Monday, November 26, 2012

የሁለት ሐውልቶች ዕጣ 3

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ እንዲያስችል በሚዘረጋው የቀላል ባቡር መሥመር ዝርጋታ ምክንያት የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት እንደሚነሳ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ 

አቶ አበበ ምህረቱ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኮምኒኬሽን አገልግሎት ክፍል ኀላፊ የሐውልቱ መነሳት ያሰፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ምን እንደሆነ ሲገልጹ “በቀላል ባቡር መስመር ዝርጋታ ምክንያት መንገዱ ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ አደባባይ ጀምሮ ወደ አውቶቡስ ተራ የሚወስደው መንገድ አትክልት ተራ ድረስ ባቡሩ በዋሻ ውስጥ ነው የሚያልፈው፡፡ በተጨማሪም የባቡሩ መስመር ከምኒልክ አደባባይ ወደ ሽሮ ሜዳ ይዘረጋል፡፡ እንደሁም ከአውቶቡስ ተራ ወደ ቅድስት ልደታ ለማርያም የሚታጠፈው መስመር መነሻም ነው፡፡ 

ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ከማዘጋጃ ቤት አጥር ጀምሮ ወደ ትግበራ የተገባበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን፡፡ ሥራው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሲደርስ ስዊድን አገር የሚገኘውና ከፍተኛ ልምድ ያለው ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ሥራውን በበላይነት የሚቆጣጠረው ሲሆን በሚያስመጣቸው ባለሙያዎች አማካይነት በክብርና በጥንቃቄ ሐውልቱን አንሰቶ የዋሻው ግንባታ እንደተጠናቀቀ አንዲትም ሣ/ሜትር ሳይዛነፍ እንደነበረ በቦታው ላይ በክብር እንዲያስቀምጥ ይደረጋል፡፡ ሐውልቱ የሀገር ቅርስና ሀብት ነው፤ ለዚህም ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራ ይሰራል፡፡” ብለዋል፡፡

21 comments:

 1. ሐውልቱ የሀገር ቅርስና ሀብት ነው፤ ለዚህም ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራ ይሰራል፡፡” ብለዋል፡፡ ተመስገን እሄን ማወቃቸዉ በራሱ ታላቅ ነገር ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 2. Hirut:

  Dani,በክብርና በጥንቃቄ ሐውልቱን አንሰቶ የዋሻው ግንባታ እንደተጠናቀቀ አንዲትም ሣ/ሜትር ሳይዛነፍ እንደነበረ በቦታው ላይ በክብር እንዲያስቀምጥ ይደረጋል፡፡ ሐውልቱ የሀገር ቅርስና ሀብት ነው፤ ለዚህም ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራ ይሰራል yalut ewnet kehone betam tiru new, egnam gudayun betikuret meketatel endalebin yisemagnal. Thanks.

  ReplyDelete
 3. ወንድም ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ጤና እና ሰላም ሰጥቶ የአግልግሎት ዘመንክን ያርዝምልን,ይባርክልን። መልካም ዜና ነው። ታዲያ መቼም ልማትን ማንስ ይጠላል። መንግስታችን ይህን ቃል ቢያፈርስ ታሪክ እና ሕዝብ ይፋረደዋል። እኛም ከተናፋሽና ምንጫቸው ከማይታወቅ ወሬዎች ሰለባ እንጠንቀቅ። የርካሽ ፖለቲካ መጠቀሚያም አንሁን። ከፖለቲካ ይልቅ የሀገር ፍቅር ይቅደም።

  ReplyDelete
 4. lemhonu mahiberesebu/yagere shimagilewoch yehayimanot abatoch.........../ bekedmiya teweyaytwebetal? if not why? this nation is not only theirs ,it is all of us too. pls leaders of EPRDF think about the community owenership.u r not out of this society dont be a full ur names will b ............bemanalebegnenet atenkesakesu

  ReplyDelete
 5. ዲን ዳንኤል፤
  የተፈጠረውን ውዥንብር ለመፍታት በግልህ ለምታደርገው ጥረት ዋጋውን አምላክ ይክፈለወህ። ሁላችንም የበኩላችን ብናደርግ ምንኛ ባማረ። ወደ ጉዳዩ ስመለስ፣ ለስለስ እያሉ ለወጡት መረዎች ይበል ያሰኛል! ለአንዳንድ አራጋቢዎች በር ስለሚዘጋ። እኔ በበኩሌ አሁንም ያልተመለሰ ጥያቄ አለኝ። የሚሰራው የባቡር መስመር አሁን ከደረስንበት ቴክኖሎጂ አንጻር ሐውልቱ ሳይነካ መዘርጋት ይቻላል። እንደሚታወቀው-ቦታዉ ጠባብ ስለሆነ የአንድ መስመር ብቻ መሆን ይኖርበታል። ይህ ከሆነ ደግሞ ሃውልቱ እንዳለ ሳይነካ ቁልቁል የሚፈለገውን ዋሻ መክፈት ይቻላል! ምን አልባት ስራ ሲሰራ አቧራውና ሌሎች ተዛማጅ ነገሮች እነዳያበላሹት ባለበት መሸፈን ይቻላል!!
  የደረስንበትን ዘመን መዋጀት ያስፈልገናል። አንዱን ነገር ሳናፈርስ መስራትን እንማር። ታላላቅ ውቂያኖሶችን ሳይገድቡ ከስር አለምን ጉድ የሚያሰኝ የዋሻ ባቡር መስመር የሚዘረጉ የሰው ልጆች እንዳሉ አንዘንጋ። በጣም ስፋት ያለውን ውሃ ሳይገድቡ ረጅም የሆነ ትልቅ ድልድይ በመስራት፤ ስራ የሚከናወንበት ዘምን ላይ መሆናችንን መርሳት የለብንም። ለአገራችን ነጻነት ሲሉ መስዋዕት የከፈሉ አባታችንን ከቦታው እንዳለ ለማሰብ ሐውልታቸው የቆመበትን ኩርማን መሬት ሳይነካ፤ ሐዲዱን መዘርጋት ይቻላል። ቅንነት ካለ አሁንም ይቻላል! ይሄ የሐይማኖት ወይም የፓለቲካ ጉዳይ አይደለም! የአገር ጉዳይ ነው። የትናንት ማንነታችንን የሚያሳይ ታላቅ አሻራ ነው። አሻራን ሳናጠፋ መስራት እንችላለን። ለእኔ፤ ምድር ባቡር ያሉ ባለሞያዎች የሚፈተኑበት ጊዜ አሁን ይመስለኛል። ሐውልቱ ሲነሳ ምንም እንዳይሆን ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የውጭ አገር ዜጎች በጥንቃቄ እንዲነሳ የሚያደርጉ አግኝተናል እንደተባለው፤ ሐውልቱ ሳይነሳ በጥንቃቄ ስራው እንዲከናወን ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የውጭ ሐገር ዜጎችን (በሃገራችን ከሌለን) ለማፈላለግ የምድር ባቡር ወይም የሚመለከተው መስሪያቡት ሃላፊነት መውሰድ አለበት።
  አሁንም-ከማንሳት በፊት፤ ሳይነሳ ስራውን ለማከናወን ቆርጠን ብንነሳ ጥሩ ነው። ካለበለዚያ፤ “ሲነግሩት ያልሰማ፤ ሲቀልቡት ይከሳል“ የሚባለው እንዳይደርስ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ohhhhh, I love u Abel with all ur comments.

   Delete
 6. EWinet kehone Egziabiher yimesigen!!! kesemahu jemiro betam terebishena min enadirig eyaliku sasib neber. I hope they will do what they said

  ReplyDelete
 7. It shows me some tiny road, that there is a root for the public interest to be heard. Thanks Dani and the Government officials...

  ReplyDelete
 8. D/n I thank for your inquiry so that the Gov. Officials replied even if I have a reservation that they will keep their words. As Abel commented, there is all possibility if they really need "Kanjet Kaleqesu ... Endilu". So, we'll have to have two personality, one that pray to the Almighty the other who boldly criticize and fight all the wrong doings in the country. No compromise with our historical heritage, our identity, etc until death.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Perhaps only those commenting here are so concerned with this issue and majority of Ethiopians are not and cant be as concerned. Majority believes that development is a priority and history and culture can be preserved while in the process. There is nothing saint. All you are talking is not based on facts. Why would you think that only you are concerned and any one else, especially government isn't? Why would you talk this long based on rumors and rumors only? How can you expect that government (no matter which) would purposely destroy such things? Do you think this issue is (let's face it) really top priority today? Isn't development in dire need in the country? What makes you think that the government is doing this project to indirectly destroy these monuments? I know most would now open your mouths wide following my comments and name call. But fact is fact! Pls accept the issue of the monuments can easily be handled and that development runs top priority than such trash talks off the seen!!

   Delete
 9. ቢዘገይም ምላሽ ነው:: ከቀርነቱ ጋር ተቀብለነዋል:: ከሰማእቱ ሐውልት ጋር በተያያዘም መነሳት ያለበት ተጨማሪ ጥያቄ አለ:: መንግሥት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንና በጎ አድራጊዎች የተባበሩበት የሰማእቱ ሐውልት መነሳቱና መልሶ መተከሉ ግድ ከሆነ ሁለት ወዶ አይሆንምና እንቀበለው:: ይሁን እንጂ ከዲያቆኑ ጥያቄዎች ጋር አብሮ የመልሶ ግንባታው ወጪ በማን እንደሚሸፈን እና ግምታዊም ቢሆን የጊዜ ገደቡ መገለጽ አለበት የሚል እምነት አለኝ:: ይህን የምለው በሕግ አግባብ ሊደረጉ የሚገባቸው ሌሎች ሁነቶችም እንዲታዩ በማሳሰብ ነው:: አብሮም ለአገር እድገት ባለው አስተዋጽኦ ምክንያት ሥራውም አድናቆች የሚቸረው እንደሆነ አምናለሁ::

  ለሰማእቱ ሐውልት በዋናነት ጥብቅና የሚቆሙለት ተቋማትም ድምጻቸውን ማሰማት አለባቸው:: ለምሳሌ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ላይ የሚሰሩ ማኅበራት፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ቢሮዎች፣ የታሪክና ቅርስ ተመራማሪዎች/ምሁራን/ ፣ ሚዲያዎች. . . የየድርሻቸውን በጋራና በተናጠል ሊወጡ ይገባል:: ይህ ማለት አመጽ መቀስቀስ አይደለም በሰለጠነ መንገድ ሀሳባቸውን ማቅረብ ይችላሉ ነው::

  አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ይህን ጉዳይ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ የወረወሩት ሀሳብን ወድጄዋለሁ:: በበኩሌ የመንግሥቱ ኃ/ማርያም ሐውልት እንኳን ተሰርቶ ቢሆን እንዲፈርስ ፈቃደኛ አይደለሁም:: ትላንትን በፊልምና በመጻሕፍት መግለጽ ባንችል ሐውልቶች አደባባይ ላይ ቆመው በሚገባ ታሪካችንን የሚናገሩ እንደሆኑ አምናለሁና ብለዋል:: በሆኑም ለአስተያየቶቻችን ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ይመስለኛል:: አንዳንዶቻችን ደርግ የሳለብን ጭራቁ ወያኔ ከሃያ ዓመት በኋላም ገና ጭራው አልተቆረጠልንም:: መንግሥት ስዩመ አምላክ ነኝ አላለም:: አንባገነንም አደለሁም እያለ ነው:: ከመካከላችሁ የወጣሁ ነኝ በመሆኑም ሥራዬ ፍጹም ሊሆን አይችልም ብሎ ግን ያምናል:: ገንቢ የሀሳብ እገዛ ለማድረግ ስንሠራ ለአገራዊ ጥቅም ቅድሚያ ሰጥተናል ማለት ነው:: ከሀሳብ ልእልና ጋር ወደፊት . . .

  ReplyDelete
 10. First of all I would like to thanks D/n Daniel kibret and those who have display their comments and shows their worries about the two symbolic historical heritage.

  You guys am not optimistic with ur ideas,cause am not confident with EPRDF, you know why!? as far as I know, EPRDF can't keep his words for 21 years.So even if the gov't articulates the above I don't think so the gov't can keep their promises.Let me tell you one thing,I hope everybody konws this, there were "pushkin hawlt" around "sarbet" before they made the ring road around.However the gov't was promised to us to returen and plugged up on the former place but they didn't it still even if after they finished the ring road.So guys pls don't be fool ok?.The gov't not to worry about Ethiopian heritage cause if the gov't worried about Ethiopian heritage they were tell us about such things before they started but not.In addition to this,the concerned bodies from the gov't not willing to tell us about it still now.So what you feel you guys? finally I have one question for D/n Daniel kibret;pls tell me your opinions what we do if.....? If I mistaken sorry!!! thanks all.Bless u and God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 11. ባለጊዜዎቹን ባንዶች ለማመስገን ግድብ መገደብ አለመገደባቸው ሳይኾን፤ "ማሰባቸው በቻ" በቂኽ ነበር። ስንት ሺ አማራጭ እያለ ያሰማዕት ሐውልት ለማፍረስ ማሰብ ብቻ ሳይኾን ተግባራዊ ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ግን እነርሱን ለመንቀፍ እና ለመገሠጥ አላነሣሣኽም። ደግሞ ጕዳዩን አስቀድመኽ የማታውቀው ለማስመሰል እየቆነጠብኽ ማቅረብኽ! ብልጥ ባለጊዜ ሰባኪ። አዬ ዳኒ፦ እንዲያ እንደሸንበቆ ወጥትኽ እንዲህ እንደሙገጫ ትንከባለል?

  ReplyDelete
  Replies
  1. yetenkebalele sew milikitu besew mefredu new. atifred

   Delete
  2. እገሌ ሆይ፦ እንዲህ ያሉ አፍ መለጎሚያ ቃላት ለእኔ አይደሉም። ያዩትና የሰሙትን መናገር ምስክርነት እንጂ ፍርድ አይደለም። ደግሞ ፍርድ በተጠቃለለው ዕድሜ ስለሚሰጥ "ረ እውነትም እየተንከባለልኹ ነው'ንዴ?" ብሎ አፈፍ ብሎ ቢነሣ፤ "ስብዐ ይወድቅ ጻድቅ ወይትነሣእ [ስብዐ]" ለተባለው ክብር ሊበቃ ይችላልና፤ ስለዚህ ነው ትችቱ። አንተ/ቺ ግን በውዳሴ ላይ ውዳሴ እየከመርኽ/ሽ ራሱን እንዳያይ ርዳ/ጂው፤ ይህ ርዳታ ከኾነ።

   Delete
  3. 'Geez Online' yetekeberewin ye haymanotachin lisan arma adirgo yetilacha poletica maramed berasu as'tseyafi new.

   Delete
 12. የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ከቦታው መንቀሣቀሥ

  በጣም የሚያሳዝን ነዉ፡፡ ለመሆኑ ሀውልቱ

  የግል ንብረት ነዉ እንዴ የሕዝብ ሀብት

  እኮ ነው፤ በሠለጠኑት ሀገሮች ሀምሣ ዓመት

  የሞላው ቤት እንደ ቅርስ ይጠበቃል፤

  ታዲያ ምነው ማስተር ፕላኑ ሆነ ተብሎ

  ቅርሶቻችን ባሉበት መሰራቱ ነው ወይስ የሸኩን

  አጥር ላለመንካት )

  ReplyDelete
 13. ‘አውቆ የተኛ እዲሉ’ ፀረ ልማት ሀይሎች በአቶ ዳንኤል አዝማችነት አዲስ የማወናደጃ ስልት ያገኙ ስለመሰላቸው ሙሾ ማውረዳቸው አይደንቅም ቀለበት መንገድ ሲሰራ ይቅርብን ተባለ አሁን መንገዱ ሲጣበብ ትራፊኩ ሲጨናነቅ መንገዱ የታለ ይላሉ:: ኮንደሚንየም ሲባል በአፍንጫችን ይውጣ እንዳላሉ ተመልሰው የቤት ያለህ እያሉ ያላዝናሉ:: አሁን ደግሞ በሐውልት አሳክከው አካኪ ዘራፍ ማለት ጀመረዋል ግን ‘ውሾቹ ይጮሀሉ ግመሉ መንገዱ ይቀጥላል’ ክቡር አቶ መለስ እንዳሉት “ዋናው ጠላታችን ድህነት ነው” የድህነት ተራራ ለመናድ በሚደረገው ትግል እንቅፋት የሚሆን ጨለምተኛ አስተሳሰብ ደግሞ አብሮ ይናዳል መንግስት የሚሰራው ያውቃል እስከ አሁን ድረስም ሲገነባ እንጂ ሲያፈርስ አልታየም ነገም ከነገ ወዲም እዲሁ ለቀቢፀ ተስፋ ጨለምተኞች የሚሆን ጆሮ ግን የለውም:: ምክንያቱም ለእነሱ ከወያነ ልማት የሚኒሊክ እና ኃይለስላሴ ድህነት ከወያነ ሰላምና ዲሞክራሲ የመነጌ ቀይ ሽብር እና ጦርነት ነው ምርጫቸው:: ውሾቹ ኢህአዴግን ባለፉት 21 ዓመታት አንዴ በኤርትራ ሌላ ጊዜ በዓሰብ ቆይተው በጎሳ …በኃይማኖት… በጠባብነት… ወዘተ… ወዘተ ያልለጠፉለት ታፔላ ያልወነጀሉት ውንጀላ የለም ግን እነሱ ይጮሀሉ ባቡሩ መንገዱ ይቀጥላል ስለዚህ የሐውልቱ ጉዳይም ነገ ከነገ ወዲያ አብረን እናየዋለን መንግስት ህዝብ የሚያስድት ወረኞች ደግሞ አፍ የሚያስይዝ ስራ እንደሚሰራ ቅንጣት አልጠራጠርም:: ሥራ ለሰሪው እሾህ ለጫሪው ነውና የከርሞ ሰው ይበለን ጎበዝ ኮምፒውተር ስር ተወሽቆ አካኪ ዘራፍ ማለቱ ግን ትዝብት ነው ትርፋ::

  ReplyDelete
 14. Ewnetu Zeleke December 4,2012
  Dear D/n Daniel
  በመጀመሪያ በሀውልቶችና በቅርስ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የምታነሳቸውን እጅግ ቁም ነገር አዘል መልዕክቶች በማስነበብህ እጅግ አድርጌ አመሰግንሀለሁ፤ አደንቅህማለሁ፡፡
  ከወልዱ ታደለ የተሰጠውን ምላሽም ተመልክቻለሁ፡፡ ለመሆኑ ልማት ማለት መንገድና ኮንዶሚኒየም መገንባት ብቻ ነው? ሰማህ ወዳጀ! ታሪክና ቅርስ የሌለው ህዝብ ሥር እንደሌለው ዛፍ ይቆጠራል! ይባላል አነዚህ በወቅቱ የነበሩ የሀገራችን የፖለቲካና የሀይማኖት መሪዎች በፈጸሙት የአርበኝነት ተግባር ነው የዛሬዋ ኢትዮጵያ የተገኘችው፡፡ ቅርሶቻችን በማይጎዱበት አግባብ ልማቱን እናፋጥን ማለት ፀረ ልማት ሀይሎች፣ጨለምተኞች የሚል ግልብ ፍረጃ የሚያሰጥ ነው? ሆኖም ከተራ ጭፍን ደጋፊ የሚጠበቅ ነው፡፡ የዛሬ 20 ገደማ ቅርሶችን ማጥፋት እንደ ጀብዱ ተግባር የሚያስሾም የሚያስሸልም እንደነበረ በወቅቱ የነበረ ሰው ወይም ታሪኩን የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ሀገራችንን ለቱሪስት ተመራች እንድትሆን የሚያደርጋት ጉዳይ ቅርሶቿ አይደሉምን?
  መንግስታት እኮ ለህዝብ ተጠሪ መሆናቸውን ማወቅ ያለብን ይመስለኛለ፤ስለሚሰራው ልማት ጥቅምና ሊኖሩት የሚችሉትን መጠነኛ ጉዳቶች በተገቢው መመዘን፣ መንግስታት ቢሳሳቱ ማረም ያለበት ህዝቡ ነው፡፡ ያላችሁትን ብትሉ ግመሉ ጉዞውን ይቀጥላል የሚለው ጊዜ ያለፈበት፣ እኔ ብቻ አውቅላችኋለሁ ከሚል አምባገነንነት የሚነሳ አስተሳሰብ ነው፡፡ ለሀገራችን የሚጠቅመው ጉዳይ በሰለጠነ አግባብ በህዝቡ ውስጥ በመረጃ እጥረትም ይሁን በሌላ ምክንያት ግልጽነት የጎደለውን ጉዳይ እያነሳን እየተወያየን ስንሄድ መንግስትን መጥቀም እንጂ መጉዳት ተደርጎ የሚታይ ከሆነ ዲሞክራሲያችን የዓመት ፈቃድ ወጥታ ተኛች ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የሌሎችንም ሀሳብና ስጋት ታሳቢ አድርጎ የመስራት ሰፊ ልቦናን ይስጥልን፡፡ ዲ/ን ዳንኤልም በእንዲህ ዓይነቱ ጭፍን ፍረጃ እንደማትደናገጥ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ወልዱም እንደስምህ እንድትሆን ይብቃህ፡፡

  ReplyDelete