Thursday, January 3, 2013

የሐሳብ ልዩነት እንደ ኃጢአትቤተ ክርስቲያን ይህንን ሰሞን ከዕርቅና ከፓትርያርክ ምርጫ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ወገኖችን የሐሳብ ፍጭት እያስተናገድች ትገኛለች፡፡ አንድ ሰው የቱንም ዓይነት ሐሳብ ይኑረው ለቤተ ክርስቲያን ይበጃል ብሎ ሐሳብ እስከሠነዘረ፣ ያንን ሐሳቡንም ከሸፍጥና ከሰይጣናዊ መንገድ በተለየ መልኩ ባገኘው የተፈቀደ መድረክ ላይ ሁሉ እስካንጸባረቀ ድረስ ለቤተ ክርስቲያን ይበጃል እንጂ አይጎዳትም፡፡
ቀደምት አበው የቤተ ክርስቲያንን አመራር ከግለሰባዊነት ይልቅ ለጉባኤ የሰጡበት አንዱ ምክንያት ውይይት፣ ክርክርና የሐሳብ ልዩነት እንዲኖር ብለው ነው፡፡ አንድ ሰው በተመደበበት የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነትና በተፈቀደለት የአገልግሎት ሜዳ ውስጥ ይበጃል ያለውን ሐሳብ ማንሣት፣ ለሐሳቡም ማስረጃ አቅርቦ መከራከር፣ በስተመጨረሻም በጉባኤው ሕግ መሠረት ለጸደቀው ሐሳብ መገዛት ይጠበቅበታል፡፡

በ51 ዓም በኢየሩሳሌም የተደረገችው የመጀመርያዋ የቤተ ክርስቲያን ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ ምክንያት በክርስቲያኖችና እነርሱንም በሚመሩና በሚመግቡ አባቶች መካከል በተነሣው የሐሳብ ልዩነት ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከአይሁድ ማኅበረሰብ ወጥታ ወደ አሕዛብ መንደር ስትገባ በአሕዛብና በአይሁድ ክርስቲያኖች መካከል ከአነዋወራቸው የተነሣ የሓሳብ ልዩነት ተፈጠረ፡፡
ይህ የሐሳብ ልዩነትም በጉባኤ ኢየሩሳሌም ታይቶ በስተመጨረሻ አባቶችና መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን ይበጃል ያሉትን ውሳኔ ወሰኑ፡፡ በጊዜው ‹ብዙ ክርክር› እንደነበረ የሐዋርያት ሥራን የጻፈው ቅዱስ ሉቃስ ገልጦታል (የሐዋ 15÷7)
እንኳን ቤተ ክርስቲያንን በሚመራው ሲኖዶስ መካከል ቀርቶ በሁለትና በሦስት አባቶች መካከል አገልግሎትንና ለአገልግሎት የተሻለ የሆነውን መንገድ በመምረጥ ረገድ ልዩነት የታየበት ጊዜም ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስን ወደ ቤተ ክርስቲያን በማምጣት፣ ከሐዋርያትም ጋር በማቀራረብና በክርስቲያኖች ዘንድ የነበረውን ተፈሪነት በማስቀረት ታላቅ ሚና በተጫወተው በቅዱስ በርናባስና በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መካከል የሐሳብ ልዩነት ተፈጥሮ ነበር፡፡
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚነግረን የሐሳብ ልዩነቱ መነሻ ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስን የተመለከተ ነበር፡፡ ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጋር ለአገልግሎት ወጥቶ የነበረው ቅዱስ ማርቆስ አገልግሎቱን አቋርጦ ወደ እናቱ መመለስ ፈለገ፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር የነበረው በርናባስም እንዲመለስ ፈቀደለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን ወደ ኋላ መመለስ የለም አለ፡፡ በርናባስ ግን ይዞት ወደ ኢየሩሳሌም አደረሰው፡፡
በሌላ ጊዜ አስቀድመው በሰበኩበት ቦታ ተመልሰው ወንድሞችን ለማየት ሲመካከሩ በርናባስ ማርቆስን ለመውሰድ አሰበ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን አስቀድሞ ከጉዞ አቋርጦ መመለሱን አስታውሶ መሄድ የለበትም አለ፡፡ በዚህ ምክንያት በሁለቱ አባቶች መካከል ‹እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ› (የሐዋ15÷36-40)፡፡ ይህ በሐሳብ መለያየታቸው ግን ቤተ ክርስቲያንን ጠቀማት እንጂ አልጎዳትም፡፡ ‹አንድ ቢሆኑ ኖሮ ወንጌል ትጸናለች አትሰፋም ነበር፤ በመለያየታቸው ግን ወንጌል ሰፋች› ይላ መተረጉማ፡፡
ዮሐንስ አፈወርቅና ቅዱስ ኤጲፋንዮስ የቁስጥንጥንያዋን ንግሥት ብርክልያን በተመለከተ የተለያየ ሐሳብ ነበራቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹ብርክልያ ለምትፈጽመው ግፍ ፊት ለፊት መወገዝ አለባት› ሲል፣ ኤጲፋንዮስ ደግሞ ‹እርሷን ማውገዙ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከባድ ፈተና ያመጣል› ብሎ ያምን ነበር፡፡ ይህ ውይይት በቁስጥንጥንያ ሲደረግ ሁለቱ አባቶች በአቋም ስላልተግባቡ እስከ መለያየት ደርሰው ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ዛሬ የሁለቱንም አባቶች ቅዳሴ ትቀድሳለች፡፡
በ13ኛው መክዘ ቤተ ኤዎስጣቴዎሳያንና ቤተ ተክለ ሃይማኖታውያን የሁለቱን ሰንበት አከባበር በተመለከተ የተለያየ አቋም ነበራቸው፡፡ በኋላ ዘመን በጉባኤ ደብረ ምጥማቅ ወደ አንድ አቋም እስኪመጣ ድረስ ከባድ ክርክር ይደረግ ነበር፡፡ እንዲያውም በገድለ ዜና ማርቆስ እንደምናነበው በዓምደ ጽዮን አደባባይ አቡነ ኤዎስጣቴዎስና አቡነ አኖሬዎስ በጉዳዩ ሲከራከሩ በመገኘታቸው ከንጉሡ ዘንድ አቡነ አኖሬዎስ ከባድ ቅጣት ገጥሟቸው ነበር፡፡ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ መጀመርያ እስክንድርያ፣ በኋላ ኢየሩሳሌም፣ ከዚያም ቆጵሮስ፣ በመጨረሻም አርመን ሄደው ያረፉት በዚህ ክርክር ምክንያት ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን አቡነ ኤዎስጣቴዎስንም አቡነ አኖሬዎስንም ቅዱስ ብላ አክብራቸዋለች፡፡
በዐፄ በዕደ ማርያም ዘመን፣ እጨጌ መርሐ ክርስቶስ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት እያሉ ከግብጽ የሚመጡትን ጳጳሳት በተመለከተ በደብረ ሊባኖስ ታላቅ የሊቃውንት ጉባኤ ተደርጎ ነበር፡፡ በጉባኤው ላይ ‹ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ጳጳሳት እንሹም‹ የሚሉ ሊቃውንት ሐሳባቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ ‹ከግብጽ እያስመጣን እንቀጥል› ያሉ ሊቃውንትም ሐሳባቸውን አቅርበው ነበር፡፡ በወቅቱ በተደረገው ከባድ ክርክር ከአቡነ መርሐ ክርስቶስ በቀር ወደ ስድስት መቶ የሚጠጉት ሊቃውንት ‹እኛው የራሳችንን ጳጳሳት እንሹም› የሚለውን አጸደቁት፡፡ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ግን አልተስማሙም ነበር፡፡ በመጨረሻም ንጉሡ ጉዳዩን በይደር እንዳቆዩት በዚያው ቀረ፡፡
እንዲህ እያልን ብንቀጥል በቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘንድ ለአንድ ችግር በሚሰጥ የመፍትሔ ሐሳብ የተለያዩ አቋሞችን መያዝና፣ በዚያ አቋም መከራከርም ያለና የነበረ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
በዚህ ወቅት ግን አባቶቻችን ዕርቁንና የፓትርያርክ ምርጫውን በተመለከተ የተለያየ ሐሳብ በመስጠታቸው ምክንያት ሁሉም ከእርሱ ሐሳብ በተቃራኒው የሆኑትን ወይም ይሆናሉ ብሎ የገመታቸውን አባቶች ያወግዛል፤ ያስፈራራል፤ እንደ ኃጢአተኛ እየቆጠረም እኛ ያልነውን ካልተቀበላችሁ በቀር ሕዝብ እንዲያወግዛችሁ እናደርጋለን ይላል፡፡
ይህ ዓይነቱ አሠራር በቤተ ክርስቲያን ጉዞ ላይ ሦስት ችግሮችን ያመጣል
1.         አባቶች ሐሳብ አንሥተው ከመከራከርና ከመወያየት ይልቅ ‹ኦሆ በሃሊ› ብቻ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ነገ የሚገጥማቸውን ማንኛውንም ዓይነት ተጽዕኖ በጥብዐት ከመመከት ይልቅ በፍርኃት እሺ ብቻ ብለው እንዲቀበሉ ያደርጋቸዋል፡፡
2.       የብዙኃንን ጭቆና ያመጣል፡፡ አምባ ገነንነት ሕዝብን እንደ ገል ቀጥቅጠው፣ እንደ ሰም አቅልጠው በሚገዙ ግለሰቦች ላይ ብቻ የሚታይ አይደለም፡፡ ቡድንም፣ ማኅበረሰብም አምባገነን የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ ቡድንና ማኅበረሰብ ‹ጊዜ የወለደውን፣ ሕዝብ የወደደውን› ብቻ ተቀበሉ ብሎ ግለሰቦችን የሚደፍቅበትና ነጻነታቸውን የሚነሣበት ጊዜ አለ፡፡ የአንድ ሰው ሐሳብ የሚመዘነው በሐሳብ አቀራረቡ፣ ባቀረበው ማስረጃ፣ በተከራከረበት ዐውድ፣ ብሎም በሐሳቡ መንገድ ሳይሆን ምን ያህል ሰው ተቀብሎታል በሚለው ይሆናል፡፡ እንዲህ ያለው አሠራር ለምርጫና ለሥልጣን እንጂ ለሐሳብ አይሆንም፡፡
ጌታችን በዚህ ምድር ሲያስተምር ከጠቅላላው ሕዝብ አምስት ገበያ ሰምቶታል፤ ከሰማው አምስት ገበያ ሕዝብ መቶ ሃያው ተቀብሎታል፡፡ ከመቶ ሃያውም አንዱ ይሁዳ ከድቶታል፡፡ የጌታችንን መዋዕለ ሥጋዌ ምን ያህል ሰው ተቀበለው? በሚለው የምንመዝነው ቢሆን ኖሮ ማናችንም ክርስቲያን ባልሆንን ነበር፡፡
3.       የሓሳብ ክርክር ወርዶ ወደ ግለሰባዊ ክርክር ይገባል፡፡ ሰው መመዘን ያለበት በአቋሙ ነው፡፡ ክርክር ሊደረግበት የሚገባውም አቋሙ ነው፡፡ ተክለ ሰብእናው አይደለም፡፡ ሐሳብ የሚፈራና ሐሳብን የሚሞግት ዐቅም የሌለው ብቻ ነው ተክለ ሰብእና ላይ የሚንጠለጠለው፡፡ ሰው ‹ሐሳብህ ትክክል አይደለም› እንጂ ‹እንዴት እንደዚህ ታስባለህ?› ሊባል አይቻልም፡፡ ያውም ደግሞ ለሕዝብ በኦፊሴል ክፍት ባልሆነ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ውስጥ ዘልቆ ገብቶ እገሌ ለምን ይህንን ሐሳብ ሰጠ፣ እገሌስ ለምን ይህንን ተናገረ፣ እገሌስ ለምን እንደዚህ ያስባል፣ እገሌስ ለምን ዝም ይላል እያሉ መክሰስና መውቀስ ከማሸማቀቅ ያለፈ ዋጋ አይሰጥም፡፡
በሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምርጫ ሕግ የፖፑ ምርጫ እስኪጸድቅ ድረስ የሲኖዶሱ አባላት ከማንም ጋር እንዳይገናኙ፣ መግለጫ እንዳይሰጡና፣ በሌሎች ጫና ውስጥ እንዳይገቡ የሚደረገው በነጻነት የመሰላቸውን ሐሳብ አቅርበው መከራከርና መወያየት እንዲችሉ ለማድረግ ነው፡፡ በኛ ዘንድ ግን ይህ ዓይነቱ አሠራር ባለመኖሩ ‹የፓርላማ አባላት እንኳን በጉባኤያቸው ላይ በሚሰጡት ሐሳብ አይከሰሱም› በሚባልበት ዘመን አባቶች በጉባኤያቸው በሰጡት ሐሳብ ምክንያት ይዘለፋሉ፤ ይከሰሳሉ፤ ማስፈራርያም ይደርሳቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የሚቀርቧቸው ሰዎች ‹ምን አስጨነቀዎት፤ ለምን ዝም አይሉም፤ ለምን ይወጋሉ› እያሉ ‹እምነ ተናግሮ ይኼይስ አርምሞ› እንዲሉ ያደርጓቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ዛሬ የአንዳንዶቻችንን ሐሳብ ለማራመድ ጠቅሞን ይሆናል፡፡ ነገ ግን ልማድ ሠልጥኖ ሕግ ይሆንና ጥቂት ክፉዎች ብዙኃኑን እንዲዘውሩት ያደርጋል፡፡
በአንድ እግር ኳስ ሜዳ ላይ ተመልካቾች፣ ተጨዋቾች፣ ዳኞችና ረዳት ዳኞች ይኖራሉ፡፡ የተጨዋቹ ድርሻ መጨዋት ነው፡፤ ሕግና ደንቡን ጠብቆ መጨዋት፡፡ የተመልካቹ ድርሻ መደገፍ ነው፡፡ ሕግና ደንቡን ጠብቆ መደገፍ፡፡ የረዳት ዳኞቹ ድርሻ ማመልከት ነው፡፡ ሕጉም ‹ለዳኛው ያመለክታል› ነው የሚለው፡፡ የዳኞቹ ድርሻ ደግሞ መወሰን፡፡ ተመልካችም፤ ተጨዋችም፣ ረዳት ዳኛም ሊወስኑ አይችሉም፡፡ ሊወስን የሚችለው ዳኛው ነው፡፡ ማመልከት፣ ማሳየት፣ መጠቆም፣ ሐሳብ መስጠት ግን ይችላሉ፡፡ ዳኛው ሲወስን ግን ሁሉ ይጸናል፡፡
ምንም ያህል ብናውቅ፣ ምንም ያህል ብንራቀቅ፣ ምንም ያህል ሐሳብ ቢኖረን፣ ምንም ያህል ሐሳባችን ትክክልም ቢሆን፣ ምንም ያህል ብንጽፍና ብናትም፣ የኛ ድርሻ ሐሳብ ማቅረብ ነው፡፡ ሐሳባችን ሊሰማ በሚችልበት መንገድ ማቅረብ፡፡ መወሰን ግን የኛ ድርሻ አይደለም፡፡ መወሰን የቅዱስ ሲኖዶስ ድርሻ ብቻ ነው፡፡ አንድ ቡድን በዳኛው ውሳኔ ላይስማማ ይችላል፡፡ ነገር ግን የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡ ቅሬታ ማቅረብ ይችላል፤ ነገር ግን ለርሱም ሥርዓት አለው፡፡ አንድ ምእመንም በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ላይስማማ ይችላል፡፡ ነገር ግን የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡ ቅሬታ ሊኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን ሐሳቡን ማቅረብ ያለበት በሕግና በሥርዓት ብቻ ነው፡፡
በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በሚቀርብ አጀንዳ መልካም ነው ያሉትን ሐሳብ ያቀርቡ፣ ለሐሳባቸውም ይከራከሩ ዘንድ የስብሰባው ሥነ ሥርዓት ሕግ ይፈቅድላቸዋል፡፡ ያ ሐሳብ በኛ መመዘኛ አይጠቅም ይሆናል፡፡ ግን መብታቸው ነው፡፡ ማንኛውም በጎ ሐሳብ መብትን እስከ መከልከል ከሔደ በጎነቱ አበቃለት ማለት ነው፡፡
ሌላው ቀርቶ ‹ፓትርያርክ ሊሆኑ ይፈልጋሉ› እየተባሉ የሚታሙት አባቶች እንኳን የሚወጣውን መመዘኛ እስካሟሉና ሥርዓቱን እስከጠበቁ ድረስ ፓትርያርክ ሊሆኑ መፈለጋቸው ነውሩ ምንድን ነው? በቅርቡ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን በተደረገው ምርጫ ከስድስት በላይ አባቶች ራሳቸውን ለዕጩነት አቅርበው አልነበር እንዴ? ቅዱስ ጳውሎስስ ‹ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካሙን ሥራ ይመኛል› ብሎ አስተምሮ የለም እንዴ? (1ኛጢሞ 3÷1) እነዚህን አባቶች መውቀስ የምንችለው ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ከተጓዙ ብቻ ነው፡፡ ለምን መንፈሳዊ ሹመት ፈለጋችሁ? ብለን ዘራቸውን፣ ብሔረሰባቸውንና ተክለ ሰብእናቸውን ልንወቅስ አንችልምኮ፡፡ መሆን የለባችሁም ስንል መከራከር ያለብን በሕጉና በሥርዓቱ መሠረት እንጂ ‹እንዴት እንዲህ ይላሉ› በሚል መሆን አይችልም፡፡ ያውም ደግሞ ከጥርጣሬና ከወሬ በቀር ምንም ማስረጃ በሌለው ነገር፡፡ 
በሌላም በኩል ደግሞ አሁን በቤተ ክርስቲያን በተፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ከኛ የተለየ ሐሳብ ሠንዝራችኋል እየተባሉ የሚወቀጡም አካላት አሉ፡፡ በአንድ በኩል ‹አቡነ መርቆሬዎስ ከነ ሙሉ ሥልጣናቸው ወደ መንበራቸው ይመለሱ› የሚሉ አሉ፡፡ በሌላ በኩል ‹አዎ ይመለሱ፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ በእንደራሴ ትመራ› የሚሉም አሉ፡፡ ‹የለም ዕርቁም ይቀጥል፤ ቤተ ክርስቲያንም ስድስተኛውን ፓትርያርክ ትምረጥ፤ እርሳቸውም መጥተው በክብር ይኑሩ› የሚሉም አሉ፡፡
እነዚህ ሁሉ ወገኖች ለቤተ ክርስቲያን ብለው ሐሳባቸውን እስከሰጡ ድረስ ሊወገዙ፣ ሊኮነኑና ሊብጠለጠሉ አይገባም፡፡ ሐሳባቸውን በማስረጃና በተጠየቅ መሞገት ግን ይቻላል፡፡ የኔ ሐሳብ ከአንተ ይሻላል ብሎ የሚሻልበትን መንገድ ማሳየት ይቻላል፡፡ ያኛው ሐሳብ ስሕተት ነው ብሎ ስሕተት የሆነበትን ምክንያት ማመልከት ይቻላል፡፡ የሁሉም ነገር ማሠርያው ግን ኃላፊነትና ሥልጣን የተሰጠው አካል ውሳኔ ነው፡፡ እርሱም ቅዱስ ሲኖዶስ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ እኔ የምፈልገውን ካልወሰነ በቀር ‹መንግሥት ተጭኖት ነው፣ ሥልጣን ተፈልጎ ነው፤ ዘር ነው፣› እያሉ የውግዘት ጋጋታ ማዝነብ በተመልካች ወንበር ላይ ተቀምጦ የዳኛ ፍርድ እንደመስጠት ያለ ነው፡፡ ‹ከእኔ ጋር ያልሆነ ሁሉ ከጠላቴ ጋር ነው› የሚለው የቀዝቃዛው ጦርነት አሠራር ዛሬ የሚሠራ አይደለም፡፡
ይልቅ አባቶቻችን ሆይ
ተከራከሩ፣ በሓሳብ ተፋጩ፣ መንፈሳዊነትን ባልዘለለ መንገድ ልዩ ልዩ ሐሳቦችን አቅርባችሁ በዚያው በሲኖዶሳችሁ ውስጥ ተከራከሩ፡፡ ሐሳባችሁ የምንደግፈውም ይሁን የምንቃወመው፤ የምንፈልገውም ይሁን የምንጠላው እናንተ ግን ለእግዚአብሔር፣ ለሕግና ለኅሊናችሁ ታማኞች ሆነችሁ በጎ ነው ባላችሁት፣ ቤተ ክርስቲያንን ይጠቅማል ባላችሁት ሐሳብ ተከራከሩ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ብዙኃን ግለሰቦችን እንደሚጨቁኑ አስቡ፡፡ ሴትዮዋ ‹አፍ ያለው ያግባሽ ከብት ያለው› ስትባል ‹አፍ ያለው ያግባኝ፣ በአፉ ከብቱን ያመጣዋል› ያለችው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሐሳባችሁን በሕግ፣ በማስረጃና በተሻለ ሓሳብ እንጂ በጩኸት ብዛት አትቀይሩ፡፡ የተጮኸለት ሁሉ ትክክለኛ አይደለም፤ ስሕተትም አይደለም፡፤ ዕድለኛ ሐሳብ ነው እንጂ፤ ያልተጮኸለትም ስሕተት አይደለም፤ ትክክለኛም አይደለም፣ ዕድለ ቢስ ሐሳብ ነው እንጂ፡፡
ይልቅ ቤተ ክርስቲያን ትጠቀም ዘንድ ተለያይታችሁ ተከራከሩ፤ አንድ ሁናችሁ ግን ወስኑ፡፡

62 comments:

 1. "ይልቅ ቤተ ክርስቲያን ትጠቀም ዘንድ ተለያይታችሁ ተከራከሩ፤ አንድ ሁናችሁ ግን ወስኑ፡፡"
  ግን ዳኒ,"አውቆ የተኛ...." በክርክር ያምናል??????

  ReplyDelete
 2. yeah thank you Dn Dani

  ReplyDelete
 3. ዳ ዳንኤል
  ጥሩ ብልሃል ነገረ ግን አሁን እየተካሔደ ያለው ነገረ
  1. ከእርቁ በፊት ለምርጫ መሮጥ በየትኛው የክርስትና መስፈረት ነዉ ትክክለኛ ሆኖ አባቶቹ እራሳቸዉን ለምርጫ ዕጩ አድርገዉ የሚያቀርቡት(መጀመሪያ መታረቅ መስማማት መፋቀር ይቀድማል)። በእርግጥ አባቶቻችን ማስፈራራት ተገቢ አይደለም
  2. እንተዉ እራስህ ባሳላፈነው ሃያ አመታት የተመለከትከው ብዙ ችግር በቤተ ክርስቲያናችን ተከስቷል። አንድም ሲኖዶሶ ባሳለፋቸው ዉሳኔዎች። ለመሳሌ ለአንድ ሀገረ ስብክት ጳጳስ ሲመድብ ችግር የሚፈጥር መሆኑ እየታዋቀ እና አቤትም ሲባል የሚሰማ ሲጠፋ አሜን ብላችሁ ከነስህተቱ ከነችግሩ ተቀበሉት ማለትህ ነው
  3. በአጠቃላይ አንተ ያልከዉ ሃሳብ የሚሰራው በአብዛኛው ከዘር የጸዳ፣ለስልጣን የማይሮጥ፣ሕይወቱን ለክርስቶስ ለቤተክስቲያን የሰጠ፣እንደ አቡነ ጴጥሮስ ለቤተ ከርስቲያን ለምዕመናኑ እራሱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ አባት ያለበት ሲኖዶስ ሲኖር ነው። ይህንን ስል አሁን አባቶች የሉም ማለቴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ። ድምፃቸው እንደሌሎቹ የመሰማት እድል አለማግኘቱ ግን በጣም ያሳዝናል

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ/ እህቴ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
   እንዴ ዳንኤል እስኪ ከላይ ለተጠቀሱት አስተያየት መሰል ጥያቄ መልስ ስጥ። አንተ የምትኖረው እኛ የምናውቃት ሀገር ውስጥ አይደለም እንዴ? ወይንስ አንተ እንዲህ ብለህ የምትጽፍላቸው አባቶች እኛ የማናውቃቸው ናቸው? ምን ግራ የገባው ነገር ነው። አንተ "ሁሉም ወደ የበኣቱ" ትላለህ። እንዴት በአሁን ሰዓት በበኣት ዝም ብሎ መቀመጥ ይቻላል። ይኸው ለአንተም አልሆነ። እኛንም ዝም በሉም አባቶች የፈለጉትን የስሩ ትላለህ እነሱማ የፈሉትን ሲሰሩ ኖረዋል፤ ሊሰሩም ተዘጋጅተዋል። እውን ቤተ ክርስቲያን የእነርሱ ብች ነች? እንዴት ነው ነገሩ። ይህ ጽሁፍ ስለ እውነት አሁን ያለችውን ቤተ ክርስቲያን በፍጹም አይገልጽም። ወቅታዊም አይደል። እንደው ምናባዊ ነው።

   Delete
 4. ዲ.ን. ዳንኤል አንተም የፈለከውን ሀሳብ እንድታነሳ ሊከለክልህ የሚችል የለምና ጽፈሃል። አከብርሃለሁ።

  ሆኖም በአሁኑ ሰዓት ከብዙ አቅጣጫ የሚሰጠው አስተያየት አንተ እንዳልከው ለምን የሀሳብ ልዩነት ተፈጠረ ሳይሆን የተፈጠረው የሀሳብ ልዩነት አሀቲ ቤተ ክርስቲያንን ከሁለትና ከዚያ በላይ የከፈለ ስለሆነ በእርቅ ይቋጭ የሚል ነው። የተለየ ሀሳብ ለማራመድ በሚል ሰበብ ብቻ የክፉ ሀሳብ ደጋፊ የሆነ መልእክት መጻፍህን ለዛሬ አልወደድኩትም። የማንም ይሁን የማን ደጋፊ ለቤተክርስቲያን አንድነት የሚቆረቆር ማንኛውም ሰው መጮህ ያለበት አንድ ጩሀት "እርቅ ይቅደም" የሚለው ወቅታዊ ጉዳይ ብቻ ይመስለኛል። የእርቁ ጉዳይ እንደተንጠለጠለ "ምርጫ እናካሂድ" የሚሉ ጳጳሳትን እንድናበረታታ ለምን እንደፈለግህ በቅጡ ከማብራራት ይልቅ በቀደምት አበው መካከል ስለነበረ የሀሳብ ልዩነት ልታስረዳን መሞከርህ ያለቦታው የገባ ይመስለኛል።

  ይህን ሀሳብ የሰጠሁት ከሞላጎደል አብዛኛው ሰው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና ሰላም ወደአንድ ሀሳብ እየመጣ ባለበት ሰዓት የሚከፍል አስተያየት መስሎ ስለተሰማኝ ነው። በርታ!

  ReplyDelete
 5. dn. daniel
  "yalteredut" neger kelay yetekesuachew abatoch bikerakeru hulum lebetechristian yitekimal yalutin hasab new.............yahunochu gin yeteleyayu sergo geb silalubin mekerakeriyachew lekomolet alama new ......Egziabiher lebetechristian selam ena fikirin yisit!!!

  ReplyDelete
 6. Ewnet belehallll....bech egeziabher abatochachen kena menged yasayachew, antenem yebarekelen....Amen

  ReplyDelete
 7. አሳብን ማክበር መልካም ነው:: ግን ደግሞ የተጮኽውን ሁሉ ማን የሚሰማ መሰለ አይ ዳኒ አይዞ:: እንኳን አሁንና የሚለውን የዘመቻ ግጥም ረሳኽው? እኛ እኮ ብሎግ ባይኖረን ፌስቡክ አለን:: ያም ባይኖረን የት ድረስ እንደምንከተላቸው አሳምረን እናውቃለን:: መቼም አንተ የ1980ዎቹን ጉዶች በሚገባ ታስታውሳለህ:: ሩቅ የሄድነው ቀጨኔ ድረስ ነው:: ኦን ላይን የት ድረስ እንሄዳለን ብለህ ነው? ያውም ዘዋሪዎቹን ከማናውቃቸው የ”ባሕትዬ” ብሎጎች ጋር::

  አይሁንብንና
  እስቲ ትሰሙ እንደሁ አይሁንብንና ሰሜን አሜሪካ ላይ ያለው ልዩነት አገር ቤት አስገብታችሁ አስባችሁት ታውቃላችሁ? ግቢ ገብርኤል የስደተኛው፣ ልደታ ገለልተኛ፣ አራዳ ጊዮርጊስ በቦርድ፣ ቅድስተ ማርያም በአገር ቤቱ፣ . . . እየተባባልን ስንለያይ:: በቴሌቪዥን ለገና 4 ተወካይ እንኳን አደረሳችሁ ሲለን፣ በየንግሥና በዓላቱ ድንዳይ ስንወራወር . . . የፈጣሪ ያለህ አይዘገንንም? አያችሁ ለአሳብ የበላይነት አልገዛ ማለት፣ ቡድኔ ምን አለ፣ ሌላው ሁሉ ስህተት ነው እኔ ብቻ ማለት፣ የሚወልደው ይህንን ነው:: ሕልም ነው ቅዥት እያሉ ከመቀባጠር ምን ማለት ሊሆን ይችላል? ያዩበት መንገድ የትኛው ነው? ማክሸፊያውስ ከየት ይመጣል? እያሉ መጠበብ አይሻልም:: ወንድማችን ፈሊጥ ያውቃል ስጋቶቹን እየፈለፈላችሁ ተመልከቱለት:: ተቀራርቦ መወያየት ብቻውን የሚፈታውን ነገር ይበልጥ ያወሳሰብነው ሕዝብ የያዝን እየመሰለን አይደል? በአሳብ ያልመራችሁትን ሕዝብ በአመጽ ልትገዙት አትችሉም:: መልኩን እንደ ማይቀይር በነቢይ የተነገረለት ሕዝብ ነው:: ታሪኩን ዘወር ብላችሁ ተመልከቱ እየሸኘ ነው የኖረው ምክንያቱም ከማንምና ከምንም ቤተ ክርስቲያኑ ትበልጥበታለች::
  ጎሽ ለልጇ ስትል ተወጋች ይላል ያገራችን ሰው አባቶች ለቤተ ክርስቲያን ሲሉ የሚቀበሉት መከራ ይኖራል:: መሰደብ ፣መወንጀል ፣መከሰስ ፣ መታማት፣ ስም መጥፋት ብዙ ነገር ምኑ ይደንቃል:: ነበር አለ ይኖራል:: የሚገርም ነገር ላንሳ:: አገር ቤት ያሉትን አባቶች የምንግሥት ናቸው:: ብሎ የሚያማ ሰው በረሀ ወርዶ አንጃ የሚያደራጀውን የሰሜን አሜሪካ ሰው ግን የግሉ ነው ይላችኋል:: እንዲህ ናት ሕሊና ያጣች ብእር:: የሚያስቅም አለ :: መንግሥት አላማውን ገለጠ እኛም አውቀናል:: ይህ እንግዲ የዜና ርእስ ነው:: ማስፈራሪያ ነው? ማስደንበሪያ ነው? ማስገደጃ ነው? ለምን ይቀለዳል? ትልልቅ ርእሶች ባዶ አንቀጾች ይዘው ጊዜ ይበላሉ::

  መግለጫዎቻችን
  ቅዱስነታቸው ካረፉ በኋላ የእንቅ አጀንዳ ለምን ገነነ በዘመናቸው የእርቅ ሰነድ አዘጋጅተው ተሳካም አልተሳካም ሞክረዋል:: ያ ነበር የቤተ ክርስቲያን አቋም:: በነበረው እርቅ የመግለጫዎቹ ሰዎች የት ነበሩ? ኩሉ ጻድቅ በጊዜ ርቱእ ሆኖ ይሆን? ምቹ ጊዜ? በዚህ ምክንያት የታዋቂ ሰባኪዎቻችን የተማጽኖም ይሁን የምን ጥሪ የምትሉት ነገር አይገባኝም:: ስለ እርቅና ሰላም አስፈላጊነት ስብከት መጻፍ አይቀልም ነበር:: አብነታቸው የሚታየው ምን ሲሆን ነው? የምንፈልገውን ሲወስኑ ወይስ? ለእርቅ ደጋግመን ካላሰብን ለምን እናስብ? እዚያው ዞናችን ላይ ፖለቲካችንን ብንጦምርስ? ወይ በአሳብ ሞግቱን የሚልቀውን አመላክቱን እንጂ በለምን ይቅርብኝ የሚሰቀሉ የሚወዱትንማ ተው:: ምነው ሌላ ነገር ትተነትኑ የለ እንዴ? የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ካልቻላችሁበት አትንኩት:: በቃ ሲኖዶስ ሲል እኮ ሁሉ ያበቃለታል:: የካበተ ልምድ አጥተን እንጂ መች እርቅ እንደሚቀድም ጠፋን? አመላክቱ የሚሻለውን የሚጠቅመውን ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ሞግቱ::
  ለክርክር የሚረዱ አሳቦች
  አንድ ወዳጄ እንዳለው 4ኛው ፓትርያርክ ራሳቸውን የማይገልጡ ለምንድን ነው? የሚለውን ሲገምት እንዳሉትም አሁንም በሕመም ላይ ይሆናሉ ነበር ያለኝ:: ካልተናገሩ አይታይ ብልሀቱ ይባል የለ:: ብልሀቱን ካጣንበት ምክንያቶች አንዱ የርሳቸው ዝምታ ነው:: ታምራት ላይኔ ድሮም እምነት የለሽ ዛሬ ደግሞ መናፍቅ ነው የርሱን ምስክርነት ለመጥቀስ ያስገደደን ግን አሁንም የርሳቸው ዝምታ ነው:: በእደግፋለሁና እቃወማለሁ የተሰበሰበ የአንድ ብሎግ ድምጽ የሚልየኖችን እጣ ፈንታ ሲወስን ይታያችሁ? ከ10 የሚበልጡት ከስንት ያንሳሉ? ብለን ብንጠይቅስ:: የቁጥር ጥያቄውን ትተን ለምን አይደግፉም? ምን አማራጭ አላቸው? እያልን የአሳብ ጥያቄ ብንጠይቅስ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. I read your comment but got confused in the process.

   You said,
   "አንድ ወዳጄ እንዳለው 4ኛው ፓትርያርክ ራሳቸውን የማይገልጡ ለምንድን ነው? የሚለውን ሲገምት እንዳሉትም አሁንም በሕመም ላይ ይሆናሉ ነበር ያለኝ::"

   If you were a truth seeker and inpartial faithful,you would have followed how your spiritual father, the 4th Patriarch, has been doing all these years. And if you do so honestly, you would have found that he is doing great and carrying out his spiritual duties. Example, he recently inaugurated a cathedral in Toronto Canda. So,your worries about his health, if geniune, should rest when you learn this fact that he is travelling the continental America carrying out his spiritual duties.

   IN HIS 'ARMIMO', I LEARN A LOT ABOUT PATIENCE.

   Delete
  2. አይሁንብንና
   እስቲ ትሰሙ እንደሁ አይሁንብንና ሰሜን አሜሪካ ላይ ያለው ልዩነት አገር ቤት አስገብታችሁ አስባችሁት ታውቃላችሁ? ግቢ ገብርኤል የስደተኛው፣ ልደታ ገለልተኛ፣ አራዳ ጊዮርጊስ በቦርድ፣ ቅድስተ ማርያም በአገር ቤቱ፣ . . . እየተባባልን ስንለያይ:: በቴሌቪዥን ለገና 4 ተወካይ እንኳን አደረሳችሁ ሲለን፣ በየንግሥና በዓላቱ ድንዳይ ስንወራወር . . . የፈጣሪ ያለህ አይዘገንንም? አያችሁ ለአሳብ የበላይነት አልገዛ ማለት፣ ቡድኔ ምን አለ፣ ሌላው ሁሉ ስህተት ነው እኔ ብቻ ማለት፣ የሚወልደው ይህንን ነው:: ሕልም ነው ቅዥት እያሉ ከመቀባጠር ምን ማለት ሊሆን ይችላል? ያዩበት መንገድ የትኛው ነው? ማክሸፊያውስ ከየት ይመጣል? እያሉ መጠበብ አይሻልም:: ወንድማችን ፈሊጥ ያውቃል ስጋቶቹን እየፈለፈላችሁ ተመልከቱለት:: ተቀራርቦ መወያየት ብቻውን የሚፈታውን ነገር ይበልጥ ያወሳሰብነው ሕዝብ የያዝን እየመሰለን አይደል? በአሳብ ያልመራችሁትን ሕዝብ በአመጽ ልትገዙት አትችሉም:: መልኩን እንደ ማይቀይር በነቢይ የተነገረለት ሕዝብ ነው:: ታሪኩን ዘወር ብላችሁ ተመልከቱ እየሸኘ ነው የኖረው ምክንያቱም ከማንምና ከምንም ቤተ ክርስቲያኑ ትበልጥበታለች::

   Delete
 8. Dani,

  I am sure you don't post this but I will keep write. For me what you write above is a politics which support TPLF. So that peoples do not comments on what ever synodos members are doing. As your heart knows, peoples are commenting on the priority of the reconciliation than working on the next patriarch. Please Dani DO NOT hide your internal feeling for the sake of politics.

  ReplyDelete
 9. This is good idea. However i am disturbed by a new development in San Diego CA. When everyone is attempting to bring the two camps together a third one is appearing. Just for once can we stop and think and what is better for the church and the laity? This third group has established a new St Taklehaimanot church and many of are saddened by it. Please stop and think twice, three times... for the hundredth time, what is going to be achieved by this? We are still unable to remove the poison that started in California twenty or so years ago and we are planting another one.

  January 3, 2013 9:08 PM

  ReplyDelete
  Replies
  1. I'm sorry for the above writer since i haven't seen any laity of orthodox is disturbed by the opening of Tewahido church. However the problem in San Diego is the two st. Gebriel churches are not there for the sake of the faith, but rather they have there own agenda. The church that used to be governed by the Ethiopian synod have declared that they are not going the respect the decision of the synod and the father there have said he is not going to pray when the synod declared "Mihila" from Puagme 1 to meskerem 10. He has a message when he said this; that is the church is not going to respect the ongoing reconciliation b/n the fathers. He also have declared that he is not going to accept spiritual organizations as we all know. He put his politics before his faith! i say this because i know for fact. The brothers and sisters in san diego have worked with me in the case of Waldba. What they have gone through is beyond my explanation. I am glad they have finally stood up and send the right message and devil is not going to stand them since they have Abune Teklehaimanot.
   By the way, do you know the above st. Gebriel churh is being led by the same "sebeka gubae" for more than 7 years.
   Do you know that the "sebeka gubae" president is not in the city for more than 2 years.
   There are too many "why's" in that church. we need to be strong in my city and found the right church too.
   I am sorry again for the above writer who doesn't understand the core of the problem.

   Delete
  2. Ebakwon chigirun bedenb yabrarut?

   Delete
  3. Hi Dani teru tsehuf neew gen kelay asteyayet yesetew sew kereesu gar menem ayegenagnem. Bedenb alanebebewem Tekesun balastawesewem Tasdekanen yemitelu yetsetsetalu yelal lemen tsadeku Abune Tekelehaimanoten endemitelu ligebagn alchalem menafekan nachew Betekerestiyanen yemimeseret Keresetos neew bedemu selezih lebuna yesetachew becha lebetekerestiyan keber sibal huletum Gebrieloch laay yalut abat nene bayoch sewu bedend biyatenachew teru neew Fetarin teto enesun endiyamelkachew eyaderegu berkata asafari dergit eyaderegu neew neseha igebu teru neew Tsadeku abune Teklehaimanoten matelelalat menafekenet neew.

   Delete
  4. ውድ ወንድሜ እኔ እስከማውቀው በሳንዲጎ በቅርቡ የተመሰረተው የፃድቁ አቡነ ተክለሐይማኖት ቤ/ክ በኢትዩጰያው ሲኖዶስ ስር የተመሰረተ እንጂ ሌላ 3ኛ ወገን ሆኖ አይደለም እዚህ ላይ ለምን እንዳነሳህውም አልገባኝም መናፍቅነትን ከፃድቁ አቡነ ተክለሐይማኖት ቤ/ክን በህግና ስርዓት መመስርት ጋር ያገናኘከውም አልገባኝም። ያልተረዳከው ብዙ ነገር ግን እንዳለ ይታየኛል። ይህ ደግምሞ ቀርብቦ በመነጋገር እንጂ እንደዚህ አይነት አስተያየቶችን በመፃፍ ሊፈታ አይችልም ስለዚህ ሌላ 3ኛ አካል መሰረቱ ካልካቸው እህትና ወንድሞችህ ጋር ቀርቦ መነጋገር መፍትሄ ይመስለኛል። እ/ር ማስተዋልና ጥበቡን ለሁላችን ያድለን አሜን

   January 9, 2013 2:50 PM

   Delete
 10. ስለዚህ ዕርቁን በተመለከተ ምን መንገድ አለ?

  1. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ለቤተ ክርስቲያን ሳላም ብዕትውናን መርጠው ፣ የፖትርክናን ክብር ንቀው(ለበጎ) ቅዱሳንን ተከትለው ለበለጠ ክብር እራሳቸውን ማጨት
  2. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ለቤተ ክርስቲያን ሳላም ሲባል ከነሙሉ ክብራቸው ወደ መንበረ ፕትርክናው እንመልሳለ ብሎ መቀበል
  3. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትሪያሪክ አድርጎ ሀገሩን እና ሁኔታውን የሚያውቅ ሊቀ ጳጳስ እንደራሴ መሾም
  4. ከላይ የተዘረዘሩትን የሚቀበል ቢጠፋ እንኳን ምርጫውን ለእግዚአብሔር መስጠት፡፡ በሃይማኖት ለሚኖር ሰው ሁሉ ቀላል ነው፡፡ ዕርቀ ሰላሙን አድርጎ ፤ ውግዘቱን አንስቶ ሁሉም አባቶች ወደ ሃገር ተመልሰው፤ ሲባኤ ታውጆ አቡነ መርቆሪዎስ በመንበሩ ይቀመጡ ወይስ አዲስ ይመረጥ የሚለውን በዕጣ ለመንፈስ ቅዱስ ምርጫውን መስጠት ይቻላል፡፡ አሊያም እጩ ሆነው በምርጫ ከሚያልፉ ሶስት አዲስ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር አራተኛ የቅዱስነታቸው ስም አምስተኛ የእግዚአብሔር ስም ገብቶ እጣ ሊወጣ ይችላል፡፡ የእግዚአብሔር ስም ቢወጣ ሁሉንም ትቶ አዲስ ሦስት እጩዎች ለማግኘት እንደ አዲስ መስራት ይቻላል፡፡
  5. ሰላም ተገኝቶ ይህ ሁሉ ማድረግ ባይቻል እንኳን 4ተኛው ፖትሪያሪክ በህይወት እያሉ ሌላ ፓትሪያሪክ አለመሾም ለምን ቢሉ የተሻለ ሰላም የሚያመጣ ከሆነ በፓትሪያሪክ ከተመራንበት ጥቂት አሥርት ዓመታት ይልቅ በመንበረ ማርቆስ ሊቀ ጳጳሳት የተመራንበት ስለሚበዛ
  6. ሌሎችም

  ReplyDelete
 11. ዳኒ ጽሁፍ ለቤተክርስቲያንና በስርአት ለሚመራ ተቋም ጥሩ ምክር አይደለም:: ቤተ ክርስቲያን የራሷ የሆነ ሰዎች እንደፈለጉ ወይም ለራሳቸው በሚመቻቸው መንገድ ሊያሻሽሉት የማይችሉት ስርአት አላት:: ያም ስርአት በመጽሐፍ ቅዱስ ተመርኩዘው አባቶች የሰሩልን ስርአት ነው:: ያንን ስርአት ሊያሻሽል ወይም ሊያስተካክል የሚችለው ቅዱስ ሲኖዶስ ሁኡም አባላት (100%) ሲያምኑበት ብቻ ነው:: ስለዚህ ስለ ፓትርያርክም የራሷ ስርአት አላት:: ፓትርያርክ በህይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ መሾም እንደማይቻል የቤተክርስቲያን ስርአት ይናገራል:: አቡነ ጳውሎስ ሲሾሙ ስርአት አፍርሰው ነው የሾሟቸው:: አቡነ ጳውሎስ በህይወት እያሉ ሁለቱ ሲኖዶሶች ቢታረቁ ኖሮ በቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ፕትርክናው ለአባ መርቆሬዎስ ትጸና ነበር:: ስርአቱ እንዲህ ይላልና “ይህች ሹመት (ፓትርያርክነት) በአንድ ዘመን በአንድ ሀገር ለሁለት ሰዎች ልትሆን አይገባም። ይህ በአንድ ሀገር ከተደረገ ግን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና።”

  አሁን ደግሞ አቡነ ጳውሎስ በህይወት የሉም:: አንድ ፓትርያርክ ብቻ ነው ያለው:: ስለዚህ ምንም ክርክር አያስፈልገውም:: አንተ ያነሳው በዚህ ጉዳይ ምንም አይነት ሐሳቦች ሊፋጩ አይገባም ነበር:: የሐሳብ መፋጨት የሚያስፈልገው ስርአት ላልተሰራላቸውና ለአዳዲስ ነገሮች ነው:: አንተ ያነሳሃቸው ነገሮች አሉ ለምሳሌ እንዲህ ብለሃል:- ''ሌላው ቀርቶ ‹ፓትርያርክ ሊሆኑ ይፈልጋሉ› እየተባሉ የሚታሙት አባቶች እንኳን የሚወጣውን መመዘኛ እስካሟሉና ሥርዓቱን እስከጠበቁ ድረስ ፓትርያርክ ሊሆኑ መፈለጋቸው ነውሩ ምንድን ነው?'' መልሱ አጭር ነው:- ፓትርያርክ በህይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ ሊሾም ስለማይገባውና ያንን ስርአት ደግሞ እረኛ ተደርጎ የተሾመው ጳጳስ ከማናችንም በላይ ሊያስጠብቅ ስለሚገባው ለአንድ ጳጳስ እንኳን እራሱ ፓትርያርክ መሆንን መፈለግ ያንን ስርአት የሚያፈርሱትን ዝም ማለትም ትልቅ ጥፋት ነው::

  ሌላው ያነሳኸው እንዲህ ይላል:- ''በሌላም በኩል ደግሞ አሁን በቤተ ክርስቲያን በተፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ከኛ የተለየ ሐሳብ ሠንዝራችኋል እየተባሉ የሚወቀጡም አካላት አሉ፡፡''

  ዳኒ አንተ ትልቅ ሰው አይደለህ? ለምን ያልተባለ ትላለህ? ህዝበ ክርስቲያኑ እያለ ያለው ለምን ከኛ የተለየ ሐሳብ አነሳችሁ ሳይሆን ከቤተክርስቲያን ስርአት ውጪ የሆነ ሃሳብ ለምን ታናሳላችሁ? ነው እያለ ያለው ህዝቡ:: ከቤተክርስርቲያን ስርአት ውጪ ሐሳብ ከሚሰነዝሩት አንዱ አንተ ነህ:: ከVOA ጋር ያረከውን ቃለ መጠይቅ አድምጨልሃለሁ:: ለታሪክም ቀድቼ አስቀምጨዋለሁ:: ከአንድ የቤተክርስቲያን መምሀር ነኝ ከሚል ሰው የማይጠበቅ ነው የሰጠውኸው ቃለ ምልልስ:: አቡነ መርቆሬዎስ ከኢትዮጵያ ከወጡ በጣም ረጅም አመታት ቢቆጠሩም አንተ እንዳልከውም በጣም ብዙ የተለወጡ ነገሮች ቢኖሩም በፓትርያሪክነት ስልጣን ላይ ሆነው ህዝቡን ለማስተማር ለመገሰጽ ለመባረክ የሚያቅታቸው ነገር የለም:: ደግሞም የሚባርከው ጳጳሱ ሳይሆን እግዚአብሔር ነው:: ዘመን ስለተለወጠ ሳይሆን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት አያሰራቸውም ብትል ያስኬዳል:: ለዚያ ደግሞ መፍትሔው ለሁለተኛ ጊዜ ስርአት አፍርሶ ስድስተኛ ፓትርያርክ መሾም ሳይሆን የፓትርያርክነቱን ቦታ እሳቸው እንደያዙ ለአስተዳደር ስራው ቅዱስ ሲኖዶስ እንደራሴ እንዲሾም ማረግ ነው::

  በአጭር ቋንቋ ቤተክርስቲያን በቀደሙ ደጋግ አባቶቻችን የተሰራ ምንም እንከን የሌለው ስርአት አላትና ምንም የሐሳብ ፍጭት አያስፈልግም:: አንተም በድረ-ግጽህና በተለያዩ ሚዲያዎች እንዲህ ቢደረግ እንዲያ ቢደረግ አትበል:: የቤተክርስትያን ስርአት ይከበር በዛ መሰረት ሁሉም ነገር ይከናወን እያልክ ተናገር አብረንም ለቤተክርስቲያን ስርአት መከበር እንጩህ:: በስርአት የማንመራ ከሆነማ መናፍቃን መጽሐፍ ቅዱስን በሚመቻቸው መንገድ ከሚተረጉሙት በምን ተለየን? ቤተክርስቲያን ስርአት አላት:: የራሳችሁን ሃሳቦች አትሰንዝሩ የምትናገሩትን ሁሉ በቤተክርስቲያን ስርአት ላይ ብቻ ተመርኩዛችሁ ተናገሩ:: አሁን ያለው ስርአት ከዘመኑ ጋ አይሔድም ብላችሁ የምታስቡ ካላችሁ አባቶች ስርአቱን በቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይተውበት ይቀይሩት:: ዶግማ ያልሆኑትን ሁሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የመቀየር ስልጣን አለው:: ቅዱስ ሲኖዶስ ሲባል ግን ጥቂት ጳጳሳት እነሱ በሚያመቻቸው መልክ የሚያወሩት ሳይሆን ሁሉም አባቶች በጉባኤው ሲስማሙበት ብቻ ነው:: ያስተካከሉትንም ስርአት በየአጥቢያቸው በኩል ለህዝበ ክርስቲያኑ ማሳወቅ አለባቸው:: እርቀ ሰላሙን በተመለከተ ዲ/ን አባይነህ ካሴ ለVOA የሰጠውን ቃል ተመልከት:: ያ በጣም በቂ ነው:: እሱ የተናገረው ከቤተክርስቲያን ስር አትጋር ይጣጣማል:: ካላዳመጥከው እልክልሃለሁ ጠይቀኝ::

  Mekonnen

  ReplyDelete
  Replies
  1. Egziabhere abzito yebarkeh wondem Mekonnen! well said

   Delete
  2. Dear Mekonen

   I have nothing to say but thank you for your wonderful comment. Dani's view in this regard, I think, is wrong.

   Delete
 12. ዋናው ለራስ ለማመቻቸትና ሰው ምን ይለኛል በምለው ላይ ተከራክሮ ከመወሰን ለእግዚአብሔር ለመልካም ታሪክ የምበጀውን ለመወስን ወደ ሗላ ማለት አያስፈልግም።

  ReplyDelete
 13. Hi Daniel Kibret: I appreciate the whole idea of dialouge and consensus if and only if the play ground is safe and has equal access even for those Sinod members. We recall the recent barbaric action of the security forces in the holy church which had been sponsered by the late patriaric Abune paul. How could we trust that our holy fathers are free to conduct geniune and proactive debate ???
  I saw one of the comments about the establishment of San Diego St. Teklehaimanot church as a third option. In the first place, in a city of more than 20000 Ethiopians,the two churches, with a very small number of members, are far than enough. Therefore; Teklehaimanot as to me is not an option, a "third" option and hence not as such planting some thing new.It is not disturbing as establishing the same Church as St Gebriel, which was done years ago. If possible, we still need more and more churches so that we reach our needy citizens. In general, we are by far better off today to have st. Teklehaimanot and should try to build up on what had been done so far. more over I call upon all of you to follow how far the principles of our church are adhered to. with in the new St. Teklehaimanot. Let the spirit of the st. be with all of us.Thank you.
  T.S,.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Peace be with you, I think the question is not about additionalchurch,but the way they opened is not acceptable. It is not named under both Et or the Diaspora sinod, its un-unkown and its bisect the 2 sinod into 3. Its totally wrong, and the person ( Pop and Kesis Dejene is fully liable for such a new big mistake)

   Delete
 14. ዳኒ ጽሑፉ እጅግ በጣም አሪፍ ነው፣ ግን ያልበላኝን ስላከከልኝ ሊያረካኝ አልቻለም በተቃራኒ ያለቦታው እዬጻፍክ ህመሜን አበዛኸው እንጅ። አሁን ማን ይሙት የሰሞኑ ችግር፣ ጳጳሳቱን ዕርቅ የሚል አጀንዳ አሳጥፎ ምርጫ ምርጫ ያስባላቸው መሰረታዊ ምክንያት ጠፍቶህ ነው? ወንጌሉንና አንተ ከላይ የጻፍካቸውን ታሪኮች ከኛ እጅግ በተሻለ የሚያውቁት እኛንም አሁን ስለምንለምነው ዕርቅ ያስተማሩን አባቶች እንኮ ናቸው ባቋራጭ ስለምርጫ ህገ ደንብ፣ አስመራጭ ኮሚቴ ምናምን እያሉ ያሉት። ለምን ሶስት ቦታ የተከፈለችን ቤተክርስቲያን አንድ አድርገዋት ከዚያ በኋላ ተሰብስበው ከፈለጉ ምርጫ ካልሆነም ሌላ አማራጭ ተስማምተው አያደርጉትም? በመሰረቱ እንኮ ከዕርቅም በኋላ ፓትርያርክ የሚሆን መልዓክ ከሰማይ አይመጣም፤ በዚህም አለ በዚያ የኛን ደካማ ስጋ የለበሱ አሁን ያሉ አባቶች ናቸው የሚመረጡት። ችግር ያለው ፕሬዝዳንቱ እንደ አንድ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመን የጻፉትን ደብዳቤ ያሳጠፈ፣ አስታራቂውን ልዑክ ዲፖርት/deport/ ያደረግ እጀ ረጅሙ መንግስታችን ለቤተክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ነጻነት ሊሰጣት ባለመቻሉ ነው። /የኔ ሃሳብ ነው አለመስማማት ይቻላል/ይህን ደፍሮ የሚጽፍ ባለጊዜዎችንም በጥብዓት ተው የሚላቸው ጠፋ። እናም አምና ራሱን/አባ ጳውሎስን/ ይዘናል ብለው "አይረቡም" ያሏቸውን ጳጳሳት ዛሬ በደኅንነት ጋጋት ዳግም ያውም ታሪካዊ ስህተት ሊያሰሯቸው ሲያስጨንቋቸው የሃሳብ ልዩነት ነው ትለናለህ። አይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይይ

  ReplyDelete
  Replies
  1. በደሕንነት መጨናነቃቸውን በምን ዐወቅክ፡፡ አንዱ ብሎግ ያለውን ተቀብለህ፡፡ በውጭ ያሉ ሰዎች ችግራቸው ሁሉንም ነገር ከመንግሥት ጋር ማገናኘት ነው፡፡

   Delete
  2. Very right the government has to take its hand off our blessed church. haymanot kezerim, kehagerim, kerasim belay mehonun linasib yigebal.

   Delete
 15. Hello Dani: I saw your idea and it is ok. But are you still optimist that our holly fathers could debate openly with out any fear of harm, especially after the barbaric act that had happened in their shelter, which had been sponsered by the late Abune paulos???? I doubt and let's be realistic. Now they are in the process of assigning the sixth Patriaric and I am afraid of all the invisible hands.
  Regarding the St. Teklehaimanot church in San Diego, I have a different idea. It is not the "third option" as my dear mentioned above. As opposed to the previous replica of st Gebriel,this is "St Teklehaimanot" and given the number of Ethiopian christian communities, we may even demand more churches. In my opinion, we shall render support to the newly established church, help them in keeping the ortodox principles.
  Regards!!

  ReplyDelete
 16. It seems fair but we have to be critical as much as possible before making a judgement !!!

  ReplyDelete
 17. ለመሆኑ እነ ቅዱስ ጳዉሎስ እና ቅዱስ በርናበስ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እና ቅዱስ ኤጲፋንዮስ እንዲሁም አንተ ያነሳሃቸዉ ኢትዮጵያዉያን የሃሳባቸዉ የልዩነት መነሻ ምንድር ነበር ብሎ መጠየቅ አይገባምን? ከታሪኮቹስ የምንረዳዉ ለቤተክርስቲያንና ለክርስቲያኖች የበለጠ ተጠቃሚነት ነዉ ወይስ ከጀርባ የታዘለን ጸረ ቤተክርስቲያንና ክርስቲያን የሆነ አላማ ለማስፈጸም የሚለዉስ መታየት የለበትምን? ዛሬስ ለተከሰተዉ የሃሳብ ልዩነት መግፍኤ ሀሳቡ ምንድነዉ ብሎ መጠየቅ አይገባምን? ከእርቅ ይልቅ ምርጫን ያዉም ፈቃደ እግዚአብሔር እንኳ እንዳይፈጸም በሰዉ ልጅ ፍላጎት ብቻ በድምጽ ብልጫ እንዲቀድም እንዲፈጸም የሚፈልግ አካል ሃሳብ ፍጭት በምን መስፈርት ነዉ ለቤተክርስቲያንና ለክርስቲያኖች ጠቃሚ ዉጤት ሊያስገኝ የሚችለዉ? የዚህ ሀሳብ አራማጆች "…ወንጌል ያልገባቸዉ ዉሃ በግድግዳ ላይ መርጨት ብቻ የሚያዉቁ…" "… ሰዉ በዘፈንም ቢሆን ከተመለሰ ግድ የለኝም …" "…ቤተክርስቲያን ስድስት ቦታ ብተከፈልም አያገባኝም…" የሚሉ አይደሉምን? እዉን በዋናዉ ጉዳይ ላይ የነጠረ ማንነት ካልያዘ አካል ጋር ሚደረግ የሃሳብ ፍጭት የጉዳዩን ባለቤት የሚጠቅም ዉጤት ያመጣልን? ይህን ዳ/ን ዳንኤል ብቻ ታዉቃለህ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ቤተ ክርስቲያን ከስድስት ቦታ ብትከፈል ግድ የለኝም የሚል አባት የለም፡፡ ይህንንም ለማለታቸው ማስረጃ የለም፡፡ የሆነ የጠላቸው አካል አስወራው እኛም ተቀበልነው፡፡ አንተና እኔ ለቤተ ክርስቲያን የምናስበወቀውን ያሕል እነርሱ አያስቡም ብለሕ ታስባለህ፡፡ ለቤተ ክርስቲያን የሚያስበውኮ ብሎግ ያለውና ለብሎግ የሚዘግበው ብቻ አይደለም፡፡

   Delete
 18. እኔ በዚህ ሰሞን አስተያየት የምትሰጡ ሰዎች ትገርሙኛላችሁ፡፤ ዕርቅ ይቅደም ያለ ብቻ ነው እኔ ትክክል፡፡ ሌላ ሐሳብ ሊኖር አይችልም፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ‹ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተከፍላ አይደለም፡፡ የተወሰኑ አባቶች መንበራቸውን ትተው ሄደው ነው፡፡ በሉቃ 15 እንደተጻፈው ደግሞ የጠፋ ልጅ ወደ ቤቱ ይመለሳል እንጂ ዕርቅ አይፈጽምም፡፡ ስለዚህ ዕርቅ የሚባል ነገር የለም መመለስ ነው፡፡ ለመመለስ ደግሞ ጊዜ አያስፈልግም፡፡ ፓትርያርክ እያለም፣ ሳይኖርም መመለስ ይቻላል› ብሎ ማሰብ አይችልም፡፡ ዕርቁ የተከናወነው አቡነ ጳውሎስ እያሉ ቢሆን ኖሮ ለመሆኑ አሁን የምታስቡትን ሐሳብ ማሰብ ትችሉ ነበር፡፡ ወይስ ሁለት ፓትርያርክ ይኖረን ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእኔ ሐሳብ ወይም ሞት አትበሉ፡፡ ‹ይቅደም› ለደርግም አልበጀ፡፡

  ReplyDelete
 19. አንድ ሰው አሳቡን ራሱ ለመግለጥ ባልቻለበት ሁኔታ ሌሎች ስለ እርሱ ያሉትን ብቻ ተቀብሎ መፍረድ ክርስቲያናዊ ጠባይ አይደለም፡፡ አሁን ስማቸውን ስለምናጠፋቸው አባቶች አንዳንድ ብሎጎች ከሚሉት በቀር ሌላ ተጨባጭ ማስረጃ የለም፡፡ እነዚህ አካላት በጥላቻ ስማቸውን ያጥፉት ወይም አሳባቸው ከሃሳብ ስላልገጠመ ርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ ስለዚህ እባካችሁ አባቶችን የምትከፋፍሉና ስማቸውን የምታጠፉ አካላት ስለ ህሊናችሁ ስትሉ ተግ በሉ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Trying to protect Abune Abraham?

   Delete
 20. ዋናው ለራስ ለማመቻቸትና ሰው ምን ይለኛል በምለው ላይ ተከራክሮ ከመወሰን ለእግዚአብሔር ለመልካም ታሪክ የምበጀውን ለመወስን ወደ ሗላ ማለት አያስፈልግም።

  ReplyDelete
 21. Tikikl Blehal minew hulum wibsitoch endante betsfu. Ketlbet thank you very much

  ReplyDelete
 22. Thank you Dn Daniel

  ReplyDelete
 23. ለመሆኑ እነ ቅዱስ ጳዉሎስ እና ቅዱስ በርናበስ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እና ቅዱስ ኤጲፋንዮስ እንዲሁም አንተ ያነሳሃቸዉ ኢትዮጵያዉያን የሃሳባቸዉ የልዩነት መነሻ ምንድር ነበር ብሎ መጠየቅ አይገባምን? ከታሪኮቹስ የምንረዳዉ ለቤተክርስቲያንና ለክርስቲያኖች የበለጠ ተጠቃሚነት ነዉ ወይስ ከጀርባ የታዘለን ጸረ ቤተክርስቲያንና ክርስቲያን የሆነ አላማ ለማስፈጸም የሚለዉስ መታየት የለበትምን? ዛሬስ ለተከሰተዉ የሃሳብ ልዩነት መግፍኤ ሀሳቡ ምንድነዉ ብሎ መጠየቅ አይገባምን? ከእርቅ ይልቅ ምርጫን ያዉም ፈቃደ እግዚአብሔር እንኳ እንዳይፈጸም በሰዉ ልጅ ፍላጎት ብቻ በድምጽ ብልጫ እንዲቀድም እንዲፈጸም የሚፈልግ አካል ሃሳብ ፍጭት በምን መስፈርት ነዉ ለቤተክርስቲያንና ለክርስቲያኖች ጠቃሚ ዉጤት ሊያስገኝ የሚችለዉ? የዚህ ሀሳብ አራማጆች "…ወንጌል ያልገባቸዉ ዉሃ በግድግዳ ላይ መርጨት ብቻ የሚያዉቁ…" "… ሰዉ በዘፈንም ቢሆን ከተመለሰ ግድ የለኝም …" "…ቤተክርስቲያን ስድስት ቦታ ብተከፈልም አያገባኝም…" የሚሉ አይደሉምን? እዉን በዋናዉ ጉዳይ ላይ የነጠረ ማንነት ካልያዘ አካል ጋር ሚደረግ የሃሳብ ፍጭት የጉዳዩን ባለቤት የሚጠቅም ዉጤት ያመጣልን? ይህን ዳ/ን ዳንኤል ብቻ ታዉቃለህ፡፡

  ReplyDelete
 24. የሰጠሁት አስተያየት ስነ ምግባርን የተከተለ ጤናማ አስተያየት ነው ነግር ግን ለምን የኔን አስተያየት እንዳላወጣህው አልገባኝም። ስለሀሳብ ነጻነት ብዙ እየጻፍክና እየሰበክህ ተሰባኪዎችህን መልሰህ እራስህ የምታፍን መሆን የለብህም። ስለዚህ ማንም ምንም ይጻፍ ጽሁፉ ስነ ምግባር ያልጎደለው ጤናማ እስከሆነ ድረስ የማስተናገድ ሌሌላው ቢቀር የሞራል ግዴታ አለብህ። ስለዚህም አስተያየቴን እንደምታወጣው ተስፋ በማድረግ ከዚህ በታች በድጋሜ እንድጽፈው ተገድጃለሁ።
  ዲ/ን ዳንኤል ያሁኑ ጽሁፍህን ወቅታዊነትና መሠረታዊ ሀሳቡ በጣም ግራ የሚያጋባ ነው። ሲሆን እንደመመህረነትህ በዚህ ዕርቅ ላይ ትልቅ ሚና መጫወት ይገባህ ነበር። ዳሩ ግን ጽድቁን ትቶ በወጉ በኮነንኝ እንዲሉ የድርሻህ አስተዋጾ ማድረግ ቢቀር ለምን እንደዚህ ማንን የማይጠቅም አደፍራሽ መልዕክት ማሰተላለፍ እንደፈልለግ ውስጡ ለቄስ ብኛለሁ። ዝም ብላችሁ አባቶችን ስሙ ነው ያልከው? እውነት ብለሀል አባት ያልተሰማ ማን ሊሰማ ኖሯል! ነግር ግን ለቀባሪው አስረዱት እንዳይሆንብኝ እንጅ መጽሐፉም እኮ የሚለው የዋኖቻችሁን ፍሬ እየተመለከታችሁ ነው? ታዲያ በአሁኑ ሰዓት ከነሱ የምናየው ፍሬ ምንድን ነው? የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሚሠራበት ቦታ ሥጋዊ ሥራ ሰልጥኖ ይዘውን ገድል ሲገቡ ምንም ልትሉ መብት የላችሁም ልትለን በተለይ ካንተ አይጠበቅም።
  አንተ እራስህ አይደለህም እንዴ ከጥቂት ቀን በፊት ስለፓትርያርክ ምርጫ «ሲኖድስ ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም »በሚለው ድንቅ መጣጥፍህ «የሚከናወነው ተግባር የቤተ ክርስቲያን ተግባር ነው፡፡ የሃምሳ አራት ጳጳሳት ተግባር ብቻ አይደለም፡፡ የሚመረጠው አባት ከ45 ሚሊዮን በላይ የሆነውን ምእመን የሚመራ እንጂ ጥቂት የቤተ ክህነት አካላትን ብቻ የሚያስተዳደር አይደለም፡፡ በመሆኑም ምእመናኑ በግልጽ መሳተፍ፣ ድምፃቸውን መስማት፣ ሃሳባቸውን መቀበልና ተረድቶ ማስረዳት ይገባል»፡፡ ያልከን ታዲያ ዛሬ ምን ነካህ እንዲህ ያላግባብ ልትገስጸን የደፈርከው።
  በግልጽ የሚታየውን የመንግስት ተጽኖ ለመሸፋፈን መሞከርህ በእውነቱ በመላው ዓለም እንደሐዋርያት ዙሮ ያስተማረና ሰዎች የደረሱበትን ከተጽእኖ ነጻ የሆነ የኖሮ ደረጃ ያየ ሳይሆን ከሌላ ፕላኔት የመጣህ አስመስሎብሀል። መመህር ዳንኤል ህዝበ ክርስቲያኑ በጉጉት ነፍስና ስጋው እየተላቀቀ የሚጠብቀን ሰላም እርሱን ምኑን ጎዳው እንድል አድርጎኛል። በመጨረሻም ምናልባት እኛን ለማስተማርና እወቀት ለማስጨበጥ ደፋ ቀና ስትል ያንተን መንፈሳዊ ሕይወት ጎድተህው የመጣብህ ጾር እንዳይሆን አንተው እንዳስተማርከኝ እኔም አንተን ወደ በአትህ ተመልስ ብያለሁ።

  እግዚአብሔር አምላክ ለቅድስት ቤትክርስቲያንችን ሰላምና አንድነትን ያወርድልን!!!

  ReplyDelete
 25. D/Dani Wondimalem eniwodihalen Amlake kidusan yitebikih.

  ReplyDelete
 26. D/Dani enwedihalen.

  ReplyDelete
 27. ቃለ ሕይወት ያሰማለን፡፡ አንድ ተረት አስታወሰኝ አንድ ሶማሌ እና አማራ በጋራ ለመነገድ ተስማመትው ተለያዩ፡፡ ሶማሌው ወደ ቤተሰቡ ሲመለስ ንግዱን አማራው ሰው ጋር አንደሚሰራ ተለጠ፡፡ ቤተሰቡም ግን ብሎ ምን አለ ነበር ያሉት የዲ/ን ዳንኤልም ሃሳቡ እናንተ ግን ለእግዚአብሔር፣ ለሕግና ለኅሊናችሁ ታማኞች ሆነችሁ በጎ ነው ባላችሁት፣ ቤተ ክርስቲያንን ይጠቅማል ባላችሁት ሐሳብ ተከራከሩ፡፡ ይህ እነዲሆን ደግሞ የብዙሃኑ ሐሳብ ይመስለኛል በእኔ እንደተረዳሁት፡፡ አሁንም ቢሆን አባቶች ሆይ ለእግዚአብሔር፣ ለሕግና ለኅሊናችሁ ታማኞች ሆነችሁ በጎ ነው ባላችሁት፣ ቤተ ክርስቲያንን ይጠቅማል ባላችሁት ሐሳብ ተከራከሩ፡፡ ወሰኑ ነው ማለት የመፈልገው፡፡

  ReplyDelete
 28. Dn Dani first of all me and my wife highly appreciate your article. But dani who can understand you? Most of us are not open to positive dialog. we need to be listend but we don't want to listen others. Your thought and our level of thinking are very different. That is why everyboy is criticizing your idea.We can comment and criticize ideas but we can not condemn individuals as a christian because of their ideas. Please Dani do not stop writing the fact wheather we like it or not.Finally let me forward one thing from my reading.
  "Our response to any mistake affects the quality of the next moment."
  May God and The Holly Mother be with you and your family

  ReplyDelete
 29. I belive that is the only way for the final reconcilation. Gudayun lemimeleketachew abatoch metew. Ene yemaygebagne neger, ye-meemne dersha eskemin deres newe? andande ke-akemachen belay eyzelelin mehonachin leb linel yegebale. Edme andand letergemu blogs, abatochen mesadebena makalele endfasihon yeteyazebet gize, Egziabher hulachene yeker yebelen ! Hawareyat egn ena menfeskedus enewsenalen balubet hezib hulunem kalwesenku belo menterarate !

  ReplyDelete
 30. Dani,

  I think you sided on the wrong side on this matter. I don't really appreciate this article. I honestly denounce all popes who is thinking to be leaders before reconciliation. I feel like these popes don't care for the church other than their mean spirit.

  ReplyDelete
 31. ለመሆኑ አባ መርቆርዮስ ካናዳ ከገቡ ይሄው ስንት አመታቸው ነው መቸ ነው ሲባርኩ የታዩት ይሄ ሁሉ ምእመን አሜሪካ ካናዳ በፖሊስ ምእመን እየተጎተተ ሲወጣ ምን ብለው ያውቃሉ አንዳንዴ ከዘረኝነት እና ክፖለተካ የጸዳ አስተያየት ብንሰጥ መልካም ነው ቤተክርስትያን በጣም ተለውጠአል ቤተ ክህነት ተለውጦአል ኦሮሞ.ጉራጌ.ወላይታ.ምእመን ብቻ አይደለም ጳጳሳት አሉ እናንተ ከ ዘረኝነት ሳትውጡ በምን ሞራል ነው ወያኔ ዘረኛ ነው ብለን የምንናገረው ሲኖዶስ ብላችሁ የ አንድ ወንዝ ሰዎች አይደላችሁም ክማፍያ ስራ ባልተናንሰ መደራደርያ በጣም ታሳዝናላችሁ ዛሬም አታፍሩም አታናግሩን እንውቅችኋለን

  ReplyDelete
  Replies
  1. Asteway Libuna yistih. Yemitinagerew yetemitata newna.

   Delete
 32. ወገኖቼ ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት ብንፀልይ አይሻልም; ደግሞስ እኛ እውነት የቀደምት አባትቻችን ልጆች ምንባል ዓይነት ነን;
  ይህን ያህል አባቶች ላይ አፋችንን መክፈት እግራችንንስ ማንሳትስ ምን ይባላል; ድሮ ድሮማ አይደለም የጳጳሳትን ቡራኬ ለማግኘት ይቅርና የቄሶችን
  ጫማ ተሯርጠን እንስም ነበር ታዲያ አሁን ምን ተገኘ እና ነው አባቶችን መሳደቡ; ክብራቸውንስ እንዲህ መገዳደሩ; ምናልባት እኛ በአለም ጥሩ ስራ ጥሩ ገንዘብ ሊኖረን ይችል ይሆናል ተፅዕኖም መፍጠር እንችላለን ብለን እናስብም ይሆናል ግን አይደለም ቤተክርስቲያን የእግዚያብሄር ናት ሁሉም መወሰን ያለበት በእርሱ ነው፡፡ እስቲ እንደ ክርስቲያን በተሰበረ ልብ እናስብ ማንኛውንም አባት መሳደብ እናቁም የቅዱስ ሲኖዶሱንም ውሳኔ እናክብር ውሳኔው ምንም ይሁን ምን በፀጋ መቀበል አለብን የመንፈስ ቅዱስ ውሳኔ ነውና፡፡ መቼም አምላክ ያልፈቀደው ነገር እደማይሆን እናምናለንና፡፡እውነቴን ነው ለሁላችንም የተሰበረ ልቡናን ያድለን ያን አባቶቻችንን የምናከብርበትን ህሊና ይመልስልን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 33. ሰላም ወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ብዙ ሀሳቦችህን እና ትምህርቶችህን አደንቃለሁ ነገር ግን አሀገር ዉስጥና በዉጭ ሲኖዶሱ ያለህ አስተያየት በኔ እይታ በጣም የተዘበራረቀ ነዉ፡ እስኪ ህዝቡ እኮ የሚፈልገዉ አንድነቱን ነዉ፡ ሙስሊሞቹ እኮ አንድ አመት ሙሉ ከመንግስት ጋር የተፋጠጡት ለሀይማኖታቸዉ ሲሉ ነዉ፡ ታዲያ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ሰባኪወች ለእዉነት ለመቆም እና ህዝቡን ለማስተባበር ምንድን ነዉ የሚያስፈራችሁ? ለመጭዉ ትዉልድ ምን እናዉርሰዉ? ወደዉጭ የተሰደዱት በወቅቶ በነበሩት ታምራት ላይኔ ፊርማ ነዉ፡ እነሱም እኮ ቀኖና ፈረሰ ፡ የሀይማኖቱ ህግ ተጣሰ፡ ፓትርያሪክ በህይወት እያለ ሌላ አይሾምም የሚለዉ ተጥሶአል በማለት ነዉ። ከሁሉም በላይ ደግሞ መንግስትን መተቸት ሁሉም ስለፈራ ነዉ እንጅ ከመጀመሪያዉም እኮ ኢህአዴጎች በኦርቶዶክስ ሀይማኖት ላይ ያላቸዉን ጥላቻ በበረሃ ላይ እያሉ ነበር ሲፎክሩ የነበረዉ፡ ተሳክቶላቸዉም ስልጣን ሲይዙ ፓትርያሪኩን አሰድደዉ ለእነሱ የሚሆናቸዉን ሰዉ አስቀመጡ፡ በዚህም ምክንያት 21 አመት ሙሉ ቤተክርስትያን እና ልጆቹዋ እርስ በርስ እንደተለያዮ አሉ። አንተስ የቤተክርስትያን አንድነት አስጨንቆህ ይሆን?

  ReplyDelete
 34. Thank you Mr anonymous who shared us the following quote from his reading on january 5,2013 at 12:21Am (above)

  "Our response to any mistake affects the quality of the next moment."
  You are right

  ReplyDelete
 35. ሁሉም ፈላስፋ፤ አዋቂ፤ መፍትሄ ሰጪ ሆኖ፤ መደማመጥ ጠፍቷል፤ ሁሉም አዋቂ፤
  ተናጋሪ፤ ሆኖ የሚታገለዉ ግን ጥቂት ሆኗል - ወሬ ወሬ ወሬ -ሀሜት ሀሜት
  ሀሜት - ኩነና ኩነና ኩነና - ተናጋኔ ተናጋሪ ተናጋሪ - አድራጊ ጠፋ (የኢንተርኔት፡
  ፓልቶክና ሬድዮ፤ ስብሰባ ታጋዮች ሆnenal

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank You Mr anonymous, that's my idea too. I have a question to D.Daniel, bebete- kerstiyan hege ye-meemene dersha eskemen deres newe beleh tamenaleh, ketechale bezih erese sefa aderegeh betesefe betam newe yemamaesgieneh.Andande sewe bemayagebaw hulu tilek sil yetayalena. Lezih hulu kedami teteyaki hizbu selehone, benedut yemineda, sichoeh abro yemichoeh--

   Delete
 36. Amlak Yemibejewin Abat Ersu becherinetu yisten amen

  ReplyDelete
 37. Dn Daniel what happen to you?

  ReplyDelete
 38. ዲ/ን ዳንኤል ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚወስነውን ያለ ምንም ማንገራገር ተቀበሉ ብለሃል። ባሁኑ ወቅት እኮ ፪ ሲኖዶስ ነው ያለን ለአንዲቷ ቤተ ክርስቲያናችን። የትኛው ሲኖዶስ የሚለውን ነው ያለምንም ማንገራገር እንድንቀበል የምትፈልገው። አባቶቻችን የሆኑትን የሃገር ቤትም ሆነ የውጭ ሲኖዶስ አባላትን እናከብራቸዋልን። ሆኖም ግን ሰው ናቸውና ድክመት አይኖርባቸውም ማለት አይቻልም። የስልጣን ጥመኝነት፣ ዘረኝነት፣ ለመንግስት ማጎብደድ፣ የገንዘብ ፍቅርና የመሳሰሉት ሃጥያቶች እንደኛም ባይሆን በመጠኑ ይጠፋቸዋል ማለት ይከብዳል። የሃገር ቤቱ የሲኖዶስ አባላት በመጀመሪያ ደረጃ የሲኖዶስ አባል ሊሆኑ የቻሉበትን መስፈርት እና ከመንግስት ጣልቃ ገብነት የፀዳ መሆን አለመሆኑን በእርግጠኝነት ማወቅ ሳንችል እንዴት የሚሉንን ዝም ብለን እንቀበላለን። ከነዚህ መሃከልም አንዳንዶቹ እርቁ ላይ እንቅፋት በመሆን የመንግስትን አቋም እያንፀባረቁ እንዴት ዝም ብለን እንቀበላቸው። ምንጊዜም ለእርቅ ቅድሚያ እንድንሰጥ መፅሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል ቂም ይዞ ፀሎት እንዳይሆንብን። እግዚአብሔር ለሁላችንም ልቦና ስጥቶን ቀናውን መንገድ እንድንከተል ይርዳን።

  ReplyDelete
 39. DEAR DANI I DO NOT UNDERSTAND WHY DONT YOU FOCUS ON TEACHING US ABOUT THE BIBLE AS YOU DO IT GREATLY LEAVE THE POLITICS TO THE POLITITIANS

  ReplyDelete
 40. ተለያይታችሁ ተከራከሩ፤ አንድ ሁናችሁ ግን ወስኑ፡፡

  ReplyDelete
 41. YES D/n I fear about the feature Ethiopian generation

  ReplyDelete