Wednesday, January 30, 2013

አባ ፊልጶስን ፍለጋ


click here for pdf

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ታላላቅ ሥራ ሠርተው ነገር ግን እጅግም ሳይታወቁ ያለፉ አባቶችና እናቶች አሉ፡፡ ዛሬ ላለንበት መሠረት የሆኑ፣ እምነታችን ሲቀዘቅዝ፣ ሞራላችን ሲናድ፣ ክብራችን ከራሳችን ላይ ሲወርድ፤ ለልባችን ብርሃን፣ ለቀቢጸ ተስፋችን መጽናኛ፣ ለባዶነታችንም መሙያ የሚሆኑ ድንቅ ሰዎች አሉ፡፡ ዐውቀው የሚያምኑ፤ ባመኑበት የሚጸኑ፣ ለጸኑበት የሚያስከፍላቸውን መሥዋዕትነት ሁሉ የሚከፍሉ፣ በጥብዐት የሚጓዙ፡፡ ሥልጣን ገንዘብ፣ ርስት፣ ክብርና ሹመት ያመኑበትንና የጸኑበትን የማያስለውጧቸው፡፡ የስቃይ ዓይነቶች፣ የመከራ ብዛቶች፣ የቅጣት ውርጅብኞች ከአቋማቸው የማያስበረግጓቸው፡፡ በአንድ በኩል መንፈሳውያን ከሚመስሉ ዓለማውያን፤ በሌላ በኩል ኃይልና ሥልጣን ከጨበጡ ነገሥታትና መኳንንት፤ በአንድ በኩል ለሆድ ካደሩ የቤተ መቅደስ ሰዎች፣ በሌላ በኩል ክብራቸውን ሽጠው ካደሩ መለካውያን ባለ ጊዜዎች ጋር የተጋደሉ አባቶችና እናቶች ነበሩን፡፡
አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ከእነዚህ አንዱ ነበር፡፡ በ1266 ዓም አካባቢ ለት በምትባል ቦታ የተወለደው አቡነ ፊልጶስ ወደ ደብረ አስቦ (ደብረ ሊባኖስ) ገዳም የገባው በ15 ዓመቱ ነበር፡፡ በዚያ መጀመርያ ወደ ደብረ አስቦ ከገቡት 17 የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዛሙርት አንዱ ነው፡፡ በዚያ ገዳም ቅዱሳት መጻሕፍትንና ምንኩስናዊ ሕይወትን ተምሮ ያደገው አባ ፊልጶስ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ዕረፍት በኋላ በ1306 ዓም የደብረ ሊባኖስ ገዳም ሦስተኛው እጨጌ ሆነ፡፡
በእጨጌነት መንበሩ እያገለገለ እያለም አቡነ ያዕቆብ የተባለ ግብጻዊ ጳጳስ ወደ ኢትዮጵያ በ1330 ዓም ወደ ኢትዮጵያ መጣ፡፡ አቡነ ያዕቆብ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ በሰሜንና በደቡብ የነበሩ አባቶችን በአሥራ ሁለት ሀገረ ስብከት እየከፈለ ለስብከተ ወንጌል ሥራ አሠማራቸው፡፡ በዚህም መሠረት የታላቁን ገዳም የደብረ ሊባኖስን ገዳም አባቶች በዚያን ዘመን ሸዋ ይባል በነበረውና በዳሞት ግዛት አሠማራ፡፡ አባ ፊልጶስንም የሁሉም አለቃ አድርጎ ‹‹ኤጲስ ቆጶስ›› ብሎ ሾመው፡፡
በዚህ ዓይነት አገልግሎት ላይ እያሉም ንጉሥ ዓምደ ጽዮን(1307-1337 ዓም) ከክርስቲያን ሕግ ወጥቶ ሦስት ሚስቶችን ማግባቱን ሰሙ፡፡ አቡነ ፊልጶስና ሌሎች አባቶችም ወደ ቤተ መንግሥቱ ሄደው ምክንያቱን ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹አንዳንድ ጥበብ ዐዋቂዎች ይህንን ብታደርግ መንግሥትህ ይጸናል ስላሉኝ ነው›› ሲል መለሰላቸው፡፡ እነርሱም ሌሎቹን ትቶ በአንዲት ሚስት እንዲጸና ነገሩት፡፡ ንጉሡ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ በዚህም ምክንያት በአቡነ ፊልጶስ ይመሩ የነበሩት አባቶች አወገዙት፡፡ እርሱም አያሌ የመከራ መዓት በላያቸው ላይ አዝንቦ ወደ ዳር ሀገር እንዲሰደዱ አደረጋቸው፡፡(በዚህ ጉዳይ ላይ ዝርዝር ነገር ከፈለጉ ረዥም ጊዜ በፈጀ ጥናት የተዘጋጀውንና በቅርብ ቀን የሚታተመውን ‹‹አራቱ ኃያላን›› የሚለውን መጽሐፍ ያንብቡ)
አቡነ ፊልጶስ በትግራይ ለሦስት ዓመታት ከተሰደደ በኋላ ዓምደ ጽዮን 1337 ዓም ሲያርፍ አቡነ ያዕቆብ ከዓምደ ጽዮን ቀጥሎ የነገሠውን ልጁን ዐፄ ሠይፈ አርዕድን(1337-1365 ዓም) ነግሮ ከስደት እንዲመለስ አደረገው፡፡ ንጉሡም በአንዲት ሚስት ጸንቶ ለመኖር ቃል ገባ፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ወራት በኋላ የንጉሡን ቀልብ ገዝቶ ርስትና ሹመት ለማግኘት የቋመጠ ‹ዘዐማኑኤል›› የተባለ ሐሳዊ መምህር ‹‹ለንጉሥ ሦስት ሚስት ማግባት በቅዱሳት መጻሕፍት ተፈቅዷል›› ብሎ ሠይፈ አርዕድን አሳሳተው፡፡ እነዚያው ጥቡዐን አባቶችም ይህንን ሲሰሙ ከያሉበት ወደ ቤተ መንግሥቱ ተሰባሰቡ፡፡ ንጉሥ ሠይፈ አርዕድንና ሐሰተኛውን መምህር ዘአማኑኤልንም ተከራከሩት፡፡
ንጉሥ ሠይፈ አርዕድ የአባቶችን ሃሳብ ከመቀበል ይልቅ አቡነ ያዕቆብን ወደ ሀገሩ ግብጽ መለሰው፤ አባቶችንም ደማቸው በከተማው ላይ እንደ ውኃ እስኪወርድ ድረስ አስገርፎ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ዝዋይ ደሴት እንዲጋዙ አደረገ፡፡ 
ከአራት ዓመታት በኋላ በ1341 ዓም አቡነ ሰላማ መተርጉም ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የተሰደዱት አባቶች እንዲመለሱ ታወጀ፡፡ አቡነ ፊልጶስ ግን ‹የንጉሥ መሳሳት ሕዝቡንም ያሳስተዋልና ንጉሡ መታረም አለበት፡፡ ንጉሡን ለመገሠጽና ለማረም ካልቻልን እኛ መነኮሳት ሳንሆን ሹመት ፈላጊዎች ነን›› አለ፡፡ ንጉሡም ከስሕተቱ መመለስን እምቢ አለ፡፡ እንዲያውም አባ ፊልጶስን በገንዘብና በሹመት ሊደልለው ፈለገ፡፡ አባ ፊልጶስ ግን አልተቀበለውም፡፡ በመጨረሻም ንጉሡ የሚገዛውን ሀገር ለቅቆ እንዲሄድ ፈረደበት፡፡
አባ ፊልጶስ በ74 ዓመት ዕድሜው በስደትና በተጋድሎ በደቀቀ ጉልበቱ እያዘገመ ወደ ደብረ ሊባኖስ ክረምቱን ሊያሳልፍ መጣ፡፡ በወቅቱ የነበሩት የገዳሙ አባቶችም ‹‹ፊልጶስን ያስጠጋ ይቀጣል›› ተብሎ የወጣውን ዐዋጅ በመፍራት ገዳሙን ለቅቆ እንዲሄድ ነገሩት፡፡ እርሱም የአባቴ ገዳም ከሚበረበር ብሎ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን መቃብር ተሳልሞ ወጣ፡፡ ከዚያም በኋላ በሄደበት ሁሉ ዐዋጁ እየተከተለው የሚያስጠጋው በማጣት እህል እስከመራብ ድረስ ደርሶ ነበር፡፡
በመጨረሻ የንጉሡ ተጽዕኖ ከነበረበት ቦታ ርቆ ጌርጌስ ወደምትባል ቦታ ተጓዘ፡፡ በዚያም አቡነ ሰላማ መተርጉምን አገኘው፡፡ አቡነ ሰላማ ከጌርጌስ ወደ ሐቃሊት ለመጓዝ በዝግጅት ላይ ነበር፡፡ አባ ፊልጶስም ‹‹ትተኸኝ አትሂድ›› ሲል ለመነው፡፡ አቡነ ሰላማ አባ ፊልጶስን በአልጋ ላይ አድርጎ በሸክም ወደ ደብረ ሐቃሊት ወሰደው፡፡ በዚያም እያለ በተወለደ በ74 ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ሐምሌ 28 ቀን ዐረፈና በደብረ ሐቃሊት ተቀበረ፡፡
አብዛኛውን እድሜውን ላመነበት እምነቱና ላመነው አምላኩ ሲል የተንከራተተው፤ ማስፈራራት፣ ግርፋ፣ እሥራት፣ ራቁቱን በገበያ መካከል ታሥሮ መዞር፣ ለውሾች መሰጠት፣ ረሃብና ጥም፣ ስደትና ግዞት፣ ያልበገረው፡፡ ሹመትና ሽልማት፣ ርስትና ጉልት፣ ወርቅና ብር ከአቋሙ የማያዛንፈው ይህ አባት የት ነው የተቀበረው? ጌርጌስ የት ናት? ሐቃሊትስ የት ናት? እንዴት የርሱን ታሪክ ደግመን መሥራት ቢያቅተን ታሪኩን አሟልተን ለትውልድ ማስተላለፍ ያቅተናል? የሚል ጥያቄ ብዙ ጊዜ በውስጤ ነበረ፡፡ በተለይም ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ መዛግብት ስለ እርሱ የተጻፉትን መረጃዎች ሳይ የማወቅ ጉጉቴ ጨመረ፡፡
አንዳንድ ሊቃውንት ጌርጌስና ሐቃሊት በትግራይ ውስጥ እንደሚገኙ ገምተዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በወሎ ውስጥ ሳይሆኑ አይቀሩም ይላሉ፡፡ ገድሉና የደብረ ሊባኖስ መዛግብት ምንም አይነግሩንም፡፡ የመጀመርያው ችግር በወረራና በሕዝቦች ፍልሰት ምክንያት የጥንት የቦታ ስሞች መቀያየራቸውና መዘበራረቃቸው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ጥንታዊ የቦታ ስሞች ላይ የሠሩ የሀገር ውስጥም ሆኑ የውጭ ሊቃውንት ስለ ጌርጌስና ደብረ ሐቃሊት የሰጡን ፍንጭ አልነበረም፡፡ ስለዚህም ያለው አማራጭ በተጠረጠሩት ቦታዎች ላይ ፍለጋ ማካሄድ ነው፡፡
የመጀመርያው ፍለጋ የተካሄደው በትግራይ ነው፡፡ አባ በጸሎተ ሚካኤል ተሰድዶበት በነበረው አኩስም አካባቢ በነበረው በጉሎ ማክዳ፣ በኋላም ዐጽሙ አርፎበት በቆየው፣ ሌሎች ደብረ ሊባኖሳውያንም በስደታቸው ወቅት በቆዩበትና ከሕዝቡ ታላቅ አቀባበልን ባገኙበት በተንቤን አካባቢ ፍለጋውን አደረግኩ፡፡ ከሀገር ሽማግሌዎች ጠየቅኩ፡፡ የአካባቢውን መዛግብት አገላበጥኩ፡፡ ምንም ፍንጭ ግን አልነበረም፡፡
ሁለተኛው ፍለጋ የተደረገው በወሎ በተለይም ያን ጊዜ ከጥንቱ ሸዋ ጋር ቅርበት በነበረው በደቡብ ወሎ (የጥንቱ የአምሐራ ግዛት) አካባቢዎች ላይ ተደረገ፡፡ በአማራ ሳይንት፣ በቦረና፣ በአምባሰል ተፈለገ፡፡ ምንም ፍንጭ አልተገኘም፡፡ የጥንቱ የአንጎት ግዛት በነበረው የጁ ገባን፤ የለም፡፡ ላስታና መቄት ወረድን፤ ምንም አልነበረም፡፡ በዋድላና በደላንታ ዞርን አንዳች ፍንጭ ጠፋ፡፡
እንዲያ ደክሞት፣ በሰባ አራት ዓመት እድሜው፣ የንጉሥ ወታደር እያሳደደው፣ በየቦታው የሚቀበለው አጥቶ፣ ‹‹አቤቱ ይህንን በእኔ ላይ ያደረጉትን ግፍ ተመልከት፤ ግማሹ ውኃ፣ ግማሹም እህል ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ግን አልሰጡኝም፡፡ እነርሱ ግን በደስታ ይበላሉ ይጠጣሉ›› ብሎ ወደ ፈጣሪው እስኪያመለክት ድረስ በረሃብ አለንጋ የተገረፈው አባ ፊልጶስ የት ይሆን የገባው?፡፡
ገድሉን የጻፈለት የደብረ ሊባኖሱ ሰባተኛ እጨጌ ዮሐንስ ከማ ከዛሬ 500 ዓመታ በፊት ይህንኑ ጥያቄ ጠይቆ ነበር፡፡ ‹‹የዚህ ነገር ተመራማሪ እንዲህ አለ፡፡ ይህ ብጹዕ አቡነ ፊልጶስ ከሀገር ወደ ሀገር ሲሰደድ የተቀመጠው ጥቂት ጊዜ በመሆኑ ስለ ገድሉና ስለ ዘመናቱ የሚነግረኝ አጣሁ፡፡ ዜናውንም በማጣት ምክንያትም እያዘንኩና እየተከዝኩ ወደ ማደርያዬ ገባሁ›› ይላል፡፡
ጌርጌስ ሆይ የት ነሽ? የታላቁን ሰማዕት የአቡነ ፊልጶስን ዐጽም የተሸከምሽው ሐቃሊትስ የት ነሽ? በቀጣይ እንመለስበታለን፡፡

43 comments:

 1. ዲ.ዳንኤል የዚህን ታላቅ ሰው ታሪክ በመዘከርህ የአባ ፊልጶስ አምላክ ቸሩ ፈጣሪያችን በረከቱን አብዝቶ ይስጥህ። ጡመራህን ባነበብኩ ቁጥር ሁሌም የቤ/ክ ታሪክንም ሆነ የሀገራችንን ታሪክ ለማወቅ ታላቅ ጉጉት ያሳድርብኛል፡ ስለሆነም እሰቲ ለኔና ለመሰሎቼ በእነዚህ ሁለት አርዕስቶች ዙሪያ ጥሩ አስተማሪ ይሆናሉ የምትላቸውን መጻህፍት ጠቆም ብታደርገን እጅጉን ባለውለታህ ትሆነናለህ ብዬ አምናለሁ። ግን ታዲያ የመጸሀፍቶቹን አርዕስት ብቻ ሳይሆን የት ማግኘት እንደምንችል ጨምረህ ብትገልጸልን ስል በታላቅ ትህትና ነው።

  ReplyDelete
 2. Dn Daniel,
  Talking and writing about the past doesn’t do that much good for today's Church. Our church today is more of a tool how to earn money, to get to power and build a relation with government. The ordinary church followers need genuine fathers, preachers and writers who are not living to please the ones who have power and money. When will we live to please the Almighty GOD? The many challenge to our church is not the wrong teachings that go around us. The real challenges are individuals who are in the Church and pretending with dressing and good words as bishops, fathers, priests, deacon, writers and the like. Always it is good to get back to our mind and do the right things before it gets too late.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Try to think again and again

   Delete
  2. የአቡነ ፊልጶስ አጽም ካረፈበት መጥቶ እዚሁ ደብረ ሊባኖስ የሚገኘው ደሀና ተብሎ በሚታወቀው ቦታ(ወደ ቀጠባ ማርያም ሲወርዱ በስተግራ) በሚገኘው የአቡነ ፊልጶስ ቤተ ክርስቲያን አርፏል የሚል ታሪክ ሰምቻለሁ፡፡ ምክንያቱንም ሲተርኩ እንዲህ ይላሉ አቡነ ፊልጶስ የጎንጊትን(በቦታው የሚገኝ የወንዝ ስም) ወንዝ ወደ ታች የሚወርደውን እሱ ወደላይ እንደ ገመድ እየተንጠላጠለበት ሲወጣ ያየች ፈት ሴት ፊልጶስን እዩት ፊልጶስን እዩት እያለች ብትጮህ ሰዉ ሁሉ ወጥቶ አየው እሱም ክብሬን እንደገለጥሽብኝ ብሎ በዚህ አገር አግብታ የፈታች ሴትም ዳግመኛ አታግባ(አትዳርበት) ብሎ ብሎ ሀገሩን ረግሞት ሄዷል፡፡ ይህ ደሀና የተባለ ሀገር በጣም ጥጋብ ያለበት እና ደሀ የሌለበት ስለነበር ደሀ ና ደሀ የሆነ ሰው ይምጣ አይነት ትርጉም ያለው ስያሜ ይዞ ይገኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ከአቡነ ፊልጶስ መሰደድ በኋላ ሀገሩ በጣም ስለተራበ እና ችግር ስላሰቃየው ገዳማውያን አበውን ሲያጠያይቅና እግዚኦ ሲል የአቡነ ፊልጶስን አጽም አፍልሳችሁ አምጥታችሁ እዚህ ብትቀብሩት ዝናብ ይጥልላችኋል፡፡ ነገር ግን የተቀበረበት ሀገር ያሉ ሰዎች አይጧችሁም፡፡ ስለዚህ ተጠንቅቃችሁ መሆን አለበት ብለዋቸዋል፡፡ ሀገሬውም ጎበዛዝት መርጦ ጎንደር ይሁን የት የረሳሁት ሀገር ወደዛ ልኳቸዋል፡፡ ቢፈልጉ ቢፈልጉ መቃብሩ ብዙ አቅጣጫውም የማይታወቅ ሆኖባቸው ሲቸገሩ የፍየል እረኛ ጉዋደኛውን አንተ ፍየሎቼን መልስልኝ ቢለው መላሹም የት ናቸው ብሎ ቢጠይቀው ከአባ ፊልጶስ መቃብር አሉልህ ብሎታል እረኛውን ተከትለው ሄደው መቃብሩን አይተዋል፡፡ በለሊትም አጽሙን አፍልሰው ይዘው መጥተዋል አጽሙን ይዘው ሲመጡ አብራቸው ተከትላ የመጣች ትንሽ ደመና አጽሙ ባረፈ ጊዜ ዝናብ ሰታቸዋለች፡፡ አጽሙንም በክብር አሳርፈውታል ይባላል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዘው የሚነስ ታሪኮች አሉ፡፡ ሀገሩ አሁንም ደሀና ይባላል የአቡነ ፊልጶስ ዋናው ቤተክርስቲያንም በዚያው ይገኛል፡፡ በቅርቡ አዲስ ቤተክርስቲያን ለመስራት በሚል የጥንቱን አፍርሰውታል ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ በተጨማሪም የጥንቱ ቤተክርስቲያን ሲሰራ ባልሳሳት አጼ ምኒሊክ ይመስሉኛል 300 ከብት ሰጥተው ሥጋውን እየበላችሁ በጠፍሩ የቤተክርስቲያኑን ጣሪያ ሥሩ ብለዋቸዋል፡፡ በዚህም አቅጣጫ ብታዩት፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡

   Delete
 3. GOD help you in your search. It's all for our benefit, spiritual or not.

  I hope Aba Pilipos hears your call and reveal all!

  ReplyDelete
 4. Minew Dani? Minew? agule bota lay akomekew?Bereketachew yideresen. Sorry Amaregna software silelelegni, be englizegna amaregna lemetsaf tegedechalehu.

  ReplyDelete
 5. Gherghes hoy yet nesh?Hakalites?ketayun begugut etebikalehu.Egziabher yebarkeh Dani.

  ReplyDelete
 6. Betemesito............. E/ber yibarkeh

  ReplyDelete
 7. Thank you bro! I am so excited to read the next part I hope you will let us soon. "አቡነ ፊልጶስ ግን ‹የንጉሥ መሳሳት ሕዝቡንም ያሳስተዋልና ንጉሡ መታረም አለበት፡፡ ንጉሡን ለመገሠጽና ለማረም ካልቻልን እኛ መነኮሳት ሳንሆን ሹመት ፈላጊዎች ነን›› አለ፡፡ ንጉሡም ከስሕተቱ መመለስን እምቢ አለ፡፡ እንዲያውም አባ ፊልጶስን በገንዘብና በሹመት ሊደልለው ፈለገ፡፡ አባ ፊልጶስ ግን አልተቀበለውም፡፡ በመጨረሻም ንጉሡ የሚገዛውን ሀገር ለቅቆ እንዲሄድ ፈረደበት፡፡" I hope God will not deny ours growl and......."እምነታችን ሲቀዘቅዝ፣ ሞራላችን ሲናድ፣ ክብራችን ከራሳችን ላይ ሲወርድ፤ ለልባችን ብርሃን፣ ለቀቢጸ ተስፋችን መጽናኛ፣ ለባዶነታችንም መሙያ የሚሆኑ ድንቅ ሰዎች አሉ፡፡"

  ReplyDelete
 8. dani kale hiwet yasemalen ye tsadeku berket hagerachenen yetbkelene.amen

  ReplyDelete
 9. kale hiwot yasemalen!

  ReplyDelete
 10. ወንድሜ ዳኒ ሰላም፣ ጤና እና የፈጣሪ ጥበቃ ካንተ ጋር ይሁን! የቅ/ዑራኤልን በዓለ ንግስ ሳከብር ከድሮ መንፈሳውያን ቤተሰቦች ጋር ተገናኘሁ፡፡ የህይወት ጎዳናችን እግዚአብሔር በፈቀደው መንገድ እንድንጓዝ፤ የፈጣሪም ቅዱስ መንፈስ እንዲመራን የዘወትር ጸሎታችን እንዲሆን ከሚያስተምሩን ቀደምት የአርባ አምሳዎቹ ከባዕታ ነገስት ገዳም ከነበሩ መምህራን መካከል አንድ ሐዋርያ በፈተና ውስጥ እንዳሉ ሰማሁኝ፡፡ ክርስትያን ሊፈተን ግድ ነውና ስለገጠማቸው ፈተና ብርቅ ድንቅ አልሆነብኝም፡፡ ለዚህም ሓዋሪያዊ ተጋድሎ በረከት በመብቃታቸው እውነተኛነታቸውን ያጎላዋል እንጂ አይቀንሰውም፡፡ እኔን እንደሰው ያስጨነቀኝ በቅዱሳን ሰፈር በቤተክህነቱ ውስጥ የዓለማዊውን ስርዓት ነግሶ ሰውን በማፈን ወንጀል ፈብርከው ስብዕናቸውን የሚያረክሱ ባለጊዜ ነን ባዮች ይሁዳዎች ተግባር ነው፡፡ እነኚህ በእግዚአብሔር አምሳያ የተፈጠሩ የቤተክህነት ማፍያዎች ስለነፍሳቸው የሚያስቡት መቼ ነው?
  በቅርቡ ያለፉት ፓትርያርክ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለስንበት ቆመው ቡራኬ የሰጡት አንድ መንፈሳዊ አባት የተናገሩት ታላቅ ቁም ነገር “ሞት ትልቅ መጽሀፍ ነው፤ የሚያነበው ግን የለም” ነበር ያሉት፡፡ በፈተና ውስጥ ያሉትን መምህራችንን እግዚአብሔር ጽናትን፣ በረከትን እና ጸጋን ያጎናጽፍልን፤ ለከሳሾቻቸው ደግሞ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ፈጣሪ ልቦና ሰጥቶ ለንስሀ ያብቃልን፡፡

  ReplyDelete
 11. OMG!!! I LIKE IT... KEEP IT UP!!!!!

  ReplyDelete
 12. ርጌስ ሆይ የት ነሽ? የታላቁን ሰማዕት የአቡነ ፊልጶስን ዐጽም የተሸከምሽው ሐቃሊትስ የት ነሽ?

  ReplyDelete
 13. It is very interesting. Dani keep it up, pls answer the first guys question as it is also my question. You are one of the lucky and gifted individuals who is able to investigate the deep and vast Ethiopian history. May God bless you.

  ReplyDelete
 14. ውድ ወንድሜ ድያቆን ዳንኤል የጀመርከው ነገር እግዚብሄር ለፍፃመሜ የደርሰህ ዘንድ እመኛለሁ፡፡ ነግር ግን ይህን ታሪክ በተመለከተ ሁለት ነገሮችን ለማለት እሻለሁ
  1ኛ. የቦታዎቹ ስም ወደ ትግርኛ የተጠጋ ሲሆን በተለይ “ጌርጌስ” የሚለው ስም በምእራባዊ ትግራይ አከባቢ ማለትም ሽሪ እና የሰሜን ጎንደር በረሃማ ካባቢዎች ተከዜን ይዘህ እሰካ ማይ ፀብሪ ድርስ የተለመድ ስለሆነ ፍለጋህን ወደዚህ አከባቢ ብታደርግ፡፡
  2ኛ. ታላቁ አባታቸን አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ “የንጉሡ ተጽዕኖ ከነበረበት ቦታ ርቆ ጌርጌስ ወደምትባል ቦታ ተጓዘ” የሚል ሀረግ በፅሁፍህ ውስጥ አለ ስለዚህ “ጌርጌስ እና ሐቃሊት” ሚባሉት ቦታዎች ከዐፄ ሠይፈ አርዕድን ግዛት ወሰን ውጭ ናቸው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ፍለጋህን ከዐፄ ሠይፈ አርዕድን ግዛ ወስን ውጭ ቢሆን፡፡
  በመጨረሻም እግዛብሄር ምልካሙን መንገድ ያመላክትህ፡፡

  ReplyDelete
 15. በጣም አሪፍ ፅሁፍ ነው ልብ አንጠልጣይ ሆነ እንጂ

  ReplyDelete
 16. ቤተሥላሴ ሆሳዕናJanuary 31, 2013 at 4:06 PM

  ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ ልክ እንዳንተ....በወንጌላዊው ቅዱስ ዮሃንስ የተጻፈው ዮሃንስ ራዕይ መጽሐፍ መጥፋት ወይም የደረሰበት አለመታወቅ ሲቆጨው ይኖር ነበር፣ በኋላ ቅድስት ሥላሴ ገልጦለት አሁን የምናነበውን ዮሃንስ ራዕይን ጻፈልን......የቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ አምላክ ላንተም የኚህን ጻድቅ የእረፍት ቦታ ይግለጥልህ፡፡
  አኛም የሚቻል ከሆነ ቦታውን እንድንሳለመውና እንድንቀደስ፡፡

  ReplyDelete
 17. ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ ልክ እንዳንተ....በወንጌላዊው ቅዱስ ዮሃንስ የተጻፈው ዮሃንስ ራዕይ መጽሐፍ መጥፋት ወይም የደረሰበት አለመታወቅ ሲቆጨው ይኖር ነበር፣ በኋላ ቅድስት ሥላሴ ገልጦለት አሁን የምናነበውን ዮሃንስ ራዕይን ጻፈልን......የቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ አምላክ ላንተም የኚህን ጻድቅ የእረፍት ቦታ ይግለጥልህ፡፡
  አኛም የሚቻል ከሆነ ቦታውን እንድንሳለመውና እንድንቀደስ፡፡
  Mamush

  ReplyDelete
 18. EWNET ELAHALEHUNG ... EMEBRHAN TEYKAT ... KDEST LEELT WEKEBRT MESGENT WELADITE AMKAL ... BETAWEN AYDELM TSADIJU ABATCHN ENKAN TASAYEHALCH ... AMNALEHUNG ... LANTEM CHER YEGETEMH ... EGZIABHER YEBARKEH ... FTSAMIHN YASAMRLH

  ReplyDelete
 19. Egziabher yistlin...yagelglot zemenhin yibarkilih.

  ReplyDelete
 20. qale hewot yasmalen Egzabher yerdah

  ReplyDelete
 21. በአንድ በኩል መንፈሳውያን ከሚመስሉ ዓለማውያን፤ በሌላ በኩል ኃይልና ሥልጣን ከጨበጡ ነገሥታትና መኳንንት፤ በአንድ በኩል ለሆድ ካደሩ የቤተ መቅደስ ሰዎች፣ በሌላ በኩል ክብራቸውን ሽጠው ካደሩ መለካውያን ባለ ጊዜዎች ጋር የተጋደሉ አባቶችና እናቶች ነበሩን፡፡አሁንስ?......

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሁንማ.....የምነኩስና ስርዓት የተጀመረው በ 300ኛው ክፍለ ዘመን በአባ ጳውሊና በቅዱስ እንጦንዮስ እንደሆነ መጸሐፍት ይናገራሉ፡፡ ኢማጅን እንግዲህ...የዛን ዘመን ነበር ቅዱስ እንጦንዮስ ስለ ቀጣዮቹ መነኮሳትና በሃታውያን ራዕይ ተገልጦለት ያየው፡፡ ካየው ራዕይ ባጭሩ መጀመሪያ ነጭር እርግቦች፣ ከዛም ቡራቡሬ በመጨረሻ ደግሞ እንደቁራ የጠቆሩ እርገቦች እንደቁራ የጠቆረችውን እርግብ ተከትለው ሲበሩ ነው ያየው አነዚህ ከሱ ጊዜ ጀምሮ በሱ ስርአት እያለፉ ከሱ በኋላ ላለፉት መነኮሳትና በሃታውያን ነው፡፡ በባሌም በቦሌም መጨረሻሳ ላይ የታዩት እርግቦች ጥቋቁሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለራስህ ፍራ እንጂ ከሚመጡ አባቶች አንዳች አትጠብቅ፡፡ ስለነሱ በራቡሬም በለው እንደቁራ የጠቆሩ ምንም በጎ ነገርና በጎ ትንቢት የለም፡፡ እራስህን አድን!

   Delete
 22. Dn. Daniel Egziabher amlak yetasdekun bereket yasaderebin. Lantem tsegana bereketun yabzalih. Ye agelgelot zemenihin yarzmilih.
  Dn. Daniel ye Abatachin ye Abune Philipos tarik ejig yemimesit talak tegadelo new be ewenet Egziabher yestilin. Yemiketilewinim tsehuf begugut entebekalen.
  Dn. Daniel anid wendeme kelay endegeletsew "የቦታዎቹ ስም ወደ ትግርኛ የተጠጋ ሲሆን በተለይ “ጌርጌስ” የሚለው ስም በምእራባዊ ትግራይ አከባቢ ማለትም ሽሪ እና የሰሜን ጎንደር በረሃማ ካባቢዎች ተከዜን ይዘህ እሰካ ማይ ፀብሪ ድርስ የተለመድ ስለሆነ ፍለጋህን ወደዚህ አከባቢ ብታደርግ፡፡"
  kalhone demo ezaw Shire wede Aba Guna meheja Mayi Weyni Abune Gebremenfes Kidus Gedam ale ena eza ke 200 amet belay edme yalachew talak abat alu ena eza hedeh beteteyekachew liyawkut yechilu yehonal. Egziabher amlak kante gar yehun. Ye tadku abatachin ye Abune Philipos bereketachew kehulachin gar yehun.

  ReplyDelete
 23. ዲ/ን በርታ።እግዚአብሔር ይርዳህ።

  ReplyDelete
 24. በዚህ ጉዳይ ላይ ዝርዝር ነገር ከፈለጉ ረዥም ጊዜ በፈጀ ጥናት የተዘጋጀውንና በቅርብ ቀን የሚታተመውን ‹‹አራቱ ኃያላን›› የሚለውን መጽሐፍ ያንብቡ)ውድ ወንድሜ ድያቆን ዳንኤል የት ይገኛ መጽሐፍ?

  ReplyDelete
 25. dani ebakehen serawochehen tolo tolo awetalen beteleyime dogmawi yehonu metseahafeten embete edmeahene tenahene tebarkew

  ReplyDelete
 26. egzihabere yabertahe

  ReplyDelete
 27. i am robel from addis
  it was very good

  ReplyDelete
 28. selestumete from addis
  dani egzihabere yitebekehe edemeaheh yarzemew lealoche serawochehe tolotolo betawetalene beteleyi dogmawi yehonuten yabatochachenen metsehafet

  ReplyDelete
 29. egzihabehere yistelen

  ReplyDelete
 30. ‹‹አቤቱ ይህንን በእኔ ላይ ያደረጉትን ግፍ ተመልከት፤ ግማሹ ውኃ፣ ግማሹም እህል ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ግን አልሰጡኝም፡፡ እነርሱ ግን በደስታ ይበላሉ ይጠጣሉ›› ብሎ ወደ ፈጣሪው እስኪያመለክት ድረስ በረሃብ አለንጋ የተገረፈው አባ ፊልጶስ የት ይሆን የገባው?፡፡

  ReplyDelete
 31. D/n Daniel Part two bagugute eyatabaku nawu enhe talake abate yate gabu yamelawune lamawake Please fatane argawu Egizabhare yerdahe.

  Thank you very much.

  ReplyDelete
 32. ወንድማችን ሰላሙን ያብዛልህና በስደት ያለነው ምእመን ወገኖችህ እንደልብ የምትለንን መጽሐፍ ገዝተን ለማንበብ እድሉ ሰፌ አይደለም። አለ ካልክ እባክህ ጠቁመን።
  የድሕረ ገጽህ ተከታተለይ!!

  ReplyDelete
 33. እግዚአብሔር አምላክ የድካምክን ዋጋ ይክፈልልን ።

  ReplyDelete
 34. bewenetu serah ejig grum new.....tadequ yeteweldubet let be ahunu alamata meerab merewa seminawi aqetacha let yemibal wenz ale kezih akaya...filegahin wed angot aqetacha bitadereg yemibeji yemeselenal....mikinayatume sel angot zerezer tari beqerebu ye raya hizb tarik bemilew mesehaf anbibalehu......fetari guzuhune ena felegahin yasakaleh...

  ReplyDelete
 35. Hi Dani i wish u to write about mitak Amanual church.There was a monk whose sound only heard until the end of 1790EC.And now there are monks still now in this church who communicate with this monk at.So Please go and collect information before they passed away.
  helen

  ReplyDelete
 36. E/R yirdachihu yihegnawm tiwlid yebereketu tekafay endihone egziabher yirdan!!!

  ReplyDelete
 37. Egziabher yredah simada wereda gena yaltaye taric alat yebzu kidusan yetegenubat ena yalubat hegere kidist nat yene aba eyesus moa ,yene welete peter's,yene aba sntun tekshe sntun ltewew yeliku yene memhr getu yebzu kidusan yelikawnt meflekiya bzu taricawie botawoch megena nat d/n ante yayehw tnsh kmsha new egzieabher yabertah yalewn mereja enredahalen kezihwnew yalenew 4 kilocampaus slalen enredahlen.

  ReplyDelete