Monday, November 26, 2012

ወርቅ የማይገዛው አገልግሎት

photo from (http://www.africaboundadventures.com)

እነሆ ሻንጣዬን እየገፋሁ ወደ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመጓዝ ላይ ነኝ፡፡ ለመንገደኛ መግቢያ ከተዘጋጁት በሮች ሁለቱ ብቻ ይሠሩ ስለነበር የገቢ መንገደኛው ሰልፍ አስፓልቱን አቋርጦ ወደ ሣሩ ደርሷል፡፡ ምስጋና በፍተሻው ላይ ለተሠማሩት ባለሞያዎች ይድረሳቸውና ጥንቃቄው እንደተጠበቀ ሆኖ እንግዶችን በፍጥነት ለማስተናገድ የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጉ ነበር፡፡
ተፈተሽንና ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ መስኮት ደረስን፡፡ ትኬታችንን አሳየንና ሻንጣዎቻችን አስረከብን፡፡ በመስኮቱ ጀርባ ለምታገለግለው የአየር መንገዱ ባለሞያ ወቅቱ የገና ጾም ወቅት ስለሆነ የጾም ምግብ ማስመዝገባችንን ገለጽንላት፡፡ እርሷም መልከት አለችና ‹‹ምንም ችግር የለውም›› አለችን፡፡ ‹‹የጾም ምግብ አለ ማለትሽ ነው›› ስንል የማረጋገጫ ጥያቄ አቀረብን፡፡ ‹‹ችግር የለውም አታስቡ›› አለችን ፈገግ ብላ፡፡
አንድ የስድስት ኪሎ ወዳጄ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ እያለን እንዲህ የሚል ግጥም አቅርቦ ነበር
አንድ ችግር አለ የችግር ካንሠር
‹ምንም ችግር የለም› የሚሉት ችግር
አንድ ሌላ ወዳጄም ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ‹ምንም ችግር የለም› በሚለውና ‹ችግር አለ› በሚለው መካከል ያለው ልዩነት የቃላት ብቻ ነው›› ብሎኝ ነበር፡፡ 
የኢሚግሬሽንን መሥመር አልፈን ወደ ውስጥ ዘለቅን፡፡ የአውሮፕላኑ የመነሻ ሰዓት ደረሰና ወደ ውስጡ ዘለቅን፡፡ እዚያም ተቀምጠን የሚነሣበትን ጊዜ በጉጉት መጠበቅ ጀመርን፡፡ የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ይወጣሉ ይገባሉ፡፡ ወዲህ ይመጣሉ ወዲያ ይሄዳሉ፡፡ የመነሻ ሰዓቱ እያለፈ ነው፡፡ ማንም ግን ምን እየሆነ እንደሆነ አይገልጥላችሁም፡፡ ዝም ብላችሁ እንድታስቡ፣ ከቻላችሁም እንድትጠነቁሉ ተፈርዶባችኋል፡፡ ዝርዝር ምክንያታቸውን ባይገልጡልን እንኳን ‹በአንዳንድ ምክንያቶች አውሮፕላኑ ጥቂት ይዘገያል› ማለት የእናት ነበር፡፡ ‹ፓይለቱም ዝም፣ ሆስተሱም ዝም›
ወደ አርባ ደቂቃ ያህል ተቀመጥን፡፡ ለምን እንደተቀመጥን፤ ከዚህ በኋስ ምን እንደሚደረግ የሚነግረን አልነበረም፡፡ በመጨረሻ ‹በመዘግየታችን ይቅርታ› አለና የአውሮፕላን አብራሪው ነገረን፡፡ ‹ዘግይቶ የደረሰን ዜና› አለ የኢትዮጵያ ሬድዮ፡፡
እንደወጉና እንደ ደንቡማ አውሮፕላኑ የሚዘገይ ከሆነ ከወዲያ ማዶ ቤተሰቦቻቸው ለሚጠብቋቸው አካላት መናገር ይቻል ዘንድ ምን ያህል እንደሚዘገይ፣ ለምን እንደሚዘገይና ምን ማድረግም እንደሚገባን አስቀድሞ መናገር ይገባ ነበረ፡፡ ደግሞ ደግነት ከተጨመረበት ሰው ያለ ምክንያት ሲቀመጥ ይጨንቀዋልና ቢያንስ የእግዜር ውኃ እያዞሩ ማደል ይገባ ነበረ፡፡ ‹ጽድቁ ቀርቶ› አለች አክስቴ፡፡
አውሮፕላኑ እንደምንም ተነሣ፡፡ ብዙዎቻችን ከዚያ በኋላ በረራ የምንቀጥልባቸው መሥመሮች ሳይሄዱ ይጠብቁናል? ካልጠበቁን ምን እናደርጋለን? እያልን እንወያይ ነበር፡፡ አንዳንዶች ጠንከር ብለው ጆሃንስበርግ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ ችግሩን እንደሚፈታላቸውና በመዘግየቱ ለሚፈጠረው መሰናክልም አንዳች ነገር እንደሚያደርግ እምነታቸውን በጽናት ይገልጡ ነበር፡፡ ‹ያመኑት ፈረስ ጣለ በደንደስ› እንዳይሆን እንጂ፡፡
ከወደ ኋላችን የበረራ አስተናጋጆቹ ምግብ እያደሉ መጡ፡፡ እኛጋ ሲደርሱ ‹የጾም ምግብ አዝዘን ነበር› አልናቸው፡፡ ቦርዲንግ ፓሳችንን ተቀበሉንና ተጓዙ፡፡ ከዚያም ተመልሰው በኛ ቁጥርና ስም የተመዘገበ ምግብ እንደሌለ ገለጡልን፡፡ ‹ምንም ችግር የለም የሚሉት ችግር› ማለት ይሄኔ ነው፡፡ ትኬት በቆረጥንበት ቦታ ይህንኑ መግለጣችንን፤ ቦርዲንግ ፓስ ስንወስድም ማሳወቃችንን ሁለቱም ቦታ ምንም ችግር እንደሌለውና እንደተስተካከለ እንደተገለጠልን ነገርናቸው፡፡ ግን እነርሱ ምን ያድርጉ፡፡
ለባለቤቴ በአስተናጋጆቹ ፈቃድ እንደምንም ተፈልጎ የሚበላ ነገር ተገኘ፡፡ እኔ ግን ስምንተኛውን የአየር መንገድ ጾም እንድጾም ተፈረደብኝ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኛ ነኝ፡፡ ያውም የሼባ ማይልስ የወርቅ አባል፡፡ በአየር መንገዱ ስጓዝ ወርቅ የማይገዛቸው ብዙ ነገሮች ያጋጥሙኛል፡፡ አንዱ የጾም ምግብ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ አስመዘ ግባለሁ፡፡ ለምን ቦርዲንግ ፓስ ላይ አትጽፉልኝም? ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ መሬት ላይ ያሉት የትኬት ቢሮዎች ግን ሁልጊዜም የሚሉኝ ‹ችግር የለም›› ነው፡፡ በተለይ መነሻዬ አዲስ አበባ ከሆነ፡፡
እንዲያውም በዚህ ጉዳይ ላይ አሜሪካ ቨርጂንያ ያለው የትኬት ቢሮ የተሻለ ሥራ ሲሠራ አይቼዋለሁ፡፡ በኢትዮጵያ በታወቁ ታላላቅ አጽዋማት ጊዜ የጾም ምግብ እንዲጫን በማድረግና በተለይም ለሽማግሌዎችና እናቶች በማቅረብ ሲያገለግሉ አይቻለሁ፡፡ አዲስ አበባ ግን ‹ችግር የለም›፡፡
እኔ ና ወዳጆቼ ይህን የአየር መንገድ ጾም ‹ስምንተኛው ጾም› እንለዋለን፡፡ ከኅዳር 15 እስከ ታኅሣሥ 29፣ ከዘወረደ እስከ ፋሲካ የሚጾም አይደለም፡፡ ከአዲስ አበባ እስከ ቀጣዩ የበረራ መዳረሻ የሚጾም ጾም ነው ‹ስምንተኛው ጾም›፡፡ የዐዋጅም የፈቃድም፣ የቀኖናም አይደለም፤ የስንፍና ጾም ነው፡፡
በ2ኛው መክዘ ተነሥቶ የነበረው መርቅያን የተባለው መናፍቅ ቅዳሜ መጾም አለባት የሚል ትምህርት ነበረው፡፡ ታድያ የአንድ የሀገራችን ባለቅኔ ቅዳሜ ቀን የሚበላው እጥቶ በተቀኘው ቅኔ
‹ቅዳሜን እንደ ረቡዕ ቀን አድርጌ ጾምኳት
መርቅያን በዐመጽ ነው እኔ ግን በማጣት›
ብሎ የተቀኘው እንዲህ ያለ ነገር ገጥሞት ነው ለካ፡፡ እነሆ በስምንተኛው የአየር መንገዳችን ጾም በዕለተ እሑድ ጦሜን ዋልኩ እላችኋለሁ፡፡ የሀገሬ ሰው ‹በሰንበት ጦም አይዋልም ቅጠልም ቢሆን መቅመስ ያስፈልጋል› ይላል፡፡ በአየር ላይ ምን ቅጠል ይገኛል፡፡ ቅጠል ቢኖርም ሰላምታ መጽሔት ላይ ብቻ ነው፡፡
የአምስት ሰዓቱ መንገድ አለቀና ጆሀንስበርግ ደረስን፡፡ እዚያ ስንወርድ አንድ ሰዓት ያህል ዘግይተን ነበር፡፡ በመዘግየቱ ሊረዳን የመጣ አንድም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰው አልነበረም፡፡ እኔ ብዙ ጊዜ ወደ አሜሪካ በርሬያለሁ፡፡ የበረራ መዘግየት ሲፈጠር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች እንደ ጉንዳን ሠራዊት በሚያስደንቅ ፍጥነት ችግሩን ለመፍታት ላይና ታች ሲሉ ነው የምታዩዋቸው፡፡ ያውም ምሳ ጋብዘው፣ ዕቃ ተሸክመው፡፡ እዚህ ያሉት ግን ‹በቅተው› ተሠውረዋል፡፡
ዕቃችንን ተቀብለን ወደ ኬፕታውን የሚወስደውን አውሮፕላን ፍለጋ ወደ ብሪትሽ አየር መንገድ መስኮት ሄድን፡፡ ‹መድረስ ከነበረባችሁ ጊዜ እጅግ ዘግይታችኋል፤ ይህን ችግር መፍታት ያለበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነውና ወደ እነርሱ ሂዱ›› የሚል ምላሽ ሰጡን፡፡ ከዚያም የኢትዮጵያ አየር መንገድ መስኮት ያለበትን ቦታ ፍለጋ ያዝን፡፡ በአውሮፕላን ማረፊያው በሚገኙ ሠራተኞች ተባባሪነት የኢትዮጵያ አየር መንገድን መስኮት አገኘነው፡፡
በመስኮቱ ጀርባ አንዲት (ምናልባት ደቡብ አፍሪካዊት) ሠራተኛ ወንበሯ ላይ ለጠጥ ብላ፤ ሌላዋ ደግሞ የሻንጣ መመዘኛው ላይ ተቀምጣ እያወጉ አገኘናቸው፡፡ ያጋጠመንንም ችግር ነገርናቸው፡፡ እነርሱ ምንም ሊረዱን እንደማይችሉ፣ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ ብንሄድ መልካም መሆኑን ምክር ሰጡን፡፡ ‹ወይ ምክር መቀበል፣ ወይ ምክር መስማት› አሉ መንግሥቱ ለማ፡፡ እኛ ምን አማራጭ አለን፤ ቢሮውን ፍልጋ ከመንከራተት በቀር፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቢሮ ከፍለጋ በኋላ ስናገኘው ዝግ ነው፡፡ ምን እናድርግ? አሁን ችግሩን ለመፍታት በመንከራተት ሌላ አንድ ሰዓት ጨምረናል፡፡ በአካባቢው ያሉ ሌሎች ሠራተኞች ‹ብዙ ጊዜ ውስጥ ሆነው ስለሚዘጉት አንኳኩ› አሉንና በመስኮቱ በኩል ማንኳኳት ቀጠልን፡፡ እዚህ ግን ‹አንኳኩ ይከፈትላችኋል› አይሠራም፡፡ ችግሩን የፈጠረው አየር መንገድ ችግሩን ለችግረኞቹ አሸክሞ በሩን ዘግቶ ሄዷል፡፡ አዲስ አበባ አንድ ሽሮ ቤት ውስጥ ‹ቤቷን ዘግታ የምትዘፍን› የሚባል ሽሮ ማየቴን አስታወስኩ፡፡
አሁን የችግሩ ሰለባዎች ከሃያ በላይ ሆነናል፡፡ ሁሉም ፊቱ በንዴት ጦፏል፡፡ ማዘግየታቸው ሳያንስ ቢሯቸውን ቆልፈው መጥፋታቸው፤ ሌሎቹ አየር መንገዶች ችግራችን ለመፍታት ከኛ ጋር ላይ ታች ሲሉ የችግሩ መነሻ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ‹ከመረቁ አውጡልኝ፣ ከሥጋው ጦመኛ ነኝ›  ማለቱ ያላናደደው አልነበረም፡፡ አንዳንዶች ሰማያዊ፣ ሌሎች ብርማ ሌሎችም ወርቅማ የሆነውን የአየር መንገዱን የደንበኛነት ካርድ ጥቅም በመጠየቅ ላይ ነበሩ፡፡ እንዲያውም አንድ መንገደኛ ‹ ወርቅ ይህን ችግር ያለበት አገልግሎት ከሆነ የሚገዛው፤ ወርቅ ምን ጥቅም አለው?›› ሲል ነበር የጠየቀው፡፡
ተመልሰን ወደ ብሪቲሽ አየር መንገድ ቢሮ መጣን፡፡ እዚያ ያገኘናቸው ኃላፊ ‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእነርሱ ጋር ይህን መሰሉን ነገር ለመሥራት የነበረው ውል ማለቁን፡፡ ራሳቸው ነገሩን ለማከናወን መወሰናቸውን፤ ነገር ግን ችግሩ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን› በምሬት ይናገሩ ነበር፡፡ አሁንም አሁንም ከኃላፊዎቻቸውና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ ጋር ይደዋወላሉ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስልክ ግን ሠራተኞቹ አለመኖራቸውን ነው የሚናገረው፡፡
ለሁለት ሰዓታት ያህል ከተጉላላን በኋላ የብሪቲሽ አየር መንገድ ሰዎች በሦስት በረራ ሊያስተናግዱን ወሰኑ፡፡ በ11 ሰዓት፣ በ12 ሰዓትና በ1 ሰዓት በረራዎች፡፡ ከሃያ የሚበልጡት የበረራ ተስተጓጓዮች እንደ ዕድል ፈንታቸው እየተስተናገዱ ወደ ቦርዲንግ ፓስ መቀበያዎች ማምራት ጀመሩ፡፡
ከሁለት ሰዓት በረራ በኋላ ኬፕታውን ስንደርስ የአየር መንገድ ስምንተኛው ጾም ከ12 ሰዓት በላይ ሆኖት ነበር፡፡ ሊቀበሉን የተዘጋጁት ሄደው፡፡ እንደገና እነርሱን ለመጥራት ወደ አንድ ሰዓት ጠብቀን፤ ለደቡብ አፍሪካውያን የአውቶቡስ ሾፌሮችም ‹የዘገየነው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ችግር ምክንያት ነው› ብለን አየር መንገዳችንን ለማማት አፍረን የቆጥ የባጡን በመቀባጠር ማረፊያችን ደረስን፡፡
እኛ እንደ እሥራኤል ጉዞ ተሰቃይተን ስንደርስ ምናልባትም የጆሃንስበርግ የአየር መንገዱ ቢሮ ‹የዛሬው በረራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል›› ብሎ ሪፖርቱን እየጻፈ ይሆናል፡፡
ኬፕ ታውን፣ ደቡብ አፍሪካ

48 comments:

 1. This is a service of GOLDEN air line .....

  ReplyDelete
 2. ዳኒ ይህ የመጀመሪያ አይደለም:: የተከበሩ ግርማ ዋቄ ከለቀቁ ወዲህ አየር መንገዳችን ከደረጃዋ በስንት እጥፍ ወርዳለች:: የሚገርመው እኮ አሁንም እንዲህ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ የበረራ ዋጋው ከKLM እና Lufthansa ጋር እኩል ነው:: ግብጽና ቱርክ በጣም የተሻለ አገልግሎት እየሰጡ ዋጋቸው ግን ከኛ በእጥፍ ይቀንሳሉ:: የተከበሩ ግርማ ዋቄ በነበሩበት ወቅት በአለም ታዋቂ ከሚባሉት አየር መንገዶች በአገልግሎትም በዋጋም እኩል ነበርን አሁን ግን ወዴት እያመራን እንደሆነ እንጃ::

  የዘወትር ተከታታይህ ከጀርመን

  ReplyDelete
  Replies
  1. I fully agree with these comments! For the past 14 years, I am a loyal if not naïve customer of Ethiopian both in local and international flights. I have opportunity to observe all service improvements and deteriorate back to old styles. As an Ethiopian, I am proud of this company. It is one of Ethiopia’s surviving businesses. But this cannot atop me to tell a friendly advice and express my dismays. During the days of Ato Girma Wake, the company had significantly improved its customer’s service both in and out of the aircrafts. Ato Girma was praised by my customers for his down to the ground personality and willingness to accept criticisms. But, even in Ato Girma’s days, the company was much criticized for baggage handlings. However, soon after Girma’s departure, everything started to fast deteriorate and now it is losing its prestige in Africa. I understand the new CEO is working hard to change this trend. But, he is not successful so far. Instead, he is unlucky to oversee the downfall of the company. We need to wake up! We shouldn’t stay too much celebrating be the 3rd airliner in the world to welcome Boeing 787. Many friends of mine and other citizens are thinking to shift to other airliners. ET is our flag carrier. They have to know we are proud of this company. The company and its management should somberly look after to it customer services again! Its employees are either tired of the job or became arrogant in their conduct especially against fellow citizens. They have every reason to excuse themselves. But, they have to know that we are paying their salaries, period!!!!!!!!!! We don’t need any more excuses and explanations. If Ato Tewelde is serious to bring impacts in the industry and leave legacy, he has to walk with sticks and carrots in hand at the corridors of the company!

   Delete
 3. ርእሱ ለሌላ ይመስላል፡፡ አሪፍ ጽሑፍ ነው፡፡ ሰሚ ካለ፡፡ ድካማችሁን ግን በወርቅ ተቀበሉ፡፡ መብታችሁ ነዋ፡፡ ብትውትም አያመሰግኗችሁም፡፡

  ReplyDelete
 4. It makes me sick reading this article. Our people do not serve us well rather they want to pretend as if they are doing good for other. That is one of those multi-problems of my country.

  ReplyDelete
 5. ዳንኤል!?
  አልጻፍከውም ትንሽ ተነፈስክ እንጂ:: በዚህች አጭር መጣጥፍማ አያልቅም የኛ ጉድ:: የእኛ እንበለው መቼም "ኢትዮጵያ" የሚለውን ወርቅ ስም ስለያዘ:: የሥርቆቱስ? የዜጋ መለየቱስ ጉዳይ? እንዲያው ብሶትህን ተነፈስክ እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጣጣ እንደዚህ በቀላል ተወርቶ የሚያልቅ አይደለም:: ለነጭ (ለፈረንጅ) ወይንጠጅ እና የአልኮል መጠጦች እየተመረጡ እየቀረቡ አንተ የጨጓራ ህመም ተነስቶብህ ውሃ ለምነህ የሚደርስብህ ማመናጨቅ ስታስበው ከእነዚህ ጋር ለምን ተፈጠርኩ ሁሉ ያስብላል:: እንዲያውም ይብስብሐል እንጂ የጨጓራው ህመም:: ብቻ ሆድ ይፍጀው. . .

  ReplyDelete
  Replies
  1. I have also experienced same. They don't want to serve Ethiopian.

   Delete
  2. enie yegetemegn yeteleye neber...be auroplan wust hulet ethiopians bicha new yenbernew betam bemigerm huneta kewuchie zegochu beteleye egnan sinkebakebun neber.

   Delete
 6. እረ እንኳን ሰላም ገባህ:: ባገር ስም የሚቀልድ ትልቁ ድርጅት በኢትዮጵያ እኮ አየር መንገድ ነው:: ከአንድ ወዳጄ ጋር በዚሁ አየር መንገድ እየተጓዝኩ በአማርኛችን ያዘዝኩት አልሰራ ማለቱ የገባው ወዳጄ ያንኑ ትዛዝ በእንግሊዝኛ ያዘዋል:: ልጅቱ ማምጣቷ አይደለም የገረመኝ ያስተናገደችበት መንገድ ሳይቀር አሳመመኝ:: ወዳጄ ግን ለርሱ ተመላልሳ ያመጣቻቸውን ሁሉ ሰብስባ ለእኔ እንድትሰጥ በአማርኛ አዞ ጥሩ አድርጎ ቀጣልኝ:: የለሊት በረራዎችን ባየህ አብዛኞቹ የአረብ አገር ተጓዥ ወገኖቻችን እንዴት ባለ መንገድ እንደሚስተናገዱ ታይ ነበር:: ኬሻ በጠረባ ዓይነት ተደርድረው ተኝተው ስታይ ማንነትህን ትጠላለ:: እቃ ይጠፋል:: ትዘገያለህ:: ትንገላታለህ:: በሄድክበት ሲያሰልፉህ ወረፋ እንዳይጠፋ የሚከላከሉ ነው የሚመስሉህ:: ይህ ሁሉ ግን ለምን እንደሆነ አይገባኝም:: በአንድም በሌላ መንገድ መብት ማስከበር የሚባል ነገር አለ:: ከዚያ በፊት ግን ወይ ስማችሁን ለውጡ ወይ እንደ እስክንድር ተዋጉ:: በአገር ስም አትቀልዱ::

  ReplyDelete
 7. This is could be done to achieve the vision of Meles. Kikikiki.....

  ReplyDelete
 8. DN Danial Endew Men Yeshalen yehon Keshtetachen Ymanemar Ena Yzar 6 Amet Endez Ayenet Cheger Agetmogh Neber Gen Eskahuen Alefetam???

  ReplyDelete
 9. fish /chicken? fish/chicken? fish/chicken?........................

  ReplyDelete
 10. እኔ ካለሁበት ስቴት በተለያ ጊዜ ከሶስት በላይ የሚሆኑ ከሰሜን አሜሪካ ወደ ሃገራችን የሚሄዱ ተሳፋሪዎች ትኬት እንድቆርጥላቸው አነጋግረውኝ ነበር፡፡ የሚገርመው ግን ሁሉም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጓዝ ፈቃደኛ ሊሆኑልኝ አልቻሉም፡፡ ያቀረቡልኝም ምክንያትም አንተው እንዳልከው የዋጋ እና የሰርቪስ አለመመጣጠን ነው፡፡ እኔም ምንም እንኳን ይህንኑ ብታዘብም ያው የሐገር ነገር ነውና ተከራክሬ ነበር ግን ምኑን ይዤ ላሳምን !!! በዛ ላይ ለአበሻ ተሳፋሪ የሚያሳዩት ግልምጫ አይሉት መስተንግዶ እኔው ላይ ስለደረሰ ምናባቴን ላድርግ ዝም ብዬ ከማለፍ ውጪ….
  Tes
  PXS, AZ

  ReplyDelete
 11. "ለደቡብ አፍሪካውያን የአውቶቡስ ሾፌሮችም ‹የዘገየነው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ችግር ምክንያት ነው› ብለን አየር መንገዳችንን ለማማት አፍረን የቆጥ የባጡን በመቀባጠር ማረፊያችን ደረስን፡፡"

  ጽ! ጽ! ጽ! አየህ ዲያቆን ዳኔል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ "አትዋሽ" እሚል ግልጽ ትዕዛዝ አለ። አይደለም ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ መዘግየት፣ ስለራስህ መጥፎ ስራዎች ሳይቀር እውነቷን አፍረጥርጠህ መናገር መልመድ አለብህ። ምናልባት እውነቱ መነገር ቢለመድ፣ እኒያ ቢሮ ዘግተው የኮበለሉት ጉብሎችም በስራ ገበታቸው ላይ ይገኙ ነበር፣ እናንተም አትስተጓጎሉም ነበር።

  ግን ታዲያ እራስ እየዋሸ፣ ሌሎች እውነት እንዲናገሩ እንጠብቃለን፣ ዲያቆን ዳኒ? አየህ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. How do you know that they were lying in the bus? do not forget that Christianity with out wiseness will lead to Paganini. Some times I believe it is good passing some critical things, not by lying, but by wiseness. What I understand from the article is that they were not lying insteady passing the ocassion through wiseness.

   Delete
 12. Well written D. Daniel Kibret
  May GOD bless u


  After spending more 10 years in exile, I decided to take flight to Ethiopia using our Airlines,even if it is expensive at least i can contribute my part for my country, but our airlines it needs a lot to progress. In short I used a connected flight, but Our airlines was very late, why 'they are fixing the cockpit toilets' what a mess/, i missed the connecting flight and slept on the coach and get the next day to my destination. I don't think so i am going to use our airlines any more.
  እኔ ና ወዳጆቼ ይህን የአየር መንገድ ጾም ‹ስምንተኛው ጾም› እንለዋለን፡፡ ከኅዳር 15 እስከ ታኅሣሥ 29፣ ከዘወረደ እስከ ፋሲካ የሚጾም አይደለም፡፡ ከአዲስ አበባ እስከ ቀጣዩ የበረራ መዳረሻ የሚጾም ጾም ነው ‹ስምንተኛው ጾም›፡፡ የዐዋጅም የፈቃድም፣ የቀኖናም አይደለም፤ የስንፍና ጾም ነው፡፡

  ReplyDelete
 13. ..‹‹.በቃ የግሌን አሮፕላን መግዛት የሻለኛል....ኤጭ...ያልተፈለገ ወጪ ላወጣ ነው......›› ላማለት የሚያስችል ሃብት ቢኖረኝ ምናለ....መጽንኤ(መጥኔ) ለኛ....አሁን ደግሞ ጓደኛዬ የአየር መንገዱ ሲኢኦ መርጥ አመራር በሚል ተሸለመ ይለኛል....እውነት ከሆነ እንግዲህ ተስፋ የለንም ማለት ነው......

  ReplyDelete
 14. wey sertgnchun aysedeste wey denbgnohcwne aysdeste semune bech zengn adergu mekrebe yemifelge hulume be Ato Girma geza kere.

  ReplyDelete
 15. እዚህ ያሉት ግን ‹በቅተው› ተሠውረዋል!!! I love it.

  ReplyDelete
 16. Thank you DK

  I really appreciate your critics. ETHIOPIAN need to do a lot! But I invite readers of this article to have a look at the bellow detail report by NYC aviation writer.

  http://www.nycaviation.com/2011/12/flying-high-on-cloud-nine-ethiopian-airlines-business-class-review/

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you very much.

   Delete
  2. that story in sep 2011 his talking about current status EAL it indicating they are leading to down let correct your fault rescue the company concerned body because ethiopian airlines is the best figure of our country Dani also indicate that in the past

   Delete
 17. ዲ/ን ዳንኤል የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ከሚያስተዋውቁ ተቋማት አንዱ የኢትዮጵየ አየር መንገድ ይመስለኛል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ለሚሠራው ስህተት ይህን ያክል አጋነህ ማተትህ ጐበዝ ተመልካች አያሰኝህም:: የጉዞ መዘግየት፣ የጾም ምግብ አለመኖር እንደ አዲስ ነገር ሃሎ ሃሎ የሚያስብልም አይደለም:: ያጋጥማል:: ለእለቱ ለራብህ የሚሆን የጾም ነገር መቼም ይጠፋል ብዬ አላስብም:: እንደው በየዓይነቱ ከቃሪያ ጋር አስበህ ይሆናል እንጂ:: እኛ መመልከት ያለብን አጠቃላይ ጐኑን ነው፡፡ አጠቃላይ ጐኑ ደግሞ ከአፍሪካ አገራት ብሎም ከዓለም አቀፍ ጋራ ተፎካካሪ እየሆነ የመጣ ድርጅት ይመስለኛል፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ችግራችን መልካሙን ገጽታ በጥቃቅንና አነስተኛ በሆኑ ሳንካዎች ጥላሸት መቀባት እንደ ጀግንነት እየቆጠርነው ነው፡፡ እና ዳኒ ስለ እይታህ እናመሰግናለን፡፡ ግን እያስተዋልክ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ስለ ኢት. አየር መንገድ አሪፍ ጐን እስኪ ጻፍ፡፡ መቼም ምንም ጥሩ ጐን የለውም እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ አላነበብክ ይሆናል እንጂ ከዚህ በፊትኮ ‹ኢትዮጵያን ከሚያስተዋውቋት ሦስቱ ነገሮች አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው› ብሎ ጽፏል፡፡ በአየር መንገድ አገልግሎት ዋናው የደንበኛ ርካታ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ በ2012 በአፍሪካ 7 ኛ ነው የወጣው፡፡ ዳንኤል የሰጠውን ካላረመ ደግሞ አስር ሆኖ ያርፈዋል፡፡ ለመሆኑ በሩን ዘግቶ ከመጥፋት በላይ ምን ስሕተት እንዲጠቆም ፈልገህ ነው ጥቃቅን ያልከው፡፡ ምናልባት በአውሮፕላን ሄደህ የምታውቅ አትመስለኝም፡፡ EAL (Ethiopian always late) ተብሎ መተርጎሙን አልሰማህም እንዴ፡፡

   Delete
  2. ጥሩ ጎን የላጨውም ተብሎ የተጻፈ አረፍተነገር አላስነበበም፡፡ የገጠመው ነገር ግን እርሱን ብቻ ሳይሆን አብረውት የነበሩትን ወደ ሃያ የሚጠጉ የተለያዩ ሃገራት ተጓዦችንን ነው ይሄ ማለት ደግሞ በዚህ ስራ የሚለጠፍበት ስም በሃያሰዎች ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ምናልባትም ሀያ አገራት እና በትንሹ በእነዚህ ሰዎች ሊቀበሉ በሚጠብቁ አብረዋቸው ቀጣ ጉዞን በሚያደርጉ … ሰዎች ዙሪያ ይሄ ችግር ይደርሳል ፡፡ ስለዚህ ለስህተት ልክ( Degree ) መስጠት ለመስተካከል ሳይሆን ለመዘናጋት ነው በር የሚከፍተው ስለሆነም እስከጥጋቸው ሊነገራቸው ይገባል!!!፡፡ ሌሎች የሰጡትን አስተያየቶች አንብበዋቸው ከሆነ ብዙዎች በተለያዩ ግዜያት ያጋተሟቸውን ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ችግሮች በምሬት ገልጠውታል ይህ ደግሞ ገጽታን ለማጉደፍ ከመትጋት ጋር ተዳምሮ ሊታይ የሚገባው አይመስለኝም፡፡ አየር መንገዳችን ሃገራችንን ወክሎ መልካም ገጽታን ለመገንባት እስከተንቀሳቀሰ ድረስ ፍጹምነትን እንጠብቅበታለን፡፡ ስለዚህ ያሉበት ችግሮች በግልጽ ሊስጣጡ ይገባል!! ዋናው ደግሞ በሃገር ቋንቋ መጻፉን እና ለውስጥ ጥቅም የጻፈው መሆኑን አይዘንጉ፡፡ ዳኒ ግን ይህችን የዕለት ገጠመኝህን ለሚመለከተው አካል በአድራሻው ብታሳውቀው አንተስ ድርሻህ ምድነው እንዳትለኝ ብቻ!

   Delete
  3. thank you brother, it is fact and it should be corrected rather than be one sided and be wise to think as Ethioian airline rather as Tplf

   Delete
  4. መሻሻል የማይፈልግ ሰው/ድርጅት ስለራሱ ሁሌ ጥሩ ነገር ብቻ መስማት ይፈልጋል፡፡ የአየር መንገዳችን ድክመት ከዚህም በላይ፤ ብዙ ለመሻሻል ድክመቶቹን የሚጠቁሙ እንደዚህ ዓይነት ብዙ አስተያየቶች ያስፈልጉታል፡፡
   እውነት ለመናገር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኩራት ብዙ ጊዜ አበሳጭቶኝ እና በሌላ ሀገር ዜጎች ፊት አሳፍሮኝ እና አሸማቆኝ ያውቃል፡፡
   ለማንኛውም ዲ.ዳንኤልን አመሰግናለሁ፡፡ የአየር መንገዱ ሰዎችም ትችት አትፍሩ ይልቁንም ለመሻሻል ተጠቀሙበት፡፡

   Delete
  5. this is a recurring issue the Airlines can not fix. Particularly the lack of fasting food.

   Delete
  6. ersu eko lezemenat yayewun new eytenagere yalew. yilkun yalewun chigir awutito tenagro mefthe mafelaleg yishalal

   Delete
 18. Coffe/tea? coffee/tea? More coffee/more tea? ..............

  ReplyDelete
 19. GOD BLESS YOU D.DANIEL KIBRET . IT'S TRUE THERE IS A LOT OF PROBLEMS ON ETHIOPIAN AIR LINES WHAT MAKES ME SURPRIS IS NO BODY IS RESPONSIBLE NO BODY WANNA CHANGE THIS EVER YEAR IS THE SAME Y?I THINK IT'S A BUSINESS THEY SHOULD DO BETTER THAN THIS .SO I STOP USING ETHIO AIRLINES FLIGHT UNTIL THEY FIX IT .IF WE PAY THE MONEY WE DISERV A GOOD SERVICE IT'S NOT FREE & IT'S VERY EXPENSIVE ALSO !THANKS AGAIN!

  ReplyDelete
 20. የአየር መንገዱ ችግር መንገደኞቹ ብቻ አይድለም ሠራተኞቹንም ጭምር ማማረሩ አየተሰማ ያለ ጉዳይ ነው ጥሩ የሚባሉ ሠራተኞቹን አይአታ የመጣበት ሁናታ ላየ ነው አሁን ባለበ ሊቀጥል የቺላል ግን አሰከመቼ አንደዝህ ያሉ ደግ አና አመላካች የሆኑ ምልከታዎች ብተቀበለን ወደ መፈተሄ መሄድ የመሰልኛ ዋናው ቁም ነገሩ ''አየር መንገዱ የሁላቸንም ነውና ''

  ReplyDelete
 21. chinkilatachinin azuren wedehuala mehed mejemerachinin yasayal!egziabher agerachinin yebarkat.

  ReplyDelete
 22. የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞቹን ሲያንገላታ የኖረ ድርጅት ነው:: እኔ መጓዝ ካቆምኩኝ ወደ አስራ አምስት ዓመታት ሞልተውኛል:: የዛሬ አስራ ስድስት ዓመት በፍራንክፈርት በኩል ወደ አሜሪካን አገር ስመጣ የአዲስ አበባው ቲኬት መሸጫ ለሆቴል ማደሪያና ለእራት ኩፖን ከሰጡኝ በኋላ ፍራንክፈርት ያሉት ግን የለም እዚሁ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አድረህ ነው ጠዋት የሚበረውን የKLM በረራ ይዘህ መሄድ የምትችለው ብለው ያንገላቱኝን አልረሳውም:: በመጨረሻ ከብዙ ክርክር በኋላ የጀርመን ተወላጅ የሆነች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ ድርጊቱ ትክክል አለመሆኑን አምናበት ሆቴል ሄጄ ለማረፍ ቻልኩ:: ይህ ሁሉ ሲሆን "ወገኖቼ" የሆኑት ሰራተኞች ግን በአጠገቤ ዝር አላሉም:: ገና ለገና "የኢትዮጵያ" በሚል አየር መንገድ እጓዛለሁ ብዬ መንገላታት ያለብኝ አይመስለኝም:: በጣም የገረመኝ ግን አሁንም ከአስራ ስድስት ዓመታት በኋላ አለመሻሻሉ ነው:: ፈረንጆቹ አንደሚሉት "If you expect nothing, you are never disappointed." ምንም የምትጠብቀው መሻሻል ከሌለ ምንም ነገር አያበሳጭህም ነውና መበሳጨት አይገባም::

  ReplyDelete
 23. No ear from the ETHIOPIAN. These thing has been told by several customers every time but they don't care. But I care for my comfort. So I just decided to stop using ETHIOPIAN after they make me to stay for 6 hours at the airport with out explanation and re-routing the flight with out consulting the passengers. This thing happened to me a couple of times before also. It is common a flight can be delayed, but why is it difficult to explain ? Delays are now the LOGO for the airline. The airline say EAL is Ethiopian Airlines, but I agree with those who say EAL stands for ETHIOPIAN ALWAYS LATE !

  ReplyDelete
 24. ere enem bezu geze agatemongale thank u daniel

  ReplyDelete
 25. ከላይ አንድ ወነድሜ እንዳለው የአየር መንገዱ እጅግ በጣም ትኝሽ ችግር ነው ዲ.ን ዳንኤል ያነሳው እዚህ መፃፍ የሌለበት በተለይ በአረብ ሀገር የሚመጡ ፣በካርጎ የሚልኩ እህቶቻችን ላይ ያለውን ችግር የደረሰባቸው ያውቁታል ፡፡ ይህን ትችት ለምን ተነገረብን ከሚሉ ለማሻሻል ቢጥሩ መልካም ይመስለኛል ፡፡

  ReplyDelete
 26. nice view ,..keep up ,b/c it helps us to improve more & more...

  ReplyDelete
 27. a writer by the name Ayele from a protestant blog called aba selama used this 'golden opportunity' to insult our church and its followers. I posted a comment which reveals their true nature but they did not post it. I want to post it here.
  To Ayele:
  we know that aba selama blog is owned and operated by satanic protetant organizations who use the name of our (EOTC) saint for their underground operations- operations that started since time immimorial to destroy TEWAHIDO and replace with dirty protestant teachings- but their tireless efforts had been a failure, as we know it. And we know that Ayele you are member of the board of directors of those protestant missionaries- missionaries who direct the objectives of pastor devil. Ayele, you are a protestant who does not fast even for one day and at the same time accuse our holy church and its sons and daughters. you evil person get away from our holy church.

  ReplyDelete
  Replies
  1. መረጃው ትክክል ከሆነ በ you tube ላይ ብትልከው ብዙ ሰው የማየት እድሉ ይኖረዋል፡፡
   ለመረጃው አመሰግናለው፡፡

   Delete
 28. Dniel,please get contact with the manager of
  ethiopian airlines and discuss the case.then after follow up the progress the company is
  doing.if not improved keep on telling them untill it gets solved. you wrote this to improve
  the service not to show you writing ability.
  tell us one day the improvements made.

  ReplyDelete
 29. Wowey, yenelege ene afer belte ladergelhe! Lemhone erhabo endet adergehe?

  ReplyDelete
 30. እንኮራባችኋለን ብለን ስንነግራችሁ ቆይተናል፡፡ መሻሻል የሚገባቸውን በተገቢው ጊዜ ፍጥነትና ጥራት ካላሻሻሉ መጨረሻው ውድቀት ለኛም እፍረት ነው፡፡ እንኮራባችኋለን ብለን ስንነግራችሁ ቆይተናል፡፡ መሻሻል የሚገባቸውን በተገቢው ጊዜ ፍጥነትና ጥራት ካላሻሻሉ መጨረሻው ውድቀት ለኛም እፍረት ነው፡፡

  ReplyDelete
 31. I totally agree with Dn. Daniel, I hate Ethiopian airline over all but "I like it also because it's ours". They don't care about their customers I don't know why. It is time to see themselves and stand for a change.

  ReplyDelete
 32. ዳኒ ‘’እቅድ ዶሮ ክንወን iሮ’’ ሲባል አለሰማህም?

  ReplyDelete
 33. I faced the worst one when I traveled to Canada by Egypt Air and Air Canada!!I was with a baby and flight was delayed.Air Canada offered a hotel room service to take a rest in transit for all passengers except me !!!!!!!! I was the one with 9 month baby and alone.No one was in office to help or answer.But thanks to God, He sent me a Lebanon Orthodox woman who helped me staying the whole time with me till we bored in the next flight !!! ( This is some of it !!!!)

  ReplyDelete
 34. Dear Deacon Daniel ,
  I can not get a word to express how I was disappointed with ETHIOPIAN when I was to fly for education which had dead line for registration. ETHIOPIAN is ,from now on ,allergic for me. I do not want even to see them ,especially the hostesses .

  ReplyDelete