Saturday, November 24, 2012

የሁለቱ ሐውልቶች ዕጣ 2

click here for pdf 
ዛሬ ጠዋት በተሰጠ መግለጫ የዐፄ ምኒሊክ ሐውልት አሁን ባለበት እንደሚቀጥል፡፡ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ግን ተነሥቶ ከግንባታው በኋላ እንደሚመለስ ተነግሯል፡፡ ዘግይቶም ቢሆን መግለጫው መሰጠቱ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም ዝርዝር የሚፈልጉ ነገሮች አሉ፡፡
 • የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ተነሥቶ የት ነው የሚቀመጠው?
 • ማን ነው የሚያነሣው?
 • የቅርስ ባለሞያዎች ተሳትፎ ምን ያህል ነው?
 • በቆይታው ጊዜ የሚደረግለት ጥንቃቄስ?
 • ሲመለስስ የት ነው የሚቆመው? አሁን ከሚሠራው የባቡር መሥመር ጋር ባለው ተዛምዶ የወደፊት አቋቋሙ ምን ይመስላል?
ለወደፊቱ እንደዚህ ዓይነት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አስቀድሞ ዝርዝርናሉ መረጃ መስጠት ሊለመድ ይገባል፡፡

21 comments:

 1. መንግሥት ለታሪካችንና ለቅርሳችን የሚገባውን ክብርና ክብካቤ ሊሰጥ ይገባዋል!

  በፍቅር ለይኩን፡፡

  እውቁ የጥቁሮች መብት ታጋይ የነበረው ማርከስ ጋርቬይ በአንድ ወቅት ታሪክ ለአንድ አገር ወይም ህብረተሰብ ሊኖረው ስለሚችለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ሲናገር፡- ‹‹A people without the knowledge of their past history, origin and culture is like a tree without roots.››በማለት ስላለፈው ታሪኩ፣ባህሉ፣ መገኛውና ማንነቱ እውቀት የሌለው ሕዝብ ስር የሌለው ዛፍ ያህል እንደሚቆጠር ገልፆአል፡፡
  ወደድንም ጠላንም ይህች አገር በሺህ ዘመናት የዳጎሰ ከአፍሪካ እስከ አሜሪካ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ ህንድና ቻይና፣ ከአውሮፓ እስከ ካረቢያንና ጃማይካ የሚዘረጋ ታሪክ፣ ቅርስና ሥልጣኔ ያላት ሀገር ናት፡፡ የዚህ አኩሪ ታሪክና ቅርስ ዋንኛ ባለቤቶች ደግሞ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ናቸው፡፡
  ከሰሞኑ አዲስ አበባን የባቡር መጓጓዥ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ በተጀመረው የባቡር መስመር ዝርጋታ የተነሳ ታሪካዊዎቹ የአፄ ምኒልክና የሰማእቱ በአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሊነሱ እንደሚችሉ ጭምጭምታ እየተሰማነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ በመንግሥት በኩል ግልፅ የሆነ መግለጫ ባይሰጥም በሀውልቶች አካባቢ እየተደረገ ያለው ቁፋሮ ግን የሀውልቶቹን መነሳት የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡
  መንግሥት ቢያንስ ስለ ሀውልቶቹ ምን እንደ ታሰበና በባቡር መንገዱ ግንባታ የተነሳ ያለውን ዝርዝር ሁኔታ ለሕዝብ የማሳወቅ ግዴታ ብቻ ሳይሆን ኃላፊነትም ያለበት ይመስለኛል፡፡ በሌላው ዓለም በሺህ የሚቆጠሩ አፍሪካያንን ለጨፈጨፈና ነፈሰ ገዳይ ለሆነው ፋሰሽስቱ ግራዚያኒ በታላቅ ክብር ሀውልትና መታሰቢያ የቆመ ባለበት ጊዜ ለፍትህ፣ ለእውነት፣ ለነፃነት የተዋደቁ ሕያዋን የታሪክ ምስክሮችን የሚገባቸውን ክብር አለመስጠት ትልቅ የታሪክ ምጸትነው የሚሆነው፡፡
  እነዚህ ሀውልቶች ታሪካዊና ሕዝባዊ ፋይዳ ከእኛም አልፎ በነፃነትና በሰው ዘር እኩልነት የሚያምኑ አገራትና ሕዝቦች ሁሉ የሚጋሩት ታላቅ ቅርስ መሆኑ ከግንዛቤው ውስጥ መግባት ያለበት ይመስለኛል፡፡ በአፄ ምኒልክና በእቴጌ ጣይቱ የክተት ዘመቻ ዘር፣ ጎሳ፣ ሃይማኖት ሳይለያያቸው ለአንድ የጋራ እናታቸው ለኢትዮጵያ በአድዋ ከትመው የጣሊያንን ጦር ድባቅ በመምታት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጥቁር ኃይል ወራሪውን የአውሮፓን ኃይል በማሳፈር ወደመጣበት የመለሰው የአድዋው ድል-ድሉ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካና ጥቁር ሕዝብም ጭምር መሆኑ ሊዘነጋ አይገባውም፡፡
  በአድዋው ድል ምክንያት በቅኝ ግዛት የነበሩ የአፍሪካና የካረቢያን ሕዝቦች ለነፃነታቸውና ለመብታቸው ኢትዮጵያንንና ኢትዮጵያዊነትን የነፃነት፣ የድል፣ የአልገዛም ባይነት…ወዘተ ዓርማ አድርገው በጨቋኞቻቸው ላይ ክንዳቸውን በማንሳት መራርና አልህ አስጨራሽ በሆነ ትግል ነፃነታቸውን ሊጎናጸፉ በቅተዋል፡፡
  ኢትዮጵያአገሬን፣ ሃይማኖቴንና ሕዝቦቿን ለባእድ አሳልፌ ለመስጠት እምነቴ፣ታሪኬና መንፈሳዊ ሰብእናዬ አይፈቅድልኝም በማለታቸው በፋሽስት የመድፍ ጥይጥ ተደብድበው እንዲሞቱ የተፈረደባቸው የሰማእቱ የአቡነ ጴጥሮስ ሞትም ለነፃነት የተከፈለ ውድና ክቡር ሞት እንጂ ተራና አልባሌ ሞት አይደለም፡፡ሀውልታቸውም የነፃነትን ክቡር ፍሬ የሚዘክር ሕያው ምስክር ለመሆን እንጂ እንደው ለጌጥ የቆመ ሀውልት አይደለም፡፡ ይህን ለመላው አፍሪካ፣ ለጥቁር ሕዝቦችና ለሰው ልጆች ነፃነትና እኩልነት ለተሰውና አሁንም እየታገሉ ላሉ ሁሉ ምልክትና መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የቆመውን የነፃነት ሀውልታቻንን ማክበርና መጠበቅ የመንግሥትና የታሪኩ ባለቤቶች የሆንን የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባዋል፡፡
  የአፍሪካ ህብረት ዋናው ጽ/ቤት የሚገኝባት አዲስ አበባ ብቸኛዋ ለአፍሪካ መዲና የመሆን ክብር ለመጎናጸፍ የቻለችበት የታሪክ ውሉ የሚመዘዘው የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሺህ ዘመናት ታሪክ፣ ስልጣኔ፣ ቅርስና የቀደሙት አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በአድዋ ላይ ባስመዘገቡት አንጸባራቂ ድል ነው፡፡ እንደሚባለውና እየሰማን እንዳለው መንግሥት ለባቡር መስመሩ ዝርጋታን በተመለከተ ከእነዚህ ከአፄ ምኒልክና ከሰማእቱ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ጋር በተያያዘ ግልፅ የሆነ መግለጫም ሆነ ሀውልቶቹን በተመለከተ ምምን እንደታሰበ ምንም የተገለጸ ነገር የለም፡፡
  በዚህ ረገድ በታሪክ፣ በቅርስና በባሕል ጉዳይ የሚሰሩ መንግሥታዊም ሆኑ የግል ተቋማት ድምፃቸውን ማሰማት ይገባቸዋል፡፡ የሚመለከተው የመንግሥት አካልም በዚህ ጉዳይ ላይ የታሪኩ ባለቤት የሆነውን ሕዝብ አክብሮ ሊያነጋግረውና ሊያወያየው ይገባል፡፡ የሀውልቶቹን ዕጣ ፈንታ በተመለከተም ከታሪኩ ባለቤት ከሆነው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመወያየት ሀውልቶቹ የሚገባቸውን የክብር ሥፍራ እንዲያገኙ ማድረግ አለበት፡፡ ክብር ለታሪካችንና ለቅርሳችን!!!
  ሰላም! ሻሎም!

  ReplyDelete
 2. እንደ ባለሙያኔተ-የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልትም ከመነሳቱ በፊት ብዙ ግልጽ ያልሆኑ ነገሮች ይታዩኛል።
  1. ለምን ማንሳት አስፈለገ? ይህ ቦታ ሰማዕትነት የተቀበሉበት ቦታ ነው። ደማቸው የፈሰሰበት ቦታ ነው። ይሄን ቦታ የግድ ለባቡር መስመር መዘርጊያ ማድረግ የተፈለገው፤ በውኑ ሌላ አማራጭ አጠን ነውን? አይመስለኝም!
  2. ተነስቶ፣ በዃላ ይመለሳል የሚባለው ነገር ቀልድ ቢጤ ይመስላል!!!
  3. ከተነሳ ደግሞ፤ የግድ መዘጋጃ ቤቱ ጭምር መፍረስ ያስፈልገዋል። ካለበለዚያ፤ ታሪክን ለማጥፋት መፋጠን ካልሆነ በስተቀር፤ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልትን መነሳቱ፤ ለሚዘረጋው የባቡር መስመር የሚሰጠው ጥቅም በጣም አናሳ ነው።
  4. የሁሉም ማሳለጫ፤ መነሻና መድረሻ ፒያሳ ስለሆነች-ከታች በኩል ሁሉንም ነገር ማድረግ ይቻላል! ይሄ መሆኑ-ሁለቱ ሐውልቶችና መዘጋጃ ቤቱ ከመፍረስ ይድናሉ። ሙሉ የሆነ፤ ሰፊ ማሳለጫ ያለው የባቡር መስመር ለመዘርጋት፣ የግድ ከላይ በኩል መሆን አለበት ተብሎ ተወስኖ ከሆነ ደግሞ፤ መንግስት መዘጋጃ ቤቱን ጨምሮ በአካበቢው ያሉ ሊነሱ የሚችሉ ቤቶችን በግልጽ ያሳውቀን።
  5. የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ከታች ከተነሳ፤ ከላይ ያለው የአጼ ምንሊክ ሐውልት ከመነሳት የሚያግደው አንዳች ምትሐታዊ ሃይል አይኖርም! ከታች ከተሰራ ከላይ መቀጠሉ አይቀርም። በእኔ አስተያየት ነጣጥሎ ርምጃ የመውሰድ ያስመስላል።
  ለማንኛውም ‘‘ቀድሞ ነበር እንጅ መጥኖ መደቆስ፤ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ‘ የተባለው ነገር እንዳይደርስ፤ መንግስት በጣም ቢያስብበት መልካም ነው!!!

  ReplyDelete
 3. ኅዳር 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
  በእንዳለ ደምስስ
  የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ እንዲያስችል በሚዘረጋው የቀላል ባቡር መሥመር ዝርጋታ ምክንያት የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት እንደሚነሳ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
  አቶ አበበ ምህረቱ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኮምኒኬሽን አገልግሎት ክፍል ኀላፊ የሐውልቱ መነሳት ያሰፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ምን እንደሆነ ሲገልጹ “በቀላል ባቡር መስመር ዝርጋታ ምክንያት መንገዱ ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ አደባባይ ጀምሮ ወደ አውቶቡስ ተራ የሚወስደው መንገድ አትክልት ተራ ድረስ ባቡሩ በዋሻ ውስጥ ነው የሚያልፈው፡፡ በተጨማሪም የባቡሩ መስመር ከምኒልክ አደባባይ ወደ ሽሮ ሜዳ ይዘረጋል፡፡ እንደሁም ከአውቶቡስ ተራ ወደ ቅድስት ልደታ ለማርያም የሚታጠፈው መስመር መነሻም ነው፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ከማዘጋጃ ቤት አጥር ጀምሮ ወደ ትግበራ የተገባበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን፡፡ ሥራው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሲደርስ ስዊድን አገር የሚገኘውና ከፍተኛ ልምድ ያለው ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ሥራውን በበላይነት የሚቆጣጠረው ሲሆን በሚያስመጣቸው ባለሙያዎች አማካይነት በክብርና በጥንቃቄ ሐውልቱን አንሰቶ የዋሻው ግንባታ እንደተጠናቀቀ አንዲትም ሣ/ሜትር ሳይዛነፍ እንደነበረ በቦታው ላይ በክብር እንዲያስቀምጥ ይደረጋል፡፡ ሐውልቱ የሀገር ቅርስና ሀብት ነው፤ ለዚህም ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራ ይሰራል፡፡” ብለዋል፡፡

  ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ብቻውን የሚያከናውነው ሳይሆን የአዲስ አበባ የጽዳትና ውበት ኤጀንሲ፤ የአዲስ አበባ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን፤ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮዎች፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች ጋር በመሆን እንደሚከናወን የገለጹት የኮርፖሬሽኑ የኮምኒኬሽን አገልግሎት ክፍል ኀላፊው በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ወደ ትግበራ እንደተገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

  “ሐውልቱ ተነስቶ የት ነው የሚቆየው?” በማለት ላቀረብንላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡም “ሐውልቱ በክብር ከተነሳ በኋላ ባለሙያዎቹ በሚያቀርቡት ጥናት መሠረት ባለ ድርሻ አካላት ተወያይተው በሚዘጋጀው አስተማማኝና ምቹ ስፍራ ላይ እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡ በመጨረሻም በክብር ወደ ቦታው ይመለሳል” ብለዋል ፡፡

  የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሐውልት በተመለከተም ”አሁን ባለው ዲዛይን መሰረት ሐውልቱን ስለማይነካው አይነሳም” በማለት ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡
  “ይህንን ጉዳይ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አሳውቃችኋል?” ብለናቸውም “ፕሮጀክቱ የሁላችንም ነው፡፡ የሀገር ነው፡፡ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ለተባሉት አካላት ሁሉ አሳውቀናል፡፡” በማለት የመለሱ ሲሆን ወደፊትም ተቀራርበው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
  “ሌላ ዲዛይን ለመስራት ለምን አልተሞከረም?” ላልናቸው ሲመልሱም “ዲዛይኑ ማእከላዊውን መንገድ ይዞ ነው የተሰራው፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ይከናወናል፡፡”በማለት መልሰዋል፡፡

  በመጨረሻም “ሐውልቱ ከተነሳ በኋላ ወደ ቦታው ለመመለሱ ኀላፊነቱን ማነው የሚወስደው?” ብለን ለጠየቅናቸው “መንግስት የህዝብን ችግር ለመፍታት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ሁሉም ሀላፊነቱን ወስዶ የሚሰራ ይሆናል፡፡ ባለ ድርሻ አካላቱም የመንግስትን ሥራ የሚያስፈጽሙ በመሆናቸው ኀላፊነት አለባቸው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኀላፊነት አለበት” ብለዋል፡:
  http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php/-mainmenu-18/1145-2012-11-24-14-59-09

  ReplyDelete
 4. Ato Daniel
  I am not writing this to post it but it’s for you just suggestion.
  Why don’t you grab adequate information before you write?
  Are you sure you don’t hear about the rail authority that disclosed?
  Or you are insisting for blood shade?
  This is the final message for you ……..
  After this the government will take the necessary action.
  We need responsible and information backed blogs but not adverse for the development.
  You are an Ethiopian, so is it how you contribute to your country?
  A.s

  ReplyDelete
  Replies
  1. feri kadre neke masferarat sayehone mereja site .EPRDF derom wenbede nebere ahuneme bewenbedena sewen yasferaral feri ka ka ka ka dani alenilihe kemanim belay geta /GOD/ will protect u .

   Delete
  2. ስንት ማሰብ የተወ አለ? ለA

   Delete
 5. Meneilik wrote to King Umberto of Italy after the Italian invaders were soundly defeated at Dogali by the Ethiopian army led by Raisi Alula ;  牋牋牋牋牋� I have now learned that Yohannes threatens my country, saying that

  牋牋牋牋牋� It was Menelik who advised the Italian government to make war over

  �Massawa. I have decided, for the salvation of my country to defend

  myself, and it is therefore necessary for me to have your help.  In October last year I signed a convention with Antonelli in which

  I promised to do nothing that would damage my friendship with the

  Italian government. Now on defending my country,I can revenge

  the Italians who have died.

  Now I ask you to immediately send help by way of arms and that

  there shall not be less than 10,000 Guns. I have confided to Antonelli

  many things that I cannot write which he should tell you. ( p 145/6 )

  ReplyDelete
 6. ክብር ለታሪካችንና ለቅርሳችን!!!

  ReplyDelete
 7. ክብር ለታሪካችንና ለቅርሳችን!!!

  ReplyDelete
 8. I suspect that these Ethiopian Engineers got a lot of money from Italian Government. " kiray sebsabi bicha"

  ReplyDelete
 9. 1.አሁን የኛ በድህረ ገጾች ላይ ማውራት በሀውልቱ ፈረሳ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?
  2.ደግሞስ ለባቡሩ መሰራት የሐውልቱ መፍረስ አስፈላጊ ከሆነ ቢፈርስስ፣ሐውልቱ ይጠቅማል መንገዱ? የእነአቡነ ጴጥስ ሐውልት ፈረሰ ማለት አቡኑ ከልባችን ውስጥ ፈረሱ ማለት ነው ???

  ReplyDelete
  Replies
  1. Banda neh, every thing is first emanated from mind and history is best for generation; if people has model to do good things the other like materials are nothing they can be get with confidence.

   Delete
 10. AnonymousNovember 26, 2012 10:50 AM
  አሳዛኝ ነው አስያየትህ። አዎ ሐውልቱ ከፈረሰ፤ ታሪካቸው አብሮ ይደበዝዛል። ላንተ ላይሆን ይችላል ነገር ግን ለወደፊቱ ትውልድ! ለዛሬ ሆዳችንን ለመሙላት የታሪክ ክፍተት ለመፍጠር ባንፋጠን ጥሩ አይመስልህም?

  ReplyDelete
 11. yegudoch ager!! gud yebekelebat!

  ReplyDelete
 12. seln yabzalh D.Daniel chilotahn amlak yadabrlih

  ReplyDelete
 13. i just wana say selamun yabzalh

  ReplyDelete
 14. some times what u talk doesn't give sense , actually what u like most is talking about the past. history is good just as a document ,beside talking about aba guba aba kirose is useless pls give as a feed back what will be our future a nd how will be a strong nation u Tess is mostly Orthodoxy

  ReplyDelete
 15. it seems Ethiopia is only for orthodox

  ReplyDelete