እነሆ ከጎንደር ከተማ ከጠዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ተነሣን፡፡ የምናመራው በአዲሱ
የጎንደር ባሕር ዳር መንገድ ወደ አዲስ ዘመን አቅጣጫ ነው፡፡ ይህ አዲሱ የአስፓልት መንገድ የገበሬዎችን እርሻና አስደናቂ
የሆኑትን የሰሜንና ደቡብ ጎንደር ተራራማ ቦታዎች እያቋረጠ የሚጓዝ በመሆኑ ዓይናችሁን ከግራና ቀኝ የተፈጥሮ ትርዒት
አትነቅሉም፡፡
በመንገድ ላይ በኩራት ከቆሙት ዐለቶች አንዱ
የሩቅ ምሥራቅ ምንጣፍ የመሰሉ እርሻዎች፣ እንደ ሞዴሊስት ወገባቸውን ይዘው የልብስ
ትርዒት የሚያሳዩ የሚመስሉ ወጥ ድንጋዮች፣ በዛፎችና ቁጥቋጦዎች የተሞሉ ተራሮች በመንገዱ ግራና ቀኝ እየተሰናበቷችሁ ያልፋሉ፡፡
ሾፌራችን ሞላ ረጋ ብሎ ለጎብኝ በሚያመች መንገድ ይነዳል፡፡ የጎንደር ልደታው ሙሉቀን ደግሞ እያንዳንዷን መሬት ልቅም አድርጎ
ያውቃታል፡፡
ምዕራፋችን የሆነው ሦስቱ ታላላቅ ገዳማት የሚገኙባት የጣራ ገዳም አካባቢ ነው፡፡
እዚህ ቦታ ጣራ ገዳም፣ ዋሻ እንድርያስና ዋሻ ተክለ ሃይማት የተባሉ ገዳማት ይገኛሉ፡፡ የመጀመርያ ጉዟችን ወደ ዋሻ እንድርያስ
ነው፡፡
ዋሻ እንድርያስ በ13ኛው መክዘ ከተሠሩት የጎንደር የዋሻ ገዳማት አንዱ ነው፡፡
ያነጹት የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር የነበሩትና ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር በሁለተኛው የኢየሩሳሌም ጉዟቸው የተገናኙት
አቡነ እንድርያስ ዘመርሐ ቤቴ ናቸው፡፡ አቡነ እንድያስና አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተገናኙት በደብረ በንኮል ገዳም መሆኑን
ገድላቸው ይገልጣል፡፡ አቡነ እንድርያስ በላስታ፣ ጎንደር መንገድ አልፈው፣ በጎጃም በኩል በመሻገር መጀመርያ ወደ ደብረ ሊባኖስ
ተጉዘው ከአሥራ ሁለት ዓመት በኋላ ወደ እብናት አካባቢ መምጣታቸውን ነው ገድሉ የሚናገረው፡፡
አቡነ እንድርያስ
ገድለ አቡነ እንድያስ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ታሪክና ጉዞ በገድለ ተክለ
ሃይማኖትም ሆነ በሌሎች መዛግብት የማናገኛቸውን አዳዲስ ታሪኮች የሚገልጥልን ልዩ መጽሐፍ ነው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ከትግራይ ወደ ላስታ ተጉዘው ከላስታ በተከዜ በኩል ወደ ጎንደር እብናት መምጣታቸውን፤ ከዚያም በዚህ በጣራ ገዳም በኩል
ማለፋቸውን ይተርካል፡፡ ይህ መንገድ ዛሬም የጎንደር ሰዎች ላሊበላን ለመሳለም ወደ ላስታ የሚሄዱበት በመልዛ በኩል ያለው
መንገድ ነው፡፡
አቡነ እንድርያስ ወደዚህ ቦታ ሁለት ጊዜ መጥተዋል፡፡ መጀመርያ ከደብረ በንኮል
ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የተከዜን ወንዝ ተሻግረው ሲሆን በኋላም በአካባቢው ወንጌል እንዲያስተምሩ ተልከው ነው፡፡
በመጀመርያው ጉዟቸው ወሎን ተሻግረው ዐርፈውበት የነበረው ቦታ እብናት ውስጥ ዛሬ ‹ደብር ተክለ ሃይማኖት› የሚባለው ሥፍራ
ነው፡፡
ዋሻው መልኩ የይምርሃነ ክርስቶስን ይመስላል፡፡ ከአንድ ተራራ ሥር የነበረውን የተፈጥሮ ዋሻ በመጠቀም የተገነባ ነው፡፡
በሮቹ ከእንጨት የተሠሩ ሲሆኑ በበሮቹ አራት መዓዝን የሚገኙት ወጣ ወጣ ያሉት ነገሮች የዘመነ ላሊበላን የሕንጻ አሠራር የሚያሳዩ
ናቸው፡፡
የዋሻ እንርያስ በር
ልክ እንደ ላሊበላ ውቀር አብያተ ክርስቲያናትና እንደ ይምርሃነ ክርስቶስ ሁሉ እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ መስኮት አንዱ
ከሌላው ጋር የማይገጥም የየራሱ ልዩ ዲዛይን አለው፡፡ በብዙዎቹ የጥንት ገዳማት ላይ የምናየው የድንጋይ ደወል እዚህም አለ፡፡ እንዲያውም
ከብዛቱ የተነሣ ሌሎች ‹አድባራት ይጠቀሙበት› ብለው ቢሰጡት በሄደበት ቦታ ድምጽ አላወጣ በማለቱ እንደተመለሰ ገዳማውያኑ ነግረውኛል፡፡
ወደ ውስጥ ስትገቡ አያሌ ጥንታውያን ነገሮችን ታያላችሁ፡፡
መሥዋዕተ ኦሪት ይሠዋበት የነበረው የደሙ ማቅረቢያ፣ በአካባቢው በነበረው ጥንታዊ የጣዖት አምልኮ ያገለግል የነበረ የጣዖት ቅሪት፣
የቀድሞውን ዘመን የገበጣ ጨዋታ የሚያሳይ ጥንታዊ የገበጣ መጫወቻ፤ ከእንጨት የተሠራ የመነኮሳት መሰብሰቢያ ቃጭል፤ የቀድሞ ነጋሪቶች፤
ወዘተ ለታሪክ ቀርተዋል፡፡
ዋሻ እንድርያስ ከተራራው ላይ ሲታይ
ዋሻ እንድርያስ የሚገኘው ከጣና ሐይቅ አጠገብ እንደመሆኑ፤ በአካባቢው በጣና ቂርቆስ ይከናወን ከነበረው ኦሪታዊ ሥርዓት፣
የአኩስም ሥልጣኔ ባለቤቶች የነበሩት የአገው ሕዝቦች በአካባቢው ከነበራቸው ቦታ አንጻር የዋሻ እንድርያስና የሥርዓተ ኦሪት ግንኙነት
በሚገባ ቢጠና ለሃይማኖት ታሪካችን ተጨማሪ ፍንጭ የሚሰጠን ይመስለኛል፡፡ በቦታው ያየሁት የኦሪት መሥዋዕት ማቅረቢያ በጣና ቂርቆስ
ከሚገኘው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
በአካባቢው የወይን እርሻ እንደነበረ የሚያሳይ የወይን ማጠራቀሚያ ጎታ፣ ለክፉ ቀን እህል ማጠራቀሚያ ያገለግል የነበረ
ጥንታዊ ጎተራ፣ የአባቶቻችንን ጥንታዊ ጥበብ የሚያሳይ ጥንታዊ ቁልፍ ይገኛሉ፡፡
ከዋሻ እንድርያስ መስኮቶች አንዱ
በግድግዳው ላይ የምታዩት ትንንሽ ጠፋጣፋ ድንጋዮችን በጭቃ እያጣበቁ ግድግዳ የመሥራት ጥበብ ልክ እንደ ይምርሃነ ክርስቶስ
ሁሉ እዚህም ጎልቶ ይታያል፡፡ በሁለቱም ቦታዎች ስለ ጥበቡ የሚተረከው ተመሳሳይ ነው፡፡ እዚያም እዚህም ጭቃው ሰባት ዓመት እንደሚቦካ
ይነገራል፡፡
በገድሉ ላይ የሚገኘውን አካባቢው ከላስታ ጋር የነበረውን ግንኙነት ስናየው የጥበቡን ትሥሥር ሊያመለክተን ይችላል፡፡
በይምርሃነ ክርስቶስ ጣራና ግድግዳ ላይ የምናየውን ዓይነት የሥዕል ጥበብ እዚህ በተሻለ ሁኔታ ተጠብቆ እናገኘዋለን፡፡
በዋሻ እንድርያስ የምናገኛቸው ሥዕሎች የጎንደርን ዘመን ሥዕሎች የሚያሳዩ አይደሉም፡፡ እንደ እኔ ግምት ከመካከለኛው
ዘመን እና ከዚያ በፊት ከነበሩት ሥዕሎች ጋር ተመሳሳዮች ናቸው፡፡ በተለይም የተጠቀሙበት ቀለምና በእንጨት ላይና በግድግዳ ላይ
በጭረት ለመሳል የተጠቀሙበት ዘዴ የላስታን ዘመን የሥነ ሥዕል ጥበብ ለመፍታት የመረጃ ምንጮች ለመሆን የሚያስችላቸው ነው፡፡
በዋሻ እንድርያስ የሚገኘው የኦሪት መሥዋዕት ማቅረቢያ የነበረ ዕቃ
አሁን ተገዝቶ መግባት ቀረ እንጂ ዋሻ እንድርያስን፣ ዋሻ ተክለ ሃይማኖትንና ዜና ማርያምን የሚያገናኝ የዋሻ ውስጥ መንገድ
አለ፡፡ ልክ ይምርሃነ ክርስቶስንና አቡነ ዮሴፍን የሚያገናኘውን መንገድ የሚመስል፡፡ አስጎብኛችን ከአምስት ዓመታት በፊት ገብተው
እንደነበር ነግረውናል፡፡ ወደ ታች መውረጃ ደረጃ፣ ከዚያም የዋሻ ውስጥ መንገድ፣ ቀጥሎም ዘይት መሰል ነገር ያለው ኩሬ እንዳገኙ
ተርከውልናል፡፡ ያ ኩሬ ጠበል መሆኑንና ብዙዎችን ሲፈውስ በዓይናቸው ማየታቸውንም አጫውተውናል፡፡ የሚገቡበት ዋናው ምክንያትም ከዚያ
ጠበል ለሰዎች ለመቅዳት እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ከኩሬው በኋላ ሰፊ ሜዳ መኖሩን ሜዳው እንዳለቀም መንገድ እንደሚገኝ ይገልጣሉ፡፡
ከእንጨት የተሠራ ቃጭል
ከእርሳቸው በፊት የገቡ አባቶች አንድ ቀን ሙሉ ሄደው ነገር ግን ከግማሽ መንገድ ማለፍ እንዳልቻሉና እንደተመለሱ እንደነገሯቸው
ተርከውልናል፡፡
የድንጋይ ደወል
ከተራራው ወደ ታች እየሰገዱ የሚወርዱት ዛፎች፤ በግራና ቀኝ የምትሰሙት የአዕዋፍ ዝማሬ፣ በመካከላቸው ጎንበስ ብላችሁ
የምታልፉት ዕድሜ ጠገብ ዛፎች እዚያው እንድትቀሩ እንጂ እንድትመለሱ አይመክሯችሁም፡፡ ከቤተ ክርስቲያኑ ስንወጣ በስተ ግራ በኩል
እናቶች በድንጋይ ወፍጮ እህል ይፈጫሉ፡፡ እኛ እየራቅን ስንሄድ ከአዕዋፉ ዝማሬ ቀጥሎ የሚሠማን ‹እርም እርም› የሚለው የወፍጮው
ድምጽ ብቻ ነበር፡፡
ዋሻ እንድርያስን በዚህ ተሰናብተን ጉዞ ወደ ዋሻ ተክለ ሃይማኖት ቀጠልን፡፡ ሳምንት እንገናኝ፡፡
KELBENEW, DANEAL EGZIABHER AMLAK BEMASTEWAL LAY MASTEWALEN, BETEBEBLAY TEBEBEN,BEWKETLAY EWKETEN, BEMEKERA GEZE TENT LEABATOCHACHEN YESETEWEN TEGST ENA TSNATEN ; BENUROH ENA BEHEYWETEH DEGMO TEBEBEN ENA FEKREN YAGONATSFEH SEMATU HULEM KEANTEGAR YEHUN
ReplyDeleteANBABIEH TERSITEWOLD KEGERMEN
Egziabher yibarkih..
ReplyDeleteየጻፈ ያጻፈ የሰማ ያሰማ ያነበበ የተረጎመ ከሚለው ቃል ኪዳን ያሳትፈን!
ReplyDeleteወንድማንች ሳምንት መቼ ነበር? እረ ልቀቀው ‘አቦ’ የምን ልብ ማንጠልጠል ነው? በነገራችን ላይ የዚያ አገር ሰዎች ሲርቅ ስለ ለንደን ምናምን ያወሩልናል እቅርብ ያለ ጠበል ሆኖ ይሆን? ሲቀርብ ደሞ ያገራቸው ታቦት ካልሆነ ስለት የሚሰማ አይመስላቸውም:: ቢጽፉም ቢናገሩም ከነሱ ድብር ውጭ ሌላ ደብር ከነርሱ መምህር በቀር ሌላ የኔታ ያለ አይመስላቸውም:: ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር የምስጢር አገሩ ነች ይሉ ነበር መምህራችን:: ፈልፍለው እስኪ ወንድሜ:: ሂድ ዙሪያዋን ጎብኛት ጻፍልንም:: ከኛ እግዜር ይስጥልኝ የምታተርፈውን ሳስበው ዋጋህን ከፍ ያደርግብኛል:: ቀጣዩን በናፍቆት . . .
God bless u Dan Daniel.
ReplyDeleteIt is good as usual. But
let me ask u about the
roads under the cave.
Which monastries have such
kind of cave roads. and their
routes b/n other monasteries.
wow
ReplyDeleteዲ/ን እግዚአብሔር ይስጥልን።የሚቀጥለውንም ክፍል በጉጉት እንጠብቃሌን።
ReplyDeleteThank You Dn. Daniel Nice Travel
ReplyDelete"አሁን ተገዝቶ መግባት ቀረ እንጂ ዋሻ እንድርያስን፣ ዋሻ ተክለ ሃይማኖትንና ዜና ማርያምን የሚያገናኝ የዋሻ ውስጥ መንገድ አለ፡፡" Why forbidden? tell us more Dani "ልክ ይምርሃነ ክርስቶስንና... በኋላ ሰፊ ሜዳ መኖሩን ሜዳው እንዳለቀም መንገድ እንደሚገኝ ይገልጣሉ" Wow! Interesting
ReplyDeleteI think he was trying to say "tezegto" (closed) not "tegezito", so it is not forbidden but the passage is closed for some natural reason i guess.
Deleteተገዝቶ ማለት መገዘት-መከልከል ማለት ነው በቤተክርስትያን አባባል!
Deleteeziybehare yeslegn
ReplyDeleteዳኒ፡እኔ በጣም ነው ያስደሰትከኝ ከምገልጸው በላይ ነው ምሲጋናየ ።እግዚአብሔር በእድሜ በጤና ይጠብቅልኝ።
ReplyDeleteዳኒ የድንግል ልጅ አንተንና ማህበርህን ይባርክ: እኛንም የልባችንን መሻት ተመልክቶ ከስደት ንሮ አምልጠን በሙሉ ልብ ከሚፀለይበት አገራችን ኢትዩጵያ ተመልሰን ጌታ በፈቀደው በድህረ ገጽህ ያስተዋወከንን ገዳሞቸ ለመጎብኘትና በረከቱን ለመካፈል ያብቃን::ግሩም ነው:በርታልን::
ReplyDeleteThank you verry much for sharing, God bless you!
ReplyDeleteWow Dinke Dinke Dinke min yebalal.
ReplyDeleteEthiopia ye EGZIABHERE ye EKA GEMIJA Betum Chimir nate. There are lots of history and places which we don't but known by GOD. likeበጉራጌ ሀገረ ስብከት ቆጠር ገድራ በተሰኘ ስፍራ ጥንታዊ የዋሻ ቤተ መቅደስ እንደተገኘና የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን እንደተተከለ ሰማን፡፡
D. Daniel Egziabhere Yeselam Menged Yadrgilachu. Ageliglotihin Yebarkilih,DINGILE Timirachu.
Amen Memhr Daniel!!!! Thanks for sharing your eye witness!!!! ye samnt sew yibelen lantem melkam yebereket gubgnit yarglik!!!
ReplyDeleteYaredinho
Good post.keep it up.
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን
ReplyDeleteBlessings!!
ReplyDeleteHgerachin bale bezu tarik nate betely sel gedamate yemanawkachw bezu tarickoch bezihe amdelay bemaweki betam tedeschalehu KALE HIWET YASEMALEN!!
ReplyDeleteSELAMAWIT
"አሁን ተገዝቶ መግባት ቀረ እንጂ ዋሻ እንድርያስን፣ ዋሻ ተክለ ሃይማኖትንና ዜና ማርያምን የሚያገናኝ የዋሻ ውስጥ መንገድ አለ፡፡" Why forbidden? tell us more Dani "ልክ ይምርሃነ ክርስቶስንና... በኋላ ሰፊ ሜዳ መኖሩን ሜዳው እንዳለቀም መንገድ እንደሚገኝ ይገልጣሉ" Wow! Interesting
ReplyDeleteDn.Daniel,would you Please write about Abune Ewostatewos` monastry.also we need to see his picture.Thank you!
ReplyDeleteDANIEL when there are a lot of things to know about this kind of places,me and my Ethiopian brothers and sisters, we only know of a few 'Lalibela, Debre Damo, Tana Gedamat" and we cant even tell the story right, how it was made, who made it with of course Gods' help and then learn from it. The reason for this is many and everyone OF US could have reasons of our own and it could be right or wrong but my point is when a person like you goes after our great heritages of the church and Ethiopia at least we get the chance to know about them and who knows maybe, one day, we could all be concerned keep them safe and tell to those who haven't found out and create the excitement you are creating on us now. so God bless you DANIEL!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteእግዚኣብሔር የኣገልግሎት ዘመንህን ይባርክ ግሩም ድንቅ ጉብኝት
ReplyDeleteየሳምንት ሰው ይበለን
diakon dani egzabher yestlen belenal becose you always tastemrnalhe egzer tenawen edmewen yestelen amen will wateing you next week.
ReplyDeleteDn. Dani May God bless you with lots and lots of Success, Prosperity, Peace, Wisdom and more Aspiration and many years to bless us with such informative, entertaining and aspiring write ups. This is a lot for most people especially for those of us who do not have the chance to go and see currently due to many reasons (living abroad, economical constraint,lack of commitment, family and social burden, and many more reasons). I will be waiting the following part with patience and hope u will publish it soon! May God bless you and you family!
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን…
ReplyDelete"የአኩስም ሥልጣኔ ባለቤቶች የነበሩት የአገው ሕዝቦች በአካባቢው ከነበራቸው ቦታ አንጻር የዋሻ እንድርያስና የሥርዓተ ኦሪት ግንኙነት በሚገባ ቢጠና ለሃይማኖት ታሪካችን ተጨማሪ ፍንጭ የሚሰጠን ይመስለኛል፡፡ "
ReplyDeletegud bel gonder! demo bileh bileh axum ye-agew new bileh arefikew? ene emigermegn, ante erasih zerih mndin new:: hulu tsihufih sanebew kezer kotera gar yeteyayaze new:: yezer chigir endalebih giltse new:: eski nigerinina enirefew:: benegerachin lay axum neftegnoch yemit-telut ye tigre silitane enji yeagew aydelem:: arifeh tekemet::
እግዚኣብሔር ጉዞህን ይባርክልህ
ReplyDelete@ biruktawit. tarik alawkim bety yishalshal ahun tgre slenorebet slitanew yetigre meselesh? mejemeria erasish tarik mermiri kemawratish befit.
ReplyDeleteThank you Dani
ReplyDeleteThank you Dan
ReplyDeleteKale Hiwot Yasemalin,Rejim Edime Selam Ena Tena Yadililin!!!
ReplyDeleteKale Hiwot Yasemalen! Ebakachu yezer guday eyanesan bekenetu gize anatefa. Hulachenem eko bekirstos and honenal!
ReplyDeleteKale Hiwot Yasemalene. Thank you very Much.
ReplyDeleteketayu ጥር 10 wed gonder mehid selhone bezaw ya yengerken denk nger ayewalehung ... cheru medhani alem gozachn yakanalen
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል እግሬ ደርሶ ባላየውም አንድ ቀን
ReplyDeleteእግዚአብሄር ሲፈቅድ ሌላው ክርስቲያን እንዲያየው
እንደምታደርግ ተስፋ አደርጋለሁ እግዚአብሄር
ኢትዮጵያን ይባርካት ላንተም እድሜና ጤና ይስጥህ