Tuesday, November 27, 2012

ለቤተ መጻሕፍትዎ


የኢትዮጵያ ታሪክ
(፲፭፭፭፻፺፯–፲፮፻፳፭)
የዐፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል
ትርጉም፡- በዓለሙ ኃይሌ (2005ዓም)
ዋጋ፡- 45 ብር
ይህ የዐፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል ለብዙ ዘመናት በግእዝ ተጽፎ የኖረ ነው፡፡ በርግጥ የውጭ ሰዎች በተለይም አውሮፓውያን በየቋንቋቸው ሲተረጉሙት ኖረዋል፡፡ ‹በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን አጣሁት› ሆነና አማርኛ አንባቢዎች ግን አሁን ማግኘታቸው ነው፡፡ በዚህም አቶ ዓለሙ ኃይሌ ይመሰገናሉ፡፡ ከዚህ በፊት ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ተርጉመዋቸው በመሥሪያ ቤቱ በኩል የታተሙላቸው ሁለት ዜና መዋዕሎች አሏቸው፡፡ የዐፄ ሠርጸ ድንግል እና የዐፄ ገላውዴዎስ ዜና መዋዕሎች፡፡ በእነዚህ ቀደምት ሁለት መጽሐፎቻቸውም ሆኑ በሚገኙባቸው መድረኮች ሁሉ ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍና ስለ ጥንታውያን ዕውቀቶች በተቆርቋሪነት መንፈስ ሲገልጡ ታገኟቸዋላችሁ፡፡ ይህ ቁጭታቸውም ሳይሆን አይቀርም ይህንን የሱስንዮስን ዜና መዋዕል ያስገኘው፡፡
የሱስንዮስ ዜና መዋዕል በዋናነት አራት ነገሮችን የያዘ ነው፡፡
 የመጀመርያው የመንግሥቱ መቀመጫ በግራኝ አሕመድ ወረራና በመካከለኛው ዘመን መጨረሻ በተከሰተው የኦሮሞ ሕዝብ ፍልሰት ምክንያት ወደ ጎንደር ካመራ በኋላ የነበረውን የሥልጣን ትግል ያሳየናል፡፡ የጎንደር ሥርወ መንግሥት መሥራች በሆነው በሠርጸ ድንግል ልጆችና ወራሾች መካከል ከፍተኛ የሆነ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሃይማኖታዊና ወታደራዊ ትግግሎች ነበሩ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው ሱስንዮስ የ‹አማራ› እና የ‹ኦሮሞ›ን ጦር አስተባብሮ የጎንደርን መንበር ሊቆናጠጥ የበቃው፡፡
በሁለተኛነት የምናየው የኢትዮጵያውያንን የውሕደትና የቅልቅል ታሪክ ነው፡፡ በአንድ ጎኑ ከኦሮሞ የሚወለደው ሱስንዮስ ያደገውና በሕይወት የተረፈው በኦሮሞዎች ተማርኮ በኦሮሞ ባህል መሠረት ነው፡፡ በኋላም ጎንደር ድረስ ዘምቶ መንበር ለመያዝ የበቃው ኦሮሞንና አማራን አስተባብሮ አሰልፎ ነው፡፡ በዚያ ዘመን ዋናው ነገር ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ነገር ስለሆነ አማራና ኦሮሞ አንድ ሆኖ ጎንደርን ሲወጋ፣ እንደገና አማራና ኦሮሞ አንድ ሆኖ ኦሮሞን ሲወጋ እናየዋለን፡፡ ጦርነቱ የፖለቲካና የጥቅም እንጂ የዘር አልነበረም፡፡
በደቡቡ ክፍል ከዳሞት እስከ ግንደ በረት የነበሩት አማሮች ኦሮሞ ሆነው እንደቀሩት ሁሉ ሱስንዮስን ተከትለውም ሆነ በወረራ አሸንፈው ጎጃም፣ ጎንደር፣ ትግራይና ኤርትራ የገቡት ኦሮሞዎችም አማሮችና ትግሮች ሆነው ቀርተዋል፡፡ እንዲያውም ሱስንዮስ ከተወቀሰበት ምክንያቶች አንዱ ከሸዋ የተከተሉትን ኦሮሞዎች የቤተ ክርስቲያንን ሰፊ መሬት ሳይቀር እየወሰደ በጎጃምና በጎንደር ስላሠፈራቸው ነበር፡፡
በጎንደርና በላስታ የነበሩት አማሮች በመንግሥቱ ላይ ሲሸፍቱ ጎንደር ሸፈተ፣ ላስታ ሸፈተ እያለ ኦሮሞና አማራ አንድ ሆኖ እንደሚወጋቸው ሁሉ፣ በደቡብ የነበሩት ኦሮሞዎች ሲገፉበትና ሲሸፍቱትም ኦሮሞ ሸፈተ እያለ ኦሮሞና አማራ አንድ ሆኖ ነበር የሚዋጋው፡፡
ይህ ከሠርጸ ድንግል ዘመን የቀጠለው የመስተጋበር ሂደት ነው የዛሬዋን ኢትዮጵያ የፈጠራት፡፡ ለዚህም ነው ታዋቂው ሰሎሞን ዴሬሳ ስለ ማንነቱ ሲጠየቅ ‹በቅድመ አያቴ ደጅ ማን እንደሄደ አላውቅም› የሚለው፡፡ የዐፄ ሠርጸ ድንግልን ዜና መዋዕል ስናነበው ኦሮሞዎች እስከ ኤርትራ ከሠርጸ ድንግል ጋር ዘምተው ቱርክን ከኤርትራ ለማባረር መሥዋዕትነት ሲከፍሉና ከፊሎቹም እዚያው ኤርትራና ትግራይ ተሸመውና ተሠርተው ሲቀሩ እናያለን፡፡
እነዚህን ዜና መዋዕሎች የሚያነብ ሰው ዛሬ የምንወዛገብባቸው ማንነቶች ራሳችን ለፖለቲካ እንዲያመቹን የፈጠርናቸው እንጂ የተሠራንባቸው አለመሆናቸውን ያያል፡፡ የሱስንዮስን ዜና መዋዕል ከምዕራፍ 23 እስከ 100 ያለውን የጻፉት አዛዥ ተክለ ሥላሴ (አዛዥ ጢኖ የተባሉት የኦሮሞ ተወላጅ) ታሪኩን ሲጽፉ ኢትዮጵያዊነት እንጂ የዘር ስሜት አይታይባቸውም፡፡
ሦስተኛው ጉዳይ ደግሞ ኢትዮጵያን ከግራኝ ወረራ በኋላ ሲያምሳት የነበረው የፖርቹጋል ካቶሊኮች ጉዳይ አጀማመሩንና አጨራረሱን በመጽሐፉ የምናገኝ መሆናችን ነው፡፡ በርግጥ ጸሐፊዎቹ የንጉሡ ዜና መዋዕል ጸሐፊዎች በመሆናቸው ለዚህ ጉዳይ እምብዛም ትኩረት አልሰጡትም፡፡ ልክ በዐምደ ጽዮን ዜና መዋዕል ላይ ከአበው ጋር የነበረውን ግጭት እንደማናየው ሁሉ፡፡ ነገር ግን አልፎ አልፎ ለነገሮች ዝርዝር መረጃ ይሰጡናል፡፡
በሱስንዮስ ዜና መዋዕል ላይ በኢትዮጵያ ጥናት ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችም አሉ፡፡ በአኩስም ያከበሩትና በውጭ ሰዎች ሳይቀር እጅግ የተደነቀው ሥርዓተ ንግሣቸው፡፡ አንዳንድ ማኅበረሰቦች ከሕዝቡ የተለየ ምግብ መብላታቸው ወደ ክርስትና እንዳይመጡ እንደማይከለክላቸው ማወጃቸው፤ እንደገና ራእየ ዮሐንስን ከላቲን ወደ ግእዝ ማስተርጎማቸው፤ የባርያ ንግድን ለማስቆም ያደረጉት ትግል፤ ሀገሪቱን ለማዘመን ያደረጉት ጥረት፤ በዚሁ ዜና መዋዕል ውስጥ ይታያል፡፡
መጽሐፉን የሚያነብ ሰው የዚያን ዘመን ባሕልና ቦታ ዛሬ ባለው ሁኔታ እንዲረዳው ለማድረግ ተርጓሚው በግርጌ ማስተዋሻ ማብራርያ በመስጠት ያግዙናል፡፡ በመግቢያ ጽሑፋቸውም አጠቃላዩን ሁኔታ ከሀገሪቱ ታሪክ አንጻር እንድንገነዘበው ሰፊ ሐተታ ያቀርቡልናል፡፡
አቶ ዓለሙ ኃይሌ ለሰጡን ስጦታ እግዜር ይስጥልን እያልን፤ ዕድሜ ሰጥቶዎት ሌሎችንም ለመተርጎም እንዲችሉ እንጸልያለን፡፡
መልካም ንባብ፡፡
ኬፕ ታውን ደቡብ አፍሪካ

20 comments:

 1. እድሜ ይስጥልን!!!!

  ReplyDelete
 2. «ጉድ በል ጎንደር!!» ይቺ እንደ ሱማሌ ቁጥቛጦ አለፍ አለፍ ብላ የበቀለች ኩርንችት ጠጉሬ ...አሄሄ! ሁልዜ ትገርመኝ ነበር። ጓደኞቸ በሙላ ሉጫ ለስላሳ ጠጉር ሲኖራቸው፣ የኔይቱ ጭፍግ ያለች ናት። እድሜ ለሱሴኖስ አልከው? እድሜ ለሱ ታሪክ፣ ዘሬን ላውቅ ነው መሰል? ጉድ እኮ ነው የዘር ነገር? እኒያ በአንድ አጋጣሚ ሁሉን ነገር ተቆጣጥረው ያሉ ቡድኖች እኮ ጉድ አፈሉ ዲያቆን ዳኒ! አሁን ይቺ ፍርንችት ዬቃ ማጠቢያ ሽቦ ጠጉሬ አርፋ ብትቀመጥበት ምን አለበት ጃል!! ጉድ በል ጎንደር አለ የጎጃም ሰው። እንዴው ዝም ይሻላል እኮ ዲቆን ዳኔል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይዞህ ቢራቱ! ጠጉርህ ኩርንችት ብቶን የግዴታ ዘርህ ሌላ ነው ማለት አይደለም ቅቅቅ! የዲያቆን ዳኔል ጥፋት ሳይሆን አይቀርም። የሱሴኖስ ዜና ማዋል በቡዙ ሞቶ ገጦች የተጣፈ ነው፣ ብዙ ብዙ ነገር ሚቃኝና ብዙ ታሪክ ያለበት ነው። ዲያቆን ዳኒ ዘሯ ላይ ስላተኮረ ምናልባት ዜና መዋሉ ግማሽ በግማሽ በዚ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን መስሎህ ሊኾን ይችላል። ግን አይደለም። መጣፉ ብዙ ጊዜውን እሚያጠፋው ስለተለያዩ ከተሞች፣ አካባቢዎች፣ ሹሞች ወዘተ ፓለቲካዊ ውጣ ውረድ በማተት ነው። ያው የዲያቆን ዳኔል የትኩረት አባዜ ዘሯ ላይ ትለሆነ፣ መጣፉ ስለዘር ብቻ እሚያዎራ መስሏል እንጂ ቅቅቅቅ

   Delete
  2. ሚሚ ሸበላ ፡ ስምሽ ማንም ሊሆን ይችላል፡ ከቻልሽ የሚነበብ ነገር ንገሪን እንጅ፡፡ አፍሽ እንዳመጣዉ አትቀባጥሪ፡ወገኛ ባንች ቤት መፅሐፉ እንዳይነበብ ማድረግሽ ነዉ፡፡

   Delete
  3. Thank you.... ሀሁሐሑ!

   Delete
 3. እግዚአብሔር ይስጥልን

  ReplyDelete
 4. በጣም ፈጠንክ እንዳትለኝ ዲ.ዳንኤል ባለፈው አመት ቢያርፉም ስለ ቀሲስ/አባ ላዕከማርያም ያልከውን ነገር አላስታውስም...ያልከው ነገር ካለ ደግሞ እባክ ሊንኩን ከዚህ ኮሜንት ስር አታች አድርግልኝ፡፡ አባ ላዕከማርያም ማለት ለመዠመሪያ ጊዜ ስንክሳርንና ግብረ ህማማትን ከግዕዝ ወደ አማርኛ ቋንቋ የተረጎሙ ሊቅ ነበሩ፡፡

  ReplyDelete
 5. EBAKOTIN MESIHFUN YET LEMEGIZAT YICHALAL ?
  Ameseginalehu

  ReplyDelete
 6. ሲመሩ ነበር ሲያስገብሩ?

  በዘመናችን ከገጠሙን ፈተናዎች መካከል የአገር ታሪክ የቱ ነው የሚለው አንዱ ሆኗል:: መጽሐፉ ደገኛም ይሁን ጠንቀኛ በእሳት የተፈተነ የሚሆነው የሀያስያን ብእር ሲነካው ነውና በየዘርፉ ቢታይ እመክራለሁ:: የዲያቆን ዳንኤል ብእር ብቻ በቂ አይመስለኝም:: እስኪ ከርእሱ እንጀምርና ጥቅል ሀሳቦችን እንደወረዱ እናዝንምበት:: መጀመሪያ የአፄው ታሪክ የአገር ታሪክ ነው ብሎ ማቅረብን ይመለከታል:: በጥንታዊው ቅጅ ወይም በመገኛ ቋንቋው ዜና መዋዕል ብሎ ያቀረበው በመሆ ኑ በዚያው መንገድ ቢያስነብቡን ደግ አልነበረም ወይ? ያልነበረ ሀሳብንስ በትርጉም ውስጥ ማካተትስ ተገቢነት አለው?

  የአፄው ታሪክንስ የአገር ታሪክ ነው ብሎ ማቅረብን እንዴት ታዩታላችሁ?

  ቀላል ምሳሌ የሀገራችን መልክዐ ምድር ባለፉት ዘመናት አሁን ካለው በቆዳ ስፋት የሚልቅ ነበር:: በትረ መንግሥቱ ግን እንደሚታወቀው ባለ አጭር ሞገድ ብቻ ነበርና ከሆነ ርቀት በኋላ መውረድ ተስኖት እናያለን:: በመሆኑም እኩል አይነት እድገት በአገሪቱ ማየት አልተቻለም:: አንዳንዶቹ እንደውም ገና አዲስ የተገኙ ምድሮች ነው የሚመስሉት:: በዚህ ምክንያትም ነገሥታት የሚያስገብሩ ባላንዳች ኃይል እንጂ መሪዎች እንኳ ተደርገው የማይታሰቡበት አካባቢ ተፈጥሯል:: ሱስንዮስ በግላቸው መልካም መሪ ሊሆኑ ይችላሉ:: ከላይ ባነሳነው መልክዐ ምድር ላይ ያስገበሩዋቸውን አካባቢዎች ካልሆነ በቀር የሀገር መሪ ነበሩ? ዜና መዋዕላቸው ምን ይዟል? ከሆነ የታል አሻራቸው? የበጎም የክፉም የታል የወጡት ዳገት የወረዱት ቁልቁለት የተሻገሩት ወንዝ የሰሩት ግድብ ያነጹት ሕንጻ የት ነው የሚገኘው? ወይ እኛ የኢትዮጵያ አልነበርንም አልያም እነርሱ ኢትዮጵያን አልመሩም:: ለነፍስ ያነጹት መቅደስ እንኳ የታለ?

  ሌላው የመጽሐፉን ርቱአዊነት እንዴት ታየዋለህ የሚል ነው? አብዛኞቹ ዜና መዋዕሎች በወገናዊነት ባለባቸው ቀርነትና በርግጥም ጥንታዊያን ቅጂዎች ናቸው ወይ በሚል ውይይት የሚካሄድባቸው እንደሆነ ይታወቃል:: በዚህ ጉዳይ አንድ ነጥብ ብቻ ነክተህ ማለፍህን አልወደድኩትም:: ያንተ አስተያየት መደቡ ከየት ነው? አሕጽሮት ነው? ማስታወቂያ ነው? ሂስ ነው? መለየት ያስቸግራል:: ያለህን ሰጥተህ ያስተነፈስከኝ አንተው በመሆን ግን ሳላመሰግንህ አላልፉም::
  በተጨማሪም የትርጉም ሥራውን ፋይዳ ስትዳስስ አሁን ያለውን የብሔርተኝነት ጽንሰ ሀሳብ ነቁረህ አልፈሀል:: ዘመኑ ግን ለብሔርተኝነት ቦታ ሰጥተን ባይሆን አንዳንድ አካሄዶችን የምንተችበት ቢሆን የሚመረጥ ይመስለኛል:: ዛሬ ብሄር በሚል መጠሪያ እንጥራው እንጂ የመደብ ትግሎች ነበሩ:: ይኖራሉ:: ተፍጥሮአዊ ነው:: በኛ ሀገር የወረደ መቅሰፍትም አይደለም:: በየትም ዓለም አለ:: እንደውም አያያዙን ካወቅንበት የኛ የመከባበር፣ የመተባበርና የሰላም ተምሳሌት መሆን የሚችልበት እድል አለ::

  ትናት አማራ ፣ ትግሬም ፣ ኦሮሞ, , , ነበረ:: ወደፊትም ይኖራል:: መሰረታዊ እንዴት ይኑር ጥያቄ ነው:: በማንነቱ አምኖ ሳይሸማቀቅና ሳያፍር፣ እንዲለውጥ ተገዶ ሳይሆን ተከብሮ ፣ከሌሎችም ጋር ተከባብሮና ፈቅዶ የሚኖርበት ሥርዓት ሰርቶ ከሆነ ችግሩ የቱ ጋር ነው? የብሔር ነገር ሲነሳ ዛሬ ተራ ጉዳይ ሊሆን አይችልም:: በሀሳብ ልዩነት የሚያደርገውን ትግል ያህል በማንነቱ ላይ የሚመጣን ጭቆና እንቢኝ ቢል የቱ ጋር ነው ስህተቱ? በአማርነቴም መጣ በኢትዮጵያዊነቴ ምላሼ እኩል ነው:: ልዩነቱ ኪሴ ሲዘረፍና ካዝናዬ ሲዘረፍ ነው:: ወደኋላ ከዞርን ብዙ ማሳያዎችም ማንሳት ይቻላል:: ታሪካችን መቼም ከውጪው እኩል የርስ በርስ ጦርነት ታሪክ መሆኑ አይረሳም:: ያ ታሪክ ሆኖ አልፏል አንድ ቀን የውሾን ነገር ያነሳ ብለን እስክንማማል በክፉም በደግም መነሳቱ አይቀርም:: እላለሁ የናንተን በሉና

  ReplyDelete
  Replies
  1. ‹‹የበጎም የክፉም የታል የወጡት ዳገት የወረዱት ቁልቁለት የተሻገሩት ወንዝ የሰሩት ግድብ ያነጹት ሕንጻ የት ነው የሚገኘው? ›› በመጀመሪያ ለአንተ የኢትዬጵያዊነት መገለጫ የዘረዘርካቸዉ ነገሮች ከሆኑ ግሩም ነዉ! ከአድሎ ያልፀዳ አተያይ! እያወዳደርከዉ ያለዉ ከኢህአዲግ ጋር ለመሆኑ ጥርጥር የለዉም፡፡ተዉ እንጅ ጃል አስተያየትና ሂስ ከመስጠትህ በፊት ወንድማችን የጠቀሰዉን መፅሀፍ ነበብ ብታደርገዉ መልካም ነዉ፡፡በግድ እኮ ኢትዬጵያዊነታችንን እንድንረሳና በጎጥ እንድንከፋፈልና አንድነታችን እንዲደረመስ እየተደረግን ነዉ፡፡አንድ ሆነን ሳለ እንደተለያየን፡ እግዚያብሔር ወደ ቀድሞ ክብራችንና አንድነታችን ይመልሰን፡፡

   Delete
 7. yezer abazie yemetew le poletica meteqemianet new enji natural neger endalihone tazebachihu???? who i'm I??? Goder siletewelediku becha amara??? Bale biweled Oromo lihon? beteley yeweqitu poletikegnoch yihinin book yanbibut elalew!!!

  ReplyDelete
 8. where we get the book

  ReplyDelete
 9. የአንድነት ውትወታ (ጥታቄ) ለምንድን ነው የአማሮችን የተለየ ትኩረት ሳቢ የሆነው? የኛን ያህል ሌሎችን ሲያንገበግባቸው አይቼ አላውቅም:: እንደው ሚስጥሩ ምን ይሆን?

  ReplyDelete
 10. yenegesetat tarik eko yehager tarik new, bergrt begeleseboch lay liyatekur yechelale gen geleseboch ketreraw geleseb yeteleyouna yenegesu nachew. begeleseboch tarik wuset yager poleticawi, economiyawi, bahelawi gesetawoch gezefew yetayalu, yahume benegesetate taric wuset. yager taric malet eresu " ye Ethiopia..." menamen belo mejemer yelebetem eko....

  ReplyDelete
 11. ስለ አንድነት ሲነሳ ኦሮሞዎች ትኩረት የሚስቡበት ዋናው ምክንያት፤የእኛ አባቶች ከወራሪና ከጠላት ሲፋለሙ የእነሱ ደግሞ ለከብቶች የግጦሽ መሬትና ለም ቦታ በማሰስ ላይ ነበሩ፡እናም ታሪክ ሲሰራ እነሱ ስላልነበሩ አሁን ስለ ታሪክና አንድነት ሲነሳ እነሱን እንደማይጨምር ስለሚሰማቸው ቶሎ ስለሚያኮርፉ ነው፡፡ቅንነቱና ችሎታው ካለ አሁንም ለአገራችን ታሪክ መስራትና ቀና ብሎ መሄድ ይቻል ነበር፡፡

  ReplyDelete