ባለፈው እሑድ ጥቅምት 25 ቀን 2005 ዓም አዋሳ ላይ ሆኜ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን
118ኛ ፓትርያርኳን ስትመርጥ እያየሁ ነበር፡፡ እጅግ ደስ የሚለው ሥነ ሥርዓቱን ከ20 በላይ ዓለም አቀፍ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች
ሽፋን ሰጥተውት ነበር፡፡ በረከታቸው ይደርብንና ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ በዘመናቸው ለግብጽ ቤተ ክርስቲያን ከሠሯቸው ሥራዎች
አንዱ ዘመናዊ የሆነ የኦዲዮ ቪዡዋል ማዕከል ባለቤት ማድረጋቸው ነው፡፡ በእርሳቸው ዘመን ታላቅ የሆነ የቴሌቭዥን ስቱዲዮ
ተገንብቷል፡፡ ኮፕቲክ ቴሌቭዥን፣ አጋፒያና ክርስቲያን ቲቪ የተሰኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን የዕለት ተዕለት ጉዳዮች የሚዘግቡ
የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ተቋቁመዋል፡፡
በዕለቱ የነበረውን ዝግጅት ከዋዜማው ጀምሮ ታላላቅ ባለ ክሬን ካሜራዎችን በመትከልና
የትኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓት መቀረጽ እንዳለበት በመለየት የኮፕቲክ ቴሌቭዥን ጣቢያ ከኮፕቲክ የኦዲዮቪዡዋል ማዕከል ጋር
በመሆን ተዘጋጁ፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥና ውጭ ከ16 በላይ ባለ ክሬን ካሜራዎች ተተክለው ነበር፡፡
ከመላው ዓለም የተገኙ ከ230 በላይ ጋዜጠኞች በተዘጋጀላቸው ልዩ ቦታ ላይ ሆነው
ከጠዋቱ ጸሎት አንሥቶ እስከ ምርጫው ፍጻሜ የነበረውን ሥነ ሥርዓት ለመላው ዓለም በቴሌ ቭዥን፣ በሬዲዮ፣ በዌብ ሳይትና በብሎግ
ያስተላልፉ ነበር፡፡ ከአሥር ሺ ሕዝብ በላይ የሚይዘው የአባስያ የቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በተመረጡ ገዳማውያን፣ ካህናት፣
ምእመናን እና ተጋባዥ እንግዶች መሞላት የጀመረው ገና ከጠዋቱ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነበር፡፡
ይህ መንበረ ፕትርክና የተገነባበት ቦታ ጥንት የግብጻውያን ክርሰቲያኖች መቃብር የነበረበት ቦታ ነው፡፡ ቦታው ለቤተ ክርስቲያኒቱ የተሰጠው በ969 ዓም ለቤተ መንግሥቱ መሥሪያ ተብሎ በተወሰደባት ቦታ ምትክ ነው፡፡ በቦታው ላይ ጥንታዊው የአባ ሮዩስ ቤተ ክርስቲያን ነበረበት፡፡
በ12ኛው መክዘ በአካባቢው 12 አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ፡፡ በ1280 ዓም አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ተነሥተው አብያተ ክርስቲያናቱን አቃጠሏቸው፡፡ ከዚያም በቦታው ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ተሠሩ፡፡
አሁን ያለውን የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ያሠሩት ፖፕ ቄርሎስ 6ኛ ሲሆኑ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረውም በ1968 ዓም ነው፡፡ በዚህ ቤተ ክርስቲያን ሥር ነው
የታላቁ ሐዋርያዊ አባት የቅዱስ አትናቴዎስ ዐጽም ያረፈው፡፡
ለወትሮው ከባድ ጥበቃ የማይለየው መንበረ ፓትርያርኩ በዚያ ቀን የፖሊሶችም ሆኑ
የወታደራዊ ጥበቃዎች ቁጥር ጨምሮ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያኒቱ በኩል የተሠማሩ ክርስቲያን የጸጥታ አስከባሪዎች
በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚከናወነውን እያንዳንዱን ንቅናቄ በንሥር ዓይን እየተከታተሉት ነበር፡፡ ከ300 በላይ ወጣት
የሰንበት ተማሪዎች እንግዶቹን ለማስተናገድና ሥነ ሥርዓት ለማስከበር ተሰልፈዋል፡፡ ‹‹የሚያለቅሱ፣ እጆቻቸውን ወደላይ ሰቅለው
የሚማጸኑ፣ አንገታቸውን ደፍተው ከልብ የሚጸልዩ፣ የሚሆነውን ለማየት ጓጉተው አገጮቻቸውን በመዳፋቸው ይዘው መቅደስ መቅደሱን
የሚያዩ ብዙዎች ነበሩ›› ብሏል አንድ በፌስ ቡክ ሁኔታውን ያስተላለፈ የካይሮ ነዋሪ፡፡
ባለፈው ሳምንት በተደረገው ምርጫ ከፍተኛውን ድምጽ ያገኙት ሦስት አባቶች ስሞች
ከመስተዋት በተሠራና ፋኖስ በሚመስል ዕቃ ውስጥ እንዲገቡ ተደርጎ በሕዝብ ፊት ነበር በሰም የታሸገው፡፡ ይህ የመስተዋት ሙዳይ
በአባስያ የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል መንበር ላይ ተቀምጦ ለአንድ ሳምንት ያህል ጸሎት ሲደረግበት ነበር፡፡
ጸሎቱ የተጀመረው ከማለዳው 12 ሰዓት ሲሆን ቅዳሴው የተጀመረው ዘግየት ብሎ ነው፡፡
በቅዳሴው ላይ ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ጳጳሳት ተሳትፈዋል፡፡ ሁሉም አብረው ቆርበዋል፡፡ ይህም የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት
ለማጠንከርና ሥራውን ለእግዚአብሔር ለማስረከብ ሲባል የሚደረግ ነው፡፡ በምርጫው ሂደት የተወቀሱ፣ ከዕጩነት የተለዩ፣ የተከፉና
ያዘኑ ይኖራሉ፡፡ ይህ ሁሉ ግን ማብቃት አለበት፡፡ እናም ከጸሎቱ በፊት በሚደረገው የዕርቅና የይቅርታ ሥነ ሥርዓት ይህ ሁሉ
ይጠናቀቅና ሁሉም ወደ ቅዳሴ ይገባሉ፡፡ አሁን የሰው ሥራ አብቅቷል ቀሪውን የሚመርጠው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ ወደ ሦስት
ሰዓት የፈጀው ቅዳሴ መጀመርያ ጳጳሳት ከዚያም ካህናት በመጨረሻም የተወሰኑ ምእመናንን በማቁረብ ተጠናቀቀ፡፡
በዚህ ቅዳሴ ልዩ ዕድል ያገኙ 12 ሕጻናት ዲያቆናት ነበሩ፡፡ እነዚህ ዐሥራ ሁለት
ሕጻናት ከመላዋ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ሕጻናት ተመርጠው የመጡ ናቸው፡፡ ጳጳሳቱን በማገልገል በቅዳሴው ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ከሦስቱ አባቶች አንዱን ለፕትርክና ዕጣ የሚያወጣው ከእነዚህ ሕጻናት አንዱ ነው፡፡
ቅዳሴው እንዳበቃ ዐቃቤ መንበሩ አቡነ ጳኩሚስ ያንን የመስተዋት ሙዳይ ከመንበሩ
አንሥተው ወደ መድረኩ ሲያወጡት ዕልልታው ቀለጠ፡፡ አሁን የፕትርክና ምርጫው ወደ መጨረሻው ደረጃ በመጓዝ ላይ ነው፡፡
አስቀድመው የዐሥራ ሁለቱ ሕጻናት ስም በወረቀት ተጽፎ እየተጠቀለለ በአንድ የመስተዋት ሙዳይ ውስጥ ገባ፡፡ ከዚያም ጸሎት
ተደረገ፡፡ ከጸሎቱ በኋላ ዕጣው ወጣ፡፡ ዕጣውም ዕድለኛ ለሆነው ለቢሾይ ጊርጊስ ማሳድ ወጣ፡፡
ዕድለኛው ሕጻን ቢሾይ ጊርጊስ ማሳድ ወደ ላይኛው መድረክ እንዲወጣ ተደረገ፡፡ ዓይኑን
በመስቀሎች በተሞላ ጥቁር መሐረብ ተሸፈነ፡፡ አቡነ ጳኩሚስ ለሁሉም ሰው እያሳዩ ከሳምንት በፊት የታሸገውን የመስተዋት ሙዳይ
ከፈቱት፡፡ ሕዝቡ በጸሎት ላይ ነበር፡፡ እንኳን የግብጽ ሕዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ እንኳን ብዙዎች በጸሎት አብረዋቸው ነበሩ፡፡
ከመላዋ ኢትዮጵያ ሥነ ሥርዓቱን እየተከታተሉት መሆኑን የሚገልጡ ከ133 በላይ የስልክ አጭር መልእክቶች ይደርሱኝ ነበር፡፡
ብዙዎች ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና የቤተ ክህነት ሰዎች ሥነ ሥርዓቱን እንዲከታተሉ በስልክ ሲጋብዙ ነበር፡፡
እኩል በሆኑ የመስተዋት ዕንቁላሎች ውስጥ ስማቸው እንዳይለይ ተደርገው የተጠቀለሉት
ወረቀቶች አሉ፡፡ የተመረጠውና ዓይኑን የታሠረው ሕጻን እጁን ሰደደና አንደኛውን አወጣ፡፡ ግብጻውያን ይህንን ‹የእግዚአብሔር
እጅ›› ይሉታል፡፡ ዐቃቤ መንበር ጳኩሚስ ከልጁ ተቀብለው እግዚአብሔር አቡነ ታዋድሮስን ለመንበረ ማርቆስ 118ኛ ፓትርያርክነት
መምረጡን አበሠሩ፡፡ ካቴድራሉ በደስታ ተሞላ፡፡ ዕንባዎች ይታዩ ዕልልታዎችም ይሰሙ ነበር፡፡ ወዲያውኑ ዜናውን እነ ሲኤን ኤን፣
ቢቢሲ፣ አልጄዚራ፣ ፕሬስ ቲቪና ሌሎችም ተቀባብለው ናኙት፡፡
አቡነ ታዋድሮስ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ረዳት የነበሩ ናቸው፡፡ እድሜያቸው ወደ
ስድሳ የሚጠጋው አቡነ ታዋድሮስ በእንግሊዝና ሲንጋፖር የፋርማሲ ትምህርት የተከታተሉ፣ ሰፊ ልምድና የአስተዳደር ችሎታ ያላቸው
አባት መሆናቸውን ለቢቢሲ ዜናውን የዘገበው ጆን ሊየን ተናግሯል፡፡ አቡነ ታዋድሮስ ከተመረጡ በኋላ ለጋዜጠኞች በዋዲ ኤል
ናትሩን ገዳም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹ይህ ሥልጣን ሳይሆን ኃላፊነት ነው፡፡ ዋናዋ ነገር እኔ ሳልሆን ቤተ ክርስቲያኒቱ
ናት›› ብለዋል፡፡ የግብጽ ብሔራዊ የዜና አገልግሎት ‹‹ሜና›› እንደተናገረውም አቡነ ታዋድሮስ ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት
በስድሳኛው የልደት ቀናቸው ነው፡፡ በ1986 ዓም በዋዲ ኤል ናትሩን ገዳም የመነኮሱት አቡነ ታዋድሮስ ቅስናንም የተቀበሉት
ከሦስት ዓመት በኋላ በ1989 እኤአ ነበር፡፡ በቀጣዩ ኅዳር 9 ቀን በሚደረገው በዓለ ሲመት 118ኛው የግብጽ ፓትርያርክ ሆነው
በመንበረ ማርቆስ ይቀመጣሉ፡፡
ግብጻውያን ከዚህች ቀን ለመድረስ ብዙ ውጣ ውረድ አይተዋል፡፡ በቆራጥነትና በጸሎት
ሊያሰናክሏቸው የነበሩትን ሁሉ ታግለዋል፡፡ በመጨረሻም ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው አሸንፈዋል፡፡ ግልጽ የሆነ የምርጫ ሕግ፣ ለሕጉ
በቆራጥነት መቆም፣ ሥራውንም ከጸሎት ጋር መሥራት ለዚህ አድርሷቸዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን የፓትርያርክነት መምረጫና መመዘኛ ዝርዝርና ግልጽ ሕግ
ያስፈልጋታል፡፡ የግለሰቦችን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኒቱን ፍላጎት የሚያሟላ፡፡ ሁላችንም የምናውቀው፤ የምንጠብቀው፡፡ ከዚያ
ቀጥሎም ግልጽ የሆነ የምርጫ ሂደት መርሐ ግብር ያስፈልጋል፡፡ ምን መቼ ይደረጋል? በማን? የሚለውን በግልጽ ማስቀመጥ ያሻል፡፡
ከዚያም ደግሞ ምርጫውን የሚያስፈጽም ከአባቶች፣ ከሊቃውንትና ከምእመናን የተዋቀረ ገለልተኛና ታማኝነት ያለው አስመራጭ አካል ያስፈልጋል፡፡ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የምርጫ ሂደት ከሕግ ውጭ ለመመረጥ
የሞከሩ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ገዳማውያን አባቶችና ምእመናን በወሰዱት ቆራጥ አቋም ሳይሳካላቸው
ቀርቷል፡፡ የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጥንካሬ የሚለካው ባጋጠማት ችግር መጠን አይደለም፡፡ በወሰደችው መንፈሳዊ ቆራጥነት
የተሞላው መፍትሔ እንጂ፡፡ ችግሩን ተቋቁማና አሸንፋ ለማለፍ በመቻሏ እንጂ፡፡ የኛ ቤተ ክርስቲያንም እየተሰሙ ያሉትን ችግሮች
ተቋቁማና አሸንፋ ለማለፍ የሚያስችላት ሕግ፣ አሠራርና ቆራጥነት ያስፈልጋታል፡፡
የምንከተለው የምርጫ ሕግ፣ ሥነ ሥርዓትና መርሐ ግብር እንኳን ክርስቲያኑ ሌላውም
ተመልክቶ የሚማረክበት፣ የሚያደንቀውና የሚመሰክርለት መሆን አለበት፡፡ ዕጣውን የሚያወጣውን ሕጻን እንኳን በዕጣ የወሰኑት
ሐሜትን ለመከላከል ሲባል ነው፡፡ ግብጻውያን እንደዚያ የዓለም ጋዜጠኞችን ሁሉ ጠርተው ‹ኑ እዩን› ያሉት የሚያሳዩት ነገር
የማያሳፍር መሆኑን ስለተማመኑ ነው፡፡ የኛስ?
በቴሌቭዥን የተላለፈው ቅዳሴና የምርጫ ሥነ ሥርዓት ቤተ ክርስቲያኒቱን በዓለም ፊት
ከፍ አድርጎ ያሳያት ነው፡፡ የመራወጡ፣ የሚያወሩ፣ የሚንሾካሾኩ አልነበሩም፡፡ አንዳንዴ እኛ ጋ ሆኖ
ቢሆን ብዬ ሳስበው ወዲያና ወዲህ እያሉ የሚራወጡ፣ ጋቢያቸውን አፋቸው ላይ ደግነው የሚያወሩ፣ ሞባይል አውጥተው የሚነጋገሩ፣ በሥነ
ሥርዓቱ አካሄድ ላይ በሃሳብ እየተለያዩ ‹ተው ተው› የሚባባሉትን ሁሉ ዓለም ሲያይ ይታየኝ ነበር፡፡
ሌላው ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን የምንማረው የመራጮችን ቁጥርና ተዋጽዖ መወሰን ነው፡፡ በእነርሱ ዘንድ የመራጮቹ ቁጥር
2411 ነበር፡፡ በኛ ዘንድስ ስንት ነው? ከምን ከምን የተውጣጡስ ናቸው? የትኞቹ ገዳማት፣ አድባራትና አህጉረ ስብከት ስንት ተወካይ
ይኖራቸዋል? የውጭ አብያተ ክርስቲያናት ተሳትፎስ? ምን ያህል ምእመናን ይሳተፋሉ? እንዴትስ ይመረጣሉ? የታዋቂ ሰዎችና የሀገር
ሽማግሌዎች ተሳትፎስ እንዴት ነው? በመጨረሻስ የሚወሰነው እንዴት ነው? እነዚህ ሁሉ ቀድመው ሊወሰንባቸው የሚገቡ ናቸው፡፡
አሁን ያለው ምእመን ያንን የመሰለውን የግብጻውያን የምርጫ ሥነ ሥርዓት ያየ ነው፡፡ የዛሬ 21 ዓመት እንደነበረው አይደለም፡፡
አሁን ያለችው ኢትዮጵያም የዛሬ 21 ዓመት እንደነበረችው አይደለችም፡፡ ዛሬ እንኳን የተነገረውና የተሠራው፣ የታሰበውም የሚሰማበት
ዘመን ነው፡፡ ስለዚህም ለመንፈስ ቅዱስ ሥራ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት፣ ለምእመናንም መንፈሳዊ ጥንካሬ አባቶች ዋናውን ትኩረት
ይሰጡ ዘንድ አደራ አለባቸው፡፡
መልክ ከፈጣሪ ተሰጥቶናል፤ ሞያን ደግሞ ከጎረቤት እንማር፡፡
Egizabehare edema yesetehe
ReplyDeleteohhh God, most of the times I wish to be Egyptian orthodox christian.
ReplyDeleteእንዲህ ዓይነቱን ሥርዓት በመገልበጥ ማምጣት አይቻልም:: እንዲህ የምናደርግ ከሆነ መንግሥታቶቻችን አዘውትረው የሚሰሩትን ስህተት ነው የምንደግመው:: በዚህ ምክንያት ይመስለኛል የመመሪያ የደንብ የሕግ ችግር ገጥሞን አያውቅም:: ብዙ ክፍተቶቻችን የአፈጻጸም እንከኖች ናቸው:: ይህ ደግሞ በመካከል ያለን ያለመግባባት የልብ ድንዳኔና የዓላማም ግጭትን ያመለክታል:: የብፁአን አበው ጉባኤ የወሰነውን ማስፈጸም የሚችልበት መዋቅራዊ ተዋረዱን የጠበቀ አሠራር ሥርዓት አለ:: የተወሰነውን የማይፈጽምና የማያስፈጽም ይልቁንም የሚቀለብስ የሚሆንበት አጋትጣሚ ግን ብዙ ነው:: ይህን እንኳ ትተን በየአህጉረ ስብከታችን ስንደርስ የተወያየነው የወሰንነውና ያመንበትን እንኳ የምናስፈጽም ስንቶች ነን? ታዲያ የቸገረን ምንድን ነው? ሙያ ከጎረቤት ስናመጣ ስንት ዘመን ተቆጠረ የሚያጠግብ ነገር ግን ማግኘት አልተቻለም:: ታዲያ አስመራጭም ከነርሱ እናምጣ? አባት ይላክላችሁ ነጻነታችን ወይም ሞት ሥርዓቱን ጠብቁና ሂዱ ወገቤን! አሁን ያለንበትን ሁኔታ ብቻ ተመልከቱ እስኪ ዋናው ጉዳያችን ምንድን ነው? ቤተ ክርስቲያን ናት? አባ እገሌ ናቸው? የኛን ሰው ማስቀመጥ ነው? ይህን ካለ መለየት የተነሳ እኔ ያልኩት እያልን ነው:: ዋና ጉዳያችንማ ቤተ ክርስቲያን ብትሆን የሚከፈለውን ሁሉ በከፈልንላት ነበር:: የእኔ ብቻ በምንለው ፈንታ ሌሎችንም ማድመጥ በጀመርን ነበር:: የራሳችንን ድርሻ ከተወጣን በኋላ የመጨረሻውን ሥራ ለመንፈስ ቅዱስ በተውን ነበር:: አሁንም በርካታ ጥናቶች ውይይቶች የመፍትሄ አሳቦች. . . የሚዘንቡባቸው ውይይቶች የሚያስፈልጉዋት ቤተ ክርስቲያን አለችንና ውይይቱ ይቀትል::
ReplyDeleteየአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጥንካሬ የሚለካው ባጋጠማት ችግር መጠን አይደለም፡፡ በወሰደችው መንፈሳዊ ቆራጥነት የተሞላው መፍትሔ እንጂ
ReplyDeleteመልክ ከፈጣሪ ተሰጥቶናል፤ ሞያን ደግሞ ከጎረቤት እንማር፡፡
ReplyDeleteperfect!"መልክ ከፈጣሪ ተሰጥቶናል፤ ሞያን ደግሞ ከጎረቤት እንማር፡፡" ለመማርም አስተዋይ ልቡና ይስጠን፡፡
ReplyDeleteI lost the respect that i had to our religious father because of their act.
ReplyDeleteመልክ ከፈጣሪ ተሰጥቶናል፤ ሞያን ደግሞ ከጎረቤት እንማር፡፡
ReplyDeleteዳኒ እግዚያብሔር ይባርክ፡፡
ReplyDelete118 የግብፅ ፓትርያርክ ምርጫ እጅግ የሚገርም ነው፡፡ አለም ትኩረት እንደሰጠው የተሳካ ሆኖ አልፏል፡፡ ዘይገርም ይደንቅ ያስብላል፡፡ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ወሬውን ናኝተውታል ፡፡ እሰይ ፡፡ መጪው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክ ምርጫ ከግብፅ የተለየ ምን ይዞ ይመጣ ; ለአለምስ ምን እናሳያል የሚለው እጅግ ያጓጓኛል ፡፡
እግዚአብሔር እኛንም ይረዳን ዘንድ ጸሎቴ ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ቅሬታ አለኝ
ReplyDeleteየእርቀ ሰላሙ እና የምርጫው ዝግጅት ጊዜ ተቀራረበ ሁሉንም አባቶች እንዲያሳትፍ እርቀ ሰላሙ ቢቀድም፡፡
ውድ ዲያቆን ዳንኤል
ReplyDeleteእጅግ አስተማሪ የሆኑ መጣጥፎችህ ተከታታይ ስሆን ሰሞኑን እንድትፅፍበት ስመኝ ነበረውን ስለፃፍክ በጣም ደስ ብሎኝ አነበብኩት፡፡የግብፅ ክርስቲያን ወንድሞቻችን መልካም እረኛ እንዲሾምላቸው በአንድነት በፆም እና በጸሎት እንዲፀኑ ያስቻላቸው እግዚአብሄር ይመስገን፡፡ ይህ አሸናፊና ተሸናፊ የሌለበት ስለፈጣሪ ክብር ጻድቃን ያሳዩት የእምነት ፅናት ነው ፡፡ ሰይጣንም አፍል፡፡
ዳኒ እግዚያብሔር ይባርክ፡፡
ReplyDelete118 የግብፅ ፓትርያርክ ምርጫ እጅግ የሚገርም ነው፡፡ አለም ትኩረት እንደሰጠው የተሳካ ሆኖ አልፏል፡፡ ዘይገርም ይደንቅ ያስብላል፡፡ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ወሬውን ናኝተውታል ፡፡ እሰይ ፡፡ መጪው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክ ምርጫ ከግብፅ የተለየ ምን ይዞ ይመጣ ; ለአለምስ ምን እናሳያል የሚለው እጅግ ያጓጓኛል ፡፡
ሀብታሙ ጥላሁን ከሀገረ አዲስ
betam des yilala dani
ReplyDeletedes yilal.thanks Dani
ReplyDeleteMOYA KE GOREBIT .... BECHA AYDELEM TSDKEM KE GOREBIT NEW ..... EGZIABHER LEMENUT SETACHEW ... ENGANM ...ENTSUM ..ENTSLI .... EGZIABHER ENMATSEN ...WETITU ENAYEWALEN ... END EMNETACHEW
ReplyDeleteGEN YEHEN SIYANSACHEW NEW ... KEZIH BELAYEM CHERU MEDHANI ALEM BE SEFIW MDAFU YEBARKACHEW ...YE ENATACHN KEDST DENGEL MARYAM WELADIT AMLAK BERKETWA AYLEYACHEW ...YE HAWARYAT KUDUSAN TSDKAN SEMAETAT REDATNET AYLEYACHEW .... AMEN
ደግ ብለሃል ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል
ReplyDeleteግና እንደ ኮፕቶች ዓይነት የፓትርያርክ ምርጫ ለማካሄድ ገና ብዙ ይቀረናል።
በነገራችን ላይ ስለኮፕቶች የተቀላቀለ ስሜት ነው ያለኝ፦
በእሥራኤል በሚገኝ ዴር ሱልጣን ገዳማችን/ይዞታችን እና በዚያው በሚገኙ አባቶቻችን ላይ የሚያደርሱትን ግፍ ሳስበው ክርስትናቸው ወዴት አለች? እላለሁ። በአንጻሩ ደግሞ በካህናቶቻቸውና በምዕመናኖቻቸው የሚገለጸውን እምነታቸውን ሳይ መንፈሳዊ ቅናት ያድርብኛል። ለማንኛውም የሚስማማንን በጎ መውሰድ የሚከለክለን የለም። በእኔ ዕይታ ለፓትርያርክ ምርጫ ከኮፕቶች መውሰድ የሌለብን የምለው የዕጩዎቹን የምረጡኝ ዘመቻ ነው። ፖለቲካዊ ምርጫ አስመስሎታል፤ በቀደሙት አባቶቻችን የአሿሿም ታሪክ የማናውቀውና ለስጋ ያደላ ነው። ሌላውስ ማለፊያ ነው።
ከላይ እንደ ኮፕቶች ዓይነት የፓትርያርክ ምርጫ ለማካሄድ ገና ብዙ ይቀረናል ካልኩበት ምክንያቶች ጥቂቱን ለማለት፦
᎐ የጎሰኝነት አስተሳሰብ ስለነገሰብን እናዳላለን
᎐ ሐሜት የዕለት ቀለባችን ስለሆነ ወገናችንን ለመውደድ ጊዜ አይተርፈንም
᎐ ከክርስቶስ ክቡር ስጋና ቅዱስ ደም ስለራቅን እምነታችን ጎዶሎ ነው (የኮፕት ክርስቲያኖች በሙሉ ማለት ይቻላል ቆራቢዎች ናቸው። በአንድ ወቅት የተዋህዶ ልጆች የሆን በአንድ የኮፕት ቤተ ክርስቲያን አስቀድሰን ስናበቃ ከመካከላችን አንድም የተቀበለ አልነበረምና ካህኑ "ክርስቲያኖች አይደላችሁም እንዴ?" አሉን፤ ነን እንጂ አልናቸው። "ታዲያ የክርስቶስን ስጋና ደም ስለምን አልተቀበላችሁም?" ቢሉን መልስ አልነበረንም)
ጎበዝ በዚሁ ጡመራ መድረክ ላይ ይመስለኛል ከአሁን በፊት እንደተነገረን "ታሪክ ላይ መተኛት" ይብቃን እንጂ! ታቦተ ፅዮን እኛ ጋር ነች? አዎ። የጌታ ግማደ መስቀል ከኛው ነው? አዎ። እግዚአብሔር ዛሬም ገቢረ ተዓምሩን በኢትዮጵያ እያደረገ ነው? አዎ። ታዲያ እኛ የዚህ ሁሉ በረከት ተጠቃሚዎች ነን? እንጃ። እንዴ! ራሳችን ሰው ሆነን ሳንገኝ እንዴት ነው ፓትርያርክ ለምምረጥ የሚቻለን? በቅዱስ ሲኖዶስ የታወጀውን የህብረት ምህላ አድርሰን ነበር። አሁን ደግሞ የግል፣ የቤተሰብ፣ የማህበራት ወ.ዘ.ተ. ሱባዔና ጸሎት ማስቀደም ለፓትርያርክ ምርጫው የሚበጅ ይመስለኛል።
እግዚአብሔር አምላክ የቸርነቱንና የምህረቱን ሥራ ይሥራልን።
ሠይፈ ገብርኤል
Amen!
Deleteእንዲህ አይነቱ ትይንት፣ እንኳን አማኞችን ኢ-አማንያንን ያስቀናል። በውኑ ይሄን ያዩ የሐይማኖት አባቶቻችን፣ ወደ ነበሩበት አባዚ ቢመለሱ፣ ሸክሙን የሚችሉት አይመስለኝም። ሕሊና ላለው፤ እጅግ ከባድ ነው። አምላክ ልቦና ሰጦን፣ ቤቱን እንድናጸዳ ይርዳን።
ReplyDeleteእግዝአበሔር ይርዳን
ReplyDeleteከሌላዉ ብንማር ምንም ችግር አለዉ...
እግዝአበሔር ይርዳን
ReplyDeleteጥሩ ብለሃል ወንድሜ ለእኛም መልካሙን መሪ እግዚአብሔር የፈቀደውና የወደደው ለቤተክርስቲያን ተቀርቋሪውን ይስጠን፡፡
ReplyDeleteYes Dani Tiru MOya kegorebet Mekorej tiru new...Menfesawe kenat aderobegnal Yegname Betekerstian Endezi Yale Tegebar Bitfetsem DEse Yilegnal Emegnalehum.Dani i have question? We & coptic orthodox have same Kenona & Dogma? pls i want to know zs in detail b/c i have a lot of question.If u can pls give me Answer
ReplyDeleteአንዱ መምህሬ እንዲህ አለ ዲያቆን መሆን ቀላል ነው' መቀሰስ ቀላል ነው 'ጳጳስም መሆን ቀላል ነው 'ፓትርያርክም መሆን ቀላል ነው ከባዱ ክርስቲያን መሆን ነው፡፡ ፓትርያርክ መሆን ቀላል ባይሆን ኖሮ በየ ባለሥልጣናቱ ቢሮ እየገቡ እኔን አስመርጡኝ ባላሉ ነበር፡፡ አሳውን ለማጥፋት ውሃውን ማድረቅ የሚለው የሚሰራው ለቤተክህነት ነው፡፡
ReplyDeleteYou are right we can learn from this alot.We must pressurize current leaders to be more open and honest to God and His people in every wisdom and prayers we have. We can make a difference if we fight for it all the way down. It starts with true reconciliation that heals the wounds of many. It follows having very clear and defined system. That is the vehicle where God picks the right servant to task lead His people. As always thank you for your insights.
ReplyDeleteGebre from Eittsa T/Haymanot
በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ የጉያ እሳት ከሆኑዋት ቤተክርስቲያን ለማደስ ከሚመኙ፣ በዘር በጐሳ ተከፋፍለው ከሚሻኮቱ፣ በአፍቅሮተ ንዋይ ከታወሩ፣ እንዲሁም ከእምነትና ከስርአቱ ውጭ ሆነውም ይህችን ቤተክርቲያን ለማጥፋት ዶግማዋን፣ ቀኖናዋን ትውፊቷን ከመኖር ወደ አለመኖር ለመቀየር ከሚጥሩ ጠብቆን ቤተክርስቲያንን የሚያስከብር፣ የሚያከብር፣ የቤተክርስቲያን ጊጥ ለሆነው ምዕመንም መልከሙን እረኛ እግዚአብሔር ይስጠን፡፡
ReplyDeleteI wonder how close our Holy Fathers in Ethiopia are paying attention to Coptic proceedings in electing new Pope? Moya ke gorebet indeed, great piece Dn. Daniel.
ReplyDeleteየአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጥንካሬ የሚለካው ባጋጠማት ችግር መጠን አይደለም፡፡ በወሰደችው መንፈሳዊ ቆራጥነት የተሞላው መፍትሔ እንጂ
ReplyDeleteEne yemaygebagn---chigrachinin/sitetachinin lemin din new eshruruuu yeminilewu?????
ReplyDeleteYe Eminetachinin sireAt yaguAdel metarem alebet/alebign. le neg yemibal neger aydelm. endihu betsuhuf bich asqemiten chila linilew aygebam.
Abatachin ke wondim, ke ehit, ke beteseb yibeltal. Erasachinin le bego sireAt enalemamid. negen nitsuh honen eniqebelat.
Dn. Daniel,
ReplyDeleteOf course there is a lot that we can learn from our sister churches. However, if you wrote this article in reference to a possible sham election that may happen in our church, I will be so sad that even you, Dn. Daniel, do not really care about the unity of our beloved Orthodox church.
We must learn from the Coptic Church that electing a so called patriarch while there is a legitimate Patriarch alive is indeed a serious mistake that damages the church badly.
In our church, this same mistake was committed 20 years ago leading to division. By the act of God, we now have an opportunity right that mistake and once again unite our church.
We MUST NOT REPEAT a grave mistake by even considering election of another 'patriarch' at this time.
Dani, brothers and sisters, our focus at this time must be how we can unite our church. Divided, we have suffered immensely. All the good points Dani outlined should follow a united and strong Ethiopian Orthodox Church.
Dear Hailu,
DeleteThe real problem of our church is not electing a new patriarch. The real problem is the division between the fathers here in Ethiopia and the fathers abroad. If our fathers are ready to reconcile WITHOUT ANY PRECONDITIONS, the rest is just procedural. I feel that the church even can survive without a patriarch... (this was the case 50 years ago).
So, please please please do not put a precondition to PEACE and UNITY. I don't think His Holiness Abune Merkoriyos would like the seat more than peace and unity. The problem is with us, the people around our fathers.... Think it through before talking about who is the next patriarch!
Egziabher Betekiristiyanachinin and yadirgilin...
Addis
Dear brother or sister,
DeleteDo you really remember how the division came about? If you are really honest, you will not miss this.
I totally agree with you Patriarch Merkorios may not care about the post if it were to come to a personal want or not.
However, the reason we must not have another shame election is not to set the precedence that anyone in the future can depose a sitting patriarch and that remains uncorrected. Then you will have anarchy. That is the concern. Not a personal matter.
The only right thing to do at this moment for the sake of the Church's unity is to have the 4th Patriarch lead a united EOTC.
enanet k areboch gare eyetewedajachuh, demetse eskemestet eyederesachu, muslimochen tekesalachu, man yaweqal yegebetse btekerestiyan b debeq ejochua yihn hizb eyaserabesh endehon. btely ye akababiyain hizb (ye abay meneshaw) say enesu yeserut tenekol mechaim keweqessa ayadenachewem.
ReplyDeleteGod Bless Ethiopia!!!!
Anonymous November 12, 2012 9:17 AM ይህ ጽሁፍ የተጻፈው ለኦርቶዶክሳውያን እንጂ ለእናንተ አይደለመም፡፡ ላስታውስህ የምወደው ጉዳይ ግን ከአረብ ህዝቦች መማር ማለትና እራስን ትቶ ወደ አረባዊነት መቀየር በጣም የተለያዩ ጉዳዬች መሆናቸውን ነው፡፡ ለመረጃ ያህል ግብጽ ክርስቲያን የነበረችው ከእስልምና መፈጠርና ከአረቦች መስፋፋት በፊት ነው፡፡ የሆነው ሆኖ በየትኛውም ቃንቃ (ልሳን) ብትጠቀም ክርስቲያናዊ ትውፊት (በነገርህ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ እራሱ የትውፊት አካል ነው፡፡) እስከሆነ ድረስ ለመማር ዝግጁ ነን፡፡ በተረፈ ወንድሜ ስግው ቃል ወልደ አብ ወልደ ማርያም አስተዋይ ልቦና የይስጥህ፡፡
ReplyDelete‹‹ይህ ሥልጣን ሳይሆን ኃላፊነት ነው፡፡ ዋናዋ ነገር እኔ ሳልሆን ቤተ ክርስቲያኒቱ ናት›› ብለዋል፡
ReplyDeleteአሁን ያለው ምእመን ያንን የመሰለውን የግብጻውያን የምርጫ ሥነ ሥርዓት ያየ ነው፡፡ የዛሬ 21 ዓመት እንደነበረው አይደለም፡፡ አሁን ያለችው ኢትዮጵያም የዛሬ 21 ዓመት እንደነበረችው አይደለችም፡፡ ዛሬ እንኳን የተነገረውና የተሠራው፣ የታሰበውም የሚሰማበት ዘመን ነው፡፡ ስለዚህም ለመንፈስ ቅዱስ ሥራ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት፣ ለምእመናንም መንፈሳዊ ጥንካሬ አባቶች ዋናውን ትኩረት ይሰጡ ዘንድ አደራ አለባቸው፡፡
መልክ ከፈጣሪ ተሰጥቶናል፤ ሞያን ደግሞ ከጎረቤት እንማር፡፡
God bless you.
thank you
I am not a great admirer of Emperor Hayleselase. But the best thing he did for Ethiopia is the Severance of relationship with the Egypt Coptic church so that we can have our own patriarch. What I am seeing in the Era of " Mahibere Kidusan" is to bring back the influence of the Egypt Coptic church with such verve and that is disconcerting. We should be close to God , not to the Egyptians or any other foreign religious entity. Let’s appreciate what we have. We had enough destruction by the Egyptian Copts for centuries and enough is enough. Read history. I know daniel, you are a good historian and I am hoping you will write some day all the atrocities and sabotages done by the Egyptian Copts .. ..including the Der-Sultan controversy.
ReplyDeleteይህ እውነት ከጎረቤት የሚገኝ ትልቅ ትምህርት ነው በኛ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ተከታዮች ዘንድ እርቀ ሰላም ለማምጣትና ልዩነትን በአንድነት ለመተካት ከሀገር ዉስጥ እና ከዉጭ እየተደረገ ያለዉ ጥረት ኮ ለሀገሪቱም ፖለቲካዊ ሰላም ደምበኛ መፍትሄ ነበር
ReplyDeleteጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ መልካም እረኛን እንድመርጥልን ሁላችን ከልባችን መፀለይ አለብን
ReplyDeleteit is good
ReplyDeleteO MY GOD! WE HAVE TO LEARN FROM THIS!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteመደምደሚያህ ደስ አላለኝም። እናስ ከ21 ዓመት በፊት አንተ እንደምትለው ኢትዮጵያ ሌላ ልትሆን ትችላለች ሀይማኖታችን ግን ከ2000 ዓመት በፊት የነበረች ወደፊትም የምትኖርና የማትቀየር ነች። ማንም ምንም ቢያይ አንተን ጨምሮ በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ የሚያሾም ሕግ የሚያስጽፍ ያለ አይመስለኝም። የአጨራረስህና የቃለ ምልልስህ አዝማሚያ እንደዛ ስለመሰለኝ ነው።
ReplyDelete