Friday, November 2, 2012

ፓርኪንግ


አሜሪካን ሀገር ወደሚኖሩ ወዳጆቼ ቤት ሄጄ ነበር፡፡ ከተጋቡ ሁለት ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ቤታቸው ስገባ የቤቱም ዕቃ የቤቱም ሰዎች ዝምታ ውጧቸዋል፡፡ አባ አጋቶን ቤት የገባሁ ነው የመሰለኝ፡፡ እርሱ ክፉ ላለመናገር ሰባት ዓመት ድንጋይ በአፉ ጎርሶ በአርምሞ ተቀምጧል፡፡ ነገር ዓለሙ አላምር ሲለኝ ‹ምነው ያለ ወትሯችሁ ዝምታ ዋጣችሁ› ብዬ ተነፈስኩ፡፡ እዚህ ቤት የነበረውን ሳቅና ጨዋታ ስለማውቀው፡፡ ‹ሳቅና ጨዋታ ዝና ካማራችሁ› ሲባል አልሰማችሁም፡፡
የመለሰልኝም የለ፡፡
በኋላ ነገሩን ሳጠናው ሁለቱም ተኳርፈዋል ለካ፡፡ ‹‹ለመሆኑ እንዲህ ሳትነጋገሩ ስንት ጊዜ ተቀመጣችሁ› ብዬ ስጠይቅ ስድስት ወር ሆኗቸዋል፡፡ ሁሉም በየሥራው ይውላል፤ ማታ ይመጣል፤ ኪችን ገብቶ ያበስላል፤ በልቶ ቴሌ ቭዥን ያያል፤ ከዚያም ይተኛል፡፡ ቢል ሲመጣ ይህንን እኔ ከፍያለሁ ብሎ አንዱ ወረቀት ጽፎ ይሄዳል፤ ሌላው በተራው ይከፍላል፡፡ ይቺ ናት ትዳር፡፡
ድሮ የሰማሁትን ቀልድ ነበር ትዝ ያሰኙኝ፤ ባልና ሚስቱ ተኳርፋው አይነጋገሩም አሉ፡፡ ቤቱ እንደ መቃብር በጸጥታ ተውጦ ከርሟል፡፡ አንድ ቀን ባል ሌሊት አሥር ሰዓት የሚነሣበት ጉዳይ ገጠመው፡፡ ከተኛ መነሣት የሚከብደው ቢጤ ነበርና የመቀስቀሻውን ሰዓት ሊሞላ ሲስበው ተበላሽቷል፡፡ አዘነም፤ ተናደደም፡፡ ምን ያድርግ፡፡ ባለቤቱ ገና ከሥራ አልገባችም፡፡ ‹የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይመርጡ› ነውና፡፡ በቁራጭ ወረቀት ላይ ‹አሥር ሰዓት ላይ ቀስቅሽኝ› ብሎ ጽፎ በራስጌው ባለው ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠና ተኛ፡፡
ሚስቱ ስትመጣ አየችውና ስቃ ተኛች፡፡ ልክ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ነቃችና በዚያው በቁራጭ ወረቀት ላይ ‹አሥር ሰዓት ሆኗልና ተነሣ› ብላ ጽፋለት ተኛች፡፡ እርሱ ዕንቅልፉን ለጥጦ ለጥጦ ሲነሣ ነግቷል፡፡ ተናደደ፤ ግን እንዳይናገራት ለካስ ተኳርፈዋል፡፡ እዚያው ወረቀት ላይ ‹በጣም ታሳዥኛለሽ› ብሎ ጻፈላት፡፡
እነዚህ ወዳጆቼ ይህን ነበር ያስታወሱኝ፡፡ አሁን እንዲህ ያለው ኑሮ ምን ዓይነት ኑሮ ይባላል? ብዬ ስም ፍለጋ ብዙ ጊዜ አሰብኩ፡፡ 
ይህን እያሰብኩ እያለ አንድ ዕቃ ለመግዛት ‹ካስኮ› ወደሚባለው አሜሪካ ውስጥ ካሉት ታላላቅ መደብሮች ወደ አንዱ ከእነዚሁ ወዳጆቼ ጋር ተጓዝን፡፡ እዚያ መኪናችን ለማቆም አራት የፓርኪንግ ፎቆችን መውጣትና እንደ አዲስ አበባ ስታዲዮም የተለጠጠውን ሰፊ የማቆሚያ ሜዳ ማካለል ነበረብን፡፡ ለዓይን እስኪያታክት ድረስ መኪኖቻ ተኮልኩለውበታል፡፡ በዓይነት ባይነታቸው፡፡ ረዥም፣ አጭር፣ ሽንጣም፣ ቁመታም፤ ያበጠ፣ የከሳ፣ ግልጽ፣ ድፍን፣ ነጭ፣ ቀይ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ፣ ወይን ጠጅ፣ ምኑ ቅጡ፤ ተደርድረዋል፡፡ ጎን ለጎን፣ ፊትና ኋላ፤ በኋላ መመልከቻቸው ሊነካኩ እስኪደርሱ ድረስ ተደርድረዋል፡፡
የሚገርመው ግን አንዱ ከሌላው ጋር አያወሩም፣ አይጫወቱም፣ ኧረ እንዲያውም አይተዋወቁም፤ አንድ ያደረጋቸው በአንድ የፓርኪንግ ሜዳ መቆማቸው፣ ጎን ለጎን መሆናቸው፣ በአንድ ጣራ ሥር ውሎ ማደራቸው ብቻ ነው፡፡ የዚያኛውን ጠባይ፣ ሥሪት፣ ዓላማና፣ የኑሮ ጓዳ ይህኛው አያውቅም፤ እንዴው በአንድ ፓርኪንግ ቦታ ብቻ አብሮ ቆሞ ማደር፡፡ እነርሱምኮ ‹ቢል› አለባቸው፡፡ የፓርኪንግ ቢል፡፡
ያኔ ስም አገኘሁለትና እነዚህን ወዳጆቼን ‹የእናንተ ኑሮኮ ፓርኪንግ ነው› አልኳቸው፡፡ ሁለቱም ወደ እኔ ዞሩ፡፡ ‹እስኪ እነዚህን መኪኖች እዩዋቸው፤ አይፋቀሩ፣ አይጣሉ፣ አያወሩ፣ አይጫወቱ፣ አይወያዩ፣ አብረው አይሠሩ፣ አብረው መከራ አይካፈሉ፣ አብረው አይደሰቱ፤ ግን በአንድ የፓርኪንግ ቦታ ቆመዋል፡፡ ሁሉም በየራሱ መጥቶ ቆመ፡፡ ሁሉም በየራሱ ተነሥቶ ይሄዳል፡፡ የእናንተስ ከዚህ በምን ተለየ፡፡ ሁለታችሁም በየራሳችሁ ትውላላችሁ፤ ማታ ስትመጡ ቤታችሁ ውስጥ ፓርክ ታደርጋላችሁ፤ በቃ›
ከልባቸው ነበር የሳቁት፡፡ ፍርስ እስኪሉ፡፡
ለሰው አንድ ቦታ መሥራት፣ አንድ ቦታ መኖር፣ አንድ አልጋ መተኛት፣ በአንድ ቢሮ መዋል፣ አንድ ሕንፃ ላይ መኖር ብቻውን ከሰው ጋር መኖር አያሰኘውም፡፡ ይኼንንማ መኪኖችም ይኖሩታልኮ፡፡ ያውም ሰላማዊ በሆነና ማንም ማንንም ሳይነካ፣ ማንም በማንም ቦታ ላይ ሳይደርስ፤ ግን ይህ ፓርኪንግ እንጂ ኑሮ አይደለም፡፡ ኑሮ ያፋቅራልም ያጣላልም፤ ያገናኛልም፣ ያወያያልም፤ ኑሮ መስተጋብር አለው፡፡ አንደኛው በሌላው ውስጥ ቦታ ሊኖረው ይገባልኮ፡፡
ወዳጅነትኮ አብሮ ከመዋልና ከመኖር፣ ከመሥራትም በላይ ነው፡፡ አንቺ ባልሽ ሳይደውል ሲቀር ሲጠፋ፣ ያስለመደሽ ነገር ሲቀር፣ አንዳንድ ነገሩ ሲለወጥ ቅር የማይልሽና ምንም የማይሰማሽ ካልሆነ ድሮም ትዳር ሳይሆን ፓርኪንግ ነበር የመሠረታችሁት፡፡ እስኪ ያንን መኪና ተመልከቱት ተነሥቶ ሄደ፤ ከጎኑ ያለው መኪና ምን ተሰማው? ምንም፡፡ ሌላው ደግሞ መጣ፤ አያችሁ ፓርኪንግ ሲሆን እንደዚህ ነው፡፡ ወዳጅህ ቢኖር ባይኖር፤ ሰላም ቢልህ ባይልህ፣ ቢመጣ ባይመጣ፣ ካንተ ቢለይ፣ ባይለይ ምንም ካልመሰለህ ይህ ፓርኪንግ እንጂ ወዳጅነት አይደለም፡፡
ለአንዳንድ ሰዎች ወዳጅነት ማለት በፈለጉበት ጊዜ መጥተው ሊያቆሙበት የሚችሉ ፓርኪንግ ይመስላቸዋል፡፡ አይደለም፡፡ ወዳጅነት ጎን ለጎን አይሆንም፡፡ ወዳጅነት አንዱ በሌላው ውስጥ ቦታ ሲኖረው ነው፡፡ ለዚህ ነው ያ ወዳጅህ ሲቀር ክፍተት የሚሰማህ፡፡ ‹ሰው ቢሄድ ሰው ይመጣል› እያሉ የሚዘፍኑ አሉ፡፡ እነዚህ ፓርኪንግ እንጂ ወዳጅነት የማያውቁ ናቸው፡፡ በወዳጅነት ውስጥ ‹ሰው ቢሄድ ሰው ይመጣል› የሚባል መፈክር ተይዞ ሲቀበሉና ሲሸኙ መኖር አይቻልም፡፡ ዘላቂ ወዳጅ የሌለው ፓርኪንግ ብቻ ነው፡፡ እርሱም እንኳን አንዳንዴ ለአንድ ሰው ተመድቦ ይሰጣል፡፡
አሁን አሁንማ በኛም ሀገር የፓርኪንግ ኑሮ እየተለመደ ነው፡፡ ጎረቤቱን የማያውቅ መንደርተኛ፣ ግድግዳ የሚጋራውን የማያውቅ ባለ ኮንዶሚኒየም፣ አብሮ ነዋሪውን የማያውቅ ደባል እየመጣ ነው፡፡ በአንድ ሕንፃ ላይ እየሠሩ ፈጽሞ የማይተዋወቁ ሰዎች እየተፈጠሩ ነው፡፡
እንዲያውም አንድ ወዳጄ ለአንድ የሥራ ጉዳይ አንድ ባለሞያ ይፈልግ ነበርና አንድ ወዳጁ ስልክ ይሰጠዋል፡፡ ጎበዝ ባለሞያ ነው በዚያውም ተዋወቀው ይለዋል፡፡ ስልኩን ተቀብሎ ይደውልለትና ስለ ሥራው ይነጋገራሉ፡፡ ይግባባሉ፡፡ እጅግ የተሻለው ነገር በአካል መነጋገሩ ነበርና ‹ቢሮህ የት ነው› ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ አድራሻውን ሲነግረው እዚያ እርሱ ያለበት ሕንፃ ላይ ነው፡፡ የቢሮ ቁጥሩን ይጠይቀዋል፡፡ እጅግ የሚገርመው ነገር የዚያ ባለሞያ ቢሮ ከእርሱ ቢሮ ጎን ነበረ፡፡ ሦስት ዓመት ሠርተዋል አይተዋወቁም፡፡
አያችሁ ፓርኪንግ እንዲህ ያደርጋል፡፡
ቤት ሲገቡ እርሱ ቴሌቭዥን ይከፍታል፣ እርሷም ኪችን ትገባለች፣ እርሱ ይተኛል፣ እርሷ ስልክ ላይ ናት፤ ልጆች ጌም ያጫወታሉ ወይም የሕፃናት ፊልም ያያሉ፤ እንግዳም ፎቴው ላይ ተቀምጦ ይተክዛል ወይም ያንጎላቻል፡፡ እንዲህ እየሆነኮ ነው ኑሮ፡፡ ኑሮ ፓርኪንግ ሲሆን፡፡ በዚህ ዘመን ትልቁ ቅጣት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? የፓርኪንግ ኑሮ በሚኖሩ ሰዎች ቤት እንግዳ ሆኖ መሄድ፡፡
ቀደምቶቻችንማ አካባቢን የሚያስተሳሥሩ አያሌ ገመዶች ፈትለው ነበር፡፡ ዕድሩ፣ ዕቁቡ፣ ሰንበቴው፣ ማኅበሩ፣ ቡና መጠራራቱ፣ ግብዣ መገባባዙ ሠፈርተኛውን ያቀራርበው ነበር፡፡ ማቀራረብ ብቻ ሳይሆን ለመረዳዳትም አስችሎት ነበር፡፡ ከዚያም ባለፈ የአካባቢው ጸጥታ እንዲጠበቅ ያደርገው ነበር፡፡ የሠፈሩ ሰው፣ የሠፈሩ ልጆች ስለሚታወቁ የማይሆን ሰው መጥቶ የማይሆን ሥራ ለመሥራት አይመቸውም ነበር፡፡ የተጣላ ሰው ቢኖር እንኳን ከእነዚያ ማኅበራዊ ሁነቶች በአንዱ ሲቀር ‹ምን ሆኖ ነው› ይባላል፡፡ ይታወቃል፡፡ አስታራቂም ይላካል፡፡
አሁንኮ መዋደዳችንም መጣላታችንም ሊታወቅ አልቻለም፡፡ በሠፈራችን ውስጥ እጅግ የረቀቀ ወንጀል ቢሠራ እንኳን ሁሉም ግቢውን ብቻ ስለሚያውቅ የሚከላከለው አይገኝም፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ታላላቅ የመኖርያ ግቢዎች መኪኖቻቸው የሚተዋወቁትን ያህል እንኳን የማይተዋወቁ ጎረቤታሞች አሉ፡፡ መኪኖቻቸው እንኳን አንዳንድ ቀን መንገድ ዘጋህ ብለው በጡሩንባ ይነጋገራሉ፡፡ ባለቤቶቻቸው ግን እንደተዘጋጉ ናቸው፡፡
‹ሠፈራችን› እንለው የነበረውኮ ስለተወለድንበትና ስላደግንበት ብቻ አልነበረም፡፡ እዚያ አካባቢ ብዙ ትዝታዎች አሉን፡፡ የወንዙ፣ የጭቃው፣ የኳስ ጨዋታው፣ የተደባደብነው፣ የጠፋነው፣ የተመረቅነው፣ የተረገምነው፣ አብረን ትምህርት ቤት የሄድነው፣ የመለያ ምት እንደሚጠብቅ ቡድን በመሥመር ተቃቅፈን የተጓዝነው እነዚህ ሁሉ ናቸው ‹ሠፈር› ማለት፡፡
አሁን የሠፈር ልጆች የሌላቸው ልጆች እያሳደግን ነው፡፡ አብረው ሆያ ሆዬ የማይሉ፣ ኳስ የማይጫወቱ፣ ሰኞ ማክሰኞ የማይጫወቱ፣ ሾላ እርግፍ እርግፍ የማይሉ፣ ጢብ ጢብ የሌላቸው፣ አኩኩሉን በተረት ብቻ የሚያውቁ ልጆች እየመጡ ነው፡፡ ይህ ሁሉ እንግዲህ የፓርኪንግ ውጤት ነው፡፡
እና ወዳጆቼ፣ ኩርፊያና ግጭት ይኖር ይሆናል፡፡ እንኳን ሰውና ሰው ጉልቻና ጉልቻ እንኳን ይጋጫል ይባላል፡፡ ግን ልክና መጠን ያስፈልገዋል፡፡ እንዲህ አንድ ቤት እየኖራችሁ ለረዥም ጊዜ ከተዘጋጋችሁማ እናንተ ፓርኪንግ ሜዳ ላይ የቆማችሁ መኪኖች እንጂ ምኑን ወዳጆችና ባለትዳሮች ሆናችሁት፡፡
እንደሳቁ ዕቃችንን ገዝተን እንደሳቁ ቤታቸው ገባን፡፡ ይኼው ዛሬም እየሳቁ ይደውሉልኛል፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ስለሆነ በተመሳሳይ ኅትመት ባይወጣ ይመረጣል፡፡


53 comments:

 1. ዳ/ን ዳንኤል በውነት የኛንም ቤት ነው ያየሀው ለሁላችንም ትምህርት ነው እግዚአብሔር እድሜና ጸጋውን ይስጥህ

  ReplyDelete
 2. እውነትም የዳንኤል እይታ:: ዳኒ እውነት እይታህ ምጡቅ ነው::

  "አሁን የሠፈር ልጆች የሌላቸው ልጆች እያሳደግን ነው፡፡ አብረው ሆያ ሆዬ የማይሉ፣ ኳስ የማይጫወቱ፣ ሰኞ ማክሰኞ የማይጫወቱ፣ ሾላ እርግፍ እርግፍ የማይሉ፣ ጢብ ጢብ የሌላቸው፣ አኩኩሉን በተረት ብቻ የሚያውቁ ልጆች እየመጡ ነው፡፡ ይህ ሁሉ እንግዲህ የፓርኪንግ ውጤት ነው፡፡ "

  ሳስበው ማኅበራዊ ኑሮ ቀስ በቀስ እየተሸረሸረብን ነው::
  በርታ ዳኒ ሁሌም እውቀትን እንገበኛል::

  ReplyDelete
 3. What an interesting read! Many thanks.

  ReplyDelete
 4. በእውነት ያስቃል፣ ያስተምራል፣ እኔም አልፎ አልፎ የፓርኪንግ ላይፍ ይመቸኛል፡፡

  ReplyDelete
 5. በጣም ጥሩ ዕይታ ነው፡፡ ዉሀ እንኳ ፏዋ ብሎ ሚፈሰው ከስንት ዐለት ጋር ከተጋጭቶ በሆዋላ ነው የሚለውን ጽሁፍህን አስታወስከኝ…

  ReplyDelete
 6. Girum tsihuf new betam betam temirebetalehugn Dani.

  Bizuwoch yetidar hiwotachew yeparking hiwot honobachew lemichegeru yihichi tiru medihanit nat iyawazach yebesihtawin senikof yemitinekil. Desta yetefabetin, selam fetsimo yrakebetin gojo selam fikir, desta indisefinibet yemiyaderig newina berta ketilibet ilalehugn.

  kebede

  ReplyDelete
 7. Many thanks D/n Daniel. It is a very nice article. I hope many of us learn alot from it.

  ReplyDelete
 8. Its a great view and expression, cheers!! But have you requested the couple for permission before posting their case? If not so, I think this is not ethically acceptable! What do others say on this....

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔንም ውስጤ የሚመላለስ ነገር ነው:: የጽሑፉ ጭብጥና ይዘት ጋ ምንም ችግር የለብኝም:: ግን ሁልጊዜ ሳነብ "ዳንኤልን እንዴት እንደ ባልንጀራ መቅረብ ይቻላል?" የሚል ስጋት ውስጤ ይፈጠራል:: በተመሳሳይ መልኩ አንድ ጊዜ "መንፈሳይ" እና "መንፈሳዊ" ብሎ የጻፈው ጽሑፍ ነበረ ከአንዲት እህት ተሞክሮ በመነሳት:: "ስለ ሰው ኃጢያት እና ድክመት ያን ያህል ለአደባባይ ይዞ መቅረብ ተገቢ ነው ውይ?" የሚል ጥያቄ ተፈጥሮብኝ ነበር ያኔም:: አንዳንድ ጊዜ የፈጠረው ፈጣሪ ያልሰለቸውን ፍጡር እኛ ኃጢያቱን እናበዛበታለን:: እናም ዳንኤል በሚያነሳቸው ሃሳቦች ብደሰትም የሰውን ልጅ ገመና በብዕር ይዞ መሮጡን አልወደድኩለትም::

   Delete
  2. This is an event, it does not need approval. They did not have ownership certificate from ....

   Delete
  3. ዳንኤል የሚያውቀው ሰው እልፍ ነው፡፡ በስም እከሌ ብሎ እስካልጠቀሰ ድረስ ከባለጉዳዩቹ ውጭ ማንም ይህን ሚስጥር ሊያውቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ ሰው ትምህርት የሚያገኘው እንዲሁ ከማህበራዊ ኑሮ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመነሳት ስለሆነ ምንም ቅር የሚያሰኝ ነገር የለውም፡፡ የነዛ ወዳጆቹ ችግር የሚሊዮኖች ችግር ነውና፡፡ ዳኒ ላመሰግንህ ወደድኩ፡፡

   Delete
  4. ትምህርት እስካገኘህት ምን አስጨነቀህ የሰው ዋጋ ለማሳነስ ምን አስሮጠህ፡ ከዳንኤል ልትማር ወዲህ መጥተህ ይቺን አንተ ያወቅሃትን ተራ ነገር መገመት ያቅተው ይመስልሀል፡፡ ምን አልባት ሌላ ሰው ታሪኩን ነግሮት ለትምህርት አቅርቦት ሊሆን ይችላል ብለህ ለራስህ ንገረው፡፡ አሁን አስተያየት ሰጠህ ማለት አይደለም፡፡ ሌላን የሚጠቅም አስተያየት ጻፍ፡፡ መጻፍ መብትህ ቢሆንም የሌላ ስሜት መንካትን እንዴት ታየዋለህ ትምህርት አገኘህበት? መልካም ምን ? ምንም አላገኘህበትም? እለፈው በቃ ጽሁፍህ ጭቃ መቀባት ይመስላል፡፡
   አስራት
   ከቨርጂንያ

   Delete
  5. Dear all,
   I appreciate the article's message, but still i have reservation. You see he has stated in the article that: he has been a guest in the couple's home, it has been two years since they got married, he knows them very well before etc. What is the need to specify it this much?! Please do not do it such a way for the future. But I guess are much resistant to accepting comments because that seems to you failure.

   Delete
  6. hey ….I think he knows what he did more than you.It might not be the real thing that happen in the couple,but he can create the way he want write the article by this way.so,don't disturb us.

   Delete
  7. በስመ ስላሴ አሜን።

   ውድ ወንድሜ ባለቤቶቹ እየሳቁ እኮ ነው ችግሮቹ ተፈቱ ማለት ነው። ሌሎቹን ደግሞ ተመልከት በኤችአይቪ የነበረውን ማስታወቂያ ላስታውስህ "ትውልድ ይዳን በኛ ይብቃ" ለዚህ በቂ ማስረጃ ይሆናል። ወይም አንድ አባባል ልንገርህ "የማይገልህ ችግር ሁላ ያበረታሃል ያጠነክርሃል" ይባ
   ላል ለነዚህ ሰዎችም መንፈሳይ ለተባለቸውም ልጅ መማር መስተካከል ከፈለጉ መልካም አጋጣሚ ነው። ገበና ያልነው ነገራቸው ስህተት እንደሆነ እያወቅን አንዴት ዝም ማለት ይገባል ብለህ ታስባለህ በኔ በኩል መልካም አይመስለኝም። ስለዚህ አንድ ነገርን በአንተ መልኩ ማየት ተገቢ አይመስለኝም ማሰብህ ግን ችግር አይደለም የሰብከው ነገር ትክክል ነው ብለህ ካመንክ ግን ችግር ይመስለኛል።

   ኪዳነማርያም ዘደብረ ይድራስ

   Delete
  8. It's up to a person's way of viewing things. Some see the bottle as half full and others see the bottle as half empty. Let's try to take the positives out of this amazing article. If it can save the lives of many so be it.

   Thank you a lot Diakon Daniel Kibret!!!

   Delete
 9. Tiru mikir newu. Hasabihin slakefelken, ameseginalehu

  ReplyDelete
 10. Dani, you have told me what life has two faces. Any way final story is very intersting.God bless you I learn more from this story Many thanks.

  ReplyDelete
 11. d/n Dan bravo bravo bravo.our social bondage is losing from time to time.I think if we continue like this one day we will forced to find our identity somewhere.so before that we should walk up from our sleeping to strengthen our forefathers social bondage system.

  ReplyDelete
 12. betam des yemil tshuf new .. nger hulu lebogo new ...ye fker AMLAK TSGAWN YABZALH... se zemenu yalew mekerareb ena metesaseb ...gorbit le gorebit gen ayders new kezihu yawtan...new yemibalew

  ReplyDelete
 13. betam des yemil tshuf new .. nger hulu lebogo new ...ye fker AMLAK TSGAWN YABZALH... se zemenu yalew mekerareb ena metesaseb ...gorbit le gorebit gen ayders new kezihu yawtan...new yemibalew

  ReplyDelete
 14. “መግባባት ሳይኖር መጋባት ግራ መጋባት ነው!”

  “ፍቅር እስከ መቃብር”

  “የማትወድህን ሰው ማፍቀር ማለት ኤርፖርት ሄዶ መርከብ መጠበቅ ማለት ነው!” ከዕለታት ፩ድ ቀን ፪ ፍቅረኛሞች በጣም ይዋደዱና “ፍቅር እስከ መቃብር” የሚለውን ታሪክ እውን ለማድረግ ከ፩ድ ትልቅ ገደል ጫፍ ላይ እራሳቸውን ወርውረው በአንዴ ሰጥ ረጭ ሙትት ለማለት ይስማማሉ። ከዚያ ከገደሉ ጫፍ ላይ ሆነው ማን ይዝለል? ማን ይዝለል? እየተባባሉ ሲገባበዙ ሁለቱም ዐይናቸውን ጨፍነው እስከ ሦስት ቆጥረው እኩል ለመዝለል ተስማሙ። ከዚያ ወንዱ ጮኽ አለና ፩ ፪ ፫ ብሎ ቆጠረና ዘሎ ከገደሉ እራሱን ሲወረውር ሴቷ በቆራጣ አየት አድርጋ…….“ህም እውነትም ፍቅር እውር ነው ወይ መቅበጥ!” ብላ ወደ ቤትዋ ትሄዳለች። ወንዱም ወደ ላይ አንጋጦ ሲመለከት ፍቅረኛውን ያጣታል። ለካስ ፓራሹት በጃኬቱ ደብቆ ይዞ ኖሯል ፓራሹቱን ወዲያው ከፍቶ እየተምዘገዘገ የአየር ላይ ግጥም ነጠላ ዜማውን እንዲህ ብሎ በአየር ላይ ለቀቀ  ፍቅር ፍቅር አሉት ስሙን አሳንሰው
  ከድንጋይ ይበልጣል ለተሸከመው ሰው

  ወይ ፍቅር ሰው ሁሉ ያወራል
  ግን ማንም አላየው ቆሞ ሲሄድ በአካል

  የሚለውን የራሱን ዘፈን እየኮመኮመ በሰላም ወርዶ ከገደሉ ስር ካለው ሜዳ ላይ ሄዶ ዘጭ አለ!

  እነሆ ልብ ያለው ልብ ይበል ጆሮም ያለው ይስማ! “መግባባት ሳይኖር መጋባት ግራ መጋባት ነው!” ይህ ያጋጠማችሁ ፍሬንዶቼ የፍቅር ጉደኛ ሳይሆን የፍቅር ጓደኛ ይስጣችሁ፤ አሪፍ አፍቃሪ አግኝታችሁ ፍቅር እስከ መቃብር ያድርግላችሁ ብዬ ተመኝቼያለሁ።


  “ነገር ያሻ ዳኛ አምጡይላል የዶሮ ሻኛ” እንዲሉ አንዱ ወዳጄ የዶሮ ሻኛ ካላመጣሽ በሚል ዓይነት ክርክርበአዲስ ዓመት ከሚስቱ ጋ ጦርነት ከፈተ። ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለውየተከበሩት ባልና ሚስት በተከበረች ጎጇቸው ጦርነት ከፈቱ። አዲሱን ዓመት ይህንበመሰለ የፍቅር መግለጫ ሞቅ ደመቅ ባለ አቀባበል ተቀበሉት። ባለፈው አመትምልክ እንደዚሁ በፍቅር ነበር አዲሱን ዓመት የተቀበሉት። የተከበረው ባልየተከበረችውን ሚስቱን ስለሚሳሳላት ደፍሮ በሙሉ ዓይኑ አያያትም ነበር። ስትናገርእንዳይደክማት ብሎ እንደ ባህታዊ አርምሞ ዝምታ ያበዛ ነበር። ጎጇቸው ገዳምእስኪመስል ድረስ ዝምታ በዛበት። ዳንኤል እንዳለው ፓርኪንግ ላይፍ ነበር የሚኖሩት እናላችሁ ሚስት “ብዙ ዝምታ ይሆናል በሽታ” አለችበልቧ። ሰዎችም “ፊት ነሳት’ኮ” ብለው አሙት። ሚስት “ደግነቱ የሰው ፊትአለመፋጀቱ” አለች አሁንም በልቧ። ሁለቱም ከፍቅራቸው የተነሳ ዓመቱን ሙሉሲጨቃጨቁ ሲከራከሩ ሲደባደቡ ኖረው ይኸው ለአዲሱ ዓመት ደረሱ። የዛሬውክርክር ለዓመት በዓሉ ድምቀት ሞቅ ደመቅ ብሎ ነበርና ሰውነታቸው ዝሎበያሉበት ተዘርረው አደሩ። አይነጋ የለ ነጋ። አቶ ባል በለሊት ተነስቶ ከተወደደችሚስቱ 30 ሺሕ ፓውንድ ደብቆ ከሶፋው ውስጥ አስቀመጠና ሀገር ቤት ለረፍት ሄደ። “እባብ አፈር ያልቅብኛል ብሎ ሲሰስትይኖራል” አሉ እቴጌ ጣይቱ። ከሚስት ተደብቃ የተሰሰተችው ገንዘብ ለባልም አትሆንም። ከጊዜ በኋላ ሚስት ባሌ ሲመጣይደሰት ብላ የቤቱን ቀለም ቀይራ ቤቱን ፋ! አደረገችው። የቤቱ እቃ በሙሉ ተቀየረ። አሮጌ እቃዎች ተጥለው በአዲስ ተተኩ።ያቺ አሮጌ ሶፋም ከ 30 ሺሕ ፓውንድ ጋር ገደል ገባች። የተከበረችው ሚስት እንዲህ አድርጋ ቤቷን ካሳመረች በኋላ በአዲሱሶፋ ላይ ዘና ብላ ተቀመጠችና “ይህች ናት ሚስት ማለት” አለች በልቧ!! አቶ ባል ከረፍታቸው ተመልሰው ቤታቸውንአንኳኩ። ሚስት ፈካ ብላ በፈገግታ በሩን ከፈተች። ገና በሩ እንደተከፈተ ሶፋውስ? ሶፋውስ? ብለው አቶ ባል እየደጋገሙመጠየቅ ጀመሩ። ሚስትም “የኔ ጌታ በጣም ናፍቀኸኛል ና እስኪ መጀመሪያ ልቀፍህ” አለች ሻንጣውን እየተቀበለች። አቶባልም “በቅሎ አባትህ ማነው ቢሉት እናቴ ፈረስ ነች አለ አሉ፤ የጠየቅኩሽን መልሺልኝ” ብሎ አፈጠጠባት። ሚስት ባልዋቅኔ ቤት ውሎ የመጣ መስሏት በተረቱ ሳቀችና “ያረጀው ሶፋ ተጥሎ አዲስ ሶፋ ተገዝቷል” አለች አሁንም ፈገግ እያለች። አቶባል ክው ብለው ቀሩ። 30 ሺሕ ፓውንድ ማለትም 840,000 ብር ገደል ስለገባ ሰውየው ግማሽ ፓራላይዝድ ሆኑ።  “የማይዘልቅ ማህበር በጠጅ ይጀመራል” እንዲሉባልና ሚስቱ የማህበር ኑሯቸውን “ጋብቻ” ብለው ለመኖር ተስማሙ። መቼስ ይህን የመሰለ ማህበራዊ ጋብቻ “አመሌ አወጣኝከማህበሬ” ማስባሉ አይቀርም። “የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል” እንዲሉ ባልና ሚስቱ በየቀኑ እየተማማሉምመኖር ጀመሩ። ሚስት ደጓ ቀን ከሌት ለፍታ ገንዘቧን ለባልዋ ታስረክባለች። አቶ ባል ደላቸውና ቁጭ ብለው ፓውንዳቸውንሲቆጥሩ ላያቸው የባንክ ሰራተኛ ይመስሉ ነበር። እናማ ኪስ ሲሞላ አቶ ባል ብራቸውን ይዘው ጠፉ። ሚስትም “ሰውን ማመንገደለኝ እኔን እየመሰለኝ” ብላ ታሪኳን አወጋችኝ። “ሰውን አትመኑ አብዷል ዘመኑ” ብንል ደገኛ ሰዎችን መበደልይሆንብናል። ብሩን ይዘው የጠፉት አቶ ባል ሌላ ሀገር ሄደው ተሸፋፍነው መኖር ጀመሩ። “ተሸፋፍነው ቢተኙ ገላልጦየሚያይ አምላክ አለ” የሚለውን ተረት ማን በነገራቸው! እናንተዬዋ የለንደን ታሪክ ብዙ ነው ለካ። “ያልሞተና ያልተኛ ብዙይሰማል” አሉ። እኔማ ሁሉን ዘክዝኬ ልነግራችሁ አሰብኩና “ሁሉን ቢናገሩ ሆድ ባዶ ይቀራል” አለኝ የገዛ ሆዴ። “የቀበሮባህታዊ ከበጎች መሃል ይጸልያል” የሚያስብሉ ብዙ ታሪኮች አሉ። ይሁንና እንኳን ሁሉን ተርኬ ጥንትም አንዳንድ ሰዎች ስለጋብቻ ሲያነቡ አልያም ሲሰሙ ከፍራቻ የተነሳ “ምነው ጋብቻ ቢቀርስ” ይላሉ። ወዳጄ እኛ መስማት ያለብንኮ የሚያስፈልገንንነው እንጂ መስማት የምንወደውን ብቻ አይደለም። የትኛው ወታደር ነው ሳይለማመድ ጦርነት የሚወጣው? “የጦር ነገር ከፈሪጋር አትማከር” እንዲሉ የምናማክረውም ሰው ይወስነዋል። ስለ ጋብቻ ጋብቻን ከሚፈሩ ሰዎች ጋር መማከር ውኃን መውቀጥነው። “እሳት መጣብህ ቢሉት እሳር ውስጥ ገብቻለሁ አለ” አሉ። በትዳር ውስጥ ፈተና አለ ማለት ትዳርን ረግሞ ራስንለፈተና ይበልጥ ማጋለጥ አለብን ማለትኮ አይደለም ጎበዝ! የትኛው ስፖርተኛ ነው ሳይለማመድ ስኬታማ የሆነው? የቅርብ ጊዜጀግኖቻችን ጥሩነሽም ሆነች መሰረት ለወርቅ የሚሆን ልምምድ አድርገው ነው ወርቅ ያገኙት። “ወርቅ ለማግኘት ወርቅ ይዞመነሳት” አለች ጥሩነሽ! ወዳጄ ሆይ ልምምድ ፈርቶ ወርቅ የተሸለመ ሯጭ አላየንም።

  -//-


  የዳንኤል ክብረት አድናቂ ከሆነው በልጅ ዮናስ ዘካርያስ ተፃፈ። ብልጥ አውራ ዶሮ በሰው ብቅል ሚስቱን ይጋብዛል አሉ!! ይህች አባባል ፈገግ ብታስብለኝም ዋናው ሐሳቤ ግን የሚያነበው ተጠቅሞ ለጸሐፌ ጥበብ ዳንኤል ክብረት ያለኝን ከበሬታ ለመግለጽ ነው።

  © የልጅ ዮናስ ቀልድ እና ቁም ነገር!

  http://yonas-zekarias.blogspot.com/

  ReplyDelete
 15. Wow, interesting analogy. Great piece, as usual!

  ReplyDelete
 16. Thank you Daniel, it’s great observation. The word parking sum up our relationship in U.S. Sew tetaleto yemayetarkebt ager new. May the good Lord give help us to love one another.

  ReplyDelete
 17. ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡

  ይህን የጡመራ መድረክ ሁሉም ቢያውቀው ብዙ ትምህርት ይገኝበት ነበር፡፡

  ግን ዲ/ን ዳኒ ብዙ ጊዜ በETV ቀርበሃል ይህ ዌብ ሳይት (ብሎግ) እንዳለህ ብትገልፅ ችግር ይኖረው ይሆን? እንደ ውዳሴ ከንቱስ ይቆጠር ይሆን? ግን የሚገለፅበት መንገድ ቢኖር፡፡

  ReplyDelete
 18. What a precious idea? we love you dani

  ReplyDelete
 19. dani betam teru yehone astemari hasab new,beteley be ahun giza be hagerachin balew yenuro lewt yeneberun melkam mahberawi nuro eyetekeyere new,silezih endezih aynet astemari yehone melekt le ETHIOPIA yasfelgatal,thank you GOD BLESS U

  ReplyDelete
 20. Des yemil eyta ketetekeminbet!!

  ReplyDelete
 21. The funniest story and the most fabulous fable I have ever read.ቃለ-ህይወት ያሰማልን::

  ReplyDelete
 22. Tiru eyeta new Dani,yehe yene hiwot new. Endet kezih hiwot mewetat edemichal gin alawekem. Ene ende lole fekadewan kalefetsemeku libe esekitefa tasadedegnalech, yemelewen semetagn atawekem. Ere silatem tematalech.' Kante mene yikerebegnal' ye afewa mefecha new. Betechalat meten bene lay yalaten yebelayenet hulum endiyawek tefelegalech. Andande 'si'ol malet yih yihon' elalehu. Lemeleyayet befelegem lijochen tito mehed kebedegn. Ena ahun yemenenorew ersua bechegna enat bemil seme new. Ezih ager bechegna enat yehonech set bezu tekem tagegnalech, tax yikeneselatal, techemari genezeb yisetatal, endiyam sil degemo ye lijochu abat yemisera kehone tekorach lelijochu endikefel yigededal.Kalseram ende eda tekorachu ende eda yikemach ena sisera endikefel yigededal. Yih degemo setochu aberewe menorun endayemertu ena fetenan endayitagesu yaderegachewal. Be gilachew mewesen kefelegu mekebel alebeh yaleza 'hide weta kante gar mane yinetarekal' afe mefechachew new. Bezihem mekeniyat wey ke lijoche ,wey ke menefesawi hiwote, wey ke segawi hiwote salehon kenaten egefalehu. Eski ande belegn Dani. Ande wedaje ende ene temesasay chiger yalebet mirer yilew ena 'beka ehedeleshalehu yilatal' min beelew tiru new 'hide kunecha mane yilemametehal.' Ezih yemenorebet bota bizu wendoch temesasay chiger alebachew.Egziabeherebn endih beye lemenekut 'kezih hiwot awetagn ebakhen.'

  ReplyDelete
 23. “መግባባት ሳይኖር መጋባት ግራ መጋባት ነው!”


  “የማትወድህን ሰው ማፍቀር ማለት ኤርፖርት ሄዶ መርከብ መጠበቅ ማለት ነው!” ከዕለታት ፩ድ ቀን ፪ ፍቅረኛሞች በጣም ይዋደዱና “ፍቅር እስከ መቃብር” የሚለውን ታሪክ እውን ለማድረግ ከ፩ድ ትልቅ ገደል ጫፍ ላይ እራሳቸውን ወርውረው በአንዴ ሰጥ ረጭ ሙትት ለማለት ይስማማሉ። ከዚያ ከገደሉ ጫፍ ላይ ሆነው ማን ይዝለል? ማን ይዝለል? እየተባባሉ ሲገባበዙ ሁለቱም ዐይናቸውን ጨፍነው እስከ ሦስት ቆጥረው እኩል ለመዝለል ተስማሙ። ከዚያ ወንዱ ጮኽ አለና ፩ ፪ ፫ ብሎ ቆጠረና ዘሎ ከገደሉ እራሱን ሲወረውር ሴቷ በቆራጣ አየት አድርጋ…….“ህም እውነትም ፍቅር እውር ነው ወይ መቅበጥ!” ብላ ወደ ቤትዋ ትሄዳለች። ወንዱም ወደ ላይ አንጋጦ ሲመለከት ፍቅረኛውን ያጣታል። ለካስ ፓራሹት በጃኬቱ ደብቆ ይዞ ኖሯል ፓራሹቱን ወዲያው ከፍቶ እየተምዘገዘገ የአየር ላይ ግጥም ነጠላ ዜማውን እንዲህ ብሎ በአየር ላይ ለቀቀ  ፍቅር ፍቅር አሉት ስሙን አሳንሰው
  ከድንጋይ ይበልጣል ለተሸከመው ሰው

  ወይ ፍቅር ሰው ሁሉ ያወራል
  ግን ማንም አላየው ቆሞ ሲሄድ በአካል

  የሚለውን የራሱን ዘፈን እየኮመኮመ በሰላም ወርዶ ከገደሉ ስር ካለው ሜዳ ላይ ሄዶ ዘጭ አለ!

  እነሆ ልብ ያለው ልብ ይበል ጆሮም ያለው ይስማ! “መግባባት ሳይኖር መጋባት ግራ መጋባት ነው!” ይህ ያጋጠማችሁ ፍሬንዶቼ የፍቅር ጉደኛ ሳይሆን የፍቅር ጓደኛ ይስጣችሁ፤ አሪፍ አፍቃሪ አግኝታችሁ ፍቅር እስከ መቃብር ያድርግላችሁ ብዬ ተመኝቼያለሁ።


  “ነገር ያሻ ዳኛ አምጡይላል የዶሮ ሻኛ” እንዲሉ አንዱ ወዳጄ የዶሮ ሻኛ ካላመጣሽ በሚል ዓይነት ክርክርበአዲስ ዓመት ከሚስቱ ጋ ጦርነት ከፈተ። ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለውየተከበሩት ባልና ሚስት በተከበረች ጎጇቸው ጦርነት ከፈቱ። አዲሱን ዓመት ይህንበመሰለ የፍቅር መግለጫ ሞቅ ደመቅ ባለ አቀባበል ተቀበሉት። ባለፈው አመትምልክ እንደዚሁ በፍቅር ነበር አዲሱን ዓመት የተቀበሉት። የተከበረው ባልየተከበረችውን ሚስቱን ስለሚሳሳላት ደፍሮ በሙሉ ዓይኑ አያያትም ነበር። ስትናገርእንዳይደክማት ብሎ እንደ ባህታዊ አርምሞ ዝምታ ያበዛ ነበር። ጎጇቸው ገዳምእስኪመስል ድረስ ዝምታ በዛበት። ዳንኤል እንዳለው ፓርኪንግ ላይፍ ነበር የሚኖሩት እናላችሁ ሚስት “ብዙ ዝምታ ይሆናል በሽታ” አለችበልቧ። ሰዎችም “ፊት ነሳት’ኮ” ብለው አሙት። ሚስት “ደግነቱ የሰው ፊትአለመፋጀቱ” አለች አሁንም በልቧ። ሁለቱም ከፍቅራቸው የተነሳ ዓመቱን ሙሉሲጨቃጨቁ ሲከራከሩ ሲደባደቡ ኖረው ይኸው ለአዲሱ ዓመት ደረሱ። የዛሬውክርክር ለዓመት በዓሉ ድምቀት ሞቅ ደመቅ ብሎ ነበርና ሰውነታቸው ዝሎበያሉበት ተዘርረው አደሩ። አይነጋ የለ ነጋ። አቶ ባል በለሊት ተነስቶ ከተወደደችሚስቱ 30 ሺሕ ፓውንድ ደብቆ ከሶፋው ውስጥ አስቀመጠና ሀገር ቤት ለረፍት ሄደ። “እባብ አፈር ያልቅብኛል ብሎ ሲሰስትይኖራል” አሉ እቴጌ ጣይቱ። ከሚስት ተደብቃ የተሰሰተችው ገንዘብ ለባልም አትሆንም። ከጊዜ በኋላ ሚስት ባሌ ሲመጣይደሰት ብላ የቤቱን ቀለም ቀይራ ቤቱን ፋ! አደረገችው። የቤቱ እቃ በሙሉ ተቀየረ። አሮጌ እቃዎች ተጥለው በአዲስ ተተኩ።ያቺ አሮጌ ሶፋም ከ 30 ሺሕ ፓውንድ ጋር ገደል ገባች። የተከበረችው ሚስት እንዲህ አድርጋ ቤቷን ካሳመረች በኋላ በአዲሱሶፋ ላይ ዘና ብላ ተቀመጠችና “ይህች ናት ሚስት ማለት” አለች በልቧ!! አቶ ባል ከረፍታቸው ተመልሰው ቤታቸውንአንኳኩ። ሚስት ፈካ ብላ በፈገግታ በሩን ከፈተች። ገና በሩ እንደተከፈተ ሶፋውስ? ሶፋውስ? ብለው አቶ ባል እየደጋገሙመጠየቅ ጀመሩ። ሚስትም “የኔ ጌታ በጣም ናፍቀኸኛል ና እስኪ መጀመሪያ ልቀፍህ” አለች ሻንጣውን እየተቀበለች። አቶባልም “በቅሎ አባትህ ማነው ቢሉት እናቴ ፈረስ ነች አለ አሉ፤ የጠየቅኩሽን መልሺልኝ” ብሎ አፈጠጠባት። ሚስት ባልዋቅኔ ቤት ውሎ የመጣ መስሏት በተረቱ ሳቀችና “ያረጀው ሶፋ ተጥሎ አዲስ ሶፋ ተገዝቷል” አለች አሁንም ፈገግ እያለች። አቶባል ክው ብለው ቀሩ። 30 ሺሕ ፓውንድ ማለትም 840,000 ብር ገደል ስለገባ ሰውየው ግማሽ ፓራላይዝድ ሆኑ።  “የማይዘልቅ ማህበር በጠጅ ይጀመራል” እንዲሉባልና ሚስቱ የማህበር ኑሯቸውን “ጋብቻ” ብለው ለመኖር ተስማሙ። መቼስ ይህን የመሰለ ማህበራዊ ጋብቻ “አመሌ አወጣኝከማህበሬ” ማስባሉ አይቀርም። “የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል” እንዲሉ ባልና ሚስቱ በየቀኑ እየተማማሉምመኖር ጀመሩ። ሚስት ደጓ ቀን ከሌት ለፍታ ገንዘቧን ለባልዋ ታስረክባለች። አቶ ባል ደላቸውና ቁጭ ብለው ፓውንዳቸውንሲቆጥሩ ላያቸው የባንክ ሰራተኛ ይመስሉ ነበር። እናማ ኪስ ሲሞላ አቶ ባል ብራቸውን ይዘው ጠፉ። ሚስትም “ሰውን ማመንገደለኝ እኔን እየመሰለኝ” ብላ ታሪኳን አወጋችኝ። “ሰውን አትመኑ አብዷል ዘመኑ” ብንል ደገኛ ሰዎችን መበደልይሆንብናል። ብሩን ይዘው የጠፉት አቶ ባል ሌላ ሀገር ሄደው ተሸፋፍነው መኖር ጀመሩ። “ተሸፋፍነው ቢተኙ ገላልጦየሚያይ አምላክ አለ” የሚለውን ተረት ማን በነገራቸው! እናንተዬዋ የለንደን ታሪክ ብዙ ነው ለካ። “ያልሞተና ያልተኛ ብዙይሰማል” አሉ። እኔማ ሁሉን ዘክዝኬ ልነግራችሁ አሰብኩና “ሁሉን ቢናገሩ ሆድ ባዶ ይቀራል” አለኝ የገዛ ሆዴ። “የቀበሮባህታዊ ከበጎች መሃል ይጸልያል” የሚያስብሉ ብዙ ታሪኮች አሉ። ይሁንና እንኳን ሁሉን ተርኬ ጥንትም አንዳንድ ሰዎች ስለጋብቻ ሲያነቡ አልያም ሲሰሙ ከፍራቻ የተነሳ “ምነው ጋብቻ ቢቀርስ” ይላሉ። ወዳጄ እኛ መስማት ያለብንኮ የሚያስፈልገንንነው እንጂ መስማት የምንወደውን ብቻ አይደለም። የትኛው ወታደር ነው ሳይለማመድ ጦርነት የሚወጣው? “የጦር ነገር ከፈሪጋር አትማከር” እንዲሉ የምናማክረውም ሰው ይወስነዋል። ስለ ጋብቻ ጋብቻን ከሚፈሩ ሰዎች ጋር መማከር ውኃን መውቀጥነው። “እሳት መጣብህ ቢሉት እሳር ውስጥ ገብቻለሁ አለ” አሉ። በትዳር ውስጥ ፈተና አለ ማለት ትዳርን ረግሞ ራስንለፈተና ይበልጥ ማጋለጥ አለብን ማለትኮ አይደለም ጎበዝ! የትኛው ስፖርተኛ ነው ሳይለማመድ ስኬታማ የሆነው? የቅርብ ጊዜጀግኖቻችን ጥሩነሽም ሆነች መሰረት ለወርቅ የሚሆን ልምምድ አድርገው ነው ወርቅ ያገኙት። “ወርቅ ለማግኘት ወርቅ ይዞመነሳት” አለች ጥሩነሽ! ወዳጄ ሆይ ልምምድ ፈርቶ ወርቅ የተሸለመ ሯጭ አላየንም።

  -//-


  የዳንኤል ክብረት አድናቂ ከሆነው በልጅ ዮናስ ዘካርያስ ተፃፈ። ብልጥ አውራ ዶሮ በሰው ብቅል ሚስቱን ይጋብዛል አሉ!! ይህች አባባል ፈገግ ብታስብለኝም ዋናው ሐሳቤ ግን የሚያነበው ተጠቅሞ ለጸሐፌ ጥበብ ዳንኤል ክብረት ያለኝን ከበሬታ ለመግለጽ ነው።

  © የልጅ ዮናስ ቀልድ እና ቁም ነገር!

  http://yonas-zekarias.blogspot.com/

  ReplyDelete
 24. dn. Daniel tebarek!!! berta.

  ReplyDelete
 25. Good view, thanks.

  ReplyDelete
 26. betam betam astemari tsihuf new. Berta Dani and may God give you His blessings all the time.

  ReplyDelete
 27. አበበ ሙ በየነNovember 5, 2012 at 3:20 PM

  ወንድሜ ዳንኤል ለመልካም አተያይህ እግዜር ይስጥህ::

  መቸም ኑሮ እና ትዳር የየራሳቸው የሆነ መስተጋብር አላቸዉ:: ከዚህ ቀደም የሚያሸነፍ ፍቅር በሚል ርዕስ አጣልቶ የሚያፋቅር አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ በሚል ፅሁፍ በአስኮመኮምከን ዕይታ " አንድ ወንበር ላይ መቀመጥና አብሮ መቀመጥ፤ አንድ አልጋ ላይ መተኛትና አብሮ መተኛት፤ አንድ ቤት ውስጥ መኖርና አብሮ መኖር በእጅጉ እንደሚለያዩ" በረጋ አስተዉሎትህ አሳይተህናል፡፡

  ከዚሁ ዕሳቤ በመነሳት ጉልቻ እና ጉልቻም እግር እና እግርም እንደሚጋጩ ሁሉ: አብረዉ የሚኖሩ ሰዎች ወይም ባለትዳሮች የሆኑ ሁሉ በሃሳብ ሊለያዩ ወይም ሊጋጩ ይችላሉ::

  እዚህ ላይ የሚደርሱ ልዩነቶችን ወይንም ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችለው ዋናዉ ቁም ነገር ዉይይት እና መደማመጥ የቤት ዉስጥ ሕግ አድርጎ የመዉሰድን አስፈላጊነት ነው::

  በሁለቱም ወገን የእኔ ሃሳብ ብቻ ትክክል ነው ብሎ የሙጥኝ ከማለት: ከአንተም ሆነ ከእኔም ሃሳብ ይሄኛዉ እና ያኛው ጠንካራ ጎን ስላላቸዉ ይሄኛዉን ከዚያኛው በማጣመር መፍትሄ መሻትን እና ማምጣትን መለማመድ ያስፈልገናል::

  በአንድ ወቅት መሐመድ ሃይከል የተባለ የግብፅ ጋዜጠኛ ስለ ዓረብ ሊግ ሲዘግብ እባካችሁ የአገሬ ሰዎች ቢያንስ ቢያንስ ላለመስማማት ተስማሙ እንዳለው ሁሉ በልዩነት መቻቻልን አስፍኖ አብሮነትን ለማጠንከር መሰረት መሆኑን መገንዘብ ያሻል::

  ቸር እንሰንብት

  ReplyDelete
 28. yanten tsihuf saneb libe ereftyisemawal. minew sew yanten tikitun enkuan kena astesaseb binorew

  ReplyDelete
 29. Lij Daniel, endet neh?
  Andeko tiz yilih indehon. you have promised us to write how to live in Ethiopia in "American style". Did I miss it?

  ReplyDelete
 30. Great View!!!! May God Bless you Dn.Daniel!

  So, what can we do as an individual, as a family, as a neighbourhood, as a community, and as a nation?????? We need to act today. It is burning issue; the meaning for life is, I think, hidden in this very important but very close to be lost, Social Interaction.

  ReplyDelete
 31. ዳንኤል የሚያውቀው ሰው እልፍ ነው፡፡ በስም እከሌ ብሎ እስካልጠቀሰ ድረስ ከባለጉዳዩቹ ውጭ ማንም ይህን ሚስጥር ሊያውቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ ሰው ትምህርት የሚያገኘው እንዲሁ ከማህበራዊ ኑሮ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመነሳት ስለሆነ ምንም ቅር የሚያሰኝ ነገር የለውም፡፡ የነዛ ወዳጆቹ ችግር የሚሊዮኖች ችግር ነውና፡፡ ዳኒ ላመሰግንህ ወደድኩ፡፡

  ReplyDelete
 32. የምን ፡ ፓርኪንግ፡ነዉ፧

  ለምን ፡መኪና፡ማቆሚያ፡ብለኽ፡አትሰይመዉም፧

  ያሳዝናል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. just not to say something.... sorry?

   Delete
 33. እንደሳቁ ዕቃችንን ገዝተን እንደሳቁ ቤታቸው ገባን፡፡ ይኼው ዛሬም እየሳቁ ይደውሉልኛል፡፡
  ያስተምራል፣ እኔም አልፎ አልፎ የፓርኪንግ ላይፍ ይመቸኛል፡፡
  very smart way of healing conflict
  long live to our brother
  you are making history

  ReplyDelete
 34. DAni tew ye sew kusil atnekaka

  ReplyDelete
 35. አባዬ እና እማዬም ከተጣሉ አራት ወር ሆኗቸዋል፡፡ እኔና እህቴም ተኳርፈናል፡፡ እኔ ከእናቴ ጋር እህቴ ደግሞ ከአባቷ ጋር አግዛ ሁለት ሁለት ቡድን ሆነን ተኮራርፈናል፡፡ ዳኒ እስቲ አንድ ቀን እኛ ቤት ልጋብዝህ፡፡ የት ነው የማገኝህ;

  ReplyDelete
 36. ዳኒ በታም ደስ የሚል ምክር ነው እኛም ፓረኪንግ እንዳንሆን ለመጠንቀቅ ይረዳናል አመሰግናለሁ፡፡

  ReplyDelete
 37. Dn.Danile Erjemena edmi ktena Ysetehe.Dani ye Parking Hiwot alkewe tekekelenehe.Sanebew betam newe yegermeye.Sebele Wongile kemetedachew biteseb tenetela.Addis ABaba yageyechewen hulu sewe selam tele neber.hulum sewe zeme bemaletu betam gera gebetute nebere......b/c hulum sewe yageyewene sewe biwekeweme bayiwekewem ye Egizibire selamta aynefegem.Danil amrica kemetahu tenshe gize bihuneyem.leke ende sebele bahire newe yaleye .mahebrawi hiwote betam ewedalhu.Ezihe meteche atahute.Hiwot temesasay hune beye betam derekebye hiwot yelewem.Ethiopia maheberawie hiwote yetem yele.Ethiopai betam kelebehe tesekalehe,Tazenalehme teradadalhe. Ezihe kelebu yemiseke alayehum.....yemichek enj.....

  ReplyDelete
 38. wow dani boy, you are great!!your thoughts are smart.God bless you


  ReplyDelete
 39. ዳኒ ጽሑፍ ትክክል ነው አስቲ ደግሞ ልጆች ከፍ ሲሉ ተምረው እራሳቸውን ሲችሉ ለቤሰተቦቻቸው ያላቸው ግምትና እንደውም እነሱ የሚያውቁትን ወላጆቻቸው እንደማያውቁ የሚቆጥሩትን የዘመኑ ዘመኛ ልጆች እንዴት ትገልጻቸዋለህ ?

  ReplyDelete
 40. Daniel! Yanet eyetawochen banebebeku kuter men yakel yanet eyetawoch eyekeretsugne endehon yesemagnal amesegenehalew e/r yebarekeh!!

  ReplyDelete
 41. ርቀት መመልከት የረቀቀዉን ያስገነዝባል…የራቀዉን ያቀርባል!!

  ReplyDelete