Friday, January 11, 2013

መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ

click here for pdf
ከጥቂት ቀናት በፊት ታዋቂው ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ› በሚል ርእስ አንድ አነጋጋሪ፣ አከራካሪና አመራማሪ መጽሐፍ አውጥተዋል፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ሃሳባቸውን በአደባባይ፣ ሕዝብ በሚረዳው መንገድና ቋንቋ ከሚገልጡ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ልሂቃን አንዱ ናቸው፡፡ በሦስት የመንግሥት ሥርዓት ፕሮፌሰር መስፍን ሃሳባቸውን ሲገልጡ፣ ሲጽፉ፣ ሲከራከሩና፣ መልካም የመሰላቸውን ሁሉ ለሕዝብ ሲያቀርቡና ሲሞግቱ የኖሩ የአደባባይ ምሁር ናቸው፡፡
አብዛኞቹ ልሂቃን በጆርናሎችና በዐውደ ጥናቶች ላይ ከሚያቀርቧቸው ጽሑፎች ባለፈ ለሀገር ሕዝብ ዕውቀታቸውን በሀገር ቋንቋ አያቀርቡም፡፡ በዚህ የተነሣም ታዋቂነታቸውም ሆነ ተሰሚነታቸው በዚያው አካዳሚያዊ በሆነው ክልል ብቻ የታጠረ ነው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ግን በአማርኛችን ከጣት ቁጥር በላይ የሆኑ መጻሕፍትን አቅርበዋል፡፡ በጋዜጦችና በመጽሔቶች ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡ በሀገራዊ መድረኮች እየተገኙ ያላቸውን ለግሰዋል፡፡ 

ይህንን መጽሐፍ ደጋግሜ አንብቤዋለሁ፡፡ ከራሴም ጋር ሆነ ከሌሎች ጋር ተወያይቼበታለሁ፡፡ ተምሬበታለሁ፡፡ አንዳንድ ነገሮችንም አንሥቼበታለሁ፡፡ ለመጻፍ ግን ጥቂት ቀናትን መውሰድ አስፈልጓል፡፡ ስለ ሦስት ምክንያት፡፡ ምናልባትም ከእኔ የተሻለ ሰው በጉዳዩ ላይ ይጽፍና ሃሳቤን፣ ያነሣው ይሆናል ብዬ፤ በሌላም በኩል ምናልባትም በሕይተወትና በጤና ያለው ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ አንድ ነገር ይል ይሆናል ብዬ፣ እንዲያም ባይሆን እነዚህ ሊቃውንትን ያፈራውና እነርሱም ያፈሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ክፍል ምልከታውን ያቀርብ ይሆናል ብዬ፡፡ ግን የሆነ አልመሰለኝም፡፡
ይህ አሁን የቀረበው የፕሮፌሰር መስፍን መጽሐፍ የኢትዮጵያን ታሪክ የሞገቱበት መጽሐፍ ነው፡፡ ጉዳዩ ገና ከርእሱ ይጀምራል፡፡ ‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ› ሲል፡፡ አነጋጋሪ፣ አመራማሪና አከራካሪነቱንም አሐዱ ይላል፡፡ ለመሆኑ ታሪክ ይከሽፋል? የክሽፈት ታሪክ ሊኖር ይችላል እንጂ የከሸፈ ታሪክ ሊኖር ይችላል? የስኬት ታሪክ ይኖራል እንጂ የተሳካ ታሪክ ይኖራል?
ፕሮፌሰር መስፍን ራሳቸው በመጽሐፋቸው ከገጽ 34 ጀምረው ስለ ታሪክ ምንነት ብያኔ ይሰጣሉ፡፡ በዚህ ብያኔያቸውም ታሪክን ‹ዘገባ› ‹መዝገብ› ‹ውለታ› ‹ሰንሰለት› እያሉ ነው የገለጡት፡፡ ይህ ገለጣቸው ደግሞ ታሪክ የማይቋረጠውን የሰው ልጆች ጉዞ የሚያሳይ ዘገባ፣ የትናንቱን የሰው ልጅ ሂደትና አስተዋጽዖ የምናነብበት መዝገብ፣ የትናንቱ ማኅበረሰብ ያቆየልን ውለታ ነው፡፡ የትናንቱንና የዛሬውንም የሚያስተሣሥር ሰንሰለት ነው፡፡
እንዲያ ከሆነ ደግሞ ታሪክ የአንድን ማኅበረሰብ የስኬትም ሆነ የክሽፈት፣ የድልም ሆነ የሽንፈት፣ የውጤትም ሆነ የኪሳራ፣ የልዕልናም ሆነ የተዋርዶ ጉዞ የሚያሳየንና የምናጠናበት፣ የምንመዘግብበትና የምናይበት ነገር ነው ማለት ነው፡፡ ስለ ክሽፈቱ እናይበት ይሆናል እንጂ ራሱ የሚከሽፍ አይመስለኝም፤ ስለ ስኬቱ እናጠናበታለን እንጂ ራሱ የሚሳካ አይመስለኝም፡፡ ሰው የስኬት ታሪክ ይኖረዋል እንጂ ታሪኩ አይሳካለትም፡፡ የሽንፈት ታሪክም ይኖረዋል እንጂ ታሪኩ አይሸነፍበትም፡፡ ለዚህ ነው አከራካሪነቱ፣ አነጋጋሪነቱና አመራማሪነቱ ከርእሱ የሚጀምረው፡፡
ያንን ብንሻገረውና ታሪክ ይከሽፋል ብንል እንኳን መከራከራችንንና መመራመራችንን አናቆምም፡፡ ‹እውነት የኢትዮጵያ ታሪክ ከሽፏል? አንድን ታሪክ ከሽፏል ወይም ተሳክቷል የሚያሰኘው ምን ምን ሲሆን ነው? የሚሉትን እንድናነሳ ያደርገናል፡፡ በፕሮፌሰር መስፍን መጽሐፍ የምናጣው ታላቁ ነገር ይኼ ነው፡፡ አልፎ አልፎ ለታሪካችምን መክሸፍ ማሳያ ናቸው ያሏቸውን ነገሮች ከማንሣታቸው በቀር ይህንነ ነገር አላብራሩልንም፡፡
በመጽሐፉ ውስጥ ያጣሁት ታላቅ ነገር የሚመስለኝ ይኼ ነው፡፡ የታሪክን ‹ክሽፈትና› ስኬት› መበየኛ ነገሮችን አስቀድመው በማሳየት፤ አንድ ታሪክ ‹ከሸፈ. ወይም ‹ተሳካ› የሚያሰኙትን መመዘኛዎች በመተንተን፣ በዚያም መሠረት የኢትዮጵያን ታሪክ እየገመገሙ እዚህ እዚህ ላይ እንዲህ ስለሆንን፣ በዚህ መመዘኛ መሠረት ከሽፈናል ይሉናል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡  ፕሮፌሰር መስፍን ግን ሌላ አካሄድ መርጠዋል፡፡
በፕሮፌሰር መስፍን መጽሐፍ ዋናውን ቦታ የያዙት ኢትዮጵያውያን የታሪክ ሊቃውንት ናቸው፡፡ ከእነርሱ በፊት ሌሎች የታሪክ ሰዎችም እየቀረቡ ሂሳቸውን ተቀብለዋል፡፡ እኔ እዚህ ላይ ፕሮፌሰር መስፍንን መጠየቅ የምፈልገው ሁለት ጥያቄ ነው፡፡
የመጀመርያው የታሪክ ክሽፈትና ታሪክ ጸሐፊዎች እንዴት ነው የተገናኙት? የታሪክ ክሽፈትን ለማሳየት የታሪክን ሂደት ተከትሎ አንድን ሁነት ከየት ተነሥቶ የት እንደደረሰ በመተንተን፣ ያም ሁነት ከሽፎ ከሆነ የከሸፈበትን ምክንያት ማቅረብ ሲገባ ታሪካችን ከሽፏል ብንል እንኳን ‹የከሸፈውን ታሪክ› የጻፉት ወይም ያጠኑት ምሁራን እንዴት ነው ከታሪክ ክሽፈት ጋር ሊገናኙ የቻሉት?
ለእኔ ይህ አካሄድ አንድ ሰው ሌላ ሰውን የገደለበትን ዜና የሠራውን፣ ለዜናው ትንታኔ ዜና ያቀረበውን ጋዜጠኛና ተንታኝ የግድያው ወንጀል አባሪ ተባባሪ፣ ወይም ደግሞ ለግድያው ምክንያትና መነሻ አድርጎ እንደማቅረብ ነው፡፡ ዘጋቢውን ‹ወንጀለኛ› ማለትና ዘገባውን ‹የወንጀል ዘገባ› በማለት መካከል ልዩነት አለ፡፡ ዘጋቢው ወንጀለኛ የሚባለው የሠራው ዘገባ ሕግን የተላለፈ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ዘገባውን የወንጀል ዘገባ የሚያደርገው ግን ስለ አንድ ስለተፈጠረ ወንጀል የቀረበ ዘገባ ከሆነ ነው፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን የኢትዮጵያን የታሪክ አዘጋገብና የታሪክ ጥናት ለብቻው ቢተነትኑትና ያም ትንተና የታሪክ አጻጻፋችንና አተናተናችን የተሳካ ነው ወይስ ያልተሳካ? አስመስጋኝ ነው ወይስ አስነቃፊ? ተመስጋኝ ነው ወይስ ተነቃፊ? የሚለውን ቢተነትኑት እስማማ ነበር፡፡
አንድ ኦዲተር የአንድን ድርጅት ሂደት የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሥራ ሊሠራ ይችላል፡፡ ያ ድርጅት ከስሮ ከሆነ የኪሳራውን መጠንና የኪሳራውንም ምክንያት ያቀርባል፡፡ ይህንን ሲያደርግ ያ ኦዲተር የራሱ ሕፀፆች ይኖሩበታል፡፡ ሁለቱ ነገሮች ግን የተለያዩ ናቸው፡፡ የድርጅቱ ኪሳራና የድርጅቱን የኪሳራ ሪፖርት የሠራው ባለሞያ ሕፀፅ፡፡ የዚህን ድርጅት ታሪክም አንድ የታሪክ ባለሞያ ሊዘግብ፣ ሊተነትንና የኪሳራውንም መነሻና ሂደት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ይህ የታሪክ ባለሞያ ይህንን ታሪክ ሲዘግብና ሲተነትን ድክመቶች ሊኖሩበት ይችላል፡፡ የሁለቱ መገምገሚያ ግን ይለያያል፡፡ የድርጅቱ መክሰርና የታሪክ ባለሞያውም የከሰረ ድርጅትን ታሪክ መዘገቡና መተንተኑ ‹የከሰረ የታሪክ ባለሞያ› አያሰኘውም፡፡
በፕሮፌሰር መስፍን መጽሐፍ ላይ የተተቹት የታሪክ ባለሞያዎችም በፕሮፌሰር ሐሳብ ብንስማማ እንኳን ‹የከሸፈውን የኢትዮጵያ ታሪክ በየአንጻራቸው ዘገቡ፣ ተነተኑ› እንጂ እነርሱ ራሳቸው የከሸፉ የታሪክ ባለሞያዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ ከሽፏል ቢባል እንኳን ለዚያ ለከሸፈው ታሪክ ማጣቀሻ ይሆኑ ይሆናል እንጂ ‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ› በሚል ርእስ ሥር የእነርሱ ሥራ መተንተን አልነበረበትም፡፡ ምንልባት ፕሮፌሰር ‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ የታሪክ አጻጻፍ› የሚል ርእሰ ጉዳይ ቢያነሡ ኖሮ የማርያም መንገድ ባገኙ ነበር፡፡ እንደዚያም ሆኖ በርግጥ ከሽፏል? በሚለው ከተስማማን ነው፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን የኢትዮጵያን የታሪክ አዘጋገብ ችግሮችና የአተያየይ ሳንካዎች ማንሳታቸውና በዚያ ላይ ትችት ማቅረባቸው አልነበረም ችግሩ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ራሱን አስችለውና ደረጃውን ጠብቀው ደግመው ደጋግመው ቢሄዱበት ለሁላችንም የዕውቀት በረከት የሚሆን ነው፡፡ ነገር ግን ‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ› በሚል ርእስ ታሪክ ጸሐፊዎቹን ከታሪኩ ጋር አብሮ መውቀጥ ‹ከተልባ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ› ዓይነት ይሆናል፡፡ ‹ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ይዘንባል› ያለውን የሜትሮሎጂ ባለሞያ ‹ለምን ዘነበ› ብሎ እንደመውቀስ ነው፡፡
ሌላው ሁለተኛው ጥያቄዬ የተነሡትን ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የሚመለከት ነው፡፡ በፕሮፌሰር መስፍን መጽሐፍ ላይ በዋናነት ተነሥተው የተተቹ አምስት ኢትዮጵያውያን የታሪክ ሊቃውንት አሉ፡፡ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት፣ ዶክተር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ፣ ፕሮፌሰር መርዕድ ወልደ አረጋይና ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ፡፡ ከእነዚህ ሊቃውንት መካከል ከፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴና ከፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት በቀር ሌሎቹ ዛሬ በሕይወት የሉም፡፡ በሕይወት ከሚገኙት ከሁለቱ ሊቃውንት መካከልም ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ታምመው በድካም ላይ ነው የሚገኙት፡፡
ምንም እንኳን በአንድ መጽሐፍ ላይ የሚደረግ ክርክርና ሂስ ሰዎቹ መልስ ሊሰጡበት፣ ሂሱንም ሊቀበሉበት ዘመን ብቻ መሆን አለበት ባይባልም፣ ይህ ዕድል ካለና ከነበረ ግን ይመረጣል፡፡ ቢያንስ ስለ ሦስት ነገር፡፡ አንደኛ እነዚህ ሊቃውንት ሂሱን ተመልክተው እንዲሻሻሉ፤ ሁለተኛም እነዚህ ሊቃውንት የእነርሱንም አተያይ የማቅረብ ዕድል እንዲያገኙ፤ ሦስተኛ ደግሞ ነገሩ ፍትሐዊ እንዲሆን፡፡ አንድን አካል መልስ ለመስጠት በማይችልበት ጊዜና ሁኔታ ማሄስና መውቀስ ከሞራል አንጻር ፍትሐዊ አይሆንም፡፡ የሀገሬ ሰው ‹ሙት ወቃሽ አትሁን› የሚለው ሙት መወቀስ ስለሌለበት ሳይሆን ‹መልስ ለመስጠት በማይችልበት ሁኔታ› ማለቱ ነው፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን የነ ፕሮፌሰር ታደሰ፣ የነ ዶክተር ሥርግውና የነ ፕሮፌሰር መርዕድ ዘመነኛ ናቸው፡፡ ይህ ዛሬ የሰጡት ትችት በዚያ በዘመነኛነታቸው ወቅት ቢሆን ኖሮ በሁለቱ ወገኖች መካከል በሚኖር ክርክር ታላቅ ዕውቀት በተገበየ ነበር፡፡ በርግጥ ልዩ ልዩ መዛግብትን ስናገላብጥ አንዳንድ ክርክሮች እንደነበሩ ያሳያሉ፡፡ እነዚህ ኅትመቶች ሲወጡም ቅሬታዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ይህ የፕሮፌሰር መስፍን ሐሳብ ቀርቦ ክርክር አልተደረገበትም፡፡
የፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት church and state in Ethiopia የሚለው መጽሐፍ የታተመው በ1964 ዓም ነው፡፡ የዛሬ 41 ዓመት፤ የዶክተር ሥርግው Ancient and medieval Ethiopian History to 1270 የታተመው በ1964 ዓም የዛሬ 41 ዓመት ነው፡፡ የፕሮፌሰር መርዕድ ጽሑፍ political geography of Ethiopia at the beginning of 16thc. የታተመው በ1966 ዓም ነው፡፡
አንግዲህ ይህንን ሁሉ ዘመን ተሻግሮ ዛሬ ላይ ትችቱ መቅረቡ ነው ለእኔ የሞራል ጥያቄ እንዳነሣ ያደረገኝ፡፡ እነዚህን ሰዎች በዘመን ያላገኘናቸው፤ ‹ጥንት› በምንለው ዘመን የነበሩ ቢሆኑ ኖሮ የሞራል ጥያቄው ሊነሣ ባልቻለ ነበር፡፡ ነገር ግን ከእኛው ጋር የነበሩ፤ መልስ ሊሰጡበትና ትችቱን ሊቀበሉበት በሚችሉት ዘመንም ሊጻፍላቸውም፣ ሊጻፍባቸውም የሚቻል፣ ነበርና ምነው? ያሰኛል፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ የኢትዮጵያን ጥንታዊና የመካከለኛው ዘመን በማጥናትና በመተንተን እንደ ሥርግው፣ እንደ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትና እንደ ፕሮፌሰር መርዕድ ያለ ሰው ዛሬ አላገኘንም፡፡ በየመድረኩም ሆነ በየመዛግብቱ እንደ ብሉይና ሐዲስ የሚጠቀሰው የእነዚሁ ቀደምት አበው ሥራ ነው፡፡ የእነዚህን ቀደምት አበው ሥራዎች በማይመለከታቸው ርእስና ጉዳይ ላይ ማንሣትም ሆነ ማሄስ ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ለቡድኑ መሸነፍ ተጨዋቾቹንና አሠልጣኙን፣ ፌዴሬሽኑንና ኮሚሽኑን መጠየቅ ሲገባ የጨዋታውን ዘጋቢና ተንታኝ ጋዜጠኛ መውቀስ ይመስላል፡፡
ከቀድሞ ጀምሮ በልሂቃኑ ዘንድ ከዕውቀት ክርክር የዘለለ ሌላ የጎንዮሽ መጎሻሸምና መነካካት እንደነበረ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ምሁራን ታሪክ የሚያጠና ሁሉ የሚደርስበት ነው፡፡ አንድ ማሳያ ብቻ ላንሣ፡፡ አንድ ጊዜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል መምህራንና በሌሎች መካከል ‹ጠብ› ተፈጥሮ ነበር፡፡ በተለይም ለአብዮቱ እንቀርባለን የሚሉ ምሁራን እነዚህን የታሪክ ክፍል መምህራን ‹ደብተራዎች› እያሉ መውቀስና እንደ አድኅሮት ኃይላት መመልከት ያዘወትሩ ነበር፡፡
ይህ ነገር እየከረረ መጣና አንድ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ምሁር ወደ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዘንድ ሄደው እነዚህን የታሪክ መምህራን በፀረ አብዮትነት ከሰሱ፡፡ በወቅቱም ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ቤተ መንግሥት እንዲመጡ ተጠሩ፡፡ እኒህ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ዶክተር ወደ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዘንድ በማን በኩል እንደ ሄዱ ፕሮፌሰር መስፍን ያውቃሉ፡፡
ፕሮፌሰር ታደሰ ከሌሎቹ ምሁራን ጋር በጉዳዩ መክረው ወደ ቤተ መንግሥት ተጓዙ፡፡ አንዳች ክፉ ነገር እየጠበቁ ነበር የገቡት፡፡ መንግሥቱ በክብር ተቀበላቸውና የአብዮቱን ታሪክ እንዲጻፍ መፈለጉን ነገራቸው፡፡ ፕሮፌሰርም ልባቸው መለስ አለች፡፡ ሁኔታዎች ከተመቻቹ ሞያዊ ሥራ ለመሥራት እንደሚቻል ገለጡ፡፡ መንግሥቱም ፕሮፖዛል እንዲያዘጋጁ ነግሮ በክብረ ሸኛቸው፡፡ ከመሸኘቱ በፊት ግን ‹ከዶክተር እገሌ ጋር ቅሬታ አላችሁ መሰል፣ አንዳንድ ነገር ነግሮኝ ነበር፤ እዚያው ተነጋግራችሁ ፍቱት› አላቸው፡፡ እርሳቸውም እንፈታዋለን ብለው ከቤተ መንግሥት ወጡ፡፡
አሁን እዚህ መጽሐፍ ላይ ቤተ መንግሥቱን አየሁት፡፡

126 comments:

 1. I am not clear with what you want to say? off course ሰውየው ተቃዋሚ ስለሆነ ምናልባት መንግስት ስለኢትዮጵያ ታሪክ ወቀሳ ከሰሳ ምናምን በማቆሙ የምሁራኑም ስራ የመንግስት ደጋፊ የሆነ መስሎት ይሆናል! እምትግባባው ከሆነ ምከረው በዕድሜ ጸሃዩ መጥለቂያ እስከአሁን የሰራቸውን ስራዎች የሚያበክት ስራ ሰርቶ አንዳያልፍ እና የወቀሳቸው ሰዎች ዕጣ እንዳይደርሰው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. bians be ethiopia weg tilk sew antu yibalalina profeserun ante bemalet erasihn ataward.

   Delete
  2. wow that is amazing danny boy

   Delete
  3. Yeshimagile mikir yemesele hateta

   Delete
 2. that is good Dani!Go a head.bick

  ReplyDelete
 3. አንድ ወቅት ሮናልድ ሬገን አሉት የተባለው ጥቅስ ትዝ አለኝ፡፡ይህም “Facts are sometimes stupid.” ያሉበት እይታ ነው፡፡እኔም “History is sometimes stupid because history is also episodes of facts that need proper honesty and wisdom for its proper interpretation and understanding.” የሰው ልጅ ትግል ሁል ጊዜ ከእውነት ጋር መሆኑንና ሰዎች እጅግ በጣም የምንፈራውም ነገር እውነትን መሆኑ ነው፡፡የታሪክ መከለስ መመረዝና መጣመም ከዚህ እውነትን ከመፍራት የመነጨ ጭምር ነው፡፡ታሪክ ሳይበረዝ ሳይከለስ ሳይጣመም እንዳለ ሲቀርብ የሰው ልጅ እራሱን በጥልቀት ወደ ውስጥ ያይበታል እንደዚሁም ይማርበታል፡፡ታሪክ ሳይበረዝ ሳይከለስ ሳይጣመም እንዳለ ሊቀርብ የሚችለው ደግሞ ሰዎች እውነትን ሳንፈራ ለመጋፈጥና ከእውነትም ለመታረቅ ስንችል ብቻ ነው፡፡ከታሪክ ለመማር የሚቻለው በዋናነት ሁለት ነገሮች ሲሟሉ ነው፡፡አንደኛው ታሪክ ሳይበረዝ ሳይከለስ ሳይጣመም እንዳለ ለመቅረብ ሲችል ነው፡፡ሁለተኛው ደግሞ ታሪክን በቅጡ በመመርመር በመተርጎምና አንድ የሆነ ድምዳሜ(understanding and interpretation) ለመስጠት ስንችል ነው፡፡So history without proper wisdom for its understanding and interpretation is such a mere bunch of facts.ስለዚህም አንድ ታሪክ ከሸፈ ሲባል አንድ ታሪኩ ሳይበረዝ ሳይከለስ ሳይጣመም እንዳለ ሊቀርብ ባለመቻሉ ነው፡፡ሁለት ታሪክ ከሸፈ ሲባል ታሪክን በትክክለኛው ብስለትና ንቃተ-ህሊና እውነትን ተከትለን በቀናነት ለመረዳት ለመተርጎምና ከዚህም ተገቢውን ትምህርት ለመውሰድ ሳንችል ስንቀር ነው፡፡አዎ ከታሪክ እንደምንማረው ሰዎች ከታሪክ ሊማሩ አለመቻላቸውን ነው የተባለው አባባል ጭምር ሲከሰት ታሪክ ከሸፈ ይባላል፡፡አዎ ከላይ እንዳልኩት ማንኛውም ክስትት(Phenomenon or fact) ታሪክ ነውና ታርክንም አጣሞ በርዞ ከልሶ ማቀረብ በራሱ የዘመናችን ሌላኛው ታሪክ የመስራት ተግባር እየሆነ የመጣ ይመስላል፡፡The child is the father of the man እንዲባል የአንድ ልጅ የልጅነት ታሪኩ/ኳ የአሁኑ የማንነት መሰረቱ/ቷ ነው፡፡ለአንድ ማህበረሰብ ህዝብና ሀገርም ታሪክ በዚህ እይታ ነው የሚታየው፡፡ታሪክ ከሸፈ ሲባል ታሪኩ በትክክል አልቀረበም እንደዚሁም ታሪኩ በትክክል አልተተረጎመም ማለት ነው፡፡አዎ ታሪክ ከሸፈ ሲባል ልክ አንድ የዘር ሀረግ አንድ የሆነ ቦታ ላይ ተበጠሰ እንደማለት ሊሆን ይችላል፡፡ሌላው ስለታሪክ መክሸፍ ለምን በዚህ ወቅት ለምን ተጨነቅን የሚል መሰረታዊ ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ማልናባትም እንደ እኔ እይታ አንድ አሁን ያለንበት ታሪካዊ ወቅት አንድ የሆነ መስቀለኛ መንገድ ላይ ኮምፓሳችን ጠፍቶብን ግራ ተጋብተንና የምንቀጥልበት አቅጣጫና መንገድ ጠፍቶን ስለቆምን ሊሆን ይችላል፡፡የከሰረ አረብ ያባቱን መዝገብ ያገላብጣል እንዲሉ እኛም እንደ ማህበረሰብ እንደ ህዝብ እንደ ሀገር ያለፈ ታሪካችንንና ማንነታችንን ቆም ብለን ለመጠየቅ የተገደድንበት ታሪካዊ ወቅት ላይ የደረስን ይመስለኛል፡፡እኔ እንደምረዳው ፕሮፌሰሩ በዝርዝር ጉዳች ላይ ምንም ይበሉ ምን ትክክልም ይሁኑ ስህተት ነገር ግን ዋናው ነጥብ እራሳችንን ቆም ብለን የዘመናት የታሪክ ጎዟችንን እንደገና ቆም ብለን መጠየቅ መመርመርና መተርጎም ከዚያም ተገቢውን ቀጣይ የአቅጣጫችንን ኮምፓስ ማግኘት የሚገባን ታሪካዊ ወቅት ላይ እንደሆንን የሚያጠይቅና ክብሪት የሚጭር አጀንዳ ነው፡፡አፄ ምኒልክ ወይንም አፄ ቴዎድሮስ ወይንም አፄ-ዮሀንስ በጥንት ዘመነ-ቅኝ ግዛት በሰፈነበት አገዛዛቸው ውስጥ ዲሞክራሲ ያላሰፈኑ አምባገነን ናቸው ብሎ ለሚራገምና በተቃራኒው ዛሬ አለማችን ፍፁም የለየላት የዲሞክራሲ ገነት የሰፈነባት ምድር እንደሆነች ለሚረዳ ትውልድ ታሪክን እንደገና ቆም ብሎ መመርመርና መረዳት አለበት፡፡የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት የአንድ መዝናኛ ካፍቴሪያ ወይንም ሬስቶራንት ወይንም የአንድ የውጪ ሀገር ሰለብሪቲ ክብርና ዋጋ ያህል የማይሰጥ ዘመነኛ ትውልድ አዎ ዛሬ ታሪኩን እንደገና ቆም ብሎ መጠየቅና መመርመር አለበት፡፡ጦርነትን ያላየ የሰላምን ዋጋ አያውቃትም እንዲሉ አዎ የነፃነትን ዋጋ ለመረዳት የግድ ባርነትን ማየት ተገቢ የሆነ ይመስላል፡፡
  አዎ ትውልዱ በቅኝ-የመገዛትንም ይሁን በቅኝ ያለመገዛትን ጥልቅ ትርጉምና ፋይዳ እንዲረዳው ዛሬ ይህንን አይነት ተዘዋዋሪ ዘመናዊ ቅኝ ግዛት ማየትና መቅመስ አለበት፡፡ያ የድሮው ያለፈ የፀረ-ቅኝ ግዛት የተጋድሎ ታሪክና የተከፈለለት መስዋእትነት በትክክል ቢቀርብ ኖሮ ዛሬ ትውልዱ እራሱ ወዶ ፈቅዶ ዘመናዊ ቅኝ ግዛትን እንደ የስልጣኔ ገፀ-በረከት አሜን ብሎ ባልተቀበለው ነበር፡፡በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ ትውልዱ በእጁ ያለውን ክቡር ነገር እንደማይረባ ነገር ለምናምንቴ ነገር በልዋጭ እየሰጠው ነው፡፡የታሪክ መክሸፍ ማለት ያለፈ ማንነትን በትክክል አለመረዳት ማለት ጭምር ነው፡፡ምክንያቱም የእራስን እውነተኛ ማንነት በመካድ የሚፈጠር ሌላ አዲስ እውነተኛ ማንነት የለምና ነው፡፡If there is no old me then there is no new me.ለእኔ የታሪክ መከሸፍ የምርጫ ግንቦት 97 ዲሞክራሲያዊ አለመሆን ማለት አይደለም፡፡ምክንያቱም አስቀድሞም የውሸት(Superficial) የሆነና ትርጉም ባለው መንገድ የሌለ ነገርን እንዳጣነው ልንቆጥረው አንችልምና ማለት ነው፡፡እንዲያውም ይህ አይነት የምርጫ ግንቦት 97 ክስተት ከውጪ ለታይታ ያለውን የውሸት ማንነታችንን ሳይሆን እውነተኛውን ድብቅ ማንነታችንን እንድንጠይቅና እንድንመረመር የሚረዳ ነው መሆን ያለበት፡፡ስለዚህም ምርጫ 97 ታሪክ ነው፡፡ታሪኩን ግን በትክክል መተረክና በትክክልም ትርጓሜ መስጠትና ከዚህም ትምህርት መውሰድ ታሪካዊ ግዴታችን ነው፡፡ስለዚህም ምርጫ 97ን እንደ ታሪክ በተወሰነው ወገን የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የጨነገፈበት ነው ብሎ መረዳት አንድ ትርጓሜ ነው፡፡እንደዚሁም በሌላኛው ተቃራኒ ጫፍ ምርጫ 97 ቀድሞውንም ያልተረገዘውን የዲሞክራሲ ፅንስ በግድ ካልተወለድክና በደዚች ምድር ካልመጣህ ብሎ እናቲቱን እንደማሰቃየት የሚቆጠር ክስተት ነበር ብሎ መተርጎምም ሌላ እይታ ነው፡፡የታሪክ መክሸፍ ከታሪክ ትክክለኛ ትርጓሜ አለመኖር የሚመነጭ ጭምር ነው፡፡

  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. I think you understood the book!

   Delete
  2. I am happy about the way you understood the book. Daniel is entitled to his opinion but it seems for me that he took only one side of the story (may distorted the intention of the professor)!!!

   Delete
  3. it is very Great!!!!!!!! i like it.
   E/r yesteh....tebarekk

   Delete
  4. Clear and nice explanation.

   Thank you!

   Delete
  5. ዳንኤል፤ ፕሮፌሰሩን ካየበት ዓይን ያንተ የተሻለ ነው። ታሪክ በራሲ ሂደት ሊበላሽ፤ መጥፎ ጥላ ሊያጠላበትና ለመጪው ትውልድ ክፉ ስምን ሊያወርስ እንደሚችል ሁሉ ታሪክ በታሪክ ዘጋቢዎችም በደንብ ባለመዘገቡ እውነቱ ተቀብሮ ከሽፎ ሊቀር እንደሚችል ዳንኤል ሊያውቅ ያልፈለገ ይመስላል። የናዚዎች ታሪክ የጀርመኖች ታሪክ ነው። ይህ ታሪክ እውነታውን ይዞ በጠቃሚነቱ ይሁን በመጥፎነቱ መከተብ አለበት።
   ዳንኤል ስለኦዲተር ባነሳው ሃሳብ ሃሳቡን ልሞግት። ኦዲተር የሂሳብ ሥራ ታሪኩን በደንብ ካልሰራው የምርመራው ታሪክ ሊከሽፍ እንደሚችል እንዴት ይሰወረዋል? ታሪኩን ከፈጸመው ትውልድ ይልቅ ታሪክ ዘጋቢ ታሪከኛ የሆነ የማዳንና የመግደል አለው። የነበረው እውነታ መክሸፉን አይቀሬ ይሆናል።
   ሌላው የዳንኤል ሃሳብ ሀዲዱን የሳተው ከ41 ዓመት በፊት የተጻፈ ስሁት ታሪክ ካለ መላሽ በሌለበት ዛሬ መነሳቱ አግባብ አይደለም ማለቱ ነው። የከሸፈ ታሪክ ካለ መርምሮ እውነቱን በአስረጂ ማቅረብ ካለፈው ስህተት እንድንማር ይበጀናል እንጂ አይጎዳንም። ጥሩም ይሁን መጥፎ ያለፈው ተከድኖ ይቀመጥ ማለት ተገቢ አይመስለኝም። በ3000 ሺህ ዘመን ረጅሙ ታሪካችን ውስጥ የወደቅንበትንና የተነሳንበትም የታሪክ ምእራፎች ራሳችንን መመልከቱ ለዛሬው እኛነታችን ወሳኝነት ይኖረዋል። ይህ ትውልድ ይህ ይጎድለዋል። የተሳኩ ታሪኮቻችንና የከሸፉት በእውነተኛ የታሪክ ዘጋቢ እጦት ደህናዎቹም እንደከሸፉ ተመዝግበዋል። እስራኤሎች በዘመናቸው ሁሉ ሲነግሱ ታሪክ ጸሐፊዎችን ይሾሙ ነበር። በዘመናቸው የተደረገውን ነገር ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ ይጽፉ ነበር። የከሸፈውንም፤ የተሳካውን መጪው ትውልድ እንዲያውቅ ያስደርጉ ነበር። የነገሥታቱ ሁሉ ታሪክ ደግሞ ያሻር በተባለው መጽሐፍ ይሰፍር ነበር። እኛ ግን ለዚህ አልታደልንም። ይህንን የሚገልጥና የአሁኑን ትውልድ ኢትዮጵያዬ ማለት በሚያስችል የታሪክ ኩራት ውስጥ ባይገኝ አንድ የከሸፈ ነገር እንዳለ እሙን ነው። ወይ ከታሪክ ሰሪው ወይም ከታሪክ ጸሐፊው!
   መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ በእርግጥም ማሰኘቱ አሌ የማይባል እውነት ነው።

   Delete
  6. ለዲያቆን ዳንኤልን ጥያቄ ይህ በቂ መልስ ነው! ነገር ግን ዳንኤል አሁንም የተጠቀሱት የታሪክ ፀሐፊዎችና ተመራማሪዎች የተሰነዘረባቸው ትችት ትክክል አይደለም ካልክ ዝርዝር ሐሳቦችን አንሳና ፕሮፌሰር መስፍንን ሞግታቸው! እኛም ብዙ እንማር! ያለ በለዚያ ግን የከሸፈ ታሪክ ከታሪክ ፀሐፊው ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ አለው! ታሪክ የሚከሽፈው የባለ ታሪኩ ውድቀቱም ሆነ ስኬቱ በትክክል ሳይዘገብ፣ ሳይተረጎም ሲቀር ነውና፡፡

   Delete
  7. better explanation.
   than the main one

   Delete
  8. Thank you, my dear endalkew Tarik yemikeshifew:Betikikil kaltezegebe,be Ethiopia-wigna ayin kalteredanew, kalteregomnew,endihum tikikilegawin ethiopia-wiga aredad behulum yehibreteseb kifil yalu zegoch endiredut ena endikorubet kaladeregin bemecheresam Abatochachin meswatnet keflew kakoyulin yeteshalech Ethiopian lemefterna letetekiw tiwlid masrekeb kalchalin Tarik keshfoal.Beterefe Daniel Yanesachew gilesebawi negeroch minem Ayanesum. Degmom Yante ewket negere haymanot ena keza gar yeteyayazu negeroch gar engi bezih mesihaf zuria mugit wust lemegbat bikat yaleh aymeslegnm. hulet egir alegn tebilo....

   Delete
  9. Very nice explanation!

   Delete
  10. Amen God! Bless Ethiopia! I actually didn't read the professor's book, but understand contextually from Daniel's point of view but I understand the professor message from your so clear explanation than Daniel.

   Delete
  11. As to me, you expressed the idea better than Diackon Daniel did.

   Delete
  12. nice view . Daniel limesegen yigebewal b/c ante tiru mabraria enditset silanesasah. Yes I like the professor's book.

   Delete
  13. I respect Diacon Daniel and the commenter with good view.

   Delete
  14. God bless you brother/sister! I am with you 100% in understanding the current movement of building a false history as real one by demonizing the history of the nation and its people made for 3000+ years. Yes when a history lacks its place in the generation or when no body is learning from his/her fathers history - it is failed! with that generation. Of course the responsible parties for its failure are not the makers but the writers, the interpreters, the Medeas like ETV are the main ones. So Dani, I like your views but here I do not think you got the professor's message - HISTORY IS IN REAL CRISIS IN ETHIOPIA IN OUR TIME. we are trying to rewrite it, we are trying to replace the monuments of our heroes by the so called hero of few; we are sold for nothing in-general. May God give the spirit of our forefathers to all of us including religious leaders! Amen.
   Little John

   Delete
  15. ውድ ዮሃንስ
   ከታላቅ አክብሮት ጋር ምስጋናዬ ይድረስህ። የልብ የልቤን ነው የተናገርክልኝ።
   ሙሉጌታ ሙላት

   Delete
  16. endenanite ayinet hasab yalewu sewu say behagere endegena tesfa adergalehu

   Delete
  17. PROF. KE 41 AMETIM NEBERU AHUNIM ALU, ESKEZARIE ASTEYAYET SAYSETU QOYITEW SEWOCHU BELELUBT METSAFACHEW WEY K 41 AMET BEHUALA NEW YEGEBACHEW WEYDEGMO HON BILEW SEWOCHU BELELUBET YETSAFUT

   Delete
  18. You are amazing writer. You felt the book enough. I understand the book as you did.

   Delete
 4. መጽሐፉ በስሜታዊነት የተጻፈ ከመሆኑም በላይ ቅናት ቢጤ ይንጸባረቅበታል፡፡ ዝንጀሮ የራሷ እንትን አይታያትም ዓይነት ነገር ነው፡፡ 45 ብሬ እንደጠፋች ባልቆጥረውም አላግባብ ባክናለች! ይልቁንስ ከፕሮፌሰር መስፍን የምንጠብቀው እርሳቸው “እንደተቿቸው” ምሁራን አረፍተ ዘመን ሳይገታቸው በደም(በሰማዕትነት) የተጻፈ ለማጣቀሻ የሚያገለግልና ለመጪው ትውልድ አለኝታ የሚሆን መጽሐፍ ጽፈው እንዲያልፉ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ere newir fira/fri talak sew nachew endih badebabay mezalef ye ethiopiawinet migibar ayidelem. bechewa denib yalenin amelekaket megilets ayishalim, mechem kegna yeteshalu sew nachew.

   Delete
  2. አይ አንተ እንኳ 45 ብርህ ነው ያንገበገብችህና ዝም በል፡፡

   Delete
 5. ለቡድኑ መሸነፍ ተጨዋቾቹንና አሠልጣኙን፣ ፌዴሬሽኑንና ኮሚሽኑን መጠየቅ ሲገባ የጨዋታውን ዘጋቢና ተንታኝ ጋዜጠኛ መውቀስ ይመስላል፡፡

  ReplyDelete
 6. አሁን እዚህ መጽሐፍ ላይ ቤተ መንግሥቱን አየሁት፡፡

  ቅሪት ካላ ታሪክን ያከሽፋል ቅሪት ካላ ታሪክን ያፀናል ቅሪት ካለ ታሪክ እንዳይከሽፍ ይሞግታል፡፡የዚህ ትውልድ አካል ስለሆንኩ ታሪክ እንዳይከሸፍ እሞግታለሁ፡፡

  ReplyDelete
 7. Daniel, I think you need to read the book again. As to me the above commentator (Anonymous)understood the book. Please try to revise your comment e.g ‹ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ይዘንባል› ያለውን የሜትሮሎጂ ባለሞያ ‹ለምን ዘነበ› ብሎ እንደመውቀስ ነው

  ReplyDelete
 8. I have not read the professor's book, I won't have a comment on it.
  I just wanted to say thank you for opening the door for civil critics/discussion on the work of Writings. I look forward to seeing many in the field of the subjuct, participate.
  GOD be with you, you have a long way to go.

  ReplyDelete
 9. ዳኔ ለመጽሐፎ ትኩረት ሰጥጨ እንዳነብ ስለአበረታታኸኝ ለአመሰግነሐህ አወዳለሁ::

  ReplyDelete
 10. Dany, did you finish your review. I felt that you were at the introduction and to give more. Please finish your comments.

  ReplyDelete
 11. Guys, there are so many ways to skin a cat!

  ReplyDelete
 12. Dani,I appreciate the courage and motivation to present your review, though I didn't get chance to read the book I am eagerly waiting Prof's response on your blog.

  ReplyDelete
 13. አንዳንዶቻችሁ ትገርማላችሁ፡፡ ፕሮፌሰሩ ለምን ተነክተው የምትሉ ዓይነት ናችሁ፡፤ እንኳን በሕይወት ኖረው መልስ የሚሰጡት ፕሮፌሰር መስፍን በሕያወት የሌሉትም እየተተቹ ነው፡፡
  እኔ ከዳንኤል ሀሳብ የተስማማሁት ታክ አይከሽፍም በሚለው ላይ ነው፡፡ እንደ ታሪክ አይነት ኮንሴፕቶች ምልአት ያላቸው ኮንሴፕቶች ናቸው፡፡ ማለትም የሆነ ቦታ የማይቋረጡ ነገሮች፡፡ ሲቋረጡ ነገር ኣለሙ የሚያልቅ፡፡ ዓለም ሲፈጠር ታሪክ ጀመረ፡፡ ዓለም ሲያልቅ ያልቃል፡፡ ታክ ክስተት ሳይሆን የማይቋረጥ የክስተቶች ቅጥልጥል ነው፡፡ የማይቋረጥ ነገር አይሳካምም አይከሽፍምም፡፡ በውስጡ ግን ክሽፈትንም ስኬትንም ይይዛል፡፡ ለምሳሌ ዓለም ምሉእ ናት፡፤ ዓለም ስትከሽፍ ያበቃላታል፡፤ በውስጧ ግን የተለያዩ ክስተቶችን ክሽፈት ይዛለች፡፡
  የኢትዮጵያ ታሪክ በውስጡ የተለያዩ ሥልጣኔዎችን፣ ሃሳቦችንና ግለሰቦችን ስኬትና ኪሳራ ይዟል፡፤ የኢትዮጵያ ታክ ግን አይከሽፍም፡፡ አንድ ነገር ከከሸፈ መቆም አለበት፡፡ ታክ ደግሞ አይቆምምና አይከሽፍም፡፡ በፕሮፌሰሩ መጽሐፍ ላይ የተተቹት ምሁራን ‹ከከሸፉት› ክስተቶቻችን ጋር ግንኙነት የላቸውም፡፡ ስለ ከሸፈው ነገር በሚገባ ጽፈዋል አልጻፉም መከራከር ይቻላል፡፡
  ሰናይ ከስድስት ኪሎ

  ReplyDelete
 14. I have to read,understand, and ask the Professor's book first. Sometimes some people rush to give comment out of the context without reasoning.

  Gebre,

  ReplyDelete
 15. Sele arestu asetat ptofeseru endante yasebubet aymeslegnim.adeneqehalew.gin sele Ethiopia tarik saseb ebakih atse minilik mekina wede Ethiopia asmetu belo kemiyadenk tsehafi yelek Djibouti ena erteran yeshetu jegna weyem mogn belo yemitsef weyim yetsafe kale tekumen.Free rasist yalhone tsehafi yefelegal legna le Adisu tewled

  ReplyDelete
 16. እርግጥ “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የሚለው የፕ/ር መጽሀፍ አወያይ ቁምነገሮች ይዟል። የኢትዮጵያ ታሪክ መለስ ተብሎ እንዲመረመር ይረዳልና ጥረታቸው መልካም ነው። የታሪክ ሊቃውንቶቻችንም ስራዎች መተቸታቸው ለመማማር፣ለመተራረምና እውቀት ለመጨመር እስከሆነ ድረስ አይከፋም። የተጠቀሱት የታሪክ ሊቃውንት ጥሩ አበርክቶ ያደረጉ ቢሆንም በስራዎቻቸው ያሉ ብዙ ችግሮች እስካሁን ለአደባባይ ውይይት አልቀረቡም ነበር። እንዲያውም እነዚህ አንጋፋ ጸሃፍት የተከሏቸው ችግሮች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ታሪክ ትምህርት ክፍል ውስጥ ስር ሰድደው ወደ ተቋም ክሽፈት አድገው ይታያሉ። በፕ/ር መስፍን የተተቹት አምስቱ የታሪክ ሊቃውንት ቢያንስ ተመራምረውና ጽፈው ፕሮፌሰር የሆኑባቸው ጠቃሚ ስራዎቸ አበርክተዋል። እኒህ የታሪክ ሊቃውንት ያሰረጿቸው ችግሮች ግን በጊዜ ባለመታረማቸው መጽሃፍ ሳይጽፉ “ፕሮፌሰር” በሆኑ ተከታዮቻቸው ጭምር እንደ ቀኖና ተጠብቀው መቆየታቸው ብዙ ጉዳት አለው። ይህንን ችግር ለመፈተሽና ለማረም የፕ/ር መስፍን መጽሃፍ በጎ ጥረት አድርጓል።
  የፕ/ር መስፍን መጽሃፉ ዋና ችግር ጥልቅ ንዴት የወለደው መሆኑ ሲሆን፤ ንዴታቸው አመክንዮን ጨፍልቆ ሁሉም ነገር ላይ ክሽፈትን የለጠፈ ይመስለኛል። ርእሱ ላይ የደመቀውና በመጽሀፉ ውስጥም እስኪታክተን የምናገኘው መክሸፍ የሚለው ቃል የያዘው ጽንሰሃሳብ በቂ ማብራርያ አልተሰጠበትም።ነገር ግን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ከጥንት እስካሁን በክሽፈት ብቻ የሚገለጹ አድርጎ ማቅረቡ ትልቅ ስህተት ነው። ፕ/ሩ ጥንት የነበሩና አሁን ያሉ ስኬቶች አይታዩዋቸውም። ማበቦችና ስኬቶች ድሮም አልነበሩም አሁንም የሉም ሲሉ በጭፍን እርግጠኝነት ነው። ጽሁፉ ወጥነት የለውም፤ ትረካቸው እዚህም እዚያም ይፋለሳል፤ ሙግታቸውም እርስ በርሱ ይቃረናል።
  ራሳቸው ፕ/ር መስፍን ያለፉበት ታሪክም ክሽፍ መሆኑ ቢያምኑም በግል የተሳተፉባቸው ወይም የመሯቸው ነገሮች ለመክሸፋቸው ግን የግል ሃለፊነትና ድርሻ ለመውሰድ አልደፈሩም። ኢሰመጉ እንዴት እደከሸፈ ሲገልጹ “ወያኔ አከሸፈው ይባላል እንጂ እኛ ከሽፈን አከሸፍነው አንልም፤ መክሸፍ ባህል ነውና ኢሰመጉም ከሸፈ!” በማለት ከምክኒያቱ “እኔ”ን አስወግደው “እኛ” እያሉ ወደ ህዝብ ያላክካሉ። መጽሀፉ የግላቸውን ክሽፈት የኢትዮጵያ ክሽፈት ለማድረግ የጻፉት ይመስላል፤ ከግማሽ ምዕተዓመት በላይ የዘለቀው ህልምና ጥረታቸው ያልተሳካው ለምንድነው የሚል መሰረታዊ ጥያቄ በማንሳት እውነቱን መንገር ሲገባቸው የኢትዮጵያ ታሪክንና የታሪክ ሊቃውንትን በማብጠልጠል ሊያልፉት ይጥራሉ። በኔ አስተያየት የሳቸውን ክሽፈት ግምት ውስጥ ሳናስገባ የመጽሀፉን ፋይዳ አሟልተን መግለጽ አንችልም። መጽሃፉ የያዘው ቁም ነገር ጠቅልለን ለመረዳት የፕ/ር መስፍን የህይወት ጉዞ ለምን በኪሳራ ተሞላ? የሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት አለበት።ከልጅነታቸው ጀምሮ እስካሁን ባሳለፉት ህይወት የሚታወቁና የማይታወቁ ነገሮች አሉ። በፖለቲካ ህይወታቸውም ውስጥም ብዙ ቋጠሮዎች አሉ፤ በድፍረት መነገር ያለባቸው። አለበለዚያ ንዴታቸው ጎልቶ የምናይበትን ይህ መጽሃፍ “መክሸፍስ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን” ብለን እንድናነብበው ያስገድደንና ጠቃሚ ጎኖቹን ወደ ሚደፈጥጥ ድምዳሜ እንዳያደርሰን እሰጋለሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. With Respect- As I understood the book,I think the professor is not trying to say he wasn't part of the downs and ups of Ethiopia by saying Us(Egna). There are different times a person should use I and Us. "Us" shows unity(country), where as "I" shows individuality(single). If a country won a war battle because of a strong war General , it would be said the country won not the General Won. It's the same concept for losing. Thus, Saying We shows being united whereas saying "I" unnecessarily shows being selfish. Otherwise, Stay informed.

   Delete
 17. እውነት ታሪክ ሊከሽፍ አይችልምን ?

  ዳንኤል በፕሮፌሰሩ የታሪክ ፍቺ ላይ ቅሬታ ያለበት አይመስልም ፡፡ የፕሮፍን መጽሐፍ አጣቅሶ የታሪክን መዝገብነት ፣ ውለታነትና ሰንሰለትነቱን አፍታቶ ነግሮናል ፡፡ የዳኒ ቅሬታ የሚጀምረው ግን ታሪክ አይከሽፍም ብሎ በመነሳት ነው ፡፡ የክሽፈት ታሪክ ይኖራል እንጂ የከሸፈ ታሪክ ሊኖር አይችልም ይላል ፡፡
  የኔ ጥያቄ ግን የታሪክ መዝገብነቱና ሰንሰለትነቱ ጥቅሙ ምንድ ነው ? ታሪክ ሰንሰለት ነው ማለትስ ምንድን ማለት ነው ? ሰንሰለትስ ቢሆን አይበጠስምን ? …. ለኔ ታሪክስ መንግድም ጭምር ነው ፡፡ ታሪክ ድልድይም ነው ፡፡ ድልድይ ደግሞ ሊሰበር ይችላል ሰንሰለቱ እንደሚበጠሰው ፡፡ ታሪክ በነበርንና በነን መካከል ነው ፡፡ ብዙውን ጊዜ ክሽፈት ከነበርን ጋር ይሄዳል …. ነንን ላልከሸፍንበት ማንነታችንና ታሪካችን እንጠቀምበታለን ፡፡ ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር ናት ማለትና ፤ ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር ነበረች መካከል አሳፋሪና አስፈሪ ልዩነቶች አሉ በመካከላቸው ፡፡ በርግጥ የታሪክ ክሽፈትን ላለማየት ካልጨፈንን በስተቀር ታሪክማ ሊከሽፍ ይችላል ፡፡ ስለኢትዮጵያ ተማሪዎች ታሪክን እንመልከት ብለን ከ60ዎቹ ተነስተን በ2005ቹ ላይ ስናርፍ በፕሮፌሰር አገላለጽ ዳገት ላየ ቆመን ቁልቁል እየወረድን የመጣን ነው ሚመስለው … የ60ዎቹ ጩኸት ሀገራዊነትና ኢትዮጵያዊነት ሲሆን የ2005ቹ ደግሞ በቅርቡ እንዳየነው በመንደርተኝነት ጠቦ በድንጋይ ውርወራ ታጅቦ እናገኘዋለን ፡፡ ታዲያ ሰንሰለት ብለን የፈታነው ታሪክ ወይ ላልታል ወይ ተበጥስዋል ማለት ነው ፡፡ ይኸየ የክሽፈት ማሳያ ይመስለኛል ፡፡ የታሪክ መዝገብነት ለዛሬ ካልፈየደ መመዝገቡ ምን ጥቅም አለው ፡፡ ታሪክ ማለት ማንነት ነውና ማንነት ደሞ ከፍ ሊልም ዝቅ ሊልም ይችላል ፡፡
  ክሽፈት የለም የምንል ከሆነ የታሪክን ፍቺ በመዝገብ ብቻ ነው ማጠር ያለብን ሊያውም ከመጠነው ፡፡ ታሪክ ውለታ ነው የምንል ከሆነ ለውለታው ክፋይ ይጠበቃል ፤ ክፍያው ይቅር ብንል እንካን ውለታው ግን ዋጋ ሊኖረው ይገባል ማለት ነው …. ያ ውለታ የተባለው ነገር ለውጥ ካላመጣ ግን ያው ያ ታሪክ ….. (ምናልባት ሁሌ የምንዘክረው ውለታ ዳርድንበር ከማስከበር ጋር ብቻ ነው … ኩሩነት.. ኢትዮጵያዊነት … የምንላቸው ነገሮች ምናልባት ዳገቱን እየወረዱ ነው ።)
  ከጀግና ይልቅ ባንዳ ከተከበረ ፣ ከሀገራዊና ሕዝባዊነት ራዕይ ወጥተን ለግለሰብ ራዕይ አጎብዳጅ ከሆንን ፣ከኢትዮጵያዊነት ስሜት የመንደርተኝነት ስሜት ካየለብን ችግር አለ ማለት ነው ፡፡ ችግር ደሞ የክሽፈት መንደርደሪያ ነው ፡፡ ያም ሆኖ ፕሮፌሰር መስፍን ክሽፈቶቻችንን በአሳማኝ አገላለጽ ነግረውናል ብዬ አላስብም … ለዛም ይመስለኛል የዳኒ …..
  ፕሮፌሰር መስፍን ከመጽሐፋቸው ጀርባ ሽፋን ላይ ሞት ማለት ብለው የሞትን ትርጉም በዉብ ቃላት አስውበው ገጥመውልናል ፡፡ በርግጥ መሞቱን ላላወቀ ሙት ስለሞት መንገሩ መሞቱን እንዲረዳ ይጠቅመዋል ፡፡ ከሞት በተጨማሪ ስለ ትንሳኤ ቢነግሩን የተሻለ ነበር እላለሁ ፡፡ አሁን ትንሳኤ ነውና የሚያስፈልገን ፡፡ የከሸፈ ሁሉ እንደከሸፈ አይቀርምና ….. ሊቀርም ግን ይችላል ፡፡
  ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!!
  አለማየሁ ደንድር ከጎላ

  ReplyDelete
  Replies
  1. I strongly agree with your idea! Well explained!

   Delete
  2. የ60ዎቹ ጩኸት ሀገራዊነትና ኢትዮጵያዊነት ሲሆን.... የቀደመኝ ትውልድ - ባሳብ የሰከረ
   በተራማጅ ባህል- አናቱ የዞረ
   በኢቮልዩሽን ህግ- ጠበል እየጠጣ
   ፈጣሪን ለመግጠም- ወደ ትግል ወጣ፤. . .››
   ግጥም- ስብሐት ገብረ እግዚሐብሔር
   The absence of this first
   educated class of Ethiopians, which could have bridged the gap between tradition and modernity, was
   painfully felt in that generation.this result create an identity for itself, not being able to associate itself with
   thé old socio-cultural order of thé ancien régime or with thé encompassing valuesof Ethiopian culture. Part of this effort was a campaign against organized religion: Islam and Orthodox Ethiopian Christianity. But especially against thé latter,because it was so much identified with thé old
   leading elites of the country.

   This attack represented another, largely unsuccessful, assault on thé cultural fabric of Ethiopian society of that generation.This flouted any idea of continuity with the past and with positive aspects of
   Ethiopian cultural traditions. Any rôle for civil society and for the expression of. In thé period of Oie Revolution there was a tendency toward thé
   émergence of a culture of violence, both in rethorical form and in actual political
   practice. However, it did not become universal among thé population at large, as
   a way of life or as a normative frame of référence, because thé idea of legitimacy
   of the state élite and its policy was never accepted, and because thé population
   was still bound to other socio-cultural values. In thé end, by persistently violating
   central tenets of social life and culture the state went asunder: the violence in thé
   authoritarian-communist form of thé Derg and thé Mengistu-regime undermined
   its own structure and viability. As said, violence had produced more violence: thé
   rebel movements ultimately pushed back the army, assisted by thé refusai of soldiers and gênerais to fight a senseless cause for a disgraced régime.
   civil sentiments was denied as well.that generation was really far from real ethiopianism and created artificial identity!thats why your conclusion is wrong!

   Delete
 18. ምሁራን እውነትንና ፍትሕን መሰረት አድርገው ወዴትም ሳይወግኑ ሞገስ ያለው አስተያየትና ሃሳባቸውን ሲገልጹ እንዴት ደስ ይላሉ፡፡ እባካችሁ ምሁራን ስለዚህ መጽሐፍ ሐቅን ተመርኩዛችሁ አስተያየት በመስጠት እውነትንና እውቀትን አመላክቱን፡፡ አስተምሩን፡፡ ውዥንብሩን የሚያጠራ እውነት ላይ አድርሱን፡፡ የተናደደም ሆነ የተደሰተ፣ ያተረፈም ሆነ የከሰረ እንደፈለገ እየተነሳ እውነትንና ታሪክን እንዳያዛባ የዜግነት ግዴታችሁን መወጣት የሚገባችሁ ይመስለኛል፡፡ በሁሉም ነገር ላይ አስተያየት የመስጠቱን ተግባርና ሃላፊነት በአርቲስቶችና በልማታዊ ጋዜጠኞች ትከሻ ላይ መጣል ግፍ ይሆንባችሁዋል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. I agreed with your clear call!

   Delete
 19. weygud tarik malet endih naw leka??????????????

  ReplyDelete
 20. hagre ethiopia monge nesh telala
  yemotelesh kerto yegedelesh bela

  ReplyDelete
 21. Well said Alex, but it seems you've some sort of confusion, make it clear, it doesn't mean side with one of them, however make sure what you're arguing about and stand for it. Other wise a guy like me start saying," YE KESHEFE SEHUF..."

  ReplyDelete
 22. ሰው ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ያረጃል ፣ ይሞታል፡፡ ፕሮፌሰሩ 3ኛው ምዕራፍ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ ብዙ በጎ ጎን እንዳላቸው ሁሉ መጥፎ ገጽታም ይኖራቸዋል፡፡ በተለይም ሰው በእርጅናው ዘመን የሰከነ፣ የበረደ፣ በስሜት የማይጓዝበት ደረጃ ነው፡፡ ምክንያቱም ተፈጥሮ በራስዋ እንዲቀዘቅዝ፣ እንዲሰክን ስለምታደርግ ማለት ነው፡፡ እዚህ ጋር ግን ስንመለከተው ፕሮፌሰሩ ስሜታዊ የሆኑ ይመስለኛል፡፡ ተጠያቂ የሚያደርጉት 2ኛ እና 3ኛ ወገንን ነው፡፡ እሳቸውን ግን እንደባዳ እየቆጠሩት ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ታሪክ እንዲከሽፍ፣ እንዲቋረጥ ከሚያደርጉት ዋነኞቻችን ውስጥ ቁጥር አንዱ እራሳቸው ፕሮፌሰሩ ናቸው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ante/anchi gin gena behuletegnawu dereja lay eyaleh newu yekeshefkewu

   Delete
 23. "...በሀገር ቋንቋ አያቀርቡም..." what do you mean? You better have mentioned those books you are interested but written in local languages. If you are interested with information they published you can go for the translations, many books, which are very important have been published with 'language' you are interested in.Books written in Geaz has been translated to "ሀገር ቋንቋ" because they are very important. It is the duty of...

  ReplyDelete
 24. I don't think that the professor does not realize that history does not collapse. I do rather think that he gave metaphorical title to describe the downward spiral of our historical journey, until the Renaissance begin by the great leader Melese Zenawi.
  I don't agree with Daniel's conceptualization of the historians themselves as simple document organizers. Their work can influence the state formation and governace which may contribute to further failure of our nation. If history is a guide to our future, it only be so, if it is written objectively. Otherwise, I do agree with Daniel that the professors may have personal odds in addition to the normal scholarly view of an issue

  ReplyDelete
  Replies
  1. Do you mean the 'Renaissance'being aired by ETV while non existant in reality? I think that's a live example to the problem which is central to this discussion.

   Delete
  2. kikikiki
   bedarge zemen yedenekor bedarge amilak sil yinoral

   Delete
 25. ሁሉንም ተሳታፊዎች በጣም አመሰገናለሁ፡፡ እኔም በዚህ ዓይነት መድረክ ስሳተፍ ይህ የመጀመሪያየ ስለሆነና የታሪክ ትምህርት ግንዛቤየ በጣም ውስን ስለሆነ የመሰጠው አስተያየት ሚዛን ባይደፋ ወይም ሰዎችን ቢያስከፋ ካለመበሰል የመነጨ እንደሆነ እንደትገነዘቡለኝ አደራ እላለሁ፡፡
  በመጀመሪያ ዲ/ን ዳንኤል ይህን መጽሐፍ ደፍሮ በመተቸቱና ይህ የውይይት መድረክ እንዲከፈት በማድረጉ በጣም አመሰግነዋለሁ፡፡ ስለሆነም እንደሱ ዓይነት ሰዎች በብዛት እንዲኖሩ ማደረግ ሲገባን እና ሀሳቡን በሐሳብ ማሸነፍ ሲያቅተን ለምን ሀሳቡን አነሳህ ብሎ መዝለፉ ተገቢ አይመስለኝም፡፡ በነገራችን ላይ ለፕሮፌሰሩም የጠቀማቸው ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በክርክሩ የአንባቢው ቁጥር ስለሚጨምር ብዙ መጽሐፍ እንዲሸጥላቸው ስላደረገ፡፡ በርግጥ ምን ያህሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ኢንተርኔት ያያል የሚለው ገንዛቤ ውስጥ ገበቶ፡፡
  ሌላው ፕሮፌሰሩ ታሪከን ጽፈው ወይም ታሪክ ጸሐፍትን ወቅሰው ከሚያስተመሩን ታሪከን ራሳቸው ኑረው ቢያስተመሩን ምንኛ በታደልን፤ እሳቸውም በታደሉ ነበር፡፡ አገቱኒ ካሉት መጽሐፋቸው እንደጠቀሱት ከአጼ ኃ/ሥላሴ እስከ ምርጫ 97 (በቅንጅት) ድረስ በሁሉም መንግስታትና በተወሰኑ ፓርቲዎች ተዋናይ እንደንደነበሩና ሆኖም ከሁሉም ጋር ባለመስማማት በራሳቸው ፈቃድ እንዳፈነገጡ ነግረውናል፡፡ ምናለ መስማማትን እራሳቸው ኑረው ቢያስተምሩን፡፡ በዚሁ መጽሐፋቸው ሰላም በኃይል እንደማይመጣ ጥሩ አድርገው አስረድተውናል፡፡ ሆኖም ግን በደርግ ጊዜ ያለፍርድ ለተጨፈጨፉት 60 የንጉሱ ባለስልጣናትና ለንጉሱም እንደዚያ መሆን እሳቸው (ፕሮፌሰሩ) የተጣለባቸውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸው እና ይባስ ብለው እሳት እንደለኮሱ ፕሬዜዳንት መንግስቱ ትግላችን (ቁ1) በሚለው መጽሐፋቸው እሰቀምጠውታል፡፡ ሆኖም ግን ይህን ያስተባበሉበትን ጽሁፍ ኣላየሁም፡፡
  ስለዚህ ባለታሪኮቹንም ሆነ ታሪክ ጸሐፊዎቹን ከሚኮንኑ ይልቅ ከራሳቸው በመነሳት ይህን መልካም ነገር በማድረጌ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሆነ ነገር ለውጥ አምጥቻለሁ፤ ይህን ባለማድረጌ ደግሞ ይሄን አጥፍቻለሁ፡፡ ስለዚህ ከኔ መልካም ተሞክሮዎችና ስህተቶች ተማሩ ቢሉን ስንት ትልቅ ሰው ባፈሩ ነበር፡፡ ሆኖም ግን እስካሁን በጻፏቸው መጻህፍት ሁሉ እሳቸው ምንም ጥፋተኛ እንዳልሆኑ ነው፡፡ ጥፋተኛ ካልሆኑ ለምን እስካሁን በተሳተፉባቸው መድረኮች ሁሉ በአንዱ እንኳ እንዳልተሳካላቸው ግን….
  ለማንኛውም ትችትን ከራሱ ጀምሮ የሚያስተምረን አፍሩልን፤ በጥፋቱ ራሱን ተጠያቂ/መስዋዕተ አድርጎ የሚያቀርብ ስው አለበለዚያ ግን ታሪክ ሰሪውም ታሪክ ዘጋቢውም በምርቃና ከተነሳን ምርቃናው ሲጠፋ ተያይዘን መከሸፋችን በቅርቡ….

  ReplyDelete
  Replies
  1. I bought the book & I am reading after Daniel wrote on it. Thanks Daniel for informing us and others for ur comments, ewodachihualehu.

   Delete
 26. ከጀግና ይልቅ ባንዳ ከተከበረ ፣ ከሀገራዊና ሕዝባዊነት ራዕይ ወጥተን ለግለሰብ ራዕይ አጎብዳጅ ከሆንን ፣ከኢትዮጵያዊነት ስሜት የመንደርተኝነት ስሜት ካየለብን ችግር አለ ማለት ነው ፡፡ ችግር ደሞ የክሽፈት መንደርደሪያ ነው ፡፡ ያም ሆኖ ፕሮፌሰር መስፍን ክሽፈቶቻችንን በአሳማኝ አገላለጽ ነግረውናል ብዬ አላስብም … ለዛም ይመስለኛል የዳኒ …..
  ፕሮፌሰር መስፍን ከመጽሐፋቸው ጀርባ ሽፋን ላይ ሞት ማለት ብለው የሞትን ትርጉም በዉብ ቃላት አስውበው ገጥመውልናል ፡፡ በርግጥ መሞቱን ላላወቀ ሙት ስለሞት መንገሩ መሞቱን እንዲረዳ ይጠቅመዋል ፡፡ ከሞት በተጨማሪ ስለ ትንሳኤ ቢነግሩን የተሻለ ነበር እላለሁ ፡፡ አሁን ትንሳኤ ነውና የሚያስፈልገን

  ReplyDelete
 27. The book shows the dark sides of us that are stopping us to move forward. It trys to depicts almost all perspectives and educate us. Getting knowledge by itself is defeating dark side. I was fearful when I don't know something, but I am fearless when I know. I found hope in the truth.
  Know about the world, and let people know.

  May Our Father protect all of us.

  ReplyDelete
 28. This Book is very important. It tells us how the Ethiopianism, Ethiopian identiy and history have been defeated due to the Albanian-minded Communist TPLF Ideology.That is all about.

  ReplyDelete
 29. ታሪክ የሚከሽፈው የባለ ታሪኩ ውድቀቱም ሆነ ስኬቱ በትክክል ሳይዘገብ፣ ሳይተረጎም ሲቀር ነውና፡፡

  ReplyDelete
 30. “በትክክል ባላውቅም በግምት እንደ ኢትዮጵያ አርበኞቹን የገደለ አገር በአለም ላይ ያለ አይመስለኝም፡፡ እነ በላይ ዘለቀ፣ አበበ አረጋይ፣ ራስ ስለሺን እና ስንትና ስንት አርበኞች ገለናል” የሚሉን መስፍን ወልደማርያም፤ “ባንዳን እያደነቁና እያከበሩ አርበኞችን እየናቁ ለአደጉ ትውልዶች አዘንሁ፤ ለኢትዮጵያ አዘንሁ፤ ስለዚህም የአሁኑ ባንዳ አክባሪ ትውልድ በአጥንት ላይ መቆሙን እንዲገነዘብ ለማድረግ ፎቶግራፎች ትንሽ ይረዳሉ ብዬ አሰብኩ” በማለት በመጽሐፉ መጨረሻ ገፆች ላይ የጣሊያን ወታደሮች በኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሱትን ስቃይ የሚያሳይ ፎቶግራፍ የማስቀመጣቸውን ምክንያት ይገልፃሉ፡፡ መግለፃቸው ባልከፋ “የአሁኑ ባንዳ አክባሪ ትውልድ” የሚለው አገላለጽ ግን ምን ለማለት ተፈልጐ እንደገባ ቢያንስ ለኔ ግልጽ አይደለም፡፡ ሌላው ቢቀር ለበላይ ዘለቀ ከዚህ ትውልድ በላይ የዘፈነለት፣ ውዳሴ ያጐረፈለት፣ ቅኔ የተቀኘለት እና የተወነለት ትውልድ ያለ አይመስለኝም፡፡ ከሸሹበት ሀገረ እንግሊዝ ተመልሰው በላይ ዘለቀን የሰቀሉት ኃ/ሥላሴ “ግርማዊነትዎ” እየተባሉ ለምን ይወደሳሉ የሚል ጥያቄ ቢሆን የተነሳው ክርክር ሊገባን ይችላል፤ ነገር ግን እዛው እነ በላይን ገደልን በሚሉበት አንቀጽ ላይ ለኃ/ሥላሴ ሀውልት እንዳይሰራ ነፈግናቸው በማለት ለገዳዩም ለተገዳዩም ጥብቅና ሲቆሙ እናገኛቸዋለን፡፡ በዚህ ሰዓት የአሁኑ ባንዳ አክባሪ ትውልድ የት እንዳለ ይጠፋብናል፡፡ ....“በምንኖርበት ዘመንም ቢሆንም የኢትዮጵያን ውድቀት ለመረዳት ብዙም ጊዜ አይፈጅም፡፡ የትልቅነትና ታሪካዊ ምልክቶች ሁሉ ደብዛቸው እንዲጠፋ እየተደረገ ነው፡፡ የብሔራዊ መዝሙሩ ሁለት ጊዜ ተለውጧል፡፡ በሰንደቅ አላማው በአየር መንገዱ፣ በቴሌ የአንበሳ ምልክት እየተነቀለ ተጥሏል” በማለት ቁጭታቸውን ይገልፃሉ፡፡
  መቼም አንድ በዚህ ዘመን የሚኖር የሰለጠነ ዕውቀት ያለው ኢትዮጵያዊ፤ “የሁሉ ነገራችን መሠረት ንጉሳችን ነው” የሚል መዝሙር ለምን ተቀየረ ብሎ የሚቆጭ አይመስለኝ፡፡
  “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ሀይል በንጉስሽ” ብሎ ጀምሮ “ድል አድራጊው ንጉሳችን ይኑርልን ለክብራችን” የሚለውን መዝሙር የአሁኑ “ባንዳ አምላኪ ትውልድ” መወቀስ ካለበት መዝሙሩን ባይቀይረው ኖሮ እንጂ በመቀየሩማ ሊወደስ ነው የሚገባው፡፡

  ባንዲራዉ ላይ የነበረው ዘውድ የጫነ አንበሳስ ግልፅ አይደለም፡፡ አንበሳው እኮ ዘውድ ብቻ አይደለም ጭኖ የሚታየው በአንዱ እጁ የጨበጠው መስቀልም ጭምር እንጂ፡፡ ሙስሊሙ እና ክርስቲያን ያልሆነው ወገናችን የማይከበርበት ግርማ እንዴት ነው የኢትዮጵያዊነት ግርማ እየተነቀለ ተጣለ ሊባል የሚችለው?
  የመስፍን ወልደማርያም ያለፈውን ዘመን መናፈቅ እና የአሁኑን ዘመን የመርገም አባዜ በዚህ ቢያበቃ ጥሩ፡፡
  በአንዱ በኩል ባንዳዎችን አከበረ የሚሉት የኃ/ሥላሴ ስርዓት፤ በሌላ በኩል አሁን ካለው ትውልድና ሥርዓት የተሻለ እንደሆነ ለማሳመን ያቀረቡት ምክንያት የእውቀት ነው ወይስ የጤና ችግር ብዬ እንድጠይቅ አስገድዶኛል፡፡ በጭፍን ጥላቻ እና በከረረ ንዴት የተዋጠ ሰው፣ ጤናማ አመለካከቱ ጥያቄ ውስጥ መግባቱ አይቀሬ መሆኑ መቼም አይካድም፡፡

  የሚከተለውን ማብራሪያ ስትመለከቱ እንደኔ እጅግ መደንገጣችሁ እና መገረማችሁ አይቀርም የሚል እምነት አለኝ፡፡ “በስንት ዘመናት ጥራትና በሰለጠነ የሰው ሀይል የተገነቡና የአገር ኩራት የነበሩ መስሪያ ቤቶች ተንኮታኩተዋል፡፡ ያሉትም ቢያንስ ሠላሳና አርባ ዓመት ወደኋላ ተመልሰዋል ወይም ጭራሹኑ ጠፍተዋል፤ ሆነ ተብሎ በስልት ከተዳከሙት ውስጥ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርስቲ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ይገኙበታል። እነዚህ ሁሉ በመክሸፍ ላይ የሚገኙ ናቸው” በማለት እጅግ በጣም ድፍረት የተሞላበት ትንታኔ ይሰጣሉ፡፡

  እየተስፋፉ ያሉትን ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ጥራት ጥያቄ በይደር እናቆየውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቴሌ እና መብራት ኃይል በምን አይነት አዕምሮ ነው ወደ ኋላ ሠላሳና አርባ አመት ተመልሰዋል ሊባሉ የሚችሉት፡፡ ልብ በሉ መስፍን ወደ ኋላ ተመልሰዋል ብቻ አይደለም የሚሉት “ጭራሽኑ ጠፍተዋል” ነው ያሉት፡፡ ይህን ጊዜ ነው የከሸፈው የመስፍን አስተሳሰብ ወይስ የኢትዮጵያ እውነት ብለን ለመጠየቅ የምገደደው፡፡
  ...Written by አማኑኤል መሓሪ...http://www.addisadmassnews.com/

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yebanda amlaki tiwlid malet mechem tirgumu saygebach qerto aymesldgnim.
   Kalgebah endante yalewun woyanena melesin amlaki zega malet new.
   Banda ahunim negem yiwdem.

   Delete
  2. Dear Godana, you must be from godana. sidibina fukera le professor mesfinim alteqemem. betilacha amiliko atiqeyed. daniel and amanel yetsafuachew negeroch bizu teqami frie alachew, beteley lendante yale bechifin tilacha leminegud.

   Delete
  3. ፕሮፌሰር ስለቴሌና የመሳሰስሉት ተቋማት የገለጹት ልክ ነው። ከሞባይል ዘመን በፊት በአፍሪካ ከነበሩት አስተማማኝ የስልክ ኩባንያዎች አንዱ የኢትዮጵያው ነበር፤ ዛሬ ግን ጭራ ሆኗል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማፈሪያ ሆኗል። እዚህ ላይ እኔ ያነበብኩት ቁጭትን እንጅ ጥላቻን አይደለም።

   ይልቅስ በአማኑኤል የተሰጠው አስተያየት ሰውዬውን በሰበብ አስባቡ መውቀስና መስደብ የማይሰለቻቸው ሰዎች ሃሳብ ሆኖ የታየኝ።

   ዳንዔል መጽሐፉን ያየበት ሁኔታ ግን ደስ ብሎኛል። ጥሩ ውይይትን የሚጋብዝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

   Delete
  4. አማኑኤል መሓሪ
   agatamiwu temechegni bileh lemesadeb newu enji min lemalet endehon yetefah ayimesilegni

   keshim woyane

   Delete
 31. ምናልባት ከላይ ስለ መክሸፍ ሌላ ማብራርያ የሰጠው ልጅ/2ተኛው ኮሜንት/ ልክ ከሆነ እና መክሸፍ ማለት ታሪክን በአግባቡ ተረድቶ ለጥቅም ማዋል ከሆነ ታሪክ ጸሃፊዎች መወቀሳቸው ልክ አይሆንም ትላላችሁ? ታሪክ ጸሃፊዎቹ ይህን "ግዴታቸውን አልተወጡምና"!!/እንደ ፕሮፌሰሩ አባባል

  ReplyDelete
 32. ለመሆኑ፣ የአገራችን ምሑራን ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ዘላቂ የሆነ ምን ማሕበራዊ አስተዋጽኦ ወይም መፍትሔ አስገኝተዋል? በመደብና በጎሣ ሕዝቡን ከፋፍለው አለመተማመንን ዘርተውበታል። ያውቃሉ የተባሉት እርስ በርስ መስማማት ሆነ መከባበር ተስኖአቸዋል። አገሪቷን ወዴት መምራት እንደሚገባቸው ገና እርግጠኞች አይደሉም፤ የሌሎችን አሳብ ለመስማት አይፈቅዱም። የጋራ በሆነች አገር፣ ያልተስማማቸውን የማግለልና የማውገዝ ባሕል ተጠናውቶአቸዋል። ይህንና ያን ሲሉ ስንት ትውልድ ፈጁ ። የቀደመኝ ትውልድ - ባሳብ የሰከረ
  በተራማጅ ባህል- አናቱ የዞረ
  በኢቮልዩሽን ህግ- ጠበል እየጠጣ
  ፈጣሪን ለመግጠም- ወደ ትግል ወጣ፤. . .››

  ReplyDelete
 33. እንደዚህ አይነት አእምሮን የሚፈትኑ : በቁጭትና በእልህ ዉስጥን የሚያጋዩ መጽሀፍት ቢነበቡ መልካም ነዉ:: በተለይም ሀሳብ የመልዋወጥ ባህላችንን ቁንጽልነት በስፋት የበረበሩት ምሁር አንድ ወሳኝ ነጥብ አስቀምጠዋል:: እርስ በእርስ ካልተሙዋገትን እና ሀሳብ ላሳብ ካለተሞራረድን ኢትዮጵያ አሁንም ለብዙ ሽህ አመታት ልታንቀላፋ ትችላለች:: የማንኛዉም ብልጽግና ስሩ ሀሳብ ነዉ::

  ሀሳብም በሙግት ይዳብራል ሲሉ አጥብቀው የሚሞግቱት ምሁር ያለብንን ቁልፍ የባህል ድህነት አግኝተዉታል:: የሰከነ የሀሳብ ፍጭትና ሙግት በእጅጉ የራቀዉ ማህበረሰብ በመሆናችን ቁልቁል እንጅ አቀብ ማለት ሳንችል ቀረን ሲሉ በመረጃና በማስረጃ እያፍታቱ ያቀርባሉ::

  ይህ ማለት ግን በሁሉም ሀሳባቸው ያሳምኑሃል ማለት አይደለም:: ከእርሳቸዉ እይታ ጋር ያልተስማማሁባቸዉም ነጥቦች አጋጥመዉኛል:: መጽሃፉ ግን ዉስጤን አናዉጦታል:: አስደንግጦታልም:: የምሁሩም የብስለት ምጥቀት ምን ያህል እየተራቀቀ እንድመጣ ማዬት ይቻላል::

  አንድ ሰዉ ይህን የፕሮፌሰር መስፍንን መጽህፍ አንብቦ ሲጨርስ በእርግጠኝነት ስለ ሀገሩም ሆን ስለራሱ የሚያራምደዉን ያልጠራ ሃሳብ ደጋግሞ ሊመርምር ይነሳል:: አንድ መጽህፍ ደግሞ ከዚህ በላይ ግብ የለዉም::

  ReplyDelete
 34. ፕ/ር መስፍን በቅርቡ በጻፉት መጽሃፍ ዙርያ ዳንኤል ክብረት አስተያየት ሰጥቶ ነበር። ከአስተያየቱ ጭዋነት የተሞላበት ነቀፌታ እና ሂስ ቢኖርም በደምብ ደፈር ብሎ ሃሳቡን ገልጿል ለማለት ይከብዳል። እንዲያውም ፈራ ተባ እያለና በአሽሙር መሳይ እየጠቆመ የተወው ይበዛል። ይህም ሁኖ ጽሁፉ ፕ/ሩን አበሳጭቷቸዋል እና መልስ ሰጥተዋል።
  እርግጥ ፕ/ሩ ለዳንኤል የሰጡት ምላሽ ስድብ ይበዛበታል። ስድቡም ስድስተኛው ተራ ቁጥር ላይ ካነሱት ነጥብ ጋር የተያያዘ መሆኑ ግልጽ ነው። ቢያንስ ከዚያ ውጭ ባሉት ነጥቦች ሃሳብን በሃሳብ መመለስ ሲገባቸው ደጋግመው መሳደባቸው የአመል ሆኖባቸው እንጂ በስድስተኛ ነጥብ የጠቀሱት ይበቃ ነበር። እዚያም ላይ ፕ/ሩንና መንግስቱ ሃይለማርያምን የሚያገናኝ ጉዳይ ሲጠቁም የሰዎች ስም ሳይጠቅስ በገደምዳሜና ባሽሙር ጽሁፉን መደምደሙ አበሳጭቷቸዋል። እሱም የደብተራ ተንኮል ሸብቦት እንጂ ዘርዝሮ ለመጻፍ መረጃ አንሶት ወይም አቅሙ ገድቦት አይደለም። እዚያ ላይ መነቀፉ ተገቢ ነው። ይህ ማለት ግን ታሪኩ ውሸት ነው ማለት አይደለም። ፕ/ሩ እዚህ ላይ ግልጽ መሆን አለባቸው። ለምሳሌ የተፈራሩበት(በደብተራኛ ብቻ እየተነቋቆሩ) ያለፉት ሚስጥር እንዲህ እናብራራው፦
  1. መልክ የሌለው፣ ስም የሌለው “እኒህ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዶክተር...” የተባለው ሰው ነብስ ይማርና ሟቹ ዶክተር ብርሃኑ አበበ ናቸው።
  2. ዳንኤል ጽሁፍ ላይ መንግስቱ ሃይለማርያም ፕ/ር ታደሰ ታምራትን ቤተመንግስት ጠርቶ‹ከዶክተር እገሌ ጋር ቅሬታ አላችሁ መሰል፤ አንዳንድ ነገር ነግሮኝ ነበር፤ እዚያው ተነጋግራችሁ ፍቱት፤ አላቸው፤›.... በሚለው ዓረፍተነገር “ዶክተር እገሌ” የተባሉት ራሳቸው ፕ/ር መስፍን ናቸው። እሳቸውም ይህንን አላጡትምና የተናደዱትም ለዚህ ነው።
  3. ...‹‹አሁን እዚህ መጽሐፍ ላይ ቤተ መንግሥቱን አየሁት፡፡›› ምን እንዳየ፣ የት እንዳየ፣ ምንና ምን እንደተገናኘ የደብተራ ምስጢር ነው፤ ያቀረበውን ሁሉ የማን ባለሙዋል ሆኖ ያገኘው እንደሆነም አይናገርም... ሲሉ ዳንኤልን ያብጠለጠሉበት ነጥብ ላይም ዳንኤል በማህበረ ቅዱሳን በኩል የደብተራዎች ማአከል ወደሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ታሪክ ትምህርት ክፍል እንደተጠጋ፣ ተነቃፊዎቹን የታሪክ ባለሙያዎች በተለይም ፕ/ር ታደሰ ታምራትን ወክሎ እንደጻፈ፣ መረጃ ያገኘውም የሺፈራው በቀለ “ባለሙዋል” ሁኖ እንደሆነም ግልጽ ነው።
  4. በደርግ ዘመን እነዚህ ምሁራን ማለትም ፕ/ር መስፍን፣ ፕ/ር ታደሰ፣ ዶክተር ብርሃኑ አበበ እና ሺፈራው በቀለ ቤተመንግስት ውስጥ ምልልስ አዘውታሪዎችና አማካሪዎች ነበሩ። በተናጠልም በጋራም መንግስቱ ሃይለማርያም ጋር ይገናኙ እንደነበር ለማያውቅ በቅርቡ የታተመው የኮሎኔል መንግስቱ መጽሀፍ (ትግላችን ገጽ 4‐5) መመልከት ነገሩን ግልጽ ያደርጋል። ይህ ሲጠቀስ ፕሮፌሰር ለምን እንደተቆጡና ዳንኤልም ለምን በዝርዝር መግለጽ እንዳልፈለገ መቼስ ይገባችኋል። ሁሉም ተጠያቂነትን ይፈራሉ።
  እነዚህ ነጥቦች ግልጽ ስለሆኑ ፕ/ር መስፍን የሚጠበቅባቸው መናደድና መሳደብ ሳይሆን ስለራሳቸውም ስለ ነዚህ ሰዎችም እውነቱን መናገር ብቻ ነው። አገርንና ትውልድን ክሽፍ ብሎ ከመሳደብ ይልቅ በቅርብ ስላለ ትንሽ ነገርም እውነት መናገር እጅግ ይሻላል። እውነት ከቅርብ ይጀምራል፤ ምሁርነትም ራስን ከመንቀፍ ይጀምራል! ፕሮፍ ስለራሳቸውም እቅጯን ነግረው ያስተምሩን እንጂ በስድብና በርግማን አይሸውዱን። የቋንቋቸው ማማር የጽሁፋቸውን ይዘት አሳማኝ አያደርግም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔም ዳንኤል በዝርዝር መግለጽ ያልፈለገዉ ነገር እንዳለ ገብቶኛ - ጽሁፉን ሳነብ፡፡ ስለገለጡልን ምስጢር አመሰግናለሁ፡፡ ነገር ግን “ደብተራ” የሚለዉን “ታፔላ” ለመለጠፍ በመፍጠንዎ እርስዎ ከሰነዘሩት ትችት እንዳያመልጡ ያደርገዎታል፡፡ ስለነገሩን ጥቂት ተጨማሪ ማብራሪያ ደግሞ በዘመኑ ላልነበሩ ወጣቶች (እኔን ጨምሮ) በእዉነትና በግለጽ ቋንቋ ቢነግሩን ምንኛ ደግ ባደረጉ፡፡ እዉነትን የተራብን ልጆች ያፈራች አገር ዉሥጥ የምኖር የሀሰተኞች ሰለባ ነኝና እውነት ሊኖር ይችላል ብዬ በጠረጠርኩበት ሁሉ መባዘኔ መቼም አያስደንቅም እና እንደማይፈርዱብኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

   Delete
  2. በጣም የሚገርመው የዳንኤል ክብረትን ጽሁፎች በሙሉ በደብተራኛ እንዲሁም የፐሮፌሰሩን መመደብህ ነው ለመሆኑ ደብተራኛ ምን ማለት ነው አነተስ በምንኛ ነው እነሱን ለመኄስ የተጠቀምክበት አፃፃፍ …ዎያኔኛ…. እንበለው አንድን ጸሃፊ ለጻፈው ጽሁፍ ተገቢዉን ምላሽ መስጠጥ ሚቻለው መጀመሪያ የጻፈውን ጽሁፍ በደንብ ከተረዳን በኋላ ቢሆን መልካም ነው ፡፡ ስብሰባ ላይ የደሰኮርከውን ደብተራ ቃል መልሰህ እኛላይ አትደስኩር ስለምታውቀው ነገር ጸፍ ስላሰብከው ነገር ዎይም ይሆናል ብለህ ስለገመትከው ሳይሆን ወንድሜ ደብተራን የምትረዳበት ራስም ይኑርህ ትርጉሙን እዎቀው !!!!በጣም የሚገርመው የዳንኤል ክብረትን ጽሁፎች በሙሉ በደብተራኛ እንዲሁም የፐሮፌሰሩን መመደብህ ነው ለመሆኑ ደብተራኛ ምን ማለት ነው አነተስ በምንኛ ነው እነሱን ለመኄስ የተጠቀምክበት አፃፃፍ …ዎያኔኛ…. እንበለው አንድን ጸሃፊ ለጻፈው ጽሁፍ ተገቢዉን ምላሽ መስጠጥ ሚቻለው መጀመሪያ የጻፈውን ጽሁፍ በደንብ ከተረዳን በኋላ ቢሆን መልካም ነው ፡፡ ስብሰባ ላይ የደሰኮርከውን ደብተራ ቃል መልሰህ እኛላይ አትደስኩር ስለምታውቀው ነገር ጸፍ ስላሰብከው ነገር ዎይም ይሆናል ብለህ ስለገመትከው ሳይሆን ወንድሜ ደብተራን የምትረዳበት ራስም ይኑርህ ትርጉሙን እዎቀው !!!!

   Delete
 35. HEY PEROFESSOR MESFIN IS NO LONGER WITH ABLE MIND. I THINK HE IS LIVING OUT OF HUMAN WITH NO BENEFICIAL PROFESSORSHIP IN HIS ENTIRE LIFE. ZENAWI GAMBLED ON HIM AND NO LONGER CAN FORWARD HEALTHY WORDS AS NORMAL AGED MAN. HE IS VIRTUALLY DEAD ALIVE. I RECOMMEND DANIEL AND OTHERS AS WELL TO REFRAIN FROM HAVING ANY KIND OF RAPPORT/DIALOGUE/DISCUSSION ETC WITH CRAZY AGED PPL. NO LONGER I AM INTERESTED TO LEARN FROM THOSE.............

  ReplyDelete
 36. Pls Dani,
  Did you see the Prof. "answer" insult...
  I dont want you to write any thing about that insult. AYIMETINIHIM seriously. You are doing the write thing, I always learn from you.
  "there is one saying '' YEMOTEN WUSHA YEMIDEBEDIB YELEM"

  ReplyDelete
 37. በእርግጥ ትልቅ ሰውን ማክበር ተገቢ ነው፡፡በተለይ እንደ መስፍን የቀለም ቀንድ…….!ፕሮፌሰሩ ግን እድሜም ተጫናቸው ብዙዎችም ሙገሳና አንቱታ አበዙባቸው መሰለኝ እሳቸውም ወሬያቸውም ጃጁ፡፡እነዳበዙት ዳኒ እንኳን ነገርካቸው!እሳቸውን የሚደፍር ባህል ስለሌለን ትውልዱን ሃሞተቢስ ታሪካችንን የክሽፈት ብቻ አድርገው ሞራላችንን አድቅቀው ራሳቸውን ብቻ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ አድርገው ያስቀሩ ነበር፡፡አሁን ግን አንተ እንኳን ጀመርክ እንጂ ሁሉም የተሰማውን መናገሩ አይቀርም፡፡እሳቸውን ግን በእድሜያቸው አፋፍ ስላሉ ለንስሃ ሞት ያብቃልን፡፡ከመንግስታት ጋር ሲጣሉ እንደኖሩ ከላይኛውም መንግስት ጋርም ለዘላለም ተቆራርጠው እንዳይቀሩ!

  ReplyDelete
 38. የታሪክ ጸሀፍት ታሪክን በስነ ሥርዓት ካልፃፉት ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉምን?

  ReplyDelete
 39. thank you all for your different view and your help to show as the idea in different way.

  ReplyDelete
 40. I appreciate Professor Mesfin Wariam's passion to vent his views freely; but mere expression of views is not an end in itself. Especially, this is true for a leader (spiritual or political). His success or failure cannot be measured by this, rather we have to look into his proven capabilities to stick into his truth, formulate it into a practically achievable goal, mobilise followers around his objectives, apply winning strategies and tactics, as well as stay along his path with discipline, consistency, commitment, sacrifice etc... And, of course, bring it into success. But Prof. Mesfin is consistently inconsistent in all these matters; and as we are living witnesses to most of his words (written and spoken) and actions, he is just a megalomaniac public figure who is truly in love with himself. That is why his world view is criticized by his close aides and colleagues as borderline insanity and nihilism. In this regard, he is a monument of failure (Yekisara Hault). May I say Good riddance!
  Having said this, I recommend everyone to read professor Mesfin’s article written to discredit Deacon Daniel Kibret, who reviewed the recently published book authored by the Professor. Not only is Mesfin’s reply a telling illustration of his ego-centric character, but also the numerous comments from viewers demonstrate how Prof. Mesfin has even embarrassed his staunchest admirers. Anyways, here is the link: http://www.mesfinwoldemariam.wordpress.com/

  ReplyDelete
 41. እኛ ኢትዮጵያውያን አንዱ ትልቅ መሰረታዊ ችግራችን በታላቅነት ውስጥ ደካማነት እናዳለ እንደዚሁም በደካማነት ውስጥም ታላቅነት እንዳለ አለመረዳታችን ነው፡፡በሰከነ ስሜትና አስተሳሰብ ውስጥ ሆነው ታላላቅ ስራንና ታሪክን የሰሩልንን እነዚህኑ ሰዎች በተቃራኒው ባለው በተረበሸ ስሜትና አስተሳሰብም ውስጥ ሆነው ከበስጭት የመነጨ ብሶታቸውንና ንዴታቸውን ጭምር ለመስማት ዝግጁነት የለንም፡፡ኢትዮጵያውያን ብዙ መልካም ስራ የሰሩልንን ታላላቅ ሰዎቻችንን ብዙውን ጊዜ ክብረ ቢስ አድርገን በስተመጨረሻ የምናዋርድበት አንዱ ከዚህ በመነጨ ነው፡፡ጠቢብ ሰው ከስድብ ምክርን ያወጣል እንዲል ቅዱስ መፅሀፍ የእኔ እይታ ከፕሮፌሰሩ ስድብና ብስጭት ውስጥ ጠቃሚውን መልካም ነገርን እንዴት አጣርቼ ለመረዳት ለማውጣትና ለመጠቀም እችላለሁኝ የሚለውን ነው የማስበው፡፡አሁን ያለነው አብዛኛች ኢትዮጵያውያን በማስመሰል አባዜ(Pretence) ተጨፍድደን የተያዝን ነን፡፡ከዚህ የተነሳም የተለመደውን Comfortable Social Consensus የሚፈጥር በይሉኝታ የታጠረና በአብዛኛው ለስሜታችንና አስተሳሰባችን የሚመቸንን የማይረብሽ አስተሳሰቦችን ከመስማት በዘለለ በተቃራኒው ለስሜታችንና አስተሳሰባችን የማይመችና የሚቆረቁረውን ለመስማት ብዙም ፈቃደኝነት የለንም፡፡ከዚህ በመነጨም ባብዛኛው ከንቱ ውዳሴን እንጂ ተግሳፃዊ ስድብን ለመስማት ፈቃደኝነትም ሆነ ዝግጁነት የለንም፡፡እንደዚሁም ኢትዮጵያውያን ባብዛኛው የተወሰነ የህፃንነት አይነት ባህሪ ጭምር ስለሚያጠቃን ጠንከር ያለ የሃሳብ ጭፍት ያለበትን አስተሳሰብንና ተግሳፃዊ ስድብን ስንሰማ ልክ እንደ ህፃን ልጅ በቶሎ እንደነብራለን እንበረግጋለን እናኮርፋለን፡፡አብዛኛውን ጊዜ እይታችን ጫፍና ጫፍ በረገጠ በነጭና በጥቁር የተሳለ ነው፡፡ልጅን ሲወዱ ከነንፍጡ ከነለሃጩ እንዲሉ ግን ምናለ የፕሮፌሰሩን ብስጭትም ጭምር ብናዳምጥ?ነው ወይንስ ፕሮፌሰሩም እንደ ዳንኤል ክብረት ሃሳባቸውንና ስሜታቸውን የግድ በተረት ተረት እያዋዙ መግለፅ ነበረባቸው?እንኳንስ ደካማ ስጋ የለበሰ ተራው የሰው ልጅ አይደለም ሰው የሆነው አምላክ እየሱስ ክረስቶስ ጭምር ቤቴ(ቤቴ መቅደሴ) የፀሎት ቤት ተብሎ ይጠራል እናንተ ግን ንግድ የመነገጃ የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት በማለት ለቤቱና ለመለኮታዊ ክብሩ ያለውን ቅንአት ለመግለፅ ሲል ቤቱን የተዳፈሩትን የዘመኑ ነጋዴዎች በጅራፍ ጭምር እያባረረ ተቃውሞውን በንዴት ጭምር ምላሽ ሰጥቶ ነበር፡፡ፀጋዬ ይበቃሃልና ሃይሌ በድካምህ ይገለጣል የተባለለት ሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም የአብያተ-ክርስቲያናት ነገር እንዳበደ ሰው ያናግረኛል ብሎ ነበር፡፡ሰዎች ለአንድ ላመንበት ነገር የተወሰነ ስር የሰደደ ጤናማ የሆነ ስሜትና ቃናኢነት ከሌለን በስተቀር ላመንበት ነገር በፅናትና በታማኝነት ለመቆምና መስዋእት ለመሆን አንችልም፡፡ፕሮፌሰሩም በመግቢያቸው ላይ ይህንን መፅሀፍ ስሜት ኖሮት የማይናደድ የማይቆጭ ሰው አያንበው ያሉት ከዚህ በመነጨ ይመስለኛል፡፡አዎ ከላይ በመጀመሪያው አስተያየቴ ላይ የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት የአንድ ዘመናዊ ካፍቴሪያ ወይንም ዘመናዊ መዝናኛ ወይንም የአንድ የውጪ ሀገር ሰለብሪቲ ያህል ክብርና ዋጋ የማይሰጥ አዲስ ዘመነኛ ትውልድ የታሪክና የታሪክ ክሽፈት ጥልቅና ሰፊ ትርጉምና ፋይዳ ምን እንደሆነ ያን ያህል አይገባውም፡፡አዎ ታሪክ ሲከሽፍም አዲሱ ትውልድ በአባቶቹ ላይ እንዲህ እያለ ሊያሾፍ ይችላል፡፡አባባ ምን ነካህ ሃወልት እኮ በቃ ዝም ብሎ አንድ የቆመ ግኡዝ ነገር ነው ስለዚህም ልማት እስከሆነ ድረስ ሃውልቶች ፈርሰው ዘመናዊ መንገድ ቢሰራባቸው የትራንስፖርት ችግር ይፈታል ሀገራችንም የሰለጠነች ትሆናለች የሚል ይሆናል፡፡አዎ ለዚህ አይነት ትውልድም የአባቶች ብስጭት ምንም ትርጉምና ፋይዳ የለውም፡፡የእነ ፕሮፌሰርም አይነት በታሪክ ክሽፈት ላይ ያነጣጠረ ብስጭታዊ መፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ ከሰነፍ ሰው ጋር ነገር አታብዛ ብትቆጣውም መልሶ ወይ ይስቅብሃል ወይንም ይቆጣብሃል እንዲሉ አይነት ይመስላል፡፡እንደሚታወቀው በእድሜ የገፉ ሰዎች ይህችን አለም ከመሰናበታቸው በፊት ውስጣቸው ያለውን የተከማቸ እውቀትና የህይወት ተሞክሮ(ቁጭትና ብስጭትንም ጭምር) ለተተኪ ትውልድ ማጋራት ይፈልጋሉ፡፡እንዲያውም ሰዎች ከ40 ዓመት በኋላ ስለራሳቸው ሳይሆን ስለሌሎችና ስለማህበረሰቡ ይበልጥ ማሰብና መጨነቅ የሚጀምሩበት እንደሆነ የስነ-ልቦና ጠበብት ይናገራሉ፡፡ቻይናዎች “Give Intelligent treatment in response to unintelligent treatment” እንዲሉ ሂስና መተቻቸት ያለ እንደሆነ አምነን ነገር ግን ይህንን የሃሳብ ልዩነታችንን የምናቀርብበት አካሄድና ስሜት ግን የሰውን ልጅ ውስጣዊ ውስብስብና ጥልቅ ስሜቶችንና አስተሳሰቦችን ለመረዳት የሚችል ስነ ስርዓት ያለው ሊሆን ይገባል፡፡ስለዚህም ፕሮፌሰሩ ለምን እስከዚህ እርቀት ድረስ ሄደው የታሪክ ክሽፈት የሚል መደምደሚያ አርእስትና እሳቤ ያለው መፅሀፍ የፃፉት በሀገራቸው አጠቃላይ የታሪክ ጉዞና በወጡበት ማህበረሰባቸው ላይ ከምን የመነጨ የዜግነትና የሰብዓዊነት ቅሬታ(Resentment and Desperation) አድሮባቸው እንደሆነ በትእግስትና በማስተዋል በጥሞና ልንረዳቸው ይገባል የሚል እይታ አለኝ፡፡ከፍተኛ የትውልድ ክፍተት (Generational Gap)ከተፈጠረ በራሱ የታሪክ ክሽፈት ነው፡፡ማለትም አዲሱ የቆየውን የቆየውም አዲሱን ትውልድ በቅጡ ለማክበርና ለመረዳት ካልቻለ ማለት ነው፡፡አዲሱ ትውልድ መረጃን በጊጋ ባይት የሚለካ ሲሆን አሮጌው ትውልድ ግን መሬትን በጋሻ የሚለካ ነው አይነት የአስተሳሰብ ደረጃው እጅግ የወረደ ጥራዝ ነጠቅ እይታ የትም አያደርሰንም፡፡ደግሞስ ጠቢቡ ሰለሞን እንዳለው ከፀሃይ በታች ምን አዲስ ነገር አለ፡፡ሁሉም ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው ነፋስንም እንደመከተል ነው ያለው ያ የጥንቱ ጠቢብ ሰው ከየትኛው ትውልድ ይሆንን?ግን ለመሆኑ መፅሀፍ ቅዱስ በራሱ ታሪክ ብቻ ነውን?በቅጡ ያልተላለፈ ታሪክ ብቻ ሆኖ ቢቀር ኖሮ ግን አዎ ቅዱስ መፅሀፍም የታሪክ ክሽፈት ይገጥመው ነበር፡፡ይልቁንስ ጠቢብ ሰው ከሆንን ታሪክ እንዳይከሽፍ የፕሮፌሰሩን አይነት በእድሜ የገፉ ሰዎችን ብስጭታቸውን ጭምር ቢሆን በአክብሮት እናድምጣቸውና የሚጠቅመንንም ከውስጡ አጣርተን እናውጣና እንጠቀምበት፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. THANK YOU ! THAT IS WHAT I WAS THINKING.

   Delete
  2. I do not know why you wrote this article and it is emotionally biased one. I thought you like the truth to be revealed. Besides you look like you wrote the article for Proffessor Messfin only. Not to other readers as you mentioned names that you have not fully expressed for readers. You criticized, not even mentioned on what you agree from the book. Besides any comment, any kind of books can be written at any times evenif the persons specified in the book are dead or alive. anyways this article is not clear for me!
   God bless!

   Delete
 42. for me i read the book professor raise some untouchable questions abt the country & the people ,its hard to arguing history but the question is who wrote this history we know many of our references (our history) wrote by the foreigners professor want to talk abt this problem.ahunem bihone keshfenal men ezich ager lay lemenor miasnafk neger ale?

  ReplyDelete
 43. Daniel I appreciate u in your work but I don't think that u have read that book or don't understood or ....

  ReplyDelete
 44. በዚህ መጽሐፍ ዙሪያ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የሰጡትን ምላሽ ሳነበው ከአስተማሪነቱ ይልቅ ከሥነ ምግባር የራቀ አመለካከት ይበዛበታል። ይህ ደግሞ ከአዛውንት ምሁር አይጠበቅምና እርማት የሚያስፈልገው ይመስላል። መተቻቸቱ መተራረሙ አስፈላጊ ቢሆንም በስሜታዊነት የሚገለጽ ነገር ሁሉ መስመር ስለሚስት ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነውና ሰው በሥራው ቢተች የሚገልጸው መሥራቱን እንጅ ስንፍናውን ስለአይደለ ፕሮፌሰር በጥሞና ነገሮችን መመልከት ይጠበቅባቸዋል። "ከአያያዝ ይቀደዳል ከአንጋገር ይፈረዳል" እንዲሉ።

  ReplyDelete
 45. ፕሮፌሰሩ ግን እድሜም ተጫናቸው ብዙዎችም ሙገሳና አንቱታ አበዙባቸው መሰለኝ እሳቸውም ወሬያቸውም ጃጁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከዚህ ስድብ ይልቅ “ዝም አይነቅዝም”

   Delete
 46. “ቁም!” ይህን አስፈሪ የኾነ ትዕዛዝ ስንቶቻችሁ በሕይወታችሁ እንደተገናኛችሁት አላውቅም። በደርግ የአገዛዝ ዘመናት ግን እጅጉን የታወቀ ነበር። አንድ ወታደራዊ ፖሊስ ወይም ‘የአብዮት ጠባቂ’ በመንገዱ ያገኘውን ሰው በድንገት አስቁሞ የሚያርበደብድበት የትዕዛዝ ቃል ነበር። ‘ሕግ’ የተላለፈ፣ በተቀመጠለት ‘ሥርዐት’ በአግባቡ አልሄደም ተብሎ የታሰበ፣ ‘ከተፈቀደለት መስመር’ የወጣ ሁሉ “ቁም!” ይባል ነበር ያኔ። ከስንት ዘመን በኋላ ዛሬ ፕሮፌሰር መስፍን በመጽሐፋቸው መግቢያ ላይ “ቁም! የሚል ማስጠንቀቂያ ይሰጣሉ። የነደደ/የከረረ ምሬት መገለጫ የኾነውን መጽሐፋቸውን ማንበብ የሚገባው ሰው ምን ዐይነት መኾኑን ለመናገር ሲፈልጉ።

  “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የሚለው መጽሐፋቸው በእውነትም አሁን ባለችው ኢትዮጵያ አጠቃላይ ኹኔታ ለማይናደድ፣ ለማይበሳጭ እና በድሎት ለተቀመጠ ፈጽሞ አይኾንም፤ ይጎረብጣል። እውነትም መንፈሱንም ሊያሸብረው ይችላል። እኔም የእርሳቸውን ቃል በመዋስ እላለሁ፤ በኢትዮጵያ ኹኔታ የደላው ካለ አይደለም ስለ መጽሐፉ ስለ ፕሮፌሰር መስፍንም እንኳ ባይሰማይ ይሻለዋል፣ የማይበሳጭ ካለም ስለኢትዮጵያ ታሪክ አመጣጥም ኾነ አሁን ላለችበት ትርጓሜ ቁብ ሊሰጥ የማይችል ነው እና አርፎ ይቀመጥ። በተለይ ይህ መጽሐፍ ባስቀመጣቸው ተግዳሮቶች ።

  ፕሮፌሰር መስፍን የአደባባይ ምሁርነትን በመምራት የሚስተካከላቸው ያለ አይመስለኝም። ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ምሁራን መካከል እንደ እርሳቸው የኾነ ምርታማ ጸሐፊ ፈልጎ ማግኘትም ከባድ ነው። በሦስት መንግሥታት ዳር ላይ ቆመው የትችት ዱላቸውን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል። በማይዛነፍ እና የሐሳብ ተከታታይነት ባለው ጽሑፋቸውም ብዙ መጻሕፍቶችን እና፣ በየጊዜው በጋዜጦች እና በመጽሔቶች እንዲሁም በጆርናሎች ላይ ታከተኝ ሳይሉ ሐሳባቸውን ሲያንጸባርቁ ኖረዋል። “አነጋጋሪ” የሚል ቅጥያም ከተሰጣቸው ከርመዋል።

  አንዳንዶች በተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ባይቻላቸውም እርሳቸውን እንደሚጠሉ ይናገራሉ። የሚያምኑበትን ከመናገር እና የመሰላቸውን ሐሳብ ከመግለጽ አለመቆጠባቸው ምናልባት ከአድርባዮች ጎራ ስለማያሰልፋቸው፤ አልያም ከአንዱ ወገን ኾነው ሌላውን ለመጥላት የሚመች ባሕርይ ስለሌላቸው ይኾናል ከሁሉም አቅጣጫ የጥላቻ አስተያየት የሚሰነዘርባቸው። ከጥቂቶች በቀር ለጎንታይ ሐሳባቸው መልሶ ጎሻሚ ሐሳብ ይዞ የሚመጣ የለም። በአዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ ሞክሼያቸው መስፍን ነጋሽ “ፕሮፍ ምን ነካቸው?” ብሎ ሁለት ተከታታይ ጽሑፍ ማቅረቡን ያስታውሷል። ሌሎችም ካሉ አንባቢያን ጨምሩበት።

  ፕሮፌሰሩ መጽሐፋቸውን ሲጀምሩ አስደንጋጭ እና ቀልብ ሳቢ የኾነውን ”መክሸፍ” የሚል ቃል ከማብራራት ይጀምራሉ። ለእርሳቸው መክሸፍ ማለት ተጀምሮ ሳይጠናቀቅ የቀረ ኹነት፤ እንቅፋት ገጥሞት ሳይሳካ እና ሳይቀጥል የቀረ ታሪክ ማለት ነው ባጭሩ። እንደርሳቸው አመለካከትም መክሸፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለብዙ ዓመታት ግዙፍ ስፍራ ይዞ የቆየ ነገር ነው። ያውም አንድም እንኳ የታሪክ አጥኚ ዞር ብሎ ሳያያው።

  ፕሮፌሰሩ በዚህ መጽሐፍ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት እና በሁዋላ የነበረችውን/ያለችውን ኢትዮጵያ ይዳስሳሉ። አብዛኞቹ የታሪክ ተመራማሪዎች እና ሊቃውንት ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ሲጽፉ ወደኋለኛው ዘመን መመለስ አይሹም። አንድም በመረጃ እጥረት አሊያም በዘመናዊ ትምህርት የተካኑት ሰዎች ስለ ኢትዮጵያ ቀይደው ያበጁት አተረጓጎም ለጉሞ ስለሚይዛቸው። ፕሮፌሰር መስፍን ግን ከሁለት ሺሕ ዓመት በፊት እና በኋላ ያለችው ኢትዮጵያ በሥልጣኔ እና በኋለቀርነት ምን ትመስላለች የሚለውን አንስተው ይዳስሳሉ። “ያኔ ሥልጡኖች የነበረነው እንዴት ነው? ዛሬስ የኋላ ቀሮች መጨረሻ ለመኾን የበቃንበት ምክንያት ምንድነው?” በሚል ጥያቄ ላይ ተመስርተው ተንኳሽ እና አመራማሪ ጥያቄዎችን ይሰነዝራሉ። የድንጋይ መሥራት ጥበብ የታየባት ኢትዮጵያ ከትውልድ ወደ ትውልድ በደሳሳ ጎጆ የሚተላለፍ ባህል ለማዳበር የበቃችውስ ለምንድነው? ሲሉም ይጠይቃሉ።

  ጥንት በኢትዮጵያ የታየው የሥልጣኔ ጅምር ዛሬ ካለችው ኢትዮጵያ ጋራ አልጣጣም ያለበት ምክንያት ተጀምሮ ያላለቀ ታሪክ ስላለን እና ክሽፈት ስለተጠናወተን ነው ባይ ናቸው። ፕሮፌሰር መስፍን የሚያነሱት ሐሳብ ስለ ኢትዮጵያ መልሰን መላልሰን እንድናስብ እና መነሻችን እና መድረሻችን ሳይጣጣም የቀረበትን ጉዳይ ልብ ብለን እንድናስተውል የሚያስገነዝብ ነው።

  የዚህን የኋላ-ቀርነት መጨረሻ እና የታሪክ ክሽፈት እንዲገልጽላቸው ኤድዋርድ ጊበን የተባለው እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊ ያለውን ይጠቅሳሉ። “ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ዓለም ረስተውት ለአንድ ሺሕ ዓመታት ያህል አንቀላፉ፤” የታሪክ ጸሐፊው ይህን ያለው የሥልጣኔ ርምጃችን ከሽፎብን ቁልቁለቱን ስንወርድ ዐይቶ ነው” ሲሉም ያስረግጣሉ።

  ኢትዮጵያውያን አሁን ላለንበት ሁኔታ የተዳረግነው በታሪካችን ውስጥ ያጣነው እና ሳንገነዘብ ያለፍነው ነገር የቱ ላይ ነው የሚለው በብዙዎች ውስጥ የሚመላለስ ጥያቄ ነው። ይህ ጥያቄ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልደው ላደጉ እና ዘር ማንዘራቸውን ሲጠይቁ ከዚያች ምድር መፍለቃቸው ለሚገባቸው ሁሉ እንቆቅልሽ ኾኗል። “ኢትዮጵያ” ስንል በየትኛዋ “ኢትዮጵያ” ላይ ነው የምንነጋገረው የሚለው ሐሳብ የተለያየ ትርጓሜ ስለተሰጠው አብዛኞቹ መስማማት ሳይችሉ ማዶ ለማዶ ኾነው እየተታኮሱበት ነው። ሩቅ እንኳ ሳንሄድ የንጉሡ ኢትዮጵያ፣ የደርግ ኢትዮጵያ፣ እና የኢሕአዴግ ኢትዮጵያ መልካቸውም ግብራቸውም ልዩ ልዩ ነው። እንደየመልኩ ተቀይደው ያሉትም ብዙ ናቸው።

  ReplyDelete
 47. Part -two

  ለፕሮፌሰር መስፍን ግን ጥንታዊት ኢትዮጵያ ራሷ በአግባቡ አልተገለጠችም፤ ወደ ኋላ ተመልሶ ያያት የታሪክ ተመራማሪም ኾነ ሊቃውንት የለም። የታሪክ አዋቂዎች እና ሊቃውንትም ከመካከለኛው ዘመን ተነስተው የጻፉልን የኢትዮጵያ ታሪክ ሙሉ ሥዕል አያሳይም የሚል አንደምታ ያለው ክርክር ያነሳሉ። የታሪክ አዋቂዎች እና ተመራማሪዎች የኋለኛውን የኢትዮጵያን ታሪክ አንዳንዱ ‘ተረት’ ነው፤ ሌላውም ‘አፈታሪክ’ ነው በሚል መነሻ ከሺሕ ዓመታት ወዲህ ባለው ላይ ማተኮራቸው እሙን ነው። ይህ ዐይነቱ የታሪክ አቀያየድ የመጣው ደግሞ ታሪክ ጸሐፊዎቹ “ቄሳራውያን ሐይሎች” ቀደው በሰፉት ኢትዮጵያዊነት ላይ በመመሥረቱ ነው የሚል መከራከርያም ያቀርባሉ። ኢትዮጵያውያን የታሪክ ጸሐፊዎች ትክክለኛውን የኢትዮጵያን ታሪክ ከምንጩ እንዳልቀዱት እና ለቄሳራውያን ሐይሎች በሚስማማ መንገድ ጽፈውታል፤ ስለዚህ ታሪክ ውሉን ስቷል ሲሉም ይሞግታሉ።

  ለእርሳቸው ይህ ዐይነቱ የታሪክ አጻጻፍ ወይም አዘጋገብ አንድም ለእንጀራ ሲባል አሊያም ቄሳራዊ ሐይሎችን ለማስደሰት ከሚደረግ ትግል የሚመነጭ ነው። በዚህ መጽሐፍ ፕሮፌሰር መስፍን ያነሱት ጭብጥ ውኃ አያነሳም የሚባል አይደለም። ክርክራቸው ውሃ የሚያነሳበት ዋነኛ ጉዳይ ስለ ኢትዮጵያ ስንነጋገር ስለ አክሱም ማንሳታችን የማይቀር በመኾኑ ነው። ስለ አክሱም ስናወራ ደግሞ ከሁለት ሺሕ ዓመት በፊት ስለነበረ ሥልጣኔ እያወራን ነው፤ አንድም አክሱም በኢትዮጵያ ምድር ላይ ከሰማይ ተውርውሮ የተተከለ የተዐምር ድንጋይ ነው ብለን ራሳችንን ካላሳመንን በቀር ወይም ለዚያ ሥልጣኔ አበርክቶት የነበራቸው ሌላ ሕዝቦች ናቸው የሚል በቂ ማረጋገጫ እስካለገኘን ድረስ ንብረትነቱም ኾነ ታሪኩ የኢትዮጵያ ከመኾን አያመልጥም። ስለ አንዲት አገር በቂ የኾነ መነሻ ከሌለን ስለመድረሻዋ መጨቃጨቁ ጉንጭ አልፋ ከመኾን የሚዘል አይመስለኝም። ፕሮፌሰር መስፍንም የሚሉት የኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጽል በኾነ መንገድ በመነገሩ “ክሽፈት” ኾኗል ነው። እስኪ ነገራቸውን ለማስረገጥ እና በማስረጃ ለመጥቀስ፣ ለትክክለኛ ታሪክ ትርጓሜ የሰጡበትን ምዕራፍ እንመልከት፤ በተጨማሪም ኢትዮጵያዊ ታሪክ ማለት ምን ማለት እንደኾነ ያዩበትንም እንይ።

  ትክክለኛ የታሪክ ትርጓሜ የሚሉትን እንዲህ ያስቀምጡታል

  “ታሪክ የሕዝብ፤ የተከታታይ ትውልዶች ሥራ ነው፤ ኑሮ ነው፤ ትግል ነው፤ ተጋድሎ ነው፤ እያንዳንዱ የቀደመው ትውልድ ኅብረቱን፣ ንብረቱን እና መብቱን፤ በአጠቃላይ የአብሮ መኖር ሕልውናውን አረጋግጦ ለሚቀጥለው ትውልድ ያስተላልፈውንና ያስተላለፈበትን ኹኔታ ጭምር የሚገልጽ ቅርስ ነው። ተከታዩ ትውልድ ከቀደመው ትውልድ የተረከበውንና ራሱ ደግሞ የጨመረውን እያካተተ የሚተርክ ዘገባ ነው። የኋለኛው ትውልድ ባለፉት ትውልዶች መስዋእትነት በተጣለው መሠረት ላይ የተሻለ፤ የጠነከረ እና የበለጸገ ማኅበረሰብ ለማነጽ የሚያደርጉትን ጥረት ካለፈው ጋራ የሚያስተያይ መዝገብ ነው። ትውልዶችን ከትውልዶች ጋራ የሚያስተሳስር እና የሚያገናኝ ሰንሰለት ነው።” ይህ የማያከራክር ሳይንሳዊ የኾነ አጥጋቢ ትርጓሜ ነው።
  ይህን ካሉ በኋላ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ታሪክ ማለት ደግሞ እንዲህ ነው ይላሉ።

  “ለኢትዮጵያውያን ታሪክ ማለት ሁልጊዜም ከእግዚአብሔር ፈቃድ እና ፍቅር ወይም ጥላቻ ጋራ የተያያዘ ነው። በሃይማኖተኛ ማኅበረሰብ ታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር ጎልቶ መውጣቱ አያስደንቅም። የሚያስደንቀው የሰው ልጅ ገና ከሕጻንነት መውጣት አለመቻሉ ነው። ከሕጻንነት አልወጣም ማለት ራሱ ለሚሠራው ሁሉ ገና ሐላፊነት መውሰድ አልጀመረም ማለት ነው። ያጠፋውንም ያለማውንም የአምላክ ፈቃድ ስለሚያደርገው ለስህተቱም ኾነ ለጥፋቱ ተጠያቂ እንዳይኾን ያደርገዋል። የእግዚአብሔር ፈቃድ ኾኖ ነው ከተባለ ማንም ሊከራከር አይችልም።” ይላሉ። ይህ ደግሞ እምነትን መሠረት ያደረገ አምጪውም ፈጪውም የማይጨበጠው አምላክ ነው በሚል መደምደሚያ ላይ የቆመ ነው።

  እንግዲህ ፕሮፌሰር መስፍን የታሪክን ትክክለኛ ትርጓሜ ካስቀመጡበት ኹኔታ አኳያ ስንመለከተው ኢትዮጵያውያን ታሪክን የሚያዩበት ዐይን ከእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ፍቅር እና ጥላቻ ጋራ በመተሣሰሩ ከጅምሩ ቅኝቱን የሳተ ነው። ለክሽፈቱ ጅምርም ይኼው አጠቃላይ የኾነ የታሪክ ግንዛቤ ይኾናል። ምንም እንኳ ለእርሳቸው በሃይማኖተኛ ማኅበረሰብ ታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር ጎልቶ መውጣት ባያስደንቃቸውም። አስደናቂው ነገር ግን የሰው ልጅ ከሕጻንነት መውጣት አለመቻሉ ነው። በርግጥ ታሪክን በዚህ ግንዛቤ የሚወስድ ማኅበረሰብ ከሕጻንነት ሳይወጣ ሐላፊነት ላለመውሰድ የሚንገታገተው ለምንድን ነው? የእግዚአብሔር ጎልቶ መውጣት በራሱ ከሕጻንነት ላለመውጣት ብቸኛው ምክንያት አይደለም ወይ? የሚል ጥያቄን ያጭራል። ፕሮፌሰር መስፍን የእግዚአብሔር ጎልቶ መውጣት ላይ በዝርዝር አልሄዱበትም። ካስቀመጡት ትክክለኛ የታሪክ ትንታኔ እና ትርጓሜ አንጻር ታሪክ የሰው ልጆች የሥራ ውጤት ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ መዝገብ ነው። ትውልድ እና ትውልድን የሚያስተሳስር ሰንሰለትም ነው። በዚህ ትርጓሜ ከተስማማን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ ፈቃድ እና ጥላቻው ጣልቃ እንዲገባ መፈቀዱ እና መወሰኑ አሁን ላለው ኋላ-ቀርነት አስተዋጽኦ ማበርከቱን በዝርዝር ያዩት አልመሰለኝም። አንድም ሃይማኖታዊ የኾነውን ማኅበረሰብ ለመጎነጥ በዚህ ሰዓት አልፈለጉም ወይም ከዋናው መሠረታዊ ችግር ይልቅ “በሕጻንነቱ” እና በሐላፊነት አልሸከም ባይነቱ ላይ ማተኮርን መርጠዋል።

  በዘመናዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ ከላይ ምንም ዐይነት ሥልጣን የሌለበት ሥርዐተ-መንግሥት ለማቋቋም በመጀመርያ ቤተ ክርስቲያን እና ሀገረ-መንግሥት መለያየት አለባቸው የሚለው ገዢ ሐሳብ ኾኖ ያገለግላል፤ ይሠራበታልም። ፍትህን ለማስፈን እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዐትን በማንኛው ሰብዐዊ ፍጡር መካከል ለማጎናጸፍ አንደኛው መደረግ ያለበት ነገር ነው ተብሎ ይታመናል። ርግጥ ነው የቤተ ክርስቲያን እና የሀገረ-መንግሥት የጋብቻ ፍቺ በብዙ አገሮች ላይ ገና ነጥሮ ያልወጣ ጉዳይ ነው። በተለያየ እና ውስብስብ በኾነ መንገድ ተጽእኖውን ከማሳረፍ አልጸዳም፤ በዴሞክራሲ ብዙ ተጉዘናል በሚሉት አገሮችም ጭምር። ኢትዮጵያ ውስጥ ችግሩ ሥር የሰደደ እንደኾነ የሚያሳየው ግን ፕሮፌሰር መስፍን ‘ኢትዮጵያውያን ሃይማኖታዊ ማሕበረሰብ ናቸው እናም ታሪክ የሚታየው በእግዚአብሄር ፈቃድ፣ ፍቅር እና ጥላቻ መስመር ነው’ ብለው ባስቀመጡት ላይ የቆመ በመኾኑ ነው። ስለዚህ የትርጓሜ ፍቺው ካልተቀየረ በቀር ከተመሠረተበት ተነቅሎ “ሕጻንነቱ”/ሐላፊነት ለመሸከም ፈቃደኛ መኾን አለመቻሉ ሁለተኛ ነገር ይኾናል። ይህን ጉዳይ አንድ ቀን አስፍተው እንደሚመጡበት ተስፋ አድርጌ ልለፈው።

  ReplyDelete
 48. part three

  ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ክሽፈት ሲያትቱ አንቱ የተባሉትን የታሪክ ሊቃውንቶች ያነሳሉ። ከእነዚህም መካከል ሦስቱን በዋነኛነት ከእነሥራዎቻቸው ይጠቅሷቸዋል። ፕሮፌሰር ስርግው ሐብተሥላሴን፣ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትን እና ፕሮፌሰር መርዕድ ወልደአረጋይን።

  እነዚህ ፕሮፌሰሮች በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የጻፉ እና ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ በተነሳ ቁጥር በቅድሚያ የሚጠቀሱ ሰዎች ናቸው። ፕሮፌሰር መስፍንም የኢትዮጵያን ታሪክ ክሽፈት ሲዳስሱ በእነዚሁ ሊቃውንት ሥራዎች ላይ በመንተራስ “ምን ዐይነት ኢትዮጵያ ነበር ያሳዩን?” ሲሉ በዝርዝር ይጠይቃሉ።
  ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኹት የመጀመርያ መነሻቸው ያደረጉት የኢትዮጵያ የታሪክ ሊቃውንት ኢትዮጵያን ያዩበት መነጽር የተንሸዋረረ ወይም ቅኝቱ ቄሳራዊ በኾነ አስተምህሮ የተለወሰ ነው በሚል ነው። ወደ አገራዊ ሊቃውንቶች ከመምጣታቸው በፊት ስለ ቄሳራውያን ምሁራን ጽፈዋል። “ቄሳራውያን ምሁራን ስለኢትዮጵያ የጻፉት አብዛኛው ነገር ለእነርሱ በሚገባቸው እና በሚያመቻቸው መንገድ ነው። እነርሱ ስለ እኛ ሲጽፉ እኛም ያለምንም ጥያቄ ጥቁር ሰሌዳ ኾነን እንቀበላለን። አስቀድሞ አብዛኛው ቄሳራዊ ምሁር የኢትዮጵያን ታሪክ የሚጽፈው የተላከበትን አገር ፖለቲካዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ነው።” ይላሉ። ይህ በርግጥ የተረጋገጠ እውነት ነው። ኢትዮጵያውያን ምሁራንም እነርሱ በቀደዱላቸው ቦይ በመፍሰሳቸው የክሽፈት ታሪክ ለመጻፍ ምክንያት ኾነዋል የሚል ነው የመከራከርያ ነጥባቸው። ለዚህም እንደማስረጃ ከሚያቀርቡዋቸው ነገሮች መካከል የፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትን እና የፕሮፌሰር መርዕድ ወልደአረጋይን የተሸማቀቀች/የተኮማተረች ኢትዮጵያ ካርታ እንደምሳሌ በመጥቀስ እና ከመጽሐፉ ጀርባ በማስቀመጥ ነው።

  በመጽሐፉ ላይ ካርታ ብቻ በማስቀመጥ ሳይኾን የእያንዳንዳቸውን መጽሐፍ በመጥቀስ በውስጣቸው በአግባቡ ስላልተተረጎሙ የእንግዚዝኛ ቃላቶች ሁሉ ትችትን ይሰነዝራሉ። “ስቴት” የሚለውን ቃል እንደ ቁልፍ ቃል ሳይኾን እንደ ተራ ቃል ችላ ብለው ማለፋቸው ተገቢ እንዳልኾነም ጽፈዋል። “ስቴት” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ዋና ትርጉሙ “ከበላዩ ምንም ሥልጣን የሌለበት ሀገረ-መንግሥት ነው” ይላሉ። መርዕድም ኾኑ ታደሰ በመጻሕፍታቸው/ጽሑፋቸው ውስጥ ኢትዮጵያ የተዋሃደች ስቴት ነች አይደለችም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። መዋሃድን የስቴት መሠረታዊ ባሕርይ አድርገውም የተቀበሉት ይመስላል ይላሉ። ይህ ትንታኔ በተለይ በዐሥራ ስድስተኛው ምዕተ ዓመት መጀመርያ እና ከዚያ በፊት የሚሠራ ነው ወይ ነው? ጥያቄያቸው። የተዋሃደ እና ያልተዋሃደ ስቴት ማለትስ ምን ማለት ነው? ሲሉም ይጠይቃሉ።

  በተቃራኒው “ኢስላም በኢትዮጵያ ውስጥ” የሚል መጽሐፍ የጻፈው እንግሊዛዊ ሊቅ ትርሚንግሃም ከሁለቱም በተሻለ መንገድ “ስቴት” በኢትዮጵያ ከሕዝብነት በላይ መኾኑን አስቀምጧል ባይ ናቸው። ዝርዝሩን እዚህ አልጠቅሰውም አንባቢያን ከመጽሐፉ ታገኙታላችሁ።

  የፕሮፌሰር የመከራከርያ ነጥብ ግን ትርሚንግሃም በኢትዮጵያ ነጥሮ እና ተረጋግጦ የወጣውን የኢትዮጵያውያንን ሕዝብነት የበለጠ ተረድቶታል ነው። በውስጡ የታመቀ የከፋፍለህ ግዛ ሐሳብ ማዘሉ እንዳለ ኾኖ። በተመሳሳይ በሦስቱም ሊቃውንት ጽሑፎች ውስጥ ሌላኛው አከራካሪ ቃል “ኢምፓየር” የሚለው ነው። በቁም ትርጉሙ ኢምፓየር በውስጡ ሁለት ዓይነት ሥርዐትን የያዘ የፖለቲካ ድርጅት ነው። አንዱ የቅኝ ገዢው (ኢምፔሪያል) አገር (ስቴት) በራስ አገር ላይ ያለው መንግሥት ሲኾን ሌላው ደግሞ በቅኝ አገዛዙ ስር ባሉት ሕዝቦች ወይም ግዛቶች ላይ ያለው ነው። ስለዚህ ከዚህ ትርጓሜ ተነስተን ስናየው ኢትዮጵያ በየትኛው ክፍለ ዘመን ነው ይህን ዐይነት አስተዳደር የነበራት የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ እንገደዳለን። በእኔ አመለካከት ፕሮፌሰር መስፍን እነዚህ ትልልቅ ጽንሰ ሐሳብን ያዘሉ ቃላቶች በኢትዮጵያ ታሪክ ትንታኔ ውስጥ መቀመጣቸው ታሪክን በተዛባ መንገድ እንድንረዳው ምክንያት ይኾናል ማለታቸው አግባብነት ያለው ነው ተብሎ ቢወሰድ ሊቃውንቱን በግል ወደማጣጣል የሚሄድ ሳይኾን አሁን ያሉትም ኾኑ ወደፊት የሚመጡት የታሪክ ሊቃውንት መስመር እንዲያሲይዙት የሚያደርግ የማንቂያ ደወል እንጂ አንዳች የጥላቻ/ የማጣጣል መንፈስን ያዘለ አይደለም።

  ፕሮፌሰር መስፍን ፕሮፌሰር ስርግውን በተሻለ ዕይታ ከጥቂት የፖለቲካ እና የእንግሊዝኛ ቃላት ችግር ውጭ አመስግነዋቸዋል። እንዲያውም መጽሐፋቸው እና ጽሑፎቻቸው በአማርኛ ተተርጉመው ቢቀርቡ መልካም መና እንደሚኾኑም ተናገረዋል። ፕሮፌሰር ታደሰ ላይ ግን ሰፋ ያለ ትችትን አቅርበዋል። የታደሰን “ክርስቲያን ኢትዮጵያ” ሸምቃቃነት አጉልተው ለማሳየት ሰፋ ያለ ትንታኔ ሰጥተዋል። በፕሮፌሰር መርዕድ ጽሑፍ ላይ አጠር ያለ ትችት ሰንዘረዋል። ከዚህ በሁዋላ የተሻገሩት ቄሳራውያን ሐይሎች ከዐፄ ዮሐንስ እና ከዐፄ ምኒልክ ጋራ ስላደረጓቸው ውሎች እና በድንበር ማስከበር ጉዳይ እና የቅኝ ገዢነት በኢትዮጵያ እንዳይስፋፋ ስለተደረገው ተጋድሎ ነው። ከዚያም የኢትዮጵያ ተሀድሶ ብለው ከዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን አንስተው ኢትዮጵያን ለመውረር ያሰፈሰፉት የቄሳራዊ ሐይሎች እንዴት ባለ አኳኋዋን ስውር ደባቸውን ሲሠሩ እንደከረሙ እና ኢትዮጵያ የተኮማተረች እና የተሸማቀቀች ለመኾን እንደተዳረገች በዝርዝር ጽፈዋል። በጊዜው በቄሳራዊ ሐይሎች እና በኢትዮጵያ ነገሥታት መካከል የተደረጉትንም ውሎች በመጽሐፉ ውስጥ አካተዋል። ለአንባቢ ፍርድ ይመች ዘንድ።

  ReplyDelete
 49. Part four

  በዚህ ዝርዝር ውስጥ አንድ የተለየ ምልከታ ይዘው መጥተዋል። ኢትዮጵያ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው ያላት የሚል ክርክራቸውን ለፖለቲካ ትርፋቸው የሚጠቀሙበት የዘመኑ ፖለቲከኞች ስለመስፋፋት ሲያነሱ ዕዳውን የሚያሸክሙዋቸው እና ቅጽሉን የሚለጥፉላቸው በዐፄ ምንሊክ ላይ ነው። የአንድነት ሐይሉ የምንሊክ ደጋፊ፣ የጭቆና ሰለባ ዀኛለሁ የሚለው ሌላው አካል ደግሞ የምንሊክ ጠላት ኾነው ተሰልፈዋል። ይህ የመስፋፋት ጉዳይ ተፈጽሟል የሚባል ከኾነ (የኢትዮጵያ ግዛት እስከ ሕንድ ውቅያኖስ ድረስ ነበር ብሎ ለሚያምን አይሠራም) የተፈጸመው በዐፄ ዮሐንስ ዘመን ነው ብለው ጥቁምታ ሰጥተው ያልፋሉ። ምክንያታቸውም ምንሊክ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዮሐንስ አራተኛ ሥር የሚተዳደር የሸዋ ንጉሥ እንጂ ንጉሠ ነገሥት አልነበረም እና ነው የሚል ነው።

  ፐሮፌሰር መስፍን ያነሷቸውን አብዛኞቹን ጉዳዮች በዚህ አጭር ጽሑፍ ውስጥ ዘርዝሮ ማቅረብ አይቻልም። ነገር ግን እኔም ወደ ጽሑፌ ማጠቃለያ ለመጓዝ በመጽሐፉ መጨረሻ ግድም ስለ “ኢትዮጵያዊ እውነት” ያሉትን ጠቅሼ ላብቃ። “ኢትዮጵያዊ እውነት ማለት ወረት ማለት ነው፤ ይህን ሐቅ መቀበል ካልቻልን ተስፋ የለንም።” {ይህን ከማለታቸው በፊት ያስቀመጡትን ዝርዝር በቀደመው የፌስ ቦክ ፖስቴ ላይ ይፈልጉት} ካሉ በኋላ “እውነት ሁለት መሠረቶች አሉት፤ አንዱ እምነት ነው አንዱ እውቀት ነው። ከእምነት የሚነሳውን እውነት የተገለጠ እውነት ልንለው እንችላለን፤ ከእውቀት የሚነሳው ደግሞ የተረጋገጠ እውነት ይባለል። በተገለጠ እውነት የሚመሩ ማሕበረሰቦች ባህላዊ ይባላሉ። በተረጋገጠ እውነት የሚመሩ ደግሞ ሳይንሳዊ ይባላሉ፤ በእውቀት የሚመሩ ማለት ነው። . . . በተገለጠ እውነት ላይ ጥያቄ ወይም ክርክር ማንሳት ፍጹም አይቻልም፤ ወይም አምኖ መቀበል ነው፤ ወይ አለመቀበል ነው። መመራመር የትም አያደርስም፤ ኢትዮጵያ የተገለጠ እውነት አገር ነች ማለት እንችላለን።” ይላሉ።

  እንግዲህ ኢትዮጵያ እንደ አገርም ኾነ እንደ ሕብረተሰብ በተረጋገጠ እውነት (ሳይንሳዊ በኾነ) ላይ ካልተመሠረተች ያልከሸፈ ታሪክ ባለቤት መኾን እንደምን ይቻላታል? ይህ ፕሮፌሰር መስፍን ያነሱት የመክሸፍ ነገር የእያንዳንዳችንን መንፈስ የሚጓጉጥ ነው። ቆመንበታል የምንለውን የእውነት መሠረትም የሚያናጋ ነው። በተለይ በተረጋገጠ እውነት ላይ ከመቆም ይልቅ በተገለጠ እውነት ላይ ላለን ሰዎች ተግዳሮቱ የበዛ ነው። ምናልባት ካንዱ እውነት ወደ ሌላኛው እውነት ለመሻገር የሚፈጀውን ጊዜ እያሰብን የምንባክን ሰዎች ካለን ደግሞ ሕመሙ ጋኔናችንን እስከማስጮህም ድርስ የበረታ ይኾናል። ክሽፈቱ እውነትን አለው፤ እውነትን ለመቀበል እንደሚያስቸግረው ሁሉ ትግሉ ትልቅ ትንቅንቅን ይጠይቃል። ክሽፈት እና እውነት እኩያ እና መንትያ ሲኾኑ ደግሞ አይጣል ነው። ቁም! ክሽፈትህን እወቅ! ክሽፈትህን እመን! ያኔ ቁም ባዩን አታገኘውም።

  ክሽፈት እና እውነት እኩያ እና መንትያ ሲኾኑ . . .
  by Masresha Mammo

  ReplyDelete
 50. ታሪክ ሊከሽፍ ይችላል
  ይህን እንድጽፍ ያነሳሳኝ ዲ. ዳንኤል በፕሮፌሰር መስፍን መጽሃፍ ላይ የጻፍውን መጣጥፍ ተከትሎ ፕሮፌሰሩ የሰጡትን መልስ ማንብቤ ነው።ማህበረሰባችን (የቱ እንዳትሉኝ) ለእውቀት ከፍተኛ ግምትን ይሰጣል። ክእውቀት ጋር ተያይዘው ለሚሰጡ የስም መጠሪያዎችም ላቅ ያለ አክብሮት አለው። እንደው ሌላውን ትተን አሁን አሁን በሰፊው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተለመደ የመጣውን ስመ ጥር ለሆኑ አርቲስቶች፤ የፖለቲካ ባልስልጣናት፤ ደራስያን ወዘት.. በሃገሪቱ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት የሰጡትናን እይሰጡ ያሉትን የክብር ዶክትሬት ዲግሪን ያስታውሷል። እንደ ልማዱ ከሆነ እጅግ ጥቂት ከሆኑ ተቋማት በቀር ይህንን ማዕረግ ለመጠሪያነት መጠቀምን እንደማይቻል በዚያው በሚሰጡት የክብር ዲግሪ ላይ ይጽፉታል። በትምህርት የሚገኝን ማዕረግ እንዳያዛባ። ቢሆንም የተወሰኑ ታዋቂ ሰዎችን ጨምሮ አንዳንዶቹ ከስማቸው ጋር አያይዘው ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። ለምሳሌ ታዋቂዋ አሜሪካዊት ደራሲና ገጣሚ ማያ አንጄሎ አንዲሁም አሜሪካዊው ሰባኪ ቢሊ ግራም የክብር ዶክተርነቱን ከስማቸው ጋር ሲጠቀሙበት እናያለን። በሀገራችን ግን ሰውዬው እንኳ ባይፈልግ እንደ መካብ እንደ ማቆላመጥ ያክል በየመድረኩ ሲጠሩት ሳይ ይደንቀኛል።ደሞ የሚገርመው በማስተማርያ መርሃ ግብራቸው ውስጥ የፒ.ኤችዲ ወይም ተነጻጻሪ የሌላቸው ዩኒቨርስቲዎች የሌላቸውን ሰው ላይ ሲለጥፉ አስገረሞኛል።
  ፕሮፌሰር መስፍን ለዲ. ዳንኤል የሰጡት የደብተራነት ማዕረግ እንዲሁ እንደማይገገኝ እሳቸውም አያጡትም። እኔ በበኩሌ ዳንኤል ድብትርና ደረጃ መድረሱን ባለማወቅ ይህው እስከ አሁን ዲያቆን አያልኩ ነው የምጽፈው። ሲመስለኝ ግን ፕሮፌሰሩ የክብሩን መጠሪያ መሳደቢያ ማድረጋቸው ነበር።ኣለማወቃቸው አሳዘነኝ። አውቀዋለሁ እና እቆረቆርለታልሁ የሚሉት የኢትዮጵያ ታሪክ ምናልባት 90 ከመቶው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተርስትያን ጋር የተያያዘ ነው።እና ፕሮፌሰር የሚል መጠሪያ ስላላቸው ብቻ የሚሉትን ያውቁታል ማለት አይደለም ግን የሳቸውን ይዞ ደብተራ የሚለው መጠሪያ ስድብ የሚምስለው ትውልድ ደሞ ያሳዝናል። በነገራችን ላይ ፕሮፌሰር እኮ የመጨረሻ ዲግሪያቸው ማስተርስ እንጂ የፈረንጁን ድብትርና ፒኤችዲን አልደረሱበትም። ፕሮፌስርነት ከዶክተርነት ጋር አይገናኝም እና ዶክተር እያላችሁ አትስደቡዋቸው። ሌላው ደግሞ አሁን ተውት እንጂ እኮ እሳቸውም ዲያቆን ነበሩ።ቢጠሩበት ጥሩ ነበር። ይህን በዚህ ልተውና…
  የአሁኑ መጽሃፋቸውን እስካሁን አላነበብኩትም።የሰጡትን መልስ ሳይ ግን ዳንኤል ስለ መጽሃፉ የሰጠው አስተያት ያስደሰታቸው አይመስልም።ይህ ጽሁፍ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በዚህ ጉዳይ ብዙ እንዳስበበት አድርጎኛል። ለዚሁም መነሻው ዳንኤል ታሪክ ይከሽፋል ወይ ብሎ ያነሳው ጥያቄ ነው። እሳቸው በሰጡት መልስ ላይ እንዳነበብኩት መክሸፍን ፡‹‹መክሸፍ የምለው አንድ የተጀመረ ነገር ሳይጠናቀቅ ወይም ሳይሳካ እንቅፋት ገጥሞት መቀጠል ሳይችል ዓላማው ሲደናቀፍና በፊት ከነበረበት ምንም ያህል ወደፊት ሳይራመድ መቅረቱን ነው፤›› ብለው ይፈቱታል።ይህን ትርጉም ይዘን ከሄድን ርዕሱን መሰረት አድርገን የኢትዮጵያ ታሪክ መቼ እንደተጀመረ እንድንጠይቅ ያስገድዳል።በዕውን ይህ የከሸፈህ ው ታሪክ መቼ የተጀመረውን ነው? የኢትዮጵያ ታሪክ መክሸፉን ይቅርና መቼ ነው እንደ ሰው ቁም ነገር ብለን አረፍ ብለን እሰክ አሁን ታሪካችን ይህን ይህን ይመስላል ይህ ድክመት አለብን ይሄ ደሞ ጥንካሬያችን ነው የተባባልነው? እረ እሱም ይቅርና ኢትዮጵያዊነት በሚባለውን እንኳ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ አድጎ ተምሮ ኢትዮጵያዊ አትበሉኝ የሚል ትውልድ በተነሳበትና ይህንንም እንደ መልካም ሃሳብ የሚያበረታታ መሳርያ ይዞ የሚያስፈራራ መንግስት ባለባት በአሁኗ ኢትይዮጵያ ስለ ቀደም የኢትዮጵያ ታሪክ መነጋገር እንደዘመኑ የተቀጽላ ስም “የድሮ ስርዓት ናፋቂ” (የደርግ ዘመንም ድሮ ኋኗል፤ ድሮ አድሃሪ ነበር) ከመባል በቀር ውይይት ሆኖ መፍትሄ የሚያመጣ አይመስልም።
  ከዳንኤል ጋር የምለያይውና ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር የምስማማው ግን እንዳሉትም ሆነ አልሆነ የተጀመረ ታሪክ ሊከሽፍ ይችላል። የተጀመረ ያልኩትን ያዙሉኝና ምሳሌ ልስጥ። የአሁኗ እስራኤል ይህንን መልክ የያዘችው በተመሰረተችበት አመት እ.ኤአ. 1948 የሚመስላቸው ብዙ አሉ። እኔን የሚገርመኝ ሌላው ዳር ተመልካች ምንም አለማወቁ ሳይሆን ጠላቶቻቸው ነን የሚሉት አረቦችም እንደዛ ማመናቸው ነው።ነገሩ ግን የአሁኗ እስራኤል መልክ ምን መሆን አለበት የሚለውን የነደፉት ገና በ20ኛ ክ.ዘ መባቻ ላይ የነበሩት ጽዮናውያን ነበሩ። ይህንንም ታላቅ ራዕይ ለማሳካት ከ 1917 በፊት በፊት በየ2 አመቱ እየተሰበስቡ የተለያየ ዕቀድ ያወጡ ነበር። ማቀድ ብቻ አልነበረም የተሰማሙበትን ሁሉ በተግባር ይተረጉሙት ነበር።ሁለት ታላላቅ የአለም ጦርነቶች ተደርገው በዚያም ምክንያት ብዙ አይሁዳውያን ቢያልቁም የጽዮናውያን ንቅናቄ ግን አላቆመም ።ቀደም ብለው ካቀዷቸውና እስራኤል እንደ ሃገር ከመቆርቆሯ በፊት ከተሰሩ ስራዎቸ እንደ ዋነኛነት የሚጠቀሰው የኢየሩሳሌሙ ሂብሩ ዩኒቨርስቲ ነው።ይህ ዩኒቨርስቲ እ.ኤ.አ በ1918 ሲመሰረትዩኒ ዋና አላማ አድርጎ የተነሳው በጸሎትና የሃይማኖት ቋንቋነት ብቻ ተወስኖ የነበረውን የእብራይስጥ ቋንቋ እንዴት ለዕለት ተዕለት አገልግሎት ማዋል እንደሚቻል ማጥናት ሲሆን፤ ይህንንም ወደ ቀድሞዋ ፓለስታይን እየፈለሱ ይገቡ ለነበሩ አይሁዳውያን ሁሉ የሚያስተምሩ መምህራንን ማሰልጠን ነበር። እስራኤል እንደ ሀገር እንዲሳካላት ካስፈለገ ከተለያየ ዓለም የሚመጡ አይሁዳውያን ሁሉ የሚግባቡበትን ቋንቋ አንድ እዲሆን ለዚህም እብራይስጥ እንዲሆን በጽዮናውያኑ ከብዙ ክርክር በኋላ ተወስኖ ስለነበረ ነው።አሁንም ድረስ በእብራይስጥ የጋራ መግባባቢያነት ሳይስማሙ ለጸሎት ብቻ እንጂ የማይናገሩት አክራሪ አይሁዳውያን አሉ።
  ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስና እንደዚህ ተመክሮ ተዘክሮ የተጀመረ ታሪክ አንድ ሁኔታ ገጥሞት ቢከሽፍ መክሸፍ እንደ.... ተብሎ ይጻፍለታል። የኢትዮጵያ ታሪክን ግን አባቶቻትን ተመካክረው የጀመሩትበትን ጊዜና ለኢትዮጵያም ያላቸውን ራዕይ ያሰቀመጡልን ኢትዮጵያ ስትባል ይህ ይህ ሊኖራት ይህን ልትመስል ይገባል ብለው ያኖሩልን ነገር የለም።ከሳባ ጀምሮ እረ ካዛም በፊት ከኢትጵና (በኢቶጵ ኢትዮፕያዊ) በወንድሙ አቢስ (በአቢስ አቢሲንያ-ሀበሻ) ጀምሮ ብዙ ታሪክ አለን መክሸፍ አለመክሸፉን ግን እጠራጠራለሁ።ያሉን ጥቂት የታሪክ ምሁራንና ጸሃፍት እኛው ጓዳ ውስጥ የራሳችንን ሳያጠኑ ፕሮፌሰር መስፍን እንደሚሉት ቄሳራውያን የውጭ ጸሃፍት የሚጽፉትን ብቻ እንደ ማጣቀሻ እየተጠቀሙ ሊተርኩልን የሚሞክሩት ግን በጣም ያሳዝነኛል። እነ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ቢያድረጉት በዙ አላዝንም የኛው ታሪክ ምሁራን ግን የራሳችንን ታሪክ ከአጼ ልብነ ድንግል መዋዕል እዚሁ እያለላቸው እንደ ገደል ማሚቶ እነ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝና ጄምስ ብሩስ እዲህ እንዲ አሉ ሲሉ የታሪክ ተራኪ መክሽፍ ገጠማቸው ያስብላል።
  ቸር ይግጠመን።
  ሙሉጌታ ሙላቱ (ቫንኩቭር ደሴት)

  ReplyDelete
 51. Dear,Dani lemedenew Rasehen kepolitica Gar yemtayyezew?

  ReplyDelete
  Replies
  1. because politics is a way of life and no one can escape from it.

   Delete
  2. Yes, don't you know that the French Scholar’s said “Those who don't do politics will be done by politics". No one can be out of such pool. Therefore, you better learn how to swim and watch the sharks, alligators and the vulnerable politician.

   Delete
 52. Mule, wendata nesh, bakish! BTW my PC could not let me write in Amharic, and I regret it!

  Coming to the point, that is it the professor argued. And it is insightful. I need our historians to debate on it so that we can make our judgement. I am closely following as to who could respond to his assertions, yet no single historian challenge the professor. alas! But, some ordinary guys are blowing trumpets-and their ground just mare emotions, be it in favour of disfavour. And Mr. MULUGETA you hit the nail on the head please keep up!
  Daniel please approve my comments!

  ReplyDelete
 53. Hey Guys pls it is good if you keep ur comment until u read the book. It is not fair to be in favor of one of them before reading the book. if you don't read believe me you can not give good comment and u will be biased. so pls first u better read the book

  ReplyDelete
  Replies
  1. First Daniel took his time to understood what the book is meant to be, he discussed with his colleagues and other professionals,finally he dare to criticize the book. I don't think you truly Understood what Daniel is onto.

   Delete
 54. ሰውን ከጀርባ መግደል ፈሪ ያሰኛል። ወንድ ከሆንክና በሀሳብህ የምትፀና ከሆነ ለምን ትናንት ብሔራዊ ትያትር መጥተህ ፕሮፍን በአካል አልሞገትክም ወዲያውም ትምህርት ትቀስም ነበር።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የደደብ አስተያየት ማየት ያስጠላኛል፡
   ይህ የሃሳብ ልዩነት እንጂ የወንድነት ጉዳይ አይደለም፣ ዳ/ ዳንኤል ያለውን ሃሳብ በአደባባይ በግልጽ አቅርቧል፣ ለዚህም በራሱ ስም በራሱ ብሎግ ላይ አስፍሯል፡፡ ከዚህ በላይ ትግል እንዲገጥም ነው የምትፈልገው ወይንስ ስድድብ፡፡
   ሙግት ምናምን አስፈላጊ አይደለም መጽሃፉን አንብቧል የገባውንና የመሰለውን አቅርቧል፣ በዚህም ለዚህ ሁሉ ሃሳብ መንሸራሸር ምክንያት ሆኗል፡፡ አንድ ሰው ፕሮፌሰሩም ሆኑ ዳንኤል ሁሌ ትክክል ላይሆን ይችላል፣ ወይንም የሚያቀርበውን ሃሳብ ለሁሉም ላይዋጥ ይችላል፣ ይህ ግን የሚጠላና የሚነቀፍ አይደለም፣ ትክክለኛው የምሁራን አካሄድ መሆን ያለበት ያልተስማማህን ነገር በበቂና አሳማኝ ምክንያት ስህተት መሆኑን ማሳየት ወይንም የሌሎችን ሃሳብ ማንበብና የሚገባሕን መውሰድ፡፡ የእገሌ ይበልጣል አይበልጥም ተራ ፍክክር አይደለም፡፡

   Delete
  2. ከምንም ተነስተህ ሰውን ደደብ ብለህ በመፈረጅ የራሽን ዽብና አሳይተሀል።ወንድ ከሆንክ የሚለውን ቃል ፍካሪያዊ ፍቹን እንጂ እማሪያውዪን አትመልከት።የዳኔል ቲፎዞ ስለሆንክም ዝም ብለህ አትንጣጣ።ያለውን ሀሳብ ምንም እንኳ ጠንካራ ባይሆንም አቅርቧል፤ነገር ግን ጸሀፊው ባለበት ቢሆን ኑሮ የበጠ ያምር ነበር።ከሽተትም ለመማር ይረዳ ነበር።ችግሩ የተፈጠረዉ እኮ ዳንኤል ሀሳቡን አሳማኝ በሆኑና የፕሮፍን ሀሳብ ፉርሽ በሚያደርግ መልኩ አቅርቧል ወይ የሚለው ላይ ነው።ሰዉን ለመፈረጅ በመሮጥ አለማወቅህን አታሳብቅ እሺ ጌታው

   Delete
 55. አሁን እዚህ መጽሐፍ ላይ ቤተ መንግሥቱን አየሁት፡፡
  አጨራረስህ ተመችቶኛል

  ReplyDelete
 56. ሰላም ዳኒ
  ሰለጭብጡ በሁለት ወገን ብዙ ተብሏል እኔ ግን አነድ ነገር ልጠይቅህ አሻው ትችቱ ተተቺዎቹ በህይወት በነበሩበት ስአት ቢሆን መልካም ይሆን እንደነበር ገልጸሀል እውነት ነው እንዳልከው ብዙ ስው ይማር ነበር ይህን ካመንክ ታዲያ ምነው አሁን በቀደም የፕሮፌሰሩን መጽሀፍ ለማብጠልጠል በብሄራዊ ቲያትር ቤት ተጋብዘ እያለ እያም ለመማር የጎጎንበት ዝግጀት ላይ ሳትገኝ ቀረህ ያንተንስ እነዴት እንመልከተው????

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሌሎችም ሰዎች እንዳንተ ጠይቀውኛል፡፡ ጭቅጭቁ አስጠልጦኝ ነበር ዝም ያልኩት፡፡ ግን ልመልስልህ፡፡ እንደዚህ ዓነት መርሐ ግብር ሲዘጋጅ ያቀርባሉ ተብለው ለሚታሰቡት ሰዎች መጀመርያ ይገለጥላቸውና ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆናቸውን ይጠየቃሉ፡፡ ፈቃደኛ ከሆኑም ጥሪ ይደረግላቸዋል፡፡ ለእኔ ስለ መርሐ ግብሩ መኖር መጀመርያ ሰምቶ የነገረኝ ብርሃኑ ደቦጭ ነበር፡፡ ለዚያውም ቦታውንና ሰዓቱን እርሱም ገና አላወቀውም ነበር፡፡ በኋላ በአንድ ፌስ ቡክ ላይ አቅራቢ መሆኔን ሰማሁ፡፡ እንግዲህ የጠየቀኝም የጋበዘኝም ሳይኖር ማለት ነው፡፡ በጉዳዩ ላይ የማነጋግረው ሰው አልነበረም፡፡ በኋላም አዲስ አድማስ ላይ ወጥቶ አየሁት፡፡
   አንደኛ ‹ደበበ እሸቱ እንዳለው የቀረሁት ቡዳ እንዳይበላኝ አይደለም፡፡ መጀመርያውኑ አልተጋበዝኩም፡፡ እንዲያውም ስሜን ያየሁት ከጋዜጣ ላይ ነው፡፡ ለእኔ የአንድን ሰው ፈቃደኛነት ሳያገኙ ስሙን በጋዜጣ ላይ ማውጣት ትልቅ ነውር ነው፡፡ ስለሆነም እኔን ሳይጠይቁ ይገኛል ብለው በጋዜጣ ላይ ስሜን በሚያወጡ፣ ለመጋበዝም ፈቃደኛ ባልሆኑ ሰዎች ፕሮግራም ላይ መገኘት ይህንን ነውር መሳተፍ ስለሆነ ቀርቻለሁ፡፡

   Delete
 57. selam beyalehu Diakon Daniel K. kuhulu askedeme endemakebreh ena endemekorabeh lenegreh efelegalehu.kezih bemeketel leteyekeh yemefelegew neger professor mesfin w/mariam bawetut metsehaf zuria maletem “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” bemilew zuria yehonal.
  1. mendenew criterion to say ye ethiopia tarik keshfual lemalet?Justify with reasons.
  2. letekesetew keshefet teteyaki lehones yemichelew man new? lemen?
  3. yeh tewled kezih keshfet men neger limar yechilal? endet?
  4. yetarik mehuran sele keshefe tarik metsaf yenorebachewal beleh tasebaleh?lemen

  please look the above questions clearly and answer them one by one.

  In addition i want to recommend you that rather than just making it a kind of debate why not it will be a forum of discussion if the other party agrees. this is not a personal case rather we talk about the development of the nation.
  thanks very much,
  Egziabher kante gar yehun.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዳንኤል እኮ ታሪክ አይከሽፍም የሚል መሰረታዊ መከራከርያ ነው ያለው፡፡

   Delete
  2. ወንድሜ ታሪክ አይከሽፍም ሲል እኮ ነው ዳንኤል ሃሳቡን ያቀረበው፡፡

   Delete
 58. ውድ ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት ጥሩ ምልከታ ነው፡፡እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ምልከታህንም ያስፋልህ፡፡ግን ለምን የብስራት አማረንም ፍኖተ- ገድል መጽሐፍ አስተያየት አትሰጥበትም???

  ReplyDelete
 59. ውድ ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት ጥሩ ምልከታ ነው፡፡እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ምልከታህንም ያስፋልህ፡፡ግን ለምን የብስራት አማረንም ፍኖተ- ገድል መጽሐፍ አስተያየት አትሰጥበትም???

  ReplyDelete
 60. I have seen Dn Daniel's comment and Prof's response on it ... in the first place Dani's comment is not fully targeted to the book rather has some personal elements by mentioning un related history. Dani, you and your blog is always the best only when you write on religious facts ... and always controversial when you try to write any thing out of it!!

  ReplyDelete
 61. Thank you Daniel for your scholarly analysis

  I am also impressed by the level of maturity displayed by audience in this thread which is unusual for Ethiopians except some just throw hate words.

  ReplyDelete
 62. Thanks Dani Enwedehalen!!!

  ReplyDelete
 63. selam dani betam temechitognal

  ReplyDelete
 64. እኔ መቼም ዳኒ ላንተም ሆነ ለ ፕሮፌሰር አስተያየት ለመስጠት ጥሩ አቅም ይኖረኛል ብዬ አልገዳደርም:
  ትሁት ለመሆን ሳይሆን ይሄን ያልኩት የናንተን በተለይ የሳቸውን(በዕድሜ ስለሚበልጡክ ነው የሳቸውን ያስበለጥኩት)ያክል ዕውቀት ስለሌለኝና ታሪክ ላይ ያተኮሩ ብዙ መጻህፍትን ስላላነበብኩ ነው፤ መክሸፍንም ሆነ ያንተን ጥናታዊ አስተያየት አንብቤዋለሁ፤ መጽሃፉ ተመችቶኛል ባለኝ የሐገሬ ታሪክ የዕውቀት ደረጃ ስመዝነው የመጽሃፉ ዕውነትነት ይበልጥብኛል፤ ፕሮፌሰሩ ለታሪክ በሰጡት ፍቺ መሰረትነት እየተንተራሱ የገነቡት የመጽሃፉ ታሪክ አብዝሃኛው ተስማሚ ነው፤ ሁሉንም ነጥብ እያነሳሁ አስተያየት ለምስጠት ከዚ በተሻለ የታሪክ ዕውቅት በተለይም ደግሞ መጽሃፉ ላይ የተተቹትን ሰዎች መጽሃፍ ማንበብ እንዳለብኝ እገምታለሁ፤ እርግጠኛ ነኝ አንተም ሆንክ እሳቸው መጽሃፍቶቹን እንብባችሁ እንደጻፋችሁ፤ ለአሁን ግን ያሳብኩትን አንድ ነገር ልነገርህ ታሪክ ጸሃፊ ከታሪኩ ጋር ሊወቀስ አይገባውም ስትል ገርሞኛል፤ እንዴ ለምንድነው እሱ የማይወቀሰው??፤ በርግጥ ፕሮፌሰሩ እንዳሉት አንድ የታሪክ ጸሃፊ ስለሚጽፈው ታሪክ ያለው የመጻፊያ አላማ ተወቃሽነቱን ሊቀንሰውም እልያም ጭራሹንም ላያሶቅሰው ይችላል፤ ልክ ፈረንጆቹ ለማጣላት፣ለመከፋፈል አልያም ደግሞ ስለሰው ለማወቅ በሚል አላማ ተነስተው የኛን ታሪክ ሲጽፉ ጽሁፋቸው ከሚፈጥረው የተንኮል መርዝ ውጪ እነሱን በዕውነተኛ ታሪክ ልንወቅሳቸው አንችልም፤ ምክንያቱም አላማቸው ከታሪኩ ባለቤት ማህበረሰብ ጋር የተያያዘ አልያም ደግሞ ዕውነተኛውን ታሪክ ለማሳወቅ ብለው ያደረጉት ነገር እንዳልሆነ ግልጽ ነውና፤ ነገር ግን የኛ ሐገር ጸሃፍት እንደፈረኝጆቹ አይነት ወይም ጋሽ መስፍኔ እንዳሉት ከፈረንጆቹ ብቻ ተምረው ከሆነ የጻፉት በጣም ተወቃሽ ናቸው፤ ምክንያቱም የነሱ መጽሃፍ በዚህ ማህበረሰብ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ እንደ ባዕዳኖቹ የፖለቲካ ጠብ ሳይሆን ስር ነቀል የወዳጅ ቡጢ ነው የሚሆነው፤
  እንዳውም እነ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት፣ ዶክተር ሥርግወ ሐብለ ሥላሴና ፕሮፌሰር መርዕድ የጻፉት መጽሃፍ የሚያትተው ታሪክ ልክ ፕሮፌሰር በመጽሃፋቸው እንዳስቀመጡት አይነት ከሆነ በዕውነት ጋሽ መስፍኔን ለመውቀስ አልሻም፤ ለምን ቢባል የነዚህን ሙሁራን መጽሃፍ(ሃሳብ) ስህተት እዛ መጽሃፉ ላይ ከመካከለኛውና ከጥንቱ ዘምን የኢትዮዺያ ነገስታት ድርሳናት እየጠቀሱ አስረድተዋል፤ በጣም የነገሩ ምስቅልቅልነት ሊረዳኝ የሞከረው በተለይ ጋሽ መስፍኔ መጽሃፉ ማብቂያ አካባቢ ባስቀመጦቸው የነፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት የኢትዮዺያን የቀድሞ ግዛት የሸራረፉ ካርታዎች ነው፤ ለማንኛውም ለመደምደም የነዚህንም ሙሁራን መጻህፍት ማንበብ እንዳለብኝ አምናለሁ፤
  በተረፈ የ ፕሮፌሰር መጽሃፍ ከምሁራዊ ዕወቅት ሳይሆን ከሰዎቹ ጋር ካላቸው ግላዊ ተቃርኖ የመነጨ ነው በሚል አይነት ጽሁፍህ አመሻሽ ላይ ያሰፈርከው ሃሳብ አንተም ላይ ጥያቄ እንዳነሳ እስገድዶኛል! ይኸውም እንተስ ይህን ጽሁፍ የጻፍከው ለጋሽ መስፍኔ ካለህ ግላዊ አመለካከት የመነጨ ቢሆንስ? ሙሁራን ሆናችሁ ህዝብ ሊጠቀምበት የሚችለውን ሃሳባችሁን ወደ ጓዳ እየወዳችሁ ድጋፍና ጥላቻ አትፍጠሩ ይሄ ካልሆነ ግን አንድ ጽሁፍክ ላይ እንዳነበብኩት ይሄንንም ትውልድ “ቶምና ጄሪ” ወረውታል ማለት ነው??!!

  አመሰግናለሁ::

  ReplyDelete
 65. I have got this reply from internet and i think this will help the debate become hot and clear....Mr. Daniel would you please approve this bechewa denb......tnx


  አቶ ዳንኤል ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው እውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ አንጂ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም፤ አቶ ዳንኤል ሳላውቀው በጻፈው ላይ አስተያየት ስሰጥ ይህ ሁለተኛዬ ነው፤ ከዚህ በፊት በአንድ ጋዜጣ ላይ በጣም የታወቀውን የአየርላንድ ችጋር በ150 ዓመታት ያህል አቅርቦት በማየቴ አስተያየት ሰጥቼበት ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ስለመክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ በጻፈው ላይ አጭር አስተያየት ልስጥ፤ እንዲያው እንትንን እንትን ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል የሚባለውን በመከተል እንጂ ትርፍ ይኖረዋል ብዬ አልገምትም፤ ከደርግ ዘመን ጀምሮ የተለያዩ ካድሬዎች ደብተራዎችም ጭምር ማነብነብን እንደተናጋሪነት ሠልጥነውበታል፤ ስለዚህም ሰውም ማነብነባቸውን እንደእውቀት እየወሰደው ይወናበዳልና በጊዜው መልስ መስጠት ግዴታ ይመስለኛል፤ የሰው ልጅ በምን ይታፈራል? በወንበር፤ በወንበር አይደለም በከንፈር፤ ይባላል፡፡

  ነገር ሳላበዛ ጥቂት ነጥቦችን በማንሣት የአቶ ዳንኤልን የማንበብ ችሎታና የተንኮል ክህነት ብቻ ለአንባቢዎች ላሳይ፤ ስለአስተያየቱ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ አይደለም፡፡

  አንደኛ፣ ደጋግሜ እንብቤዋለሁ ይላል፤ ይህንን ባይነግረን ጥሩ ነበር፤ በመናገሩ ብቻ እንዳናምነው ማስረጃ ይሰጠናል፤ ያላነበበውን ደጋግሜ አንብቤዋለሁ ማለት ያስፈለገበት አስገዳጅ ምክንያት ምንድን ነው? አውቃለሁ ብሎ በመነሣት ለማሞኘት ወይም ለማታለል ካልሆነ በቀር ሌላ ምክንያት ያለ አይመስለኝም፤ እንደአቶ ዳንኤል ያለውን ለማስጠንቀቅ ደጋግሜ አነበብሁት በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ‹‹የዩኒቨርሲቲን ዓለም የማያውቁ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት እንዳይሳሳቱ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በአካል በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሆነው ልባቸው ከደብተራ ተንኮል ላልጸዳም ቀናውን የእውነት መንገድ እንዲያመለክታቸው እመኛለሁ፤›› የሚል ተጽፎ ነበር፤ ይህንን አቶ ዳንኤል አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡

  ሁለተኛ፤ ‹‹ለመሆኑ ታሪክ ይከሽፋል? የክሽፈት ታሪክ ሊኖር ይችላል እንጂ የከሸፈ ታሪክ ሊኖር ይችላል? የስኬት ታሪክ ይኖራል እንጂ የተሳካ ታሪክ ይኖራል? አንድን ታሪክ ከሽፏል ወይም ተሳክቷል የሚያሰኘው ምን ምን ሲሆን ነው? … በመጽሐፉ የምናጣው ታላቁ ነገር ይሄ ነው፤›› በዚህ ትርጉም የማይሰጥ የቃላት ድርደራ ላይ ምንም አስተያየት መስጠት አይጠበቅብኝም፤ ይቀጥልና ‹‹.. የታሪክን ክሽፈትና ስኬት መበየኛ ነገሮችን አስቀድመው በማሳየት አንድ ታሪክ ከሸፈ ወይም ተሳካ የሚያሰኙትን መመዘኛዎች …›› ይላል አቶ ዳንኤል፤ ካላነበበው ‹ደጋግሜ አንብቤዋለሁ› በማለት ብቻ ጭንቅላቱ ውስጥ አይታተምለትም፤ የሚከተለው እንደሚነበብ ሆኖ የተጻፈ ነበር፤ ‹‹መክሸፍ የምለው አንድ የተጀመረ ነገር ሳይጠናቀቅ ወይም ሳይሳካ እንቅፋት ገጥሞት መቀጠል ሳይችል ዓላማው ሲደናቀፍና በፊት ከነበረበት ምንም ያህል ወደፊት ሳይራመድ መቅረቱን ነው፤›› ይህ ተጽፎአል! አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡

  ሦስተኛ፤ ‹‹ታሪክ ጸሐፊዎቹን ከታሪኩ ጋር አብሮ መውቀጥ ከተልባ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ ዓይነት ይሆናል››! ይላል፤ ይህ ሰው አንብቤአለሁ፤ አውቃለሁ፤ ሲል በመሃይም ድፍረት ነው፤ የሚከተለው ተጽፎአል፤ ‹‹አንድ ሰው በአገርና በሕዝብ ጉዳይ ላይ ከጻፈ ‹‹ማንም ዜጋ በጉዳዩ ላይ የመሳተፍና ሀሰቡን በሙሉ ነጻነት የመስጠት መብት አለው፤ አለዚያ በየጓዳችን በሐሜት ብቻ እየተዘላዘልን እውነትን አንጥሮ በአደባባይ የማውጣቱን ዘዴ ሳንማር ሌላ ሦስት ሺህ ዓመታት እንቀጥላለን፤›› ይህንን አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡

  አራተኛ፤ በራሱ ላይ ሲፈርድ ቶሎ ሳይጽፍ መቆየቱን ለማስረዳት ምናልባት ከእሱ የተሻለ ሰው ቢጽፍ፣ ምናልባት ፕሮፌሰር ባሕሩ ቢጽፍ፣ ምናልባት የታሪክ ሊቃውንትቱ ተማሪዎች ቢጽፉ፣ ምናልባት የታሪክ ክፍሉ ቢጽፍ በማለት ጠብቆ እንደነበረ ይገልጻል፤ እነዚህ ሁሉ የሱን ምኞት እሱ በፈለገው ፍጥነት ሳያሙዋሉለት ቀሩና እነፕሮፌሰር ባሕሩን ላጨበት ሥራ ራሱን አቀረበ፤ የሱ ድፍረት የሌሎቹን እውቀት የሚበልጥ ለማስመሰል ጻፈ፤ ድፍረቱን ልናደንቅለት ይገባል፤ በማያውቁት ጉዳይ ደረትን ገልብጦ በሙሉ እምነት ማነብነብ የካድሬዎች ባሕርይ ሆኖ በቤተ እግዚአብሔርም ገብቶአል፡፡  አምስተኛ፤ አቶ ዳንኤል ከአዋቂነት ወደመንፈሳዊነት ይሸጋገርና ‹‹አንድን አካል መልስ ለመስጠት በማይችልበት ጊዜና ሁኔታ መሄስና መውቀስ ከሞራል አንጻር ፍትሐዊ አይሆንም፤ የሀገሬ ሰው ‹ሙት ወቃሽ አትሁን››› እዚህ ደግሞ ጭራሽ ሊወጣበት ከማይችለው የአለማወቅ ማጥ ውስጥ በድፍረት ገባ! ‹‹ሞራል›› ስለሚለው ነገር ምንም እንደማያውቅ ሳያውቅ አወጀ፤ ድፍረት ብቻውን በምንም መንገድ እውቀት አይሆንም፤ ለመራቀቅ ፈልጎ ራሱን በአለማወቅ አዘቅት ውስጥ ከተተ፡፡

  ስድስተኛ፤ በጽሑፉ መደምደሚያ ላይ የደብተራ ተንኮል አፈትልኮ ይወጣል፤ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ያነሣና በደብተራ ተንኮል አንዱን ‹‹ዶክተር›› የሚለውን መልክ የሌለውና ስም የሌለው የደብተራ ምሥጢር ያደርግና፤ ‹‹እኒህ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ዶክተር ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዘንድ በማን በኩል እንደሄዱ ፕሮፌሰር መስፍን ያውቃሉ፤›› ብሎ ይለጥፍብኛል፤ እግዚአብሔር ያሳያችሁ ስሙን ያልጠቀሰውንና የማላውቀውን ሰው የእኔን ስም ጠርቶ እንደማውቀው አድርጎ ሌላ ስሙን ያልጠቀሰውንና እኔ የማላውቀው ‹‹ዶክተር›› ወደመንግሥቱ ያቀረበ እያለ ውሸት ሲያጠነጥንና ሲፈትል ጊዜ ያጠፋበት ምክንያት አልገባኝም፤ ተንኮሉ እዚህ ላይ አያበቃም፤ ታደሰ ታምራትን ‹‹መንግሥቱ ከመሸኘቱ በፊት ግን ‹ከዶክተር እገሌ ጋር ቅሬታ አላችሁ መሰል፤ አንዳንድ ነገር ነግሮኝ ነበር፤ እዚያው ተነጋግራችሁ ፍቱት፤ አላቸው፤›› ይልና የመጨረሻዋን የደብተራ ተንኮል ጣል አድርጎ ይደመድማል፤ ‹‹አሁን እዚህ መጽሐፍ ላይ ቤተ መንግሥቱን አየሁት፡፡›› ምን እንዳየ፣ የት እንዳየ፣ ምንና ምን እንደተገናኘ የደብተራ ምስጢር ነው፤ ያቀረበውን ሁሉ የማን ባለሙዋል ሆኖ ያገኘው እንደሆነም አይናገርም፤ እንዲህ ያለ ሞላጫነት! ስለእውቀት ከተጻፈ መጽሐፍ ተነሥቶ ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ጓዳ ገብቶ፣ ስሙ የማይጠራ ዶክተርን መነሻ አድርጎ፣ ይህን ሁሉ እኔ እንደማውቅ ተናግሮ በድንቁርና ምርጊት ይደፍነዋል! እንዲህ ያለ ሰው ስለእውቀት ለማውራት ለምን ይነሣል? ከበሽታ በቀር ምን ሌላ ይገፋፋዋል?

  ReplyDelete
 66. Both Dani and Prof Mesfin are real andrespected people, who voice their point without fear , with their name , picture and live in Ethiopia. For me both of you are HEROs. Please Ethiopians lets allow opinions run freely, why do we insult one another for opinion. How comes we want a democrat government while we are not democrats and do not believe in free speech and do not respect people's opinion. Please let's change.
  Beth

  ReplyDelete
 67. የመንግስቱ ኃይለ ማርያም አገዛዝ ያለፈና ያበቃለት ስርዓት ነው፡፡በተፈጥሮዬ የወደቀውን
  ዛፍ መጨፍጨፍ ያለቀለትን ነገር መጭመቅ አልወድም፡፡የማላምንበትን ነገር ሲሰራ
  ያለፈውን ሳይሆን ያለውን ሥርዓት መታገል እመርጣለሁ፡፡እስርቤት ያሉትንም ሰዎች
  በተመለከተ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የተያዘ ስለሆነ ስለዚህ ወቅት መናገር አልፈልግም፡፡እሱ
  መንግስቱ ኃይለ ማርያም ደስ ካለው ስለኔም ሆነ ስለሌሎች የፈለገውን ይበል፡፡እኔ ግን
  ስለሱ አስተያየት ከመስጠት ጠቆጥቢያለሁ፡፡ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም(የገነት አየለ
  ቁጥር 2 መጽሀፍ ከተናገሩት የተወሰደ)........pls

  ReplyDelete
 68. Would Daniel tell us how he saw the palace in the story, and if he can what he saw,too? Or am I expected to expect a reveled truth?

  ReplyDelete
 69. It makes me laugh when people talk in about History. The EPRDF gov't attempted to bury the Ethiopian history. Is it maybe the gov't want to hide its dark secrets like that of the Eritrean case? once ato berket simon mentioned about this generations claim on Eritrea as a dead end. however, not only the case of Eritrea but a lot of dark weyane secrets attempted to be destroyed. Gov'ts may fall, empires may collapse but history would survive as a living expression. on the name of encouraging science they attacked the history of the people. look at our high schools today every student would ask u " what is the importance of history if it does bot beak a bread?" period all is about survival............

  ReplyDelete
 70. lole hula
  prof. Mesfin is our hero

  ReplyDelete
 71. i may misunderstood the content of the book. but i think prof. book didnt mean it. it doesnt say that "tarik yikeshfal". i couldnt find the page/ paragraph that talks about your say. he literaly tried to discuss esues that failed though out the history of ethiopia.those which were good start but directed to wrong direction. eduction...politics...economic policies. the effects of our nation as an ethiopian hasnt been outshined.

  ReplyDelete