲሆን ማድረግ
    2.  ሁላችንም ምሕላውን በንስሐና በፍቅር እንጀምር
         -ምናልባት ሁላችንም ሲባል እንደ ድፍረት ባይቆጠርብኝ። ምክንያቱም አበው “ከገቢር
          ቢነፁ ከኀልዮ አይነፁ” ይላሉና ነው። እርስ በርሳችን እኔ የኬፋ እኔ የአጵሎስ ብለን
         ብንጀምረው ፍቅር ስለሚጎድለን ልመናችን ቅድመ መንበሩ አያርግልንምና ነው።
2.      አባቶቻችንን ከምንወቅሳቸው በፍቅር ቀርበን መሆን አለበት የምንለውን ምክንያታዊ
በሆነ መልኩ ብናስረዳቸው። ምናልባት እኛ አይተን እነርሱ ያላዩት፣ እነርሱ አይተው
እኛ ያላየነው ነገር ሊኖር ይችላልና።
3.      ያቅማችንን ፍፁም መንፈሳዊ በሆነና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በተከተለ አካሄድ ከተወጣን የተቀረውን በሙሉ እምነትና ተስፋ ለእግዚአብሔር እንስጠው
4.      ብፁዓን አባቶችም ለመጨረሻው ውሳኔ ሳትቸኩሉ ይኖራሉ ተብለው የሚታሰቡ የመፍትሔ አሳቦች እንዳሉ ከልጆቻችሁ ጋር በመነጋገር አሉ በተባሉ የመፍትሄ አሳቦች ላይ ለመነጋገር ዕድል ስጡ።
የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ምእመናን ከውስጥ ከውጪ ያሉባቸውን ጫናዎች ተቋቋመው የቀደሙት አበው የሠሩላቸውን ቀኖና አክብረው ለዓለም ኅብረተስብ ቤተ ክርስቲያኒቷ በትክክል በክርስቶስ ዓለትነት መመሥረቷን፣ እነርሱም በትክክል የቅዱሳን አባቶቻቸው ልጆች መሆናቸውን አሳይተዋል። ኢትዮጵያ ሀገራችን የሥልጣኔና የአምልኮ ጀማሪ መሆኗን፣ ሕዝቦቿም ሕግንና ሥርዓትን ጠንቅቀው የሚያውቁና የሚፈጽሙ መሆናቸውን ታላላቅ የዓለም ታሪክ ፀሐፊዎች ሳይቀሩ መስክረዋል።
እንግዲህ በእግዚአብሔርና በዓለም ሕዝብ ፊት ማንነታችንን የምናሳይበት ጊዜው አሁን ነው። ታሪክ ከመቃብር በላይ ይኖራል። ማንኛውም ዓይነት ሥራችንም በእግዚአብሔር ዘንድ ይቆየናል። ስለዚህ መለያየትን መነቃቀፍን አስወግደን በፍቅርና በእምነት ሰንሰለት ታስረን ለወገኔ ይጠቅማል ሳንል ወይም በጊዜያዊ ነገር ሳንደለል ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመጪው ትውልድ ከነ ሙሉ ክብሯ ለማስተላለፍና የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማስፋት የሚያስችለንን የምእመንና (የአማኝ) የባለ አእምሮ ሥራ እንሥራ።

ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ተራዳኢነት አይለየን። አሜን።


47 comments:

 1. እንዲህ ማስተዋል በታጣበት ዘመን የሚያስተውል፣ የሚያረጋጋ፣ የሚያጽናናም አለ ለካ! ቃለ ሕይወት ያሰማልን ቀሲስ፡፡

  ReplyDelete
 2. ዳንኤል

  ሠሞኑን መጣጥፎችህ ሲዘገዩ ምን ሆነህ ነው ብየ ነበር

  መድሐኒዓለም ክርስቶስ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት

  ቀናኢ የሆኑትን እና ጥበበኛ አባት ይስጠን፡፡

  ሰው ፊትን ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል፤

  ይህን ያልኩት አንድ የቤተክርስቲያናችን ልጅ

  የስብከተ ወንጌል ሀላፊ ሆንኩ እያለ በደስታ ሲፈነጥዝ

  ስላየሁት ዛሬ ቤተክርስቲያን ልክ እንደ ገቢ ምንጭ ነዉ እየታየ ያለዉ

  ስለዚህ ካልÕሸ አይጠራም ነዉ፡

  ከላይ ጀምሮ እስከታች ስለተበላሸ እግዚአብሔር ቤቱን ያጽዳ ፡፡

  ወለተ ሚካኤል ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 3. አዎ ዋናው ነገር መለያየትን መነቃቀፍን አስወግደን በፍቅርና በእምነት ሰንሰለት ታስረን ለወገኔ ይጠቅማል ሳንል ወይም በጊዜያዊ ነገር ሳንደለል ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመጪው ትውልድ ከነ ሙሉ ክብሯ ለማስተላለፍና የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማስፋት የሚያስችለንን የምእመንና (የአማኝ) የባለ አእምሮ ሥራ እንሥረራ የሚለው ነገር ነው ስለዚህም ሁሉም ማድረግ የሚገባው ከዚህ አንፃር በመነሳት መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር ያግዘን አሜን!!

  ReplyDelete
 4. Thank you so much for your valuable idea. I'll agree.

  ReplyDelete
 5. ቤተ ክርስቲያናችንን አባቶቻችንን የሚያምሰው ችግር አንዳንዶች እንደሚያስቡት አባቶች መንፈሳዊነትን አጥተው ወይም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት አይሎ አይመስለኝም። Please shut this blog!!

  ReplyDelete
 6. Do you mean that first,election should be taken place before the reconciliation process?

  ReplyDelete
 7. kala heiwattt yasamalen

  ReplyDelete
 8. It is a great article related to our church. Such kinds of writers are not recognised at this time.God bless you,kessis.

  ReplyDelete
 9. ከታህሳስ አፈራ

  ለቄሲስ ስንታየሁ አባተ ቃለ ሕይወት ያሰማልን። እንደሚታወቀው ላለፉት ጥቂት ወራት የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ በተገኙት አጋጣሚዎች ሁሉ የውይይት አርእስት ሆኗል። ከቄሲስ ፅሁፍ ላይ ልቤን የነካው ከዚህ በታች ያለው ነው።

  “ቤተ ክርስቲያናችንን አባቶቻችንን የሚያምሰው ችግር አንዳንዶች (ብዙዎች) እንደሚያስቡት አባቶች መንፈሳዊነትን አጥተው ወይም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት አይሎ አይመስለኝም። እግዚአብሔርን ያላስደሰትንበት አንዳች ጉድለት ይኖራል ብዬ አምናለሁ። እግዚአብሔር ለሕጉና ለፈቃዱ ቀናተኛ አምላክ ነው። በገዛ ደሙ የዋጃቸው ምእመናን ከአሕዛባዊ የኖሮ ሥርዓት ርቀው በቀናነትና በንጽሕና እንዲያመልኩት ይፈልጋል። ይኽ አልሆን ሲል ግን ወደ በጎ ፈቃዱ እስኪመለሱ ድረስ ለማይመች አካሄድ ኣሳልፎ ይሰጣል።

  ስለ አንድ ነገር በአንድ ቋንቋ እየተነጋገርን እንዳንግባባ ማስተዋሉን ይነሣናል። እስቲ ራሳችንን እንጠይቅ፤ ከመቅደስ እስከ ዓውደ ምሕረቱ ያለው አገልግሎት በእምነትና በፍቅር ይፈጸማል? በትዳራችን፣ በማኅበራዊ ኑሮአችን፣ በሥራ ገበታችን፣ በጓደኝነታችን ታማኝነትና እውነት አሉ? መታመንን ሰብከን እምነት አጉዳይነትን ገንዘብ ካደረግን፣ ፍቅርን አስተምረን ጥላቻን በልቡናችን ካነገሥን፣ ከእግዚአብሔር፣ ከሕዝብና ከመንግሥት አደራ ተቀብለን አደራ ካጎደልን፣ ዘረኝነትን በአደባባይ ኰንነን በመካከለችን ዘረኝነትን መሸሸጊያ ካደረግን……እግዚአብሔር እንመለስ ዘንድ በትንሹ ይቆነጥጠናል።

  ለእኔ አሁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሆነ ያለው እገሌ ብለን ጣታችንን የምንቀስርባቸው ሰዎች ያመጡት ሳይሆን የሁላችን የኀጢአት ውጤት ነው ብየ አምናለሁ። ስለዚህ አሁን ጊዜው የመነቃቀፊያ አይደለም፤ የንስሐ እንጂ።”

  ሰው ያለውን ሀሳብ ከማካፈሉ በፊት ከልብ ለመፍትሄው የአቅሙን ለማዋጣት መፈለጉን መፈተሽ ኖርበታል። ለእግዚያብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ ሁላችንንም እንስማማለን። ቤተክርስቲያናችን የተለያዩ ፈተናዎችን አልፋለች። ወደፊትም ታልፋለች። የክርስትና ህይወት ፈተና የበዛበት መሆኑን እናውቃለን። መፍትሄውም የሚገኘው ከእንደእግዚያብሄር ዘንድ ብቻ እንደሆነ እናምናለን ። እግዚያብሄር ፀሎታችንና ልመናችን ይሰማል። ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም። ማንን ደስ እንዲለው? ዳቢሎስ ያፍራል።ሊነጋጋ ሲል ይጨልማል አይደል የሚባለው። በጸሎትና በጾም እንበርታ። የግድ ሱባኤ እንዲታወጅ መጠበቅ አያስፈልግም። የጋራ የሆነውን ጉዳያችንን በግል፣በየጓዳችን ተንበርከን አምላካችንን እንለምን።
  ምጥ ለናቷ እንዳይሆንብኝ እየፈራሁ ውስጤ የሚመላለሱ ነጥቦች ላስቀምጥ ፣
  1. የምንፈልገውን ቡድን ለመደገፍ ብለን የእግዚያብሄርን ስም ባናነሳ። የመፅሃፍ ቅዱስ ጥቅስ፣የትላን ታሪክ፣ የሌሎች ልምድ መጥቀስ የሚያስፈልገው ለመፍትሄው የሚረዳ ከሆነ ብቻ ነው። ችግሩን ለማስፋት ተጨማሪ ምክንያት አያስፈልግም።
  2. እግዚያብሄር ስራውን የሚሰራው እኛ በምናስበው መንገድ እንዳልሆነ እጅግ ብዙጊዜ አይተናል። እናታችን ቅድስት፣ብጽዕት ማርያም ያለወንድ፣ በድንግልና ፀንሳ ፣በድንግልና ወልዳለች በለን እናምናለን። ይህ በተፈጥሮ ህግ አይሆንም። ኤልያስ በሰረለጋ በህወት እያለ አርጓል። ይህም በተፈጥሮ ህግ አይሆንም። አዛውንቶች፣ በሽተኞች ይሞታሉ ሲባሉ፡ ህፃናቶች ጤነኞች ይጠራሉ። ኧረ ስንቱን ሰው ከሚያስበውና ከሚጠብቀው ውጪ የተከናወኑ ሁኔታዎች እናውቃለን። ማን ነው ይህንን ማድረግ የሚችለው። ባለቤቱ ፈጣሪያችን አማላካችን መሆኑን የማይስማማ የለም።
  3. ትልቅነት፣ አዋቂነት፣ልምድ፣ትምህርት፣መልካም አንደበት………. በእጅጉ የሚያስፈልጉት ለዚህ ዓለም ህይወት ነው። ኢየሱስ ቤተመንግስት ሲጠቅ በበረት ነው የተወለደው። አሳ አጥማጆችን ነው አስተምሮ መንፈ ቅዱስ የላከላቸው። የእውቀትም፣ የጉልበትም፣ የጊዜም፣…….. የሁሉም ባለቤት ስለሆነ ንፁህ ልብ ያላቸውን፣ ከታናናሾች መካከል መርጦ ስራውን በጊዜው ይሰራል።
  4. ኖሕ መርከቡን በአደባባይ ላይ ሲሰራ ያሾፉበት ነበር። ንሰሃ ግቡ ሲላቸው ይሳለቁበት ነበር። እኛ ዛሬ ተጨማሪ አንድ ቀን ለንስሃ ሲሰጠን ቀን ከሌሊት፣ በህልማችንና በውናችን፣ በጉልበታችንና በገንዘባችን፣ በህሊናችንና በአንደበታችን……. ሃጥያታችንን እናባዛለን።
  5. እንኳንስ ፓትሪያርክና ጳጳስ ላይ ቀርቶ አንድ እኔን የመሰለ በኋይማኖቱ እርከን የታችኛው ወለል ላይ የሚገኝን ምእመን በክፉ ማንሳት፣ በየአደባባዩ መንቀፍና ማዋረድ፣ ማነው የጽድቅ ስራ ነው ብሎ የሰበከው/ያስተማረው? ማክበር ቢቀር ከማዋረድ ብንታቀብ ታላቅ መንፈሳዊ ምግባር ነው።
  6. ቄሲስ እንዳሉት ሰዓቱን ለንስሃ ብንጠቀምበት ቸርነቱ የማያልቅበት አምላክ በተጨማሪ የሚሳነው ነገር እንደሌለ ያሳየናል። እንደ ራሔል ያለ እንባ ያስፈልጋል።

  አምላክ ሆይ እንደ ቸረነትህ እንጂ እንደበደላችን እይሁን። አሜን።

  ReplyDelete
 10. ቀሲስ ስንታየሁ የት ገቡ እያልኩ ሳስብ አሜሪካ አገር የሚኖሩ ይመስለኝ ነበር:: እረ እንኳን ጠበቀልን ደግሞ መግለጫ ያወጡና ተስፋ ያስቆርጡን ነበር:: ተጽናንቼበታለሁ አባታችን እድሜ ጤናውን ያድልልን:: እኔና የቢሮዬ ልጆች በምክርዎ ደስ ከመሰኘታችን የተነሳ አዋጁ እስኪታወጅ መጠበቅ አላስፈለገንም:: በዓለ እግዚእነ ባለፈ ረቡእ እንጀምረዋለን ብለን ወስነናል:: መምህራን፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ . . . ሌሎችም እባካችሁ መፍትሄያችሁን እንጂ መግለጫችሁን አቆዩት:: ጋዜጠኛ እንኳ የማይለውን የምትጽፉ ጦማሪዎች ለአባቶቻችን የምንሰጠውን ክብር አታቅሉብን:: አባት ምን ጊዜም አባት ነው:: ሃይማኖት አልለየን:: የሚሻል የመሰላቸውን ያድርጉ የኛ ዘመን ማቴዎስ፣ጳውሎስ፣ ጴጥሮስ . . . እነርሱ ናቸው:: ካለ ለስህተታቸውም መልስ የሚሰጡትና የሚጠይቃቸው ባለቤቱ ነው:: ሃይማኖቱም ይሁነን ብለን ያቋቋምነው ሳይሆን የወረስነው ነው:: የቤታችንን ችግር ቤታችን ሆነን እንፍታው::

  ብሎገሮች ሆይ! እኛ አናውቃችሁ ይሆናል ሥራችሁ ማንነታችሁን ይገልጥልናልና በከንቱ ትደክማላችሁ:: ሁሉን የሚያውቅ አምላካችንም በግልጥ ዋጋ ይከፍላልና ለገዛ ሕሊናችሁ ታመኑ እባካችሁ:: እንደኔ እንደኔ መረጃው እንኳ ቢኖር የማይገለጡ ነገሮችን ብትለዩ እላለሁ:: መገለጡ ይበልጥ የሚጎዳ የመረጃ አይነትም አለ:: ይሁዳ ሌባ የተባለበት ጊዜ ሌላ ነው ሲዘርፍ የኖረበት ጊዜ ሌላ ነው:: እንዳንዶች ሆን ብለው፣ ሌሎች ተደልለው፣ ጥቂቶችም ካለማወቅ፣ . . . ዘገባዎቻቸው ጽርፈት የተሞላባቸው ሆነዋል:: ሌላው ችግር በኃላፊነት ስሜት የማይሰሩ፣ ማንነታቸው የማይታወቅ፣ ዓላማቸው ግልጥ ያልሆነ ግለሰቦች የሚዳልቧቸውም ናቸው:: ምእመናን የእረኞቻችንን ድምጽ የመለየት ልምድ ማዳበር ያስፈልገናል::

  ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር ዘንድ የሚሰራ ሰው ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አፍርሶ ማለት አባቶችን ተሳድቦ፣ አብጠልጥሎና አስጠልቶ እንዴት ይሆናል? እንዲህ አይነቱን አካሄድ ዲ/ን ዳንኤል በሲኦል በኩል ወደ ገነት መጓዝ ይለዋል:: ያዋጣል? የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል የምትሉ ብሎገሮች ሲያገባችሁ እኮ ከኃላፊነት ጋር ነው:: ሲያገባችሁ እኮ ከተጠየቅ ጋር ነው መሆን ያለበት:: ምእመናንም ይህን አግባብ የማይከተሉ እና ማን እንደሚጦምርበት ለምን እንደሚጦምር ሳናውቅ ተጠቃሽ ገጽ አድርገን የማንንም ብሎግ የመውሰድ ግዴታ የለብንም:: ይህማ እባብ አሳተኝ እንደ ማለት ይሆናል:: ብሎጉ ሲጠየቅስ ማንን ይጠቅስ ይሆን?
  ለማንኛውም ቀሲስ እንዳሉት የባለ አእምሮ ሥራ ከሁላችን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ይጠበቃል:: አባታችን ትምህርቶን የምናገኝበት፣ ምክርዎን የምንካፈልበት ገጽ ቢኖርዎ ደግሞ የበለጠ እንታነጽበት ነበር:: ካልዎትም እባክህ ወንድማችን አስተዋውቀን::

  ReplyDelete
 11. So, you support daniel's view.

  ReplyDelete
 12. “ቤተ ክርስቲያናችንን አባቶቻችንን የሚያምሰው ችግር አንዳንዶች (ብዙዎች) እንደሚያስቡት አባቶች መንፈሳዊነትን አጥተው ወይም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት አይሎ አይመስለኝም። እግዚአብሔርን ያላስደሰትንበት አንዳች ጉድለት ይኖራል ብዬ አምናለሁ። እግዚአብሔር ለሕጉና ለፈቃዱ ቀናተኛ አምላክ ነው። በገዛ ደሙ የዋጃቸው ምእመናን ከአሕዛባዊ የኖሮ ሥርዓት ርቀው በቀናነትና በንጽሕና እንዲያመልኩት ይፈልጋል። ይኽ አልሆን ሲል ግን ወደ በጎ ፈቃዱ እስኪመለሱ ድረስ ለማይመች አካሄድ ኣሳልፎ ይሰጣል።" ጎሽ እንዲህ ነው እንጂ!!! ብሎ ብሎ ነገሩ ወደ እግዚአብሔር ዞረ። የእግዚአብሔር ፍቃዱ እኳ የሚታወቅ ሰው ሲንቀሳቀስ ነው። ዝም ብሎ "እግዚአብሔርን ያላስደሰትንበት አንዳች ጉድለት ይኖራል" ተብሎ እንዴት ይተዋል። ወዲያው ደግሞ ጥያቄ እግዚአብሔርን ለምን አላስደሰትንም የሚለው ነው? ቀሲስ እስኪ ነገሩን በደንብ ያጢኑት። እውን መንግስት አልተፈራም? በሀገራችን ሱባኤ አታውጁ ምህላ አታድርጉ አልተባልንም? አባቶች ለእምነታቸው ቅናኢነትን አላጎደሉም? ይህ ስለሆነ እኳ ነው እግዚአብሔርን ያላስደሰትነው። ስለሆነም አሁን እርቅ ቀድሞ ሌላው ይከተል። እግዚአብሔርን በእርቅና በፍቅር ብቻ ነውና ማስደሰት የሚቻለው የሚል ድምፅ ያየለው። እንደው ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ። እረ እንደው እግዚአብሔር ይታዘባል። ወይ ዘንድሮ። ባለቤቱን ራሱን ተጠያቂ ማድረግ?! እእምምም! ለእኔ ይህ ጽሁፍ እርስ በእርሱ የሚጋጭና ነው።
  ልብ ይስጠን። አሜን።

  ReplyDelete
 13. May God bless Kesis Sintayehu.

  It is in all a greatly constructive message.

  I especially liked the following.

  "ብፁዓን አባቶችም ለመጨረሻው ውሳኔ ሳትቸኩሉ ይኖራሉ ተብለው የሚታሰቡ የመፍትሔ አሳቦች እንዳሉ ከልጆቻችሁ ጋር በመነጋገር አሉ በተባሉ የመፍትሄ አሳቦች ላይ ለመነጋገር ዕድል ስጡ። "

  "የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ምእመናን ከውስጥ ከውጪ ያሉባቸውን ጫናዎች ተቋቋመው የቀደሙት አበው የሠሩላቸውን ቀኖና አክብረው ለዓለም ኅብረተስብ ቤተ ክርስቲያኒቷ በትክክል በክርስቶስ ዓለትነት መመሥረቷን፣ እነርሱም በትክክል የቅዱሳን አባቶቻቸው ልጆች መሆናቸውን አሳይተዋል። ኢትዮጵያ ሀገራችን የሥልጣኔና የአምልኮ ጀማሪ መሆኗን፣ ሕዝቦቿም ሕግንና ሥርዓትን ጠንቅቀው የሚያውቁና የሚፈጽሙ መሆናቸውን ታላላቅ የዓለም ታሪክ ፀሐፊዎች ሳይቀሩ መስክረዋል።

  እንግዲህ በእግዚአብሔርና በዓለም ሕዝብ ፊት ማንነታችንን የምናሳይበት ጊዜው አሁን ነው። ታሪክ ከመቃብር በላይ ይኖራል። ማንኛውም ዓይነት ሥራችንም በእግዚአብሔር ዘንድ ይቆየናል። ስለዚህ መለያየትን መነቃቀፍን አስወግደን በፍቅርና በእምነት ሰንሰለት ታስረን ለወገኔ ይጠቅማል ሳንል ወይም በጊዜያዊ ነገር ሳንደለል ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመጪው ትውልድ ከነ ሙሉ ክብሯ ለማስተላለፍና የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማስፋት የሚያስችለንን የምእመንና (የአማኝ) የባለ አእምሮ ሥራ እንሥራ።"

  Amen.

  ReplyDelete
 14. ቀሲስ ቃለ-ሕይወት ያሰማልን እንዲህ እውነትን እና የቀና መንገድን የሚያሳዩን አባቶች አያሳጣን፡፡ አዎ አባቶችን መንቀፍና መስደብ ፀያፍ ነውና እናቁም እኛ ማንም እንሁን ማን እነርሱ ከእኛ በብዙ መንገድ ይበልጡናል የቀደመ ክብራቸውን በውስጣችን እንመልስ ብናከብር ምንከበር እኛ ብናነግስ ምንነግስ እኛ ስለዚህ ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ፡፡እርግጥ ነው አንድ ጥያቄ ሁላችንም እራሳችንን መጠየቅ አለብን ብየ አስባለሁ ባሉን ደብሮች ኪዳኑ ቅዳሴው ይደርሳል፡በየ ገዳማቱ የማይታጎል ፀሎት ሳያቋርጥ እንደ ጅረት ውሃ ይፈሳል ታዲያ ይህ ሁሉ እየሆነ ሳለ ለምንድነው መነቃቀፉና መተቻቸቱ፡አለመከባበሩና ሰላም ማጣቱ እንዲህ የበረከተው;በሕይወታችን አንድ ትንቅ ችግር አለ ያም የንስሀ ሕይወት ልምምዳችን ነው ክርስትናን ከማውራት ይልቅ ብንኖረው ኖሮ ከክፋት ይልቅ በጎነትን፡ከስድብ ይልቅ መመረቅን፡ፈሩን ከለቀቀ ትችት ይልቅ ቀና ሀሳብን፡ከጠብ ይልቅ ፍቅርና ሰላምን እንሰብክ ነበር ክርስትናን በገቢር ብንኖር ኖሮ፡፡ክርስትናን በገቢር የኖሩትማ የግብፁ አባ ሙሳን አየናቸው አይደል; ለመንበረ ፕትርክናው ተወዳደሩ ሲባሉ እንቢኝ አሉ እንዲህ ነው ክርስትና እንዲህ ነው መንፈሳዊነት በረከታቸው የበዛ አባቶችን አምላክ አያሳጣን፡፡እባካችሁ በቤተክርስቲያን ላይ የምትፅፉ ብሎጎችም ጥንቃቄ አድርጉ የራሳችንን ሀሳብና ስሜት ሳይሆን ለቤተክርስቲያናችን የሚበጀውን ፃፉ እናንተን እንደ መረጃ ምንጭነት የሚጠቀሙ ብዙዎች አሉና፡፡ቃሎቻችንም፡ ምኞትና ሃሳባችንም የእውነተኛ መንፈሳዊ አይነት መሆን አለበት፡፡አምላክ የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ለኛም ቀናኢ ልቡናን ያድለን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 15. Dn.Daniel

  Ere danie they lost their soul eko,long time whne they change the rule in regarding the law that talks about the wealth of this so called papasat,so don't try to defend them,you can defend an individual papas that u can realy know beyond that they all selfish,corrupt and racisist papas,monk.priest,preacher,zemari,diaqon..

  Danie the better way is to discuss for once for all the truth about our fathers and lets clean it once for all, it will be messy and discusting but once it clear it will be better other wise it is just a matter of time it will come back again and we will fight about it.

  In my view there is some questions the fathers in america needs to answer .... like

  1= If they agree with synodos in Ethiopia. will they except what ever comes from ethiopia synodos? including
  -money
  -Transfer of the Fathers from one location to onather location will they except?
  2=what will hapen u.s.citizen papasat? is it legal for them to lead trhe church?
  3=Do you believe that some of the preachers in diaspora,if they transfered by the synodos to Ethiopia do u believe they will do it? if u ask me they will say hell to the nooooooo not only this preachers monks,priests and so on so my point is the fathers here in america they will work hard not to agree with ethiopia synodos becayse non of them would want to go back to ethiopia.so i would say move on hagere ethiopia and foreget about america,clean up yr house from fake papasat,priest,preachers, and move on to the mountain high to see that Tewahedo is great.

  ye-vegasu

  ReplyDelete
 16. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሆነ ያለው እገሌ ብለን ጣታችንን የምንቀስርባቸው ሰዎች ያመጡት ሳይሆን የሁላችን የኀጢአት ውጤት ነው ። ስለዚህ አሁን ጊዜው የመነቃቀፊያ አይደለም፤ የንስሐ እንጂ።first confession then.....

  ReplyDelete
 17. kale hiwot yasemawo tiru eyita new lehulachnm mastewalun yadlen

  ReplyDelete
 18. እግዚያብሄር ይስጥልን እንዲህ ጊዜዉን የሚዋጅ ስራ ያስፈልጋል በተለይበዉጩ ዓለም ያለን ሰዎች ተቸግረናል እስቲ እናስተዉል ስለሁሉም እናስብ የሚል ካለ ወያኔ የሚል ታርጋ ይሰጠዋል በተለይ ስለ ሃገሩና ሰለቤ/ክ ያለዉሁኔታ መስማት የሚፈልግ የቤተክርስትያን ጉዳይ ከኢሳት ሬድዮና ቲቪ መልስ ስለሚከታተል የቤተክርስትያንም ጉዳይ በዛዉ መንፈስ ትርጉም ይፈልግለታል ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ለቤተክርስትያን ቆምኩ የሚል ማህበርም ይሁን ግለሰቦች በዚህ አቅጣጫ እዉነትን ይዞ በተለይ በዉጩ ዓለም ብዙ ስራ መሰራት እንዳለበት ይታየኛል

  ReplyDelete
 19. i am afraid that the fear of our bishops are uncommon and not expected from the religious fathers.The Egyptians and ours are not comparable.Please kesis i do not think that your piece do not reflect the reality of Coptic popes.They are very few.But ours are most.For the last 20 years they are under the chain of fear.If they fear,where lies the principle.How can we learn from them.Unless we are lying the flowers. Let us speak the truth.

  ReplyDelete
 20. እግዚአብሔር ይስጥልን።ከዕውቀት በላይ የሆነውን ማስተዋል ለሁላችን ይስጠን።

  ReplyDelete
 21. D/n Daniel Egzabeher Yibarkeh Berta Fetnawen Yarekeleh!

  ReplyDelete
 22. Thank you Dn. Daniel that was I felt "እግዚአብሔርን ያላስደሰትንበት አንዳች ጉድለት ይኖራል ብየ አምናለሁ። እግዚአብሔር ለሕጉና ለፈቃዱ ቀናተኛ አምላክ ነው። በገዛ ደሙ የዋጃቸው ምእመናን ከአሕዛባዊ የኖሮ ሥርዓት ርቀው በቀናነትና በንጽሕና እንዲያመልኩት ይፈልጋል። ይኽ አልሆን ሲል ግን ወደ በጎ ፈቃዱ እስኪመለሱ ድረስ ለማይመች አካሄድ ኣሳልፎ ይሰጣል"።

  ReplyDelete
 23. amennnnnnnnnnnnnnnnn!!!!!!!!!!!!!!for all who said amen

  ReplyDelete
 24. GOD BLESS YOU! GETA YABERETANAL.IWNET BEFETENA YETAGEBECH NAT.

  ReplyDelete
 25. Kale Hiwot yasemalin kesis. I believe that at this critical time, we badly need valuable, constructive and corrective ideas from our fathers, so that we would not miss our longlasting route and objective. Thank you very much Kesis Seyntayehu.

  But, I do have some comments/ideas:

  Our bishops were sometimes quarrel each other in Betekehinet, some other time they work with protestants, e.g. Tehadiso orthodox, and now were working on to divide the church. Do we say nothing about our church? The most activist of the division, as everybody knows is the bishops from one ethinic group. Why does this happened.
  In the political environment of our country, as we all know some poeple from the same ethinic group had tried all the best and were doing day and night to divide our country into pieces, and they are doing again in the church. While these few political-religious people perform these satanic agendas, do the rest of us just sit and see them without commenting/saying something againist their evil job on this country, on this poeple, on this religion? For me, we are supposed to say something. Like, for example, let them know our stand, our awarness of the situation and what they are doing. We need to say at least, we all aware of you bishops your agenda, activity, or mission, etc. Okay? We are supposed to mention their names and tell them publicly and tell them the evil they are doing on our church. We need not gossip them.
  We Ethiopian do not have culture of saying "the bad thing is bad and the good thing is good".
  Whenver, anybody from wherever status or position does good thing we should be able to say good job and when bad thing is done we should be able to say bad job publicly! We should avoid "Shifinfin, shifinfin" from our culture.
  Do you remember that some of the current bishops who are activily engaging in dividing the church were even abused by the governemnet armys in betekehinet due to the unexplain disagreement with the pop Paulos before. In fact, most us, the church members of the country did not know the cause of the episode and was not publicly explained to the church, Shifinfin, shifinfin, which is not good for all of us. Now, most of us from the church now deadly sure that the past reason of their quarrel was not surely for the unity and integrity of the church, rather, from their current activity, it is understood that thier objective was another, which our almighty God reveals us in the later time of the rebirht of our church. Anyway, we need to avoid shifinfin, shifinfin for the wellbeing of our religion and country!!!
  regards,

  ReplyDelete
 26. Geremew
  Kesis Kale hiwot yasemalen letarikem letsidekim yemitekiem hasabiwon legisewal mesihafum kefit yielk ahun tigu yilalena talk fetana bemetabine gize yemitekimw Tsome selote engie metechachetu letelat ber selemikeft enem hasabiwon egrawalehu...

  ReplyDelete
 27. መልካም ሃሳብ ነው፡፡ እግዚአብሄር ይስጥልን!!

  ReplyDelete
 28. ቃለ-ሕይወት ያሰማልን ቀሲስ::
  “እኔ አሁን ዕድሜየ ሰባዎቹ ውስጥ ገብቷል፤ አሁን እኔን ሾማችሁ ገና ደስታችሁን ሳትወጡ ብሞት ለሌላ ድካምና ወጪ ትዳረጋላችሁ። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ እኔ አባቴ ብፁዕ ወቅዱስ ሺኖዳ ሣልሳዊ በተቀመጠበት መንበር እቀመጥ ዘንድ ብቁ አይደለሁም”
  “ለእኔ አሁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሆነ ያለው እገሌ ብለን ጣታችንን የምንቀስርባቸው ሰዎች ያመጡት ሳይሆን የሁላችን የኀጢአት ውጤት ነው ብየ አምናለሁ። ስለዚህ አሁን ጊዜው የመነቃቀፊያ አይደለም፤ የንስሐ እንጂ።” God bless you.

  ReplyDelete
 29. እንደ ግለሰብ የጠለቀ የሃይማኖት እውቀት የለኝም ነገር ግን የሚሰማኝን ጥቂት ልበል፡፡
  በመጀመሪያ ደረጃ ካለው ጠባብ የሃይማኖት ማእቀፍ ወስጥ ወጣ ብለን ያለውን ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ሰፋ ያለ ትልቅ ምስል(Big Picture) ለመረዳት እንሞክር፡፡ስለዚህም አሁን ባለው በዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ነገሮች ሁሉ እርስ በርሳቸው እንደ ድር የተጠላለፉና የተሳሰሩ ናቸው፡፡በዚህ የተነሳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ከዘመነ ቅኝ ግዛት ጀምሮ በኢትዮጵያዊነት ላይ ያላት እንደ አለት የጠነከረ የማይነቃነቅ መሰረት አለ፡፡ይህ ለጥንቱ ቀጥተኛ ቅኝ ግዛትም ሆነ ለአሁኑ ተዘዋዋሪ ዘመናዊ ቅኝ ግዛት ትልቅ ፈተና ነው የሆነው፡፡የእነ ስብሃት ነጋ ኦርቶዶክስና አማራን ከስልጣን ለያየናቸው የተባለው የቅርቡ መሰሪ አስተያየት ቅኔው ከዚህ ጋር ጭምር የሚያያዝ ነው፡፡የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በራሱ በታሪኩ ፀረ-ኮሎኒያሊዝም ነው፡፡ለግሎባል ካፒታሊዝም ስርዓትም እንደማይመች እንቅፋትና ኋላቀር ተደርጎ ነው የሚቆጠረው፡፡የእነ አቡነ ጴጥሮስ ፀረ-ቅኝ ግዛት የተጋድሎ ታሪክም ይህንን የሚመሰክር ነው፡፡የእንደነዚህ አይነት ታሪካዊ ሰዎች ሃውልታቸውም እንደ ተራ ነገር መንገድ እንዲወጣበት የተፈለገውም ለዚህ ነው፡፡ስለዚህም ኦርቶዶክስ እምነት ለግሎባል ካፒታሊዝም ስርዓት በሚመች መንገድ ተስማሚ ሆኖ እንዲሰራ ሪፎርም(Reform) እንዲደረግበት እየተደረገ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ወያኔ ስልጣን ላይ ሲወጣም ልክ እንደ አለማዊው ሁሉ በሃይማኖቱም መኩል ጳጳስ በሕይወት እያለ ሌላ ጳጳስ ከውጪ ሀገር አስመጥቶ መፈንቅለ- መንግስት ያካሄደው ለዚህ ነው፡፡ነገርን ከስሩ እንዲሉ አበው አሁን ለተፈጠረው ሁኔታ የችግሩ ዋና መንስኤ ከዚህ የሚጀምር ነው፡፡ለምን ወያኔ ይህንን ያልተለመደ የጳጳስ ለውጥ ያስከተለ መፈንቅለ- መንግስት በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ውስጥ አካሄደ? ለምን? በእርግጥ እንደተባለው እግዚአበሄርን የሚያስከፋና ፊት የሚመልስ አጠቃላይ የሃጢያት አረንቋና ማጥ ውስጥ ብቻ ሳንሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥልቀትና ስፋት ያለው አጠቃላይ ማህበረሰባዊ የትውልድ ዝቅጠት (Generational Systemic Crisis) ውስጥ ነው ያለነው፡፡ከዚህ መርገምት ልንወጣ የምንችለው ደግሞ በፆም በፀሎት ፊታችንን ወደፈጣሪ ለመመለስ ስንችል ብቻ ነው፡፡ብዙዎቻችን የችግሮቹን ወይንም የበሽታውን ምልክቶች እንጂ እራሱን በሽታውን እና የበሽታውን ዋና መንስኤ ለመለየትና ለማስቀመጥ አልቻልንም፡፡ቀድሞውኑ አንድ የሆነ ዝቅጠትና ሃጢያት ውስጥ ስለገባን እንጂ አበበ ወይንም ከበደ ጳጳስ ቢሆን ይህንን ያህል የምፅአት ቀን (dooms day) ያህል ባላስጨነቀን ነበር፡፡ስለዚህም ችግሩ ያለው ጳጳሱ ማን ይሁን የሚለው ላይ ሳይሆን ከዚህም በዘለለ ከዚህ በስተጀርባ ያለው ነገር ላይ ነው፡፡ስለዚህም ከበስተጀርባ ያለውን በመጀመሪያ ደረጃ ያለ ዋና ውስብስብ ችግር በፆም በፀሎት በሰከነ መንገድ ሰፋና ጠለቅ አድርገን በማየት ስንፈታው ጳጳሱ ማን ይሁን የሚለው ችግር በሁለተኛ ደረጃ የሚታይና በተወሰነ የሚቃለልና የማያስጨንቀን ጉዳይ ይሆናል፡፡ይህንን ስል ግን ጳጳስ የመምረጥ ጉዳይ አያስጨንቅም ለማለት አይደለም፡፡እያልኩኝ ያለሁት ግን በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ውስጥ ያለው ችግር የሀገራዊ ውስብስብና ፈታኝ የሆነ ጥልቁና ሰፊው ችግራችን መገለጫ ነው፡፡So this is a symptom of the disease not the disease or cause of the disease by itself.ደግሞስ በሃይማኖት ተቋም ውስጥ ልክ አንደ አለማዊው አይነት ይህንን ያህል የስልጣን ሽኩቻ የጤና ነውን?ይቅርታ ይደረግልኝና የሃይማኖት አባቶች ወደ አለማዊው ምቾትና ድሎት እያዘነበሉ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡አቡነ ፓውሎስም ከመእራቡ አለም አለማዊነትና የድሎት ሀይወት የሚጫነው አለማዊ ቀመስነት የኑሮ ዘይቤ መጥተው ነው ለጵጵስና በመፈንቅለ-መንግስት ስልጣን ላይ በወያኔ አማካኝነት የወጡት፡፡ይህ የአቡነ ጳውሎስ አለማዊ ዘመናዊነት የተላበሰ የኑሮ ዘይቤ የፈጠረው ሁኔታ ቀስ በቀስ ወደሌሎቹ የሃይማኖት አባቶች እየተስፋፋና እየተላመደ መጥቶ እነሆ ዛሬ ቤተክርስቲያኒቱን ፈተና ውስጥ የከተታት ሆነ፡፡ሰይጣንም ክርስቶስን በምዋእለ ስጋዌው ለእኔ ብትሰግድልኝ ይህንን ሁሉ የአለም ስልጣንና ሀብት እሰጥሃለሁኝ ብሎ ለመጨረሻ ጊዜ በሃይለኛው የፈተነበት አንዱ የመጨረሻ ነገር ስልጣንና ገንዘብ ነው፡፡ ግሎባል ካፒታሊዝምንም ያነሳሁትም ከዚህ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ይህንን ስል ግን የሃይማኖት አባቶች እንደ እኛ ስጋዊ ፍላጎት የላቸውም ወይንም እንደ ሰው አይሳሳቱም ለማለት ሳይሆን ወይንም ደግሞ የክርስትና ሃይማኖት አለማዊ ሰልጣኔን ሳይንስን ቴክኖሎጂን ይቃወማል ለማለት ሳይሆን አጠቃላይ ሂደቱ ግን ወዴት ነው የሚለውን ለማጠየቅ ነው፡፡የሃይማኖት አባቶች ግን ከሌላው በበለጠ በዋናነት ከሚታየው ከአለማዊው ይልቅ ለረቂቁና ለማይታየው ለመለኮታዊው አለም ቅድሚያ እንደሚሰጡ ግን የሚጠበቅና ተገቢም ነው፡፡ነገር ግን አሁን በሚታየው ነባራዊ ሁኔታ ቤተ-ክርስቲያኒቱንና የሃይማኖት አባቶችን አለማዊው ነገር በእጅጉ እየተፈታተናቸው ያለ ይመስላል፡፡ከስልጣን ሽኩቻ በስተጀርባ ያለው እውነታም ይህ ነው፡፡በዘመነ ግሎባል ካፒታሊዚም ገንዘብ የሰውን ልጅ ከፍተኛ ፈተና ውስጥ ነው እየከተተው ያለው፡፡እያንዳንዱ የእለት ተእለት የህይወት ዘይቤያችንና እንቅስቃሴያችንም በዚህ አለም አቀፍ ስርዓት ቅኝትና ማእቀፍ ውስጥ ነው ያለው፡፡ሃይማኖቱ ፖለቲካው ኢኮኖሚው ስልጣኔው ባህሉ ታሪኩ ስነ-ልቦናው ሞራልና ስነ-ምግባሩ ወዘተ ሁሉ በዚህ ቅኝትና ማእቀፍ ውስጥ ነው እየገባ ያለው፡፡ዛሬ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያውያን በዚህ ባእድና አዲስ መጥ ፈተና ውስጥ ነን፡፡ነፍሳቸውን ይማረውና በምእራቡ አለም ብዙ ዓመታትን ያሳለፉት አቡነ ጳውሎስ ሲበዛ አለማዊ እንደነበሩ ነው የሚወራውና እኔም ያየሁት፡፡ይህ አይነት አለማዊነት የሚጫነው ሰው ቀድሞውኑም ለመለኮታዊ ጵጵስና ያውም በመፈንቅለ-መንግስት አካሄድ የተመረጠበት ቅኔው ምን ይሆን?ስለዚህም ከጳጳስ ምርጫ በፊት ከበስተጀርባ ያለውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ውስብስብ ነገር እንመርምርና እንረዳ፡፡
  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡  ReplyDelete
  Replies
  1. ያነበብነው መልእክትነው መልካም አና ኣስተማሪ ነው፤
   እኔ ሁልጊዜ ኣንድ ነግር በሁላችንም ሂወት ውስጥ አስገራሚ ነገር ግን ሊታረም የሚገባው ንገር አንዳለ እመለከታለሁ፤ኣባቶችን አንነቅፋለን፤እነሱ እንደዚህ ሆኑ ፤እንደዚህ ኣደረጉ፤አንላለን፥ ነገርግን ኣንድም ቀን እራሳችን የመፈትሄ ኣካል ኣደርግን የ ቤታችን ችግር ለመፈታት ኣልሮጥንም፥ኣንድም ቀን ለቤተክርስትያን ኣልደረስንባትም፤አንደውም የቅድስት ቤተክርስትያን ስምን በኣደባባይ በእምነት ከማይመስሉን ጛር ስናጠፋ በዚህም ምክንያት ስማችን የኣለማዊ ጋዜጣና መፅሂት ማድመቂያ፤ የኣባቶቻችን ምስል የገንዝብ መስብሰብያ ሆናል፦ ለዚ ተጠያቂው ደግሞ ሌላ ኣካል ኣይደለም..እኛው ነን!!! ተናንት ከኣጃቸው መስቀል አንዳልተሳልምን፣ ቡራኬ አንዳለተቀበልን፣ አባ አቡነ ብልን አንዳልዘመርን፦ እኛ ማን ስለሆን ፣ በምን ስልጣናችን ፣ በየትኛው ቅድስናችን ነው...ኣባቶችን የምንነቅፈው? እኛ ድቁናን አንኮን በቅጡ ያልያዝን አንዴት ጳጳሳትን የምንነቅፈው? በመሰረቱ ሳኦልንም ዳዊትንም የሾመ እግዚያብሄር ስለሆነ የሚያነሳም አሱ ስለሆነ ኣባቶችን መንቀፉን ለሱ እንተው።
   በመጨረሻ አኔም አንተም እሱም እሷም ሁላችንም ስለቤተክርስቲያን ይመለከተናል ብለን በኣንድ ሃሳብ በኣንድ ልብ ሆነን አንደ ቤተክርስቲያን ልጅነታችን ልንቀሳቀስ ይገባል። ነግርግን የውጪ እርዳታ የምንጠብቅ ከሆነ በቤተክርስቲያን ህልውና ላይ እየተረማመድን መሆኑን ልንገነዝብ ይገባል።

   ዦሮ ያለው ይስማ!!!!

   Delete
 30. Amen, Kale Hiywot Yasemalin Kesis!!!

  ReplyDelete
 31. Thank God for giving us a good spirited teacher.

  ReplyDelete
 32. ለእኔ አሁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሆነ ያለው እገሌ ብለን ጣታችንን የምንቀስርባቸው ሰዎች ያመጡት ሳይሆን የሁላችን የኀጢአት ውጤት ነው ብየ አምናለሁ። ስለዚህ አሁን ጊዜው የመነቃቀፊያ አይደለም፤ የንስሐ እንጂ። Ewnet Newu...

  ReplyDelete
 33. እግዚኦ መሃረነ ክርስቶሰ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ እ……ግ……ዚ……ኦ…….. መ……ሃ…..ረ….ነ….. ክ……ር…..ስ….ቶ….ስ…..
  ትንቢት በእንተ ሳምኒት ዘመን
  አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር
  ወውኅደ ሃይማኖት እምዕጓለ እመሕያው
  በከናፍረ ጒሕሉት ልበ ወበልብ ይትናገሩ
  ይሤርዎን እግዝአብሔር ለከናፍረ ጒሕሉት
  ወለልሳን እንተ ተዓቢ ነቢበ
  እለ ይብሉ ነዐቢ ልሳናቲነ
  ወከናፍሪነኒ ኀቤነ እሙንቱ
  መኑ ውእቱ እግዚእነ በእነተ ሕማሞሙ ለነዳያን
  ወበእንተ ገዓሮሙ ለሙቁሓን
  ይእዜ እትነሳእ ይቤ እግዚአብሔር
  እሬሲ መድኃኒተ ወአግህድ ቦቱ
  ቃለ እግዚአብሔር ቃል ንጹሕ
  ከመ ብሩር ጽሩይ ንጡፍ ወፍቱን እምድር
  ዘዓጽረይዎ ምስብዒተ
  አንተ እግዚኦ እቀበነ ወተማኅፀነነ
  እምዛቲ ትውልድ ዘለዓለም
  አውደ የሐውሩ ረሲአን
  ወበከመ ዕቤየ ልዕልናከ ሠራዕኮሙ ለደቂቀ እምዕጓለ እመሕያው
  ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
  ለዓለም ወለዓለመ ዓለም

  ReplyDelete
 34. Thank you so much for your valuable idea. I'll agree.

  ReplyDelete
 35. Kale Hiwoten yasemalen Kesis

  ReplyDelete
 36. Qale hiwet yasemaln Qesis and Dn. Daniel !

  "በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሆነ ያለው እገሌ ብለን ጣታችንን የምንቀስርባቸው ሰዎች ያመጡት ሳይሆን የሁላችን የኀጢአት ውጤት ነው ። ስለዚህ አሁን ጊዜው የመነቃቀፊያ አይደለም፤ የንስሐ እንጂ።"

  i saw the comments and some do not want to confess ...

  እስኪ መንግስት የፈለገውን ፓትርያርክ አደረገ እንበልና እኛ ንስሐ ገብተን በንጽህና፣ በፍቅር ኖረን ህይወቱን ለቤተ ክርስቲያን አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ ልንለውጠው አንችልም ወይ?
  በዚህች በትንሿ በእግዚአብሔር ያለንን እምነት ካጎደልን እንዴት በትልቁ እንታመናለን?
  እግዚአብሔር አምላክ የጨለመው ልቦናችንን ያብራልን !
  አሜን !

  ReplyDelete
 37. አምላክ ሆይ ቤትህን አንተ ካላ ፀዳህ ማንም ሊያፀዳ አ ይችልምና አምላክ ሆይ አስበን! !!!

  ReplyDelete
 38. ከብዙ ጭንቀት በኋላ ሁሉን ላንተ ሰጥቼ ቁጭ ያብለሁና አ ምላ ክ ሆይ ስለቤትህ ዝም አትበል!!!

  ReplyDelete
 39. የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ምእመናን ከውስጥ ከውጪ ያሉባቸውን ጫናዎች ተቋቋመው የቀደሙት አበው የሠሩላቸውን ቀኖና አክብረው ለዓለም ኅብረተስብ ቤተ ክርስቲያኒቷ በትክክል በክርስቶስ ዓለትነት መመሥረቷን፣ እነርሱም በትክክል የቅዱሳን አባቶቻቸው ልጆች መሆናቸውን አሳይተዋል።

  ReplyDelete
 40. እንደ ሚመስልኝ ኤርትራዊ ጳጳስ ቢመረጥ ኣይሻልም ነበር፤ ምክንያቱ ኣሁን ያለው ኣማኝ በጎሳ የተከፋፈለ ያለሱ ወይ ውገኑ ካልሆነ ሌላ ወገን መሾም ማይፈልግ ነውና ስለዚ ኣንድ ኑትራል የሆነ ወገን ኣምጥተህ ብትሾም ያንን ሁሉ ጥላቻ ያርፋል ቢየ ኣምናለው፤ ይህ ግን የኔ ሃሳብ ነው እንጂ ይእግዚኣብሔር ፍቃድ ማን ያውቀዋል፤ ሁልግዜ ይርሱ ነው የተሻለና የበለጠ፤፤

  ReplyDelete
 41. qale hiwet yasemaLn qesis gin TMHRtunna Mkru zegeye k meskrM jemro tiru sra bisera nuro HZbum abatoChM Bzu sira Ysra neber :: yaM hon yih tiru abat Yisten::

  ReplyDelete
 42. Ewunet new endbale bale aemiro enasib!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete