በዘመናዊው የስፖርት ታሪካችን ውስጥ
በእግር ኳስ ዓለም እንደ ትናንቱ አንገታችንን ቀና አድርገን በኩራት የሄድን አይመስለኝም፡፡ ለካስ እንችላለን፤ ለካስ ከሠራን
የማንሆነው የለም፣ ለካስ ጥረት ካለ ለእኛ ያልተፈቀደ ነገር የለም፤ ለካስ ትብብር ካለ እንዳንወጣው የተከለከለ ተራራ፣
እንዳንሻገረም የታጠረ ገደል የለም፤ ለካስ ‹እችላለሁ› ብሎ ማሰብ ከተቻለ የማይቻል ነገር የለም፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ብራዚል
ስትጫወት፣ እንደ ጣልያን ስትከላከል፣ እንደ ስፔን ስታጠቃ ከማየት በላይ ምን መታደል አለ፡፡ ልጆቹ ከባርሴሎና ማሠልጠኛ የወጡ
ናቸው እንዴ? የአፍሪካ ዋንጫ የተጀመረው ዛሬ ነው እንዴ? እያሉ እነ ቢቢሲና ሲኤንኤን፣ አልጄዚራና ሱፐር ስፖርት ውዳሴ ሲያዘንቡ
መስማት መታደል ነው፡፡
ምርጥ ደራሲ ደርሶት፣ ምርጥ ዳይሬክተር
አዘጋጅቶት፣ ምርጥ ተዋንያን እንደተወኑት ምርጥ ድራማ፤ የተጠና፣ የተቀናበረ፣ ምት ያለው፣ የተሠናሰለ፣ ምርጥ ጨዋታ ነበር
ልጆቻችን ያሳዩን፡፡ በዚህኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመርያውን ቀይ ካርድ አይተን፣ በዐሥር ተጨዋች ተጫውተን፣ አስቀድሞ ግብ ገብቶብን
በሙሉ መተማመንና፣ በኢትዮጵያዊ ወኔ መጨዋት፣ መረበሽን ተቋቁሞ ከመከላከል ወደ ማጥቃት መዞር፣ በራስ የግብ ክልል እንኳን
ተረጋግቶ ኳስ መቀባበል፣ ይህ ነው መጀመርያ የተሸነፈው ቡድን፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሀገሩ ወጥቶ
ሲጫወት ብዙዎቻችን የምንፈራው ብዙ ግብ አስተናግዶ እንዳይመጣ ነበር፡፡ ሽንፈቱ ቀለል ያለና አጥንት የሚሰብር እንዳይሆን
ነበር፡፡ ዛሬ ይህ አስተሳሰብ ተሸንፏል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ መጀመርያ ያሸነፈው ዛምቢያን አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያንን ነው፡፡
‹ድብልቅልቃቸው ወጥቶ፣ ደርዘን ግብ አስተናግደው፣ የሌሎች የነጥብ መሰብሰቢያ ሆነው፣ አንገታችንን አስደፍተው ይመጣሉ፤ እኛ
ሩጫ እንጂ እግር ኳስ አይሆነንም፤ እንዲያውም ሳናልፍ በቀረብን› የሚሉ የሀገር ቤት ቡድኖችን ነው ያሸነፉት፡፡ ሳላህዲን
በዛምቢያ ላይ የተሰጠውን ፍጹም ቅጣት ምት ስቶታል፡፡ በደካማ አስተሳሰቦች ላይ፣ አይሆንም፣ አይሳካም፣ አይቻልም፣ የትም
አንደርስም በሚሉ ቀድመው የሚሸነፉ ስሜቶች ላይ የመታውን ፍጹም ቅጣት ምት ግን በሚገባ አስቆጥሮታል፡፡
በጨዋታው አጋማሽና በጨዋታው መጨረሻ በዲኤስ
ቲቪ ሱፐር ስፖርት ጨዋታውን ይተነትኑ የነበሩት ባለሞያዎች በኢትዮጵያውያኑ አጨዋወት፣ በራስ መተማመን፣ መናበብ፣ ታክቲክና
ጥንካሬ ላይ አስደናቂ የሆኑ አስተያየቶችን ሲሰጡ ነበር፡፡ ያውም ከብራዚል ጋር እያነጣጠሩ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ይተላለፉ ከነበሩ
የሬዲዮ ፕሮግራሞች በአንዱ የተገኙ አንድ የእግር ኳስ አሠልጣኝም ‹የእኔም ሥጋት ዛሬ ተቀርፏል›› ብለው ነበር የተናገሩት፡፡
ከዚህ በላይ ምን ድል አለ?
አስቀድሞ ሳላህዲን ሰኢዲ ፍጹም ቅጣት ምት
ሲስት፣ በኋላም ኢትዮጵያዊው ግብ ጠባቂ በቀይ ሲወጣ የተከፈተው የተስፋ መስኮት ገርበብ ያለ መስሎ ነበር፡፡ በወቅቱ በፌስ ቡክ
አስተያየታቸውን ይሰጡ የነበሩ ኢትዮጵያውያንም ‹‹አይይይ›› ‹‹ኡፍፍፍ›› ‹‹ውይይይ›› የሚሉ የንዴት፣ የተስፋ መቁረጥና
የቁጭት ድምጾችን ያሰሙ ነበር፡፡ ልጆቹ ግን የነበረውን እንዳልነበረ፣ የተደረገውን እንዳልተደረገ ቆጥረው ግብ እንዳገባ ተጨዋች
ነበር የሚጫወቱት፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ያስመዘገበው አዲስ ድል ይህ ነው፡፡ ዳኛው በግብ ጠባቂው ላይ ቀይ ካርድ ቢመዙም፣
ተጨዋቾቹ ግን በመደናገጥና በመረበሽ፣ ተስፋ በመቁረጥና ከንግዲህ አለቀልን በሚለው ስሜት ላይ፣ ከፊሽካ በፊት በመሸነፍና
ከፍጻሜው በፊት በመጨረስ ድክመት ላይ ነበር ቀይ ካርዳቸውን የመዘዙት፡፡
እውነታቸውን ነው ዓለም እንደሆነ ምንጊዜም
አትሞላም፡፡ ‹‹ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ›› የሚሆነው ለማስታወቂያ ብቻ ነው፡፡ የዚህ ዓለም ጉዞ ሲሞላ ሲጎድል ነው፡፡ ታድያ ለምን
ያለንን እንጂ የጎደለንን እናስባለን፡፡ ዓይን ላይኖረን ይችላል፤ ግን አእምሮ አለን፤ እጅ ላይኖረን ይችላል፤ ግን ዓይን
አለን፤ ሥራ ላይኖረን ይችላል፤ መሥራት የሚችል ሙሉ ጤና ግን አለን፤ እናት ላይኖረን ይችላል፤ ከእናት የሚመረጥ አባት ግን
አለን፤ አባት ላይኖረን ይችላል፤ እንደ አባት የሚከባከቡ ብዙ አጎቶች ግን አሉን፤ ውጤት ማምጣት ያለብን ስንሟላ ብቻ ነው
እንዴ?
የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ‹ጎደሎ
እንደሆንን አናስብ፡፡ በቤታችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በቢሯችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በትዳራችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡
በንግዳችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በሀገራችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በትምህርታችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በጤናችን ያልተሟላ
ነገር አለ፡፡ በአካላችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በፍላጎታችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ ግን ለምን ጉድለታችንን ብቻ
እናስበዋለን፡፡ ለምንስ መጉደላችንን ብቻ እየሰብን እንብሰከሰካለን፡፡ ለምንስ የወደፊቱን ላለፈው ነገር ስንል እንሠዋለን፡፡
ለምንስ ነገን በትናንት ምክንያት እናበላሸዋለን፡፡
ተጨዋቾቹ ምንድን ነው ያደረጉት? አንድ
ተጨዋች ጎድሎብናል፡፡ አዎ፡፡ ልንተካው እንችላለንን? አንችልም፡፡ ታድያ ምን እናድርግ? ጎደሎውን በሌላ ነገር እናሟላው፤
በምን? ባለን ነገር ጎደሎውን እንሙላ፡፡ ምን አለን? ተናብቦ፣ ተገናዝቦ፣ ተሳስቦና ተረባርቦ የመጨዋት ችሎታ አለን፡፡ ሀገራዊ
ወኔና፣ ኢትዮጵያዊ የማሸነፍ መንፈስ አለን፤ ስለዚህም ይህ ችሎታችን አሥራ አንደኛ ተጨዋች ሆኖ ይጫወታል፡፡ የጎደለን ነገር
የለም፡፡ እኛ ሙሉ ነን፡፡ ጎደሎ አይደለንም፡፡ ይህ ነበር ውሳኔው፡፡ ይህ ነበር መርሑ፡፡
ጎደሎውን ባልጎደለው ነገር መሙላት
እንጂ ጎደሎውን እኝኝ እያሉ ማሰብ ጉድለትን አያስቀረውም፡፡
የአንዳንዱ ጉድለት የሚታይ ነው፡፡ የሌላው ጉድለት ግን የማይታይ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሙሉ ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን
አንድ ተጨዋች ቢጎድለውም የዛምቢያ ቡድን ደግሞ ብዙ ነገር ይጎድለው ነበር፡፡ በአንድ ተጨዋች የማይሟላ ብዙ ጉድለት
ነበረበት፡፡ እንዲያውም ትናንት ፍጹም ቅጣት ምቱ ባይሳት ኖሮ የዛምቢያ ቡድን ተሸናፊ ነበር፡፡ ለምን? ቢባል ከአንድ ተጨዋች
የሚበልጥ ብዙ ጉድለት ነበረበት፡፡ የእነርሱ ጉድለት እንደኛ ስላልታየ፤ ስላልተቆጠረና በዳኛ ውሳኔ የተፈጸመ ስላልሆነ ነበር
ልዩነቱ፡፡
በትናንትናው ጨዋታ ሦስት ነጥብ ያመጣንበት ትልቅ ድል ቢኖር ‹‹ጎደሎ ነን ብሎ በማሰብና በመጨነቅ›› ላይ የተቆጠረው ሦስት ነጥብ ነው፡፡ እንደዚያ የምንወዳቸውና የምንንሰፈሰፍላቸው ወላጆቻችን እንኳን ስንት ጉድለት አለባቸው፡፡ እንዲያ ነፍሳችንን የምንሰጥላቸው የአብራካችን ክፋይ፣ የማኅፀናችን ፍሬ የሆኑ ልጆቻችን እንኳን ስንት ጉድለት አለባቸው፡፡ እኛ ራሳችን ስንት ፈልገን ያላገኘነው፤ ጥረን ያልደረስንበት፣ አስበን ያልሆንነው፤ ታግለን ያልጨበጥነው ስንት ጉድለት አለብን፡፡ ግን ጎደሎነታችንን አናስብ፡፡ ያጣነውን ትተን ያገኘነውን እናስብ፤ የሌለንን ትተን ባለን እንጠቀም፤ ያልሆንነውን ትተን በሆንነው እንሥራበት፤ ያልደረስንበትን ትተን በደረስንበት እናፍራበት፡፡ የማይጎድል የለምና፡፡ የዚህ ዓለም ጉዞ አንዱን ጎደሎ እየሞሉ ሌላ ጎደሎ መፍጠር ነው፡፡
ደረጃችን የሚመጥን ጨዋታ ተጫውታችኋል፡፡
አንገታችን ቀና አድርገን እንድንሄድ አድርጋችኋል፡፡ ብዙ ነጥብ አስቆጥራችኋል፡፡ ስለ እናንተ በኩራት እንዲወራ አድርጋችኋል፡፡
ሌሎች ቡድኖች በአውሮፓ ታላላቅ ቡድኖች የሚጫወቱ ተጨዋቾች ይዘዋል፤ እናንተ የላችሁም፡፡ ግን ጎደሎአችሁን አታስቡ፡፡ ሌሎች
ቡድኖች ብዙ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፈዋል፤ እናንተ ከሠላሳ ዓመት በኋላ መጥታችኋል፤ ይህንን እንደ ጉድለት አታስቡት፤ ስለ
ሌሎቹ ብዙ ይነገር ይሆናል፤ ይህንን እንደ ጉድለት አታስቡ፡፡ ሌሎች የሌላቸው፣ እናንተ ብቻ ያላችሁ ብዙ ነገር አለና ያንን
አስቡት፡፡ ለጎደላችሁ ሳይሆን ላላችሁ ነገር ቦታ ስጡት፡፡ ደግሞም ይህ የአድዋ ጦርነት አይደለም፡፡ እግር ኳስ መሆኑንም
አትርሱት፡፡ አንችልም፣ አይታሰብም የሚለውን ቡድን አሸንፋችሁ ‹‹የይቻላል ዋንጫ›› ካመጣችሁ እኛ በኩራት ጉሮ ወሸባዬ እያልን
እንቀበላችኋለን፡፡ ‹ካፍ› ያልሰጣችሁን ዋንጫም እንሰጣችኋለን፡፡
መልካም ዕድል፡፡
ውስጤን የማላውቀው ስሜት እየወረረኝ ጽሁፉን አነበብኩት ምን ይሆን?
ReplyDeleteየሐገር ፍቅር ይሉት ነገር ስለሆነ እንኳን ደስ ያለን፡፡
Deletemelkam yehone betam yemimarke tsufe new may God bless you
ReplyDeletethank you.... yes we can.... we can open our eyes and see what we can... the team performance is for all Ethiopians to open our eyes to make everything happen for good cause...
ReplyDeleteGood observation!!Thank you Sir!!
ReplyDeleteDani.talaqyehaymanot fiqir bicha sayhon yehager fiqirim tatkehal lekka?
ReplyDeleteመልካም ጽሑፍ፡፡ በደስታ ላጦዙን ወንድሞቻችን እግዜአብሔር አምላክ ፍጻሜውን ያሳምርላቸው፡፡ ድንግል ትርዳቸው፡፡ አሜን፡፡
ReplyDeletedani, 10q. you could express our feeling as ur thought and Ethiopian thought. yes, it seemed difficult, however, all thing would be possible. long live for our country and also our national team.
ReplyDeleteአንበሳ ናቸው
ReplyDeleteበቅድሚያ ብሄራዊ ቡድናችን 1-1 መውጣቱ ጥሩ ነው፡፡ምክንያቱም ከዚህ ውጪ ብንሸንፍም የሞራል ውድቀቱና ህመሙ ከባድ ይሆን ነበር በተቃራኒው ደግሞ ብናሸንፍም ጉራውና ደስታው በዚህም የተነሳ መዘናጋቱ ለዘለቄታው ጥሩ አይሆንም ነበር፡፡ስለዚህም እኩል ለእኩል መውጣታችን ብድናችንን በትክክል ያለበትን ደረጃ እንድንመዝነው የሚያደርግ ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ እግር ኳስ እድልም ጭምር ስለሆነ ምን እንደሚፈጠር አስቀድሞ ለመገመት በጣም ይከብዳል፡፡
ReplyDeleteወንድም ዳንኤል ፅሁፍህ ጥሩ ይዘት ያለው ነው፡፡ነገር ግን ስለ ብሄራዊ ቡድናችን አጠቃላይ ምንነት ትክክለኛና ተገቢ የሆነ ምዘናና አስተያየት ለመስጠት ግን ጊዜው ገና ነው፡፡ስለ እግር ኳስ ምንነት በቂ ግንዛቤ የሌለን እንዳንሆንም ያስፋራል፡፡ስሜታችንና አመለካከታችን እንደ ፔንዱለም ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላኛው አንዱ ጫፍ በከፍተኛ ፍጥነትና እርቀት የሚወዛወዝ ይመስላል፡፡ስለመሸነፍም ሆነ ስለማሸነፍ በውስጣችን የሚፈጠረው ስሜት የሚመነጨው ቅድሚያ በዚህ አይነት ውድድር ላይ ስለመሸነፍም ሆነ ስለማሸነፍ ካለን የቅድሚያ አመለካከት (Perception) የመነጨ ነው፡፡ስለዚህም ስለመሸነፍም ሆነ ስለማሸነፍ ጤናማ የሆነ አመለካከትና ስሜት ቢኖረን ጥሩ ነው፡፡ጠንካራ የሚባል ቡድን በአንድ ደካማ ቡድን ሊሸነፍ ይችላል፡፡እግር ኳስን ይበልጥ አጓጊ የሚያደርገውም ይህ ተፈጥሮው ነው፡፡ስለዚህም ውድድሩን የሞት የሽረት ጉዳይ እያደረግንና በሚፈጠረው ነገርም ሌላም አይነት ተገቢ ያልሆነ የተለየ የተለጠጠ ትርጓሜ እየሰጠን ማየት ጤናማ አይመስለኝም፡፡ብሄራዊ ቡድኑ በራሱ ከዛምቢያ ጋር እያደረገ በነበረው የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ላይ ከፍተኛ የሆነ የስሜት መረበሽ ይታይበት ነበር፡፡
በሰከነ መንገድ እያሰቡ መረጋጋትና ከሁካታ መራቅ ለቡድኑ ጥሩ ውጤት ማምጣት ወሳኝነት ያለው ይመስለኛል፡፡የሚገጥሙትን ማንኛውንም ቡድን መመዘን የሚገባው ሜዳው ላይ ባለችው ዘጠና ደቂቃ ውስጥ ነው መሆን ያለበት፡፡ሃያል ቡድን ነው ስለተባለ ከልክ በላይ አግዝፈው ማየት እንደዚሁም በተቃራኒው ደካማ ነው ስለተባለም ከልክ በላይ አቅልሎ ማየት ለሽንፈት ይዳርጋል፡፡በዘጠና ደቂቃው ውስጥ እያንዳንዱን አጋጣሚና እድል እንዳያመልጥ በብልሃት መጠቀም ለሚገኘው ድል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ምክንያቱም የእያንዳንዱ ውድድር ውጤቱ የሚመዘነው በዚያው በዘጠና ደቂቃው ውስጥ ባለው እንጂ ከዚያ በፈት ወይንም ከዚያ በኋላ በሚሆነው ነገር አይደለም፡፡ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፋችን እጅግ ደስ የሚል ነገር ነው ነገር ግን ከመስመር የወጣና ያልተመጣጠነ ጤነኛ ስሜትና አመለካከት ካለን ግን በቃ ዋናውን ውድድሩን እዚሁ የጨረስነው ያህል እንደተሰማን ያህል ማለት ነውና በማለፋችን ብቻ ሌላ ውድድር እንደሌለብን አድርገን ነው የሚሰማን ማለት ነው፡፡በዚህ አይነት ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፋችን የሚሰጠውም የተለያየ የተደበላለቀ ስሜት ውዥንብርና አመለካከትም በራሱ በዘለቄታ ላለው ለእግር ኳሳችን እድገት ፀር ነው፡፡አሁን በሄራዊ ብድናችንም ያለበት አጠቃላይ አቋም የተደበላለቀ ስሜት(Inferiority complex as well as superiority Complex) ውስጥ እንዳይሆን መጠንቀቅ ጥሩ ነው፡፡ማን እንደሚያሸንፍ አስቀድሞ የሚታወቅ ነገር ቢኖርማ ኖሮ ለምንስ አስቀድሞ ውድድሩ ያካሄዳል፡፡ዋናው ቁምነገር በዋናነት በዘጠና ደቂቃ ውስጥ ያለው ነገር ላይ ማተኮር ብቻ ነው፡፡ስለ ገንዘብ ሽልማትና ዋንጫ ስለመውሰድ ተገቢ ያልሆነ ውዥንብር ውስጥ መግባት ላልተጠበቀ ውድቀት ይዳርጋል፡፡ቡድኑ ስለ ውጤት ሳይሆን መጨነቅ ያለበት በዘጠና ደቂቃ ውስጥ ማድረግ ያለበትን ነገር ስለማድረግ በማሰብ የሚችለውን ነገር ሁሉ በልበ ሙሉነት ማከናወን ብቻ ነው፡፡ስለውጤት ከልክ በላይ እየተጨነቁ ውጤት ለማምጣት ይከብዳል፡፡ውጤት የሚመጣው ከሚሰራው ነገር መንጭቶ ነውና ስራው ላይ ማተኮር ነው ዋናው፡፡ሌላው አንድ መረዳት ያለብን ነገር ለምሳሌ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በዚህ ውድድር ዋንጫ ወሰደ እንበል፡፡ነገር ግን ይህ ማለት የኢትዮጵያ ኳስ አደገ ማለት ግን አይደለም፡፡ምን ሁኔታ ላይ እንዳለን በቅጡ የምናውቀው ነገር ነውና፡፡እራሳችንን መመዘን ያለብን በጥቂት ውድድሮችና ውጤቶች ሳይሆን የብዙ አመታትን አጠቃላይ ጉዞ በመመዘን ነው መሆን ያለበት፡፡የአፍሪካን ዋንጫ አንድ ወቅት የወሰድን ሀገር ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አለፍን ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ካልን ይህ እራሱ ዳንኤል አንድ ወቅት ላይ እንዳለው የታሪክ ምፀት ነው የሚሆነው፡፡በእርግጥም በቀይ ካርድ ከወጣ ተጨዋች በላይ እንደ ኢትዮጵያዊ የጎደለን ነገርም እኛነታችንን የምናይበትና የምንመዝንበት በተቃርኖ የተሞላና ያልተመጣጠነ ውዥንብር የበዛበትና ግራ የተጋባ እይታችን ነው፡፡ትንሽ ነገር ስናገኝም ሆነ ትንሽ ነገር ስናጣ ያዙኝ ልቀቁኝ የምንል መሆን የለብንም፡፡በህይወታችን ውስጥ ሰላም ያለው ዘላቂ እውነተኛ ስኬትና ደስታም ያለው ነገሮችን እንዳመጣጡ በፀጋ ለመቀበል ካለን ዝግጁነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ከአጠቃላይ ሁኔታው እንደምረዳው ከሆነ ሽንፈትን በፀጋ ተቀብለን ለማስተናገድም ብቻ ሳይሆን ዝግጁነት የጎደለን በተቃራኒው ያለውንም የአሸናፊነት ድልንም ቢሆን ተቀብለን በተገቢው ጤናማ ስሜትና አመለካከት ለማስተናገድ ይህንንም ድል ለወደፊቱ እንደ ጥሩ ስንቅ ለመያዝ ዝግጁነት ያለን አልመሰለኝም፡፡If we are not ready and sober to entertain failure then we are not also ready and sober to entertain success as well. I think this is the deepest sense of our self that is some how wallowing out of some sort of confusion and instability.ስለዚህም እያንዳንዱ ክስተት ትክክለኛ የአንደምታ ትርጓሜ ስለሚያስፈልገው ዳንኤልም ስለ ብሄራዊ ቡድናችንና ስለተገኘው ውጤትም ትክክለኛውን ትርጓሜ ብትሰጠው ጥሩ ይመስለኛል፡፡የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል እንዳይሆንብን ስለ ብሄራዊ ቡድናችንና ኳሳችን ትክክለኛ ምዘና ለመስጠት ቢያንስ ቢያንስ የመጀመሪያውን ዙር ውድድሮች እንኳን እንያቸው፡፡መልካም እድል ለብሄራዊ ቡድናችን፡፡
፡የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል እንዳይሆንብን ስለ ብሄራዊ ቡድናችንና ኳሳችን ትክክለኛ ምዘና ለመስጠት ቢያንስ ቢያንስ የመጀመሪያውን ዙር ውድድሮች እንኳን እንያቸው፡፡
Deleteእኔ በበኩሌ የተፃፈው ወይም ዳንኤል የፃፈው ስለብሄራዊ ቡድናችን ብቻ ሳይሆን ስለ እያንዳንዱ ጉዳያችን ማለትም ስለማንነታችን ስለማህበራዊ ስለኢትዩጺያችን ስላለብን አጠቃላይ ችግሮች ነው ምናልባት ስታነብ እያንዳንዱን ፅሁፍ በጥንቃቄ ማንበብ ያስፈልጋል አለበለዚያ ቀጥታ መተርጎም ብቻ ብዙ ችግሮች ይፈጥራል
okay i like your idea, which says "Let's not celebrate early", and in Daniel's defense we need to hope for better and be positive about the future also, but in a limited way.
DeleteStop whining and enjoy the moment buddy.
Deleteየጅብ ችኩል እዚህ ላይ የሚያገለግል ኣይመስለኝም። የዳኒኤል እይታ ከዛ አንፃር አይደለም። በዛ ጨዋታ ላይ እንችላለን የሚለው አስተሳሰብ መፈጠሩ ስላስደሰተው ነው። እነም በዛ ደስተግኛ ነኝ። ከአሁን በኃላ ብንሸነፍም እይከፋኝም። በቃ መቻላቸዉን አሳይተዋል!!!
Deletebetam des yelale koran
ReplyDeletethank you our brother. i always appreciate your way of writing ...as u said our player removed our long time frustration ...may GOD with them.....
ReplyDeleteግሩም እይታ ነው በእውነት፡፡ጀግንነቱ ይቀጥላል ቡርኪና ፋሶ እና ናይጄሪያ ይጨነቁ እኛ እንችላለን!!!
ReplyDeleteEnamesegnalen Dany, teru adrgeh geltsehewal, lagerachin Melkam Edil Enemegnalen.
ReplyDeleteThank u Memeher !!! All the best for the next game also!!!
ReplyDeleteበጣም ጥሩ መስታዎት ነው የሆነልኝ ቃለ ህይወት ያሰማልኝ!!!
ReplyDeleteለእኔ በትክክል በኢትዮጵያ የእግር ኳስ አብዮት ፈንድቷል፤በትክክል አትዮጵያችን በእግር ኳስ አንድነትንና ልዩ ህብረትን ለዓለም አሳይታለች፤በእውነት ስለ እውነት-እኛው ራሳችን እኛን ያሸኘፍንበት እና ለተቀረውም ዓለም በህብረታችን ውስጥ ልዕልናችንን ያሳየንበት ትለቁ አደባባይ ሆኗል፡፡ አይደለም በአሥራ አንድ በአሥር ተጫውቶ ማሸነፍ እንደተቻለ የመንፈስ አንድነታችን ዐቢይ ምሥክራችን ሆኗልና እንኳን ደስ አለን!!
ReplyDeleteThanks Dani, but" askedmo mamesgen lehamet yichegral" endayhonibn. Any ways thanks God
ReplyDeleteለእኔ የትናንቱ በቂዬ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ የሚመጣውን ሁሉ በደስታ መቀበል ነው፡፡ ያልሠራንበትን እኛም ብዙ መጠበቅ የለብንም፡፡
DeleteThanks Dani for your response. You are right. Like this response, why don't you publish the questions that we asked you at d.t time about church & any kind of confusions in christian life. Personally I asked you two times in face book & e_mail,but no response. I think you know four books of Pop shinoda III that says "so many years with problems of people". We Ethiopians expect from you to collect questions raised while you preach, in e_mail,facebook, post etc. As to me no one is better than you to do this.
DeleteAny ways think on it.And congra for you openned a book store. Now a days it is becoming difficult to get your books in any store.
I'm so impressed.Thank you Daniel. It's not about football.It's a wide scope of view.
DeleteBless you!
lek new yetenantu beki new i'm not worry about tomorrow .
Deleteበጣም ደስ ብሎናል እይታህ ያምራል::
ReplyDeleteDo you know why people see their weakest side and feel they can not succeed ? It is because of us (the rest people) and the society who tell them that they lack something. We categorize people based on their age, sex, educational status, physical appearance, experience etc (social, economic, physical, behavior traits) and attach their level of success accordingly. Specially, we, Ethiopians are very fast in identifying people weaknesses and continuously remind them the same. Egzer yiqir yibelen!
ReplyDeleteThank you Dany you are our hero too
ReplyDeleteGod bless you !!!
ኡኡኡኡኡኡፍፍፍፍፍፍፍ ዳኒ ጭንቅላቴን ያነበብከው መሰለኝ
ReplyDeleteGreat article !
ReplyDeleteሌሎች የሌላቸው፣ እናንተ ብቻ ያላችሁ ብዙ ነገር አለና ያንን አስቡት፡፡ ለጎደላችሁ ሳይሆን ላላችሁ ነገር ቦታ ስጡት፡፡ Egziabher Yibarkih
ReplyDeleteዳንኤል ያንተ ጽሁፍም ሶስት ነጥብ ይገባዋል::
ReplyDeletekezih befit metsaf yeneberebh neger alneberem?
ReplyDeleteslebetekrstian neger! ahun sport gemerk? semonegna tifozo felagi neh.
I hate your kind of christian. we are not "Gedamawian" just to talk only about church. we live in this world. Really I love Daniel b/c he showed us how to live in this world by following christ. What is the matter talking about football? Is it a sin? Previously I consider my self as a non christian b/c I watch football, I read other books... But now I learn from Daniel that it is not a sin.
DeleteDaniye betam new emiwodih.
I have not seen you responding to comments immediately before as I remember. Keep responding like this when important question being asked. Keep it up, keep going... Thanks for your good will work! God bless !!!
ReplyDeletethank you Deakon Daniel for this wonderful reflection.
ReplyDeleteዳኒ በቅድሚያ በሸገር ስፖርት ቀርበህ ሃገር የሚለውን የተነተንክበት ቃል በእጅጉ አስደስቶኛል ፣ ምንም እኩለ ለሊት ቢሆንም የብሄራዊ ቡድን ውጤቱን ተክትሎ ካለቀ ቡሃላ ሳላውቀው እንባየ ይወርድ ነበር አንዳንዴ በጎደሎ ከአምናው ሻምፒዮና ጋር ነጥብ ተጋርቶ መውጣት በጣም ትልቅ ነው፥. ይህ ማለት ከ፪፯ አመት ቡሓላ በአፍሪካ መድረክ ጎል አስቆጠርን ፪፩ አመት ቡሃላ ተሳትፎአችን በ ጎደሎ መጫወታችን ይህ ሁሉ ተደምሮ ደስታችንን እጥፍ ድርብ አድርጎታል ነገ ሌላ ውጤት ቢመጣ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ በተረፈ ነገ ውጤቱ ቢከፋ ተናግረን ነበር ለማለት ነው « አንተን ከመላው ቤተሰብህ እግዚአብሂር ይባርካችሁ።
ReplyDeleteGena zare tiru ''Optimistic Article'' Tetsafe bante! Try to be Optimistic like today.but I dislike all other articles written by This man!Go team Ethiopia!
ReplyDeleteWhere was your mind before!!!
Deletekal hiwoten yasmalen dani...
ReplyDeleteKal hiwoten yasamalen
ReplyDeleteabo tebarek. amazing understanding and explanation ...
ReplyDeletegin betam des yemilew aselitangu Ethiopiawi mehonu new. enam yihe chaweta bizu timihirtna melikt alew lechigrochachin hulu mefitihew engaw gar endale tekumonal
ReplyDeleteahunm goodluck mirt opinion.
ReplyDeleteወንድሜ ዳንኤል ግሩም የሆነ አመለካከት ነው ያንጸባረከው። ልጆቻችን ከዛምቢያ ጋር አቻ ቢለያዩም እንዳልከው በእርግጥ እኔን አሸንፈውኛል፤ ሦስት ነጥብም ሰጥቻቸዋለሁ። በጣም እንሸነፋለን በዬ ከመስጋቴ የተነሳ ጨዋታውን ላለማየት እንኳን ቃጥቶኝ ነበር። በስተኋላ ላይ ግን ያስተዋልኩት እና ከአውሮፓውያኑ የስፖርት ጋዜጠኞች የሰማሁትን(በቀጥታ ስርጭቱ ላይ)ማመን ተስኖኝ ስደመም ነው ውዬ ያደርኩት። እግዚአብሔር ይመስገን፤ አሜን ያዝልቅልን።
ReplyDeleteወንድሜ ዳንኤል
ReplyDeleteእንኩዋን አብሮ ደስ አለን:: ሃገራችን ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ከመሰረቱት ሃገሮች ቀዳሚዋና ዋነኛዋ ሆና እያለ ለሠላሳ አንድ ዓመታት ያህል ከዉደድሩ እርቃ የበይ ተመልካች መሆናችን ሲያስቆጨን እና ሲያሳዝነን ነበር::
እነሆ ዛሬ ሃያ ዘጠነኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ሃገራችንን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድ እና የምስራቅ አፍሪካን ወክለን የመጀመሪያዉን ጨዋታ ከአምናው ባለድል ዛምቢያ ጋር አድርግን በጨዋታ ብልጫ ጭምር አቻ ወጥተናል::
በእኔ ግምት ጨዋታዉን አሸንፈናል:: መቸም ጀግና የሚወለደው ጦርሜዳ እንደመሆኑ መጠን ተርብ የሆኑት ተጫዋቾቻችን አስቀድሞ ጎል ተቆጥሮባቸውም ጭምር አንበገርም: አንሽነፍም: ኢትዮጵያዊ እኮ ነን ብለው በአስር ተጫዋቾች ብቻ ከሃገራቸው ዉጪ ተጋጣሚያቸዉን አርበድብደው በአቻ ዉጤት መለያየታቸው ከድልም ድል ነው::
ከብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች መሃል ምንያህል ተሾመን ሱዳንን አሸነፈን ገና ለዋንጫ ውድድሩ እንደአለፍን አግኝቸው ስናወጋ አሁን በአለን ስብስብ እና የተጨዋቾች ሁኔታ ከማንም ቡድን ጋር ገጥመን አንሸነፍም ብሎኝ ነበር:: ለእኔ የሁለታችን ወግ ብሄራዊ ቡድናችን የመንፈስ ዝግጅቱ ከፍተኛ እንደሆነ አሳይቶኛል:: በዚህ መነሾ ከዛምቢያ ጋር የተደረገው ጨዋታ በሃገርም ሆነ እሰው ሃገር ያሉ ኢትዮጵያን ሁሉ አንገታቸዉን ቀና እንዲያደርጉ አስችሏል:: ብሔራዊ ቡድናችን ሲጫወት በሃገራችን ባንዲራ ያሸበረቁ ኢትዮጵያዉያን ደጋፊዎች ቡድኑን ሲደግፉ የነበረው ሁኔታ ልብ ይነካ ነበር:: በዚሁ ሁኔታም እስከመጨረሻው ድረስ ይዘልቃሉ ብዬም አምናለሁ::
እንደ እኔ አተያይ ይህ ዘመን የኢትዮጵያዉያን መልካም ዘመን ነው ብዬ አምናለሁ:: የማይደፈሩ የሚመስሉ እንደ አባይ ግድብ የመሰሉ ነገሮችን ደፍረን እየሰራን በመሆኑ እኛ ኢትዮጵያዉያን ሙሉ መሆናችን እያሳየን ነው::
ቀሪዎቹ ጨዋታዎች በመልካም ዉጤት እና በድል እንዲጠናቀቁ እየተመኘሁ:: ሁላችንም በአለንበት ሥፍራ ሆነን የአገር ገፅታ ግንባታ ላይ እንድናተኩር እጠይቃለሁ:: እግዚአብሔር አባታችን ኢትዮጵያን ይባርክ::
ቸር እንሰንበት
አንበሳ ናቸው, Betam betam yatadasatkubte kene yimachachew.
Deleteለምንስ ነገን በትናንት ምክንያት እናበላሸዋለን፡፡
ReplyDeletekoy nege wanchawin binwesdew destacinin endet linigeltsew new?...gena kegimiru destachin yeteganene aymesilihim ?
ReplyDeleted.t
Andnet min yahil wesagn endehone abronet yet endemiaderese kebiherawi budnachin meredat yasefelgal egna ketebaberen yetenayet medres enechilalen ebakachihu bandnet enezemer 1 kal yinuren 1 enehun yalem wanchan bicha saihon yalem ekonominim mekotater enechilalen! Kalebelezia endih keteleyayen hulunem neger enatalen?
ReplyDeletewow wow wow this is rely nice view !!! Dani I appreciate u always !! keep it uppppppppppppppppppppp
ReplyDeleteዳኒ ብቻፈጣሪ ይርዳቸው በጣም ደስ ይሚል ምልከታ ነዉ ገና ከዚህ በላይ እንጓዛለን ያለንን በአግባቡ ከተጠቀምን
ReplyDeleteAmen Melkam edil Yihunilin
ReplyDeleteGreat observation Dani
ReplyDeleteWhy don't you write on sport newspapers? What is the role of foot ball for the people who lives in extreme poverty? For that matter, they are playing for 2 million birr. It is good to do one thing for identity case and with full sense of nationalism. Then, we always become winners!Those of you who will be offended by my comment, please forgive me.
ReplyDeleteI will not forgive you!
Deleteopen our eyes to make everything happen for good cause..
ReplyDeleteእንደ ኢትዮጵያዊ የጎደለን ነገርም እኛነታችንን የምናይበትና የምንመዝንበት በተቃርኖ የተሞላና ያልተመጣጠነ ውዥንብር የበዛበትና ግራ የተጋባ እይታችን ነው፡፡ትንሽ ነገር ስናገኝም ሆነ ትንሽ ነገር ስናጣ ያዙኝ ልቀቁኝ የምንል መሆን የለብንም፡
ReplyDeleteInstead of telling your difficult problems to God, tell to your problems that God is almighty.
ReplyDeleteI like it really!!!!!!!!!!!!!!!!
Deleteእውነት ነው ያለንን ነገር ማሰብ ነው የሚበልጠው።
ReplyDeleteአባቶቻችንስ የአድዋን ጦርነት ባላቸው ነገር እና በእግዚአብሔር ረዳትነት አልነበር ድል ያደረጉት የጎደላቸውን ቢያዩ ኖሮ የማይሆን ነበር ምክንያቱም ጣሊያኖቹ ይዘውት የነበረው መሳሪያ ኢትዮጵያ ከያዘችው በፍፁም አይመጣጠንም ነበርና። ዳኒ እግዚአብሔር ይባርክህ! አስታዋሽና መካሪ ወንድም አያሳጣን።
"ያለንን እንጂ የሚጎድለንን አናስብ"
Thanks dani this is what they deserve. what ever the result is we have to be together and appreciate each other to get good result in anything in our life. Appreciation is back bone of our strength.
ReplyDeleteድንግል ማርያም ትርዳቸው !
ReplyDeleteAwosem!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteኢትዮጵያዊነታችን በትክክል እየተነሳ ነው፡፡
ReplyDeleteገና በአንድነታችን በፍቅራችን በጀግንነታችን እንደ ከዚህ በፊቱ ታሪካችን አሁንም ለዓለም እናሳያልን፡፡
በጨዋታው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተደስቻለው፡፡ ነገር ግን ከጨዋታው በስተጀርባ የተንጸባረቀው የፖለቲካ ጨዋታ፣ የዘረኝነትና ጎጠኝነት ትርኢት ትኩረትን የሚስብ ነበር፡፡ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ስንት ሰንደቅ ዓላማ ነው ያላት? አንዳንዶች የኢትዮጵያን ብሄራዊ መዝሙር ላለመስማት ጆሯቸውን ሲደፍኑ ማየት ያሳዝናል፡፡ አዳነ ግርማ ያስቆጠረው ጎል የኢትዮጵያ ሳይሆን የደቡብ ነው ብለው ሲሟገቱ ማየት ያሳፍራል፡፡ ከደቡብም ወደሲዳማ፣ ከሲዳማ ወደ ………… እያለ ጎጠኝነቱ ይቀጥላል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም አዳነ ጎል እንዲያስቆጥር ያደረገው አዲስ ህንጻ በመሆኑ ጎሉ የአዳነ ሳይሆን የአዲስ ህንጻ ነው ብለው ሲከራከሩ መስማት ይዘገንናል፡፡ ለነገሩ የዚህ ሁሉ ውጤት የኢሕአዴግ የከፋፍለህ ግዛ መርህ ነው፡፡ በመጠኑም ቢሆን እየተሳካለቸው ነው፡፡ የገብያ ግርግር ለወንበዴ ይመቻል እንዲሉ፡፡ ስለአንድነት ሲወራ እንደእሬት የሚመራቸውና የሚያንገፈግፋቸው!!!! ጣት ቆሰለ ተብሎ ተቆርጦ አይጣልም እንደሚባለው አንዱ አንዱን እንዲጠብቅ የማይታይ መንፈስ አስተሳስሮናል፡፡
ReplyDeleteNormally it is natural to focus on locality. But not to this extent. We should give priority to being Ethiopia specially at this time. Hawassa always get mad when Adane scored. This is expected, since he grow here. But that doesn't mean that he is ethnically totally sidama or Debub.shame on such kind of persons.
DeleteThank you Lord for letting us see our unity and our beauty.
DeleteForgot bad side views as they will lead us no where.
I, the younger one, know we're all Ethiopian.
Even though American's recruit sport players from every state(some states as same size as Ethiopia),they say America scored. It doesn't mean the place where the individual player came from is neglecting, but there is time and place assigned for it.
Melkam edil budinachin endigtmewu emegnalehu.
Yekedmo siriat nafaki atihun. Lijiet temeliso ayimetam. Wedefit bicha!
Deleteenamesegnalen !!!
ReplyDeletenice
ReplyDeleteGreat performance. I know our boys will keep making us proud. Just the draw is a win for us. You have already won for me, now continue showing us nice game.
ReplyDeleteCheers
Guys this is not about Ethiopian team!This is about all Ethiopian mentality,about our daily life/life style This is about YOU AND ME.I dont know about you but I AM INSPIRED ...Powerful message."All HABESHA MUST READ IT" God bless you Daniel!
ReplyDeleteThank You Dani. This is a nice article that tell us what should we do in our life. We should develop such type of attitude in every walk of life if we want to see a better Ethiopia in the future. Yes it seems a lot of things are going wrong but nothing is impossible. We have to say "Yes we can do!".
ReplyDeleteYour view is so good, a lesson should be taken from this view by our political leaders who blame the previous regime or other political rivals .This should be a lesson to some political leaders and their followers who did believe that Ethiopia has no hope without port and blame the current regime for this.What did happen is already passed,but the future is in our hand.There are many countries which has no any natural resources on which they depend on,but they are numbered as one of the most developed countries.For example Germany has no much natural resource other than coal.But they have the best human capital in the world.After all it isn't the resource that makes us prosperous ,it is the human capital which change this resource to real wealth.The human capital we should have is a capital who believes that the problem and the solution is with in us.If we live in the past ,blame others and project all the mistakes on others, the future will be like the past.If our leaders lack something , let us try to find a solution together. If not together ,let us try to be part of the solution.
ReplyDeleteDid the economy of Germany Germany destroyed in the second world war? yes,but did they blame each other for their current problems? No, they would rather put themselves as part of the problem and part of the solution.So they decided to work for their country 8hours for free for 2 years.Soon the manufacturing sector started to boom and the faced electric power problem.And they made themselves part of the problem and part of the solution.They didn't blame the gov't for establishing many factories beyond the power grid can handle.But many of them put a solar panel over their roof and feed the power grid and they started to get some money.By doing so they became part of the solution.To criticize is good ,if it is followed by solution and implementation of the solution.Let us leave the past for the historians and living in the present ,let us struggle for the future.
Dani God bless you,I saw the 2nd half of the game, and i never realized that they were 10, i heard that by the next day.anyways, May God be with them till the end.
ReplyDeleteየአገር የወገን ፍቅርን ከልብ ይዜን በአንድነት መንፈስ ከሰራን የአገራችን ትንሳኤ በጣም ቅርብ ነው።
ReplyDeleteThanks Dani ...... good luck for Team Ethiopia! PROUD!PROUD!PROUD!
ReplyDeleteያጣነውን ትተን ያገኘነውን እናስብ፤ የሌለንን ትተን ባለን እንጠቀም፤ ያልሆንነውን ትተን በሆንነው እንሥራበት፤ ያልደረስንበትን ትተን በደረስንበት እናፍራበት፡፡ የማይጎድል የለምና፡፡ የዚህ ዓለም ጉዞ አንዱን ጎደሎ እየሞሉ ሌላ ጎደሎ መፍጠር ነው፡፡
ReplyDeleteyou are right
ReplyDeleteGood observation and thought."በፍላጎታችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ ግን ለምን ጉድለታችንን ብቻ እናስበዋለን፡፡ ለምንስ መጉደላችንን ብቻ እየሰብን እንብሰከሰካለን፡፡ ለምንስ የወደፊቱን ላለፈው ነገር ስንል እንሠዋለን፡፡ ለምንስ ነገን በትናንት ምክንያት እናበላሸዋለን፡፡"
ReplyDeleteያጣነውን ትተን ያገኘነውን እናስብ፤ የሌለንን ትተን ባለን እንጠቀም፤ ያልሆንነውን ትተን በሆንነው እንሥራበት፤ ያልደረስንበትን ትተን በደረስንበት እናፍራበት፡፡ የማይጎድል የለምና፡፡ የዚህ ዓለም ጉዞ አንዱን ጎደሎ እየሞሉ ሌላ ጎደሎ መፍጠር ነው፡፡
ReplyDeletethis is hana, it is a great view dani but we need a goooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooooal!!!!!!
ReplyDeleteበጣም ጥሩ መስታዎት ነው
ReplyDeleteበመጀመሪያ ዳንኤል ላመሰግንክ እወዳለሁ ያነበብኩት ፅሁፍ በጥልቀት ላነበበው ሰዉ ብዙ ትምህርት ይሰጣል እኔም ትምህርት ወስጀበታለሁ በእግር ኳስ ብቻ ሳይሆን በሌላዉ ህይወታችንም ቶሎ ተስፋ መቁረጥ የለብንም በተለይ እኛ ኢተዮጵያኖች ሁሉንም ነገር ማድረግ እንችላለን! አፄ ሚኒሊክ ሁሉንም አሰተምረዉን አልፈዋል አድዋ ላይ ድል እንደተቀናጀን ሁሉ ድህነትንም ድል እንቀናጅበታለን የምን ተስፋ መቁረጥ የምን ሽንፈት We are Ethiopians ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ አሜን!!!
ReplyDeletealways positive thanks Dani God bless you
ReplyDeleteAWESOME ARTICLE....
ReplyDeleteመለ
ReplyDelete