ድንግል ማርያም ሆይ
ባለፈው እንደሰማሽኝ ዛሬም ትሰሚኛለሽ ብዬ ነገሬን እቀጥላለሁ፡፡
አንቺ በቤተልሔም ከተማ ማደርያ አጥተሽ እንደተንከራተትሽው ሁሉ ነፍሰ ጡር ሆኖ ቤት መከራየትማ የማይታሰብ ነው፡፡
አከራዮቹ የልጁን የሽንት ጨርቅ ማጠቢያ፣ የገንፎውን ማብሰያ፣ የጡጦውን መቀቀያ፣ የእንግዳውን ማስተናገጃ ሁሉ አስበው የቤት መሥሪያ
ያስከፍሉሻል፤ ያለበለዚያም አንቺን እንዳሉሽ ‹ማደርያ የለም› ይላሉ፡፡
እኔማ ሳስበው አሁን አሁን ሕዝቡ መጥኖ መውለድ የጀመረው የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት ገብቶት አይመስለኝም፡፡ አከራዮች
ናቸው የሕዝባችንን ቁጥር እየቀነሱት የመጡት፡፡ ልጅ ካለሽ፣ ያውም ከሦስት በላይ ከሆኑ፣ ማን ያከራይሻል፡፡ ብትከራይም ልጆችሽን
እንደ ጥጃ ስትጠብቂ መኖርሽ ነው፡፡ ‹ይህንን ነኩ፣ ያንን ሰበሩ፣ ይህንን ቆረጡ፣ ያንን አበላሹ፣ እዚህ ገቡ፣ እዚያ ወጡ› እየተባለ
በየቀኑ ሮሮ ነው፡፡ ልጅ ደግሞ በተገዛና በተከራየ ቤት መካከል ያለው ልዩነት አይገባውም፡፡ እና በዚህ ምክንያት ቤት ሳይሠራ ላለመውለድ፣
ከወለደም ከሁለት በላይ ላለመውለድ ስንቱ ወስኗል፡፡
ድንግል ሆይ
‹‹ምነው ለድኻ ኮንዶሚኒየም እየተሠራ አይደለም ወይ?›› ትይኝ ይሆናል፡፡ እውነት ነው ተሠርቷል፡፡ ምን ምን የመሳሰለ
ኮንዶሚኒየም ተሠርቷል፡፡ እንዲያውም ሪል ስቴት ገብተሽ በገዛ ገንዘብሽ ከማረር ኮንዶሚኒየም ተመዝግበሽ አንድ ቀን ቢደርስሽ ይሻላል፡፡
አንዳንድ ሪል ስቴት ማለትኮ ገንዘብ ሰጥቶ የጨጓራ በሽታ መግዛት ማለት ነው፡፡ ሪል ስቴት ማለትኮ በገዛ ገንዘብሽ ቤትሽ ያልተሠራበትን
ምክንያት የሚገልጠውን ሪፖርት ሲቀበሉ መኖር ማለት ነው፡፡ ሪል ስቴት ማለትኮ ባለቤት የሌለው ኮንዶሚንየም ማለት ነው፡፡ ኮንዶሚኒየምስ
መንግሥት የሚባል ባለቤት ስላለው ከቀበሌ እስከ ክልል፣ ከባሰም እስከ ፓርላማ አቤት ይባልበታል፡፡ ይኼ ምርጫ የሚባል ነገር ሲመጣም
በእግር በእጅ ተብሎ ቢያንስ ግምሹ ይታደላል፡፡ ከዚያም ከባሰ ግምገማ ሲመጣ ተጣድፈውም ቢሆን ጋዜጣ ያወጣሉ፡፡
አቤት የሚባልበት ቦታ የሌለበት፣ ምርጫ የማይነካው፣ ግምገማ የማይፈራ ሪል ስቴት አለልሽ አይደል እንዴ፡፡ እዚህ ሀገርኮ
ሀብታምንም ድኻንም የሚያስተካክሏቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፡፡ የቤት ችግርና ሞት፡፡ ይኼ ቀን ቀን ምን በመሰለ መኪና ሽር ብትን
የሚለው ዘናጭ ሁሉ መኪና መግዛት ሳይሆን መኪና ማሳደር ነው የቸገረው፡፡ መኪና እንጂ መኪናውን የሚያህል መሬት እንኳን የለውም፡፡
ባይሆን እርሱ አከራዩ ውጣ ቢሉት ዕቃውን በገዛ መኪናው ጭኖ ይወጣልና ከኛ ከኛ ይሻላል፡፡
እስኪ ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ ማታ ማታ ተመልከች፡፡ ግቢውኮ የሞኢንኮ ወይም የፎርድ ግቢ ነው የሚመስለው፡፡ የኮንዶሚኒየሙን
ውበት የሚያስንቁ መኪኖች ጎን ለጎን ቆመው ግቢውን ሲፎትቱ ታያለሽ፡፡ ኮንዶሚኒየምን ‹ድኻ ይደርሰዋል፣ ሀብታም ይከራየዋል› የሚባለው
ለዚህ ነው፡፡ እዚያም ቢሆን የሠፈሩ ደላሎች በተኛሽበት ነው ለሌላ አከራይተው የሚጠብቁሽ፡፡ አንቺ ኮንዶሚኒየም መከራየትሽን ለጓደኞችሽ
በስልክ እየነገርሽ ባለሽበት ሰዓት ደላላና አከራይ ተስማምተው ለሌላ አከራይተው ይጠብቁሻል፡፡ ከዚያስ? ከዚያማ አንቺ በቤተልሔም
እንደገጠመሽ ማደርያ ፍለጋ መንከራተት ነዋ፡፡
ይኼው አንቺ ቤት ብታጭ ጌታን በረት ውስጥ አይደል የወለድሽው? ዛሬምኮ መንገድ ላይ፣ የሰው ቤት ማድቤት ውስጥ፣ ላስቲክ
ቤት ውስጥ፣ የሚወልዱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይኼው ለባለኮንዶሚኒየሞቹ በጋራ መጠቀሚያ ተብለው የተሠሩት ቤቶች እንደ ቤተልሔሟ በረት
የድኾች ማደርያ ሆነዋልኮ፡፡
ድኻ ቤት ብቻ አይደለምኮ መቃብርም እያጣ ነው፡፡ ይኼው ለመቃብር እንኳን ሀብታምና ድኻ ተለይቶበት የመቃብር ሪል ስቴት
መጥቷል አሉ፡፡ ታድያ ስሙን ቀይሮ ‹ፉካ› ተብሎ ይጠራል፡፡ እዚያ ሀብታም ነው የሚቀበረው፡፡ ኮንዶሚኒየምስ በዕጣ አንድ ቀን ይደርሰን
ይሆናል፡፡ ይኼ መቃብር ግን ዕጣ ያለውም አይመስለኝም፡፡ እንግዲህ ሲኖር አንጀቱ የተቃጠለ ድኻ ሲሞትም አስከሬኑ ካልተቃጠለ በቀር
የት ይቀበራል፡፡ ሲኖር ተንከራትቶ፣ ሲሞት ተንከራትቶ ድኻ እንዴት ይችለዋል? ለዚህ ነው ከሌላው ሁሉ የገና በዓል የሚገባኝ፡፡
ተከራይ ርካሽ ቤት ፍለጋ ወደ ከተማ ጥግ ሲሄድ፣ የከተማ ጥግ እያደግ የከተማ መሐል ሲሆን፤ ተከራይ ርካሽ ቤት ፍለጋ
የድኻ ሠፈር ሲሰደድ፤ የድኻ ሠፈር እየተሸጠ የሀብታም ሠፈር ሲሆን፤ ይሄው መጨረሻችን ምን እንደሆነ አይታወቅም፡፡
ምነው ግን በቤተልሔም ከተማ የተከራይ አከራይ የለም እንዴ፡፡ የዚያ ሀገር ሰዎች ከኛም ሀገር የባሱ መሆን አለባቸው፡፡
የኛዎቹ እንኳን በርካሽ ተከራዩትን የመንግሥት ቤት፣ ለሌላው በማዘን›› ዋጋ ጨምረው ቆርሰው ያከራዩታል፡፡ በኋላ ዘመን ታድያ
‹የተከራይ አከራይ› ተብለው ሕግ ወጣባቸው፡፡ እኔን የገረመኝ ግን መንግሥት ራሱ ‹የወራሽ አከራይ› ሆኖ የተከራይ አከራዮችን መከልከሉ
ነው፡፡ ይኼ አሁን መንግሥት የሚያከራየው ቤት አብዛኛው በቀድሞው መንግሥት የተወረሰ ቤት ነው፡፡ ወርሶ ማከራየት ወንጀል ካልሆነ
ተከራይቶ ማከራየት እንዴት ወንጀል እንደሆነ መጠየቅ ቤት አጥቶ ከመንከራተት ስለማያድን ትቼዋለሁ፡፡
እመቤቴ ሆይ
ይህንን ሁሉ ብሶት የምነግርሽ መቼም ትሰሚኛለሽ ብዬ ነው፡፡ በዚህ ዘመንኮ የሚናገር እንጂ የሚሰማ ባለ ሥልጣን ማግኘት
ከባድ ነው፡፡ እንቺ ግን የምትችይውን ታደርጊኛለሽ ያለበለዚም ሁሉ ለማይሳነው ልጅሽ ትነግሪልኛለሽ፡፡ ‹ወይ ግበርሎ፣ ወይ ንገርሎ›
ይባላል በትግርኛ፡፡ ወይ አድርግለት፣ ያለበለዚያም ለሚያደርግ ንገርለት ማለት ነው፡፡
ለዚህ ነው እመቤቴ እኔ ያንቺ መንከራተት የሚገባኝ፤ የገና በዓልም የኔ በዓል የሚመስለኝ፡፡
በእውነቱ በዚህ ደብዳቤ እነዚያ እረኞችን
ሳያመሰግኑ ማለፍ በራስ ላይ ርግማን ማምጣት ነው፡፡ ምንም እንኳን ቤት ባይኖራቸው በረታቸውን ግን ላንቺ ሰጥተውሻል፡፡ የሀገሬ
ሰው ‹ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም› ይላል፡፡ እኔስ ‹ያለውን የሰጠ ታሪክ ያያል› ቢባል ነበር የምመርጠው፡፡ እነዚያ እረኞች
የዓለምን ታሪክ ሲለወጥ ለማየት አልነበረም በረቱን የሰጡሽ፡፡ እንዴው ደግ ስለሆኑ ነው፡፡ ደግ ሰው ማለት እንደ ቀላል ነገር
የሠራው ደግነት ተአምር ሲሠራ የሚያይ ነው፡፡
ዛሬኮ እመቤቴ እረኞቹ እንደዚያ ዘመን
ለሌሎች በረታቸውን አይሰጡም፡፡ እንዲያውም የዛሬ ዘመን እረኞች ኢንቨስተሮችና ቤት ሠሪዎች፣ ቤት አከራዮች ሆነዋል፡፡
ምእመናንኮ ከአባቶቻቸው ከእረኞች ቤት እየተከራዩ ነው፡፡ እረኞች ዛሬ ቤት ላጡ ቤት እየሰጡ አይደለም፡፡ እንዲያውም ቤት
ይገዛሉ፣ ቤት ይሸጣሉ፣ ቤት ይሠራሉ ቤት ያከራያሉ፡፡ አንቺ ደጎቹን እረኞች አግኝተሻቸው ነው፡፡
አቤት ያች የታደለች በረት፡፡ የሰማይ
መላእክት ከምድራዊ ሰዎች፣ የሩቅ ሀገር የጥበብ ሰዎች ከእሥራኤላውያን እረኞች የተስማሙባት ቦታ፡፡ ምናለ ይህችኛዋ በረት ቤተ
ክርስቲያን እንዲህ ሁላችን የምንስማማባት ቦታ እንድትሆን ብታማልጅን፡፡ እንኳን የሰማዩ ከምድሩ፣ እንኳን የሩቁ ከቅርቡ የአንድ
ቦታ ሰዎች እንኳን መስማማት አቅቶናል፡፡ ለዚህ ሳይሆን ይቀራል የጎንደሩ ባለቅኔ ክፍለ ዮሐንስ
እምነ ከዊነ ካህን ይኄይስ ከዊነ ኖላዊ
ወጎለ እንስሳ ይትበደር እም ቤተ መቅደስ
ዐባይ
እስመ ቤተ መቅደስ ኮነ ቤተ ፈያታይ
ወበላዕለ ኖሎት ኢሀለወ ላዕለ ካህናት
ዘሀሎ እከይ
ትእምርተ ዝኒ ክመ ንርአይ
በጎለ እንስሳ ሠረቀ ዘየአርብ ፀሐይ
ያለው ለዚህ ነበር፡፡
ይኼውልሽ አንቺ በስደትሽ ወቅት በመልካም
ሁኔታ ያስተናገዱሽ ኢትዮጵያውያን እንኳን ወገናቸውን የሰው ሀገር
ሰው የሚያለምዱ ነበሩ፡፡ ‹እኔስ በሀገሬ እንኳን ሰው ወፍ
አለምዳለሁ› ብለው ያንጎራጎሩትኮ ወደው አልነበረም፡፡ ስንቱ ከውጭ መጥቶ እዚሁ ለምዶ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ቀርቷል፡፡ ዐረቡ፣
እሥራኤላዊው፣ ግብጻዊው፣ አርመኑ፣ ግሪኩ፣ እንግሊዛዊው፣ ፈረንሳዊው፣ ፖርቹጊዙ፣ የመናዊው፣ ሕንዳዊው፣ ሶርያዊው፣ ኧረ
ስንቱ፡፡ እንኳን ሰው በ15ኛው መክዘ ከሜክሲኮ የመጣው በርበሬ እንኳን ‹ፒርፒሬ› የሚለውን ስሙን በርበሬ አድርጎ ፍጹም
ኢትዮጵያዊ ሆኖ፣ የኢትዮጵያውያን የሞያ መለኪያ ለመሆን በቅቶ የለም እንዴ፡፡
አሁንማ እንኳን የሰው ሀገር መቀበል ሰው
ከጎረቤቱ ጋር በሰላም መኖር እየተሳነው ነው፡፡ አንድ ወንዝ የጠጣን የአንዲት ሀገር ሰዎች በሃይማኖትና በዘር ተቧድነን አትየኝ
እየተባባልን ነው፡፡ እንኳን አልተማረም የሚባለው ትምህርት ገባው የተባለው ወገን እንኳን ኮሌጅ ውስጥ በዕውቀት መከራከሩን ትቶ
በዘር ይቧቀስልሻል፡፡
መቼም የቸገረው ሰው ነገሩ ረዥም ነው፡፡
ባለጠጋማ ነገሩ አጭር ነው ፡፡ እንዲያውም የድኻ ፍታትና የባለጠጋ ጸሎት አጭር ነው ይባላል፡፡ ድኻ ብዙ ማመልከቻ አለው፡፡ ሀብታምማ
‹ያለኝን ጠብቅልኝ› ካለ በቃው፡፡ የቀረኝን ደግሞ ሳምንት ነግሬሽ ጉዳዬን እጨርሳለሁ፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ
ነው
Great view Dani
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል
ReplyDeleteየግዕዝ ችሎታችን በጣም ውሱን ነውና ይህንን ቅኔ
እምነ ከዊነ ካህን ይኄይስ ከዊነ ኖላዊ
ወጎለ እንስሳ ይትበደር እም ቤተ መቅደስ ዐባይ
እስመ ቤተ መቅደስ ኮነ ቤተ ፈያታይ
ወበላዕለ ኖሎት ኢሀለወ ላዕለ ካህናት ዘሀሎ እከይ
ትእምርተ ዝኒ ክመ ንርአይ
በጎለ እንስሳ ሠረቀ ዘየአርብ ፀሐይ፡፡
እባክህ ፍቺውን ጻፍልን፡፡
what you want to say
Deletekal bekal siteregom
Delete"imne kewin kahin yiheyis kewine nolawi"
kahin kemehon eregna mehon yishalal
"wegole insisa yitbeder im betemekdes abay"
ye insisat beret kebetemekdes yilik betam yiwededal
"isme betemekdes kone bete feyatay"
betemekdes yewenbedewoch bet honualina
"webelaile nolot ihalewe laile kahinat zehalo ikey"
bekahinat lay yale ekuy(metifo neger) be iregnoch lay yelem
"timrte zini keme niray"
yezihin milikit enay zend
ene endegebagn kal bekal endezih new wanaw meliektu ke Getachin lidet(beberet meweled,yeregnoch mistirun lemayet metadel) gar yiyayazal
so you think the person who posted this did not know the meaning? I just wanted to know what he/she wants to say. Direct comments are better because you know who the message is intended to
Deleteእንኳን አልተማረም የሚባለው ትምህርት ገባው የተባለው ወገን እንኳን ኮሌጅ ውስጥ በዕውቀት መከራከሩን ትቶ በዘር ይቧቀስልሻል፡፡
ReplyDeleteDaniel,sega enjera endemefelege hulu menefeseme be ante tsehufoch seletegebe egeziabehere rejeme edemene yesetelegne ke anete bezu yememarewe selalegne
ReplyDeletetimely written article.God bless you Dani.
ReplyDeleteዳንኤል እንደምነህ
ReplyDeleteእግዚብሔር ይስጥህ፡
እኔ በጣም ነው የሳቅኩት፤
ማሽላ ሲያር ይስቃል ይባል የለ
እኔም የገጠመኝ ስለሆነ ነው፡፡
በእድሜ ዘመኔ ሰው ለሰው በቤት ኪራይ
የተጨካከነበት ዘመን ሳይ ፤ ምን አለፋህ በአጠቃላይ
መሬት ላይ ብተኛ ጉንዳኑ መከራ
ዛፉ ላይ ብወጣ አሞራው መከራ
ካቡ ላይ ብተኛ እባቡ መከራ፡
አገሬ በጌምድር በየት ብየ በየት ልደር ሆነ ነገሩ
ወለተ ሚካኤል ነኝ
‹‹ እንቺ ግን የምትችይውን ታደርጊኛለሽ ያለበለዚም ሁሉ ለማይሳነው ልጅሽ ትነግሪልኛለሽ፡፡ ‹ወይ ግበርሎ፣ ወይ ንገርሎ› ይባላል በትግርኛ፡፡ ወይ አድርግለት፣ ያለበለዚያም ለሚያደርግ ንገርለት ማለት ነው፡፡ ››
ReplyDeleteኧረ በጣም ይከብዳል፡፡ ከለመንክ መለመን ነው እንጂ ከቻልሽ አድርጊልኝ ካልቻልሽ ንገሪልኝ የሃይማኖተኛ ፀሎት አይመስለኝም፡፡
ወርሶ ማከራየት ወንጀል ካልሆነ ተከራይቶ ማከራየት እንዴት ወንጀል እንደሆነ መጠየቅ ቤት አጥቶ ከመንከራተት ስለማያድን ትቼዋለሁ፡፡
ReplyDeleteYou need to publish this. Sir. The bible says that "በመጀመርያ ከሁሉ በፊት አስቀድማችኁ የእገግዚአብሄርን ፅድቅ ፈልጉ ከዚያ በኋላ ሁሉ ነገር ይጨመርላቸኋል". We all need to work in that direction. The above thing, you mentioned, indicated that we lacked commitment in searching God's truth way, rather we are focusing in obtaining comfort while we are living in this temporary world
ReplyDeleteከዋልድባ ገደም የተፈናቀሉት የእግዚአብሔርን ጽድቅ ስላልፈለጉ ይመስልሃል? እዬዬም ሲዳላ ነው ያለው ማን ነበር? በምድር የሚኖር ሁሉ ገዳማዊ አይደለም፡፡ በገዳም ሁሉን ትተው ጽድቅን ለሻቱት ማረፍያ ቦታ ከቸገረ ለጽድቅ ለምንፍጨረጨረው ደግሞ የዳኒ እይታ እውነት አይመስልህም? ለማንኛውም ቅድምያ ጽድቁን ፈልገህ የማረፍያ ጉዳይ ከተሟላላህ እንኳን ደስያለህ፡፡ የሰው ልጅ ግን በእምነቱ የሚፈተነው ባለው ነገር ሳይሆን በሌለው ነውና ምስጋና እንኳን ለማቅረብ ጸጥታ ስፍራ ላጡት ወገኖች ሁሉ ለማይሳናት የወልዴ እናት በአማላጅነቷ ማረፍያ ትስጠን፡፡
DeleteSolomon, that is why you are reading this article, you just act like "Feresawi"
DeleteI think u need to differentiate the duties and responsibilities of those christian who live in the world and those who live in the monastery. Sir. U do not have to defend the author. U need to use your reasoning OK!
Deleteዛሬኮ እመቤቴ እረኞቹ እንደዚያ ዘመን ለሌሎች በረታቸውን አይሰጡም፡፡ እንዲያውም የዛሬ ዘመን እረኞች ኢንቨስተሮችና ቤት ሠሪዎች፣ ቤት አከራዮች ሆነዋል፡፡ ምእመናንኮ ከአባቶቻቸው ከእረኞች ቤት እየተከራዩ ነው፡፡ እረኞች ዛሬ ቤት ላጡ ቤት እየሰጡ አይደለም፡፡ እንዲያውም ቤት ይገዛሉ፣ ቤት ይሸጣሉ፣ ቤት ይሠራሉ ቤት ያከራያሉ፡፡ አንቺ ደጎቹን እረኞች አግኝተሻቸው ነው፡፡
ReplyDeleteአቤት ያች የታደለች በረት፡፡ የሰማይ መላእክት ከምድራዊ ሰዎች፣ የሩቅ ሀገር የጥበብ ሰዎች ከእሥራኤላውያን እረኞች የተስማሙባት ቦታ፡፡ ምናለ ይህችኛዋ በረት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ሁላችን የምንስማማባት ቦታ እንድትሆን ብታማልጅን፡፡ እንኳን የሰማዩ ከምድሩ፣ እንኳን የሩቁ ከቅርቡ የአንድ ቦታ ሰዎች እንኳን መስማማት አቅቶናል፡፡
e.....hi....hi...!
ReplyDeleteDan Daniel yemitisifachewen hulu sus honobing eyeteketateliku new E/r edime ena tena yisitih.
ReplyDeleteDear Daniel, thanks for your article. I hope that the problem addresses most citizens living in Addis Ababa and other towns. As to my knowledge it is difficult to say that you are self employed. Because throughout your life,you have been serving your church directly or indirectly. You have a car even though this does not mean a house. Your wife is working in an international organization and probably you have your shelter. If not, don't worry. Many of us are leading the same life. I left AA and went to region to teach in one of government universities. I bought? a condominium house. I borrowed from micro finance institution to pay the download. "mamsham edme new". I advise others even not to marry before they have a home. I understand it now that shelter is a basic need, not while I was learning Abraham Maslow's hierarchy of needs. Wendime Egziabher tsegawn yabzalih binaweraw bizu gud ale.
ReplyDeleteበዚህ ዘመንኮ የሚናገር እንጂ የሚሰማ ባለ ሥልጣን ማግኘት ከባድ ነው፡፡
ReplyDeletethank you
እነዚህን ተከታታይ ጽሁፎች ሳነብ ባንድ ወቅት አከራያችን ያደርሱብን የነበረው ስቃይ ትዝ ይለኛል።
ReplyDeleteአንድ ጓደኛ ይዘህ ስትዘልቅ ከታየህ ሁኔታዎችን ለመከታተ ከበሯ ነቅነቅ አይሉም። ጓደኛህ እጁን ታጥቦ ሲያዳርቅ ወይም ሽንት ቤት ደርሶ ሲመለስ ከታየማ በቃ አለቀልህ፤ነገር ተበላሸ። "የትም ያቆሸሸውን እጁን እኔ ቤት ነው እንዴ የሚታጠበው? የትም እየበላ እኔ ቤት ነው እንዴ የሚጸዳዳው? ለስንት ዘመን ይሆነኛል ያልኩትን ጉድጓድ ባንድ አመት ልትሞሉት ነው እንዴ? በእናንተ ምክንያት በየአመቱ ገንዘቤን እየከሰከስኩ ሳስመጥጥ ልኑር እንዴ?" ኧረ ስንቱ!!! ስንተኛው እንደነበረ ትዝ አይለኝም እንጅ ባንድ ወቅት የአለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ለማየት ያየነውን ስቃይማ አትጠይቀኝ። ስንት ቀን ባጥር ዘልየ ገብቻለሁ መሰለህ! ስንት ቀን ጎረቤት ቤት አድሬአለሁ! የመብራቱ እና የውሃውን ነገር እማ አታንሳው። ቧንቧው ቁልፍ ስላለው በተመደበልህ ሰዓት ተገኝተህ ካልቀዳህ በውሃ ጥም ትሞታታለህ እንጅ ውሃ አታገኝም። በሰዓቱ ብትገኝም ከተወሰን ሊትር በላይ መቅዳት አትችልም። መብራትም እንደዚያው። ግቢ ውስጥ የተከራየነው አብዛኞቻችን ተማሪዎች ስለነበርን እያመሸን ማጥናት ይጠበቅብናል። ሰውየው ግን የዋዛ አይምሰሉህ። ሌሊት እየዞሩ እያንዳንዱን ቤት ቼክ ያደርጋሉ፤ ወይ በበር ቀዳዳ ያያሉ ወይም ጠጋ ብለው ድምጽ ለመስማት ይማክራሉ። ድንገት አንዱ መብራቱን አብርቶ ሲያጠና ድንገት እንቅልፍ ጥሎት ካዩት ወይም ከሰሙት ወዲያው መብራቱን ከቆጣሪው ያጠፉብናል። በማግስቱ ጠዋት በቃ ተማሪ እርስ በእርሱ ይባላል አልኩህ ፤ አንተ ነህ አንተ ነህ እንቅልፋም ሆነህ መብራታችንን ያስጠፋህብን እየተባባለ። ኧረ ስንቱ....ብቻ እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ሁሉም አልፏል፤ ዛሬም የራሴ ቤት ገና ባይኖረኝም በአሜሪካ አትላንታ ከተማ ከተከራየሁት ከሚያምረው አፓርትመን ውስጥ አልጋየ ላይ ቁጭ ብየ ይህንን ለመጻፍ በቃሁ፤ አይለቅበት መድኃኒዓለም።
እንኳን አልተማረም የሚባለው ትምህርት ገባው የተባለው ወገን እንኳን ኮሌጅ ውስጥ በዕውቀት መከራከሩን ትቶ በዘር ይቧቀስልሻል፡፡ Belew Yen
ReplyDeleteአቤት ያች የታደለች በረት፡፡ የሰማይ መላእክት ከምድራዊ ሰዎች፣ የሩቅ ሀገር የጥበብ ሰዎች ከእሥራኤላውያን እረኞች የተስማሙባት ቦታ፡፡ ምናለ ይህችኛዋ በረት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ሁላችን የምንስማማባት ቦታ እንድትሆን ብታማልጅን፡፡ እንኳን የሰማዩ ከምድሩ፣ እንኳን የሩቁ ከቅርቡ የአንድ ቦታ ሰዎች እንኳን መስማማት አቅቶናል፡፡
ReplyDeleteጀሮ ያለው ከተገኘ መልካም ብለሐል አልያም በስደት ምክንያት ሳቅ ለረሳን ሰዎች ገንዘብ ከፍለን የማናገኘውን የገና ሰጦታ አበርክተሀል።ኦናመሰግን አለን።
ReplyDeleteቢሮከራሴ ከአከራይ ቤት - መሰሪያ ቤት
ReplyDeleteI am tired of leading a beaurocratic woven life….why did not find a solution that suffice for all.
God Bless You!!
ReplyDeleteወይ ግበርሎ፣ ወይ ንገርሎ
ReplyDeleteዳኣቆን ዳኒኤል ወንድሜ በጣም ደስ ሰለሚለ ያንተ ፅሑፍ ሁሉ ጌዛ ኣነብዋለሁ ዛሬ የግረመን ነገር ግን በትግርኛ ምስላ መጻፍህ ነው
በጣም ደስ ኣለኝ ምክንያቱ የኔ ላንጎጅ ሰለሁነ ነው ግን ስፔሊን ኣልተስተካክለም ያለና እና ወይ ግበረሉ፣ ወይ ንገረሉ በለው ይቅርታ ኣድርግልን ግን
Ante rasih spelling altestekakelem bileh yetsafkew wrong new silezih yesewun sihtet lemarem atchekul
Delete....ልጅ ደግሞ በተገዛና በተከራየ ቤት መካከል ያለው ልዩነት አይገባውም፡፡ እና በዚህ ምክንያት ቤት ሳይሠራ ላለመውለድ፣ ከወለደም ከሁለት በላይ ላለመውለድ ስንቱ ወስኗል፡፡....
ReplyDeleteDear Daniel, I appreciate your article. But, I
ReplyDeletehave just a little doubt on the title. I don't have much knowledge to the spiritual world as much as you do, but don't u think it is a little bit unrespectful to use our holy Mary's name just to magnify our blog title, As I said ,
correct me if I am wrong, but I just felt a little bit unconfortable about it. apart from that, the contect and idea of the article is perfect !!!!
I don't see any disrespect in the article my friend. If you've read the entire article,you can clearly observe that it was an appeal to the Almighty God via Holy Mary. I'm not a deeply spiritual person too,but I can understand that when a person lost hope in every earthly means to satisfy his/her needs, the last resort is in the Heavenly Authority. Don't forget that in Orthodox Christian teachings, the virgin Mary is the way for a person to pass his/her spiritual requests and redemptions to Jesus Christ. And I believe this article followed that same suit.
DeleteAnchi huletegnawa anonymous, why don't you let Dn Daniel respond himself? Yergo Zinb atihugni. You smell like someone paid to defend the author no matter what.
DeleteYou are very right anonymous. Not good to mention MARY here!
DeleteThe article is to small to carry the topic
Deleteአንድ የመረረው የፌስ ቡክ ጎረቤቴ የጻፈውን ግጥም አስታወሰከኝ
ReplyDeleteኢትዮጵያ ሀገሬ የጀግኖች እናት
እስኪ ፈልጊልኝ የሚከራይ ቤት
ዳኒ የሚሰማ ጆሮ ካለ የሕዝቡን ጨኸት ነውና የጮኸክልን እግዚአብሔር ረጅም እድሜ ይስጥልኝ ፡፡
የብዙሃኑን ኢትዮጲያዊ ችግር ነው የዳሰስከው ደግሞ የት አቤት ማለት እንዳለብህ አውቀሃል። እግዚአብሔር ይባርክ።
ReplyDeletei agree with Anonymous. i don't think it is proper to use the name of the Holy Mother for this this way.
ReplyDeleteDear Daniel, you talk about having kids? didn't u hear about them saying that they will not rent their houses to married couples or more than one person living together? who knows what is going to happen 2morrow!
ReplyDeleteወንጌል በአንድም በሌላም መንገድ ይነገራል ይኽው አንዱ መንገድ:: የእመቤታችን ስም ቢነሳ ምልጃዋ ቢነገር ተገደን እኮ ነው የምናደርገው:: ድንግል ማርያም እኮ በኢትዮጵያዊው ሕይወት ብዙ ነገር ናት:: እናንተ ሀይማኖት ብቻ አታድርጉት:: ምናልባት ዳኒ ይመለስበት ይሆናል:: ንጉሥ የሚምልባት፣ ጀግና የሚፎክርባት፣ የተማሪ ስንቁ፣ . . . ይህና ይህ ሁሉ እኮ ነገረ ማርያም ላይ የለም:: እኛ አገር ግን ይለያል:: የቤት ኪራይ አይደለም፣ የእለት ጉርስ ይለመንበት የለም እንዴ ስሟ? ዘፋኝ/አዝማሪው ሁሉ ቢያወሳት ምን ይደንቃል? ለምን ማለት አይቻልም:: ስሟን ከውልደት እስከ ሞት የሰማነው ስለፈለግን ብቻ ሳይሆን ሀይማኖት ባሕል ሲሆን በሚፈጠር ማኅበራዊ ስምምነትም ነው:: ካለማክበር የሚመነጭ ሳይሆን በውዴታ ከመገደድ የሚመጣ ነውና አለመስማማት ይቻላል:: ማስቀረት ግን አይቻልም:: ጻፍ ጻፍ ጻፍ ወዳጄ!!
ReplyDeletedes sitil, jal. everything you right is real.
DeleteDani, It is really lovely. You have tried to address the problem of the people. Can you please suggest solutions for the existing problems on your last script? One suggestion is, why don't we the Orthodox Christians in abroad and in addisababa bid for a plot of land and construct condominium houses.This will have a big help for our christian life. What do u think? I would be glad to be the member of this group that could be led by you.My e-mail is meles222000@yahoo.com.
ReplyDeleteHabtamu Meles(Oslo)
wooooow thanks Habtamu for ur great idea. really I feel happy.
Deleteየሚገርም እይታ ነው! ዳኒ እግዚአብሔር ይጠብቅህ!
ReplyDeletewondimie D/n Daniel E/r yibarkih
ReplyDeletebetam enwodihalen hulem tsafilin,asitemiren
GOOD BLESS YOU!!!
HIRUT (GONDAR)
Dn. Daniel Egizihabeher yesteh! Dingelem bemelegawa Chgere lay yalenewen Taseben. Le Lejua yemisanew neger yelemena!
ReplyDeleteI always adore you!
ReplyDeleteDear Dani ,have u seen that a plot of land for residence sold 12,000 per m2 (yerer), the gov't is playing a game with realestates. For example realestate owners can pay someone to participate in the bid and he gives 12,000 per m2 that person will only lose the 14,000birr paid to participate in the bid and won't participate again,but by doing so the real estate owners will get a chance to sale their homes with a better price.Otherwise how could a person pay 2.4million for 200m2,the land isn't for commercial use.It is for residence.They only lose 14,000birr ,if they don't claim the land they won.But the person paid by these investors has already brought big fortune for them.Otherwise while there are many houses on 250m2 plot which can be sold for even less than 2.4 million,why would one give 12,000birr per m2 for 200m2 plot not for commercial ,it is for residence.
ReplyDeleteአቤት ያች የታደለች በረት፡፡ የሰማይ መላእክት ከምድራዊ ሰዎች፣ የሩቅ ሀገር የጥበብ ሰዎች ከእሥራኤላውያን እረኞች የተስማሙባት ቦታ፡፡ ምናለ ይህችኛዋ በረት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ሁላችን የምንስማማባት ቦታ እንድትሆን ብታማልጅን፡፡ እንኳን የሰማዩ ከምድሩ፣ እንኳን የሩቁ ከቅርቡ የአንድ ቦታ ሰዎች እንኳን መስማማት አቅቶናል፡፡ Mamush, MN
ReplyDeleteHi Danny! I wanna ask you that why U didn't post these articles on facebook? I tried to go through ur wall but you checked ur facebook account on may 22, 2012 for the last time. I guess there are around 10000 people subscribed to ur facebook page they may probably also have difficulties to visit this personal blog of urs. Therefoe for the benefit of many subscribers and for easy access to other religion followers u better post ur articles on face book. God Blees You!
ReplyDeleteIt is a good view but I don't like the title. You had better not use the Name of Mary-the Virgin. you have been mentioning the Honorable Name unnecessarily.Mary is not a spice for your article. you were not supposed to do so. shame on you! Ato Daniel
ReplyDeleteIt is not correct to use St Mary's namae us title of this article. Somteimes you are making thinks messed!
ReplyDeleteእግዚያብሔር ይባርክህ
ReplyDeleteWiy ... Ewnet new Dani betam yastelalim ysferalim esu yitebiken enji lela min yibalal
ReplyDelete
ReplyDeleteDn.Daniel is really quite perfect!!!
ReplyDeleteእግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛላችሁ።
ReplyDelete