እስኪ ታላቅ ነው በምንለው ቦታ ደርሰናል ብለን የምናስብ ሰዎች ለአፍታ ዘወር ብለን
ተንጠላጥለንባቸው የተሻገርንባቸውን አያሌ ሰዎች ለማስታወስ እንሞክር፡፡ እዚህ ለመድረሳችን የምናውቀውንም የማናውቀውንም ድርሻ
የተወጡ፣ እነርሱነታቸው እኛነታችን ውስጥ ያለ፡፡ አሁን የተቀመጥንበት ወንበር፣ የምንተኛበትም አልጋ፣ የምንኖርበትም ቤት፣
የምንቆጥረውም ብር፣ የወጣንበትም ከፍታ የእነርሱ ጭምር የሆነ፡፡ እነርሱ ባይኖሩ ኖሮ እዚህ ቦታ ለመድረስ ቀርቶ ወደዚህ
አቅጣጫ እንኳን ለማየት የማይቻለን፡፡ እስኪ የሚቀጥለውን ታሪክ እየተከታተላችሁ እነዚህን አስቧቸው፡፡
መምህራን፣ የቤት ሠራተኞች፣ ሞግዚቶች፣ የሠፈር ሽማግሌዎች፣ አያት፣ አጎት፣ አክስት፣
የጥበቃ ሠራተኞች፣ ሾፌሮች፣ ጓደኞች፣ ሐኪሞች፣ ፖሊሶች፣ አንድ መሥሪያ ቤት ሄደን በጎ ያደረጉልን ሰዎች፣ ሳያስቡትም
ሳናስበውም ዕድል የከፈቱልን ሰዎች፣ ሕይወታችንን የቀየረችውን አንዷን ብር የሰጡን ሰዎች፣ ከሞት ያተረፉን፣ ከመከራ የታደጉን
ሰዎች፤ ያበረታቱን፣ ያጨበጨቡልን፣ የመረቁን፣ መንገድ ያሳዩን፣ በልብሳቸው አጊጠን፣ በምግባቸው ጠግበን እንድንጓዝ የረዱን፤
ከኛ በፊት ሕይወታቸውን ሰጥተው፣ ለኛ ሲሉ ተሠውተው ያለፉልን ጀግኖች፤ እነማን ነበሩ? እስኪ ይህንን ታሪክ እያነበባችሁ
አስቧቸው፡፡
ሁለቱም ባገኙት መሣርያ ሊሠሩ፣ በየጊዜው እየተገናኙ ሊወያዩና ሊጠያየቁ፣ ብሎም
በርትተው ሊጸልዩ ተስማሙ፡፡ በስምምነታቸውም መሠረት ወደ ደረሳቸው ቦታ ተጓዙና ሕይወትን ጀመሯት፡፡ መጀመርያ ከዛፉ እየዘነጠፉ
ቤት መሳይ ነገር ሠሩ፡፡ ከዚያም ደግሞ የዱር ፍራፍሬ መለቃቀሙን ጀመሩ፡፡
ከተራራው ፊት ለፊት ያነበረው ሰው በጠዋት ተነሥቶ እግዚአብሔር ቤቱን እንደ ጥንት
ቤቱ እንዲያደርግለት ጸለየ፡፡ ካጎነበሰበት ሲነቃም ትናንት በቅጠል የሠራው ቤት ምርጥ ቪላ ሆኖ አገኘው፡፡ የሰበሰበውንም
ፍራፍሬ እዚያ በየመልኩ አስቀመጠ፡፡ በማግስቱም አምላኩ ቤቱን በቤት ዕቃዎች እንዲሞላለት ለመነ፡፡ ከጸሎቱ በኋላም እንዳለው
ሆነለት፡፡ እርሱም እንጨት ሰብስቦ ፍራፍሬዎችን እያበሰለ ተመገበ፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላም እግዚአብሔር ሚስት ይሰጠው ዘንድ ለመነ፡፡ በማግሥቱም አንዲት
ቆንጆ ሴት እየዋኘች ወደ ደሴቱ ስትመጣ አያት፡፡ ዐወቃትም፡፡ እርሷን ሲያገኝ ደግሞ ልጆችን ፈለገ፡፡ እነሆም ልጆችን አገኘ፡፡
መኪናም ተመኘ፤ እነሆም አገኘ፤ ታላላቅ ፎቆችን ማየትም ተመኘ፤ እነሆም አገኘ፡፡
በየወሩ መጨረሻ ከዚያኛው ጓደኛው ጋር ተገናኝተው ይነጋገሩ ነበር፡፡ ያኛው ጓደኛው እርሱ
ከሚኖርባት በቅጠል የተሠራች ጎጆ በቀር ምንም አልነበረውም፡፡ በየጊዜው ይህኛው እያለፈለት ሲሄድ ያኛው ባለበት እየረገጠ ነው፡፡
ይህኛው ጸሎቱ መልስ ሲያገኝ ያኛው ግን ጸሎት እንጂ መልስ አልነበረውም፡፡ ይህኛው ሲጨመርለት ያኛው ግን ሕይወት እንደረጋችበት
ናት፡፡
ጓደኛው ግራ ተጋባ፡፡ ‹‹ይህ ጓደኛዬ ኃጢአተኛ ሰው ነው ማለት ነው፡፡ ምናልባትም መርከባችንን የሰበራት እርሱ እንደ
ዮናስ ኃጢአት ሠርቶ በመኮብለሉ ይሆናል›› ብሎ ገመተ፡፡ የራሱንም ጽድቅ አሰበና እጅግ ደስ አለው፡፡ ከዚህ አካባቢ ይህንን ኃጢአተኛ
ሰው ትቶ መውጣት እንዳለበትም ወሰነ፡፡ አብረው አድገው አብረው በመርከብ ተጉዘው፣ አብረው በመርከብ አደጋ ተካፍለውና አብረው ወደ
ደሴቷ በመጡ ሁለት ጓደኛሞች መካከል እንዴት ይህንን ያህል ልዩነት ሊከሰት እንደቻለ አልገባውም፡፡ እርሱ ባለ ቤት፣ ባለ ሚስት፣
ባለ ገንዘብ፣ ባለ መኪና፣ ባለ ፎቅ ሆኗል ያ ግን ‹ያ› እንደሆነ ው፡፡
ባለ ሀብት፣ ባለ ንግድ፣ ሚሊየነር፣ ቢሊየነር መሆን ተመኘ፡፡ ለዚህ ደግሞ መጀመርያ ደሴቲቱን ለቅቆ መውጣት አለበት፡፡
እናም ከዚህ ደሴት ይዞት የሚያወጣው መርከብ ይልክለት ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው፡፡ እግዚአብሔርም አንድ ትልቅ መርከብ ላከለት፡፡
ዕቃውን ጫነ፤ ሀብቱንም ሰበሰበ፡፡ ሚስቱንና ልጆቹንም አሳፈረ፡፡ ያኛውን ጓደኛውን ግን ሊሰናበተው እንኳን አልፈለገም፡፡
ርግጥ ነው አብረው ክፉና ደግ አሳልፈዋል፤ አብረው ታግለዋል፣ አብረው ተጉዘዋል፣ አብረው መርከ ባቸውን አጥተዋል፣ አብረው እዚህ
ደርሰዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ‹ተለያየን› ወንዝ ላይ ደርሰዋል፡፡ አሁን ሁሉም ነገር ተረት መሆን አለበት፡፡
ወደ መርከቧ ገብቶ የመርከቧን መሪ ጨበጠ፡፡ ነገር ግን መርከቧ ልትነሣ አልቻለችም፡፡ ቀድሞ የሚያውቃቸውን ዕውቀቶች
ሁሉ ሞከረ፡፡ ይህችን መርከብ ግን ማስነሣት አልተቻለውም፡፡ የመርከቧ ዕቃዎች አዳዲሶች ናቸው፡፡ የተበላሸ ነገር አይታይባትም፡፡
እጅግ ሲጨንቀው ወደ ፈጣሪው ለመነ፡፡ ፈጣሪም መልስ ሰጠው፡፡
‹‹ጓደኛህን ጥለህ ለመውጣት ለምን ፈለግክ?››
‹‹ይህ ጓደኛዬ ፈጣሪ የተጣላው ነው፡፡ ይጸልያል ነገር ግን አይመለስለትም፡፡ ምናልባትም አንዳች ችግር ቢኖርበት ይሆናል፡፡
ይህ ሁሉ በረከት እኔ ብቻዬን በጸሎት ያገኘሁት ነውና እርሱን መጨመር አይገባኝም›› አለው፡፡
ፈጣሪም መልሶ ‹‹ ለመሆኑ ይህ ሁሉ የተደረገልህ ለምን ይመስልሃል?›› አለው፡፡
‹‹ከልቤ ስለጸለይኩና ጸሎቴም መልስ ስላገኘ ነው›› አለው፡፡
‹‹አይደለም›› ሲል ፈጣሪ መለሰለት፡፡
‹‹ታድያ ለምንድን ነው?›› አለና ጠየቀው፡፡
‹‹በጓደኛህ ምክንያት ነው›› አለው ፈጣሪም፡፡ አሁን ይበልጥ ግራ ተጋባ፡፡
‹‹ይህማ ሊሆን አይችልም፤ እርሱ እንኳን ለእኔ ለራሱም መሆን አልቻለም››
‹‹ሁለታችሁን የለያችሁ የጸለያችሁት ጸሎት ነው››
‹‹እንዴት?››
‹‹አንተ ይህንንና ያንን ስጠኝ እያልክ ትጸልይ ነበር፡፡
እርሱ ግን እባክህን ‹ጓደኛዬ የሚለምንህን ስጠው› እያለ ነበር የሚጸልየው፡፡ ይህንን ሁሉ ያገኘኸውም ባንተ ሳይሆን በርሱ ጸሎት
ነው፡፡ ያንተ ጸሎት የተሰማው በእርሱ ጸሎት ምክንያት ነው፡፤ አንተ የከበርከው፣ ባዕለ ጸጋ የሆንከው፣ ሀብት የሰበሰብከው፣ ያሸነፍከውና
ዛሬም ለመውጫ የሚሆን መርከብ ያገኘኸው በእርሱ ምክንያት ነው፡፡ እርሱ ከራሱ ይልቅ ለአንተ በማሰቡ ነው፡፡ አንተ ግን ስለ ራስህ
ብቻ የምታስብ ስስታምና ስግብግብ ነህ፡፡ ማካፈልን የማትወድ፣ መነሻህንም የምትረሳ ነህ፡፡
‹‹በሌሎች ትግል ለሥልጣን የበቁ፣ በሌሎች ንግድ ያተረፉ፣ በሌሎች ፈተና እነርሱ ያለፉ፣ በሌሎች ሥራ እነርሱ ደመወዝ
የተከፈላቸው፣ ሌሎቹ ታመውላቸው እነርሱ በጤና የሚኖሩ፣ ሌሎቹ መርፌውን ተወግተውላቸው እነርሱ የዳኑ፣ ሌሎቹ አዝነውላቸው እነርሱ
የሚደሰቱ አያሌ ናቸው፡፡ የሁሉም ችግር ግን እንዳንተ ዓይነት ነው፡፡ ‹ይህ ሁሉ የተገኘው በእኔ ብቻ ነው› ብለው ያስባሉ፡፡
ለእነርሱ እዚህ ቦታ መድረስ አብረዋቸው የለፉትን እንዲያውም ከእነርሱ በላይ የደከሙትን ይረሳሉ፡፡ እነርሱ ካገኙት ጥቂት
እንኳን ሊያካፍሏቸው ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ እስኪ ጳጳሳትን አስተምረው ለዚህ ያበቁትን የአብነት መምህራን ተመልከት፡፡ አሁን እነርሱን
የሚያስታውሳቸው አለ? በጳጳሳቱ ሕይወት ውስጥ የአብነት መምህራኑ አስተዋጽዖ አለ፡፡ በአብነት መምህራኑ ሕይወት ውስጥ ግን የጳጳሳቱ
አስተዋጽዖ የለም፡፡
እስኪ እናንተን አስተምረው ለዚህ ያበቋችሁን ከአንደኛ እስከ ኮሌጅ ያሉትን መምህራን አስታውስ፡፡ ይህ ሁሉ ባለ ሀብት፣
ባለ ሥልጣንና ባለ ጊዜ የእነዚህ ሰዎች አሻራ አርፎበታል፡፡ ግን እነርሱ የት ናቸው? እናንተስ የት ናችሁ? ለመሆኑ ሀገራችሁ እዚህ
ስትደርስ በስንት ሰዎች ትከሻ ላይ ተራምዳ ነው፡፡ እነዚያ ሀገር የተራመደችባቸው ሰዎች ግን ዛሬ የት ናቸው? እንኳን ካገኛችሁት
ልታካፍሏቸው ቀርቶ ስማቸውንስ በበጎ ታነሡታላችሁ? አሁን እናንተ የምትበሉትኮ አባቶቻችሁ ወታደሮች ሆነው አድዋና ማይጨው የዘመቱበት፣
አምስት ዓመት ከጣልያን ጋር የተዋጉበትን ደመወዛቸውን ነው፡፡ እነርሱ አልተከፈላቸውም፤ እነርሱ መረማመጃ ሆኑ እንጂ አልተረማመዱም፡፡
እናንተ ግን በእነርሱ ትከሻ ላይ ናችሁ፡፡
አሁን ከባለ ሥልጣን እስከ ተራው ድረስ የምትበሉት እነርሱ ሊከፈላቸው ሲገባ ሳይከፈላቸው ትተውት የሄዱትን ደመወዛቸውን
ነው፡፡ ይህንን አስተውል፡፡ ይኼ ከተማዋን የሞላት ፎቅና ሕንፃ የባለቤቶቹ ብቻ እንዳይመስልህ፤ የብዙ ሰዎች ጭምር ነው፡፡ ልዩነቱ
ሥራውን አብረው ሠሩት ፣ ምግቡን ግን ለብቻ በሉት፡፡ እነዚህ በሥልጣን የምታያቸው ሰዎች ብቻቸውን ታግለው፣ ብቻቸውን ሞተው፣ ብቻቸውን
እዚህ የደረሱ እንዳይመስልህ፡፡ ብዙ ሺ ዎች፣ የሚታወቁና የማይታወቁ፣ የተመዘገቡና ያልተመዘገቡ፣ ይህቺን ቀን ያዩና ያላዩ አብረው
ነው የታገሉት፣ አብረው ነው የሞቱት፤ ነገር ግን ጥቂቶች ናቸው አዲስ አበባን ማጣጣም የቻሉት፡፡ ‹‹በሺ ቢታለብ ያው በገል ነው››
ያለችውን የድመት ተረት እየተረቱ የተቀመጡ ሚሊዮኖች ናቸው፡፡ እንደዚህ እንዳንተ መርከቡ ሲመጣ ማንም እነርሱን አያስታውሳቸውም፡፡
እና ልጄ፣ ይኼ እስከዛሬ እየጸለየ እዚህ ከፍታ ላይ ያደረሰህን ወዳጅህን ረስተህ ብቻህን እሄዳለሁ ካልክ፣ እየጸለየ
ሊያወርድህ እንደሚችልም አስብ፣ በርሱ እንደበለጸግክ ሁሉ በርሱ ልትደኸይ ትችላለህ፡፡ ቁልፉ አንተ ጋር ሳይሆን እርሱ ጋ ነው፡፡
‹በረዥም ገመድ የታሠረች ጥጃ ገመዱ ሲላላ ገመዱ የሌለ ይመስላታል› እንደሚባለው ገመዱ ላልቶ ነው እንጂ አለ፡፡ ለዚህም ነው እሄዳለሁ
ስትል ስቦ ያቆመህ፡፡››
ከመርከቡ ወርዶ በፍጥነት ወደ ተራራው ጀርባ መሄድ ላይ ነበር፡፡ ልጆቹና ሚስቱም ተከተሉት፡፡
ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፤ በተመሳሳይ ኅትመት ላይ ማውጣት ነውር
ነው፡፡
‹በረዥም ገመድ የታሠረች ጥጃ ገመዱ ሲላላ ገመዱ የሌለ ይመስላታል›
ReplyDeleteMay GOD Bless you, Deacon Daniel...It is very touching...Keep it up!
ReplyDelete"እና ልጄ፣ ይኼ እስከዛሬ እየጸለየ እዚህ ከፍታ ላይ ያደረሰህን ወዳጅህን ረስተህ ብቻህን እሄዳለሁ ካልክ፣ እየጸለየ ሊያወርድህ እንደሚችልም አስብ፣ በርሱ እንደበለጸግክ ሁሉ በርሱ ልትደኸይ ትችላለህ፡፡ ቁልፉ አንተ ጋር ሳይሆን እርሱ ጋ ነው"
ReplyDeleteበእውነት መልካም እይታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ባለውለታዎቻችንን እድናስብ ይርዳን
Very nice views. God Bless You.
ReplyDeleteግሩም! ማስተዋሉን ይስጠን፡፡
ReplyDeleteእና ልጄ፣ ይኼ እስከዛሬ እየጸለየ እዚህ ከፍታ ላይ ያደረሰህን ወዳጅህን ረስተህ ብቻህን እሄዳለሁ ካልክ፣ እየጸለየ ሊያወርድህ እንደሚችልም አስብ፣ በርሱ እንደበለጸግክ ሁሉ በርሱ ልትደኸይ ትችላለህ፡፡ ቁልፉ አንተ ጋር ሳይሆን እርሱ ጋ ነው፡፡
ReplyDeleteRely this is such a grate view . let God help us always to think about የተሻገርንባቸው Amen!
በጣም ጥሩ ምክር ሰጪ ምልከታ ነው:: በርታ!!
ReplyDeleteእና ልጄ፣ ይኼ እስከዛሬ እየጸለየ እዚህ ከፍታ ላይ ያደረሰህን ወዳጅህን ረስተህ ብቻህን እሄዳለሁ ካልክ፣ እየጸለየ ሊያወርድህ እንደሚችልም አስብ፣ በርሱ እንደበለጸግክ ሁሉ በርሱ ልትደኸይ ትችላለህ፡፡ ቁልፉ አንተ ጋር ሳይሆን እርሱ ጋ ነው፡፡
ReplyDeleteRely this is such a grate view . let God help us always to think about የተሻገርንባቸው Amen!
Dani, this is very great view. What I feel is that those people who enabled us to be here don't expect anything back from us. But they thought us to enable others in need of help. Thank you.
ReplyDelete"ye abatochachn tselot eske ahun degfo yakoyen" kemilew hasab gar yemismama ymeslegnal.
ReplyDeleteDeacon Daniel, great view, God bless you.
“ተለያየን ወንዝን” የት ነበር የማውቀው? ወደ አቡነ ዮሴፍ ገዳም ስንሄድ ይሆን ? ወይንስ ወደ ይምርሃነ ክርስቶስ ?...ተማሪ ነኝ ያልገባኝ የምታውቁ አስረዱኝ
ReplyDeletewede "gishen" sinhed yimeslegnal
Deleteእግዚአብሔር ይባርክህ!!
ReplyDeleteዳኒ ጥሩ ምልከታ ነው፡፡ ሰው ከጅምሩ የዉሃ፡አፈር፤እሳት፤ነፋስ ድምር ውጤት ነው፡፡ ሲቀጥል የእሱ አስገኝ ከሆኑት አባትና እናቱ የአበራክ ክፋይ ነው፡፡ ከፍ ሲልም የቤተሰብና የአካባቢው የአስተሳሰብ ውልድ ይሆናል፡፡እንዲህ እንዲያ እያሉ አዳሜ ና ሔዋኔ ያገኝትን እያጠረቃቀሙ ለጌታነት ይደርሳሉ፡፡ከዚያማ አንዱ ገዥ ሌላዉ ምናምን እየተባለ ይቀጥላል….
ReplyDelete...ሥራውን አብረው ሠሩት ፣ ምግቡን ግን ለብቻ በሉት፡፡ እነዚህ በሥልጣን የምታያቸው ሰዎች ብቻቸውን ታግለው፣ ብቻቸውን ሞተው፣ ብቻቸውን እዚህ የደረሱ እንዳይመስልህ፡፡ ብዙ ሺ ዎች፣ የሚታወቁና የማይታወቁ፣ የተመዘገቡና ያልተመዘገቡ፣ ይህቺን ቀን ያዩና ያላዩ አብረው ነው የታገሉት፣ አብረው ነው የሞቱት፤ ነገር ግን ጥቂቶች ናቸው አዲስ አበባን ማጣጣም የቻሉት፡፡
ReplyDeletedani hulem tsehuf astemari new abo god bless u!!!!!!!!!!!!
ReplyDeletedn dani it is so interesting. i have read all ur views recently but what i observe is that all are free of any attachment rather they are very interesting and encouraging articles. Further i assure u that most of the reader of your article may have time to change themselves.
ReplyDeleteአወ ዲያቆን ዳንኤል። ያው እንደምታውቀው መለስ ዜናዊም ብዙ ሳይታኮስ እዚያው ዋሻ ውስጥ ተደብቆ ነበር ስንቱን የድሃ ገበሬ ልጅ ያስፈጀው። በነሱ ጀርባ ተንጠልጥሎ አዲስ አበባ ገባ። ከዚያማ ምኑ ቅጡ። ፳፩ ዓመት ሙሉ ስልጣን ላይ ፊጢጥ ብሎ እነሱም እንዲጠሉ፣ እሱም የስልጣን ጥሙን እንዲያረካ ሆነ። አንተ እንዳልከው በኋላ የአምላክም ቁጣ ነደደበት እና አረፈ። ይገርማል ብቻ ዳኒ። ስለ ሞተው ስግብግብ ስለጻፍኩልህ እንደማትቀየመኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
ReplyDeleteመለስ ስንቱን ሲለውጥ አንተን ግን ሳይለውጥህ ሞተ ልጄ ምስኪን! ለምን መሰለህ የኢትዮጵያ ህዝብ ደረቱን እየደቃ ያለቀሰለት? የዘመኑ ሙሴ ዘኢትዮጵያ ነበር። አንተ ብትሞት ከዘመድ ወዳጆችህ ውጪ ማንም ትዝ አትለው። ቅናተኛ።
Deleteአይምሮህ በስድብ የበለጸገ ነው። ቅን ሁንና አይምሮህን ክፈት። ሌሎችን መንቀፍ ትተህ ራስህንና አገርህን ለውጥ።
Meles bizu hiwot lewutual.
DeleteSelamawi tekawmo yemiyadergu wetatochin be tiyt ke hiwot wede mot lewtual.
Gedamatn wede zeregnnet lewtual. Min yalewetew ale?
ከወ/ት መስከረም
ReplyDeleteወንድሜ ዳንኤል የዚህ ፅሁፍ መልእክት አልገባኝም። በህይወት ዘመናችን ያለፍናቸው በርካታ ውጣ ውረዶች እንዳሉ የታወቀ ነው። ከጠቀስካቸው ውስጥ ለምሳሌ ያህል መምህራንን እንመልከት። ያለምንም ማጋነን እኔን ያስተማሩኝ መምህራን ቁጥር ከ፻ (100) ቢበልጥ እንጅ አያንስም። እነሱን በማሰብ የማመጣው ለውጥ ወይንም ጥቅም አይታየኝም። እኔ ላይ የዘሩትን ዘር ፍሬ እነሱ ላያዩት ይችላሉ። ነገር ግን መልካም ዘር ከሆነና መልካም ፍሬ ካፈራ እነሱ ሳይሆኑ ፍሬውን የሚበሉትም ይሁን የሚያዩት ሌሎች ናቸው። ትላንትን መሰረት በማድረግ ወደፊት እንጂ ወደኋላ ማሰብ የትም አያደርስም። ከታሪክ ብዙ እንማራለን። ታሪክ ለመስራት የተሰጠንን ጊዜ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ግን የነገው ታሪክ ይወቅሰናል። ዛሬ የኛ ነው። እንጠቀምበት።
I secound.
DeleteVery educational. Thanks Dani
ReplyDeleteተለያየን ወንዝ ወደ ግሸን ማሪያም ስትሄድ የሚገኝ ወንዝ ነዉ፡፡
ReplyDeleteGreat wisdom and perspective D. Dani
ReplyDeleteI wanted to take this moment to give a heartfelt thank you for all your support! Thank you so much!
I hope you have all you wish for yourself and those dear to you, and all your dreams come true...
አሁን ከባለ ሥልጣን እስከ ተራው ድረስ የምትበሉት እነርሱ ሊከፈላቸው ሲገባ ሳይከፈላቸው ትተውት የሄዱትን ደመወዛቸውን ነው፡፡ ይህንን አስተውል፡፡ ይኼ ከተማዋን የሞላት ፎቅና ሕንፃ የባለቤቶቹ ብቻ እንዳይመስልህ፤ የብዙ ሰዎች ጭምር ነው፡፡ ልዩነቱ ሥራውን አብረው ሠሩት ፣ ምግቡን ግን ለብቻ በሉት፡፡ እነዚህ በሥልጣን የምታያቸው ሰዎች ብቻቸውን ታግለው፣ ብቻቸውን ሞተው፣ ብቻቸውን እዚህ የደረሱ እንዳይመስልህ፡፡ ብዙ ሺ ዎች፣ የሚታወቁና የማይታወቁ፣ የተመዘገቡና ያልተመዘገቡ፣ ይህቺን ቀን ያዩና ያላዩ አብረው ነው የታገሉት፣ አብረው ነው የሞቱት፤ ነገር ግን ጥቂቶች ናቸው አዲስ አበባን ማጣጣም የቻሉት፡፡ ‹‹በሺ ቢታለብ ያው በገል ነው›› ያለችውን የድመት ተረት እየተረቱ የተቀመጡ ሚሊዮኖች ናቸው፡፡ እንደዚህ እንዳንተ መርከቡ ሲመጣ ማንም እነርሱን አያስታውሳቸውም፡፡
ReplyDeleteእና ልጄ፣ ይኼ እስከዛሬ እየጸለየ እዚህ ከፍታ ላይ ያደረሰህን ወዳጅህን ረስተህ ብቻህን እሄዳለሁ ካልክ፣ እየጸለየ ሊያወርድህ እንደሚችልም አስብ፣ በርሱ እንደበለጸግክ ሁሉ በርሱ ልትደኸይ ትችላለህ፡፡ ቁልፉ አንተ ጋር ሳይሆን እርሱ ጋ ነው፡፡ ‹በረዥም ገመድ የታሠረች ጥጃ ገመዱ ሲላላ ገመዱ የሌለ ይመስላታል› እንደሚባለው ገመዱ ላልቶ ነው እንጂ አለ፡፡ ለዚህም ነው እሄዳለሁ ስትል ስቦ ያቆመህ፡፡››
Great observation! great message!for those who can see, hear and understand religious thought.There are many people who lived for others but never lived for themselves even for one minute. Lets not forget them!
ዲን ዳኒ
ReplyDeleteየአባቶቻችንን ገድል አሰስታወሰኝ፡፡
ደስ ይላለል!
10 q!
ReplyDeleteየዲያቆን ዳንኤል ክብረትን እይታ ባነበብኩ ጊዜ በጣም ደስ አለኝ @ ተማርኩም ; በጣም ግሩም ጡመራ እግዝያብሄር ይጠብቅልን፡፡
ReplyDeleteዲ.ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልን ጥሩ አስተውለሃል፡፡
ReplyDeleteበተለይ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ለትምህርት ስኮላር ሺፕ አግኝተው፣ በጉብኝት ስም በዚያው ለመቅረት አስበው እንዲሁም በስራ ምክንያት ከወጡ በኋላ ላለመለስ የሚወስኑ የኛው ወገኖች በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ እድሉን ስላገኙ ብቻ አንዳንዴ የሳምንት ቀለብ እንኳን የማይሸፍን ገንዘብ ብቻ ይዘው ይመጣሉ፡፡ በሚሄዱበትም አገር ተረጋግተው የሚኖሩትን በተለይም ወንዶቹ ሴት እህቶችን በመንፈሳዊነት ስም በመቅረብና ለፍቅር ጓደኝነት የሚፈልጓቸው በማስመሰል በገዛ ቤታቸውና ገንዘባቸው ክፉ ጊዜያቸውን ካሳለፉ በኋላ የኑሮአቸው ሁኔታ መስተካከል ሲጀምር አክብረው የተቀበሏቸው ወገኖቻቸውን ስራ፣ ማህበራዊ ኑሮና አጠቃላይ ህይወት ወዘተ ለማናናቅና እነርሱ ደግሞ በሌሎች ዘንድ ትልቅ ሰው ለመሆን ሲጥሩ ማየት እየተለመደ መጥቷል፡፡ በርግጥም አንተ እንደጠቀስከውና ‹በረዥም ገመድ የታሠረች ጥጃ ገመዱ ሲላላ ገመዱ የሌለ ይመስላታል› እንደሚባለው እግዚአብሔር ይህንን ግፍ ተመልክቶ ገመዱን ያጠበቀው ጊዜ ምስክር የሚሆን እንኳን እንደማገኝ አለማሰብ ሞኝነት ነው፡፡
ስለሆነም እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች "እስኪ ታላቅ ነው በምንለው ቦታ ደርሰናል ብለን የምናስብ ሰዎች ለአፍታ ዘወር ብለን ተንጠላጥለንባቸው የተሻገርንባቸውን አያሌ ሰዎች ለማስታወስ እንሞክር፡፡" ማለት ተገቢ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
ለሁሉም አስተዋይ ልቦና ይስጥልን!
ዘይገርም በእዉነት መልካም እይታ ነዉ።
ReplyDeletekalehiwet yasemalin .....ብዙ ሺ ዎች፣ የሚታወቁና የማይታወቁ፣ የተመዘገቡና ያልተመዘገቡ፣ ይህቺን ቀን ያዩና ያላዩ አብረው ነው የታገሉት፣ አብረው ነው የሞቱት፤ ነገር ግን ጥቂቶች ናቸው አዲስ አበባን ማጣጣም የቻሉት፡፡ ‹‹በሺ ቢታለብ ያው በገል ነው›› ያለችውን የድመት ተረት እየተረቱ የተቀመጡ ሚሊዮኖች ናቸው፡፡ እንደዚህ እንዳንተ መርከቡ ሲመጣ ማንም እነርሱን አያስታውሳቸውም፡፡
ReplyDeleteLANT KALE HIWET YASEMALEN...MEMEHRACHN.... LB YALEW LBE YEBEL ... KE MESALLU BETACH YALUTN YAMENASBBET ...WEDLAY SAYEHON WD TACHM ZEK BELEN YEMNAYBET ZEMEN YAMTALEN
ReplyDeleteእውነት እውነት እውነት ነው::
ReplyDeleteእውነት እውነት እውነት ነው::
ReplyDeleteIt is much helping for all of us who we are today is a result of the many ups and downs of life we came with the society. Very nice words to read. Keep up the good work Dn. Daniel.
ReplyDeleteNice
ReplyDeleteit's nice look
ReplyDeletenice look
ReplyDeletenice look
ReplyDeletewedjelhalehu be ewnert yamiyaneka eyita new
ReplyDeletedani leyu new be ewnet
ReplyDelete