(የመጨረሻው ክፍል)
የኢፋግ የባርያ ንግድ ገበያ ዋርካ
|
‹ላላዋቂ ፎገራ ዱሩ ነው› ሲባል ሰምታችሁ ከሆነ አሁን ስላለሁበት ቦታ እየተነገራችሁ ነው ማለት ነው፡፡ ፎገራ በደቡብ
ጎንደር፣ ዓባይን ከተሻገራችሁ በኋላ ጣናን ባሻገር እያየ የሚገኝ ሰፊ ሜዳ ነው፡፡ ለዚህ ነው ‹ላላዋቂ ፎገራ ዱሩ ነው› የሚባለው፡፡
ፎገራ አለቃ ገብረ ሐናን የመሰሉ ሊቃውንትን ያፈራ ታዋቂ ቦታ ነው፡፡ እዚህ ናበጋ ጊዮርጊስ ነው አለቃ ትውልዳቸውም፣ ዕረፍታቸውም፡፡
ፎገራ ውኃ ገብ ረግረግ መሬት በመሆኑ ከአፍ እስከ ገደፉ በሩዝ ምርት ተሸፍኗል፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም ‹ሕንድ በኢትዮጵያ›
እያሉ ይጠሯታል ፎገራን፡፡ የፎገራ ገበሬ የነቃ የበቃ ገበሬ ነው፡፡ ፎገራ መንደር ውስጥ ስትገቡ የምታገኟቸው የቴክኖሎጂ ምርቶች
ገጠር መሆናችሁን ያስረሷችኋል፡፡ ንግግራቸው አማርኛ፣ አለባበሳቸው ወደ ኦሮምኛ ይጠጋል፣ ፎገራዎች፡፡ በመንደሩ ውስጥ ትግርኛ፣
አማርኛና ኦሮምኛ ተቀላቅሎ ሲነገር ትሰማላችሁ፡፡
ለምን? አትሉም፡፡ ፎገራ በጥንቱ የሲራራ ነጋዴዎች መንገድ የምትገኝ ቦታ ናት፡፡ ከጣና በስተ ሰሜንም ሆነ ከጣና በስተ
ደቡብ አቋርጠው የሚያልፉ ሁሉ በፎገራ መሔዳቸው ግድ ነው፡፡ ፎገራ ደቡቡን ኢትዮጵያ ከሱዳን ገበያና ከቀይ ባሕር ወደቦች ጋር የምታገናኝ
የንግድ መናኸርያ ነበረች፡፡
ልጥጥ ያለው ሜዳዋ ለአጋሰሶች አመቺ መሆኑ፣ የከብቶች መኖ ለማግኘትም ቀላል መሆኑና ውኃ በአካባቢው መኖሩ ለነጋዴዎች
ምቹ የማረፊያ ቦታ አድርጓት ነበር፡፡ ከዚያም በተጨማሪ የነገሥታቱ ቤተ መንግሥቶች በአካባቢዋ በመኖራቸው ለጥበቃ የተመቸች ሥፍራም
ነበረች፡፡ በጎንደር የመጀመርያው ቤተ መንግሥት የሆነው የዐፄ ሠርጸ ድንግል የጉዛራ ቤተ መንግሥትም የሚገኘው እዚያው አለፍ ብሎ
ነው፡፡
የፎገራ ሩዝ |
በሩዝ ሰብል የተሞላውን የፎገራን ሜዳ አልፋችሁ ስትሄዱ
ሀገርሽ ወዴት ነው ብዬ ብጠይቃት
ከምከም ብላ ሳቀች ነገሩ ቢደንቃት
የተባለባትን ሊቦ ከምከምን ታገኛላችሁ፡፡ እዚህ ነው እንግዲህ ኢፋግ ያለችው፡፡
ኢፋግ በጥንቲቷ ኢትዮጵያ ዋነኛ ከነበሩት የባርያ ገበያዎች አንዷ ነበረች፡፡ በምዕራብ በለሳ በኩል ወደ ሱዳን በዚያውም
ወደ ግብጽና ዓረብ ሀገሮች፣ በሰሜን ደንቢያ በኩል ደግሞ ወደ ትግራይና ኤርትራ፣ በዚያውም አድርጎ ወደ ዓረቡ ዓለም ይሻገሩ ለነበሩት
ባሮች አንዷ ገበያ ነበረች- ኢፋግ፡፡
ከባሕርዳር ወደ ጎንደር የሚወስደውን መንገድ ተከትላችሁ፣ የፎገራን ሜዳ ካለፋችሁ በኋላ፣ ወደ ግራ ስትታጠፉ የኢፋግ
ከተማ ትታያችኋለች፡፡ ወደ ውስጥ የሚያስገባው መንገድ አመቺ ነውና ባጃጆች እንኳን ሳይቀሩ ይጎበኟታል፡፡ ከተማውን በስተቀኝ አቋርጣችሁ
ስታልፉ የምታገኙት ዕድሜ ጠገብ ዋርካ ነበር ዋነኛው የባርያ ገበያ ማዕከል፡፡
ዙርያውን በቤቶች ተከብቦ ዛሬ ተንቆ የተቀመጠው ዋርካ ለብዙዎች የሀብት ማከማች ለብዙዎች ደግሞ የልቅሶና የዋይታ ቦታ
ነበረ፡፡ እንዲህ ዓይነት ታሪኮቻችን በሚገባ ተመዝግበውና ተጠብቀው መቆየታቸው ካለፈው ስሕተታችን እንድማር፣ እንዳንደግመውም ያደርገናል፡፡
እኛ ግን እንደዚያ አንመስልም፡፡ የኢፋግን የባርያ ገበያ ታሪክ ረስተነው ዛሬ በዘመናዊ ባርነት እኅቶቻችን እየተሸጡ የጥንቶቹ ባሮች
ይሄዱባቸው ወደነበሩት ሀገሮች በመሔድ ላይ ናቸው፡፡
እዚያ በዋርካው አካባቢ ያገኘኋቸውን የሀገር ሽማግሌ ‹ኢፋግ ማለት ምን ማለት ነው?›› ብዬ ጠየቅኳቸው፡፡ እርሳቸውም
‹‹‹ይፋ ግፍ› ማለት ነው›› አሉኝ፡፡ እንዴት? ስል ነገሬን አስረዘምኩ፡፡ እርሳቸውም እንዲህ ተረኩልኝ፡፡ ‹‹በድሮ ጊዜ እዚህ
ገበያ ላይ ከየሀገሩ በባርያ ፈንጋዮች እየተያዙ ባሮች ለገበያ ይመጡ ነበር፡፡ ታድያ ከመጡ በኋላ እንዳያመልጡ እዚህ ዋርካ ሥር
ከዋርካው ጋር ታሥረው ቆመው ይውላሉ፡፡ ገዥውም እየመጣ እያየ መርጦ ይገዛ ነበር፡፡ ታድያ አንድ ክፉ ሰው ባሮችን ሰብስቦ በገመድ
አሥሮ ሲያመጣ አንዱ ባርያ በረኃብ መንገድ ላይ ይሞትበታል፡፡ ጨካኝ ስለነበር ባርያውን ከመቅበር ይልቅ አብሮ አሥሮ አመጣውና እዚህ
ዛፍ ሥር አቆመው፡፡ በኋላ ገዥ መጥቶ አሥሩንም ባሮች ገዝቶ ገንዘቡን ከሰጠ በኋላ ባሮቹን በገመድ እየጎተተ ሲወስዳቸው ያ ባርያ
ዝንጥፍ ብሎ ወደቀ፡፡ እንዲህ ያለ ግፍ በአደባባይ ስለተሠራባት፣ ሬሳ ስለተሸጠባት ይፋግ ተባለች›› አሉኝ አዛውንቱ፡፡
በአካባቢው ስትቆሙ በዚያ ዘመን ሰው በሰው ላይ ሲሠራ የኖረው ግፍ በዓይነ ኅሊናችሁ ይመጣባችኋል፡፡ ሰው ሰውን ሲሸጥ፣
ሰውም ሰውን ሽጦ ሲተዳደር፡፡ ግን የባርያ ንግድ ቆሟል? ይህንን ነበር እኛ ስንጠያየቅ የነበረው፡፡ የገበያ ቦታውንና አሠራሩን
ቀይሯል? ወይስ ቆሟል?
የኢፋግ ከተማ |
የኢፋግን ከተማ ተሰናብተን ጉዟችን ወደ አዲስ ዘመን ከተማ ሆነ፡፡ አንዳንዶች ይህቺ ከተማ ‹አዲስ ዘመን› የተባለችው
አዲስ ዘመን ጋዜጣ ‹አዲስ ዘመን› ከመባሉ በፊት ነው ይላሉ፡፡ እንዲያ ከሆነ አዲስ ዘመኖች የቅጅ መብት ጥያቄ ማንሣት አለባቸው፡፡
የጎንደሩ ደብረ ብርሃን ሥላሴ ከሰሜን ሸዋው ደብረ ብርሃን ሥላሴ ‹ደብረ ብርሃን ሥላሴ›› የሚለውን ስም ሲወስድ ዐፄ ኢያሱ አድያም
ሰገድ ለሰሜን ሸዋው ደብረ ብርሃን ሥላሴ ሁለት ሺ መክሊት ወርቅ
ከፍለው ነበር ይባላል፡፡ እንግዲህ ለአዲስ ዘመኖች መከራከርያ ማቅረቤ ነው፡፡
አዲስ ዘመን ከተማ ጥንት አሁን በነበረችበት ቦታ ላይ አልነበረችም ይባላል፡፡ የተመሠረተችው አሁን ጣራ ገዳም ካለበት
ተራራ ሥር ነበር አሉ፡፡ ታድያ የከተማዋ ሴቶች ውኃ ሊቀዱም ሆነ እንጨት ሊሠብሩ እዚህ ተራራ ሥር ይመጣሉ፡፡ ወደ ገዳሙም ክልል
ይገባሉ፡፡
ከእነዚህ እንጨት ሰባሪ እኅቶች መካከል አንዷ አንድ ቀን ወደ ገዳሙ ክልል ገብታ በነበረ ጊዜ ምናምን አደናቅፏት ከአንዱ
የገዳሙ ሰው ጋር ትሰናከላለች፡፡ የገዳሙ ሰውም በፈጸሙት ድርጊት ተፀፅተው ራሳቸውን በሾተል ጃንደረባ ያደርጋሉ፡፡ ነገሩም ለገዳሙ
መነኮሳት ኀዘን ይሆናል፡፡ መነኮሳቱ ነገሩን ይወያዩበትና ወደ አካባቢው ገዥዎች ያመራሉ፡፡ ‹‹ችግሩ እየተከሰተ ያለው ገዳምና ከተማ
አብረው በመሆናቸው ነውና ከተማው ይነሣ›› ብለው ይጠይቃሉ፡፡ አገር ገዥዎቹም ጥያቄያቸውን ተቀብለው ከተማዋን ከጥንቱ ቦታዋ በማንሣት
ዛሬ ያለችበት ቦታ ተከሏት፡፡ ስሟንም ‹‹አዲስ ዘመን›› አሏት ይባላል፡፡
እስኪ አዲስ ዘመንን እንለፋት፡፡
ወደ ጉዛራ ቤተ መንግሥት መግቢያ |
ጉዟችንን ወደምናጠናቅቅበት እንፍራንዝ ወደሚገኘው ወደ ጉዛራ ቤተ መንግሥት፡፡ ጉዛራ ማለት በግእዝ መሰባሰቢያ ቦታ፣
የጉባኤ ቦታ ማለት ነው፡፡ ወደ እንፍራንዝ ከተማ ከመድረሳችሁ በፊት ወደ ቀኝ ስትመለከቱ ጉዛራን በጉብታው ላይ ጣናን ፊት ለፊቱ
እያየ ታገኙታላችሁ፡፡ በመግቢያው ላይ ያለው ሰሌዳም ይህንኑ ይነግራችኋል፡፡ የአካባቢው ሰዎች በመኪና መግባት እንደሚቻል ይናገራሉ፡፡
እኛ ግን የገባነው በእግራችን ነው፡፡ እየታጨዱ ባሉት እርሻዎች መካከል እያቆራረጣችሁ ዙርያ ጥምጥም የሆነውን መንገድ መከስከስ
ነው፡፡
ከአስፓልቱ የአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለው የጉዛራ ቤተ መንግሥት የጎንደር መንግሥት መሥራች በሚባሉት በዐፄ ሠርጸ
ድንግል (1556-1589 ዓም) ዓም አማካኝነት የተሠራ ነው፡፡ ንጉሡ በቦታው ቤተ መንግሥቱን እንዲያንጹ ያደረጓቸው የተለያዩ ምክንያቶች
አሏቸው፡፡ ወደ ሰሜን የሚሄደው የንግድ መሥመር በዚያ የሚያልፍ መሆኑ፤ ጣና ሐይቅ ከፊቱ የተንጣለለ መሆኑ፤ አካባቢው ደጋ መሆኑና
ከወባ በሽታ ነጻ መሆኑ፤ አካባቢው በእህል ምርት የታወቀ መሆኑ፣ ዋናው የወርቅ ገበያ ለነበረው ፋዞግ ቅርብ መሆኑና ሌሎችም ነበሩ፡፡
ቤተ መንግሥቱ የጎንደርን ቤተ መንግሥት መልክ ይዞ በጉብታ ላይ የታነጸ ነው፡፡ ፎቅና ምድር ቤት የነበረው ይህ ቤተ
መንግሥት የንጉሡን እልፍኝ፣ የፍርድ አደባባይ፣ የግብር አዳራሽ፣ ማዕድ ቤትና ሌሎችንም ክፍሎች ይዞ ነበር፡፡ ቤተ መንግሥቱ ከድንጋይና
ከእንጨት የተገነባ ሲሆን ከጎንደር ቤተ መንግሥት የሰባ ዓመት ቅድሚያ እንዳለው ይነገራል፡፡
የሚገርመው ነገር በጎንደር ዘመን የተሠሩት አብያተ መንግሥት ‹ጎ› የሚለውን ስም ተከትለው የተሠሩ መሆናቸው ነው፡፡
ጉዛራ፣ ጎርጎራ፣ ጎመንጌ፣ ጎንደር፡፡ ለምን ይሆን? ብዬ ጠይቄ ነበር፡፡ በቀድሞ ጊዜ ‹ጎ ይነግሥ› የሚል ንግር ስለነበረ ነው
ብለውኛል፡፡
የጉዛራ ቤተ መንግሥት ከሩቁ ሲታይ |
የጉዛራ ቤተ መንግሥት እንደሌሎቹ ሁሉ በሚገባ አልተያዘም፡፡ ራሱን ጠብቆ ለ400 ዓመታት ቢቆይም ከአሁን በኋላ እገዛ
ሳያስፈልገው አይቀርም፡፡ ቤተ መንግሥቱ ከዛሬ ሃያ አምስት ዓመታት በፊት ከዚህ የተሻለ ይዞታ ላይ እንደነበር የአካባቢው ሰዎች
ይናገራሉ፡፡ በአካባቢው የተደረገው የኢሕአዴግና የደርግ ውጊያ በቤተ መንግሥቱ ላይ የመፈራረስ አደጋ አስከትሎበታል፡፡ አሁን ያለውም
ከዚያ የተረፈው ነው፡፡
ጉዛራ ቤተ መንግሥት ግድግዳ |
ከጉዛራ እንውጣ፤ እናንተንም አካባቢውንም ተሰናብተን ወደ ጎንደር እናቅና፡፡ ሌላ ጊዜ ከዓባይ እስከ ደሴ በምሥራቅና
ምዕራብ ጎጃም በኩል፣ በደቡብ ጎንደር ስማዳን አልፈን፣ በጨጨሆ በኩል በመቄት ወጥተን ዋድላና ደላንታን አቋርጠን ተመልሰን አዲስ
አበባ የገባንበትን የ1700 ኪሎ ሜትር ጉዞ እተርክላችኋለሁ፡፡ እስከዚያው ደኅና ሰንብቱ፡፡
«ንግግራቸው አማርኛ፣ አለባበሳቸው ወደ ኦሮምኛ ይጠጋል፣ ፎገራዎች፡፡ በመንደሩ ውስጥ ትግርኛ፣ አማርኛና ኦሮምኛ ተቀላቅሎ ሲነገር ትሰማላችሁ፡፡»
ReplyDeleteአላልኩም ዳኒ ቅቅቅቅ ተምትጥፋቸው ጡፎች 80% ከዘር ጋር የተገናኘ ነው? እንኳን የጣፍከውን...ልትጥፈው ያሰብከውን ጮጮ መተንበይ ይችላል.... ቂላቂል ደጋፊዎችን አስጠንቅቃቸው... ቧላ ተንቅልፋቸው ቲባንኑ...በቁስል እንዳይሞቱ ቅቅቅቅቅቅ
Tebarek Dani! The guy commenting on ethnicity has no mind to think with. am thinking like he/she is a TPLF cadre who is merely a receiver but not a creator of idea at all. he/she opens his/her mouth to spit bad words but unfortunately inviting a wide view unto his/her empty mind. this blog is not for u and ur likes.
Deletechocho Zer Wodaju he/she is bare minded
Deletethis cadre who is ethnically polluted by TPLF propoganda, leave just him you guys he is norrow minded as his bosses but the day come to end for them.
Deletethank you boy
what is your point?..Is that true or not?
DeleteDani tsegaw yibzalih edmena tena yistih.
ReplyDeleteD Daneil Abienih Yetegazin Yahil Yitayenal Enameseginalen
ReplyDeleteThanks Dn Dani ! hope u will tell us more including ' checheho Medhanialem'
ReplyDeleteMay God Bless you and flourish your service to the people.
ReplyDeleteWho did this, this days? Again May God Almighty Bless your work.
የኢፋግን የባርያ ገበያ ታሪክ ረስተነው ዛሬ በዘመናዊ ባርነት እኅቶቻችን እየተሸጡ የጥንቶቹ ባሮች ይሄዱባቸው ወደነበሩት ሀገሮች በመሔድ ላይ ናቸው፡፡ ዳንኤል እናመሰግናለን///
ReplyDeletebeDani bet karma mehonu new:: yeDani chinqilat tinish teleq bitil noro, aleqine besebara shigut hono neber negeru hulu LOL
Deleteit's nice i will expecting you ok. God bless you!!!!!!!!!!
ReplyDeleteDani thank you for details of our back history going back to 400 years. We should have to lean from their weakness and improve ,admire their strength.
ReplyDeleteዛሬም ማን ያውቃል እላለሁ የሚገርሙትንና የሚደንቁትን የሀገሬን ቅርስና ቦታዎች ጎብኝቼ ሀገሬን በደንብ እንዳውቃት እግዚአብሔር ይረዳኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ካለሁበት ከተማ የሚታዩትን በአቅሜ በማየት እንድጀምር የሚያነሳሳ ጥሩ ዕይታ ነው እግዚአብሔር የልቤን መሻት ያሳካው ይሆናል ማን ያውቃል በአይነ ህሌናችን ለሳልከው ለአንተም ዕድሜና ጤና ይስጥህ አሜን
ReplyDeletewtbhm
ዛሬም ማን ያውቃል እላለሁ የሚገርሙትንና የሚደንቁትን የሀገሬን ቅርስና ቦታዎች ጎብኝቼ ሀገሬን በደንብ እንዳውቃት እግዚአብሔር ይረዳኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ካለሁበት ከተማ የሚታዩትን በአቅሜ በማየት እንድጀምር የሚያነሳሳ ጥሩ ዕይታ ነው እግዚአብሔር የልቤን መሻት ያሳካው ይሆናል ማን ያውቃል በአይነ ህሌናችን ለሳልከው ለአንተም ዕድሜና ጤና ይስጥህ አሜን
DeleteDn. Daniel Kal Hiwot Yasemalen! @ Chocho zer Wodaju- It seems you are the one with Ethnicity Problem. All the writer want to say is the reality in the place. Before you post this Unfair comment try to think twice.
ReplyDeleteThanks Dani. you are great. We are proud of u as Ethiopian , specially as member of EOC. You know enemies of the church are following each & every activities of you & express their bad feeling. Ignore them. Silemikenu new. B/c they do not have your kind of talent & positive thinking.For many young & adult Ethiopians u r our Icon. please Daniel take care of ur self not only for u but for us. When we lose hope about our country & church, we get relief in persons like u. I cry several times by thinking that persons may kill you. Let God of our fathers protect you.
ReplyDeletecho cho Zer Wodaju December 19,20012 are you normal??? Daniel wrote the reality that exists in that environment. you gays you are ignoring or insulting the people of Fogera by having them the diversity of culture!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteDani I want to appreciate your capability & the way of expressing your feeling.I wish God to bless you in your future carrier.
ReplyDeleteThank you very much.
ReplyDeleteእግዜር ከመጻህፍት ያለፈውን ምሥጢር ይግለጥልህ....ደግሞ እባክህ ቀስስ፡፡
ReplyDelete@chocho zer wedaju, Andebteh melekam neger endaynager Ayemerohe melekam endayasebu honehale!!!!!! so E/Z mehertun yestehe.
ReplyDeletelewendemachen Dn Daniel edemihen yzrezemlen
thank u dani. I am happy by u'r talented work.please be strong than before!
ReplyDeleteዉድ ጸሐፊያን ሁሉም መከታተል እንዲችል ይህን ድረ ገጽ ተጠቀሙ http://www.lexilogos.com/keyboard/amharic.htm ከላይ ባለዉ ክፍት ቦታ ጽፋችሁ ኮፒ አድርጎ መዉሰድ ነዉ። ለመጻፍ የምትፈልጉትን ፊደል በከርሰፘ ክሊክ አድርጉ።
ReplyDeleteeven to tell the peoples around me about the great places i know, i say to myself, they wouldn't care, b/c people now think about business, personal matters and many other things, so no body cares why should i tell peoples when i know they are not interested???????????? but Dani you never care, you here to serve us so thank you!!!!!! EMEBRHAN KANTEM KEHULACHIN GAR TIHUN!!!!!!
ReplyDeleteዳኒ በፅሁፍ መልካም የሆነ ጉብኝት ነው ያደረጉት በጣም ደስ ብሎኛል ድንግል ትጠብቅህ ጌታ ፀጋህን ያብዛው፡፡ እባካቹ አስተያየት ሰጪ ቀስስ አትበሉ፤ ሰው በተሰጠው ፀጋ ያገለግላል፡፡ ማህበራዊ ጉዳዮችን እየተነተነ የሚፅፍልን ነው የምንፈልገው፤ ዳኒ የምትፅፈቸው ፅሁፎች በአይምሮአችን፤በባህላችን ፤በአኗኗራችን ልክ ነው የምትፅፍልን ከቀሰሰ ግን ውስን የሆነ ነገሮች ነው ሊፅፍ የሚችለው፡፡ ስለሆነም በዚሁ ቀጥል ነው የምለው፡፡ ቄስ መቼ አጣን ሞልቶናል እነሱን ለፍሬ ያድርግልን፡፡
ReplyDeleteእናመሰግናለን
ReplyDeleteዲን ዳንኤል,
ReplyDeleteምነው ዝምታን መረጥክ ቤተክርስቲያን እንዲህ አጣብቂኝ ውስጥ ገብታ? አንተን ለዚህ ዝና እና ሃብት ያበቃችህ ቤተክርስቲያን እንጂ መንግስት አይደለም። ደግሞ በገሃድ መንግስትን መደገፍም ይቻላል። አቋምህን ግን በግልጽ ብታሳውቅ ጥሩ ነው።
You are writing interesting stories. Do you get them from local people or books? Why you kept your self away from the current EOTC affairs. Church leader election and Peace deal
ReplyDeletedear daneal God belles you? You are large library. I know the area and I born at addis zemen. You are correct and interesting.God be with you and us. thanks
ReplyDeleteno thing is to say! GREAT!
ReplyDeleteስለ ፓትሪያርክ ምርጫስ ምን ትላለህ ዲያቆን ዳንኤል
ReplyDeleteDani 10 Q
ReplyDeleteShame on us,for those who are talking about ethnicity in this civilized century. I think ethnicity emanates from inferiority, so please let us eradicate racism by educating ourselves.
Soddo wolaita
አይ ዳኒ ዛሬም እዛው ጣራ ላይ እንዳለህ ነው? ለምን መሰረትህ ስለ ነበረችው ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለመጻፍ ብዕርህ ነጠፈ ዐይምሮህስ ተዘጋ ዛሬ ያልተናገርክ መቼ ልትናገር ነው።
ReplyDeleteI think Cho Cho Zer wedaju should be victim of devils like protestants. He shoul go to face to face to memihir Girma Wondimu so as to get devil free life. amlak yitebiken! Danny beta.
ReplyDeletevictim of devils like protestants
Deletekikikikikikiki............
ማንነትህ/ሽ የማን ልጅ መሆንህ/ሽ በንግግርህ/ሽ ይታወቃልና ንስህ!!!!! ንስሃ!!!!!!!
I wish you focus on our church unity in stead of talking things that are not untimely. Please tell your "follower" again and again how our church is on a cross road. We don't need your smart look explanation after things are over (the date is right in our hand).
ReplyDeletethank you Dani. u r the best.
ReplyDeleteHo! Dani I told you frankly I like you very mach ...... any your idea a good written during you are my bast Some times pls
ReplyDeleteDani betam teru Akerareb new berta
ReplyDeleteI like it
ReplyDeletei like ur righting
ReplyDeleteየኢፋግን የባርያ ገበያ ታሪክ ረስተነው ዛሬ በዘመናዊ ባርነት እኅቶቻችን እየተሸጡ የጥንቶቹ ባሮች ይሄዱባቸው ወደነበሩት ሀገሮች በመሔድ ላይ ናቸው፡፡ ዳንኤል እናመሰግናለን///
ReplyDeletedear diakon Daniel,first of all, may god bless you for what you are doing.what ever you write,it has some thing in it that teaches.of course,it is my first time to see your website and go through your views and posts,but i found them educative and important.i learnt a lot and thank you for that.
ReplyDeletewhen i come to my comment,the overall story you wrote is so good,but the statements you wrote about "FOGERA"that "ንግግራቸው አማርኛ፣ አለባበሳቸው ወደ ኦሮምኛ ይጠጋል፣ ፎገራዎች፡፡ በመንደሩ ውስጥ ትግርኛ፣ አማርኛና ኦሮምኛ ተቀላቅሎ ሲነገር ትሰማላችሁ፡" is i think not real.because i know the people of fogera very well, i have never seen any one whose dressing is like the oromos,and who speeks either tigregna or oromifa.even their clothing and style of life is typical of the Gonderians dressing style.and is very far appart from oromos dressing style and no one can speak any language other than amharic.
in addition, i am not clear where you get the word E-FAG. i know by the name YI-FAG but you used the word E-FAG.where did you get it? even ethiopian history uses the word YIFAG.
so, Dani,when you write such kinds of story i think it is better to base on a bit reliable sources as you write what you get from local people i think.
very constructive unlike the crazy @chocho!appreciate.
Deleteዳንኤል መቼ ነዉ የምትጽፍልን
ReplyDeleteቀጣዩን ታሪክ
ወለተ ሚካኤል
please every one,can you tell me one person you know !? who cares about, Ethiopia and her historical places,peoples,social aspects at this time !!may be their is but, i don't know him !only i know is Daniel keberet b/c he is doing some thing real !!please.every body, when some one trying to do nice work admire him or don't be Jules of him!Dani may God bless you!!
ReplyDelete