Friday, November 23, 2012

የሁለት ሐውልቶች ዕጣclick here for pdf
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ የመነጋገርያ አጀንዳ የሆነ አንድ ጉዳይ አለ፡፡ የአቡነ ጴጥሮስና የምኒሊክ ሐውልትና የባቡሩ መሥመር ያላቸው ዝምድና፡፡ ስለ ባቡር በመዝፈን ከመቶ ዓመት በላይ ያሳለፍን ሕዝቦች የከተማ ባቡር ማግኘታችንን በዕልልታ የምንቀበለው ነገር ነው፡፡ ዘግይተን ይሆናል እንጂ አልቸኮልንም፡፡ ሥራው በቁርጠኝነት መጀመሩና ከወሬ አልፎ ሲተገበር ማየታችንም እሰዬው የሚያሰኝ ሆኗል፡፡
ግን ደግሞ  ጥያቄ አለን፡፡

ይህ የባቡር መሥመር የአቡነ ጴጥሮስንና የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት እንዲነሡ ያደርጋል?
ለዚህ ጥያቄ ምላሹ ‹አዎን› ከሆነ ስለ ባቡሩ የሚኖረን ግምት ይለያል፡፡ ኢትዮጵያን እናሳድጋለን ስንል ያሳደጓትን እየዘነጋንና መታሰቢያቸውን እያፈረስን መሆን የለበትም፡፡ ‹በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ› አለ ያገሬ ሰው፡፡ የምናመጣው አዲስ ነገር ባለን ላይ የሚጨመር እንጂ ያለንን የሚያጠፋ መሆን የለበትም፡፡ መኪና ያስፈልገናል፣ ግን እግር የሚቆርጥ መሆን የለበትም፡፡ ወደድንም ጠላንም ይህች ሀገር የታሪክና የቅርስ ሀገር ናት፡፡ 

ይህ ታሪኳና ቅርሷ ደግሞ የህልውናዋም ምንጭና መሰንበቻም ጭምር ነው፡፡ ይህን ታሪክና ቅርስ እያጠፉና እያበላሹ የሚመጣ ለውጥ አንገት ቆርጦ ፀጉርን እንደማስተካከል ነው የሚቆጠረው፡፡ እናም የሚመለከታቸው ሁሉ ወደ ርምጃ ከመግባታቸው በፊት ሦስት ጊዜ ሊያስቡ ይገባል፡፡ መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡
ምላሹ ‹አይደለም› ከሆነ ደግሞ እሰዬው፡፡ ግን አሁን በሐውልቶቹ አጠገብ የሚከናወነው ቁፋሮ ወደ መሠረታቸው እየሄደ ነው፡፡ እንደሚሰማውም የባቡሩ መሥመር በሐውልቶቹ ሥር የሚዘረጋ ነው፡፡ ታድያ የሐውልቶቹ ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው? ለሕዝቡስ ግልጽ ማብራርያ የማይሰጠው ለምንድን ነው? ‹ለጊዜው ተነሥተው በኋላ ይመለሳሉ› የሚል መረጃም እየተሰማ ነው፡፡ ለጊዜውስ ተነሥተው የት ነው የሚሄዱት? በኋላስ በምን ሁኔታ ነው የሚመለሱት? ታሪካዊ ቦታቸውንስ ይለቃሉ?
ግልጽ መልስ ያስፈልጋል፡፡
እንዲያውም ሕዝቡ በመንገድ ምክንያት ቤት የፈረሰባቸው ሰዎች ኮንደሚንየም እንደሚሰጣቸው ሁሉ እነርሱም ከዚያ ቦታ ተነሥተው ኮንደሚንየም ሊሰጣቸው ይችላል እያለ መቀለድ ሁሉ ጀምሯል፡፡

126 comments:

 1. መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በሚካሄደው የባቡር መስመር ግንባታ ምክንያት የአቡነ ጴጥሮስና የዳግማዊ ምኒልክ ሃውልት ይፈርሳል በሚል የሚነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው አለ የኢትየጵያ ምድር ባቡር ኮረፖሬሸን።

   በግንባታው ምክንያት የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ለደህንነቱ ሲባል ለጊዜው እንዲነሳ የሚደረግ ሲሆን በቅርቡ በነበረበት ስፍራ መልሶ ይተከላል ብሏል። የምኒልክ ሃውልትን ግን ግንባታው ጭራሽኑ አይነካውም ነው ያለው ኮርፖሬሽኑ።

   የአዲስ አበባ ከተማን የትራስፖርት ችግር ለማስተካከል የባቡር መስመር ፕሮጀክት ግንባታ እየተካሄደ ነው።

   የባቡር ግንባታው ከሚከናወንባቸው አንዱ በሆነው ፒያሳ ጊዮርጊስ አካባቢም ከግንባታው በተቀራኒው የሆነ ሀሳብ ሲነገር እየተሰማ ሲሆን ፥ በተለይ የማህበረሰብ ድህረ ገፆችና የተለያዩ አካላት የአቡነ ጴጥሮስና የሚኒልክ ሀውልት በባቡር መስመር ግንባታው ምክንያት ሊፈርሱ ነው በሚል ሰፊ ዘመቻ እየተካሄደ ነው።

   በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑትን አቶ አበበ ፥ በአካባቢው አሁን እየተከናወነ ያለው ስራ በእቅዱ መሰረት እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው ፥ የአቡነ ጵጥሮስ ሀውልት ይፈርሳል የሚለው ፍፁም ስህተትና ተራ ወሬ ነው ብለዋል።

   ሀውልቱ ምንም ችግር ሳይደርስ የባቡር መስመር ዝርጋታው ይከናወናል ያሉት ሃለፊው ፥ የባቡር መተላለፊያ ዋሻ ከሃውልቱ ስር ስለሚገነባ ፤ ግንባታው እስኪያልቅ ድረስ ሃውልቱ ለጥቂት ጊዜ ተነስቶ ከዋሻው መጠናቀቅ በኋላ ወደ ቦታው እነደሚመለስ ተናግረዋል።

   አያይዘውም ይህ የባቡር መስመር ግንባታ የዳግማዊ ሚኒሊክ ሀውልትን በምንም መልኩ እንደማይነካው የሚወራው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑንም ነው ያስረዱት።

   የባቡር መስመር ግንባታው በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን እና ስራው ፥ ከአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ፣ ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ከአዲስ አበባ ውበትና ጽዳት ኤጀንሲና ከሌሎችም ጋር በትብብር ነው የሚሰራው ብለዋል አቶ አበበ።

   የክትትል ስራውም በጋራ እንደሚከናወን ጠቅሰው ስራው አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በመከናወን ላይ ነው ማለታቸውንም ብርሃኑ ወልደሰማያት ዘግቧል።

   Delete
 2. it is surprizing dani i did't informed like that but if it is true, the respective organ better thing seriously before run for destruction and creating people opposition.
  bye
  from gondar

  ReplyDelete
 3. Agreed! we must remember our icons and give to credit for what they do for their country. and we are living now with liberty because of them.

  ReplyDelete
 4. ለፍርድም የተሰየሙት ዳኞች ሦስት ሲሆኑ እነዚህም ጣልያኖችና የጦር ሹማምንት ናቸው። የመካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር። የቀረበባቸውም ወንጀል ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ ራስዎም ዐምፀዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምፁ አድርገዋል የሚል ነበር። ዳኛውም «ካህናቱም ሆኑ የቤተ ክህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የኢጣልያን መንግሥት ገዥነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን ዐመፁ? ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?» ሲል ጠየቃቸው።
  አቡነ ጴጥሮስም የሚከተለውን መለሱ። «አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም። እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኃላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ። ስለዚህ ስለአገሬና ስለቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ። ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም። ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ። እኔን ለመግደል እንደ ወሰናችሁ ዐውቃለሁ። ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። ግን ተከታዮቼን አትንኩ» አሉ። alemayehu dendir

  ReplyDelete
  Replies
  1. it is a very interesting way of looking at it. Most of us (I am talking about me) forgot our origin in the name of modernization. So the builders do not the care. We the moderns do not care.

   Delete
  2. This is what our country lacks now.... wow we have missed such type of father......and.....

   Delete
 5. በጣም ጥሩ እይታ ነው

  ReplyDelete
 6. Daniel:I hope you are not the only concerned and all knowing individual like the fictitious gods you are preaching about.Abune Petros and Emperor were not special human beings no matter how much you and your blood sucking church glorify them. They lived their allotted life and they died, that's all. Now cannot condemn us to suffer from lack of transport for ever lest these idolatry monuments might be displaced. You are luxuriously touring all over the world wasting the church's money extravagantly. You don't also bother about the chronic problem of lack of public transport as you are enjoying the streets of Addis driving your car. That's why you are more concerned about the man made monuments than those who are suffering alive. Really absurd!

  ReplyDelete
  Replies
  1. you My brother , you are totally looking in the darkest side of your history and trying to accuse your brother , i think you are one of EPRDF Members who does not care about the country history and culture more than the material Development!

   Delete
  2. @ anon 10:58
   Your idea is just nonsense. You sir are sick. You don't have to insult someone's God to advance your atheist view.

   Delete
  3. Shame on you men!

   Delete
  4. Dear Brother/Sister:
   If you have any problem with our brother Daniel, you should handle it in a wise way. But here, the discussion is about our beloved country and our heroes, whom we have to give respect. And I should say that you are wrong in stating Abune Petros and Emperor Minilik are not special.The fact that we started the railway just now as a solution for transportation problem, a century after the emperor brought it, would be enough to say Minilik is a hero and special, let alone other details.... So, we need to progress forward, while keeping our rich history. We can build ultra-modern rail way system with out affecting the stated monuments, it is an engineering task, though not simple. And I hope this is straight forward unless you block your own mind....

   Delete
  5. Are u a human being, are u an Ethiopian, I doubt... A human being can easily understand that this two persons are special, especially Ethiopians are very proud of them. You better check your mind status. I pray for your mind status

   Delete
  6. Hi my brother,

   I read all your comment and I couldn't keep my mouth shut. Are you really an Ethiopian? If all this kind of thing doesn't bother you, you may ask your self from were you were from?

   You know I have some engineering back ground and they can build this transportation system using other alternative. They can take other route.

   But our history doesn't have other alternative. It means who we are.

   And please don't try to point out your figure on our brother. He tried to inform us.

   It is really a bad idea. It looks like they did it on purpose.

   I know even in USA they don't want to touch even a house which was constructed during their oldies time. And they keep the monument of their historical bad people also.

   Because it is an image that we can see the past.

   Their secret of civilization is not based on by destroying the past.

   We have to be positive fist and accept the reality.

   BZW Italians are building monument and garden for graziani.
   Is destroying our's the complement of that.

   Oh my God I feel so sorry by all these thing.

   God bless Ethiopia

   Delete
  7. መስፍን ከአዋሳNovember 29, 2012 at 5:49 PM

   አረ ወዳጄ እንደነገርከን ከሆነ የአዲስ አበባ ነዋሪ ነህ አይደል? በወንድምነት ልምከርህ አሁኑኑ ወይ ፀበል፤ ወይ አማኑኤል ግባ። 100% እርግጠኛ ነኝ ሃይማኖቱ ምንም ይሁን ምን አንድ ኢትዮጵያዊ እንዲህ አይነት አሳፋሪ አባባል አይወጣውም ንክ ካልሆነ በስተቀር። ስለዚህ ነገ ለነፍስህም ሳትሳሳ ወደ መኪና ውስጥ እራስህን ልትወረውር ስለምትችል ምክሬን ቸል አትበል አደራ። ወይ ስልጣኔ፤ ድንቄም ስልጣኔ እቴ.....

   Delete
  8. You must be stupid. if not you would have understood what Dn Daniel said in a very strait forward manner. 'Sint sew ale be Egziabher'.

   Delete
 7. ውድ ዲያቆን ዳንኤል፡

  የአጤ ምኒልክን ሐውልት በ1983 መለስ ለማፍረስ ሞክሮ ነበር። እሱ ፈርሶ ቀረ እንጅ። ፍርሃት መጥፎ ነገር ነው ዳኔል። ቡዙ ነገሮችን ከመስራት ያስቀራል። መንግስቱ ቢሆን ኖሮ ሃውልቱ መፍረስ ካለበት በዳይናማይት አፍርሶ ይገላገል ነበር። ይህ መንግስት ግን ከአሁኑ ላፍርስ አላፍርስ እያለ እየዋለለ፣ የሰውን ልብ ለመስለል ይሞክራል። ህዝቡም በግልጽ ባያውቀውም፣ በውስጡ እየተረዳ፣ ከንቀት ላይ ንቀት እየጨመረ ይገኛል። አለም በአንዲት አሜሪካ እማይገዛ ቢሆን ኖሮ፣ እስካሁን የዚህ መንግስት ህልውና ተደምድሞ ነበር። ፍርሃት መጥፎ ነገር ነው ዳንኤል። ልትሰራው ያሰብከውን ነገር ያስተጓጉላል። በውስጥ ጥላቻም እንድትብገነገን አድርጎህ፣ መንግስቱ፣ ገንዘቡ፣ ሁሉ ነገር ያንተ ሁኖ፣ ግን የውስጥ የኅሊና ስቃይ ውስጥ ገብተህ እንድትዋዥቅ ያረግሃል።

  ብቻ መከራ ነው ጃል!

  ReplyDelete
 8. Yichine Yiwedal YeAto Meles RaEye.....Ayte lemotua Yedimet Afincha Tashetalech Alu....Nikich argoatina eniteyayalena.....Koy gin YeWeyanna Engineeroch KIYESSA Altemarum ende ?????

  ReplyDelete
  Replies
  1. men yemaralu, tarikena kirse maferese new yetemarute

   Delete
 9. የምናመጣው አዲስ ነገር ባለን ላይ የሚጨመር እንጂ ያለንን የሚያጠፋ መሆን የለበትም!!!

  ReplyDelete
 10. መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡

  ReplyDelete
 11. ጣሊያናዊያን ለፋሽስቱ ግራዚያኒ መታሰቢያ ሲያቆሙ ኢትዮጵያዊያን የአቡነ ጴጥሮስን እና የአጴ ምኒልክን ሀውልት ሊያፈርሱ ነው ይባላል፡፡ እንዲህ ነው ልዩነት እና እድገት…

  Reporter Amharic 14, November 2012 : የኢትዮጵያን ሕዝብ ለጨፈጨፈው ፋሽስት ግራዚያኒ መታሰቢያ መናፈሻና ሙዚየም መገንባቱን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ድምፃቸውን ያስተጋቡ!
  WEDNESDAY, 14 NOVEMBER 2012

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thanks for reminding all of us this. It is rediculous. Who is going to stand for us, for Ethiopia if ourselves can not stand for our history.

   Yigermal, min ayinet tiwulid eyehonin new?????

   Delete
  2. ቤተክርስቲያንን እና አገርን የሚንቁ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ይጣላሉ፡፡ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው፡፡

   Delete
  3. አዎ መብላት ሲያቅታት በተነችዉ እንደምባለዉ ለአገራቸዉ መስራት ሲያቅታቸዉ የተሰራዉን ያፈርሳሉ

   Delete
 12. This is a pre colonialism era, destructing every thing which is not done by the regime.

  ReplyDelete
 13. ዲን ዳኒ, እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ! ይህን ነገር ከሰማሁ ጀምሬ ብሎግህን ስከታተል ነበር መረጃ ለማግኘት። በጣም በጣም ታምሚያለው ከእራሴ ጋርም ተከራከርኩ እንዴት ሊያስቡት ቻሉ በማለት?
  ሐውልት የሚያፈርስ ባቡር ከሆነ ለዘላለም ባቡር አንፈልግም!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 14. Nege degimo beneka ejachew fasiledesina lalibelan yafersulinal

  ReplyDelete
 15. መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡

  ReplyDelete
 16. Dn daniel yihenin sira behalafinet yeyazutin sewoch manager ena yetifat zemechaw mikomibet amarach bifeleg melkam yimesilegnal.please do your best!Egziabherm yiredahal.

  ReplyDelete
 17. መቼም ምን ይደረግ ተብሎ ሊታለፍ አይቻልም፡፡ የአዲስ አባባን የጠዋትና የማታ የትራንፖርት ችግር የቀመሰን ናዋሪዎቻ አነኳን ባቡር አይደለም ባህርና መርክብ የገባል ብንባል ሙሉ ለሙለ እሰየው የምንል ይመስለኛል፡፡ ግን የግድ በነዚህ የህንን አገር አገር ባሰኙ ለሰሩት ስራ አጅግ ቢሚያንሳቸው ጅግኖቻችን ቅርስ ላይ ብቻ ነው ባቡር ፤ ባህር ወይም መረከብ የሚያልፈው /የሚገባው/ ፡፡ የህ አሳዛኝና አሰገራሚ ድራማ አንላዋለን የኔ ዘመዶች ሲተርቱ “ ከንኮ ቂጫን ቀራጩማቲ “ ይላሉ በአማርኛ ለኔ ያው በገሌ ነው አንደማለት ነው ባቡሩ ቢቀር ይሻላል ፡፡

  ReplyDelete
 18. Is is a rumor or something that is going to materialize? If yes, it is unacceptable. I say borrowing Ephrem Eshete's line in his article regarding Waldiba Monastery;some thing like this 'Ethiopian needs both sugar and history'. We need both the railway and our history. We have to build on our history not the other way around-destroy history and build railway...No!

  ReplyDelete
 19. እንዲያውም ሕዝቡ በመንገድ ምክንያት ቤት የፈረሰባቸው ሰዎች ኮንደሚንየም እንደሚሰጣቸው ሁሉ እነርሱም ከዚያ ቦታ ተነሥተው ኮንደሚንየም ሊሰጣቸው ይችላል እያለ መቀለድ ሁሉ ጀምሯል፡፡

  ReplyDelete
 20. Daniel, thanks for sharing your thoughts. I would have loved to see pictures showing how close they are digging.
  regards,
  Milli

  ReplyDelete
 21. The condominium part was very funny :) :)
  BA

  ReplyDelete
 22. ıt is very surprising! ı am just wondering why the train project doesnt use some underground pass in some areas. we dont need to destroy monoments and buildings. when our economy grows, we will do underground metro without affecting the city atmosphare. for now ın very important places we can just do underground pass. this is the case in most countries.

  ReplyDelete
 23. ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡

  ReplyDelete
 24. Dany, yemiyaregut aymeslegnim, karegut gin Ethiopiyawiyan aymeslugnim,ይህን ታሪክና ቅርስ እያጠፉና እያበላሹ የሚመጣ ለውጥ አንገት ቆርጦ ፀጉርን እንደማስተካከል ነው የሚቆጠረው፡፡ እናም የሚመለከታቸው ሁሉ ወደ ርምጃ ከመግባታቸው በፊት ሦስት ጊዜ ሊያስቡ ይገባል፡፡ betam betam liyasibubet yigebal. melkam ababal.

  ReplyDelete
 25. አሁንስ በዛ ! ከልክም አለፈ ! ከሰማይ እሳትና ዲን ወርዶ የየግል በኩሮቻቸውን ሲበላ ካላዪ መኩዋንቱ አይነቁም ማለት ነው? የቤተ ክህነቱ (ቤተ ትክነቱ) እና የቤተ መንግሥቱ በኩራት መሄድ ብቻውን በቂ ደወል አልሆነም ማለት ነው?

  ReplyDelete
 26. ታሪካችንን ልናስከብርና ቀጣይነቱን ልናረጋግጥ የሚገባን እኛዉ ነን፡፡ ታሪክ መስራት ታሪክን ማጥፋት አይጠበቅብንም፡፡ ይህ ጉዳይ የአንድ ወገን ጉዳይ አይደለም፡፡ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ጎሳ ሌላም ሌላም አይለየዉም፡፡ ይከበርልን! ይጠበቅልን!

  ReplyDelete
 27. This is wrong ppl....where are we heading to?.. I am so confused... Please tell them to stop this stupidity...

  ReplyDelete
 28. ‹በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ› አለ ያገሬ ሰው፡፡

  ReplyDelete
 29. abo tarik dabo ayhonim kkkkk

  ReplyDelete
 30. ይህን ታሪክና ቅርስ እያጠፉና እያበላሹ የሚመጣ ለውጥ አንገት ቆርጦ ፀጉርን እንደማስተካከል ነው የሚቆጠረው፡፡

  ReplyDelete
 31. ye selam gize ale,yetornet gize ale, ye amets gizem ale. Ahun ye amets gize new.wetatu tenesa hagerihn astekaklat.maninetihn askebir.mot lelijochih atawrs.

  ReplyDelete
 32. Mass destruction is continued unless we create valuable solution !!!

  ReplyDelete
 33. ካርታውን የሰራው ጣሊያናዊ ነው እንዴ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔም በጣም ተጠራጠርኩ፡፡ አመላቸውን የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡

   Delete
 34. የኮንደሚንየሙ ይቆየንና ግን ከመጣሽ ማርያም ታምጣሽስ ይባል የለ? ምናለ ብንወያይ::

  መንግሥት የርሱን እንደሚለን አልጠራጠርም:: የሱን እየጠበቅን ግን እናውጋ በጨዋ ደንብ እንወያይ:: ይህን ስል የዲያቆኑን ትጋትም በማድነቅም ነው:: ሀሳቡን ወዲ ብሏልና:: የአቡነ ጴጥሮስም ሆነ ሐውልተ ምንሊክ ያስፈልጋል አያስፈልግም አጀንዳ ሊሆን አይችልም:: ስለ ማንነታቸውም ያለ ግጻዌው ማውሳት የሚገባም አይደለም:: ስለነጻነትማ ሞቱልን አዎ አሁን የቸገረንንስ ሰማእታቱ ምን ትፍጠሩልን? ለቀጣዩ ትውልድ የሞቱለትንም የሚኖርበትንም በጋራ ብናወርሰው አይሻልም? ከሆነ ዘንድ ተነስተው መተከላቸው የአክሱምን ሀውልት ካላሳሰቡን በቀር ስህተት የለውም::

  ቦታ መቀየሩን የጠላነው ይመስላል:: ምክንያታዊ ግን አልሆንም:: ለምን? ሁለት ነጥቦችን ላስታውሳችሁ የአቡኑ ረፍት ቦታ የት እንደሆነ የአይን እማኞችና አካባቢው ላይ ያለው ታሪክ የሚያዘክረው ከመንገዱ ዝቅ ብሎ ባለው ቦታ ላይ ነው:: አደባባዩ ላይ አይደለም:: አደባባዩ አመቺ ቦታ ነው:: ወደፊት አመቺ ቦታ ላይ መሥራቱ ስህተት የሚሆንበት ምክንያት የቱጋር ነው? የእምዬ ምንሊክም እንዲሁ:: ሌላኛው ነጥቤ ከሀውልትና ከመቅደሰ አምላክ የቱ ይበልጣል? በተለምዶ ከርቸሌ ይባል የነበረው እስረኛው ሚካኤልን የተሳለማችሁ በመቅደሱ ቆማችሁ ያስቀደሳችሁ ደጃፉን ረግጣችሁ የተሳላችሁና ብጽአን የገባችሁ ታስታውሳላችሁ? የት ነበር ቦታው? ለምን ሀውልት ላይ ጠነከርን? ሀውልት በታሪክ ቦታው ብቻ ካልን የአቡኑስ ይሁን የምንሊክ የት መሆን ነበረበት? አመች ቦታ በሚለው ከተስማማን ግን መስመሩን ዘርግተን የዚያን አካባቢ ጣቢያ ጭምር ምኒልክ/ጴጥሮስ ማለትም ይቻላል:: የሚቆዩበት ቦታ የሚያሳስበን ከሆነ ደግሞ ጥቆማም ማከል ሳያስፈልገን አይቀርም:: ቆይቶም ሐውልቶቹም ተገቢው ቦታ ላይ የሚቆሙበት ሁኔታ ይመቻቻል:: የሚል ግምት አለኝ::

  ሳጠቃልለው ልምዶቻችንን ተጠቅመን መንግሥትን ስንገመግመው:: ይህን ዓይነቱን ወሬ የሚወደው ይንመስለኛል ቶሎ መልስ አይሰጥም:: ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም ለሀውልቶቹ መጠበቅ ያደረገው አስተዋጽኦ ሚዛን ይደፋ ካልሆነ በቀር አፍራሽ ሚና አለው የሚል ግምት የለኝም:: እንዲህ ዓይነት ስህተቶች የሚደጋገሙበት አጋጣሚ ምንድን ነው? ማለቱስ የሚበጀ አይመስላችሁም? ብዙውን ጊዜ ሥራዎቹን የሚያከናውኟቸው ባለሙያ ድርጅቶችም ሆኑ አማካሪዎቻቸው የውጪ ሰዎች መሆናቸው ይመስለኛል:: በተጨማሪም ለክንውኖቹ በቂ መረጃ በውቅቱ አለማግኘታችን ነው:: ታስታውሱ ከሆነ የቀለበት መንገዶቹ እኮ የበቀሉ ነው የሚመስለው:: የጋራ መኖሪያዎቹም ቢሆኑ በተወሩ ሰሞን ነበር እሸታቸው የደረሰው:: ይህ ዓይነት አካሄድ ግን ጠቃሚ አለመሆኑን መረዳት ያለበት ይመስለኛል :: ምንም ቢሆን መስማታችን አይከፋም:: ሀሳብ ባናቀርብ ችግራችሁን መረዳት እንችላለን:: ባናዋጣም እንመርቀዋለን:: የሚሠራልንስ ለኛ አይደለ እንዴ? ሀሳብ ሀሳብ ሀሳብ ወደፊት...

  ReplyDelete
  Replies
  1. I repeatedly read ur comment to get the point. I like ur idea but I don't agree.

   Delete
  2. እስማማለሁ፡፡ እኔ የማይገባኝ የቁምነገር እና የቧልት ቦታ አለመታወቁ ነው፡፡ የባቡሩ ነገር በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ሐውልቶቹን ከነሙሉ "ክብራቸው" ተገቢውን ቦታ መስጠቱ ሳይሻል አይቀርም፡፡

   ውድ የባቡር ፕሮጀክት ኃላፊዎች፤ እባካችሁ ሥራችሁን በጥራት እና በጥንቃቄ ስሩ፡፡ እርሱም ለእኛ ሐውልታችን ይሆንልን ይሆናላ፡፡ (የቦስተኑን ባቡር ልብ ይሏል፡፡

   Delete
  3. ኮፍያዬን በአክብሮት ከፍ ድርጌልሃለሁ (ለአኖኒመሱ መዳጄ

   Delete
 35. Ethiopia is the only African country with real and unique history non contaminated with colonialism...look how much is UK's tourism income from the royals weeding and displaying our antiquities in their museums.how could any one with his right mind think development on the expense of identity! look around other African countries they lost their identity, their language, their culture, religion everything...they still don feel alive,lost their self being w/c they could never recover it. think for a second what this patriots granted us sacrificing them selves..it is valuable! we can't import our identity from Europe of China!

  ReplyDelete
 36. This is not stupidity. We need the construction of the rail road. These monuments can be put somewhere else if they have a negative impact on the on construction or development of the rail road.

  ReplyDelete
  Replies
  1. WHAT IS THE MEANING OF NEGATIVE IMPACT JAL???

   Delete
  2. መስፍን ከአዋሳNovember 29, 2012 at 6:07 PM

   Do you know what you are talking about, a shame on you

   Delete
 37. Don't touch our great king & our great patriots memorial please.

  ReplyDelete
 38. http://www.fanabroadcasting.com/index.php?option=com_content&view=article&id=1229%3A2012-11-23-17-04-15&catid=102%3Aslide

  ReplyDelete
 39. lehulim Ethiopian lekirisitayanu lemuslimu lehulum balewileta nachew hawilitachew liferis ayigebawim. bahilina turisim min yilal silezih gudaylay?

  ReplyDelete
 40. የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ግራ እየግባኝ ነው። መንግስታችን በቅርሶቿ ላይ ያለው አቋም ምን እንደሆን ግራ ያጋባል። ከአልጠፋ መሬት ገዳማትን አፍርሶ ፋብሪካ፣ ሀውልት ነቅሎ መንገድ ምን የሚሉት ልማት ነው? በሌላ በኩል ለታላቁ መሪያችን ሙዚየም አሰርተን አጽሙን ከዚያ እናኖራለን ይባላል። ጥሩ ነው። ግን የቀደሙት ታናሽ መሪ ስለሆኑ ነው ሀውልታቸው የሚነቀለው። ለነገሩ መብራት ሃይል፣ ውሃ ልማት፣ ቴሌ እና ለሎች ተቋማት የዘረጉትን መሰረተ ልማት መንገዶች ባለ ስልጣን በሚያፈርስባት ሀገር ምን ይጠበቃል። ችግሩ የዦሆኖች ጠብ ለሳሩ መሆኑ እንጅ። እንግዲህ ከታሪክ እደምናውቀው ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት መልቀቂያ ምልክቱ ሀግርን፣ ሕዝብን፣ ቅርስን፣ እምነትን መዳፈር ሲጀምር መሆኑ ነው። ከፈጣሪ ቁጣ ካልተማሩ ምን ይደርግ።
  እግዚአብሔር ሀገራችን ይባርክ።

  ReplyDelete
 41. ‹‹የእሷ ውበት .... የእኔ ጠባሳ››
  አንድ ልጅ ፊቷን እሳት የለበለበው እናት ነበረችው፡፡ ልጁ የተማረና ዐዋቂ ተብሎ በከተማው የሚከበር ነበርና ጓደኞቹ ወደ ቤቱ ሲመጡ እንዳያፍር እናቱን ጓዳ ደብቋት ይኖር ነበር፡፡ ነገር ግን ከዕለታት በአንድ ቀን እናቱ ጠራችውና ‹‹ልጄ መልኬ ለምን እንዲህ እንደሆነ ብታውቅ ኖሮ አታፍርብኝም ነበር›› አለችው፡፡ ልጇም መልሶ ‹‹ግን ለምንድን ነው? እማዬ›› አላት፡፡
  ‹‹በልጅነትህ በአልጋ አስተኝቼህ እኔ ውጭ ሳለሁ በቤት ውስጥ እሳት ተነሳ፡፡ ያን ግዜ አንተን ለማውጣት በእሳቱ መካከል ገባሁና እኔ እየተለበለብኩ አንተን በብርድ ልብስ አቅፌ ወጣሁ፡፡ ያን ግዜ እኔ ባልለበለብ ኖሮ አንተ ዛሬ በሕይወት ቆይተህ ለክብር ባልበቃህ ነበር›› አለችው፡፡
  ልጁም የሠራው ሁሉ ጸጸተው፡፡ ወዲያው ጓደኞቹን ጠርቶ ሰማዕቷ እናቴ ይህች ናት! የእርሷ ውበት ከኔ ላይ ነው የኔ ጠባሳ ደግሞ ከእርሷ ላይ ነው አላቸው ይባላል፡፡
  የዚያች ሴት ተምሳሌት እናት ኢትዮጲያ ናት፡፡ የጀግኖች እናት ኢትዮጲያ ልጆቿን በነፃነት ለማሳደግ ያልተቀበለችው መከራ የለም የመርዝ ጢስ አጥቁሯታል፡፡ የጦርነት እሳት ገርፏታል ጠባሳውም በዓለም ተደናቂ የነበረ ውበቷን ለውጦታል፡፡ ከልጆቿ መካከል አንጋፋዎቹ እንኳን በሰው ዘንድ በእግዚአብሔርም ዘንድ ተወዳጅ የሆነች አኩሪ ታሪክ ያላት መሆንዋን ስለሚያውቁ የሚመኩባትና የሚኮሩባት ሲሆኑ የአእምሮ ጨቅላነት ያለቸው ጥቂቶቹ ልጆቿ ግን ከድህነት ጠባሳዋ የተነሳ የኢትዮጲያ ልጆቿ ነን ለማለት ሲያፍሩ፤ሲሸማቀቁ ይታያሉ፡፡ ይህም ጡት ነካሾች፤ተስፋ ቢሶች ከሚያሰኛቸው በቀር የእነሱ ክዳት ትዕቢት ክብሯን አይቀንሰውም ሉዓላዊነቷን ዝቅ አያደርገውም ምክንያቱም የጥቁር ህዝብ እመቤት የነፃነት ባለቤትና የጀግኖች እናት ናትና፡፡ ታላቁ መንፈሳዊ አርበኛ ቅዱስ ጴጥሮስም የእሷን ማንነት ለማድመቅ፤የታሪኳን እርከን ከፍ ለማድረግ የሃይማኖታችንንም ልዕልና ለማስጠበቅ በጥይት አሩር ቆስለውና ተጎሳቅለው ለእኛ ነፃነት ሰጥተው ስላለፉ ሰማዕቱ ቅዱስ አባታችን ሆይ ዘላለማዊ ክብር ይገባዎታል፡፡ የእርስዎ እንደ ጥይት መበሳሳት የእናት ኢትዮጲያ ውበት የሚለውጥ የተዋህዶ ልዕልና የሚገልጽ ሰማዕተነት በመቀበልዎ አኩሪ መንፈሳዊ የክርሰቶስ አርበኛ እያልን ከፍ ከፍ ልናደርግዎ የተገባ ነው፡፡ ፍስሓ ከጉለሌ

  ReplyDelete
  Replies
  1. alem gebregziabiher(mekelle)November 29, 2012 at 9:28 AM

   @ anonymous nov 24 3:35 wooooooooow!!!!! i like it ma bro.it's so amazing & awesome idea.keep it up pls.

   Delete
 42. This is the plot of "Mussolini and his followers" who has been defeated by our beloved King Minilik II and Abune Petros and the "Banda" Woyane is their robot that can be manipulated by a remote control or by their long hands. So, we must fight this nonsense idea, which destroys our heritage, our identity our history.

  ReplyDelete
 43. uuuuuuuuu ere geta hoy temeliketen niketachew ejig bezitual.....le grazi hawilt sisera yenesun mafires ??????????? andand sewoch dani yehone neger endiyaderig kemeteyek hulachinim betsom beniseha,betselot wede amilakachin enchuh. mefitihem enagegnalen

  ReplyDelete
 44. It is a fair share of worry and concern that every one should take a part. Daniel Kibret has said some and others next. But still we seen some people who try to blame the government by blaming these innocents like Daniel together. Well for full brain thinkers this man doesnt have any relation with Woyane. He only shared what he feel about the worry that we all have about wrong ideas of government for good purpose. So lets not blame him together.
  We can be sure to something from our pasts. If we think the way we use to, change is hard to come. But we if think differently it is going to be easy to accept or reject new ideas and even find ideas. Lets pay the engineer to the work to find a solution to change the plan, Lets pay a different attention to our old historical places to be seen and protected as a means of income even to contribute to the city so that government will not dare to destroy them, Lets think that the rummer is out of real fact and we will get everything ok after a year, Lets think that we have a government body that only knows what he does is on the free consent of the whole people so that the train idea is the idea of the 80 million, so we have to tell them how much we will be hurted if they destroy it, and a lot more ideas....Re think the way we think bc it is all possible ............

  ReplyDelete
 45. DN amelk yetbekhu Melkam Eyta !!!!

  ReplyDelete
 46. የምናመጣው አዲስ ነገር ባለን ላይ የሚጨመር እንጂ ያለንን የሚያጠፋ መሆን የለበትም!!!

  ReplyDelete
 47. እናንተዬ አሁንስ ግራ ገባኝ ምን አየተደረገ ነው ምነው ለባቡር የሚሆን ቦታ ጠፋ እንዴ በቃ እነዚህን ቅርሶች /ቅርሶች ብቻ አይደሉም ማንነትም ጭምር እነጂ/ ማንነታችንን ከነካ በሌላ ቦታና በአመቺ ስፍራ ለምን አይሰራም ምነው ቀለበት መንገድ ሲገነባ የነገሌን ኤንባሲ ይነካል ተብሎ እኮ የተደረገውን እናውቃለን ምነው እምዬ ሚኒልክና አቡነ ጴጥሮስ ላይ ይህ መታሰቡ ከነገሌ አምባሲ ክልል መነካት የኛ ማንነት አይበልጥም ማንነቱን ጠብቆ ሃገርን የሚያለማ ገዥ ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 48. ከዕለት ዕለት አልገባኝ እያለ የመጣው ነገር ቢኖር ሰዎች ለማሰቢያ የተፈጠረልንን ጭንቅላት የት እየተውነው እንደሆነ ነው፡፡ ወይስ ኢትዬጵያ የምትባለው ምድር ላይ መኖር የጀመሩት ጸረ ኢትዬጵያውያን ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት የሆኑትን እስቲ መለስ ብለን እናስታውሳቸው .....ኤርትራ ፤ አሰብ ፤ ባንዲራ ፤ ኦጋዴን ፤ (እስታዲየም የገባ ሕዝብ አቶ ታምራት ላይኔን ቢወዳቸው ነበር የሚከፋኝ) ፤ (የአክሱም ሃውልት ለሲዳማው ምኑ ነው) ፤ (የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲን ለምን እንዳላፈረስነው እስካሁን መልስ የለኝም) ፤ ባድመ ፤ የአሸባሪነት ሕግ ፤ መሬት ለሳውዲ እስታር ፤ መሬት ለሱዳን ፤ ዝቋላ ፤ ዋልድባ ፤ የሰማዕተ ጽድቅ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ፤ የአጼ ምንሊክ ሃውልት .....ሌሎችም ብዙ ያልጠቀሰኳቸው... በዚሁ ገጽ እንኳን ካላይ የጻፍከው ወንድሜ (AnonymousNovember 23, 2012 10:58 AM) ምን እያልክ እንደሆነ ገብቶሀል ወይስ ለመጻፍ የፈለግከውን ነገር ከጭንቅላትህ ቁጥጥር ውጪ ነው የሚወጣው መቼ ነው ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ደም ስትመጥ ያየከው የኢትዬጵያ ቤተክርስቲያንን አንድ ሰው ሊጠላት የሚችለው አንድም ጸረ ኢትዬጵያ አንድም ጸረ ጥቁር ሲሆን ብቻ ነው፡፡ አልያም ይሄ እንደቀየሱለት የሚፈሰውን የራሱ የሆነ ምንም ዓይነት አመለካከት የሌለውን ጎርፍ መሳይ ተንቀሳቃሽ አካል እስካልሆነ ድረስ..የድንግል ማርያም ልጅ ወልደ አብ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኢትዬጵያን ለኢትዬጵያውያን ያርግልን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 49. @AnonymousNovember 23, 2012 10:58 AM

  ሆዳም ነገር ነህ ሰዉ መላ ሂዎቱን ሰዉቶ ባመጣዉ ነፃነትና በጠበቃት ሀገር ላይ እየኖርክ ስለነሱ ማሰብ አትፈልግም ጭራሽ ትሳደባለህ፡፡ እንዳንተ አይነቱ ደደብ እኮ ነዉ ሀገሪቷን እየገደላት ያለዉ፡፡ ኢትዮጵያዊነት ካልተሰማህ ባህር ማዶ ሂድና በግዞት ተቀምጠህ የሰዉ ሳንዲዊች እየበላህ ሆድህን ሙላ ከርሳም፡፡

  ReplyDelete
 50. “አቡነ ጴጥሮስ ለሊቱን በግራዚያኒና በግራዚያኒ ባንዶች ሲደበደቡ አደረሩ፡፡ በገነተ ልዑል ጉርጓድ ቤት ውስጥ ሲገረፍ ሲመረመር ኢትዮጵያን ከድተህ በሞሶሎኒ እመን ተብሎ ሲብጠለጠል አድሮ በማግስቱ ጠዋት ሰኔ 21 1931 ዓ.ም በአደባባይ በጥይት ተደበደበ”
  ከሎሬት ፀጋዩ ገ/መድህን የተወሰደ
  እኔ የምለው ተደብድበው የተገደሉባት ቦታ ላይ ያለችው ትንሽዬ የመታሰቢያ ድንጋይ /በእምነበረድ የተሰራችና እዚህ አረፉ የምትል ፁሁፍ ያለባት መታሰቢያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር አጥር ስር መወሸቋ ሁሌም ይገርመኝ ነበር አሁን አጥሩን ሲያጥሩ ምናለ ዝቅ አድርገው አጥረውት በግልጽ ቤታይ እል ነበር ይባስ ብሎ ከሱ ፊት ለፊት የለውን የአብኑን ቅርጽ የያዘውንና በጉልህ የሚታየውን ለማንሳት ታሰበ እኔ የምለው ይሄ ዘመቻ ማን ነው የሚባለው ደግሞ በአንድ የወረራ ታሪ ክ የተሳተፎ የአገር ገዚንኛ የሀይማኖት መሪን ታሪክ ለማጥፋትሰ ለምን ተፈለገ ጊዜው ይለያይ እንጂ የሁለቱም ታሪክ ተመሳሳይ ነው ፋሽስት ኢጣሊያ እኔ የምለው የፋሽስቱን ክፉ ስራ የሚያዘክረን የኛንም አልበገሪ ባይነት የሚሰብከንን ይህን ሃውልት ለማንሳት ተወሰነ አላችሁኝ ቆይ ቆይ ግዲላችሁም የስድስት ኪሎውንስ አይነካውም ማን ያውቃል ፋሽት ዛሬስ በኛ ልብ ውስጥ አድሮ ቢሆን በባንደዎቹ እኛ የታሪክ ባንዳ ልንሆን አይደል ያሳዝናል

  ReplyDelete
 51. here is amazing and unbelievable for the moment i don`t know for the furure what happen

  ReplyDelete
 52. The stupid is the one like Daniel Kibret who wants to disseminate his own dirty ideas. By any means we Ethiopians should desire the development of our nation rather than worrying about lifeless stones stood there.

  ReplyDelete
  Replies
  1. You are lifeless stone rather! You don't know what these monuments mean. I can't explain their meanings and benefits to those lifeless stones like you.

   M.G

   Delete
  2. WE ETHIOPIANS ARE UNDERGOING UNBEARABLE SUFFERINGS BECAUSE OF THE DAMN STONE HEAD MONSTERS LIKE YOU. TRUE ETHIOPIANS KNOW THAT WOYANES ARE BRAVE ONLY IN DESTROYING THE RICH HISTRY ETHIOPIANS ARE VERY MUCH PROUD OF. LIFE LESS STONE...? ITS YOU WHO IS LIFE LESS WHO CHASES THE TAIL OF THE WHITES FOR THEIR LEFTOVER BURGERS...DAMN YOU...YOU ARE NOT AN ETHIOPIAN...YOU ARE A MAN IN DEVIL WHORE.

   Delete
  3. Are you even listening to yourself? I don't want to go down to your level of "dirty name-calling" fiasco, but I'd like to say this to you my friend. You said "we Ethiopians," but I don't think you have got a single tissue of Ethiopianness running through your veins. A person who claims to have a country will not dump its history and heritage into the ditch.
   No one's against the development scheme. We all loved it, and we all need it. All Daniel said was "Let's also think of the historical significance of those statutes alongside the railway project," and I hope the project will take that into consideration.
   We didn't became "Ethiopians" by a mere miracle. Our forefathers and foremothers have fought, won, and died for this land. It should be the responsibility of the current and future generations to treasure their good deeds and strive to materialize the nation's prosperity. So get that through your head, before you start bad-mouthing your country (if Ethiopia's trully your country).

   Delete
  4. መስፍን ከአዋሳNovember 29, 2012 at 6:25 PM

   ላንተ ከርስህ ታሪክህም እድገትህም ህይወትህም....ነው አይደል? እሺ አሁን ካህያ የምትለየው በምንድን ነው? ማፈሪያ፤ ድሮስ ሆዳም እንዴት ታሪክ ያውቃል? "ሁፍህ በጣም ገማኝ ጭንቅላትህ ደግሞ እንዴት ይገለማ ይሆን? ዙሪያህ ላሉ ሰዎች ፅናቱን ይስጣቸው። ለማንኛውም ታጠብ

   Delete
  5. yedanin yahl aynina chinkilat binorh bemin edlih that is why beafih yemitaraw. dani keep it up

   Delete
 53. ቅንነቱ ካለ ሁሌም መፍትሔ አለ። አገራዊ አሻራዎቻችንን ለማጥፋት ከመፋጠን በፊት ተረጋግቶ ማሰብና መነጋገርን ይጠይቃል። እኔ የከተማ መሬት አጠቃቀም (Urban Land use planning) ባለሙያ ነኝ። አዳዲስ የማስፋፊያ ግንባታዎች ሲመጡ እንዲህ አይነት ነገር እንደሚያጋጥም አውቃለሁ። ከውዥንብሩ ለማትረፍ የሚሞክሩ አካላትም አይጠፉም። እንደ ባለሙያ ግን ጥቅምና ጉዳቱን ለይቶና ተንትኖ ማቅረብ ግድ ይላል። ይሄን ነገር ፓለቲካዊ ወይም ሀይማኖታዊ ቅርጽ በማስያዝ፤ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ መምራት የሚጎዳው አገርንና በውስጧ ያሉትን ሕዝቦቿን ነው። መንግስትም ከዚህ ምንም አያተርፍም። በታሪክ ተጠያቂ ከመሆን ውጭ። ባለሙያዎችን ጠርቶ በግልጽ፣ ፊት ለፊት እንዲከራከሩበት ማድረግ ያስፈልጋል። በውኑ ለታሰበውና ለታቀደው አላማ፤ ሐውልቶቹ እንቅፋት የሆኑበትን ምክንያት መተንተን የባለሙያዎች ድርሻ ነው። እኔ እንደሚገባኝ፤ አዲስ አበባ እየሰፋች፤ እየዘመነችና እያደገች ያለችው ሐውልቶቹ ባሉበት አካባቢ አይደለም! መንገድ መዘርጋትና መስፋት ያለበት ደግሞ እድገት ባለበት አካባቢ ነው። ከሚዘረጋው ባቡር መስመር የልቅ፤ የሐውልቶቹ ቦታቸው ላይ የመቆየቱ ፋይዳ፤ ለከተማዋ ተወዳጅነት፤ ለቱሪስት መስህብነት ታላቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ይመስለኛል። የነጻነታችን ምልክቶች ናቸው። ለታሪክ ሲሰብኩ የሚኖሩ አንዳች ሀይል ያላቸው -ሐብቶቻችን። በአለም ላይ የተከለከለን መርዝ በአውሮፕላን እየረጨ፤ ውድ የቀድሞ ወገኖቻችን እንዲያልቁ ትዕዛዝ ያስተላለፈው ግለሰብ አገሩ ላይ ሐውልት ሲቆምለት፤ ይህ ፈጽሞ አይሆንም፣ የነጻነት አገር ነች፣ ህዝቦቿም፣ ምድሯም ላንተ አትገዛም፤ ብለው በአደባባይ መስከረው ያለፉት አባታችንን ግን፤ የተሰውበትን ቦታ ቢያንስ ለማስታወስ አለመፈለግ ታላቅ ስህተት ነው። ያን ቦታ አጥፍቶ ባቡር እንዲሄድበት ለማድረግ መከጀል፤ ሰው መሆንንም መርሳት ነው! ሞሶሎኒ ለፈጸመው በደል ማስተዋሻ ሲቆምለት፤ እኛ ደግሞ ሌላውን አማራጭ ለመከተል መሞከር፤ ምን አይነት ጉዶች ነን ያሰኛል! ባርነትን ናፋቂዎች ናቸው የሚለውን የአንዳንድ ሰዎች አሽሙርም ያጠነክራል። እንዲህ እያሉ መቀጠል ይቻላል! ልቦና ካለን አንዳ ቃል በቂ ነች!!! ወደ ራሳችን እንመልከትና-ስራችንን እንመርምር!

  ReplyDelete
 54. አላዋቂ ሳሚ ይሏል እንዲህ ነው ዳኒ .......

  ReplyDelete
 55. Guys i mean is that impossible to shift the location of the monuments as i understand those historical peoples did history not on that place ( on current location of monument) so why don't we think like that if they are shifting the location because of the railway line.

  ReplyDelete
 56. ደኒ የሚሰማ አካል አለ ብሰህ ነው። የታሪክ ጉዳይ እኮ የቤተክርስቲያን ጉዳይ አድርገው ነው የሚያስቡት።።

  ReplyDelete
 57. ኢጣሊያ የስንት ንጹሃን ኢትዮጵያውያንን ደም ላፈሰሰና በእብሪት ተሞልቶ ሉዓላዊነታችንን ለደፈረ ለሞሶሎኒ ጀግና ብላ ሐውልት ስታሰራ የኛዋ ሃገር ኢትዮጵያ ግን አገራቸውን፣ ሕዝባቸውን፣ እምነታቸውን ከወራሪ ጠላት በጸሎታቸው እና በደማቸው ሲጠብቁና ሲያስጠብቁ የኖሩትን የታላቁን ሰማዕት የአቡነ ጴጥሮስን እና የዐፄ ምኒልክን ሐውልት ለማፍረስ ደፋ ቀና ማለት ምን ይሉታል? በታሪክና በማንነታችን ላይ የተቃጣ ትልቅ አደጋ ነውና ታሪክ እያፈረሱ ታሪክ መስራት ስለማይቻል መንግስት ሆይ ቆም ብለህ አስብ።

  ReplyDelete
 58. alneqa belen new enji yemimerun yetalian banda lejoch ena talianoch fashistoch meselugn,anawuqem ende?endemayawuq sew lemen tadenaquralachihu?

  ReplyDelete
 59. Dear Ethiopian government, i appreciate your effort to establish railway in Addis. That is great! But when i heard this news, i feel very sad. This news hurts me very much. I am in deep sorrow.... So please reconsider the planning.

  ReplyDelete
 60. Tarken lemaferares sayhone tareken lemakyete yabekane aye Dani gezew keftwale mane ketenantu temare beleh new endeante yalewen bewentu yabezalen berta wendeme.

  ReplyDelete
 61. I hope this relieves every one

  http://www.fanabroadcasting.com/index.php?option=com_content&view=article&id=1229%3A2012-11-23-17-04-15&catid=102%3Aslide

  ReplyDelete
 62. what about building a tunnel? It is possible to keep our heritage in thier current form. If their is a will, that should be considered unless the primary goal is to destroy these land marks in the name of development.

  ReplyDelete
 63. እኔ የምለው እራ ባካችህ ከእንቅልፋችን እነንቃ ….በ ሀውለቴች መፍረሰሰ እኔም አልስማም ነገር ግን በዚህ በስለጠነበት ዘመን መፍትሄ አይጠፈም …በዛ ላይ መንግሰት ተመለሶ እንደሚተከሉ መግለጫ ስጥቶል ….እንካን የሚኒለኪ የመንግሱቱም ሀውልት አልፈረሰም ….የለመረጃ በጭፍን አነናገረ ወንድሞች…ስንት ስራ ከ ፊታችን እየተጠበቀን ነው …..

  ReplyDelete
 64. why don't they try other approach rather than destroy it please stop them!!!!!
  IF THERE IS NO PAST THERE WILL NEVER BE FUTURE

  ReplyDelete
 65. Guys,

  Let think out of the box. If we believe that development has to come it has to come at a reasonable price. Those who just are living their luxurious life, should not disseminate rumors that hinder our development. The government has clearly mentioned that the monument will be taken to a safe place until the rail way is build and will be re-erected. Some people can not see just a little bit above their personal cult. Most of you may be living out side the country. But for us living in Addis, TRANSPORT is a critical problem we are facing every day. Hence, we don't want any body to be obstacle to the government effort to solve this big problem of ours, the poor. It is not fair to link development efforts as degrading culture, history and region which seems to have some political motive. We know that some bloggers are promoting politics in the pretext of religion and would like to say Enough is Enough!

  ReplyDelete
  Replies
  1. As you said, thinking out of the box, is important. Do you believe that those cultural identities of the country not important? And is it possible to establish as they(monument) was in the past? If possible it is OK! But here i want to say in open and clear attitudes....
   I did not agree by the saying enough is....

   Delete
 66. enae yemelew neger yehi hager yega aydelhem endae ebakahu menem deh benhonem betarikation batisalku teru new egzabehare tagashe new tagesom yeferdal ahune lalenbet nesanetena manenet yabekune enzhi hawltohe nahew manem yekom bimeselew edywedke yetenkeke.

  ReplyDelete
 67. tarikachnen yemiyazaba neger mengistachn endemaysera b.ergitegna negn!.

  ReplyDelete
 68. Wow Yekotun awerdalew bela yebebetwan talech.

  ReplyDelete
 69. Talian yegrazianin haulit siteklu egna degmo ye minilikin linaferse new

  Good Job EPRDF

  ReplyDelete
 70. I want to give a reply to the eigth anonymous form top to bottom. you must be one of those bloody woyanes(TPLF) who are the enemies of our country and its people. you guys are eating my people. those monuments are our identity. you stupid TPLF people tried to destroy our monastries. you know what OUR GOD had done. 'Aba' paulos and evil Melese are dead together in a week. your bloody leader Melese is gone once and for all and he will burn in hell for eternity. you stupid and idiot TPLF assholes, it will not be long before you will be dumped from our country. you evil people you will get what you have done. death to TPLF. you destroyed my country. God is great: He took the life of bloody MELESE ZENAWI !!!!!! thank GOD,ellllllll

  ReplyDelete
 71. አፍርሶ መገንባት አሁንም አፍርሶ መገንባት እንዲህ እንዲህ እየተባለ ቀዳሚ የነበርን ህዝቦች ወደኇላ ቀርተናል

  ReplyDelete
 72. መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡

  ReplyDelete
 73. እንደምንድነህ ዲያቆን ዳንኤል፣ ሐውልቶቻችን የእኛነታችን መገለጫ፣ መኩሪያችን፣ ኩራታችን ናቸው፡፡ ቅርሶቻችን ናቸው፡፡ ታሪክ ጥሩም መጥፎም በቃ ታሪክ ነው፡፡ መነሻና ማመዛዘኛ ነው፡፡ በሥልጣኔውም ቢሆን የመጀመሪያዎቹ ነን አሁን ደርሰን ወደኋላ ብንሆንም፡፡ የአቡነ ’@ጥሮስ ሐውልት የሃይማኖታችን ምልክት ነው፡፡ እምቢ ለሀገሬ ባይነታቸው፣ ሀገሬን አልሸጥም ጥቃት አይገባትም፣ ለጣሊያን አልገዛም፣ ሀገሬን አልከዳም፣ ከአንድ የጦር መሪ ያልተናነሰ ተጋድሎ በማድረጋቸው ለሀገራችን በሃይማኖትም ሆነ በኢትዮጵያዊነት የሚከበርና የሚያኮራ ነው፡፡ ለጣሊያንም ቢሆን ሐውልቱ ቆሞ ሲያየው እንዳይመስለን ጥንካሬያችንን ያደንቅበታል ታሪክ ነውና፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለፈጀው ግራዚያኒ ዘመዶቹ ሐውልት ሲያቆሙ እንኳን ትንሽ አይቆረቁራችሁም? አፄ ምኒልክም ቢሆኑ ኢትዮጵያ ሀገር የገዙ ንጉሥ፣ አድዋ ላይ ጣሊያንን ድል ያደረጉ፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሣይሆን ለአፍሪካ ኩራት የሆኑ የጥቁር መሪ ናቸው፡፡ እንዴት ነው ነገሩ አረ ማስተዋልን ይስጠን፣ መነሻ የሌለው ሰው እኮ አይደለንም፡፡ እኔ የማነኝ ማለት ያስፈልጋል፡፡ አፍ እንዳመጣ እይናገሩም እግር እንዳደረሰ አይሄዱም መሞት መታሰር እና ገደል መግባት ይመጣል፡፡ ሊታሰብ እና ሊገመት ያስፈልጋል፡፡ አፄ ምኒልክ የባለ ብዙ ድልና ባለውለተኛ ናቸው፡፡ ለሥልጣኔ ቀድመው ባቡር ያስገቡትን ትላንት፣ እናንተ ዛሬ ተነስታችሁ ልታፈርሱ? አረ ለመሆኑ እንዴት መጣላችሁ? አረ የሠይጣን ጆሮ ይደፈን ነው የምንለው፡፡ አረ ቆም ብላችሁ አስቡ እናንተ ፀረ ታሪክ አትሁኑ፡፡ ምነው ዲዛየኑን ሲሰጥ ይህን ቦታ ለሀገሪቱ አስፈላጊ ስለሆነ በማይነካው መልኩ ማለት አይቻልም? ከዚያስ በኋላ ከመቀበል የለም ማሻሻያ ይደረግበት ይባላል እንጂ ምን እዳይሆኑ ነው በውድም በግድም ይሆናል በማለት ነው? ከሆነም ባለነፍጥነን ምን ያመጣሉ ነው? የትውልድ ጥያቄ አለበት፡፡ የዓለም ጥያቄ አለበት ይህንን ማወቅ ና ማሰብ ያስፈልጋል ፀሎች ነው የሚያስፈልጋችሁ ማስተዋሉን ይስጣችሁ ይገለጥላችሁ፡፡ ገነት ታምራት

  ReplyDelete
 74. በመጀመርያ እይታ ግሩም ነው ምክንያቱም ክእዝብ ነውና ታድያ ምኑነው ጥፋአቱ? የድያኰን ዳንዔል አንዳንድ የእዝብ አስተያየት አንብቤ ነው ጥፋአተኟ አድርገው ስለተመለከቱት ክመንግስት በጥናት የተደገፈ መረጃ ለእዝቡ ያለማስያዝ ነው እንጂ የእዝቡም የድያኰንም ጥፍአት አይደለም እውነት በአውልቶቹ ላይ ጥፋት የማይደርስ ከወነ መንግስት መቼም እጁን ከቤተክርስቲያን አላነሳአምና ዲ/ዳኒ አንተን በመወከል መልስ ለመመለስ ብዬ እንዳልወነ ይታወቅልኝ አንተ ምርጥ ኦርቶዶክሳዊ የኢትዬጵያ ልጅ ነእና

  ReplyDelete
 75. ye aba samuiel amlak abune PAWLOSNm yawkachewl!!!! ahunm HAYLACHIN KINDACHIN yehonew amlak sirawn yketilal... ene amnalehu YFERDAL ayzegeym

  ReplyDelete
 76. minim malet alchilim,egzabher ethiopian yitebikat.

  ReplyDelete
 77. Abune Petros apart from being Martyr for the National hero of struggle against fascism and for freedom, he is a world heritage by the fact that he is one of the 40 Martyrs of the Millemium chosen by UNESCO. His Statue is therefore a world heritage, and cannot be displaced w/o prior consent from UNESCO. God Bless and protect Ethiopia from misguided zealots.

  ReplyDelete
 78. I don't know when we, Ethiopians, think in a way we be able to build a common national interest where differences are compromised. this is not politics or religion, it is our sense of nationhood. there is no question that these historical monuments are very much essential not only for Ethiopians but also for all other Africans who had been in a terrible condition for many years by colonizers. these monuments are our legacies of self-confidence and liberty. so how are we going to be sure that the state is with us given the demolition of the monuments we only have today? if the government wants to assure its legitimacy, there is no way to destruct the statues. I am confident that Ethiopians will never tolerate such deeds but I also sure that the government acknowledges the statues and special care will be given.
  "think globally, act locally." let's civilize ourselves, by depending solely on arguments not on emotions.


  ReplyDelete
 79. I would ask to the people of Ethıopıa We have to stop and rvise our history. Because the histroy of Ethıopıa is consıdered the history of royal kings. It does not represent the history of the people of nation and natoınalıty.

  ReplyDelete
 80. I would ask to the people of Ethıopıa We have to stop and rvise our history. Because the histroy of Ethıopıa is consıdered the history of royal kings. It does not represent the history of the people of nation and natoınalıty of Ethiopia. Minilik has aleardy separated Eritrea from the motherland of Ethiopia. Why do you say he is a hero. Minilık has sloughted the breast of oromo how do you call him a hero of Ethiopıa. And at the same tıme in the buttle of Ethiopia there were alot of hero from oromo and Tigray. But no monement ıs established for this hero because they are not from the main royal family. So Ethiopians must revise theır history and must be established to represent the ethiopian people not the royal family.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Same old cries, same old accusations. I can tell you why Menilik's called Hero in Ethiopia. He led the Ethiopian peoples' remarkable defensive campaign against the Italian occupiers and the subsequent victory at Adwa. He's a hero because he took up his predecessors' endavours to modernize Ethiopia to a whole new level. He may have done some bad things along the way, but he had the unity and prosperity of the nation in his heart. Can you tell the story of a single Ethiopian leader, past or present, who hadn't shade a bit of blood during his reign? I bet you can't. This is part of any given nation's emergence, not a unique case for our country.If you have a better historical reference, bring it on.Don't just cry over the dead fish. And for your information; Eriteria became an Italian colony during Emperor Yohannes'reign, not on Menilik's. We cannot blame either Yohannes or Menilik for not liberating Eriteria then, for they knew the military might of the Italians during that time, and they were curious about the consequences of such actions.So please, don't mix up Menilik's legacy in defending Ethiopia from forign aggression with the local"ethnic opperession," since domestic and foreign affairs have different patterns.

   Delete
 81. ለአቶ ወልዱ ታደለ ለመሆኑ ምን ዓይነት አሳዳጊ ነዉ ያሳደገዎት

  ሰው እንዴት ዉሻ ይባላል ይህን ቃል የተጠቀሙት የእንግሊዝ ቅኝ

  ገዥዎች ናቸዉ፡፡ ህንድን በገዙበት ወቅት፤ እና እርስዎ ተረፈ ባንዳ

  ነዎት እንዴ) ብረት እንን በእሳት እና በመዶሻ ተቀጥቅጦ ይለዝባል፡

  እርስዎን ግን ሥለ ቅርስ ማስተማር ይከብዳል፡፡ በልቶ መተኛት ብቻ

  ሰዉን ሰዉ አያደርገዉም፡፡


  ወለተ ሚካኤል ነኝ

  ReplyDelete
 82. you don`t know the History of Ethiopia and Minilik brother am saying you brother but not you sorry for my mistake!! please before saying some thing this big issue you have to ask your self where i came from and where is my root? really the History of Ethiopia is not for only Minilik and Royal Family please read more and more am sorry for your suggestion.

  ReplyDelete
 83. ‹በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ› አለ ያገሬ ሰው፡፡ የምናመጣው አዲስ ነገር ባለን ላይ የሚጨመር እንጂ ያለንን የሚያጠፋ መሆን የለበትም፡፡

  ReplyDelete
 84. Ante degmo yeman hilmegna neh ibakih? Tarik digami yitsaf? Atasibew. .....

  Menelik was a hero, he is a hero in our heart, and he will ever be memorized as a hero in our children's and their childrens heart. Don't full us in your fictitious history of extremism. He is the only black king who defeated the colonialists. Read your history! He is not a king of one nation, he is the king of black people all over the world.

  ReplyDelete
 85. I always surprised with what I saw on the 125 yrs old Addis Ababa. why the gov't trying to create a second capital of Ethiopia like the other country of Africa (like Nigeria).

  our ancestors create Addis Ababa the way they can, why we create our new Addis Ababa like what we want? why we destroy the valuable assets?

  you know in France no one is interested to re-contract the ancient civilization.why we Ethiopians can't do this?

  ReplyDelete
 86. The project managers seem to be from abroad which want to destroy our history.We shall take a serious look.If they were really Ethiopians their design will not focus on our core heritages.

  ReplyDelete
 87. ይህ የታሪከ ደምሳሽነት ባህሪ ከማን ተወረሰ አምላክ ያውቃል ብቻ መልስ ያለው ፈጣሪ መልስ ይሰጣል

  ReplyDelete
 88. ‹በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ› አለ ያገሬ ሰው፡፡ የምናመጣው አዲስ ነገር ባለን ላይ የሚጨመር እንጂ ያለንን የሚያጠፋ መሆን የለበትም፡፡

  ReplyDelete
 89. menew weodaja:- Talian derse Hedu YE AXUMEN Hwelt memeles Asfelege?

  ReplyDelete
 90. please our leaders do not see yourself as a hero, you know what the country Ethiopia we live here today is with the blood of Abune Petros, Atse Minilik,...please read the history of Ethiopia
  /Please throw your 17 years back-warded philosophy/

  ReplyDelete
 91. bezu awekalew yemalete terefu yeha becha new!
  bewenete egeziyabehare yedagnachew lela men yebalal....

  ReplyDelete
 92. Daniel, I like your thoughts. We have to strive keeping our history.

  ReplyDelete
 93. keamliko yaliweta hizb. benegerachin lay yeninim hone yemanim beminim ayinet mikinyat hawlit serto kebotaw enkuan endayinesa tebikina yemikom sew ke amilko netsa mehon aychilim. eskemigebagn dres gin sewoch tarik yemiserut hawelit endiseralachew aydelem reay silalachew bicha new enante gin reay silelelachu yebalereay sewochin hawilt tamelikalachuh enezi sewoch bisemwachu mineya besakubachu meslachu lemanigawum ayinachun gelet ayimrachun kefet mareg yitekmachuhal egziabher yirdachu. dani berta yemisadebut mesadeb bicha slemichilu new

  ReplyDelete
 94. መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡

  ReplyDelete