click here for pdf
በአንድ ገዳም የነበሩ አበው አንድ ጉዳይ ይገጥማቸውና ከየበኣታቸው ወጥተው በገዳሙ
ዐውደ ምሕረት ላይ ይከራከራሉ፡፡ ክርክሩ ወደ መጋጋል ይሄድና ኃይለ ቃል መውጣት ይጀምራል፡፡ ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩ
አረጋውያን አባቶች ወጡና በየወገኑ የነበሩ ተከራካሪዎችን ሊያስማሟቸው ሞከሩ፡፡ ነገር ግን የሚያስማማ ሃሳብ ማምጣት
አልቻሉም፡፡ በዚህ ጊዜ በገዳማውያኑ ዘንድ በብቃታቸው የሚታወቁ አንድ አባት ከበኣታቸው በር ላይ ቆሙና ‹በሉ ሁላችሁም
ወደየበኣታችሁ ግቡ፤ ከዚያ በኋላ ለክርክራችሁ መፍትሔ ታገኛላችሁ› ሲሉ ተናገሩ፡፡
እርሳቸው እንዳሉትም ሁሉም ገዳማውያን ወደየበኣታቸው ገቡ፡፡ ወደ ዋሻው የሚገባም
ገባ፤ ወደ መቅደስ የሚሄድም ሄደ፤ ወደ ምርፋቅ የሚሄድም ሄደ፤ ወደ ተግባር ቤት የሚሠማራም ተሠማራ፤ ወደ እርሻም የሚሄድ
ሄደ፡፡ ያን ጊዜም ማዕበሉ ጸጥ አለ፡፡ ዐውደ ምሕረቱም ዐውደ ምሕረት ሆነ፡፡ ሁሉም ገዳማዊ ወደ በኣቱ ተመልሶ በረጋ ኅሊናና
ነገሩን ማሰላሰል ጀመረ፡፡ አንዳንዱ በማያውቀው፣ አንዳንዱ በማያገባው፣ አንዳንዱ መልካም የሠራ መስሎት፣ አንዳንዱ ለሌላው ሰው
ደጋፊ በመሆን፣ አንዳንዱ ያለ ችሎታው ነበር በነገሩ የገባው፡፡
ሁለትና ሦስት የጸጥታ ቀናት አለፉ፡፡ ሁሉም ሰው ወደ ልቡ ተመለሰ፡፡ እኒያ አባትም
ሁሉም ከሄደ በኋላ የሚገባቸውንና የሚያገባቸውን የገዳሙን ሰዎች ጋበዙ፡፡ የገዳሙን አበ ምኔት፣ ሊቀ አርድዕቱን፣ መጋቢውን፣
ገበዙንና የአብነት መምህሩን ጠርተው በተነሣው ጉዳይ ላይ ተነጋገሩበት፡፡ መነጋገርም ብቻ ሳይሆን ተግባቡ፡፡ ገዳሙም ከነ ሰላሙ
ቀጠለ፡፡
‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ›
በቤተ ክርስቲያን ሞገድና ማዕበል ሲነሣ የሚያዋጣው ‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ› ብሎ
መጮህ ነው፡፡ አሁን የዕርቀ ሰላ ጉዳይ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል በቅዱስ ሲኖዶስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አይደለም ውይይቱ
እየተደረገ ያለው፡፡ በሕዝብ አደባባይ ነው፡፡ አቡነ እገሌም፣ እነ እገሌም፣ የሚናገሩት በዚህ ወይም በዚያ ሬዲዮ፣ በዚህ ወይም
በዚያ ብሎግ፣ በዚህ ወይም በዚያ መግለጫ ሆኗል፡፡
አሁን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም ወደ በኣታቸው ይግቡ፡፡ የመግለጫውን ጋጋታ ትተው ወደ
ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ገብተው ይወያዩ፤ ሃሳባቸውን ያቅርቡ፣ ይከራከሩ፡፡ እዚህ ወይም እዚያ መግለጫ ማውጣቱ ነጥብ ከማስቆጠር
ውጭ ችግሩን አይፈታም፡፡ ችግሩን የሚፈታው ወደ በኣት ገብቶ መጀመርያ የጸጥታ ጊዜ ከወሰዱ በኋላ ነገሩን በምልዐተ ጉባኤ ማየት
ነው፡፡
ከፊታችን የታላቁ የቅዱስ ገብርኤል በዓል ይከበራል፡፡ ይህ መልካም አጋጣሚ ነው፡፡
ይህንን ጊዜ የጸሎትና የመረጋጋት ጊዜ አድርጎ መጠቀም ነው፡፡ ከዚያም ሁሉም አባቶች ወደ በኣታቸው ገብተው ይወያዩ፡፡ የአባቶች
የመወሰኛ መድረክ የቅዱስ ሲኖዶስ አዳራሽ እንጂ ሚዲያዎቹ አይደሉም፡፡
አሁንም ሌሎቹ ሁሉ ወደየበኣታቸው ይግቡና ቅዱስ ሲኖዶስ ከልዑካኑ ጋር በጋራ የሚሠሩ
ሊቃውንትን ይመድብ፡፡ እነዚህ ሊቃውንት ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ታሪክ፣ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ልምድ፣ ከሀገሪቱ ሕጎች፣
ያኔ ችግሩ ሲነሣ ከተፈጠሩት ክስተቶች አንጻር አማራጭ ሃሳቦችን የሚያቀርቡ፣ ልዑካኑን በቴክኒክ የሚያግዙ፣ የልዩነት ጉዳዮችን
ቀድመው አውቀው መፍጥሔ የሚጠቁሙ መሆን አለባቸው፡፡
ከእነዚህ ሊቃውንት መካከል ሂደቱን ለታሪክና ለሪፖርት የሚመዘግቡ፣ ለሚመለከታቸው
አካላት ወጥ የሆነ መግለጫ የሚሰጡ፣ የልዑካኑን መዛግብት የሚይዙ፤ ቦታውንና ሂደቱን አስቀድመው አይተው መንገድ የሚጠርጉ ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡
አስታራቂ ኮሚቴውም ወደ በኣቱ ይግባ፡፡ በባህሉም ሆነ በእምነታችን ለማስታረቅም ሆነ
ለማግባባት ልምድና ችሎታ፣ ብቃትና ታማኝነት፣ ገለልተኛነትና ብስለት ይጠይቃል፡፡ ምንም እንኳን በጎ ዓላማ ቢኖር በጎውን ዓላማ
ከግብ ለማድረስ ግን ለዓላማው ብቁ የሆነ ኃይል ያስፈልጋል፡፡ ዘሩ መልካም መሆኑ ብቻ እንዲያፈራ እንዳላደረገው ወንጌል
ነግሮናል፡፡ መሬቱ መልካም ባለመሆኑ ምክንያት ከተዘሩት አራቱ ዘሮች ሦስቱ 75% ሳያፈራ ቀርቷል፡፡ የዕርቁም ሃሳብና ዓላማ
ምንም መልካም ቢሆን የአስታራቂዎቹ ብቁና መልካም መሆን አለመሆን ግን ለፍሬያማነቱ ወሳኘ ነው፡፡
ሲሆን ሲሆን ምንም አስታራቂ አያስፈልግም፡፡ ነገር ግን አመቻማች
(facilitator) ካስፈለገ ሁለቱም አካላት በጋራ ሊሰይሙ ይችላሉ፡፡ አሁን ያለው አስታራቂ አካል ገለልተኛነቱ ጥያቄ ውስጥ
ወድቋል፡፡ የተለያዩትን አንድ ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ ጭራሽ አንድ የሆኑትን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከፊሎቹን ‹ጥቂት የቅ/ሲኖዶስ አባላት› እያለ ‹የመንጋው እንባና ጩኸት የማይገዳቸው ጥቂት የሲኖዶስ
አባላት› ብሎ ሲዘልፋቸው ሌሎቹን እያሞገሰ ይከፋፍላቸዋል፡፡
ለአንድ አመቻማች ወይም አስታራቂ አካል ደግሞ ትልቁ መመዘኛ ገለልተኛነቱ ነው፡፡
ሰሞኑን አስታራቂው ራሱ ያወጣውን የቅዱስ ሲኖዶስን አባላት የዘለፈበትና የከፋፈለበት መግለጫ እንደሚያሳየው ይህ አካል አመቻማች
ሳይሆን እንደ ጸጥታው ምክር ቤት የበላይ አካል ሆኖ የሚቆጣጠርና የሚያዝ ሆኗል፡፡ ‹በዚህ ቀን ተሰብሰቡ፣ በዚህ ቀን
አትሰብሰቡ፣ እኔ ሳልመጣ አትሰብሰቡ፣ እነ እገሌ እረፉ፣ ተጠንቀቁ› የሚል አካል ሆኗል፡፡ ሂደቱንም በሀገር ቤትና ከአሜሪካ ውጭ
ካሉት አባቶችና ምእመናን ዕውቅናና ሱታፌ ውጭ አድርጎታል፡፡
ስለዚህም ወደ በኣትህ ተመለስ ማለት ያስፈልጋል፡፡ የዕርቁን ሂደትም ሆነ
የአስታራቂዎቹን ማንነት፣ የዕርቁንም ቦታ ቅዱስ ሲኖዶስ በድጋሚ ቢያየው፣ ቢመረምረውና ቢያርመው መልካም ነው፡፡
በዚህ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኗ ካለችበት አጣብቂኝ አንጻር የተለያዩ ሃሳቦች ሊሠነዘሩ
ይችላሉ፡፡ ይህ በትክክለኛው መንገድ ከመጣ፣ የራስን ሐሳብ በኃይልና በሥልጣን በሌላው ላይ ለመጫን የሚደረግ ነገር ከሌለ፤
የሃሳቦች ከየቦታው መሰጠት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይጠቅማታል እንጂ አይጎዳትም፡፡ እንዲያውም ቅዱስ ሲኖዶስ እነዚህ ሃሳቦች
እንዲፋጩ አድርጎ የተሻለውን ለመምረጥ ያስችለዋል፡፡
በቤተ ክርስቲያን በሚከሰቱ ፈተናዎች በአባቶችና በሊቃውንት ዘንድ ሃሳቦች ሲለያዩ ይህ
የመጀመርያው አይደለም፡፡ በ13ኛውና በ14ኛው መክዘ በቤተ ክርስቲያን የሰንበትን አከባበር በተመለከተ በአባቶች መካከል የሐሳብ
ልዩነቶች ነበሩ፡፡ ቤተ ኤዎስጣቴዎሳውያን የሚባሉት አበው የሁለት ሰናብትን መከበር ሲደግፉ ቤተ ተክለ ሃይማኖታውያን ደግሞ
የአንድ ሰንበትን መከበር ይደግፉ ነበር፡፡
ይህ ሃሳብ በአባቶች መካከል ሲንሸራሸር መልካም ነው ያሉትን ሐሳብ ከመከተል ባለፈ
እገሌ ስለሚያዝንና ስለሚቆጣ፣ እገሌም ስለሚደሰት ብለው የሚቀይሩት ሐሳብ አልነበራቸውም፡፡ በቤተ ተክለ ሃይማኖት ሥር ከነበሩት
ገዳማት አንዱ ደብረ ብሥራት ዜና ማርቆስ በቦታ ለደብረ ሊባኖስ ቢቀርብም በአቋም ግን በኤርትራና በትግራይ እንደ ነበሩት
ገዳማት የሁለት ሰንበትን መከበር ይደግፍ ነበር፡፡ የአንድ ሰንበትን መከበር ያስተምሩ ከነበሩት ከሐይቅ እስጢፋኖስ መምህራን
የተማረው አባ ጊዮርጊስ በአቋም ግን ከእነርሱ ተለይቶ የሁለት ሰንበትን መከበር ይደግፍ ነበር፡፡ የሁለት ሰንበትን መከበር
በመደገፋቸው የደብረ ቢዘኑን አቡነ ፊልጶስን በሐይቅ እስጢፋኖስ በግዞት ያስቀመጣቸው የዐፄ ዳዊት ባለቤት ዕሌኒ ግን የአቡነ
ፊልጶስን ትምህርት ትቀበል ነበር፡፡
የተለያዩ ሐሳቦችን ይዞ መከራከርና በመጨረሻ ግን ለሚወሰነው ውሳኔ ተገዥ መሆን ያለና
የነበረ የቤተ ክርስቲያን ባህል ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሐሳቦች በደብረ ምጥማቁ ጉባኤ በተወሰነው ውሳኔ ነው ወደ አንድ አቋም
የመጡት፡፡
ዛሬም ቢሆን የተለያዩ ሐሳቦች መነሣታቸውና መንሸራሸራቸው ክፋት የለውም፡፡ ቅዱስ
ሲኖዶስ በምልዐት ተሰብስቦ አንድ አቋም ሲይዝና ያም የቤተ ክርስቲያኒቱ አቋም ሲሆን ሁላችንም ለዚያ ተገዥ እንሆናለን፡፡
ስለዚህም ‹ይህንን ወይም ያንን ሐሳብ ለምን ትሰጣላችሁ፤ እኛ የምንላችሁን ብቻ አራምዱ
የሚሉ አካላትም ወደ በኣታቸው ሊመለሱ ይገባቸዋል፡፡ ‹ጴጥሮስ ሆይ ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ› ሊባሉም ይገባል፡፡ የተለየ
ሐሳብ ያለውን ሁሉ ማውገዝ ፍቅርን ከማሻከርና የቤት ሥራ ከመጨመር በላይ ጥቅም እንደሌለው በቅርብ ጊዜ ታሪካችን የተማርን
ይመስለኛል፡፡
እናም ‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ›
‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ›
ReplyDelete"እኛ የምንላችሁን ብቻ አራምዱ የሚሉ አካላትም ወደ በኣታቸው ሊመለሱ ይገባቸዋል፡፡"
የዕርቁን ሂደትም ሆነ የአስታራቂዎቹን ማንነት፣ የዕርቁንም ቦታ ቅዱስ ሲኖዶስ በድጋሚ ቢያየው፣ ቢመረምረውና ቢያርመው መልካም ነው፡፡
ስለዚህ ሁላችንም የእግዚአብሔርን ስራ ቸል ብለናልና ወደየበኣ ታችን ብቻ ሳይሆን ወደ ልቦናችንም እንመለስ.
WE NEED INDEPENDENT,COMPETEN AND INPARTIAL BOADY TO DEAL WITH THIS HUGE AND VERY COMPLICATED MATTER IN RECENT EOTC HISTORY.
ReplyDeleteGOOD BE WITH ALL OF US
‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ› ጥሩ መልዕክት ነው ወድጄዋለሁ፡፡ ግን ዳኒ ‹‹የተለየ ሐሳብ ያለውን ሁሉ ማውገዝ ፍቅርን ከማሻከርና የቤት ሥራ ከመጨመር በላይ ጥቅም እንደሌለው ‹በቅርብ ጊዜ ታሪካችን› የተማርን ይመስለኛል፡፡›› የሚለው አ/ነገር አልገባኝም፤የትኛው የቅርብ ጊዜ ታሪካችን? የገባው ሰው ቢመልስልኝ ደስ ይለኛል፡፡
ReplyDeleteLike it!
Deletele 21 amet teleyayiten yenornew newa?
Delete‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ› እግዚአብሔር ይባርክህ ዲ/ን ዳኒ መልካም እና አስተማሪ እይታ ነዉ።
ReplyDelete‹በሉ ሁላችሁም ወደየበኣታችሁ ግቡ፤ ከዚያ በኋላ ለክርክራችሁ መፍትሔ ታገኛላችሁ›
ReplyDeletebetun bealet lay yalsera mabel simeta.... Benegeroch hula E/rn maskedem enji Shifesaw/Shiferaw Welde Mariam, VOA, Dochvile... Maskedem yelebnm yealem yehone hula yealem newna. "sew zm sil hlinawn yadamtal hlina zm sil ewnetan(Egziabharn) yademtal, yawkal. "YEMESKELU SR KUMARTEGNOCH" Kemehon abatochachnen tebko abune "Petrosawinetn" yalabsln.
ReplyDeleteMuch better argument and suggestion than your prrvious post. I was really disapointed with your low level and mean spirited argument earlier. GOD bless you and may GOD give peace to our church.
ReplyDeleteሁሉም ወደየበዓቱ ይመለስ !!!
ReplyDelete"ሁሉም ወደየበዓቱ ይመለስ !!" Yes!! Yebetekerestianchin Lemed Yeheneber.Thanks Dani!
ReplyDeleteአሁንም ሌሎቹ ሁሉ ወደየበኣታቸው ይግቡና ቅዱስ ሲኖዶስ ከልዑካኑ ጋር በጋራ የሚሠሩ ሊቃውንትን ይመድብ፡፡
ReplyDeleteHulum wedebatu yemeles. i agree with you peace mediators role should be verified
ReplyDeleteይገርማል አንተም ዳንኤል ...ስተትን ነቅዞ ማውጣት ብቻ አይደለም የችግሩ መፍት ሔ የኛ አባቶችም እኮ በጣም እያጠፋ ነው የሰውን ትእግስት እየተፈታተኑ ነው እነሱን ማን ሀይ ይበላቸው ይሄ መግለጫ ለችግሩ ማባባሻ መሆን አልነበረበትም አሁን አበቃ ማለት ነው. የእርቁ ጉዳይ ስለዚ ላልታወቀ ዘመን የቤተክርስቲያን ችግር ሊቀጥል ነው .ያሳዝናል. ሰሚ ያጣ ህዝብ ሆንን~~
ReplyDelete
ReplyDeleteበኔ አመለካከት ኣባቶቻችን በጣም ዘግይተዋል ይህውላቹ ወገኖቼ እኔ የምኖረው በዳላስ ቴክሳስ ነው የተሰራው ደራማ የሚያናድ ነበር ከአስታራቂዎቹ መካከል ለምሳሌ አንዱ ዲያቆን አንዱኣለም ነው በዚህ በዳላስ እና በአካባቢዋ ላሉ አብያተ ክርስቲያናት በጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ ስጋበዝ አንኳን መረጦ ነወ የጠራው ግን ያልተጠሩት አብያተ ክርስቲያናት ካህናት የሰንበት ትምትርህ ቤት መዘምራን እና ምእመናን እሱ እንዳሰበው ሳይሆን እነሱ ግን የቤትክርስቲያኔ ጉዳይ ነው ብለው እንደዛ ባማረ መልኩ ኣባቶቻችንን ተቀበሏችው ይህንን ያደረገ እግዚአብሄር ይመስገን ይህንንም ላደረጋቹ እግዚአብሄር ይባርካቹ።ከዛም በዋላ አባቶች ወደሌላ አብያተ ቤተ ክርስቲያናት እንዳይሄዱ ተከላከለ ሁለቱን ኣባቶች ቢያግዳቸውም አቡነ ቀዎስጦስ ግን እዚህ ድረስ መጥቼ ሳላገኛቸው አልሄድም በማለት ሰኞ እለት በደብረ ፀሀይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወአቡነ አረጋዊ እንዲሁም በደብረ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ሊመጡ ቻሉ ወደ ማህበረ ቅዱሳን ፅህፈት ቤት መሄዳቸውንም ሰምቻለሁ ሽማግሌ ተብዬዎቹ ሲሰሩት ክነበረው ነገር ሌላም ሌላም ተጨማሪ ነገር ማለት ይቻላል ይሄ አኔ የምለው ግን ፍጥጥ ያለውን ኣድሎ ነው ሰዎች ግን የልጁ እንጂ የኮሚቴው ሃሳብ አይደለም እሱ የተወከለው በስደተኛዎቹ ስለሆነ ነው ሲባል ነበር አሁን ግን የሱ ብቻ አለመሆኑን ተረድቻለሁ ቢዘገይም ጥሩ ብላቹዋል ወገንተኛ ደጋፊ እንጂ ሽማግሌ ሊሆን አይችልም።
ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ
ReplyDeleteቅዱስ ሲኖዶስ በምልዐት ተሰብስቦ አንድ አቋም ሲይዝና ያም የቤተ ክርስቲያኒቱ አቋም ሲሆን ሁላችንም ለዚያ ተገዥ እንሆናለን፡፡
ReplyDeleteበአሁኑ ጊዜ በግልጽ እንደሚታየው ይህን አጋጣሚ እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የግል ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም በወንድማማች መካከል ጠብ የሚዘሩ አያሌ ሃይማኖተኛ ያልሆኑ ሰዎች አሉ፡፡ ይህን ጉዳይ ደግሞ አባቶቻችን የተገነዘቡት አልመሰለኝም፡፡ በተለይም የውጭ ውሃ የቀመሰ ሰው አለመረጋጋት በብዛት ይታይበታል፡፡ ለፀሎት ጊዜም የላቸው፡፡ ከሥር በል በል የሚል ርኩስ መንፈስ በዙሪያዎቻቸው እንደሚያገሳ አንበሳ ከቦዋቸዋል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ወደ ባዕቱ ይመለስ እንዳልከው ለእርቅ ውጭ የሄዱትም ወደሃገራቸው ተመልሰው ተረጋግተው እዚህም ያሉት ተረጋግተው መድኃኔ ዓለም ቋጠሮውን እንዲፈታልን ቢፀልዩልን መልካም ነው፡፡
ReplyDeleteምዕመናን በጸሎት ፤ እውቀቱ ያላቸው እንዲህ ከላይ እንደምናነበው ያለ ቀና ሀሳብ በመስጠት የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት ብናስብ ሌላውን ሥራ ከእግዚአብሔር ሥልጣን ለተሰጣቸው ቅዱሳን አባቶቻችን ብንተወው!!!
ReplyDeleteit is much better than your earlier article
ReplyDeletethis is better than your previous post
ReplyDeleteto be the real DANIEL KIBRET ANTEM WEDE BEATIH
LITGEBA YIGEBAL
ዳኒ፤አዎ፤ሁሉም99%ስራን ለእግዚአብሔር ይስጥ,1%ቱን ብቻ ይስራ።እኔ ሁሉንም ካልተናገርኩ ሁሉንም ካልሰራሁ ማለት አያዋጣም።ምክንያቱም እግዚአብሔር ለቤቱና ለልጆቹ ከማንም በላይ ስለምያስብ።
ReplyDeleteነጌ ይሔ ሁሉ በእርሱ ፍቃድ ተስተካክሎ መተዛዘብ በታሪክ መወደስ ወይም መወቀስ ስለምኖር ሁሉም ወደእየህሊናውና ወደእየበኣቱ ተመልሶ ብያስብ መልካም ነው።
Thank you so much Dani. You realy understand the problem. Egzeabher yibarkih
ReplyDeleteውድ ወንድሜ ዲን ዳንኤል-ሐሳቡ አይከፋም። ነገር ግን አይናችሁን ጨፍኑ፤ እኛ እንደፈለግነው እንናድርግ የሚባልበት ደረጃ የደረስን ይመስለኛል። አባቶቻችንን አንዳች ነገር ጠፍንጎ ይዟቸዋል። አንድን አባት አባት የሚያስብለው እንደ አባት የሚጠበቅበትን እስከ አደረገ ድርስ ነው። ጫናዎች እንዳሉ ይገባናል። ጥያቄው ጫናውን ለመቋቋምና ከሕዝብ ጎን ለመሆን ለምን አንዳች ድፍረት ጠፋ? ምዕመኑ ነው ወይስ አባቶች አረጋጊ መሆን ያለባቸው? የተገላጦች የሆነ ነገር ይታያል። ሁሉም ነገር ያደባባይ ሚስጢር ሆኗል። አባ እንትና የእገሌ ደጋፊ፣ አባ እንትና የእገሌ ጠላት፣ አባ እኒያኛው መሃል ሰፋሪ እየተባሉ በምድብ መምድብ ሲቀመጡ ማዬት ታላቅ ውርደት ነው። ይሄን እያዩ ወደ በአት መግባት-ውጤቱ ምን ይሆን? ለእኔ “ወይ ስምህን ወይ ግብርህን“ እንዳለው ያ የአገራችን መሪ፤ ቁርጣቸውን መንገር ያለብን ይመስለኛል። ለምን ይሆን የአባትነት ውላቸው እንዲህ የጠፋው? ምነኩስና ምን ይሆን? እኒያን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶች ያበቀለች አገር፤ እንዴት አሁንስ ልጆቼን አድምጡ ብሎ ድምጹን አሰምቶ የሚናገር አንድ አባት ይጠፋል? የምን ከዚህም ከዚየም መንገራገጭ ነው? ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ? ይህ የአባቶቻችን እንካ ስለካቱያና ትዕቢት በአገራችን መዓት ሊያመጣም ይችላል። ያ ምስኪን ወገኔ ምን ተዳው? ዛሬ ምን እበላ ይሆን እያለ እያሰላሰለ፣ አምላኩን በተሰበረ ልብ የሚለምን ምስኪን ወገኔ ጫንቃ ላይ ተቀምጠው፤ የቃላት መረጣውና ውርወራው፤ ቅድመ ሁኔታ ድርደራው ምን ይሆን? ለሁሉም ልብ ይስጠን!
ReplyDeleteአስተያየቴ በሰው ሰውኛ መሆኑ ይታወቅልኝ። አምላካችን ዝም አይልም፤ አንዳች ነገር ያደርጋል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። እያደረገም ነው። ነገሮቹን ሁሉ ለትንተና እንዳይመቹ አድርጎም አሳይቶናል!
"ሲሆን ሲሆን ምንም አስታራቂ አያስፈልግም፡፡ ነገር ግን አመቻማች (facilitator) ካስፈለገ ሁለቱም አካላት በጋራ ሊሰይሙ ይችላሉ፡፡ አሁን ያለው አስታራቂ አካል ገለልተኛነቱ ጥያቄ ውስጥ ወድቋል፡፡ የተለያዩትን አንድ ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ ጭራሽ አንድ የሆኑትን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከፊሎቹን ‹ጥቂት የቅ/ሲኖዶስ አባላት› እያለ ‹የመንጋው እንባና ጩኸት የማይገዳቸው ጥቂት የሲኖዶስ አባላት› ብሎ ሲዘልፋቸው ሌሎቹን እያሞገሰ ይከፋፍላቸዋል፡፡"
ReplyDeleteዛሬ ደግሞ አስታራቂዎቹ ላይ የስጠኸው አስተያየት ይገርማል!
እውን በዚህ ጉዳይ እየሰጠህ ያለኸው አስተያየት ያንተ ነው?
በቤተ ክርስቲያን ሞገድና ማዕበል ሲነሣ የሚያዋጣው ‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ› ብሎ መጮህ ነው፡፡
ReplyDeleteከነገሮች መደበላለቅ የተነሳ በዓታቸው ወዴት እንደሆነ የጠፋባቸው ካሉ እግዚአብሔር ይርዳቸው፣
ReplyDelete‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ›!!!!
ReplyDelete1.የዕውቀት እንጂ የሕይወት ሰዎች መሆን ተስኖናል።
2.የሚታየን የሰው ጉድለት እንጂ የራሳችን አይደለም።
3.እምነታችንን ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ፥ በገድላት ፥ በተአምራትና በድርሳናት ከተጻፉት የእምነት ታሪኮች አንፃር ስናየው ባዶ ሆኖ ነው የምናገኘው። የዔሊ ልጆች አፍኒን እና ፊንሐስ በእግዚአብሔር ማደሪያ በደብተራ ኦሪት እያገለገሉ እግዚአብሔርን አያውቁም ነበር። ፩ኛ ሳሙ ፪፥፲፪። በቅድስናውም ስፍራ ያመነዝሩ ነበር። ፩ኛ ሳሙ ፪፥፳፪። ማንኛውም ሰው እምነት ሲጐድለው እንዲህ ነው ፥ ፈሪሃ እግዚአብሔር አይኖረውም። እምነቱ ሙሉ የሆነ ዮሴፍ ግን በአሕዛብ ምድር ሆኖ እግዚአብሔርን ፈራ። በቤተ ክርስቲያን እየኖርን ፦ በመጸለይና ባለመጸለይ ፥ በመጾምና ባለመጾም ፥ ንስሐ በመግባትና ባለመግባት ፥ በማስቀደስና ባለማስቀደስ ፥ በመቁረብና ባለመቁረብ ፥ መስቀል በመሳለምና ባለመሳለም ፥ ጠበል በመጠጣትና ባለመጠጣት ፥ በመጠመቅና ባለመጠመቅ ፥ ቃሉን በመስማትና ባለመስማት ፥ በመዘመርና ባለመዘመር ፥ አሥራት በማውጣትና ባለማውጣት ፥ በዕርቅና ጥል ፥ በሃይማኖትና በፖለቲካ መካከል ልዩነቱ እየጠፋብን የሄደው እምነታችን እየጐደለ በመሄዱ ነው።
ስለዚህ:-የዘወትር ጸሎታችን « አለማመኔን እርዳው ፤», « እምነት ጨምርልን ፤» መሆን አለበት::
4.ሃላፊነት አለመወጣት ያስጠይቃል...:- « እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳዊያን መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ፥ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም ፥ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።» እንዳለ። ማቴ ፳፫፥፲፫።ስለዚህ በሩን ይዘን እንቅፋት አንሁን::
የተለያዩ ሐሳቦችን ይዞ መከራከርና በመጨረሻ ግን ለሚወሰነው ውሳኔ ተገዥ መሆን ያለና የነበረ የቤተ ክርስቲያን ባህል ነው፡፡ ነገር ግን 4 የተለያዩ ሐሳቦችን ይዞ ወደነፈሰው ....???? አያዋጣም::
"Ale mamenen erdawu, Emnet chemrilign"
Deleteጆሮ ያለው ይስማ
ReplyDeleteገበያ ቢያመቻት እናትዋን ሸጠቻት እንዳይሆን
ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን አማኞች ብልህ መሆን አለብን
ወለተ ሚካኤል ነኝ፡፡
Dear Dn Daniel,
ReplyDeleteThis is the kind of article we expected from you; your previous article on this issue was referring to the past event, which we can't help! Thanks anyway.
Yes Dani..this is timely message. ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ....The Addis Synod, the America (migrant) Synod,the mediators, the government, Mahiber Kidusan, Deje selam, Andadrgen, Hara Tewahdio and other EOTC blogs all let them get back to their Be'ats. Dani including your self ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ....This is the time for prayer....
ReplyDeleteእግዚኦ መሃረነ ክርስቶሰ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ እ……ግ……ዚ……ኦ…….. መ……ሃ…..ረ….ነ….. ክ……ር…..ስ….ቶ….ስ…..
ReplyDeleteትንቢት በእንተ ሳምኒት ዘመን
አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር
ወውኅደ ሃይማኖት እምዕጓለ እመሕያው
በከናፍረ ጒሕሉት ልበ ወበልብ ይትናገሩ
ይሤርዎን እግዝአብሔር ለከናፍረ ጒሕሉት
ወለልሳን እንተ ተዓቢ ነቢበ
እለ ይብሉ ነዐቢ ልሳናቲነ
ወከናፍሪነኒ ኀቤነ እሙንቱ
መኑ ውእቱ እግዚእነ በእነተ ሕማሞሙ ለነዳያን
ወበእንተ ገዓሮሙ ለሙቁሓን
ይእዜ እትነሳእ ይቤ እግዚአብሔር
እሬሲ መድኃኒተ ወአግህድ ቦቱ
ቃለ እግዚአብሔር ቃል ንጹሕ
ከመ ብሩር ጽሩይ ንጡፍ ወፍቱን እምድር
ዘዓጽረይዎ ምስብዒተ
አንተ እግዚኦ እቀበነ ወተማኅፀነነ
እምዛቲ ትውልድ ዘለዓለም
አውደ የሐውሩ ረሲአን
ወበከመ ዕቤየ ልዕልናከ ሠራዕኮሙ ለደቂቀ እምዕጓለ እመሕያው
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም
Amen::
Deleteabetu adnn
ReplyDeleteabetu adnen
ReplyDeletemin ydereg abatochachin fit lefit wotuna hulum afunkefete
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥህ የሰለቸን ነገር ቢኖር የማያገባውን የማይገባውን
ReplyDeleteየሚናገረው ነው ምን አባቶች ብቻ ምዕምኑም ወደ በአቱ ይግባ እረ በቃ ይበለን
Hulum wedeyebe'atu yimeles!!!!!
ReplyDeleteለተቀማጭ መሪት ቅርብ ናት! የመለያየቱ ጉዳይ አሳስቡአቸው ለማስታረቅ የተነሱት እኮ እነሱ ናቸው. የሚሰራን ሰው ከመተቸት ቢያጠፉ እነኩአን ለራሳቸው ትነግራቸዋለህ እንጂ በ አደባባይ "መግለጫ" አታወጣባቸውም. እራስህም በዚ ጉዳይ ያለህን አሳብ ሳትፈራ ወደባእትህ ተመልሰህ አስብ
ReplyDeletemy point exactly!
Deleteእግዚአብሔር ይስጥህ የሰለቸን ነገር ቢኖር የማያገባውን የማይገባውን
ReplyDeleteየሚናገረው ነው ምን አባቶች ብቻ ምዕምኑም ወደ በአቱ ይግባ እረ በቃ ይበለን
ወቅታዊ አባባል። ይበል ብለናል
ReplyDeleteለሁሉም እግዚአብሔር ይጨመርበት
ዳላስ፤ቴክሳስ
ዳንኤል በሌሎቹ ጽሁፎቹ ስላለው የምለው የለኝም ነገር ግን 'ሁሉም ወደ የበአቱ ይመለስ' በሚለው ጽሁፍ እርጋታን ሰከን ብሎ ለአባቶች ምክክር ቅድሚያ ሰጥቶ ማየት እንደሚገባ መምከሩን እኔም ደግፋለሁኝ አንድ ስለእውነት መመስከር የምንፈልግ ሰዎች ማወቅ ያለብን ይሄንን የእርቅ ሂደት ሃገር ቤትም ውጭም ያሉ ፖለቲከኞች በከፍተኛ ሁኔታ ሊጠቀሙበት እንደሚፈልጉ ሲሆን፡ እኔም በዳላስ ነዋሪነቴ መሀከለኝነት የጎደለው ሁሉንም እንቅስቃሴ በሆነ ንፋስ አቅጣጫ ብቻ እንዲጓዝ የማድረግ መንፈሳዊ መሳይ ጫና በአባቶችም ላይ ጭምር ሲደረግ ታዝቤአለሁኝ። ድሮም አባቶች መሃል ፖለቲከኞች ገብተው ነው ልዩነት የፈጠሩት አሁንም መንፈሳዊ መሳይ የግል ጥቅመኞች የ/ ፖለቲካ፣ ዘር፣ ስልጣን፣ ስም/ ጥቅም የሚፈልጉ ሰዎች እየረበሹ ይመስለኛልና አሁንም አባቶች ከ Special Interest Group ነጻ ሆነው እስካልተወያዩ ድረስ እኔ እንጃ። እንደምናየው በሃገር ቤት ባለው ሁኔታ የኢህአዴግን ነፃነት ገፋፊነት እርሱ በፈለገው ሁኔታ ብቻ እጅ እየጠመዘዘ ማስኬዱን ሃገር መበተኑን ተቃውሞና ተጋፍጦ ህዝባችን እና ቤተክርስቲያናችንን ነጻ የሚያወጣ ወይም ሰማእት ሆኖ ለውጥ የሚያመጣ ወይም የለውጡን ጉዞ የሚያፋጥን ዘር ስላልተረፈ እስኪ ቢያንስ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሰዎች አባቶችን ነጻ ለቀው እንዲስማሙ ቢፈቅዱላቸው። ቤተክርስቲያን አንድ ሆነች ማለት እኮ ሃገር አንድ ሆነች ማለት ነው በእርቁ ስም የጎደለን ለመሙላት ከመጣር አባቶች ንጹህ እርቅ ታርቀው ሃገራችንና ቤተክርስቲያናችን በሚፈስላቸው የፍቅር ጸጋ የጎደለን እንዲሞላ ብንፈቅድ። ቤተክርስቲያን አንድ ስትሆን የኢትዮጵያ ትንሳኤ እንደሚሆን ጠንቅቀው የሚያውቁ የኢትዮጵያ ጠላቶች አሉኮ ጎበዝ።
ReplyDeleteDani, You have written really a good article on this very important issue on a very high time. It is high time for us to come together and to end that boring separation/meleyayet. Let Emebirhan Tirdan.Let egizihabiher bekachuh yibelen!!!"ሁሉም ወደየበዓቱ ይመለስ !!"
ReplyDeleteThank you Dani, Emebirhan yeageligilot zemenihin tibarkilih!!!
Please somebody explain to me if this teaching of our lord Christ has any implication to the holly father's or it’s meant only for the rest of us.
ReplyDeleteMatthew 5:3-13
Blessed are the poor in spirit: for theirs is the kingdom or heaven.Blessed are they that mourn:for they shall be comforted.Blessed are the meek:for they shall inherit the earth.Blessed are they which do hunger and thirst after righteousness:for they shall be filled.Blessed are the merciful:for they shall obtain mercy.Blessed are the pure in heart:for they shall see God.Blessed are the peacemakers:for they shall be called the children of God.Blessed are they which are persecuted for righteousness sake:for theirs is the kingdom of heaven.Blessed are ye,when men shall revile you,and persecute you and shall say all manner of evil against you falsely,for my sake.Rejoice,and be exceeding glad:for great is your reward in heaven:for so persecuted they the prophets which were before you.
ye are the salt of the earth:but if the salt have lost his savour, wherewith shall it be salted? it is thenceforth good for nothing, but to be cast out,and to be trodden under foot of men.
melkam new. Egziabher leabatochachen kena lebuna yistelen;
ReplyDeleteለእኔ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ዛሬ ሥር ሰድዶ የሚታየኝ ኃጢኣት ይህ ነው- ትዕቢት፡፡ C.S. Lewis የሚባሉ የሃያኛው ክፍለ ዘመን የቤተክርስቲያን ሊቅ “ትዕቢተኛ ሰው ከእነማን በላይ እንደኾነ ለማየት ቁልቁል ቁልቁል በመመልከት ስለሚጠመድ ቀና ብሎ እግዚአብሔርን ለማየት ጊዜ የለውም፡፡” ይላሉ፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡
ReplyDeleteበቤተክርስቲያን ጉዳዮች ውስጥ ሱታፌ እናደርጋለን የሚሉ ምእመናንም ኾኑ ጳጳሳት እውነት ክርስቶስ ብቻ ስለኾነ እውነቱ እኔ ያልኹት ብቻ ነው የምትልን በአጉል አርበኝነት ውስጥ የምትሸሸግ ትዝኅርት ከውስጣቸው ሊያወጧት ይገባቸዋል፡፡ አንድ አባቴ በአንድ ወቅት እንዳሉት “ሰይጣን IDIOT አይደለም፡፡” ከጌታችን የሚለየንን ኃጢኣት የሚያሠራን ከጌታ ጋር ያቀራረበን አስመስሎ ነው፡፡ ዘፍጥረት እንደሚተርከው እባቡ አዳምና ሔዋንን የጣላቸው “እንደእግዚአብሔር ትኾናላችሁ፡፡” በምትል መልካም በምትመስል ምክር አልነበረምን? ሐዋርያቱንስ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ብለው እዲፎካከሩ ያደረጋቸው የጌታ የቅርብ ወዳጆች ለመኾን የነበራቸውን በጎ የምትመስል መሻት በመጠቀም አልነበረምን? ገጣሚና ሠዐሊው ገብረ ክርስቶስ ደስታ
“የዓለም መራራነት ነው የሚጣፍጠን
መቼ መጣፈጧ፤
ኮሶውን በማሯ ጠቅልላ ስትሰጠን
ስትሰጠን እሳቱን
አመድ አስመስላ ሸፍና ረመጡን፡፡
ስትሰጥ ማየ ሕይወት ስሰጠን መድኃኒት
መርዟን ጨምራበት፡፡”
እንዳለው ትክክል እየመሰሉን የምንሠራቸውን ነገሮች ኹሉ ከትክክለኛው ከእግዚአብሔር አንጻር ብቻ መመልከት መጀመር ያለብን ይመስለኛል፡፡ የምናደርገው ነገር ወይም የምናስተምረው ትምህርት ሰዎች “ትክክል ናችሁ!” ስላሉን ወይም ብዙ ደጋፊዎች ስላገኘን ወይም እኛ ትክክል እየሠራን ስለመሰለን ወይም “ትክክለኛ” የሚል ስም ስለለጠፍንበት ብቻ ትክክል ሊኾን አይችልም፡፡ ድርጊቶቻችን፣ ንግግሮቻችንና ሐሳቦቻችን ትክክል የሚኾኑት በፍቅር ላይ ሲመሠረቱ ብቻ ነው- እግዚአብሔር ፍቅር ነውና፡፡ ይህ ፍቅር ደግሞ እንኳን ቤተክርስቲያን ውስጥ ትዳር ላይ እንኳ በተግባር የሚገለጥ “የወንድሞችን እግር በማጠብ” ላይ የተመሠረተ ነው እንጂ በግላዊ ተጠቃሚነት ወይም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ “እኔ” ሳልኾን ወንድሞቼ የሚከብሩበት፣ ወንድሞቼ የሚጠቀሙበት፣ ወንድሞቼ የሚገለገሉበት ነው፡፡ ድርጊቴ፣ ንግግሬ፣ ሐሳቤ በዚህ እግዚአብሔራዊ መንገድ ከተቃኘ ብቻ የምናገረውም የምሠራውም የማስበውም እውነት ብቻ ይኾናል፡፡ ከዚህ ውጪ ግን እውነት የለችም፡፡ እውነትም ፍቅርም እግዚአብሔር ብቻ ነውና፡፡ በቅርቡ በዚሁ በአንተ ብሎግ ላይ “ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ (በረከታቸው ይደርብንና) “ያለ ፍትሕ ሰላም ያለይቅርታ ደግሞ ፍትሕ የለም፡፡” ብለዋል፡፡” የሚሉ አስተያየት ሰጪ ነበሩ፡፡ እውነት ነው፡፡ ተበድለናል የሚሉ እንዲካሡና ፍትሕ እንዲያገኙ መጀመሪያ ይቅር ለማለት ዝግጁ መኾን አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ትናንት የተደረገን ጥፋት ዛሬ ላይ ኾነን እንደኮምፒወተር አንዱ “Undo” ልናደርገው አንችልምና፡፡
ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ችግሮች እንዲፈቱ የቤተክርስቲያን ቅን አሳቢዋ የኾንኸው አንተ ካነሣኻቸው ሐሳቦች በተጨማሪ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ሐሳቦች በመንፈሳዊ አቅጣጫ ጠቃሚ ይመስሉኛል- ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ምሥጢራዊ መንፈሳዊት አካሉ ናትና፡፡
አንድም የቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚመሰክርልን ቤተክርስቲያን መዋቅራዊ ችግሮች የሚገጥሟት የምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት በኃጢኣት ሲነቅዝ ስለኾነ በቅድሚያ መንፈሳዊ አቋሟን ልታስተካክል ይገባታል፡፡ የሦስተኛው ክፍለ ዘመን ሊቅ ቅዱስ አምብሮስ ቤተክርስቲያንን “Casta Meretrix” (Chaste Prostitute) ይላታል፡፡ በአማርኛ “ንጽሕት ጋለሞታ” ማለት ነው፡፡ “ንጽሕት” አላት፤ ምክንያቱም የክርስቶስ ስለኾነች፤ እርሱ በደሙ ስለመሠረታት፤ ከአደፍና ከፊት መጨማደድ ኹሉ ያነጻት ዘንድ ስለተሰዋላት፡፡ “ጋለሞታ” አላት፤ ምክንያቱም በፈቃዳችን ኃጢኣት እየተመላለሰ የሚያረክሰን የእኛ የምእመናን ጉባኤ ስለኾነች፡፡ ስለዚህም ነው በየጊዜው ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን ግንኙነት የምናድስበት የመንፈሳዊ ሕይወት ተሐድሶ የሚያስፈልገን፡፡ ግልሙትናችን ሲበዛ እታወካለን፡፡ ቅዱሳን አበው ያሳዩንን መንገድ ትተን በእግዚአብሔር ፈንታ ሌሎች ነገሮችን አምባ፣ መጠጊያ፣ መታመኛ ስናደርግ እግዚአብሔርንም የእነዚህ ጣዖቶቻችን ጠባቂ እንዲኾንልን ስንፈልግ ወይም ጠባቂ እንዲኾንልን ጠፍጥፈን ለመሥራት ስሞክር የተፈጠርንበትን ዓላማ ስተናልና እንታወካለን፤ እንሸበራለን፤ እንፈራለን፡፡ ልክ እንደአዳም ሊሸሽገን ይችላል ብለን በምናስበው ነገር ሥር በመደበቅ ከለላ ለማግኘት እንሞክራለን፡፡ መጽሐፍ ግን “በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።” (ኤር. 17፣ 5) ይለናል፡፡ ስለዚህም፡-
ReplyDeleteኹሉም ወደ ውስጡ ተመልሶ ድርጊቶቹን ከእግዚአብሔር አንጻር ቢመለከትና ቢገመግም ለዚህም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከቅዳሴ ውጪ ምንም ቃል የማይሰማበት የዝምታ ሱባኤ በምእመናኑ ኹሉ ቢያዝ
ምሥጢረ ክህነት የተፈጸመለት ሰው በሙሉ ክህነቱ ለእርሱ ምን እንደኾነች (“መዓርግ” ወይስ ምሥጢር) ኹሉን በሚያይና በሚያውቅ በእግዚአብሔር ፊት በዝምታ እርሱና እግዚአብሑር ብቻ ወደሚያውቁት ወደውስጡ ራሱን ቢፈትሽ
ጳጳሳቱ ኹሉ ከቻሉ እርስበርሳቸው ተነጋግረው እነርሱ ብቻቸውን ማንም ጣልቃ ሳይገባባቸው ከቻሉ አንድ ላይ፣ ካልቻሉ በያሉበት ለአንድ ሳምንት ሕዝብና አሕዛብን አንድ ያደርግ ዘንድ፣ ቤተክርስቲያንን ከልዩ ልዩ ወገን ይሰበስብ ዘንድ በመስቀል ላይ እጁን በምስማር የተቸነከረላትን የኢየሱስን ሕማማት በማሰብ፣ በማሰላሰልና በማስተንተን ቢጸልዩ
ማንም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቦ ዝም እንዲል ቢደረግና እንደእመቤታችን እግዚአብሔር የወደደው ብቻ እንዲኾልን “ነየ አመቱ ለእግዚኣ ኵሉ፤ ይኵነኒ በከመ ትቤለኒ” የሚለውን የቃሏን ምሥጢር ብናስተነትን
እኛ ዝም ካላልን እግዚአብሔር አይናገርም፤ ቢናገርም አንሰማውም፡፡ እርሱ ላይ ካልተመሠረትን ደግሞ ብንረዝም እንኳ ሳንወድቅ አንቀርም፤ ብንበዛ እንኳ አናሸንፍም (1ኛ ነገ. 19፣ 12)፡፡
"Egna zim kalalin Egziabher aynagerim, binagerm anisemawum:: Ersu lai kaltmseretin degmo binlezim enkua sanwodiq aniqerm, binbeza enkua anashenfim::"
Deletesile qalu abatachin yimsgen. qalun lakafelun commenter degmo yinurulin
ጂቦች ተሰበሰቡ አሉ
ReplyDeleteሁሉም ባንድነት ውሳኔ አሳለፉ
ምን ብለው ?
እ ን ብ ላ ው::
TADYA 1 ENKAN YE BEKA ABBAT YELENM MALET NEW .... EBAKACHU TSOLOT ENADRG .... KEZIH YETSHAL GIZI LAYNOREN YECHLAL... EBAKACHU TSELIU ... ENGANM WED BEATACHN ENGEBA ENA ENTSELI ... MEMHRACHN DYAKON DANIEL KIBRET ANTEM....SELZIH BETKRSTIAN YEMGEDACHEW AGELGAYOCH HULACHU TSOLTEN TGU...
ReplyDeleteTru, mkniyatawina astaraki hasab new!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteሁሉም ወደየበዓቱ ይመለስ
ReplyDeleteA religious person in North America once said
ReplyDelete{the danger of christianity is too much knowledge and too little practice).We all fall
in this fruitless affair.No body gives priority
to God more than his income generating hole.
D.God reads our hearts.Are we really committed
to peace?Which situation is better to those who
like run business and harm Orthodox?
‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ›
ReplyDeleteአኔ ተመልሻለሁአኔ ተመልሻለሁ