Monday, December 3, 2012

ወርቅ እንዲህ ሲገዛባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወደ ጆሃንስበርግ በሚሄደው ኢትዮጵያ አየር መንገድ የደረሰብኝን መጉላላት ዘርዝሬ በዚህ ጦማር ላይ ጽፌ ነበር፡፡ ያንን ሳደርግ ዋናው ዓላማዬ የኢትዮጵያ አንዱ መለያ የሆነው አየር  መንገዳችን እንዲሻሻል በማሰብ ነው፡፡ ‹ጠላት ያማል ወዳጅ ይወቅሳል› እንዲሉ፡፡ ታላቁን መርከብ የአንዲት ብሎን መውለቅ ለአደጋ እንደሚ ዳርገው ሁሉ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ታላላቅ ተቋማትንም በየአካባቢው የሚፈጠሩ ትናንሽ የሚመስሉ ስሕተቶች ዋጋ ያስከፍሏቸዋል፡፡   
ዛሬ ከጆሃንስበርግ ወደ አዲስ አበባ ስመለስ በደቡብ አፍሪካ የኢትጵያ አየር መንገድ የአካባቢ ሥራ አስኪያጅ በተፈጠረው ጉዳይ ላይ አነጋግረውን ነበር፡፡ ባለፈው ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቀው፣ በቀጣይ ተመሳሳይ ስሕተቶች እንዳይፈጠሩ አሠራራቸውን ማረማቸውን ገልጠውልናል፡፡ ያለፈውንምንም ለመካስ በቢዝነስ ክላስ ወደ አዲስ አበባ እንድንመለስ አድርገዋል፡፡
በመጀመርያ ቅሬታችንን በመስማታቸው፤ ቆይቶም ቢሆን ይቅርታ በመጠየቃቸውና ስሕተቱን ለማረም አሠራር መዘርጋታቸው ያስመሰግናቸዋል፡፡ ችግሮች መቼምና የትም ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ ሁለት ነገሮችን ግን ይፈልጋሉ፡፤ አንድ ሲፈጠሩ በቅርብ ተገኝቶ ሳይብሱ የሚፈታ አመራርና፣ ችግሮቹ ዘላቂ ሆነው እንዳይቀጥሉ የሚያደርግ አሠራር ናቸው፡፡ ያኔ ያጣነው ይሄንን ነበር፡፡
ደንበኞች ቅሬታቸውን የሚሰማና የሚፈታ ካገኙ ከአየር መንገዱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይቀጥላሉ፡፡ ቅሬታቸውን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ከተደረገ ግን በዚህ የውድድር ዘመን ፊታቸውን ወደ ሌሎች ያዞራሉ፡፡
በመሆኑም አየር መንገዳችን ቅሬታውን ተቀብሎ ለማረምና ይቅርታ ለመጠየቅ ያደረገው አሠራር አስደስቶኛል፡፡ ወርቅ እንዲህ ሲገዛ ያምርበታል፡፡ ነገም እንዲሁ እየተሰማማን እንደምንቀጥልም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጥበቡን በልቡናችሁ፣ መልካሙን መስተንግዶ በአውሮፕላናችን ላይ ያሳድርብን፡፡ አሜን፡፡
ከጆሃንስበርግ ወደ አዲስ አበባ በረራ ላይ

32 comments:

 1. በአንተ በጣም ኮራሁ ዲያቆን ዳንኤል,, የቱን ያክል ያንተን ብሎግ በፍርሃት እንደሚከታተሉ ተረዳሁ። በአንዲት ጽሑፍ ይህን ያክል ካስበረገግካቸው፣ በሌላማ ምን ሊሆኑ ነበር... በጣም ደስ ይላል። አየህ ዳንኤል፣ ለሳምሶን ጸጉሩ ሃይል እንደሆነው ሁሉ ላንተም ይቺ ብሎግህ ከባድ ሃይል ሆናሃለች። እግዚአብሔር ይባርክልህ። እነሱንም ልብ ይስጣቸው።

  ፊፊ

  ReplyDelete
  Replies
  1. I don't agree Fifi. u have to thank them. what if,if they don't give any response like any other questions of people ?

   Delete
 2. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞቹን ለማስደሰት የሚያደርገው ጥረት በጣም ያስመሰግናል፡፡ የኛ ባይሆን ይቆጨን ነበር፡፡

  ReplyDelete
 3. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞቹን ለማስደሰት የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግን ነው፡፡ የኛ ባይሆን ይቆጨን ነበር፡፡ "ጥበቡን በልቡናችሁ፣ መልካሙን መስተንግዶ በአውሮፕላናችን ላይ ያሳድርብን፡፡ አሜን፡፡"

  ReplyDelete
 4. Deacon Daniel! A "watch dog" of his people,a well articulated and proud Ethiopian.Really "eagle eyed" indeed that locates where some crucial and peculiar necessity for Ethiopians has slipped off the right track. A devoted advocate of his fellow country people.Keep on weeding out the diabolic acts of bottle neck bureaucracies to the root.

  Wow! that's really amazing. I cannot believe it such a down to earth response after admitting an error from an Ethiopian company.The label "world class company" deserves them perfectly.The saying,"To err is human to forgive divine" completely fits here.This company is special and I'm really proud of it.

  Most Ethiopian companies don't have such an attitude.If anyone ever tries to point out where they made an error whether by accident like that of Ethiopian Airlines case, or out of negligence they just overreact. They blame you and label you as a cause for their folly.What can you do when a bolt rigidity strikes you unexpectedly? Nothing. You just feel sorry for their immaturity and leave them to play with their baby things.

  Thank you Deacon Daniel.

  ReplyDelete
 5. አየር መንገዳችን ቅሬታውን ተቀብሎ ለማረምና ይቅርታ ለመጠየቅ ያደረገው አሠራር አስደስቶኛል፡፡ ወርቅ እንዲህ ሲገዛ ያምርበታል፡፡ ነገም እንዲሁ እየተሰማማን እንደምንቀጥልም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጥበቡን በልቡናችሁ፣ መልካሙን መስተንግዶ በአውሮፕላናችን ላይ ያሳድርብን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 6. ዳንኤል የአንተን ቅራኔ፤ በጽሑፍህም ምክንያት ይሁን ወይም ሕሊናቸው ቀስቅሷቸው ይቅርታ መጠየቃቸው ያስመሰግናቸዋል።የሚቀጥለውን ብሶታቸውን 15 November 2012 ላቀረቡት አቶ Joe Crane (USA)እንደዚሁ ይቅርታ አቅርበው ይሆን? "At one time, I was a gold member with Ethiopian Air and left due to the poor plane quality, treatment of business class customers and staff. This was more before their Star Alliance designation and new fleet. Unfortunately, it does not seem much has changed. On the 6 hour flight from Johannesburg to Addis, the business class seats barely recline, meal service takes most of the flight and there is no personal entertainment system which is standard on most economy flights let alone business. Lounge in Addis which should be their flagship is still overcrowded with slow internet and no priority boarding for business passengers. On the plane from Addis to Nairobi, my original seat was taken when I boarded. I asked the flight attendant and simply redirected me to another seat even though I was originally seated next to my wife. Very little room for overhead luggage so the stewardess said she would take care of it. I asked her not to put my bags in the back and she agreed. I look behind and she is already halfway down the plane. I hope the Star Alliance designation will eventually force a higher standard. Until then, Ethiopian remains a carrier of last resort."

  ReplyDelete
 7. በመጀመርያ ቅሬታችንን በመስማታቸው፤ ቆይቶም ቢሆን ይቅርታ በመጠየቃቸውና ስሕተቱን ለማረም አሠራር መዘርጋታቸው ያስመሰግናቸዋል፡፡ ችግሮች መቼምና የትም ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ ሁለት ነገሮችን ግን ይፈልጋሉ፡፤ አንድ ሲፈጠሩ በቅርብ ተገኝቶ ሳይብሱ የሚፈታ አመራርና፣ ችግሮቹ ዘላቂ ሆነው እንዳይቀጥሉ የሚያደርግ አሠራር ናቸው፡፡ ያኔ ያጣነው ይሄንን ነበር፡፡

  ReplyDelete
 8. ዲያቆን ዳንኤል
  ከሀገር ስትወጣ ትሳደባለህ፤ ወደሀገር ቤት ስትመለስ ታመሰግናለህ፡፡ ይህችን ማረሚያ ባትጽፍ ኖሮ ይኼኔ ቃሊት ወርደህ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 9. በዘመነ ደርግ አቶ ቆምጨ አምባው ስለ አብዮቱ ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ወደ ገጠር ከበላይ አካል ታዝዘው ይሄዳሉ ። ከዚያም ባላገሩን ሰብስበው " የቻይና? አብዮተኞች ለአብዮታቸው ሲሉ ጫማቸውን እስከመብላት ድረስ መስዋእትነት ከፍለዋል" እያሉ ሲሰብኩ አንድ ባላገር ተንስቶ "ጓድ ቆምጨ እነሱ/ቻይናዎች?/ጫማ ስላላቸው ጫማቸውን በሉ እኛ ጫማ የሌለን ገበሬዎች ለአብዮቱ ስንል ምናችንን እንበላለን/" ብሎ ይጠይቃቸዋል እርሳቸውም "እንኳን ተናገር የተባልሁትን ተናገርሁ እንጅ ቁርጭምጭምትህን ብትበላ ግድ አለኝ እኔ ቆምጨ አምባው?" አሉት ። ዲ.ን ዳንኤል ከዚህ ላይ ዋናው ነጥቤ አንተስ ብሎግ ስላለህ ቁጭትህን/ጉዳትህን/ በብሎግህ ላይ በመጻፍህ ሰሚ አገኘህ እኛ ብሎግ የሌለንስ ብሶታችንን በምን ላይ እንግለጸው? አደራህ መቸም በግምባርህ ላይ ብትጽፈው ግድ አልኝ ? እንዳትለኝ ። ቢሆንም ግን "ፈረንጅ ነው እኮ" ካለችህ የቴሌ ሰራተኛ /ከኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን/ ይልቅ ስምንትኛ ጾም ያስጾመህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እጅግ የተሻለ ነው መጽሃፉም እኮ አድልው ለጾም ነው የሚለው። ስለዚህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይቅርታ መጠየቁ የሚያስመስግን ነው። በተረፈ፦
  ኢትዮጵያዊ ወንድማቸውን ለሚገላምጡ
  ፈረንጅ ሲያዩ ለሚሽቆጠቆጡ
  የአየር መንገዳችን ሰራተኞች እግዚአብሄር የሃገር ልጅ የሚያከብር ልቦና ይስጣቸው። አሜን።

  ReplyDelete
 10. Wow Good Job D. Daniel Kibret

  ‹ጠላት ያማል ወዳጅ ይወቅሳል› We proud of u, Good Job also Ethiopian Airlines Excellent Job taking the complain and take immediate action, We proud of u as well. May God bless u all.

  ዛሬ ከጆሃንስበርግ ወደ አዲስ አበባ ስመለስ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአካባቢ ሥራ አስኪያጅ በተፈጠረው ጉዳይ ላይ አነጋግረውን ነበር፡፡ ባለፈው ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቀው፣ በቀጣይ ተመሳሳይ ስሕተቶች እንዳይፈጠሩ አሠራራቸውን ማረማቸውን ገልጠውልናል፡፡ ያለፈውንምንም ለመካስ በቢዝነስ ክላስ ወደ አዲስ አበባ እንድንመለስ አድርገዋል፡፡

  ReplyDelete
 11. "ጥበቡን በልቡናችሁ፣ መልካሙን መስተንግዶ በአውሮፕላናችን ላይ ያሳድርብን፡፡ አሜን፡፡"
  አዎ አሜን!

  ነገር ግን ዳንኤል ይህንን ለብዕር ፍራቻ የተደረገ ምላሽ ብቻ እንደሆነ አድርጌ ነው የማየው::አንድ አሳዛኝ ክስተት ላንሳልህ አንድ ጓደኛዬ ገንዘብ ተዋጥቶለት በልመና የልብ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ወደ ህንድ ለመሄድ በዚሁ አየር መንገድ ደካማ አሠራር የተነሳ ከበረራው ሳይሆን ቀረ:: ቀጥሎ ለመሳፈር ያለውን ብሮክራሲ አሁን እዚህ ላይ አልዘረዝረውም፤ የሚያሳዝነው ግን በዚህች ስህተት ምክንያት መሳፈር ባለመቻሉ ቀዶ ጥገናውን ሳያደርግ ቀረ ሕይወቱም አለፈች:: ይህንንሳ "በብዝነስ ክላስ" ይክሱት ይሆን? "ከአምላክ የመጣ ጥሪ ነው እነሱ ምን ያድርጉ?" እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ:: ተገቢ አገልግሎት ለማግኘት አየር መንገዱ የሚጠይቀው ክፍያና መስፈርት ከማሟላት ያለፈ አንድ ተሳፋሪ ማድረግ ያለበት ጠጨማሪ ነገር አይታየኝም:: ያሳዝናል!!!

  ReplyDelete
 12. እነ ቴሌና መብራት ሃይል እነ ገቢዎችና ወረዳዎች ምነው እንዲህ እርማት ሲሰጣቸው ወዲያው ማረም ቢችሉ የት ይደረስ ነበር ?

  ReplyDelete
 13. ያለፈውንምንም ለመካስ በቢዝነስ ክላስ ወደ አዲስ አበባ እንድንመለስ አድርገዋል፡፡
  << በቢዝነስ ክላስ >> ምን ማለት ነው ?

  ReplyDelete
 14. ብሎግህ ጉልበት አለው፡፡ እንደ አንዳንድ አጨብጫቢዎች በመንደር ብቻ የሚቀር አይደለም፡፡ በርታ ወገኔ፣ የአገር አለኝታነትህን አስመስክረሃል፡፡ ምናለች በለኝ፡፡ ይህን መልካም ሥራ ስለሠራህ፣ “የወያኔ ካድሬ” የሚል ስም ያሰጥሃል፡፡ ግን ተወው ሥራህን ብቻ በተመቸህ መንገድ ከመሥራት እንዳታቋርጥ፡፡

  ReplyDelete
 15. ከተባበርን፣ ከተስማማን እና ከተዋደድን፤ ትልቅ እንደነበርን ትልቅም እንሆናለን።

  ReplyDelete
 16. betam arif new dani huletunm be gilits silaskemetik igziabher yibarkih gin koy lelochachinm chigrachin indifetulin blog inawta inde?anyhow bisotachin be ante bekul astelalfenal yikrtawnm be ante bekul tekeblenal b/c ye ante blog yegna newna.betesebihn geta yibarkilih bro

  ReplyDelete
 17. hmmm....what you talking about D.Danial? what about others who do not have blog like you? Do you think the other 19 people get the same sorry phone call and next fight 1st calss service? Do you think you got sorry call coz of ur gold card? plz let see some change before we thank them. They desrive thank you when they try to fix thier peroblems. How many people care how the hostess is butiful while she don't have good smile and respect. They even didn't try to give us fruit or berad while I were face same problem what u got, i also didn't get sorry call.

  BTW when i read ur comment about it, i were happy coz we need such kind writer who could see people problems and bring to public, which will help to eliminate our peroblems.
  You have a best viwes keep it up D.Danila. Thanks!!!

  Zumira

  ReplyDelete
 18. ብርና ወርቅ የሌለን ስምንተኛውን የአየር መንገዳችን ጾም መጾም ነዋ እንግዲህ ።

  ReplyDelete
 19. አንደ አየር መንገዳችን እንዲሁ ከስህተቱን የሚማር መንግስትን ይስጠን
  አሜን በሉ
  አዜብ ዘሚኒሶታ

  ReplyDelete
 20. Hope other government bodies as well listen to our comment and critique for mutual understanding and betterment of our country.

  ReplyDelete
 21. Dear Daniel,
  The hospitality observed in the photos above depicts the real feature of Ethiopian airway hostesses. They provide the warmest service for whites. That would have been awesome, had not it been at the expense of Ethiopian basic service requests. Ethiopian airway cannot afford losing its Ethiopian customers. Therefore, the management should train their hostesses to bring about real change in the way they treat their guests irrespective of colour or other economic criteria.

  ReplyDelete
 22. Nice Ethiopian airlines our airlines i proud our airlines .automatically give a solution

  ReplyDelete
 23. !!!! የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኛ ባይሆን ይቆጨን ነበር !!!!

  ReplyDelete
 24. እንዴት ሰው የማያውቀውን ሰው ይጠላል? በሂዮቴ ያየሁህ አንዴ በ 1995 ዓ ም በግምት ለ2 ደቂቃ ያህል ነው በዚያች ደቂቃ ውስጥ ትቢት በአንተ ላይ ተጭኖ ተመለከትኩ እንዴት ነው ነገሩ ብየ ስጠይቅ ጠባዩ ነው የክፋት አይደለም አለኝ አንድ የጋራ ወዳጃችን ታዲያ ያች 2 ደቂቃ በፊት ስለአንተ የነበረኝን ቀና አመለካከት በተወሰነ መልኩ ቢያደፈርስብኝም ያንተን እንቅስቃሴ ግን ከመከታተል አልቦዘንኩም ብዙ ስራወችህን እወዳቸዋለሉ ቢሆንም ግን እንደአንተ ያሉ ሰወች ለቤተክርስቲያን አንድነት መስራት ይጠበቅባቸው ነበር ምንም ባልጠቅም እጎዳለሁ እንዳለችው ሰተኛ አዳሪ ሰውን መናቅ አያስፈልግም በርግጥ አሁንም የቤተክርስቲያን አባቶች ድጋሚ ከመሳሳት የማዳንና ቤተክርስቲያናችን አንድ ሲኖዶስ አንድ ፖትሪያሪክ ምእመኑም ስደተኛ ገለልተኛ ወያኔ እየተባባለ ተለያይቶ እንዳይቀር ቤተክርስቲያናችን ወደነበረበት አንድነቷ በምትመለስበት ዙሪያ ልትሰራና ከእግዚአብሄር ባገኜኽው ተሰጦ አንተም ወደነበርክበት መንፈሳዊ ህይወትህ ብቻ እንድትመለስና እንድታገለግል ለዚህም እግዚአብሄር እንዲረዳእ ጸሎቴ ነው::

  ReplyDelete
 25. But not for me. I always fly Luftanza just because some employees treat me differently.In addition I get excellent service at German Air plane.Shame on Ethiopian/Weyane airliens.

  ReplyDelete
 26. D/Daniel:GOD BLESS YOU . PLEAS BE STRONG AND DON'T GIVE UP !

  ReplyDelete
 27. For all Ethiopian passengers: let us have a positive attitude and understanding because the airline belongs to all Ethiopians. please understand the employees, it is a life full of hardship!!! Wish u a safe and pleasant flight at all times.

  ReplyDelete
 28. AnonymousDecember 7, 2012 9:16 PM
  SELEMEN ENDEMTAWERA/I baygebanem yetsafchew melkam aydelem yesewen yegel neger metsaf ayasfelegem ASTEWELESH/H KANEBEBCHEW TELEK TEMEHERT YESETAL ( yehe yekenat ena yemekegnet yemeslal!!!!!)


  tersit kegermen

  ReplyDelete
 29. Dani Kalhywet yasemalne .....

  Blen
  MN

  ReplyDelete
 30. እግዚአብሔር ይጠብቅህ፡፡

  ReplyDelete