Tuesday, November 13, 2012

እኛ፣ የመጨረሻዎቹበፌስ ቡክ የተለቀቀ አንድ ጽሑፍ በምዕራቡ ዓለም የ1950ዎቹን፣60ዎቹን፣ 70ዎቹንና 80ዎቹን ትውልዶች በተመለከተ ‹‹እኛኮ በቶምና ጄሪ ፊልም ያደግን፣ በመንገድ ላይ የተጫወትን፣ በሬድዮ ካሴት ሙዚቃ ያዳመጥን የመጨረሻዎቹ ትውልዶች ነን፡፡›› ይላል፡፡
እኔም ይህንን ሳይ የራሴ ትውልድ ትዝ አለኝ፡፡
እውነትም እኮ እኛ የ1940ዎቹ፣ 50ዎቹና 60 ዎቹ የኢትዮጵያ ትውልዶች ጠቅላይ ግዛት የሚባል አከላለል ክፍለ ሀገርም የሚባል አካባቢ፣ አውራጃ የሚባል ቦታ፣ ምክትል ወረዳ የምትባል ጎጥ ያየን፣ የኢትዮጵያ ንጉሥ በምድር ላይ ሲጓዝ የተመለከትን፣ የንጉሥ ግብር የበላን ወይም ሲበሉ ያየን፣ ንጉሥ ሲወርድ፣ መሪም ሲኮበልል ለመታዘብ የቻልን፣ ደጃዝማችነት፣ ቀኝ አዝማችነት፣ ራስነት፣ ባላምባራስነት፣ ፊታውራሪነት፣ ነጋድራስነት፣ ጸሐፌ ትእዛዝነት፣ አጋፋሪነት፣ እልፍኝ አስከልካይነት ዓይናችን እያየ ታሪክ ብቻ ሆነው ሲቀሩ ምስክር የሆንን የመጨረሻዎቹ ትውልዶች ነን እኛ፡፡ 
የዛሬይቱ ኢትዮጵያን ጋዜጣ፣ መነንና መስከረም መጽሔት ገዝተን ያነበብን፣ የምሥራች ድምጽን ያዳመጥን፤ ሐዲስ ዓለማየሁንና ከበደ ሚካኤልን ጳውሎስ ኞኞንና ዳኛቸው ወርቁን፣ በዓሉ ግርማንና አቤ ጎበኛን በዓይናችን ያየን፣ አበበ ቢቂላ ሲሮጥ፣ ማሞ ወልዴ ሲያሸንፍ፣ ምሩጽ ይፍጠር በሞስኮ ኦሎምፒክ አረንጓዴው ጎርፍን እየመራ ሲፈተለክ፣ መንግሥቱ ወርቁ ሲጠበብ፣ ይድነቃቸው ተሰማ የአፍሪካን እግር ኳስ ሲመራ፣ፍቅሩ ኪዳኔ እግር ኳስን ሊያስተላልፍ ሲታትር፣ ደምሴ ዳምጤ ‹ዳኙ ዳኙ ገልግለን› ሲል ያየንና የሰማን የመጨረሻዎቹ ትውልዶች ነን፡፡
እኛ የመጨረሻዎቹ፤
በ15 ሳንቲም አውቶብስ፣ በ35 ሳንቲም ታክሲ የሄድን፣ በውይይት ታክሲ የተሳፈርን፣ ከቀበሌ በቤተ ሰብ ልክ ስኳርና ዘይት የገዛን፣ በ50 ሳንቲም የቀበሌ ቤት ኪራይ የኖርን፣ የ10 ሳንቲም ዳቦ በአምስት ሳንቲም ሻሂ የጠጣን፣ ያምስት ሳንቲም ጮርናቄ የገመጥን፣ የመቶ ብሮች ጤፍ፣ የአሥር ብሮች ዶሮ የበላን፤ የሃያ ብር ቤት የተከራየን፤
እኛ የመጨረሻዎቹ፤
ጎረቤት ሄደን ቴሌቭዥን ያየን፣ ቴሌቭዥን ለማየት ብለን ለሀብታም ጎረቤት ያገለገልን፣ በነጭና ጥቁር ቴሌቭዥን የተዝናናን፣ በአባባ ተስፋዬ ተረት ያደግን፣ በወጋዬሁ ንጋቱ ትረካ ጥርሳችን የነቀልን፣ ‹‹ሾላ እርግፍ እርግፍ›› የተጫወትን፣ በ‹‹ማዘር ኢንዲያ›› ያለቀስን፣ ንፋስ እንደመታው የገብስ እህል እየተወዘወዝን ‹ሀ ግእዝ፣ ሁ ካእብ ሂ ሳልስ›› ብለን በልጅነት ያዜምን፣ ለትምህርት ቤት መመዝገቢያ ሃምሳ ሳንቲም፣ ለስፖርት አንድ ብር የከፈልን፤ በጆንትራ ቮልታ ያጌጥን፣ ሎሚ ተራ ተራ ዘፍነን ቡጊቡጊ የጨፈርን፤
እኛ የመጨሻዎቹ፤
በቪሲአር ካሴት ፊልም ያየን፣ በፎቶ ብቻ ያለ ቪዲዮ ሠርግ የሠረግን፣ ወይም ሲሠረግ ያየን፣ ፎቶ ተነሥተን በአሥር ቀን የደረሰልን፣ ከትምህርት ቤት ጓደኞቻችን ጋር ተደርድረንና ተቃቅፈን በነጭና ጥቁር ፎቶ የተነሣን፣ ያለ ሙዓለ ሕፃናት አንደኛ ክፍል፣ ያለ ‹ፕሪፓራቶሪ›› ኮሌጅ የገባን፣ ‹‹በየኔታ ጉሮሮ ጠጅ ይንቆርቆርበት፣ በኛ ጎሮሮ አጥንት ይሰካበት›› ብለን ለመምህራችን ያዜምን፤ ትምህርት ቤት ለመግባት በቀኝ እጃችን በአናታችን በኩል ጆሯችንን እንድንነካ የተደረግን፣
እኛ የመጨረሻዎቹ፤
ለዕድገት በኅብረት እንዝመት
ወንድና ሴት ሳንል በአንድነት
እየተባለ ዕድገት በኅብረት ሲዘመት ያየንና የተሳተፍን፣ ለሶማልያ ጦርነት ሲዘመት የነበርን፣ ለእናት ሀገር ጥሪ ቆሎ የቆላን፣ እንጀራ የጋገርን፤ ሲጋገርም ያየን፤ የ66ቱንና የ83ቱን አብዮት ያየን፤ መሬት ላራሹ ሲታወጅ፣ ትርፍ ቤት ሲወረስ፣ ‹የፍየል ወጠጤ ልቡ ያበጠበት› በሬዲዮ ሲዘፈን ልባችን የቆመ፤ ነጭ ሽብርና ቀይ ሽብር ሲፋፋም በመካከሉ ያለፍን፤ መኢሶን፣ ኢዲዩ፣ ኢጭአት፣ ኢማሌድህ፣ እየተባለ ሲፎከር ብናውቀውም ባናውቀውም የፎከርን፤ ከጫካ ይተላለፍ የነበረውን የኢሕአዴግ ሬዲዮ ተደብቀን ያዳመጥን፤
እኛ የመጨረሻዎቹ፤
የይለፍ ወረቀት ከቀበሌ አውጥተን ክፍለ ሀገርን ያቋረጥን፣ በኬላ ላይ ቆመን መታወቂያ አሳይተን ያለፍን፣ አኢወማ ገብተን፣ መኢሰማን አልፈን፣ አኢሴማ ተሳትፈን፣ በመኢገማ ተደራጅተን የፎከርን፣ የተሰለፍን፤ በዘመቻ ተወልደን በዘመቻ ያደግን፤ የውይይት ክበብ፣ የማሌ ጥናት የተሳተፍን፣ የሞስኮ ሬዲዮ ያዳመጥን፣ ወዛደራዊ ዓለማቀፋዊነትን ያነገብን፣ መደብን ከመተኛነት ወደ መደብ ትግል ያሸጋገርን፤ አድኃሪ፣ አቆርቋዥ፣ መሐል ሠፋሪ፣ ጨቋኝ፣ ተጨቋኝ፣ ቡርዡዋ፣ ከበርቴ፣ የአድኅሮት ኃይላት በሚባሉ ቃላት ዐርፍተ ነገር ሠርተን የተማርን፤ 
የኮምፒውተር መልኩን ብቻ ሳይሆን ስሙንም ሳንሰማ ኮሌጅ የደረስን፤ በዱላው ሞባይል ያናገርን፤ ከጎኑ እንደ ጉድጓድ ውኃ መዘወርያ እየተዘወረ በሚደወልበት ስልክ የደወልን፤ ከአናቱ አሥር ጊዜ ቀዳዳው ተይዞ እየተሸ ከረከረ በሚደወልበት ስልክ ሃሎ ያልን፤ ገንዘብ ስናጣ በተዘዋዋሪ የደወልን፡፡ የቤታችን ቴሌቭዥንና ስልክ ብርቅ ሆኖ በአበባ ተንቆጥቁጦ የተጠለፈ ልብስ ሲለብስ ያየን፤ ያለ ሞባይል፣ ያለ አይፎን፣ ያለ አይ ፖድ ያደግን፤ ያለ ዓረብ ሳትና ያለ ናይል ሳት፣ ያለ ኤፍ ኤምና ያለ ፍላት ቴሌቭዥን የኖርን፣ በታይፕ ራይተር የጻፍን፣ በታይፕ ራይተር የተፈተን፣ ያለ ዲኤስ ቲቪ እግር ኳስን በዜና ብቻ የተከታተልን፤ ከነ ማንቸስተር በፊት እነ ሊቨርፑልን የደገፍን፤
እኛ የመጨረሻዎቹ፤
እርሳሳችንን በምላጭ የቀረጽን፣ የአሥራ አራቱ ክፍላተ ሀገራት ካርታ ባለበት ደብተር የጻፍን፣ በአምስት ሳንቲም ሁለት በሚሸጥ ሉክ የተፈተንን፤ በጨርቅ ቦርሳ ደብተራችንን የያዝን፣ ምሳ ሳንይዝ ትምህርት ቤት የሄድን፣ በሁለትና በሦስት ፈረቃ የተማርን፤ የነ ጫልቱን ቤት፣ ለማ በገበያን፣ ሽልንጌን አንበን፣ በውሸታሙ እረኛ ተገሥጸን፣  የያደግን፤ እነ ማኦ ሴቱንግን፣ እነ ኪም ኤልሱንግን፣ እነ ማርሻል ቲቶን፣ ያደነቅን፤
እኛ የመጨረሻዎቹ፤
ውጭ ሀገር ለመሄድ ለኢሚግሬሽን ገንዘብ ያስያዝን፤ የመውጫ ቪዛ ያስመታን፣ በትንሷ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ውጭ የተጓዝን፣ የቦሌ ሠገነት ላይ ወጥተን ወዳጆቻችንን የሸኘን፣ ጣልያን በሠራው ድልድይ ዓባይን ያቋረጥን፣ ሮንድ ሲታደርና ስናድር ያየን፣ በሰዓት እላፊ ተይዘን የታሠርን፣ ሕዝብ ሃምሳ ሚሊዮን ሲሆን ምን እንደሚመስል የታዘብን፣ ከኮንዶም በፊት ተወልደን አሥር ሆነን ያደግን፤ ኢምፔሪያሊስቶች ባዘጋጁት ኦሎምፒክ አንሳተፍም ብለን የቀረን፤
እኛ የመጨረሻዎቹ፤
በአድዋ ጦርነት የነበሩ ሰዎች ሲናገሩ ያየንና የሰማን፣ በሦስት መንግሥት ብሮች የተገበያየን፤ በአለባቸውና በልመንህ ቀልዶች የተዝናናን፣ ኮንደሚንየም የሚባል ቤት ሳናውቅ በቁጠባ ቤት ያደግን፣ ‹ሪል እስቴት› የሚባል ስም ስናረጅ የሰማን፣ በማኅበር ተደራጅተን የቤት መሬት በነጻ ያገኘን፣ በሪል ካሴት ዜማ ያዳመጥን፣ በሬዲዮ ካሴት ብቻ የተቀረጹ ነገሮችን የሰማን፣ የቤት ውስጥ ማድ ቤት(ኪችን) ሳናይ ያደግን፣ በከተማ ወንዞች የዋኘን፣ ኢንተርኔት ሳናይ ብሎግ ሳናነብ፣ ዌብ ሳይት ሳናገላብጥ፣ ‹ሚሴጅ ቴክስት› ሳናደርግ፣ ያደግን፤
እኛ የመጨረሻዎቹ፤
በማይነከር ሻይ ቅጠል የጠጣን፣ ከኤይድስ በፊትም ከኤይድስ በኋላም የኖርን፣ የጣት እንጅ የመንገድ ቀለበት ሳናይ ያደግን፣ የሚፈስ እንጅ የሚታሸግ ውኃ ሳንጠጣ ለወግ ለማዕረግ የደረስን፣ በፌስቡክ ሳንወጣ፣ በትዊተር ሳንጽፍ ነፍስ ያወቅን፤
እኛ የመጨረሻዎቹ፤
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሕይወታችንን መዳረሻ የወሰነልን/ብን፣ 12ኛ ክፍል ተፈትነን መሠረተ ትምህርት የዘመትን፣ ታፍሰን ብሔራዊ ውትድርና የተላክን፣ ከኮሌጅ ወጥተን በመንግሥት ምደባ ሥራ የተቀጠርን፣ ሳንከፍል በመንግሥት ገንዘብ ኮሌጅ የበጠስን፣ አራት ኪሎንና ልደታን በጥንት መልኳ ያየን፣ በአንድ የክፍለ ሀገር አውቶብስ ተራ ሁሉንም ክፍለ ሀገር የተሣፈርን፣
እና የመጨረሻዎቹ፤
እንዲሁ ካሰብነው ስንቱ ነገር አልፎ ስንቱ ነገር መጥቷል፡፡ ለስንቱ ነገርስ እኛ የመጨረሻዎቹ ሆነናል፡፡ የትናንት አባቶቻችንና እናቶቻችን በሃምሳ ሳንቲም ዶሮ፣ በሁለት ብር በግ፣ በዐሥር ብር በሬ፣ በአምስት ብር ኩንታል ጤፍ ገዛን ሲሉን እንደተረት እንሰማው ነበር፡፡ ዛሬ እኛም ተረት ልንሆን ነው፡፡ አሁን ዶላር በሁለት ብር መነዘርን፣ ስኳር በአንድ ብር ገዛን፣ ጤፍ በአርባ ብር ሸመትን፣ ቤት በዐሥር ሺ ብር ሠራን፣ ብንል ማን ያምነናል? እኛ ራሳችን ተረት ልንሆንኮ ትንሽ ነው የቀረን፡፡
እስኪ እናንተም የመጨረሻ የሆናችሁበትን አስታውሱት፤ እኔ የረሳሁትን ብዙ ነገር ታገኛላችሁ፡፡ ለካስ ታሪክና ተረት እንዲህ እየሆነ ነው የሚፈጠረው፡፡ ‹ነበር ለካስ እንዲህ ቅርብ ኖሯል›› አሉ እቴጌ ጣይቱ፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ስለሆነ በተመሳሳይ ኅጥመቶች ማውጣት ነውር ነው

113 comments:

 1. Dn. Daniel Letsufehe Thank you But << Kekondem Befit>> Yalkew Aletemechegnim bihon bihon Yewolid Mekelakeya / mekotateria / betel yamrale tolo awutaw.yemesenakeya denegaye atehun

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ ዲያቆን ዳኒ፣ እንኳን እናንተ የመጨረሻወቹ ልትሆኑ የናንተን ለማግኘት እሚፍልግ ስንት ኢትዮጵያዊ አለ። በጨርቅ ቦርሳ ደብተር ያዝን እኛ የመጨረሻወቹ አልክ። ቅቅቅቅቅ ። ትምህርት ቤት እድል ምንም የሌላቸው፣ እንኳን ከጨርቅ ከምንም የተሰራ ቦርሳ የሌላቸው ስንት ኢትዮጵያውያን አሉ። ርሃቡና ስቃዩ እሚያንገላታቸው። ያው ለካድሬወቹ ከአሜሪካ እምትወረወረው የልመና ምጽዋት በሽ በሽ ስለሆነች ሌላው እሚኖረውን አኗኗር ያለማወቅ ችግር አለ። አይመስልህም ዳኒቹ? ኢትዮጵያ ከአለም የመጨረሻውን የትምህርት ቦታ እንደያዘች አለማወቅህ ይገርመኛል።

   አሜሪካና ኢትዮጵያ በጣም የተለያዩ አገሮች ናቸው፣ ዲያቆን ዳኒ። አሜሪካ፣ ጤነኛ መንግስት ያለበት፣ ከቀን ወደ ቀን እሚቀየር፣ ወደ ጥሩ፣ ወደ አዲስ እሚሄድ አገር ነው። ስለዚያ ነው አዲሱ ትውልድ፣ ያረጀው ትውልድ እያሉ እሚያወሩ። ጥራዝ ነጠቅ ኩረጃ እማይሰራወ ለዚህ ነው። አሜሪካኖች ስላለፈው ጻፉ ብለህ ስለኢትዮጵያ፣ ከድጡ-ወደ-ማጡ ብታወራ ስው መሳቂያ ነው እሚያረግህ። አሜሪካ እኮ ኢንተርኔት በየቦታው፣ በየቤቱ ያለበት አገር ነው። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ እንኳን አትነሳም። ከሶማሊ በታች፣ ከአፍሪካ ቂጥ ነው ያለቸው። እናንተ የወያኔ ካድሬወች እምትኖሩት ኑሮ ቤርግጥ ከአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ስለሚለይ የማዮጲያ ችግር አለ።

   እና ዳኒ፣ ጥራዝ ነጠቅ ኩረጃ ይቅርብህ። ግን ደግሞ ይሄ ከቀረብህ፣ አንተስ ምን ሰርተህ ትበላ? ቅቅቅቅ ሁሉ ጽሑፍህ የሌሎችን ሃሳብ እየሰረቅክ የራስህ አስመስለህ መጻፍ ነው ያንተ ነገር...ድንቄም ዲያቆን! ቅቅቅቅቅቅቅ አይዞህ፣ አውቄ ላናድድህ ነው የጻፍኩት። ወያኔ ነህ ብየ አላምንም..... መልካም ቀን።

   Delete
  2. አንተን ነው የመጨረሻ(ሰው) ማለት ፤ አንተ ምታወራው እኮ የማይገናገኝ ነገር ነው፡፡ ብሎግ ተሳስተህ ይሆናል፡፡ እስኪ እኔም በተራየ እንትን ልበልብህ ፤ ምን አትለኝም ቂ ቂ ቂ ቂ ቂ…….ቂል

   Delete
  3. ሰው እውነትን ከተናገረ ለናንተ የወያኔ ካድሬ ነው። የጻፈው እውነት ነው። እንደናንተ በጥላቻ አይምሮው ደንዝዞ ሃሰት ስላላወራ! እግዚዖ! ዳኒ በርታ ከወገንተኛነትና ከጥላቻ የጸዳ ጽሁፍህ እና አስተሳሰብህ በጣም ነው ሚመቸኝ። እደግ ተመንደግ ልጄ በርታ! ለዛ ነው እነ እንትና ቅንት! የሚሉብህ። ነጻ አይምሮ እንዴት ይናፍቃል!

   Delete
  4. what is wrong people ? why dont u express ur idea in manner? it is a bad habit to be a person of immoral. u should hv to express ur idea in a manner. every body hv a right to express his /her idea freely with manner. pls...... dont be an .......am from hawassa !

   Delete
  5. ዳንኤል የዱሮውን ያለፍንበትን እያስታወሰ በለዛ አስነብቦናል፡፡ አንተ ግን ቁርስህን የበላኸውን እንኳን የማስታወስ ብቃት የለህም፡፡ ለምን ብትል አእምሮህ በስድብ፣ በጥላቻ፣ በቅናት፣ በማጣት፣ በሥራፈትነት፣ በሱስ ልክፍት ተጣቧልና፡፡ ስለዚህ ወደ ራስህ ዘንበል በልና አቋምህን አስተካክል፡፡

   Delete
 2. ከኮንዶም በፊት ተወልደን Please change this word.I don't want see it from you spiritual blog.Please Please Please Please Please

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከኮንዶም በፊት ተወልደን Please change this word.I don't want see it from you spiritual blog.Please Please Please Please Please

   Delete
  2. ከኮንዶም በፊት ተወልደን i think there is no any problem.becoz he state the word condom only as event and its true that it was bizarre for Ethiopians! እንዲህም ተብሎ ነበር 'የኮንዶም ትራፊ' i think the problem is the way u understand!

   Delete
  3. it is a reality...i born before the word condom known by. i think Dani is writing about our past ....i cannot see any wrong

   Delete
  4. Min maletachihu new? Kondom Kondom Kondom... esti tifenedu endehu eniy? Kondom mallet mindinew chigiru? Menfesawinet kondom alemalet hone endie? Ere yidebiral

   Delete
  5. እንደ’ኔ ሀሳብ ‘’ከኮንዶም በፊት’’ ምንም ችግር የለውም ይህ îሁፍ አሰተማሪ ታሪክ ነጋሪ እንጂ ሃይማኖታዊ አይደለም:: ሃይማኖታዊ ቢሆን እን£ን እወነትነ እውነት ብለን እንጂ giተን የትመ አናመለÖውም:: call a spade a spade ይላሉ ፈረንጆቹ ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል እግዚአበሄር እውቀቱን ያብዛልህ::

   Delete
 3. ye 1 birr 4 enkulal yegezan .

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተማ የበቀደሙ ነህ። እኛ በብር 20 ዕንቁላል የገዛነው ምን እንበል?

   Delete
  2. Hi it is yesterday, not the last. It was 20 eggs by one birr. And we heard that the cost of a goat was less than its 'koda'.

   Delete
 4. እረ ስንቱ ተነግሮ ያልቃል ይጻፍ ቢባል ምን ወረቀት ይበቃዋል
  በማስመሪያ የተገረፍ አሻዋላ የተንበረከክን በጣታችን መካከል እስኪርብቶ ገብተን የተቀጣን
  ባንዲራ ሲሰቀልና ሲወርድ ቆመን የጠበቅን ፈረንጅ ለማየት የሮጥን ከጨበጥን አለምን የጨበጥን የሚመስለን ቀበቶ ተሰቅሎ ከአጠፋችሁ ትናገራለች ተብለን እንዳታየን ከተሰቀለችበት ተደብቀን
  የምንሰራው ስራ ግን መገረፋችን ላይቀር ማንነገረት ያልን እረ ስንቱ ቀበሌ ኪነት ሆነን ወይ ኢህአፓ እኔ ጉድ አረገችኝ
  በፀረ አብዪት ካንብ እኔ አሰለፈች ብለን የዘመርን ኢሰፓ ኢሰፓ ብለን የዘመርን ……………………..እረ ይብቃ ስንቱ

  ReplyDelete
 5. ዳኒ በጣም ቆንጆ ምልከታ ነው፡፡ ዳኒ እኔም እስኪ ትንሽ ልበል፤ እኛ በጭቃ መኪና፡ ቤት የሰራን፤ጎርፍ የገደብን ፤እኛ በጭቃ በቡድን ውርውር የተጋጠምን፤እኛ በ አስር ሳንቲም ሁለት ጢቢና(ሙልሙል) ገዝተን የበላን፤እኛ ጥጋባችን ለማስታገስ እርግጫ የተጫወትን፤እኛ ደረቅ ና ሎንቤ ሾላ ለቅመን ና አውርደን የበላን፤እኛ እኮ የቤት ስራ ስላልሰራን አንድ አልበቃ ብሎን በድርብርብ ጨንገር የተገረፍን፤እኛ አስተማሪዎቻችን እንትን ገዝተህ ቤት አድርስልኝ ተብለን ትምህርት አቀርጠን የተላክን፤እኛ እኮ አርብ ሲደርስ የክፍል አለቃችን እየደበደበ ከወንዝ ውሀ ቀድተን በከብት አዛባ ክፍላችን አሳምረን ስማችን የተጠራን፤የመጨረሻዎቹ ትውልዶች ነን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. yante milketa yenenim astawesegn, lemin bitil ye dani yeketemawun yamakele bicha sile meselegnm, igna degmo kursi sanbela bekolo misa sanbela iyewalen 3 se'at mulu be igrachin teguzen yetemaren, and astemari bicha ke andi iske 11 amarigna yastemaren,astemari aten temariw yastemaren bicha min yadergal........ tizitachin bizu neber.

   Delete
  2. ere meche tewerto yalkale.... lemanegawem dn daniel enamesagnalelnl!

   Delete
 6. ‹‹ ቃል ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም፡፡ ››

  አደራህን አንተም እንደ በዕውቀቱ ስዩም ቅዱሳንን መስደብ እንዳትጀምር የጻፍከውን በመንፈሳዊ እይታ ብትመረምረው

  ReplyDelete
  Replies
  1. Why you write such extreme concept. It seems you are developing guiltiness on him. But if it was moderate I believe it will be an advise.You better see a constructive advise next to your comment. It seems extra addition, but it is an advise also. Better to be out of feeling in writing. Writing has its own character.

   Delete
  2. Hey Anonymous Nov. 13,2012 3:44 PM
   Please tell us the wrong part of Dani, please share your comment also. ሾላ በድፍኑ ሆንክብን እኮ

   Delete
 7. እኛ የመጨረሻወቹ
  ግርማ ሞገሳቸው የሚያስፈራ፤ ጺማቸው ረጃጅም የሆነ፤ጥምጣም ጠምጥመው፤ ጋቢያቸውን አጣፍተው መስቀላቸውን ጨብጠው፤ እንደ ዘመኑ ሞንታርቦ በሌለበት በቃላቸው ብቻ ታምረ-ማርያምን አንብበው የእለቱን ጻድቅ ከስንክሳር ላይ ታሪኩን አንስተው አውስተው፤ ጸሎተ ምህላ አድርሰው፤ ህዝቡን የሚያሰናብቱ ካህናት የነበሩበት ዘመን፤ እንደ ዘመናችን ቄንጠኛ መኪና የለ ፋሽን መጫሚያ የለ አበል የለ ጫጫታ የለ... እንደ አሁኑ አንድ መዝሙር ዘምሮ ለመውረድ እስኪ እጃችሁን ቸብ ቸብ አድርጉት አይሰማማ የታል ታዲያ እልልታው...እስኪ እዛ ጋር ምንምን የለ "ማርያም ፊደል የሁሉ መማሪያ" በቃ እርሱንም በእርጋታ። ዋ ዘመን፤ እንደ አሁኑ ሆዳቸው የሞላ ደረታቸው የቀላ "ሰባኪያን" መምህራን አላልኩኝም ልብ በል በል ሰባኪያን ነው ያልኩት የ 30 ደቂቃ ትምህርት ለማስተማር አውደ ምህረቱ ላይ ከግራ ወደ ቀኝ ተንገዋለው 30 ጥቅስ ደርድረው ተውኔት አሳይተው ህጻናቱን አስቀው አዛውንቱን ግን አሰቅቀው እንደሚወርዱት አልነበሩም፤ ፊታቸው የማይፈታ እንደ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቁጽረ ገጽ የሆኑ ቆፍጣና ቆምጬ ቆምጫጫ ደረቅ የተዋህዶ ካህናት የነበሩበት ዘመን ሰዎች ነን መንግሰቱ ኅይለ ማርያምን ሳይፈሩና ሳያፍሩ በሸንጎው ፊት ወጣቱን ለእሳት ማግደህ አገር ጥዬ እጠፋለው ብትል ታሪክ ይወቅስካል የቴድሮስን ጽዋ መጠጣት አለብህ የተቀመጥክበት ወንበር ላይ እንደ ቋንጣ መድረቅ አለብህ ብለው የተናገሩ ደፋር ካህናትን ያየን የተመለከትን ያዳመጥን ሰዎች ነን "ነበር" ቁጥር ሁለትን ተመልከት።

  ReplyDelete
 8. you forgot one thing, bekalsi kuas yetechawetin!

  ReplyDelete
 9. የእኛ ትውልድ
  የኔታ ጋር ስንሄድ በፍርሀት የሄድን
  አንገት ላንግት ተቃቅፈን ፊደል የቆጠርን ጅስ ሳይሆን
  በጠርሙስ ውሃ ውስጡ ቆሎ አድረገን የሄድን ከወንድ ጋር መቀመጥን
  እንደጦር የፈራን በፌስ ብክ ሳይሆን የልብ ቅርስ ተስሎ ልቡ በጦር ተወግቶ የፍቅር ደብዳቤ የደረሰን በሱ ያፈርን ሰው እንዳሰማብን የተሸማቀቅን ሰኔ 30 ሲደርስ ቀጠሮ ይዘን የተደባደብን
  ሻይ ቤት መግባት ያፈርን አስራ አምሳንቲም አተን በእግራችን የሄድን የመጨረሻው ትውልድ
  አይ ዳኒ አሁን ብንረሳው ምን አለበት

  ReplyDelete
 10. አዎ! እኛ የመጨረሻዎቹ:- እሸት ሲደርስ እሸት ቅመሱ ብለን ለወዳጅ ዘመድ ጭነን የሄድን: ዓመት በዓል ሲሆን ጥገት ላም ለሌላቸው ጎረቤቶቻችን በጥዋት ተነስተን ወፍራም እርጎ ስለ አውዳመቱ ብለን ያደረስን: ጠላ ሲጠመቅ ድልህ(አዋዜ) ሲደለህ ኑ ቅመሱ ተብለው በትኩስ እንጀራ ለጎረቤት እና እግሩ ለጣለው ወዳጅ ሲሰጥ ያየን ወይም የተሳተፍን: በየሄድንበት ሁሉ ከየት አካባቢ መጣህ እንጂ ብሄርህ ምንድን ነው ተብለን ያልተጠየቅን እረ ስንቱ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ere sintu...betam des yilal.

   Delete
  2. I miss those old days. you said it well!

   Delete
 11. ጐረቤት ሄደን ቴሌቭዥን ያየን፣ ቴሌቭዥን ለማየት ብለን ለሀብታም ጎረቤት ያገለገልን፣ በነጭና ጥቁር ቴሌቭዥን የተዝናናን፣ቄስ ትምህርት ቤት ተምረን 1ኛ ክፍል የተገባን ከልብስ ሰፊ ቤት ብጥስጫሽ ጨርቅ ለቅመን አሻንጉሊት የሰፋን፣ፔፕሲ ጢባጢቤ ሱዚ /ገመድ እያጠላለፉ መጫወት ፣የመኪና ጐማ እያሽከረከርን የእናታችንን ሻሽ ቋጥረን ሼሎ ብለን ሰርተን ሙሽራዬ ብለን የተጫወትን ፣ ጠጠር ለቅመን ቅልብልቦሽ የተጫወትን፣ሴንተሪንግ የመታ እያልን የተጫወትን፣ከት/ቤት ስንመጣ መንገዱን ዘግተን መደማመጥ የሌለበት ወሬ ያወራን የምንሄድ፣ በየመንገዱ የባስ ትኬት እየለቀምን እንደብር እየቆጠርን የምናድር ውውውው ምኑ ቅጡ ስንቱ ይወራ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዳሁኑ የቪሲዲ ፊልም በየመንገድ ላይ ሳይሸጥ ቅዳሜ ቅዳሜ ብቻ በኢቲቪ የሚተላለፈውን ታላቅ ፊልም እሰከ ሌሊቱ 6 ተኩልና 7 መሬት ላይ ቁጭ ብለን ያየን፣ ታናሹ ፊልም የቱ ነው ብለንም ያልጠየቅን፣ ሰኞ ጠዋትም ፊልሙን ለጓደኞቻችን ጨማምረን የተረክን፣ ያለምንም ማጣቀሻ(ሪፈረንስ ቡክ) በመማሪያ መጽሐፍ ብቻ ተምረን በግማሽ ሴሚስተር ደብል ያለፍን፣ በአንድ አመትም ከ4ኛ ክፍል ወደ6ኛ የተሸጋገርን፣

   Delete
  2. አዎ እኛ የመጨረሻዎቹ

   Delete
 12. Dn. Daniel, as to me, please don't bother to change the word "Condom"...it is such kind of backward mental state that is holding us back from freely expressing our ideas. whoever reads this blog have definitely heard the word 'condom' thousands and millions of times before. If it offends them, that is not your problem, it is theirs. Weather we like it or not, we are living in the 21st century and we can not avoid using words which are already in the public domain and no more considered to spoil our culture. That is a reality of life. People please grow up...don't be like those Pharisees who crucified our lord Jesus Christ. "Woe to you, teachers of the law and Pharisees, you hypocrites! You are like whitewashed tombs, which look beautiful on the outside but on the inside are full of dead men's bones and everything unclean". Matthew 23:27

  ReplyDelete
 13. Dn.Dani,

  what about letters before mobile and internet?
  i would love to hear more about that.
  pls guys post memories about that if possible excerpts from the letters .
  thanks,

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yesemay riketun, Yewukiyanos tilketun...
   ende injera lemitribign, endewuha lemitemign wud... ha ha ha, of course I was born in 1970s. But to a certain extent we also share some of the earlier generations.

   Delete
  2. Lewid abate...
   Lewid enate...
   Lewid wondime...
   Lewid wondime...
   Lewid ihite....
   .
   .
   .
   keteleyahenibet kenina se'at indihum dekikana second jemiro letenachu indemin alachu?...( this letter may arrive after a month)

   Delete
 14. timihir be radio yetemarin haha temariwoch....yezih tiyake mels yetu new?..ha new alachihu gobez temariwoch yetebalin.
  musica nurozede ena ersha yetemarin.le nuro zede tit yefetelin,sifet yesefan kebetachin yetesera wesden mark yeteseten.wereket abukiten sahin yeseran muk amuken yeletefin....le ersha ke wenz wiha kediten betera yetmhirt betun karotina key sir yatetan.
  lib lelib lay yefikir debidabe yelakin lol yefikir guadegna meyaz biligina tebilen yadegin...

  ReplyDelete
 15. Ere sintu dani/berberena shiro sifech legorebet akmsu teblen yetelakin,kezikir behuala kirari legorebet yadelin,tilik sew siyalf komen yasalefin,lelken hulu eshi yalin,gorebet siketan yetekebelin,astemari sigeba yetenasan..etc. yemechereshawothu.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Astemari sigeba yetenesan yemechereshawochu!

   Delete
  2. hahahaha...ere ahunm ennesalen

   Delete
 16. የትናንት አባቶቻችንና እናቶቻችን በሃምሳ ሳንቲም ዶሮ፣ በሁለት ብር በግ፣ በዐሥር ብር በሬ፣ በአምስት ብር ኩንታል ጤፍ ገዛን ሲሉን እንደተረት እንሰማው ነበር፡፡ ዛሬ እኛም ተረት ልንሆን ነው፡፡ አሁን ዶላር በሁለት ብር መነዘርን፣ ስኳር በአንድ ብር ገዛን፣ ጤፍ በአርባ ብር ሸመትን፣ ቤት በዐሥር ሺ ብር ሠራን፣ ብንል ማን ያምነናል? እኛ ራሳችን ተረት ልንሆንኮ ትንሽ ነው የቀረን፡

  ReplyDelete
 17. የተለያዩ ድንጋዮችን እየፈጨን ሽሮ; በርበሬ ;ጥቁር አዝሙድ(ከስሉን) እያልን በከርመላ ላስቲክ የተገበያየን በበረኪና ላስቲክ ዋንጫ ሰርተን በክረምት "ፕሪሜሊግ" ያካሄድን ;ኩኩሉ ብቻ ሳይዎን የካስ ኩኩሉ የተጫወትን በባዶ ኦዳችን ት/ቤት የሄድን(ይቅርታ ለድኦች):: እኛ የመጨረሻዎቹ:: ግን የአሁኑ ትወልድ ገና ብዙ ይቀረዋል....... ከኮንዶም በፊት ተወልደን አልተመቸኝም::

  ReplyDelete
 18. ከኮንዶም በፊት ተወልደን ማለት ምን ነዉር አለዉ? እዉነቱን ነዉ በኛ ዘመን አልነበረም አሁን ነዉ ሃይማኖተኛ ነኝ የሚለዉ ሁሉ በቤቱ ሸሽጎ እየተጠቀመዉ ያለዉ፡፡ ፈሪሳዊ አንሁን እንጂ ያለዉን ነገር ጻፈ እንጂ ተጠቀሙ አላለ ደግሞስ ቅዱሳንን ከመሳደብ ጋር ምን አገናኘዉ፡፡ ግንዝነት መልካም አይደለማ፡፡ ለማንኛዉም ዲን ዳንኤልን ወደ ጥንቱ ትዝታ ለአፍታ ስለመለስከን እናመሰግናለን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. "እዉነቱን ነዉ በኛ ዘመን አልነበረም አሁን ነዉ ሃይማኖተኛ ነኝ የሚለዉ ሁሉ በቤቱ ሸሽጎ እየተጠቀመዉ ያለዉ፡፡ ፈሪሳዊ አንሁን እንጂ ያለዉን ነገር ጻፈ እንጂ ተጠቀሙ አላለ" tebarek abo!

   Delete
 19. Thank you Dani Your Blog its very Interesting Good bless you and yours!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 20. በፊት በፊት አንድን ጉዳይ አስረጅ የታሪክ ምስክር ተብለው የሚጠየቁት አዛውንት ነበሩ አሁን አሁን እኛ ሦሰት አስርት ዓመታትን በቅጡ ያልኖርን ሰዎች የታሪክ ምስክሮች ስንሆን ይደንቀኝ ጀምራል ፡፡ የሚያሳዝነኝ ግን አብዛኞቹ አሉታዊ የታሪክ ለውጦች መሆናቸው ነው፡፡ ከላይ ባነበብኩት በብዙዎቹ ትዝታዎቻችን ከልቤ ሳቅኩኝ፡፡ እግዚአብሔር በቀሪው ዘመን መልካሙን ያብዛልን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 21. የህ ፅሁፍ ብዙ ትዝታዎችን መለስ ብለን እንድናስብ ያደርገናል ለካስ ይረሳል በጣም አመሰግነናለሁ ብዙ ብዙ ማስታወስ ችያለሁ ጥሩ እይታ ነው ዳንኤል

  ReplyDelete
 22. ዳኒ ስለ ሁሉም ፅሁፉችህ እጅግ በጣም እናመሰግናለን፡፡ ስለ ኮንዶም አስተያየት የሰጠህው ግን ዳንዬል ስለፃፈው ብቻ ነው ነውር የሆነ አበዛኛውቻችን የምንጠቀምበት አይደለ? በቀን ስንት ጊዜ ነው በሬዲዎ እና በቴቨ ስንሰማ አይደለም የምንውለው? አንድ አባባል ትዝ አለኝ
  አንድ የአገራችን መሪ ስለ ኮንዶም ዋጋ 5 ብር መግባቱን እና መወደድ ተጠይቀው እንዲ መልሰዋል አሉ "ፈንጅውን 500 ከገዛቹ ማምከኛውን 5 ብር ብትገዙ በጣም ቀላል ነው"

  ReplyDelete
 23. Benatachihu alkish alkish alegn.Hod basegn. Mnew Dani batnekekan.

  ReplyDelete
 24. እቃቃ እያልን ባልና ሚስት የተጫወትን፣ ቅጠል በጥሰን እንጀራ እያልን የተጐራረስን፣ አፈር በጥብጠን ወጥ ሰራን ብለን ቅጠሉ ላይ የጨመርን፣ ሶዝ ለመጫወት ሌላ ሰፈር ሂደን መንገዱ የጠፋን፣ ጭራቅ መጣ ተብለን ልባችን እስኪጠፋ የሮጥን፣ የእጅ ቦንብ ብለን ኳስ በካልሲ ሰርተን የተጫወትን፣ የኮካ እና የፔፕሴ ኮርኪ ልጠን አሪፍ ቀበቶ የሰራን እረ ስንቱ ዋ ጌዜ ዋ ዘመን!

  ReplyDelete
 25. እቃቃ እያልን ባልና ሚስት የተጫወትን፣ ቅጠል በጥሰን እንጀራ እያልን የተጐራረስን፣ አፈር በጥብጠን ወጥ ሰራን ብለን ቅጠሉ ላይ የጨመርን፣ ሶዝ ለመጫወት ሌላ ሰፈር ሂደን መንገዱ የጠፋን፣ ጭራቅ መጣ ተብለን ልባችን እስኪጠፋ የሮጥን፣ የእጅ ቦንብ ብለን ኳስ በካልሲ ሰርተን የተጫወትን፣ የኮካ እና የፔፕሴ ኮርኪ ልጠን አሪፍ ቀበቶ የሰራን እረ ስንቱ ዋ ጌዜ ዋ ዘመን!

  ReplyDelete
 26. ከኮንዶም በፊት ተወልደን አሥር ሆነን ያደግን.... I was also born before condom but my "illiterate" families, getting married at their early twenties, had four babies. What about yours?

  ReplyDelete
 27. It really nice Dn.Dan....For these conservatives it is batter to write you memory....
  thank you

  ReplyDelete
 28. እኛ የትናንትናዎቹ ደግሞ ምን እንበል?
  ቁርስ በልተን ምሳ እና ራት የሸወድን ፤ በሁለት አይነት ጫማ ትምህርት ቤት የሔድን ፤ በአንድ ደብተር ሁለት አይነት ሳብጀክት የጻፍን ፤ ጠዋት ተምረን ከሰዓት የተሸከምን አሊያም ፎርፈን ስራ የሰራን ፤ ምግብ ለማግኘት ጎረቤት ያገለገልን ፤ ረሀብ ሲጠናብን ከቆሻሻ ገንዳ ለቅመን የበላን ፤ ቤተሰብ ለማስተዳደር ወደ ዓረብ ሀገር የሄድን ወይም ሴተኛ አዳሪ የሆንን ፤ ኽረ ስንቱ የኛስ ከሰው አይተካከልም መከራ…መከራ…መከራ ብቻ

  ReplyDelete
 29. ‹ነበር ለካስ እንዲህ ቅርብ ኖሯል›› አሉ እቴጌ ጣይቱ፡፡

  thank you

  ReplyDelete
 30. ዳኒ! በእውነት ትልቅ ሰው ነህ!ወደፊት መተንበይ የሚችል፤ ወደ ሁዋላ ማስታዎስና፤ ዛሬን በደንብ መመልከት የሚችል የብሩህ አእምሮ ባለቤት ነህ! እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይሁን!

  ReplyDelete
 31. ለችግር ለመከፋፈል ለኮንዶሚኒየም ለዲሞክራሲ ለቀዥቃዣ ጳጳሳት ለታይታኒክ ለ ማሪዮ ጌም ለፌደራሊዝም ለኒው ሊብራሊዝም ለኤርትራ መገንጠል ለ ላይቭ ፖርን አርሰናልን ለመደገፍ ሞዴል ገበሬ ለማየት ለደንበል ህንጻ ለ ሼህ አላሙዲን ለ ላፕቶፕ ከነጻነት ይልቅ ቅኝ ብንገዛ የምንመርጥ ሂፓፕ ለማዳመጥ ወዘተ እኛ የመጀመሪያዋቹ ነን(1980ዎቹ)

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔ ‹ ከኮንዶም በፊት › የሚለውን ሃሳብ የተቃወሙት ሰዎች ለምን ተጠራ በሚለው ብቻ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም የተዘረዘሩት ነገሮች ሁሉ እየቀሩ ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ኮንዶም አለመጠቀም እንደቀረ ያስመስላል ወይም ኮንዶምን ያሁኑ ትውልድ በሙሉ የሚጠቀመው ያስመስላል፡፡ ይህንን ደግሞ ቤተክርስቲያን አጥብቃ ትቃወማለች፡፡ ስለዚህ አገባቡ ስህተት ያለው ይመስለኛል፡፡

   Delete
 32. Brilliant account of what has happened in the past; amazingly, the time is passing by the pace we could not cope with and we are witnessing history being written in our very eyes. After reading this article, I got older.

  ReplyDelete
 33. Kidy Konjo- engidih anchi ketesededut tesedabiwoch andua nesh.
  One thing I want to tell you and your diaspora friends is Etiopia and the Ethiopians are changing like the rest of the world.we didnt stack to Ethiopia you know befor 20+ years.and we pass through all this and we have the other side too.
  one thing i realize in America, when you meet people"Diaspora" they expect you to say wow what is it? how does it work?....but we know those technologies.and some of us we have access. surprisingly, people in Ethiopia they have time to read , to disscuss even to brouse. so please dont get surprised. Addis Neger yelem! May be hulum access laynorew yichilal gin atlease we read.even thanks to our FM radios we know about holywood celebrities,yemayagebanin. you know many girls in addis wear disigner cloths perfume.. than those live in America. so dont get things wrong. you know some people complain to their diaspora families to get money.

  kumnegeru gin Min tadergiwalesh Teqeyirenal!

  ReplyDelete
 34. ግሩም ቅኝት ነው፤...ብዕርህ ስንት መንገድ ወደ ሓላ ተጉዛ እንደሆነ የዘመኑንን ልክ መስፈር ይከብዳል፡ግን ስንት ግዜ መጀመሪያ ነበረን?.....እስከመችስ መጨረሻ ላይ እንሆን ይሆን፡በጥቅሉ ጅራትና አናት የአንድ አካል ክፍሎች ናችውና..ምን ታደርገዋለህ? ምኞቴ ብዙነህ ከፍሎሪዳ ጫካ

  ReplyDelete
 35. ጋዴ /ሞጋ/,ሸራ,አንበሳ ቀይረን ቻይና ላይ የቆምን: ቢሊጮ/ቁንጮ/ ሆነን የዘነጥን: የወስፋትን ትል በአይን ያየን: /ዛሬ ላብ ቴክኒሻኖቹም ለማየታቸው እርግጠኛ አይደለሁም::/ ለመምህራኖቻችን እንቁላልና ዶሮ የእጅ ሥራ የወሰድን: ባህታዊን ሬስቶራንት ሰባኪን ውስኪ ቤት ጳጳስን ሰርግ ቤት . . . ያየን
  እኛ የመጨረሻዎቹ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለመምህራኖቻችን እንቁላልና ዶሮ የእጅ ሥራ የወሰድን: ባህታዊን ሬስቶራንት ሰባኪን ውስኪ ቤት ጳጳስን ሰርግ ቤት . . . ያየን
   እኛ የመጨረሻዎቹ

   Delete
 36. One of My favorite post D. Danni…Thank you my dear for bringing back some of the best memories of my life.
  Everything we live through helps to make us the person we are now.

  May God bless you and keep you always in His care, on this journey and beyond.

  ReplyDelete
 37. I am still confused why you still support Woyane? What is wrong with you? I thought you can write about spiritual issues, not some damn politics. If you want to mention politics, why do you forget about racist activity against Amhara people(I know you are from Amhara, Gojjam); why you forget to mention about high living cost of the community; whey you forget to mention the divided Ethiopia by ethnicity; what about the problem of religion and looting of community property by effort company; what about the massacre of innocent children and young adults in the street of Addis Ababa in 1997 election,and so on. Probably, your family might suffer during Derge Regime,therefore, you may think that what ever TPLF done wrong in this country,you may count it as a revenge for the problem you have faced so far during the previous regime. If by chance,you think like that,this is the most selfish thing which I have ever heard in my life. Dear Danny!! Please differentiate personal issues from current country problem. Now if you have concern for this country(Ethiopia) and the church, please remember that we are in the middle of something to decide whether this country to continue as Ethiopia or divided 9 different countries including the church. If you want to write politics, these were the really matter which you should have mentioned. Otherwise, you do not have moral issues to mention above problems. By the way, you will not obtain any extra benefit from Tigray government by supporting directly or indirectly through mahibere kidusan or whether through interfering church affairs. Thrust me!! I am telling you the truth. Remember that Ethiopia is the property of God, not some damn gangster and racist groups. My final advise to you is that please do not measure the kind of benefits which you have obtain in order to write something relevant. You have to be the man of forgiveness, if you are not, remember that always innocent people will be victimized or die in the process. The power of forgiveness is not an easy issue. It requires understanding of yourself and help from the God. Please learn something from Aleka Ayalew if you are the true believer of the church and stand for the benefit of Ethiopia people. May God be with us!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hi you are still fanatic in politics. Politics was not the issue of the article, but what you want as i look you through your comment is blaming dn daniel. Personally I do not like blamer's. If you have an issue that resembles the topic in the area of politics try to finish the article by your comment.

   Delete
  2. ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ይላሉ ያገሬ ሰዎች፡፡ ምን ለማለት ፈልገህ ነው ይህን ሁሉ የምትቀባጥረው? ለመሆኑ ዳንኤል የጻፈውን ጽሑፍ አቅል አግኝተህ አንብበህ ጨርሰኸዋል? ወይስ ላይ ላዩን ነው? ወይ ደግሞ የቆየ የቂም እርሾ አለብህ ከሱ ጋር? ደም ተቃብታችኋል? ለጻፈው ጽሑፍ መልስ የማይሆን ምንም የማይገናኝ ነገር እኮ ነው የጻፍከው፡፡ ዳንኤል በወያኔ ጊዜ ተሻሻልን፣ አለፈልን፣ ተንደላቀቅን፣ ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ ሆነልን አያለ አላዜመ፤ የድሮውን ትውስታ ነው ከብዙ በጥቂቱ ያስቃኘን፡፡ ለነገሩ በፈረንጅ አገር በግዞት የኖረ ሰው የአገራችንን ድሮና ዘንድሮን በምን መልኩ ሊያስተያይ ይችላል???

   Delete
  3. ok lets think as u said. If EPRDF is doing what u indicated, What Daniel can do on this? He can pray as a religious person. Is there any other thing that he can do? Or do u want he to go through EPRDF comes. Chaka megbatun lante aynetu titenal. Eski mokrat, Jegina hun.Or do u want him to go Jail? Why not u try it? u crazy diaspora people, don't disturb us. Egna ke EPRDF gar techachilen eyenorn new.

   Delete
  4. @solomon please don't comment again in this site. coz they are not important for every one!

   Delete
  5. ለምን አንዘባርቃለን የህ ጽኁፍ ደንኤል ላወጣው እኛ የመጨረሻዎቹ ለሚለው አንዴት አስተያየት ይሆናል ዝም ብለን ኢንተርኔት ሰላገኘን መልቀቅ የለብንም ደግሞ Try to use Amharic!!! አንዳልከው ኮንፊውስድ ከሆንክ አርፈህ መቀመጥ

   Delete
  6. why do u hate ,blame Solomon as he did . it is not fair to blame the one that blame u. i understand his fear, i got some nice idea from his anti daniel writing. he do have some truth but he doesn't express his felling in manner . people pls let us teach each other in a manner . Manner is very important for all of us. k weyane gare techachilen newe eyenoren yalenewe newe yalkewe ......? i disagree with zis idea . i think u do .but at least i am not. LET US TEACH EACH other WITH MANNER PLS.i am from HAWASSA....

   Delete
  7. ምን ነካህ አባው!? እረ ነቃ በል በናትህ!?! የሌለ ትላለህ እንዴ!?ቀድመህ በደንብ አንብበው!!

   Delete
 38. Dear Solomon what are you talking about? let me remind you that the name of the blog in which you are writing your comment is Daniel’s Views, so he can write whatever he feels. I do not know you but I can identify you as one of the so called “ ya tewled” member because those people always want to dictate everything. Whatever you said or whatever you do has the meaning not that you said but that they feel should have. Please Please and again please leave our brother to do whatever he feels, you can agree or oppose on what he said but you can never never force him to be your spokesman, you can do it by yourself if you are really a man. May God bless you………

  ReplyDelete
 39. ከቤት አትወጡም ስንባል አፈር የሆነውን ቤታችንን ቆፍረን ብይ የተጫወትን

  ReplyDelete
 40. Mr Solomon,

  What the haile are you blabering about? What he wrote and what you understood are very different things (that's if you even start to understand). I really feel sorry for you. Is this how you live your life? mixing up everything??????????

  ReplyDelete
 41. የባሕታዊ ሚስት፤ የሰባኪ ቀሳጢ ፤የጳጳስ ቪላ፤ የፓትርያርክ ሊሞዚን ያየን እኛ የመጨረሻዎቹ:: ተመችቶኛል!

  ReplyDelete
 42. ኣንተ ከላይ ፖለቲከኛ ምናምን እያልክ በእንግልጣርኛ የምትጽፈው ሰውዬ::

  ይህን ያንተን ሀሳብ አክብሮ ያወጣልህ እኮ ቢያከብርህ መሰለኝ:: በግሉ የመረጠውን መሆን የሚችል መሆኑን ማመን የመጀመሪያ ግዴታህ ነው ከዚያ ደሞ ለመሆኑ እርግጠኛ መሆን ነበረብህ ከመናገርህ በፊት:: የተናገርከው እውነት እንኳን ቢሆን እኮ ደግሜ እልሀለሁ ምርጫው አሁንም የእርሱና የርሱ ብቻ ነው:: ሌላው የጠቀስካቸው ሊቅ እውነት ለመናገር ነፍሳቸውን ይማርና ከግዝታቸው በላይ ሥራቸው ዛሬም እያገለገለ ነው:: ግዝታቸው ግን ተወው በዚያ መንገድ ማንም እንዲሄድም አትምከር:: ምን ተጠቀሙ አለቃ? እውነት ጽፈውና ተናግረው ካወረሱን ይልቅ የጅምላ ግዝታቸው ምን ጠቀመን? መንግሥቱን ለቤተ መንግሥት የመከሩትን ምክር እርሳቸው እኮ ለቤተ ክህነት ቢጠቀሙበት ኖሮ ምንኛ መልካም ነበር:: መቸም መች ለዳንኤል ይህን አልመኝም:: የወንድማችን ብእር ሁለት አፍ ያላት ናት ተቃዋሚና ደጋፊ አማኝና ኢአማኒ ሳትል ላነበባት በየደረጃው ለየራሱ መልእክት የምታስተላልፍ ናት:: ጸሐፊውም ሲጦምር ለነእከሌ ሳይሆን ለአማርኛ አንባቢዎች ሁሉ ትደርስ ዘንድ ነው:: በሀሳብ እንከራከር እንጂ ወገን?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምን ተጠቀሙ አለቃ? እውነት ጽፈውና ተናግረው ካወረሱን ይልቅ የጅምላ ግዝታቸው ምን ጠቀመን? መንግሥቱን ለቤተ መንግሥት የመከሩትን ምክር እርሳቸው እኮ ለቤተ ክህነት ቢጠቀሙበት ኖሮ ምንኛ መልካም ነበር:: መቸም መች ለዳንኤል ይህን አልመኝም::

   Delete
 43. I also believe this government is against the church (mostly). but what is this to do with dn. daniel and MK? I Don't get your point...

  ReplyDelete
 44. thank you dani you took me 30 years back how many of us listen ye zefen mircha on radio sunday night tereka like tamera tore and go studium and begging some body to take you with him sharing SEMEMEN love story book with friends on break time in school buy SHENKORA 10C WITH ANGUA 25C WITH OUT O MY GOD YOU MAKE CRY

  ReplyDelete
 45. Thank u Dani!

  Ye haymanot ena ye
  ager meriwechin be 1 samnt be
  enbachin eyesakn yekebrnachew:
  motewm be keri adrbay zeregna
  mengist eynachin be photos
  joroachin be TV lemedfen
  bemitru asfari sewech yeminmera

  ye Adisu zemen lijochm alien!!

  ReplyDelete
 46. ትርጉምና አንባቢያን፤ ‘ፈርስ ባለበት ...’ይባል ነበር ዛሬ ምን እንደሚባል አላውቅም ብቻ ምንም ይፃፍ ምን ስለፍቅርም ይነገር ስለእርቅ፤ስለውበትም ይነገር ስለህይወት፤ያው ትርጉማችን ሁሉ ፖለቲካ(ቦተሊካ)ሆነ እንዴ? ለምን ዙሪያ ጥምጥም መሔድ ይስፈልጋል ደግሞ ለምን ሌላውን መተራስ ይስፈልጋል እስኪመተርጉማን ነን የምትሉ ሁሉ ሌላ መድረክ (ብሎግ) ጀምሩና በግልፅ ተንፍሱ፤ እንወያይ...አልያ’ ፈርስ ባለበት ጥንብ አይጠፋም ፤’...ሊሆን ነው ነገሩ ምኞቴ ብዙነው ከፍሎሪዳ ጫካ፤

  ReplyDelete
 47. Yihun eski! Yezerezerkew bemulu yehulunm ethiopiawi smeit ygaral bye alasbm! Asbiem alawkm. Lenegeru ayferedbhm miknyatum yesetuhn enji yetesethn balemasferh altesasatkm. Kkkkkkkkkk.......

  ReplyDelete
  Replies
  1. I do not think you are an Ethiopian. I perceive, if you are an Ethiopian, you lost your identity. Or you want to be blamed. No body will blame you, because you are nobody.

   Delete
 48. Selam Dani,

  I can't open your PDF file check it.

  thank you

  ReplyDelete
 49. ለምን ቅን አንሆንም ሁለገዜ ነገሮቸን ከፖለቲካል አንጻር እንመለከታለን የታሪክን አወራረድ እና አመጣጥ በዚሁ መልኩ እነደሚቃኝ የገለጸው እንጂ ከብላክ ቴሌቪዝን ወደ ከለር ቴሌቪዝን በዚህ መንግሰት ተለወጠ አላለ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ስለራቀን ወይም ስለራቅነው ማስዋሉ ከኛ ገሸሽ አለ ቢያነሰ እንካነ የተሰማንነ ስሜት በተገቢው አካሃን መገለጽ አንቸልም እኛ እኮ የመጨረሻዎቹ የክፋት ጣሪያ ድሩን ሲሰራበን የተመለከትንን ያየነ ነን ዳኒ ይህንን አስተያየት ከተመለከተከው የቃላት አመራረጥ መቼም ለአንተ አይነገረም ስለዚህ ኮንዶመ የምትለውን ቃል የወሊድ መቆጣጠሪያ ብትላተ ይሻላል ለአፍ ወይም ለሰባኪ አፍ ስላልተለመደ በተረፈ ጥሩ ነው በርታ

  ReplyDelete
 50. lebana police eyaln yetechawetin, bekoba qirinchaf betikesha yeminegeb tiliq yeTor shiguT serten, "gisha gisha gisha" bemalet yahunun 007nin yetekan, Tibatibi ehitochachin sichawetu egnam amiron yetechawetin, meret qofiren tinanish gudguad serten biy yetechawetin, bekorki litach yahunochun designers yemiasniq qebeto yeseran, bedesta keremela litach dingay molten christmas tree laay yanteletelin, genna sider ketimihirt bet melis beyemengedu yesigara litach sebisiben yiheninu christmas tree yaswabin, lebalitina timihirt enqulal tebisen biniwesid misa seat sayders bezaw betimihirt seat kifil wisit bilu tebilen yebelan, yescience timihirt beradio yetemarin, sinarefid meqemechachin beqebetu yenefere, kifil wisit sinatefa ersas betatochachin mehal tedergo tatachin eskiqelana eskiabit yetashen, betesebochachin yegorebet lijoch egnam begorebetochachin tetebiqen yadegin, keremela belomi yemetetin, keguadegnochacnin gaar set wond sanil teqeqefen wedebet begir yemetan, yeneta gaar simaru banimarim gibiwin sinalif yeseman, ere sintu tewerito yaliqal hulu befiqir yetederegebet zemen. ahunim fiqirun ayinfegen

  ReplyDelete
 51. ውድ ዳንኤል ይህን ጽሁፍ እንዳየሁት ደስ ስላለኝ
  ብቻ ፕሪንት አድርጌ ወደበቴ ኣስገባሁ
  ክዚያም ለእናተ የተውሰኑትን አነበብኩላት ከዛ በኋላ አንዴ በትካዜ አንዴ በፈገግታ እናንተ የመጨረሻዎችሁን ዝርዝር አድርጋ ነገረችኝ ዳንኤልንም እናተንም አመሰገንኩ
  መልካም ቀጣይ እይታ

  ReplyDelete
 52. I will add,

  the generation who saw a leader who hated his country, fought more for Eritrea, dismantled all what Ethiopian people loved and respected.... a generation who saw the death of a PM kept secret for over a month from the people he loved....a generation whose dear leader was preserved in a refrigerator for so long while the people he loved prepare for mourning ceremony....

  How about that? Well my narrative perhaps does not quit fit into the 'the last people who....' It rather fits the "first people" who just saw and did what I mentioned above. I hope this will be the last time the Ethiopian people went through this.

  ReplyDelete
 53. yeah funny, you took me back in those days in thought. Really missed that blessed time. I wish if i could leave in those days all my life long.

  Abebaw from America

  ReplyDelete
 54. እኛ የመጨረሻዎቹ አረ ስንቱ ገነት ታምራት
  የሚገርም ነው ትዝታ በትዝታ አደረግኸን የ5ዐዎቹ፣ የ6ዐዎቹ፣ የ7ዐዎቹ መጀመሪያ ድረስ በትንሹ፣ የትምህርት ቤት ሥርዓት፣ ጠዋት ሥነገባ ባንዲራ ዘምረን ሠቅለን፣ ሠልፍ ላይ ሐይጅን ይባላል ንጽህና ልብሳችን፣ ደግሞ ዩኒፎርም ነው የሚለበሰው ከማን በልጬ እና አንሼ የለም፣ ፀጉራችን ምን አልባት ቅጫም ካለው በመቀስ ይጎበኛል ያለበለዚያም
  ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፣ ማታም ስነወጣ ዘምረን ባንዲራ አውርደን አስረክበን ወደቤታችን ይህ የዕለት ተዕለት ሥርዓት ነው፡፡ እስቲ አስተውሎት በፍቅርም ቢሆን አዩኝ አላዩኝ ተብሎ በልብ ቅርጽ ደብዳቤ ተጻጽፎ ያቼም ሰው እንዳያየት ተደብቃ ቢታይ እንኳን የአጎቴ የአክስቴ ልጅ ተብሎ፣ የሚገርመው ፍቅሩም እውነተኛ ነው፡፡ ይዘልቃል፡፡ ጎረቤት ተጎረቤት አቤት ትዝታው ሽሮ፣ በርበሬ እና ቅቤ ሲነጠር ቅመሱ፣ ጠላው ሲጠመቅ አብሮ አተላ መድፋቱ፣ ሁሉ እንደየአቅሙ ዓውደዓመት ሲመጣ ተጠራርቶ ባለቁርጡም ባለክትፎውም ባለዶሮውም ባለሹሮውም እኩል ተሳስቦ አብሮ በልቶ፣ አብሮ ደግሶ ድሮ፣ አብሮ አልቅሶ ቀብሮ፣ ልጅ አብሮ አሳድጎ የኔ ብሎ የእከሌ ልጅ ነው የለም የጎረቤት ልጅ የራስ ነው አብልቶ ቢያጠፋ ቀጥቶ እናቱ ገበያ ብትሄድ አብልቶ ሰብስቦ አረ ስንቱ፣ ዛሬ ለመሆኑ ጎረቤት ጎረቤቱን ያውቅ ይሆን? ከጎረቤቱስ ጋር ይበላ ይሆን ደፋር ሆኖ እንኳን ቤቱ ቢሄድ ግባ ሣይሆን ማነህ አንተ? ምነው በደህና? እንኳን እንደ ጎረቤት አብሮ መብላት ልጆች አብሮ ማጫወታ የሚሞከር አይመስለኝም ምን አልባት በመኪና ሲተላለፋ የመኪና ቀለም ወይም ዓይነት ይተዋወቁ ይሆናል፡፡ ልጆችስ ቢሆን የዛሬውማ ምን ይወራል ለመሆኑ የወለደችው እናትስ ብትሆን መቼም ሁሉም አይሁኑ እንኚ ልታዘው ልታገራው ትችላለች? ውሎአቸው እነሱ ባሉበት፣ ዘመድ እንጠይቅ ቢባሉ እኔ ኘሮግራም አለኝ የሚሉ፣ ፍቅራቸው የዕለት፣ በየመንገዱ እና በየታክሲው ውስጥ መተቃቀፍ ዲያ. ዳንኤል መቼ መሰለህ የእፍረት ቆብ የተቀደደው ከእድገት በሕብረት በኋላ ያው እብደት በሕብረት ተብሎ አልነበረም፡፡

  ReplyDelete
 55. I personally share few of those, the problem is it is too hard to classify generations. In the western world they have such things they call 'Generation X', 'Generation Y'... Which may not work for our case. I think we need to have our own classifications among Ethiopian generations.

  ReplyDelete
 56. እንደ ሰማይ ለራቅሽኝ፣ እንደ ውሃ ለምትጠሚኝ፣ እንደ እንጀራ ለምትርቢኝ እያልን ሌተር የተጻጸፍነው፡፡ ሶፍት ለምኔ ብለን ብሳና ሶፍቱ የተባልነው እኛ፣ ጫማ ብርቁ የነበርነው እኛ፣ መነጽር ቂጡ የነበርነው እኛ፣ በአሥር ዓመት መጣበስ ሳይጣባን ያለፍነው እኛ፣ የኤርትራን አንድነት አጥብቀን የፈለግነው፣ የአሰብን ከፈለጉ ግመል ያጠጡበት የሰነፍ ቃል የተቃውምነው፣ ፌደራሊዝምን በዘርና በጎሳ በመሸንሸን ኢትዮጵያዊነት ማጽረስ እንደማይቻል ገና በእንጭጩ በመጮህ ያስረዳነው፣ አቶ መለስ ይመጣ ዘንድ ያለው ተመላኪ ጣኦት መሆናቸው ቀድሞ ገብቶን ተዉ ይህን ሰው ብለን ያሳሰብነው፣ እኛ የመጨረሻዎቹ ዛሬም የኢሕአዴግ የጨቀየ መንገድ ከድጡ ወደማጡ ነው እያል እየጮህን ያለነው፣ ነገም በኢሕአዴግ መበጠራረቅ የሚደርሰውን የሕዝቦችና የአገሪቱን መራቆት ብለን ነበር ብለን የምንናገረው እኛ የመጨረሻዎቹ ...

  ReplyDelete
 57. FIRST OF ALL THANK YOU VERY VERY MUCH DN. DANIEL
  YOU DO HAVE REALLY SHARPE AND DYNAMIC MIND AND PERSPECTIVE;
  THIS ARTICLE IS THE BEST ARTICLE EVER I RAD ON YOUR BLOG(THIS IS MY OPINION)
  LET ME GIVE MY IDEA ON THOSE THAT PROVIDE COUNTER TO YOUR VIEW FIRST.

  1. WHAT IS THE MEANING OF 'CONDOM' DOES IT HAS ANY OTHER MEANING OTHER THAN THIS 'VERY THIN RUBBER WORN OVER... DURING SEXUAL INTERCOURSE';
  IF YOUR ANSWER IS NO, SO WHAT IS THE PROBLEM OF SAYING CONDOM? I HIGHLY OPPOSE THOSE PERSONS' IDEA WHICH IS TRICKY, VERY OLD AND NEED A COURSE OF 'INTRODUCTION TO 21 CENTURY; PLEASE THOSE PERSONS TRY TO UPDATE YOUR DOS(DISC OPERATING SYSTEM SOFTWARE); HE USED THE WORD CONDOM APPROPRIATELY AND CONTEXTUALLY; SO DON'T TRY HIS SPIRITUALITY AND PREACHER AS A COUNTER TO THE USAGE OF THE TERM BECAUSE THE NAME OF THE WEBSITE/BLOG IS DANIEL VIEW NOT YOUR VIEW AND MY VIEW BUT WE DO HAVE THE RIGHT TO SAY WHAT WE FEEL AND THINK BUT CONSTRUCTIVELY
  2. THIS IS FOR THOSE/THAT PERSON WHO BLAME DANI BECAUSE HE IS NOT INCORPORATING POLITICAL IDEAS ON THIS ARTICLE; MY FIRST RESPONSE IS THIS IS NOT THE BLOG TO DUMP YOUR POLITICAL AGENDA; RATHER THIS IS A PLACE TO CONVEY YOU INTELLECTUAL OR UNIQUE SOCIAL PERSPECTIVE OR VIEW; IF YOU ENJOY SUCH KIND GO TO OTHER WEBSITES/BLOGS AND ATTEND THEM; BUT THIS IS UNIQUE AND SHARP PERSPECTIVE; LIFE IS NOT A MERE POLITICS BUT POLITICS IS ONE PART OF LIFE NOT ALL.

  IN ADDITION I LIKE TO SHARE MY PAST LIFE

  - WEDE KES TIMHIRT BET KESEFER GUDEGNOCHACHIN GAR YEHDNIBET HA HU HI HI HA HE HE H HO BEZEMA YALNIBET BE EREFT SEAT BE SHROP TERMUS YEYAZNEWIN WUHA YETETANIBET BEWIST YALEWUN BAKEL YEBELANIBET
  _ ELEMENTATY TIMHIRT BET BE EREFT SEAT KE SET LIJOCH PARTINI,BOMBOLINO,... NETKEN YEROTNIBET
  - TEWAT TIMIRT BET ARFIDEN BEZA BEBIRD BE LIMICH YETEGEREFNIBET.. SHINTBET YASEDANIBET..
  _ BE SAMINT ANDE WEYIM HULETE KESEAT KEHONIN BET TERAGI TEMEDIBET YEMEMARIA KIFLACININ YASEDANIBET
  _ TEWAT TIMIRT BET SINGEBA MEZMUR ZEMIRET BANDIRA YESEKELNIBET..KESEAT SINILEKEK BESELF BANDIRA YAWEREDNIBET
  _ YEBET SIRA SANSERA KERTEN YETEGEREFNIBET
  _ SEFER KUAS NEW BILEN BEKALSI YETETEKELELE DINGAY LE MENGEDEGNA YASMETANIBET .YESAKNIBET
  _ YEKORKI ZEMEN, YEMEKINA ZEMEN, YEGIRAF, ZEMEN,
  _ BUHE BET BELASTIK SERTEN YAKEBERNIBET, BUHE CHEFIREN SANTIMINA MULMUL DABO BEYEBETU ZUREN YELEMENIBET
  _ KESEFER LIJOCH GAR LEMEWAGNENET WEDE WENZ YEHEDNIBET, SINIWAGN YETEDEFAFEKINIBET, KEWANA MELS BETESEB ENDAIKOTA WEYIM FITACHIN NECH ENDAYHON KIBAT WEYIM FITACHININ MIRAK YETEKEBANIBET
  _GOBEZ TEMARIWCH TEBILEN 'SPECIAL CLASS' FETENA YETEFETENIBET
  _ SENE 30 DULAHIN ANSA BILAN LE SENE 30 KE LELOCH SEFER LIJOCH GAR YETEDEBADEBINIBET

  Ere sintu Really I impressed and turned back to 20/25 years back I am 28 years old

  i will write more on other time

  ciao
  thank you dani berta God/Allah bless you  ReplyDelete
  Replies
  1. Well come our muslim(?) brother. we appreciate ur involvement. But, would u choose the best font style to read easily what u will write for the future? Times new roman is good.

   Delete
 58. ዳኒ! በእውነት ትልቅ ሰው ነህ!ወደፊት መተንበይ የሚችል፤ ወደ ሁዋላ ማስታዎስና፤ ዛሬን በደንብ መመልከት የሚችል የብሩህ አእምሮ ባለቤት ነህ!መቸሰ ምሰጋና ከሁሉም አካባቢ እንደሜደርሰህ እርግጠኛ ነኝ:እኔ ግን ለአንተ ለአንድ ነብሰ ብቻ ብየ ሳይሆን ለዚሁ ሁሉ የጽሑፈሕ ተከታታይ እና ቃለ ወንጌል አዳማጭ ሲባል ለአገሪ:ለወገኔ:ለቤተሰቤየ:እንዲሁም ለዝች ላለሁበት አገር አሜሪካ ሰጸልይ ለአንተም እድሜና ጤና እንዲሁም መቻሉን ፡ማሰተዋሉን:ትእግሰቱን :እንዲሰጥህ ከልብ እጸልይልህ አለሁ::እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይሁን!አሜን!

  ReplyDelete
 59. Dn. Daniel! I would like to thank for the views on your interesting and memorable article. God bless you! As a historian I want to say sth. on the the way;i.e. every thing passed with time and people must understand whatever they did on their life time have its own contribution to the generation history in that specific country. The problem is our understanding about history. History is all about past generation politics, economics, societal make up and activities, thinking, livelihood, culture, lifestyle,etc. That is why scholars said that "Past politics is present history and present politics is future history". Dn. Daniel article is a contribution to rewind our mind so there is no problem on the article he wrote to us. Of course, there are three stream of people; people who make history, people who admire history and people who ignore the value of history (not see worth of history)rather focus on blame on people achievement through out their life time and history makes them history themselves.

  ReplyDelete
 60. እኛ የመጨረሻዎቹ አረ ስንቱ ገነት ታምራ
  የሚገርም ነው ትዝታ በትዝታ አደረግኸን የ5ዐዎቹ፣ የ6ዐዎቹ፣ የ7ዐዎቹ መጀመሪያ ድረስ በትንሹ፣ የትምህርት ቤት ሥርዓት፣ ጠዋት ሥነገባ ባንዲራ ዘምረን ሠቅለን፣ ሠልፍ ላይ ሐይጅን ይባላል ንጽህና ልብሳችን፣ ደግሞ ዩኒፎርም ነው የሚለበሰው ከማን በልጬ እና አንሼ የለም፣ ፀጉራችን ምን አልባት ቅጫም ካለው በመቀስ ይጎበኛል ያለበለዚያም ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፣ ማታም ስነወጣ ዘምረን ባንዲራ አውርደን አስረክበን ወደቤታችን ይህ የዕለት ተዕለት ሥርዓት ነው፡፡ እስቲ አስተውሎት በፍቅርም ቢሆን አዩኝ አላዩኝ ተብሎ በልብ ቅርጽ ደብዳቤ ተጻጽፎ ያቼም ሰው እንዳያየት ተደብቃ ቢታይ እንኳን የአጎቴ የአክስቴ ልጅ ተብሎ፣ የሚገርመው ፍቅሩም እውነተኛ ነው፡፡ ይዘልቃል፡፡ ጎረቤት ተጎረቤት አቤት ትዝታው ሽሮ፣ በርበሬ እና ቅቤ ሲነጠር ቅመሱ፣ ጠላው ሲጠመቅ አብሮ አተላ መድፋቱ፣ ሁሉ እንደየአቅሙ ዓውደዓመት ሲመጣ ተጠራርቶ ባለቁርጡም ባለክትፎውም ባለዶሮውም ባለሹሮውም እኩል ተሳስቦ አብሮ በልቶ፣ አብሮ ደግሶ ድሮ፣ አብሮ አልቅሶ ቀብሮ፣ ልጅ አብሮ አሳድጎ የኔ ብሎ የእከሌ ልጅ ነው የለም የጎረቤት ልጅ የራስ ነው አብልቶ ቢያጠፋ ቀጥቶ እናቱ ገበያ ብትሄድ አብልቶ ሰብስቦ አረ ስንቱ፣ ዛሬ ለመሆኑ ጎረቤት ጎረቤቱን ያውቅ ይሆን? ከጎረቤቱስ ጋር ይበላ ይሆን ደፋር ሆኖ እንኳን ቤቱ ቢሄድ ግባ ሣይሆን ማነህ አንተ? ምነው በደህና? እንኳን እንደ ጎረቤት አብሮ መብላት ልጆች አብሮ ማጫወታ የሚሞከር አይመስለኝም ምን አልባት በመኪና ሲተላለፋ የመኪና ቀለም ወይም ዓይነት ይተዋወቁ ይሆናል፡፡ ልጆችስ ቢሆን የዛሬውማ ምን ይወራል ለመሆኑ የወለደችው እናትስ ብትሆን መቼም ሁሉም አይሁኑ እንኚ ልታዘው ልታገራው ትችላለች? ውሎአቸው እነሱ ባሉበት፣ ዘመድ እንጠይቅ ቢባሉ እኔ ኘሮግራም አለኝ የሚሉ፣ ፍቅራቸው የዕለት፣ በየመንገዱ እና በየታክሲው ውስጥ መተቃቀፍ ዲያ. ዳንኤል መቼ መሰለህ የእፍረት ቆብ የተቀደደው ከእድገት በሕብረት በኋላ ያው እብደት በሕብረት ተብሎ አልነበረም፡፡
  ዲያቆን ዳንኤል፣ አረ ስንቱ ጋሼ ማረኝ ማረኝ ዶሮም ብር አወጣች እኔም ሥጋ አማረኝ ሆነ ሁሉም ቀረ ዘመን ተለወጠ ብቻ እጋዜአብሄር በበጎ እና በምህረቱ ይጎብኝንን አሜን፡፡  ReplyDelete
 61. This is one of the best articles I have read via this blog. God bless you bro!

  ReplyDelete
 62. ዲያ.ዳንኤል እግዚአብሔር መልካሙን ነገር ሁሉ ያድርግልህ ይህ ፁሑፍ ከተለቀቀ ጀምሮ ሁል ጊዜ አነበዋለሁ በጣም ደስ ብሎኝ ተምሬበት፤ግን አንድ ነገር ቸገረኝ የ7ዐዎቹ ምን እንሁን ድሮ ብለን ለማውራት የፈጠንን አዲሱ ነገር የተንደረደረብን ጀምረን በደንብ ሳንጠግበው ለድሮ የሚፈጥንብን ከፃፍከው የማስታውሰው አለ የማላውቀውም አለ እኛ የመጨረሻዎቹ ያለው ሰው ጋርም ያገኘሁት አለ ግን የመጨረሻዎቹ አንሆንም እንደ 8ዐዎቹ አይደለንም ለኛ ሌላ የትውልድ ክፍል ይፈጠርልን እንዴ ለማንኛውም ወንድማችን እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልህ እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ፡፡

  ReplyDelete
 63. በዚህ ጽኁፍ እኔም ባልሳተፍ ደስ አይለኝም፤ ባንዲራ ከሩቅ ሲሰቀል አይተን ማንም ሳያስገድደን በደስታ ቀጥ ብለን (ፖዝ ሆነን) ሌሎችንም ቀጥ እንዲሉ መክረን የቆምን እኛ፣ ፋኖስና ብርጭቆን ጨምሮ በአማርኛ መጽሀፍ ያሉ ግጥሞችን ለመሸምደድ የተወዳደርን እኛ፣ በዲሞ (6 ቆርኪዎችን በማስቀመጥ ከ6 ርምጃ ያህል ርቀት ማፍረስና የተቃራኒ ቡድን በኳሷ ጀርባን የሚደልቅበት ጨዋታ) የተዝናናን እኛ፣ አስተማሪችንን ከመንገድ ስናይ ተደብቀን ያሳለፍን እኛ፣ …. በእዉነት ዳኒ ከጻፍካቸው ጽሁፎችህ ሁሉ በጣም የሚነካው ይሄ ነው…በቃ በጣም ያሳዝናል፣ አዝናኝነቱና አተራረኩ ደግሞ ግጥም ሳይሆን ከጌትነት እንየው “ኳስ እንይበታ” ግጥም ጋር ይስተካከላል፤ ድንቅ አንባቢያንም በድንቅ ሁኔታ ተሳትፈዋል፡፡ ያቆይልን ዳኒንም ተሳታፊዎችም፡፡

  ReplyDelete
 64. God bless you Dani. a lot of negative mind people out there. don't be discourage by there evil idea. u wrote what u felt in a right way that's a good thing we need to develop. HATER PLZ STAY AWAY !!!!

  ReplyDelete
 65. እኛ የመጨረሻዎቹን ለመጨረሻ ጊዜ መቼ ነው የማነበው?

  ReplyDelete
 66. harif new yetelatn worie atsma

  ReplyDelete
 67. "ታሪክ የመጨረሻዎቹ እስኪያደርገን፤ እኛ የመጀመርያዎቹ ነን!"
  Published by Asnake lebawi on July 14, 2015 at 2:00amView Blog
  በማስተርስ ስራ ያጣን፣ በድግሪ ኮብልስቶን የፈለጥን፣ መቶ ብር የአንድን ብር ዋጋ ሲያጣ የታዘብን፣ ጤፍ በሶስት ሺህ ብር የሸመትን፣ ደሞዝ 3ቀን የማይበረክትልን፣ ኑሮ ባላየ ያለፈን፣ ፋሲካን በበግ ቅርጫ ያከበርን እኛ የመጀመርያዎቹ ነን. . . .
  ለእንጀራ ለሚሰደደዉ ፀልየን ሳንጨርስ እንጀራም ሲሰደድ(ኤክስፓርት ሲደረግ) ያየን፣ ጤፍ ትቶን ላብራቶሪ የገባ፣ ማስቲካ በስድሳ ብር ገዝተን ሳይጠዘጥዘን አላምጠን የተፋን፣ ግድግዳችንን የሚያስንቅ TV ያየን፣ በ3D የተደመምን በ7D ነፍሳችን እስኪወጣ የጮህን፣ ባቡር ብርቅ የሆነብን እኛ የመጀመርያዎቹ ነን. . . .

  ቡና ከአቦል ወዲያ አመድ አመድ ያለብን፣ ቡና በቂቤ ያልቀመስን፣ ነጭ ጠጅ የጠጣን፣ በወጉ ያልሰከርን፣ ሲያብዱ አይተን ያበድን እኛ የመጀመርያዎቹ ነን. . . .

  በፌስቡክ ያጨን፣ በሰርጋችን ማግስት 'ብርአምባር ሰበረል ሆ' ተብሎ ያልተዜመልን፣ ድንግልና ከምድረገፅ የጠፋን (አይተን የማናዉቅ)፣ ቀብርን እንደሰርግ የቀረፅን፣ ሞተን በተቀበርንበት እያለ በሚያስመኝ የሬሳ ሳጥን ሲቀበሩ ብናይ በሟች
  የቀናን እኛ የመጀመርያዎቹ ነን. . . .

  አንድ መሆን የጠፋን፣ የጀበና ቅርፆ ቢፈርስብን ክዳን የሌለዉ ማንቆርቆሪያ መሳይ የእናት ሃገር ካርታ የሳልን፣ ከ97 የተረፍን፣ ከኢቦላ ብናመልጥ ከአይኤስ የወደቅን እኛ የመጀመርያዎቹ ነን. . . .

  ለቦብ ሃዉልት ያቆምን፣ የኛን የረሳን የሰዉ ያሰብን፣ በሌጋሲ የተመራን በራእይ የበለፀግን፣ ታሪክ ስናነሳ ታሪክ ስንጥል የ3ሺ አመት ታሪክ ስናጎድፍ የ24 አመት ታሪክ ስናደምቅ የከረምን፣ መዉደቅን በተግባር የኖርን እኛ የመጀመርያዎቹ ነን. . .

  "ታሪክ የመጨረሻዎቹ እስኪያደርገን፤ እኛ የመጀመርያዎቹ ነን!"

  ReplyDelete