Wednesday, January 2, 2013

‹መግደል ደስ ይለኛል›

ሰሞኑን በኒውዮርክ በበጎ ፈቃድ በተሠማሩ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ላይ እሩምታ የከፈተው ተኳሽ ይህንን ያደረገበትን ምክንያት ‹መግደል ደስ ይለኛል› ብሎ ነበር የገለጠው፡፡ በዚያው ዕለት በአንድ የዋና ቦታ ከልጆቼ ጋር ሄጄ ነበር፡፡ በዚያ የዋና ቦታ በውኃ የሚሠራ የልጆች መጨዋቻ ሽጉጥ የያዙ ሕጻናት በገንዳው ውስጥ ገብተው ልባቸው እስኪጠፋ ይጫወታሉ፡፡
‹አይ ኪል ዩ› ይለዋል አንዱ ሌላውን፡፡
‹‹ኖ ኖ›› ይላል ተገድለሃል የተባለው፡፡
 ‹ኖ ኖ ዩ ኦልሬዲ ዴድ› ይላል ‹ገዳዩ›፡፡
ገርመውኝ ጠጋ አልኩና አዋራቸው ጀመር፡፡
‹‹መግደል ጥሩ ነው እንዴ ልጆች›› አልኳቸው፡፡
‹‹አይ ላይክ ኢት›› አለኝ ‹ሽጉጡን› የያዘው ልጅ፡፡
‹‹መግደል ትወዳለህ›› አልኩት፡፡ ዝም ብሎ ያየኝ ጀመር፡፡ 

‹‹መግደልኮ መጥፎ ነው፤ ወንጀልም ነው›› አልኩት ድምጼ ሊጠፋ ደርሶ፡፡ አንድ ሰምቼው የማላውቀውን ፊልም ጠራልኝና ‹እዚያ ላይ አላየኸውም፤ እንትና እንትናን ሹት ሲያደርገው›› አለኝ፡፡
ልጆቻችን የሚያዩዋቸው ፊልሞች፣ የሚጫወቱባቸው ‹ጌሞች›፣ የሚለብሷቸው ልብሶች፣ የሚጠቀሙባቸው ደብተሮች፣ የሚይዟቸው የምሳ ዕቃዎች ይታዩኝ ጀመር፡፡ ለእኛ ልጆች ‹ጀግና› ምንድን ነው? እነርሱ የሚያደንቁትና ቢሆኑት የሚወድዱት ምንድን ነው? አርአያቸውና አይከናቸው ማነው?
ሰው አርአያውን ወይም ጀግናውን የሚወስደው ከማኅበረሰቡ ነው፡፡ ማኅበረሰቡ ሲያደንቅለት፣ ሲያወራለት፣ ሲያሞግሰው፣ ሲዘፍንለት፣ የሰማውን፤ ብሎም እርሱ ራሱ ደጋግሞ ያየውን የሰማውንና የተከታተለውን ጀግናና አርአያ ያደርገዋል፡፡ ሰው የማያውቀውን ሰው ጀግና አያደርገውም፡፡ ስሙ ከፍ ብሎ ያልሰማውን ሰው አይከን አያደርገውም፡፡ ደጋግሞ ያላየውን ወይም ያልሰማውን ሰው አያደንቀውም፤ አይከተለውምም፡፡
ለመሆኑ አሁን ስለነማን ነው በብዛትና በስፋት እየተወራ፣ እየታየስ ያለው? ይህንን ስንመልስ የልጆቻችን ዕጣ ፈንታን ማየት እንችላለን፡፡
ስለ ዘፋኞችና የፊልም ተዋንያን፣ ስለ ኳስ ተጨዋቾችና ስለ ሞዴሊስቶች፣ በየሚዲያው ይተረካል፣ በየጋዜጣው ይጻፋል፣ በየኢንተርኔቱ ይለቀቃል፣ በየማኅበራዊ ሚዲያው ይበተናል፡፡ የበሉትና የጠጡት፣ ያወጡትና ያወረዱት፣ የለበሱትና የተጫሙት፣ ያገቡትና የፈቱት፣ የነዱትና የገዙት፣ ያጠፉትና ያለሙት ሁሉ ይዘከዘካል፡፡ የእነዚህ አካላት የየዕለት ውሏቸው እንደ ዜና መዋዕል በየቀኑ ይፈተፈታል፡፡ እንኳን ያወሩትና ያደረጉት ያሰቡትና የተመኙት ሁሉ ይቀርባል፡፡ ፎቷቸው በደብተር ላይ ይለጠፋል፣ በልብስ ላይ ይታተማል፣ በፖስተር ይዘጋጃል፣ በቦርሳ ላይ ይወጣል፡፡
ለልጆቻችን ጀግኖች ማለት እነዚህ ናቸው፡፡ ደጋግመው ሲወደሱ የሚሰሟቸው፤ ደም ከፍለው የሀገራቸውን ነጻነት ከጠበቁት ይልቅ የሀገራቸውን ሚዲያ ሳንቲም ሳይከፍሉበት የወሰዱት የልጆቻችን ጀግኖች እነዚህ ናቸው፡፡ ፎቷቸውንና ሥዕላቸውን ለማየት ሙዝየም መሄድ ከሚያስፈልጋቸው የሀገራቸው ጀግኖች ይልቅ ፎቷቸውን እንደ ልብ ደብተራቸውና ቦርሳቸው ላይ የሚያገኟቸው የልጆቻችን ጀግኖች እነዚህ ናቸው፡፡
እነዚህ የልጆቻችን ጀግኖች በተሠማሩበት ሞያ ጎበዞችና ታዋቂዎች ቢሆኑም ገልበጥ ተደርገው ሲታዩ ግን አንዳንዶች ሌላ ገጽታም ደግሞ አላቸው፡፡ ያገባሉ ይፈታሉ፣ ይማግጣሉ፣ ይቀብጣሉ፣ አደንዛዥ ዕፅ ይጠቀማሉ፣ እሥር ቤቶችን በተደጋጋሚ ይጎበኛሉ፣ የዘረኝነት ስድብ ይሳደባሉ፣ ይደባደባሉ፣ ያልተፈቀደ መሣርያ ይይዛሉ፣ ሕጻናትን ያባልጋሉ፣ ለፍቅረኞቻቸው ታማኝ አይሆኑም፡፡ ስለ እነርሱ ሲተረክ ግን ይኼ ሁሉ ይነገራል፤ ይዘከዘካል፤ ይተነተናል፡፡ ‹ታዋቂው እገሌ› እየተባለ አስነዋሪውም ነገር አብሮ ይነገርለታል፡፡ ልጆቻችንም ይህንን ይሰማሉ፡፡ ለእነርሱ የሚያደንቁት ሰው ያደረገው ሁሉ የሚደነቅ፣ የሠራው ሁሉ ትክክል፣ የፈጸመውም ሁሉ ሊከተሉት የሚገባ አድርገው ይወስዱታል፡፡
አሁን ልጆቻችን ጀግኖቻቸውን የሚወስዱት ከኢንተርኔት፣ ከፊልምና ከሚዲያ ነው፡፡ ከተረቶች፣ ከቀድሞ ታሪክና ከማኅበረሰባዊ ክዋኔዎች ጀግኖችን የሚወስዱበት ዕድላቸው እየተሟጠጠ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሳይንቲስቶች፣ ደራስያን፣ የሀገር መሪዎች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ ለሰው ልጅ ደኅንነት በጎ የሚያደርጉ ሰዎች፣ የፈጠራ ባለሞያዎች፣ አዳዲስ ነገሮችን የሚያገኙ አሳሾች፣ ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው ነጻነትና መብት የተሠው አርበኞች፣ እውነትንና መረጃን ፍለጋ ሕይወትን የሚከፍሉ ሰማዕታት ጋዜጠኞች፣ የሚዲያዎችን ውቃቤ መሳብ አልቻሉም፡፡ ስለእነዚህ እናቅርብ ብለው የሚነሡ ሚዲያዎችንም ስፖንሰር የሚያደርጋቸው የለም፡፡ የሚዲያ ባለቤቶችም ‹›ገንዘብ አታመጡም› ብለው ፊታቸውን ያዞሩባቸዋል፡፡
በአንድ ወቅት የእንግሊዟ ልዕልት ዲያናና የካልካታዋ ቅድስት ማዘር ቴሬዛ ተከታትለው ይህችን ዓለም ተሰናበቱ፡፡ የዓለም ሚዲያዎች ሰፊውን ሽፋን የሰጡትና ብዙ ሰዎችም መስማት ይፈልጉ የነበሩት ስለ ልዕልት ዲያና ነበር፡፡ ልዕልት ዲያና አሟሟቷ አሳዛኝ ቢሆንም ለሰዎች ልጆች በሰጡት ክብርና ፍቅር፣ አገልግሎትና ደግነት ግን ማዘር ቴሬዛ ከልዕልት ዲያና ይበልጡ ነበር፡፡ በልዕልት ዲያና ሞት ከተጎዱትም በላይ በማዘር ቴሬዛ ሞት የተጎዱት ይበልጡ ነበር፡፡ ነገር ግን የልዕልት ዲያና ጉዳይ የማዘር ቴሬዛን መሞት እንኳን እስከ ማስረሳት ደርሶ ነበር፡፡
ለዚህ ነው እኛ ወላጆች ‹በትምህርት ጎበዝ መሆን አለብህ፣ ማጥናት አለብህ፣ አንደኛ መውጣት አለብህ፣ ሳይንቲስትና ሐኪም፣ ጎበዝ ነጋዴና መምህር፣ የሀገር መሪና ተመራማሪ፣ መሆን አለብህ› እያልን ልጆቻችንን የምንመክራቸው ምክር አንጀታቸው ጠብ ሊል ያልቻለው፡፡ እኛ ሁኑ ስለምንላቸው ነገሮች ከእኛ ውጭ ማን ሲያወራ ሰምተው ያውቃሉ? ለአንድ ሐኪም ሦስት ሺ ብር ለእንድ የፊልም ተዋናይ ደግሞ ሦስት ሚሊዮን ብር፣ ለአንድ ሳይንቲስት አምስት ሺ ብር ለአንድ ተጨዋች ግን ሃምሳ ሚሊዮን ብር ሲከፈለው እያዩና እየሰሙ ‹ማን ፉል አለ›፡፡ ለሀገሩ ድንበር ከተዋጋው ይልቅ ስለውጊያው ፊልም የሠራው ታዋቂ ሲሆን እያዩት፣ ላቦራቶሪውን ዘግቶ የካንሰር መድኃኒት ለማግኘት ከሚኳትነው ይልቅ ስለ ካንሰር የዘፈነችው ስትደነቅ እያዩ፤ ምን አድርጉ ነው የምንላቸው፡፡
ይኼ መሣርያ ይዞ የሚተኩሰው፣ የኼ እንኳን እንትናን አናቱን የበረቀሰው፣ ይኼ እንኳን ተገለባብጦ ተራራውን ያለፈው፣ ረ ማነው እንኳን እቴ ይኼ በካራቴ ሰዎቹን የረፈረፋቸው እርሱኮ ነው የምናምንና የምናምን ሽልማት አሸንፎ ሚሊዮኖች ሲያጨበጭቡለት፣ ሚሊዮን ብሮች ሲጎርፉለት፣ ሚሊዮን ወንዶች ሲሞቱላት፣ ሚሊዮን ሰዎች የፌስቡክና የትዊተር ገጽዋን ሲጎበኙላት የምንሰማው፡፡ አሁን ማ ይሙት የአንስታይን ፎቶ ያለበት ቦርሳ፣ የሞዛርት ሥዕል ያለበት ደብተር፣ የጋሊሊዮ ምስል ያለበት ምሳ ዕቃ፣ የሐዲስ ዓለማየሁ ሥዕል ያለበት ቲሸርት፣ የቶማስ ኤድሰን ሥዕል ያለበት ፖስተር፣ የምኒሊክ ሥዕል ያለበት እስክርቢቶ አግኝተን እናውቃለን? ልጆቻችንስ ይዘው ያውቃሉ?
ታድያ ‹መግደል እወዳለሁ› ቢሉ ምን ይፈረድባቸዋል፡፡ በየቤታችን የገጠምናቸው ዲሾች በየቀኑ ‹ጀግና ገዳዮችን› ሲያሳዩዋቸው አይደል እንዴ የሚውሉት፡፡ በገዛ ገንዘባችን፣ በገዛ ዲሻችን፣ በገዛ ቴሌቭዥናችን እነርሱ አይደሉ እንዴ ሳይከፍሉ አድናቂ እያፈሩበት ያሉት፡፡ ‹በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን አጣሁት› አለ ያገሬ ሰው፡፡ በተለይማ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የልጆቻቸውን ጭቅጨቃ ለመገላገል ቴሌቭዥን ላይ አፍጥጠው እንዲውሉ ፈርደውባቸዋል፡፡
‹እዚያ ምን ወሰደህ› አትሉኝም፡፡ እዚሁ በየልጆች ማጫወቻውኮ ልጆቹ ተኩሰው እንዲጫወቱ የተዘጋጁ ብዙ ‹መግደያዎች‹ አሉ፡፡ በልደት ቀናቸውም ሽጉጥና መትረጊስ ገዝተው ‹እንኳን ለዚህ አደረሰህ› የሚሉ ወዳጆችም አሉ፡፡ በየሞባይላችንም የተኩስ መለማመጃ ‹ጌሞች› ሞልተዋል፡፡
እና ‹መግደል ደስ ይለኛል› የሚል ትውልድ ብናፈራ ምን ይገርማል፡፡ ይኼው በስለት ሚስቶቻቸውን ከሚወጉት ጀምረን እንደ ጦርነት ፊልም በቦሌ ጎዳና በመትረጊስ ሚስቶቻቸውን እስከሚረፈርፉት ድረስ አፍርተናል፡፡ አንበሳ ገዳይ፣ ነበር ገዳይ፣ ዝሆን ገዳይ፣ ቀጭኔ ገዳይ ዛሬ ተለውጠው፣ ዘምነው ዘምነው ሚስት ገዳይ፣ ባል ገዳይ፣ ልጅ ገዳይ፣ ወላጅ ገዳይ ሆነው ከመጡ ‹መግደል ያባቴ ነው ጠላትን ማደን› ብለን መዝፈን ሲያንሰን ነው፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው

31 comments:

 1. YES DN DANIEL IT IS A BURNING ISSUE, AM ALWAYS WORRY WHEN IT THINK HOW CAN WE CONTROL IT.

  ReplyDelete
 2. Tnx Dani, its a gud view. " lib awka" neh eshi. Egziabher Amlak tsegawn yabzalih.

  ReplyDelete
 3. the big problem which aggravates the situation is the media.and parents must carefully select toys to their children.

  ReplyDelete
 4. ለሀገሩ ድንበር ከተዋጋው ይልቅ ስለውጊያው ፊልም የሠራው ታዋቂ ሲሆን እያዩት፣ ላቦራቶሪውን ዘግቶ የካንሰር መድኃኒት ለማግኘት ከሚኳትነው ይልቅ ስለ ካንሰር የዘፈነችው ስትደነቅ እያዩ፤ ምን አድርጉ ነው የምንላቸው፡፡

  ReplyDelete
 5. I think dani the burning is issue about our church can u say samthing pls

  ReplyDelete
 6. ዳኒ ጽሑፉ በጣም ተመችቶኛል ሁሉም እኔ ውስጥ ሲመላለሱ የነበሩ ጥያቄዎች ናቸው በተለይ አንዱን መዘዝ አድርጌ ሳወጣ በኤፍ ኤም ራዲዮኖቻችን ላይ በሚተላለፉት ፕሮግራሞች ላይ ያነሳኸው ሐሳብ ነው ይህ ነገር ለእኔም ጥያቄ ሆኖ ቀርቷል ማንንስ እንደምጠይቅ ያላወቅኩበት ነው:: ብዙ ግዜ ሬዲዮ አዳምጣለሁ ነገር ግን የሐገርን ታሪክ እና ስለሌላ መወራትና የህዝቡን አስተሳሰብ የሚቀይሩ (በበጎው መንገድ) ፕሮግራሞች ሁሉም ማለት ይቻላል ፕራግራማቸውን ያለአጋር ድርጅቶች ነው የሚያቀርቡት:: ለምሳሌ ያህል በኤፍ ኤም 97.1 ከሚቀርቡት ፕሮግራሞች መሐከል ርዕዮት: አዲስ ዜማ:ብራና እና የሸገር በኤፍ ኤም አብዛኛዎቹን መጥቀስ ይቻላል:: ይህ ለምን ሆነ? እኔ አላውቅም ድርጅቶቹ ያውቃሉ:: እውነቱን ለመናገር እነዚህ ድርጅቶች ገና የስፖንሰር ምንነት አልገባቸውም:: በአሁን ሰዓትም ሕዝቡ ምን ይፈልጋል የሚለውን ራሱ ማወቅ የተሳናቸው ይመስለኛል:: ለማንኛውም እነዚህ ድርጅቶች ይህንን ጽሑፍ ቢመለከቱት የሆነ ነገር የሚያገኙ ይመስለኛል:: በመጨረሻም ዳኒ በጣም አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ...በኤፍ ኤም 97.1 ከሚቀርቡት ፕሮግራሞች መሐከል ርዕዮት: አዲስ ዜማ:ብራና እና የሸገር በኤፍ ኤም አብዛኛዎቹን መጥቀስ ይቻላል...I couldn't understand the thing you mentioned about fm programs. specially most of sheger fm (which i listen most of the time) programs are not against daniels or your comment. I wish somebody can explain for me.

   Delete
 7. “አሁን ገና በራልኝ አለች እብድ ቤቷን አቃጥላ!”

  ጆን ደብልዩ ሎረንስ የተባለ ፀሐፊ በመጽሐፉ እንዲህ ብሏል፡-

  ልጅ እየተወቀሰ ካደገ ማውገዝን ይማራል፡፡
  ልጅ በጥላቻ አካባቢ ካደገ መደባደብን ይማራል፡፡
  ልጅ እየተፌዘበት ካደገ ዓይነ አፋርነትን ይማራል፡፡
  ልጅ በሐፍረት ካደገ ጥፋተኝነትን ይማራል፡፡
  ልጅ በመቻቻል ካደገ ትዕግሥተኝነትን ይማራል፡፡
  ልጅ በመበረታታት ካደገ በራስ መተማመንን ይማራል፡፡
  ልጅ በመሞገስ ካደገ ማድነቅን ይማራል፡፡
  ልጅ በአግባብ ካደገ ፍትሕን ይማራል፡፡
  ልጅ ዋስትና ባለው ኑሮ ካደገ ሰውን ማመን ይማራል፡፡
  ልጅ በተቀባይነትና በወዳጅነት ካደገ በአጠቃላይ ዓለም ፍቅርን ማግኘት ይማራል፡፡


  “ልጅ ለእናትዋ ምጥ አስተማረቻት” ቢሉ ማን ያምናል? ሕጻናትን ሳይንከባከቡ ፍሬውን መጠበቅም እንዲሁ ነው። “አለሽ መስሎሻል ተበልጠሽ አልቀሻል” አለች እምዬ ኢትዮጲያ። ፊት ለፊቴ አንድ ትንሽ ብላቴና ኳሷን እንደ ጉድ እያንከባለለ ትንፋሹ ቁርጥ እስክትል ድረስ እንደ ጉድ ይሮጥ ነበር። “የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች አሉ አባባ ተስፋዬ! የዛሬ አበባዎች ናቸው ለነገ ፍሬ የሚሆኑት” አለኝ ሕሊናዬ። ዛሬ ሕጻናት አበቦችን በስስት ሳንንከባከብ ፣ የተስፋ ውኃ ሳናጠጣ ፣ በስጦታ ሳንኮተኩት፣ ፀሐይ ጊዜያችንን ሳንሰጣቸው ምን ዓይነት ፍሬ ይሆን የምንጠብቀው? አለኝ ሕሊናዬ ደገመና።


  “ልጅህንም አባትህንም ስታጎርስ ለአንዱ ታበድራለህ ለሌላው ትከፍላለህ” እንዲሉ እስኪ ለልጆቻችን ሞራል እናበድራቸው። ለሕጻናቱ ትኩረት መስጠት በኛ ሀገር እንደ ሕልም ነው የሚታየው። የኛ ነገር “ሞት ሲደርስ ቄስ ጦር ሲደርስ ፈረስ” ሆነብንኮ ሰዎች! የልጆች አስተዳደግ ፣ ፍላጎት፣ ዓላማ ወዘተ ተረፈዎች ለኛ ትርፍ ነገር ናቸው። በመንፈሳዊም ሆነ በዓለማዊ ሕይወት አንዳች ድጋፍ አናደርግላቸውም። “በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ” የሚለው ቃል ተረስቶ “በአባቶችሽ ፋንታ ልጅ የሚወልድልሽ ጠፋ” እንዳይሆንብን ያሰጋል። የሰለጠነው ዓለም ግን ልቡና ዓይኑ በታዳጊዎች ላይ ነው ያለው። ሩኒ ፣ ጄራርድ ፣ መሲ እና ሮናልዶ ከሰማይ የወረዱ አይደሉም። እነዚህ ፍሬዎች ሁሉ በዓላማቸው ላይ ከጎናቸው በቆሙ ወላጆችና በሕብረተሰቡ ታቅፈው ያፈሩ የወይን አትክልቶች ናቸው። ይህ ሁሉ እኛ ቤት ቢዘገይም እስከ መጨረሻው ግን አይቀርም። “ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላል” አለች ሴትዮዋ። እስኪ ሁላችንም ሕጻናቱን በፍላጎታቸው እንደግፋቸው። ሴቷ ስትሮጥ ዘላል ወንዱ ኳስ ሲያንከባልል ዱርዬ ከማለት እስኪ የአስተሳሰብ ለውጥ እናምጣና እናበረታታቸው። ያኔማ በርቱ ብለን ብናሞግሳቸው አልፎም ስጦታ ብንሰጣቸው በሞራልና በራስ መተማመን ያድጋሉ። በሞራልና በድፍረት ያደገችው ሴቷ ብትሮጥ መሰረት ደፋር ትሆናለች!

  ከተበላሸ ወተት ጥሩ እርጎ አይገኝምና ሕፃናትን ሀገር ወዳድ አድርገን እናሳድጋቸው! እስኪ በአካባቢያችን ያሉትን ሕጻናት ኮትኩተን ኢትዮጲያን የሚያኮሩ ከዋክብት እናድርጋቸው!! እስኪ ሕጻናቱን ለመኮትኮት በተከበረችው በሀገራችን በኢትዮጲያ ሥም ቃል እንግባ!!

  Visit this Blog! http://yonas-zekarias.blogspot.com/
  ReplyDelete
  Replies
  1. endet des yemil eyta new? yemimekir, yemiyastemir!!!!!!!!!!

   Delete
  2. አሪፍ እስተያየት ነው ፣አባባሎቹም በጣም ደስ ይላሉ...ለማንኛውም ፍጣሜዬን ያሳምረው እንጂ..እኔ በራሴ ምናምንቴ ነገር ብሆንም ልጆቼን እንደካህንነቴ እቤቴ ፊደል ለማስቆተርና በዜማ ኢንስፓየር ለማድረግ እየሞከርኩ ነው...ማመን እያቃተኝ ያለውና መላው የጠፋኝ ነገር ቢኖር ትምህርት ቤት ሄደው የሚማሩት ነገር ነውና ስለሱ እባክ ደግሞ የሆነ ነገር በል(በሉ)! እግዜር ይስጥልኝ!

   Delete
 8. thx dani it is my idea too.God bless you

  ReplyDelete
 9. አበበ ሙ በየነJanuary 3, 2013 at 10:34 AM

  ወንድሜ ዳንኤል

  ለድንቅ ዕይታህ እግዚአብሔር ይባርክህ::

  የእኛ ትውልድ ምግባር የቀደሙ አባት እና እናቶች ዉጤት ነው:: የአሁንም ትውልድ ሁኔታ የሚወሰነው ከእኛ በሚወስደው አስትምህሮት ለመሆኑ ዋቢ መጥቀስ አያስፈልገዉም::

  አባቴ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ልጅነቱን እንዴት እንዳሳለፈው ሲያወጋኝ ችቦ ይዞ ቤተሰቦቹን እራት ያበላ ነበር:: ይህን በማድረጉም ጥሩ ጉርሻ ይሸለም እንደነበር ከአወጋኝ ወግ ትዝ ይለኛል:: እኔን ሲያሳድገኝ በዚያ መንገድ ባላልፍም እንጨት ሰብሬ ዉሃ ቀድቼ አድጌያለሁ::

  ይህ እንግዲህ የሚያመለክተው አባቴ በአደገበት መንገድ እኔ ያለማደጌን ቢሆንም ለቤተሰብ መታዘዝ እና አክብሮት መስጠትን ግን በተለያየ መንገድ እኔም ላይ ሆነ አባቴም ላይ ማህተሙ አርፎአል::

  ስለዚህ የእኛም ልጆች አባቴ ችቦ በያዘበት እኔ እንጨት በሰበርኩበት መንገድ ይደጉ ባይባልም ለቤተሰባቸው የሚታዘዙና አክብሮት ያላቸው እንዲሆኑ መታተር ያስፈልገናል::

  ለሰዉ ልጅ ክብር መስጠት የሚቻለው ቤተሰብን ማክበር የአወቅን እና የተማርን እንደሆነ ብቻ ነው::

  ልጆቻችንን መግደልን በአሻንጉሊትም ቢሆን እንዲለምዱት ከአደረግን በሰው ልጅ ላይ የማይሞክሩበት ምንም ምክንያት አይኖርም:: በህፃንነቱ እሳት የሚወድ ወይንም የቤት እንስሳ የሚያሰቃይ እና የሚገድል ልጅ አድጎ ሰው ላለመግደሉ ምንም ዋስትና መስጠት አይቻልም::

  ስለዚህ ለልጆቻችን ጥፋትም ሆነ ልማት ተጠያቂ የምንሆነው እኛው ነን::ስለዚህ የአሁኑ ትዉልድ ቀጣዩን ትዉልድ በተገለጠ (ዕምነት ) ወይንም በተረጋገጠ (እዉቀት) እዉነት ልንገነባቸው ይገባል::

  ሲያዩት ያላማረ ሲይዙት እንደሚቀደደው ሁሉ ልጆቻችን በካርቶን ፊልም አይናቸዉን ሰክተው ከሚውሉ የአባባ ተስፋዬን ተረት ቢኮመኩሙ መልካም ነው እላለሁ::

  ቸር እንሰንበት

  ReplyDelete
 10. tanx dany i always learn 4m u i dont have enogh word to tell u abt ur writing...........am so crazy abt u

  ReplyDelete
 11. "ድንቅ ዕይታ"
  በጣም አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ::
  ትልቅ ሥራ ይጠይቃል!!!!

  ReplyDelete
 12. ዳኒ እኔ በጣም የተመቸኝ አባባልህ ፦እውነትንና መረጃን ፍለጋ ሕይወትን የሚከፍሉ ሰማዕታት ጋዜጠኞች፣ የሚዲያዎችን ውቃቤ መሳብ አልቻሉም፡ያልከው ነው።

  ReplyDelete
 13. Dani an amazing man i heard lately that you were in Gondar and i tried to contact you but your phone was not answering, i was wondering if we can talk, !!! god bless Ethiopia and Ethiopian!!!

  ReplyDelete
 14. What shall I say???? Nothing Eme Amlak Tetebkeh......Tsegawun yabzaleh, Endih lek lekachen eyenegerk yemtarmen wendemachen yabertalennnnnnnn...... You are my ever hero!

  ReplyDelete
 15. I concur. Melkam yemahiberawi Eyita new.

  ReplyDelete
 16. Very thoughtful article, you have the opportunity to reach Ethiopian people, therefore you can teach in your congregation.

  ReplyDelete
 17. Yamafeteha hasabe betakomane tero nawe
  Leje yalawe hemamone yawekawale

  ReplyDelete
 18. እግዚአብሄር ብቻ ይሁነን

  ReplyDelete
 19. ለአንድ ሐኪም ሦስት ሺ ብር ለእንድ የፊልም ተዋናይ ደግሞ ሦስት ሚሊዮን ብር፣ ለአንድ ሳይንቲስት አምስት ሺ ብር ለአንድ ተጨዋች ግን ሃምሳ ሚሊዮን ብር ሲከፈለው እያዩና እየሰሙ ‹ማን ፉል አለ›፡፡ ለሀገሩ ድንበር ከተዋጋው ይልቅ ስለውጊያው ፊልም የሠራው ታዋቂ ሲሆን እያዩት፣ ላቦራቶሪውን ዘግቶ የካንሰር መድኃኒት ለማግኘት ከሚኳትነው ይልቅ ስለ ካንሰር የዘፈነችው ስትደነቅ እያዩ፤ ምን አድርጉ ነው የምንላቸው

  ReplyDelete
 20. ለሀገሩ ድንበር ከተዋጋው ይልቅ ስለውጊያው ፊልም የሠራው ታዋቂ ሲሆን እያዩት፣ ላቦራቶሪውን ዘግቶ የካንሰር መድኃኒት ለማግኘት ከሚኳትነው ይልቅ ስለ ካንሰር የዘፈነችው ስትደነቅ እያዩ፤ ምን አድርጉ ነው የምንላቸው፡፡

  ReplyDelete
 21. Dear Dn.Daniel,I really liked it.What we can see here is ,how media is powerful in shaping the society.When the media is fully controlled by the private sector, since their most target is profit they publish or broadcast anything which is taboo in the society and finally considered as normal.A little after EPRDF controlled Ethiopia, there were a number news papers,bulletins which were totally out of the society culture.

  ReplyDelete
 22. Dear Daniel, i understand your point but we need to be careful as to what we really are saying. we don't need to discredit or disrespect the profession of being a musician or an actor to our children. because there are still very good role models in our country who are doing a good thing. yes i understand the concern i share that strongly too. that our medias are so caught up with the estranged lives of celebrities around the world. and i also understand that the youth are really eager as to what they are saying including football players. however, after reading your article, i feel like some might get the message that there is nothing good being a musician or an actor that you can do nothing good about it. people like that meaning, famous actors or musicians can use their fame for good cause, even in our country, so we need to tell our children like you said that adultery is not a fancy thing or being a drug addict is nothing to be proud of. on the other hand, when we are telling them this we should not completely disregard the entire profession. thank you.

  ReplyDelete
 23. am always proud of your writing point of view. you always show us hidden truths which we don't give much care. specially for our ethiopians we are on the verge of loosing all values and our identity even we have lost our fear of God. so writers like you are so much essential for every restoration. anyways Keep it up!!!!


  ReplyDelete
 24. ድንቅ ጹሁፍ ነው ዳኒ እግ/ር ፀጋውን ያብዛልህ

  ReplyDelete
 25. ስለ እምዬ ማርያም ብለህ ተለመነኝ! ስለትምህርት ቤቶችና ስለ ልጆቻችን ውሎ በናትህ አንድ ቀን ዘወር በልባቸውና አንጀቴን አርስልን....

  ReplyDelete
 26. Amen Melikam Edil enmegnalen

  ReplyDelete