Wednesday, December 12, 2012

ከጣራ እስከ ጉዛራ (ክፍል ሁለት)


 click here for pdf

ዋሻ ተክለ ሃይማኖት
ያለነው ደቡብ ጎንደር ጣራ ገዳም አካባቢ መሆኑን አስታውሰን እንጓዝ፡፡
ከዋሻ እንድያስ ወጣንና ወደ ግራ በኩል ታጥፈን መጓዝ ጀመርን፡፡ አሁንም እየተንደረደርን ነው ወደ ታች የምንወርደው፡፡ ግራና ቀኛችን በልምላሜ የታጠረ ነው፡፡ በአካባቢው ምንነቱን ለመለየት የሚያስቸግር በጎ መዓዛ ያውዳል፡፡ ወፎች ሲዘምሩ፣ ዛፎችም ሲያሸበሽቡ ለማየት የሚመኝ ሰው ካለ ወደ ዋሻ ተክለ ሃይማኖት መውረድ ነው፡፡ 
እነሆ ከፊት ለፊታችን በቀለም የተዋበ ዋሻ ገጭ አለ፡፡ ከፊት ለፊቱ አዲስ ግንብ ተሠርቶለታል፡፡ ከግንቡ በኋላ ደግሞ የቀድሞው የዋሻ ግድግዳ ይታያል፡፡ የዋሻ እንድርያስ ቅርስና ታሪክ በግራኝ ዘመን እንደጠፋ መነኮሳቱ ይናገራሉ፡፡ እንደ እኔ ግምት ግን ዋሻ ተክለ ሃይማኖት በ13ኛው መክዘ ከነበረው ‹‹የደብረ ሊባኖሳውያን› ስደት ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የፓሪሱ ዜና አጭሩ መዋዕል በዚህ ዘመን ‹የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት ከአንቆ እስከ ጋሼና ተሰደዱ› ይላል፡፡ ‹አንቆ› ወይም ‹አዕንቁ› ደቡብ ጎንደር ስማዳ ውስጥ የምትገኝ ስትሆን ‹ጋሼና› ደግሞ ከላሊበላ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በጎንደርና ወሎ መለያያ ላይ ትገኛለች፡፡


ጣራ ገዳም ኤዎስጣቴዎስ ከሩቁ ሲታይ
ከዋሻ ተክለ ሃይማኖት ወጥተን ወደ ጣራ ኤዎስጣቴዎስ ገዳም ነው የምንሄደው፡፡ አሁን ወደ ታች ሳይሆን ወደ ላይ ነው የምንወጣው፡፡ 83.5 ሄክታር በሆነ ደን የተሸፈነው ጣራ ገዳም ኤዎስጣቴዎስ ከአዲስ ዘመን ወደ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ምክንያት ከሁለት የተከፈለ ነው፡፡ አስጎብኛችን መንገዳችን በዝግታና በጸጥታ እንዲሆን መከሩን፡፡ ለምን? አልናቸው፡፡ ‹‹እዚህ ነብሮች አሉ፡፡ ወደ ገዳሙ ስትመጡ ሥርዓቱን ካልጠበቃችሁ አደጋ ያደርሳሉ›› አሉና ነገሩን፡፡
አሁን የምናደርገው ጥንቃቄ ነብሮቹም ከሚጠብቁብን በላይ ሳይሆን አልቀረም፡፡ ተራራ እንደሚወጣ ሰው ትንፋሻችን እንኳን ሲወጣ አይሰማም ነበር፡፡ ተራራውን ወጥተን በጫካዎቹ መካከል አልፈን የአቡነ ኤዎስጣቴዎስን ገዳም አገኘው፡፡
ታሪካችንን በሚገባ ስንመረምረው ከሆንነው በተቃራኒው ሆነን እንገኘዋለን፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ትውልዳቸው ሸዋ፣ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ትውልዳቸው ኤርትራ፤ ሁለቱም ግን ጎንደር ላይ በታላቅ ሁኔታ ይከበራሉ፡፡ ባይገር ማችሁ ደግሞ በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን ገዳሙን የመሠረቱት አቡነ ገላውዴዎስ ጎጃም ዲማ አካባቢ ‹ናጫ አቦ› ከተባለ ቦታ ነው የመጡት፡፡ እኛ እንዲህ ነን፡፡ እምነትና ምግባር እንጂ ዘር ቁብ የማይሰጠን ነበርን፡፡ ማን ሆነህ መጣህ? ምን ይዘህ መጣህ? እንጂ ከየት ዘር መጣህ? ጉዳያችን አልነበረም፡፡ ‹ለሰው ሀገሩ ምግባሩ› አይደል የሚባለው፡፡
በአካባቢው የሚገኙት አባቶች አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ሆኑ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በዘመናቸው ወደ ቦታው መጥተው እንደነበር ይተርካሉ፡፡


የጣራ ገዳም ኤዎስጣቴዎስ ቤተ ክርስቲያን
ከአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ቤተ ክርስቲያን ባሻገር ጥቅጥቅ ያለ ደን አለ፡፡ ከቤተ ክርስቲያኑ ይጀምርና በተራራው ላይ አልፎ የተራራው አናት ይደርሳል፡፡ የገዳሙ አበ ምኔት ‹‹እዚያ የተሠወሩ አባቶች ስላሉ ደኑን መንካት ክልክል ነው፡፡ የወደቀ ዛፍ ካላገኘን በቀር ከዛፉ ቅጠል አንቆርጥም፡፡ ይህንን ደን ሰው እንዳይመስላችሁ የሚጠብቀው፤ ነብር ነው›› አሉን፡፡
‹‹እንኳን ደኑን ነክተውት›› አሉን አበ ምኔቱ ‹‹ተቀያይሞና ተኳርፎ እዚህ ገዳም አንድ ቀን ማደር አይቻልም፡፡ አንድ ቀን ሁለት አባቶች በሥራ ምክንያት ተጋጩ፡፡ እነዚሁ አባቶችም አሉ›› አሉን በጣታቸው ወደ አባቶቹ እያመለከቱ፡፡ እነርሱም በአዎንታ ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡ ‹‹በትንሽ ነገር ተጋጭተው ሳይታረቁ አደሩ፡፡ በማግሥቱ አንደኛው አባት ሊያጥኑ ማልደው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ነብሩ በሩ ላይ ተኝቶ አላሳልፍ አላቸው፡፡ እርሳቸው በሌላኛው በር በኩል ሲሄዱ ይከተላቸዋል፡፡ ወደ በሩ ሲጠጉ ያጉረመርማል፡፡ ሲቸግራቸው ተመለሱና ከእኒያ አባት ጋር ታረቁ፡፡ ሲመለሱ በቤተ ክርስቲያኑ አካባቢ ነብሩ የለም፡፡ ድምፁን ግን በሩቁ አሰማቸው›› ብለው አስደመሙን፡፡
ከመካከላችን አንዳንዶቻችን ደንገጥ ደንገጥ ብለን ወዲህና ወዲያ ስንመለካከት አዩንና ‹‹እናንተ ለሰማችሁት ትፈራላችሁ፤ ትንሽ ብታመሹኮ ውኃ ለመጠጣት እዚሁ ሲመጣ ታገኙታላችሁ፡፡ እዚያ ግብር ቤቱ ጋ ውኃ ሊጠጣ ይመጣል፡፡ እኛ ዘንድ ውኃም ምግብም ክፍት ነው፡፡ የተራበ መብላት የተጠማ መጠጣት አለበት፡፡ እርሱም ሊጠጣ ይመጣል፡፡ ታድያ ጠጥቶ ማንንም ሳይተናኮል ይሄዳል፡፡ እኛኮ ከብቶቻችን ገደል እንዳይገቡ ነው እንጂ አውሬ እንዳይበላቸው አናስብም፡፡ እዚህ ቦታ ዝንጀሮና ጅብ አይገባም፡፡ ግዝት ነው፡፡ ሌባም ቢመጣ ያው ጠባቂው (ነብሩን ማለታቸው ነው) አለ፡፡›› አሉን፡፡
በገዳሙ ውስጥ እስከ ኮሌጅ ትምህርት ደርሰው በኋላ ግን የመነኑ አባቶችን ማየት የተለመደ ነው፡፡ ተራ ልብስ ለብሰው እንጨት ሲያጓጉዙ የምታገኟቸው አባቶች ያ እንጨት ከምን ከምን እንደተሠራ በታትነው የተማሩ የባዮሎጂ ምሩቅ ሊሆኑ እንደሚችሉ መጠርጠር አለባችሁ፡፡
ከአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ቤተ ክርስቲያን ወደ እመቤታችን ቤተ ክርስቲያን እንድንሄድ አስጎብኛችን መሩን፡፡ እኛም ተከተልን፡፡ ለዚህ ገዳም ታላቁን ውለታ ከዋሉት ሰዎች መካከል እቴጌ ምንትዋብ አንዷ ናት፡፡ እቴጌ ምንትዋብ የጎንደር ዘመን ካፈራቸው ኃያላንና ጠቢባን ሴቶች መካከል አንዷ ናት፡፡ በጎንደር አካባቢና በጣና ገዳማት የሚገኙትንና እስከ ዛሬም ብርታቷንና ጽናቷን የሚመሰክሩላትን አያሌ አብያተ ክርስቲያናት ሠርታለች፡፡ 

እቴጌ ምንትዋብ ያሠራችው ቤተ ክርስቲያን
የጣራ ገዳም አካባቢ ታሪክ እንደሚነግረን ከሆነ ደግሞ ትውልዷ እዚህ ነው፡፡ እናቷ እንኮየ ትባላለች፡፡ ከቋራ ዘመን አልፎባት የተሰደደች እናት ነበረች፡፡ ትኖር የነበረበትን ቦታ አሁን ‹ወይዘሮ መሬት› እየተባለ ይጠራል፡፡ ‹ወይዘሮ› በድሮ ዘመን ከነገሥታትና መኳንንት ለሚወለዱ ሴቶች ብቻ ይሰጥ የነበረ መዓርግ ነው፡፡ እንኮየ ምንትዋብን ወልዳ ለዐቅመ ሔዋን እንዳደረሰች በወቅቱ የገዳሙ አበ ምኔት የነበሩት ዓይነ ሥውሩ አባት አቡነ ኤርምያስ ‹‹እርሷ ትልቅ ዕድል አላትና ይዘሻት ጎንደር ሂጂ›› አሏት፡፡ እርሷም ሄደች፡፡ የቤተ መንግሥት ሰዎች አላስገባ ብለዋት ብዙ ጊዜ በደጅ ጥናት ቆየች፡፡ በኋላ ግን በአንዳንድ ሰዎች አማካኝነት ትገባለች፡፡ የደረሰባትንም ችግር ታመለክታለች፡፡ ንጉሡም ችግሯን አዩላት፡፡ አብራ የወሰደቻትን ምንትዋብንም ወደዷትና አገቧት፡፡ ምንትዋብም የዐፄ በካፋ ባለቤት ሆና ቤተ መንግሥት ገባች፡፡
ጎንደር ‹እንኮየ በር› እና ‹እንኮየ መስክ› የሚባል ቦታ አለ፡፡ ምናልባት ከምንትዋብ እናት ከእንኮየ ጋር ይገናኝ ይሆን? ጥናት ይፈልጋል፡፡
እቴጌ ምንትዋብ በቤተ መንግሥት ከተደላደለች በኋላ ይህችን ክርስትና የተነሣችባትን ቤተ ክርስቲያን በጎንደር የግንባታ ጥበብ መሠረት አስጊጣ አሠራቻት፡፡ ለመነኮሳቱ ምስጋና ይግባቸውና ‹‹አፍርሰን እንሥራ›› የሚለውን የብዙዎች ውትወታ ተቋቁመው እስከ ዛሬ ጠብቀው ይዘዋታል፡፡ የኖራ ግንቡ፣ መስኮቶቹና በሮቹ፤ በእንጨት ሥራው ላይ የሚታየው ጥበብና የጣራው አሠራር የዚያን ዘመን ሥራ እየመሰከሩ አሉ፡፡
የገዳሙ መነኮሳት ‹ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እዚህ አስተምረዋል› ብለውኛል፡፡ እንደ እኔ ግምት ግን እዚህ እንፍራንዝ አካባቢ መጥቶ ያስተማረው ፈላስፋው ዘርዐ ያዕቆብ ነውና በስመ መኩሼ ታሪኩ ወደ ንጉሡ የሄደ ይመስለኛል፡፡ ፈላስፋው ዘርዐ ያዕቆብ በስደት ወደዚህ አካባቢ መጥቶ እንደነበር ይገልጣል፡፡ ደቀ መዝሙሩ ወልደ ሕይወትም የእንፍራንዝ ሰው ነውና ‹‹ወወልደ ሕይወት እንፍራንዛዊ›› ይላል በመጽሐፉ፡፡ 


እቴጌ ምንትዋብ ያሠራችው ቤተ ክርስቲያን ጣራ
በንብ ርባታ፣ በእርሻና በከብት ርባታ ራሳቸውን ችለው ገዳማዊ ሕይወታቸውን መቀጠል የሚፈልጉት ገዳማውያኑ ዋናው ችግራቸው ውኃ ነው፡፡ ‹‹ውኃ ብናገኝ ከራሳችን አልፈን ለሌሎች በተረፍን ነበር፡፡ እኛ የዕለት ርዳታ አንፈልግም፡፡ እጅ እግር አለን፡፡ ዕውቀቱም አለን፡፡ ያጣነው ውኃ ነው፡፡ ውኃ ካገኘን ይህንን መሬት እናስገብረዋለን፡፡›› ብለውኛል አበ ምኔቱ፡፡ በአካባቢው ውኃ የሚገኘው ከተራራው ሥር ተቆፍሮ ነው፡፡ ከዚያም በሞተር ኃይል ወደ ላይ መሄድ አለበት፡፡ ለዚያ ግን ዐቅም የላቸውም፡፡ በዐቅማቸው በሰው ጉልበት ሁለት ሦስት ጉድጓድ ቆፍረው ውኃ ለማውጣት ሞክረዋል፡፡ ግን አልሆነም፡፡ 


የመነኮሳቱ የንብ ርባታ
ስንለያቸው ‹‹እዚህ ገብቶ ሳይቀምሱ መውጣትማ ነውር ነው›› ብለው አንዱ ስለ ዐሥር እንጀራ የሚቆጠር ዳቤ እጅ በሚያስቆረጥም ወጥ አቀረቡልን፡፡ ይህንን ስጽፍ እንኳን ጣዕሙ ይመጣብኛል፡፡ ‹‹ግን ይሄ ለእንግዳ ነው የሚቀርበው፡፡ የኛን ብንሰጣችሁ አትችሉትም›› አሉን አበ ምኔቱ፡፡ በነብር የሚጠበቀውን የጸጥታ ገዳም ትተን ወደ ታች ወረድን፡፡ አሁን ቀጥለን የምንጓዘው ወደ ታሪካዊቷ የኢፋግ ከተማ ነው፡፡ የባርያ ንግድ ዋና ገበያ ወደ ነበረችው ኢፋግ፡፡
ቸር ያሰንብተን፡፡

46 comments:

 1. ማን ያውቃል እግዚአብሔር ከዚህ ከአንተ ጽሁፍ እያነበብኩ ለማየት የቀናሁባቸውን ቦታዎች ሀገር ውስጥ ያሉትን እንኳን እንዳይ ያሳካልኝ ይሆናል ከዛም ይህችን የምኞቴን መግለጫ የፃፍባትን ማስታወሻ እንደታክ መልሼ አነባት ይሆናል የተቀደሱን ቦታ ለማየት ተመኘው እግዚአብሔርም ፈቀደልኝ ብዬ እፅፍባት ይሆናል ለአንተም በአይነ ህሌናችን እንድናየ ስላስነበብከን እግዚአብሔር ይስጥልን አሜን

  ReplyDelete
 2. t'amer new! Twahedo ytadlech haimanot...Ethiopia ytbarkch hager.

  ReplyDelete
 3. << እኛ እንዲህ ነን፡፡ እምነትና ምግባር እንጂ ዘር ቁብ የማይሰጠን ነበርን፡፡ ማን ሆነህ መጣህ? ምን ይዘህ መጣህ? እንጂ ከየት ዘር መጣህ? ጉዳያችን አልነበረም፡፡ >>

  ቅቅቅቅቅ... ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ይሉ ነበር እሜቴ ድም ይበሉ። ዳኒ፣ ከምትጽፋቸው ጥውፎች 80 በመቶው ስለዘር እንደሆነ ታውቃለህ? ነው በደመነፍስ ነው ምትጥፈው? ቅቅቅቅቅ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰነፍ ምንም ሳይሰራ የተሰራውን ለመተቸት ይቀነዋል።

   Delete
  2. @chocho zer wedaju
   yedanin tshufoch bedemenefs yemtanebachew yimeslegnal.woym degmo ante 'zer' yalkew melkam fre yemiaferawn 'zer' kehone yikrta ,ersum bihon bdemenefs ayzeram ,tasbobet ,tewetto tewerdo new.....
   =degmos 80 bemeto yedanin tshufoch kanebebk endih yemitle aymeslegnm,....ere ahun "yanebebkew" enqua bizu endtasb ,endtastewl badergeh neber,anebenebh enji alanebebkhma.

   Delete
  3. what the hell is wrong with you? what this guy did wrong? he is doing his best to teach people like you. please try to think positive.shame on you.

   Delete
  4. chocho betam tasazinaleh ahun be ante bet beka danin astekureh motehal but from ur comment i knew one thing that there is some people don't understand what they read what they heard even what they talk exactly like u,if u think u r a great cos u say something wrong abt him u r totally wrong so after this time before u post u should read it 10 times pls and then ask some ppl around u to post it sure they gonna tell u no

   Delete
  5. you stupid and shallow minded

   Delete
 4. Egzere yisteh, and ken egnam megobeget bicha sayhon siga wodemu enkebelbet yihonal. egzire hulachinnm yitebeq!

  ReplyDelete
 5. tarikachenena emnetachen yakoralllllllllll

  ReplyDelete
 6. Dn Daniel Agelglotk yibarek.e/r kante ga yihun!Tara gedame lemin endetebale bitgeltsln melkam new wondmachin!

  ReplyDelete
 7. ይስጥህ
  በአንድ ወቅት ታላቁ ደራሲ ማሞ ውድነህ እንዴት ወደ ድርሰት ሥራ እንደመጡ ሲናገሩ ፥ጋዜጣ እያነበብቡ የሚመረቁ ሰዎችን አይቼ በቤተሰቦቼ ጀመርኩት:: ወላጆቼ ይመርቁኝ ስለነበር ደስ እያለኝ ቀጠልኩበት የበለጠ ለመመረቅ ያደረግሁት ጥረት ለዚህ ክብር አበቃኝ በማለት ተናግረው ነበር:: ዳኒ ለምን ትሠራለህ ብንልህ መቼም አንደኛ ምክንያትህ እንደሚሆን አልጠራጠርም::የሚገርመው የዚህን ሁሉ ሕዝብ ወጪ ችለህ መጓዝህ ነው:: በተለይ እንደነዚህ መሰል ሥራዎችህን ስመለከት አፍራለሁ:: የኔ አስተዋጽኦ ምን ጋር እንዳለ አላውቅም:: ለማንበብ ግን አልሸማቀቅም የምር ስመርቅህ ግን ከልቤ ነው:: ሆድ ይመርቅ ይላል ደሀ አብልቶ ያጠገበውን ባለጠጋ:: የሚከፍለው የለውማ:: ለነፍስ ያደረ ባለጠጋም ብድራቱን ከሰማይ እየጠበቀ የቸርነቱን ያደርጋል:: ዳኒ ምን ይመርቅ ልበልህ? ይስጥህ:: ባጎደልኩ ሥላሴ ይሙሉበት ይላል ጉራጌ ሲመርቅ ፥ካህናቱ በአፈ መላእክት ይቀበልልን የሚሉት ዓይነት:: ይስጥህ ጨምሮ ጨምሮ! የዚህን ሳምንት ሂሳብ ዘግቻለሁ::

  ReplyDelete
 8. ማን ያውቃል እግዚአብሔር ከዚህ ከአንተ ጽሁፍ እያነበብኩ ለማየት የቀናሁባቸውን ቦታዎች ሀገር ውስጥ ያሉትን እንኳን እንዳይ ያሳካልኝ ይሆናል ከዛም ይህችን የምኞቴን መግለጫ የፃፍባትን ማስታወሻ እንደታክ መልሼ አነባት ይሆናል የተቀደሱን ቦታ ለማየት ተመኘው እግዚአብሔርም ፈቀደልኝ ብዬ እፅፍባት ይሆናል ለአንተም በአይነ ህሌናችን እንድናየ ስላስነበብከን እግዚአብሔር ይስጥልን አሜን

  ReplyDelete
 9. እግዚአብሔር ጥበቡን ያብዛልህ።

  ReplyDelete
 10. ‹እንኳን ደኑን ነክተውት›› አሉን አበ ምኔቱ ‹‹ተቀያይሞና ተኳርፎ እዚህ ገዳም አንድ ቀን ማደር አይቻልም፡፡

  ReplyDelete
 11. ዳኒ ፅሁፉ በጣም የሚመስጥ ነው ልብን የሚያሸፍት ነው፡፡ ማን ያውቃል በዚህ ፅሁፍ የተጠሩ ይኖራሉ፡፡ ፀጋ ይበዛልህ ድንግል ትጠብቅህ፡፡

  ReplyDelete
 12. Amen kala hywit yasmalen!grum nwe

  ReplyDelete
 13. Dn. Daniel Egzihaber ken betsebeh yetebkeh!

  ReplyDelete
 14. «...እኛ እንዲህ ነን፡፡ እምነትና ምግባር እንጂ ዘር ቁብ የማይሰጠን ነበርን..» ድንቅ ኣባባል.. መንፈሳዊነት የዘርና የቋንቋ ልዩነት ኣይገድበውም ብፍቅር ሁሉን ያሸንፋልና። ቀጥልበት እግዚኣብሔር ያግዝህ

  ReplyDelete
 15. chocho zer wedaju
  ebkowt tiru tiru neger yesbu Egzihberen yefiru!

  ReplyDelete
 16. chocho zer wedaju
  ebkowt tiru tiru neger yesbu Egzihberen yefiru!

  ReplyDelete
 17. MEMEHRACHN ...KALEHIWET YASEMALEN.... BE EWNET LECHGRACHEW MEFTHI MESTET ALEBEN ... LEZIHM ADERA ELHALEHUNG

  ReplyDelete
 18. Dn. Daniel Kale hiwot yasemalin Egizabhare rageme edemana tena yestilne ba ewenate yemanawekawne tarke nawu yasawakane.
  Egizabhare yagalegelote zamanhene yebarekelhe.
  Thank you very much.

  ReplyDelete
 19. wondime daniel e/r talak yadirigih! lehagerih gena talak siran tiseraleh!!!

  ReplyDelete
 20. ዳንኤል በጣም ነው የማመስግንህ ብዙ ሄጄ ማየት ያልቻልኩት ገዳማት በዓይነ ህሊና እንዳይ አድርገህኛል ደሞም ለማየት እንድመኝ ተመኝቼም አንድ ቀን አየዎለሁና ተስፋ አለኝሰለዚህ አንተም እንድትፅፍ እኛም እነድናነብ እድሜና ጤና ይሰጠን አንድ ነገር ግን የከነክነኝ ነበር አሁን ግን በዚህ ጽሑፍህ ነካ አድርገህው ሰላገኘሁት ልጠይቅ ፈልጌ ነው ስለ ፈላሰፋው ዘርዐ ያዕቆብ ትንሽ ብታሰነብበን ለማለት ፈልጌ ነው ምክንያቱም በአንድ ወቅት ታሪኩ ከአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተቀላቅሎ ግር ሰላለኝ ነው ለሁሉም ወላዲት አምላክ ከነልÍ አትለይህ

  ReplyDelete
 21. ዳንኤል በጣም ነው የማመስግንህ ብዙ ሄጄ ማየት ያልቻልኩት ገዳማት በዓይነ ህሊና እንዳይ አድርገህኛል ደሞም ለማየት እንድመኝ ተመኝቼም አንድ ቀን አየዎለሁና ተስፋ አለኝሰለዚህ አንተም እንድትፅፍ እኛም እነድናነብ እድሜና ጤና ይሰጠን አንድ ነገር ግን የከነክነኝ ነበር አሁን ግን በዚህ ጽሑፍህ ነካ አድርገህው ሰላገኘሁት ልጠይቅ ፈልጌ ነው ስለ ፈላሰፋው ዘርዐ ያዕቆብ ትንሽ ብታሰነብበን ለማለት ፈልጌ ነው ምክንያቱም በአንድ ወቅት ታሪኩ ከአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተቀላቅሎ ግር ሰላለኝ ነው ለሁሉም ወላዲት አምላክ ከነልÍ አትለይህ

  ReplyDelete
 22. ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 23. Dn dani it very interesting. Some of the literature is similar with "Dertogada", "Ramatohara" and "Zhantozhara" of Yismaek Worku Fictions. From this we can conclude that there is underground way between the monasteries of Tana and its surrounding. Any way thanks.

  ReplyDelete
 24. Kale hiywot Yasemalin Daniel

  ይስጥህ
  በአንድ ወቅት ታላቁ ደራሲ ማሞ ውድነህ እንዴት ወደ ድርሰት ሥራ እንደመጡ ሲናገሩ ፥ጋዜጣ እያነበብቡ የሚመረቁ ሰዎችን አይቼ በቤተሰቦቼ ጀመርኩት:: ወላጆቼ ይመርቁኝ ስለነበር ደስ እያለኝ ቀጠልኩበት የበለጠ ለመመረቅ ያደረግሁት ጥረት ለዚህ ክብር አበቃኝ በማለት ተናግረው ነበር:: ዳኒ ለምን ትሠራለህ ብንልህ መቼም አንደኛ ምክንያትህ እንደሚሆን አልጠራጠርም::የሚገርመው የዚህን ሁሉ ሕዝብ ወጪ ችለህ መጓዝህ ነው:: በተለይ እንደነዚህ መሰል ሥራዎችህን ስመለከት አፍራለሁ:: የኔ አስተዋጽኦ ምን ጋር እንዳለ አላውቅም:: ለማንበብ ግን አልሸማቀቅም የምር ስመርቅህ ግን ከልቤ ነው:: ሆድ ይመርቅ ይላል ደሀ አብልቶ ያጠገበውን ባለጠጋ:: የሚከፍለው የለውማ:: ለነፍስ ያደረ ባለጠጋም ብድራቱን ከሰማይ እየጠበቀ የቸርነቱን ያደርጋል:: ዳኒ ምን ይመርቅ ልበልህ? ይስጥህ:: ባጎደልኩ ሥላሴ ይሙሉበት ይላል ጉራጌ ሲመርቅ ፥ካህናቱ በአፈ መላእክት ይቀበልልን የሚሉት ዓይነት:: ይስጥህ ጨምሮ ጨምሮ! የዚህን ሳምንት ሂሳብ ዘግቻለሁ::

  @chocho zer wedaju
  yedanin tshufoch bedemenefs yemtanebachew yimeslegnal.woym degmo ante 'zer' yalkew melkam fre yemiaferawn 'zer' kehone yikrta ,ersum bihon bdemenefs ayzeram ,tasbobet ,tewetto tewerdo new.....
  =degmos 80 bemeto yedanin tshufoch kanebebk endih yemitle aymeslegnm,....ere ahun "yanebebkew" enqua bizu endtasb ,endtastewl badergeh neber,anebenebh enji alanebebkhma.

  ReplyDelete
 25. Let me tell you about my father, I love him so much and I have learned many things from him. He went through many things to put me where I am today, every single day he thought and cared about me and our family and made many sacrifices, his deeds, everything he has done, his great efforts comes to my mind…… words can’t express how much he have worked for the well being of our family and words can’t also express how much we love him.
  Like I am doing right now, I proudly tell his greatness to all my friends and to any one I meet believing that there is so much to learn from him. I watch over him and make sure he is doing great or well.
  Imagine after everything he has done, after all the sacrifices he made, after all the ups and downs, imagine if I completely forget him, never think of his deeds when they have showed me how to live doing the right thing, which road (FNOT) I should take, how I could help myself and many others, imagine if I turn my back on him for whatever reason . . . what would that make me???
  My father only worked for me or our family but our fathers worked for all the peoples, for all of us and did so many great things for the life we have today, went up and down and left us so many treasures, heritages, some died in doing that, some bleed, some were cruelly tortured and some had no life of their own, they all lived it for us and us only, like our lord Jesus Christ didn’t live for himself.
  Imagine if we turn our back on them and forget everything they have done for us,. . . . What would that make us???
  I don’t know many of the places and great stories our fathers have left us and I never searched for them and find them and helped keep them safe with my Ethiopian brothers and sisters, when I know they have done so much!!!! There are many of us out there!!!
  Dani thank you for keeping our heritages and stories only a blog away until one day we go there to visit them!!!!!!!!!!!!!!!! EMEBRHAN KANTE GAR ENA KEHULACHIN GAR TIHUN!!!

  ReplyDelete
 26. Dn. Daniel it is an interesting article and history! may GOD bless you.

  ReplyDelete
 27. Realy nice Memhr Daniel, Dani sle gedamochu stnegren gedamu ena kdusanu ke Egziabher yetegebalachewn kalkidan ena gedlm be achirum bihon btgeltsiln tru neber!! wedefit etebkalehu.
  Kale hiwot yasemah!!!

  ReplyDelete
 28. እግዚአብሄር እድሜና ጤና ይስጥልን

  ReplyDelete
 29. Astounding. "እኛ እንዲህ ነን፡፡ እምነትና ምግባር እንጂ ዘር ቁብ የማይሰጠን ነበርን፡፡ ማን ሆነህ መጣህ? ምን ይዘህ መጣህ? እንጂ ከየት ዘር መጣህ? ጉዳያችን አልነበረም፡፡ ‹ለሰው ሀገሩ ምግባሩ› አይደል የሚባለው፡፡"
  That was what were and what we should continue to be. Ethnic division is an anomaly the engulfed us recently.

  God bless you.

  ReplyDelete
 30. DARIOS from Dessie

  @cho cho's Comment

  I think you are a beginner reader of this page. Even beginner no one understand like you. Your idea is coming from the brain that engaged by " ZEREGNINET" please avoid such criticism... all your friends those engaged by the same idia of you never understand Daniel's view as you think. Why not you updated your self those people were thinking about "ZEREGNNET" now turn back to UNITY

  ReplyDelete
 31. ውኃ ካገኘን ይህንን መሬት
  እናስገብረዋለን፡፡ እኛ እንዲህ ነን፡፡ እምነትና ምግባር እንጂ ዘር ቁብ የማይሰጠን ነበርን፡፡
  thank you dani

  ReplyDelete
 32. አይ ዳንኤል በአሁኑ ሰዓት ስለጣራ የሚወራበት ሰዓት ነው? ወይስ የአሁኑ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የማይመለከትህ ስለሆነ

  ReplyDelete
 33. ዲን. ዳንኤል ክብረት እግዝያብሄር ያገልግሎት ዘመንህን ያብዛልን;ወንድማችን ገንዘብ ሊገዛዉ የማይችል አገልግሎት! በኢትዮጵያዉያን ላይ የወረደዉን የዘር ወረርሽኝ አባዜ ለመቀየር የምታደርገዉ አስተፅ“ ቀላል አይደለም በርታ ፡፡ስለዚህ ፅሁፍህ ምን እንደምል አላቅም ግን የእግዝያብሔር ፈቃዱ ሆኖ እኔም እንደማየዉ ተስፋ አለኝ፡፡ሁሌም አከብርሃለዉ ኢትዮጵያዊዉ ወንድሜ፡፡

  ReplyDelete
 34. ዲ\ን ዳንኤል ስለሁሉም አገልግሎት መጨረሻህን አሳምሮ እ\ር ዋጋህን ይክፈልህ።አንባቢያን ሁላችን በጎ ያልሆነ አስተያየት ለሚሰጡ ወንድሞች እ\ር በጎ አእምሮ እንዲሰጣቸዉ መጸለይ እንጂ አንራገም። ከተራገምን\ከተሳደብንማ ምኑን ተሻልን።የሰይጣንስ ዓላማ ይህ አይደለምን፤የሁላችንንም መጨረሻ ያሳምርልን።አሜን።

  ReplyDelete
 35. ዳኒ እግዚአብሄር ይባርክህ!

  ReplyDelete
 36. ብዙ ድብልቅልቆችን ሰምተንና አይተን እግዚአብሔር ቤተክርሰቲያንን ረሳት እንደ ለምንል እዉነተኞቹ አባቶች ባሉበት እንዳለ የሚያሳይ ፅሁፍም ነዉና ባለተስፋነታችንን በማረጋገጥ የበለጠ እንድንጠነክር ያደርገናልና እግዚአብሔር ጥበብን ያብዛልህ !ብዙ ድብልቅልቆችን ሰምተንና አይተን እግዚአብሔር ቤተክርሰቲያንን ረሳት እንደ ለምንል እዉነተኞቹ አባቶች ባሉበት እንዳለ የሚያሳይ ፅሁፍም ነዉና ባለተስፋነታችንን በማረጋገጥ የበለጠ እንድንጠነክር ያደርገናልና እግዚአብሔር ጥበብን ያብዛልህ !

  ReplyDelete
 37. I apreshet u r effort!

  ReplyDelete
 38. betam des yemil yebereket bota new.
  Egiziabher fekido aychew neber .betam yemiyasdest yebereket bota new.sile washa T/haymanot tsebel tikit bitlen des yelegnal.talak mihret yemiset new yalebet botam gerami new.

  ReplyDelete
 39. Egiziabhek kenanta gar yuhn

  ReplyDelete
 40. ዲያቆን ዳንኤል እግሬ ደርሶ ባላየውም አንድ ቀን
  እግዚአብሄር ሲፈቅድ ሌላው ክርስቲያን እንዲያየው
  እንደምታደርግ ተስፋ አደርጋለሁ እግዚአብሄር
  ኢትዮጵያን ይባርካት ላንተም እድሜና ጤና ይስጥህ

  ReplyDelete
 41. God bless you. I wish to see this place.

  ReplyDelete