Tuesday, January 29, 2013

ለኢትዮጵያውያን የፕሬስ ውጤቶች

ይህ የጡመራ መድረክ አገልግሎቱን ከጀመረ በቅርቡ ሦስተኛ ዓመቱን ያከብራል፡፡ በዚህ የሦስት ዓመት ጉዞ ውስጥ ከገጠሙት ችግሮች አንዱ የብሎጉ ጽሑፎች ባለቤትነታቸው እንደ ሥነ ቃል የሁሉም እየሆኑ መምጣታቸው ነው፡፡
በዚህ የጡመራ መድረክ የሚወጡት ጽሑፎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በሚታተሙ ልዩ ልዩ የፕሬስ ውጤቶች ላይ ይወጣሉ፡፡ አንዳንዶቹ አንድ ወይም ሁለት ጽሑፍ ለማውጣት አስፈቅደው በዚያው ማውጣት የቀጠሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹም ማንንም ሳያስፈቅዱና ሳያናግሩ በራሳቸው ሥልጣን የሚያወጡ ናቸው፡፡
ይህንን ሁኔታ ለተወሰኑ ዓመታት በዝምታ ያለፍኩበት ምክንያት ነበረኝ፡፡ የመጀመርያው እነዚህ ፕሬሶች እየቆዩና እየተደራጁ ሲሄዱ እነርሱ ራሳቸው ሥነ ምግባሩን ወደጠበቀ አሠራር ይገባሉ፡፡ ራሳቸው ከሂደት ይማራሉ በሚል ነበር፡፡ ሁለተኛው ደግሞ እየወደቀ እየተነሣ በሚሄደው የሀገሪቱ የግል ፕሬስ ላይ ጫና ላለማብዛትና ነገሩን በመነጋገር ብቻ ይፈታ ይሆናል በማለት ነበር፡፡ ላለፉት ሦስት ዓመታት በዚህ መንገድ ነበር የቀጠልነው፡፡
አሁን አሁን ግን አራት ችግሮች በመከሰት ላይ ናቸው፡፡ አንዳንድ የፕሬስ ውጤቶች ጽሑፉን ከየት እንዳገኙ ምንጭ ሳይጠቅሱ ልክ ለዚያ ፕሬስ እንደተጻፈ አድርገውና ዓምድ ሰጥተው በተከታታይ እያተሙ ይገኛሉ፡፡ ይህ ደግሞ እኔ ራሴ የትኛው ጽሑፌ በየትኛው ፕሬስ እንደታተመ ወደማላውቅበት ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል፡፡ በሁሉም የፕሬስ ውጤቶች ላይ ገንዘብ ተከፍሎኝ እየሠራሁ የሚመስላቸውን ሰዎችንም አበራክቷቸዋል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የትኛው ጽሑፌ በየትኛው ጋዜጣና መጽሔት (ከአዲስ ጉዳይ በቀር) እንደወጣ የማውቀው እንደሌላው አንባቢ ከታተመ በኋላ ነው፡፡

ሁለተኛው ችግር ደግሞ የኔ ያልሆነውን ጽሑፍ በእኔ ፎቶና ስም የሚያትሙ ጋዜጦችና መጽሔቶችም እየመጡ ነው፡፡ ይህ በዚሁ እንዲቀጥል ከተደረገ ደግሞ ሃይማኖትን፣ ሥነ ምግባርንና ሕግን የሚጥሱ ጽሑፎችንም በስሜ ሊወጡበት የሚችሉበትን ዕድል ይከፍታል፡፡ አንድ እግረኛ ያበላሸውን ደግሞ ሃምሳ ፈረሰኛ አይመልሰውም፡፡ ሦስተኛው ደግሞ በብሎጉ ላይ የወጡትን ጽሑፎች አሳጥረው፣ አሻሽለው፣ ቀይረውና አዘባርቀው የሚያትሙ ፕሬሶችም እየመጡ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ አንድን ጽሑፍ ሁለትና ሦስት ዓይነት ቅጅ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡
አራተኛው ችግር ደግሞ ከዚህ ብሎግ የተገለበጡ ጽሑፎችን የራሳቸውን ስምና ፎቶ ለጥፈው በስርቆት የሚያትሙ፤ ምንጭም ሳይጠቅሱ ስምም ሳይጠቅሱ በጋዜጣቸውና በመጽሔታቸው የሚያወጡ፤ ከሌሎች ሰዎች ጽሑፍ ጋር አዳብለው የሚያወጡ ፕሬሶችም አሉ፡፡  
እንደ እውነቱ ከሆነ በሀገሪቱ ሕግ የተቋቋመ ፕሬስ ሕጉን የማክበር ግዴታ ብቻ ሳይሆን ለሰዎች መብቶችም የመቆም ግዴታም አለበት፡፡ ራሱ መብት የሚጥስ ፕሬስ ግን ለሌሎች መብቶች ጠበቃ ለመሆን አይችልም፡፡ በአንድ ሰው ስምና ፎቶ ለመጠቀም፣ የአንድን ሰው የጥበብ ሥራዎችንም ለማተም የባለቤቱ ፈቃድ መገኘት አለበት፡፡ ከዚህ ውጭ የሚሠሩ ነገሮች ዶክተር ላጲሶ እንዳሉት በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባሕል ነውር፣ በሕግም ወንጀል ይሆናሉ፡፡
ስለሆነም ከዚህ ብሎግ ጽሑፎችን እየወሰዳችሁ የምታትሙ የፕሬስ ውጤቶች ከእኔ በጽሑፍ ፈቃድ ካላገኛችሁ በቀር እንዳታትሙ አሳስባችኋለሁ፡፡
የዚህን ብሎግ ጽሑፎችን የምታነብቡ አንባቢዎችም እኔ በቋሚነት የምጽፈው አስቀድሞ በአዲስ ነገር ጋዜጣ በኋላም በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ብቻ መሆኑን እንድታውቁ፡፡ ከዚህ ውጭ የሚታተሙት ጽሑፎች ሁሉ ከዚህ ብሎግ እየተገለበጡ እንጂ ለመጽሔቶቹ ወይም ለጋዜጦቹ እየተጻፉ አለመሆኑን እንድትገነዘቡ አሳስባለሁ፡፡
እንደእኔ እምነት እነዚህ ችግሮች በመነጋገርና በመግባባት ይፈታሉ ብዬ አምናለሁ፡፡ ከዚህ ወደባሰ ነገርም እንገባለን ብዬ አላምን፡፡ ነገር ግን መግባባቱና መተራራሙ ብሎም ጨዋነት በተሞላበት የፕሬስ ሥነ ምግባር ችግሩን መፍታት ካልተቻለ የመጨረሻው አማራጭ ወደ ሕግ አደባባይ መጓዝ ሊሆን ነው፡፡ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እዚያ አንደርስም፡፡

33 comments:

 1. Dear Dn. Dani i am very worried about this kind of plagiarism , which is believed to be the worst sin in the the history of literature and academic and i strongly condemn this act and please keep teaching them those who stole someone's work ......


  GOD BLESS ETHIOPIA AND ETHIOPIAN!!!

  ReplyDelete
 2. እውነት ነው ወንደማችን ዳንኤል ኣንተ ተጨንቀህና ተጠበህ በሰራሀው ስራ ላይ ማንም ስልጣን የለውም ይህ በ እግዚኣብሔርም በሰውም በህግ ያስጠይቃል:: እያወቁ ማጥፋት ይሉሃል የሄ ነው እንግዲ:: ለመሆኑ ፈጠራ ኣልቆባቸውነው? ፈጠራ ያልቃል እንዴ? ግን ለመሆኑ ዳኒ በ ሬዲዮ የሚነበቡትን ይጨምር ይሆን እንዴ? ብቻ መፍጠር እንኳን ባንችን ተጨንቀው እየፈጠሩ የሚጽፉትን ኣናዳክማቸው ኢትዮጲያችን በእነርሱ የብዕር ቀለም ወዝ ነው ደምቃ እየታየች እየወጣች ያለቸው ነገሮችን በጥልቀት ስለሚመለከቱ:: እግዚኣብሔር ጸጋውን ያብዛልህ ወንደሜ::

  ReplyDelete
 3. Hi Dani,

  How much yourself is sure that your writings are purely your clean work? I have a lot of doubt on that.

  ReplyDelete
  Replies
  1. well said Dear Anonymous KalHiwot yasemalin , Leba Leban Leba sil ayigermim?
   Nice view and I hope Dani anbessaw will agree on that too .
   What do u think Dn. Danisha , Lebisha, Kadresha, Tijisha, Qoshasha!!!!!!

   Delete
  2. Sira fet neh, hulum endante yimeslehal liju sirawun yisrabet

   Delete
  3. If you have evidence do not hesitate to write. But do not depict your feeling like this, which may show your jealous on him.

   Delete
  4. To anonymous January 29,
   What you write is very funny. But in the eye of literature it is very kiddish /'Chewa, Tseyaph, Tserfet'/. But I do not think even you know the words in bracket. Do not drive your self on blind jealousy path /if it is from your heart, I hope it is for fun/.

   Delete
  5. @ AnonymousJanuary 29, 2013 at 6:37 PM እንዴት ነዉ ባክህ የምትናገረዉ ማሰብ ከሚችል ሰዉ የማይጠበቅ አነጋገር፡ ብልግናነዉ የሰዉን ልጅ ክብር የሚያዋርዱ ቃላትን መጠቀም፤ለነገሩ ሰይጣነዊ ቅናት ነዉ እንደዚህ የሚያረጋችሁ፡፡ ወንድም ዲን. ዳንኤል እግዚያብሄር ፀጋ በረከት ያብዛልህ፡፡ በሰዉ ስራ ለመክበር ለምትፈልጉት ልቦና ይስጣችሁ፡፡

   Delete
  6. Doubting his writings might not be bad and its strongly advisable if we challenge the writer with rational and logical evidences. As of me I don't think he did plagiarism because most of his writings are based on national current affairs and nobody had been claim that Dani took his/her idea. His critics over Pro.Mesfin book might be an example for supporting ma idea.

   Delete
  7. ምነው? የምትሰርቀው ከሆነ አስፈቅድ።

   Delete
  8. @AnonymousJanuary 29, 2013 at 6:37 PM
   kelebochu wanegnaw ante satihon atikerim. Minew betam tenadedik? All his woks are scholarly. He uses standard sitations. If you have an evidence, let's see it. Then only I will appreciate you. But avoid uncivillized insuts and act at least as a normal human.

   Delete
 4. i appreciate your patiency keep it up its better if you solve it with discussion

  ReplyDelete
 5. Hey Dani Selam New
  I share your idea too, those personalities who publish your writing as of them are really plagiarizing your intellectual property, so take action they are getting service with out either paying you or acknowledging .
  But i appreciate your patience and method of teaching them.

  ReplyDelete
 6. The most worrying of all i think is printing faking as u wrote it.....dangerous dani....this is where u must be firm. The rest i was considering it as ur thoughts r being availed to those who don access internet but share magazine. anyway ur stand is worth supporting so all readers will be aware i guess.

  ReplyDelete
 7. lemiserana lemiTir sew fetenaw kebadna kebad new silezih.....

  ReplyDelete
 8. min yadrgu bileh new Dani ewket kelele keyet amtitew yitsafut bileh new
  bizu gize mebtachin tedefere bilew yemichohu sewoch[like extremist muslism] yemejemerya defariwoch honew yigegnalu migermew medferachew bicha aydelem MEBTACHIN new yiluhal.
  igziabher yirdah min yibalal kenesu ga fird bet le fird bet mengatetu rasu mekera new

  ReplyDelete
 9. ከዚህ ውጭ የሚሠሩ ነገሮች በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባሕል ነውር፣ በሕግም ወንጀል ይሆናሉ፡፡ good expression!!!

  ReplyDelete
 10. Hi Dani,
  I stand with you on this one. The irony is I have asked you to give us the source you have been using on your blog many times. Nevertheless, you remained deaf ear for so long time. I asked you because I know the owners of some of the articles you post them-that pissed me off a lot. Now when others did it the same ways you have been doing, you are getting mad. Not surprises at all!
  I hate plagiarism no matter who did it. I strongly oppose and condemn it!!!!
  Please Dani, you come clean first and you have moral obligation to accuse others!!!

  Who knows after accusing others the court finds out it is not yours because you all are copyiny, altering,and puplishing as if you are originators of the document.

  Gebre Ke Etissa T/Haymanot

  ReplyDelete
 11. ዳንኤል፣ እውነት ብለሀል፤ ሃላፊነት እንዲሰማን ብ…ዙ… መድከም ይጠበቅብናል፡፡ ምንጭ መጥቀስ፣ ሃሳብን ሳያዛቡ ማቅረብ እና መልካም ፍቃድን የመጠየቅ ልምዳችን እጅግ ዘቅጧል፤ምንጭ ለመጥቀስ የሰው ጓዳ እየበረበርን፣ “ሼክስፒር እንዲህ አለ” ለማለት በምንተጋበት አገር ፣ እንደዚህ አይነት የጸሐፊ መብት ረገጣ መፈጸሙ በሃፍረት ሊያስጎነብሰን ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 12. Dear Daniel:

  This is a crime that is being committed to you and to your person. This is intolerable. You need to take action. Somebody above said your articles are copied from others as well. But does he have any evidence? I dislike people who write without evidence.

  Thank you

  Good luck

  ReplyDelete
 13. ከዚህ ሁሉ እግዛ ብጠሔር ይርዳህ ።ድርጌቱ ግን አሳፉሪ ነው።

  ReplyDelete
 14. Dani,

  Those people know we(you) don't take legal action. Right!

  Protestant Churches has been stealing our church intellectual and spiritual assets (properties). Especially "full gospel church" has been blackmailing and stealing our church for long time including fake "abuna yared". I think no one take them to the court for that mischief.

  Now, they are stealing our yardawui zema, kebero, senasil, mequamia... I know that they have doing this for long time. Please watch this YouTube video https://www.youtube.com/watch?v=PVSnyahUD9U. Are we just keep watching their damage? The catholic church has a Legal Office that protect the intellectual property right of the church they do it to preserve the integrity of church message. What about us? The church enemies steal everything we have but we keep argue in church in what issues...

  ReplyDelete
 15. ዳኒ ፀጋ ይብዛልህ፡፡
  ምን አለ የምትፅፉ ሰውች እራሳችሁን ብትሆኑ እና ብትፅፉ መልካም ነው፡፡ ያንድ ሰው ያፃፃፍ ዘየ ወይንም ቃና ያስታውቃል ስለዚህ ጥሩ የሆነ ፅሁፍ ይዛቹ ቅረቡ ተከታይ ማፍራት ትችላላቹ የራሳቹ የሆነ እስከ ሆነ ድረስ ደግሞ ልተበልጡም ትችላላቹ ፕሬሱንም ወደ ኃላ አትጎትቱት&ጊዜያዊ የሆነ ጥቅም አይታያቹ ለትውልድ የሚተላለፍ መልካም ስራ ይኑራቹ፤የፃፊውን ሞራን ጠብቁ፡፡ ልጁ ሲሰረቅበት ያማይጮኸ ማን አለ? በአቋራጭ መበልጸግ በፕሬስ ይቅር፡፡

  ReplyDelete
 16. dani: tarikin,haymanotawi gudayin, aznagn tsihufochin,limidoch ena mikirichin, sainsawi hidetochin... wzt... be yekifilachew beye woru bemiwota mesthihet sayhon bemestihaf bitazegaj ena leanbabi bitakerib melkam neger yimeslegnal. mingizem bihon leba kemesirek aykotebim... enesum woi yiketilalu.... enayachewalen. bilog lay yemitwotaw keza behuala bihon

  ReplyDelete
 17. Dn Daniel....plagarism shall not be tolerated at any rate...yeketefa sera yelemedu leboch....take them to court.

  ReplyDelete
 18. Interesting, I really appreciate your patience; I hope they will come with the fact mean stop plagiarism.

  ReplyDelete
 19. - you didn't mention one thing, is their any thing we can help you to stop this type of violence? Mamush, MN

  ReplyDelete
 20. ከዚህ ውጭ የሚሠሩ ነገሮች ዶክተር ላጲሶ እንዳሉት በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባሕል ነውር፣ በሕግም ወንጀል ይሆናሉ፡፡ thank you

  ReplyDelete
 21. Tikkikil neh d.daniel alziyama 'yeberewn misgana wesedew feresun' mehonu new!

  ReplyDelete
 22. dani minalbat 3 amt mexbekih higawi yehonu mesiluachewu lihon yichilal kezi behulla yant tsihuf yemanim metsihetina gazexa madaberiya endihon batfeqid xiru newu zare tsihuf yeserqu nege blogu yegna newu lemalet birtat yagegnaluna.

  ReplyDelete
 23. ዶክተር ላጲሶ እንዳሉት በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባሕል ነውር፣ በሕግም ወንጀል ይሆናሉ፡፡

  ReplyDelete
 24. Mint bke zeeinesaeke emkaleke

  ReplyDelete
 25. መልካም ብለሀል ዳኒ : እያደገ ያለዉ የብሎግ ጽሑፍ እንድለመልሙ ማድረግ ብያቅተን እንዲቀጭጩ ማድረግ የለብንም እላለሁ::
  እነደታዘብኩት አንድ አንዶች የሀሳብ ልዩነትን የመግለጽ ደካማ አቅማችሁ ለስድብ እየዳረጋችሁ ይመስለኛል::
  በብዙ ሕዝብ በሚነበብ ሳይት ላይ አጸያፈ ቃላት አታስቀምጡ::
  በተጨማሪም እንደነዚህ አይነት አጸያፈ ቃላት ፓስት ባይደረግም የተቃዉሞ አስተያየት ማስቀረት አይመስለኝም::
  እግዚአብሔር ይረዳን::

  ReplyDelete